Telegram Web Link
#ዜና

Panasonic የአውቶሞቲቭ ቢዝነሱን ሊሸጠው ነው።


ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ አምራች ካምፓኒ Panasonic ከሰሞኑ ትልልቅ ጉዳዮችን ይፋ አርጎዋል። Panasonic automotive system የተባለውን የአውቶሞቲቭ ቢዝነሱን Apollo Global Managment ለተባለ የግል ኩባኒያ አሳልፎ ሊሸጠው ነው።

ቢዝነሱ የpanasonic ኩባንያን 15% ሽያጭ የሚሸፍን ሲሆን በዋነኝነት የኢንፎቴመንት ሲስተም ላይ እና ሌሎች የመኪና ውስጣዊ ክፍሎች ላይ ነው ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራው።

የሽያጩ ዋጋም ከ2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ሲሆን ስምምነቱም በቀጣይ አመት የመጀመሪያ እሩብ አጋማሽ ላይ ያልቃል ተብሎ ተገምቷል። ነገር ግን Panasonic ሙሉ በሙሉ ከአውቶሞቲቭ ቢዝነስ ጋር ያለውን ቋጠሮ አልፈታም። አዲሱ ካምፓኒ ላይ የ20% ድርሻ ይኖረዋል። ይህም ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ያስጠብቃል።

በተጨማሪ Panasonic Energy የተባለው ክፍሉ ለMazda cylindrical lithium-ion ባትሪ cellሎችን ለማቅረብ ተፈራርሞዋል።

#panasonic #Auto_Business
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የአውቶሞቲቭ እንዱስትሪው አሁን ላይ ማይክሮቺፖችን በመግዛት በአለም የ3ኛነት ደረጃውን ይዞዋል።


ተሽከርካሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በተራቀቁ እና የኤሌክትሪክ መኪኖች ገበያው ላይ ያላቸው ተፈላጊነት በጨመረ ቁጥር የመኪና አምራቾች Semiconductor ቺፖችን ይበልጥ እየገዙ ነው።

እንደ World Semiconductor Trade Statistics ጥናት ከሆነ የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ከኮምፒውተር እና ኮሚኒኬሽን ላይ ከሚሰሩ ካምፓኒዎች በመቀጠል 3ኛ ትልቁ የsemiconductor ቺፖች ገዢ ሆኗል።

የአውቶ ኢንዱስትሪው አምና በ2023 ላይ የቺፕስ ሽያጩን 17% ሸፍኖ የነበር ሲሆን ከካች አምና በ3% ጭማሪን አሳይቶዋል። እንደ የ Semiconductor industry Association መረጃ ከሆነ አሁን ላይ ተሽከርካሪዎች በውስጣቸው ከ1,000 - እስከ 3,500 ቺፖች አላቸው። S&P Mobility ይፋ እንዳረገውም ከሆነው 2020 ላይ አዲስ መኪኖች ላይ ይገጠመው የነበረው የቺፕስ ዋጋ 500 ዶላር የነበረ ሲሆን ይሄ ቁጥር 2028 ላይ ወደ 1400 ዶላር ያድጋል።

የአውቶ ኢንዱስትሪው የSemiconductor ቢዝነሱ ላይ ያለው ድርሻ እያደገ መሄዱ የሚጠበቅ ሲሆን እንደ Silicon Carbide ያሉ የተራቀቁ ቺፖችንም መጠቀም ይጀምራል።

#Auto_Industry
#Semiconductor
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BRIDGESTONE አዲስ  የLunar(የጨረቃ ተሽከርካሪ) ጎማ ይፋ አደረገ።


Bridgestone ቀጣይ ወር በኮሎራዶ በሚካሄዴው የSpace Symposium ላይ የሚያቀርበውን የLunar Rover(የጨረቃ ተሽክርካሪ) ጎማ ይፋ አደረገ።

ካምፓኒው ከዚ ቀደም የlunar ጎማ ፕሮቶታይፕ ሰርቶ የነበረ ሲሆን የአሁኑ በብዙ የተለየ ነው። Bridgestone ለመኪኖች እና ለባለ ሁለት ጎማ ተሽከርካሪዎች አዘጋጅቶት ከነበረው አየር አልባ Non_pneumatic ጎማ ጋር ተመሳሳይነት ሲኖረው ይሄኛው ግን Rubber ወይም ፕላስቲክን በመጠቀም ምትክ ከብረት የተሰራ ነው።

Bridgestone አንዳለው ከሆነ አዲሱ የጎማ ዲዛይን ከቀድሞ አንፃር የተሻለ ዘለቄታ ያለው እና አስቸጋር መልከአ ምድሮች ላይ መጓዝ የሚችል ነው።

አንዳንዶቻችሁ እንደምታውቁት Toyota Lunar Rover( የጨረቃ ተሽከርካሪ እየሰራ ያለ ሲሆን እነዚህን ጎማዎች ለተሽከርካሪው ሊጠቀምበት የሚችልበት ጥሩ እድል አለ።

#Bridgestone #Lunar_Tire
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

CATL በጠቅላላ የአገልግሎት ዘመኑ 1.5 ሚሊየን ኪሎሜትሮችን  መጓዝ የሚችለውን ባትሪው ይፋ አደረገ።


የቻይናው የመኪና ባትሪ አምራች ካምፓኒ የሆነው CATL በአገልግሎት ዘመኑ እስከ 1.5 ሚሊየን ኪሎሜትሮችን መጓዝ የሚችሉ እና እስከ 1 ሚሊየን ኪሎሜትሮችን መጓዝ የሚችሉ (Lithium ion phosphate) ባትሪዎችን የሰራ ሲሆን በጣም ፈጣን የሚባል የቻርጂንግ ፍጥነት ነው ያላቸው።

ባለ 1.5 ሚሊየን ኪሎሜትር የአገልግሎት ዘመን ያለው ባትሪው የቻርጂንግ ፍጥነቱ 300 kw(Kilowatt) ሲሆን እንደ የህዝብ ማመላለሻ ባሶች፣ለቀላል እና ከባድ የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ጥቅም ላይ ይውላል ።

ባለ 1 ሚሊየን ኪሎሜትር የአገልግሎት ዘመን ያለው እንድ ቴስላ፣ፎርድ እና ጀነራል ሞተርስ ያሉ የመኪና አምራቾች በቅርቡ መጠቀም የሚጀምሩት ባትሪው የ500 kw super fast ቻርጂንግ ፍጥነት ያለው ሲሆን እንደ ከፍተኛ ሙቀት እና ከፍተኛ ቅዝቃዜ ባሉ የአየር ንብረቶችም ላይ አገልግሎቱን መስጠት ይችላል።

#CATL
#OnlyAboutCarsEthiopia
Only About Cars Ethiopia
#ዜና BYD Yuan Up ቻይና ውስጥ በ 13,400 ዶላር የመነሻ ዋጋ ለገበያ ቀረበ። ከብዙ ጊዜ ማስጠበቅ በሗላ በመጨረሻም የቻይናው የኤሌክትሪክ መኪኖች አምራች የሆነው BYD Yuan Up የተባለውን ኮምፓክት SUV መኪናው በ13,000 የአሜሪካ ዶላር መነሻ ዋጋ ለገበያ አቀረበው። Yuan Up ከተማሪ ጀምሮ እስከ ባለትዳሮች ያለውን ሰፊውን የማህበረሰብ ክፍል እንዲያማክል ታስቦ የተሰራ ሲሆን…
#ዜና

BYD በአንድ ቀን ውስጥ 20,000 መኪናዎችን (order) ተደረገ።


BYD March 26 ላይ ለሽያጭ ባቀረበው እና እኛም አንደተለቀቀ ስለመኪናው ዝርዝር መረጃ ለእናንተ  አጋርተንበት በነበረው መኪናው Yuan Up ለገበያ በቀረበ በ 1 ቀን ውስጥ 20,000 ሰዎች pre order አደረጉት።

ከዋጋው አንፃር በጣም አሪፍ የሚባል መኪና የሆነው Yuan Up አሁን ላይ ብዙ ሰዎች ዘንድ እየተወደደው ያለው (compact crossover/suv) ቦዲ ስታይል ያለው መኪና ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነም በሰዎች ዘንድ ጥሩ ተቀባይነትንም አግኝቷል።

#BYD #Yuan_Up
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

OAK Ridge laboratory  የመኪና ገመድ አልባ (wireless) ቻርጀርን አበለፀገ።


በአሜሪካ Tennessee ግዛት ውስጥ የሚገኘው OAK Ridge National Laboratory የተባለው የምርምር ተቋም በኤሌክትሪክ መኪኖች የገመድ አልባ (wireless) ቻርጀርን በማበልፀግ ሂደቱ ወሳኝ ምእራፍ ላይ ደርሶዋል። ተመራማሪዎቹ በገመድ አልባ (wireless) ቴክኖሎጂ ላይ ትልቅ የተባለውን  የኤሌክትሪክ ሃይል ወደ የቤት መኪና ሲያስተላልፉ( wirelessly charge) ሲያረጉ በተግባር አሳይተዋል።

ይሄንም ያረጉት  polyphase electromagnetic coupling coil በተባለው የፈጠራ ባለቤትነቱ በራሳቸው በOAK Ridge የምርምር ተቋም በሆነው ቴክኖሎጂ ነው። ተመራማሪዎቹ Hyundai Kona  መኪናን በገመድ አልባው ቴክኖሎጂ በ100kh ሃይል ቻርጅ በማረግ ለአለም አያሳይተዋል።

የምርምር ተቋሙ እንደገለፀው ከሆነ ያበለፀጉት የገመድ አልባ ቻርጂንግ ሲስተም ከተለመደው wireless ቻርጅ ማረጊያ የCoil ቴክኖሎጂ ከ8-10 እጥፍ ሃይል ያለው ሲሆን በ 20 ደቂቃ ውስጥም መኪናን በ50% ቻርጅ ያረጋል።

#OAK_Ridge_laboratory #EV_Wireless_Charging
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Nissan እና Mitsubishi በሰሜን አሜሪካ አንድ ላይ በመሆን መኪኖችን ለመስራት ተስማሙ


Nissan እና Mitsubishi አንድ ላይ በመሆን ለጃፓን ማርኬት ትንንሽ መኪኖችን ከዚህ በፊት ሰርተው ነበር :: አሁን ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በሰሜን አሜሪካ አንድ ላይ መኪና ለመስራት የተስማሙት :: ስለዚህ Nissan ለሰሜን አሜሪካ የመጀመሪያውን PHEV(Plug-in Hybrid) መኪና ሲያቀርብ የ Mitsubishi ፓርቶችን ሲጠቀም Mitsubishi ደግሞ ኤሌክትሪክ መኪናው ላይ ኒሳንን ቴክኖዎሎጂ ይጠቀማል ::

ከዚህም በተጨማሪ ሁለቱ ካምፓኒዎች ፒክአፕ ትራክ በሜክሲኮ ይሰራሉ :: ይህ መኪና Frontier ሞዴልን ሊተካ የሚችል ሲሆን ከ 2027 እስከ 2031 ድረስ ባለው ለገበያ ይቀርባል :: ሁለቱ ካምፓኒዎች ከ 2016 ጀምሮ አንድ ላይ እየሰሩ የቆዩ ሲሆን ይህም የዴቨሎፕመንት ወጪያቸውን ቀንሶላቸዋል ::

#Nissan #Mitsubishi
@OnlyAboutCars
#ዜና

SAIC የ General Motors እና የ Volkswagen ሰራተኞችን ሊቀንስ ነው


ይህ ዜና ለ General Motors እና የ Volkswagen ቻይና ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞችን ጥሩ አይመስልም :: ምክንያቱም SAIC ለእነዚህ ድርጅቶች ቻይና ውስጥ መኪኖችን በማምረት የሚታወቅ ሲሆን አሁን ላይ 30% የሚሆኑ አሴምብሊ ፕላንት ላይ የሚሰሩ ሰራተኞችን የ GM እንዲሁም 10% የ VW ሰራተኞችን ሊቀንስ መሆኑ ተገልጿል :: እሱ ብቻ ሳይሆን የራሱ ኤሌክትሪክ ሰብሲደሪ Riding Auto ላይ የሚገኙ ሰራተኞችን በግማሽ እንደሚቀንስ ገልጸዋል ::

በመንግስት ባለቤትነት ለሚንቀሳቀስ ድርጅት ይህ በጣም የተለየ ነው ተብሏል :: ምክንያቱም አንድም እነዚህ ድርጅቶች መኖራቸው ለነዋሪው የስራ እድል መፍጠር ስለሆነ :: ግን ደግሞ የ VW እና የ GM መኪኖች ሽያጭ እየቀነሰ ስለሆነ ነው ::

#SAIC
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የኤሌክትሪክ መኪና ፈላጊዎች ቁጥር እየበዛ ነው ነገር ግን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ ከሆነ።


በእርግጠኝነት ኤሌክትሪክ መኪኖች በደንብ እየተሸጡ ባይሆን ኖሮ ዋጋ በመቀነስ ትልቅ ልዩነት ማየት ይቻላል :: ለምሳሌ አሜሪካ ውስጥ Ford Mustang Mach-e ጥር ላይ በ 50% ሽያጭ ቀንሶ ነበር ይህም የሆነው 3,750 የፌደራል የታክስ ክሬዲት በመነሳቱ ነው :: ይህም የሆነው የባይደን አስተዳደር ጥሬ እቃዎቹ ከየት እንደሚገቡ እየታየ ቅናሽ ስለሚያደርግ ነው ::

ፎርድ ይህንን በማሰብ የመኪናው ዋጋ ላይ 8,000 ዶላር በመቀነስ በየካቲት ወር ወደ 64% እንዲያድግ አድርጎታል :: የመጋቢትን ሪፖርት ደግሞ በመጪው እሮብ ይፋ ያደርጋሉ :: ይህ ነው እንግዲህ የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ የዋጋ ልዩነት ወይም ቅናሽ ካለ የትም የኤሌክትሪክ መኪና ፍላጎት አለ የሚያስብለው ::

#Electric_cars
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

በአሜሪካ የሚገኘው Stellantis ወደ 6ኛነት ደረጃ ሊወርድ ይችላል።


በሰሜናዊው የአሜሪካ ግዛት በሚገኘው Stellantis የቀድሞው COO(Chief Operating Officer) የነበረው Mark Stewart የGOODYEAR CEO ለመሆን ስራ ከለቀቀ ቡላላ ብዙ አስተዳደራዊ ለውጦች ተደርገዋል።

ከወር በፊት Stellantis የretail sale፣ የcommercial sales፣ እና የካናዳው Stellantis የሚያስተዳድሩ የበላይ ሃላፊዎችን ስራ ለዋውጧቸው ነበር። አሁን ላይ ይሄ ለምን ሆኖ እንደነበር ትንሽ ፍንጭ አግኝተናል።

Cox Automotive እንደዘገበው እንደ Hyunda፣ Kia፣ እና Genesis ያሉ በHyundai group ስር ያሉ የመኪና አምራቾች በአሜሪካ ገበያ በመጀመሪያው የእሩብ አመት አጋማሽ ሽያጭ ላይ ሊበልጡት ይችላሉ። እንዲሁ Honda ሳይቀር በዚህ አመት መጨረሻ ላይ በሽያጭ ሊበልጠው ይችላል።
ይህ ከሆነ Stellantis ከGM፣ ከFord ፣ከToyota፣ ከHyundai group፣ እና ከHonda ኋላ በመሆን ወደ 6ኛነት ደረጃ ይወርዳል።

#Stellantis
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አንዳንድ የመኪና ሸማቾች በElon musk ምክንያት ቴስላ ላይ ያላቸው ፍላጎት ጠፍቶዋል።


የቴስላ መኪና የሽያጭ መቀነስ ምክንያቾች አንዱ እራሱ የካምፓኒው ባለቤት Elon musk ሳይሆን አልቀረም።
Routers 5 የማርኬቲንግ እና የመኪና ኤክስፐርቶችን አናግሮ ነበር። ኤክስፐርቶቹ እንዳሉ ከሆነ ጥቂት የማይባል የማህበረሰቡ ክፍል በElon Musk የRight wing ፕለቲካ አቋሙ እና በየግዜ በሚናገራቸው controversial ንግግሮቹ ምክንያት በቴስላ መኪኖች ላይ ያላቸው ፍላጎት ሞቶዋል።

እናም አብዛኞቹ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመሸመት ሲያስቡ የቴስላን መኪኖች ከምርጫ ዝርዝራቸው ውስጥ አያካትቱትም።
CivicScience የተባለ ካምፓኒ አሜሪካ ውስጥ ባረገው የዳሰሳ ጥናት ካናገራቸው 43% የሚሆኑ ሰዎች ለElon Musk ጥሩ አመለካከት የላቸውም። የዛሬ 2 አመት ይሄ ቁጥር 34% ነበር።

እንዲህም ሆኖ በመኪና ኢንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ የብራንድ loyalty በቴስላ የመኪና ባለቤቶች የተያዘ ነው። 68% የሚሆኑ የቴስላ መኪና ተጠቃሚዎች በቀጣይ ጊዜ መኪና ሊሸምቱ ወደ ገበያ በሚያቀኑበት ወቅት ሌላ የቴስላ መኪናን ነው ሚገዙት።

#Elon_Musk #Tesla
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

መኪናዎትን ለመሸጥ ተቸግረዋል?

የተለያዩ መኪኖቻችሁን በሁሌመኪና በማስተዋወቅ መሸጥ እና ማከራየትም ትችላላችሁ
በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም ቴሌግራም ላይ @Hulemekinaadmin ላይ የመኪኖቻችሁን ፎቶ (እስከ 10 ፎቶዎችን) በመላክ 300 ብር ብቻ ቴሌብር ላይ በመክፈል መሸጥ እና ማከራየት ትችላላችሁ ::

@hulemekina
#ዜና

አለም ላይ በፍጥነት ቻርጅ የሚያደርገው ኤሌክትሪክ መኪና


ቻይና አለም ላይ በፍጥነት ቻርጅ የሚያደርጉ ኤሌክትሪክ መኪኖችን በመስራት ትታወቃለች :: አዲሱ የ Zeekr 001 መኪና 264 ኪሎሜትር በ 5 ደቂቃ ቻርጅ መድረስ ይችላል :: ይህም የሆነው በ 546 Kw (Kilowatt) ቻርጂንግ ሬት ነው ::ይሄ ቅርብ ጊዜ Li Auto ካወጣውም ቫን ትንሽ በለጥ ያለ ነው :: ምንም እንኳን 001 ተለቅ ያለ ኪሎዋት ቻርጂንግ ሬት ይኑረው እንጂ የ Li Auto ቫን ከ 10-80% የሚደርስበት ፍጥነት ከ Zeekr 001 በአንድ ደቂቃ ይፈጥናል ::ሁለቱም Zeekr እና Li Auto ይህንን ቁጥር ለማስመዝገብ በጣም ፈጣን የቻርጅ ስቴሽን ይፈልጋሉ :: አሁንም ግን የሚቀር ነገርም ቢኖር ከነዳጅ መቅዳት ጋር ተቀራራቢ ለማድረግ እየተሰራ ያለው ነገር የሚገርም ነው ::

#zeekr_001 #Liauto
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የቮልክስዋገን ቴክኖዎሎጂ ካንጋሮዎችን አስደንግጦ ከመኪኖች እንዲሸሹ እያደረገ ነው


ምንም እንኳን የሚገባውን ያህል ትኩረት ባያገኝም በአጋዘን ምክንያት የሚደርሰው የመኪና አደጋ ብዙ ነው :: ባሳለፍነው አመት በአውሮፓ ብቻ 300 ሰዎች ከአጋዘን ጋር በነበረ የመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል :: ወደ 10,000 የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል :: በአሜሪካ ደግሞ 200 የሞት አደጋዎችን እና 10,000 ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል :: የአስትራሊያ ደግሞ ትንሽ ለየት የሚያደርገው ከካንጋሮ ጋር መሆኑ ነው :: ይህንንም በማሰብ የ ቮልስዋገን አውስትራሊያ የኤሌክትሮኒክ ድምፅ የሚፈጥር ቴክኖዎሎጂ በመስራት ካንጋሮዎቹን እንዲፈሩ ለማድረግ እና መንገድ እንዲለቁ የሚያደርግ ነው ::

RooBadge የሚል ስያሜን የሰጡት ሲሆን GPS እና አፕልኬሽን በመጠቀም መኪናው በብዛት ካንጋሮዎቹ የሚገኙበት ቦታ ስትደርሱ በማብራት ይሰራል :: RooBadge አሁንም ሙከራ ላይም ቢሆን ቮልስዋገን ግን ለአጋዘን እና ለሌሎች እንስሳቶችም መሆን ይችላል እያለ ነው ::

#VW #RooBadge
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Liberty MotoGPን ገዝቶታል


Liberty ሚዲያ የፎርሙላ 1 የኮሜርሻል ፈቃድ ያለው ካምፓኒ ሲሆን አሁን ደግሞ አንድ አዲስ ድርጅት በስሩ አካቷል :: Doma የሚባል ድርጅት ሲሆን እሱም በስሩ MotoGP ሞተርሳይክል ውድድርን ያቀፈ ድርጅት ነው :: በ 4.5 ቢሊየን ዶላር እንደተስማሙ የተገለፀ ሲሆን ስምምነቱን እስከ እዚህ አመት መጨረሻ ድረስ ይጨርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል :: Liberty F1 በ 2017 ላይ የገዛው ሲሆን ከዛ ጊዜ ጀምሮ በጣም ተወዳጅ እና ተፈላጊ የሆነ ውድድር ሆኗል :: ይህንን ስኬት ነው እንግዲህ ወደ MotoGP የሚያመጣው ::

#Liberty #MotoGP
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የአሜሪካ የመኪና አደጋ እየቀነሰ ነው ግን ደግሞ ከኮቪድ በፊት ከነበረው ቢጨምርም


በአሜሪካ እየደረሰ ያለው የመኪና አደጋ ባለፈው አመት እየቀነሰ መሆኑ ተዘገበ :: ምንም እንኳን እየቀነሰ ነው ቢባልም አሁንም ከኮቪድ በፊት ከነበረው ግን ከፍ ያለ ቁጥር ነው ያለው :: በ ናሽናል ሀይዌይ ትራፊክ ሴፍቲ አድሚኒስትሬሽን (NHTSA) 40,990 ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ሲዘገብ ከ 2022 በ 3.6% ቀንሷል :: በኮቪድ ጊዜ የመኪና አደጋ የጨመረበትን ምክንያት መንገድ ላይ በጣም ትንሽ ቁጥር ያላቸው ተሽከርካሪዎች ስለነበሩ አብዛኛው ሰው ከፍጥነት በላይ በሚያሽከረክርበት ሰአት ነው እነዚህ አደጋዎች ሊደርሱ የቻሉት ::

NHTSA በሌላ ሪፖርት ባወጣው መሰረት የእግረኞች እና ሳይክል የሚጠቀሙ ሰዎች ላይ የሚደርሰው አደጋ እየጨመረ ነው :: በ 2022 ላይ በእግረኞች ላይ በ 0.7% ሲጨምር ሳይክል የሚጠቀሙ ላይ ደግሞ አደጋው በ 13% ጨምሯል ::

#NHTSA #Traffic_Accident #US
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Toyota በአይነቱ ለየት ያለ የጥናት እና ምርምር ጣቢያ ገነባ።



ታዋቂው የመኪና አምራች Toyota ከተለመደ የመኪና አምራቾች አሰራስ ማለትም የተለያዩ የ research & development ቡድኖች ለየብቻ በተለያየ ጣቢያ ውስጥ ይሰሩበት የነበረው አሰራር በመቀየር ሁሉም ሰራተኞች አንድ ላይ አንድ ጣቢያ ውስጥ መስራት የሚያስችላቸውን ግዙፍ የጥናት እና ምርምር ጣቢያ ጃፓን ላይ ከ2018 ጀምሮ ሲገነባ የነበር ሲሆን አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ግንባታው ተጠናቀቀ።

ጣቢያው በጀርመን የሚገኘውን nurburgring የተባለው የሞተር ስፖርት የውድድር track ስሜትን እንዲሰጥ እና እንዲመስል ተደርጎ ነው የተሰራው። እናም ጣቢይው ላይ እንደ planning & design፣ development & engineering ፣prototype እና ግምገማ ላይ ሚሰሩ ሰራተኞች አንድ ላይ መስራት ይችላሉ።

Toyota ከሌሎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎቹ እና ከሁለት ስፔሻላይዝ test truckዎቹን በመጠቀም የተሻሉ መኪኖችን መስራት እንደሚችል ያምናል።

#Toyotal #RandD_Center
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የ Korean pop አድናቂዎች Hyundai አድርጎት የነበረውን የአሉሚኒየም ስምምነት አሰረዙት።


Hyundai ብረት በማምረት ወቅት አካባቢው ላይ ሊደርስ የሚችለው ተፅእኖ ያሰጋቸው የKorean pop ዘፈን አድናቂዎች እና የአየር ንብረት ተሟጋቾች ባደረጉት campaign ምክንያት የአልሙኒየም ስምምረቱን አፈረሰ።

በ2022 Hyundai ከኢንዶኔዢያ Adaro Minerals ጋር አልሙኒየም ሊያቀርብለት ተፈራርሞ ነበር። ነገር ግን በk-pop አድናቂያን የታገዙት የተፈጥሮ ተሟጋቾች በምርት ወቅት አልሙኒየሙን በድንጋይ ከሰል ሃይል በመታገዝ ለማቅለጥ በሚደረገው ሂደት ውስጥ ወደ ከባቢው አየር ሊለቀቅ በሚችለው የካርበን መጠን በመስጋት ዘመቻ አስጀምረው ነበር። ሀዩንዳይም ጫናው ስለበዛበት ስምምነቱን ሊሰርዝ ችሎዋል።

#Hyundai #k_pop_Fans
@OnlyAboutCarsEthiopia
# ዜና

የHyundai ሹፌር አልባ መኪና (AV) የአሜሪካ የመንጃ ፈቃድ ፈተናን አለፈ።


የHyundaiዩ ሹፌር አልባ Robotaxi አሪፍ በመሆኑ አሜሪካ ላይ የመንጃ ፍቃድን ሊያገኝ ይችላል። የመኪና አምራቹ IONIQ 5 የተባለው ሹፌር አልባ (Autonomous መኪናውን በአሜሪካ ላስ ቬጋስ የመንጃ ፍቃድ መሰናክል ፈተናን የDMV ፍቃድ ባላት ፈታኝ ሲፈተን ያሳየ ሲሆን በሚገር ሁኔታ ፈተናውን አልፎዋል።

Hyundai እንደተናገረው ሹፌር አልባው መኪና በአሜሪካ ውስጥ ማንኛውም ሰው የመንጃ ፈቃድን ለማውጣት የሚፈተነውን ፈተና ነው የተፈተነው።
Motional የተባለው በHyundai እና የቴክኖሎጂ ካምፓኒ በሆነው Aptiv በጋራ በመሆን የተመሰረተው ካምፓኒ አሁን ላይ በላስ ቬጋስ ሹፌር አልባ IONIQ 5 እያበለፀገ ነው።
ለሚዲያ ያጋሩት የፈተናው ቪዲዮም በሰዎች ዘንድ ስለመኪኖቹ ይበልጥ እምነት እንዲኖር በማሰብ ነው።

#Hyundai #Motional #IONIQ_5 #AV
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Cadillac Lyriq በአውሮፓ የቅንጡ መኪኖች በደንብ እየተሸጠ ነው ::


General Motors 594,000 የቤት መኪኖችን, ትራኮችን እና SUV መኪኖችን ሽጧል :: ግን ደግሞ ለ GM አይኑን የከፈተለት የኤሌክትሪክ መኪና Cadillac Lyriq ሲሆን በ 5,800 መኪንችን በመሸጥ አውሮፓ ውስጥ የቅንጦት ኤሌክትሪክ መኪኖች ከሚባሉት የተሻለ ሽያጭ አለው ::

GM ከዚህም መኪና ውጪ Chevrolet Blazer ev 600 ፍሬ Chevrolet Silverado ev ከ 1,000 በላይ እና 1,668 Hummer ev ለደንበኞቻቸው አስረክበዋል :: እነዚህ ቁጥሮች ትንሽ ናቸው ግን ይህ አመት ሲጠናቀቅ ወደ 300,000 የሚጠጉ መኪኖችን እንደሚያቀርቡ ገልፀዋል ::

#Cadillac_Lyriq #GM
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/23 04:33:18
Back to Top
HTML Embed Code: