Telegram Web Link
መንግስት ነዳጅ የሚጠቀሙ መኪኖች ላይ የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ አዋጅ ለማፅደቅ እየሰራ ይገኛል

በዚህም መሰረት አዲስ መኪኖች ማለትም እስከ 1 አመት ድረስ ያሉ እና እስከ 4000 ኪሎሜትር የተጟዙ መኪኖችን ስታስገቡ በሚሻሻለው ኤክሳይስ ታክስ መሰረት ከ 1500 cc በታች 10%, ከ 1500cc እስከ 2500cc 20%, ከ 2500cc እስከ 3000cc 30%, ከ 3000cc በላይ ደግሞ 60% እንደሚሆን ገልጸዋል :: በዚህ ሁለት ሳምንት ውስጥ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል :: እሱ ሲወጣ ደግሞ የምንገልጽ ይሆናል ::
ተጨማሪ መረጃዎችን በቲክቶክ እና በዩትዩብ ፔጃችን ላይ የምንለቅ ነው የሚሆነው ::

ፍክት ያለ ቀን ተመኘን
#Ethiopia #Excisetax
@OnlyAboutCarsEthiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያው Toyota BZ4X መኪና ነው ::

Toyota ለመጀመሪያ ጊዜ ለአለም አቀፍ ገበያ ከዲዛይኑ ጀምሮ ለኤሌክትሪክ መኪና ብሎ የሰራው መኪና ነው :: እንደእድል ሆኖ በሌላ ስራ ምክንያት የመኪናውን አስመጪ የማግኘት እድል አግኝቼ መኪናው እንደገባ በደንብ ሳይታወቅ ነው የሰራሁት :: ያመጡትም ትልቁን ትሪም ሌቭል ስለሆነ በጣም ለየት ያሉ ፊቸሮችን አካተውበታል :: ብቻ እዩት እና ያላችሁን ሀሳብ እዛው ላይ አስቀምጡልን ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/qTL80md_qMk

መኪናው ለግል አገልግሎት ሳይሆን ለመሸጥ ስላስመጡት መግዛት የምትፈልጉ ተጨማሪ መረጃ በ 0991157053 ወይም በ 0911663121 ላይ በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ ::

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#Toyota #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ፍሬቻችሁ በፍጥነት ብርት ጥፍት ሲል ሊሆኑ የሚችሉት 3 ምክንያቶች አሉ ::

1. ሲገጠም በትክክል ካልተገጠመ
2. ሾርት የሚያደርግ ከሆነ እና
3. ሊቃጠል ሲል ይህንን ምልክት ያሳያል ::

ስለዚህ ከእነዚህ ምክንያቶች አንዱ ሊሆን ስለሚችል በተራ ቼክ አድርጟቸው ::

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Turnsignal #Light
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለብዙዎች የገቢ ምንጭ የነበረው የላዳ ታክሲ ታሪክ | LADA Riva

ይህንን ላዳ ታክሲ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ደግሞ አዲስ አበባ የማያውቀው ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም :: አሁን ላይ ሌሎች የታክሲ ድርጅቶች መተው እያስወጧቸው ቢሆንም በጊዜው ግን የከተማው መለያ ነበሩ :: ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት ገቡ? ምን ነበር እንደዚህ እንዲበዙ ያደረጋቸው ምክንያት? እንዴት ተሰሩ የሚለውን የዩትዩብ ቪድዮ ለቀናል ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/JyxYlRMIiOI

በዚሁ ደግሞ የቆሙ ክላሲክ እና የቆዩ መኪኖች ያላችሁ ሰዎች የምትሸጡ ከሆነ ገዝተን ቪድዮ ሰርተን ለማሳየት ስለሆነ አናግሩን ::

ገራሚ ከሰአት ተመኘን
#Lada #Taxi
@OnlyAboutCarsEthiopia
Ford Mustang Mach 1

ይህ የ 2021 Ford Mustang Mach 1 ኢትዮጵያ ውስጥ የገባ መኪና ነው ::
Stone gray ቀለም ያለው 5 liter V8 ሞተር ሲኖረው 454 HP ወይም የፈረስ ጉልበት እና 390 Nm of ቶርክ ያለው መኪና ነው ::
Mach 1 ላይ 19 inch ጎማዎችን ስታገኙ Brembo brakeም አንድ ላይ ታገኛላችሁ ::
የጀርባው Axle Cooler አለው :: ይህም ትራክ ላይ ለረጅም ሰአት ሲነዳ እንዳይሞቅ በማሰብ ነው ::
ማሞቅያ እና ማቀዝቀዣ ያላቸው ወንበሮች, የትራክሽን ኮንትሮል ሲስተም, መሪውን ኮንትሮል ለማድረግ የሚመች በተን እና የድራይቪንግ ሞድ በተን ታገኛላችሁ ::
በ 10 ማርሽ Automatic ወይም በ 6 ማርሽ manual transmission ይመጣል ::
ዋጋው ከ 53,400 የአሜሪካን ዶላር ጀምሮ ነው ::
አጠር ያለ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ለቀናል ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMYr6EkCX/

ማንኛውንም መኪኖቻችሁን እየነዳን ሪቪው እንድንሰራ ፈቃደኛ የሆናችሁ ሰዎች @Yonathandesta ላይ መልእክት ላኩልን ::

ፍክት ያለ ምሽት ተመኘን
#Ford #Mustang
@OnlyAboutCarsEthiopia
ከ Mercedes EQC400 ይሻላል?

2022 BMW IX3

BMW አሁን ላይ በብዛት ከሚሸጣቸው ኤሌክትሪክ መኪኖች አንዱ ነው :: IX3 ቀጥታ ከ X3 ሞዴል ላይ ነው ዲዛይኑን የወሰዱት :: በአንድ ቻርጅ 462 ኪሎሜትር ይጟዛል ብለዋል ግን ምን ያህል ይሄዳል? እውነት ከ Mercedes EQC400 ይሻላል? እና ኤሌክትሪክ መኪና ከመግዛታችሁ በፊት ማወቅ አለባችሁ ያልናቸውን ሁለት ዋና ዋና ነጥቦች አንስተናል :: በዝርዝር ዩትዩብ ላይ ለቀናል
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/4f-q3A61a-Q

ይህንን መኪና መግዛት ከፈለጋችሁ በ 0991157053 በመደወል ሙሉ መረጃ ታገኛላችሁ :: ሌሎችም መኪኖች ከፈለጋችሁ ከተማ ውስጥ ከሚሸጡበት ባነሰ ዋጋ ታገኛላችሁ :: መኪናችሁንም መሸጥ ከፈለጋችሁና በአሪፍ ዋጋ የምታቀርቡልን ከሆነ @yonathandesta ላይ አውሩን ::

ግሩም ምሽት ተመኘን
#BMW #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
እነዚህ የደበዘዙ ነጠብጣቦች ምን እንደሆኑ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?


በንፋስ መከላከያው ዙሪያ ያለው ጥቁር መስመር "ፍሪት" ይባላል እና ሙጫውን (ማጣበቂያውን) ለመደበቅ እዚያ ይገኛሉ :: ጥቁር ስለሆኑ ሙቀቱን ከፀሀይ ብርሀን የበለጠ ይቀበላሉ እና የተቀረው የንፋስ መከላከያ ቀዝቀዝ እንዲል ያደርጋሉ :: ስለዚህ የሙቀት ልዩነቱ መስታወቱን ይሰብራል :: እነዚህ ትናንሽ ጠማማ ነጠብጣቦች መስታወቱ እንዳይሰበር እና ቀስ በቀስ የሙቀት ልዩነት ለመፍጠር ነው የሚጠቅሙት ::

ብሩህ ቀን ተመኘን
#Window #CarFacts
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለኤሌክትሪክ መኪኖች 500 የቻርቺንግ ስቴሽን በአመት ሊገጠም እንደሆነ ተነገረ

ካርዲናል ኢንደስትሪስ በ 25 ሚሊየን ዶላር ካፒታል በአመት 500 የቻርጅ ስቴሽኖችን አዲስ አበባ ውስጥ ሊገጥም እንደሆነ አስታውቋል :: ከኢትዮጵያ መብራት ሀይል ጋር በመተባበር ሲሆን ይህም በብዛት ወደሀገራችን እየገቡ ላሉት ኤሌክትሪክ መኪኖች መፍትሄ ይሆናልም ብለዋል ::
በጣም የተለያዩ ኤሌክትሪክ መኪኖችን በዝርዝር መመልከት ከፈለጋችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
HTTPS://youtube.com/yonathandesta

ምንጭ- VOA

እርፍ የምትሉበት ቀን ተመኘን
#Electric #Charger
@OnlyAboutCarsEthiopia
Only About Cars Ethiopia
Dodge አዲሱን የ 2023 Hornet ሞዴላቸውን ለእይታ አቅርበዋል :: ይህ መኪና ለ Dodge የመጀመሪያው ኮምፓክት SUV ሲሆን ይወዳደራል ተብሎ የሚጠበቀውም ከ Toyota RAV4, Honda CR-V እና Nissan X-Trail ጋር ነው :: በሶስት ትሪም ሌቭል እንደአማራጭ ያቀረቡ ሲሆን በ GT, GLH እና R/T ሞዴል አቅርበዋል :: GT ላይ 2.0 ሊትር 4 ሲሊንደር 268 የፈረስ ጉልበት(HP)…
Dodge የ 2023 Hornet ሞዴላቸውን ዋጋውን ይፋ አድርገዋል ::

ይህ መኪና ለ Dodge የመጀመሪያው ኮምፓክት SUV ሲሆን ይወዳደራል ተብሎ የሚጠበቀውም ከ Toyota RAV4, Honda CR-V እና Nissan X-Trail ጋር ነው :: በሶስት ትሪም ሌቭል እንደአማራጭ ያቀረቡ ሲሆን በ GT, GLH እና R/T ሞዴል አቅርበዋል :: GT ላይ ዋጋው 31,000 የአሜሪካን ዶላር ሲሆን መነሻው ወደ R/T ትሪም ሌቭል ስንመጣ ደግሞ ሀይብሪድ ሞዴሉ ላይ እስከ 53,000 የአሜሪካን ዶላር ይደርሳል ::

ስለ ሀይብሪድ አይነቶች ደግሞ ለመመልከት
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/AhbvADJUeKg

ውብ ምሽት ተመኘን
#Dodge #Hybrid
@OnlyAboutCarsEthiopia
በአንድ ቻርጅ 80 ኪሎሜትር የሚጟዘው የ BMW ሀይብሪድ መኪና

BMW XM Hybrid

BMW እስከዛሬ ከሰራቸው የ M series መኪኖች የሚለይ መኪና ነው :: ከዲዛይኑ ጀምሮ ውስጡ ቴክኖዎሎጂው እና በ ሀይብሪድ ሲስተም መምጣቱ ከሌሎቹ ወጣ ብሎ እንዲታይ አድርገውታል :: ከዛም ውጪ ከ Lamborghini Urus, ከ Aston Martin DBX እና ከ Ferrari Purosangue መኪኖች የሚፎካከር ነው :: ያ ማለት በጣም ፈጣን እና ጉልበት ካላቸው SUV መኪኖች ተርታ የሚመደብ ነው :: በዛ ላይ በ Plug-in ሀይብሪድ ነው የሚመጣው :: በዝርዝር ዩትዩብ ላይ ለቀናል :: ካያችሁት በሗላ ሀሳባችሁን አስቀምጡልን ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/oH4SQ9p4xfI

ስለ ሀይብሪድ አይነቶች ደግሞ በደንብ ለመረዳት
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/AhbvADJUeKg

ግሩም ከሰአት ተመኘን
#BMW #Hybrid
@OnlyAboutCarsEthiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከላይ የምትመለከቱት የናኖ ቴክኖዎሎጂ ነው :: በሀገራችንም ከብዙ አመታት በፊት ጀምሮ ሲሸጥ የነበረ ቢሆንም አሁንም ገበያ ላይ በአዲስ መልክ እንደገና እየተሸጠ ይገኛል :: ግን እውነት እንደሚባለው ነዳጅ ይቆጥባል አይቆጥብም ብዙ ሪሰርቾችን ለማየት ሞክረን ነበር :: ስለሱ እራሱን የቻለ ቪዲዮ ለመስራት የተጠቀሙ ሰዎችን አስተያየት ማወቅ ስለፈለግን የምትጠቀሙ ሰዎች ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አጋሩን ::

የተለየ እሁድ ተመኘን
#Nanotechnology
@OnlyAboutCarsEthiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉ የማታውቋቸው ክላሲክ መኪኖች ክፍል 1

እኛ ሀገር ላይ ብዙ የተደበቁ የማይታወቁ ከተመረቱ የቆዩ ክላሲክ እና አንቲክ መኪኖች ይገኛሉ :: ግን እነዚህ መኪኖች ከስንት አንዴ ለመነዳት ሲወጡ ወይም እንደዚህ አይነት ዝግጅት ሲኖር ስለምናይ በጣም ነው የምንገረመው :: ባሳለፍነው ወር የክላሲክ እና የ Antique መኪኖች Show በለገሀር ባቡር ጣቢያ ተዘጋጅቶ ነበር :: የማየት እድሉ አጋጥሞኝ ስለነበር እዛ ላይ ከነበሩ መኪኖች ስለአንዳንዶቹ መኪኖች ለየት ያሉትን ነገሮችን አብረን እናያለን :: በ 3 ጎማ የሚሄድ መኪና, በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ የተያዘ ቼቭሮሌት ፒክአፕ እና ፎቶ ላይ የምታዩት Mustang ላይም ክላክስ ማድረግያው እንዲሁም 2 ለየት ያሉ ነገሮችን አካትቻለሁ :: እስኪ እዩአቸውና መኪኖቹን የእናንተን ሀሳብ መስማት እንፈልጋለን :: ክፍል 2 ላይ እናስተካክላለን ::

የዩትዩብ ቪዲዮ ሊንክ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/Dnk-V-VLfTY

ፍክት ያለ ምሽት ተመኘን
#ClassicCars #Ethiopia
@OnlyAboutCarsEthiopia
Job Title: Sales Person (Hulemekina Sales department)

Job Type: Sales

Work Location: Anywhere/remote (Addis Ababa)

Vacancies: 1

Description: We are seeking Sales person who already have experience on selling cars to join our team.

Education and Experience:

Currently in a related field of study (e.g. Marketing, Car Stuff, Media Studies)
Experience with digital media
Mostly works with car stuff and know the technical details on cars

If you fulfill the requirements
Contact us - @ArielAtom4s

From: @OnlyAboutCarsEthiopia
የኤሌክትሪክ ወይስ የነዳጅ መኪና?

በተለይ አሁን ላይ አዲስ መኪና ለመግዛት ሲታሰብ ከነዳጅ መኪኖች እኩል የኤሌክትሪክ መኪኖችንም አብዛኛው ሰው ምርጫ ውስጥ እያከተተ እና እየገዛ ይገኛል :: ግን እውነት ኤሌክትሪክ መኪና ከነዳጅ መኪና አሁን ባለው ሁኔታ ይሻላል? ጉዳቱስ ጥቅሙስ ምንድነው? በተለይ አዲስ መኪና መግዛት አስባችሁ የትኛውን መምረጥ እንዳለባችሁ ለከበዳችሁ ይህ የዩትዩብ ቪዲዮ ለእናንተ ነው ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/VMCwxTVThp8

ውብ ምሽት ተመኘን
#Electric #Fuel
@OnlyAboutCarsEthiopia
የሚፈለጉ መኪኖች ዝርዝር

- 2022/23 Mitsubishi Attrage በብድር ማመቻቸት የሚችል
- ከ 2021 በላይ Audi Q7
- የ 1990ዎቹ Toyota LandCruiser Longbase ሽፍን
- 2022/23 Hyundai Tucson ሁሉም አይነት የዱባዩም የአውሮፓውም እንዲሁም ሀይብሪዱ ካላችሁ
በ 0911663121 ላይ በመደወል ተጨማሪ ነገሮችን መነጋገር እና በ @Yonathandesta አካውንት ላይ ሙሉ ኢንፎርሜሽን ከፎቶ ጋር መላክ እንዳትረሱ ::
መኪናችሁን መሸጥ ካሰባችሁ ሁሌመኪና ላይ በነፃ መልቀቅ ትችላላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://hulemekina.com/
ቴሌግራም ቻናል 👉🏽 @Hulemekina

ግሩም ቀን ተመኘን
#CarSales #Hulemekina
@OnlyAboutCarsEthiopia
ከ ID4 በግማሽ የሚቀንሰው አዲሱ የቮልስ ኤሌክትሪክ መኪና እና ሌሎች አዳዲስ መኪኖች

ባለፉት ሳምንታት አብዛኛዎቹ የኤሌክትሪክ መኪና አምራቾች የመኪኖቻቸውን ዋጋ እየቀነሱ ይገኛሉ :: ይህንንም በማሰብ ቮልስ ዋገን አዲስ ID.2 all ሞዴላቸውን አውጥተዋል :: ዋጋውም በጣም የሚቀንስ ነው የሚሆነው :: ሌላው ደግሞ Dodge የሚገርም Demon 170 የሚባል ሞዴላቸውንም አውጥተዋል :: ከ 0-97 ኪሎሜትር በሰአት በ 1.66 ሰከንድ ብቻ በመድረስ ፈጣኑ የምርት መኪናም ሆኗል :: ሌሎችም ልክ እንደ Lamborghini Ferrari Ford እና Kia አዳዲስ መኪኖችን አውጥተዋል :: በዛሬው ቪዲዮ ስለእነሱ እናያለን ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/GYRFbnR7weU

እርፍ የምትሉበት ምሽት ተመኘን
#VW #NewCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
ያላሰብኩትን መኪና የ 1972 K5 Blazer ላይ አገኘሁ

የቆዩ ክላሲክ መኪኖች ሾው ላይ ከሄድኩ በሗላ የሚገራርሙ ክላሲክ መኪኖች ያላቸው ሰዎች ሪቪው እንድሰራ እየጠየቁኝ ይገኛሉ :: ይሄም አንዱ ነው ::
የ 1972 K5 Blazer
5.7 ሊትር V8 ሞተር ሲኖረው ይሄ መኪና ፒክአፕም ኤስዩቪም መሆን ይችላል :: እሱ ብቻ ሳይሆን በጣም ብዙ ገራሚ ፊቸሮች አሉት ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/cJciWIYfpJY

ፍክት ያለ ምሽት ተመኘን
#Chevy #SUV
@OnlyAboutCarsEthiopia
አንዳንድ የ 2009 የመጀመሪያ ጀነሬሽን Tesla Roadster መኪኖች ባትሪያቸው እንደሞተ የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ :: ይሄም አንድ ባትሪ ምን ያህል ለረዥም ጊዜ እንደሚቆይ የሚያሳይ ነው :: የባትሪ ቴክኖዎሎጂም ላለፉት 14 አመታት ምን ያህል እየተሻሻለ እየመጣ እንዳለ የሚታወቅ ነው ::

ውብ ቀን ተመኘን
#Tesla #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለምንድነው ኤሌክትሪክ መኪኖችን ሙሉ 100% ድረስ ቻርጅ አታድርጉ የሚባለው?

ከ 80% በላይ ሲሆን ቻርጅ የሚያደርግበት ፍጥነት ይቀንሳል :: በዛ ላይ መኪኖቹ እንደዚህ ቻርጅ ሲደረጉ የባትሪው እድሜ እየጨመረ ስለሚመጣ ነው :: አብዛኛዎቹ የመኪና አምራች ካምፓኒዎችም እስከ 80% ቢበዛ እስከ 90% ቻርጅ እንድታደርጉት ነው የሚመክሩት :: ለምሳሌ Ford በየቀኑ ለመጠቀም እስከ 90% ቻርጅ እንድታደርጉት ነው የሚመክረው :: BMW ደግሞ በ 10 እና 80% ውስጥ እንዲሆን ነው የሚመክሩት :: ስለዚህ በአጠቃላይ እስክሪናችሁ ላይ እስከ 80% ሊሚት በማድረግ ቻርጅ ብታደርጉት የተሻለ ስለሚያደርግ ባትሪያችሁን ለረዥም ጊዜ በጣም ሳይቀንስ መጠቀም ትችላላችሁ ::
በደንብ ከምሳሌ ጋር አብራርቼ የሰራሁትን ቪዲዮ ቲክቶክ ላይ ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMY4YSwDs/

የሚሸጥም ለመግዛትም የምታስቡት መኪና ካለ Hulemekina ዌብሳይት ላይ በመግባት መገበያየት ትችላላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

HTTPS://hulemekina.com/
@Hulemekina

ውብ ቀን ተመኘን
#Electric #Charger
@OnlyAboutCarsEthiopia
የ ቮልስ ID.4 እና ID.6 የሹፌሩን እስክሪን እንዴት እንቆጣጠራለን?

ቮልስ ዋገን ID.4 በብዛት ከተማችን ውስጥ እየተሸጠ ያለ መኪና ነው :: አብዛኛው ሰው መኪኖቹ ላይ ያሉትን ፊቸሮች ሙሉ በሙሉ እየተጠቀሙ ስላልሆነ ይህንን ቪዲዮ ለመስራት ወስነናል :: ስለዚህ እነዚህ መኪኖች ያላችሁ እንዲሁም ያላቸው ሰዎችን የምታውቁ ብታዩት የተሻለ ነው ::
በዛሬው ቪዲዮ ስለ ሹፌሩ እስክሪን መሪው ላይ ስላሉ በተኖች እና በሩ ላይ እንዲሁም ስለመብራቶቹ አጠቃቀም እናያለን ተከታተሉን ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/t0mUxSPdugM

ግሩም ምሽት ተመኘን
#VWID4 #VWID6 #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/25 14:22:19
Back to Top
HTML Embed Code: