Telegram Web Link
#ለሰው_ልጅ_ትልቁ_ደስታ_መልካም_ትዳር_ነው
✿✿<>✿✿<>✿✿<>✿✿<>✿✿<>✿
💐💐💐💐💐💐
#ሴት_ሆይ_ለትዳርሽ_ብቁ_ነሽን?!"
➊.ባለቤትሽ ወደ ቤት በገባ ጊዜ በእጅሽ ያለውን ነገር ትተሽ እሱን ለመቀበል ካልሄድሽ፣ ከፊቱ ላይ የተመለከትሺውን የድካም ስሜት ካላስረሳሽ
{ አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➋.ባለቤትሽ አንቺ በእጅሽ ሰርተሽ የማታባይው ከሆነ ከምግብ ቤቶች ከተመገበ ፣ ልብሶቹን የማታዘጋጂለት ከሆነና ወደ ማጠቢያ ቤት ከወሰደ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➌.ባለቤትሽ በተቆጣ ጊዜ በአስር ቃላት የምትመልሺለት ከሆነ፣ድምፅሺን ከፍ አድርገሽ ካወራሽው{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➍.ከባለቤትሽ አጠገበ በተቀመጥሽ ጊዜ ጠረንሽ ጥሩ ካልሆነ፣የልብስሽን ንፅህና ካልጠበቅሽ፣እሱን የሚማርኩ ካልሆኑ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➎.ከሱጋ በተጣላሽ ወቅት ወደ እናትሽ ቤት፣ወደ እህትሽ፣ ወደ ጓደኛሽ ቤት የምትሄጂ ከሆነ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➏.ከባለቤትሽ ቤተሰቦች ጋር ስትሆኚ የሱን ቤተሰቦች መልካምን በማድረግ የማትንከባከቢ ከሆንሽ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➐.በፀሎት ጊዜ እሱን የማትቀሰቅሺ ከሆንሽ፣ ፈጣሪን በመታዘዝ ላይ የማተበረታቺው ከሆነ፣ ክልክል ነገራቶችን እንዲተው የማታደርጊ እና ወደ ተውበት የማትገፋፊው ከሆንሽ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➑.ባልሽ የሚወዳቸውን እና የሚጠላቸውን ነገሮች ለይተሽ ካላወቅሽ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
❖❖~❖❖~❖❖< >❖❖~❖❖~❖❖
:💐💐💐💐💐💐
#ወንድ ሆይ ለትዳርህ በቁ ነህን?
:
➊.ሚስትህ ምቾት እና እንክብካቤ ስለምትፈልግ
ካልተንከባከብካት እና ያለህን ነገር በሙሉ ሳትሰስት ካላጋራሃት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➋.ሚስትህ ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች። ባገኘከው አጋጣሚ ከንፈሯን እየሳምክ ፍቅርህን የማትገልፅላት ከሆነ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➌.ሚስትህ ግትር ባል ትጠላለች። ደካማ ባልን ደግሞ ትንቃለች አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር መሆንን ካልቻልክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➍.ሚስትህ መልካም ንግግር፣ ወንዳ ወንድ ገጽታ፣ በስፖርት የተገነባ ሰውንት፣ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ይማርካታል እነዚህን ማድረግ ካልቻልክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➎.ለሚስትህ ቤቷ ቤተ መንግስት ነው። ይህን ቤተመንግሥቷን ካስደፈርክባት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➏.ሚስትህ እጅግ በጣም ብትወድህም ቤተሰቦቿን ማጣት አትፈልግም። ቤተሰቦቿን ብትንከባከብ ከነበረው ፍቅር ላይ ሌላ ፍቅር ትጨምራለህ ይህ ካልታየህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➐.ሚስትህ አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች። (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል። ይህን ባህሪዎቿን ባትወድላት ሌሎች የሚወደዱ ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት ከዘነጋህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➑.ሚስትህ አካላዊ ድካም፣ ተፈጥሯዊ ወይንም ወራዊ ህመም እና ስነልቦናዊ ጫና እየተፈራረቁ ስለሚያጠቋት ልትነጫነጭ ትችላለች። ይህን ዘንግተህ እሷን ከመንከባከብ ፈንታ አንተም
እንደሷ ከተነጫነጭክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➒.ባገኘሁ አጋጣሚ ሚስትህን እቀፍ፣ ሳም፣ ፀጉሯን ወገቧን እሽ ሚስትህ ላንተ ሁሌም ቆንጆ እንደሆንች አስመስክር። ሚስትህ እንደ አንተ አልጋ ላይ የፍቅር ጨዋታ ያምራታል በግልፅ ፍላጎቷን በሚገባ አርካት ይህ ካልታየህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
➓.ሚስትህ እንደ አቅሟ ተውባ እና አጊጣ መታየትን ትፈልጋለች።
የመጀመሪያ የውበቷ አድናቂ ቧልዋ መሆኑን አትዘንጋ ስለዚህ ሁሌም ውበቷን አድንቅላት።
ሚስትህ ተውባ እና አጊጣ ማየት ካልፈለክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
➊➊.ደስታን፣ ሀዘንን፣ ችግርን እና ቅሬታን ለሚስትህ በግዜ ንገራት። ደስታውን አመስግኑ። ሀዘኑን ተፅናኑ፣ ችግርን እና ቅሬታን ብቻችሁን በውይይት ፍቱ። ሚስትህን በፍፁም አታኩርፍ እንዚህን መምራት ካቃተህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➊➋.ሚስትህ ስትናገር እስከመጨረሻው በጥሞና ካላደመጥካት ችግሯን ካልፈታህላት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
➊➌.ከፈጣሪ ቀጥሎ ከምንም እና ከማንም በላይ መጀመሪያ አንተ፣ ሚስትህ፣ እና ልጆችህን ብቻ አስቀድም። ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት እና ሌላው ከእናንተ ቀጥሎ ናቸው። ይህን ማስተዋል
ከተሳነህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
❖❖~❖❖~❖❖< >❖❖~❖❖~❖❖
# ወዳጆቼ፥
እንግዲህ አሏህ የራሳችሁ በሆነ ሰው ባርኮ የስጣችሁ፡፡
በተረፈ ፈጣሪ ላገባነውም ላላገባነውም ማስተዋል ይስጠን እላለሁ
❖❖~❖❖~❖❖< >❖❖~❖❖~❖❖
☞በትዳር ዓለም ውስጥ ላላችሁም መልካም ትዳር ፡፡

ለወደፊት ትዳር ለምትመሠርቱ ሁሉ ትዳራችሁ የሏህ አንዱ ኒእማ ነዉ እና ፡፡
ፍቅር የበዛበት ያድርግላችሁ!
አሚን
ዚክር፣ የዘነጋነው ሃብት
~~~~~~
መቼም ሰው ነንና ፈራሽ እንደሆንን እናውቃለን። እንደ ሙስሊም ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ እናምናለን። ስለሆነም የአኺራችን ጉዳይ ያስጨንቀናል። ለዚህም ሲባል በጌታችን ህግ ለመኖር፣ ትእዛዛቱን ለመፈፀም ክልከላውን ለመራቅ፣ ስለ ድክመታችን ተውበት ለማድረግ እንሞክራለን። ሆኖም ግን አንድ በቀላል ጥረት ብዙ ትርፍ የምንሸምትበትን ነገር ስንዘነጋ እንስተዋላለን።
አዎ ስራሽን እየሰራሽ፣ መኪናህን እየሾፈርክ፣ ወረፋ እየጠበቃችሁ፣ በመኪና እየተጓዝክ፣ ሰው እየጠበቅሽ፣ በእግራችን እየተንቀሳቀስን፣… ዚክር ቢደረግ በየእለቱ ስንትና ስንት አጅር በሰበሰብን ነበር። ዚክር ከምናስበው እጅግ የላቀ ፋይዳ አለው። ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
"أَلَا أُنَبِّئُكُمْ بِخَيْرِ أَعْمَالِكُمْ، وَأَزْكَاهَا عِنْدَ مَلِيكِكُمْ، وَأَرْفَعِهَا فِي دَرَجَاتِكُمْ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ إِنْفَاقِ الذَّهَبِ وَالْوَرِقِ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ أَنْ تَلْقَوْا عَدُوَّكُمْ، فَتَضْرِبُوا أَعْنَاقَهُمْ، وَيَضْرِبُوا أَعْنَاقَكُمْ ".
قَالُوا : بَلَى.
قَالَ : " ذِكْرُ اللَّهِ تَعَالَى".
* "ከ(መልካም) ስራዎቻችሁ በላጭ፣
* ከንጉሳችሁ ዘንድ የጠራ፣
* ደረጃዎቻችሁን ከፍ የሚያደርግ፣
* ወርቅና ብር ከመለገስ የሚሻላችሁ፣
* ጠላቶቻችሁን አግኝታችሁ አንገቶቻቸውን ከምትመቱና አንገቶቻችሁን ከሚመቱ (ከጂሃድ) የሚበልጥባችሁን አልነግራችሁምን?"

√ (ሶሐቦች):– "እንዴታ! (ይንገሩን) የአላህ መልእክተኛ ሆይ" አሉ።
* "አሸናፊና የላቀውን አላህ ማውሳት" አሉ።
[ቲርሚዚ ዘግበውታል: 3377]

ትልልቅ ምንዳ ያላቸው አጫጭር ዚክሮች
~~~~~~~~~~~~~~~~~
① ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(مَن قال: سبحان الله وبحمده، في يوم مائة مرة، حُطَّت خطاياه وإن كانت مثل زبد البحر)؛
"በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ‘ሱብሓነላ፞ሂ ወቢሐምዲሂ’ ያለ ሰው ወንጀሎቹ እንደ ባህር አረፋ ቢሆኑ እንኳን ይረግፉለታል።" [ቡኻሪ]

② እናታችን ጁወይሪያህ ቢንቲል ሓሪሥ ረዲየላ፞ሁ ዐንሃ ባስተላለፈችው በአንድ ወቅት ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም ሱብሕን ከሰገዱ በኋላ ማለዳ ላይ ከሷ ዘንድ ወጡ። እሷ መስገጃዋ ላይ ተቀምጣ ዚክር ላይ ነች። እዚያው እንደተቀመጠች ረፋድ ላይ ተመለሱ።
"ካንቺ ከተለየሁ ጊዜ አንስቶ እስካሁን በተለየሁብሽ ሁኔታ ላይ ከመሆን አልተወገድሽም?" አሏት።
"አዎ" አለች።
በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ:–
" لَقَدْ قُلْتُ بَعْدَكِ أَرْبَعَ كَلِمَاتٍ ثَلَاثَ مَرَّاتٍ، لَوْ وُزِنَتْ بِمَا قُلْتِ مُنْذُ الْيَوْمِ لَوَزَنَتْهُنَّ : سُبْحَانَ اللَّهِ وَبِحَمْدِهِ عَدَدَ خَلْقِهِ، وَرِضَا نَفْسِهِ، وَزِنَةَ عَرْشِهِ، وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ ".
"በእርግጥም ካንቺ በኋላ አራት ንግግሮችን ሶስት ጊዜ ተናግሬያለሁ። ከንጋት ጀምሮ አንቺ ካልሺው ጋር ቢመዘኑ (እኔ ያልኳቸው) ይመዝናሉ።
* ሱብሓነላ፞ሂ ወቢ ሐምዲሁ ዐደደ ኸልቂሁ፣
* ወሪዷ ነፍሲሂ፣
* ወዚነተ ዐርሺሂ፣
* ወሚዳደ ከሊማቲሂ።" [ሙስሊም የዘገቡት]

③ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(كلمتان خفيفَتان على اللسان، ثقيلَتان في الميزان، حبيبَتان إلى الرحمن: سُبحان الله وبحمده، سبحان الله العظيم)؛
"ምላስ ላይ የቀለሉ፣ ሚዛን ላይ የከበዱ እና አረ፞ሕማን ዘንድ የተወደዱ ሁለት ንግግሮች አሉ። ‘ሱብሓነላ፞ሂ ወቢሐምዲሂ፣ ሱብሓነላ፞ሂል ዐዚም።" [ቡኻሪና ሙስሊም]

④ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም ከጀነት ድልብ ሃብቶች ውስጥ እንደሆነ የገለፁት የዚክር አይነት
(لا حول ولا قوة إلا بالله)؛
"ላ ሐውለ ወላ ቁወ፞ተ ኢላ፞ ቢላ፞ህ" [ኢብኑ ሒባ፞ን]

⑤ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(مَن قال: لا إله إلا الله وحده لا شريك له، له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير - عشر مرات - كان كمَن أعتق أربعة أنفُسٍ مِن ولد إسماعيل)

"አስር ጊዜ ’ላ ኢላሀ ኢለ፞ላ፞ህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ። ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ። ወሁወ ዐላ ኩሊ፞ ሸይኢን ቀዲር’ ያለ ሰው ከኢስማዒል ልጆች አራት ነፍሶችን ነፃ እንዳወጣ ነው።" [ሙስሊም]

⑥ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(سيِّد الاستغفار أن تقول: (اللهمَّ أنت ربي، لا إله إلا أنت، خلقتَني وأنا عبدُك، وأنا على عهدك ووعدك ما استطعتُ، أعوذ بك من شرِّ ما صنعتُ، أبوء لك بنعمتك عليَّ، وأبوء لك بذنبي، فاغفر لي، فإنه لا يغفر الذنوب إلا أنت، قال: ومَن قالها من النهار موقنًا بها، فمات من يومه قبل أن يُمسي فهو مِن أهل الجنَّة، ومَن قالها من الليل وهو مُوقن بها، فماتَ قبْل أن يُصبح، فهو مِن أهل الجنَّة)؛
"የኢስቲግፋር ሁሉ አለቃ ‘አላ፞ሁመ፞ አንተ ረቢ፞ ላ ኢላሀ ኢላ፞ አንተ። ኸለቅተኒ። ወአነ ዐብዱከ። ወአነ ዐላ ዐህዲከ ወወዕዲከ መ’ስተጦዕቱ። አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ፞ ማ ሶነዕቱ። አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፞። ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ። ፈግፊር ሊ። ፈኢነ፞ሁ ላ የግፊሩ ዙ፞ኑበ ኢላ፞ አንተ’ የሚለው ነው።
በሷ አረጋግጦ በቀኑ ካላት በኋላ ሳያመሽ በእለቱ የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው። በሷ አረጋግጦ በሌሊት ካላት በኋላ ሳያነጋ የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው።" [ቡኻሪ]

እነዚህ ምሳሌዎች ብቻ ናቸው። ሌሎችም ብዙ አሉ። ከነዚህ በተጓዳኝ ከውዱእ በኋላ፣ ከአዛን በኋላ፣ መስጂድ ስትገባ፣ ከመስጂድ ስትወጣ፣ ከሶላት በኋላ፣ ከምግብ በኋላ፣ ስትተኛ፣ ስትነሳ፣ ወዘተ ያሉትን ብትል ቆጥረህ የማትዘልቀው አጅር አለህ።
በጥቅሉ ጊዜህን መድበህ ዚክርን የህይወትህ አካል አድርገው። ለዚህ ከተቸገርክ እየሰራህ፣ እየተጓዝክ ብዙ መፈፀም ትችላለህ። ዚክር ትኩረት እንጂ የረባ ጥረት አይጠይቅህም። መልእክተኛው ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዳሉት "ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።"
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተመልከቱት 😍😍😍😍😍 አላህ እውቀትን ጨምርልን ( العلم في الصغر كالنقشي في الحجر ( በልጅነት ማወቅ ድንጋይ ላይ እንደመቅረፅ ነው 👏

@ONLYFORTRUTHERSJ
አሏህን መች እናስታውስ?
.
.
.
አብዛህኛዎቻችን አሏህን የምናስታውሰው የችግራችን ጊዜ ነው። አሏህን ጠይቄው ሰማኝ፣ በአሏህ ተመክቼ ዳንኩኝ፣ ጠይቄው ሰጠኝ፣ በሱ ተጠብቄ ጠበቀኝ። እንል እንደሆነ እንጂ በተሰጠን ነገር ከማመስገን ባሻገር የሰጠንን ነገር እንዲያዘልቅልን ዱዓ የምናደርገው ጥቂቶች ነን። አብዛህኛው አይደለም ሀጃ ሳይኖረው ዱዓ ሊያደርግ ቀርቶ ለተቸረው ውለታ ምስጋና ማድረሱንም እንጃ! ለዚህም ይመስላል በችግር ሰዓት መፈናፈኛ እስኪታጣ ድረስ በባለ ጉዳዮች የተጨናነቁት መሳጅዶች በአማን ጊዜ ጭር ማለታቸው። አብዛህኛዎቻችን አሏህን ባጣ ቆየኝ አድርገነዋልና!

ዱዓ ልታደርጉ አስባችሁ ምን ብላችሁ ዱዓ ማድረግ እንዳለባችሁ ጠፍቶባችሁ አያውቅም? ምክኒያቱም ዱዓ ሁለት አይነት እንደሆነ አናውቅማ! አዎ! ዱዓ ሁለት አይነት ነው፦ #የአምልኮ_ዱዓ እና #የጥያቄ_ዱዓ። የጥያቄ ዱዓ ሁላችንም ሲቸግረን የምናደርገው የዱዓ አይነት ሲሆን፤ የአምልኮ ዱዓ ደግሞ ምንም ጉዳይ ባይኖረንም እንኳ ከአሏህ ተብቃቂ አለመሆናችንን፣ ከሱ ሀጃ ኖረንም አልኖረን እሱን ችላ አለማለታችንን የምንገልፅበት፣ ከዚህ በፊት ስለሰጠን ፀጋ የምናመሰግንበት፣ የሰጠንን እንዲያዘወትርልን የምንማፀንበት የዱዓ አይነት ነው።

በጥቅሉ #አልሐምዱሊላህም ዱዓ ነው ለማለት ነው። አዎ! ለኛ ለሙስሊሞች የኦክስጅን ያህል ዱዓም ያስፈልገናልና ከርሱ አንዘናጋ! የነብዩላህ ሱለይማንን ፈለግ እንከተል እንዲህ እንበል፦

«ጌታዬ ሆይ! ያቺን በእኔና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን የምትወደውንም በጎ ሥራ እንድሠራ ምራኝ፡፡ በችሮታህም በመልካሞቹ ባሮችህ ውስጥ አግባኝ»[ ሱረቱ አል-ነምል - 19 ]
.
@ONLYFORTRUTHERSJ
قَالَ ﷺ: «مَنْ صَلَّ عَلَيَّ صَلاةً صَلَّ اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشَراً»

☞ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

እንዳሉት‘መን ሶላ ዓለየ ሶላተን ሶለልሏሁ ዐለይሂ ቢሃ ዐሸራ

በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ አስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል

❤️❤️🍃🍃🍃መልካም ጁምዓ🍃🍃🍃❤️❤️

@ONLYFORTRUTHERSJ
🌸🍃:::::::በዚህ ዱኒያ ለይ::::::::🍃🌸

☞ሁሌም ካንተ የባሱ ሰዎች አሉ

☞አንተ የምትጠላውን ህይወት
በዙ የሚመኛት ሰው ይኖራል ።

☞ሌላው ኖሮት አንተ የሌለህን ነገር
በመመልከት አትዘን‥

አንተ ኖሮህ ሌላው የሌለውን ነገር
ተመልከትና አላህን አመስግን። 🌹


@ONLYFORTRUTHERSJ
❥:::::::::::::::::::::::❥❥:::::::::::::::::::::❥

አንድ ሰዉ ለሶስት ቀናት በሰኸረተል መዉት ተሰቃየ ባለቤቱ ረሱል ( ﷺ ) ዘንድ አቀናች፡፡

ወይ ሞቶ አያሳርፈን እሱም አያርፍ ወይ ምላሱ ሸሐዳ አትል ግራ ገባን እኮ ያ ረሱለላህ ( ﷺ ) አለቻቸዉ፡፡

ረሱል ( ﷺ ) እናቱን አምጡልኝ አሉ፡፡ እናቱም ተጠርታ መጣች፡፡ ልጅሽ ምን አይነት ሰዉ ነዉ? ብለዉ ጠየቋት፡፡ እናትየዉም እንዲህ በማለት መለሱላቸዉ:– ከሰጋጆቹ ከዛኪሮቹ መሀል ነዉ አለቻቸዉ፡፡

ረሱልም ( ﷺ ) እሱን አደለም የምልሽ ካንቺ ጋራ እንዴት ነዉ? አሏት፡፡ እሷም ልቤ አዝኖበታል ያ! ረሱለላህ ( ﷺ ) ዋሽቼዎት በዋሕይ መጋለጥን አልፈልግም፡፡ ፈገግተኛ ፊቱን ለሚስቱ ኮስታራዉን ለኔ፣ መልካም ንግግርን ለእሷ ለዛ ቢሱን ለኔ፣ ከምግብ ጥሩዉን ከልብስ ቆንጆዉን ለእሷ እሷ ከመረጠችዉ የተረፈዉን ለኔ ስትል ብሶቷን ገለፀች፡፡

ይህኔ ረሱልም ( ﷺ ) እሳት አምጡልኛና ላቃጥለዉ አሉ፡፡ እናቲቱ ጮኸች ያ! ረሱለላህ ( ﷺ ) ልጄ የአካሌ ክፋይ እኮ ነዉ፡፡ ነብሴን ፊዳ አደርግለታለሁ አትንኩት አለች፡፡

ረሱልም ( ﷺ ) ይህን እኮ ነዉ የምልሽ አንቺ ይቅርታሽን ካልሰጠሽዉ የጀነትን ሽታ አያገኝም አሏት፡፡ ይኸዉ ጌታዬ መልዕክቶቹም ከልቤ ይቅር እንዳልኩት ምስክሮቼ ናቸዉ አለች፡፡ ሰዎችን ወደ ሰዉዬዉ ቤት ላኩ፡፡ ሰዉየዉም ሸሐዳ ከምላሱ እንደወጣ ነብስያዉ ወጣች።

ወዳጄ ሆይ!

ባልዋን በጀነት ማግኘት የምትፈልግ ሴት በእናቱ ሐቅ ላይ ታበረታዋለች ጀነትን የሚመኝ ሰዉ በወላጆቹ ሐቅ አይደራደርም፡፡ ከአላህ ሐቅ ቀጥሎ ከባዱ የነሱ መሆኑን አይዘነጋም እነሱ ማለት አጥፍተህም የሚወዱህ ዉብ ልቦች ናቸዉና ሁሌም ብታጠፋ ሁሌም ሁሌም ይቅርታን ጠይቅ። አደራ አደራ

📩::::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::📩


@ONLYFORTRUTHERSJ
ጉዛህን ቀጥል !

አንዲት መርከብ በዙሪያዋ ውሃ ስላለ አይደለም የምትሰምጠው።ወደ ውስጧ በሚገባው ውሃ እንጂ። አንተም በዙሪያህ ለከበቡህ ስህተት ለቃሚዋች ፣ ተቺዋች ፣ ተሳዳቢዋች ቦታ አትስጣቸው ቦታ የሰጠሃቸው ለት ያሰመጡሃል !!


🍂 @ONLYFORTRUTHERSJ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
☞ አይናችን ሃላልን ለማየት ይናፍቃል፤

☞ ጆሮዋችን ሀላል የፍቅር ቃላቶችን ለመስማት ናፍቀዋል፤

☞ እጆቻችን ሃላልን ለመንካት፣ ስጦታን ለመቀበል ጓግተዋል

☞ እግሮቻችን ሃላል ላይ ለመቆም ቸክለዋነል፤

☞ አንደበታችን ከሃላል ጋር ለመጫወት ናፍቀዋል፤

☞ ጥርሳችን፣ፊታችን በሃላል ፈገግ ለማለት ተርበዋል፤

☞ ጐናችን በሃላል ጋደም ለማለት መጠባበቅ ተያይዘዋል፤

☞ ያረብ አንዳች አካላችንን ሃራም ላይ ሳታሳርፍ በሃላል ዘውጀን

አሚን ያረብ 🤲🤲

@ONLYFORTRUTHERSJ
አላህ ወድሱ ተመላሽ ወጣቶችን ይወዳል። በመላእክቱም ላይ ስለ ወጣት ዓቢዶች ያወሳል። በወጣትነት አላህን መግገዛት፣ እሱን መታዘዝ ትልቅ ጀግንነት ነው። አትሂዱ ተመለሱ። አላህ ይወዳችኋል።

ከቂያማ ቀን የሐሩር ጭንቀትም ጥላ እንደምታገኙ ቃል ተገብቶላችኋል።


@ONLYFORTRUTHERSJ
Forwarded from ABX
ከቻልክ ... ከሆነልህ ...
***
የዕለቱን የሶላት ማሰርያህን ዊትር አድርግ፡፡ ወቅቱም ከሱብሒ ሶላት በፊት ይሁን፡፡ በአንዲት ረካዓም ብትሆን ወትር፡፡
ከዚያም በመስገጃህ ላይ ትንሽ ተቀመጥ፣ አላህን አውሳ፣ ኢስቲግፋር አድርግ፣ አላህን ቀድስ፣ ለዱዓ እጅህን አንሳ፣ ወሳኝ ሰዓት ነዉና፡፡

ትንሽ ቆይቶ ሱብሒ ሶላት ይገባል፤ ለአዛን አድራጊው ተከታተለዉና የሚለዉን በል፣ ከአዛኑም በኋላ ለአላህ መልዕክተኛ ወሲላን ለምን፣ ምልጃቸዉን ልትታደል ትችላለህና፤
ቀጥሎ የሱብሒን ሶላት ሁለት ረከዐህ ሱንና እንዳትረሳ፣ ከዚያም በጀማዓ ሱብሒን ስገድ፣ ከሱብሒ በኋላ አዝካሮችን አድርግ፣ ከቁርኣን ትንሽ አንብብ፣
እንዳትተኛ፣ ዚክር እያደረግክ ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ቆይ፡፡ ስትነሳ ፊትህ እንደሚበራ፣ ሪዝቅህ እንደሚሰፋ፣ ልቦናህ እንደሚረጋጋ እወቅ፡፡ በየቀኑ ይህንኑ ደጋግም፤ ዉሎህ ደስ ስለሚል ደስ ይበልህ፡፡


http://www.tg-me.com/MuhammedSeidABX
2024/06/19 19:12:48
Back to Top
HTML Embed Code: