Telegram Web Link
ሰላም የእግዚአብሔር  ቤተሰቦች የእግዚአብሔር  ፀጋ እና  ሰላም  ከሁላችን  ጋራ  ይሁን  አሜን ።
  የፊታችን  ሐሙስ  በ26/03/2017 ዓ.ም  የዝክረ  መድኃኔዓለም  እንዲሁም  የጥምቀት  መዝሙር ጥናት  መጀመሪያ  የሚሆን  ጉባኤ  ስለሚኖር  ሁላችሁም  የሰ/ት/ቤታችን  አባላት  በሙሉ የጉባኤው  ተሳታፊ  እንድንሆን  ስንል  ጥሪያችንን  እናስተላልፋለን ።
 
   ናክብር ሰንበቶ ወኢንኅድግ ስርዓቶ  ንዝክር በዓሎ  ለመድኃኒነ  ኢየሱስ  ክርስቶስ ።

                           @መዝሙር  ክፍል።
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

            የሀዘን መግለጫ

     በሰንበት ትምህርት ቤታችን በመምርህነት ሲያገለግል የነበረው የክብረ ሐይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት አባል የሆነው ወንድማችን መምህር ሄኖክ ጎበና በድንገተኛ ህመም ስላረፈ  የሰንበት ትምህርት ቤታችን ፅ/ቤት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን ።

`` ኢየሱስም ትንሳኤ አና ሕይወት እኔ ነኝ ፤
የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳን ሕያው ይሆናል።``

የዮሐንስ ወንጌል 11: 25

ነፍሱን በአፀደ ገነት ያኑርልን

ለቤተሰቦቹ አና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ መፅናናትን ይስጥልን ።

            የሰ/ት/ቤቱ ፅ/ቤት
#ድምፅ_መስጠት_ተጀመሯል!

#አንቴክስ_ፉድ_ኤይድ_ፕላስ ባዘጋጀው BIWs prize ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን የሰላም ዘርፍ እጩ ተሸላሚ አድርጓቸዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በሰላም ዘርፍ ከአምስት እጩዎች ውስጥ ተክትተዋል የዘርፉ አሸናፊ ከሆኑ #10ሚሊየን ብር ይሸለማሉ!!!

ብፁዕነታቸውን BIWን በማስቀደም ኮድ08 (BIW08) በማስገባት በSMS - 9355 ላይ አሁኑኑ ይምረጡ!!!

ድምጽ መስጠቱ እስከ ሐሙስ ታህሳስ 17/2017 ዓም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይካሄዳል!

በSMS 9355 ላይ BIW08 በማለት ብፁዕነታቸውን አሁኑኑ ይምረጡ!!!

#10ሚልዮን #አንቴክስ #ፉድኤይድፕላስ #biwsprize #BTM #ብፁዕአቡነኤርምያስ #ይምረጡ

Vote Abune Ermias now for the BIWs prize!

#AbuneErmias
#10million #BIWS2024 #Prize #ANTEXETHIOPIA #ANTEXTEXTILE #FOODAIDPLUS #BESHATUTOLEMARIAMMULTIMEDIA
“የገና ስጦታ ለሰንበት ት/ቤታችን

እግዚአብሔር በሥጋ ተገልጦ ራሱን ለዓለም በሰጠበት በዓለ ልደት (ገና)
✝️   ሰብአ ሰገል ወርቅ ዕጣን ከርቤን አቀረቡለት (ማቴ 2፡11) 
✝️   መላእክት እና እረኞች ምስጋናን አቅርበዋል (ሉቃ 2፡14-20)
✝️   እንስሳት በበረት ትንፋሻቸውን ገብረዋል (ሉቃ 2፡7)

እርስዎስ ለመሠረተ ህይወት ሰንበት ቤትዎ ምን ለመስጠት አስበዋል?
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን!
ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅ ያዳነበት ዕለት ነው፡፡
የመልአኩ ምልጃ አይለየን ለዓመቱ በቸር ያድርሰን!
ታህሳስ 19

የእለቱም ወንጌል
ሉቃስ 1፡11-21


የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው። ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፥ ፍርሃትም ወደቀበት። መልአኩም እንዲህ አለው ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል። በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል። እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል። ዘካርያስም መልአኩን እኔ ሽማግሌ ነኝ ምስቴም በዕድሜዋ አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ? አለው። መልአኩም መልሶ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፤ እነሆም፥ በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ መናገርም አትችልም አለው.........

👉2 ተሰሎንቄ 1:6-ፍጻሜ
👉ይሁዳ 1:20-ፍጻሜ
👉ሐዋ.ሥራ 7:30-35


👉ቅዳሴ  ዘእግዝእትነ  (ጐሥዓ)  

ምስባክ
መዝሙር 137፥ 1-2

በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ

ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ

ወእገኒ ለስምከ
ቅዱስነታቸው ለመላው የዓለም ማኅበረሰብእ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት
በቤተልሔም የተወለደው ጌታ ዛሬም በእኛ ሕይወት ይወለድ።
ሰባሰገልም ካዩት እና ከሰሙ የተነሳ ያደነቁት መደነቅ በእኛም ልቡና ይፈጠር።
የምስጋና ሁሉ ባለቤት አምላካችን እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን።
አሜን እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
መልካም በዓል ይሁንላችሁ የመሠረተ ሕይወት ሰ/ት/ት ቤት ትምህርት ክፍል።
ስለዚህ ምስል አጠር ያለ ጽሁፍ ለሚጽፍ ሰው ሽልማት ይኖረናል።

እዚሁ ከስር መጻፍ ይቻላል።
ማሳወቂያ

፩.ለጥምቀት አገልግሎት የምትወጡ አባላት ለአጋፔ የተባለውን መዋጮ ይዛችሁ እየመጣችሁ ልብሰ ስብሃት እንድትወስዱ

፪.ዛሬ ቀረጻ ስለሚኖር “ወንድሞች” ነጠላ ለብሳችሁ ከተባለው ሰዓት አስቀድማችሁ እንድትመጡ።

እግዚአብሔር አገልግሎታችንን ይባርክ።
2025/02/05 18:56:58
Back to Top
HTML Embed Code: