Telegram Web Link
The 39th Ethiopian Higher Education Institutions Students Union general Assembly announcement that was hosted by Arbaminch Uni will be posted after an hours ,all our students are supposed to read it.
Thank you.
Join @MUSUofficalchannell
On behalf of the Dereja Family, We Thank you for your participation and support of the Nation's first Virtual Career Expo's resounding success . Moreover, We are happy to announce that we will be having second round Virtual Career Expo in November.

#Dereja
#Virtualcareerexpo
#Findyournextstep
39ኛው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት  ጉባኤ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከነሃሴ 21-23/2012 ዓ.ም በሰላም አጠናቀናል ፡፡

በስብባችን ያነሳናቸው ዋና ዋና ጉዳዮች፦
1. በCovid-19 ምክንያት አጠቃላይ የተማሪዎች  ሂወት በእቅድ ለመምራት የደረሰውን ማህበራዊ ምስቅልቅል በስፋት ተነስቷል ፡፡ ተማሪዎች የግል ስራ እንኳ ለመስራት ቁርጥ ያለ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን አለመታወቁ በእቅድ ለመመራት እንደተቸገርንና አሁንም የበሽታው ተሎ መጥፋት አሳሳቢ ስለሆነ በጥንቃቄ ጎን ለጎን ት/ት ይጀመርልን የሚለው በስፋት ተንፀባርቋል ፡፡
2. ኮሮና እንደ አለም የመጣ ችግር  ስለሆነ ትግሉ እንደ ዓለም ቢሆንም ነገር ግን እንደ ሃገራችን ደግሞ ከግዜ ወደ ጊዜ እያሳሰበን የመጣው የፖለቲካው ብልሽትና የዘረኝነት ጉዳይ በእጅጉ እንዳሳሰበንና የተማሪዎች መገደል ፡አፈና መፈፀም በትኩረት ቁጭት በተሞላበት መንገድ ተነስቷል ፡፡
3.ዩኒቨርሲቲዎች አለም አቀፍ አስተሳሰብ የሚንፀባረቅባቸው የፌዴራል ተቋም መሆናቸውን ቀርቶ የክክል ወይም የፅንፈኛ ፖለቲከኛ መፈንጫ መሆናቸው ተማሪዎቻችን እንደ ዩኒቨርሲቲ ተማሪነታቸው ለመምራት የተማሪዎች ህብረት ፈተና ውስጥ እንደገባን ተነስቷል ፡፡
4.የፌዴራል መንግሥት ሃገር ለሚያፈርሱ ፖለቲከኞች ለማወያየት  ትኩረት የሰጠው ጊዜ  ያክል  በግማሽ እንኳ ትኩረት ሰጥቶ አወያይቶን ና በሃገር ጉዳይ የተማሪዎች ስሜት አንጸባርቀን የምናውቅበት የፌዴራል መንግሰት መድረኮች በአግባቡ እያገኘን እንዳልሆ ተነስቷል ፡፡
5. የእኛው ዘመን መወሰን ያለብን እኛ እንጂ እድሚያቸው በመገጋደልና በመናቆር ጨረሰው የእኛ ዘመን በመገዳደል  እንዲያልቅ ከሚሰሩ ፖለቲከኞች እራሳችን ቆጥበን ከምንመራቸው ተማሪዎች ጋር ሃይማኖትና ብሄር ሳይለየን በዩኒቨርሲቲ ተማሪነታችን ልንታገላቸው እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
6. መንግሥት ጠንከር ያለ ህግ የማስከበር ስራ መስራት አለበት እንጂ ተማሪ እየተገደለ፡ ተማሪ እየታፈነ መቀጠሉ የህሊና ጠባሳ እንደሆነብን ተንፀባርቋል ፡፡
7.በcovid-19 የተቋረጠው ት/ት ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ይደረግ ቢባልም አንደኛው ወሰነ ት/ት ፋይናል ፈተና ሳይጨርሱ የቀሩ ዩኒቨርሲቲዎች እንዳሉና እንዲታሰብበት የሚለውም ተነስቷል ፡፡
በጥቅሉ በሶስት ቀን ቆይታችን ያልተነሱ የተማሪዎች ጉዳይ አለ ማለት አይቻልም ፡፡
-
ከሳይንስና እና ከፍተኛ ት/ት ሚኒስተር የመጡ ባለ ድርሻ አካላት በመድረኩ ያንፀባረቁት ነገር በCovid-19 ምክንያት ባለው አለም አቀፍ ሁኔታና የበሽታው ባህሪ  በግልፅ አለመታወቁ ዝግጀት እንዲደረግ አቅጣጫ ከመስጠት ባሻገር ቁርጥ ያለው ቀን ለመወሰን እንደተቸገሩ ገልፀዋል ፡፡ በተለይ ት/ት ከፍተው እንደገና የዘጉ ሃገራት ስላሉ እንዲህ አይነት ጉዳይ ቢያጋጥመን ተማሪዎቻችን የበለጠ ሞራላቸው ሊጎዳ ስለሚችል የሚለው ውዝግብ እንደከተታቸው ገልፀዋል ፡፡
ያም ሁኖ ትምህርት ይከፈት የሚለው የመንግሥትም አቋም እንደሆነ እና ለዛም ሲባል የምርመራ ዘመቻ በስፋት ተካሂዶ ብዙ ቁጥር ያለው ሰው እየተያዘ እንደሆነ ገልፀዋል ፡፡
በተለይ ደግሞ ዩኒቨርሲቲዎች ኳራታይ መሆናቸው ተጨማሪ ፈተና እንደሆነ ገልፀዋል ፡፡ ከዝግጅቱ በተጨማሪ ጎን ለጎን ከሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ጋር ት/ት ሲጀመር እንዴት መቋቋም አለብን በሚለው ውይይት እንደሚካሄድ አመላክተዋል ፡፡
እስከዛው ግን የሚጠሩበት ጊዜ ቅርብ ሊሆን ስለሚችልና የሚጠናቀቅበትን ጊዜ አጭር ስለሚሆን ተማሪዎች እያነበቡ በመንፈስም ተረጋግተው እንዲጠብቁ የሚል ምክራቸው ለግሰዋል ፡፡
****-***
ሌላው እኛም እንደተማሪ ህብረት የመፍትሔ አቅጣጫ የምንለውን ነገር ከተማሪዎች አስተያየት በመሰብሰብ ጭምር ተጨማሪ ውይይት በቅርብ ቀን የሚኖረን ይሆናል፡፡
ከዛ ባሻገር Covid-19 ዓለም አቀፍ ስለሆነ ያደረሰብን ጫናም እንደ አለም ነው፡፡
አሁንም እያሳሰብን ያለው ነገር ተማሪዎች በነፃነት እየተማሩ እንዳልነበርና በተለይ ከሚኖሩበት ክልል ውጭ የሚሄዱ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ሳይሆን በቅኝ ግዛት ተማርከው የሄዱ ያክል ተሳቀው፡ አለፍ ሲልም ግድያና አፈና እደረሰባቸው እየተማሩ መሆናቸው አሳስቦናል፡፡
*-*
ሚዲያዎችና መንግሥት ፈቃደኛ ከሆኑም በቅርብ ጊዜያት አጠቃላይ ባለፉት ዓመታት በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የደረሰው ጉዳት፡የስነልቦና ጫና እና መፍትሄዎቻቸው በተጠና መልኩ እንደ ሃገር  በኢትዮጵያ ከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አማካኝነት መግለጫ የምንሰጥ ይሆናል፡፡
   
"🇪🇹እናት ሃገራችን ለዘላለም ትኑር🇪🇹 "
    
 የኢት/ከፍ/ት/ተቋ/ተማሪዎች ህብረት

Addis Abeba, Ethiopia
          
     join  @MUSUofficalchannell
Breaking news!
Mekelle University is preparing to start Community centered TV channel. Community radio is already giving service. #We_really_care MU
Join @MUSUofficalchannell
የሞሞና ቴሌቪዥን ጣቢያ ለማቋቋም የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናዎን እንገኛለን። የመቐለ ዩኒቨርስቲ ኮሚኒቲ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ አካል የሆነው የሞሞና ቴሌቪዥንን በሳተላይት ለማሰጀመር የማሳራጭያ እቃዎች ዝርዝር ጥናት እና የስቱዲዮ ግንባታ ቅደመ ዝግጅት ዛሬ በ26/12/2012 ዓ/ም በዘርፉ ላሉ ባለሞያዎች ቀርቦ አሳብ እና አስተያየት ተሰጥቶበታል።

በውይይት መድረኩ ላይ የኮሚኒኬሽን ምህንድስና ኢንጂነሮች፣ የእንፃ ግንባታ እና ዲዛይን ባለሞያዎች፣ የኤሌክትሪክ ኢንጂነሮች፣ የጋዜጠኝነት እና ኮሚኒሽን መምህራን፣ የትያትር እና ጥበባት መምህራን እና ባለድርሻ አካልት የተሳተፉ ሲሆን ገንቢ ሃሳብ እና አስተያየት እንዲሁም በቅደመ ዝግጅት ስራዎቻችን ላይ የታዩ ጉደለቶች ከመድረኩ ተሳታፊዎች ተነስተዋል።

የዩኒቨርስቲያችን የማሕበረሰብ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ
በዘርፉ ላሉ ባለሞያዎች፣ ተማሪዎች እና መምህራን የተግባር ትምህርት ማሰልጠኛ እንዲሁም ለማሕበረሰባችን አማረጭ የመረጃ ምንጭ በመሆን የማሕበረሰብ አገልግሎት የሚሰጥበት ይሆናል።

https://www.facebook.com/110168646998819/posts/325094585506223/

"We really care"

(VIA Mr Bereket Hasen).
Join @MUSUofficalchannell
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ጉባዔ ተካሄደ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
39ኛው የህብረቱ ጉባኤ የተካሄደው በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት አጀማመርና የኮቪድ -19 ተፅዕኖ እንዲሁም ሰላማዊ መማር ማስተማርና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ሚና ላይ ትኩረት አድርጎ ተካሂዷል፡፡
ነሐሴ 21 ቀን 2012 ዓ.ም በተካሄደው ምክክር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራስን ከመግዛትና የባህል ብዝሃነትን ከማስተናገድ አንፃር የተማሪዎች ህብረት ሚና በሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል፡፡
በማጠቃለያው የተማሪዎች ህብረት አመራሮች በመማር ማስተማር ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት በሚደርጉት ሂደት ተገቢውንና ትክክለኛውን አቅጣጫ ይዘው በሰላማዊ መንገድ በማስተባበር ሊሆን ይገባል ተብሏል፡፡
በጉባዔዉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መምህራንና ተማሪዎች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ኢዶሳ ተርፋሳ፣ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንትና አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተጋበዙ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች እና አሰልጣኞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዉይይት በማድረግ ተሳትፈዋል፡፡
Hawassa University's Notice is for postgraduate pls dont be confused.
Join @MUSUofficalchannell
Forwarded from MIT Information Posting board
Topic
RAISING CAPITAL FOR START UPS
Description
The Young Entrepreneurs Forum (YEF) provides start-ups and early stage businesses with tools, skill sets and networks to effectively engage in the national policymaking process for an improved business environment in Ethiopia. Implemented in collaboration between Precise Consult International PLC (Precise) and the Center for International Private Enterprise’s (CIPE), the YEF opens doors of opportunities for young entrepreneurs to unlearn unfounded presumptions, learn new skills and relearn successful approaches of policy engagement.
Time

Sep 3, 2020 03:00 PM in Nairobi
Add to calendar
Webinar ID
881 1552 2451
To Join the Webinar
Join from a PC, Mac, iPad, iPhone or Android device:

Please click this URL to join. https://us02web.zoom.us/w/88115522451?tk=TG_1GegklgjyP5GjgPUcrmfZNsZhDt38JaGfmeU4rRc.DQIAAAAUhBgrkxZGRi1iU29lcVRUMjNzU01Sa1hEcG53AAAAAAAAAAAAAAAAAAAAAAAAAAAA&pwd=UlZTQUR5TTFYYVNwaE1uS0ZiN0htdz09&uuid=WN_tyBg27mKS4Wt7mVn9HvOYw
በ2013 ትምህረት ለማስጀመር በትምህርት ሚኒስቴር የተያዙ አማራጮች!

የ2013 ዓመት ትምህርትን ለመጀመር የሚስችሉ ሁኔታዎችን በማጥናት ላይ እንደሚገኝ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ እንደ አማራጭ እየታዩ ያሉ ጉዳዮችም፡-

- በአንድ ክፍል ውስጥ ከ20 እስከ 25 ተማሪዎችን ለማስተማር የሚያስችል አቅም ስለመኖርና አለመኖራቸው ልየታ አየተካሄደ ነው፡፡

- የተማሪዎችን ርቀት ለማስጠበቅ በአንድ ወንበር አንድ ተማሪ እንዲቀመጥ የሚደረግ ታስቧል፡፡

- ትምህርትን በፈረቃ መስጠት እንደ አማራጭ ቀርቧል፡፡

- ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡

- የማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ለማስተማሪያነት መጠቀም እንደ አማራጭ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ አየተጠና ነው፡፡

- በትምህርት ቤቶች ውስጥ ውሃ እንዲኖር ማድረግ፣ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘርና ማስክ የማቅረብ ስራዎችም እንደሚሰሩ ተገልጿል፡፡
Join @MUSUofficalchannell
መልእክቲ ካብ ማሕበር ተራድኦ ኬብርን -መቀለ!
ፃውዒት ሰናይ ተግባር
"One Pack for One Child"
ኣብ ዝሓለፉ ኣርባዕተ ዓመት ኣብ ከተማ መቐለ ሓደ ጥማር ንሓደ ህፃን (One Pack for One child) ብዝብል መሪሕ ቃል ንልዕሊ 3000 ሰገናት ናይ ፅሕፈት መሳርሕቲ ድጋፍ ማሕበር ተራድኦ ኬብሮን ኣካይዳ እያ፡፡
👉ሎሚ ዓመት ድማ ቫይረስ ኮሮና ዳተኸላኸልና ፀገም ማሕበረሰብና፣ ፀገም ሰገናትና ክንፈትሕ ኢና፡፡ኣብዙይ ሰናይ ተግባር ክትሳተፉ ትደልዩ ኣድራሻታትና
👇👇👇👇👇👇👇👇
ፊት ንፊት ማይ ካፌ ኩመል ህንፃ ቢሮ ቁ 19
ወይ ድማ ኤላዝ ካፌ ትሕት ኢልካ ዝርከብ መካተቻ ኢንተርተይመንት፡፡

"ህፃንነተይ ተቀበሉኒ ዋሕስ ፅባሕኩም እየ፡፡"

ማሕበር ተራድኦ ኬብርን
መቐለ

for more info visit @Kebroncharity


Join @MUSUofficalchannell
ማስታወቂያ
ለመላው የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ማህበረሰብ:

።።።
በኮቪድ 19 ወረርሸኝ ምክንያት የገጽ ለገጽ ትምህርት መቋረጡና ለበለጠ ጥንቃቄ ሲባል ተማሪዎች በልዩ ዝግጅት ወደቤተሰቦቻቸው መሸኛታቸው ይታወሳል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል የሚያስችሉ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን ቀደም ብለን መግለጻችንም ይታወቃል።

ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ዩኒቨርስቲዎች የሚከፈቱበት ቀን እንደተቆረጠ ሆኖ በተለያዩ አካላት የሚወጣው መረጃ የተሳሳተ እንደሆነና የተቋረጠው ትምህርት ሊቀጥል የሚችለው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ትምህርት ማስቀጠል የሚያስችል መረጃ ሲገኝ ብቻ እንደሆነ እና መረጃውም የሚሰጠው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል ብቻ መሆኑን እያሳወቅን እስከዛው ድረስ የቫይረሱን ስርጭት ለመከለካል የሚያስችል አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ እያደረጋችሁ ከክፍያ ነጻ በሆነው የዲጂታል ላይበራሪያችን http://ndl.ethernet.edu.et በመግባት አጋዥ መጻህፍትን እያነበባችሁ እንድትጠባበቁ እናሳስባለን።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
ጳጉሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
።።።።

አዲስ ዓመት ለብዙዎች የአዳዲስ እቅዶች እና ኃሳቦች መነሻና ማስተግበሪያ ነው። ትልቅ የተስፋ አድማስ የሚታይበትም ነው! በአዲስ ዓመት ብዙዎች ትምህርት ለመጀመር፣ የተጀመረን ለማጠናቀቅ፣ ንግድ ለመጀመርና ቤተሰብ ለመመስረት ወዘተ ያስባሉ። ያቅዳሉ።

ሰዎች እንደግለሰብ ብቻ ሳይሆን ተቋማትም በአዲስ ዓመት ከአዲስ አሰራርና አካሄድ ጋር ይመጣሉ። አዳዲስ ስራዎችን፣ ቴክኖሎጂዎችን፣ ፈጠራዎችን፣ የአሰራር ስርዓቶችንም ያስተዋውቃሉ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር 2012 ዓ.ምን ሲቀበል "በአዲስ ዓመት አዲስ አስተሳሰብ" በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የለውጥ ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ ነበር። በዚህም የመጀመሪያ ዓመት የጋራ ኮርሶችን ተግባራዊ በማድረግ የተማሪዎች የዩኒቨርስቲ አነስተኛ ቆይታ ጊዜ 4 ዓመት እንዲሆን ተደርጓል፣ ዩኒቨርስቲዎችን በተልዕኮ መለየትም ሌላው ወሳኝ የዓመቱ የለውጥ ስራ ነበር።

በአዲሱ 2013 ዓ.ም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዳዲስ አሰራሮችን ይዞ በመምጣት በተለይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያለውን ለውጥ መሸከም የሚችል ቀልጣፋ እና ወጥ የአሰራር ስርዓትን መዘርጋት ላይ አተኩሮ ይሰራል። ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልዕኳቸው ላይ ብቻ አተኩረው እንዲሰሩ የማመቻቸትና የመከታተል፣ ለመምህራን ትኩረት ሰጥቶ መስራት፣ ተቋማት ችግር ፈቺ አሰራሮችን እንዲከተሉና እንዲሰሩ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ የመረጃ ልውውጥ በአንድ ቋት የማደራጀትና መሰል የትምህርት ጥራት ላይ የሚያተኩሩ ስራዎች የሚከናወኑ ይሆናል።

የትምህርትና ስልጠና ማህበረሰቡ በራቸውን ለአዳዲስ አሰራሮችና ለውጦች በመክፈትና ኃሳብ በማመንጨት በዛው መጠን ፈጻሚ በመሆን ምርምሮች ችግር መፍታት ላይ እንዲያተኩሩ፣ ሳይንሳዊ አሰራሮች እንዲዳብሩ፣ ለሌላው ሴክተር ተምሳሌታዊ የሆኑ የአሰራር ስርዓቶችን ለመገንባት በሚደረገው ሁሉ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀርባለሁ።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በዓለም ላይ ያለውን የትምህርት ሴክተር በእጅጉ የተፈታተነ የ2012 ዓ.ም ክስተት ነው።
ይሄ ክስተት ጤናን ብቻ ሳይሆን ማህበራዊና የኢኮኖሚ ሴክተሩንም በእጅጉ የፈተነ ነው። ተማሪዎች በኮቪድ 19 ምክንያት በቤታችሁ መሆናችሁ ከባድ ጊዜ እንደሆነ እገነዘባለሁ። ነገር ግን ኮቪድ 19 የብዙዎችን ነፍስ የነጠቀ እንደመሆኑ ጥንቃቄና ትዕግስት ከእናንተ ይጠበቃል። አዲሱ ዓመት 2013 መልካም ነገር ላይ የምትደርሱበት ያለማችሁበት የሚፈጸምበት እንዲሆን ሁሌም ራሳችሁን ለመጠበቅ አትዘናጉ።

በምናደርገው ጥንቃቄና በምንወስደው እርምጃ የቫይረሱን ስርጭት መግታትና አደጋውን መቀነስ እንችላለን፡፡ በቅርቡ ለምትመለሱበት መማር ማስተማር ይሔው ጥንቃቄ ወሳኝ በመሆኑ በዚህ ረገድ የተሻለ ስራ እንድንሰራ አደራ እላለሁ!
የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትም ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል የሚደረገውን ዝግጅት አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ አሳስባለሁ!

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የአንድነት ይሁንልን!
መልካም አዲስ ዓመት

ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
ጳጉሜ 05/2012
Message from the students Union.
The year 2012ec had been very challenging, there was challenges beyond the pandemic and it just put its own record, we had all individual comments and we ware pushing accordingly. at national level we made the union s General meeting to set a new direction and possible solution even if the pandemic. we reputedly make good contact with the responsible bodies and Until the final political decision of the date of return, pls make necessary Covid19 prevention mechanisms and some other academic preparation. Finally i wish a Happy New year to all our dearest Students! on the be half of Students Union , wishing New 365 days with new 365 chances and Just Wave goodbye to the old and embrace the new with hope, dreams and ambition. Wishing you a Happy New Year full of happiness!
Abrhaley Arefaine -MUSU President and EH/HI/ED/INS/SU V/President.

"Stay home, stay safe"

hope you back soon!!

Thank you.
👇👇👇👇👇👇
Join @MUSUofficalchannell
New is the year, new are the hopes, new is the resolution, new are the spirits, and new are my warm wishes just for you. Have a promising and fulfilling New Year! Hope a bright new year for all Ethiopia students as well as all my people. With a hope of union and back to school.
Oli bedane
EHISU & Ambo university president

Join @MUSUofficalchannell
Forwarded from Balli G
እንኳን አደረሳችሁ
Forwarded from Balli G
Baga geessan
2025/07/04 05:11:56
Back to Top
HTML Embed Code: