Telegram Web Link
አቶ አደም ፋራህ ለሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ 

-በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ለሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ አደም በማህበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፣ ኢትዮጵያ የበርካታ ውብ እና አስደናቂ ታሪክ፣ ቅርስ፣ ባህል እና እሴቶች ባለቤት መሆኗን ገልጸዋል።

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በቀረጽነው የለውጥ ፍኖተ ካርታ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ድልብ የሆኑ የማኅበራዊ እሴቶቻችንን በማጎልበት የማኅበራዊ ልማታችንን ማጠናከር እና በሀገራችን ያሉ የቱሪዝም ፀጋዎችን በማልማት የብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ መገንባት ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

በዚህ የለውጥ ዓመታት ጉዞ ውስጥ በበርካታ የአገራችን አካባቢዎች የሚገኙ የሕዝባችንን መልካም እሴቶች የሚያጠናክሩ ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገር ለመገንባት የሚያስችሉ ባህሎቻችን እና እሴቶቻችንን በማጎልበት ረገድ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ ሲሉም አክለዋል።

በዚህ ረገድ ባለፉት ዓመታት በማይዳሰስ ቅርስነት በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገበው የሸዋል ዒድ (ሹዋሊድ) ባህላዊ ክብረ በዓል አንዱ እንደሆነ ነው የገለጹት።

በመሆኑም ይህ በዓል በሐረሪ ክልል የቱሪዝም ዘርፉን ከማጎልበት አንፃር ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነም አመልክተዋል።

በተጨማሪም ሹዋሊድ ሐረር የምትታወቅበት የአብሮነት እና የመቻቻል እሴትም ጎልቶ የሚታይበት የከተማዋ ነዋሪ የሆኑ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችም በጋራ የሚሳተፉበት ባህላዊ ክብረ በዓል ነው ብለዋል።
የጠቅላይ ምክርቤቱ ሐጅና ዑምራ ዘርፍ እየተከናወነ ያለው የኮታ ማሟያና የተጠባባቂ ሁጃጆች ምዝገባ ሂደትን የመስክ ምልከታ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ነጃሺ ቲቪ :- መጋቢት 28፣ 2017 ዓ.ል

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሐጅና ዑምራ ዘርፍ የሑጃጆች ቪዛ ህትመት ያለበትን ደረጃ በሀጅ ምዝገባ ጣቢያዎች ተዘዋውሮ እየጎበኘ አስታውቋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ከሺዛ ህትመት በተጨማሪ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች በከፈታቸው የምዝገባ ጣቢያዎች እየተከናውነ ያለውን የኮታ ማሟያና የተጠባባቂ ሁጃጅ ምትገባ ሂደትን መመልከቱን ዘርፉ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ እንዳሳውቀው የሀጅ ምዝገባ የመጨረሻው ምዕራፍ በተሻለ ሂደት ላይ እንደሚገኘ ነጃሺ ቲቪ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሀጅና ዑምራ ዘርፍ አክሎም ህትመታቸው ተጠናቆ ለጉዞና ለክትባት አገልግሎት ዝግጁ የሆኑ ፖስፖርቶች በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች እንዲሰራጩ መደረጉን ጠቅሷል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የUጅ አገልግሎት መስተንግዶውን ቀልጠፋና እንግልት አልባ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እየፈፀመ የሚገኝ ሲሆን ጥረቱን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግም ሁጃጆቹን በየ45 ቡድኖች በማደራጀት በአሚር እንዲመሩ ለማስቻል የሚረዳውን ስልጠና እየሰጠም ይገኛል።

የኮታ ማሟያና የተጠባባቂ ሁጃጆች ምዝገባ የሳውዲ ሀጅ ሚኒስቴር ያስቀመጠው የጊዜ ገደብ ከመገባደዱ በፊት ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቃቅ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየሠራ እንደሚገኝም ሀጅና ዑምራ ዘርፉ መረጃውን አድርሶናል።
ግብፅ፣ ዮርዳኖስ እና  ፈረንሳይ በእስራኤል ላይ  ግፊት እንዲደረግ ጠየቁ

ነጃሺ ቲቪ ሚያዚያ 1/2017

የግብፅ፣የዮርዳኖስ እና የፈረንሳይ መሪዎች እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የምታደርሰውን አደገኛ ጥቃት እንድታቆም አለም አቀፍ ጫና እንዲደረግ ትናንት ጠይቀዋል።

ባሳለፍነው ሰኞ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ፣ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የዮርዳኖስ ንጉስ አብዱላህ 2ኛ በተገኙበት በፍልስጤም ግዛት ስላለው ሁኔታ በካይሮ  የመሪዎች ጉባኤ ተደርጓል።

የግብፅ ፕሬዝዳንት በሶስትዮሽ የመሪዎች ጉባኤ ላይ "መሪዎቹ ወደ ተኩስ አቁም በአስቸኳይ እንዲመለሱ፣ ፍልስጤማውያንን ለመጠበቅ እና አስቸኳይ ሰብአዊ ርዳታ እንዲያገኙ ጠይቀዋል።"

የዮርዳኖስ ንጉሣዊ ፍርድ ቤት ባወጣው መግለጫ ፣ ሦስቱ መሪዎች ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርገውን ጦርነት እንዲታቆም ግፊት እንዲያደርግ፣ የተኩስ አቁሙ  ወደነበረበት እንዲመለስ  እንድሁም  በጋዛ እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ለማስቆም በቂ የሆነ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲጀምር ጠይቀዋል።

ንጉስ አብዱላህ የእስራኤል ጥቃት መቀጠሉ ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ እና ሰብአዊ ጥረቶችን እንደሚያዳክም እና ቀጠናውን  ወደ ትርምስ እንደሚያስገባው አስጠንቅቀዋል።

በሁለቱ መንግስታት መፍትሄ ላይ የተመሰረተ ፍትሃዊ እና ሁሉን አቀፍ ሰላም ለማምጣት ቀጣናዊ መረጋጋትን መፍጠር እና የፖለቲካ አድማስ ለማግኘት መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

የዮርዳኖስ ንጉሠ ነገሥት ግብፅ ለአረብ ጉዳዮች በተለይም ለፍልስጤም የምታደርገውን ድጋፍ እና  ፈረንሳይ  የተኩስ አቁምን በመደገፍ እና  ጋዛን እንደገና ለመገንባት የአረቦችን እቅድ አወድሳለች  ሲል መግለጫው ያትታል።

ንጉስ አብዱላህ በተጨማሪም ፍልስጤማውያንን ከጋዛ እና በተያዘው ዌስት ባንክ ማፈናቀል ዮርዳኖስ ውድቅ እንዳደረገች ገልፀው “በዌስት ባንክ ፍልስጤማውያን ላይ ቀጣይነት ያለው አንድነት ያለው እርምጃ እንዲሁም በእየሩሳሌም የሚገኙ የሙስሊም እና የክርስቲያን ቅዱሳን ስፍራዎችን መጣስ አደጋ ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ሦስቱ መሪዎች በተለይ እንደ ፈረንሣይ ካሉ የአውሮፓ ኅብረት አገሮች ጋር  የአረብ የጋዛን የመልሶ ግንባታ ዕቅድ ለመደገፍ የተዋሃደ ዓለም አቀፍ ጥረቶች እንደሚያስፈልጉ አፅንዖት ሰጥተዋል መስጠታቸውን መግለጫው ገልጿል።

በተጨማሪም “ምስራቅ እየሩሳሌም ዋና ከተማዋ የሆነችውን የፍልስጤም ነጻ መንግስት ለመመስረት የሚያደርስ ፖለቲካዊ መንገድ፣ እንዲሁም በአካባቢው ዘላቂ ሰላምና ደህንነት እንዲሰፍን ፣ የእርስ በርስ ግጭት እንዲቆም” መጠየቃቸውን ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል።
B
በካይሮ ሰኞ ዕለት የተካሄደው  የመሪዎች ጉባኤ  የእስራኤል ወረራ ጦር በፍልስጤም ግዛት ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት እያባባሰ ባለበት ወቅት።

እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 18  እስራኤል የተኩስ አቁም እና የእስረኞች ልውውጥ ስምምነቱን ካፈረሰችበት ጊዜ ጀምሮ 1,400 የሚጠጉ ሰዎች ሲገደሉ 3,400 ሰዎች  በአየር ጥቃቱ  ቆስለዋል።
እስራኤል በዌስትባንክ የ14 ዓመት ታዳጊ መገደሏ ቁጣ ቀሰቀሰ።

ነጃሺ ቲቪ ሚያዚያ 1/2017

ፍልስጤማዊ-አሜሪካዊ ታዳጊ በእስራኤላዊ ወታደሮች በተያዘው ዌስት ባንክ ተገደለ

የፍልስጤም ባለስልጣናት እንዳስታወቁት  የ14 አመቱ አሜሪካዊ ታዳጊ  ኦማር መሀመድ ራቤይ ይባላል

የፍልስጤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እሁድ  እለት ተጎጂው  በራማላ ከተማ ሰሜናዊ ምስራቅ በምትገኘው ቱርሙስ አያ ከተማ አቅራቢያ በጥይት መመታቱን አስታውቋል።

የእስራኤል ጦር ድንጋይ እየወረወረ ያለውን “አሸባሪ” ገድያለሁ ብሏል።

ግድያውን ተከትሎ በርካታ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች መገለጫ ያወጡ ሲሆን አንድ ዩሮ ሜደ የተሰኘ የሰበአዊ መብቶች ቡድን ድንጋይ መወርወር አሽባሪነት አይደለም በማለት እስራኤል የአሜሪካና የፍልስጤም ዜግነት ያለውን የ14 ዓመቱን ታዳጊ መግደሏን አውግዟል።

መቀመጫውን በጄነቫ ያደረገው ቡድኑ  ኦማር መሀመድ ራብያ የተሰኘው ታዳጊ አሸባሪ ነው ድንጋይ ሲወረውር ነበር በማለት የእስራኤል ጦር  የሰጠውን ማስተባበያ ውድቅ ያደረገ ሲሆን  በወቅቱ ሌሎች ተጨማሪ ሁለት ታዳጊዎች መቁሰላቸውን ገልጿል።

ቡድኑ አክሎም ታዳጊውን ሆን ተብሎ እንደተገደለ በኤክስ ላይ ባጋራዉ መረጃ አስታውቋል።
ቡድኑ ድንጋይ እየወረወሩ የሚጫወቱን ህፃናት አሸባሪ የሚል ታፔላ ለጥፈህ መግደል እስራኤል ፍሊስጤማውያንን ለመግደልና በአለም አቀፍ ህግ ተጠያቂ ላለመሆን በየቀኑ አዳዲስ የመግደያ ምክንያቶች ይዛ እየመጣች ነው ይህም ከነዚህ ምክንያቶች አንዱ ነው በምንም መለኪያ ድንጋይ የያዘን የ14 ዓመት ታዳጊ አሸባሪ ነው ብለህ መግደል ልክ ሊሆን አይችልምም ሲል ተደምጧል።

ይህ ስልት የስቴት ጭፍጨፋ ለመፍጠርና እያንዳንዱን ፍሊስጤማዊ ወንጀለኛና አሸባሪ ነው የሚል ታርጋ ለመለጠፍ የተሰራ ነው ያለው ቡዱኑ በሚያሳዝን ሁኔታ ህፃናትን ሁሉ ወንጀለኛ አድርጎ የሚፈርጅ ስርዓት ምህረት እየተደረገላቸው አለመሆኑ ነው ብሏል።

ቡዱኑ በመጨረሻም ድንጋይ መወርወር አሸባሪ አያስብልም፣ ህፃናትና ታዳጊዎች መግደል  ሀገር ማዳን አይደለም ይህ ጥይት እየተጠቀምክ የሚፈፀም አፓርታይድ ነው ማለቱን አልጀዚራ ዘግቧል።
መረጃቸው በኑሱክ የመረጃ ቋት ውስጥ ያልተካተቱ ግለሰቦች ለሑጃጆች ተብለው የተዘጋጁ አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ ከተገኙ ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ተገለፀ።

ነጃሺ ቲቪ ሚያዚያ 2/2017

የሳዉዲ አረቢያ ሀጅና ዑምራ ሚኒስቴር ህጋዊ የአሰራር ሂደትን ሳይከተሉ ለሐጅ ስነ ስርዓት ወደ ሳውዲ ለመግባት የሚሞክሩ ግለሰቦችን ለመከላከል እንዲያስችለው ኑሱክ የተሰኘ የመረጃ ቋት አዘጋጅቶ ወደ ስራ አስገብቷል።

ሚኒስቴሩ የሁሉም ሀገራት የአሏህ እንግዶች መረጃዎች ወደዚህ የመረጃ ቋት ቀድመው እንዲገቡም አስገዳጅ መመሪያ አስተላልፏል።

አስፈላጊ መረጃዎችን ወደኑሱክ የመረጃ ቋት ያልገቡለት የየትኛውም ሀገር ዜጋ በህገ ወጥነት ተፈርጆ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድበትም የሀጅ ሚኒስቴሩ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ (https:/masar.nusuk.sa) ባስተላለፈው በዚሁ መመሪያው አመላክቷል።

በስራ፣ በዚያራ፣ በጉብኝት ወይም በሌላ መንገድ ሳውዲ የተገኘ የየትኛም ሀገር ዜጋ ከሁጃጆች ጋር ተቀላቅሎ ሀጅ እንዳያደርግ ለመቆጣጠርና ተከታትሎ ተገቢ እርምጃ ለመውሰድ እንዲያመች ታስቦ እንደተዘጋጀ የተነገረለት ይህ የመረጃ ቋት በሀጅ ወቅት ሁጃጆች ላይ ሊደርስ የሚችልን መስተጓጎል ያስቀራልም ተብሎለታል።

አስፈላጊ መረጃዎች በኑሱክ የመረጃ ቋት ውስጥ ያልተካተቱለት ግለሰብ የሐጅ ስርዓት በሚፈፀምበት የትኛውም ቦታ መገኘትና ለሑጃጆች ተብለው የተዘጋጁ አገልግሎቶች ሲጠቀም ከተገኘም ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጣልበትም በሚኒስቴሩ መረጃ ተጠቅሷል።

የሀጅና ዑምራ ሚኒስቴሩን የስራ መመሪያ መሰረት በማድረግም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለሀጅ ጉዞ የተመዘገቡ የአሏህ እንግዶችን መረጃዎች ወደኑሱክ የመረጃ ቋት እያስገባ መሆኑን የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኅላፊው ሐጅ አብዱልፈታህ መሐመድናስር ተናግረዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የ1446 ዓ.ሒ የአሏህ እንግዶች በሳውዲ አረቢያ በሚኖራቸው የሀጅ ቆይታ የተሻለ  አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ በቂ ቅድመ ዝግጅት እንዳደረገ የገለፁት ሐጅ አብዱልፈታህ ህጋዊ የአሰራር ሂደትን ሳይከተሉ በሀጅ ስርዓት ላይ የሚገኙ ግለሰቦችን ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

ህጋዊ ሁጃጆችን ከሌሎች ለመለዬት የሚያስችልም ባለሚስጢራዊ ኮድ የደረት ባጅና በእጅ ላይ በሚታሰሩ ኮዶች መዘጋጀታቸውንም ሀጅ አብዱልፈታህ አክለዋል።
መረጃው
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ነው
2025/04/11 17:52:29

❌Photos not found?❌Click here to update cache.


Back to Top
HTML Embed Code: