Telegram Web Link
ስለ ጋብቻ ጥቂቱ

በመጅመሪያ ለዚህ ታላቅ ቀን ለደረሳቸው ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ም/ሰብሳቢ ወንድማችን ብሩክ ወ/አለማሁ እና ለመታሰቢያ ገዙ እንኳን ደስ አላችሁ ።
የክርስቲያናዊ ጋብቻ መገለጫዎች
አንድነት ፦ቤተክርስትያን የምታስተምረው የጋብቻ ትምህርት አንድ ለአንድ {Monogamy} የሚባለውን ነው በመጀመሪያ እግዚአብሔር ያዘጋጅው አንድ አዳምን ለአዲት ሄዋን ነው።
በስርዓተ ተክሊል እና በቅዱስ ቁርባን ሁለቱ የነበሩት ተጋቢዎች በክርስቶስ አንድ ይሆናሉ
ስለዚህም ወደ ፊትም አንድ እንጂ ሁለት አይባሉም ።
ስው አባቱ እና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ {ኤፌ?
5፥21}
ዘላቂነት ፦ ጋብቻ ሁለቱ ጥንዶች ያለ መለያየት እስከ እድሚያቸው ፍፆሜ በአንድነት የሚቆዬበት ሕይወት ነው።
ፍሬ ማፍራት ፦በመንፈስ ቅዱስ ረዳትነት በቅዱስ ጋብቻ ሕይወታቸውን የሚመሩ ጥንዶች በርካታ ፍሬዎችን ያፈራሉ።ፍሬዎቻቸውም ፦ፍቅር በጎነት የቤተክርስትያን አገልግሎት እንዲሁም ልጆች ናቸው።
ማጠቃለያ ፦የጋብቻ ሕይወት ጥንዶች በንፅህናና በቅድስና ሆነው በጋራ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን በመምራት ክርስትያናዊ ተጋድሎ እየፈፀሙ ራሳቸውን ለመንግስተ እግዚአብሔር የሚዘጋጅበት ሕይወት ነው።

     
የሰ/ት/ቤት/ፅ/ቤት
     📸@redetkebede
2025/02/06 08:46:57
Back to Top
HTML Embed Code: