Telegram Web Link
 
╔══════════════════════╗
🌟 #የሙስሊም_ወላጆች_ምሬት_ከጊዜ
            #ወደጊዜ_መጨመር
╚══════════════════════╝
  ብዙ ወላጆች የሚነቁትና የሚባንኑት ልጆቻቸው ጉዳት ላይ ከወደቁና መዘዙ ከተረፋቸው በኋላ ነው፡፡በተለይ ያሁኑ ወላጆች በቢዝነስና በዱንያዊ ጉዳዮች ስለሚጨናነቁ ለልጆቻቸው ተገቢውን ትኩረት አይሰጡም፡፡ ከዚህም የተነሳ አዳጊ ልጆች ምንም እንኳን ወላጆች አጠገብ ሲሆኑ ጨዋ ቢመስሉም ዳሩ ግን ደጅ ብዙ ሱስና ፀያፍ ነገሮችን መልመዱንና ማዘውተሩን ተያይዘውታል፡፡በተለይ አዳጊ ሴት ልጆች ለበርካታ ፈተናዎች እየተጋለጡ ይገኛሉ፡፡ ከሰፈር ጎረምሳና ምራቁን የዋጠ ዘልዛላ ወንድ አንስቶ፣በትምህርት ቤት፣በመጓጓዣ ላይ፣ የወሲብ ደላሎች ውትወታ ሰለባ መሆን፣ በየመዝናኛ ስፍራው ለተለያዩ ወሲባዊ ትንኮሳዎች፣ ወዘተ የመጋለጥ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ታዲያ በዚህ ላይ የወላጆች እንዝላልነት ከታከለበት መዘዙን አያድርስ ያስብለዋል፡፡

ነገሮች እኛ ከምንገምታቸው በላይ በፍጥነት ይቀናጃሉ፡፡በተለይ በሱስና በብልግናው መስክ ሁሉ ክስተት ቅፅበታዊ ሆኗል ማለት ይችላል፡፡

#ለምሳሌ በአንድ አጋጣሚ ብቻ ከሱሰኛ ጓደኛዋ ጋር ወደጫት መቃሚያና ሺሻ ቤት ጎራ ያለች አንዲት ያልተነካካች ሴት በአንድ ጊዜ ሙዷ ሁሉ ተቀያይሮ ይህቺ ምንም አልተነካችም የምትባለው ልጅ ከሌሎች ጋር ለመመሳሰል ስትል ዓይን አውጣ ሆና ልትገኝ ትችላለች፡፡አንዴ እዚያ ከገባች በኋላ የፈለገችውን ያህል ጨዋና ለቦታውም እንግዳ ብትሆን እንኳን ግን ፋራ ላለመባል ስትል ያቺ ቀድማ በወሲብ አክቲቭ የሆነችው ጓደኛዋ የምታዳርገውን ነገር ሁሉ ታደርጋለች፡፡በዚያኑ ዕለት ከጓደኛዋ ጋር ለመመሳል ስትል ጓደኛዋ ከወንድ ጋር ከወጣች እንግዳይቷም አንዳችም ሳታንገራግር ከወንድ ጋር ትወጣለች፡፡

ታዲያ ይህች ልጅ ይህንን ሁሉ ጉድ የምታደርገው ግንዛቤ ኖሯትና አውቃ ላይሆን ድንገት ያላዩት ሀገር ይናፍቃል እንደሚባለው ሄዳ በዚያው ለዝሙት ተጋልጣ ነው፡፡ ከዚያም የሰማይን ያህል እሩቅ ለሚመስለው ያልተፈለገ እርግዝና ትጋለጣለች፡፡ እርሷ የምትባንነው ምናልባትም ሆዷ ከፍ ሲል ይሆናል፡፡ታዲያ ይህ ሁሉ ጉድ ወላጆች ዘንድ የሚደርሰው የዚህን ጊዜ ነው፡፡የዚህን ጊዜ ወላጆች የልጆቻቸውን ገመና ሳይሆን መዘዙን ነው የሚያዩት፡፡ይህ እየተለመደ በመምጣቱም በርካታ ወላጆች ስሞታቸውን እያሰሙና ምሬታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

✏️✏️በተደጋጋሚ ከሚሰሙ የወላጆች ምሬት መካከልም
☞ልጄ እኮ ተበላሸች
☞ልጄ እኮ እንደዚህ ሆና ሱሰኛ ሆነችብ
☞ልጄ እኮ ለቅሶ ታበዛለች፤ ምን እንዳስነኳትም አላውቅም»፣
☞«ልጄ እንደዚህ ዓይነት መዘዝ አመጣችብኝ፣
☞«ልጄ እንደዚህ ዓይነት አዲስ ጠባይ አመጣች,, የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡ሳይቃጠል በቅጠል እንደሚባለው አንዴ የአዳጊ ልጆች ሕይወት ከተበላሸ በኋላ የወላጆች ወይታ የአዞ እንባ ከመሆን አይዘልም፡፡
ሴት ልጅ አንዴ የህይወት መስመሯ ከተበላሸ ሳይክሪስት ጋር ብትሄድ..ሩቃ እያለች ጂን ነዉ እየተባለ ቁርአን ቢቀራባት .ሀገር ከተማ ብትቀይር አንዴ መስመር ከሳተች ሳተች ነዉ፡፡ የባቡር ሀዲድ ሀዲዱ መስመሩን ከሳተ ገደል እንደሚገባ ሴትም ልጅ ህይወቷ ከተባላሸ እንደባቡሩ ነዉ የመጨረሻ ህይወቷ፡፡

«አሳዳጊ የበደለው ልጅ, እንደሚባለው ልጅህ ላይ አስቀድመህ የወላጅነት አሻራ ካላኖርክ፣ የአላህን ተቆጣጣሪነት ካላስተማርከው ልጁ በልብ ፅላቱ ላይ የሚያፅፈው የጓደኛውን ምክር ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ በልጆች ልብ ላይ የወላጆች አሻራና የአምላካቸው ትዕዛዝ በልባቸው ፅላት ላይ ሳይፃፍ ልጆች በየሄዱበት ሁሉ በማንም የሚነዱ ጭፍን ተከታዮች ይሆናሉ፡፡

ይህ የወላጆች ምሬትና ስሞታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና ችግሩም ሥር እየሰደደ መጥቷል፡፡ ቢያንስ በየቤቱ በሴት ልጁ ወይ በወንድ ልጁ የሚያማርር ቤተሰብ በየሁላችንም ቤት አለ፡፡ችግሩ የብዙዎችን በር ያንኳኳ ይመስላል፡፡ችግሩን የበለጠ ያባባሰው ደግሞ የልጆቹ ዕድሜ ገና ለጋ መሆኑና ምንም አያውቁም የሚባሉ አዳጊዎች ተበላሽተው መገኘታቸው ነው፡፡በተለይ በርካታ ወላጆች አዳጊ ሴት ልጆቻቸው በሚያመጡት ዝሙት ክብራቸውና ሞራላቸው እየተነካ ይገኛል፡፡ ይህም ዝሙትና ሌሎችም ሱሶች በሙስሊሙ መካከል መስንራፋቱንና ሥር መስደዱን ይጠቁማል፡፡
=======\=======\======\======
ቤተሰብ ሆይ ለልጅህ  የሱሀቦችን ገደል እያስተማርክ አሳድጋቸዉ፡፡የ15,000 ስልክ ገዝተህ ቲክቶክ ላይ ተዘፍዝፈዉ ከሚዉሉ...አሁን ላይ መፅሀፍ ዋጋዉ ስለጨመረ 50መፅሀፍ ገዝተህ እዉቀት ብትሰጧቸዉ መጥፎና ጥሩዉን እንዲለዩ ማድረጉ ይሻላል፡፡

አንድ ሌባ የትልቅ ሰዉ ስልክ መስረቅ ፈልጎ ሲከታተል ስልካቸዉ ጠራ...ሌባዉ ስልካቸዉን ለመዉሰድ ጥሩ አጋጣሚ ሆነለት...ፋዘር ስልኩህ እየጮሀ ነዉ አላቸዉ
...እሳቸዉ ግን ይጩህ ግድ የለም ቡሀላ እኔ ከምጮህ ስልኩ አሁን ቢጮህ ይሻላል አሉት፡፡

ቤተሰብ የኔ ልጅ ትለያለች ብለዉ ሽንጣቸዉን ገትረዉ መከራከሩን ያቁሙ..አስተዳደግ ላይ ሴት ልጅህን ሚስጥረኛህ እስከምትሆን ድረስ ቅረባት አባት ልጅህ እህትህ አድርገህ ያዛት...ወንድምም ለእህትህ ቀርበህ ትክክለኛ ወንድም ሁናት፡፡

በራሴ አመለካከት ከእናት በላይ ሴትን ልጅ ማስተካከል የሚችቸዉ አባት ነዉ ብየ አስባለሁ፡፡ለምን ብዙ ሴቶች እየተሸወዱ በአጂነብይ ወጥመድ የገቡት ከወንድ ልጅ ያጡት የአባት ፍቅር ወይም የወንድም እንክብካቤ መንስኤ ነዉ፡፡ቦይ ፍሬንድ እሷን ለማበላሸት አዳማጭ ሰሚ ያጣችዉን ወንድ አባት ይተካና ህይወቷን አበላሽቶ እንደመኪና ጥቁር ዘይት በየአቅጣጫዉ ይደፋታል፡፡
ሴቶች ሆይ የመኪና ጥቁር ዘይት ጠቁሮ ከመዳፋቱ በፊት መጀመሪያ ላይ ታሽጎ ከፋብሪካ ሲወጣ የሚያምር መልክ የታሸገ ነበር ግን በሂደት መኪና ዉስጥ ገብቶ ሲሰራ ሲታዘዝ የመጨረሻ እድሉ ጥቁር ሁኖ አስጠልቶ ቆሻሻ ቦታ መደፋት ሆነ እጣዉ፡፡ አንቺም በሀራም ፍቅር በወንዱ እንደፈለገ በየካፌዉ በየፔንሲዩኑ የወደደሽ መስሎሽ ሲያዞርሽ ኑሮ በርገር ፒዛ በልተሽ  ቡሀላ አግልግሎትሽ ሲያልቅ ኤክስፓየርድ ስትሆኝ እሱ አዲስ ሞዴል ይዞ በመጨረሻም እንደ መኪና ጥቁር ዘይት ቆሻሻ ቦታ እንዳትደፊ ተጠንቀቂ...አንቺ ሶብረኛ አላህን ፈሪ ከሆንሽ ትዳርና እንቅልፍ በራሷ ጊዜ ይመጣል፡፡

#ብዙ ሴቶች ትዳር እየተላለፋቸዉ እየዘለላቸዉ ያለዉ ትዳር ፈላጊዉ በዉጭ በሚያቃት ቤተሰብ ሲያስጠይቅ ቤተሰብ እንደሚያቃት ደግሞ ልጄ ለእሱ አመጥነዉም የኔ ልጅ እኮ እንዲህ ናት ብለዉ ይከለክላሉ፡፡አረ ወገን አላህ ይድረስልን ሴትልጅና ቤተሰብ ሳይተዋወቅ  በማስመሰል ተደባብቆ አንድ ላይ እየኖሩ ይገኛሉ፡፡
ይቅርታ አርጉልኝና ከሴቶች የምታስቀኝ ቃል አለች...ወንድ ልጅ ለትዳር ገና መስመር ሊጀምር ሲል የሚላት ቃል ኮስተር ብለዉ እኔ እንደሌሎች ሴቶች እንዳልመስልህ🙄የሚሏት ቃል አለች...በጣም የምትአጅበኝ የምታስቀኝ  ቃል ነች ከምር ለምን እንዲህ የምትል ሴት እሷን ጨምሮ አንድ ስለሚሆኑ ሳክስ ነዉ ወዳጄ

#በቀጣይ ክፍል
በአዲስ አበባ ታዋቂ የግል ትቤት
9ሴቶች 11ወንዶች በትምህርት ቤት ፓርቲ አዘጋጅተዉ ምን ሲሰሩ አደሩ?ወላጅስ?ከዛስ ምን ተፈጠረ የሚለዉን የሚያሳፍር እዉነተኛ  ታሪክ አቀርባለሁ ..እየተከታተላችሁ ሼር እያደረጋችሁ ስለሆነ አላህ ምንዳችሁን እጥፍ ድርብ ያርግልኝ

#ምዕራፍ ➎...ይቀጥላል
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
           🔰 #ምዕራፍ_አምስት
                አሚር ሰይድ


╔══════════════════════╗
   #አዲስ_አበባ_በተማሪዎች_የተፈጠረ
                  #አሳፋሪ_ተግባር      
╚══════════════════════╝


   📌📌  በርካታ ወላጆች ልጆቻቸው የሚገቡበትንና የሚወጠብትን ሰዓት፡ የት እንደሚውሉ፣ ውሎአቸው
ምን እንደሚመስል፤ ከት/ቤት ሲወጡ በቀጥታ ወደቤታቸው ይምጡ አልያም በየጫት መቃሚያው ወይም መሸታ ቤቱ ያምሹ ትዝ አይላቸውም፡፡ ወላጆችም እንዘላሎች ልጆቻቸውም ልቅ ሁነዋል፡፡



      በአንድ አጋጣሚ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና በአንድ ታዋቂ የግል ት/ቤት መካከል አንድ ችግር ተፈጥሮ ነበር፡፡ የችግሩ መንስኤም ይህን ይመስላል፡- የዚያ ት/ቤት ተማሪዎች በት/ቤታቸው ውስጥ ፓርቲ ያዘጋጃሉ፡፡ ተማሪው ከቤቱ ምግብ፣ መጠጥ፣ ቪዲዮ ካሜራ፣ የሙዚቃ መሳሪያ ሳይቀር ይዘዉ መጥተዋል:: የዝግጅቱ ዕለትም ቅዳሜ ነበር፡፡ 20 የሚሆኑ ተማሪዎች ነበሩ 9 ሴቶችና 11 ወንዶች፡፡ ቀኑን ሙሉ በግቢው ውስጥ ሲበሉ፤ ሲጠጡ፤ ሲዝናኑና ሽር ብትን ሲሉ ዋሉ፡፡ እስከ ማታም ሲጠጡና ሲጨፍሩ ቆዩ፡፡ ሳይወጡም ቀጠሉበት፡፡

በዚያው ጥንድ ጥንድ ሆነው መዋሰብ ጀመሩ፡፡ ትርፍ የመጡት ሁለት ወንዶች ግን ይህንን አሳፋሪ ትዕይንት በቪዲዮ ካሜራ መቅረፁን ተያያዙት፡፡ ሁሉም ዓይነት ወሲባዊ እብደቶች ተደረጉ፤ ተቀረፁም፡፡ ከሚቀርፁት መካከል አንዱ ሙስሊም እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ ዓይነት ዲያብሎሳዊ ድርጊት ውስጥም እስከ ሌሊቱ 9፡00 ቀጠሉበት፡፡ ቀረፃውም ወሲባዊ እብደቱም ቀጠለ፡፡ በስተመጨረሻም ዘበኛው ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ መጣና ግቢውን ለቀው እንዲወጡ አዘዛቸው፡፡ ተማሪዎቹ ግን በእብደት ውስጥ ስለነበሩ አልሰሙትም፡፡

    ከዚያም ዘበኛው በዚያው ሌሊት ወደ ት/ቤቱ አስተዳደሪ ደውሎ ተማሪዎቹ እስካሁንም ከግቢው እንዳልወጡና እምቢ እንዳሉትም ነገረው፡፡ አስተዳዳሪውም እስካሁን ካቆየኋቸው በኋላ በዚህ ሰዓት ምን ማድረግ እችላለሁ??»ብሎ ስልኩን ዘጋ፡፡
..አስተዳዳሪው ማልዶ ሲመጣም ተማሪዎቹ ከግቢው አልወጡም ነበር፡፡ስም ዝርዝራቸው ተያዘ፡፡የቀረፁት ቪዲዮም ተያዘባቸው፡፡ሲሰሩት ያደሩት ብልግና ሁሉ ተጋለጠ፡፡ት/ቤቱም አባረራቸው፡፡ሁኔታው ተካረረ፡፡ጉዳዩም በት/ቤቱና በተማሪዎቹ መካከል ሊፈታ ባለመቻሉ ለአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ተመራ

አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ የት/ቤቱን እንዝላልነትና በተለይም ከ12 ሰዓት በኋላ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ እንዲያመሹ በመፍቀዱ ት/ቤቱን ከሰሰው፡፡ከዚህ በኋላ የፍርድ ሂደቱን ግልፅ ማውጣቱ አግባብነት ስለሌለው እዚህ ላይ እንገታዋለን፡፡ግን ተማሪዎቹ ከተባረሩ የባሰ ሊበላሹና ሕይወታቸውም አደጋ ላይ ሊወድቅ ስለሚችል ወደ ትምህርታቸው መመለሱ የተሻለ እንደሆነ በት/ቤት ቢሮው በኩል ፅኑ አቋም ተያዘና ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ፣ ግን ት/ቤቱና ተማሪዎቹም በመማር-ማስተማር ሂደታቸው ላይ ሆነው የፍርድ ሂዴታቸውን እንዲከታተሉ ተወሰነ፡፡የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮም በት/ቤቱ ላይ የከፈተውን ክሰ ይዞት ቀጥሏል፡፡ከዚህ ከስተትም ወላጆች ልጆቻቸው ውጭ ቢያድሩ እንኳን ምንም አለማለታቸው ወላጆች ዘንድ ያለው ችግር ምን ያህል የገዘፈ እንደሆነ ትልቅ ትምህርት እንወስድበታለን፡፡

🔴 #ይህ_የተፈጠረዉ ከ2009 በፊት ባለዉ ጊዜ ነዉ፡፡ዛሬ ላይ ስንት ፓሪ ይዘጋጃሉ??ተማሪ ተብየዎች 8ወይም 10 ወይም 12 ዩኒቨርስቲ ..የግል ኮሌጅ ትምህርት ሲጨርሱ ፕሮግራም እየዘጋጁ ካሉበት ሀገር ወጣ ብለዉ ብዙ ፈሳድ ነገሮች እየተፈጠሩ መሆኑ እርግጥ ነዉ..ግን ለነዚህ ልጆች ፕሮግራም አለ ሲባል ብር የሚሰጠዉ ወላጅ ነዉ፡፡ልጄ ትዝናና በሚባል መርህ ተማሪዎች እየተጨመላለቁ ነዉ፡፡ብቻ ነገ አገርን ይረከባል ዲነል ኢስላምን ይረከባል የተባለዉ ትዉልድ በወላጆች ቁጥጥር መሳሳትና በጓደኛ በሚዲያ ተፅእኖ ዉስጥ ወድቋል...በግልም በህብረትም ተሁኖ ከባድ ጥረት ይጠይቃል፡፡ፈጣሪ ልቦና ይስጠን



╔══════════════════════╗
⚡️ #ግን_በዚህ_ሁኔታ_ወደየት_እያመራን_ነዉ??       
╚══════════════════════╝


☞ረጃጅም ሕንፃዎች ትናንሽ ትዕግስቶች
☞ሰፋፊ መንገዶች ጠባብ አመለካከቶች
☞የምናወጣው ብዙ የሚኖረን ጥቂት ብዙ እንገዛለን
☞ትላልቅ ቤቶች ትናንሽ ቤተሰቦች፥
☞ የተሻለ ምቾት ጥቂት ጊዜ
☞ ብዙ ድግሪ ጥቂት ማመዛዘን/ግንዛቤ፣
☞ ብዙ ዕውቀት ትንሽ ጥበብ፣
☞ብዙ አዋቂዎች ብዙ ችግሮች፣
☞ብዙ መድሀኒት ትንሽ ጤንነት

ብዙ እንጠጣለን፤በቸልተኝነት ብዙ እናባክናለን፤ ትንሽ አንስቃለን፣በፍጥነት እንናደዳለን፤ በቶሎ እንናደዳለን፤

☞ብዙ እናመሻለን፤ደክሞን እንነሳለን፤ ጥቂት እናነባለን፤ብዙ ቴሌቪዥን እንመለከታለን፤ አልፎ አልፎ እንፀልያለን

☞ ብዙ እናወራለን፤ትንሽ እናፈቅራለን፤አብዝተን እንጠላለን፡ስለ ጥሩ አኗኗር ተምረናል፣እንዴት እንደሚኖር ግን አልተማርንም

☞ የራሳችንን ኑሮ እናቀለጣጥፋለን፤ ለሌላው ግን አንኖርም፡ኑሮን እንጂ ሕይወትን ትተናል
☞  ሥልጣንን ለማገልገል ሳይሆን ኪስና ሆድ ለመሙላት፣ሆድ ተንዘርጥጦ አዕምሮ ግን ኮሰመነ፡፡መከባበር በመናናቅ መተዛዘን በመጠፋፋት፣ ሕሊና በሆድ ተተኩ

☞ ጨረቃን ላይ ደርሰን ተመለስን፤ ግድግዳ የሚለየውን አዲስ ጎረቤታችንን መተዋወቅ ግን አቀበት ሆነብን
☞ከምድራችን ውጭ ያለውን ህዋ ተቆጣጠርን፤ በውስጣችን የሚገኘውን ትንሽ ቦታ ግን አልተቆጣጠርንም

☞ ትላልቅ ነገሮችን እንጂ የተሻሉ ነገሮችን አልሠራንም፡አካባቢያችንን እያፀዳን ነፍሳችንን ግን እየበከልን ነው፡፡አቶምን ሰንጥቀን፤ መሠረተ ቢስ ጥላቻዎቻችንንና ቅራኔያችንን አልፈታንም

☞ ብዙ እናነባለን፤ ትንሽ እንለወጣለን፡፡ ብዙ እናቅዳለን፤ ጥቂት እናሳካለን፡፡መቸኮልን እንጂ መጠበቅን አልተማርንም፡፡የተሻለ አንጂ ያደገ ሥነ-ምግባር የለንም፡፡

☞ ብዙ መረጃ የሚይዝና ብዙ ሥራ ባጭር ጊዜ የሚያከናውን ኮምፒዉተር ፈጠርን እንጂ በመካከላችን ግን ብዙ ተግባቦት አልፈጠርንም፡፡ በብዛት ብዙ ሄደናል፤ በጥራት ግን ወደኋላ ተጎትተናል።

🔰🔰 ጊዜው እንዲህ ሆነ፦ሰው በሁለት ገቢ የሚተዳደርበት፣ ትዳር ግን የሚበተንበት፡ የተሰነጣጠቁ ቤተሰቦች የሚኖሩባቸው ግን የተዋቡ መኖሪያዎች፡፡ እርጋታ ሳይሆን ጥድፊያ ፡ልብ ማለት ሳይሆን ልብ መጥፋት፣የሕይወታችን መሊያ ሆኑ፡፡ ወቅቱ ፈጣን ጉዞ የሚደረግበት፣ ለአንድ ሌሊት ትዳር የሚወጣበትና ግብረ ገብነት ተሸቀንጥሮ የተጣለበት ዘመን ወዴት ነው እያመራን ያለነው??
አላህ ይድረስልን ልቦናዉን ይስጠን

 #ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ሸርሙጣ፣ ሴተኛ አዳሪ፣ የቡና ቤት ሴት፣ ሸሌ፣ ባር ሌዲ፣ ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ_ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ ሂያጅ፣ አመንዝራ፣ ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ወንድኛ አዳሪ፣ ወንድ ሸሌ፣ ሸርሙጣ፣ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል

ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት አላህ ይወፍቀን

በቀጣይ ክፍል
ከአጂነቢ ሴት ጋር የመቀመጥ አደገኝነት ላይ ያተኮረ ፁሁፍ ይቀርባል
#ምዕራፍ
ይቀጥላል....
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
           🔰 #ምዕራፍ_ስድስት
                አሚር ሰይድ


╔══════════════════════╗
⚠️ #ከአጂነቢ_ሴት_ጋር_የመቀመጥ_አደገኝነት     
╚══════════════════════╝


       አሏህ ሱወ በተከበረ ቁርአኑ እንዲህ ብሏል
  በቤቶቻቸሁም ውስጥ እርጉ፡፡ እንደ ፊተኛይቱ መሀይምነት ጊዜ መገለጥም በማጌጥ አትግለጡ፡፡» (አል-አሕዛብ፡33)

💚 ሀቢቡና ሰይዱና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-

«አንድ ሰው ከአንዲት ሴት ጋር ብቻውን በሚሆንበት ጊዜ ዲያብሎስ ሶስተኛቸዉ ይሆናል፡፡(ቲርሚዚ)

☞ ከታላላቅ ኸሊፋዎች አንዱ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አምስተኛው ኸሊፋ ዑመር ቢን ዐብድል ዐዚዝ እንዲህ ብለዋል፦ «ከሴት ጋር ፈፅሞ ብቻህን አትሁን፤ ቁርአን የምታቀራት'' ቢሆን እንኳ፡፡»ብለዋል

     ሙእሚኑ ከአጂ ነቢይ ሴት ጋር ብቻውን ሊሆን በጭራሽ አይፈቀድለትም፡፡ እናም ለርሱ ያለው ብቸኛው መፍትሔ የሚወዳትን ሴት ጠይቆ ማግባት ነው፡፡ በዚህ ድርጊቱም እርሱ ፈፅሞ ሀፍረት ሊሰማው አይገባውም፡፡ ምክንያቱም ከባዳ ሴት ጋር ለመሆን ብቸኛው ትክክለኛ መንገድ ይህ ነውና፡፡ ፋታም ሆነ እፎይታ የሚገኘው በዚህ ብቻ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፡-

እኛ ለሁለት ለሚፋቀሩ ጥንዶች ከጋብቻ የተሻለን ዕረፍት ለነርሱ አናውቅላቸውም፡፡..

አቡ ዘር (ረ.ዐ) እንዳወሩት አንድ ጊዜ ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉ፡-

“አንድ ሙስሊም ከሚስቱ ጋር በሚፈፅመው ወሲባዊ ድርጊቱ ውስጥ ሰደቃ አለበት አሉ፡፡ ሱሀቦቹ (ረ.ዐ) «የአላህ መልዕከተኛ ሆይ! ከኛ መካከል አንዳችን የራሱን ወሲባዊ ፍላጎት በሚያሟላበት ጊዜ ለርሱ ለዚያ ምንዳ ይሰጠዋልን ??ሲሉ ጠየቋቸው፡፡ እርሳቸውም ለመሆኑ እርሱ ይህንን በሐራም መንገድ ቢያደርገው ኖሮ ኃጢአት አይሆንበትምን?? ሲሏቸው «አዎን ይሆንበታል›› አሉ፡፡ እርሳቸውም መልሰው ‹ስለዚህ እርሱ ይህንኑ በህጋዊ መንገድ ካደረገው ምንዳን ያገኝበታል» አሉ፡፡ (ሙስሊም)



╔══════════════════════╗
  🚫🚫 #ኢኽቲላጥ_እና_አሁን_ያለዉ_ሁኔታ🚫
╚══════════════════════╝

        እነሆ ዛሬ ዛሬ ሴቶቹ የሚውሉት ከቤት ውጭ ነው፡፡ ይባስ ብሎም ለዘመኑ ሴቶች እቤት መዋል እንደ ነውር ይታያል፡፡ ከቤት ከወጡ ደግሞ መገላለጣቸው አይቀርም፡፡ ያም በግልፅ እየታየ ነው፡፡ ይህም በሐዲሡ የተጠቀሰው እውነታም እንደፀናባቸው ከወዲሁ ያረጋግጣል፡፡ ታዲያ ሴቶችን ለዚሁ ሁሉ ያበቃቸው በቤቶቻቸው አለመርጋታቸው ነው፡፡ ከዚህም በኋላ ቢሆን ይኸው እኩይ ልማዳቸው በስፋት ይቀጥላል፡፡ ቃል የተገባላቸው ቅጣትም እየፀናባቸው ይሄዳል፡፡

🧡ሀቢቡና ሙሀመድ  ﷺ የሴቶች ከቤት መውጣት የተከለከለበትን ምክንያትና ተከትሏቸው የሚመጣውን መዘዝ ሲያስረዱ አንዲት ሴት ከቤቷ ስትወጣ ኢብሊስ በሁለት እጆቹ ስለሚቀበላት ነው ብለዋል፡፡ ይህንኑም እንዲህ ሲሉ ገልፀዋል፡-

«ሴት ዐውራህ ናት፡፡ ወደውጭ በምትወጣበት ጊዜ ሸይጧን ያጎላታል፡፡ብለዋል

✏️✏️ታዲያ ሰይጣን ወደውጭ የምትወጣዋን ሴት ተቀብሏት ሲያበቃ የመጀመሪያ እርምጃው እርሷን እንድትገላለጥና ወሲብ ቀስቃሽ ጨርቆችን እንድትለብስ ማድረግ ነው፡፡ ምክንያቱም የአደምን ልጆች እርቃነ ስጋቸውን ማስቀረት መቻል ለርሱ ቀዳሚው ትልሙ ነውና፡፡ ከቁርአን እንደምንማረውም አባታችንን አደምንና እናታችንን ሐዋን እርቃነ ስጋቸውን ሊገልጥላቸው ዘንዳ በተደጋጋሚ ሲገፋፋቸው ነበር፡፡ በዚህም ተሳክቶለታል፡፡ ይህም በመሆኑ ያለ አስገዳጅ ምክንያት ከቤቷ የምትወጣ ሴት ልክ እንደወጣች በሰይጣን እጅ ውስጥ ትገባለች ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አንዲት ሴት ወደ አላህ (ሱ.ወ) በቀረበች ቁጥርም በቤቷ ለረጅም ጊዜ የበለጠ ትቆያለች፤ ትረጋለች፡፡

ይህንኑ አስመልከቶም 💛 ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «ሴት የግል ሕይወትህ አካል ናት፡፡ እናም በቤትህ ያዛት፡፡ምክንያቱም እርሷ ወደውጭ የምትወጣ ከሆነችጓደኞቿ አንቺ የት እየሄድሽ ነውን ብለው ይጠይቋታል፡፡ እርሷም እኔ ታማሚን እጎበኛለሁ ወይም የቀበር ሥነ-ሥርዓት ላይ እገኛለሁ ትላለች፡፡ እርሷ ከቤቱ እስከትወጣ ድረስም ሸይጧን እርሷን መፈታተኑን ይገፋበታል፡፡ በመሆኑም አንዲት ሴት የአላህን ውዴታ የምትፈልግ ከሆነች፣ በቤት ውስጥ መቆየት መርጋት ፣ እላህን መገዛት እና ባሏን መታዘዝ ለርሷ በላጭ ነው፡፡››(ጠበራኒ)

   #በሱሀቦች_ዘመን ሴቶች ወደመስጊድ ይመጡ ነበር፡፡ ነገር ግን ሲመጡም ሆነ ሲመለሱ ፈፅሞ ከወንዶች ጋር አይቀላቀሉም ነበር፡፡ የተለየ መንገድና የተለየ መግቢያ በር አላቸው፡፡ ከሰገዱ በኋላም ቢሆን ከመስጊድ ወጥተው ሲያበቁ ከዕይታ እስከሚሰወሩ ድረስ ወንዶቹ ከመስጊድ አይወጡም ነበር፡፡ በተለይ ሰይዲና ዑመር (ረ.ዐ) ይህንኑ መመሪያን በተግባር ላይ አውለዋል፡፡ ሴቶቹ ከዕይታ እስከሚሰወሩ ድረስ አንድም ወንድ ከመስጊድ እንዳይወጣ ከልክለዋል፡፡ ሱሀቦቹ (ረ.ዐ) የዚህ ኡምማ ወንዶች ትልቁ ፈተናቸው ሴቶች እንደሆኑና ሴቶችንም ተጠንቀቋቸው ተብለው እንደታዘዙ ስለሚያውቁ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጉ ነበር። ይህንኑ አስመልከቶ
💙 ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ማለታቸው ይታወሳል-

በውነቱ ዱንያ (ይህች ዓለም) አረንጓዴና ጣፋጭ ናት፡፡ አላህም በርሷ ውስጥ ተተኪዎች ያደርጋችኋል፤ ምን እንደምትሠሩ ሊያያችሁ ዘንዳ፡፡ እናም ዱንያን (ይህችን ዓለም) ፍሩ ተጠንቀቋት፡፡ ሴቶቹንም ፍሩ ተጠንቀቋቸው፤ ምክንያቱም የእስራኤልን ልጆች የገጠማቸው የመጀመሪያው ፊትና ሴቶችን የሚመለከት ነበርና፡፡›› (ሙስሊም)

 ⚠️“ኢኽቲላጥ የዝሙት ቡፌ ከመሆኑም በላይ ልብን ከሚያደርቁ ነገሮች መካከል አንዱና ትልቁ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ልብን የሚያደርቁ አራት አበይት ነገሮች አሉ። እነርሱም
➊ዕይታን ማብዛት፣
➋ ንግግርን ማብዛት፣
➌ምግብን ማብዛትና
➍ኢኽቲላጥን ማብዛት ናቸው፡፡

ለዕይታ ማብዛትና ለንግግር ማብዛትም ዋናው መንስኤ ኢኸቲላጥ ነው፡፡ ይህም ማለት ለልብ ድርቀት ሶስት አራተኛው መንስኤ ኢኸቲላጥ ነው ማለት ነው:: ስለዚህም ኢኸቲላጥን ልብ አድራቂው ደዌና የዝሙት ብፌ ብለን ብንጠራው አግባብነት አለው።


╔══════════════════════╗
  ⚠️⚠️ #በኢኽቲላጥ_በኩል_በሙስሊሞች_ላይ
                #የተካሄደዉ_ጥናት 
╚══════════════════════╝

  
    ከቅርብ ዓመታት በፊት ኢኸቲላጥን አስመልከቶ በሙስሊሞች ላይ አንድ ጥናት ተደርጎ ነበር፡፡ የጥናቱ ውጤት ይፋ እንዳደረገውም ከጥናቱ ተሳታፊዎች መካከል 76% የሚሆኑቱ ሙስሊሞች እንኳን ኢኸቲላጥን ሊደግፉ ቀርቶ ይልቁንም ምንም ዓይነት የፆታዎች ቅልቅል በሌለበት አካባቢ መሥራትን እንደሚመርጡ ተናግረዋል፡፡ ሸሪዓዊ ዕውቀታቸውንም በተመለከተ መቶ በመቶ ተቃራኒ ፆታዎችን መቀላቀል ፈፄሞ ተቀባይነት እንደሌለው በፅኑ እንደሚያምኑበት ተናግረዋል፡፡ ከተሳታፊዎቹ መካከል 12% የሚሆኑት ግን ኢኸቲላጥ ባለበት አካባቢ ቢሰሩ እምብዛም እንደማይቸገሩና ኢኽቲላጡም በሸሪዓዊ ገደቦች ውስጥ ከሆነ ይበልጥ እንደሚበረታታና ተቀባይነትን እንደሚያገኝ ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ 12% የሚሆኑት ሙስሊሞች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቀላቀል ይፈቀዳል ብለዋል፡፡
እነዚያ በሸሪዓዊ ገደቦች ውስጥ ተቃራኒ ፆታዎችን መቀላቀል ይቻላል ያሉት ወገኖች ከዘልማድ (ዑርፍ) እና ከባህል በመነሳት ነዉ፡፡👇👇👇
የዝሙት መዳረሻዎች ከሞላ ጎደል እየለፈለፉ የተንሰራፉ ሲሆኑ ኢኽቲላጥ ግን ድምፁን አጥፍቶ ውስጥ ለውስጥ የገዘገዘን የዝሙት መጋዝ ነው፡፡ እንደነርሱ እምነት ከሆነ እነዚህ መስፈርቶችም ኢኸቲላጥን በተገቢው ገደቦች ውስጥ የሚጠብቁ ናቸው::

     ሆኖም ግን ለመሆኑ እናንተ ይፈቀዳል የምትሉት ኢኸቲላጥ  ዛሬ ዛሬ በየት/ቤቱ፣ በየኮሌጁ፣ በየዩኒቨርሲቲው፤ በየመሥሪያ ቤቱ፣ በየገበያ ማዕከሉ፣ በየንግድ ታዎሩ፣ በየመጓጓዣው፣ በየአደባባዩ፣ በየማህበራዊና ሕዝባዊ ስብስቦቹ ላይ የምናየው ዓይነት ነውን? እሺ! እነዚህ ሁሉ የኢኸቲላጥ ዓይነቶች እናንተ ይፈቀዳሉ በምትሏቸው ገደቦች ውስጥ ናቸውን? ለመሆኑ እናንተ ይፈቀዳሉ የምትሏቸው የኢኸቲላጥ ዓይነቶች በገሀድ አሉን? ሲባሉ አጥጋቢ ምላሽ የላቸውም፡፡ በእውነቱ ዛሬ ዛሬ በየቦታው የምናያቸው የኢኸቲላጥ ዓይነቶች በአለባበስ፣ በአነጋገር፣ በወንዶችና ሴቶች መካከል ባለው ኢንተራከሽንና በምግባር ረገድ በሸሪዓዊ ገደቦች ውስጥ የሉም፡

ዛሬ ዛሬ ባሉ ኢኸቲላጦች ውስጥ የሴቶች መገላለጥ (ተበርሩጅ)፣ የሒጃብ መስፈርቶች ጥሰት፣ የሴቶች ልቅነትና በአጠቃላይም ሥርዓት አልበኝነት የሰፈነበት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

እነሆ በኢኸቲላጥ ሳቢያም ቁጥር ስፍር የሌላቸው ፊትናዎችን እያየን ነው፡፡ በተቃራኒ ፆታዎች መካከል ለሚፈፀሙ ወንጀሎች ሁሉ ምንጩና መፈልፈያው ኢኸቲላጥ ነው፡፡ ሌላው ቢቀር ኢኽቲላጥ ሲኖር በወንዶችና በሴቶች መካከል በቀላሉ የሚያስጠርጥሩ ግንኙነቶች ይፈጠራሉ፡፡ስለዚህ ዛሬ ዛሬ እየተከሰተ ያለው የኢኸቲላጥ ዓይነት ምንም ተቀባይነት የለውም፡፡

✏️✏️ ከሴቶች ልቅነት የተነሳ በሸሪዓዊ ገደቦች ውስጥ የሚደረጉ ኢኽቲላጦችም ተውጠዋል፤ ከስመዋል ማለት ይቻላል፡፡ ወጣም ወረደም ሸሪዓው እንዲህ በታመቀበት አግባብ ውስጥ በሸሪዓዊ ገደቦች ውስጥ የሚደረጉትን ኢኽቲላጦች እንኳን ማበረታታቱ አግባብነት የለውም፡፡

    ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ለዝሙት ለም የሆነ የማብቀያ መሬትን በማዘጋጀት ይህንን ደዌ ለዚህ ደረጃ ያበቃው ትልቁ ነገር ኢኸቲላጥ (የፆታዎች ቅልቅል) ነው፡፡ዝሙትን መሥራት ውሀን የመጠጣት ያህል ቀላል ያደረገውና ከዚያም አልፎ ሰዎች በዝሙት እንዲፎካከሩ ያደረገው ይኸው ኢኽቲላጥ የተባለው ደዌ ነው፡፡

ዛሬ ዛሬ የዓለምን ማህበረሰብ ቀፍድዶ የያዘው የዝሙት ዛር በዋናነት የተፈለፈለው ከኢኸቲላጥ ነው፡፡እናም ከኢኸቲላጥ ጋር የተያያዘውን እውነታ መገንዘብና ማህበረሰቡን ከገባበት ሕመም መፈወስ እንገብጋቢ ጉዳይ ሆኖ ይታያል፡፡ እንደ ኢኸቲላጥ በዝምታ የዝሙትን መርዝ የረጨው ሌላ የመዳረሻ መንገድ የለምና፡፡ሌሎች የዝሙት መዳረሻዎች ከሞላ ጎደል እየለፈለፉ የተንሰራፉ ሲሆኑ ኢኽቲላጥ ግን ድምፁን አጥፍቶ ውስጥ ለውስጥ የገዘገዘን የዝሙት መጋዝ ነው፡፡

ዛሬ ላይ ኢኽቲላጡ ያለማካበድ ከሌሎች ሀይማኖት በላይ ሙስሊሙ ላይ ይስተዋላል፡፡የኢኽቲላጥ መንገድ በኸይር ስራ ስም፡በሙስሊም የመድረክ ዝግጅቶች፡በሙነሺድ ተብየዎች በሚያዘጋጁት የነሺዳ ማስመረቂያ ሰም ኢህቲላጥ ተበራክቷል፡፡በፊት ታስታዉሱ ከሆነ የዛሬ 3አመት በፊት ሙነሺዶች መጣን መጣን ባሉ ጊዜ እነዚህ ሰዎች ይዘዉ የመጡት ነገር ከባድ ነዉ ለወደፊት ከባድ መዘዝ ይዘዉ መጥተዋል እያልኩ ብቻየን ፁሁፍ ሳዘጋጅ በጣጣም ተቃዋሚ ይበዛ ነበር ትችቱ ከአቅሜ በላይ ሲሆን ተዉኩኝ..ይሄዉ ዛሬ ነሺዳና ሙዚቃ መለየት እስከሚያቅተን በዜማ ሲጣሉ ሊደባደቡ ሲደርሱ
ነሺዳና ሙዚቃ ሲሰራረቁ እያየን ነዉ፡፡

የአሁን ሴት ሮል ሜድልሽ ማን ነዉ ብትባል አንዱን ሙነሺድ ነዉ😬 የምጠራዉ...ሚዲያ ላይ በፊት ብዙ ሴቶች በማስረጃ እንደነገሩኝ በጣጣም ብዙ የሙነሺዶች ገመና አቃለሁ የሚሰቀጥጡ ነገሮች በማስረጃ የማቀዉ አለ

አሁን ላይ የሚሻለዉ እነሱን አለመከታተል ነዉ ለምን የሚሰሩት ለአሏህ ብለዉ የአላህን ወዴታና የነብዩን ዉዴታ ለማግኘት ሳይሆን ታወቂ ለመሆን ለሴቱ የተሻለ ስራ እኔን ሴቱ እንዲወደኝ የትኛዉ ስራ ልስራ ስለሆነ እነሱን መከታተሉን ትቶ...አላህ ሆይ ቀጥተኛ መንገድ ምራቸዉ ወይ በዚሁ በዱንያ በሙነሺድ ስም የሚሰሩትን ግፍ ያሳየን ብሎ ዱአ ማድረጉ ይሻላል፡፡

«አደገኛው የኢስላም ጠላት አላዋቂ ሙስሊሞች ናቸው።በአላዋቂነታቸው ላይ ስሜታዊ ይሆኑና በድርጊታቸው የኢስላምን እውነተኛ ውበት ያጠለሻሉ።የሌላው ዓለም ሰዎች የነርሱን ድርጊት በመመልከት ኢስላም ያ እንደሆነ ያስባሉ። (ሽህ ኢሕመድ ዲዳት) የተናገሩት ንግግር የአሁን ዘመን ሙነሽዶችን ያካትታል👌👌


🫵 በተጨማሪ ዛሬ ላይ ኢኽቲላጡ በሙስሊሙ በዲን ስም ተጋኗል፡፡

🔶 #ሙነሺዶች፡ሚንበር ቲቪ የተለያዩ ሙሀለጣ ባላቸዉ ፕሮግራሞች አኽቲላጥ አለ በዚህ ኢኽቲላጥ ወደ ዝሙት መስመር የሚገቡ አሉ

🔶 #የሙስሊም_በጎ_አድራጎት_ማህበር እየተባሉ ሴትና ወንድ የሚደባለቁበት አለ፡፡አረጋዉያንን መንከባከብ..የተቸገሩ ለመርዳት ስበብ ለጀመአችን ማጠነከሪያ እየተባለ የሙስሊም ሴቶች ተበጃጅተዉ አንፀባራቂ ሎሚ ከለር ልብስ ለብሰዉ ከአጂ ነብይ ወንድ ለጀመአ ማጠናከሪያ በሚል ብር ማሰባሰብ..ለጀመአችን እየተባለ ሲዋክ መሸጥ...ቡና እያፈሉ በየመንገዱ መሸጥ...ጫማ የሚጠርጉ አለ...
የደካሞች ቤት ተብሎ የጀመአየ ልጅ አብረዉ ወንድ ጋር ሂደዉ ሴቶች ልብስ ሲያጥቡ ወንዱ ቤት ያስተካክላል..ሰዉ ያላስተዋለዉ ሙዱን የቀየረዉ የዝሙት መንገድ ነዉ☺️

#አሁንም እየሆነ ነዉ ለወደፊትም ታዩታላችሁ የዝሙት መንገድ ነዉ አሁንም አንዳንዶችም በድብቅ ገብተዉበታል::

የአላህን ዉዴታ አጅር ለማግኘትና ሴት ልጅ ቡና የምታፈላዉ ቤተሰቦቿን ለመሀደም እንጂ መንገድ ላይ ወንድ እንዲያት አይሆንም ነበር...ለጀመአየ ብላ ጫማ የምጠርገዉ የእናቷን የአባቷን ጫማ ረግጣ ወጥታ ነዉ...የአረጋዉያን ልብስ ልጠብ ብላ ስትወጣ የእናት የአባቷ ልብስ ግን ቆሾሾ ተቀምጧል...መቅደም ያለባቸዉ የአክስት የአጎቶቿ ልብስ የሚያጥብላቸዉ ተቸግረዋል ወይም ጎረቤቷ እማማ እንትና ልጅ የላቸዉ የሚንከባከብ የላቸዉ ልብሳቸዉን የሚያጥብላቸዉ የለ በርሀብ እየተሰቃዩ ይሆናል..ይህን ሁሉ አልፎ ሂዶ ጀመአየ አዘዘኝ አሚሬ አዘዘኝ ብሎ መንጦልጦል  ከምር አስመሳይነት ነዉ🙄፡፡በፊት ወንድ ሴትን ልጅ ለማዉራት ካፌ ወይ ወጣ ያለቦታ ነበር ዛሬ ግን  የጀመአ ፕሮግራም አለ በሚል ስም መገናኘት ሆነ አልሸሹም ዘወር አሉ ነገር ግን ኮዱን ቀየሩ😊 ነዉ የምንለዉ ወዳጄ..ቤተሰብ ሆይ ንቁ እባካችሁ‼️‼️

ግን ሴቶች ለብቻ ወንዶች ለብቻ የሆነ በጎ አድራጎት ወይ ጀመአዎች አሉ በተጨማሪ ትላልቅ ሰዎች ባለሀብቶች አሉ ለኸይር ስራ የተቋቋሙ እነዚህን ግን እንደማያካትት ልታቁልኝ ይገባል፡፡የእኔ ሀሳብ ኢኽቲላጥ ያለባቸዉ የወጣቶች ጀመአዎችን ነዉ


#በቀጣይ_ክፍል...የእጅ ዚና የጆሮ ዚና ላይ ያተኮረ ፁሁፍ ቢኢዝኒላህ ይዤ እቀርባለሁ


 #ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ሸርሙጣ፣ሴተኛ አዳሪ፣የቡና ቤት ሴት፣ሸሌ፣ባር ሌዲ፣ ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ሂያጅ፣አመንዝራ፣ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ ወንድኛ አዳሪ፣ ወንድ ሸሌ፣ ሸርሙጣ፣ ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል
ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት አላህ ይወፍቀን

#ምዕራፍ
ይቀጥላል....
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከአሏህ ስሞች አንደኛዉ ሽኩር ነዉ.

አላህ አመስጋኝ ባርያዎችን ይወዳል

join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
           🔰 #ምዕራፍ_ሰባት
                አሚር ሰይድ




አቡ ሁረይራ ረዐ  እንዳስተላለፉት የአላህ  መልዕክተኛ የሆኑት ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ «በአደም ልጅ ላይ የዝሙት ድርሻ ተጽፎበታል። ይህን ድርሻውን  ያለ ጥርጥር ያገኛል። ሁለት ዓይኖች ዝሙታቸው ማየት ነው፡፡ሁለት ጆሮዎች ዝሙታቸው  መስማት ነው፡፡ የምላስ ዝሙት መናገር ነው፡፡ የእጅ ዝሙት መጨበጥ ነው። የእግር ዝሙት መራመድ ነው።ልቦና ያስባል፤ይመኛል። ብልት ደግሞ ይህን ምኞት እውነት ወይም ሐሰት ያደርጋል።» (ቡኻሪና ሙስሊም)

ዚና አይነቱ ብዙ ነዉ የአይን ዝሙት ብዙዎቻችን የተጠመድንበት ነዉ በየመንገዱ በየሰፈሩ ሴቱም ወንድም አፍጥ አግጥን ሆነን ኢማናቻን ከተንሸራተተ ዋል አደር ብሏል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በtiktok የምናየዉ ተቀራኒ አጂነብይ የአይን ዚና መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል፡፡

ዛሬ ሰፋ ያለ ፁሁፍ ያዘጋጀሁት የእጅ ዚናና የጆሮ ዚና ላይ ያተኮሩ ናቸዉ፡፡ወደ ፁሁፉ እናማራ

╔══════════════════════╗
    🔰🔰 #የእጅ_ዚና_ምንነትና_አደገኛነት 🔰🔰
╚══════════════════════╝


💚 ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
  ከናንተ አንዳችሁ ከዚያ ያቺን ለርሱ የተከለከለችውን ሴት ከመንካት ይልቅ ጭንቅላቱ በብረት ወስፌ ቢሰፋ ይሻለዋል፡፡»ብለዉናል

    ይህ እንግዲህ የእጅ ዚና ቅጣትን የሚመለከት ነው፡፡ ታዲያ ከዚህ የባሱ ፀያፍና ሕገ-ወጥ ድርጊቶች:- ለምሳሌ መተቃቀፍ፣ መሳሳም፣ መተሻሸትና  ወሲብን መፈፀም ከዚህ የክፉ ቅጣቶችን እንደሚያስከትሉ ከዚሁ መገመት ይቻላል፡፡

⚡️⚡️ለምሳሌ ሕገወጥ መሳሳምን በተመለከተ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-

«እርሱ ያ ያቺን ለርሱ ያልተፈቀደችውን ሴት በምኞት በጋለ የወሲብ ስሜት የተነሳ የሚነካት ሰው፣ በፍርዱ ቀን እጁ ከአንገቱ ጋር ታስሮ ይቀሰቀሳል፡፡ እርሱ ስሟት ከሆነ ከንፈሮቹ በእሳት ውስጥ ይቃጠላሉ፡፡ በመጨረሻም እርሱ ዝሙት ላይ ወድቆ ከሆነ ጭኖቹ እኔ ያልተፈቀደ ነገር ላይ ተኝቻለሁ ሲሉ በፍርዱ ቀን በርሱ ላይ ይመሰክራሉ፡፡ ከዚያ ከአላህ ቁጣ የተነሳ ወደርሱ ይመለከታል፡፡ በዚህን ጊዜ የሰውየው የፊቱ ሥጋ ተገሽልጦ ይወድቃል፡፡ እርሱም በትዕቢት እኔ ፈፅሞ ይህንን አልሠራሁም የሚል ከሆነ ከዚያም ምላሱ እኔ ያልተፈቀደን ንግግር ተናግሬያለሁ ሲል ይመሰክርበታል፡፡ እጆቹም እኔ ያልተፈቀዱ ነገሮችን ነክቻለሁ ይላል፡፡ ዓይኖቹም እኔ ያልተፈቀደውን ነገር አይቻለሁ ትላለች፡፡ እግሮቹም እኔ የሄድኩት ወደተከለከሉ ነገሮች ነበር ይላሉ፡፡ በመጨረሻም ብልቱ እኔ በገቢር እዋልኩት ይላል፡፡ ጠባቂ መላእኮችን በተመለከተ አንዱ እኔ ሰምቻለሁ ሲል ሌላኛው ደግሞ እኔ ፅፌዋለሁ ይላሉ፡፡ በመጨረሻም አላህ እኔ ሁሉንም አውቃለሁ፣ ነገር ግን ለርሱ ደብቄለት ነው እንጂ ይላል፡፡

ከዚያም አላህ (ሱ.ወ) ለመላኢኮቹ እርሱ ይቀጣ ዘንድ ወደ ጀሀነም🔥🔥🔥🔥እሳት ውሰዱት፡፡ የኔ ቁጣ በነዚያ ከኔ ምንም ሐያእ በማያደርጉት ላይ በረታች ይላል፡፡ ይህም በአላህ (ሱ.ወ) በቁርአኑ  በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውሞ ይሠሩት በነበሩት እኩይ ነገር በሚመሰከሩባቸው ቀን ከባድ ቅጣት አላቸው ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ (አን-ኑር 24:24), (ኢማም ዘሀቢ አል-ከባኢር ውስጥ እንደጠቀሱት)


🌙🌙  በዑለሞች አተያይ የእጅ ዚና ሲባል የዘመኑ ቴከኖሎጂን በመጠቀም ባዳ ሴቶችና ወንዶች የሚፃፃፉትና የሚላላኩት የተለያዩ ሕገወጥ መልዕከቶችም በዚህ ውስጥ ይጠቃለላሉ፡፡
☞ስልክ ቁጥሮችን የሚከትቡና
☞ቴክስት ሜሴጆችን የሚፅፉ ጣቶችም ከእጅ ይቆጠራሉ፡፡
☞የሞባይል ሰክሪኖችን የሚነካኩና
☞በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ ቻት ሴክስን፥ ፎን ሴከስንና የወሲብ ፊልምን ሳይቀር ጠቅ ጠቅ የሚያደርጉ ጣቶችም በዚሁ ውስጥ ይካተታሉ፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ይህ እውነታ ወደ ዓይን ዚና፣ ወደ ምላስ ዚና፤ . ጆሮ ዚናና ወደሌሎችም ሁሉ በየፊናቸው በሚኖራቸው ተሳትፎ ልክ ይለጠጣል፡፡


╔══════════════════════╗
    🔰🔰 #የጆሮ_ዚና_ምንነትና_አደገኛነት 🔰🔰    
╚══════════════════════╝

የጆሮ ዚና ማለት ብዙ አይነት ነዉ ከነዛ ዉስጥ በጥቂቱ

☞ወሲባዊ ውይይቶችን ማዳመጥ፣
☞ወሲብ ቀስቃሽ ዘፈኖችን መስማት
☞በስልክና በሌሎችም የርቀት መገናኛ ዘዴዎች ስለወሲብ መስማትና ማዳመጥ፣
☞የወሲብ ፊልሞችን ከላሲካል ማጀቢያዎችን ማዳመጥ፣ ወዘተ ከጆሮ ዚና የሚቆጠሩ ናቸው::

   ብዙውን ጊዜ ግን ከዚና ጋር የተያያዙ ድምፅ-ነክ ነገሮች ወደ ጆሮ የሚገቡት ዘፈንን በማዳመጥ በኩል ነው፡፡ እንደሚታወቀው ዘፈን ዛሬ ዛሬ የዚና ነዳጅ ሆኗል፡፡ እዎ ዘፈን ከዝሙት አበይት መዳረሻ መንገዶች አንዱ ከመሆኑም ባሻገር ልብን ያሸፍታል፤ በአድማጩ ልብ ላይም ኒፋቅን ያሰርፅበታል፡፡ ይህም በግለሰቦች ኢማናዊ ኃይላቸው ላይ ከፍተኛ ድከመትንና መንኮታኮትን ያስከትላል፡፡

✏️✏️ ዘፈንን አስመልከተው ታላቁ ሊቅ ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) አል-ፈዋኢድ ውስጥ እንዲህ ብለዋል፦
የዘፈን ፍቅርና የቁርአን ፍቅር በአንድ ግለሰብ ልብ ውስጥ በጋራ አይመጡም! አንዱ ሌላውን የሚያስወጣው ቢሆን እንጂ፡፡”

✏️✏️ አንድ ሌላ ሰለፍ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፡-

መሳም የወሲብ፤ ዘፈን የዝሙት፣ ማየት የፍቅር፣ በሽታ የሞት መነሻ እንደሆኑ ሁሉ ወንጀልም የከህደት መነሻ ነው፡፡,,ብለዋል




╔══════════════════════╗
🔰#ወንዶች_ሴትን_በሀራም_መቀያየር_ደስታ_የለዉም
╚══════════════════════╝

    አንዳንድ ጋጠወጦች (ፋሲቆች) ሴት ሲያዩ በሙሉ ዓይናቸው አፍጠው ያያሉ፡፡ ልባቸውም ይከተላታል፡፡ ቁመናዋንና ፈታኝ ውብቷን በማሰላሰል ይባዝናሉ፡፡ ሊያግኟትም ይመኛሉ፡፡ ብሎም ያዱንያ ጣፋጭ ነገር፣ ደስታ ሁሉ በርሷ ውስጥ የተወሰነ ብቻ መሰሎ ይታያቸዋል፡፡ የዱንያ ሰቆቃና ስቃይ ደግሞ እርሷን በማጣት የሚመጣ ይመስላቸዋል፡፡በዱንያ ውስጥ የሚፈለገው ሁሉ በርሷ ውስጥ ያለ መስሎ ይታያቸዋል፡፡ ባስታወሳት ቁጥር ያብድላታል፡፡ ይህን ሁሉ አስቦ ያግኛት እንደሆነ ደስታው የግማሽ ደቂቃ ያህል ብቻ ሆና ትቀራለች፣ ትከስማለች፡፡ ሳይጠግባት ይሰለቻታል፡፡

በሐሳቡ ሲስላት የነበረው ነገር ሁሉ ከንቱ ይሆንበታል፡፡ ከዚያም ስለሌላ ሴት ማሰብ ይጀምራል፡፡ የሚያስባትን ሊያገኝ ደግሞ እንደዚሁ ተስፋው ይከስማል፡፡ እንደገና ሌላ ይመኛል፡፡ ከዚህችኛዋ ያጣውን ደስታ ከሌላኛዋ የሚያገኝ መስሎ ይሰማውና እንደገና ሌላ ለማግኘት ማሰላሰል ይጀምራል፡፡ ይህችንም ሲያገኝ እንደዚሁ ተስፋው ይከስማል፡፡ እንዲህ እያለ ሊያገኘው የማይችለው ደስታን በመፈለግ እንደባዘነ አንዷን ካንዷ ሲያቀያይር አንድም ቀን የፈለገውን እርካታ ሳያገኝ፣ ሐሳቡ ሳይሞላለትና ሳይጠግብ ዕድሜው ያከትማል፡፡👇👇👇
እናንተ ሰዎች ሆይ! እርካታን ማግኘት ማለት ምንድን ነው? እርካታን ማግኘት ማለት ወሲባዊ ግንኙነት ብቻ ነው ትላላችሁ? አይደለም! አይደለም! ሰዎች፡፡ እርካታን ማግኘት ማለት ወሲባዊ ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ልብ ለልብ መገናኘት፣ ሴትና ወንድ ባንድ በተቀደሰ የትዳር ትስስር ሥርዓት ውስጥ መተሳሰር ነው፡፡



 ✏️✏️ለሴቶችም እንደዚሁ የዚህ ዓለም ወንዶች ሊያረኳቸው ቢሰበሰቡም እርካታን አያገኙም፡፡ ግን ይሆን አልረካ ያለ ስሜት አንዲት የሐላል ሴት አንድ የሐላል ወንድ ያረኩታል፡፡

ሰዎች ሆይ፤ አንድ ሰው ገንዘቡ ሀብቱ እጁን ወደፈለገው ለመሰደድ ቢያስችለውም ጉልበቱ ይችል ይሆን? አካሉስ ስሜቱን መሸከም ይችል ይሆን? ቢችል እንኳ አንድ ቀን መሸነፉ! በበሽታ መጠቃቱ አይቀርም፡፡ ማድረግ እየፈለገ አይችልም፡፡ ዓይኑ እያየ እያማረው ያጣዋል፤ ያቅተዋል፡፡ እንደዚህ ከሆነ ታዲያ ለምን ከወንጀሉ አይታቀብም? አካሉንና ከብሩን ለምን አይጠብቅም? አካሉንና ከብሩን አጥቶ፣ነፍሱን በበሽታ አስጠቅቶ፣ያማረውን እርካታ ከማጣት በአዱኛ ከመሰቃየት በአኼራ ወደ ገሀነም ከመወርወር አሁን ቢቆጠብ አይሻለውም ትላላችሁ?

ወንድሞቼ ሆይ! ከአላህ (ሱ.ወ) አፈጣጠር ተአምራት ውስጥ አንዱ በቁንጅና የሚመሳሰሉ ሴቶችንም ሆነ ወንዶችን አለመፍጠሩ ነው፡፡ ሴቶች ሁሉ አይመሳሰሉም፡፡ ወንዶችም እንደዚሁ:: ከሁሉም ሴቶች ወንዶች የሚገኘው እርካታም አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ ነገር ግን ሕጋዊ ባለትዳሮች በተፈጥሯቸው የሰመረ ወሲባዊ ጥምረትን መፍጠር የተሻለ እርካታን ማግኘት ይችላሉ፡፡

#በቀጣይ_ክፍል ☞ዝሙት ስለሚያመጣዉ አደገኛ መዘዝ ይቀርባል


 #ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ሸርሙጣ፣ሴተኛ አዳሪ፣የቡና ቤት ሴት፣ሸሌ፣ባር ሌዲ፣ ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ሂያጅ፣አመንዝራ፣ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ ወንድኛ አዳሪ፣ ወንድ ሸሌ፣ ሸርሙጣ፣ ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል
ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት አላህ ይወፍቀን


#ምዕራፍ
ይቀጥላል...
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
           🔰 #ምዕራፍ_ስምንት
                አሚር ሰይድ



  ዛሬ ደግሞ እንደ ቀልድ የያዝነዉ ዝሙት ከአኼራ ቅጣት ከጀሀነም ቀጥሎ በዱንያ የተለያዩ ችግሮችን ይዞ ብቅ ብሏል ከዛ ችግሮች የተወሰነዉን እንዳስሳለን

╔══════════════════════╗
   🔰 #የኤች_አይቪ_ኤድስ_በሽታ 🔰         
╚══════════════════════╝

    በመጀመሪያ ደረጃ እዚህ ቻናል ላይ ኤች አይቪ ኤድስ ያለባቸዉ ተከታታዮች እንዳሉ አቃለሁ ..ብዙዎቻችሁ ከቤተሰብ ከልጅነት ጀምሮ በበሽታዉ እንደተያዛችሁ አቃለሁ..እናም ይህን ፁሁፍ ሲዘጋጅ እናንተን ለመንካት አስቤ አይደለም፡፡እናንተንም አይመለከትም ..ይህ ፁሁፍ አላማዉ አሁን ላይ ወጣቱ ዚናን ቀላል አድርጎ ይዞ በሀራም እየተሽከረከረ ስለሆነ ለእነሱ ማስተማሪ ቢሆን ብየ በማሰብ የተዘጋጀ ነዉ፡፡



 ✏️✏️ከዝሙት አበይት መዘዞች መካከል አንዱና በመላው ዓለም የተሠራጨዉ የዝሙት ካንሰር የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በሽታ ነው፡፡ ይህ በሽታ በገዳይነቱ አቻ የሌለው ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ መኖሩ የተረጋገጠው እኤአ 1981 በአሜሪካ ነበር፣ በ UNAIDS መረጃ መሠረት ኢኤ.አ በ2007 በዓለም አቀፍ ደረጃ በኤች.አይ.ቪ ኤድስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 33.2 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን፣ እስከ 2.4 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በዚያው ዓመት በኤድስ የተነሳ ሞተዋል፡፡ በዚያው ዓመት እስከ 4 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

መረጃው አያይዞ እንደጠቆመው በቫይረሱ ከሚያዙት አዳዲስ ሰዎች ውስጥ 40 በመቶው የሚሆኑቱ ዕድሜያቸው ከ15-24 ዓመት የሚሆኑ ወጣቶች ነበሩ፤ ☞ከሰሐራ በታች ባለው ክፍለ አህጉር ደግሞ ሴቶች ከአጠቃላይ የኤችአይቪ ተጠቂዎች ውስጥ 60 በመቶውን፣
☞ አዲስ ከሚያዙት ውስጥ ደግሞ 77 በመቶውን ድርሻ ይዘዋል፡፡ በውጤቱም ኤች.አይ.ቪ የዚህች ዓለም ትልቁ ሰጋት ሆኖ ተገኝቷል፡፡


📌📌እንደው ለአብነት ያህል የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በዓለም፣ በኢትዮጵያና በአዲስ አበባ ያለውን ሥርጭት በመጠኑ ብናይ ጥሩ ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ እኤአ በ2011 UNAIDS ባወጣው ሪፖርት መሠረት ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የተገኘባቸው ወገኖች 34.2 ሚሊዮን ሲሆኑ፣
☞በኢትዮጵያ 789,900 ዜጎች!
☞በአዲስ አበባ ደግሞ 91,680 ሰዎች ላይ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ተገኝቶባቸዋል፡፡

አሁን ደግሞ በቅርብ በተደረገው ጥናት መሠረት የበሽታው ሥርጭት እምብዛም ሳይቀንስ
☞በኢትዮጵያ 741,487 የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው የሚገኝባቸው ወገኖች እንዳሉ ታውቋል፡፡ በዚህም መሠረት በሀገር አቀፍ የበሽታው ሥርጭት 1.2% ሆኗል፡፡


📌📌በ2008 ደግሞ ኢትዮጵያም በኤድስ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው አገራት አንዷ ስትሆን
🔸አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ሰዎች በኤች.አይ.ቪ ተይዘዋል፤
🔸 129 ሺህ አዳዲስ ሰዎች ደግሞ በየዓመቱ ይያዛሉ፡፡
🔸 ዕድሜያቸው ከ15-49 ባሉ አዋቂዎች ላይ ሶስተኛው የሞት መንስኤ ከመሆኑ በላይ በየዓመቱ ከ30ሺህ የሚበልጡ ሕፃናት ኤች.አይ.ቪን በደማቸው ይዘው ይወለዳሉ፡፡



📌📌 በአዲስ አበባ ደግሞ 117.320 ኤች.አይ.ቪ በደማቸው የሚገኝባቸው ወገኖች እንዳሉ የተጠቆመ ሲሆን፣ የበሽታው ሥርጭትም 3.5% ደርሷል፡፡ በፆታ ስብጥርም
🔻ሴቶች 4.9% እና
🔻 ወንዶች 2.5% እንደሆነ EPHl estimate 2015 ያሳያል፡፡ ስለዚህ ይህ በሽታ አምራችና የተማረ (ብዙ የሥራ ልምድ ያለውን) እና ዕድሜያቸው ከ15-49 ያሉ ዜጎችን፤ በተለየ ሁኔታ ሀገር ገንቢ የሆኑ የሕብረተሰብ ከፍሎችን በማጥቃት በአጠቃላይ በሀገር ዕድገት ላይ ትልቅ እንቅፋት ሆኗል፡፡

🧷በደቡብ አፍሪካ ከ5 ሰዎች አንዱ ኤች.አይ.ቪ አለበት፡፡
🧷 በድሬዳዋ ከ10 ሰዎች መካከል በ2ቱ ላይ ቫይረሱ አለባቸው፡፡
🧷አዲስ አድማስ ሕዳር 17 ቀን 2009 ባወጣዉ ዘገባ መሠረት ከ4 ሴተኛ አዳሪዎች መካከል አንዷ ኤች አይ ቪ አለባት፤

....በዓመት 17,000(አስራ ሰባት ሺህ) ሰዎች በላይ በቫይረሱ ይያዛሉ፡፡ በቀን ደግሞ ከ40 ሰዎች በላይ በበሽታው ይሞታሉ፤ እንደዚሁም በዓመት ከ24 ሺህ ሰዎች በላይ በቫይረሱ ይያዛሉ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ቫይረሱ የተገኘባቸው ዜጎች ብዛት 740 ሺ ሲሆኑ ከነዚህም ውሰጥ አብዛኞቹ ባለትዳሮች ናቸው፤

የሴት ተጠቂዎች 450 ሺህ የወንዶች ደግሞ 290 ሺህ ነው ፡፡በመኪና አደጋ ህይወታቸዉን ከሚያጡት ይልቅ በኤድስ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በ500% ይበልጣል፤ በሌላ አነጋገር ከዋና ገዳይ መንስኤዎች መካከል አንዱ፣ ዛሬም ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ነው፡፡


,,, የዝሙት መዘዞች በሀገሪት ላይ ከፍተኛ ወጪን ያስከትላሉ፡፡ ለምሳሌ ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መድኃኒት መግዣና ሕከምና የሚወጣው ከፍተኛ ወጪ የዝሙት መዘዝ ነው፡፡ ለኮንደምና ለእርግዝና መከላከያ መድኃኒቶች ከፍተኛ ወጪ ይወጣል፡፡ ዛሬ ዛሬ በዓለም ደረጃ ድህነትን ለመዋጋት ሳይሆን የዝሙትን መዘዞች ለማከም ከፍተኛ ገንዘብ እየፈሰሰ ነው፡፡ ለምሳሌ ጁን 9 ቀን 2016 የወጣው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የበጀት ጥየቃ እንደሚያመለከተው ከሆነ ለ2017 የበጀት ዓመት ለፌዴራል ኤች.አይ.ቪ መርሃ ግብር 34 ቢሊዮን ዶላር እንዲመደብ ጠይቋል፡፡ ከዚህ ፈንድ ውስጥ 27.5 ቢሊዮን ዶላር ለሀገር ውስጥ ፀረ- ኤች.አይ.ቪ መርሃ ግብር የሚውል ሲሆን 6.6 ቢሊዮን ዶላር ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚደረግ ፀረ-አይ.አይ.ቪ ሥራዎች የሚውል ነው:: የ2017 የበጀት ዓመት የኤች አይ ቪ ጭማሪ ጥየቃ ከባለፈው ዓመት የ1 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪን ያሳየ ሲሆን የዚህም ምክንያት ለሕከምናና ለመከላከል የሚውለው ውጪ ከፍ ማለት አለበት ከሚል እሳቤ የተነሳ እንደሆነ ከዋይት ሐውስ የወጣው መረጃ ያመለከታል፡፡

....እንግዲህ ይህ ሁሉ ገንዘብ በኤች.አይ.ቪ ላይ ሲፈስ በተቃራኒው ድህነትን ለማጥፋት ቢውል ኖሮ ምን ያህል ለውጥ እንደሚያመጣ ለአፍታ እናስብ፡፡ ይህ እንግዲህ የዓለማችን ከፍተኛ ገንዘብ ወዴት እየሄደ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ ዝሙት ቁጥር 1 ዓለም አቀፍ እኩይ ሀይማኖት በመሆኑ ለዓለማችን ድህነትን ማስወረሱን ያረጋግጥልናል፡፡

╔══════════════════╗
🔰 #የእርግዝና_መከላከያ_ፓስትፒል 🔰
╚══════════════════╝
    ☞በአፍሪካ ዉስጥ በአመት 8ሚለየን ዉርጃ ይካሄዳል፡በጦርነት ግን 8 ሚሊየን ህዝብ አያልቅም::


    ወጣቱ ዘንድ ዝሙትን መፈፀም ተራ ነገር ሁኗል፡ ነገር ግን እንደፈለጉ የዝሙት ዛር እንዳይጫጫሱ እርግዝና ትልቅ እንቅፋት ሆኖባቸዋል:: በብልግናው እንደፈለጉ እንዳያተረማምሱ እርግዝናው ገድቧቸዋል፡፡ የአሁን  ወጣቶች ትልቁ ስጋትም እርግዝናው እንዳይፈጠርና ሆድ ከፍ እንዳይል ነው፡፡ ግን #ፖስትፒል ከጭንቀታችን ገላግሎናል ይላሉ፡፡ እንደነርሱ እሳቤም እርግዝናን በፖስትፒል ሸውደዋል፡፡ ይህም በተራው የፖስትፒል ጥገኞችና ሱሰኞች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።በተደጋጋሚ ፒስትፒል መጠቀሙ የሚያደርሰዉን ጉዳት አላወቁትም፡፡ አንድ ሴት በህይወት ዘመና ፒስትፒል ልዉሰድ ካለች ከ3ቴ በላይ መዉሰድ ከባድ የህይወት አደጋ ተጓዳኝ በሽታ ያመጣል፡፡👇👇👇
ነገር ግን ይሄን ባለማወቅ በብልግናው ረገድ ይኸው እንከብል የተለመደ ሱስ ሆኗል፡፡ ዝሙት እራሱን የቻለ አደገኛ ሱስ ነው፡፡ የእንከብሉ ሱስ ሲታከልበት ደግሞ በሱስ ላይ ሌላ ደባል ሱስ ስለሚሆን አደጋውን አያድርስ ያስብላል፡፡ ታዲያ በፖስትፒል ሱስ የተደፋፈረውና ይበልጥ ለማተረማመስ የልብ ልብ የተሰማው ወጣት ዓላማው ዝሙትን እንተው፤ ከዝሙት እንራቅ የሚለው ሳይሆን ዝሙትን ልማዳችን አድርገን እንውሰድ የሚል ይመስላል፡፡ ለዚህም ማረጋገጫ የፖስትፒል ሱሰኞች መሆናቸው ነው::

📚 ዘመናዊዎቹ የሸገር ወጣቶች በልቅ ወሲብ አየተጫጫሱ ነው፡፡ በአዲስ አበባ በተደረገ ጥናት  ወሲብ ፈፅመው ከሚያውቁ 24 ሴቶች ውስጥ ቢያንስ ለአንድ እና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ሁሉም ልቅ ወሲብን ፈፅመዋል። ከእነዚህ ውስጥ

ተመርምረን የጋብቻ ጥርጊያ መንገድ እያሰናዳን ስለሆነ የሚል ምክንያት ሶስቱ ያቀረቡ ሲሆን፣
አራቱ በባዶ ወሲብ ከመፈፀማቸው በፊት የኤች.አይ.ቪ የደም ምርመራ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
17ቱ ግን ቅድመ የደም ምርመራ ሳያከናውኑ አንዴ እና ከዚያ በላይ ለሚሆን ጊዜ በልቅ ወሲብ ተደስተዋል፡፡ ሁሉንም የሚያመሳስላቸው ወሲብ ከፈፀሙ በኋላ ሁሌ ፖስትፒል መጠቀማቸዉን ተናግረዋል፡፡


     ╔═════════════════╗
      🔰 #የሴቶች_ዉርጃ_መበራከት 🔰    
     ╚═════════════════╝



እኤእ የ2014 የውርጃ ዳታ እንደሚያሳየው
☞በመላው ሀገሪቷ 73,167 ውርጃዎች ተካሄደዋል፡፡
☞በአዲስ አበባ ውስጥ ደግሞ 135,999 ውርጃዎች ተፈፅመዋል፡፡ ይህም በቀን በአማካይ 373 ውርጃዎች ይካሄዳሉ ማለት ነው፡፡

አሁን የሚወጡ መረጃዎች ደግሞ በአዲስ አበባ ውስጥ የውርጃ መጠኑ በእጥፍ መጨመሩን ያሳያሉ፡፡
በአፍሪካ ደግሞ በዓመት 8 ሚሊዮን ውርጃ ይፈጸማል፡፡ ከዚህም ውስጥ የኢትዮጵያ ብቻውን አስር ከመቶውን ይዟል፡፡

⚡️⚡️በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ በሁለት ጥንዶች መካከል ከጋብቻ በፊት ብዙውን ጊዜ ያልተፈለገ እርግዝና ሲከሰት እንስማለን፡፡ ታዲያ ይህ ችግር እጅጉን የሰፈና የበዛ በመሆኑ በተለይ በአፍሪካ ቲቪ የፋታዋ ፕሮግራም ላይ በብዛት የሚጠየቀው ይህንኑ ነጥብ አስመልከቶ ነው፡፡ በተጨማሪም በአዲስ አበባ በርካታ ኢማሞች በተደጋጋሚ እየተደወለላቸው ከጋብቻ ውጭ ላረገዙ ሴት ልጆቻቸው ኒካህ እንዲያስሩላቸው በወላጆች ይጠየቃሉ፡፡

╔══════════════════════╗
   🔰 #ዓረብ_አገር_ያሉ_ኢትዮጵያዉያን
          #ሙስሊሞች_የሚስተዋሉ_ችግር 
╚══════════════════════╝



    ዓረብ አገር ያሉ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ዘንድ ከጋብቻ ዉጭ እያረገዙ ኒካህ ይታሰርንል በማለት በብዛት ሥር ሰድዶ ይገኛል፡፡ ደግሞ ከቁጥጥር ከአቅም በላይ ሥር ሰድዶ የሚገኘው ችግር ማግባትና መፍታት ሱስ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡ አረብ ሀገር አንድ ወንድ ምናልባትም በዓመት ውስጥ በአማካይ ሁለት ጊዜ ይፈታል፤ ሁለት ጊዜ ቀያይሮ ያገባል፡፡ ይህም እንደ ልማድ ተወራርሶ በርካቶች ይህንኑ የሙጥኝ ብለውታል፡፡ እነርሱ ዘንድ መፍታትና ማግባት ውሃ የመጠጣትን ያህል ቀላል ሆኖ ይታያል፡፡


╔══════════════════════╗
  🔰 #በአረብ_ሀገር_የኢትዮጲያ_ሴቶች
              #በዝሙት_መሰማራት    
╚══════════════════════╝

    ሌላው ዓረብ ሀገር የተለመደው ችግር የሴቶች ልቅነትና በተለያዩ የዝሙት ሥራ ላይ መሰማራት ነው፡፡ በርካታ ሰዎች እማኝነታቸውን በመናገር እንደገለፁት በተለይ ዱባይ ያሉ ኢትዮጵያዉን ሒጃቢ ሴቶች ሳይቀሩ በየሀገሩ ካሉ ዜጎች ጋር ይማግጣሉ፡፡ ብሎም በርካታ ቋንቋዎችን በአጭር ጊዜ በመማር በርካታ ወንዶችን ማጥመድ እንደቻሉ ይነገራል፡፡ እነዚህ ሴቶች ወንድን የጫማን ያህል በመቀያየር የሚታወቁ ናቸው፡፡ የተለያዩ ቋንቋዎችንም በመናገር ተከነውበታል፡፡
ስራቸው ዚና ብቻ ሁኖ ሀብት የሚያጠራቅሙ በዙ ኢትዮጲያን ዱባይና ሳዑዲአረቢያ እንደሚገኙ ብዙ ሰዎች ምስክረት ሰጥተዋል፡፡ከዚህ ስራ አላህ ተዉበት ወፍቋቸዉ የተገላገሉ ሴቶች በዱባይና በሳዑዲ አረቢያ በጣጣም ልቅነት እንዳለ ይመሰክራሉ፡፡



╔══════════════════════╗  
 🔰#አባታቸዉ_በዉል_የማይታወቅ_ልጆች_መበራከት     
╚══════════════════════╝

የዝሙት ትልቁ መዘዝ ለዝሙት ልጆች መበራከትና ከዚህም የተነሳ በማህበረሰቡ ውስጥ የተለያዩ ወንጀሎች መበራከትና መስፋፋት ነው፡፡
  ዝሙት እና አባታቸው በውል የማይታወቁ ልጆች የታጨቁባት ዘመናዊዋ ዓለማችን ምን ደረሰቸ???

   ጥናቶች እንደሚያመለከቱት
☞ 40% አሜሪካዉያንና
☞ 50% እንግሊዛዉያን አባቶቻቸውን በውሉ አያውቁም፡፡ (ዓለምን የሚመሩት እነዚሁ መሆናቸውን ልብ ይበሉ፡፡)

☞እንደዚሁም 65% ስዊዘርላንዳዉያን አባቶቻቸውን አያውቁም::
☞ በ እንግሊዝ 2/3ኛው ሕፃናት የሚያድጉት በነጠላ ወላጆች አማካኝነት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር እነዚህ ሁሉ ከጋብቻ አልጋ ዉጭ የተወለዱ ናቸው፡፡ የዓለም አባቶቻቸውን በወጉ በማያወቁ ሕዝቦች መመራትም ዝሙት በዓለም አቀፍ ደረጃ ምን ያህል ስር እንደሰደደ ይጠቁማል። ሌላው ጥናት እንዳመለከተው አሁንም 40% እሜሪካዉያን ልጆች የሚወለዱት ከነጠላ ወላጆች (በትዳር ካልተጣመሩ) ነው::

  እንግሊዞች ከመቶ ርዕሰ መምህር አንድ አባት ይሻላል የሚል አባባል ቢኖራቸዉም ግን 2/3ህፃናት የሚያድጉት ያለ አባቶቻቸዉ እንክብካቤ ከእናቶቻቸው ጋር ብቻ ነው:


✏️✏️«እንደ ግለሰቦች ሁሉ ሀገር እና ማህበረሰብም ይታመማሉ፡፡ በቶሎ ሕክምና ካለገኙም እንደ ግለሰቦች ሁሉ ሀገርና ማህበረሰብም ይሞታሉ፡፡ (ዶ/ር ዴሚ አሚሮስት)


✏️✏️አንድ ሀገር ታሟል፤ ከባድ ማህበራዊ ውድቀትም ከፊቱ ተደቅኗል.. የሚባለው የማህበረሰቡ አስኳል የሆነው ወጣቱ በተሳሳተ አስተሳሰብ ሲሞላና በተሳሳተ የሕይወት ጎዳና ላይ ሲጓዝ ነው፡፡.. (ዶ/ር ዴሚ አሚሮስት)

#በቀጣይ_ክፍል ስለቦይ ፍሬንድ ገርል ፍርድ የዝሙት መግቢያ መንገድና ...በፊት የቦይፍሬንድ አመጣጥ ከምዕራባዉያን እንዴት ወደኛ ጓዳ እንደገባ እንዳስሳለን

#ምዕራፍ
ይቀጥላል........

አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
           🔰 #ምዕራፍ_ዘጠኝ
                አሚር ሰይድ

╔══════════════════════╗ 
🔰--------------🔰-------------🔰 #ቦይ_ገርልፍሬንድነት( #የወንድ_ሴት_ፍቅረኛነት)  
╚══════════════════════╝


አላህ (ሱ.ወ) በተከበረ የቁርአን ቃሉ እንዲህ ይላል፡-
   መጥፎ ሥራዎችንም ከእርሷ የተገለፀውንም የተደበቀውንም ሁሉ አትቅረቡ፡፡ (አል-አንአም 151)

       በዓለም አቀፍ ደረጃ ለዝሙት መንሰራፋትና ይፋ መውጣት ትልቁን ድርሻ ያበረከተውና ወጣት ሙስሊሞችን ሳይቀር ያጠመደው ዓለም አቀፉ የዝሙት መረብ ቦይፍሬንድ እና ገርልፍሬንድ የሚባለው ሕገ-ወጥ የወንድና የሴት ግንኙነት ነው። ይህ የተኩላን ለምድ ለብሶ የመጣው የምዕራቡ ዓለም እኩይ ባህል የዝሙት ሌላኛው ስሙ ነው፡፡ ለሰው ሠራሽ የዝሙት መዳረሻ መንገዶች ዋናው ምንጭም ይኸው ሚዲያ መራሹ የዝሙት ርዕዮት ነው፡፡ ይህ ርዕዮትም ታላቅ የዝሙት አብዮትን አስከትሏል፡፡ ዝሙትም በተለያዩ ማህበረሰቦች ውስጥ ስር እንዲሰድ ከፍተኛ የሆነ ሕገወጥ ወሲባዊ ንቅናቄን አቀጣጥሏል፡፡ በርካቶችም በዚህ ንቅናቄ ውስጥ አቀንቃኝ ሆነው ብዙ ተከታዮችን አፍርተዋል፡፡

   የምዕራቡ ዓለም በሥልጣኔ ስም ወደ ዓለም ካሰረፃቸው እኩይ ነገሮች ዋናዋናዎቹ
☞ዝሙት
☞ቦይፍሬንድነት
☞ግለኝነት
☞የወሲብ ፊልም
☞ አልኮሊዝም  ሲሆኑ ከነኝህ መካከል ግን በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ ሳይቀር  ተቀባይነትን ያገኘው ቦይገርልፍሬንድነት ነው:: የተኩላ ለምድን ለብሶ ወደ ሙስሊሞች ቤት ዘው ብሎ የገባው ፀያፍ ነገር ቢኖር ይኸው ቦይ ገርልፍሬንድነት ነው:: የሚገርማችሁ ከቦይገርልፍሬንድነት በስተቀር ዝሙት እንኳን ሙስሊሞች ቤት የገባው እየተሳበና እየዳኸ ነው፡፡

   #በብዙዎች_ዘንድ ቦይ-ገርልፍሬንድነት ለወደፊቱ ትዳር መሰረትን ይጥላል ተብሎ በየዋህነት ስለሚወሰድ ይኸው ደዌ በዚሁ ደካማ ጎን በመግባት ሰዎችን በቀላሉ ለማጥመድ ችሏል፡፡ ይህም የቦይ-ገርልፍሬንድነት አደገኛነትን ያሳያል፡፡

ሌላው የቦይ–ገርልፍሬንድነት አደገኛነቱ ግንኙነቱ በራሱ ገና ከጅምሩ ሕገወጥ መሆኑ ነው፡፡ ወሲብ እንኳን ባይኖርበት ድርጊቱ ሙሉ በሙሉ ሕገወጥና ለበርካታ ዓመታት መዝለቅ የሚችል ነው፡፡ ከዚህም በላይ ለማህበረሰቡ መጥፎ አርአያ የሚሆን ነው፡፡ የማህበረሰቡን ወሲባዊ እሴቶች የሚሸረሽር ነው፡፡ ወሲብ እንኳን ባይኖርበት ሁለመናው ይፋዊ ዝሙት ነው፡፡

ለምሳሌ አንድ ወንድ አንዲትን ሴት በገርልፍሬንድነት ይዞ ሲያበቃ ከርሷ ጋር በግልፅ ቢታይና ብሎም እርሷን በገርልፍሬንድነት ስም ለሌሎች ቢያስተዋውቃት ይህ ሁሉ ድርጊቱ ይፋዊ ዝሙት ነው፡፡ ሕገወጥ ወሲብ ከታከለበት ደግሞ ወንጀሉ እየተነባበረ ይሄዳል፡፡


╔══════════════════════╗
  🔥 #የቦይፍሬንድ_እና_ገርልፍሬንድ_ምንነት🔥
╚══════════════════════╝



  በርካታ ሙስሊሞች፣ በተለይም ወላጆች ቦይፍሬንድ እና ገርልፍሬንድ የሚሉትን ቃላት ሲሰሙ ተራ የወንድና የሴት ጓደኝነት ስለሚመስላቸው እንዲሁ እንደዋዛ ያዩታል፡፡ ከዝሙት ጋር የሚያያዝም አይመስላቸውም፡፡ ምዕራባዊ ባህል መሆኑን እንጂ ሕገወጥ መሆኑን አይገነዘቡትም፡፡ ሥልጣኔ እንጂ ሰይጣኔ መሆኑንም አያስተውሉትም፡፡

ከዚህም የተነሳ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ይህንኑ እኩይ ባህልን በትዕግስት ተቀብሎ በራሱ ውስጥ ለማንሰራፋት ሁሉ በቅቷል፡፡ ይፋም ወጥቷል፡፡ አሁን አሁንማ #እናቶች_ሳይቀሩ «ከያዝሽ አይቀር ደህናውን የቦይፍሬንድ ያዢ› እያሉ ልጆቻቸውን ማበረታታት ጀምረዋል፡፡ በዚህ ይሁንታ በመደፋፈርም ሴት ልጆች ሳይቀሩ ቦይፍሬንዶቻቸውን ለወላጆቻቸው ማስተዋወቅ ጀምረዋል፡፡ የሙስሊም ት/ቤቶች ሳይቀሩ የቦይ ገርልፍሬንድ መፈልፈያዎች ሆነዋል፡፡


💫💫 ቦይ ፍሬንድ ማለት የአንድ ግለሰብ በሮማንቲክ ግንኙነት ውስጥ በፍቅር ወዳጅነት ውስጥ መደበኛው የወንድ የወሲብ አጋሩ ማለት ነዉ:: ባጭሩ ቦይ ፍሬንድ ማለት የአንድ ግለሰብ ሕገወጥ ባል ማለት ነው::

#ይህ_አንድ ግለሰብ የተባለው አካል ወንድም ሴትም ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ አንዲት ሴት መደበኛ የወሲብ አጋር ወይም ቦይ ፍሬንድ መያዝ ትችላለች ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ቃሉን መገደብ ስለማንችል #አንድ_ወንድም ቦይፍሬንድን መያዝ ይችላል ማለት ነው:: ይህ ደግሞ #ለግብረሰዶማዊነት_ግንኙነት የሚውል ነው፡፡ ይህንን ቃል ወደ አማርኛ ስናመጣው ደግሞ በአንድ ቃል መተካት አዳጋች ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን የከንፈር ወዳጅ የሚለው ትንሽ ይቀርበዋል፡፡

የከንፈር ወዳጅ የሚለውም ድፍን ያለ ስለሆነ በመጠኑም ቢሆን የቦይ ፍሬንድነትን በርካታ መገለጫዎችን በውስጥ ይይዛል፡፡

#በሌላ_በኩል_ገርልፍሬንድ ሲባል የአንድ ግለሰብ በሮማንቲከ ግንኙነት ውስጥ ወይም በፍቅር ግንኙነት ውስጥ መደበኛው የሴት የወሲብ አጋሩ ናት፡፡ ከመደበኛው የወሲብ አጋር ፆታ በስተቀር ቦይፍሬንድና ገርልፍሬንድ ምንነታቸው ተመሳሳይ ነው፡፡



╔══════════════════════╗
 🔥#የቦይፍሬንድ_እና_ገርልፍሬንድ_አመጣጥ 🔥
╚══════════════════════╝



   እውነታውን እንነጋገር ከተባለ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከዝሙት ጋር በተያያዘ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ይኸው ቦይ–ገርልፍሬንድ የተባለው በሽታ ነው፡፡ ይህ በሽታ በቀደምት ሥልጣኔዎች ውስጥ ከናካቴው ያልነበረና ህብረተሰቡም ፈፅሞ የማይታግሰው ፀያፍ ነገር ነበር፡፡ ግና የሳይንስና ቴከኖሎጂ ምጥቀትን ተከትሎ ሴኩላሪዝም ሲንሰራፋ መንፈሳዊነት እየተዳከመ ሄደ፡፡ በዚህን ጊዜ በሳይንስና ቴክኖሎጂ በመታገዝ «ፀያፍ የሚባል ነገር የለም፤ ከመች ወዲህ ነው ዝሙት ኃጢአት የሆነው? ማንም የፈለገውን ማድረግ ይችላል›› በሚል ሰይጣናዊ ርዕዮት መነሻነት ቅድመ-ወሲብ ልፊያዎችና ወሲባዊ ትዕይንቶች ለዓለም ሕዝብ ይፋ መደረግ ጀመሩ፡፡

 ⚡️⚡️⚡️ይህንኑ ተከትሎ #Free_Sex  (ነፃ ወሲብ) የሚል አዲስ የዝሙት ማስፋፊያ አስተሳሰብ ተቀመረና በሰፊው ዕውቅናን እንዲያገኝ በየሚዲያዎቹ ማስተዋወቅ ተጀመረ፡፡ ይህም የበለጠ ተደራሽ እንዲሆን ተብሎም ቦይ‐ገርልፍሬንድነት በስፋት ተቀባይነትን ያገኝ ዘንድ የሙቪዎች፣የፊልሞች፣የጋዜጦች፣ የመጽሔቶች፣ የመጻሕፍት፣ የድራማዎች፣ የልበወለዶች፣ የቲቪዎች፣የሕትመት ውጤቶች የዘወትር ሥራቸው ሆነ፡፡

በዚህም መንፈሳዊ ማህበረሰቦች ሳይቀሩ ተወረሩና ቦይ–ገርልፍሬንድነትን ተቀብለው ለማስተናገድ ተገደዱ፡፡ ይህም አስተሳሰብ ወደ ብዙኃን ማህበረሰቦች ተጋባና ቦይ ፍሬንድና ገርል-ፍሬንድ የሚሉት ፋሽኖች እንደጉድ ተቀባይነትን አገኙ፡፡ በዚህም የዝሙት አክሰስና ተደራሽነት በየቦታው እንደ ድር ተዘረጋ፡፡ ሰዎችም በዚህ የዝሙት ድር በመጠለፍ ሕገወጥ ወሲቦችን መሥራት ጀመሩ፡፡ የኋላ ኋላም ሴትን በገርል ፍሬንድነት መያዝ ሀይላንድን የመያዝ ያህል ቀላልና ተደራሽ ሆነ፡፡ ዝሙት መስራትም ውሀን የመጠጣት ያህል ቀላል ሆነ፡፡ ሙስሊሙም ከዓለማችን ተፅዕኖ ውጭ መሆን ስለማይችል አነሰም በዛም በዚህ ድር ተጠለፈ፡፡

 ⚡️⚡️ በርካታ ሀይማኖተኛ የነበሩ ማህበረሰቦችም ተፍረከርከው እነሆ ዛሬ ዛሬ ለቦይ ገርልፍሬንድነት ሁኔታዎችን እያመቻቹና መፈልፈያዎችንም እያዘጋጁ ይገኛሉ፡፡ በተቋም ደረጃ እንኳን ብናይ ከት/ቤት እስከ ዩኒቨርሲቲ ቦይ-ገርልፍሬንድነት ሰፊ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡ በጥቅሉ የትም እየተሠራበት ያለ ነገር ነው ማለት ይቻላል፡፡👇👇👇
#ለምሳሌ ወደ ማህበረሰባዊ የአገልግሎት ዘርፎች ብንመጣ፣ ካፌዎች፣ ልዩ ልዩ የመዝናኛ ቦታዎች፣ ሆቴሎች፣ ገስት ሐውሶች፣ ወዘተ ሁሉም ፊታቸውን ከማህበረሰቡ ቀደምት እሴቶች አዙረው ቢዝነሳቸው ሁሉ የቦይ‐ገርልፍሬንድ ግንኙነት ተኮር እንዲሆን አድርገዋል፡፡ ለሕገወጥ ጥንዶች የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ማዕከላት በጣም በዙ፡፡ በውጤቱም ለብዙ ዜጎችም ይኸው ፀረ-ትዳር ግንኙነት የኢኮኖሚያቸው አውታር ሁሉ ለመሆን በቅቷል፡፡



 ✏️✏️ ቦይፍሬንድ እና ገርልፍሬንድ ወደ ዝሙት መግቢያ ኬላ ሲሆን በተለይም አዳጊ ሴቶችን ጨምሮ ወደ ዝሙት ለማምጣት የተቀመረ ሴራ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ወንዱ ለአዳጊዋ ሴት «እኔ ወደፊት ለትዳር ስለሚፈልግሽ ገርልፍሬንዴ ሁኚኝ ይላታል፡፡ እናም ወንዱ የሴቶችን የትዳር ወዳድነትን ተፈጥሯዊ ባህሪያቸውን ስለሚያውቅ በቀላሉ በዚህ በኩል ይግባባና ብዙም ሳይቆይ ይተኛታል፡፡ ከዚህ በኋላ የልጅቷ ሕይወት ምስቅልቅሉ ይወጣል፡፡ ሴት ልጅ አንዴ ቀይ የደም ሴሏን ከኒካህ ውጭ ካጣችው ለወደፊቱ ከባድ የሆነን ዋጋ እንደሚያስከፍላት እሙን ነው፡

✏️✏️ #ቦይ_ፍሬንድ እና ገርልፍሬንድ ግንኙነት ሴቶችን ወደ ወሲባዊ ዕቃነትና እና የስሜት ማራገፊያ ሸቀጥነት ለመለወጥ ታስቦ የተወጠነ ሴራ ነው፡፡

📌📌 #በተፈጥሮ አንድ ወንድ አንዲትን ሴት በቀጥታ ለዝሙት ቢጠይቃት እርሷ በተፈጥሯዊ ስብዕናዋ ላይ ከሆነች እሺ አትለውም፡፡ ግና አሁን በተዘረጋው ሰይጣናዊ መረብ እርሷ የወደፊት ትዳሬን በዚህ አጋጣሚ እውን አደርገዋለሁ በሚል ምኞት ለገርልፍሬንድነት ስትጠየቅ እሺ ትላለች፡፡ በዚህ ዓይነት አካሄድም ቦይ ገርልፍሬንድ ግንኙነት ሴቷን ለወንዱ የስሜት ማራገፊያ ያደርጋታል፡፡

የሆነ ሆኖ ከቦይፍሬንድ እና ገርልፍሬንድ በስተጀርባ በርካታ ሰይጣናዊ የእጅ ሥራዎች አሉበት፡፡

⚠️ #በቀጣይ_ክፍል#ስለ_ፓርኖግራፊ(የወሲብ ፊልም)ላይ ያተኮረ ይቀርባል.....


#ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ሸርሙጣ፣ሴተኛ አዳሪ፣የቡና ቤት ሴት፣ሸሌ፣ባር ሌዲ፣ ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ሂያጅ፣አመንዝራ፣ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ ወንድኛ አዳሪ፣ ወንድ ሸሌ፣ ሸርሙጣ፣ ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል
ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት አላህ ይወፍቀን

⚠️⚠️⚠️⚠️ አደራ ለአንድ ሰዉ እንኳን ቢሆን ሼር ማድረግ እንዳይዘነጉ


#ምዕራፍ
ይቀጥላል......
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
           🔰 #ምዕራፍ_አስር
                አሚር ሰይድ


╔══════════════════════╗
 🎖🎖 #ፓርኖግራፊ ( #የወሲብ_ፊልም)🎖🎖
╚══════════════════════╝


   ማንም ይሁን ማን  እነዚያ በሙእሚኖች መካከል ፀያፍ ነገሮች እንዲስሩ የሚወዱና የሚያስፋፉ ወገኖች በቁርአን ከባድ ዛቻ ተሰንዝሮባቸዋል፡፡


‹‹እነዚያ በእነዚያ ባመኑት ሰዎች ውስጥ መጥፎ ወሬ እንድትስፋፋ የሚወዱ ለእነሱ በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ አላህም ያውቃል እናንተ ግን አታውቁም፡፡ (አንኑር 24፡19)

   ምንም እንኳን ቁርአን ፀያፍ ነገሮችን በሙእሚኖች መካከል የሚያስፋፉ ሰዎችን አብዝቶ ቢያስፈራራቸውም ነገር ግን በተለያዩ መንገዶች በርካታ ፀያፍ ድርጊቶች ወደ ማህበረሰባችን ተሰርፀዋል፡፡ ከነዚህም መካከል አንዱና አይደፈሬ ሲባል የቆየው #የወሲብ_ፊልም ነው፡፡ ይህም የብልግናዎች ሁሉ ጥግ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ያም ሆኖ ግን በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቶ ሱስ እስከመሆን ደርሷል፡፡ በርካቶቹ የወሲብ ፊልም ሱሰኞችም ከርሱ እኩይ ልምዶች በማካበት ወደ ወሲባዊ እብደቶች ገብተዋል፡፡

     የወሲብ ፊልምን ማየት ያለ ምንም ጥርጥር #ሐራም ነው፡፡ ለአንድ ሙስሊም በማንኛውም ሁኔታ የሌላን ሰው ዐውራ” (የግል አካላት) ማየቱ ለማንም አይፈቀድምና፡፡ የወሲብ ፊልምን ተከትሎ የሚመጣው ሴጋም እንዲሁ ሐራም ነው::

🟢 ከዚህም በላይ በፊልሙ ውስጥ የሚሳተፉ ተዋንያን ዝሙትን እየሠሩ ነው፡፡ ታዲያ አንድ ሙስሊም እንኳን የዝሙትን ትዕይንት ሊመለከት ቀርቶ በሕጋዊ ጋብቻ ውስጥ የሚሠራውን የሌላን ሰው ሕጋዊ የወሲብ ትዕይንት ማየቱ እንኳን ፈፅሞ አይፈቀድለትም፡፡ እንኳን የፖርኖግራፊ አርቲስቶችን ወሲባዊ አካላት መመልከት ቀርቶ የነርሱን ዐውራ እንኳን መመልከቱ ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡



╔══════════════════════╗
🎖#በወሲብ_ፊልም_ላይ_የተደረጉ_ጥናቶች🎖
╚══════════════════════╝


 ☞ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ከአለም አቀፍ ደረጃ #የኢትዮጲያ የፓርን ፍጆታ ከታይላንድ ቀጥሎ ሁለተኛ ናት፡፡
☞ጥናቶች እንደሚያመለከቱት ከ400 ሚሊዮን በላይ አንላይን ፍለጋዎች መካከል 12.5% ለወሲብ ፊልም ነው፡፡
     

🟡 እንደሚታወቀው በአስቀያሚው የወሲብ ፊልም ውስጥ ፊት ለፊት የሚሳተፉት አብዛኞቹ ተዋንያንና ገፀ-ባህሪያት ያው እንደኛው ሰዎች ናቸው፡፡ እንደዚሁም የስራው ስፖንሰሮች፣ አቀናባሪዎች፣ ከስክሪኑ በስተጀርባ ያሉ ሠራተኞችና ሌሎችም እነዚያ በፊልሙ ላይ ፊት ለፊት የማይታዩ ግለሰቦች ያው የሰው ልጆች ናቸው፡፡

☑️ #ጥናቶች እንደሚያመለከቱት ከሆነ እነዚህ ግለሰቦች ለዚህ ዓይ ዓይን አውጣነትና ድርቅና የበቁት #የአሳማ_ሥጋን ከመብላትም አልፈው አዘውትረዉ በመመገባቸው ነው፡፡ እንደሚታወቀው አሳማ ኃፍረተ ቢስ እንስሳ ነው፡፡ ወንድና ሴት አሳማ ግንኙነት ሲያደርጉ ሌሎቹ አሳማዎች ትዕይንቱን ከበው ያያሉ፡፡ ነጮች «You are what you eat» (አንተ ማለት የምትመገበው ነገር አምሳያ ነህ) እንዳሉት ሁሉ እነዚህም የአሳማን ሥጋ በማዘውተር ሀፍረተ ቢሶችና ዓይን አውጣዎች ሆኑ። የኋላ ኋላም የአሳማን ወሲባዊ ትዕይንት ለዓለም ሕዝብ አስተዋወቁ፡፡

 ☑️ አሳማን በተመለከተ ሌላው እውነታ አሳማ #ቅናተ_ቢስ (የቀናተኛነት መንፈስ የራቀው) እንስሳ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ሚስቱን ሳይቀር ለሌላው ያቃጥራል ሌላ ወንድ አሳማ ጋር ሴክስ እንድታደርግ ያመቻቻል፡፡በሌላ በኩል የአሳማ ትል ያለው ሥጋ፣ የፈለጉትን ያህል ቢቀቅሉትም ትሉ አይሞትም፡፡ ታዲያ ይህ ትል ከሥጋው ጋር ከተወሰደ በቀላሉ ወደ ተመጋቢው ደም ስሮች ይሰረፃል፡፡ በተመጋቢው የደም ስርዓት ውስጥም ይዘዋወራል፡፡ በዚህ ምክንያት የግለሰቡን ባህሪም ከአሳማ ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ታዲያ የሚገርመው የወሲብ ፊልም ተመልካቹም ይህንኑ ባህሪን መወረሱና ጨቅላ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡

🔵 ሄለን አሰፋ #የቦሌ_ጉዶች በሚለዉ መፅሀፏ ገፅ 31 ላይ እንዲህ ብላ አስፍራለች

  «የወሲብ ንግድ ስሙ የነሱ ቢሆንም ብልግናው ግን የጋራችን ሆኗል፡፡ እንግዲህ እኔ የቤት ልጅ ነኝ፡፡ የቤት ልጅ ሆኜ እንዲህ ዓይነት የብልግና ታሪከ ካለኝና ይህን በኔ ያልተጀመረውን ብልግና በተግባር ካደረግሁ ከየትኛው ክፍል ልትመድቡኝ ትችላላችሁ? ከቡና ቤት ሴቶች አትመድቡኝ ነገር ከነሱ በላይ ነኝ፡፡ የቤት ልጅ አትሉኝ ነገር በጨዋ ደንብ ወሲብ አልፈፀምኩም፡፡ የኔ ታሪክ ከሴተኛ አዳሪዎች ታሪክ ጋር ተካቶ አልተፃፈም፡፡ የሌሎቹ የቤት ልጆች ታሪከም አልተፃፈም፡፡ ከቡና ቤት ሴቶች በላይ መፃፍ ያለበት የብልግና ታሪክ ያለው ግን የቤት ልጆች ላይ ነው፡፡ በዚህ ዓይነቱ ከገደብ ያለፈ ብልግና ውስጥ እንድንገባ ካደረጉን ነገሮች ውስጥ አንዱና ዋናው ምከንያት የነጮቹን የወሲብ ፊልም መውደዳችን ነው፡፡ መውደድ ብቻ አይደለም፤ ፈልገን ማየታችን እንጂ፡፡ በቀድሞዋ እኔ ላይም ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳደረው ይሄው ነጥብ ነበር፡፡ ያ የያኔው ዓይን አውጣነት የመጣው ከየት ነው? ብዬ በወቅቱ አስብ ነበርና ምላሹ ከወሲብ ፊልም የሚል ሆኖ ነበር ያገኘሁት፡፡››



🔵 በተጨማሪ ሄለን አሰፋ #የቦሌ_ጉዶች በሚለዉ መፅሀፏ ገፅ29-30 እንዲህ ብላለች

  በተለይ በአሁኑ ወቅት ተዓምር የሆነ ነገር ነው ያለው፡፡ በወጣቱ ስልክ ላይም አለ፡፡ ብዙኃኑ ኢትዮጵያዊ ኢንተርኔት ላይ የሚተከለውም ይህንኑ የብልግና ፈልም ለማየት ነው:: ሁሉም ባይባልም ከግማሽ በላዩ ተበላሽቷል! ያንን ያየ ደግሞ ኖርማል ወሲብ ምንም ስሜት አይሰጠውም፡፡ ስለዚህ እንደኔ ያየውን በተግባር ማድረግ ይፈልጋል፡፡ የራሱን ሴት ካፈረ ወደብልግና ቤቶቻችን ይመጣል፡፡,”


🔵 ሮዛ ቁጥር ➋ በሚለዉ መፅሀፍ ገፅ121 ላይ እንዲህ የሚል ሰፍሯል
    «የዚህ ዘመን ልጆች ከምንጊዜውዏ ይብሳሉ፡፡ የ8ኛ ክፍል ተማሪ ሳሉ አስተማሪ ጥቁር ሰሌዳ ላይ ሲፅፍ በሞባይሎቻቸው ልቅ የወሲብ ቪዲዮዎችን ከወንድና ከሴት ጓደኞቻቸው ጋር ይለዋወጣሉ፡፡ የዘመን ልዩነት ገረመኝ፡፡ እኔ የወሲብ ፊልም ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ማትሪክ በወሰድኩበት አመት የክረምት የዕረፍት ወቅት ላይ አንዲት አብሮ አደግ ጓደኛዬ ቤት ነበር፡፡ እንዳሁኑ ሲዲ፣ ዲቪዲ፣ ኮምፒዉተር፣ ላፕቶፕ፣ ሞባይል፣ አይ ፎን፣ አይፓድ የሚባል የዕቃ ዕቃ መዓት አልነበረም፡፡ የጓደኛዬ ወንድሞችና ወላጆች ሲወጡ እግራቸውን ጠብቀን ነበር የወሲብ ፊልም ካሴቱን ዴክ ውስጥ ከተን ላጥ ላጥ አድርገን የኮመኮምነው፡፡ በእርግጥ የ11ኛ ከፍል ተማሪ እያለን Playboy የሚባል የወሲብ መፅሔት በቦርሳዋ ደብቃ በዕረፍት ሰዓት የምታሳየን ልጅ ነበረች፡፡ አዲሱ ትውልድ ፈጣን ነው፡፡ ነገሮችን በፍጥነት ይረዳል፤ በጥድፊያ ይሞከራል፡፡ እንደሰማሁት ከሆነ በአንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች በትምህርት ክ/ጊዜ ሞባይሎቻቸውን፣ አይፎንና አይፓዳቸውን እንዳይጠቀሙ ከልክለዋል፡፡ የክልከላው ዋና ምክንያት ተማሪዎቹ በስፋት የተለዋወጧቸው የወሲብ ቪዲዮዎችና የቻት መልዕክቶች ናቸዉ ብላለች፡፡ በመፅሀፏላይ


✏️✏️ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ከ5የሞባይል ኦላይን ፍለጋዎች መካከል አንዱ ለፓርኖግራፊ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡👇👇👇
በተጨማሪም የ «Covenant Eye ስታትስ እንዳመለከተው ከሆነ ከ10 አዳጊ ወንዶች መካከል 9ኙ 18 ዓመት ሳይሞላቸው ለወሲብ ፊልም የተጋለጡ ናቸው፡፡
✏️✏️ ስታትሱ አያይዞ እንደጠቆመው እንድ አሜሪካዊ ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማካይ በ12 ዓመቱ ለፊልሙ ይጋለጣል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ጥናቶች እንደሚያመለከቱት የሙስሊሞች የወሲብ ፊልም ተጠቃሚነትም ሙስሊም ካልሆኑ ወገኖች እምብዛም አይተናነስም፡፡  የዒባዳ ሙስሊም መሆንና በቀን አምስቱን ዕለታዊ ሶላቶች በወቅታቸው መስገድ ብቻውን ግለሰቡን ከዚህ እኩይ ድርጊት ሊጠብቀው ዘንዳ በቂ ላይሆን ይችላል፡፡ በመሠረቱ ዒባዳ ብቻውን ሙስሊሙን ከኃጢአትና ከፀያፍ ነገሮች አይጠብቀውም፡፡ በዚህ ረገድ ትልቁን ሚና የሚጨዋተው ግብረገብነትና ሰናይ ሥነ- ምግባር ነው፡፡ አንድ ሙስሊም ዒባዳን እዳው አድርጎት ሊፈፅመው ይችላል፡፡ ከዚህ ዓይነት ፀያፍ ነገር የሚጠብቀው ግን የአላህን ተቆጣጣሪነት (ሙራቀባን) ከግምት ውስጥ ማስገባትና የራስህን ስሜት ለመቆጣጠር በአላህ (ሱ.ወ) መታገዝ ነው፡፡ እነዚህ መፍትሔዎች መልካም ሥነ-ምግባርና ግብረገብነት ጋር ተደማምረው አንድን ሙስሊም በርግጠኝነት የወሲብ ፊልምን ከመመልከት ይጠብቁታል፡፡



╔══════════════════════╗
 🎖🎖🎖-----🎖🎖🎖------🎖🎖🎖 #የወሲብ_ፊልምን_የሚያወግዙ_ነብያዊ_ንግግሮች
╚══════════════════════╝

ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺእንዲህ ብለዋል

ማንም ወንድ ወይም ሴት ካልተጋቡ በስተቀር አንዱ የሌላውን እርቃነ ስጋ መመልከት አይፈቀድለትም፡፡›› (ሶሒሕ ሙስሊም)

ታላቁ ሰሓባ ሰልማን አል-ፋሪሲ (ረ.ዐ) እንዳወሩት የአላህ መልዕከተኛ የሆኑት ሀቢቡና ሙሀመድ  ﷺእንዲህ ብለዋል፦ «በአላህ እምላለሁ! እኔ ከሰማያት ላይ መወርወርንና ወደተለያዩ ክፍሎች መበታተንን እመርጣለሁ፤ ከዚያ የአንድን ሰው የግል አካላትን ከመመልከት ወይም አንድ ሰው ወደግል አካላቴ እንዲመለከት ከመፍቀድ፡፡›› (አል-መብሱሥ ኪታቡል ኢስቲሕሳን)

ታላቁ ኸሊፋ ዐሊ ቢን አቡጧሊብ (ረ.ዐ) እንዳወሩት  ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «ጭናችሁን ለማንም አታጋልጡ፤ ወደሌላ ሰው ጭንም ፈፅሞ አትመልከቱ፣ እርሱ የሞተ ሰው እንኳ ቢሆን፡፡» (ኢብን ማጀህ፣ አቡ ዳዉድና ደረቁጥኒ)

ሰሓባው ጀርሃድ አስለሚ (ረ.ዐ) እንዳወሩት አንድ ጊዜ የአንድ ሰው ጭን በሰዎች ፊት ተገለጠ፡፡ ነብዩም ﷺ ወዲያው «ጭን ተሸፍኖ መቆየት እንዳለበት እታውቅምን?.› አሉት፡፡ (ሙዐጥ-ጠእ ኢማም ማሊከ፣ ቲርሚዚ፣ አቡ ዳዉድ)



╔══════════════════════╗
   🎖🎖 #ፖርንን_የሚመለከቱ_እስታቶች🎖🎖
╚══════════════════════╝

  ይህ ጥናት የዛሬ 8አመት በፊት የተጠና ጥናት ነው ዛሬስ ቢሆን?ስንት እጥፍ ይጨምር ይሆን?

⚡️ የሞባይል ዳታ ዲቫይሶች መፈብረከ በዓለም ላይ እጅጉን የተለመዱ 11 የፖርን ሳይቶችን ወደ 300 አሳድጓቸዋል፡፡

⚡️ከአጠቃላይ የፖርን ሳይት ጎብኚዎች መካከል 60% ሞባይላቸዉን በመጠቀም  ነው።

⚡️ በሞባይል ፎኖች የሚተላለፉ የፖርን ፊልሞች በወር ውስጥ ከ1.3 ቢሊዮን ጎብኚዎችን ይስባሉ፡፡


⚡️ ፖርን በሚጨምር ሁኔታ ሰፊ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡ አዳጊዎችና ወጣቶችም ስለፖርን በሚያወሩበት ጊዜ የበለጠ ከርሱ ፈላጊዎች ሆነው ነው፡፡
⚡️ 13% አዳጊዎችና 17% ወጣቶች ስለፖርን በአዎንታዊና በግድ የለሽነት መንገድ
ያወራሉ፡፡ 40% አዳጊዎችና 43% ሁሉም ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ፖርንን ይመለከታሉ ብለው ያስባሉ፡፡ 37% አዳጊዎችና 36% ወጣቶች ፖርንን ስለመመልከት ሞራሊቲ አያወሩም፡፡


╔══════════════════════╗🎖#በህንድና_በደቡብ_አፍሪካ_የተደረገ_ጥናት🎖
╚══════════════════════╝


📌 በህንድ በ400 ተማሪዎች ላይ በተደረገው የአሰሳ ጥናት መሠረት፡-
☞70% ወንዶች ልጆች ፖርንን ማየት የጀመሩት በ10 ዓመታቸው ነው፡፡
☞93% ወንዶች ልጆች እንዳሉት ፖርንም ልክ እንደመጠጥ ሁሉ ሱስ አስያዥ ነው
☞86% እንዳሉት ፖርን ወደ ወሲባዊ ድርጊቶች መርቷቸዋል፡፡

📌 በሕንድ ውስጥ በ8ሺ ልጃገረዶችና ሴቶች ላይ በተደረገው ጥናት 49% እንዳሉት ስለወሲብ የተማሩት የፖርን ፊልሞችን በማየት ነው፡፡

📌በደቡብ አፍሪካ ከ4ሺ ወንዶች በላይ በተደረገው የአሰሳ ጥናት መሠረት
☞ 67% ፖርንን ተመልክተዋል፡፡
☞27% ደግሞ በሳምንት ውስጥ ለበርካታ ጊዜያት ግለወሲብን ፈፅመዋል

📌 በቅርብ የተሠራው አንድ የአሰሳ ጥናት እንዳመለከተው ከ10 ባለትዳር ደቡብ ኮሪያዉን ወንዶች መካከል 4ቱ ለሚስቶቻቸው ታማኞች አይደሉም፡፡

📌 በአየርላንድ ውስጥ በ1002 የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ላይ በተደረገው ጥናት መሠረት 83% ወንዶችና 56% ሴቶች ፖርንን ተመልከተዋል፡፡

📌 በባሎቻቸው ላይ የሚማግጡ እንግሊዛዉያን ሴቶች ቁጥር ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ ብቻ በ40% ጨምሯል፡፡


🟡 #በቀጣይ_ክፍል☞ስለወሲብ ፊልም በኢትዮጲያና በአለም ሙስሊሞች የደቀነዉን መዘዝ እንዳስሳለን




#ምዕራፍ
ይቀጥላል......
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot



join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
          🔰 #ምዕራፍ_አስር_አንድ ➊➊
                አሚር ሰይድ

 
.................... ከምዕራፍ 10 የቀጠለ................
╔══════════════════════╗
   #ምዕራባዉያን_ለወሲብ_ፊልም_ለማሰራጨት
        #ምንያህል_ወጭ_ያወጣሉ
╚══════════════════════╝



     አበልቃሲም ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- መጥፎና ፀያፍ ነገር በህዝቦች ዉስጥ በምንም መልኩ ግልፅ አትሆንም ፡በዉስጣቸዉ ቀደምት አባቶቻቸዉ የማያዉቅት ወረርሽኝ እና የተለያዩ በሽታዎች ቢከሰቱ እንጂ በማለት ይገልፃሉ

   ፓርኖግራፊ(ልቅ ወሲባዊ ፊልሞች እና ምስሎች)መመልከት ያልተገደበ ወሲባዊ ጡዘትን እና የአእምሮ መረብሽን ያስከትላል፡ልቦናን መረጋጋት እንዳይኖረዉ በማድረግ ላልተፈለገ የወሲብ ሩጫ እና መልከስከስ ይጋብዛል፡፡ አንድ ቀን የሚታይ የወሲብ ፊልም ወይም ምስል ሁለት ወይ ሶስት ቀን ሙሉ አእምሮ ይረብሻል በተደጋጋሚ በአይነ-ህሊና እየመጣ የዉስጣችንን ሰላም የሚያናጋ ክስተት ነዉ፡፡


 🎖🎖🎖 ኢስላም የተራቆቱ ገላዎች መመልከት ግልፅ በሆነ ቁርአናዊ አንቀፅ የተከለከለ እና በተለያየ ነብያዊ ሀዲሶች አፅንኦት ተሰጥቶት የተወገዘ ተግባር ነዉ ፡፡ ይህን አስመልክቶ አሏህ በተከበረ ቁርአኑ እንዲህ ይላል ፡-
""ለምእመናን ንገራቸዉ ዓይኖቻቸዉን ያልተፈቀደን ከማየት ይከልከሉ ፡ብልቶቻቸዉንም ይጠብቁ፡ይህ ለነርሱ የተሻለ ነዉ ፡ አላህ እነርሱ በሚሰሩት ሁሉ ዉስጥ አዋቂ ነዉ፡፡""(ሱረቱ ኑር 30)

ይህ የፊልም ሱስ አመጣጣጡ ምዕራባዉያን ዲነል ኢስላምን ለማቀጨጭ ለማዳከም...ማንኛዉንም ወጣት የማይጠቅም የማይጎዳ ለማድረግ እና ወጣቱን ለማዳከም እና ሴቶች እናትነትን ረስታ የባለጌ ወንዶች መጫወቻ እንድትሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነዉ ፡፡ በዚህ የወሲብ ፊልም የተነሳ
☞በርካታ ወጣቶች ለሞት ዳርጓል
☞በርካቶች ለተለያዩ ህመምና ስቃይ ዉስጥ እያቃሰቱ እንዲኖሩ አድርጓል፡
☞በርካቶች በዚሁ ተለክፈዉ የቀን ዉሏቸዉ የለሊት አዳራቸዉ እርሱ ሁኗል...በዚህ ምክንያት ዉድ የሆነ ሒወታቸዉ ጊዜያቸዉን የገንዘብ ብኩንነት ..ሰላማቸዉ ተናግቶ ደስታ የራቀዉ ሒወት እየተገደዱ ነዉ፡፡

እንደ ተርብ እስታስቲክስ መረጃ ከሆነ ለፓርኖግራፊክስ(ለልቅ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎች)ድህረ ገፆች የሚወጣዉ ገንዘብ በአመት

☞57.8ቢሊዮን ዶላር ሲሆን
☞በአሜሪካ ብቻ 12 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረጋል..
☞የፓርናግራፊ ድህረ ገፆች ብቻ 4.2ሚሊየን እና 420.ሚሊየን ገፆች ይጠጋሉ፡
በአጠቃላይ ድህረ ገፅ 12በመቶ ለዚሁ ርካሽ ተግባር ማስፋፊያነት ተመድቧል ፡፡
☞በሳምንት 70ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች የብልግና ምስሎችን በኢንተርኔት ይመለከታሉ ከእነዚህ ሰዎች መካከል 20ሚሊየኑ የሚገኙት በአሜሪካ እና በካናዳ ሲሆን በአዉሮፓ ደግሞ ጀርመን እንግሊዝ ስፔን ቀጣዮችን ቦታዎች ይይዛሉ..ምዕራባዊያን እራሳቸዉን ሆነ የዓለምን ህዝብ ወደ አልሆነ መጥፎ አቅጣጫ እየመሩት እንደሆነ መመልከት ይቻላል፡፡

እንደ እስታስቲካዊ መረጃዎች ከሆነ
#ሙስሊም_በሆኑ_ሀገሮች_ላይ_ያሉ_ወጣቶች_ቁጥር ሙስሊም ባልሆኑ ሀገር ላይ ካሉት ወጣቶች ቁጥር በጣም በልጦ ይገኛል ..

በአጠቃላይ የሙስሊም ዓለም ወጣት ብዛት 70 በመቶ ሲጠጋ
በምዕራቡ ዓለም ያለዉ ወጣት ቁጥር 25 በመቶ መሆኑን ያሳያል ፡፡ስለዚህ ለወደፊቱ አለምን የሚረከበዉ ጠንካራ ትዉልድ ያለዉ በሙስሊሙ ዓለም መሆኑ ምዕራቡን አለም ክፉኛ ስላሳሰባቸዉ ሙስሊሙን ወጣት በዚህ የፊልም ሱስ ተለክፎ ከአላህ ጋር ከቁርአን ከሀዲስ ከመስጊድ ያለዉን ግንኙነት ቀንሶ ከዲነል ኢስላም ርቆ ለኢስላም የማይጠቅም የማይጎዳ ትዉልድ ለማድረግ የመጣ ነዉ፡፡


ምእራባዉያን ለወደፊት ለሚመጣዉ ሙስሊም ትዉልድ እንዲበላሽ ከበፊት ጀምሮ ዛሬም ጭምር ቀን ለሊት እየሰሩ ነዉ ፡፡ እኛስ ለሚመጣዉ ትዉልድ ዲነል ኢስላምን ለማስረከብ ምን እየሰራን ነዉ???


    በጣም የሚያሳዝነዉ ይህን ፊልም መመልከት ለተለያዩ የወሲብ ችግሮች መፍትሄ ይሆናል በሚል እምነት የሚናገሩና የሚተገብሩ መኖራቸዉ ነዉ፡፡ ወጤቱ ግን በለቃራኒዉ መሆኑን ዘንግተዉታል

📚📚 አላህ ከብልግና ፀያፍ ነገር..ከማንኛዉም መጥፎ ተግባር እንዲሁም ወሰንን ከማለፍ ይከለክላል
በሱረቱል ነህል 90 ላይ ..በዚህ አንቀፅ ፋህሽ ሙንከርና አል-በግይ የሚሉ ቃላቶች ሰፍረዋል ፡፡
☞ ፋህሽ ማለት ብልግና እፍረተቢስና ቆሻሻ ማለት ሲሆን ወሲባዊ ፊልሞችና ምስሎችን ያካትታል፡፡

☞ ሙንከር የሚለዉ ደግሞ ማንኛዉም በአለም ዙሪያ ያሉ ኢሞራላዊ መጥፎ ስነ-ምግባሮች መገለጫ የሆኑ ባህሪያትን ያካትታል ፡፡ አልበግይ የሚለዉ ኢፍትሀዊ የሆኑ ተግባሮችን ድንበር ያለፈ ጋጠወጥነትን ያካትታል፡፡ከዚህ የተነሳ ልቅ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎች በዚህ የቁርአን አንቀፅ ዉስጥ የተገለፀ ስለሆነ ህዝቡን የሚጎዱ ለክፉ ዉድቀት የሚዳርጉ ስለሆነ ህዝበ ሙስሊሞ ሊርቃቸዉና ሊያወግዛቸዉ ሀራም መሆኑን አዉቆ ሊጠነቀቅ ይገባል፡፡





╔══════════════════════╗
#የወጣቱ_የስከሪን_ቀበኛነትና_የወሲብ_ፊልም               #ተጠቃሚነቱ_ከፍ_ማለት
╚══════════════════════╝



    የኢትዮጲያ መረጃዎች እንዳመለከቱት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚለቀቁትን የወሲብ ፊልሞች በመጠቀም የብልግና ፊልምን በማየት ኢትዮጵያ ከታይላንድ ቀጥላ የሁለተኛነት ደረጃን ይዛለች፡፡ ይህንኑ እውነታም የኢትዮጵያ መንግስትም ተቀበሎታል፡፡ በርግጥ ከመቀበል ውጭ የትም መሸሽ አይቻለውም፤ ምክንያቱም እያነፈነፉ ወደኋላ መሄድና የሀገሪቷን ገመና ማየት ይቻላልና፡፡ እውነታውንም የኢትዮጵያ ቴሌኮም በግልፅ ያውቀዋል፡፡በየአመቱ   በቢሊዮን ብር የሚያተረፈው ኢትዮ ቴሌኮም ለዚህ ሁሉ ትርፋማነት እንዲበቃ ያደረገው አንዱ ምክንያት የዜጎቿ የወሲብ ፊልም ፍጆታ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩ እንደሆነ ይነገራል፡፡

   በተለይ ወጣቱ ሙስሊም አማራጭ መዝናኛ ስለሌለውም ሊሆን ይችላል፤ አልያም ሱስ ሆኖበት ይሆናል፤ ከሞባይሉ ስከሪን ስር አድብቷል፡፡ ይህ ዕቃ ዕቃ ጨዋታም ሰፌድ በሚያከል ሞባይል መሆኑ የሆነን እኩይ ተልዕኮ እንደሚያሳካ ያሳብቅበታል፡፡ ወጣቱ ከሞባይሉ ስከሪን ሥር የሚያደባው ብቻውን ሆኖ ነው፡፡ አንድ ግለሰብ ብቻውን ሆኖ ይህንን ልቅና ጋጠወጥ የሆነውን ሶሻል ሚዲያን ሲቀጠቅጥ ደግሞ ኢብሊስ ወዲያው መጥቶ ሥራን ይሰጠዋል፡፡ ግለሰቡም ወዲያው ወደወሲብ ሳይት ይገባል፡፡ ይህንን ባያደርግ እንኳ በርካታ #ቀበጥ_የኦንላይን_ሒጃቢስቶች ብቅ ይሉለታል፡፡ እርሱም ከነርሱ ጋር ቻት ይጀምራል፡፡ ብሎም ፎን ሴክስ ይሰራል፡፡ በቀን ውስጥ እስከ አስር ጊዜ ፎን ሴክስ የሚሠሩ መኖራቸውም ታውቋል፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታም ወጣቱ በዝሙት ድርጊት ውስጥ ይዳከራል፡፡

🔶🔶 በእውነቱ የስክሪን ቀበኛ የሆነ ወጣት ለወሲብ ፊልም፤ ለፎን ሴክስ፣ ለቻት ሴክስና ለመሳሰሉት ብልግናዎች የመጋለጥ ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህንን የሚያከል ሰፌድ ሞባይል ሲዘረጋም በዚያው ልከ ዕይታውም ልቅ ስለሚሆን ዓይኖቹም ወደፈለጉ ሳይቶች ይወረወራሉ፡፡ በዕይታ የገባ ነገር ደግሞ በቀጥታ ሐሳብ ይሆናል፡፡ ሐሳብ የሆነው ነገር ደግሞ ወደ አስተሳሰብነት ይለወጣል፡፡ አስተሰሳብ ማለት ደግሞ ራሱ ግለሰቡ ነው፡፡👇👇👇
2024/10/02 00:43:39
Back to Top
HTML Embed Code: