Telegram Web Link
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
          đŸ”° #ምዕራፍ_አስር_ስድስት ➊➏
                  ✍አሚር ሰይድ



╔════════════════════════╗
🎖#መፅሀፍ_ቅዱስ_ስለሁለተኛ_ሚስት_ምን_ይላል?
╚════════════════════════╝


     መፅሀፍ ቅዱሱም ሌሎች የሌላ ሀይማኖት መለኮታዊ መፅሀፍ ለልሹ አልከለከሉም...
#ለምሳሌ መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ በህጋዊ መንገድ በጋብቻ ከ 2 በላይ ሚስት ያገቡትን ሰዎችና ነብያቶችን  እና ቅዱሳን ሰዎች እንመልከት:-


☞ ”ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች አንዲቱም የተጠላች ሁለት #ሚስቶች_ቢኖሩት: ለእርሱም የተወደደችው ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ…”(ዘዳግም:21:15)

☞ ሌላ ሴት (ሚስት) ቢያገባ ለመጀመሪያ ሚስቱ ምግቧን ፣ ልብሷንና , የጋብቻ መብቷን አይከልክላት።
( ዘጸሃት 21፡10)


📌ነቢዩ ሰለሞን (ጠቢቡ ሰለሞን) ከ1000 ሚስቶች በላይ ነበሩት‼

➊ ነገሥት 11:3 ለእርሱም ወይዛዝር የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶች ሶስት መቶም ቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ልቡን አዘነበሉት።(1ኛ ነገሥት 11:3)
700 ሚስቶች + 300 ቁባቶች = 1,000 ሚስቶች✔

➋ ☞አብራሃም (ነቢዩ ኢብራሂም) #3ሚስቶች ነበሩት።
“የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባሪያዋን አጋርን ወስዳ ለባልዋ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።”(ኦሪት ዘፍጠረት 16:3)

  #በተጨማሪ የዱሮ ስርአት ናፋቂዎች ከአንድ በላይ ሚስት ሲቀልዱ ሲሳለቁ እናያለን..ነገር ግን የድሮ መንግስቶች አፄዎች ስንት ሚስቶች ነበራቸዉ?የሚለዉን እንመልከት

╔══════════════════╗
     đŸŽ– #አፄ_ቴድሮስና_እቁባቶቻቸው🎖
╚══════════════════╝


   አብደል ጀሊል ሸህ አሊ ካሳ ኪነት ያገነነዉ አፄ በሚለዉ መፅሀፉ ከገፅ 229-231 ድረስ ስለአፄ ቴድሮስ እቁባቶች የተወሰነ ነጥብ አስቀምጧል፡፡ አፄ ቴድሮስ ከ100 በላይ ሚስት ነበራቸዉ ይለናል....ከመፅሀፉ የተወሰነዉን  ፁሁፍ እነሆ ፡-

   ምንም እንኳን የንጉሡ ግልባጭ የሆነትና ፀሀፊ ትዕዛዛቸው የሆኑት ደብተራ ዘነበ ንጉሱን ምንዝር የማይዎድ!Âť ቢሏቸውም ንጉሱ የፈለጓትን ሴት ወስደው ሚስታቸው ያደርጉ ነበር። ማን ያርዳ የቀበረ ማን ያውራ የነበረ ነውና የእሱ እስረኛ ሆርመዝ ራሳም በግልፅ እንዳስቀመጠው ቴዎድሮስ የክርስቲያን ጠላቶቻቸውን ሚስቶች እንኳን ቢሆን ባሎቻቸው በህይወት እያሉ ወስደው አያገቡም ነበር። ግን የሙስሊም ወንዶችን ለማዋረድ ባሎቻቸውን በሕይወት እያሉ ነጥቀው ስለማግባታቸው ተዘግቧል።

☞ሆርሙዝ ራሳም እንዳስቀመጠው ቴዎድሮስ አስገድደው የሰው ሚስት ክርስትናን አስጠምቀው ያገቡ ነበር።  የፈለጓትን በውበቷ የፈዘዙባትን ሁሉ።

☞ሪቻርድ ፓንክረስት ንጉሱ ለእተመኙ የጻፉትን ደብዳቤ ባጠኑበት ፁሁፍ ላይ ራሳምን ዋቢ አድርገው ወይዘሮ እተመኙ የጁ ሙስሊም ኦሮሞ ስትሆን የየጁ ሙስሊም ኦሮሞዎች የአንዱ ሚስት የነበረች፣ ስለ ውበቷ ማማር ቴዎድሮስ በሰማ ጊዜ አስመጥቶ አስገድዶ ክርስትና እንድትነሳ በማድረግ አግብቷታል።ብለዋል፡፡

☞ ሐጅ አደም ኩርማን ስለ ተባሉ በሃይማኖታቸው ምክንያት ከጎንደር ስለተሰደዱ ባለሀብት፣ ውብ ሚስታቸውንና ንብረታቸውን በቴዎድሮስ ስለተቀሙ ሰው ሆርሙዝ ራሳም በቅጽ አንድ መጽሐፉ ላይ አስፍሯል። ሐጅ አደም ኩርማን ለሆርሙዝ ራሳም ሚስታቸው በጎንደር ከተማ ላይ በውበቷ የምትታወቅ፣ ከልጅነቷ ጀምረው የሚያውቋትና ያገቧት ሴት እንደ ነበረች ነግረውታል። ስለ ደም ግባቷ ንጉሡ መረጃ እንደደረሳቸው ተመኟት፣ ምንም እንኳን #ከመቶ_በላይ ሚስት ቢኖራቸውም ሀይማኖቷን ለውጠው ወስደዋታል፤ በኋላም የማእድ ቤት ሰራተኛ ሆና ሆርሙዝ በቴዎድሮስ ማጀት ውስጥ አግኝቷታል።

ወልደዩሃንስ ወርቅነህ እና ገመቹ መልካ በመፅሀፋቸው ላይ የአቶ አፈወርቅን ፅሁፍ ጠቅሰው እንዲህ ፅፈዋል፡- “በዘመኑ በድሃው ቤተሰብ በተለይ በኃይል በተወረሩ ህዝቦች ላይ የማይሠራ ግፍ አልነበረም፡፡ ከታጣቂ ነፍጠኞች እስከባላባቱና ሀገር መሪው ቤተሰብ በማፍረስ ጭምር ቆንጆ› ሆና የታየቻቸውን ሴት ነጥቀው ይወስዳሉ፡፡ ባል እያለ ሚስቱን እፊቱ ይደፍራሉ፡፡ የደረሰች ሴት ልጁን አምጣልኝ ብለው ለአባቷ ትእዛዝ ከሰጡ እስከ ቤት ድረስ ይወስዱላቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ አቶ አፈወርቅ ገብረየሱስ በቴዎድሮስ  ዘመን ከተፈፀመው በመነሳት ያቀረቧቸው አንድ ጉዳይ የጊዜውን የነፍጠኞች ግፍ ሊያንፀባርቅ የሚችል ነው::ይላሉ ጽሀፊዎቹ፡፡

አንዳንድ አጥባቂ ሀይማነተኞች አፄ ቴድሮስ ሀይማኖተኛ ነበር ወዘተ ይባላል ግን ከ100 በላይ ሚስቶች እንደነበሯቸዉ መናገርም መስማትም አይፈልጉም



╔════════════════════╗
   🎖#የቀዳማዊ_ኀይለ_ሥላሴ_ሚስቶች🎖
╚════════════════════╝


    
ቀዳሚዊ ሀይለ ስላሴ እኔ የሰለሞን ዘር አለብኝ ስዩመ እግዝአብሄር ነኝ ይላሉ፡፡ ለሙስሊሞችም ሀይማኖታቸዉን ለማስቀየር የተራቀቀ ፓሊሲ የነበራቸዉ ንጉስ ነበሩ፡፡
   ቀዳሚ ሀይለ ስላሴ ብዙ ሚስቶች ነበሯቸዉ፡፡የቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ሚስቶች፣ቁባቶች እና ሴሰኝነት ፣ #ከጋብቻ_ውጭ_የበራቸውን_ጾታዊ ግንኙነት እንመልከት፡፡ከንጉሡ ሕልፈት በኋላ፣ በታተሙና ገና ባልታተሙ የታሪካቸው ድርሳናት ተመስክሯል፡፡ግን ፀሀፊዎች ልጅ እያሱ አራት ሚስት ማግባቱን ሲያጣጥሉ ሲያንቋሽሹ እናዳለን...ምናልባት'ኳ እንደ ልዩነት ሊታይ ይችላል ከተባለ፣ ልጅ ኢያሱ የ በአብዛኛው ከመሳፍንት፣ ከመኳንንት፣ ከባላባት፣ እስላም ሴት ልጆች ጋር በህጋዊ መንገድ ያገባ ሲኾን፣ ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ግን፣ የነበራቸው ጾታዊ ግንኙነት በይበልጥ ከቤተ መንግሥት ሴት አገልጋዮች ጋር መኾኑ ነው፡፡

⚡️⚡️ የጥላኹን ብርሃነ ሥላሴ ቤተ፣ 1ኛ መጽሐፍ (ገጽ 345 - 82) የሚከተለው ሰፍሯል፡፡ « አንድ ልጅ ከጋብቻ ውጭ ከተወለደ፣ ላባቱ ክብር ሲባል ብቻ፣ ልጁን አባት አልባ ማድረግ ፍትሐዊ ስለማይኾን፣ መዘርዘሩ ተገቢ እንደ መኾኑ መጠን፣ እኔም የጃንሆይ ልጆች ናቸው የሚባሉትን ኹሉ መርምሬ፣ የደረስኹበትን እንደ ሚከተለው ዘርዝሬያለኹ፡፡

➊ ከወሎዬይቱ ወይዘሮ ወይኒቱዐመዴ፣ ሮማነ ወርቅን፣

➋ ከወይዘሮ ይመኙሻል ክብረት ከተባሉት የቤተ መንግሥት ሠራተኛ☞አቶ ኪዳኔ ተፈሪን ወልደዋል

➌ የልዑል ዐልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን ግቢ ሠራተኛ ከነበሩትየአቶ ግርማ ባለቤት (ስማቸውን ማግኘት አልተቻለም) ☞አቶ መንግሥቱን፣

➍ የቤተ መንግሥት ፅዳት ሠራተኛ ከነበሩት ከወይዘሮ አሰገደች አበራ፣ ትግሥት ካላና ቴዎድሮስ ካሳ እየተባሉ፣ በእንጀራ አባታቸው ስም የሚጠሩትን፡፡

➎ የቤተ መንግስት ሰራተኛ ከነበሩት ወይዘሮ አልማዝ☞ መክብብ አበበ የሚባል፣ በእንጀራ አባቱ ስም የሚጠራ ልጅ፣

➏ የቤተ መንግሥት ሠራተኛ ከነበረችው ፀሐይ መገርሳ☞ ኹለት (ለጊዜው ስማቸው ያልተገለጡ) ልጆች፡፡

➑ የቤተ መንግሥት ሠራተኛ ከነበሩ ወይዘሮ ፀሐይ ድፋባቸው☞ ሰለሞን ሠርፀ ወልድ እየተባለ በእንጀራ አባቱ ስም የሚጠራ ልጅ ወልደዋል።»

ጃንሆይ፣ ከነዚህ ስምንት ልጆች ሌላም፣ በርካታ ዲ*ቃ*ሎች እንዳሏቸው ታምተዋል፡፡ ጃንሆይ በይፋ ያልቆበቷቸው፣ ነገር ግን ሸማ የተጋፈፏቸው ሴቶች ቁጥር፣ ኢያሱ ከነበሯቸው ቁባቶችና ሚስቶች በቁጥር እንደሚበዙ አንዳንድ ገና ይፋ ያልወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡👇👇👇👇
⚡️⚡️ ከ1954-64 ዓ.ም. የግርማዊ ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ የእልፍኝ አሽከር የነበረ፣ስዩም ጣሰው የተባለ ታዛቢ «የንጉሡ ገመና» በሚል ርዕስ ካዘጋጀው ዜና መዋዕል የተቀነጫጨበ ዘገባ እነሆ፡፡

«ከግርማዊነታቸው ጋር ግንኙነት ያላቸው ሴቶች፣ አብዛኞቹ በዚህ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ የሚሠሩ ናቸው፡፡ የሴቶቹም ዓይነት እንደሚከተለው ነው፡፡ እነርሱም
☞የጽዳት ሠራተኞች፣
☜የአበሻ ወጥ ቤቶች፣
☞እንጀራ ቤት፣
☞ ቅንጬ ቤት ሲኾኑ፣ ከውጭ ደግሞ ያሉት ከተለያዩ ቦታዎች ነው፡፡ ሴቶቹ አብዛኛውን ጊዜ የሚገቡት ቀን ከምሳ መልስ፣ ዕረፍት በሚያደርጉበት ጊዜ፣ ከ8- 10፡3ዐ ሰዓት ባለው ሰዓት ውስጥ ነው፡፡ ጃንሆይ ገብተው ከተኙ በኋላ፣ ትንሽ ቆይተው ደወል ይደውላሉ፡፡ በዚያን ጊዜ፣ በዚህ ነገር የተለየ ባለሟል የኾኑ አሽከሮች በተራቸው ይገቡና < #እከሊትን_ጥራ> ሲባል ይጠራል።

«ምናልባት እርሱ ከተጠራችው ሴት ጋር ሽርክና ከሌለው፣ ወይም ከምትወስደው ገንዘብ በብዛት ካላካፈለቸው፣ <እርሷ አኹን የለችም> በማለት፣ የርሱ ሽርክ፣ ብዙ ገንዘብ በየጊዜው የምትሰጠውን ሴት <እከሊት አለች፡፡ እርሷ ከሥራዋ አትጠፋም> በማለት ይቀላምድና ይጠራል፡፡ሲገቡና ሲወጡ የተለየ ጥንቃቄ ይደረጋል፡፡ነገር ግን፣ ሴቶቹ በሚያሳዩት መለዋወጥ የተቀረው ሰው እዚያ ቦታ እንደ ደረሰች ይገባዋል፡፡ ቢሮ የሚደረገው ደግሞ ሌላ ነው፡፡ ቢሮ በሚሠሩበት ጊዜ፣ ረፈድ ሲልና አንዳንድ ባለሥልጣኖችን ካነጋገሩ በኋላ፣ ገለል ብለው ቢሮ አጠገብ ካለው መኝታ ቤት ጐራ ይላሉ፡፡ ከዚያም፣ በዚያ አካባቢ ከሚሠሩት ሴቶች ውስጥ የፈለጉዋትን አስጠርተው፣ ትንሽ ከተጨዋወቱ በኋላ፣ ወደ ቢሮአቸው ይገባሉ፡ መኝታ ቤቱና ቢሮው በጣም የተቀራረበ በመኾኑም ሌላ፣ በዚያ አካባቢ ማንም ሰው አይገኝም፡ መግቢያውም የተለያየ ስለሆነ፣ጃንሆይ ወደዚያ ሲሄዱ፣ ወደ ሽንት ቤት እንጂ፣ ወደ ሌላ ቦታ ይሄዳሉ ብሎ ከቢሮ ያለው ባለሥልጣን አይገምትም፡፡ሆስቴሶቶችንና ሌሎችን ደግሞ ምድር ቤት ካለው ቢሮ ነው የሚያገኙዋቸው፡፡

«የገንዘብ አሰጣጣቸው ደግሞ ሌላ ነው፡ የሚሰጣቸው እንደ ሴትየዋ ኹኔታ ነው፡፡ለምሳሌ፣ ለሥራ ቤት፣ እንጀራ ቤትና ወጥ ቤት የሚሰጣቸው በጣም አነስተኛ ነው።በመቶ የሚቆጠር ሲሆን፣ከፅዳት ሠራተኞች ደግሞ እንደ ሴትየዋ ሁኔታ ነው፡፡ ነቃ ነቃ ያሉት፣በብዙ ሺህ ብር ይወስዳሉ፡፡ ይሀውም፣ ከ70-80 ሺህ ብር ይሰጣታል፡፡ ከዚሁ ውስጥ ከ5-10 ሺህ የሚጠጋ ብር ለአስገቢዋ ቀረጥ ትከፍለዋለች፡፡ ስለዚህ፣ በዚያ ቦታ ያሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የወጣላቸው ሀብታሞች ይሆናሉ።በዚያ ውስጥ ያሉ ሴት ሠራተኞች መጠነኞቹ ማለቴ ነው፡፡በተቀጠሩ ከ7-10 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ፣ በሺህ ሳይሆን፣ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር ንብረት ይኖራቸዋል። ግማሾቹ! እንዲያውም ለሽርሽር ፈረንጅ አገር ድረስ መሄድ አለብን እያሉ፣ በመንግሥት ኪሳራ ለራሳቸውና ለአስተርጓሚያቸው ጭምር እየተከፈለ፣ ተንሸራሽረው የተመለሱ አሉ

«ጃንሆይ ፈረንጅ አገር ሂደው ሲመለሱ፣ ለየአንዳንዱዋ ገረድ የአልማዝ፣ የወርቅ ጌጣጌጥና ሰዓት በብዛት ያመጡና ያከፋፍላሉ፡፡ ከውጭ በተመለሱ ስሞን፣ በዚያ አካባቢ የሚታየው  ፍፁም ሌላ ነው፡፡ ተጠርታ በምትገባበት ጊዜ፣ መታሰቢያ ያመጣንልሽ› እየተባለ፣ከየዓይነቱ ተሸክማ ትወጣለች፡፡ አንዳንዶቹ ያላቸው ጌጣጌጥ ዓይነትና ውድነት በፍፁም ለማመን ያስቸግራል፡፡ ብዙዎቹ፣ የግርማዊት እቴጌ መነንን ጌጥ እየተሰጣቸው ሲያጌጡበት በማየት፣የግርማዊት አሽከሮች እንባቸውን ሲያጐርፉ ይታዩ ነበር።

«በጉዳይ ሰበብ እየቀረቡ፣ በዙ የዘረፉ፣ ከቤት ውስጥ ብቻ ሳይሆን፣ ከውጭም ጭምር ነበር፡፡ ለምሣሌም ያህል፣ የአየር መንገድ መሥሪያ ቤት፣ ሆስቴስ ከሴት አዳሪ ደግሞ፣ የቢትወደድ ነጋሽ ልጅ ሲኾኑ፣ ከባለትዳሮችም ጋር ግንኙነት ነበራቸው። የሚገናኙትም አብዛኛውን ጊዜ ከቢሮ ነው፡፡»

ይህን የዓይን ምስክርነት ማስተባበል ያስቸግራል፡፡ የኢያሱ ውንጀላ ሲጤን፣ ዐመድ በዱቄት ይሥቃል እንደ ተባለው ኾኖ ይታያል
#ምንጭ:-አቤቶ ኢያሱ አነጋገስና አወዳደቅ በአጥናፍሰገድ ይልማ ሚያዚያ 2006


╔═══════════════════════╗
  🎖 #በቀድሞ_አረቦች_የነበረ_የጋብቻ_አይነት
╚═══════════════════════╝

      አቡ ዳውድ ዓኢሻን ረዐ  ጠቅሰው እንደዘገቡት በቅድመ ኢስላም ከዐረቦች ዘንድ አራት የጋብቻ አይነቶች ነበሩ
#አንደኛው ጋብቻ ዓይነት☞ የተለመደው አይነት ጋብቻ ነው። ወንዱ የእንስቷን ቤተሰብ ያናግራል። ሲፈቀድለት ጥሎሿን ሰጥቶ ያገባታል።
#ሁለተኛዉ ጋብቻ ዓይነት ☞ባል ሚስቱን ከወር አበባ ስትፀዳ ወደ ሌላ ወንድ ሄዳ እንድታረግዝ ያደርጋታል።ወደተባለው ሰው ትሄድና ይገናኛታል። ማርገዟ እስኪረጋገጥ ድረስ ባሏ አይደርስባትም። ማርገዟ ሲረጋገጥ ባሏ ከፈለገ ይገናኛታል። ይህን የሚያደርገው ልጅ ፍለጋ ነው። ይህ ዓይነቱ ጋብቻ «ኢስቲብዳዕ» ይሰኛል።
#ሶስተኛው ጋብቻ ዓይነት ☞ቁጥራቸው ከአስር የማይበልጥ ወንዶች አንዲትን እንስት ይገናኟታል። በነዚህ ግንኙነቶች አርግዛ ከወለደች ከቀናት በኋላ ወደ ወንዶች መልዕክት ትልካለች። ክእሷ ጋር ግንኙነት የፈፀመው ወንድ ፈፅሞ ሊቀር አይችልም ሁሉም ሲመጡ፡-ሁላችሁም እንደተገናኛችሁኝ ታውቃላችሁ።እነሆ ወልጃለሁ።እገሌ ሆይ! ልጁ ልጅህ ነው።»በማለት የአንዱን ስም ትጠራለች። እርሱም አባትነቱን ይቀበላል
☞ #አራተኛው የጋብቻ ዓይነት☞ ብዙ ወንዶች አንዲትን ሴት ይገናኟታል። ይህች ሴት መገናኘት ለሚፈልጋት
ወንድ ምልክት ይሆን ዘንድ በሩቅ የሚታይ ምልክት ከበሯ አጠገብ ታንጠለጥላለች። ወንዶች ምልክቱን እያዩ ገብተው ይገናኟታል።እምቢ አትልም። ስትወልድ የተገናኟት ሁሉ ይሰበሰባሉ። ዘር አዋቂ ልጁን ወደ አንደኛው ያስጠጋል።ሰውየውም አባትነቱን ወዶ ይቀበላል።ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ሲላኩ ይህን የመሀይምነት ዘመን ጋብቻ ውድቅ በማድረግ የአሁኑን የእስልምና ጋብቻ ብቻ አፀደቁ፡፡

በጦርነት ወቅት እንስቶች ከወንዶች ጋር ይሆናሉ፡፡ አሽናፊው ወገን የተሸናፊውን እንስቶች እንደልቡ ያለ ገደብ ይገናኛል።በዚህ ግንኙነት የሚወለዱ ልጆች እድሜልካቸውን ሐፍረት እንደተሰማቸው ይኖራሉ።

የመሐይምነት ዘመን ወንዶች የሚያገባቸው ሚስቶች ገደብ አልባ ነበሩ። እሁትማማቾችን፤ የአባትን ሚስቶች እርሱ ከሞተ ወይም ከፈታቸው በኋላ ያገባሉ።

ፍች የወንዶች ያልተገደበ ስልጣን ነበር። ዝሙት በሁሉም የሕብረተስቡ ክፍሎች ተስፋፍቷል። ከዚህ ውርደት ውስጥ ነፍሶቻቸውን ላለመዘፈቅ የወስኑና የጸኑ በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ካልሆኑ በቀር መላ ማሕበረሰቡ ከዝሙት ባህር ውስጥ ተዘፍቋል። ከባሮች ይልቅ ጨዋ ሴቶች ከዝሙት በመራቅ ይሻላሉ።ባሮች እጅግ በሚያሳቅቅ ሁኔታ በዝሙት ተዘፍቀዋል።አብዛኛዎቹ የቅድመ ኢስላም ሰዎች ከዚህ ውርደት ውስጥ በመዘፈቃቸው ነውር መስሎ አይታያቸውም።
ነብዩ ﷺ ከተላኩ ይሄን አስቀርተዉ አንድ ወንድ ከአራት በላይ እንዳያገባ ሀራም መሆኑ ታወጀ፡፡

እስኪ እሰቡት ከክርስትና ከበፊቱ ከአረቦች ባህል የኢትዮ የጥንት ንጉሶች ለሴቶች ክብር የሰጠዉ እስልምና መሆኑን ላስተነተነዉ ሰዉ ግልፅ ነዉ፡፡
አንድ ልጅ ተወልዶ አባቱ አይታወቅም እየተባለ ..አባቱን በእናቱ አያት ስም አርገዉ ከሚጠሩ..አራት አግብቶ አባትህ እንትና ነዉ ብሎ መናገር ይሻላል


#በቀጣይ_ክፍል
ስለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ገመና እንዳስሳለን

ክፍል ➊➐ ይቀጥላል


join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💚ነብዩ ﷺ አኢሻ ረዐ ለምን 9 አመቷ ላይ አጯት?ብለዉ ለሚጠይቁ ሰዎች መልስ


join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
          đŸ”° #ምዕራፍ_አስር_ሰባት ➊➐
                  ✍አሚር ሰይድ


╔═════════════════╗
      🎖 #የዩኒቨርሲስቲ_ገመና 🎖
╚═════════════════╝

ዩኒቨርስቲዎች ሁለት ጥቅም አላቸዉ ለሀገር የሚጠቅሙ ተማሪዎችን ማፍሪያና በዛ በተዘዋዋሪ ደግሞ ዩኒቨርስቲ ከገቡ ቡሀላ  ለአገር የማይጠቅሙ እነሱ ተበላሽተዉ ሌላ ትዉልድን የሚያበላሹ ተማሪዎች መፈልፈያ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ዩኒቨርስቲዎች ለወላጆች #ወልዶ_መጣያ ከሆኑ ሰነባብተዋል፡፡
ወላጅ ተጨንቆ አስቦ ከራሱ ቀንሶ ለተማሪ ልጄ ይላል ..ተማሪ ግን በጓደኛ ግፊት..የቤተሰብ ቁጥጥር ዩኒቨርስቲ ዉስጥ አለመኖር አላማቸዉን ዘንግተዋል፡፡በፊት ሴት ልጅ ሰነፍ ከሆነች አትማር ስል ብዙ ተከታዮች ለሌላ ይመስላቸዋል ግን ዩኒቨርስቲ ገብተዉ ያለዉን ፈተና መቋቋም ስለማይችሉ በማሰብ ነዉ ለምን በፊት ተማሪ በዉጤቱ በጉብዝናዉ ሳይሆን በኩረጃዉ በትቤት ህግ መላላት ምክንያት ነበር ወደዩኒቨርስቲ የሚገቡት..,እድሜ ይስጠዉና ዶክተር ብርሀኑ ነጋ እየሰራ ያለዉ ስራ በጣጣም አበረታች ነዉ...ተማሪን እያየን የtiktok ትዉልድ እያየን ነዉ በጀመአ ሲወድቅ፡፡ እኔ የሚገርመኝ እኛን የሚያስተዳድሩን በየመስሪያ ቤቱ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች ከስንት አንድ ካልሆነ ጎበዝ ሁነዉ በትምህርት ደረጃቸዉ የሚያስተዳድረን እንጂ ከዛ ዉጭ ያለዉ በፊት በነበረዉ የዩኒቨርስቲ ፓሊሲ የተማሩ መሆናቸዉ በነዚህ ሰዎች ሙስና ይቀራል ማለት ዘበት ነዉ፡፡ ግን አሁን የተጀመረዉ ዩኒቨርስቲዎች ራሳቸዉን በራሳቸዉ ማስተዳደራቸዉ በጣም አሪፍ ነዉ፡፡
የዩኒቨርስቲ ትርጉሙና ትክክለኛ ተማሪ የሚገባት ከዘንድሮ ጀምሮ ይሆናል፡፡
በተጨማሪ በግል ኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎችም ከዩኒቨርስቲ ህይወት ጋር በዚና መስመር እንደሚመሳሰሉ ማወቅ አለብን....

ለወደፊት ትምህርት ጥረት ይጠይቃል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተዘፍዝፎ የtiktok ፎሎዉ በመቁጠር ትምህርትን መጨረስ አይቻልም፡፡


ከታች ያለዉ ፁሁፍ በዝሙት መዘመን ስልጣኔ ወይስ የአለም ፍፃሜ በሚለዉ መፅሀፍ ከዛሬ 8አመት በፊት የተፃፈና የጥናት ፁሁፍ አቀርባለሁ...ዛሬስ ከ8ወይከ9አመት ቡሀላ የዚና ስልጣኔ መንገዶች በዝተዉ ዛሬ ላይ የዩኒቨርስቲ ዘመቻ በስንት ፐርንሰት ጨምሮ ይሆን??

╔══════════════════╗
        🎖 #ሐዋሳ_ዩኒቨርስቲ 🎖
╚══════════════════╝

«ዩኒቨርሲቲው ፆሙን ነው የሚያድረው፡፡» (ብሌን ሰይፈ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማጅመንት

ሄለን አለሙ የዩኒቨርስቲ ገመና በሚለዉ መፅሀፏ ሀሐዋሳ ዩኒቨርስቲ  ከተማረች ይሄንን ፅፋለች

‹‹ከዩኒቨርሲቲው ልጀምር፤ በተለይ ማታ ላይ ባዶ ይሆናል፡፡ ተማሪው ውልቅ ብሎ ይወጣል፡፡ ከዚህ ይልቅ ‹ዩኒቨርሲቲው ፆሙን ነው የሚያድረው የሚለው ቃል ይገልፀዋል፡፡ የቀን ተማሪ ከማታ ተማሪ ጋር ተቀላቅሎ በባጃጅ እየተጋፋ ይወጣል። የሚገርመው የማታ ተማሪዎች የባጃጅ እጥረት እየገጠማቸው ግማሽ መንገድ በእግር ለመሄድ ይገደዳሉ፡፡ ለቀን ተማሪዎች ያ ሰዓት የማምለጫ ሰዓት ነው የሚመስለው። ውልቅ ብለው ሲሄዱ ሴት ከወንዱ በጣም ብዛት አለዉ

   አንዳንዴ ትልልቅ የቤት መኪኖች ቆመው ሲታይ ሠርግ እየታጀበ ይመስላል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ የመኪና ኤግዚቢሽንም ሊመስል ይችላል፡፡ በርካታ መኪና ይቆማል፡፡ መኪኖቹ የሚቆሙት ተማሪ ጥበቃ መሆኑ ይታወቃል። ሆን ተብሎ እዚያ አካባቢ ሴት ተማሪዎችን ለመጠበቅ ይቆማሉ፡፡ ተማሪዎች የሚወጡበት ሰዓት ይታወቃል፤ ይቀጣጠራሉም፡፡

ተማሪዎችን የሚያሻሽጡ ደላሎችም አሉ፡፡ ደላላ የሌለበት ምን ነገር አለ? ያለ ደላላ ይሄ ነገር ሊፈጠር አይችልም፡፡ ለምሳሌ አንድ ሀብታም ዩኒቨርሲቲ መጥቶ ተማሪ ለመጥበስ ይጓተታል ማለት ዘበት ነው:: ቢሞከርም የሚሳካለት ከስንት አንዱ ነው፡፡ ይሄም ይሳካል ብዬ የማስበው አንዳንዴ ከግቢ በፀሐይ ትወጪና ባጃጅ ልታጪ ትችያለሽ፡፡ ያኔ ሊፍት ሲሰጥ የሚሄድ ተማሪ ሊኖር ይችላል፡፡ መጠባበሱም
ሊፈጠር የሚችለው በዚህ አጋጣሚ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ብዙ ነገር የሚጧጧፈው በደላላ ነው፡፡ ሀብታምም መጥቶ በር ሲቆም ያለቀ ነገር ይዞ ለመሄድ ነው፡፡ ልክ ተጠቅሎ እንደተቀመጠ የሱቅ ዕቃ እንጂ ገና ዋጋ አይደራደርም፡፡ ደላሎቹ ደግሞ ከውጭ ብቻ የሚመጡ አይደሉም፡፡ ከውስጥም (ከተማሪዎች) አሉ፡፡ የእነሱ የሱሳቸው የመሸፈኛ ገቢ የሚገኘው ሴትን ከሀብታሞች ጋር በማቃጠር ነው::


╔═══════════════════╗
     🎖 #አርባ_ምንጭ_ዩኒቨርሲቲ 🎖
╚═══════════════════╝


«የሴቶችና የወንዶች ዶርም በጣም ተቀራራቢ ስለሆነ ሴት ለማግኘት ድካም የለብንም፡፡»(ዳዊት ተስፋሁን፣ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒዉተር ሳይንስ ተማሪ)

«እንደ እንስሳ በየሜዳው የሚፈፅሙት ወሲብ ከአዕምሮ በላይ ነው የሆነብኝ (አዜብ ኃይሉ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዎሎጂ ዲፓርትመንት ተማሪ)

‹‹የካምፓስ ሕይወት ከባድ ነው፡፡ወደዛ ስንገባም ብዙ ነገሮች ይነገሩናል፡፡ተማሪ ጥሩም መጥፎም እንዳለ፣ ተማሪ በኤች.አይ.ቪ እንደሚያዝ፣ ከእንዲህ ዓይነት ልጆች ጋር አትግጠሚ፤ እንዳትበላሺ የሚሉና መሰል ምክሮች ከቤተሰብ ተነግሮኝ ነበር፡፡ ያኔ ምክሩን ባልንቅም ግን እውነት አይመስለኝም ነበር፡፡ነገር ግን ብዙ ነገር አየሁ፡፡ጥሩ የሚሆነው ግልፅ ካወራን ነው፡፡ ግልፅ እንነጋገር ከተባለ እዛው ሜዳው ላይ በግልፅ ወሲብ ይደረጋል፡፡ ወሲብ በጣም ከሚደረግባቸው ቦታዎች ውስጥ በጣም ከፍተኛው ስቴዲየም አለ፤ ኳስ ሜዳው ላይ ጨለም ሲል እዛ ሁሉም ተማሪ ወሲብ ያደርጋል፡፡
ከማስታውሰው ነገር አንዱን ልናገር፡፡አንድ ቀን እያጠናን ድንገት መብራት ይጠፋል፡፡አብራኝ ስታጠና የነበረችው የዶርሜ ልጅ ናት፡የሄደችውም እንደኔው ከአዲስ አበባ ነው፡፡እና ከዚህች ጓደኛ ጋር ስናጠና መብራት ጠፍቶ ወደ ዶርም ለመሄድ መንገድ ስናቋርጥ ድምፅ ሰማን፤ እያጠኑ ነው ብለን ነበር፡፡ነገር ግን እነሱ ወሲብ እያደረጉ ነው፡፡ የምሬን ነው! እረግጠናቸው ነው የተራመድነው፤ በጣም በጣም የሚያስጠላ እንደዚህ ዓይነት ነገር አለ፡፡ እኔ ይህ እንደ እንስሳ በየሜዳው የሚፈፅሙት ወሲብ ከአዕምሮዬ በላይ ነው የሆነብኝ፡፡ በየሜዳው ወሲብ ሲያደርጉ በጥበቃዎች ይያዘሉ፡፡»የላይኛዉ ምንጭ መፅሀፍ ገፅ 61


╔═════════════════╗
     🎖 #ባህር_ዳር_ዩኒቨርሲቲ 🎖
╚═════════════════╝

    

«በ2003 ብቻ 600 ተማሪዎች አስወርደዋል፡፡» (እየሩሳሌም ፍቃዱ - በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሊትሬቸር ተማሪ)

«እዚህ ገምቼ የሄድኩት ትምህርት ፈልጌ ነው፡፡ነገር ግን እዚያ ከሄድኩ በኋላ ብዙ ነገር አይቻለሁ፡፡ እኔ በነበርኩበት ጊዜ ግቢ ውስጥ በፀረ-ኤድስ ክበብ እሳተፍ ነበር፡፡ እዚያ ውስጥ ስታቶች ሲሰሩ አያለሁ፤ በዓይናችንም የምናየው አለ፡፡ ብዙ መጥፎ ነገሮች አሉ፡፡ በዚያው ልክ ብዙ ጥሩ ነገሮች አሉ፡፡

#ለምሳሌ እኔ ካየሁት ዉስጥ ባህርዳር ፓፒረስ የሚባል ትልቅ ሆቴል አለ፡፡ፈረንጆች ይጠቀሙበታል፡፡የግቢ ልጆች ስልክ ቁጥር ከሆላ የተፃፈበት ፎቷቸዉ ከዚያ ይገባል፡፡ልክ እንደ ካታሎግ፡፡የመረጣትን ደዉላችሁ ጥሩልኝ ይላል፡፡በዚህ መልክ ከትምህርት ባሻገር ሌላ ስራ ይሰራሉ ማለት ነዉ፡፡ግቢ ዉስጥ በ2003 ብቻ 600 ተማሪ ነዉ ያስወረደዉ፡፡በአንድ አመት ዉስጥ የተሰራ ስታቲክስ ነዉ፡፡ግቢ ዉስጥ የሚወልዱም አሉ፡፡👇👇👇
እኔ በአይኔ ሁለት ልጆች ወልደው አይቻለሁ፡፡»የላይኛዉ ምንጭ መፅሀፍ ገፅ 54

🔰 እቴጌ ገረመዉ ባዘጋጀችዉ የጭን መነባንብ በሚለዉ መፅሀፏ ገፅ 98 ላይ እንዲህ ብላለች

    «የኮሌጅ ተማሪዎች ድብቅ እውነታዎች ባሕር ዳር፦ የሀገራችን ተማሪዎች ከሚታሙባቸው የዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች ይማግጣሉ ከሚባሉት ከተማ እንደመሆኗ ለመታዘብ ቸኮልን፡፡ ወሲብ ንግድ ያጧጡፋሉ የተባለላቸውን ተማሪዎቻችን አመሸሽ ለመቃኘት የሚባለውን ነገር ለመታዘብ አንድ ቤት ከ30ደቂቃ በላይ መቆየት እያስፈልግም::ግን ይህን የሚያዩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ አፎን ከፍተው ሲመለከቱ ሊመሽብዎት ይችላል፡፡

  የአብዛኞቹን የሴት ልጆች አለባበስ የቡና ቤት ሴቶችም ሲሞክሩት የምንሸማቀብበት አይነት ነዉ፡፡እጆቻቸዉ እግሮቻቸዉ ሁሉ ሾል የበዛባቸዉ ናቸዉ፡፡ በአንድ እጅ ሲጋራ በአንድ እጅ ቢራ፣ መጨፈር፣ መጮኸ፤ በየሙዚቃዉ የሚያስጨፍሩት ወንድ መለያየት
ከሚያስጨፍሩት ወንድ ስልክ መቀበል፣ በሚያስጨፍሩት ወንድ አንገት ውስጥ መወሸቅ፣ በሚያስጨፍሩት ወንድ መተሻሸት፣ወዘተ ....እነዚሁ ሁሉ እጅግ አሸማቃቂ ድርጊቶች ናቸው፡፡ ይሄ ለእነሱ ጀብዱ ሁሉ የመሰላቸው ይመስለኛል፤ ያለማፈራቸውና ድንገት የሚያውቀኝ ሰው ቢመጣ ብለው ግራ ቀኝ ያለመገለማመጣቸው፡፡ ተመልካች ሆነው እንኳን ያፍራሉ፡፡ በተለይ እነሱን በማስተናገድ የሚታወቁት ቤቶችም ጢም ያሉ ናቸው:: እኛ ተማሪዎች የሚገኙበት ቤት ብለን እንደመጣን ሁሉ የመጡ ይሄኔ ስንት ይኖራሉ? በዚያ ላይ ጥሩ ዋጋ ያወጣሉ ሲሉም ሰማሁ፤ እንግሊዘኛ ይሞካከራሉና፡፡ የዚያኑ ያህል ሴቶቹ ከገንዘቡ ይልቅ የሚማርካቸው ግዳይ ጥለው ማደራቸው መሆኑ ይወራል፡፡



     ╔═══════════════╗
        🎖 #ዲላ_ዩኒቨርሲቲ 🎖
     ╚═══════════════╝

 
በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የሚስተዋሉ አጓጉል ወሲባዊ ባህሪያት (ዓባይነህ አናሾ እና ታረቀኝ ታደሰ የታተመ ጥናታዊ ጽሑፍ)

     እስካሁን እንደተገለፀው በዲላ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የሚታዩ ዋና ዋና አደገኛ ተያያዥ የወሲብ ባህሪያት እርስ በርስ ለወሲብ መነሳሳት።በአደባባይ መሳሳምና መተሻሸት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ያለ ኮንዶም ወሲብ መፈፀም፣ በርካታ የወሲብ ጓደኞችን ማፍራት፣ ያልተፈለገ እርግዝና፣ ማስወረድና ከሴተ አዳሪዎች ጋር መዳራት ናቸው፡፡

አደገኛ ወሲባዊ ባህሪይ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ላይ፣ በኮሌጆችና በዩኒቨርሲቲዎች፣ የ ኮሌጆችን ጨምሮ የሚስተዋል ነው፡፡



╔═════════════════╗
   🎖 #ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ 🎖
╚═════════════════╝

    

   ከአዲስ አበባ ከተማ 513 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘውና በ2010 እ.ኤ.አ ለ14ሺ ተማሪዎች የትምህርት ገበታ በዘረጋው ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ላይ የኤች.አይሺ ሥርጭትን የሚገመግም ጥናት ተካሂዶ በአቶ ታሪኩ ደንጌታ አማካኝነት ለሕትመት በቅቷል፡፡ በጥናቱ መግቢያ ላይ ከቤተሰቦቻቸው ርቀው በዩኒቨርሲቲ የሚኖሩ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ከሌሎች ወጣቶች በተለየ መልኩ ለኤች አይ.ቪ በሚያጋልጡ አደገኛ ድርጊቶች ላይ እንደሚሰማሩ ተገልጿል፡፡

⚡️⚡️በጥናቱ ላይ ከተሳተፉት ተማሪዎች ዉስጥ  
☞ 22.8% የሚሆኑት ወሲብን ለመጀመሪያ ጊዜ የፈፀሙት ዩኒቨርሲቲ ከገቡ በኋላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
☞ ወሲብ የመፈፀም ልምድ እንዳላቸው ከተናገሩት ወንድ ተማሪዎች ውስጥ ግማሽ ያህሉ ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር አንሶላ የሚጋፈፉ መሆናቸውን እራሳቸው አምነዋል፡፡
☞ እንዲሁም ኮንዶም በአግባቡ የማይጠቀሙት 60% መሆናቸው ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡

   ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሌሎች ወጣቶች በተሻለ ተምረዋል የሚባሉ ቢሆኑም ኮንዶም አለመጠቀምን ጨምሮ ሌሎች ጥንቃቄ የጎደላቸው ድርጊቶችን ሲፈፅሙ የሚስተዋሉ እነርሱ ናቸው፡፡ በተለይ ወሲብ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈፅሙ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ኮንዶም የመጠቀም ዝንባሌያቸው በእጅጉ ያነሰ ነው፡፡ የዚህ ምክንያቱ መደብር ጎራ ብለው ኮንዶም ለመግዛት ስለሚያፍሩ ነው፡፡

╔═══════════════════╗
    🎖 #አዲስ_አበባ_ዩኒቨርሲቲ 🎖
╚═══════════════════╝
      

እትጌ ገረመዉ የጭን መነባንብ ሌሎችም በሚለዉ መፅሀፍ ከገፅ44-45 ድረስ ስለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ይህ ሰፍሯል

   (ሊሊ!) እኔ የምልሽ! የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወንዶች እናንተ ጋ ሊዝናኑ አይመጡም? ሊሊ ይመጣሉ፤ ግን እነሱን ሌላ ቢዝነስ መፈለጊያ ነው የምንጠቀምባቸው፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከየት አምጥቶ ያወጣሻል? ማታ ቺቺኒያ አመሸሁ ለማለት ነው የሚመጡት፡፡ ለአልጋ መያዣ እንኳን ብር ስለማይተርፋቸው እስኪነጋ ድረስ ሲጨፍሩ ነው የሚያድሩት፡፡ እነሱን ለዳንስ ነው የምንጠቀምባቸው፡፡ በጣም አሪፍ ደናሾች ናቸው፡፡ ከነርሱ ጋር ሰትደንሺ የሚጎትትሽ አይጠፋም፡፡ ደግሞም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ቢኖረውም ማውጣት የለብሽም፤ አይፋቱሽማ፡፡ አንድ ቀን ካወጡሽ በቀን ሊያገኝሽ ይፈልጋል፤ ካልቃምን፣ ወደድኩሽ ምናምን እያሉ ይጃጃላሉ፡፡ስራ ቦታ በዚያ ምሸት ባዶ እጁን መጥቶ ውጭ አስጠርቶ እትት ሊል ይፈልጋል፡፡ አሁን አሁን ሁሉም ሴት ሰላወቀ ብር ቢኖራቸው እንኳን ማንም እሺ አይላቸውም፡፡»

በምን ታውቋቸዋላችሁ? ይለያሉ ማለት ነው? ልጅነታቸው፣ ሁለትና ሶስት ሆነው መምጣታቸው፤ አስሬ ብራቸውን እያወጡ መቁጠራቸው በአንድ ዕይታ ያሳልቀባቸዋል:: የሚጀምሩት በዳንስ መሆኑ መለያቸው ነው፡፡ እየደነሱ ሊገቡ ሁሉ ይችላሉ፡፡ ብታያቸው በዳንስ እና ስራችን የሆነ ቢዝነስ ማሯሯጫ በየቀኑ የምናስነካዉ እንኳን አንደርስባቸው ... የመጀመሪያ ጥያቄያቸው ፌስቡክ የለሽም? የፌስቡክ አድራሻሽን ስጪኝ ስለሆነ #ላይክ ነው የምንላቸዉ፡፡ካለ እነሱ አራዳ ያለ አይመስላቸዉም፡፡ነገ ከቤተሰብ ስለሚላከልኝ ለዛሬ ተቸገሪልኝ የሚለው ብዛቱ ቀላል እንዳይመስልሽ፤ ባለፈው ሳምንት እምቢ ብለሽው ተመልሶ እንደ ጫትና ሲጋራ ለዱቤ ጥየቃ ይንጓተትሻል፡፡ ዱቤ መጠየቅ ከልክል ነው ብለን እንነቀስላቸው እየተባለ ሙድ የሚያዝባቸው ናቸው:፡»”


  âœď¸âœď¸á‰ áŒĽá‰…ሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻችን ገመና ባጭሩ ከሞላ ጎደል እስካሁን ያየነውን  ይመስላል፡፡ የዩኒቨርሲቲዎች መብዛት ብቻውን ለምሁር መፍለቅ በቂ አይደለም፤ ምናልባትም ትምህርትን ለብዙኃን ለማዳረስ ካልሆነ በቀር፡፡ ልክ ዩኒቨርሲቲዎች የበዙትን ያህል ተማሪውን ከትምህርቱ የሚያግዱ ነገሮችም አብረው ይበዛሉ! ምናልባትም ከዚያ በብዙ እጥፍም ሊያድጉ ይችላሉ፡፡ በዚህን ጊዜ ተማሪው ከትምህርቱ ይታገዳል፡፡ ተማሪው ካልተማረ ደግሞ አስተማሪው አያስተምርም፡፡ ይህም በመሆኑም ተማሪው ትምህርቱን እንዲማር የተለያዩ ሥራዎች መሠራት አለባቸው:: በዚያው ልክ ተማሪውን ከትምህርቱ የሚያግዱ ነገሮችም እንዲጠፉ አብዝተው መሥራት ግድ ይላል፡፡


#በመጨረሻዉ_ክፍል
በዚና የተበከለ ትዉልድ የመጨረሻ ዉጤቱ
ጋብቻን ማዘግየትና ማጣጣል..የፍች መበራከት...እራስን የማጥፋት ወንጀሎች መበራከት በህብረተሰቡ ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ እንዳስሳለን


join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዉብ ቃሪዕ የቁርአን ግብዣ
ያዳምጡት ...ሼር አይዘንጉ

https://www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
          đŸ”° #የመጨረሻዉ_ክፍል
                  ✍አሚር ሰይድ


ዚና ላይ ያለ ትዉልድ መጀመሪያ የሚያጣጥለዉ ትዳርን ነዉ...ከቤተሰብ ጉትጎታ ወይም ጫና ያገባ ከሆነ ደግሞ ለፍች ይቸኩላል፡፡ በተጨማሪ በሀራም ላይ መዘዉተር የአእምሮ እረፍት ስለሌለዉ ራሳቸዉን የሚያጠፉ ወጣቶች ተበራክተዋል፡፡ይህ ሁሉ ዚና ያመጣብን መዘዝ ነዉ፡፡

╔═══════════════════╗
🎖 #ጋብቻን_ማዘግየትና_ማጣጣል🎖
╚═══════════════════╝



     ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአዳጊ ሀገራት ውስጥ ወጣቶች ወደ ትዳር የሚገቡበት አማካይ ዕድሜ ከ25-30 ዓመት ነው፡፡ ነገር ግን አንድ አዳጊ ወንድ በአማካይ በ16 ዓመቱ ለወሲባዊ ጉልምስና ይደርሳል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም በዚሁ ጊዜ ወሲባዊ ኃይሉ ጣሪያ ይነካል፡፡ አንዲት ሴት ደግሞ አሁን አሁን ባለው ጥናት ከ8 ዓመት አንስቶ ለአካለ መጠን ልትደርስ ትችላለች፡፡ ታዲያ በርካታ ወጣቶች ይህንኑ ስሜታቸውን የሚያስተናግዱት የወንድ ወይም የሴት ጓደኛ በመያዝና ዝሙትን በመፈፀም ነው፡፡
#ለምሳሌ የሀይስኩል ተማሪዎችን ብናይ በአንድ ክፍል ውስጥ የወንድ ጓደኛ የማይኖራቸው ጥብቅ ሴቶች ከአስር አይበልጡም፡፡ ይህም ዝሙት ምን ያህል እንደተስፋፋ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡

✨✨ ሌላው ሴት የኮሌጅ ተማሪዎች ዘንድ የወንድ ጓደኛ መያዝን ማበረታታትና ትዳርን ማጣጣል እየተለመደ መጥቷል፡፡ ሴት ሙስሊም የመንግስት ሰራተኞች ዘንድም ይኸው ችግር እየተወራረሰ ይገኛል፡፡ ሁሉንም የሚያመሳስላቸው ነገር ደግሞ ቦይፍሬንድ መያዝን እንደ ጤናማ የህይወት ልማድ ማየታቸው ነው፡፡ በእውነቱ ይህ ትልቅ ውድቀት ነው፡፡ ለዝሙት መስፋፋትም ትልቁን አስተዋፅኦ እያበረከተ ያለው ይኸው ቦይ-ገርልፍሬንድነት ነው፡፡ ደዌው ወደ ሙስሊሞችም ተጋብቷል፡፡





         ╔════════════╗
          🎖  #የፍቺ_መበራከት🎖
         ╚════════════╝



   በሙስሊሙ ማህበረሰብ መካከል የፍቺ መበራከት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረና ከባድ ቀውስን እየፈጠረ ያለ አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በቅርቡ በተገኘው አንድ መረጃ እንኳን ከ14 ትዳሮች መካከል 12ቱ ሶስት ወር ሳይሞላቸው ፈርሰዋል፡፡ ይህ በውነቱ በጣም አስደንጋጭ ነው፡፡ አንዳንዶች ሙስሊሙ ወጣት ወደ ትዳር ሲቻኮልና በከተማዋም የሙስሊም ሰርግ በዝቶ ሲያይ ይደሰት ይሆናል፡፡ ግና በዚያው ልክ የሚፈርሱትን ትዳሮች ቢያይ በእጅጉ ያዝናል፡፡ ሙስሊሙ ወዴት እየሄደ ነው? በሚል ሀሳብም ይባዝታል፡፡ ለፍቺ መበራከት ትልቁ መንስኤ ደግሞ የተጋቢዎች ከትዳር በፊት በየፊናቸው የሚፈጥሩት ፆታዊ ግንኙነትና ዝሙት ነው፡፡

እንደሚታወቀው ከትዳር በፊት በርካታ ወጣቶች በቦይ–ገርል ፍሬንድነት (በወሲብ አጋርነት) አብረው ይቆያሉ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ አብረው የሚቆዩቱ ግን አብዛኞቹ ግንኙነታቸው በጋብቻ አይቋጭም፡፡ ከዚህም የተነሳ ሁሉም በየፊናው ሌላ የትዳር አጋር ፍለጋ ይሄዳል፡፡ ግን ከዚህ በኋላ የሚመሰርቱት ትዳር ስኬታማ የመሆን ዕድሉ በጣሙን ዝቅተኛ ነው፤ ምከንያቱም ከትዳር በፊት ያለውን የወሲብን ሕግ ያላከበረ ከትዳር በኋላም ይህንኑ ልማዱን ይደግመዋልና ነው፡፡ ከዚያም ሁለቱም በየፊናቸው ሂያጅነትን ይጀምራሉ፡፡ ሂያጅነት ወደ ትዳራቸው ሲገባ ደግሞ ትዳሩ ወዲያው መናወጥ ይጀምራል፡፡ ቤቱ መረጋጋት ይሳነዋል፡፡ በውጤቱም ፍቺ ወሃን የመጠጣት ያህል ይቀላቸዋል፡፡ ከዚያም ወጣቱ « #ኒካህሽን_እንቺ››፣ «ትሄጃለሽ ወይስ ታድሪያለሽ በሶስት ፈትቼሻለሁ ወዘተ እያለ ትዳርን መቀለጃ ያደርገዋል፡፡ይህም ችግር ስራ የሰደደና ትልቅ ማህበራዊ ቀዉስን ፈጥሯል፡፡

እኔ ብዙ ለትዳር የደረሱትን ለምን አታገቡም?ትዳር ሲመጣላችሁ ለምን ትመልሳላችሁ?ብየ ስጠይቅ የብዙዎች መልስ ከተጋባን ቡሀላ ቢፈታንስ እያሉ በጓደኞቻቸዉ የደረሰዉን የፍች ታሪክና ሳይፋቱ ደግሞ ሴቶች ባለቻቸዉ ጋር እየኖሩ እንደሆኑ በማስረጃ ነግረዉኛል፡፡የፍች ስታቲክስ በየአመቱ የሚያሳየዉ በብዙ እጥፍ እንደሆነ ነዉ፡፡ደግሞ የሚገርመዉ በፍች ብዛት የሚያሳየዉ ሙስሊም ማህበረሰብ ቀዳሚ መሆኑ ነዉ፡፡



╔══════════════════════╗
  🎖 #እራስን_የማጥፋት_ወንጀሎች_መበራከት
╚══════════════════════╝




    ጥናቶች እንዳመለከቱት ዝሙትና እራስን የማጥፋት ወንጀሎች የተቆራኙ ናቸው፡፡ በተጨማሪም እነዚያ በወሲብ ንቁ (አክቲቭ) የሆኑ ልጆች ከነዚያ እስከ ኒካህ ድረስ ወሲብን ከመፈፀም ከሚታቀቡት ይበልጥ ከሁለት ጊዜ እጥፍ በላይ በጭንቀት የመወረር ዕድላቸው ከፍ ይላል፡፡ ጥናቶቹ አያይዘውም እንደጠቆሙት እነዚያ በወሲብ ንቁ የሆኑ አዳጊ ወንዶች ከአስር ጊዜ እጥፍ በላይ እራሳቸውን የማጥፋት ሙከራን ያደርጋሉ፡፡

📌 #ሴቶችን_በተመለከተ ደግሞ እነዚያ ከጋብቻ በፊት ወሲብ የሚፈፅሙ አዳጊና ወጣቶች ሴቶች ከነዚያ ከማይፈፅሙቱ ሶስት እጥፍ እራሳቸውን ለማጥፋት ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ እንግዲህ የዝሙት ዋጋ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ተመልከቱ፡፡ የዝሙት ፈጣን ዋጋው ሴሰኝነት ነው፡፡ ሴሰኝነትን ተከትሎ ደግሞ ከበሽታ ባሻገር ጭንቀት ብቅ ይላል፡፡ ጭንቀት ደግሞ ራስን ለማጥፋት ትልቅ መንስኤ ነው፡፡ ታዲያ ከዚህ በኋላ ምንድነው ይሆናል ብለህ የምትጠብቀው? አዎን! ጭንቀት እራስን ለማጥፋት ትልቁ መንስኤ ነው፡፡


✏️✏️ #ራስን_ማጥፋትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ውስጥ ከሁለት ዓመታት በፊት በእስጢፋኖስ አበራ የተዘጋጀና በጥልቅ የዳሰሰ ጥናት የተደገፈው መጽሐፍ ላይ እንድ አስደንጋጭ እውነታን ቀርቧል፡-

ለምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ነገር ግን የነገሮች ግጥምጥሞሽ ሁሌም ያስደነግጠኛል፡፡ የነገሮች ግጥምጥሞሽ ሁሌም ያስጨንቀኛል፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ ተመሳሳይ ነገሮች በአንድ ጊዜ ሲከሰቱ ሳይ በጣም እረበሻለሁ፡፡ ለምን እንዲህ ሆነን ብዬም እራሴን ደጋግሜ እጠይቃለሁ፡፡ መልስ ፍለጋም እራሴን ብዙ ጊዜ አስጨንቃለሁ፡፡ መልስ እስከማገኝ ድረስም ስለተፈጠረው ጉዳይ ጊዜ ሰጥቼ ማሰብ እና ማሰላሰል እጀምራለሁ፡፡»የሚል አካቷል

በተጨማሪ የመፅሀፉ ርዕስ «ውስጠ አዋቂ - ከአዲስ አበባ ጓዳ እስከ አደባባይ.. የተሰኘ ሲሆን እራስን ማጥፋት ሌላኛው የአዲስ አበባ ፋሽን፡ በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር በአዲስ አበባ እራስን የማጥፋት ወንጀል በወጣቶች ዘንድ እጅጉን መጨመሩን ይገልፃል፡፡


✏️✏️ #ወደ_ሙስሊሞች_ስንመጣ ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ከኮልፌ መስጂድ ኢማም በመስጊድ ሲናገሩ እንደተሰማው እራስን የማጥፋት ወንጀል ተበራከቷል፡፡ እንደሚታወቀው በተለምዶ ኮልፌ አዲሱ መስጂድ ጀናዛ ሶላት በብዛት ይሰገዳል፡፡ በዚህም መነሻነት ለኢማሙ የሰዎችን አሟሟት አስመልከቶ በርካታ መረጃዎች ይደርሷቸዋል፡፡ የሟቾችን ሁኔታ ሲጠይቁ እራሳቸው ያጠፉ ወጣቶች እንደሚገኙባቸው ይነገራቸዋል፡

የወንጀል መጨረሻዉ ይሄ ነዉ መፍትሄዉ ከዝሙት መራቅ በዝሙት መስመርም ያለ እንደ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት ቶብቶ አልቅሶ ከወንጀል ፀድቶ አዛኝ ረሂም ለሆነዉ ጀሊሉ እጅ መስጠት ነዉ፡፡ በዝሙት ላይ እገፋለሁ ያለ ምርጫዉ በእጁ ነዉ በዱንያ ደስታ ማጣት የእርዚቅ መገፋት እና አሏህ እንዳለን ለወንጀለኞች ብርቱ የሆነ ቅጣት ይጠብቃቸዋል እንዳለዉ የአሏህን ቅጣት እወጠዋለሁ ጀሀነም ይሻለኛል ያለ ምርጫዉ በእጁ ነዉ፡፡👇👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሚያምር ድምፅ የጁምአ ግብዣ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
⚡️ #ከአንበሳ_ጋር_የተናነቀው_ሙጃሂድ
            ✍አሚር ሰይድ

ሙስሊሞች እና የፐርሽያን ወታደሮች የሠይፍ ትንቅንቅ ቢያደርጉ ሁለቱም በተንጣለለ ሜዳ ላይ ተሰልፈዋል። ከሁለቱም በኩል የሚታየው ትዕይጓት ያስፈራ።

ግጥሚያው ከመጀመሩ በፊት ሁለቱም ቡድኖች ተርታቸውን ይዘው ለጥቂት ደቂቃዎች ከፎከሩ በኋላ ያለምንም ማስጠንቀቅያ ፐርሺያኖቹ የጦር አንበሳቸውን ወደ ሙስለሙ ቀጠና ሰደዱ።

ድልብ አንበሳውም የፐርሺያኖቹን ሠልፍ ሰንጥቆ እየጋለበ ወደሙጃሂዶቹ ሠልፍ መገስገስ ጀመረ። ይህን የተመለከተው ጀግና የሙስለሙን ሠልፍ ሰንጥቆ በመውጣት አንበሳውን ሊጋፈጥ ወደሱ አቀና። ይህ ሲሆን የሁለቱም ሠራዊቶች ትዕይንቱን በዝምታ እየተከታተሉ ነበር። ይህ ጀግና አካሄዱ አንበሳው ሊጋፈጠው ሳይሆን አሱን አጓበሳውን የሚጋፈጥ ነበር የሚመስለው።

አንበሳውም አየጋለበ ሙጃሂዱም እየሮጠ እኩል ሜዳ ላይ ተፋጠጡ። ብልህ ጀግና ነበርና በአንበሳው ጀርባ ላይ  በመውጣት ከላዩ ቁጭ ብሎ በሠይፋ ይቆራርጠው ጀመር። በመጨረሻም አንበሳውን ገድሎ ወደ አጋሮቹ ተመለሰ።

ይህን የተመለከቱ የፐርሺያ ሠራዊቶች አንበሳ ከማይፈሩ ህዝቦች ጋር መጋፈጥ ቢከብዳቸውም ሰልፉን ትተው ከመሸሽ መጋፈጥን መርጠው በሙጃሂዶች የሠይፍ እራት ሆነው አደሩ። ሙስሊሞች ድልን ተጎናፀፉ። በጊዜው የጦር አዛዥ የነበረው ጦርነቱ ከተረጋጋ በኋላ አንበሳውን ወደ ገደለው ጀግና በመሄድ ግንባሩን ሳመው።

ያ ጀግናም ከፈረሱ ወርዶ ዝቅ በማለት የጦር አዛዡን በመሳም፦ " ያንተ ዓይነቱ የኔን ግንባር ሊስም አይገባም” ብሎ ኢስላማዊ መተናነስን በታሪክ መዝገብ ላይ አሰፈረልን። ይህ ጀግና ስሙ #ሐሺም_ኢብኑ_ኡትባ ይባል ነበር።

"አናንተ መኖርን አንደምትወዱት መሞትን የሚወዱ ህዝቦችን ይዤላችሁ መጣሁ" በማለት የተናገረው ኻሊድ አብኑል ወሊድ ያለ ምክንያት አልነበረም!

ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንድ ፓስተር በነብዩ ﷺ እና ሙስሊሞችን በምሳሌ በመጥቀስ እንዴት አማኞችን እንደሚያተምር ይመልከቱ

join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_pubIlic_group
  #እናቴ_ሆይ_የክብር_ሞት_ነዉ_የሞኩት_እንዳታለቅሺ 😔


      ✍አሚር ሰይድ

     ትውልደ ኢራናዊት የግራፊከስ ባለሙያ፣ ሱናን የምትከተል ፅኑ ሴት ናት። ሪሐና ጀባሪ ትሰኛለች። አንደ አውጳውያን የዘመን ቀመር በ2007 የቀድሞው የኢራን ባለሥልጣን የቤቴን የውስጥ ክፍል ባማረ ዲዛይን እንድትነድፊልኝ አፈልጋለሁ በማለት ወደ ቤቱ አስጠራት። በአፓርታማው ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ሒጃቧን ገፎ ሊደፍራት ሞከረ።

የሺዐ አምነት ተከታይ ነበርና በእሷ የሱና አቋም እየተበሳጨ "አንቺ የአላህ ጠላት አንቺ ሴተኛ አዳሪ" አያለ የሱሪውን ዚፕ በመክፈት በኃይል መሬት ላይ ሲዘርራት ወደፊት ተጠጋት። በዚህ ጊዜ ነበር ከቦርሳዋ የማይለያትን ስለታማ ቢለዋ መዛ ደረቱ ላይ የወጋችው። ክብሯን ለማስጠበቅ የሰነዘረችው ስለት ሰውየውን ከአፈር ቀላቀለው።

የሺአ እምነት ተከታይ ብሎም የቀድሞ ባለ ስልጣን የነበረን ሰው ሱንይ የሆነች አንዲት ሴት ገደለችው ይህ የተቀነባበረ ሴራ ነው በሚል ተይዛ በኮሀርዳሽት፣ በፋሻፋዬ፣ በአቪጓ፣ በሻህር-ሬይ፣ በራሚን እና በቴህራን ታላቁ አሥር ቤት አየተዘዋወረች ሰሰባት ተከታታይ ዓመታት ማቀቀች።
....ዳኛ ፊት ቀርባ “ለምንድነው የገደልሽው??" ሲል ጠየቃት

“ከክብሬ ለመከላከል ሰሒጃቤ ዘብ ለመቆም” ስትል መለሰች
....ትኩር ብላ የዳኛውን ዓይን እየተመለከተች።

"የሰው ነፍስ ለማጥፋት ይህ በቂ ምክንያት አይደለም" አላት።
..... የሚጉረጠረጡ ዓይኖቿን ፍጥጥ አድርጋ
“ልክ ነህ ለእንዳንተ ዓይነቱ ክብር ሸረፍ ለሌለዉ ሰው ይህ በቂ ምክንያት አይደለም። ክብርህን ስለሸጥክ ምንነቱን አታውቀውም"
.....አለችው የሞት ፍርድ ተወስኖባት ወደ መሰቀያዋ ገመድ እየተራመደች “ #እናቴ_ሆይ የክብር ሞት ነውና የምሞተው አንዳታለቅሽ😔 አንዳታዝኒ” እያለች በ2014 አንገቷ ከገመዱ ገብቶ ተሸመቀቀች።

አላህ በእዝነቱ ይቀበላት!

⚠️የአሁን ዘመን ያለን ሴቶች አስተካክለን ሂጃብ የማንለብስ  ነገ የዉመል ቂያማ ስንቀሰቀስ ለእስልምና ለሂጃባቸዉ ዋጋ የከፈሉ እንስቶች ጋር እንዴት አብረን እነሱ ጎን እንቆም ይሆን??
እስልምና በወንድ በሴት ሸሂዶች ደም ዋጋ ተከፍሎበታል...እኛስ ለእስልምና ለሂጃብ ምን ሰራን???

ምንጭ_ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ

ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ከኢማኒያን ለሙስሊም የተጠየቀ ጥያቄና ሙስሊሙ የሰጠዉ ምላሽ


www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  #ስለሒጃብ_የተከፈለ_መስዋዕትነት
         ✍ አሚር ሰይድ

ይህ ለሒጃባ ስትል የተሰዋችው ለጅልባቧ ስትል የሞተችው የአንደሉሷ ሙስሊም ሴት እውነተኛ ታሪክ ነው። ከስላና ተቃጥላ ስሰሒጃብ ስለክብሯ የወደቀች ድንቅ ሴት! ታሪኳ ሲደመጥ የብዙዎች ቀልብ አንብቷል። ስቃያቸው በስቃይዋ ተደምጧል። በሒጃባቸው ክብር ያልሰጡ አንስቶች ይገሰፁበት ዘንድ ታሪኳን እነሆ

ክስተቱን በአንደበቷ አንዲህ ትተርከው ይዛለች።

“የትውልድ ቀዬዬ አንደሉስ ምድር ነው። በሃያዎቹ የዕድሜ እርከን ውስጥ የምገኝ በሰውነት ቅርጼ ሞላ ደልደል ያልኩ ለግላጋ እንስት ወጣት ነኝ። ግና ይህን ሰውነቴን በጀልባብ ሸፍኜና ጠብቄ ሒጃቤን በአግባቡ እለብሳለሁ። የአንደሉስ ሙስሊሞች የስቃይን ፅዋ በመስቀላዊያኑ እጅ ሲጎነጩ እኔም አልቀረልኝም። ለሁለት ዓመታት የለበስኩትን ጅልባብ ሳላወልቅ ሳላጥብና ሳልቀይር እሥር ቤት ከረምኩ። በወታደሮች ግልምጫና ድብደባ መደፈርና መወገር ብዙ መከራዎችን አሳልፌ የመጨረሻዋ ቀን ላይ ደረስኩ።

    የለበስኩት ጅልባብ ተሰብስቦ ጉልበቴ ጋር ደርሷል። ሰውነቴ በጭቃ ተለውሶ በእግረ ሙቅ ተጠፍሬያለሁ። እጄ የፊጥኝ ታስሮ አንገቴ ላይ በጠለቀው ሰንሰለት እየተጎተትኩ ወደፊት አነዳ ይዣለሁ። በብረት ፍርግርጉ ኋላ ሳልፍ ታሳሪዎቹ በሾሉ ዓይኖቻቸው አፍጥጠው እየተመለከቱኝ የስድብ ናዳ አወረዱብኝ ተፉብኝ። አፈር እየበተኑ ድንጋይ ወረወሩብኝ። የእሥር ቤቱ ጠባቂዎች ጅራፍ በእጃቸው ይዘው ከበቡኝ።

ቀሳውስቱ በአንድነት ቆመው መዝሙራቸውን ያሰማሉ። ባለሥልጣናትና ግብዣ የተደረገላቸው እንግዶች በክብር ወንበራቸው ላይ ተቀምጠው በሚደርስብኝ ስቃይ ለመደሰት ወደ እኔ በትኩረት ይመለከታሉ። ከአንድ ግንድ ጋር ታስሬ ማገዶ በዙርያዬ ተበትኗል። ዘይትና ጋዝ ተርከፍክፎበታል። ከቀሳውስቱ አንዱ ወደእኔ ተጠጋ። ሁለት ምርጫ አቀረበልኝ። ጀልባቤን አውልቄ በህዝብ ፊት ይቅርታ እጠይቅ ዘንድ ዓለይያም ተቃጥዬና🔥🔥ሰውነቴ ነዶ በመሞት መካከል ምርጫ ሰጠኝ። ሒጃቤን እንጂ ሌላን አልመረጥኩም። ከፈለጋችሁ አቃጥሉኝ አልኩ ስለሒጃቤ መሞቴ ለኔ ክብር መሆኑን አላወቁም። አልንበረከክም ፈፅሞ የጌታዬን ትዕዛዝ አልጥስም ብትፈልጉ ሰውነቴን ቆራርጡት በያሻችሁም አካሌን አንድዳችሁ አክስሉት። አዎ! በፍፁም በሒጃቤና በክብሬ አልደራደርም። የክብር መገለጫዬ በከፍታ የሚውለበለብ አስላማዊ ዓርማዬ ነው ብዬ መለስኩለት።

ቄሱ የእሳቱን ነበልባል አንስቶ እንጨቱን ለኮሰው። ሰውነቴ መቃጠል ጀመረ። በቀላሉ አንድሞት አልፈቀዱልኝም እሳቱን አጠፋዉ ። ወደ እሥር ቤቱ ወሰዱኝ። ይህ የእሥር ቤቱን አጥር ተደግፌ የፃፍኩት እውነተኛ ታሪኬ ነው

#ይህን ማስታወሻ የአስር ቤቱ ግርግዳ ላይ አስፈራው ተገኝ፡፡  አጀብ ለአኛ ክብር ስንቶች አልቀዋል።

በጋታው ጠዋት በተመሳሳይ ቦታ የፊጥኝ ታስራ ተሰቃይታ በእሳት ነደደች። ዛሬ ግን አንደ ትላንቱ አላጠፉላትም። ለዓመታት የኖረችበት ስቃይ እነሆ አበቃ። ግን ነፃነቷን አንደሰጧት አላወቁም።

#አላህ መልካም ስራዋን ተቀብሎ ቀብሯን ኑር ማረፊያዋን ፊርደውሰል አዕላ ያድርግባት።

⚠️የአሁን ዘመን ያለን ሴቶች አስተካክለን ሂጃብ የማንለብስ  ነገ የዉመል ቂያማ ስንቀሰቀስ ለእስልምና ለሂጃባቸዉ ዋጋ የከፈሉ እንስቶች ጋር እንዴት አብረን እነሱ ጎን እንቆም ይሆን??
እስልምና በወንድ በሴት ሸሂዶች ደም ዋጋ ተከፍሎበታል...እኛስ ለእስልምና ለሂጃብ ምን ሰራን???



#ምንጭ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ



join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትዳር ማለት ምን ማለት ነዉ፡፡
ትዳር መስፈርትስ?ከአገቡስ ቡሀላ

ደስ የሚል ለአገቡም ላላገቡም መጠነኛ የሆነ ትምህርት👌

join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
ጋ *ዛ

የ 8 አመቱ ህፃን Zain Mhanna እናቱ ከሞተች 2 ወር ጀምሮ ማታ ማታ ሄዶ ቀብሯ ላይ ይተኛል።😢

"ቀብሯን ሄጄ አቅፌ ስስመው እሷ ጋር በአካል የተገናኘሁ ይመስለኛል ወዲያው ልቤ ውስጥ ሰተት ብላ ትገባለች ይላል።

የጋዛው ጋዜጠኛ Saleh Al-Jafarawi በ Instagram አካውንቱ ባጋራው መረጃ መሠረት የልጁ እናት ሸሂ ድ የሆነችው ጋ *ዛ Nuseirat camp ላይ በተፈፀመ የእስራ *ል አየር ጥቃት ነው። እናቱ ሸሂድ ከሆነችበት ቀን ጀምሮ ህፃኑ አንድም ቀን ማታ ላይ ቀብር ከመዘየር ቀርቶ አያቅም ይላል።

ጋዜጠኛው ማታ ላይ በዚ ጨለማ በዚ ከባድ የአየር ድብደባ ብቻህን ሁልጊዜ እዚ ስትመጣ ጨለማና ቦምብ አትፈራም ወይ? ብሎ ህፃኑን ጠይቆት ነበር።

ህፃኑ ሲመልስ_ እኔ በዚች ምድር ምንም ምፈራው ነገር የለም። እናቴ በጣም ትናፍቀኛለች😔 እሷ ጋር መሄድ እፈልጋለሁ ሲል መልሶለታል።

ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎖🎖ቢስሚላህ ብሎ የመጠጣትና የመብላት ጥቅሞች፡፡ነብዩ ሰዐወ ከ1400 አመት በፊት የተናገሩትን በዚህ ዘመን ሳይንቲስቶች ያረጋገጡት እዉነታ

join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
        #ዞምቢ
   ✍ አሚር ሰይድ

የቦሊዩድ ሲኒማዎች ዞምቢ ማለት የሙታን መንፈስ እንደሆነ አድርገው በመሳል ልጆችን ያስፈራሩበታል። ግን እሱ በብራዚል ታላቅ ስብዕና ያለው ኢስላማዊ መንግሥትን የመሰረተ ሙስሊም ንጉሥ ነው። ውልደቱ በአፍሪካ እምብርት፣ አትበቱ የተቀበረው በኮንጎ ምድር ነው። በጀግንነቱ ምክንያት ዞምቢ ጋጓጋ ብለው ይጠሩታል ጥቁሩ ደፋር እንደማለት ነው።

    በ 17 ክፍለ ዘመን ፖርቹጋል በኃይል የባሪያ ፍንገላ ዓለምን ያሸችበት ወቅት ነበር። በተለይ ከምእራብ አፍሪካ ወደ ብራዚል የሚጋዙ ባሪያዎች በርካታዎቹ ሙስሊሞች ነበሩ። የባህር ዳርቻዎችን በማጥቃት ሙስሊሞችን ማርከው በመርከቧ የታችኛው ክፍል በሚገኙ እስር ቤቶች ውስጥ ያጉራቸዋል። የጉልበት ሼል እንዲሰሩና ክርስትናን አንዲቀበሉ ያስገድዷቸዋል።

ከእነዚህ ሰዎች መሐል አንድ ወጣት ጦረኛ ተፈጠረ። ጀግናችን “ #ዞምቢ” ሰዎችን ወደ ትክክለኛው እምነት ወደ አስልምና ሳይሰለች ሳይታክት መጣራት ጀመረ። ተከታዮቹ ሲበዙ ከባርነት ቀንበር አምልጠው ጂሃድ አወጁ። የኢስላምን ጠላቶች ማጥቃት ጀመሩ። እስልምና በብራዚል መስፋፋቱ የእግር አሳት የሆነባቸው መስቀላዊያኖች እርሱንና ጓደኞቹን ለማጥፋት ተባበሩ፡፡ ለተከታታይ አስር ዓመታትም በርካታ የመስቀል ጦርነቶች ተደረጉ። በየመስኩ ተደጋጋሚ

ሽንፈቶችን አከናነባቸው፡፡

    ሾር መሰረቱ የኮጓጎ ንጉሳዊ ቤተሰብነት የነበረው ይህ ሙስሊም ወጣት ዞምቢ ዶስ ፓልማሬስ ይሰኛል። በተዋጣ አስላማዊ ዲሲፕሊን፣ በቆራጥ ተፋላሚነቱ የሚደነቀው ይህ ጀግና በሀያዎቹ አድሜው በብራዚል የሙስሊሞች ግዛት Quilombo dos Palmares ንጉሥ መሆን ቻለ። ኢስላማዊ መንግሥትንም በይፋ አወጀ። በቆዳ ስፋቷ ፖርቹጋልን የሚስተካከለው የዞምቢ ግዛት ህዝቡ በፍፁም ኢስላማዊ መንፈስ ይታዘዘው ጀመር።

የዞምቢን ኃያልነት ያስተዋሉት የኢስላም ጠላቶች በእነሱ አስተዳደር ስር ሆኖ በነጻነት አንዲኖርና ለሌሎች አፍሪካውያን ሙስሊሞች ነጻነት አንዳይታገል ጠየቁት። ለሌሎች ሙስሊም አፍሪካውያን አገዛና እርዳታዬን አልነፍጋቸውም በማለት የፖርቹጋሎቹን ጥያቄ ውድቅ አደረገ። በዚሁ ወደ ግልፅ ጦርነት ገባ።

#ሙላቶ በተባለው የጦር መሪው የተከዳው ዞምቢ በአውሮጳውያን አቆጣጠር ኖቬምበር 20/1695 በፖርቹጋሎች ቁጥጥር ስር ዋለ። ሰውነቱን ጭንቅላቱንና የአካል ክፍቹን በጭካኔ ቆራረጡት😔። ተከታዮቹን በባርነት ሰጧቸው። ዞምቢ ጋጓጋ ምንም ታሪክ አንዳይኖረው ተደረገ። በብራዚል የሰፈሩ አፍሪካውያን ሙስሊሞችን በኃይል የካቶሊክ ኃይማኖትን አንዲቀበሉ አደረጓቸው።

ዞምቢ ምንም ያህል ለብራዚል ክብር የወደቀ ስለ ሙስሊም ወንድሞቹ የተፋለመ ጀግና ቢሆንም ኢስላማዊ ማንነቱ የጎረበጣቸው ብራዚላዊ ፀሀፊዎች በልብወለድ ታሪኮቻቸው ላይ አንደ አስፈሪ ፍጡር ስለዉ ይፅፉት ጀመር። ከ1968 ወዲህ በሆሊውድ የሚሰሩ አስፈሪ ፊልሞች ሁሉ የዞምቢን ስም እንደገፀ ባህሪ በመጠቀም በብዙ ሚለዮን ኮፒዎች ተቸበቸቡ።

በኢስላም ታላቅ መስዋዕትነትን የከፈለው አፍሪካዊው የላቲን አሜሪካ እንቁ ታሪኩን ለማድበስበስ የተጠቀሙበት መንገድ ዛሬም በሌሎች ሙጃሂዶች ላይ እየተጠቀሙና ስም እያጠፋ ነውና በቀደዱልን ቦይ አንፍሰስ ለማለትም ነው።

ምንጭ ☞ታሪኮችን ተርክላቸዉ መፅሀፍ


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፍልስጤም ጋዛ የልጆች ለቅሶ የምግብ የዉሀ ችግር ጫማ የሚለብሱት እስኪያጡ ድረስ

ለቅሷቸዉ ልብ ይነካል😔


ያኢላሂ ድረስላቸዉ😔


join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
   ታዋቂው አሜሪካዊ ዳዒ ሼህ ኻሊድ ያሲን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦"እናቴን ወደ ኢስላም ለማስገባት 35 ዓመት ዳዕዋ አድርጌላት አሻፈረኝ አለችኝ፣በመጨረሻ ግን በባለቤቴ እጅ ኢስላምን ተቀበለች፣ ባለቤቴ ዉዱዕ ትጥበት ታደርግላታለች ትንከባከባታለች።"

ሴትነት ማለት ይህ ነዉ❤️

  ሼህ ኻሊድ ያሲን ለብዙ ሺህ አሜሪካውያንና አውሮፓውያን መስለም ትልቅ የሒዳያ ሰበብ ነበሩ፣በመላው ዓለም በሳቸው ዳዕዋ በመማረክ የኢስላምን ብርሀን ያገኙ በሺዎች ናቸው።
አላህ ይቀበላቸው ይጠብቃቸው።

join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
2024/11/16 11:45:52
Back to Top
HTML Embed Code: