Telegram Web Link
everyone
am Mikiyas,🙏please be calm this isnt Mekelle University Management's telegram account this is owned by Mekelle University Student Union so you have to aware of what you are asking to Us. we can't announce and put date of return, but as we are your representatives we are eagerly asking when is the perfect date our student will  return.we now that all of us suffered by those days and always pass through difficulties this is understandable and righteous and that is true we are at worst time of our life as student .and what i would like to say is the idea raised by all of you is right and precise.

We are trying to come with Good news ! God help Us all!
Thank You.
Good Breaking News
For Raya University Students

ራያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአካል ቀርበው እንዲመዘገቡ ጥሪ አቀረበ።

ራያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና ተከታታይ ትምህርት መርሐ ግብር ትምህርታቸውን ለመከታተል ቀደም ሲል ዩኒቨርሲቲዉ ባወጣዉ ማስታወቅያ መሰረት የተመዘገቡ (የዩኒቨርሲቲዉና ከሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያመለከቱ) ተማሪዎች ሰኔ 6 እና 7 / 2015 ዓ.ም በራያ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት በአካል በመገኘት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

Via/Source - @tikvahethiopia
Hello all of you, really and sure mekelle university is fully prepared to resume the students to campus and the declaration will happen soon
"የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ በስተቀር ሦስቱ ዩኒቨርሲቲዎች በመጭው ወር ነባር ተማሪዎችን መቀበል ይጀምራሉ።"
- ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ሥራ አቁመው የነበሩ ዩኒቨርሲቲዎች ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ በስተቀር ከአንድ ወር በኃላ ነባር ተማሪዎቻቸውን እንደሚቀበሉ ከመስከረም (2016) ጀምሮ ደግሞ #ሙሉ_ለሙሉ ሥራ እንደሚጀምሩ አስታውቋል።

የሚኒስቴሩ የአስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሀ (ዶ/ር) ለኢፕድ የሰጡት ቃል ፦

" ከአክሱም ዩኒቨርሲቲ በስተቀር ሦስቱ ዩኒቨርሲቲዎች በመጭው ወር ነባር ተማሪዎችን መቀበል ይጀምራሉ።

በመጪው ዓመት በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

ዩኒቨርሲቲዎቹን ወደ ሥራ ለማስገባት የትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎቹ ያሉበት ሁኔታ ከዩኒቨርሲቲዎቹ አመራሮች ጋር በመቐለ ተደጋጋሚ ውይይት አድርጓል።

ሥራ ለማስጀመር የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመስራት ወደ ተግባር ተገብቷል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የመማር ማስተማር ሂደት ከመጀመራቸው በፊት  ፦
- የምግብ ፣
- የመኝታ፣
- የሕክምና አገልግሎቶች ቅድሚያ የሚያሟሉበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው።

ራያ ዩኒቨርሲቲም ይህንን አሟልቶ በትናንትናው ዕለት የተማሪዎች ምዝገባ ጀምሯል።

መቐለና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በቀጣይ ወር ትምህርት መጀመር የሚያስችላቸውን ተግባር ጨርሰው ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎች በበለጠ በጦርነቱ ጉዳት በማስተናገዱ የተወሰነ ጊዜ ሊዘገይ ይችላል።

አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች ከጦርነቱ በፊት 45 ሺሕ ተማሪዎችን ሲያስተምሩ ነበር። ከእነዚህ ውስጥም ባለፉት ዓመታት 22 ሺሕ የሚሆኑ ተማሪዎች እንዲወጡ ተደርጎ በጊዜያዊነት ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ተመድበው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ተደርጓል።

እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎችም አሁን ላይ ቅበላ የሚያደርጉት ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሳይመደቡ የቆዩ 20 ሺሕ የሚሆኑ ተማሪዎችን ነው።

በመጪው አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው የሚያልፉ ተማሪዎችም የዩኒቨርሲቲዎቹ ዝግጁነት ተጠንቶና ታይቶ ተማሪዎች ሊመደቡባቸው ይችላል።

ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩና ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ሄደው ያጠናቀቁ ተማሪዎች ውጤታቸውን የሚገልጽ የትምህርት ማስረጃ ሳያገኙ መቆየታቸውን ይታወሳል ፤ አሁን ላይ ከነበሩበት ዩኒቨርሲቲ ያገኙት ውጤት ወደ ትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲላክ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ዩኒቨርሲቲዎቹም ውጤቱ ሲደርሳቸው የነበራቸውን ውጤት ደምረው ጥቅል ውጤታቸውን የሚገልጽ ጊዜያዊ ዲግሪ ማግኘት ይችላሉ። "

Via EPA

@tikvahethiopia
#Raya University

ራያ ዩኒቨርሲቲ ከሰኔ 06/2015 ዓ.ም ጀምሮ ነባር ተማሪዎቹን እየተቀበለ ነው።

ዩኒቨርሲቲው ከ900 በላይ ነባር ተማሪዎችን መቀበሉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታደሰ ደጀኔ ተናግረዋል።

Via @tikvahuniversity
#Welcoming of Student
Raya University
Some additional pics on Raya Uni
Source -Gebru Desalegne on fb
Really our university trays to resume students to campus and our beloved students don't believe any notification pasted by media and Facebook, telegram.
You should have to follow only our university notification stamped by concerned part and by mekelle university student union notification
And student union coordinator es are nearly communicated with university management to announce you the specific time to enter
Not more than two weeks
Pls share this channel to get new information and additional information
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲያስተምሩ ለነበሩ መምህራን ጥሪ ሊደረግ ነው፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራን የሰሜኑ ጦርነት መቀስቀስን ተከትሎ ተፈናቅለው በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በጊዚያዊነት ተመድበው ሥራቸውን እንዲጀምሩ መደረጉ ይታወሳል።

"ነገር ግን አሁን ላይ ሁኔታዎች እየተስተካከሉ በመሆኑ መምህራኑ ወደቀድሞ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ተመልሰው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ እንደሚደረግ" በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

Via @tikvahuniversity
2024/09/23 09:20:31
Back to Top
HTML Embed Code: