Telegram Web Link
የሞባይል መተግበሪያ ማበልጸግ (Mobile App Development)

📱 መግቢያ:
የሞባይል አፕሊኬሽን ማበልጸግ ማለት ለስማርት ፎኖች፣ ታብሌቶች እና ሌሎች የሞባይል መሳሪያዎች አፕሊኬሽኖችን የመፍጠር ስራ ነው። እነዚህ መተግበሪያወች ለተለያዩ አላማወች የተሰሩ ናቸው።

ከበርካታ አይነቶቻቸው መካከል
1) ከተግባር አንፃር:
→ የማህበራዊ ትስስር አፖች:
ምሳሌ: ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ሊንክድኢን፣ ዋትስአፕ
→ ለፕሮዳክቲቪቲ የሚውሉ እንደ ጎግል ድራይቭና ማይክሮ ሶፍት ኦፊስ አይነት አፖች
→ ለመዝናኛነት የሚውሉ እንደ ዩ ቲዩብአ ቲክቶክና ስፖቲፋይ
→ የኢኮመርስ አፖች እንደ አሊባባ፣ አማዞን፣ ሾፒፋይና ኢባይ
→ ለመገልገያነት የሚውሉ እንደ ፍላሽ ላይት፣ ካልኩሌተር፣ QR ስካነር
→ ለስፖርትና ለጤና የሚውሉ እንደ ማይፊትነስና ሄድስፔስ
→ ለትምህርት የሚውሉ እንደ ኻን አካዳሚ፣ ዩደሚና ኮርሴሪያ
→ ለገንዘብ ዝውውር የሚውሉ እንደ ፔይፓልና ቬንሞ
2) ከደቨሎፕመንት ሂደት አንፃር:
የሞባይል ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች በዋናነት ገበያውን የተቆጣጠሩት የጎግሉ አንድሮይድ እና የአፕሉ አይኦኤስ ናቸው:: ከነዚህ በተጨማሪ የቻይናው ሁዋዌ የጀመረው ሃርሞኒ ኦኤስ አለ። አንድ የሞባይል መተግበሪያ አበልፃጊ በዋናነት ታሳቢ የሚያደርገው ኦፕሬቲንግ ሲስተማቸው አንድሮይድ እና አይኦኤስ ለሆኑ ስልኮች ነው። ይህ ኔቲቭ አፖች ይባላሉ። ለአንዱ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ብቻ እንዲሰራ ተደርጎ የተሰራ አፕ ኔቲቭ አፕ ነው።
ስለዚህ ከማበልፀግ ሂደት አንፃር:
→ ኒቲቭ የሆኑ አሉ! ምሳሌ WhatsApp (iOS), Google Maps (Android).
→ የተዳቀሉ (ሃይብሪድ) አሉ! ምሳሌ ኢንስታግራምና ትዊተር አይነት
→ ዌብ አፖች አሉ! ምሳሌ ጎግል ዶክስ እና ፍሊፕቦርድ
→ ፕሮግረሲቭ ዌብ አፖች አሉ! ምሳሌ ስታርባክና ፒንተረስት
3) ከኢንዱስትሪና ዶሜይን አንፃር:
→ እንደ ዙምና ሴልስፎርስ ያሉ ቢዝነስ አፖች አሉ
→ እንደ ካንዲክረሽ ያሉ ጌም አፖች
→ እንደ ጎግል ማፕስ፣ ኡበር፣ ራይድ፣ ፈረስ፣ ያንጎና ኤየር ቢኤንቢ ያሉ የመጓጓዣና ናቪጌሽን አፖች
→ እንደ ቢቢሲ ኒውስ ያሉ የዜናና መረጃ ሰጪ አፖች አሉ።



💻 ዋና የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች:

1. Android አፖችን ለመስራት:
- Java
- Kotlin
- Android Studio IDE ገበያው ላይ ይታወቃሉ!

2. iOS አፖችን ለመስራት:
- Swift
- Objective-C
- Xcode IDE

3. Cross-Platform (በሁለቱም ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ላይ የሚሰራ አንድ አፕ ለመስራት):
- Flutter (Dart)
- React Native (JavaScript)
- Ionic (Angular/React)

አሁን ላይ ተፈላጊ የሆነው  ይህ 3ኛው ነው። ምክኛቱም ለምሳሌ ራይድና ፈረስ ሞባይል አፓቸውን ለማሰራት የግድ ሳምሰንግና መሰል ኦኤሳቸው አንድሮይድ የሆኑ ስልክ ያላቸው ደንበኞቻቸው የሚጠቀሙት አንድሮይድ አፕ ይፈልጋሉ፣ የሆነ ደንበኛቸው ደሞ አፕል ስልክ ሊኖረው ይችላል። ስለዚህ ለሁሉም ደንበኞቻቸው ተደራሽ እንዲሆኑ ሁለት አፕ ያስፈልጋቸዋል፣ ለሁለቱም ሁለት የተለያየ ባለሙያ አፕ ሰሪ ሊያፈልጋቸው ነው። ከዚህ ይልቅ ሁለቱም ሲስተሞች ላይ የሚሰራ አንድ ባለሙያ ቢቀጥሩ ከክፍያም አንፃር አዋጭ ነው:: አንድሮይድ አፕ ለሚሰራላቸው 100 ሺ ብር፣ አይኦኤስ አፕ ለሚሰራላቸው 100 ሺህ ብር ከመክፈል፣ ለሁለቱም የሚሰራ አንድ አፕ በ150 ሺ ብር ማሰራት ይበልጣል::

በኛ ተቋም 3ቱም ይሰጣሉ፣ ግን በዋናነት ገበያው ላይ ወደፊት ተፈላጊ የሆነው Flutter ይሰጣል!

📊 የገበያ እድሎች:

በአለም አቀፍ ደረጃ:
- $206.7 ቢሊዮን የገበያ መጠን (2024)
- 18.4% የዓመታዊ እድገት
- 6.3 ቢሊዮን የሞባይል ተጠቃሚዎች

በኢትዮጵያ:
- 25+ ሚሊዮን የስማርትፎን ተጠቃሚዎች
- 200% የዓመታዊ የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት
- እያደገ ያለ የፊንቴክ ዘርፍ

💰 የገቢ እድሎች (በወር):

1. Junior Developer:
- የአካባቢ: 15,000 - 25,000 ብር
- ዓለም አቀፍ: $800 - $2,000

2. Mid-Level Developer:
- የአካባቢ: 30,000 - 70,000 ብር
- ዓለም አቀፍ: $2,500 - $5,000

3. Senior Developer:
- የአካባቢ: 70,000+ ብር
- ዓለም አቀፍ: $6,000+

4. Freelancing:
- በፕሮጀክት: $500 - $5,000
- ወርሃዊ ኮንትራት: $1,000 - $4,000

🎯 የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች:

1. ፊንቴክ:
- የክፍያ አፕሊኬሽኖች
- የባንክ አፕሊኬሽኖች
- የዋሌት አፕሊኬሽኖች

2. ኢ-ኮመርስ:
- የሽያጭ መደብሮች
- የማድረስ (ዴሊቨሪ) አገልግሎቶች
- የእቃ መከታተያ

3. ማህበራዊ ሚዲያ:
- የመልእክት መላላኪያዎች
- የይዘት መጋሪያዎች
- የኔትወርኪንግ መድረኮች

📚 የስልጠና ይዘቶች:

1. መሰረታዊ ክህሎቶች:
- Programming Fundamentals
- UI/UX Design
- Database Management
- API Integration

2. የልማት ሂደቶች:
- Agile Development
- Version Control (Git)
- Testing & Debugging
- App Store Deployment

3. የንግድ ክህሎቶች:
- Project Management
- Client Communication
- App Monetization
- Marketing Basics


📱 የገበያ ፍላጎት:

1. የአካባቢ (የሎካል ማርኬት) ፍላጎቶች:
- የባንክ አፕሊኬሽኖች
- የትራንስፖርት አፕሊኬሽኖች
- የድርድር መድረኮች

2. ዓለም አቀፍ እድሎች:
- Freelance Platforms
- Remote Jobs
- Startup Opportunities

🎁 በMiT የሚያገኙት ጥቅሞች:

1. ተግባራዊ ልምምድ:
- እውነተኛ ፕሮጀክቶች
- የግል ፖርትፎሊዮ
- የስራ ልምድ

2. የባለሙያ ድጋፍ:
- የግል አሰልጣኝ
- ቴክኒካል መድረክ
- የስራ ምደባ

3. ሪሶርሶች:
- ዘመናዊ ሶፍትዌሮች
- የመማሪያ ቁሳቁሶች
- የተሳኩ ፕሮጀክቶች

📞 ለመመዝገብ:
ይደውሉ: +2519-89-26-30-30
ቴሌግራም: @MizanInstituteOfTechnologyEthio
ድረ-ገጽ: www.mizantechinstitute.com

አድራሻ: Apple Plaza, 7ኛ ፎቅ፣ በቤቴል፣ አዲስ አበባ


"ዛሬ ጀምረው ነገ የሞባይል አፕ ገንቢ ይሁኑ!"



ለበለጠ:

https://mizantechinstitute.com/course-category/mobile-app-development/


https://www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnology
📱 🔠🔠🔠🔠3️⃣ 🔤🔤🔤🔤🔠🔠🔠🔠🔡

🔗 www.mizantechinstitute.com

📞0️⃣9️⃣8️⃣9️⃣2️⃣6️⃣ 3️⃣0️⃣ 3️⃣0️⃣


📱 www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnologyEthio
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የምዝገባ መርሃ ግብራቹህን ያጠናቀቃቹ ሆናቹ ወደ ዋናው የክላስ ግሩፕ add ያልተደረጋቹ ካላቹ ወይም ከፍላቹ ያልተመዘገባቹህ ካላቹህ በውስጥ አናግሩንና add እናድርጋቹህ።

ተመዝግባቹ ወርሀዊ ክፍያ እና የመመዝገቢያ የከፈላቹበትን ደረሰኝ ያላካቹ በቴሌግራም @MizanInstituteOfTechnologyEthio ላይ ላኩልን።
📱 🔠🔠🔠🔠⚡️ 🔤🔤🔤🔤🔠🔠🔠🔠🔡

🔗 www.mizantechinstitute.com

📞0️⃣9️⃣8️⃣7️⃣1️⃣4️⃣3️⃣0️⃣3️⃣0️⃣ 🔤 0️⃣9️⃣8️⃣9️⃣2️⃣6️⃣ 3️⃣0️⃣ 3️⃣0️⃣



📱 www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnologyEthio
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ እሁድ ቢሯችን ክፍት ነው።



📱 🔠🔠🔠🔠⚡️⚡️ 🔤🔤🔤🔤🔤🔠🔠🔠🔠🔡

🔗 www.mizantechinstitute.com

📞0️⃣9️⃣8️⃣7️⃣1️⃣4️⃣3️⃣0️⃣3️⃣0️⃣ 🔤 0️⃣9️⃣8️⃣9️⃣2️⃣6️⃣ 3️⃣0️⃣ 3️⃣0️⃣



📱 www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnologyEthio
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Mizan Institute of Technology - MiT🇪🇹
ስለምንሰጣቸው ኮርሶች ማብራሪያ ✅ ክፍል 2️⃣ ለዛሬ ፓይተን ፕሮግራሚንግን በተመለከተ የተወሰኑ ሃሳቦችን እናካፍላችሁ! ፓይተን ከፕሮግራሚን ቋንቋዎች መካከል አንዱ ስለሆነ ሃሳቡን እንረዳው ይረዳን ዘንድ ቅድሚያ ስለ ፕሮግራሚንግ ቋንቋ ምንነት ትንሽ እንበል። በመጀመሪያ ወደ ፕሮግራሚንግ ዓለም እንኳን ደህና መጡ! (Introduction to the World of Programming) ግን ግን… ከኮምፒውተር…
ስለምንሰጣቸው ኮርሶች ማብራሪያ ✅ ክፍል 3️⃣
የዳታ ሳይንስ (Data Science): የመረጃን ምስጢር መፍታትና መተንተን!

ከዚህ በፊት ስለ ፉል ስታክ ዌብ ደቨሎፕመንት (ክፍል 1) እና በተወሰነ መልኩ ስለ ፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች ጥቅል ገለፃ እና በተለይም ስለ ፓይተን (ክፍል 2) አይተናል። አሁን ደግሞ ወደ ዳታ ሳይንስ እንሸጋገራለን።

ዳታ ሳይንስ ምንድን ነው? ለምን ይጠቅማል? እንዴትስ እንማረው? እነዚህን እና ሌሎች ጥያቄዎችን እንመልሳለን።


✅ዳታ ሳይንስ ምንድን ነው? (What is Data Science?)
በዙሪያችን ያለው ዓለም በመረጃ (data) የተሞላ ነው። የአየር ሁኔታ፣ የሽያጭና የግብይት መረጃ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎች (ፖስቶች)፣ የጤና መረጃ፣ የትራፊክ ፍሰት፣ የትምህርት ተቋማት መረጃዎች፣ የመንግስትና የግል የአገልግሎት ተቋማት... ሁሉም መረጃ ነው። ግን ይህ መረጃ ብቻውን ብዙም ትርጉም የለውም። ልክ ያልተሰራና ያልተነጠረ አልማዝ ወይም ወርቅ ነው። የወርቅ ወይም የአልማዝ ማዕድን ተነጥሮና ተሠርቶ በቀለበት መልክ፣ በአንጌት ጌጥ መልክ፣ በጆሮ ጌጥ መልክ… ወዘረ ካልተዘጋጀ ዝም ብሎ ቅርፅ የሌለው ድቡልቡል ነገር ከሆነ ምን እንኳ ወርቅ ወይም አልማዝ ቢሆንም ምናችን ላይ እናደርገዋለን? ውበቱም ሆነ ጥቅሙ የሚታየን በጌጥ መልክ ለፈለግነው ነገር ሲዘጋጅ ነው።

ዳታ ሳይንስ ይህንን በየቦታው (በጤና ተቋማት፣ በግብርና ተቋማት፣ በትምህርት ተቋማት… ወዘተ)  የሚገኝ ጥሬ መረጃ (raw data) ወስዶ፣ አቀናጅቶ፣ ተንትኖ፣ ትርጉም ያለው ድምዳሜ (insight) የሚያወጣበት ሂደት ነው። በሌላ አነጋገር፣ የመረጃን ምስጢር መፍታት እንደማለት ነው! ልክ ወርቅና አልማዙ ተነጥሮና በጌጥ መልክ ተሠርቶ ካላየነው በስተቀር ውበትና ጥቅሙ እንደማይታየን ሁሉ፤ በየቦታው የምናየውና የምናገኘው ጥሬ መረጃም ካልተቀናጀና ካልተተነተነ ትርጉም አይሰጠንም።


💰ዳታ ሳይንስ እንደ ታሪክ ተራኪ (Data Science as Storytelling)
ዳታ ሳይንስን ለመረዳት አንድ ምሳሌ እንውሰድ። አንድ መርማሪ (detective) የወንጀል ቦታ ላይ የተለያዩ ፍንጮችን (መረጃዎችን) ይሰበስባል። የጣት አሻራ፣ የደም ናሙና፣ የምስክሮች ቃል... እነዚህን ፍንጮች በማቀናጀት እና በመተንተን የወንጀለኛውን ማንነት እና የወንጀሉን ሂደት ይደርስበታል። ልክ እንደዚሁ፣ ዳታ ሳይንቲስትም የተለያዩ መረጃዎችን በመሰብሰብ፣ በማቀናጀት እና በመተንተን ጠቃሚ ድምዳሜዎችን ያገኛል። መረጃው የሚናገረውን ታሪክ ይገልፃል።

💰የዳታ ሳይንስ ጥቅሞች (Benefits of Data Science):

➡️የተሻሉ ውሳኔዎችን ማድረግ (Better Decision Making): ኩባንያዎች፣ መንግስታት፣ ግለሰቦች... ሁሉም የተሻሉ ውሳኔዎችን ለማድረግ ዳታ ሳይንስን መጠቀም ይችላሉ። ለምሳሌ፡- አንድ ኩባንያ የደንበኞቹን ፍላጎት በመተንተን የትኞቹን ምርቶች ማምረት እንዳለበት መወሰን ይችላል።

➡️አዳዲስ ግኝቶችን ማግኘት (Discovering New Insights): ዳታ ሳይንስ ከዚህ በፊት ያልታወቁ ነገሮችን ለማግኘት ይረዳል። ለምሳሌ፡- አዳዲስ የመድሃኒት ግኝቶችን፣ አዳዲስ የግብይት ስልቶችን።

➡️ችግሮችን መፍታት (Solving Problems): ዳታ ሳይንስ ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት ይረዳል። ለምሳሌ፡- የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ፣ የወንጀል መጠንን ለመቀነስ።

➡️የወደፊቱን መተንበይ (Predicting the Future): ዳታ ሳይንስ ያለፉትን መረጃዎች በመተንተን የወደፊቱን ለመተንበይ ይረዳል። ለምሳሌ፡- የአክሲዮን ገበያን ለመተንበይ፣ የደንበኞችን ባህሪ ለመተንበይ። 100% ፐርፌክት ላይሆን ይችላል፣ የሚተነብየውም ዝም ብሎ በደፈናው ሳይሆን ያለፉ መረጃዎችና ፍንጮች ላይ ተመርኩዞ ነው።

💰የስራ እድል (Career Opportunities): ዳታ ሳይንቲስቶች በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ በጣም ተፈላጊ ከሆኑ ባለሙያዎች መካከል ናቸው። በተለይም አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ከምንግዜውም በላይ እያደገ መምጣቱን ተከትሎ፣ ዳታ ሳይንቲስቶች ተፈላጊ ሆነዋል። ምክንያቱም ያለ ዳታ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ምሰሶ የሌለው ቤት ነው።

💰የዳታ ሳይንስ የስራ ሂደት (Data Science Workflow):
ዳታ ሳይንስ በአጠቃላይ የሚከተሉትን ደረጃዎች ያካትታል፡-

➡️ችግሩን መረዳት (Understanding the Problem): ምን አይነት ጥያቄ ነው መመለስ የምንፈልገው? ምን አይነት መረጃ ነው የሚያስፈልገን?

➡️መረጃ መሰብሰብ (Data Collection): ከድረ-ገጾች (web scraping), ከመረጃ ቋቶች (databases), ከዳሰሳ ጥናቶች (surveys)... መረጃዎችን መሰብሰብ።

➡️መረጃ ማጽዳት (Data Cleaning): የተሳሳቱ መረጃዎችን ማረም፣ የጎደሉ መረጃዎችን መሙላት... መረጃውን ለትንተና ዝግጁ ማድረግ።

➡️መረጃን መመርመር (Data Exploration): መረጃውን በግራፎች እና በቻርቶች መልክ ማየት፣ መሰረታዊ ስታቲስቲክሶችን (ለምሳሌ፡ አማካይ፣ መደበኛ መዛባት) ማስላት።

➡️ሞዴል መገንባት (Model Building): የማሽን ለርኒንግ ሞዴሎችን በመጠቀም መረጃውን መተንተን እና ትንበያዎችን ማድረግ።

➡️ውጤቶችን መገምገም (Model Evaluation): ሞዴሉ ምን ያህል ትክክለኛ እንደሆነ መገምገም። ይህን evaluate ማድረጊያ ራሳቸውን የቻሉ ሜትሪክሶች አሉ።

➡️ውጤቶችን ማስተላለፍ (Communicating Results): ውጤቶችን ለሌሎች ሰዎች (ለምሳሌ፡ ለደንበኞች፣ ለአለቆች) ግልፅ በሆነ መንገድ ማቅረብ።

💰በዳታ ሳይንስ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ መሳሪያዎች (Tools Used in Data Science):

➡️Python (ፓይተን): ለዳታ ሳይንስ በጣም ታዋቂው የፕሮግራሚንግ ቋንቋ ነው። (ስለ ፓይተንክፍል 2ን ይመልከቱ!)

➡️NumPy: ለቁጥራዊ ስሌቶች።
➡️Pandas: መረጃዎችን ለማቀናጀት እና ለመተንተን።
➡️Matplotlib & Seaborn: መረጃዎችን በግራፍ እና በቻርት መልክ ለማሳየት።
➡️Scikit-learn: ለማሽን ለርኒንግ።
➡️R: ሌላው ታዋቂ የፕሮግራሚንግ ቋንቋ ለዳታ ሳይንስ።
➡️SQL: ከመረጃ ቋቶች (databases) ጋር ለመገናኘት የሚያገለግል ቋንቋ።

➡️Tableau & Power BI: መረጃዎችን የተገናኘ (interactive) በሆነ መልኩ ለማሳየት የሚያገለግሉ መሳሪያዎች።

➡️Jupyter Notebook/Lab.
➡️Excel. (አሁን ላይ በ5 ሚሊዮን ኮደርስ ላይ እንደ ጀማሪ የሚሰጠው ኮርስ)


✅በMizan Institute of Technology (MiT) የዳታ ሳይንስ ስልጠና የምንሸፍናቸው ርዕሶች (በዝርዝር):

✅የፕሮግራሚንግ መሰረታዊ ነገሮች (Programming Fundamentals): በፓይተን ላይ ትኩረት እናደርጋለን። (ክፍል 2ን ይመልከቱ!)

✅ስታቲስቲክስ (Statistics): መሰረታዊ የስታቲስቲክስ ፅንሰ-ሀሳቦችን እናስተምራለን።

✅የመረጃ አያያዝ (Data Handling): መረጃዎችን እንዴት መሰብሰብ፣ ማጽዳት፣ ማቀናጀት እና መተንተን እንደሚቻል እናስተምራለን።

✅የመረጃ ምስላዊነት (Data Visualization): መረጃዎችን በግራፎች እና በቻርቶች መልክ እንዴት ማሳየት እንደሚቻል እናስተምራለን።

✅ማሽን ለርኒንግ (Machine Learning): የተለያዩ የማሽን ለርኒንግ ስልተ-ቀመሮችን (algorithms) እናስተምራለን።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Mizan Institute of Technology - MiT🇪🇹
ስለምንሰጣቸው ኮርሶች ማብራሪያ ✅ ክፍል 2️⃣ ለዛሬ ፓይተን ፕሮግራሚንግን በተመለከተ የተወሰኑ ሃሳቦችን እናካፍላችሁ! ፓይተን ከፕሮግራሚን ቋንቋዎች መካከል አንዱ ስለሆነ ሃሳቡን እንረዳው ይረዳን ዘንድ ቅድሚያ ስለ ፕሮግራሚንግ ቋንቋ ምንነት ትንሽ እንበል። በመጀመሪያ ወደ ፕሮግራሚንግ ዓለም እንኳን ደህና መጡ! (Introduction to the World of Programming) ግን ግን… ከኮምፒውተር…
✅Regression: ተከታታይ እሴቶችን (continuous values) ለመተንበይ። ለምሳሌ፡- የቤት ዋጋን ለመተንበይ።

✅Classification: ነገሮችን በተለያዩ ምድቦች ለመከፋፈል። ለምሳሌ፡- ኢሜይሎችን እንደ "spam" ወይም "not spam" መለየት።

✅Clustering: ተመሳሳይ የሆኑ ነገሮችን በቡድን መከፋፈል። ለምሳሌ፡- ደንበኞችን በተለያዩ ቡድኖች መከፋፈል።

✅ ዲፕ ለርኒንግ (Deep Learning): መሰረታዊ የdeep learning ፅንሰ-ሀሳቦችን እናስተምራለን።

✅Big data handling.
✅Data Ethics.

✅እውነተኛ ፕሮጀክቶችን መስራት (Hands-on Projects):
በMiT ስልጠናችን፣ ቲዎሪ ብቻ አይደለም የምናስተምረው። የተማራችሁትን በተግባር የምትፈትሹበት፣ እውነተኛ ፕሮጀክቶችን የምትሰሩበት እድል ይኖራችኋል።

➡️የደንበኞችን ባህሪ መተንተን: የአንድን የችርቻሮ መደብር (retail store) የሽያጭ መረጃ በመተንተን የደንበኞችን ባህሪ መረዳት።

➡️የአክሲዮን ገበያን መተንበይ: ያለፉትን የአክሲዮን ዋጋዎች በመተንተን የወደፊቱን ለመተንበይ መሞከር።

➡️የምስል መለያ (Image Recognition): ምስሎችን የሚለይ ሞዴል መገንባት። ለምሳሌ፡- የድመቶችን እና የውሾችን ምስሎች መለየት።

➡️Natural Language Processing projects.

✅የስራ እድሎች (Career Opportunities):
ዳታ ሳይንቲስቶች በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ በጣም ተፈላጊ ከሆኑ ባለሙያዎች መካከል ናቸው። በተለያዩ ዘርፎች መስራት ይችላሉ። ለምሳሌ፦
➡️ቴክኖሎጂ: Google, Facebook, Amazon, Microsoft...

➡️ፋይናንስ: ባንኮች፣ የኢንቨስትመንት ኩባንያዎች...

➡️ጤና: ሆስፒታሎች፣ የመድሃኒት ኩባንያዎች...

➡️ችርቻሮ: የችርቻሮ መደብሮች, የኦንላይን መደብሮች...

➡️መንግስት: የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች...
➡️ Consultancy


✅ግምታዊ ደመወዝ:

➡️በኢትዮጵያ: እንደየልምድና ብቃቱ ይለያያል። ከጀማሪ እስክ ከፍተኛ ልምድ ላላቸው 15,000 - 100,000+ ብር በወር ክፍያ ማግኘት ይቻላል።
በተለይ የውጭ ሃገር ተቋማት ሆነው እኛ ሃገር ላይ በዚህ ዘርፍ የሚሰሩ ተቋማት አሪፍ ይከፍላሉ። ግን የኤአይ ጉዟችን ደካማ ስለሆነ ለጊዜው አሁን ባለንበት ተጨባጭ በሃገር ውስጥ ያን ያክል ብዙ የስራ እድሎች አሉ ማለት አንችልም። ከቅርብ ጊዜ በሗላ ግን ተገደንም ቢሆን መግባታችን ስለማይቀር ያኔ ቀድሞ ይህን ዘርፍ ተምሮ መገኘት ይጠቅማል።

➡️በውጪ: በአሜሪካ ለምሳሌ ጀማሪ ዳታ ሳይንቲስት በዓመት ከ80,000 ዶላር በላይ ሊያገኝ ይችላል። ልምድ ያላቸው ዳታ ሳይንቲስቶች ደግሞ ከ80,000 ዶላር በላይ ሊያገኝ ይችላል። ልምድ ያላቸው ዳታ ሳይንቲስቶች ደግሞ ከ120,000 - $250,000+ ዶላር በዓመት ያገኛሉ።


📶ማጠቃለያ:
ዳታ ሳይንስ የመረጃን ምስጢር በመፍታት የተሻሉ ውሳኔዎችን ለማድረግ፣ አዳዲስ ግኝቶችን ለማግኘት እና ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ኃይለኛ መሳሪያ ነው። በMiT ጥራት ያለው ስልጠና፣ እውነተኛ ፕሮጀክቶችን የመስራት ልምድ እና ለስራ ገበያው የሚያዘጋጅዎትን ክህሎት እናቀርብልዎታለን።

አሁኑኑ ይመዝገቡ! የወደፊትዎን በዳታ ሳይንስ ይገንቡ!

በMizan Institute of Technology የዳታ ሳይንስ ኮርስ ረዳት ኢንስትራክተር የተዘጋጀ።
አሁን ላይ እየተካሄደ ባለው 8ኛ ዙር ምዝገባችን መሳተፍ ከፈለጉ: www.mizantechinstitute.com ላይ ገብተው ይመዝገቡ።

ስለሚመዘገቡት ኮርስ በቂ መረጃ ከሌለዎ: በቴሌግራም ወይም በአካል ቢሯችን በመገኘት ያናግሩን::

✅ቴሌግራም: http://www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnologyEthio
🗺 በአካል ተገኝተው በቂ ማብራሪያ አግኝተው ለመመዝገብ: ቤተል አፕል ፕላዛ 7ኛ ፎቅ (ቢጫ ፎቅ ፊት ለፊት)

ስለሌሎች ኮርሶች ምንነትና ማብራሪያ ለማወቅ ፍላጎቱ ካለዎት ኮመንት ላይ ያሳውቁን።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የምዝገባ መርሃ ግብራቹህን ያጠናቀቃቹ ሆናቹ ወደ ዋናው የክላስ ግሩፕ add ያልተደረጋቹ ካላቹ ወይም ከፍላቹ ያልተመዘገባቹህ ካላቹህ በውስጥ አናግሩንና add እናድርጋቹህ።

ተመዝግባቹ ወርሀዊ ክፍያ እና የመመዝገቢያ የከፈላቹበትን ደረሰኝ ያላካቹ በቴሌግራም @MizanInstituteOfTechnologyEthio ላይ ላኩልን።
📱 🔠🔠🔠🔠⚡️ 🔤🔤🔤🔤🔤🔠🔠🔠🔠🔡

🔗 www.mizantechinstitute.com

📞0️⃣9️⃣8️⃣7️⃣1️⃣4️⃣3️⃣0️⃣3️⃣0️⃣ 🔤 0️⃣9️⃣8️⃣9️⃣2️⃣6️⃣ 3️⃣0️⃣ 3️⃣0️⃣



📱 www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnologyEthio
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Just ⚡️ hour Left ✈️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔤🔤🔤🔤🔤🔤
📢 Registration Closed! 📢

We want to thank everyone who registered for our cutting-edge courses at Mizan Institute of Technology. Registration for this round is now officially closed.

Stay tuned for future opportunities and updates. For those who missed out, we look forward to welcoming you in our next enrollment period.

For any inquiries, contact us on Telegram at https://www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnologyEthio or email us at [email protected].

Thank you for your interest in MiT! 🎓✨ #MiT #RegistrationClosed #StayTuned
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Mizan Institute of Technology - MiT🇪🇹
🔤🔤🔤🔤🔤🔤 📢 Registration Closed! 📢 We want to thank everyone who registered for our cutting-edge courses at Mizan Institute of Technology. Registration for this round is now officially closed. Stay tuned for future opportunities and updates. For those who missed…
🎉 የምስራች! 🎉

የሚዛን የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 8ኛ ዙር ምዝገባ ምዕራፍ ሁለት ተጀምሯል!
ምዕራፍ አንድ ላይ ምዝገባውን ላመለጣችሁ በሙሉ፣ አሁን እድሉ በድጋሚ ተከፍቷል! አዲስ ክላስ ከ19 ቀናት በኋላ ሰኞ መጋቢት 22/2017 (March 31, 2025) ይጀምራል።

በሁሉም ኮርሶች፣ በሁሉም ክፍለ ጊዜዎች (መደበኛ፣ የማታ፣ ቅዳሜና እሁድ፣ ኦንላይን) ምዝገባ ተጀምሯል። ቦታዎች ውስን ስለሆኑ ቶሎ ይመዝገቡ!

ለበለጠ መረጃ፡
💊@MizanInstituteOfTechnologyEthio
🔗https://mizantechinstitute.com/
✍️[email protected]/




🎂Good News! 🎂
Phase Two of Mizan Institute of Technology's 8th Round Registration is Now Open!

To those who missed the Phase One registration, your opportunity is here again! New classes will start in 19 days, on Monday, March 31, 2025.
Registration is now open for all courses and all sessions (Regular, Extension, Weekend, and Online). Limited slots only, so register ASAP!


For more information:
💊@MizanInstituteOfTechnologyEthio
🔗https://mizantechinstitute.com/
✍️[email protected]/
Register Now!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🎉ሁለተኛ ምዕራፍ ምዝገባችን እንደቀጠለ ነው

የትኛውን ኮርስ መመዝገብ ይፈልጋሉ❓

✅ዲጂታል ማርኬቲንግ

✅ፉል ስታክ ዌብ ዴቨሎፕመንት

✅ግራፊክ ዲዛይን

✅ፓይተን

✅ቪዲዮ ኤዲቲንግ

✅ማሽን ለርኒንግ

✅ዳታ ሳይንስ

✅ሞባይል አፕ ደቨሎፕመንት

✅ቋንቋ እና ቲቶሪያል

በፈለጉት እና በተመቾት አማራጭ መማር የምችሉበትን ጊዜያት አመቻችተናል።
✅በኦንላይን

✅በሬጉላር

✅በኤክቴንሽን እንዲሁም

✅በዊክንድ አማራጮች ይዘንላቹ ቀርበናል።


ስለ ኮርሶቹ ማብራሪያ ከፈለጋችሁ ከታች ያሉትን ሊንኮች በመንካት ማየት ይችላሉ።

1️⃣ ስለ ፉል ስታክ።
https://www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnology/381


2️⃣ ስለ ፓይተን።

https://www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnology/385

3️⃣ስለ ሞባይል መተግበሪያ

https://www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnology/400

4️⃣ስለ ግራፊክ ድዛይን

https://www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnology/399

5️⃣ስለ ዲጂታል ማርኬቲንግ

https://www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnology/398

ስለ ሌሎችም ማብራሪያ እዚሁ ዌብ ሳይታችን ላይ ያገኛሉ።🔗https://mizantechinstitute.com/

ለመመዝገብ👇👇👇
🔗 www.mizantechinstitute.com

በቴሌግራም ለማግኘት 👇👇👇
💊@MizanInstituteOfTechnologyEthio


በስልክ ለማግኘት👇👇👇
📞0️⃣9️⃣8️⃣9️⃣2️⃣6️⃣ 3️⃣0️⃣ 3️⃣0️⃣
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሁለተኛ ምዕራፍ ምዝገባችን ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ይቀራሉ።

መመዝገብ የምትፈልጉ ከወዲሁ ቶሎ ተመዝገቡ።

ለመመዝገብ👇👇👇
🔗 www.mizantechinstitute.com

በቴሌግራም ለማግኘት 👇👇👇
💊@MizanInstituteOfTechnologyEthio


በስልክ ለማግኘት👇👇👇
📞0️⃣9️⃣8️⃣9️⃣2️⃣6️⃣ 3️⃣0️⃣ 3️⃣0️⃣
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከአንድ ወር በፊት በኢንስቲትዩታችን 'Remote Work'ን እና 'Freelance Work'ን በተመለከተ በዘርፉ ልምድ ባላቸው ተጋባዥ እንግዶች ብርሃን ነጋ እና ቢኒያም ኃይሌ የተሰጠውን ምክርና ጥቆማዎች ያለበት ዝግጅት በቪድዮ ልንጋብዛችሁ ወደድን።

Discover your potential in the booming era of freelancing and remote work.

This masterclass by Mizan Institute of Technology (MiT) offers effective solutions and requisite tools to initiate a successful profession. With insight from Birhan Nega and Biniam Haile. Learn now and reinterpret your career:

https://youtu.be/_F8e98VDSy4?si=OuysIu23XFpaXnFp

#RemoteWork #Freelancing #CareerGrowth #MiT #MizanMiT #MizanTech #Upwork #Fiverr #FutureJob
Mizan Institute of Technology - MiT🇪🇹
🎉 የምስራች! 🎉 የሚዛን የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 8ኛ ዙር ምዝገባ ምዕራፍ ሁለት ተጀምሯል! ምዕራፍ አንድ ላይ ምዝገባውን ላመለጣችሁ በሙሉ፣ አሁን እድሉ በድጋሚ ተከፍቷል! አዲስ ክላስ ከ19 ቀናት በኋላ ሰኞ መጋቢት 22/2017 (March 31, 2025) ይጀምራል። በሁሉም ኮርሶች፣ በሁሉም ክፍለ ጊዜዎች (መደበኛ፣ የማታ፣ ቅዳሜና እሁድ፣ ኦንላይን) ምዝገባ ተጀምሯል። ቦታዎች ውስን ስለሆኑ ቶሎ ይመዝገቡ!…
ውድ የሚዛን የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች፣

የትላንትናው ቀን የ8ተኛው ዙር ምዝገባ ሁለተኛ ምዕራፍ የሚጀመርበት ቀን ስለነበር ተጀምሯል።
ይሁን እንጂ፣ በአዲሱ ዙር ምዝገባ ምዕራፍ ሁለት ላይ ለመመዝገብ ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች በሙሉ፣ በሁሉም ኮርሶች፣ በሁሉም ክፍለ ጊዜዎች እና በአካልም ሆነ በኦንላይን ለመመዝገብ የመጨረሻ 48 ሰዓት እድል ተሰጥቷችኋል።

በተጨማሪም፣ በ8ተኛው ዙር ምዝገባ ምዕራፍ ሁለት ላይ ተመዝግባችሁ የክላስ ግሩፕ ላይ add ያልተደረጋችሁ ወይም ክፍያ ከፍላችሁ ምዝገባችሁን ያላጠናቀቃችሁ ተማሪዎች በሙሉ በአስቸኳይ በሚከተሉት አድራሻዎች አግኙን።
@MizanInstituteOfTechnologyEthio ወይም [email protected]

ምዝገባውን በዚህ ሊንክ ያጠናቅቁ፡ www.mizantechinstitute.com



Dear Mizan Institute of Technology Students,
Yesterday marked the official second phase start date of our 8th round registration.
But for those who are still interested in registering for our second phase of our 8th round, we are providing a final window of registration in all courses, for all sessions (Regular, Extension, Weekend, and Online) for 48 hours.

Additionally, if you had enrolled during the second phase of the 8th round but have not been added to your class group or have paid without successfully completing registration, kindly get in touch with us as soon as possible at:
@MizanInstituteOfTechnologyEthio or [email protected]

Complete your registration at: www.mizantechinstitute.com
Mizan Institute of Technology - MiT🇪🇹
ስለምንሰጣቸው ኮርሶች ማብራሪያ ✅ ክፍል 3️⃣ የዳታ ሳይንስ (Data Science): የመረጃን ምስጢር መፍታትና መተንተን! ከዚህ በፊት ስለ ፉል ስታክ ዌብ ደቨሎፕመንት (ክፍል 1) እና በተወሰነ መልኩ ስለ ፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች ጥቅል ገለፃ እና በተለይም ስለ ፓይተን (ክፍል 2) አይተናል። አሁን ደግሞ ወደ ዳታ ሳይንስ እንሸጋገራለን። ዳታ ሳይንስ ምንድን ነው? ለምን ይጠቅማል? እንዴትስ እንማረው?…
ስለምንሰጣቸው ኮርሶች ማብራሪያ ✅ ክፍል 4️⃣
ማሽን ለርኒንግ (Machine Learning): ኮምፒውተሮች ከተሞክሮ እንዲማሩ ማድረግ!

ሰላም! በክፍል 1 ስለ ፉል ስታክ ዌብ ዴቨሎፕመንት፣ በክፍል 2 ስለ ፓይተን ፕሮግራሚንግ፣ እንዲሁም በክፍል 3 ስለ ዳታ ሳይንስ ምንነትና ጠቀሜታ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አይተናል።

ዛሬ ደግሞ በዳታ ሳይንስ እና በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ (AI) ውስጥ እጅግ በጣም ቁልፍ ሚና የሚጫወተውን ማሽን ለርኒንግ (Machine Learning) እንመለከታለን።


✅ ለመሆኑ ማሽን ለርኒንግ ምንድን ነው? በዕለት ከዕለት ህይወታችን ውስጥ እንዴት እንጠቀምበታለን? ለምንስ መማር አስፈለገ? እነዚህንና ተያያዥ ጥያቄዎችን በቀላሉ ለመመለስ እንሞክራለን!


✅ ማሽን ለርኒንግ ምንድን ነው? (What is Machine Learning?)

ስሙ እንደሚጠቁመው፣ ማሽን ለርኒንግ ማለት ኮምፒውተሮች (ማሽኖች) ልክ እንደ ሰው ከተሞክሮ (ከልምድ) እንዲማሩ የማስቻል ሂደት ነው። እንዴት? እስከዛሬ ከኮምፒዩተር ጋር የምንግባባው በፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች አልነበር? አለበለዚያ ኮምፒዩተር እንደ ጠረንጴዛ ግዑዝ ነገር ነው፣ የተሰራበት ትራንሲስተር እንዳለ ሆኖ።

አሁንስ? ለኮምፒውተሩ በሆነ ፕሮግራሚንግ ቋንቋ "ይሄን ስራ በዚህ መልኩ ስራ!" ብለን እያንዳንዱን እርምጃ በግልፅ ከመንገር ይልቅ፣ እጅግ በጣም ብዙ መረጃ (data) እንሰጠዋለን። ከዚያም ኮምፒውተሩ ከዚህ መረጃ በራሱ በመማር ስርዓተ-ጥለቶችን (patterns) ይለያል፣ ግንኙነቶችን (በእያንዳንዱ መረጃ መካከል ያለውን relationship) ይረዳል፣ እናም በአዲስ (ከዚህ በፊት ባላየነው) መረጃ ላይ ተመስርቶ ውሳኔዎችን መስጠት ወይም ትንበያዎችን ማድረግ ይችላል።

በሌላ አነጋገር፣ ኮምፒውተሩን በቀጥታ ፕሮግራም ከማድረግ ይልቅ፣ እንዴት መማር እንዳለበት እናስተምረዋለን! መማርን ማስተማር!

ልክ አንድ ህፃን ድመትን ከውሻ ለመለየት ብዙ ጊዜ የተለያዩ የድመትና የውሻ ምስሎችን አይቶ "ይሄ ድመት ነው"፣ "ይሄ ውሻ ነው" እየተባለ ከተነገረው በኋላ፣ አዲስ የድመት ወይም የውሻ ፎቶ ሲያይ በራሱ መለየት እንደሚችለው ማለት ነው። ማሽን ለርኒንግም ኮምፒውተሮች ይህን የመሰለ የመማር ችሎታ እንዲላበሱ ያደርጋል። መጀመሪያ በበርካታ ዳታ እናስተምራቸዋለን፣ በሗላ ላይ ያልተማሩት ዳታ ላይ ውሳኔ መወሰን ይችላሉ።


✅ ማሽን ለርኒንግ በዕለታዊ ህይወታችን ውስጥ (Machine Learning in Everyday Life):
ምናልባት "እኔ ማሽን ለርኒንግ አልጠቀምም" ብለው ያስቡ ይሆናል። ነገር ግን እውነታው፣ በየቀኑ ሳናውቀው እንኳን በተደጋጋሚ እንጠቀምበታለን! እስኪ ጥቂት ምሳሌዎችን እንይ፦

➡️የማህበራዊ ሚዲያ ፊድ (Social Media Feeds): ፌስቡክ፣ ቲክቶክ፣ ዩቲዩብ ወይም ኢንስታግራም ላይ ስንገባ መጀመሪያ የምናያቸው ፖስቶች ወይም ቪዲዮዎች ዝም ብለው የሚመጡ አይደሉም። ከዚህ በፊት የወደድናቸውን (like ያደረግናቸውን)፣ ያየናቸውን (watched)፣ ወይም ኮመንት የሰጠብንባቸውን ነገሮች መሰረት በማድረግ "ይሄ ሰው ይህን አይነት ነገር ይወዳል" ብሎ ማሽን ለርኒንግ ስርዓቱን ስለሚማር ለእኛ የሚስማማውን ይዘት እየመረጠ ያቀርብልናል።

➡️ የምርት ምክረ-ሀሳቦች (Product Recommendations): ኦንላይን ሸምተን የምናውቅ ከሆነ (ለምሳሌ Amazon, Jumia, AliExpress, Shein...) አንድን እቃ ስንገዛ ወይም ስንመለከት "ይህን የገዙ ሰዎች ይህንንም ገዝተዋል" ወይም "ለእርስዎ እነዚህ እቃዎች ይመከራሉ" የሚሉ ምክሮችን አይተን እናውቃለን። ይህ የሚሆነው፣ የእኛንና የሌሎች ተመሳሳይ ተጠቃሚዎችን የግዢ ባህሪ ማሽን ለርኒንግ ሞዴሎች ስለሚተነትኑ ነው።


➡️ የኢሜይል ስፓም ማጣሪያ (Email Spam Filtering): ጂሜይል (Gmail) እና ሌሎች የኢሜይል አገልግሎቶች የማይፈለጉ (spam) መልዕክቶችን ለይተው ወደተለየ ፎልደር የሚያስገቡት በማሽን ለርኒንግ ነው። ስርዓቱ ከብዙ ሚሊዮን ኢሜይሎች በመማር የትኛው ኢሜይል የማይፈለግ እንደሆነ እና እንዳልሆነ ይለያል።



➡️ Auto-Correct & Grammar Check): በስልካችን ወይም በኮምፒውተራችን ላይ ስንጽፍ ቃላትን በራሱ የሚያስተካክልልን (auto-correct) ወይም ቀጥሎ የምንጽፈውን ቃል የሚገምትልን (predictive text) ቴክኖሎጂ ከበስተጀርባው ማሽን ለርኒንግን ይጠቀማል።


➡️ የትራፊክ ትንበያ (Traffic Prediction): ጎግል ማፕስ (Google Maps) ወይም መሰል መተግበሪያዎች መንገዶች ላይ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ተንብየው "ይሄ መንገድ የተሻለ ነው" ብለው አማራጭ የሚሰጡን ያለፉትን እና የአሁኑን የትራፊክ ዳታ በማሽን ለርኒንግ በመተንተን ነው።


➡️ የቋንቋ ትርጉም (Language Translation): እንደ ጉግል ትርጉም (Google Translate) ያሉ አገልግሎቶች ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ በአስገራሚ ፍጥነት እና ጥራት መተርጎም የቻሉት እጅግ በጣም ብዙ የጽሑፍ መረጃዎችን በመጠቀም የሰለጠኑ የማሽን ለርኒንግ ሞዴሎች ስላሏቸው ነው።


➡️ የባንክ ማጭበርበር መከላከል (Fraud Detection): ባንኮች ከእኛ የክፍያ ካርድ (ATM/Credit Card) ያልተለመደ ወይም አጠራጣሪ ግብይት ሲፈጸም በፍጥነት ለይተው በማስጠንቀቅ ወይም ግብይቱን በማገድ ገንዘባችንን የሚጠብቁት የማሽን ለርኒንግ ስርዓቶችን በመጠቀም ነው።

እነዚህ ጥቂቶቹ ምሳሌዎች ናቸው! ማሽን ለርኒንግ በጤና፣ በግብርና፣ በትራንስፖርት፣ በመዝናኛ እና በሌሎችም በርካታ ዘርፎች ውስጥ ትልቅ አሻራ እያሳረፈ ይገኛል።


✅ የማሽን ለርኒንግ ጥቅሞች (Benefits of Machine Learning):

✅ተደጋጋሚ ስራዎችን በራስ-ሰር መስራት (Automation): ሰዎች የሚሰሯቸውን ድካም የሚጠይቁና ተደጋጋሚ ስራዎችን ኮምፒውተሮች እንዲሰሯቸው ማድረግ።

✅ የብልህ ትንበያዎችን መስጠት (Intelligent Predictions): ካለፈው መረጃ በመነሳት ስለወደፊቱ (ለምሳሌ የአየር ሁኔታ፣ የሽያጭ መጠን፣ የበሽታ ስርጭት) የተሻለ አድርጎ መተንበይ።


✅ የተሻሻለ ውሳኔ አሰጣጥ (Improved Decision Making): ውስብስብ መረጃዎችን በመተንተን የተሻሉ እና በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ውሳኔዎችን ማድረግ።


✅ ግላዊነትን ማላበስ (Personalization): ለእያንዳንዱ ተጠቃሚ እንደየፍላጎቱ እና ባህሪው የተለየ አገልግሎት ወይም ይዘት ማቅረብ (ከላይ እንዳየናቸው ምሳሌዎች)።


✅ ስውር ቀመሮችን ማግኘት (Discovering Hidden Patterns): ሰዎች በቀላሉ ሊያስተውሏቸው የማይችሉ በመረጃ ውስጥ የተደበቁ ግንኙነቶችን እና ስርዓተ-ጥለቶችን መለየት።


✅ ከዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ (AI) ጋር ያለው ግንኙነት:

ማሽን ለርኒንግ የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ (AI - ሰው ሰራሽ አስተውሎት) አንዱ ቁልፍ እና ዋና ዘርፍ ነው። AI ማለት ኮምፒውተሮች የሰውን ልጅ አስተሳሰብ እና ባህሪ መኮረጅ እንዲችሉ ማድረግ ሲሆን፣ ማሽን ለርኒንግ ይህን ለማሳካት ከሚረዱ ዋና መንገዶች አንዱ (በተለይ የመማርን ክፍል) ነው።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Mizan Institute of Technology - MiT🇪🇹
ስለምንሰጣቸው ኮርሶች ማብራሪያ ✅ ክፍል 3️⃣ የዳታ ሳይንስ (Data Science): የመረጃን ምስጢር መፍታትና መተንተን! ከዚህ በፊት ስለ ፉል ስታክ ዌብ ደቨሎፕመንት (ክፍል 1) እና በተወሰነ መልኩ ስለ ፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች ጥቅል ገለፃ እና በተለይም ስለ ፓይተን (ክፍል 2) አይተናል። አሁን ደግሞ ወደ ዳታ ሳይንስ እንሸጋገራለን። ዳታ ሳይንስ ምንድን ነው? ለምን ይጠቅማል? እንዴትስ እንማረው?…
በተመሳሳይ፣ ማሽን ለርኒንግ በዳታ ሳይንስ (ክፍል 3 ላይ እንዳየነው) ውስጥ እጅግ አስፈላጊ መሳሪያ ነው። ዳታ ሳይንቲስቶች መረጃን ከሰበሰቡ፣ ካጸዱ እና ከመረመሩ በኋላ፣ ትንበያዎችን ለመስራት፣ ነገሮችን ለመመደብ (classify ለማድረግ)፣ ወይም የተደበቁ ስርዓተ-ጥለቶችን ለማግኘት የሚጠቀሙት የማሽን ለርኒንግ ስልተ-ቀመሮችን (algorithms) ነው። ዳታ ነዳጁ ከሆነ፣ ማሽን ለርኒንግ ሞተሩ ነው!


✅ በማሽን ለርኒንግ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ዋና ዋና መሳሪያዎች:

➡️ Python (ፓይተን): ለማሽን ለርኒንግ ቀዳሚው እና ተመራጩ የፕሮግራሚንግ ቋንቋ ነው። (ክፍል 2ን ይመልከቱ!)

➡️ Scikit-learn: ለተለያዩ የማሽን ለርኒንግ ስራዎች (classification, regression, clustering) ዝግጁ የሆኑ ስልተ-ቀመሮችን እና መሳሪያዎችን የያዘ ላይብረሪ።

➡️ TensorFlow & PyTorch: በተለይ ለዲፕ ለርኒንግ (Deep Learning - የማሽን ለርኒንግ ንዑስ ዘርፍ) በስፋት ጥቅም ላይ የሚውሉ ኃይለኛ ላይብረሪዎች።

➡️ Pandas & NumPy: መረጃን ለማደራጀት፣ ለማጽዳት እና ለስሌት ለማዘጋጀት አስፈላጊ የሆኑ የፓይተን ላይብረሪዎች።

➡️ Matplotlib & Seaborn: የመረጃ ትንተና ውጤቶችን እና የሞዴል አፈጻጸምን በምስል (በግራፍ እና ቻርት) ለማሳየት።

🔼 በMizan Institute of Technology (MiT) የማሽን ለርኒንግ ስልጠና የምንሸፍናቸው ርዕሶች (በከፊል):

⬅️የማሽን ለርኒንግ መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳቦች (Fundamentals): ምንነት፣ አይነቶች፣ የስራ ሂደት።

⬅️ Supervised Learning (በተቆጣጣሪ መማር):
✅ Regression: ተከታታይ እሴቶችን መተንበይ (ለምሳሌ፡ የቤት ዋጋ፣ የተማሪ ውጤት)። Linear Regression, Polynomial Regression...

✅ Classification: መረጃን በተለያዩ ምድቦች መከፋፈል (ለምሳሌ፡ ኢሜይል ስፓም ነው/አይደለም?፣ እጢ ካንሰር ነው/አይደለም?)። Logistic Regression, K-Nearest Neighbors (KNN), Support Vector Machines (SVM), Decision Trees, Random Forests...

⬅️ Unsupervised Learning (ያለተቆጣጣሪ መማር):
✅Clustering: ተመሳሳይ የሆኑ መረጃዎችን በቡድን መከፋፈል (ለምሳሌ፡ ደንበኞችን በግዢ ባህሪያቸው መቧደን)። K-Means Clustering...

✅ Dimensionality Reduction: የመረጃን መጠን መቀነስ (ለምሳሌ፡ ለምስል ትንተና)። PCA...

⬅️ ሞዴል መገምገም እና ማሻሻል (Model Evaluation & Tuning): የገነባነው ሞዴል ምን ያህል ትክክል እንደሆነ መለካት እና አፈጻጸሙን ማሻሻል። (Accuracy, Precision, Recall, F1-Score, Cross-Validation, Hyperparameter Tuning...)

⬅️ Feature Engineering: ሞዴሉ በተሻለ ሁኔታ እንዲማር መረጃውን ማስተካከል።

⬅️ መሰረታዊ የዲፕ ለርኒንግ (Introduction to Deep Learning): የነርቭ መረቦችን (Neural Networks) መረዳት።


🔉 ተግባር ተኮር ፕሮጀክቶች (Hands-on Projects):
🔼የበሽታ ትንበያ ሞዴል (ለምሳሌ፡ የስኳር በሽታ)
🔼የደንበኛ መክሰር (Churn) ትንበያ
🔼የእጅ ጽሑፍ መለያ (Digit Recognition)

✅ የስራ እድሎች (Career Opportunities):
የማሽን ለርኒንግ እውቀት በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተፈላጊነት ካላቸው ክህሎቶች አንዱ ነው።

🎁 ማሽን ለርኒንግ መሐንዲስ (Machine Learning Engineer): የማሽን ለርኒንግ ሞዴሎችን በመገንባት፣ በማሰልጠን እና ወደ ስራ በማስገባት ላይ ያተኩራል።

🎁 ዳታ ሳይንቲስት (Data Scientist): ማሽን ለርኒንግን እንደ ዋና መሳሪያ በመጠቀም ከመረጃ ጠቃሚ ግንዛቤዎችን ያወጣል።

🎁 AI ስፔሻሊስት (AI Specialist): ሰፋ ባለ የ AI መስክ ላይ ይሰራል፣ ማሽን ለርኒንግ አንዱ ክፍል ነው።

🎁 ሶፍትዌር መሐንዲስ (Software Engineer with ML skills): የማሽን ለርኒንግ ሞዴሎችን ወደ ሶፍትዌር መተግበሪያዎች ያዋህዳል።

✅ግምታዊ ደመወዝ:
(ከዳታ ሳይንስ ጋር ተመሳሳይነት አለው፤ ብዙ ጊዜ ሚናዎቹ ይጣመራሉ)
በኢትዮጵያ: እንደ ልምድና የድርጅቱ አይነት ይለያያል። ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ባለሙያ በወር ከ 15,000 ብር እስከ 100,000+ ብር ሊደርስ ይችላል። አሁንም ቢሆን የሀገር ውስጥ ገበያው ገና በማደግ ላይ ቢሆንም፣ የውጭ ኩባንያዎች ወይም ከውጭ ጋር የሚሰሩ ድርጅቶች የተሻለ ይከፍላሉ። የወደፊቱ ተስፋ ሰፊ ነው።

☀️በውጪ ሀገራት (ለምሳሌ አሜሪካ/አውሮፓ): የማሽን ለርኒንግ ባለሙያዎች ከፍተኛ ተፈላጊነት ስላላቸው ደመወዛቸውም ከፍተኛ ነው። ጀማሪዎች በዓመት ከ$90,000 ዶላር በላይ ሊጀምሩ ይችላሉ፤ ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች ደግሞ $130,000 - $250,000+ ዶላር እና ከዚያ በላይ በዓመት ሊያገኙ ይችላሉ።

📶ማጠቃለያ:
ማሽን ለርኒንግ ኮምፒውተሮች ከዳታ እንዲማሩ በማድረግ ዓለማችንን እየቀየረ ያለ አስደናቂ እና ኃይለኛ ቴክኖሎጂ ነው። በየቀኑ ከምንጠቀምባቸው መተግበሪያዎች ጀርባ ያለው አንቀሳቃሽ ሞተር ነው። በ Mizan Institute of Technology (MiT) የምንሰጠው ስልጠና ይህን አስፈላጊ ክህሎት በተግባር በተደገፈ መልኩ በማስተማር ለወደፊቱ የስራ ገበያ ዝግጁ ያደርግዎታል።
አሁኑኑ ይመዝገቡ! በቴክኖሎጂው የፊት መስመር ላይ ይሰለፉ!

በMizan Institute of Technology የዳታ ሳይንስ እና ማሽን ለርኒንግ ኮርስ ረዳት ኢንስትራክተር የተዘጋጀ።
አሁን ላይ እየተካሄደ ባለው 8ኛ ዙር ምዝገባችን መሳተፍ ከፈለጉ: 💊www.mizantechinstitute.com ላይ ገብተው ይመዝገቡ።
ስለሚመዘገቡት ኮርስ በቂ መረጃ ከሌለዎ: በቴሌግራም ወይም በአካል ቢሯችን በመገኘት ያናግሩን::
✅ቴሌግራም: http://www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnologyEthio
⭐️በአካል ተገኝተው በቂ ማብራሪያ አግኝተው ለመመዝገብ: ቤተል አፕል ፕላዛ 7ኛ ፎቅ (ቢጫ ፎቅ ፊት ለፊት)

Website: www.mizantechinstitute.com

Telegram: https://www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnology

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/mizan-institute-of-technology/

Tiktok: https://www.tiktok.com/@mizantechinstitute?_t=ZM-8vAg6nCU9rD&_r=1

Facebook: https://www.facebook.com/MizanInstituteOfTechnology/
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Mizan Institute of Technology - MiT🇪🇹
ስለምንሰጣቸው ኮርሶች ማብራሪያ ✅ ክፍል 4️⃣ ማሽን ለርኒንግ (Machine Learning): ኮምፒውተሮች ከተሞክሮ እንዲማሩ ማድረግ! ሰላም! በክፍል 1 ስለ ፉል ስታክ ዌብ ዴቨሎፕመንት፣ በክፍል 2 ስለ ፓይተን ፕሮግራሚንግ፣ እንዲሁም በክፍል 3 ስለ ዳታ ሳይንስ ምንነትና ጠቀሜታ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አይተናል። ዛሬ ደግሞ በዳታ ሳይንስ እና በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ (AI) ውስጥ እጅግ በጣም ቁልፍ…
ስለምንሰጣቸው ኮርሶች ማብራሪያ ✅ ክፍል 5️⃣
ሳይበር ሴኩሪቲ (Cybersecurity): የዲጂታል አለማችንን መጠበቅ!
ባለፉት ክፍሎች ስለ ፉል ስታክ ዌብ ዴቨሎፕመንት (ክፍል 1)፣ ፓይተን ፕሮግራሚንግ (ክፍል 2)፣ ዳታ ሳይንስ (ክፍል 3) እና ማሽን ለርኒንግ (ክፍል 4) ሰፋ ያለ ግንዛቤ ወስደናል።
ዛሬ ደግሞ በዘመናችን እጅግ በጣም አስፈላጊ እና ወሳኝ ወደ ሆነው የ ሳይበር ሴኩሪቲ (Cybersecurity) መስክ እንዳስሳለን። ሁላችንም በቴክኖሎጂ በታገዘ አለም ውስጥ ስንኖር፣ ይህ መስክ ለምን ወሳኝ እንደሆነ፣ ምን እንደሚያካትት እና ለምን መማር እንዳለብን እንመለከታለን።

✅ ሳይበር ሴኩሪቲ ምንድን ነው? (What is Cybersecurity?)

በቀላሉ ለማስረዳት፣ ሳይበር ሴኩሪቲ ማለት የኮምፒውተር ስርዓቶችን፣ ኔትወርኮችን፣ ፕሮግራሞችን እና መረጃዎችን (data) ከዲጂታል ጥቃቶች፣ ከስርቆት፣ ከጉዳት ወይም ካልተፈቀደለት መዳረሻ የመጠበቅ ልምድና ቴክኖሎጂ ነው።

እስኪ በተጨባጩ አለም ምሳሌ እንውሰድ፦ ቤትዎን ወይም ንብረትዎን ከሌቦችና ከጉዳት ለመጠበቅ በሮችን ይቆልፋሉ፣ አጥር ያጥራሉ፣ ምናልባትም የጥበቃ ካሜራ ወይም ዘበኛ ይኖርዎታል። ሳይበር ሴኩሪቲም ልክ እንደዚሁ ነው፤ ነገር ግን ጥበቃው የሚደረገው ለዲጂታል ንብረቶቻችን ነው። እነዚህም፦

• የምንጠቀምባቸው ኮምፒውተሮች እና ስልኮች፣
• የምንገናኝባቸው ኔትወርኮች (ኢንተርኔት፣ ዋይፋይ)
• የምንጠቀምባቸው መተግበሪያዎች (apps) እና ሶፍትዌሮች
• የምናስቀምጣቸው እና የምንለዋወጣቸው መረጃዎች (የግል መረጃ፣ የባንክ መረጃ፣ የንግድ ሚስጥሮች፣ ወዘተ) ናቸው።


ሳይበር ሴኩሪቲ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ከሰርጎ ገቦች (hackers)፣ ከማልዌር (ቫይረሶች፣ ራንሰምዌር)፣ ከማጭበርበር (phishing) እና ሌሎች ዲጂታል ስጋቶች የሚከላከል የዲጂታል ዘበኛ ወይም መከላከያ ስርዓት ነው!


✅ ሳይበር ሴኩሪቲ ለምን አስፈለገ? በዕለት ከዕለት ህይወታችን ያለው ቦታ:

በአሁኑ ጊዜ ህይወታችን ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው። ለግንኙነት (ሶሻል ሚዲያ፣ ኢሜይል)፣ ለገንዘብ ልውውጥ (ሞባይል ባንኪንግ)፣ ለመረጃ ፍለጋ፣ ለስራ፣ ለትምህርት፣ ለመዝናኛ... ኢንተርኔት እና ኮምፒውተር/ስልክ እንጠቀማለን። ይህ ግንኙነት የጥቅም ያህል ስጋትም አለው። ያለ ሳይበር ሴኩሪቲ ጥበቃ፦
የባንክ አካውንታችን ሊዘረፍ ይችላል።
የግል ፎቶዎቻችን፣ ቪዲዮዎቻችን ወይም መልዕክቶቻችን ሊሰረቁ ወይም ሊጋለጡ ይችላሉ።

የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶቻችን በሌሎች እጅ ገብተው መጥፎ ነገር ሊሰራባቸው ይችላል።
ኮምፒውተሮቻችን በቫይረስ ተጠቅተው ሊበላሹ ወይም ፋይሎቻችን ሊቆለፉ (ransomware) ይችላሉ።

የምንሰራባቸው የድርጅት ወይም የመንግስት ሚስጥራዊ መረጃዎች ሊወጡ ይችላሉ።
አስፈላጊ አገልግሎቶች (እንደ ኤሌክትሪክ፣ ውሃ፣ ትራንስፖርት ያሉ) በዲጂታል ጥቃት ሊስተጓጎሉ ይችላሉ።

ስለዚህ፣ ሳይበር ሴኩሪቲ የባለሙያዎች ወይም የትላልቅ ድርጅቶች ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሁላችንም የዕለት ከዕለት ጉዳይ ነው። ልክ በመንገድ ላይ ስንሄድ ግራ ቀኝ እንደምናየው፣ በዲጂታል አለም ውስጥም ጥንቃቄ ማድረግ እና እራሳችንን መጠበቅ አለብን።

✅ የሳይበር ሴኩሪቲ ተግባራዊ ምሳሌዎች (በእኛ የምንተገብራቸው):

➡️ጠንካራ እና ልዩ የይለፍ ቃል (Password) መጠቀም: ለእያንዳንዱ አካውንት የተለየና ለመገመት የሚያስቸግር የይለፍ ቃል መፍጠር።

➡️ባለ ሁለት-ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Factor Authentication - 2FA) ማንቃት: ከይለፍ ቃል በተጨማሪ በስልካችን የሚላክ ኮድ ወይም ሌላ የማረጋገጫ ዘዴ መጠቀም (ልክ እንደ ባንክ ካርድ እና ፒን)።

➡️የማስመሰል (Phishing) ኢሜይሎችን እና መልዕክቶችን መለየት: "ሽልማት አሸንፈዋል"፣ "የባንክ አካውንትዎ ታግዷል" እያሉ የይለፍ ቃል ወይም የግል መረጃ የሚጠይቁ አጭበርባሪ መልዕክቶችን መጠንቀቅ እና ሊንኮችን አለመንካት።

➡️ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንተርኔት ግንኙነት (Secure Wi-Fi) መጠቀም: የህዝብ ዋይፋይ ላይ (ሆቴል፣ ካፌ...) የባንክ ግብይት ወይም ሚስጥራዊ መረጃ ከመለዋወጥ መቆጠብ።

➡️ሶፍትዌሮችን እና መተግበሪያዎችን በወቅቱ ማዘመን (Update ማድረግ): ማሻሻያዎች ብዙውን ጊዜ የደህንነት ክፍተቶችን ስለሚደፍኑ።

➡️የጸረ-ቫይረስ (Antivirus) ሶፍትዌር መጠቀም እና ማዘመን።

➡️መረጃን ባክአፕ (Backup) ማድረግ: ኮምፒውተር ቢበላሽ ወይም በራንሰምዌር ቢጠቃ መረጃ እንዳይጠፋ።


✅ የሳይበር ሴኩሪቲ ትምህርት ጥቅሞች (Benefits of Learning Cybersecurity):

➡️ራስን እና ቤተሰብን መጠበቅ: በኦንላይን አለም ውስጥ ደህንነትን ማረጋገጥ።

➡️ድርጅቶችን እና ተቋማትን መርዳት: የንግድ ድርጅቶችን፣ ባንኮችን፣ ሆስፒታሎችን፣ መንግስታዊ ተቋማትን ከሳይበር ጥቃት በመከላከል ወሳኝ ሚና መጫወት።

➡️ከፍተኛ የሥራ ገበያ ፍላጎት: በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በሀገር ውስጥ ከፍተኛ የባለሙያ እጥረት እና ፍላጎት ያለበት መስክ ነው።

➡️አዕምሮን የሚፈታተን እና ተለዋዋጭ መስክ: አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና የስጋት አይነቶችን መማር ይጠይቃል።

➡️ለሀገር ደህንነት አስተዋጽኦ ማድረግ: የሀገርን ወሳኝ የመሰረተ ልማት አውታሮች ከጥቃት መጠበቅ።


✅ በሳይበር ሴኩሪቲ ውስጥ ያሉ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች:

⬅️የኔትወርክ ደህንነት (Network Security): የኮምፒውተር ኔትወርኮችን ከሰርጎ ገቦች መጠበቅ።

⬅️የመተግበሪያ ደህንነት (Application Security): የምንጠቀምባቸውን ሶፍትዌሮች እና መተግበሪያዎች (apps) ከጥቃት መጠበቅ።

⬅️የመረጃ ደህንነት (Information Security): ሚስጥራዊ እና የግል መረጃዎችን መጠበቅ።

⬅️የክላውድ ደህንነት (Cloud Security): በክላውድ (ለምሳሌ Google Drive, AWS) ላይ ያሉ መረጃዎችን እና አገልግሎቶችን መጠበቅ።

⬅️ሥነምግባራዊ ሰርጎ ገብነት (እንበለው) (Ethical Hacking / Penetration Testing): እንደ ሰርጎ ገብ በማሰብ የደህንነት ክፍተቶችን መፈለግ እና ማስተካከያ እንዲደረግ ማሳወቅ (ይህ በጣም ተፈላጊ ክህሎት ነው!)።

⬅️ለጥቃት ምላሽ መስጠት (Incident Response): ጥቃት ሲደርስ በፍጥነት እርምጃ መውሰድ እና ጉዳትን መቀነስ።

⬅️ዲጂታል ፎረንሲክስ (Digital Forensics): የሳይበር ወንጀሎችን መመርመር።


✅ በሳይበር ሴኩሪቲ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ዋና ዋና መሳሪያዎች እና ቴክኖሎጂዎች:

✅ፋየርዎል (Firewalls): በኔትወርክ መግቢያ ላይ እንደ በረኛ ሆነው ያልተፈቀደ ትራፊክን የሚከለክሉ።

✅ጸረ-ቫይረስ/ማልዌር (Antivirus/Anti-malware): ቫይረሶችን እና ሌሎች ተንኮል-አዘል ሶፍትዌሮችን የሚለዩ እና የሚያስወግዱ።

✅Intrusion Detection/Prevention Systems (IDS/IPS): አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን የሚከታተሉ እና የሚከላከሉ ስርዓቶች።

✅Vulnerability Scanners (e.g., Nessus, Burp Suite): የደህንነት ክፍተቶችን የሚፈትሹ መሳሪያዎች።

✅Encryption Tools: መረጃን በማመስጠር ሌሎች እንዳያነቡት ማድረግ።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Mizan Institute of Technology - MiT🇪🇹
ስለምንሰጣቸው ኮርሶች ማብራሪያ ✅ ክፍል 4️⃣ ማሽን ለርኒንግ (Machine Learning): ኮምፒውተሮች ከተሞክሮ እንዲማሩ ማድረግ! ሰላም! በክፍል 1 ስለ ፉል ስታክ ዌብ ዴቨሎፕመንት፣ በክፍል 2 ስለ ፓይተን ፕሮግራሚንግ፣ እንዲሁም በክፍል 3 ስለ ዳታ ሳይንስ ምንነትና ጠቀሜታ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አይተናል። ዛሬ ደግሞ በዳታ ሳይንስ እና በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ (AI) ውስጥ እጅግ በጣም ቁልፍ…
✅SIEM (Security Information and Event Management) Tools: የደህንነት መረጃዎችን ከልዩ ልዩ ምንጮች ሰብስበው የሚተነትኑ።

✅Kali Linux: ለሥነምግባራዊ ሰርጎ ገብነት እና ለደህንነት ፍተሻ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ኦፕሬቲንግ ሲስተም።


✅ በMizan Institute of Technology (MiT) የሳይበር ሴኩሪቲ ስልጠና የምንሸፍናቸው ርዕሶች (በከፊል):

✅የሳይበር ሴኩሪቲ መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳቦች እና መርሆዎች

✅የኔትወርክ ደህንነት መሰረታዊ እና አድቫንስድ ዕውቀት (Networking & Security)

✅የኦፕሬቲንግ ሲስተም ደህንነት (Windows & Linux)

✅የምስጠራ (Cryptography) መሰረታዊ ነገሮች

✅የዌብ አፕሊኬሽን ደህንነት እና የተለመዱ ጥቃቶች (Web Security)

✅ሥነምግባራዊ ሰርጎ ገብነት እና የደህንነት ፍተሻ (Ethical Hacking & Penetration Testing)

✅በተግባር የተደገፈ
የማልዌር ትንተና መሰረታዊ ነገሮች (Malware Analysis Basics)

✅የደህንነት ስጋት አስተዳደር እና ተገዢነት (Risk Management & Compliance)

✅የተለያዩ የሳይበር ሴኩሪቲ መሳሪያዎች አጠቃቀም (Hands-on with Tools)


✅ ተግባር ተኮር ፕሮጀክቶች እና ላብራቶሪዎች (Hands-on Labs):
በMiT ስልጠናችን ቲዎሪ ብቻ አይደለም! የተማራችሁትን በተግባር የምትፈትሹበት፣ የደህንነት መከላከል እና የማጥቃት ዘዴዎችን (በሥነምግባራዊ መንገድ) የምትለማመዱበት ሰፊ የላብራቶሪ ጊዜ ይኖራችኋል።
➡️ደህንነቱ የተጠበቀ ኔትወርክ ማዋቀር
➡️የደህንነት ክፍተቶችን መፈተሽ (Vulnerability Assessment)
➡️የተለያዩ የጥቃት አይነቶችን መከላከል
➡️የሥነምግባራዊ ሰርጎ ገብነት ልምምዶች (ለምሳሌ፡ Capture The Flag - CTF)


🎂 የስራ እድሎች (Career Opportunities):
የሳይበር ሴኩሪቲ ባለሙያዎች በዓለም ላይ ከፍተኛ ተፈላጊነት አላቸው። በኢትዮጵያም የዲጂታል አገልግሎቶች እየተስፋፉ ሲመጡ የባለሙያዎች ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ነው!

📶የደህንነት ተንታኝ (Security Analyst): የደህንነት ሁኔታዎችን ይከታተላል፣ ስጋቶችን ይለያል፣ ሪፖርት ያደርጋል።

📶ሥነምግባራዊ ሰርጎ ገብ/የደህንነት ፍተሻ ባለሙያ (Penetration Tester / Ethical Hacker): የድርጅቶችን ስርዓት በመፈተሽ ክፍተቶችን ያገኛል።

📶የደህንነት መሐንዲስ (Security Engineer): የደህንነት ስርዓቶችን ይቀርጻል፣ ይተገብራል፣ ያስተዳድራል።

📶የጥቃት ምላሽ ሰጪ (Incident Responder): ጥቃት ሲደርስ በፍጥነት ምላሽ ይሰጣል፣ ጉዳትን ይቀንሳል።

📶የደህንነት አማካሪ (Security Consultant): ለድርጅቶች የደህንነት ምክር እና አገልግሎት ይሰጣል።

📶የደህንነት ኦዲተር (Security Auditor): የደህንነት ፖሊሲዎችና መመሪያዎች መከበራቸውን ያረጋግጣል።

በተለይ ባንኮች፣ የቴሌኮም ኩባንያዎች፣ የመንግስት ተቋማት፣ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ሌሎችም ትልልቅ ድርጅቶች የሳይበር ሴኩሪቲ ባለሙያዎችን በስፋት ይፈልጋሉ።

🎁 ግምታዊ ደመወዝ:
🔼በኢትዮጵያ: እንደ ልምድ፣ የክህሎት አይነት (ለምሳሌ፡ Penetration Testing) እና እንደ ድርጅቱ ይለያያል። ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ባለሙያ በወር ከ 20,000 ብር እስከ 120,000+ ብር እና ከዚያ በላይ ሊደርስ ይችላል። በተለይ ከፍተኛ ክህሎት እና ሰርቲፊኬሽን ያላቸው ባለሙያዎች ጥሩ ክፍያ ያገኛሉ። ፍላጎቱ እያደገ በመምጣቱ ክፍያውም እየጨመረ ይሄዳል።

🔼በውጪ ሀገራት (ለምሳሌ አሜሪካ/አውሮፓ): ከፍተኛ ፍላጎት ስላለ ደመወዙም ከፍተኛ ነው። ጀማሪዎች በዓመት ከ$85,000 ዶላር በላይ ሊጀምሩ ይችላሉ፤ ልምድ ያካበቱ እና ልዩ ሙያ ያላቸው ባለሙያዎች ደግሞ $120,000 - $250,000+ ዶላር እና ከዚያ በላይ በዓመት ሊያገኙ ይችላሉ።

⚙ ማጠቃለያ:
በዲጂታል ዘመን፣ ሳይበር ሴኩሪቲ የአማራጭ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የግል መረጃዎቻችንን፣ የድርጅት ሀብቶችን እና የሀገርን ደህንነት ለመጠበቅ ወሳኝ ነው። በ Mizan Institute of Technology (MiT) የምንሰጠው ተግባር-ተኮር የሳይበር ሴኩሪቲ ስልጠና በዚህ ተፈላጊ እና ወሳኝ መስክ ውስጥ ስኬታማ እንድትሆኑ የሚያስፈልጓችሁን ዕውቀትና ክህሎት ያስታጥቃችኋል።

አሁኑኑ ይመዝገቡ! የዲጂታል አለምን በመጠበቅ የበኩሎን አስተዋጽዖ ያበርክቱ!
በMizan Institute of Technology የሳይበር ሴኩሪቲ ኮርስ ኢንስትራክተር የተዘጋጀ።

አሁን ላይ እየተካሄደ ባለው 8ኛ ዙር ምዝገባችን መሳተፍ ከፈለጉ: www.mizantechinstitute.com ላይ ገብተው ይመዝገቡ።
ስለሚመዘገቡት ኮርስ በቂ መረጃ ከሌለዎ: በቴሌግራም ወይም በአካል ቢሯችን በመገኘት ያናግሩን::
🛫ቴሌግራም: http://www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnologyEthio
🗺 በአካል ተገኝተው በቂ ማብራሪያ አግኝተው ለመመዝገብ: ቤተል አፕል ፕላዛ 7ኛ ፎቅ (ቢጫ ፎቅ ፊት ለፊት)
🌐Website: www.mizantechinstitute.com
🛫Telegram: https://www.tg-me.com/MizanInstituteOfTechnology
✅LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/mizan-institute-of-technology/
🎵Tiktok: https://www.tiktok.com/@mizantechinstitute
📞Facebook: https://www.facebook.com/MizanInstituteOfTechnology/


#cybersecurity #infosec #ethicalhacking #security #kalilinux #networksecurity #mit #mizan #mizantech #mizanmit #tech #ethiopia #digitalethiopia #career #training #skill #itsecurity #dataprotection
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/04/15 12:04:29
Back to Top
HTML Embed Code: