Telegram Web Link
ተቋማችን ተማሪዎችን ጥር 29 - 30/2013 ዓ/ም ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል። የምዝገባ ጥሪው በሁሉም መርሃግብሮች፦
✍️በመጀመርያ ዲግሪ ፤
✍️ በማስተርስ ፤
✍️በፒ ኤች ዲ ፤
✍️በተከታታይ ትምህርት ፤
ፕሮግራሞች ለሚማሩ ሁሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን!

ከ መቐለ ዩኒቨርስቲ ሕጋዊ ትዊተር ገፅ
የተወሰደ
To All MU PG(Post Graduate)Students and New Applicants
--------------
Reporting/Registration Date: Feb 8-14, 2021

Entrance Exam Dates for New Applicants:
For EiT-M Only - Feb 12, 2021
For All Colleges/Institutes - Feb 15 - 17/2021 https://t.co/an0XuF557X
Congratulations!
የዓዲ ግራት ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች ነገ ዕለት(06/06/2013) የምርቃት ስነ ስርዓት በመቐለ ዩኒቨርስቲ ያከናውናሉ።በተለያዩ ምክንያት ያልተመረቁ የዩኒቨስትያችን ተማሪዎችም ኣብረው ነገ ይመረቃሉ።እንኳን ደስ ኣለችሁ።በምርቃት ሰነ ስርዓት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር - ሚኒስቴር ይጠበቃሉ።
💥መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማሩን ሥራ መጀመሩን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር ከሰተ ለገሰ፣ የመማር ማስተማሩን ሥራ የጀመሩት ከሚጠበቁት 13ሺህ ተማሪዎች ውስጥ አብዛኛዎቹን በመቀበል ላይ መሆኑንና የቀሩትንም እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል።

ተማሪዎቹ በመቀሌ ማኅበረሰብ እና ተማሪዎች ኅብረት አቀባበል እየተደረገላቸው ከየካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም አንሥቶ ትምህርታቸውን መከታተል መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎች፣ መኝታ ቤቶች፣ ምግብ ማብሰያ እና መመገቢያ አዳራሾችን የኮሮና ወረረሽኝን ለመከላከል ታሳቢ ባደረገ መልኩ ቀድመው መሰናዳታቸውን ዶ/ር ከሰተ አስረድተዋል።

ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ዓመት ድረስ የሚማሩት እነዚህ ተማሪዎቹ የተቋሙን ሕግ እና ሥርዓት አክብረው ትምህርታቸውን መከታታል እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል።

ትምህርታቸው መከታተል ከጀመሩት መካከል ከደቡብ ክልል የመጣው የአዲሀቂ ካምፓሰ የሶሾሎጂ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ ቸርነት ሺፈራው ትምህርት በመጀመሩ መደሰቱን ገልጾ፣ በንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት በኩል ግን እጥረት ስላለ እንዲስተካከል አስተያየቱን ሰጥቷል።

የእኛ ተማሪዎች ሕልም በሰላም እና ፍቅር ትምህርታችንን መከታተል እና ተመርቀን ራሳችንና ሀገራችን መጥቀም ነው ያለው ደግሞ የሁለተኛ ዓመት ሶሾሎጂ ተማሪ እንድሪስ አብዱ ነው።

ከኦሮሚያ ክልል የመጣው ተማሪ ጫላ ሳፋይ በበኩሉ ዩኒቨርሲቲው ለመማር ማስተማር የሚያስችል የግቢው መሠረተ ልማት ማሟላቱን ገልጿል።

በምግብ ሰዓት ግን በወረፋ ብዛት ምክንያት ለብዙ ሰዓታት እየጠበቅን መሆኑን ታውቆ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል።

#EBC
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የመቐለ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች የጋራ ፎረም ምስረታ ዛሬ ተካሄደ !

በትግራይ የሚገኙት አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች (መቐለ፣ ራያ ፣ አክሱም ፣ ዓዲግራት ) ወደቀድሞ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ የሚያስችል ፎረም ምስረታ ዛሬ በመቐለ ተካሄደ።

ፎረሙ በተለይም ከየካቲት 29 ጀምሮ የሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱትን በትግራይ ያሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎቹ ገብተው እንዲፈተኑ ለማድረግ ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል።

በተጨማሪ በክልሉ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በሚሰራው ስራ አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ ነው የተገለፀ።

በሌላ በኩል አራቱም ዩኒቨርሲቲዎች በትግራይ የተፈጠረው ሰብዓዊ እና ማህበራዊ ቀውስ ለመፍታት ለሚደረገው ስራ የ20 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

መቐለ ዩኒቨርሲቲ 10 ሚሊዮን ብር ፣ አክሱም 4 ሚሊዮን፣ ዓዲግራት 4 ሚሊዮን እንዲሁም ራያ ዩኒቨርሲቲ 2 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from Aksum university student's union
ለሁሉም ተመራቂ ላልሆናችሁ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ

የተከበራችሁ እና የተወደዳችሁ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኮረና ቫይረስ እንዲሁም በክልሉ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በዩኒቨርስቲያችን ውስጥ መማር ማስተማር ተቋርጦ ለ11 ወራት ያህል ከትምህርት ገበታ እንደራቃችሁ እና ይሀን አልበቃ ብሎ ስለዩኒቨርስትያችን አጠቃላይ ወቅታዊ ሁኔታ እናዩኒቨርስቲዉን ስለሚያወጣቸው አዳዲስ መረጃዎችን እየተከታተለ የሚያሳውቅ አካል አጥታችሁ ስትቸገሩ እና ስትጉላሉ መቆየታችሁ የሚታወቅ ነው።
በ "ኢንተርኔት"እና "ኔትዎርክ" መዘጋት ምክንያት
ስለዩኒቨርስቲያችን ወቅታዊ ጉዳዮች እና አዳዲስ መረጃዎች በአግባቡ ተከታትለን ስላላሳወቅናችሁ ይቅርታ እየጠየቅን የግቢ መግብያ ቀን በተመለከተ በቅርበት እየተከታተልነው እና በተቻለ መጠን እንዲፈጥን እየሰራን መሆናችን እና ዩኒቨርስርቲው በጦርነቱ ምክንያት የወደሞውን ንብረት በመተካት ተማሪ ለመቀበል የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እያጠናቀቀ መሆኑን ላበስራችሁ እወዳለሁኝ።ስለዚህ የተከበራችሁ ተማሪዎቻችን ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ወደ ግቢ የሚገቡበት ቀን አስመልክቶ በመገናኛ ብዙሃን እስክያሳውቅ ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁ እጠይቃለሁኝ።
"በሰላም ያገናኘን"
ጎይተኦም ሃይሉ
የአክ/ዩኒ/ተማ/ሕብረት ፕረዚዳንት
Training at DKT-Ethiopia , Bishoftu , Addis Abeba.
#Amazing facility, thank you
Mekelle University Student Union
Photo
#Family, great family. ❤️❤️❤️ , thank you Mr Shime. #DKT -Ethiopia.
2024/09/23 11:21:01
Back to Top
HTML Embed Code: