Telegram Web Link
ሉቅማን አል-ሐኪም ልጁን እንዲህ ሲል መክሮታል፡፡

>> “ልጄ ሆይ ከሰው ልጅ ጀርባ ያለውን ነገር ሳታውቅ ፈገግታው እንዳያታልልህ !! ምክንያቱም የሰው ልጆች የማንነት መቃብር ልቦናቸው ውስጥ ሲሆን የሚያስጐመዥ ፍሬያቸው ደግሞ ፊታቸው ላይ ይገኛል፡፡

ስለዚህ እሮሮህና አቤቱታ ዘውትር ይህን ዘመን ወደ ፈጠረው አላህ (ሱ.ወ) ይሁን፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ጥሩውንም ሆነ መጥፎውን ነገር ባንተ ላይ ከሻተ ሰዎች ወደዱም ጠሉም አንተ ላይ ከመከሰት ወደኋላ እንደማይል ጠንቅቀህ እወቅ፡፡"

@አሚር ሰይድ


https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAESAIxFIdM3tYVwa1g
#በሰባት_ጣዖታውያን_ላይ_ያደረጉት_ዱዓ

ቡኻሪና ሙስሊም ኢብኑ መስዑድን በመጥቀስ እንደዘገቡት፡

«ነቢዩ ﷺ ከዕባ ውስጥ ይሰግዱ ነበር። አቡ ጀሀልና ባልደረቦቹ ተቀምጠዋል። «ሙሐመድ ሱጁድ ሲያደርግ ፈርስ የሚያፈስበት ማን ነው?» ተባባሉ። ከመካከላቸው ይበልጥ ተንኮለኛው ፈርስ ይዞ መጣ። ሱጁድ እስኪያደርጉ ጠበቀና ከጀርባቸው ላይ አፈሰስባቸው፡፡ እኔ ሁኔታውን እከታተል ነበር። ምንም ላደርግ አልቻልኩም። ጉልበት ቢኖረኝ ኖሮ ይህ ነገር በነቢዩ ላይ እንዳይደርስ በተከላከልኩ ነበር።

ሰዎቹ ይሳላቁ ጀመር። አንተ ነህ አንተ ነህ እየተባባሉም ይቀልዱ ጀመር። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሱጁድ እንዳደረጉ ናቸው" ራሳቸውን ከሱጁድ አላቀኑም። ልጃቸዉ ፋጡማ(ረ.ዐ) መጣችና ቆሻሻውን ከጀርባቸው አስወገደችላቸው። ራሳቸውን ቀና አደረጉና፡ «አላህ ሆይ! ቁረይሾችን ተበቀልልኝ» በማለት ሦስት ጊዜ በመደጋገም ዱዓ አደረጉ።

እርግማኑን ሲስሙ ሰዎች ተጨነቁ። በዚያ ሀገር ውስጥ የሚደረግ ዱዓ ተቀባይነት እንዳለው ያምኑ ነበር። ነቢዩ በመቀጠልምሰዎችን በስም ጠርተው ዱዓ አደረጉባቸው፡፡ እንዲህ አሉ  «አላህ ሆይ!
>አቡ ጀህልን ተበቀልልኝ።
> ዑትበት ኢብኑ ረቢዓህን'
>ሸይበት ኢብኑ ረቢዓህን፡
>ወሊድ ኢብኑ ዑትባህን
>ኡመያ ኢብኑ ኸለፍንና
> ዑቅበት ኢብኑ አቢ ሙዒጥን ተበቀልልኝ»
አንድ ሰውም ጨምረው ጠሩ። ስሙን አላስታወስኩትም።

ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ፣ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ስማቸውን ጠቅሰው የረገሟቸው እነዚህ ሰዎች በድር ላይ ተገደሉ። ገደል ውስጥም ተጣሉ።


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ያአሏህ😢

አረ በዱአ አንዘንጋቸዉ ልብ ይሰብራል😔

ይቺ ህፃን ልጅህ(ልጅሽ) ወይም እህትህ(እህትሽ)ብትሆን የስቃይ ስሜታችን መቆጣጠር እንችል ይሆን😔
⚠️#ኢስላምን_በዉርስ_ያገኘነዉ_ሀይማኖት_ስለሆነ_ዝሙትን_ተዳፈርን
     አሚር ሰይድ

«በአሜሪካ ያሉ ሰለምቴ ሙስሊሞች ከምንም በላይ ከሁለት ወንጀሎች በግልፅ እንደራቁ አስረግጦ መናገር ይቻላል፡፡ አዎን! ማንኛውም ሰለምቴ አሜሪካዊ ሙስሊም ከሪባ የራቀ ነው፡፡ እንዲሁም ማንኛውም ሰለምቴ አሜሪካዊ ሙስሊም ከዝሙት የራቀ ነው፡፡» (ኑእማን አሊ ካን - አሜሪካዊ ዳዒይና የቁርኣን ተንታኝ)


         እንደሚታወቀው አብዛኛው የሀገራችን ሙስሊም ኢስላምን የሚወርሰው ከቤተሰብ ነው፡፡ ቤተሰቡ ሙስሊም የሆነ ልጅ እርሱም ሙስሊም ይሆናል፡፡ ከዚህም የተነሳ ኢስላምም በውርስ የሚያገኝ ሃይማኖት ይሆናል፡፡ ኢስላምን በውርስ የሚያገኝ ልጅ ደግሞ ስለእምነቱ ይህንን ያህል የበዛ ትኩረት ሰጥቶት ላያጠናው ይችላል፡፡

ነገር ግን አሜሪካዉያን ሙስሊሞችን በምሳሌነት ብንወስድ እነርሱ ዘንድ አብዛኞቹ ኢስላምን የተቀበሉት አንብበው፣ አጥንተው፣ ተመራምረው፣ አነፃፅረውና እዉነቱን አንጥረው ካወቁ በኋላ ነው፡፡ ከዚያም በዚህች ምድር ላይ ብቸኛው እውነት ብቸኛው መለኮታዊ ሀይማኖትና ታላቁ ፀጋ ኢስላም መሆኑን ስለሚረዱ ወደ ኢስላም ሲመጡ ዲኑን በሚገባ ለመተግበር ነው፤ በሙሉ ልባቸው፡፡

በተለይም ምዕራባዉያን ዜጎች ሙስሊም ከሆኑ በኋላ አንዳች ሲሠሩት የነበረው ነገር በኢስላም የተከለከለ መሆኑን ካወቁ ወዲያው ያንን ነገር ይተውታል፡፡

⚡️⚡️አሜሪካዊው ታላቁ ዳዒይና በቁርኣን ተፍሲር ትልቅ ዕውቅናን ያገኘው ኑእማን አሊ ካህን በበኩሉ በምዕራቡ ዓለም እጅጉን የተንሰራፉ ነገሮች በተለይ ወለድና ዝሙትን የመሳሰሉ ኃጢአቶች እነሱ ዘንድ ከሞላ ጎደል እንደማይታወቁ ይናገራል፡፡ በተለይም ከጥቂት ዓመታት በፊት የደረሰውን የምዕራቡን ዓለም የገንዘብ ቀውስን አስመልክቶ ቀውሱ ሙስሊሞችን እምብዛም እንዳላጠቃቸው በመጥቀስ አሜሪካዊው ሙስሊም ከወለድ የራቀ መሆኑን እንደማሳያ ያነሳል፡፡

#ቀጥሎም ዝሙትን አስመልከቶ አሜሪካዉያን ሙስሊሞች ከዚህ መራቃቸውን እንደ ማሳያ የሚያነሳው ነገር ቢኖር የመስሊም ሴቶችን ታላቅ ግብረገብነትና የሒጃብ አለባበሳቸውን በመጥቀስ ነው::

በዚህች ሀገር የሴቶች ትልቁ መከበሪያቸው ሒጃብ ነው:: የራስ መተማመናቸውና ለኢስላም ያላቸው ፍቅር ያስደንቅሃል፡፡ ሴቶቹ እንዴ ከሰለሙ በኋላ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስን ሊከተሉ ቀርቶ ከቶውኑ አያስቡትም፡፡ ቀድሞውኑ ኢስላምን አጥንተውትና መርጠው ስለሚመጡ ሰዉ ምን ይለኛል የሚለውን ነገር ከመጤፍ አይቆጥሩትም፡፡ ወንዶቹም ቢሆኑ አብዛኞቹ ያገቡ ስለሆኑ ስለዝሙት አይነሳባቸውም፡፡

እንደውም በአንድ አጋጣሚ የተከሰተውን ነገር ለምን አልነግራችሁም? በአንድ ወቅት አንዲት ደምቃና የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ተሸሞንሙና የወጣች እንስት ከአንድ ወጣት ሙስሊም ጋር በባቡር ላይ ይገናኛሉ፡፡ ሰዉ ሁሉ አተኩሮ ያያታል፡፡ እርሷም እየተገማሸረች የምትወጣው ለዚህ ነው፡፡ ወንዱ ሁሉ በአድናቆትና በምኞት ይመነጥራል፡፡ ይህ ወጣት ግን አንዳችም ትኩረት ላይሰጣት ቀረ፡፡ እርሷ ግን አልፎ አልፎ ትገረምመዋለች፡፡ እርሱ ወይ ፍንክች አላለም፡፡ ታዲያ ተሳፋሪው ቀስ በቀስ እየወረደ ሲቀንስ እርሷ አውቃ የወጣቱ ዓይን ውስጥ ለመግባት ተጠጋችው፡፡ እርሱ ግን አሁንም ከምንም አልቆጠራትም፡፡ ወዲያ ወዲህ ብትቀበጥም አላተኮረባትም፡፡
..... በመጨረሻም በኃይለኛው ተቆጥታ ለመሆኑ አንተ ወደኔ አንዴም የሚታየው እኔ ይህን ያህል ቀፋፊ ነኝ እንዴ? ቆይ እንዲህ ከሆነ እኔ ለማነው ተጋጊጬ የምወጣውን ስትል አቧረቀችበት፡፡

እርሱ ግን በተረጋጋና የራስ መተማመን መንፈስ በተሞላበት ሁኔታ ይህንን ለምን እንደማያደርግ አስረዳት፡፡ አየሽ! እኛ ሙስሊሞች ዕይታችንን እንድንቆጣጠር ታዘናል፡፡ ስለዚህ ወደ ባዳ ሴት ሆነ ብሎ መመልከት የተከለከለ ነው፡፡ ለዚህ ስል ብቻ ነው እኔ ወደ አንቺ የማላየው፡፡ ከዚህ ውጭ በግል ምንም ያደረግሸኝ ነገር የለም፡፡ የእምነት ጉዳይ ሆኖብኝ ነው ወዳንቺ የማልመለከተው አላት፡፡ ልጅቷ በሰማችሁ ነገር ተገረመች፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰውና እምነት እንደዚያ ሰይጣንን አብዝታ በምታበረታታው ሀገረ አሜሪካ መኖሩ አስደነቃት፡፡ እምነት ሰውን ከብልግና ሲታደግ አስተዋለች፡፡ እናም ለመሆኑ ያንተ እምነት ምንድነው? ስትል ወጣቱን ጠየቀችው፡፡ እርሱም እምነቱ ኢስላም መሆኑን ነገራት፡፡ ስለኢስላምም አንዳንድ ነገሮችን ነገራት፡፡ ከዚያም ስልክ ተለዋወጡና በዚሁ ተለያዩ፡፡

ልጅቷ በሰማቸውና ልጁ ላይ ባየችው እፁብ ድንቅ ምግባር እጅጉን ተደምማለች፡፡ እንዲህ ዓይነት ወጣት ገጥሟት ስለማያውቅ ስለርሱ እምነት ልታጠና ጓግታለች፡፡ ወዲያው በነጋታው ደውላ የቁርአንን ኮፒ እንዲሰጣት ጠየቀቸው:: እርሱም የቁርአን ኮፒ ሰጣት ልጅቷም ቁርአንና ሌሎችንም ኢስላማዊ መጻሕፍት ለስድስት ወራት አከታትላ አጠናችው፡፡ ስድስት ወሩ እንዳለቀም ለልጁ ደወለችና ኢስላምን መቀበል እንደምትፈልግ አበሰረችው፡፡ እሱም ወደመስጊድ ወሰዳትና ሰለመችም፡፡ የአላህን አንድነትና ብቸኛ አምላክነቱን መሰከረች፡፡ገና ልትሰልም ስትመጣ እራሱ ሒጃቧን በወጉ ለብሳ ነበር፡፡ እናም አሁን በኛ ማዕከል ውስጥመደበኛ ሴት ዳዒይ ስትሆን በርሷ ሰበብም በርካታ ሴቶች ወደ ኢስላም መጥተዋል፡፡
(ምንጭ፡- ቮይስ ኦፍ ኢስላም - አሜሪካ)

በመጨረሻም ኑእማን አሊ ካን አያይዞም እንዲህ ይላል፡-
«በአሜሪካ ፊትናው ከባድ ነው:: ግና የሰለምቴው ንቃተ ሕሊና ከፍተኛ ነው::

ሙስሊሙ ሐራምና ሐላልን በሚገባ ለይቶ ያውቃል፡፡ እዚህ በአላህ (ሱ.ወ) ሕግ ማቻቻል የሚባል ነገር የለም፡፡ አንዳች ነገር ሐራም መሆኑን ካወቁ ከቤተሰብ ጋር የሚያለያይ እንኳን ቢሆን ለኢስላም ሲሉ ያደርጉታል፡፡,, (ምንጭ፡- ቮይስ ኦፍ ኢስላም - አሜሪካ)

✏️አላዋቂነት ለሁሉም ኃጢአት አብይ ምክንያት ነው፡፡ በተለይ ዝሙት ላይ የድንቁርና አሻራ እጅጉን ይጎላል፡፡ የሰው ልጅ ዓይን ስላለው በጭለማ ውስጥ እንደማያይ ሁሉ ጭንቅላት ስላለው ብቻ ዕውቀት አለው ማለት አይቻልም፡፡ ዕውቀት ከሌለው ደግሞ ድንቁርና መጥቶ እንደ ወቃቢ ይሰፍርበታል፡፡ በርግጥም ከድንቁርና የበለጠ ክፉ ውቃቢ የለም፡፡ ታዲያ የድንቁርና ውቃቢ ያለበት ሰው ቢያንስ በአራት መንገዶች ዝሙት ላይ የወድቃል በአይኑ በምላሱ በእጁ...

🙄እኛ ኢትዮጲያን የነጃሺ ሀገር በአለም ሁለተኛ ሙስሊም የተቀበልን የኢትዮ ግማሽ ፐርንሰት በላይ ሙስሊም ነን ..ዲነኛ ነን ኪታብ ቀርተናል ..መስጊድ ተነካ..ኢስላም ተደፈረ ..ወዘተ በምላስ እንላለን በጎን ዚና እንሰራለን🤔

☞ክርስቲያኖች ኢትዮ የሙሴ ፅላት አለ ..አርባ አራት ታቦት አለ ..ኢትዮ ገማደ መስቀሉ አለ ይሄን ያህል ገዳም አለን ኢትዮ የኛ ናት በጎን ዚና እንሰራለን🤔

ለወደፊት የማዘጋጀዉ ፁሁፍ አዲስ አበባ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም አራተኛ የዝሙት ሀገር መሆኗን በአለም ተረጋግጧል በዚህ ሰፋ ያለ ፁሁፍ ጊዜ ሳገኝ አዘጋጃለሁ፡፡

ግን ኢትዮጲያ አዲስ አበባ ያለዉ ሀይማኖተኛ ሀይማኖት ያለዉ ነዉ ግን ከአፍሪካ 1ኛ የዝሙት ሀገር ነዉ...ኢንሻ አሏህ ስለ አዲስ አበባ  የማይታመኑ 100% እዉተኛ ነገሮች በፁሁፍ ይቀርባሉ፡፡ሀይማኖት በልብም በተግባር ነዉ

ፈጣሪ የምላስ ሀይማኖተኛ አስመሳይ ከመሆን ይጠብቀን፡፡
ከዝሙት እንጠንቀቅ ..በዝሙት መስመር ያለን እንቶብት!!!

#ምንጭ ☞በዝሙት አንዘምን መፅሀፍ



ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
አንድ ብቻውን የሚኖር አቅመ ደካማ ሽማግሌ ነበር፡፡ ሁሌም አላህን ሲለምን ...አላህ ሆይ!!! ለቡጋስ እንደምትለግሰው ሁሉ ለኛም ለግሰን፡፡› ይላል፡፡

ቡጋስ የወፍ ዝሪያ ሲሆን ሲወለድ ምንም ዓይነት ፀጉር የሌለው ሆኖ ነጭ ሰውነት ይዞ ነው፡፡ ጥቁር ባለመሆኑ ምክንያት እናትና አባቱ የኛ ነው ብለው ስለማያስቡ ይመስላል አይቀልቡትም፡፡ እሱም ቢሆን የመብረር አቅም ስለሌለው ሄዶ ሪዝቁን ማምጣት አይችልም፡፡

ነገርግን ሪዝቅ ቢርቅም አርረዛቅ አለ፡፡ ቡጋስ ሽታው አንዳንድ ጉንዳኖችን የመሳብ ሀይል አለው፡፡ ፀጉሩ እስኪበቅልለት ድረስ እነኚህኑ ይመግባል፡፡ በዚህ ጊዜ እናቱ ታውቀውና እሱን መመገብ ትጀምራለች፡፡


#እውነትም_ለቡጋስ_እንደምትለግሰው_ሁሉ_ለኛም_ለግሰን፡፡

@አሚር ሰይድ

join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
#የኪፍል_ተዉበትና_የአሏህ_አቀባበል
    አሚር ሰይድ


  ማንኛወም ሰዉ ከተዉበት ተዘናግተናል..በተለይ ብዙዎቻችን አሁን ላይ ቦይፍሬድ ገርልፍሬንድ ስም በተጨማለቅንበት  በዝሙት ላይ ሁነን ለመቶበት አንዴ ገብተንበታል በሚል አስተሳሰብ የብስ በወንጀል ላይ ወንጀል እየደራረብን ነዉ፡፡ነገ ይሄን ዛሬ ሞቻችንን ሳናቀዉ በጊዜያዊ ደስታ ዱንያችንን  አኼራንም እያጣን ነዉ...እስኪ ዝሙት የሚሰራዉ በአራጣ በቁማር ወንጀል ላይ የነበረዉ ኪፊል  ለሊት ሙቶ አደረ አላህም ተዉበቱን ተቀበለዉ በምን ይሆን ተዉበተን የተቀበለዉ??እስኪ የሀቢቡና ሙሀመድ የተናገሩትን ሀዲስን ልጋብዛችሁ



ዐብደሏህ ቢን ዑመር(ረ.ዐ)እንዳወሩት እኔ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ  ከሰባት ጊዜ በላይ እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:-

    በበኒ አስራኤል ውስጥ ኪፍል የሚባል ሰው ነበረ:: ይሄ ሰው ማንኛዉም ወንጀል በመሥራት ይታወቃል። አላህን የማይፈራ የለየለት ሙጅሪም ሰው ነበረ፡፡ ያገኘውን ሀጥያት የሚሠራ ሰው ነበረ፡፡

አንድ ቀን አንዲት ሴት ተቸገረችና (መቼስ አላህ ድህነትን ያላለጠበት ሰው ፈተናው ከባድ ነውና) እርሱ ጋ መጥታ ገንዘብ ጠየቀችው፡፡ እርሱ ሃብታም ሰው ነበር፡፡ ወንጀል የሚባል ግን አንድም የቀረው ነገር የለም፡፡ ከዚያም ስድሳ ዲናር ሊሰጣትና እርሷ ደግሞ ለዚና እራሷን ልታመቻችላት ዘገድ እነጋገራት፡፡ እንግዲህ አስቡት! በዚያን ጊዜ 60 ዲናር ማለት  በጣም ከፍተኛ ብር ነው፤ በኃይለኛው ያማልላል፡፡

ይህች ሴትም ፈቃደኛ ሆነች  ተቸግራለችና ድህነቱ አስገደዳት)፡፡ ከዚያም ስድሳወጣም ዲናር ሰጣት፡፡ ከዚያም እርሷ እራሷን አመቻቸች፡

እርሱም ዚና ለመስራት  እላይዋ ላይ ተቀምጦ ሳለ  ይህች ሴት ከመቅፅበት ተንቀጠቀጠች አለቀሰች😢 ተርገበገበች፤ ተንዘፈዘፈችና በኃይለኛውም አነባች፡፡
.... ኪፍልም ምን ነካሽ? ብዙ ገንዘብ አይደል እንዴ የሰጠሁሽ? አስገድጄሻለሁ እንዴ? በፍላጎትሽ አይደለም እንዴ? እናም ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሺዉ?? አላት፡፡
....ከዚያም ይህች ሴት ወሏሂ! እኔ ይህንን የዚና ኃጢአት በዕድሜዬ እኮ ሠርቼው አላውቅም፤ ችግሩ አስገድዶኝ ነው እንጂ። ፈፅሞ ሠርቼው የማላውቀው ወንጀል ስለሆነ አሁን አላህን ፈርቼ ነው የማለቅሰው አለቸው፡፡ ......አርሱም አላህን ፈርተሽ ነው የምታለቅሺውን??
...... አላት፡፡ አዎ› አለችው፡፡

አስቡት አንግዲህ! ይሄ ዕድሜ ልኩን ወንጀል ሲሠራ የኖረ ሰው ነው፡፡ መች ይህ ብቻ እንድም መልካም ሥራ ሠርቶ አያውቅም፡፡  የዚህች ሴት ተቅዋና የርሷ መንቀጥቀጥ ልቡን ነካውና ወዲያው ይህንን ሁሉ ስድሳውን ዲናር ውሰጂው፡፡ እኔ አሁን ተወብት ገብቻለው እናም አልነካሽም ዚና አልሰራሽም፡፡ እኔ ካሁን ጀምሮ አበደን አላህን አልወነጅልም፡፡ ኃጢአት፣ ዝሙት፣ ፀያፍ ድርጊት የሚባል ነገር ካሁን ወዲያ ምንም አልሠራም፡፡ አንቺ ችግሩ እያለብሽ፣ ገንዘቡንም ለመውሰድ እየፈለግሽ ግን የአላህ ፍራቻው ገታሽ፡፡ አኔም ከዚህ በኋላ አላህን ፈፅሞ አላምፅም አለ፡፡


ከዚያም ነብዩ ﷺ እንደተናገሩት ይህ ሰው በዛቸው ለሊት ሞቶ አደረ፡፡ መሞቱም በበሩ ላይ ተፅፎ በተገኘዉ ፁሁፍ  ተረዳ፤ በአላህ መላእክት አማካኝነት፡፡


አላህ ለኪፍል ምሮታል የሚል ዐ.ነገር በበሩ ላይ ለየት ባለ ጽሑፍ ተፅፎ ተገኘ፡፡» (ቲርሚዚ ዘግበዉታል)


⚠️⚠️  ከዝሙት እንቶብት አሁን ዝሙትን መሥራት ውሃን የመጠጣት ያህል እና እጮኛን መያዝ ሻንጣን የመያዝ ያህል ቀላል በሆነበት ዘመናዊት ዓለም ውስጥ በመዘናጋት ያለተዉበት ሞትን እየጠበቅን ነዉ...ይቺ ነገ እንቶብታታለን ያልናት ቀን ነገ ሳትደርስ ሞት ቀድማን ከነገ ወዳ ያለዉን የአኼራ ህይወት  የቀብር ህይወት የነኪርና ነኪር ጥያቄ ...አላህ ፊት ያለ አስተርጓሚ ለጥያቄ ለመቅረብ  ምን ያህላችን ዝግጁዎች ነን??
ምን ያህሎቻችን ለመቶበት ዝግጁዎች ነን??


ሼር በማድረግ ኢስላማዊ ግዴታዉን ይወጡ..በዚህ ፁሁፍ የተነሳ አንድ ሰዉ ቢቶብት ትልቅ ነገር ነዉና...


join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
ድል ያለ ሰርግ ተደግሶ ባል እና ሚስት ቃለ መሀላ ለመፈጸም እየተዘጋጁ ሳለ ነው ባል ቃል ከመግባታችን በፊት መናገር የምፈልገው ነገር አለ በማለት ማይኩን የተቀበለው።

ቀጠለናም የታሸገ ፖስታ ለሁሉም የሰርጉ ታዳሚዎች እንዲሰራጭ እና ታዳሚዎቹም ፖስታውን ከፍተው እንዲመለከቱት ያደርጋል፡፡ 

የታሸገው ፖስታ ውስጥ ያለው ሚስቱ ለመሆን ቃለመሃላ ለመፈፀም እየተቁነጠነጠች ካጠገቡ የቆመችው ሴት እና አንደኛ ሚዜው የኔ ፍቅር የኔ ውድ እየተባባሉ ሲማግጡ የሚያሳይ ፎቶ ነበር፡፡ 

ሙሽራው አሁንም ማይኩን እንደያዘ  “በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ምስል ውዷ እጮኛየ እና የልብ ጓደኛዬ ማንም አያየንም ብለው ተደብቀው ሲማግጡ የሚያሳይ ነው። ታዲያስ  ከእንደዚች አይነት ሴት ጋር ትዳር ባልመሰርት የሚፈርድብኝ አለ?!"ብሎ ታዳሚውን ጠየቀ።መልስ አላገኘም።

ኋላም ሙሽሪት በድንጋጤ በቆመችበት ደህና ሁኚ ብሏት ከቤተሰቦቹ ጋር የሰርጉን አዳራሽ ጥሎ ወጥቷል፡፡
☞ የዴይሊ ሜይል ዘገባ ነው

#ከዝሙት እንጠንቀቅ እንቶብት...ዝሙት ዛሬም ነገም ከነገ ወዳም መዘዙ ሰፊ ነዉ፡፡ለ15 ሰከንድ የሀራም እርካታ የ40 የ50 አምት ፕላናችንን አናበላሽ፡፡
አላህን አምፀን አላህ በዱንያ ዋጋችንን ያስከፍለናል ብድር በምድር‼️

ነገ እኛም በዝሙት ላይ ያለን እኛን በምን እንደሚያዋርደን አይታወቅም፡፡

ወላሂ ዝሙተኛ ሰዉ ሰላም የለዉም...በዱንያ ድህነት ጭንቀት ነዉ፡፡ሴቷም እራሷን ዝቅ ታደርጋለች.ዝሙተኛ ሴት ቤተሰብ የማያቃት ሴተኛ አዳሪ ማለት ነች..ለምን ዚና ስትሰራ ቤተሰቧ ሳያያት ነዉ፡፡ልጄ ጎበዝ ናት ዲነኛ ናት ይላል ቤተሰብ..እሷ ግን ቤተሰብ የማያቃት ሴተኛ አዳሪ ነች


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
#አይነስዉሩ_ልጅ
አሚር ሰይድ

አንድ ሰውዬ ነበር ሁለት ልጆች አሉት በዲኑ ላይ ብዙም አይደለም፡፡ብዙን ጊዜ በሰዎች በማሾፍና በማላገጥ የተጠመደ ነው።አንድ ቀን መንገድ ላይ የሚሄድ ዐይነ ሥውር አጋጠመው ሰዎችን ሊያስቅበት ብሎ ከጎኑ  እየሄደ በዚህ ሰው ማላገጥ ጀመረ፡፡በዚህን ጊዜ ዐይነ ስዉሩ ሰው ልቡ ተሰበረበ እጅጉ😔ተሰማው፡በውስጡ ያለውን ደግሞ አላህ ይወቅ፡፡ከወራት በኋላ ይህ ሰው ዐይነ ስውር የሆነ ልጅ ተወለደለት፡፡ በዚም የተነሳ ተደናግጦና ሃሳብ ገብቶት ከዚህ ልጅ ጋር ግንኙነቱን አቋረጠ፡፡ እሱን ትቶ ለሌሎቹ ሁለት ልጆች ትኩረት ሰጠ፡፡ አዲሱን ልጁን ለእናቱ በመተው የሚያስፈልገውንም ወጭ ለሷ መስጠት ያዘ።ሆኖም ግን ውስጡ በእጅጉ ተጎድቶ ነበር፡፡ ይህ ልጅ ለመጥፎ ድርጊቶቹ መቀጫ ይሆን ዘንድ የተላከበት መሰለው፡፡የአባትነትን ፍቅር ለልጁ ነፈገዉ


ህፃኑ ልጅ ስድስት ዓመት ሞላው።አንድ ቀን እናት ከሁለት ልጆቹ ጋር ወጣ ብላ ስለነበር አባት ከዐይነ ስውር ልጁ ጋር ብቻውን ቤት ውስጥ ቀረ፡፡ቀኑ ጁሙዓ ነውና ልጁ አባቱ ወደ መስጊድ እንዲወስደው ጠየቀ፡አባት የስድስት ዓመት ልጁ የሚሰግድ መሆኑን ባወቀ ጊዜ ደነገጠ፡ከዚህ በፊት መስጅድ ይወስደው የነበረ ማን እንደሆነ ጠየቀው። ልጁም እናቱ እንደሆነች ነገረው፡፡ አባት ልጁን ወደ መስጅድ ይዞት መሄድ ጀመረ።

አንድ የሚያውቀው ትልቅ ሽማግሌ ይዞ የሚሄድ ዓይነት ተሰማው። ልጁ ከቁርአን የአል ከህፍን ምዕራፍ እያነበበ ነበር፡፡ አባት ይህን ሲሰማ ማልቀስ ጀመረ፡፡ በልጁ ሰበብ አላህን አወቀ፡፡ ልጁ በቃሉ ቁርኣንን መሸምደዱ ገረመው፡፡

ስብራቱ የነበረው ልጅ በዚህ መልኩ ወደ ፀጋ የተለወጠ ሆኖ አገኘው:: ሱብሀነሏህ፡
ትበድልና  ይሰብርሃል፡፡ ትግጎዳለህም፡፡ወደሱ ተጠግተህ በለመንከው ጊዜ ግን ስብራቱን ወደ ፀጋ ይለውጥልሀል፡፡
💚እናትነት ይህ ነዉ
🔴🔉🔉ታላቅ የምስራች ተጅዊድን መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች🟡📢📢

🔊
#ዚክራ_ኦንላይን_የቁርአን_ማእከል
የተጅዊድ ትምሀርት  ይዞላችሁ መጥቷል

🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘

   
#የሚሰጠው_ኪታብ📚
البرهان في تجويد القرآن📚

    
#የሚሚሰጡ_ትምህርቶች📜📜

🔶
#የቁርአን አነባበብ ህጎች
🔶
#የቁርአን መጀመሪያና ማቆምያ ህጎች
🔶
#የፊደላት መውጫ (መኻሪጁል ሁሩፍ
🔶
#የፊደላት ባህሪያት (ሲፋቱል ሁሩፍ)
🔶
#የኑነ ሳኪና ወተንዊን ህጎች
🔶
#የመድ (የመሳብ) ህጎች
🔶
#የ ''ሯ'' ህጎች
🔶
#የሚመሳኪና ህጎች
🔶
#የሀምዘተል ወስል እና ቀጥእ ህግ
🔶
#የኢድጋም ህጎች
🔶
#የቀልቀላ ህጎች

📚📚📚📚📚
#የትምህርቱ_አሰጣጥ📘📕

1,በዙም አፕልኪሼን
2,በቴሌግራም አፕልኬሽን
    
       
#የቆይታ_ጊዜ 🕙

በሳምንት 4 ቀን


#ትምህርቱን_ለመከታተል_የሚያስፈልጉ

🔹ዋይፋይ(ፈጣን ኔትወርክ)
🔸ስማርት ስልክ

ይህን ሁሉ ደርስ በ #500 ብር ብቻ ይማሩ

ለመመዝገብ
👇👇👇👇
@zikra0835


👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/zikraquran



   በተጨማሪም
👉 ቁርአንን በተጅዊድ ማንበብ
👉  ለጀማሪዎች ቃኢዳ
👉  ሀዲስ እና የአቂዳ ኪታቦችን በግል(VIP)  እና በግሩፕ እናስቀራለን።
በግል ለመመዝገብ
https://www.tg-me.com/+251931800835

#ዚክራ_የቁርአን_መድረሳ
#ምድራዊውና_ዘልዓለማዊው_ዓለም

ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ “በርግጥ አላህ ሲሳያችሁን በመካከላችሁ እንዳከፋፈለ ሁሉ ሥነ-ምግባራችሁንም በመካከላችሁ ከፋፍሏል፡፡ አላህ ለሚወደው ሰውም ሆነ ለማይወደው ሁሉ ሁበት ይሰጣል፡፡ ሃይማኖትን ኢስላምን ለሚወደው ሰው ካልሆነ በስተቀር አይሰጥም፡፡
አላህ ሃይማኖት የሰጠው ሰው በርግጥ አላህ ወድዶታል፡፡


ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! የአንድ የአላህ ባሪያ ልብና ምላስ ኢስላምን በወጉ እስካልተቀበሉ ድረስ ኢስላምን አይቀበልም፡፡ ጐረቤቱንም ከችግሮቹ ካልጠበቀ አያምንም፡፡" ሰዎችም "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ችግሮቹ ምንድን ናቸው?" ሲሉ ጠየቋቸው፡፡ እሳቸውም “ተንኮሉና በደሉ ናቸው፡፡ አንድ ሰው ገንዘብ አያግኝ፡ በእሱም ይባረክለት ዘንድ ያገኝ ዘንድ ከእሱ አይመፅውት፡፡ ከበስተጀርባውም አይተወውም፡፡ ይህ በራሱ ወደ እሳት የሚከተው ካልሆነ በስተቀር፡፡ አላህ መጥፎ ነገርን በመጥፎ አያጠፋም፡፡ ነገር ግን መጥፎ ነገርን በመልካም ነገር ያጠፋል።"

አሚር ሰይድ



join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
#በታሪክ_ትልቁ_ሶላት_አልጀናዛ


 
ሱልጧን ሱለይማን አልቃኑኒ ከእለታት በአንዱ ለሊት
አንድ ህልም አዩና ተደናግጠው ከእንቅልፋቸው ተነሱ
የቅርብ ዘባቸውን ተጣርተው
ፈረስ እንዲያዘጋጅላቸውና ሲነጋ ጎዳና ላይ ወጥተው
የህዝቡን የቀን እንቅስቃሴ ማየት እንደሚፈልጉ አስረዱት
ከነጋ በኋላ በተዘጋጀላቸው ፈረስ ብቻቸውን ጎዳና ላይ
በመውጣት የህዝቡን እንቅስቃሴ መቃኘት ጀመሩ በዚህ
መካክል አንድም ሰው ያልተከተለው አንድ አስከሬን
በጎዳናው ላይ ሁለት ሰዎች ብቻ ወደ መቃብር ሲወስዱት
ተመለከቱ
ሱልጧን ሱለይማንም ቀርብ ብለው ይሄ ብቻውን ወደ
መቃብር የሚሸኘው አስከሬን የማነው? ብለው ሲጠይቁ
ይሄማ ዝሙተኛና ኸምር ጠጪ ከሚስቱ ውጭ ልጅም ሆነ
ቤተሰብ የሌለው ግለሰብ አስከሬን ነው ስለዚህ የዚህን
ዝሙተኛ እና መጠጥ ጠጪ አስክሬን ማንም ሰው
ሊሸኘውና ሊሰግድበት ፍቃደኛ የሆነ ሰው የለም ይሏቸዋል
ሱልጣን ሱለይማንም በጣም ይቁጡና ይሄማ እንዴት
ይሆናል የሙሀመድ ኡመት አይደለምን? ይሉና አስከሬኑን
ተሸክመው ወደ ባለቤቱ ይመልሱታል
እዛም እንደደረሱ ባለቤቱ እጅግ አዝና ታነባለች ሱልጣኑም
በመገረም እንዴት እንደዚህ ታለቅሻለሽ ባለቤትሽ
ዝሙተኛና ጠጪ አልነበረም አንዴ? ይሏታል
የሟች ሚስትም የሚጠይቃት ሰው ሱልጣን ሱለይማን
መሆናቸውን አታውቅም
ባለቤቴ አላህ ይዘንለትና አላህን የሚፈራ ነበር ልክ
እንደሱ አላህን ፈሪ ልጅ ይመኝ ነበር ነገር ግን ሞት
ቀደመው ትላቸዋለች
ሱልጣኑም ባለቤትሽ ከዝሙተኝነቱና ከጠጪነቱ ውጭ
ምን የተለየ ነገር ይሰራ ነበር ? ይሏታል
ሚስትም ባለቤቴ ሁልጊዜም በእየመንደሩ እየዞረ መጠጥ
ወደሚገኝበት ቦታ በመሄድ መጠጦችን በብዛት በመግዛት
ወደ ቤት ያመጣና ግቢ ውስጥ ባዘጋጀው ጉድጓድ ውስጥ
ይደፋውና አልሀምዱሊላህ ዛሬ ለብዙ ሙስሊም ወጣት
ወንድሞቼ ብዙ ወንጀልን ቀነስኩላቸው እያለ ጌታውን
ያመሰግን ነበር
በማስከተልም ሁልጊዜ ምሽት በሆነ ቁጥር ወደ ሴተኛ
አዳሪዎች መንደር በመጓዝ ለብዙ ሴተኛ አዳሪዎች ዝሙት
ሰርተው የሚጋኙትን ሙሉ የቀን ገቢያቸውን ክፍያ
ከሰጣቸው በኋላ ወደቤታቸው እንዲመለሱ ያደርግና እቤቱ
መጥቶ አልሀምዱሊላህ ዛሬ ለብዙ ሙስሊም ወጣት
ወንድሞቼ የዚናን ወንጀል ቀነስኩላቸው እያለ ጌታውን
ያመሰግን ነበር
እኔም ሰዎች ከላይ የምትሰራውን ብቻ ነው የሚመለከቱት
አንድ ቀን መሞትህ አይቀርም ያኔ ጀናዛህን አጥቦ ሶላተል
ጀናዛ የሚሰግድብህና የሚቀብርህ አንድም ሰው አታገኝም
እለው ነበር
እሱም እያሰቀ ጀናዛየን ሱልጣን ሱለይማን አጥቦ በጀናዛየ
ላይም ሱልጣን ሱለይማን ከእነ ሰራዊቱ ከእነ
ምኒስትሮቹና ከታላቅ የሀገሪቱ ሼኮች ጋር ሆኖ የሀገሪቱ
ሁሉም ሙስሊሞች ሲሰግዱብኝ ታያለሽ እያለ ይነግረኝ
ነበር በማለት የባሏን የህይወት ታሪክ አጠገቧ ለቁመው
ሰው ትነግረዋለች
ሱልጣን ሱለይማንም ከልቡ በማልቀስ አዎ ልክ ነው እኔ
ሱልጣን ሱለይማን ነኝ እኔው እራሴ ጀናዛውን አጥበዋለሁ
ይለና የዚህን ምርጥ የአላህ ባሪያ ጀናዛ እራሱ ካጠበ
በኋላ
ለሀገሪቱ ሙሉ ሰራዊት ለሀገሪቱ ሙሉ ባለስልጣናት
ለሀገሪቱ ሙሉ መሻኢኾች ለሀገሪቱ ሙስሊሞች በሙሉ
ትዕዛዝ በማስተላለፍ በዚህ የአላህ ባሪያ ጀናዛ ላይ
እንዲገኙ በማድረግ ሱልጧን ሱለይማን አልቃኑኒ በታሪክ
ትልቁን ሶላተል ጀናዛ በዚህ ድንቅ የአላህ ባርያ ላይ
አሰገዱ።
ውጭ ላይ ለእኛ በተገለጠልን ነገር ላይ ብቻ ተመርኩዘን
የአላህን ባሮች መለካት መመዘን ደረጃን መስጠት ከባድ
ነገር ነው ከእኛ እውቀትም ውጭ ነው...


በዚህ አስተማሪ ታሪክ ብዙዎች ሊማሩበት ይችላሉና ለወዳጅ ዘመዶችዎ  ሼር ሳያደርጉ አይለፉ!!


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔰#የሙስሊሞችን_ሥጋ_የተመገበው_የእንግሊዙ_መሪ_ሪቻርድ


   አውሮፓውያን "የአንበሳ ልብ" ሲሉ ያሞካሹታል። ታሪኩን በሚገባ ያወቁት ደግሞ “የአሳማ ልብ ባለቤት” ብለው ይጠሩታል። እርሱ አያቶቹ መስቀላዊያን በይተል መቅዲስን በተቆጣጠሩ ጊዜ ያደረሱትን በደል በአካ ከተማ የደገመው ሪቻርድ ነው። 
   ከግብፅ እስከ ዱባይ ከቦሊዩድ እስከ ፎረስት ጋምብ ጸሐፊዎች ገፃቸውን፣ ዳይሬክተሮች ስክሪብታቸውን ፕሮዲዩሰሮች ፊልሞቻቸውን በስሙ አስውበውበታል። በጀግንነት እያወደሱ ስብእናውን እያገነኑ አውስተውታል። ግና እርሱ ሙስሊሙን ጀግና ፈረሰኛ ኢሳ አል አዋምን ወደ ክርስቲያን ጦረኛ የቀየረ፣ የሙስሊሞችን ስጋ የበላ ሙስሊም ጠሉ ሪቸርድ ነው።
"ከቀናቶች በአንደኛው ቀን ምግብ ሰሪ አገልጋዩን ለምሳ ትኩስ የአሳማ ሥጋ እንዲያቀርብለት አዘዘ። ጣፋጭ አድርጎ እንዲሰራለትም ተናገረ። ምግብ ሰሪው አሳማ የት ሀገር እንደሚገኝ አያውቅም። ቢፈልግም ማግኘት አልቻለም። ከየት ያምጣ ግራ ገባው።  በምግብ ጠረጴዛው ላይ የአሳማ ስጋ ከሌለ መገደሉ አይቀሬ ነውና ተጨነቀ። አንድ መላ ዘየድ። ሁለት ሙስሊም እስረኞችን አረደና ስጋቸውን አብስሎ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ😔። የምሳ ሰአት ደረሰ። ንጉስ ሪቻርድ ምግቡን መብላት ጀመረ። ተመግቦ እንዳበቃ በጥፍጥናው ተገረመ። የሰራለትን ሰው አመሰገነ ግና ስጋው የአሳማ አለመሆኑን ተገነዘበ። ምግብ ሰሪውን አስጠራና  "የአሳማውን ጭንቅላት አምጡ" ሲል አዘዘ።
   ምግብ ሰሪው ምን ያርግ? ምንስ ይበል?! ምላሱ ተኮላተፈ። በእጅጉ ተሸበረ። በፍርሃት ራደ። በድንጋጤ ተንቀጠቀጠ። በመጨረሻም እውነቱን ለማሳየት ወሰነ። የታረዱትን የሁለቱን ሙስሊም ምርኮኞች ጭንቅላት ወደ ሪቻርድ ማምጣት ነበረበትና ፊት ለፊቱ አቀረበ።
ሪቻርድ ቅንቅላቶቹን ሲመለከት በሳቅ እና በደስታ ቦረቀ። እንዲህም አለ:- "ስልሳ ሺህ ሙስሊም እስረኞች እስካሉን ድረስ የአሳማ ሥጋ ከእንግዲህ አንፈልግም እነሱን እያረዳችሁ አቅርቡልኝ ስጋቸው ጣፋጭና ጥዑም ነው" አለ።
ሰላሐዲን አልአዩቢ ሙስሊም ምርኮኞቹን እንዳይገድል ሠላሳ መልዕክተኞችን ላከ። ግና ሪቻርድ ሠላሳዎቹንም መልዕክተኞች ገድሎ ስጋቸው ተጠብሶና ተቀቅሎ እንዲመጣ በማድረግ ለጓደኞቹ የክብር መስተንግዶን አዘጋጀላቸው። ጭንቅላታቸው ተቀቅሎ እንደመረቅ ቀረበ።
በአካ ከተማ ሀያ ሺህ በሌላ ዘገባ ስልሳ ሺህ ሙስሊሞችን ጨፈጨፈ። ወንዶች ከከሴቶች ሳይለይ ህፃን ከአረጋውያን ሳይመርጥ አረደ። በርካቶችን ማርኮ አረደ። ብዙዎችን በቁማቸው ቀበረ"
   ይህ ነው የሙስሊሞችን ሥጋ ተመጋቢው ሪቻርድ።


ምንጭ-
                  البداية والنهاية
                  النوادر السلطانية والمحاسن اليوسفية
Mahi mahisho


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
           🔰 #ምዕራፍ አንድ ➊
                አሚር ሰይድ

ነሀሴ 23/12/2016 ተጀመረ
╔══════════════════════╗
              #ዝሙትና_የሚያመጣዉ_መዘዝ
╚══════════════════════╝



   #በመጀመሪያ ደረጃ ይሄን ተከታታይ  ፁሁፍ ሼር አድርጋችሁ ለብዙ ሙስሊም ወንድም እህቶች እንዲደርስ በአላህ ስም እጠይቃችሆለሁ አይታወቅም በዚህ ተከታታይ ፁሁፍ የአንድ ሰዉ መቶበት ከአላህ ዘንድ ሼር ያደረገዉም የወንጀላችንን መማሪያ ሊሆን ይችላልና፡፡በተጨማሪ ቻናል ያላችሁ ይህን ፁሁፍ በታስተላልፉት ብዙ ሰዉ ይማርበታል፡፡ፀሀፊ አሚር ሰይድ የሚለዉን አጥፍቶ መፓሰት ይቻላል፡፡አላማየ ለማስተማር እና ተደራሽነቱን ለማስፋት ነዉ፡፡

ይህን ተከታታይ የሆነ ፁሁፍ ሳዘጋጅ ከእናንተ የተሻልኩ ሁኜ ሳይሆን ከአበብኩት ከሰማሆቸዉ ተንተርሼ ነዉ...ይህ ፁሁፍ 65%የተዘጋጀዉ በዝሙት መዘመን ስልጣኔ ወይስ የአለም ፍፃሜ ምልክት ከሚለዉ መፅሀፍ ሲሆን 35%ደግሞ ከሌሎች መፅሀፎችና በራሴ የጨመርኳቸዉ የተሻሉ አመለካከቶች ተሰናድተዋል፡፡በዝሙት መዘመን የሚለዉን መፅሀፍ ገዝታችሁ ብታነቡት በጣም ትምህርት ትወስዱበታላችሁ፡፡ይህ መፅሀፍ 408 ገፅ ያለዉ ሲሆን በ2009 ዓም የተፃፈ ነዉ ጥቅሙ ግን ብዙ ነዉ

🔰ይህ ፁሁፍ ሲዘጋጅ በጣም ፈታኝ ነበር ከ408ገፅ ተለቅሞ የተፃፈ እና ኦርደር ለማደረግ ፈታኝ ነበር በምናነበዉ ተጠቃሚ ያድርገን

አሁን ያለነዉ ማህበረሰብ ብዙ ሰዉ ዝሙትን ዉሀ የመጠጣት ያህል ቀላል አድርጎ ይዞታል፡፡በዚህ ፁሁፍ ማንበቡና ለሌሎች ሼር ማድረጉ ብዙ ጠቀሜታ አለዉ፡፡ፁሁፉን ለማዘጋጀት በጣም ብዙ ቀናት ፈጅቻለሁ ለምን የዝሙት ጉዳይ በጣጣጣም አሳሳቢ ላይ ደርሷል...የሀይማኖት አባቶችም ስለዝሙት በአደባባይ ማስተማር እስከሚፈሩ ድረስ ዝሙት በየቤቱ በር አንኳክቷል በተለየይ አዲስ አበባ ላይ ዝሙት ከቁጥር ዉጭ  ሁኗል በዝሙት ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም አራተኛነትን ደረጃ ላይ ነች፡፡
ኢትዮጲያ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም ሀይማኖተኛ ነኝ በሚልባት ሀገር ዝሙትግን በጣም ተንሰራፍቷል ከቁጥጥር ዉጭ ሁኗል፡ቤተሰብና ሴት ልጅ ሳይተዋወቁ እየኖሩ ይገኛሉ፡፡አላህ ለሁላችንም ይድረስልን፡፡

                  እነሆ ወደ ፁሁፉ

ዝሙት ማለት በቀላል ቋንቋ አንድ አላህን የማይፈራ ኢማን የሌለዉ ወንድ አላህን የማትፈራ አጂ ነብይ የሆነች ሴት ማህፀን ዉስጥ በሀራም ግንኙነት ጊዜያዊ ደስታ ፈጥሮ..የዱንያም ለአኼራም ፈተና ላይ መዉደቅና ነገ ጀሀነም ከሚገቡት ሰዎች መሰለፍ ማለት ነዉ

ዝሙት የአላህን ቁጣ እንደሚያመጣ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- በአንድ መንደር ዉስጥ ዝሙትና ወለድ ይፋ ከወጡ እነርሱ የአላህን ቁጣ በራሳቸዉ ላይ አድርገዋል(አልሀኪም ዘግበዉታል)

☞በሌላ ሀዲስ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል ከሺርክ ቀጥሎ ያለዉ ሀጥያት ባልተፈቀደለት ማህፀን ዉስጥ በሰዉየዉ የተረጨ የወንዱ የዘር ፈሳሽ ነዉ፡፡



☞በሌላ ሀዲስ ሰይዲና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል
ብእርግጥ እኔ ለናንተ እምፈራላችሁ ርካሽ ስሜቶችን ነው:: በሆዳችሁና በብልቶቻችሁ ምከንያት የሚፈጠሩ አጥፊ ስሜቶቻችሁን ነው፡፡ (አሕመድ) ብለዋል፡፡


     በዘመናችን በርካታ የተዛቡና በካይ የሆኑ አስተሳሰቦች ብዘዎች ዘንድ በተለይ ወጣት ማህበረሰቡ ላይ ተይዘዋል፡፡Sex is Life»! «Sex is Free» «Sex is Gift from God! ወዘተ የሚሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡በርግጥ ኢስላምም የከለከለው ወሲብን ሳይሆን ዝሙትን ነው፡፡ ማንኛውም ሕጋዊ ወሲብ ከሀላል ሚስቱ ጋር በኢስላም አልተከለከለም፡፡ነገር ግን ወሲብ በሚል ሽፋን አብዛኛው ወጣት ዝሙትን እንደ መዝናኛ ይዞታል።ከዚህም የተነሳ ለዝሙትም የወሲብን ስያሜ በመስጠት ከአስተሳሰብ ጀምሮ ብዙ ሰዎችን በዝሙት ባሕር ውስጥ ለማስመጥ ተችሏል፡፡

ሀቢቡና ሙሀመድﷺ እንዲህ ብለዋል፦

#ሙስሊሞች_ሆይ! ዝሙትን ተጠንቀቁ ራቁት፡፡ እርሱም ስድስት ጉዳቶችን ያስከትላል፤ ሶስቶቹ በዚህ ዓለምና ሌሎቹ በቀጣዩ ዓለም ሲሆኑ፡፡

#ዱንያዊ ጉዳቶቹን በተመለከተ
➊ የፊት መገርጣት/መደብዘዝ፣
➋አጭር ዕድሜና
➌ረጅም ድህነት ናቸው

#የቍጣዩ ዓለም ጉዳቶቹ ደግሞ
➊የአላህን ቁጣ መውረስ፣
➋ጥብቅ (ኮስተር ያለ) ምርመራና
➌በእሳት ውስጥ መቀጣት ናቸው፡፡»(ኢብን ዐዲይ)

     ዝሙት በርካታ ዓለማዊና አኼራዊ ጉዳቶችን ያስከትላል፡፡ መዘዙና አስከፊነቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ዝሙት ለተለያዩ በሽታዎች ይዳርጋል፡፡ከነዚህም መካከል
☞ኤችአይቪ/ኤድስ የዝሙት አብይ ጉዳት መሆኑ አይካድም
☞ዝሙት ለውርጃ ይዳርጋል፡፡
☞ ዝሙት ለአስከፊው የሴተኛ አዳሪነት ሕይወትና ለሴሰኝነት ይዳርጋል፡፡
☞ዝሙት ከትዳር ያርቃል
☞ ዝሙት ለትዳር አለመረጋጋትና ለቤተሰብ መበታተን አብይ መንስኤ ነው::
☞ ዝሙት ለተለያዩ ደባል ሱሶች ይዳርጋል፡፡
☞ዝሙት አባቶቻቸው የማይታወቁ ልጆች በማህበረሰቡ ውስጥ እንዲበዙ ያደርጋል
☞ዝሙት ድህነትን ያስወርሳል፡፡
☞ዝሙት በረካን ይነሳል፡፡
☞ ዝሙት ሰብአዊ ክብርን በመግፈፍ እንስሳዊ ባህሪን ያላብሳል፡፡


   ዝሙተኛ ወንድ ዝሙተኛ ሴትን ዳግም ሊያገኛት ይችላል፤አንድም ድርጊቱ ስርቆት ስለሆነ የተገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም በአነቃቂ መድሀኒቶች በርካታ ዙሮችን ይሄዳል።በተለይ አሁን አሁን ወንዱ ዝሙተኛ የተለያዩ የወሲብ ማነቃቂያ ዕፆችን በመጠቀም የወሲብ ጀብደኛ ለመሆን ይፈልጋል፡፡ በብልግናው ዘርፍ የወሲብ ጀብደኛ ማለት ደግሞ በሕገወጥ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ላይ ረጅም ሰዓትን የሚያሳልፍ ሰው ማለት ነው፡፡ነገር ግን ከኢስላማዊ አስተምህሮት አንፃር ዝሙተኛው ዝሙትን በሚፈፅምበት ጊዜ ኢማኑ ከልቡ ውስጥ ወጥቶ ከላዩ ላይ ያንጣልላል፡፡የዚህም ምሳሌ ልክ አንድ ሰው ሸሚዙን አውልቆ እንደሚሰቅለው ማለት ነው፡፡ይህም ማለት ግለሰቡ በዝሙት ድርጊት ላይ ረጅም ጊዜን የሚያሳልፍ ከሆነ ኢማኑ በልቡ ውስጥ የሚቆየው ለአጭር ጊዜ ብቻ ይሆናል፡፡ ልክ እንደዚሁ ይህንኑ ፀያፍ ድርጊቱን አብዝቶ የሚደጋግም ከሆነ ኢማኑም በዚያው ልክ በተደጋጋሚ ከልቡ ውስጥ ወልቆ ከላዩ ላይ ያንጣልላል፡፡ይህ እንግዲህ ዝሙትን መሥራት፣ በዝሙት ጀብደኛ መሆን፤ ዝሙትን እንደ መዝናኛ የመውሰድ አባዜ፣በዝሙት መዘመንና ዝሙትን የሕይወት ልማድ አድርጎ መያዝ ምን ያህል በኢማን መጫወት እንደሆነ ያሳየናል፡፡
ምክንያቱም
ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺዝሙተኛ ዝሙትን በሚሰራበት ጊዜ እርሱ ሙዕሚን ሆኖ አይደለም ብለዋልና፡፡


    እንደሚታወቀው ዝሙት በራሱ ትልቅ ደዌና አደገኛ ሱስ ነው::ለሴሰኝነት ይዳርጋል፤እዚያም እዚሀም ያልከሰከሳል፡፡ምክንያቱም መንገድነቱ የከፋ ነውና፡፡ወደ ዝሙት ለመግባት ከባድ ነው፡፡ አንዴ ከገቡበት በኋላ ግን ለመደጋገም ቀላል ነው፡፡ በዚያው ልክ ለመተው ከባድ ነው፤ምክንያቱም ዝሙት አደገኛ ሱስ ነውና፡፡በዚህን ጊዜ የዝሙት ሱሰኛው ከሱስ መላቀቁ ይቀርና ወደባሰው እርከን ይሸጋገራል፡፡ቀማሽና አተራማሽ ይሆናል፡፡ከዚያም በኖርማል ወሲብ መርካት ይሳነዋል፡፡ቀጥሎም የወሲብ ፈልም ቅጥቅጥ ለመሆን ይሞከራል፡፡ ይህንኑ እውን ለማድረግ ደግሞ ልዩ ልዩ ሱስ አስያዥ ዕፆችን መጠቀም ይጀምራል፡፡ይህም በተራው ለተለያዩ ወሲባዊ እብደቶች አሳልፎ ይሰጠዋል፡፡ግለሰቡ የጥፋት ጎዳናን ተከትሎ ይሄዳል፡፡ከዚህም በላይ ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው አንድ ሰው በማንኛውዏ ጊዜ ዝሙት ላይ ሲወድቅ ኢማኑም እንደዚያው ከልቡ ወልቆ በላዩ ላይ ማንጣለሉን👇👇👇
ይቀጥልበታል፡፡ ይህም እውነታ የዝሙትን ድርጊት እጅግ አደገኛና የማይወጡት የወንጀል አዙሪት ያደርገዋል፡፡ ለዚህም ነው «ዝሙትን አትቅረቡት» የሚባለው፡፡


 🌙🌙 ታላቁ ሊቅ ኢማም ኢብኑል ቀይም እንዲህ ብለዋል፡- ስሜትን ከዚና መቆጣጠር ምንዳው ጀነት ነዉ
ዩሱፍ (ዐ.ሰ) መጀመሪያ ባሪያ ነበር፡፡ የዓለም ግማሽ ቁንጅና እንደፈሰሰበት ይነገርለታል፡፡ እርሱን በባለቤትነት የያዘችው የባለሥልጣኑ ሚስትም በፍቅሩ ናወዘች፡፡ ለዝሙትም ገፋፋችው፡፡ እርሷ ውበትና ሥልጣን ያላት ሴት ናት፡፡ እርሱ ግን እምቢ አለ፡፡ ስሜቱንም ተቆጣጠረ፡፡ ከዚያም ተዶልቶበት ወደ ዘብጥያ ተላከ። ነገር ግን የኋላ ኋላ የግብጽ ገዥ (ዐዚዝ) ሆነ፡፡ ስሜቱን የሚቆጣጠር ሰው ምንዳ ይሉሀል ይሄ ነው::

አላህ ሱወ  በተከበረ ቁርአኑ ላይ በሱረቱል ናዚዓት ላይ እንዲህ  ብሏል
በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ፤ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ (አን-ናዝዓት፡40-41)
   ╔══════════════════════╗
     95%በላይ ሴቶች ይህን የሀቢቡና               ሙሀመድﷺሀዲስ በተደጋጋሚ ሰምተዉታል    ╚═══════════════════════

ማንኛዉም ሽቶን ተቀብታ በሰዎች ፊት የምታልፍና ከማዕዛዋ የምታደርግ ሴት እርሷ ዛኒያ(ዝሙተኛ)ናት፡፡
ግን ሽቶ ሳይቀቡ አይንቀሳቀሱም..ሴቶች ሆይ ማወቅ ያለባችሁ ግዴታ ሽቶ ብቻ ሳይሆን የምትቀቡት ፌር ጥፍር ቀለም  ሊፒስቲክ ቻፕስቲክ ሽታ ስላለዉ ሽቶ ጋር እንደሚካተት ልታቁ ይገባል፡፡


ዝሙት ስንሰራ አላህ እንደሚያየን ልናቅ ልንገነዘብ ይገባል፡፡አሏህ ሱወ አንዲት ቅጠል የምወድቅበትን ቦታ የሚያቅ ጌታችን ዝሙት ስንሰራ ጀሊሉ ፊት ወንጀል እየሰራን እንደሆነ ልናስተነትን ይገባል፡፡


አላህ (ሱ.ወ) ወንጀልን ለሚሰሩ ባርያዎቹ እንዲህይላል፦

እነርሱ ያንን ቀን ሩቅ አድርገዉ ያያሉ፡እኛም ቅርብ ሆኖ እናየዋዉለን(አል መዐሪጅ 6-7)
ሰአቲቱ እነርሱ የማያዉቁ ሆነዉ በድንገት ልትመጣባቸዉ እንጅ ይጠባበቃሉን(አል ዙህሩፍ 66)


⚠️ አንዲት ሴት ከብረ ንፅህናዋን መጠበቅ እንዳለባት ካላወቀች ለነገ ህልም ከሌላት ድንግልና ለጥብቅ ሴቶች የትዳር ዋስትና መሆኑን ካላወቀች ሀያዕ ከሌላት ህይወቷ በዝሙት ምክንያት ምስቅልቅሉ ይወጣል፡፡ ክብረ ንፅህናዋን ለመጠበቅ ደግሞ ሐያእ (የእፍረት ስሜት) ወሳኝ ባህሪ ነው፡፡ ሴት ልጅ ከሐያእ ከተራቆተች ለክብረ ንፅህናዋ ተገቢውን ከለላ አላደረገችም ማለት ነው፡፡
☞ከኢኽቲላጥ ከተቃራኒ ፆታዎች ልቅ ቅልቅል ካራቀች ለዝሙት መንገድ ከፍታለች ማለት ነው፡፡
☞ዕይታዋን ዝቅ ካላደረገች ለዝሙት መንገድ ከፍታለች ማለት ነው፡፡
☞ምላሷን መቆጣጠር ካልቻለች አሁንም ለዝሙት መዳረሻ መንገድ ከፍታለች ማለት ነው፡፡
☞ከምንም በላይ ሴት ልጅ ጆሮዋን ከዘፈን ካልጠበቀች ለዝሙት የመጋለጥ ዕድሏ ሰፊ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ፆታዊ ፍቅር ወደሴቶች የሚገባው በዋናነት በጆሮ ሲሆን ወደ ወንዶች ደግሞ በዓይን ነው፡፡

ለወንዱም ቢሆን ዕይታውን መቆጣጠርና ዓይኖቹን ዝቅ ካላደረገ የዝሙት መዳረሻ መንገድን ተዳፈረ ማለት ነው፡፡
ጥብቅነቱን መጠበቅ እንዳለበት፣ አልያም አቅሙ ከቻለ ካልፆመ  ከተቃራኒ ጾታዎች ጋር ከተቀላቀለ የዝሙትን መዳረሻ መንገዶች ተዳፈረ ማለት ነው፡፡
ከሴት ጋር የርሷ መሕረም አጠገቧ በሌለበት ሁኔታ እሷ ጋር ከሆነ የዝሙት መንገድን ተዳፈረ ማለት ነው፡፡

በጥቅሉ ደግሞ ዝሙት ሐራምና መንገድነቱም የከፋ መሆኑን እያወቀ የሚያጠፋ፣ ትዳር የተቀደሰና የተባረከ ሕይወት መሆኑን፣ ከትዳር በፊት የወንድም ሆነ የሴት ጓደኛን መያዝ ሐራም መሆኑን የሚያዉቅ አዉቆ ጠፍ በዝሙት ላይ የመውደቅ ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ ስለዚህ የዚህ አዉቆ ጠፍ  ከዝሙት የመራቁ ጉዳይ ከባድ ነው፡፡

  ሰይዲና ሙሀመድ  ﷺ ዝሙትን ቀጥታ ከኢማን ጋር አያይዞታል፡፡ እንዲህም ሲሉ ተናግረዋል፡-

«ዝሙተኛው ዝሙትን በሚሠራበት ጊዜ እርሱ ሙእሚን ሆኖ አይደለም (የርሱ ኢማን ከርሱ ጋር የለም)፡፡» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል፡፡

ዝሙት በምንም መልኩ አሁን በርካታ ወጣቶች እንደሚያስቡት የመዝናኛ ዓይነት ሳይሆን ቀጥታ ከኢማን ጋር የተያያዘ ነገር መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን አለማወቅ በወንጀሉ ውስጥ ለመውደቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡

 ⚠️በኢትዮጵያ ሀገራችን የዝሙት ጉዳይ በጣጣም አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ደርሷል ፡ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥናቶች እንዳመለከቱት ከአዳጊዎች መካከል ከ21.5%-24.8% የሚሆኑት በወሲብ ንቁ ናቸው፡፡ እንዲሁም የመጀመሪያ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አማካይ ዕድሜ ከ15-16 ዓመት ነበር፡፡ ይህም ችግር ሥር የሰደደ ሲሆን የቅድመ ጋብቻ ወሲብ የማህበራዊ ጤና ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡ አዳጊዎች በለጋነት ዕድሜያቸው ወሲባዊ መነሳሳቶች ውስጥ በሚገቡበት ጊዜ ያልታሰቡ በርካታ ማህበራዊ ችግሮች ይከሰታሉ፡፡ ለምሳሌ
☞ በአዳጊነት ውስጥ የእናትነት ሕይወትን መምራት፣
☞ለነጠላ ወላጅነት መዳረግ፣
☞ ለአባላዘር በሽታዎች መጋለጥ ናቸው፡፡


ግን እንደዚህ ሁነን ወደየት ወደየት እያመራን ነዉ???

🙄እኛ ኢትዮጲያን የነጃሺ ሀገር በአለም ሁለተኛ ሙስሊም የተቀበልን የኢትዮ ግማሽ ፐርንሰንት በላይ ሙስሊም ነን ..ዲነኛ ነን ኪታብ ቀርተናል ..መስጊድ ተነካ..ኢስላም ተደፈረ ..ወዘተ በምላስ እንላለን በጎን ዚና እንሰራለን ዚናን መከላከል አልቻልንም

ክርስቲያኖች ኢትዮ የሙሴ ፅላት አለ ..አርባ አራት ታቦት አለ ..ኢትዮ ገማደ መስቀሉ አለ ይሄን ያህል ገዳም አለን.. ኢትዮ የኛ ናት የክርስቲያን ደሴት ናት ይባላል በጎን ዚና እንሰራለን🤔ዚናን መከላከል አልቻልንም፡፡
   ወዴት እያመራን ነው? ያልተፈታ የዘመናችን እንቆቅልሽ ...


 #ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ ሸርሙጣ፣ ሴተኛ አዳሪ፣ የቡና ቤት ሴት፣ ሸሌ፣ ባር ሌዲ፣ ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ ሂያጅ፣ አመንዝራ፣ ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ ወንድኛ አዳሪ፣ ወንድ ሸሌ፣ ሸርሙጣ፣ ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል
ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት አላህ ይወፍቀን

⚡️#በቀጣይ_ክፍል በዝሙት እንዴት ሴቶች ጉዳት እንደሚደርስባቸዉ እንዳስሳለን

#ምዕራፍ
ይቀጥላል......

አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለሌሎች ማከፈልዎን አይዘንጉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የነብዩ ﷺ የዘር ሀረጋቸዉ

ጁምአ ሶሉ አላሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ💚

join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
2024/09/27 23:20:23
Back to Top
HTML Embed Code: