Telegram Web Link
ረመዷን ሆይ ጥለኸኝ ልትሄድ ነው

አንተስ ትመጣለህ ይሄ የታወቀ ነው!
መገናኘታችንን አላህ ነው የሚያውቀው
የጀመርኩት እንጂ ያጋመስኩት ሳይማስለኝ!

🌿 ለካስ ተነስተሃል ልትሄድ ጥለህን ።
ረሂሙ ጌታዬ ዳግም ያገነኘን ያረቢ🤲🤲🌺
Forwarded from Salah Jibril via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from "ኡማ ቲቪ " Tv
ዒድ ሙባረክ!

ጨረቃ ባለመታየቷ የኢድ አል-ፊጥር በዓል የፊታችን እሁድ መሆኑ ታውቋል!

ዛሬ ጁምዓ ግንቦት 14 የሸዋል ወር አዲስ ጨረቃ በሳዑዲ አረቢያ ባለመታየቷ የኢድ አልፊጥር በዓል የፊታችን እሁድ ግንቦት 16 ወይንም ሜይ 24 መሆኑ ተገልፆል::

ነገ ቅዳሜ ግንቦት 15 ወይንም ሜይ 23 የረመዳን የመጨረሻው 30ኛ ቀን እንደሚሆን ተገልፆል፡፡

የነገዋንም ቀን የመጨረሻ የረመዳን ቀን ናትና ሳንዘናጋ በኢባዳ እናሳልፋት!

አላህ ፆማችንን ይቀበለን

ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም!
------------------------------------------
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም አድራሻችንን ይቀላቀሉ
Join ይበሉ 👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFACld9qu1NhysxDHw
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የፍርዱ ቀን ባለቤት የሆንከው
ጌታዬ አላህ ሆይ:-የፆምነውን
የረመዳን ፆም እና የቀራነው ቁርዓን
የቂያም ጊዜ የሚመሰክሩልን እንጂ የሚመሰክሩብን አታድርጋቸው!
አሚን!

JOIN US
👇👇👇
@ONLYFORTRUTHERSJ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😭😭። እናቴን ማን ነው የሚገዛኝ ?🚫

💞ኡሚ ኡሚ ኡሚ 💞

አንድ ወጣት በጣም ቆንጆ የሆነች ልጅ ይወድና ለጋብቻ ያጫታል ከተጫጩ በኃላ ግን ግልፅ በሆነ አረፍተ ነገር እናቱን እንደማትወዳት እና አብራቸው መኖር እንደማትፈልግ ትነግረዋለች ።

እሱን ብትወደውም እናቱን ግን ልትወድለት አልቻለችም እናቱም
በእድሜ የገፉ ስለነበሩ ልጂቷ ብዙ ታስቸግራቸው ጀመር።

ከዛም ልጅ እንደማያገባትና እንደሚለቃት አስረግጦ ሲነግራት ልጂቱ ልጁን ስለምትወደው ደነገጠች እንደምታስተካክልና እናቱን እንደምታከብር እንዲያገባት ተማፀነችው።

ልጁም ካስተካከልሽ ብሎ እሽ አላት ከዛም የሰርጋቸው ቀን ደረሰ ምሽቱ ላይ ሠዎች በተሰበሰቡበት መሐል እናቱ ተጋባዥ እንግዶችን ለማስተናገድ በደስታ ሽር ጉድ ሲሉ

ሙሽሪት በንዴት ይህችን አሮጊት እናትክን ወዲያ በልልኝ አታሳየኝ ከቻልክ እንደውም ሽጣት አለችው።

ልጁም ፈገግ ብሎ ተነሳና ሰዎች ከተሰበሰቡት መካከል
እናቴን ማን ነው የሚገዛኝ "ለ 3 ጊዜ በተከታታይ ማለት ጀመረ

እናቱም ከልጃቸው አንደበት የሰሙትን ማመን አቃታቸው ማዘንና ማልቀስ ጀመሩ እንግዶቹን በጣም ተገረሙ አዘኑ ከዛም ሙሽራው ወደ ሙሽሪት ዘወር አለና
"አየሽ እናቴን ማንም ሊገዛት አልቻለም
ለምን እንደሆነ ታቂያለሽ? ምክንያቱም እናት ውድ ነች እናቴ ከምንም በላይ ውድ ነች ዋጋ አይተምናትም እኔ ግን
እናቴን እገዛታለው አንችን ደግሞ ሸጨሻለው

ፈትቼሻለው በማለት የሰርጉ ቀን ቀለበቱን ከፊቷ ላይ በመወርወር ትቶላት እናቱን ይዞ ሲወጣ ወዲያው ከእንግዶቹ አንዱ ተከተለውና እንዲህ አለው "

ለሴት ልጄ ከአንተ የተሻለ ጥሩ ልጅ
አላገኝም ፍቃደኛ ከሆንክ ልጄን ልዳርልክ
ብሎት ልጁን ይዞ ወደ ቤቱ ወሰደው ልጁም የዛን ሰው ልጅ ሲመለከታት እጅግ ውብና አደበኛ ነበረች አገባትም ለባሏም ሆነ ለባሏ እናት ፍቅሯን ያለ ገደብ ትሰጣቸውና ትንከባከባቸው ጀመር።

የወለደቻት እናቷ እስክትመስላት ድረስ
የሚጠበቅባትን ሁሉ መወጣት ጀመረች።

መልካምና ደስተኛ የሆነ ህይወት ይኖሩ ጀመር።

አንድን ነገር ለ አሏህ ብሎ የተወ አሏህ የተሻለውን ይወፍቀዋል

እህቴ ከታሪኩ ብዙ ቁምነገሮችን ተማሪበት፣ ለጓደኞችሽም አጋሪው።

🌹:::::::::::::Telegram:::::::::::::🌹

@ONLYFORTRUTHERSJ
አደራ እንዳይረሱ

የአላህ መልዕክተኛ(ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል፡―

«ዘካተል ፊጥርን ከሰላት በፊት የሰጠ ተቀባይነት ያለው ዘካ ይሆንለታል። ከሰላት በኃላ የሰጠ ግን እንደማንኛውም ተራ ሰደቃ ይሆንለታል»
094 616 9555:
🌷🌷
💚 የኔ ውድ ጓደኝ❤️
💛 የኔ ሁሉ ነገር 💛
❤️ አንተን/ቺን/በመተዋወቄ በጣም ደስተኛ ነኝ 💚
💐 የዘንድሮ የኢድ አል ፈጥር በዓል
😊 የደስታ
😌 የጤና
🤑 የብልጽግና
😘😘😘 መልካም ነገሮች ሁሉ ወዳንተ/ቺ/ ሚመጡበት
💐💐💐 ስኬታማ ምትሆንበት/ኝበት/ 💐💐💐🌹🌷🌹🌺🌺🌸🐓🐑🐃 ይሁንልህ/ሽ/🐓🐑🐂🌷🌹🌺🌸💐🌼💐💐🎍🎍🎍
💚
💛
❤️
ይህን የመልካም ምኞት መገለጫ ለሚወዱት ሰው ሁሉ ያካፍሉ ከነዛ ሠዎች መሃል እኔ አንዷ ከሆንኩ forward ማድረግ ይቻላል

💐🌹🌷🌺🌸🌼💐🌷🌸🌷🌺🌷🎍🎍🎍🎍🌺🌺💐
ምኞት ከላክላቸው/ሽላቸው/ሰዎች =ዕሩቡን መልሰህ/ሽ/ካገኘህ/ሽ👉 🙂 ግማሹን " " 👉👍
ሙሉዉን " " 👉 በጣም እድለኛ ሰው ነህ/ሽ/
❤️ መልካም እድል ❤️
ኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢ
ድድድድድድድድድድድድድ..
.....................................
Eid Mubarak ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
May Allah (s.w) accept all our good deeds that we have made in the sacred month and I wish you and your families all the best version of happiness ... May your Eid be full of joy and peace .. 🥰🥰🥰🥰
Sister yasmina
@ONLYFORTRUTHERSJ
😍😍😍😍😍😍😍😍😍

​አንድ ከአላህ መንገድ የራቀ ዱንያውን በአኺራው የገዛ ወጣት ነበር። ወጣቱ የሚኖረው አላህን ሱብሃነሁ ወተዓላ ከሚፈሩ ሰዎች መንደር ሲሎን ሰዉ ሁሉ እንዲስተካከል እንዲሁም የታላቅ ወንድሙን ፈለግ እንዲከተል ይመክሩታል። ይህ ልጅ ግን የሚሰማ አይደለም። ስለ ታላቅ ወንድሙ ካነሳን አይቀር የዚህ አስቸጋሪ ወጣት የ4አመት ታላቁ ነው። ቁርዓንን ከመጨረስም አልፎ በቃሉ ሃፍዟል። እንደ ዘመኑ ሃፊዞችም ሃፍዞ ከሃፈዘው ቁርዓን ተቃራኒ አይተገብርም። ባይሆን አላህ እንዲሸመድድ በወፈቀው ቃሉ ውስጥ ያሉትን ትዕዛዛቶች እንዲሁም ክልከላዎች በጥንቃቄ ያከናውናል።

ከእለታት አንድ ቀን ይህ አስቸጋሪ ወጣት ከዚያ አላህን ከሚፈራው ከታላቅ ወንድሙ ይማር ዘንድ አባት ሁለቱን ለጉዞ ያሰናዱ ጀመር። ለታላቅ ወንድሙ የጉዞውን አላማ በደንብ ያወጉት ሲሆን ለታናሽ ወንድሙ ግን አልነገሩትም። ታናሹ አስቸጋሪ ወንድም ይህን ጉዞ ባይቀበልም አባት እናት እንዲሁም ወንድሙ እንደምንም ብለው አሳምነውታል። እነሆ በጉዟቸው ቢያንስ የታላቅ ወንድሙን ባህሪ ይላበስ በማለት ከቤት ወጥተው መጓዝ ጀምረዋል።

ከቤት የተነሱት የሱብሂን ሰላት ሰግደው ሲሆን ከረጅም ጉዞ በኋላ ወደ ረፋድ አካባቢ የሆነ ጫካ ውስጥ ይገባሉ። ይሄና ታላቅ ወንድሙ የለመደውን #የዱሃ ሰላት ለመስገድ ውዱዕ ማድረግ ጀመረ። ታናሹም እኔ አሁን መስከድ ስለማልፈልግ ሽንቴን ሸንቼ መጣሁ በማለት ከወንድሙ ተለይቶ ይጓዛል። ይሄኔ አላህ ይህን ወጣት ሊያስተካክለው ይመስል አንድ አይቶት የማያውቀውን #ፍጡር ይልክበታል። ፍጡሩን ሲመለከቱት ያስፈራል። ሰውነቱ ሙሉ በሙሉ ጥቁር ነው።አብዛሃኛው የሰውነቱ ክፍል በፀጉር የተሸፈነ ሲሆን ከድፍን ጥቁርነቱ ጋር ተዳምሮ ላየው ሰው እጅክ ያስፈራል።

ወጣቱ ይህን አላስተዋለውም ነበር። ድንገት ይህ ፍጡር ከዛፍ ላይ በመዝለል ፊት ለፊቱ ድቅን አለበት። የሚያደርገውን አጣ ተርበተበት እየሮጠም ለማምለጥ ሞከረ። ነገር ግን ሊሳካለት አልቻለም። ምክንያቱም ይህ ፍጡር በጣም ፈጣን ስለነበር ዞሮ እፊት ለፊቱ ድቅን አለበት። አንዳንዴ ስንደነግጥ ለማያወራን ነገር እንደምናወራው ወጣቱም ለዚህ ፍጡር ያወራ ይመስል "አንተ ማን ነህ?" በማለት እየተርበደበደ የተቆራረጡ ሲቃ የተናነቃቸው ቃላቶቹን ሰነዘረ።

ዳሩ ግን እንስሳ መናገር አይችልምና የዚህ #አስፈሪ #ፍጡር ምላሽ ዝምታ ነበር። ላጩን እያንጠባጠበ ከቀጭ ወደ ግራ ይዟዟራል። አንዳንዴ አፋን በሃይል ይከፍተዋል። የሚያጉረመረም ድምፁ ከርቀት ለሰማው ልብ ይሰብራል። ወጣቱ የሚሆነው አጣ። መሬት ጠበበችበት። ይሄኔ ያኔ ከአላህ መንገድ ርቆ ሲከውናቸው የነበሩትን እኩይ ተግባሮች ማስታወስ ጀመረ። እያንዳንዱ ስራው እንደ መፅሐፍ ፊቱ ላይ ይገለጥ ጀመር። የሰፈሩ ሰው፣ እናቱ፣ አባቱ፣ ወንድሙ ሲመክረው እንቢ ማለቱ ቆጨው። በውስጡም እንዲህ ሲል ተናዘዘ። 'አላህዬ !! ከዚህ ጭንቅ ገላግለኝ እንጂ ዳግም አንተን ላለማመፅ ቃል እገባለሁ"

ይህንን ንግግሩን ሳይጨርስ ታላቅ ወንድሙ ከሩቅ ትልቅ ዱላ ይዞ ወደ እንስሳው መሮጥ ጀመረ።ይህም ወጣት ወንድሙን እንዲመለስ ተማፀነው። ነገር ግን ያኛውም ጀግና ስለነበር በያዘው ዱላ አስፈሪውን ፍጡር ይነርተው ገባ። እንስሳ ቢጎዳ ሳይጎዳ አይተውም እንዲሉት አንድ ተሳክቶለት ያ አደገኛ ፍጡር ታላቅ ወንድሙን አንድ ግዜ በሃይል ነከሰው። ይሄኔ በታላቅ ወንድሙ መነከስ የተማረረው ወጣት እንስሳብጅውን በሃይል ባገኘው ዱላ ቀጥቅጦ ገደለው።

ወዲያውኑ አይኑ በእንባ እንደተሞላች ወደ ታላቅ ወንድሙ በመዞር ሲመለከተው ታላቅ ወንድሙ ጣቱን ወደ ሰማይ ቀስሮ እያጣጣረ ነው። ወንድሜ!! ወንድሜ!! እያለ ቢጮህም ማንም ሊደርስለት አልቻለም። ብዙ ደም ስለፈሰሰው ወደ ቀጣዩ አለም አኺራ ሸሃዳን ብሎ በሰላም ተሰናበት።

ይሄኔ ኑበር ያ ወጣት የወንድሙን ጀናዛ አጥቦ፣እራሱን ከዚህ በፊት ጀናዛ እንደነበር በማሰብ ንፁህ በሆነ መልኩ ገላውን ታጥቦ ወደ አላህ መንገድ ተመለሰ። ከዚያም በኋላ ወደ ተለያዩ ሃገራት እየዞረ ኢልም በማካበት ሃገሪቱ ውስጥ አለ የተባለ ታዋቂ ዓሉም ለመባል በቃ።

ከዚህ አጭር ልብ-ወለድ የምንማረው አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ማንኛውንም ሰው በፈለገው መንገድ ያቀናል። የፈለገውንም ያጠማል። እኛ ግን ጥሪ አድራሾች ሆነን ተሹመናል።

@ONLYFORTRUTHERSJ
@ONLYFORTRUTHERSJ
@ONLYFORTRUTHERSJ
@ONLYFORTRUTHERSJ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስሞት.....

- ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣

- ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ

ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡

1- ልብሴን ያወልቃሉ፣

2- ያጥቡኛል፣

3- ይከፍኑኛል፣

4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣

5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣

6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣

7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡

ከነኚህ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡

8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል

- ቁልፎቼ

- መጽሐፎቼ

- ጫማዎቼ

- ልብሦቼ …..

በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡

- በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣

- የዓለም እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣

- የኢኮኖሚው ቀውስም አልተፈጠረም፣

- በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ ይወጣል፣

- ንብረቴ የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣

- ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤

- ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል

- ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤



ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! …

በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ

1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ

2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣

3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣

የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ

ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!!

1- መልክህ፣

2- ሀብትህ፣

4- ጤናህ፣

5- ልጅህ፣

6- ቪላህ፣

7- ዝናህ፣

8- ሚስትህ/ባልሽ

ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ

እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡

እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ

ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡

እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ

1- በግዴታዎች፣

2- በሱንና ነገሮች፣

3- በድብቅ መፅውት፣

4- መልካም ሥራ አብዛ፣

5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣

ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡

መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡


ምንጭ ፡ ጠሪቁ ተውበህ
ከ abu kalid wa islam


ይነበብ ይነበብ 👆👆👍 አንብበው ከሚጠቀሙት ጋር ያድርገን አሚንንንንን
😭😭😭😭😭😭😭😭😭
°•:
ቤታችን በር አለው !
"ቀናዓ" ወይም አላህ የሰጠንን #መውደድና በዚያ መብቃቃት ከሙስሊሞች መልካም ባህሪያት አንዱ ነው!
በአንድ አካባቢ እጅጉን ደካማ በሆነ ቤት ውስጥ የሚኖሩ አንዲት ባሏ የሞተባት ሴት እና #ህፃን ልጇ ነበሩ ። ምንም እንኳ ድሆች ቢሆኑም አላህ በሰጣቸው #ፀጋ አመስጋኞችና ደስተኞችም ነበሩ። ታዲያ ቤታቸው እጅጉን የደከመ ከመሆኑ የተነሳ በክረምት ወቅት ዝናብ በጣም ያስቸግራቸው ነበር። ከእለታት አንድ ቀን ምሽት ላይ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ #ዝናብ አስቸገራቸው ፤ በከተማው የነበሩ ሰዎች ሁሉ ወደ ቤቶቻቸው ገበተው ቢጠለሉም እነሱ ግን ከላይ እንደ ጣሪያ አድርገውት የነበረው ብጥስጣሽ ጨርቅ ምንም ሊጠቅማቸው አልቻለም ነበርና ውሃም ወደ ቤት ይገባ ጀመር። የዝናቡን ክብደት የተመለከተው #ህፃንም ወደ እናቱ ሰውነት ጠጋ ብሎ ልጥፍ ይላል። ምን አልባትም ከእናቴ እቅፍ ሙቀትን ባገኝ ብሎ ነበር! " #እናት " ይሁንና የእናቱ ልብስ በጣም በውሃ ረጥቦ ነበርና ምንም ለውጥ አላገኘም። የልጇን ሁኔታ የተመለከተችው #እናት በፍጥነት እንደምንም ብላ የቤታቸውን #በር በመገንጠል ከአንድ የቤታቸው ኮርነር ጋር አስደግፋ በውስጡ እንዲጠለሉ አደረገች። ይህንን የተመለከተው ልጇም በጣም ተደስቶና ፈገግ ብሎ እናቱን እየተመለከተ ፦ (እነዚያ ለቤታቸው #በር የሌላቸው #ድሆች ግን ይህን ያህል ዝናብ ሲወርድባቸው እንዴት አድርገው ከዝናቡ ይጠበቃሉ?) ሲል ጠየቃት።
#ህፃኑ ልጅ በዚህ በጭንቀት ወቅት እራሱን ከሃብታሞች ተርታ አሰልፎ ከርሱ የባሱ #ድሆችን ማስታወሱ አስገራሚም አስተማሪም ነበር!
#አላህ በሰጠን መብቃቃት እና እርሱ የወሰነልንን ወድዶ መቀበል ምንኛ ያማረ ባህሪ ነው !?
#ጌታችን ሆይ!
በሰጠሃቸው ተብቃቂዎችና ደስተኞች አድርገን!

JOIN US
👇👇👇
@ONLYFORTRUTHERSJ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/29 20:25:29
Back to Top
HTML Embed Code: