ድንግል ሆይ ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ!
ጾሙን በሠላም አስጀምሮ በሠላም ላስፈፀመን አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው! ጾም፣ ጸሎታችንን እና ሱባዔያችንን ትቀበልልን!
የዓመት ሰው ይበለን
📸 @tzar_on

የደብራችን አገልጋይ ዲ/ን ልዑለቃል ያወጣው መዝሙር እነሆ:: የአገልግሎት ዘመኑን ይባርክልን!
https://youtu.be/GM1FfY-sqpQ?si=j2TWyTnYzDDEQau2

YouTube
🔴ኪዳንኪ ኮነ|አዲስ የእመቤታችን ዝማሬ ቪዲዮ |ዘማሪ ዲ/ን ልዑለቃል እሸቱ |new Orthodox Mezmur 20 August 2024
New Orthodox Mezmur By Zemari D.N Luelekal Eshetu Kidanki Kone#betefikir #orthodoxmezmur #duet #mezmur #share #subscribe #thanksforwatching
+ ከታቦር ተራራ አትቅር +
"አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ። "
ማር 9: 3
/ሽራፊ ሃሳቦች ከደብረ ታቦር ንባብ/
የወንጌላውያን ትሕትና ይደንቃል ፣ ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ስለ ደብረ ታቦር ሲጽፉ ዮሐንስ አልጻፈም። ዮሐንስ ተመርጦ የተገኘበትን ታሪክ "ተመርጬ" ብሎ አልጻፈም። የቀሩት ወንጌላውያን ደግሞ "እኛ የሌለንበትን ነገር አንጽፍም" አላሉም። አንድ ወንጌል እየሰበኩ የሚፎካከሩ ፣ የአንድ ቤት ጣሪያ እየሠሩ ቆርቆሮ የሚሻሙ የእኛ ዘመን አገልጋዮች አልነበሩምና እነርሱ ያልተመረጡበትን ታሪክ ለመናገር ተሯሯጡ። እኛን የማያካትት ክብር ፣ እኛን የማይጨምር ድግስ ጉዳይ ሲነሣ ለማይጥመን ፣ እኛ የሌለንበትን ፎቶ እንኳን ለማየት የማንፈልግ ፣ በእኛ በኩል ያለፈን ነገር ብቻ የምናራግብ ፣ የሌለንበትን ነገር ጥሩም ቢሆን እንኳን ለምናጣጥል "በእኔ በቀር ባዮች" ትምህርቱ ድንቅ ነው።
ሌላ ማሳያም አለ ማቴዎስ ወንጌላዊው ስለ ራሱ ታሪክ ሲጽፍ "ማቴዎስ የተባለ ቀራጭ በመቅረጫው ተቀምጦ" ብሎ በኃጢአት ከተዘፈቀበት ሥራ ላይ ወደ ክርስትና እንደተጠራ በግልጽ ሲጽፍ ሌሎቹ ወንጌላውያን ግን በሐዋርያት ዝርዝር ላይ ማቴዎስ ያሉትን ሰው ስለ ቀድሞ የቀራጭነት ሥራው ሲጽፉ ግን ሌዊ የሚል ተለዋጭ ስሙን ተጠቅመዋል። ትሑቱ ማቴዎስ ግን በሌሎች ወንጌላውያን የተሸሸገ የቀድሞ የኃጢአት አኗኗሩን ለእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ማሳያ እንዲሆን ስለፈለገ ጭራሽ በሐዋርያት የስም ዝርዝር ላይ "ቀራጩ ማቴዎስ" ብሎ ራሱን ጠርቷል።
የሚገርመው ከቀራጭነት ከተጠራ በኋላ በቤቱ ታላቅ ድግስ ደግሶ ጌታችንን ከኃጢአተኞች ጓደኞቹ ጋር የተቀበለ መሆኑን በሌሎች ወንጌላውያን ሲጽፉ ማቴዎስ ግን ቀራጭነቱን አጉልቶ እንዳልጻፈ ሁሉ የግብዣው ነገር ደጋሹ እርሱ መሆኑን አድበስብሶ በመጻፍ አልፎታል።
★ ★ ★
ቅዱስ ጴጥሮስ "ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው" አለ። "ለእኛ" መልካም ነው የሚለው ቃል ድንቅ ነው። በእግዚአብሔር ቤት መኖራችን መልካምነቱና ጥቅሙ ለእኛ ነው እንጂ ለእግዚአብሔር አይደለም። የማንጠቅም ባሪያዎቹ ስሙን በአሕዛብ ዘንድ ከማሰደብ በቀር ለእርሱ ምን እንጠቅመዋለን። ለዚህም ነው ቅዱስ ባስልዮስ "ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም" ያለው።
ስለዚህ ጴጥሮስ "ለእኛ መልካም ነው" አለ።
"ብትወድስ ሦስት ዳስ እንሥራ" አለ ፣ ጌታ ካልወደደ እንኳን ሦስት አንድ ዳስ መሥራት አይቻልም ፣ እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ" ስለዚህ "ብትወድስ" አለ።
የዋሁ ጴጥሮስ ለእኔ ልሥራ አላለም ፣ የሐዲስ ኪዳን ሐዋርያ ነኝ ብሎ የብሉይ ኪዳን ነቢያትን ከማክበር ወደ ኋላ አላለም። "አንተ ዓለት ነህ በዚህች ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራታለሁ" በተባለ ማግስት ለነቢያቱ ድንኳን ሊቀልስ የጠየቀ ከጴጥሮስ በቀር ማን አለ?
ከእግዚአብሔር አብ ግን "አትሙት" እስከማለት ለደረሰው ለነጴጥሮስ ንግግር "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" የሚል ትእዛዝ መጣ። ሃሳቡ ድንቅ ቢሆንም ቃሉን ሳይሰሙ ዳስ መሥራት መጀመር አይቻልም።
በዚያ ላይ ጌታ የመጣው በደብረ ታቦር ድንኳን አስጥሎ ሊኖር ሳይሆን በቀራንዮ በተሰቀለበት በመስቀሉ ካስማ በደሙ ድንኳን ተክሎ ሊያስጠልለን ነው። ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ "ጴጥሮስ ሆይ ለአንተ የፊቱን ብርሃን እያየህ በዚህ መኖር መልካም ነው ፣ እኛ ግን የምንድነው በተራራው ሲኖር ሳይሆን ወርዶ ፊቱን በጥፊ ሲመታ ነው" ብሎታል።
ጴጥሮስ የዋሁ "በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ" ላለው ለክርስቶስ ድንኳን ሊቀልስ ጠየቀ። በሰማይ "በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ድንኳን" ላለችው ሊቀ ካህናት ድንኳን ሊሠራ ለመነ። እዚህ አለ ሲሉት እዚያ ለሚገኘው ፣ በመንፈስ እየተነጠቀ አድራሻውን ለመወሰን ያስቸግር ለነበረው ኤልያስ እንዲቀመጥ ተስፋ አድርጎ ድንኳን ልሥራ አለ። እጅግ የተዋበችና በወርቅ በሐር ያጌጠችን የኦሪት ድንኳን ለሠራው ሙሴ ዓሣ አጥማጁ ጴጥሮስ ድንኳን ልሥራለት አለ። ሐዋርያት ነቢያቱን ሊያስተናግዱ የለመኑባት ደብረ ታቦር ፣ ሐዋርያት ነቢያቱን ለጌታ ቀኝ አዝማች ግራዝማች አድርገው በድንኳን አስቀምጠው እነርሱ እንደ ሎሌ ከደጅ ሊኖሩ የጠየቁ እነ ጴጥሮስ እንደምን ይደንቃሉ? ጴጥሮስ ሆይ አሁን በሰማይ ድንኳኖች ውስጥ እያገለገልህ ይሆንን? ደብረ ታቦርን አይተህ በደስታ "እንኑር" ያልከው ጴጥሮስ ሆይ የገነት ደስታ ስታይ ምን ተሰምቶህ ይሆን?
በእሳት ድንኳን ለመኖር ተስፋ የምናደርግ "በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል" የተባልን እኛስ ምንኛ የታደልን ነን?
★ ★ ★
በታቦር ተራራ ላይ የጌታችን ልብስ እንደ ፀሐይ አበራ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ከፀሐይም በላይ ነው ፣ ፀሐይ አይቶ የወደቀ የለም የጌታችንን ልብስ ሲያዩ ግን የወደቁት ያበራው ከዚያ በላይ ስለሆነ ነው" ይላል።
ከጌታችን በዚያ ተራራ ከሙሴና ኤልያስ ጋር ነበረ። ሙሴ እንደምናውቀው ጽላቱን ተቀብሎ ሲወርድ ሕዝቡ "እባክህን ተሸፈንልን" ብለውት ፊቱን በመጎናጸፊያው ሸፍኖ ነበር። የሙሴ አምላክ ክርስቶስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ሲወድቁ አይቶ በልብሱ እንዳይሸፈን ያበራው ፊቱ ብቻ ሳይሆን ልብሱም ነበር።
" አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ" ማር 9: 3
የሚለው ቃል ምንኛ የሚደንቅ ነው። በምድር ላይ ያለ አጣቢ ቢፈትግ ቢታገል የዚያን ያህል ሊያነጻው የማይችለው ነጭ እንዴት ያለ ነው? መቼም ሁላችን የምናውቀው ነጭ ነገር ሁሉ በምድር ላይ ባለ አጣቢ የታጠበ ስለሆነ እንዲህ ነው ማለት አንችልም። ብቻ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በምድር ያሉ አጣቢዎች ከሚያነጡት በላይ ልብስን ማንጣት ይችላል።
ይህ ቃል በኃጢአት እድፍ ልብሳችን ላደፈ ሁሉ መጽናኛችን ነው።
መቼም የምድር አጣቢዎች አቅማቸው ውስን ነው።
ቆሽሸን ያዩን ሰዎች ብንታጠብም አያምኑንም ፣ ቢያጥቡልንም በኅሊናቸው የሚያስቀሩብን ቆሻሻ አለ።
በሰው ዓይን አንዴ ቆሽሸህ አትገኝ እንጂ ከተገኘህ መቼም ነጭ አትሆንም። አንተ ግን የደብረ ታቦሩ ብርሃን መድኃኔ ዓለምን ብቻ "እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ" በለው "ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች። " ብሎ በገባው ቃል መሠረት ነጭ ያደርግሃል።
እርሱ ወዳለባት የቅድስት ቤተክርስቲያን ተራራ በንስሓ ከደረስክና በታቦር ያበራውን ብርሃኑን ካበራልህ ነጭ ትሆናለህ። ከዚያ "አጣቢ የማያነጻውን ያህል ትነጻለህ" ከአብ የባሕርይ ልጅ ከብርሃኑ ፀዳል ስትቀርብ አንተም በጥምቀት ያገኘኸው የጸጋ ልጅነትህ ያንጸባርቃል። ነጭ በሆንህ ጊዜ የሚያዩህ ሁሉ "በበጉ ደም ልብስህ መታጠቡን"ና ነጭ መሆኑን አይተው ይደነግጣሉ ፣ ሊሰሙህ ያልወደዱ ሁሉ ለባሕርይ ልጁ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" ብሎ እንዳዘዘለት ለአንተም ጆሮ እንዲሠጡህ ያደርግልሃል።
አንተ ብቻ ከደብረ ታቦር አትቅር ፣ ካልሞትህ እንደ ኤልያስ ፈጥነህ ና ፣ በበደል ከሞትክም እንደሙሴ ተነሥተህ ና። ብቻ ወደ ደብረ ታቦር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት ተስፋ አትቁረጥ ፣ እንደ ሙሴ ትሞታለህ እንጂ ምድረ ርስትን አታይም ብትባል ፣ እንደ ኤልያስ ትኖራለህ እንጂ ሞትን አታይም ብትባል ብቻ አንተ ከደብረ ታቦር አትቅር።
©ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
፳፻፲ ዓ/ም የተጻፈ
@redetkebede

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የሀዘን መግለጫ
የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባል የሆነችው የእህታችን ትዝታ ገዝሙ ወላጅ አባቷ አቶ ገዝሙ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ስላረፉ የሰንበት ትምህርት ቤታችን ፅ/ቤት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ ነገ ማክሰኞ 21/12/2016 ዓ.ም ከቀኑ6:00 ሰዓት በአስኮ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቀብር ስነስርዓቱ ላይ እንድትገኙ። እንዲሁም እሮብ በ22/12/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ላይ የማጽናኛ መርሐ ግብር ስለሚኖረን እንድትገኙ እናሳስባለን ።
ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን
ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ መፅናናትን ይስጥልን ።
የሰ/ት/ቤቱ ፅ/ቤት

በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ ወደ ትግበራ ስለገባው ወጥ የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርትና መዋቅር የመመሪያ አቅጣጫ እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ተካሔደ ።
(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ነሐሴ 20 /12/2016 ዓ.ም
በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ ወደ ትግበራ ስለገባው ወጥ የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርትና መዋቅር የመመሪያ አቅጣጫ እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር የዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፤ ሀገር አቀፍየሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው፤ የዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ ላዕከ ኄራን መንክር ግርማ ና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ዛሬ ነሐሴ 20 በዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሒዷል።
የግንዛቤ ማስጨበጫው የተሠጠው በአ.አ ውስጥ ለሚገኙ አቢያተ ክርስቲያናትና ገዳማት አስተዳዳሪ ፣ ጸሐፊ ፣ የሰበካ ጉባኤ ም/ሊቀ መናብርት ፣ የስብከተ ወንጌል ሓላፊዎችና ለሰንበት ት/ቤት ሰብሳቢዎች ነው። በመርሐ ግብሩም የዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ ላዕከ ኄራን መንክር ግርማ ከመንበረ ፖትርያሪክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ቤቶች አንድነት እስከ አጥቢያ ሰንበት ት/ቤት ድረስ ያለውን መዋቅር ፤ የሰንበት ት/ቤቶች ጠቅላላ ጉባኤ በበዓለ ጰራቅሊጦስ እንደሚካሔድ በዚያ የሚተላለፉ መመሪያዎች ተግባራዊ እንደሚሆኑ፤ የሰንበት ት/ቤቶች የውስጥ ደንብ በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጸድቆ ወደታች እንደሚወርድ እንዲሁም የሰንበት ት/ቤቶች የምርጫ ጊዜ በተመሣሣይ ወቅት እንደሚሆን ለተሣታፊዎች ገለፃ አድርገዋል። በመቀጠልም የሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው ስለ ሥርዓተ ት/ት ገለፃ ሲያደርጉ ሥርዓተ ትምህርቱ የዕድሜ ደረጃቸውን ያማከለ እንደሆነና ከ1ኛ-12ኛ ክፍል በ6 ክፍላተ ትምህርትና 1 አጋዥ ክፍለ ትምህርት የተከፋፈለና እንደሆነ አስረድተዋል። ከ1ኛ-4ኛ ክፍል ያሉት 23 መጽሐፍት በ4 ጥራዝ በ13ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ማስመረቁ ይታወሳል። በቀጣይም የቀሩትን መጻሕፍት ለማሳተም ዕቅድ መያዙን እንዲሁም ከሊቃውንት ጉባኤ ጋር የአርትዖ ሥራ እየተደረገባቸው እንደሆነ አስረድተዋል። አያይዘውም የመማሪያ ቦታ ፣ መምህራን ና መጽሐፍቱ ለሥርዓተ ትምህርቱ ትግበራ ጉልህ ድርሻ እንዳላቸውና ይሄንን ማሟላት የሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዎል።
በመጨረሻም የዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ" ሰንበት ት/ቤት የቤተ ክርስቲያን ናትና የሰንበት ት/ቤት ዓባላትም ቤተክርስቲያኒቱን በሓላፊነት መምራትና መቆጣጠር ይገባቸዋል ፤ የሰበካ ጉባኤ ዓባላትም ከሰ/ት/ቤቶች ጋር በመመካከር መሥራት ይኖርባቸዋል።" ብለዋል አያይዘውም " የአጥቢያው ሰበካ ጉባኤ ከ1-4 ኛ ክፍል ያሉትን መጽሐፍት ከየአንዳንዱ ስድስት ስድስት መጽሐፍት ለሰንበት ት/ቤቶቹ እንዲገዙ" መመሪያ አስተላልፈዋል። ከተሣታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም መልስ ተሰጥቶባቸው ጉባኤው ተጠናቋል።
(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

እንዴት ሞተች እንጂ እንዴት ተነሣች ብለኽ አትገረም፡፡
ከሰው ኹሉ መርጦ እናቱ ያደረጋት ጌታ፥ ከሰው ኹሉ መርጦ ከሞት አሥነሳት፤ አሳረጋት፡፡
ከሰው ኹሉ ተመርጣ ሰማይና ምድር የማይችሉትን ጌታ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ጸንሳ ወልዳው የለምን? ከተገረምክ በዚኽ ተገረም፡፡
እናት ኾና ድንግል፥ ድንግል ኾና እናት መኾን የምትችል ሴት በምድር ላይ አልነበረችም፤ ወደፊትም አትኖርም፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ግን በዐለም ያሉ ሴቶች ኹሉ የማይኾኑትን ኾነች፡፡ ድንግልም እናትም፡፡ ከትንሣኤዋ ይልቅ ይኽ አይደንቅምን?
የክብር ትንሣኤና ዕርገትማ በሃይማኖትና በምግባር ለጸኑ ሰዎች ኹሉ ጊዜው ሲደርስ ይፈጸምላቸዋል፡፡ይነሣሉ ያርጋሉ፡፡ ከአንስተ ዐለም ተለይታ አምላኳን ልጄ ብላ መጥራት የቻለች የሕይወት እናት፥ መሞቷ እንጂ መነሣቷ ምን ይገርማል??
ሙሴ በሲና ያያት ዕፅ፥ ቀርበው ካላይዋት በስተቀር እሳት ያቃጠላት ትመስላለች፡፡
እንደሙሴ ቀርቦ ለተመለከታት ግን እሳት ቢነድባትም ዕፀ ጳጦሷ አትቃጠልም፡፡
ይኽ እሳት የመለኮት ምሳሌ ኾኖ በሊቃውንቱ ተተርጉሞ ነበር፡፡ ዛሬ ግን እሳቱ የሞት ምሳሌ ኾኖ ይገለጣል፡፡ እሳት ያላቃጠላት ቅጠል ደግሞ እመቤታችን ናት፡፡
ዳሩ ይኽን ለመረዳት ወደደብረ ሲና መውጣት ብቻም አይጠቅምም፡፡
እንደ ሙሴ ጫማንም ማውለቅ ይበጃል፡፡
ሊቃውንቱ፥ ሙሴ የለበሰው ጫማ ከሞቱ እንስሳት ቆዳ የተሠራ በመኾኑ ያን ተጫምቶ እንዳይቀርብ ተከለከለ ብለው ተርጉመዋል፡፡
የሞቱ እንስሳት ቆዳ ውጤት የኾነው ጫማ፥ ሙታነ ሕሊናን ይወክላል፡፡
ጌታችን ክርስቶስ በእናቱም ለእናቱም ያደረገውን ድንቅ ነገር የማያምን ልብ፥
የሙሴ ጫማ ነው፡፡ መውለቅ አለበት፡፡ እግርን ሳይኾን ዐይንን የሚጋርድ ግርዶሽ ነውና፡፡
ዕፀ ጳጦስ የተባልሽ ድንግል ኾይ፥ጫማችንን የፈታን ሙሴዎች ኾነን ክብሩን እናይ ዘንድ ለምኝልን፡፡
ምንጭ :-መምህር ስሙር

የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት የሆኑት የወንድሞቻችን ታምራት ደምስስ፣ እንዳሻው ደምስስ፣ ተመስገን ደምስስና የአብስራ ደምስስ አያት ስላረፉ የሰንበት ትምህርት ቤታችን ፅ/ቤት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን ።
ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን
ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ መፅናናትን ይስጥልን ።
የሰ/ት/ቤቱ ፅ/ቤት
የሀዘን መግለጫ
የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት የሆኑት የወንድሞቻችን ታምራት ደምስስ፣ እንዳሻው ደምስስ፣ ተመስገን ደምስስና የአብስራ ደምስስ አያት ስላረፉ የሰንበት ትምህርት ቤታችን ፅ/ቤት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን ።
ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን
ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ መፅናናትን ይስጥልን ።
የሰ/ት/ቤቱ ፅ/ቤት
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤ በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ፡፡
ሁለመናችንን በሐዲስ ምግብና እየመገበ የሚጠብቀን አምላካችን እግዚአብሔር እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ 2016 ዓ.ም. ወደ ዘመነ ማቴዎስ 2017 ዓ.ም. በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!
‹‹ሐድሱ መንፈሰ ልብክሙ፤ የልባችሁን መንፈሳዊ አእምሮ አድሱ›› (ኤፌ. ፬÷፳፫)፤ በገሃዱ ዓለም በግልጽ እንደምናስተውለው ከሞላ ጎደል የማያረጅ የለም የማይታደስም የለም፤ መታደስ ባይኖር ኖሮ ሕይወታውያን ፍጡራን በሕይወት መቀጠል አይችሉም ነበር፤ የዘመን መታደስም የሥነ ፍጥረት አንዱ አካል ነው፤ እኛ ሰዎችም የሕዳሴው መሪዎች ሆነን የተሾምንባትን ምድር በየጊዜው በልማት እንድናድሳት እግዚብሔር አዞናል፤ የሃይማኖት ትልቁ ተስፋም መታደስ ላይ የተመሠረተ ነው፤ ዘመንም እንደ ሌላው ያረጃል፤ ይታደሳልም፤ “ወናሁ እገብር ኵሎ ሐዲሰ እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” የሚለው የእግዚአብሔር ቃልም የዚህ አስረጅ ነው፤ በዚህ ሕገ እግዚአብሔር መሠረት እነሆ አሮጌውን ዘመን የምንሸኝበት አዲሱን ዘመን ደግሞ የምንቀበልበት ምዕራፍ ላይ ነን፤የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡-
ፍጥረታትን በማደስ ሕይወትን የማስቀጠል ሥልጣን በዋናነት የእግዚአብሔር ብቻ መሆኑ ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፤ ይሁን እንጂ ሰውም ሥነ ፍጥረትን በማደስና በማጐስቈል ረገድ ያለው ሚና ቀላል አይደለም፤ ይህም ሰው በምድር ላይ እንዲሠለጥን ወይም ፍጥረትን እንዲገዛና እንዲመራ በፈጣሪ ከተሰጠው ሥልጣን የሚመነጭ ነው፤ ዛሬም ዓለማችን በመታደስ ያይደለ በማርጀት ላይ የምትገኘው ከሰዎች ድርጊት የተነሣ እንደሆነ እንገነዘባለን፤ የአየሩ መለወጥ፣ የበረዶው መቅለጥ፣ የሙቀቱ ማሻቀብ፣ የዝናሙ ማጥለቅለቅ፣ የባሕሩ መናወጥ ወዘተ. እየተፈጠረ ያለው ኃላፊነት ከጐደለው የሰው አጠቃቀም የተነሣ እንደሆነም ተደጋግሞ እየተነገረን ነው፤ እኛም በዓይናችን እያየን ነው፤
ከዚህ በተለየ ደግሞ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሰው ምድረ በዳውን ወደ ሐመልማለ ገነት ሲቀይር የሚስተዋልበት ሌላ ገጽታ አለ፤ ይህ የሚያሳየው ሰው በሥነ ፍጥረት ላይ የማደስና የማጐስቈል ብሎም የማጥፋት ሚና ያለው መሆኑን ነው፤ ሰውም እንደሌላው ሥነ ፍጥረት የሚያረጅም የሚታደስም ነው፤ ይህም በብዙ አቅጣጫ ሊከሠት ይችላል፤ ሰዎች በተናጠልም ሆነ በጋራ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሁለቱንም ማለትም ማርጀትና መታደስን ሊያስተናግዱ ይችላሉ፤ ሰዎች በመንፈሳዊ፣ በኢኮኖሚያዊ በማኅበራዊና በመልካም አስተዳደር ወዘተ. የላቀ ዕድገትን ሲያስመዘግቡ በመታደስ ላይ እንደሆኑ ይታወቃል፤ የዚህ ተቃራኒ የሆነውን ይዘው እየተጓዙ ከሆነ ደግሞ ተቃራኒውን ወይም ማርጀትን እያስተናገዱ እንደሆነ ይታወቃል፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰዎች በመንፈሳቸውም ሆነ በአእምሮአቸው፣ በነፍሳቸውም ሆነ በአካላቸው በመታደስ እንዲኖሩ እንጂ እርጅና እንዲጫጫናቸው አይፈልግምና “የልባችሁን መንፈስ አድሱ” በማለት ያስተምረናል፤
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት!
የክርስትና ሃይማኖት የመጨረሻው ግብ የፍጥረት መታደስ ነው፤
ይህም ማለት የሃይማኖቱ አስተምህሮ መዳረሻ ከሞት በኋላ ትንሣኤ ከዚያም ፍጻሜና እንከን የሌለው ጣዕመ ሕይወት አለ ብሎ ሰውን ለዘላለማዊ ሕዳሴ ማብቃት ነው ማለት ነው፤
ከዚህ አንጻር የሰው የመጨረሻ ዕድሉ ማርጀት ሳይሆን መታደስ እንደሆነ እንገነዘባለን፤ እግዚአብሔር የሰውንና የፍጥረታትን መታደስ የሚሻው በሰማያዊው ዓለም ብቻ ሳይሆን በምድራዊው ዓለምም ጭምር ነው፤ ለዚህም ነው በየወቅቱ የሥነ ፍጥረትን ውበት እያደሰ የሚመግበን፤ አሁን ትልቁ ጥያቄ የሚሆነው እኛስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመታደስ ተዘጋጅተናል ወይ? የሚለው ነው፤ ዛሬ እያንዳንዳችን ይህንን ጥያቄ አንሥተን ኅሊናችንን በጥልቀት መጠየቅ አለብን፤ በዚህም ሳናበቃ መልሱን በትክክል ማግኘት አለብን፤ በሁለንተናችን ለመታደስም ቈራጥ ውሳኔ በራሳችን ላይ ማሳለፍ አለብን፤ አዲሱ ዘመን አዲስና ብሩህ የሆነ የደስታ ሕይወት ሊያጐናጽፈን የሚችለው በዚህ መንፈስ ተቀብለን ስንጠቀምበት ነው፤

እኛ ኢትዮጵያውያን ለብዙ ዘመናት የታደሱ ያይደሉ በርካታ ዓመታት ተጭነውን አልፈዋል፤ ቀድሞ እንበልጣቸው ከነበሩ አህጉር በታች ሆነንም በርካታ ዓመታትን አስቈጥረናል፤ የእርስ በርስ ግጭት፣ ረኃብ፣ ጦርነት፣ ድህነት፣ ኋላ ቀርነት የመልካም አስተዳደር እጦት በዓለም ፊት ልዩ መለያችን ሆኖአል፤ ዛሬም ከዚህ አልተላቀቅንም ብቻ ሳይሆን እንዲያውም አጠናክረን ለማስቀጠል ውል የገባን እስክንመስል ድረስ እየቀጠልንበት እንገኛለን፤ በእውነቱ እንዲህ የመሰለ ልምድ ልናፍርበትና ንስሐ ልንገባበት እንጂ ልናስቀጥለው አይገባም፤
በተፈጥሮ የታደለች ሁሉንም አሟልታ የምትገኝ ኢትዮጵያን የመሰለች ሀገር ይዘን ከሰው በታች ሆነን ስንገኝ በስንፍናችሁ ከምንባል በቀር የሀብተ ጸጋ እጥረት አለባችሁ የሚለን አናገኝም፤
ስለዚህ አሁንም ለኢትዮጵያውያን ልጆቻችን በአጽንዖት የምናስተላልፈው መልእክት ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውን አይደለም ለዓለም የሚተርፍ ሀብተ ጸጋ አላትና ለኔ ለኔ በመባባል የሕዝባችንን ሰቆቃው አናስረዝም፤
ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ናት የሚለውን ጥሬ ሓቅ በደምብ አላምጠን መዋጥ አለብን፣ ከዚያም በእኩልነትና በአንድነት ሀገራችንን እናድስ፤ ከሌሎች በደባል የሚመጡ ነገሮችን ሳይሆን የሀገሪቱ በሆኑ ዕሤቶች እንመራ፤ ለበርካታ ዓመታት የተሸከምነው ደባል የአስተዳደር ስልት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የሚጣጣም ሆኖ አልተገኘም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከምንም ከማንም በላይ በፈጣሪው እንደሚመካ እሱንም አጥብቆ እንደሚያምን ልኂቃኖቻችን ተገንዘቡልን፤
እኛ ኢትዮጵያውያን ከሦስት ሺሕ ዓመታት በላይ ባስቆጠረ ታሪካችን ከእግዚአብሔር ተለይተን አናውቅም፤ በዚህም ተጠቃሚዎች እንጂ ተጐጂዎች የሆንበት ጊዜ የለም፤ በለመደው እምነት ባህልና ዕሤት ሕዝቡን ብንመራው ሁሉም ነገር ቀላል ይሆንልናል፤ ከዚህ ውጭ እንምራህ ብንለው ግን ያጋጠመንን ችግር ማስቀጠል ነው የሚሆነው፤ ስለዚህ የሁሉም መነሻ ማለትም የክፋትም ሆነ የደግነት መነሻ ውሳጣዊ አእምሮአችን ነውና እሱን በማደስ በአዲሱ ዓመት አገራችንን እንድናድስ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በመጨረሻም
አዲሱ ዘመን በሃይማኖት መንፈስ ግጭትን በውይይት፤ መለያየትን በአንድነት፤ አለመግባባትን በዕርቅ ፈትተን በመታደስ ማማ ላይ የቆመ ማኅበረ ሰብን ለመገንባት ሁላችንም ጥረት እንድናደርግ በእግዚአብሔር ስም መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
አዲሱ ዓመት የሰላም የዕርቅ የእኩልነትና የአንድነት ያድርግልን፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
አሜን::
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
መስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ለሰ/ት/ቤታችን አባላት በሙሉ እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገረን/አሸጋገራችሁ።
እግዚአብሔር አምላካችን ዘመኑን የሰላም የፍቅር የንስሐ የጽድቅ የአገልግሎት ዘመን ያድርግልን:: መልካም አዲስ አመት።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
የሰ/ት/ቤቱ ጽ/ቤት

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ሁለት በዚህች ቀን የካህኑ የዘካርያስ ልጅ የከበረ አጥማቂው ዮሐንስ ሕግን አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ ሰማዕት ሆነ::ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ በአጥማቂው ዮሐንስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን::
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ውድ የሠንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በሙሉ እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገረን/አሸጋገራችሁ።እንዲሁም ለታላቁ አባታችን ለቅዱስ ዮሐንስ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ። በዓሉን የሠላም እና የፍቅር ያድርግልን!

መልክዐ_ዮሐንስ_መጥምቀ_መለኮት_በግዕዝና_በአማርኛ_ገብረ_ሥላሴ.pdf
540.1 KB
እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ለቅዱስ ዮሐንስ በዓል በሠላም አደረሰን አደረሳችሁ!
ሁላችንም ከቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት እና በረከት እንሳተፍ ዘንድ ነገ ለአገልግሎት ከመምጣታችን በፊት የዮሐንስን መልክዐ እንዲሁም ዘወትር ምናደርሰውን ጸሎት ጸልየን በጠዋት እንገናኝ!
እግዚአብሔር የሚቀበለው አገልግሎት ያድርግልን!