የእትዮጵያ የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ!!!
_______

1ኛ ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡

2ኛ የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡

3ኛ ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች:-
፩=በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው
፪=በራሱ ፈቃድ
፫=በጤና ጉድለት
፬=በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት
፭=በሞት ናቸው፡፡

4ኛ የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:-
፩= በእርጅና
፪=በህመም
፫= ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ
፬= በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ
፭=በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡

5ኛ የጡሮታ አበል በይርጋ የሚዘጋው:-
፩=የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ3 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡
፪=የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 3ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም)::

6ኛ በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:-
= ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል፡:ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡

7ኛ በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ,ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡

8ኛ በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ ፡፡

9ኛ የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው፡፡

10ኛ ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:-
፩=በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2)
፪=የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ
፫= የጡረታ መለያ ቁጥር
፬= የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ
፭= የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ
፮= የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ
፯= የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ
ናቸው፡፡

የደሞዝ አሰራር እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን? ክፍል -1
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱት!
👇👇👇👇
https://youtu.be/rNcfrxbTyxo
https://youtu.be/rNcfrxbTyxo
https://youtu.be/rNcfrxbTyxo
የደሞዝ አሰራር እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን? ክፍል -2
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱት!
👇👇👇👇
https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg
https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg
https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg
🛑 ዳታ ማይኒንግ ምን ዓይነት ጥቅም አለው?

ዳታ ማይኒንግ ብዙ መጠን ያለውን ዳታ በመመርመር እና በመተንተን በተለያዩ መስኮች ችግር ፈቺና ትርጉም አዘል መረጃዎችን ለይቶ ለማወቅ ትልቅ አበርክቶው አለው።

በዘርፉ አሜሪካ፣ ቻይና፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን እና እስራዔል ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ እና ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ከሚሰሩ ሀገራት መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡

ተመራማሪዎች የንግድ ተቋማት እንዲሁም መንግሥታት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔን እንዲያሳልፉ ዘርፉ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው የሳይንስ ዳይሬክት ድረ-ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

ዳታ ማይኒንግ እንደ ጤናና ትምህርት ባሉት መስኮች የሚያጠነጥኑ መረጃዎችን በተገቢ መልኩ በመረዳት ዜጋ ተኮር ስራዎች ላይ ለመስራት ዕድል ይፈጥራል፡፡ አገልግሎት ሰጪ እና በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማትም የደንበኞችን ፍላጎት በማወቅ እርካታን ለማሳደግ እንዲችሉ ጉልህ ሚና አለው፡፡
#MCT
ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድን ነው?

ይህን ቃል በተለያዩ አጋጣሚዎች ሳንሰማው አንቀርም በተለይ አሁን ላይ ይህ ቃል ለብዝዎቻችን እምዛም አዲስ አይደለም ፤ በተለያዩ ሚዲያ ነክ በሆኑ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ወይም ቢዝነሶች አገልግሎታቸውን ሲያስተዋውቁ ከዝርዝራቸው መካከል "ዲጂታል ማርኬቲንግ" የሚል እናገኛለን ፣ "ዲጂታል ማርኬቲንግ አሁን ላይ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ ውጤታማ የማርኬቲንግ ዘዴ ነው" ሲባል እንሰማለን ፣ "ዲጂታል ማርኬቲንግን በመጠቀም ዘመናዊዉን የማርኬቲንግ ዘርፍ ሊቀላቀሉ እና ቢዝነስዎን ሊያሳድጉ ይገባል" የሚል መልዕክት ያዘሉ የማነቃቂያ ጽሁፎችም አጋጥመውን ይሆናል ... ለመሆኑ ይህ ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድን ነው? ከተለመደው የማርኬቲንግ ዘዴስ በምን ይለያል? እውነት ዲጂታል ማርኬቲንግን በመጠቀም ቢዝነስን ማሳደግ ይቻላል? በየትኛው ደረጃ ላይ ያሉ ቢዝነሶችስ ናቸው ዲጂታል ማርኬቲንግን መጠቀም የሚችሉት?

እስቲ እነዚህን እና መሰል ከዲጂታል ማርኬቲንግ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በሚመልስ መልኩ በዲጂታል ማርኬቲንግ ዙርያ አጭር ዳሰሳ እናድርግ።ዝግጁ ናችሁ? ተከተሉኝ፦

በመጀመሪያ ደረጃ ዲጂታል ማርኬቲንግን በቀላሉ እንድንገነዘብ  ስለማርኬቲንግ (Marketing) ጥቅል የሆነ ግንዛቤ እንውሰድ። ማርኬቲንግ (marketing) ማለት   "በምርት እና አገልግሎቶች ላይ የገበያውን ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል እሴትን (Value) የማጥናት  ፣ የመፍጠር እና ለተጠቃሚው የማቅረብ ሂደት ነው። " ከዚህ ገለጻ እንደምንረዳው ማርኬቲንግ "ሂደት" (process) ነው። ይህ ሂደት :-  ምርቱን  ወይም አገልግሎቱን ይገዛሉ ተብለው የሚታሰቡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማጥናት እና መለየት ፣ ፍላጎታቸውን መረዳት  እና ችግራቸውን ማዳመጥ ፣ ፍላጎታችውን ሊያሟላ ፤ ችግራቸውንም ሊፈታ የሚችል እሴትን አጥንቶ በምርቱ ወይም አገልግሎቱ ላይ ማከል ፣ ከዚያም ማስተዋወቅ ፣  ቀጥሎም ለተጠቃሚዎች አመቺ በሆነ መልኩ ለሽያጭ ማቅረብ እና ከሽያጩም በኋላ ሸማቹ  ለምርቱ ወይም አገልግሎቱ ያለው ደንበኝነት ዘላቂ እንዲሆን መስራትን አቅፎ የያዘ ነው።

ማርኬቲንግ ማለት በጥቅሉ ይህ ከሆነ፤ ዲጂታል ማርኬቲንግ፡ ዘመናዊ የሆነ አንድ የማርኬቲንግ አካል ሲሆን ፤ ይህም ዘመኑ ያፈራቸውን አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን( በዋናነት ኢንተርኔትን በመጠቀም) ደንበኞችን የማፈላለግ ፣ ምርት እና አገልግሎቶችን የማስተዋወቅ እና ከደንበኞች ጋር ጥሩ ግንኙነትን በመፍጠር ደንበኝነታቸውን ዘላቂ የማድረግ  ሂደት ነው።ይህ  እንግዲህ በአጭሩ ስንገልጸው እንጂ ዲጂታል ማርኬቲንግ ሰፊ እና   የተለያዩ ዘርፎች ያሉት እራሱን የቻለ አንድ መስክ ነው።

ማርኬቲንግ ለየትኛውም ቢዝነስ መሳካት ትልቅን ሚና ከሚጫወቱ መሳሪያዎች መካከል አንዱ እንደሆነ ይታወቃል።ዲጂታል ማርኪቲንግ ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት ፤  ደንበኞችን ማፈላለግ እና ምርት እና አገልግሎቶችን ማስተዋወቅ የመሰሉ የማርኬቲንግ ስራዎች እንደ ጋዜጣ እና መጽሔት ባሉ የህትመት ውጤቶች ፣ እንደ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ባሉ የሚዲያ አውታሮች እንዲሁም በየመንገዱ በተተከሉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ይሰራ ነበር።ዲጂታል ማርኬቲንግ ከመጣም በኋላ ቢሆን  እነዚህ የማስተዋወቂያ መንገዶች ዛሬም ድረስ ይሰራባቸዋል።

ኢንተርኔት እና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ብቅ ብቅ ማለታቸውን ተከትሎ ጥቅም ላይ እየዋለ የመጣው ዲጂታል ማርኬቲንግ በተለመዱት የማርኬቲግ ዘዴዎች ለመስራት አስቸጋሪ የነበሩ የማርኬቲንግ  ስራዎችን በቀላሉ እና እጅግ ውጤታማ በሆነ መልኩ በመፈጸም  በማርኬቲንግ ዘርፉ ላይ ከአሰራር ጀምሮ ትልቅን ለውጥ ፈጥሯል።

ምንም እንኳን በኢንተርኔትን አማካኝነት የሚሰሩ የማርኬቲንግ ስራዎች ከዲጂታል ማርኬቲንግ ዘርፍ ትልቁን ድራሻ ቢይዙም ፤  ያለ ኢንተርኔት የሚሰሩ በዲጂታል ማርኬቲንግ ስር የሚካተቱ የማርኬቲንግ ስራዎች አሉ።ለምሳሌ :- በሞባይል መተግበሪያዎች (mobile apps) እና በአጭር የጽሁፍ መልዕክቶች (SMS) አማካኝነት የሚሰሩ የማርኬቲንግ ስራዎች በዲጂታል ማርኬቲንግ ዘርፍ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።ምክንያቱም ዲጂታል ማርኬቲንግ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው "አዳዳኢስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የሚሰራ የማርኬቲንግ ስራ ነው"።

ዲጂታል ማርኬቲንግ "E-CRM"  ላይ የተመሰረተ የንግድ አካሄድ ላይ የሚያተኩር ሲሆን "E-CRM (Electronic Customer Relationship Management)" ቃል በቃል ሲተረጎም "ኤሌክትሮኒክ የደንበኞች ግንኙነት አስተዳደር" እንደማለት ሲሆን ፤ ይህም አንድ ቢዝነስ ወይም ድርጅት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የደንበኞቹን መረጃ የሚያሰባስብበት እንዲሁም ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት እና መስተጋብር የሚያስተዳድርበት ስርዓት ነው።
#MCT
Xiaomi 2TB Orginal Flash Drive
USB 3.0 Metal U Disk
Strong and Durable
Scope of application: Mobile Phone,Computer ...
Working Current: Working Temperature 0°-60°C
👉Price 2500 1999 ETB 🇪🇹

🚨 On hand Available 👉@Four_lovee ያናግሩን ❗️❗️❗️

Visit our group https://www.tg-me.com/newmktttt

https://www.tg-me.com/Newmkttt
Myhammed Computer Technology MCT
እናመሰግናለን! 70,000+
MCT YouTube 7️⃣0️⃣0️⃣0️⃣0️⃣+ subscribers ደርሰናል
👇👇👇ሰብስክራይቭ ያድርጉ👇👇👇 https://www.youtube.com/c/MuhammedComputerTechnology
#Telegram ሰለ ቴሌግራም ማወቅ ያለብን 10 ወሳኝ ነገሮች

1ኛ :- ያለንበትን #ቦታ ለጓደኞቻችን መላክ እንችላለን መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የምንልክለትን ሰዉ እንመርጣለን ከዛ መላኪያዋን ከፍተን location የሚለውን ተጭነን ያለንበትን ቦታ መላክ ይቻላል ::

2ኛ :- ከኛ ወጪ ማንም ሰው ቴሌግራማችንን ማንም ሰዉ እንደይጠቀም ከፈለግን password ማዘጋጀት ይቻላል መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ሦስት መሰመር አለ እሱን አንዴ እንነካለን ከዛ setting የምለውን እንነካለን ከዛ privacy and security የሚለውን እንነካለን ከዛ passcode የሚለውን እንነካለን ከዛ passcode lock on እናደርጋለን ከዛ የምንፈልገውን password እናስገባለን ::

3ኛ:- እንዴት ቴሌግራም ብር እንዳይበላ ማድረግ ይቻላል
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ያለውን ሦስቷን መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ data and storage የሚለዉን እንነካለን ከዛ
when using mobile data -OF-አድርጉት ::

4ኛ :- የላክነዉን message ከደረሰ በኃላ delete ማድረግ ይቻላል እንዴት መጀመሪያ የላክነዉን message እንከፍታለን ከዛ ቦታዉ ላይ አጥብቀን እንዛለን ከዛ ከላይ የሚለውን Also delete receive የሚለውን ራይት እናደርጋለን ከዛ ሁለቱም ጋ delete ይሆናል ::

5ኛ :- እንዴት በአንድ የቴሌግራም አፕሊኬሽን ሁለት account እንጠቀማለን
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ
በቴሌግራሙ ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ ይህችን ምልክት ይንኩ ( v ) ከዛ new account ይለናል ከዛ መክፈት

6ኛ :- በተለይ ማታ ማታ ስንጠቀም ዓይናችን እንደይጎዳ ቴሌግራማችን በጥቁር መልክ እንድሆን ከፍለግን dark ,, black ,, colour እንድትሆን ከፈለግን ...
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ ገብተን ከሚሰጠን የመልክ ምርጫ የፈለግነዉን እንመርጣለን ::

7ኛ :- ቴሌግራም ያሉ ጽሁፎች አልነበብ እያሎት ተቸግረዋል ማለት ፊደሎቹ አንሰዉ ለዓይን አልታይ ካለ ፊደሎቹን ትልቅh ማድረግ ይቻላል እንዴት ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ እንገባለን ከዛ message text size የምል አለ እሱን እንነካና የፈለግነዉን ያህል ትልቅ ማድረግ ይቻላል ::

8ኛ:- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም ቻናል መክፈት እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን
ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ New channel የሚለውን ነክተን create new channel የሚለውን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፈት የፈለግነዉን የቻናል ስም እናስገባለን ::

9ኛ :- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም ግሩፕ እንከፍታለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ new group የሚለውን እንነካለን ከዛ create new group የሚለዉን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፍት የፈለግነዉን የግሩፕ ስም እናስገባለን ::

10ኛ :- እንዴት አድርገን profile photo መቀየር እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ set profile photo የሚለውን በመንካት የፈለግነዉን ፎቶ መቀየር ይቻላል ፡፡

https://www.tg-me.com/MuhammedComputerTechnology
በዘመናዊ ዲጂታል ቴክኖሎጂ መረጃ መያዝና አገልግሎት መስጠት ብልሹ አሰራርን የሚከላከልና የአገልግሎት አስጣጥ ችግሮችን  የሚፈታ መሆኑ ተገለፀ ።

ዲጂታለይዜሽን አስራርን በመጠቀም  ከዚህ በፊት በማዘጋጃ ቤቶች የነበረውን  የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር እንደፈታላቸው  የቻግኒ ከተማ ነዋሪዎች  ተናገሩ ።

በቻግኒ ከተማ አስተዳደር  በማዘጋጃ ቤት ሲስተናገዱ ያገኘናቸው  አቶ ሰይድ አሊ፣ መሪጌታ ልዑል ንጋቱና አቶ ዮሴፍ  ዑመር በሰጡት  አስተያየት ከዚህ በፊት ከቻግኒ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት  አገልግሎት  ለማግኘት  ለብዙ ጊዜያት ተመላልሰው ጊዜና ጉልበት እያባከኑ  እንደነበር  ጠቅሰው  አገልግሎት ለማግኘት እጅ መንሻ  በመስጠት ወደ ብልሹ አሰራር  እየገቡ  እንደነበር  ተናግረዋል ።

ማዘጋጃ ቤቱ ለዜጎች  ፈጣን፣ ቀልጣፋና ከብልሹ አሰራር  የፀዳ አገልግሎት  ለመስጠት  መረጃዎች  በዘመናዊ  ዲጂታል  ቴክኖሎጂ  በማደራጀት  ለአገልግሎት ፈላጊ ዜጎች  በፍጥነት  ተገቢውን  አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተገልጋዮች  ገልፀዋል ።

የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ምክትል  ከንቲባና ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ኃለፊ አቶ ገበየሁ አልማው ከዚህ በፊት በማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ፈልገው ለሚመጡ  ደንበኞች  አገልግሎት  ለመስጠትና  መረጃዎችን  ለማደራጀት  ከፍተኛ ችግር እንደነበር  ጠቅሰው ይህንን ችግር  ለመፍታት  ሙሀመድ ኮምፒውተር ቴክኖሎጂ  ያበለጸገውን በመጠቀም መረጃዎችን  ለማጠናከርና ፈጣንና  ቀልጣፋ  አገልግሎት  ለመስጠት  የሚያስችል  አዲስ ቴክኖሎጂ  እየተጠቀሙ  መሆናቸውን  ተናግረዋል ።

ይህ ቴክኖሎጂ ፈጣንና ቀልጣፋ  አገልግሎት  ለመስጠት  የሚያስችል፣ ብልሹ አሰራሮችን  የሚከላከልና ለመረጃ  ድህንነት  ከፍተኛ  ጠቀሜታ  ያለው መሆኑን የጠቆሙት  አቶ ገበየሁ መረጃዎችን በማዘመን ኦንላይን አገልግሎት  ለመስጠትና የውሸት  መረጃን  ለመከላከል  የማይተካ  ሚና ያለው መሆኑን  ገልፀዋል ።

የአዊ ብሄረሰብ  አስተዳደር ምክትል  አስተዳዳሪና ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ  ኃላፊ አቶ አይተነው  ታዴ በበኩላቸው እንደ ብሄረሰብ  አስተዳደር የከተማና መሠረተ ልማት ተቋማት የመረጃ አያያዝና  አገልግሎት  አስጣጥን ለማዘመን  በ6 ወረዳዎች  በዲጂታላይዜሽ አገልግሎት ለመስጠት  እየሰሩ መሆኑን  ጠቅሰው  በተወሰኑ  ወረዳዎች  ዘመናዊ  ቴክኖሎጂ  በመጠቀም  ፈጣንና ቀልጣፋ ወረቀት አልባ አገልግሎት መስጠት  መጀመራቸውን  ተናግረዋል ።

  ዲጂታላይዜሽ አገልግሎት የመልካም አስተዳደርና አገልግሎት በርካታ ችግሮችን  የሚፈታ መሆኑን የጠቆሙት ምክትል  አስተዳዳሪው  ይህንን ቴክኖሎጂ  በሁሉም  ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች  በመተግበር  የሚስተዋለውን  የአገልግሎት  አሰጣጥና የመረጃ አያያዝ  ችግሮችን  በዘላቂነት ለመፍታት  እንደሚሰሩ ገልፀዋል ።

የሙሀመድ ኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ባለቤትና
ቴክኖሎጂውን ያበለጸገው  ሙሀመድ አሚን  ቴክኖሎጂው ለመረጃው ደህንነት ፣  ፈጣን አገልግሎት  ለመስጠት ፣ ብልሹ አሰራርን  ለመከላከልና ለመቆጣጠርና የከተማው  ገቢ ለማሳደግ  ከፍተኛ ጠቃሜታ  ያለው ወረቀት  አልባ  አገል መሆኑን ተናግረዋል ።

  ቴክኖሎጂውን የተጠቀሙት  ተቋማት  ኦንላይን  አገልግሎት መስጠት  እንደጀመሩ  የጠቀሱት  ሙሀመድ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት  በመጠቀም  የሚስተዋሉ የአገልግሎት  አሰጣጥና የመረጃ አያያዝ ችግር መፍታት  እንደሚችሉ  ገልፀዋል ።
  የቻግኒ ከተማ አስተዳደር  የማዘጋጃ ቤት  የመረጃ አያያዝና አገልግሎት  አሰጣጡን  የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደርና የቻግኒ ከተማ አመራሮች  ጎብኝተዋል።

#contact mobile number
#0929273364
telegram
@mctplc

የአማራ ሚዲያ ኮፖሬሽን ዘገባ ከታች ያለው ይመልከቱ
https://youtu.be/1O4QGq3ym28
https://youtu.be/1O4QGq3ym28
https://youtu.be/1O4QGq3ym28

Awi Communication Facebook page ዘገባ ከታች ያለውን ይመልከቱ

https://www.facebook.com/100064870471180/posts/pfbid02xBQCtk8mjs6ojcsyM64gY35fLAWi5XaX7T4bMF4HJiD4QErE1M1ghGZNFuMc7iKSl/?app=fbl

https://www.facebook.com/100064870471180/posts/pfbid02xBQCtk8mjs6ojcsyM64gY35fLAWi5XaX7T4bMF4HJiD4QErE1M1ghGZNFuMc7iKSl/?app=fbl

https://www.facebook.com/100064870471180/posts/pfbid02xBQCtk8mjs6ojcsyM64gY35fLAWi5XaX7T4bMF4HJiD4QErE1M1ghGZNFuMc7iKSl/?app=fbl
2025/04/16 10:16:02
Back to Top
HTML Embed Code: