አልጄሪያ  የፀጥታው ምክር ቤት  በፍልስጤም ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ  ጠየቀች
ነጃሺ ቲቪ መጋቢት 25/2017

በትላንትናው ዕለት አልጄሪያ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም ጉዳይ ላይ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲደረግ ጠይቃለች።

እንደ አልጄሪያ የዜና አገልግሎት ዘገባ  አልጄሪያ በትላንትናው እለት የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ የጠየቀች ሲሆን  ስብሰባውም  ዛሬ  ከሰአት በኋላ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

የአልጀሪያ  ጥያቄ የመጣው  በተያዙት የፍልስጤም ግዛቶች በተለይም በጋዛ ውስጥ እስራኤል ጥቃቷን በመቀጠሏ እና የሰበአዊ ርዳታዎችን ጨምሮ የኤሌክትሪክ ፣ የውሀ እና ሌሎች አገልግሎቶችን ማገዷን ተከትሎ ነው።


በተጨማሪም  ከፍልስጤም ቀይ ጨረቃ፣ ከፍልስጤም ሲቪል መከላከያ እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር ግንኙነት ያላቸው የ15 የአደጋ ጊዜ እና የእርዳታ ሰራተኞች አስከሬን በጋዛ መገኘቱን ተከትሎ ጥያቄው እንዲነሳ አድርጎታል።

የአልጄሪያ ጥያቄም የመጣው “በዌስት ባንክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የሰፋሪዎች ብጥብጥ  በታየበት ወቅት ነው።

እስራኤል መጋቢት 18 ቀን በጋዛ ላይ ድንገተኛ የአየር ላይ ዘመቻ ከጀመረች በኋላ ከ1,000 በላይ ሰዎችን የተገደሉ ሲሆን  ከ2,500 በላይ የሚሆኑት ቆስለዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ በዚህ ሳምንት የሁጃጆችን ቪዛ ህትመት እንደሚጀምር አስታወቀ።

ነጃሺ ቲቪ መጋቢት 25/2017

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ባደራጃቸው 30 የምዝገባ ጣቢያዎች የሀጅ ምዝገባ ከጥር 15/2017 ጀምሮ ሲያከናውን መቆየቱ ይታወቃል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ሂደቱን አስመልክቶ ለሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች በፃፈው ደብዳቤ ምዝገባው የሳዉዲ ሀጅ ሚኒስቴር ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት መጠናቀቁንና ከመጋቢት 24 2017 ጀምሮ የኮታ ማሟያና የማጣሪያ ምዝገባ እንደሚከናወን አመላክቷል።

ዘርፉ የሀጅ ምዝገባ ቀጣይ አቅጣጫን ባመላከተበት በዚህ ደብዳቤው የሁጃጆች ቪዛ ህትመት በዚህ ሳምንት እንደሚጀምርም ጠቅሷል።

የሀጅ ምዝገባ አከናውነው ክፍያ ያልፈፀሙ ሁጃጆች ክፍያቸውን እንዲፈጽሙና የፓስፖርት ጥያቄ አቅርበው ስማቸው ወደ ኢሜግሬሽ የተላከላቸው ሁጃጆች አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተው ፓስፖርታቸውን በእጃቸው እንዲያስገቡ እንዲደረግም ዘርፉ ለምዝገባ ጣቢያዎች በፃፈው ደብዳቤ የስራ አቅጣጫ አስቀምጧል።
መረጃው
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ነው
ሳውዲ ኢትዮጲያን ጨምሮ በ13 ሀገራት ላይ  ጥላለች የተባለውን የቪዛ  እገዳ ውድቅ አደረገች ።

ነጃሺ ቲቪ መጋቢት 26/2017

ሳውዲ አረቢያ በናይጄሪያ እና በሌሎች 13 ሀገራት ላይ የቪዛ ገደብ ወይም የመግቢያ እገዳ ማውጣቷን በሚመለከት የወጡትን  ሪፖርቶች ውድቅ አድርጋለች።

የሳዑዲ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ፣ናይጄሪያ፣ ግብፅ፣ ህንድ፣ ፓኪስታን፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ የመን፣ አልጄሪያ፣ ዮርዳኖስ፣ ሱዳን፣ ኢራቅ፣ ኢንዶኔዢያ  እና ባንግላዲሽ ላይ  የቪዛ እገዳ/የጉዞ እገዳ ተጥሎባቸዋል በሚል የወጣውን ሪፓርት     ውድቅ አድርገዋል።

በሪፓርቱ  የተዘረዘሩት አገሮች ለንግድ ቪዛ፣ ለጉብኝት ፣ ለቱሪዝም እና የቤተሰብ ጉብኝቶችን ጨምሮ ለአዲስ የአጭር ጊዜ የሳዑዲ ቪዛ እንዳይያመለክቱ ተገድቧል።

እገዳዎቹ በፈረንጆቹ ከሚያዚያ  13 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተነግሮ ነበር።

ሰነዱ አክሎም ከተዘረዘሩት ሀገራት የመጡ ዜጎች ህጋዊ ቪዛ ቢይዙም ከተፀናበት ቀን ጀምሮ ወደ ሳዑዲ አረቢያ መግባት እንደማይፈቀድላቸው አስታውቋል ።

መግለጫው አክሎም ይህን ህግ ያላከበሩ ለ  5 አመት ወደ ሳዑዲ እንዳይገቡ  እገዳ እንደሚጣልባቸው ገልጾ ነበር።

ሆኖም የሳውዲ የቱሪዝም ማእከል ሪፓርቱን  ትክክል አይደለም ሲል ውድቅ አድርጓል።

ኤጀንሲው እንደገለጸው ማንኛውም  የቱሪስት ቪዛ ያለው ሰው ሃጅ ማድረግ እንደማይፈቀድለት የሳኡዲ ባለስልጣናት ባወጣው  የሐጅ ጉዞ መመሪያ  ላይ ሰፍሯል።

በትላንትናው ዕለት የሳውዲ  ፕረስ ድርጂት  እንዳስታወቀው  “የቱሪስት ቪዛ ያለው ማንኛውም ሰው ከዙል ቃዒዳ 1  እስከ ዙል ሂጃ 14   1446ኛው አመተ  ሂጅራ ባለው ጊዜ ውስጥ ሐጅ ማድረግ፣ መግባት ወይም መካ ውስጥ መቆየት እንደማይፈቀድለት  ዘግቧል።

ናይጃ ኒውስ እንደዘገበው የሳውዲ የሀጅ ቪዛ ለሀጅ ጉዞ ብቻ የሚሰጥ ሲሆን  የቱሪስት ቪዛን ጨምሮ ሌሎች ቪዛዎች ለሀጅ እንዳማያገለግሉ ገልጿል።
ግብፅ እና ዮርዳኖስ እስራኤል በሶሪያ ሉዓላዊነት ላይ እየደረሰች ያለውን ጥቃት አወገዙ

ነጃሺ ቲቪ መጋቢት 26/2017

ግብፅ እና ዮርዳኖስ እስራኤል በሶሪያ ላይ ያደረገችው  የአየር ጥቃት ዓለም አቀፍ ህግን የጣሰ እና በሶሪያ ሉዓላዊነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲሉ   አውግዘዋል።

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የእስራኤል ጥቃት የሶሪያን ውስጣዊ ሁኔታ በማየት የተደረገ “የዓለም አቀፍ ህግን በገሃድ የጣሰ እና የሶሪያን ሉዓላዊነት፣ ነፃነት እና የግዛት ውህደቷን የሚጥስ ነው ብሏል።

ግብፅ ተደማጭነት ያላቸው ዓለም አቀፍ አካላቶች “እስራኤል የምትፈጽመውን ተደጋጋሚ በደል በተመለከተ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ፣ እስራኤል በሶርያ ግዛቶች ላይ የምታደርገውን ይዞታ እንድታቆም ማስገደድ እንዳለባቸው እና የ1974ቱን  ስምምነት እንዲያከብሩ” አሳስባለች።

የዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ
  የእስራኤል ጥቃት “የአለም አቀፍ ህግን የጣሰ፣ የሶሪያን ሉዓላዊነት እና አንድነት የሚጋፋ እንድሁም  በአካባቢው ተጨማሪ ግጭትና ውጥረት እንዲፈጠር የሚያደርግ አደገኛ ሁኔታ ነው” ሲል ገልጿል።

ሚኒስቴሩ  እስራኤል በሶሪያ ግዛት ላይ የምታደርሰውን ጥቃት በ1974ቱ በእስራኤል እና በሶሪያ መካከል የተደረገውን የመለያየት ስምምነት በግልጽ የጣሰ መሆኑን ገልጿል።

መንግሥቱ ከሶሪያ ጋር ያለውን ሙሉ አጋርነት የገለጸ ሲሆን የሶሪያን ደህንነት፣ መረጋጋት ጠይቋል

በተጨማሪም  ሉዓላዊነቷን” በማረጋገጥ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ “ሕጋዊና የሞራል ኃላፊነቶቹን እንዲወጣ፣ እስራኤል በሶርያ ላይ የምታደርገውን ቀስቃሽ እና ሕገ-ወጥ ጥቃት እንድታቆም  አሳስቧል።

ሃማስ  በበኩሉ እስራኤል በሶሪያ ላይ ያደረሰችው ጥቃት “በአሸባሪው ኔታንያሁ መንግስት እየተከተለ ያለው የትምክህት እና ግድየለሽነት ፖሊሲ አካል ነው”  ብሏል።

ረቡዕ ዕለት የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በዋና ከተማይቱ ደማስቆ እና በምዕራብ ሃማ እና ሆምስ አውራጃዎች ላይ በርካታ የአየር ድብደባዎችን አድርሰዋል።

የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሶሪያ በዳራ የምድር ጥቃት የከፈተ ሲሆን ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

የበሽር አል አሳድ መንግስት በታህሣሥ ወር ከወደቀ በኋላ፣ እስራኤል ከወታደራዊ ቁጥጥር ነፃ የሆነዉን የሶሪያን ጎላን ሃይትስ በመያዝ ይዞታዋን አስፋፍታለች።

እስራኤልም የአገዛዙን ውድቀት ተጠቅማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥቃቶችን ያደረሰች ሲሆን ተዋጊ ጄቶች፣ ሚሳኤሎች እና የአየር መከላከያ ተቋማትን ጨምሮ   በሶሪያ ወታደራዊ ቦታዎችን እና ንብረቶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈጽማለች።
አቶ አደም ፋራህ ለሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ 

-በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ለሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ አደም በማህበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፣ ኢትዮጵያ የበርካታ ውብ እና አስደናቂ ታሪክ፣ ቅርስ፣ ባህል እና እሴቶች ባለቤት መሆኗን ገልጸዋል።

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በቀረጽነው የለውጥ ፍኖተ ካርታ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ድልብ የሆኑ የማኅበራዊ እሴቶቻችንን በማጎልበት የማኅበራዊ ልማታችንን ማጠናከር እና በሀገራችን ያሉ የቱሪዝም ፀጋዎችን በማልማት የብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ መገንባት ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

በዚህ የለውጥ ዓመታት ጉዞ ውስጥ በበርካታ የአገራችን አካባቢዎች የሚገኙ የሕዝባችንን መልካም እሴቶች የሚያጠናክሩ ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገር ለመገንባት የሚያስችሉ ባህሎቻችን እና እሴቶቻችንን በማጎልበት ረገድ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ ሲሉም አክለዋል።

በዚህ ረገድ ባለፉት ዓመታት በማይዳሰስ ቅርስነት በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገበው የሸዋል ዒድ (ሹዋሊድ) ባህላዊ ክብረ በዓል አንዱ እንደሆነ ነው የገለጹት።

በመሆኑም ይህ በዓል በሐረሪ ክልል የቱሪዝም ዘርፉን ከማጎልበት አንፃር ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነም አመልክተዋል።

በተጨማሪም ሹዋሊድ ሐረር የምትታወቅበት የአብሮነት እና የመቻቻል እሴትም ጎልቶ የሚታይበት የከተማዋ ነዋሪ የሆኑ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችም በጋራ የሚሳተፉበት ባህላዊ ክብረ በዓል ነው ብለዋል።
የጠቅላይ ምክርቤቱ ሐጅና ዑምራ ዘርፍ እየተከናወነ ያለው የኮታ ማሟያና የተጠባባቂ ሁጃጆች ምዝገባ ሂደትን የመስክ ምልከታ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነጃሺ ቲቪ :- መጋቢት 28፣ 2017 ዓ.ል

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሐጅና ዑምራ ዘርፍ የሑጃጆች ቪዛ ህትመት ያለበትን ደረጃ በሀጅ ምዝገባ ጣቢያዎች ተዘዋውሮ እየጎበኘ አስታውቋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ከሺዛ ህትመት በተጨማሪ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች በከፈታቸው የምዝገባ ጣቢያዎች እየተከናውነ ያለውን የኮታ ማሟያና የተጠባባቂ ሁጃጅ ምትገባ ሂደትን መመልከቱን ዘርፉ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ እንዳሳውቀው የሀጅ ምዝገባ የመጨረሻው ምዕራፍ በተሻለ ሂደት ላይ እንደሚገኘ ነጃሺ ቲቪ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሀጅና ዑምራ ዘርፍ አክሎም ህትመታቸው ተጠናቆ ለጉዞና ለክትባት አገልግሎት ዝግጁ የሆኑ ፖስፖርቶች በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች እንዲሰራጩ መደረጉን ጠቅሷል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የUጅ አገልግሎት መስተንግዶውን ቀልጠፋና እንግልት አልባ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እየፈፀመ የሚገኝ ሲሆን ጥረቱን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግም ሁጃጆቹን በየ45 ቡድኖች በማደራጀት በአሚር እንዲመሩ ለማስቻል የሚረዳውን ስልጠና እየሰጠም ይገኛል።

የኮታ ማሟያና የተጠባባቂ ሁጃጆች ምዝገባ የሳውዲ ሀጅ ሚኒስቴር ያስቀመጠው የጊዜ ገደብ ከመገባደዱ በፊት ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቃቅ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየሠራ እንደሚገኝም ሀጅና ዑምራ ዘርፉ መረጃውን አድርሶናል።
2025/04/06 13:06:11
Back to Top
HTML Embed Code: