Telegram Web Link
Channel created
አውጣኝ
————
ዥዋዥዌ ቢያምራት፥የግልቢያ ዘመቻ
አውጣኝ ትለኝ፥ጀመር ተፈረስ ኮርቻ
በዚህ በማያርፈው...
በስሜት ጋላቢ፥በበዛበት አለም
እንዴት ብዬ ላውጣት፥ሳላስገባ ልጓም

«ሚኪ እንዳለው»
@ Mebacha
''ምቹ'' ልማድሽ
———————
አንጥረሽ ያላሽኝ ፥ ደርሶ ትዝ ቢለኝ
እ'ከንፈሬ ዳር ዳር ፥ ጀመር ያሳክከኝ
ሱስ ገዳይ የነበር ፥ ተንሳፎ ባ'ቦል ላይ
ቅቤሽን ለምጄ ፥ ...መላስ ከላይ ከላይ
ጥላሽ የጠፋ ቀን...
ያ ''ምቹ'' ልማድሽ ፥ አማታኝ ከፀሐይ
.
« ሚኪ እንዳለ »
@Mebacha
ናማ ! እንዋቀስ
--------------
ስልቻህን ጭነህ ፥ በግልገሏ ጥጃ
በዝግማኔ ጉዞ ፣ በኤሊ እርምጃ
ላትጠጋ ዝንዝር ፥ ላትሔድ እርቀህ
በመዳሰስ እምነት ፣ በቀልን ሸምቀህ
በትላንት ቅራሪ ፣ እሽክርክሪት ናውዘህ
አያትህ ባኘኩ...
ያንተ ጥርስ ይቦርቦር ፣ ለምን ትለኛለህ ?
.
በ' ጠል ከመረስረስ ፣ አንተን ከከለለህ
ከሞላው ሳር ክዳን፥አንዲት ሙጃ መዘህ
ስለ ሙሉ ጎጆ ፣ ለምን ታውራለህ?
እንኳንስ በሐገር ፥ በትልቋ መድረክ
ከቤተሰብህ ስር ፣ አንተም ነጠላ ነክ
አባትህ በበላው ፣ የማይሞላ ሆድክ
.
አይታመም ጥርስህ ፣ ባያትህ እኝካት
ጭንቅላትህ አይዙር
በከረመች ድፍድፍ ፣ አባትህ በጠጣት
በልሐ ልበልህ ፥ ናማ ! እንዋቀስ
በስልጡን እይታ በቃላት እንገስግስ
እንደ ላሜ ቦራ...
ከታች እየታለብክ ፥ አሞሌን አትላስ
በስሜት ብዕርህ ፣ ታሪክን አትውቀስ
እንደ ጠላ አሻሮ
ለቆላህ ሰው ሁሉ ፥ በገፍ አትታመስ
በላ መልስልኝ…
እነሱን ባባላች ፣ በድፍርስ አተላ
አባትህ አባቴ ፣ ባነገቧት ዱላ
እንደምን አድርጌ ፣ ካንተ ጋር ልጣላ?
.
ከእርሻው መስክ ላይ፥ከውድማው ራስ
ከወጣህ በኋላ ፥ እርፍ ይዘህ አትመለስ
እንደ ደጀን በሬ ፣ እፊት…ፊቱን እረስ
ኋሊትን ላትይዘው...
ጠርበህ ላትሞርደው…
ታሪክ እንደ መንገድ ፥ ላይታደስ ጅናው
ተሰርቶ ያለፈን ፣ አትውቀስ ከኋላው
እግርህ የዛለ ቀን ፥ ከምታርፍባት ጥድ
ከዛሬዋ ጥላ ፣ ቅጠልን አትመድምድ
እንደ ውሃ ድፋት...
በቁልቁለት ፈፋ፥ተስገምግመህ አትንጎድ
ላንዲት መናኛ ቃል…
አተን የገነቡ ፥ .....'ሺ' ገፆች አትቅደድ
ቅን አውጣ ከክፋት
ከስድብ ምርቃት
ትምርትን ግለጣት፥ከታሪክህ እልፈት
ከተልወሰወሱት፥ከቦኩት እንደ ሸጥ*
ተከትለሃቸው ፣ አትነከር ከድጥ
አጥር ተቀብለህ ፣ ሃገርህን አትስጥ
ያንተን ግዙፍ ዳቦ፥በጢቢኛ አትለውጥ
ለበይ እንዲቀለው
አንተም እንዳትቦካ፥ሙዝ ልጠህ አትሽጥ
.
«ሚኪ እንዳለ»
@Mebacha
ከንፈር ልሶ ማደር
———//————
መለየቱ ሲያምርሽ ፥ ከላዬ'ላይ መብረር
ከኔ ጉያ ርቀሽ ፣ ከዛኛው ለማደር
በለመድኳት ም'ኛት እንዲ ትይኝ ነበር...
በጊዜ ካልገባው ፥ ይቆጣኛል ፋዘር !!
ግና ከኔ ርቀሽ
ሳደርሺ ካባትሽ
እንደ መንገድ እሸት ፥ የወይን ዘለላ
ይቆርጥሽ ነበር...
ከመሃል ላይ ቆሞ ፣ የለመድሽው ገላ
እኔም በባዶዬ ፥ ጾሜን ላለማደር
አንቺን ተከትዬ ፥ ከደስታቹ መንደር
የሐሴት ግርፋት ፣ ሲወርድብሽ በትር
ሲቃሽን ላደምጠው ፣ እቆማለው ከበር
ልማዴ ነውና…
ጩህትሽን ሰምቶ ፣ ከንፈር ልሶ ማደር
.
«ሚኪ እንዳለ»
@Mebacha
ፍቀጂልኝ
————
ከለምለሙ መስክሽ ፥ እርጥበት ካዘለው
ኮትኳች አራሚ ጣት ፥ ዘር ዘሪ ካልነካው
ከውሃ ገቡ ጓሮሽ ፥ ከሚለሰልሰው
ፍቀጂልኝና…
ፍሬሽ እንዲበዛ ፥ ጠምጄ ልረሰው
.
« ሚኪ እንዳለ »
@Mebacha
ጨረቃውም ቀላ ፣ ፀሐዩም ጠቆረ
ግዑዝ በጌታው ቃል...
እርቃን የመደበቅ ፣ ሚስጥርን ተማረ
ሰውም ሰለጠነ ፣... ..መጠቀ በረረ
ነገር ግን እሳቤው ፣ ከግዑዝ አጠረ
እንኳን የሰው እርቃን…
የራሱን መሸፈን ፣ ይሳነው ጀመረ
.
« ሚኪ እንዳለ »
የስቅለት ቀን የተከተበ
@Mebacha
ይሁዳ ተሻለኝ
——//——-
ካለኝ ሁለት ዲናር…
ሳልሰስት በሰጠው ፣ ባካፈልኩ ከቀረኝ
የንግድ ዓለም ልቧ...
ፍቅሬን በአሞሌ ፣ ለሌላው ሸጠብኝ
በባዶ ያሰረኝ…
አልቦ ያለበሰኝ…
በንብረት ዓለም ውስጥ ፣ ድህነቴ ጎዳኝ
አመደ አፋሽ አርጎ ፣ ከኩሽና አዋለኝ
.
ወትሮም ሙዳይ ያጣ ፣ መመርኮዣ ማገር
ይገፋል እድሜውን...
እኳን በሰው ቀርቶ ፣ ሲከዳ በምድር
አንቺን ምገልጽበት ፣ ቃላትም አለቀኝ
............ያ ልብሽ ሚያፈቅረኝ
በንዋይ ሚዛን ላይ…
አቅልሎ አቅልሎ ፣ ቅጠል አሳከለኝ
እንግዲ ምን ይሁን…
አንቺን ምይዝበት ፣ አልቦ ጥሪት የለኝ
ብር አልባ ወራዙት ፣ ምስኪን መጻጉ ነኝ
ኪሴን ባዶ አድርጎ…
ከማይነቅዝ ሃብቱ ፣ ጥበብን የሰጠኝ ፡፡
.
ያን ለታ ትፍረደኝ....
''ወድሃለው'' ያልሺኝ ፣ ያቺ ቃል ተቀምጣ
በይሁዳ ልብሽ…
በሠላሳ ዲናር ፣ ከመስቀል ስወጣ
ድንገት ለሚሰበር ፣ ለእንቁላሉ አሳቤ
ከስርሽ ላልጠፋው ፣ ለጫጩቱ ልቤ
ምነው አሸከምሽው…
የቀጸባን ቋጥኝ ፣ ማይቻል ምንዳቤ
በመገረም ሳደንቅ ፣ የጥርስሽን ንፃት
ዘንግቼው ነበር…
ጥቁር ጥርስ እንዳለ ፣ የሚስቅ በጽልመት
ካንቺ ሲሦ ክደት ፣ እንደ ሸጥ ካቦካኝ
የጸጸት ልብ ያለው...
ጌታውን የሸጠ ፣ ይሁዳ ተሻለኝ
.
አንተም የፈጠርከኝ...
በቁጣ በትርህ ፣ በመአት ስትመጣ
እባክህ ፍጡርህን ፣ በፍጡር አትቅጣ
ያተው እጅ ትዳሰኝ ፣ ያንተው እጅ ቆንጥጣ
ከጥንቱ ስትሰራኝ...
ችግርን የማይችል ፣ ልብን ከሰጠህኝ
እሬት አታድርገው ፣ ነገር እንዳይጥመኝ
በከባድ አርጩሜ ፣ ባክህ አትግረፈኝ
በማላውቀው ጢሻ ፣ እሾህ አትጣለኝ
ሳላስብ አትውሰድ ፣ ሳላስብ ሰተህኝ
.
ይልቅ ተለመነኝ !!!
ሃጢያቴን እያየህ ፣ አትመራመረኝ
ጠላቴን እንድወድ ፣ ያላቅሜ አትፈትነኝ
ቅንጣት ማይጸጽተው ፣ ዋሾ በበዛበት
እንደ ዩ'ዳ ምላስ ፣ ....ከምወድ በሐሰት
እንደ ቅዱስ ጳውሎስ፥ጠዪ አርገኝ በእውነት

( ሚኪ እንዳለ )
የምናየው በዝቶ ፥ ሆነን የጭን ሎሌ
ዘንድሮስ አልጦምናት ፥ ተፋጠን ተዳሌ
ምን የሚሉት ጦም ነው እስኪ ስም አውጡለት
ለአፍ ስጋ ነስቶ ፥ ባ'ይን ዳሌ ማየት

«ሚኪ እንዳለ»
እናት
-----
በአሐቲ ግብሩ ፣… እግዜር ተሳሳተ
ለልጆች አድልቶ ፣ ለ'እናት ሰሰተ
በዝቶ ካልጠቀመ !
መናኛ ከሚያበጅ ፣--እየደጋገመ
ከሚባክን ጭቃ…
ልጆችን ቀንሶ ፣--እናት በደገመ
እንደ ሮሐ ውቅር
እንደ ደብረ ኤረር
እንደ ዙፋንህ አምድ ፣ አንተን ተሸካሚ
ዘላለም የማቶድቅ
እናትስ በሆነች ፥ .…እንደ ኪሩብ ቋሚ
.
« ሚኪ እንዳለ »
@Mebacha
መስጠት
--------
በምናብ ዝማሜ ፣ በሹሩሩ ስሜት
የኋሊት ተጉዘህ ፣ በትዝታ ቅሪት
ከቁጭት ተጋብተህ
ትካዜን አርግዘህ
ትላንትን ለመውለድ ፣ ለምን ታምጣለህ?
አንተን ነው ማናግር
ስማኝማ አተኩር
በኩሸት አለም ውስጥ ፣ አደብህ ይበቃል
ከመቀበል ይልቅ ፣ መስጠትህ ይበልጣል
ያየህ ትቶ ቢሔድ ፣ .… የሰማን ያመጣል

« ሚኪ እንዳለ »
ፍካሬ እምነት
——————
ፀሐይ እንዲ ሳትጠነክር
አናት የሚበሳ ፣ ጦሯን ሳትወረውር
ቃጠሎ አብዝታ ፣ ..ፊትን ሳታሳርር
እላዩአ ላይ ሄጄ ፣ ወደም እጫወት ነበር
ያለችኝን '' አዎ አምኛለው ''
ምክያቱም 'ወዳታላው
.
አይኔ በጨለማ ያበራል
ከምስር መሃል እኳን ጠጠር ባክቴሪያ ይለቅማል
በኮኮብ ላይ ሚጫወቱ ፣ ህጻናትን ያያል
አስኮ ቁጭ ብሎ ፣ ራሺያን ይሰልላል
ያለችኝን '' አዎ አምኛለው ''
ምክያቱም 'ወዳታላው
.
ጸጉሬ እንዲ አጥሮ ሳይከረክር
የቁመቱ የርዝማኔው ነገር
መነሻውን አርጎ መሃል ሃገር
መዳረሻው በጌምድር
ያለችኝን '' አዎ አምኛታለው ''
ምክያቱም 'ወዳታላው
.
ቅድመ አያቴ ፣ ከጥንት ኃያላን አንዱ ነበሩ
እስከ ፑሉቶ ድረስ ፣ ታላቁ እስክንድርን አባረሩ
ጨረቃን በምንሽር ፣ አልመው ሰባባሩ
ከአናብስት ጋር ፣ ያድሩ ነበረ እያወሩ
ያለችኝን '' አዎ አምኛለው ''
ምክያቱም 'ወዳታለው
.
ድብር ሲለኝ ቀኑ ፣ ውሎዬ ሲበላሽ
ከባህር ዳር እወጣና ፣ ረፈድ ሲል በአመሻሽ
በውቅያኖስ ውስጥ ፣ እጠልቅና ያለ ትንፋሽ
ከሻርኮች ጋር ፣ እጫወት ነበር አባሮሽ
ከጀርባቸው...ቼቼ …እንጥልጥሎሽ
ያለችኝን አዎ ''እምነት'' ነው አምኛለው
ምክያቱም 'ወዳታለው
.
ግና ስትሰማሽ ፣ ነፍሴ ዝም ብላ
ከቃልሽ ጋር ስትሔድ ፣ የጎንዮሽ እንደ ጥላ
እውቀት እንደሌላት ፣ አይምሰልሽ ተጃጅላ
በእርግጥ አዎ አዎ
ብላሻለች ልቤ ሁሉን ተቀብላ
እምነት ማለት...
የሚወዱትን መከተል እንጂ፣ አይደለምና ሌላ
.
እስታይል(በእውቀቱ ስዩም)
ግጥም ( ሚኪ እንዳለ )
2024/07/01 04:17:05
Back to Top
HTML Embed Code: