Telegram Web Link
መስከረም 02/2017 ዓ.ም በዚህች ቀን የተመረጠ የቅዱስ ዮሐንስን የንግስ በዓል በዚህ መልኩ በእግዚአብሔር ፈቃድ አክብረናል።
የዓመት ሰው ይበለን

📸 @weguu1996 @wina_k
የሰንበት ትምህርት ቤቶች ከመዘመር ባሻገር መሠረተ ሃይማኖት ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል  ሲሉ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ገለጹ።


መስከረም 2 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
የወልድያ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ትናንት መስከረም 1 ቀን የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት ለሀገረ ስብከቱ ብፁዓን አባቶች የእንኳን አደረሳችሁ መርሐ ግብር አካሂዷል።

በዕለቱ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በመርሐ ግብሩ ለተገኙ የሰንበት ት/ቤት አባላት አባታዊ መልእክትና የአገልግሎት መመሪያ አስተላልፈዋል።

አቡነ ቄርሎስ የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ለማጠናከር የደከሙት ድካም ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሱት ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የብፁዕነታቸውን ህልም ለማሳካት ሀገረ ስብከቱ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም አብራርተዋል።

መሪ ዕቅዱ ለይስሙላ ሳይኾን በትክክል ተግባራዊ እንዲሆን ሰንበት ትምህርት ቤቶችን የሚያጠናክር የሐዲሳት መጻሕፍት ትርጓሜ መምህር የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኀላፊ አድርጎ ከመመደብ ባሻገር 5 አሠልጣኝ መምህራን በጠቅላይ ቤተ ክህነት መሠልጠናቸውንና ሥርዐተ ትምህርቱን ለመተግበር ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ  ተናግረዋል።

በተጨማሪም የሀገረ ስብከቱና የወረዳዎች የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ለሚስተዋሉ ክፍቶች የመፍትሒ አካል እንድሆኑና አባላቱም እንድያግዟቸው አሳስበዋል።

ክርስትናችንን ማስፋት የምንችለው መሠረተ እምነቱን ማወቅ ስንችል ነው ያሉት ብፁዕነታቸው የጸሎተ ሃይማኖትን 12 ቱን አንቀጾች መያዝና ማብራራት መቻል፣ በትምህርተ ሃይማኖት፥ በነገረ ቅዱሳን፣ በምሥጢረ ሥላሴና በምሥጢረ ሥጋዌ ትውልድን ለመቅረጽ መዘጋጀት እንዳለባቸው አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል ሲል የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ገልጿል።
መሠረተ ህይወት ሰ/ት/ቤት ❤️ pinned «የዛሬውን የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንግስ በዓል በምስል📸 ላጋራችሁን ወንድምና እህቶች እግዚአብሔር ይስጥልን እናመሰግናለን።🙏.»
Forwarded from አፄ አሌክስ
ሰላም እንዴት አመሻችሁ የ6ቱ አጥቢያ የተማሪዎች ምርቃት መርሃግብር ሊከናወን ሰዓታት ቀርተውታል። በመሆኑም የመጓጓዣ ትራንስፖርት ስለተዘጋጀ ጠዋት 2፡00 ሰዓት መድኃኔዓለም መግቢያ (የላይኛው በር) እንድትመጡ።
ሠንበት ትምህርት ቤታችን "መሠረተ ህይወት ዘደብረ መንክራት" ብሎ የከፈተው Tiktok አካውንት እነሆ:: ሁላችንም ፎሎው እና ሼር በማድረግ ደብራችንን ምናስተዋውቅ ይሁን::


https://vm.tiktok.com/ZMh2Xwa7x
🌻ዝንቱ መስቀል ኅብስተ ሕይወት አፍረየ አውኀዘለነ ደመ ወማየ አውኀዘለነ
ከመጌራ ወርቅ ጽሩይ ሥርግው በባህሪ መስቀል ነቢሮ
ያስተርዕይ ላእለ ርዕስ🌻

ትርጉም
🌻ይኸ መስቀል የሕይወትን ኅብስት አፍርቷል
ደምና ውሃንም አመንጭቷል
እንደጠራ ንጹህ ወርቅ በባህርይ አጊጦ በአላማ ላይ ይታያል።🌻

🌻🌻እንኳን አደረሰን🌻🌻
2025/02/06 15:21:24
Back to Top
HTML Embed Code: