Telegram Web Link
እንድታውቅሉኝ||To be Noted:
I am getting so many messages and calls, i am giving service what i can .I am so busy ,tried and working . all your question are Noted in a well manner. If any new info i will update you ASAP. don't worry.
Thanks , stay in touch!

Respectfully yours;

Abrhaley Arefaine;

Join @MUSUofficalchannell
ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፡-

ደብረ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመቀበል በአስተዳደርና የአካዳሚክ ዘርፉ የተሰሩ ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ገመገመ፡፡
ደማዩ ጥቅምት19/2013 ዓ/ም፦ ዩኒቨርሲቲው የመጨረሻ ዓመት (Graduate Class Student) ተማሪዎች ጥቅምት 5 እና 6/2013 ዓ/ም ለመቀበል ወስኗል፡፡
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሲባል ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ላልተወሰነ ጊዜ ተመልሰው መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ በመሆኑም የጤና ሚኒስትር እና የሳይንስና ከፍ/ትምህርት ሚኒስትር በሰጡት አቅጣጫ መሰረት ተቋርጦ የነበረውን የ2012ዓ/ም ትምህርት ለማስቀጠልና የ2013ዓ/ም የትምህርት ዓመት ስራ ለማስጀመር የተሰሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ግምገማ መስከረም 19/2013ዓ/ም ተካሂዷል፡፡
በዚህም በአስተዳደር ዘርፉ ለተማሪዎች ምግብ ቤት፣ ምኝታ ቤት ፣ ክሊኒክ አገልግሎትና ሌሎች ግብዓቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎችን መቀበል የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁንና በአንድ ምኝታ ክፍል ሶስት ተማሪዎች ብቻ ድልድል የተሰራ መሆኑን የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አለቃ አስረድተዋል፡፡
በአካዳሚክ ዘርፍም ተማሪዎችን ተቀብሎ መማር ማስተማሩን ለማስቀጠል የቤተ-መጽሃፍት፣ ቤተ ሙከራዎችን በግብዓት የማሟላት ፣ የክፍል ጥምርታ ፣የትምህርት ዓይነቶች (Course) ድልድል በየዘርፉ መሰራቱን የአካዳሚክ ጉዳዮች ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር በለጠ ያዕቆብ አስረድተዋል፡፡ የተማሪዎች የክፍል ውስጥ ጥምርታ እንደየመማሪያ ክፍሎች መጠን በክፍል 35 ተማሪ እንዲሆን መታቀዱን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም የትምህርት ዓይነቶች (Course) ድልድል በየትምህርት ክፍሎች የተሰራ ሲሆን የአንድ ክፍለ ጊዜ ቆይታም በ35 ደቂቃ መሆኑን ዶ/ር በለጠ ያዕቆብ ተናግረዋል፡፡
የተማሪዎችን የመማር ማስተማር ሂደት በማስመልከት የወጣው የጊዜ ሰሌዳ (Tentative Academic Calendar) በ2012 ዓ/ም የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች (graduate class student) በመጀመሪያው ምዕራፍ ጥቅምት 5 እና 6/2012ዓ/ም እንዲጠሩና ያቋረጡትን ትምህርትም የምረቃ ዝግጅቱን ጨምሮ በ54 ቀናት እንዲሚያጠናቀቁ የሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ ዶ/ር ገብሩ ታደሰ አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም ኮሮና ቫይረስን ግምት ውሥጥ በማስገባት የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል መላው የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ በትልቅ መነቃቃት ለተፈጻሚነቱ መረባረብ እንዳለባቸው በማሳሰብ በተለይም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2012ዓ/ም ያለምንም የጸጥታ ችግር ተቋሙን በመምራት ደረጃ የነበረው ግሩም ተሞክሮ ተጠናክሮ ሰላማዊ መማር ማስተማር ነባህል እንዲቀጥል የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች እንዲሁም የትምህርት ክፍሎት ትልቁን ስራ መስራት እንዳለባቸው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ በአጽኖት አሳስበዋል፡፡
በተማሪዎች ቅበላ ቅድመ ዝግጅት ላይ ያልተጠናቀቁ ስራዎች በትኩረትና በአስቸኳይ እንዲፈጸሙ የስራ ክፍል ሃላፊዎችም በሙሉ ትኩረት ክትትል እንዲያደርጉ በማሳሰብ የተማሪዎች ክሊኒክ ተገቢውን የመድሃኒት ግብዓት በማሟላት ተማሪዎችን ስንቀበልም ሆነ ስናስተምር የኮሮና ወረርሽኝን በመከላከልና በመቆጣጠር ተገቢው የህክምና ዝግጅት እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡
በመሆኑም ተመራቂ መደበኛ ተማሪዎች ጥቅምት 5 እና 6/2013ዓ/ም ወደ ዪኒቨርሲቲያቸው በመምጣት ሃሙስና አርብ ገብተው እሁድና ቅዳሜ ተቋማቸውን ተላምደው ሰኞ ጥቅምት 9/2013 ዓ/ም ትምህርት እንዲጀምሩ በፕሬዚደንቱ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
ፕሬዚደንቱ አክለውም የመጨረሻ ዓመት የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች (Graduate Class Student) ተቀያሪ ማስታወቂያ ካላወጣን በስተቀር ጥቅምት 5 እና 6/2013ዓ/ም ወደ ዩኒቨርሲቲያቸው ለመምጣት ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ አድርገዋል፡፡

Via ደብረ ማርቆስ ዩኒ ተማሪዎች ህብረት

Join @EHEISUOfficialChannell
የሕግ ትምህርት የመውጫ ፈተና ከሕዳር 1-4 ባለው ጊዜ ውስጥ ይሰጣል

የ2012 ዓ.ም የሕግ ትምህርት የመውጫ ፈተና በኮሮና በሽታ ምክንያት መራዘሙን ተከትሎ ፈተናውን በ2013 ለመስጠት የፍትሕና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢኒስትቲውት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ ከሕዳር 1-4 ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲሰጥ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

@capital_news1
@capital_news1
Forwarded from Deleted Account via @Giyonbot
➡️DW info® ፈጣን፣ እዋናውን ሓቃውን ሓበሬታ ዘቅርብ ብሉፅ ቴሌግራም ቻነል'ዩ።
የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጥሪ ይደረግላቸዋል በሚል የተሰራጨው ዜና ስህተት መሆኑ ተገለፀ፡

🎲ከሰሞኑ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮችን የተሳተፉባቸው ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡ በዋናነት በጅማ ዩንቨርሲቲ ሲካሄድ የቆየው የሦስት ቀናት ጉባኤ እንዲሁም በጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት የተካሔዱ ውይይቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

🎲ባለፈው ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የ2013 ዓ.ም ትምህርት በሚጀመርበት ሁኔታ ላይ የመከረው ጉባኤ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጥሪ እንደሚደረግላቸው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መገለፁን ከተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ሰምተናል።

🎲ይሁን እንጂ ኢትዮ ኤፍ ኤም ያነጋገራቸው የባህርዳር፤ የድሬደዋ እና የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንቶች ባለፈው ሳምንት የ45 ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በጅማ ሲያካሂዱት በቆየው የሦስት ቀናት ጉባኤ ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎቻችሁን ተቀበሉ የሚል አቅጣጫ አለመቀመጡን ገልፀዋል፡፡

🎲ኢትዮ ኤፍ ኤምም የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጥሪ ይደረግላቸዋል የሚለው ዜና ከመሰራጨቱ በፊት በጊዜ ገደቡ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እንዲጠሩ የተቀመጠ አቅጣጫ ሳይኖር መረጃውን ለምን ማሰራጨት አስፈለገ ስንል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።

🎲የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጉርሙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፁት በወቅቱ በነበረው ውይይት ላይ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጥሪ እንደሚደረግላቸው ስምምነት ላይ ተደርሷል በሚል የተሰራጨው ዘገባ ስህተት ነው ብለዋል፡፡

🎲በውይይቱ ወቅት በምክረ ሀሳብ ደረጃ የተነሳ እንጂ ውሳኔ ላይ ያልተደረሰበት ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው በሰዓቱ የተገኙ ሚዲያዎች የተሳታፊዎችን ሀሳብ በመውሰድ በስህተት የዘገቡት መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

🎲ትምህርት ማስጀመርን በተመለከተ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መመሪያ የተሰጠ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ደቻሳ ከዛሬ ጀምሮ ይህንን የሚገመግም ቡድን እናሰማራለን ብለዋል፡፡

🎲ቡድኑ አጠቃላይ የግምገማ ሪፖርቱን እንዳደረሰን እያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎቹን የሚጠራበትን ጊዜ ወደ ፊት እናሳውቃለን በማለት ነግረውናል፡፡

ምንጭ፦ #EthioFMn

join @MUSUofficalchannell
SAT Exam at Mekelle University , be ready for Oct 03,2020.
From Ethiopian Institute of Technology Mekelle -EITM
``````````````

ለድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት-መቐለ (EiT-M) ለ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከዚህ በታች በተገለጹት የድህረ ምረቃ መርሐ ግብሮች በቀንና በማታ አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የመማር ፍላጐት ያላችሁና የትምህርት ሚኒስቴርን የመግቢያ መስፈርት ማሟላት የምትችሉ አመልካቾች ከስር በተቀመጠ የግዜ ሰሌዳ መሰረት በኦንላይን መመዝገብ የምትችሉ መሆኖችሁን ያሳውቃል፡፡
Ph.D. Programs
1 PhD in Energy Technology
2 PhD in Manufacturing Engineering
3 PhD in Design Engineering
4 PhD in Quality and Productivity Management
5 PhD in Engineering and Technology (with Specialization)
Masters Regular
1 Computer Engineering
2 Communication Engineering
3 Industrial Control Engineering
4 Electrical Power Engineering
5 Structural Engineering
6 Geotechnical Engineering
7 Construction Technology and Management
8 Hydraulic Engineering
9 Irrigation and Drainage Engineering
10 Road and Transport Engineering
11 Environmental and Sustainable Infrastructure Engineering
12 Thermo-fluid Engineering
13 Energy Technology
14 Production and Industrial Systems Engineering
15 Product Development and Design
16 Quality Engineering and Management
17 Kaizen
18 Automotive Engineering
19 Manufacturing Engineering
20 Materials Engineering
21 Mechatronics Engineering
22 Architectural design and Technology
23 Urban Planning and Development
24 Chemical Engineering specialization Process Engineering
25 Chemical Engineering specialization Environmental Engineering
26 Computer Science
27 Software Engineering
የማመልከቻ ጊዜ፤ እስከ መስከረም 30: 2013
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ዕለት፤ ከመስከረም 30፣ 2013 በኃላ
ምዝገባ ቦታ፤ በኦንላይን (online) ሲሆን
ለዝርዝር መረጃ በዩኒቨርስትያችን ድረገፅ www.mu.edu.et ይከታተሉ

Join @MUSUofficalchannell
የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ ዝግጅት የሚያረጋግጡ 11 ተቆጣጣሪ ኮሚቴዎች ሥራቸውን ጀምረዋል!

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የቅበላ ዝግጅት የሚያረጋግጥ 11 ተቆጣጣሪ ኮሚቴዎች የዩኒቨርሲቲዎችን ዝግጅት ለማረጋገጥ ከትላንት ጀምሮ መሰማራቱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ተቋማቱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ከግምት ያስገባ ዝግጅት አድርገው በቀጣዩ ወር ተማሪዎችን የሚጠሩበትን ቀን ያሳውቃሉ ሲሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጉርሙ ለኢዜአ ገልጸዋል።

የተቋማቱ የኮሮና ቫይረስን እየተከላከሉ የሚያስተምሩበትን ሁኔታ መፍጠራቸውን ኮሚቴዎቹ ካረጋገጡ በኋላ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ቅበላ ፕሮግራማቸውን ይፋ ያደርጋሉ ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ትምህርት የሚመለሱበት ቀን እስካሁን እንዳልተወሰነ የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ ከተቋማቱ የተማሪዎች ቅበላ ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያና በሌሎች ምንጮች የሚሰራጨው መረጃ ስህተት እንደሆነ ገልጸዋል።

ኢዜኣ

Join @MUSUofficalchannell
#UPDATE

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የቅበላ ዝግጅት ለማረጋገጥ የተሰማራው 11 አባላት ያሉት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የዩኒቨርስቲዎችን ዝግጁነት ካረጋገጠ በኋላ ተማሪዎቻቸውን የሚጠሩ ይሆናል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጉርሙ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል።

- የተቋቋመው ኮሚቴ ከመሰረተ ልማት አኳያ ተማሪዎች የመኝታ፣ የውሃ፣ የመፀዳጃና መሰል የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የሚረዱ ዝግጅቶች ላይ ትኩረት ያደርጋል።

- ቫይረሱን መከላከያ መመሪያዎችን የሚያስተገብሩ የተቋማቱ አመራሮችና የሚመለከታቸው አካላት መሟላታቸውን ኮሚቴው ከግምት ውስጥ ያስገባል።

- ዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው አቅምና ዝግጁነት ልክ ተመራቂ ተማሪዎችን አስቀድመው ሌሎች ተማሪዎች የሚጠሩበት ሁኔታ ይመቻቻል ይህም ተማሪዎቹ በመማሪያ ክፍልም ይሁን በሌሎች መገልገያ ቦታዎች እንዳይጨናነቁ ያደርጋል

- በአንድ ማደሪያ ክፍል ውስጥ እስከ ሶስት ተማሪዎች እንደሚኖሩም ገልጸዋል።

- ተቋማቱ ካለፉት ዓመታት በመማር ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሁኔታን ለመፍጠር ያደረጉት ዝግጅትም ከግምት ውስጥ እንደሚገባም አስረድተዋል።

Via Tikva

Join @EHEISUOfficialChannell
Mekelle University Student Union
Photo
We are excited to have SAT Exam today for the first time in Tigray , Mekelle University. Thanks Prof Fetien - President, great did. Pic creadit; Prof Fetien.

Join @MUSUofficalchannell
Additional||SAT Exam:
1.Frist round SAT exam is already done at Arid campus today.
2. Second round will be on December 2020. In addition We will have testing and training center of SAT, TOFEL, IELTS & GMAT. This is great to us, we would like to thank Prof Fetien Abay - Our MK Uni President for making this possible to our students.

Join @MUSUofficalchannell
መቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ለመቀበል ኣስገላጊ የሚባል ዥግጅት ላይ ነው።ዝግጅቱን ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባረጋገጠለት መሰረት በታቀደው መጀመሪያ ተመራቂ ተማሪዎችን የሚጠራ ይሆናል።ሙሉ መረጃ በዩኒቨርስቲው ድረ ገጽ ፡ማህበራሚ ሚድያ እና በህብረቱ ማህበራዊ ሚዲያ እናሳውቃለን።

"በያላችበት መልካም ቆይታ"

Join @MUSUofficalchannell
Breaking news ! Mekelle University

Join @MUSUofficalchannell
2024/09/25 09:15:30
Back to Top
HTML Embed Code: