Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ


            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
          
                 ⭐️ #ክፍል👉 ስድስት 6⃣



አንድ ታካሚ መዳኑን ሲያዉቁ ድግምት የሚያሰሩ ሰዎች ድግምቱን ለማሳደስ ወደ ደብተራ ጠንቋይ  ዘንድ ይሄዳሉ፡፡ ስለዚህ ታካሚዉ ስለመፈወሱ ለማንም መንገር የለበትም፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የሚከተሉት መከላከያዎች በድግምት እንዳይያዝና እንዳይታደስበት ይከላከሉለታል፡፡ ስለዚህ አጥብቆ ሊይዛቸዉ ይገባል፡፡ መከላከያዎቹ የሚከተሉት ናቸዉ፡፡

➊ ሶላት በጀመዓ መስገድ
➋ ሙዚቃን መዝሙርን አለመስማት
➌ ከመኝታ በፊት ዉዱዕ አድርጎ እና አያት አል ኩርሲይን ቀርቶ መተኛት
➍  ከማንኛዉም ነገር በፊት ቢስሚ አላህ  ብሎ መጀመር
➎ላኢላሀ ኢለ አላህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁ ሀምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር .... ከሱብህ ሶላት በኋላ እና ከዓስር ሶላት በኋላ 100 ጊዜ ማለት
>>> መቶ ግዜ ያለ አስር ባሮችን ነፃ እንዳወጣ ይቆጠርለታል፤ መቶ መልካም ሥራ ይመዘገብለታል፤ መቶ ሀጢያቶችን ይማራል፣ በዚያ ቀን እስከማምሻ ድረስ ከሰይጣናት መጠበቂያ ትሆነዋለች፡፡ ከመቶ በላይ ያለ ካልሆነ በቀር የሚበልጠዉ የለም፡፡

➏ በየቀኑ ቁርአን መቅራት፣ቁርአን ያልቀራ ከሆነ እቤቱ ቁርአን መክፈት በስልኩ ማዳመጥ
➐ዉሎዉን ሷሊህ (መልካም) ከሆኑ ሰዎች ጋር ማድረግ
➑ጠዋትና ማታ የሚባሉ ዚክሮችን ሳያቋርጥ ማለት
እነዚህ ድግምቱ እንዳይታደስና ለወደፊት ጥንካሬን ይሰጡናል

⚠️⚠️ ማወቅ የሚገባን ነገር አለ፡፡ ይኸዉም አንድ ደብተራ ወይም ጠንቋይ ድግምት ወደ ሚደረግበት ሰዉ ጂኒ (ሰይጣን) ይልካል። ጂኒዉ እንዲሁ ወደ ሰዎች ሰዉነት ዉስጥ መግባት ስለማይችል ለመግባት _ ምቹ ሁኔታ ይጠባበቃል። ጂኒ ወደ ሰዉ ሰዉነት ዉስጥ የሚገባዉ ከሚከተሉት ሁኔታዎች አንዱ ሲከሰት ነዉ፡፡
ከፍተኛ ፍርሃት
ከፍተኛ ንዴት (ቁጣ)
ከፍተኛ እንቅልፍ (እራስን አለማወቅ)
በስሜት (በሀጢያት) ዉስጥ መዘፈቅ


ከነዚህ ሁኔታዎች በአንዱ ተዘፍቆ ካገኘዉ ጂኒዉ ሊገባበት ይችላል። ነገር ግን ዉደዕ አድርጎ ከሆነ ወይም አላህን ካወሳ በምንም ዓይነት ሁኔታ ጂኒዉ ሊገባበት አይችልም፡፡

አንድ ሰዉ ጂኒ ሊገባበት ሲል አላህን ካስታወሰና  ካወሳ ጂኒዉ ይቃጠላል። በጂኒዎች ህይወት ዉስጥ አስቸጋሪዉ ህይወት በሰዉ ዉስጥ የሚገቡበት ጊዜ ነዉ፡፡



       🔰🔰🔰    #መስተፋቅር 🔰🔰🔰

   መስተፋቅር ማለት ባል ሚስቱን እንዲወዳት ወይም እሱ ሚስቱ እንድትወደዉ  ለማድረግ ሲባል የሚሰራ ድግምት ወይ ሌላ ነገር ነው

🟢 #በመስተፋቅር_ድግምት_በተለከፈ_ሰዉ_ላይ_የሚታዩ_ምልክቶች

➊ ከተለመደዉ ወጣ ያለ ፍቅር ይታይበታል
➋ ግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት ያድርበታል
➌ ሚስቱን ለማየት በጣም ይጣደፋል ይቻኮላል
➍ ሚስቱ ስታዘዉ በጭፍን ያለማገናዘብ ይታዘዛታል
➎ ያለ እርሷ ትዕግስት ማጣት
➏ ስለ እርሷ ይተናል

🟡  #መስተፋቅር_እንዴት_ይከሰታል?

በባልና ሚስት መካከል ብዙ ጊዜ አለመግባባቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ አለመግባባቶች ወዲያዉኑ ተወግደዉ ህይወት ወደ ነበረችበት ትመለሳለች፡፡ አንዳንድ ሴቶች በቀላል አለመግባባት ትዕግስት ስለማይኖራቸዉ መስተፋቅር ለማሰራት ሮጠዉ ጠንቋይ (ደብተራ) ቤት ይሄዳሉ፡፡ ይህም የሚሆነዉ እንግዲህ ከሴትየዋ የኢማን ማጣት ወይም እንዲህ ያለ ስራ የተከለከለ ሀራም መሆኑን ካለማወቅ የመነጨ ሊሆን ይችላል፡፡ ሴትየዋ ጠንቋይ ዘንድ መስተፋቅር  ለማሰራት ስትሄድ ጠንቋዩ የባሏን የላብ ፋና ማህረቡን፣ ኮፍያዉን፤ የልብሱን ቁራጭ እንድታመጣለት ያደርጋል፡፡ ከዚያም ከልብሶቹ ላይ ክሮችን በመምዘዝ እየደገመ ይቋጥራቸዋል፡፡ ከዚያም ሰዉ በማይደርስበት እንድትቀብረዉ ያዛታል፡፡

>>>> ወይም በሚበላ ወይም በሚጠጣ ነገር ላይ ድግምት ይሰራና እንድታበላዉ ወይም እንድታጠጣዉ ያደርጋል። ድግምቱ በነጃሳ ነገር ላይ የተሰራ ከሆነ በጣም አስከፊ ይሆናል፡፡ በወር አበባ ደም ከሆነ ደግሞ እጅግ በጣም አስከፊ ነው፡፡

☑️ መተትን ድግሞምት  ከትዉልድ ወደ ትዉልድ የሚወራረሱ ቤተሰቦች በተለያዩ አካባቢዎች ይገኛሉ፡ ስለሆነም ሁላችንም ብንሆን ለጋብቻ ስናጭ የልጅቷ ቤተሰቦች ምን እንደሆኑ በቅድሚያ ልንመረምር ይገባል፡፡

#ለምሳሌ፡- የልጅቷ እናት በየጠንቋዩ እና በየቃልቻዉ ቤት የምትንጦለጦል  ወይም በቤቷ ዉስጥም ቢሆን ለቃልቻ የምታደገድግ ከሆነ ከእንዲህ ያለ ቤተሰብ  ጋር በጋብቻ ልትተሳሰር አይገባም፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ሰዎች ባሎቻቸዉን የመተት የድግምት መሞከሪያ እንደሚያደርጉዋቸዉ እና ለሰይጣን እንደሚገብሯቸዉ ይታወቃል።

🔴 #የመስተፋቅር_ተቃራኒ_ዉጤት

➊ በመስተፋቅር ድግምት ሳቢያ ባል ሊታመም ይችላል፡፡ በዚህ የተነሳ ለብዙ አመታት ባሎች ህመሙ ሳይታወቅ ይታመማል

➋ የመስተፋቅር ድግምት ይቀለበስና ባል ሚስቱን እንዲጠላት ሊያደርግ ይችላል። ይህም የሚሆነዉ በርካታ ጠንቋዮች ስለ ድግምት አሰራር በቂ እዉቀት ስለማይኖራቸዉ ነዉ፡፡
➌ አንድ ሴት ባሏ ሴቶችን በሙሉ ጠልቶ እርሷን ብቻ እንዲወዳት ለማድረግ ሁለት ዓይነት ድግምት ልታሰራ ትችላለች እነርሱም
#አንደኛ፦ ድግምት ከርሷ በቀር ያሉ ሴቶችን እንዲጠላ የሚያደርግ ሲሆን
#ሁለተኛዉ፡ ደግሞ እርሷን ብቻ እንዲወድ የሚያደርግ ይህም ባል እህቶቹን፣ እናቱን፣ አክስቶቹን ባጠቃላይ ሴት ዘመዶቹን በሙሉ እንዲጠላ ያደርገዋል፡፡

➍ እንዲህ ዓይነቱ ሁለት ዓይነት ድግምት ይቀለበስና ባል ሴቶችን በሙሉ ሚስቱን ጨምሮ እንዲጠላ ያደርገዋል፡፡ አንድ ሚስት የዚህ ዓይነት ድግምት ባሏ ላይ ታሰራበታለች፡፡ በዚህ የተነሳ ባል ሚስቱን ይጠላትና ይፈታታል፡፡ ሚስት ድግምቱን ለማስፈታት ወደ አሰራችበት ጠንቋይ ዘንድ ስትሄድ ሞቶ አገኘችዉ፡፡

      #የመስተፋቅር_መንስኤዎች

➡️ የባልና የሚስት አለመግባባት
➡️ ሚስት ለባሏ ገንዘብ መቋመጥ በተለይ ሃብታም ከሆነ
➡️ ባለቤቷ ሌላ ሁለተኛ ሚስት ሊያገባ ይችላል ብላ መጠርጠር። ሆኖም ከአንድ በላይ እስከ አራት ሚስት ድረስ ማግባት የተፈቀደ ነዉ፡፡ ነገር ግን የዘመናችን ሴቶች በተለይ ተልዕኳቸዉን ጥፋት ላይ ባደረጉ ሚዲያዎች ተፅዕኖ ያረፈባቸዉ ባል  ሁለተኛ ሚስት ለማግባት መፈለጉን የጥላቻ ምልክት አድርገዉ ይወስዱታል፡፡ ይህ ደግሞ ከባድ ስህተት ነዉ፡፡ ምክንያቱም ባል ሚስቴን እየወደዳት ሌላ ተጨማሪ ሚስት እንዲያገባ የሚያደርጉት በርካታ አሳማኝ ምክንያቶች ስለሚኖሩ ነዉ። ከነዚህም ጥቂቶቹ በርካታ
☞ልጆች መፈለግ፤
☞ ሚስት የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም በምታይበት ጊዜ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት ሊያድርበት ይችላል፡፡
☞ ከተለየ ቤተሰብ ጋር በጋብቻ አማካኝነት ትስስር ለመመስረት ሊፈልግ ይችላል እና ሌሎችም ምክንያቶች ይኖራሉ።

ብዙ ሴቶች ሁለተኛ ሚስት የሚለዉን ይጠሉታል...ወንድም ሁለተኛ ሚስት የምትለዉን ኪታብ የቀራዉም ያልቀራዉ ጃሂሉም አሊሙም ከምላሱ የማትጠፋ ነች👇👇
ለሴቶች ጆሮ ሸክም ቃል ቢኖር ሁለተኛ ሚስት ላግባ የምትለዉ ንግግር መችም አትዋጣላቸዉ...ሁለተኛ ያገቡ ወንዶች ብዙዎች ደስታ አጥተዋል ወይ የመጀመሪያ ወይ ሁለተኛዋ ሲህር እያስደረጉባቸዉ
ከአንዷ ጋር ይጣላሉ ቤተሰብ ሲበተን እየተስተዋለ ነዉ፡፡ የሚገርመዉ አንዷ ጋር ሲሆኑ ጤነኛ የሆኑት ሌላ ሚስት ጋር ለመገናኘት አይችሉም ስንፈተ ወሲብ ይገጥማቸዋል፡፡ ብቻ ሁለተኛ ሚስት የሚያገባ አላህ ካዘነለት ከጠበቀዉ በቀር ከባድ ነዉ ፈተናዉ ሙሲባዉ ብዙ ነዉ፡፡

  🌐 #መስተፋቅር_በተደረገባት_ሴት_የሚታዩ_ምልክቶች

✏️ ሴቷ ወይም ወንዱ ስለ አንድ ሰው በአንድ ወቅት ስላዩት ይሁን ስለሰሙት ሰው ከምንግዜውም በላይ ማሰብ ማሰላሰል ይጀምራሉ፡፡ ያን ሰው ከዚህ በፊት ሊቀርቡት ይገባል፡፡ ቀርበውትም ከእህትነት ወይም ከወንድምነት የዘለለ ፍላጎት የሌላቸው ሲሆን ይህ ሲህር ከተሰራባቸው ጀምሮ ግን ስለዚያ ሰው ህልም ማየት ማሰብ ፡፡

✏️ ያን ሰው አብዝቶ መናፈቅ ለደቂቃ ከነርሱ ጋር መሆን ከምንም በላይ ለነርሱ ልዩ ስሜትን ይፈጥራል፡፡ ከነርሱ ሲለያዩ እጅግ በጣም መፍራት ይፈጠርባቸዋል፡፡

✏️ ከርሱ ወይም ከርሷ ሲጣሉ እራስን ወደማጥፋት ማምራት ፡፡ ያለ ምንም ጥያቄና ቅድመ ሁኔታ እራስን ወደማጥፋት ሲሄዱ የገዛ ማንነቶ ህሊናዎ እንኳን ሊከላከሎት አይችልም፡፡ ይህን ሲያደርጉ ሰው እንዲያዮት ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ሲህር ለየት የሚለው በድብቅ እራስን ማጥፋት የሚያስፈፅም ሳይሆን በምስክር ፊት እራሶን ሊያጠፉ ይቃጣሉ፡፡

✏️ ድንገት ከመሬት ተነስተው ባልሆነና ባልታሰበ ሁኔታ ስለወደዱት ሰው መጥፎነትና አይረቤነት ቢነገራቸው እንኳን አለመስማት፡፡ ብሎም ይህ ከምቀኝነት የመነጨ ወሬ መሆኑን አምኖ ሰውን በሙሉ ለወደዱት ሰው ሲሉ መራቅና መጣላት፡፡

✏️ ያን ሰው እስከማምለክ መሞከር ፡፡ በዚያ ሰው ይምላሉ በዚያ ሰውም እድለኛ ይሆናሉ፡፡ ያ ሲህር ያደረገባቸው ሰው ላይ ሰው የማያየውን ልዩ እና አስደሳች ፀባዮችን እነርሱ ብቻ ይታያቸዋል፡፡ 

✏️ ልብ ሊባል የሚገባዉ ነጀር ሲህሩን ያደረገው ሰው ለአፍቃሪው የተለየ ስሜት የለውም ፡፡ በአፍቃሪው ላይ መጥፎ ነገሮችን ሲሰራ ነው የሚታየው አፍቃሪውን ሲያሰቃይ ነው የሚታየው፡፡ ይህ ግን ለአፍቃሪው አይታወቀውም፡፡

✏️  አልፎ አልፎ ጥዋትም ይሁን ከሰአት እንቅልፍ ተኝተው ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ወደ ማንነት መመለስና በሰሩት ስራ በሙሉ መፀፀት እራስን በጣም መጥላት፡፡ እነኚህ ሰዎች በዚህ ወቅት ከሰው ደብቀው የሚያስቀምጡት ዲያሪ ነክ ነገሮች ሊኖሩዋቸው ይችላል፡፡ ፍፁምም ከሰው የተደበቁ ደብተሮች ብዙ ምስጢር የያዙ ነገሮችን ይይዛሉ፡፡ ይህን ግን ለማንም ቢሆን አያሳዩም፡፡ ሞትንም ይመርጣሉ፡፡ ይሁንና ወደ ቀድሞው ማንነት በሚገቡበት በዚያች ቅፅበት ቡና በሚጠጡበትና በቃ ሲገፋፋቸዉ ወ ያን ምስጢር የማሳየት ግፊታቸው ሀይለኛ ነው፡፡

✏️ ጥርሷን በጣም ታፋጫለች ይህም በተኛችበት ጥርስ ጥርሶቿን መብላት ትጀምራለች፡፡

✏️ ከኢማን  ከሰላት ከቂርአት ትሸሻለች፡፡ ይህ ሰው ቢርቃት እንኳ ካላገባሁት ሙቼ እገኛለሁ ትላለች፡፡ 

✏️ ይህ ሲህር ሲጀምር ሰውየውን መፍራት የምትጀምር ሲሆን ያም ፍራቻ ወደ ወሲባዊ ፍቅር ተለዋጭ ነው፡፡

✏️ ጅኖችም በዚህች ሴት አናት ላይ ያረፉ ሲሆኑ ይህች ሴት አብዛኛውን ግዜ የራስ ህመም(ማይግሬን) አለባት በመድሀኒት የማይፈታ፡፡

✏️ ብቻን ማልቀስ ብቸኝነት መሰማት ከሰዎች መሀል ውስጥ ሁና ብቸኝነት ይሰማታል፡፡ ይህም ስለርሱ ላታስብ ትችላለች ግና ብቸኝነቱ ከባድ ነው፡፡ 

🔰🔰  ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች የተወሰነም ቢሆን ምልክቱ ከአንቺ ጋር ካለ
👉 በመጀመርያ ዳእዋዎችን ማዳመጥ ስለ ቀብር ስለ አላህ ውዴታ የሚያስተምሩ ዳእዋዎችን መከታተል፡፡
👉 በቀጣይም አያተል ኩርሲን መቅራት ያም ልጁን ስታስብ መቅራቱ ይረዳታል፡፡
👉 በመቀጠልም ውዱእን መጠበቅ ከውዱእ ውጭ አለመሆንና
👉 የሰሃቦችን ታሪኮች ማንበብ
👉 ስሜት ቀስቃሽ ከሆኑ ነገሮች በሙሉ ልትርቅ ይገባታል፡፡

⚠️⚠️ እንዲህ አይነት ነገር እንዳይገጥማችሁም ምሽት ላይ በአዳበ ነውም መሰረት እንቅልፍን መተኛት ጥዋትም በሚነሱበት ወቅት አያተል ኩርሲን ማንበብ ተገቢ ነው፡፡

      🟢 #የመስተፋቅር_ህክምና

➊ የአል ሩቅያ አንቀጾችን በታካሚዉ ላይ ትቀራለህ፡፡ ከአል ሩቅያ አንቀጾች ዉስጥ የአል በቀራ ምዕራፍ አንቀጽ 102 ን በመተዉ በምትኩ ከአል ተጋቡን ምዕራፍ አንቀጽ 14፣ 15 እና 16 መቅራት

በመስተፋቅር ድግምት የተለከፈ ሰዉ ሲቀራበት አብዛኛዉን ጊዜ እራሱን አይስትም፡፡ ሆኖም በእጆቹና በእግሮቹ አካባቢ የመደንዘዝ ስሜት ይሰማዋል።
>> እራስ ምታት፣
>> ደረት አካባቢ የማፈን
>> ከፍተኛ የ የሆድ ህመም ይሰማዋል (በተለይ ሆዱን የሚያመዉ ድግምቱን በልቶት ወይም ጠጥቶት ከሆነ ነዉ)፡፡ ምን አልባትም : ሊያስመልሰዉ ሁሉ ይችላል፡፡ በተለይ የሆድ  ህመም የሚሰማዉ  ወይም ለማስመለስ የሚቃጣዉ ከሆነ
☞ ሱረቱ ዩኑስ 81-82
☞ ሱረቱ ዩኑስ81
☞ ሱረቱል ጦሀ 69
☞ ሱረቱል በቀራ 255
☞  የቁርአን አንቀጾች
በዉሃ ላይ ትቀራና ፊት ለፊትህ እንዲጠጣዉ አድርግ፡፡

ታካሚዉ እነዚህ የቁርአን አንቀፆች የተቀሩበትን ዉሃ ሲጠጣ ቢጫ ወይም ቀይ ወይም ጥቁር ነገር ካስመለሰዉ ድግምቱ ፈሰደ (ተፈታ) ማለት ነዉና ምስጋና ለአላህ አድርስ፡፡


ይህ ነገር ካልተከሰተ ደግሞ እነዚህ አንቀች የተቀሩበትን ዉሀ ለሶስት ተከታታይ ሳምንታት ወይም እንደ አስፈላጊነቱ ከዚያ በላይ ድግምቱ እስኪፈታ ድረስ ይጠጣ፡፡ ይህን ሲያደርግ ሚስቱ ማወቅ የለባትም፡፡ ምክንያቱም ህክምና እየተከታተለ መሆኑን ካወቀች ዳግመኛ ልታሳድስበት ትችላለችና፡፡

ሴትም ከሆነች የተደረገባት ባልየዉ ማወቅ  የለበትም መልሶ ሂዶ ሊያሳድስ ይችላልና...ከትዳር በፊት ከሆነ የተደረገዉ ዝምታ ነዉ የሚሻለዉ ከሰማ ወይ ከሰማች መልሶ ማሳደሱ በጣም ቀላል ስለሆነ ....

#ክፍል 7⃣
ይቀጥላል.....



አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot


ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
Audio
የ____ስጦታ❤️🌟🌻🌻⭐️⭐️

#ቢስሚከ_ነህያ_አል_ሙጁብ📚

🌙🌙🌙🌙🌙🌙⚡️⚡️⚡️🌟🌟🌟☀️

አልሙጁብ ማለት ምን ማለት ነው?
💥💥💥💥💥💥💥💥

#ሬድዋን🎤🎤

https://www.tg-me.com/+-zHkXQeSZdc4MjY0
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ


            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
          
                 ⭐️ #ክፍል👉 ሰባት 7⃣


  🔰🔰 #ሳይታይ_የሚጮኽ_ድግምት(ሲህር)

#ሳይታይ የሚጮህ ድገምት አንዲት ይከሰታል?

     ደጋሚው ድግምት ወደ ተደረገበት ሰዉ ጂኒ ይልካል። ይህን ስጡ በህልሙም በዉኑም እንዲያዋክበዉ ጂኒዉን ያዘዋል፡፡ ጂኒዉም በህልሙ የሚያጠቃዉ አስፈሪ አዉሬ በመምሰል፣ በዉኑም በስሙ እየጠራዉ እንዲያዉም ሰዉዬዉ በሚያዉቃቸዉ እና በማያዉቃቸዉ ሰዎች ድምፆች እየተጣራ ግራ ያጋበዋል፡፡ ዘመዱንም ባእዱንም እንዲጠራጠር ያደርገዋል፡፡

#ምልክቶቹም እንደ ድግምቱ ክብደትና ቅለት ይለያያሉ፡፡ አንዳንዴም የህመሙ ምልክቶች አይለዉ ወደ እብደት ሊያደርሱ ሲችሉ ሌላ ግዜም አንሰዉ ከዉስወሳ ላይዘሉ ይችላሉ፡፡

🟢 #የዚህ_ድግምት_ምልክቶች

☞ አስፈሪ ቀዠቶችን ማየት
☞ የሆነ ነገር ሲጠራዉ በህልሙ ያያል
☞ በዉኑ (በቀን) የሚያናግረዉ ድምፅ ይሰማል ሰዉ ግን አያይም
☞  በብዛት መወሳወስ ይበዛበታል
☞ ዘመዶቹንና ጓደኞቹን በትንሽ በትልቁ ይጠራጠራል
☞ እንስሳት ሲያሳድዱት በህልሙ ያያል
☞ ከከፍተኛ ቦታ ላይ ሲወድቅ በህልሙ ያያል

    🟡 #ሳይታይ_የሚጮኽ_ድግምት_ህክምና

1) የአል ሩቅያ አንቀጾችን በታማሚዉ ላይ ትቀራለህ፡፡
2) እራሱን ሲስት ከዚህ ቀደም እንዳየነዉ ታደርጋለህ፡፡
3) እራሱን ካልሳተ ታካሚዉ የሚከተሉትን ያደርጋል፡፡
➢ ዉዱእ አድርጎ እና ኢያት አል ኩርሲይ ቀርቶ መተኛት
➢ ከመኝታ በፊት ሁለት መዳፎቹን ዘርግቶ አል ኢኽላስ፤ አል ፈለቅ እና አሳ ናስን መቅራትና መዳፎቹ ላይ እንትፍ እንትፍ በማለት መላ አካላቱን መዳበስ፡፡ ይህንንም ሶስት ግዜ መደጋገም።
➢ የአል ሳፋት ምዕራፍን ጠዋት ላይ፣ የአል ዱኻን ምዕራፍን በመኝታ ጊዜ መቅራት ወይም መቅራት ካልተቻለ በስልክ ማዳመጥ
➢ በየሶስት ቀኑ የአል በቀራ ምዕራፍን መቅራት ወይም ማዳመጥ
> ጠዋት እና ማታ የሚከተለዉን ዚክር ሰባት ጊዜ ማለት ‎ احَسْيَ اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَهُوَ رَبُّ الْعَرْشِ العَظِيمِ، ‎
ሀስቢየ ላሁ፡ ላኢላሃ ኢላ ሁወ ዓለይሂ ተወከልቱ፣ ወሁወ ረቡል አርሺያል አዚም

➢ ከመኝታ በፊት የአል በቀራ ምዕራፍ የመጨረሻዉን ሁለት አንቀጾች መቅራት
የሚከተሉት የቁርአን አንቀጾች በስልክ በቀን ሶስት .. ያዳምጣል፡፡ እነሱም፡- ፉሲለት፤ አል ፈትህ አል ጂን
➢ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን በሙሉ ለአንድ : ወር : በተከታታይ መፈጸም፡፡ ፈዉስ በአላህ ፈቃድ ይመጣል።




  🟢 #ሲህር_አል_ሃዋቲፍ (የመጥፎ ህልሞችና ለሰው የማይሰሙ የጥሪ ድምፆች ሲህር)
ዶክተር አቡ ፈርሀን መጣጥፍ ላይ የተወሰደ

#ምልክቶቹ

➊ በሚተኙበት ወቅት ሁሌም ቅዠት መኖር ፡፡ በጣም የሚያስፈሩ የሚያስጠሉና የተቆራረጡ ህልሞችን ማየት፡፡

➋ ታማሚው በሚተኛበት ወቅት በህልሙ ሰው ስሙን ሲጠራው ይሰማል፡፡

➌ ታማሚው ሹክሹክታዎችን (ውስዋሶችን) ያዳምጣል፡፡

➍ ታማሚው ቤተሰቡብን ጓደኞቹን ልጆቹን ሳይቀር መጠራጠር ይጀምራል፡፡

➎ ታማሚው ከእንቅልፉ እየነቃ ሳለ ለሌላ የማይሰማ ነገር ግን ለርሱ የሚሰማ ድምፅ ይኖራል፡፡

➏ ታማሚው በእንቅልፍ ውስጥ ከከፍተኛ ቦታ ሲወድቁ ማየት እና መባነን፡፡

➐ በህልሙ ታማሚው በእንስሳት እየተሳደደ የሚበላ ነገር እያሯሯጠው ይነቃል፡፡
ለዚህም ህክምና 
🔻 ሲተኙ በሱና መተኛት
🔻 ከእንቅልፎ ሲባንኑ ዱአ አድርገው መተኛት
🔻 አያተል ኩርሲ መቅራት በተደጋጋሚ መቅራት ነዉ


   🟡 #በስራ_ቦታ_ላይ_የሚሰራ_ሲህር
ከዶክተር አቡ ፈርሀን መጣጥፍ ላይ የተወሰደ፡፡


……እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ፡፡ ሷሂሮችኮ አይተኙላችሁም፡፡ ከቤታችሁ አልፎም ስራ ቦታችሁን አጥንተው በዚያ በምትሰሩበት ሲህር ቢደቁሳችሁ እንኳ በምታገግሙበት ስራ ቦታችሁ የሀላልን ገንዘብ የምታመጡበት ቦታ ድረስ አንዴ ታካሚ አንዴ ባለጉዳይ አንዴ ገዢ ሆነው መጥተው ሲህር ጥለውባችሁ ይሄዳሉ፡፡ አሏህም ከእንዲህ አይነቶቹ ጀነት ሀራም ከተደረገባቸው ወራዶች ይጠብቃችሁ፡፡ አጅርን በስቃይ የሚሸምት ሰው ማለት ሲህር ተሰርቶበት ሰብር ያደረገ በሰው ነው……

  #ምልክቶቹ
🔶 የስራ ቦታ ገበያ መቀዝቀዝ፡
🔷 አንተጋ ወይም አንቺ ጋ ኳሊቲ የሆነ እቃ  ማግኘት እየቻለ ያ ሰው ግን ያንቺን ወይም ያንተን እቃ አይገዛም፡፡ ይልቁንም ያን እቃ ትቶ የማይረቡ እቃዎችን ይገዛል፡፡

🔶 ብዙውን ግዜ በነጋዴዎች ላይ የሚታየው እቃ ይበዳደራሉ፡፡ ሌሎች ካንተ ወይም ካንቺ የሚበደሩት እቃ ተፈልጎ ሲሸጥላቸው አልያም አንተ ጋር ተመሳሳይ እቃ 50 ብር እየተሸጠ ሊያውም ፈላጊ ሳይኖረው ቀርቶ ልክ ሌላው እጅ ላይ ግን ሲገባ እስከ አምስት መቶ ብር ድረስ ሲሸጥ እውነትም እኔ ላይ ሲህር አለ ያስብላል፡፡

🔷 ከውጭ ተፈላጊ እቃ ጭነው አምጥተው ባልሆነ ምክንያት ያ እቃ እነሱ እጅ ውስጥ መግባት አይችልም፡፡ ያም ሲባል እቃው ላይ ችግር ሳይኖር አመጣጡ ስርአቱን ጠብቆ መጥቶ በፍፁም ሲህር የተሰራበት እጅ ውስጥ ከመግባት ይርቃል፡፡ ቆይቶም ከከሰረ እቃው ከተባለሸ ኋላ ይወጣል፡፡ ይህ ሲደጋገም ለነጋዴው ይታወቃል፡፡

🔶 የድርጅት ባለቤት ሆነው ሳለ ድርጅቶ ትርፋማ ሆኖ እየተንቀሳቀሰ አንድ የወጪ ቀዳዳዎች እጅግ ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ ድርጅቱ እራሱን በራሱ የሚበላ ይሆናል፡፡ ወደ ቤትዎ ይዘውት የሚሄዱት ትርፍ የለም፡፡ 

🔷 የቢሮ ሰራተኛ ከሆኑ፡፡ ወደ መስርያ ቤት መሄድ ሞት መስሎ ነው የሚታየው፡፡ ይህም ተጫዋች ሁነው አካባቢው እጅግ የሚወዱት እንደነበረ ቢገነዘቡም ወደ ቦታው መሄድ ሰላም አይሰጦትም፡፡ ይህ ነጋዴውም ተቀጣሪውም የድርጅት ባለቤቱም ላይ የሚታይ ነው፡፡ 

🔶 ከአለቃ ጋር ባልሆነ በሆነው መጣላት፡፡ ስራዎትን በአግባቡ ሰርተው ሳለ ሌላው ባልሰራው እንኳ ሲመሰገን እርሶ ግን ማንም መስራት የማይችለውን ሰርተው ምስጋና ቢስ ተወቃሽ ኖት፡፡

🔷 ስለ ስራ ሲያስቡ ፍርሃት ጭንቀት መረበሽ ይህ ዋነኛ ምልቱ ሲሆን ሲህሩ መጀመሩን መጠንከሩንም በዚሁ ማወቅ ይቻላል፡፡ 

🔶 የሚፈልጉት እረፍት ብቻ ነው፡፡ ንግዱ አትራፊ ሁኖ ደሞዝዎ ጥሩ ሁኖ እርሶ ግን እረፍት ብቻ ይፈልጋሉ፡፡ ስራዎትን ዞር ብለው ባያዩት ይመርጣሉ፡፡ ይበልጡኑ መታመም ይጀምራሉ፡፡ በዚህም ሰአት ከገጠሙን ውስጥ ያለ አቅም የሚወፍሩና ከስተው ከስተው በአጥንት ብቻ የሚቀሩትንም ታዝበናል፡፡

🔷 ካሁን ካሁን ከስራዬ ተባረርኩ ፡፡ ካሁን ካሁን ከሰርኩ ፡፡ ካሁን ካሁን እንዲህ እንዲያ ሆንኩ በሚል ፍርሃት ብቻ ከአላህም እንዲርቁ ያደርጎታል፡፡ ሰላቶ ላይ እስከዚም ይሆናሉ፡፡ ኢባዳዎ ላይ ያዘናጋዎታል👇👇👇
⚠️⚠️ በዚህ ዙርያ ሷሂሮትን የሚለዩባቸው አጋጣሚዎች እነሆ፡፡ ይህን ሲህር የሰራቦትን ሰው ሲያዩ፡፡
♦️ ልቦ መፍራት መምታት ይጀምራል፡፡
♦️ ጭንቀት ይወሮታል፡፡ አጠገቡ መቀመጥን አይቻሎትም፡፡
♦️ ያ ሰው የፈለገውን ነገር አድርገው መገላገል ምኞቶ ነው፡፡ በተቃራኒ ግን ያ ሰው እጅግ እርጋታ የተሞላበት ሁኖ ያገኙታል፡፡ ምክያቱም ለግዜው አሸናፊ የሆነ ስለሚመስለው ነው፡፡ አሏህም ካርታውን ያጠፋበታል፡፡ አንዴ ሩቅያህ ከጀመሩ ኋላ፡፡
♦️ ከሱ ጋር ላለመገናኘት የማያደርጉት ጥረት አይኖርም ሰውየው ግን ሁሌም እርሶ ባሉበት ስፍራ አይጠፋም፡፡ ይህም ከብዙዎቹ በጥቂቶቹ ላይ የሚታይ ነው፡፡ 
======   =====   ====   ===== ===== =====

 🟢 #ከተለመደዉ_የወር_አበባ_ቀናት_ዉጪ ደም እንዲፈስ የሚያደርግ ድግምት አንዴት ይከሰታል?

>>> ይህ ዓይነት ድግምት በሴቶች ላይ ብቻ የሚከሰት ነዉ፡፡ አንድ ጠንቋይ ድግምት ወደ ሚደረግባት ሴት ደም እንዲፈሳት እንዲያደርጋት ጂኒ ይልካል፡፡ ጂኒዉም በሴትየዋ ዉስጥ በመግባት በደም ስሮቿ ዉስጥ ይዘዋወራል።

.... ይህን በማስመልከት ነብዩ እንዲህ ይላሉ ሰይጣን በሰዉ ሰዉነት ዉስጥ ደም እንደሚዘዋወረዉ ይዘዋወራል” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል) ጂኒዉ ወደ ሴቷ ማህፀን የደም ጋን በመድረስ ይረግጠዋል በዚህም ደም ይፈሳታል፡፡

  ከተለመዱ የወር አበባ ቀናት ዉጪ ስለሚፈስ ደም ተጠይቀዉ ነብዩ እንዲህ አሉ
>>> “ይህ ዓይነት ደም የሰይጣን እርግጫ ዉጤት ነዉ” (ቲርሚዚ ዘግበዉታል ሃስኑን ሶሂህ ነዉ ብለዉታል)

በሌላ ዘገባም ይህንኑ አስመልክተዉ ነብዩ እንዲህ ይላሉ "የሰይጣን እርግጫ ዉጤት ነዉ፣ የወር አበባ ደም አይደለም፡፡" አህመድና ነሳኢ ቢሰነዲን ጀይድ" ዘግበዉታል)

ከነዚህ ሁለት ዘገባዎች የምንገነዘበዉ ከተለመደዉ የወር አበባ ቀናት ዉጪ የሚፈስ ደም በሰይጣን እርግጫ ሳቢያ ከማህፀን የደም ጋን የሚፈስ መሆኑን ነዉ፡፡

               #ህክምናዉ

የእል ሩቅያ አንቀፆችን በዉሀ ላይ ትቀራና ታማሚዋ ትጠጣለች ለሶስት ተከታታይ ቀናትም ሰዉነቷን ትታጠብበት፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ደሙ ይቆማል፡፡


🟡 #ሰዉ_እንዳያገባ_ለማድረግ_የሚደረግ_ድግምት

አንድን ሰው ከትዳር ለማራቅ ሚደረጉ ሲህሮች እጅግ አስነዋሪዎች ናቸው፡፡ ከእነዛ ምልክቶች ዉስጥ
☑️ የውስጥ አለመረጋጋት እጅግ በጣም ለነገራቶች መጨነቅ
☑️ ቀን ላይ ትዳር ፈልጎ የመጣው ሰው ውሳኔ አጥቶ ወድያው መመለስ! አለመፈለግ፡፡ መጀመርያ ፍላጎት ኑሮ ከዛንም ፍላጎት ማጣት፡፡
☑️ ልብ በየቀኑ ‹‹ቀኔ እያለፈ ነው ሲል መጨነቅ፡፡›› ይህ ሁሉም ሰው ይጨነቃል ግን ደግሞ ያንቺ ይብሳል ልብሽ እስኪፈነዳ ድረስ መጨነቅ፡፡
☑️ ብሩህ የወደፊት ተስፋን ‹‹ትዳርን›› ፈላጊ መሆን ግን ደግሞ ትዳር ሲመጣ እጅግ መጥላት!!
☑️ ዶሮ ከመጮሁዋ እና ከመንጋቱ ፊት በተለይ ሱብሂ ሰላት አካባቢ በህልም ከጥቁር መልኩን ከማታውቂው ሰውነቱ ፈርጣማ ከሆነ ሰው ጋር ወሲብ ማድረግ፡፡
☑️ ክንውንን ወይም በውስጠ ህሊና ሀራም ማሰብ ወይም ማስተርቤሽን ማብዛት፡፡ ሃታ ሰላት ላይ ሳይቀር ማስተርቤሽንን ማሰብ! የመሳሰሉት ናቸዉ

📌📌 ምቀኛና ተንኮለኛ የሆነ ሰዉ ጠንቋይ ዘንድ በመሄድ እገሊት የእገሌ ልጅ እንዳታገባ የሆነ ነገር አድርግ ይለዋል፡፡ ጠንቋዩም የልጅቷንና የእናቷን ስም ይጠይቀዋል፡፡ የላቧ ጠረን ያለበትን ልብስ፤ ፀጉር... እንዲያመጣለት ያደርግና ድግምት መስራት ይጀምራል፡፡ ለዚህ ድግምት አንድና ከአንድ በላይ ጂኒዎችን ይወክላል፡፡ ከዚያም ጂኒዉ ወደ ልጅቷ በመሄድ ለመግባት እድል እስከሚያገኝ ድረስ ይከታተላታል፡፡ ከሚከተሉት አራት ምክንያቶች አንዱ ሲከሰት ጂኒ ወደ ስዉ ልጅ ስነት ሊጋባ ይችላል።
➊ ከፍተኛ ፍርሃት ሲኖር
➋ ከፍተኛ ንዴት (ቁጣ) ሲክስት
➌ ከፍተኛ እንቅልፍ ወይም እራስን አለማወቅ በሚኖርበት ወቅት
➍ በማንኛዉም በትንሽም በትልቅ በሀራም ስራዎች ዉስጥ መዘፈቅ

በዚህ ጊዜ ጂኒዉ ሁለት አማራጮች ይኖሩታል፡፡

1⃣ ልጅቷ ዉስጥ በመግባት ለማጨት የሚመጣ ወንድ ስታይ እንድትጨነቅ እና እንድትተወዉ ማድረግ፡፡ ወይም
2⃣ ልጅቷ ዉስጥ ለመግባት ሳይችል ከቀረ ከልጅቷ ዉጪ በመሆን የማስመሰል አስማት መስራት ይጀምራል፡፡ በዚህም ልጅቷን ለማጨት የሚመጣን ሰዉ መልከ ጥፉ መስላ እንድትታየዉ  በማድረግ  ይወሰዉሰዋል፡፡ ልጅቷንም እንደዚሁ ይወሰዉሳታል፡፡

በዚህም የተነሳ ሊያጫት የሚመጣ ሁሉ ሲተዋት ይስተዋላል፡፡ በመጀመሪያዉ ቀን ሊያገባት የተስማማ ከቀናት በኋላ ሲያፈገፍግ ታየዋለህ፡፡ ይህ እንግዲህ የሚሆነዉ በሰይጣን ውስወሳ ሳቢያ ነዉ፡፡

🌟 የተሰራዉ ድግምት ጠንካራ በሚሆንባቸዉ ሁኔታዎች ልጅቷን ለማጨት የሚመጣዉ ስዉ ገና ወደ ቤት ሲገባ ከፍተኛ ጭንቀት ይሰማዋል። ልክ እስር ቤት እንዳለ ሰዉ ህይወት ትጨልምበታለች፡፡ በዚያዉ ሳይመለስ ይቀራል፤ የዚህ ዓይነት ድግምት በሚቆይባቸዉ ጊዜያት በልጅቷ ላይ ብቅ እልም የሚል እራስ ምታት ወይም ማይግሬን የሚባለዉ የራስ ህመም
(ግማሽ ራስን ከፍሎ የሚያም) ይስተዋላል።


🌟 #ሰዉ_እንዳያገባ_ለማድረግ_የሚደረግ_ድግምት_ሲህር_ምልክቶች

⚡️ መድሃኒት በመዉሰድ የማይሻል ሄድ መጣ የሚል የራስ ምታት
⚡️ከባድ የራስ ምታት (ማይግሬን)
⚡️ደረት ዉስጥ ጭንቅ የሚል ስሜት በተለይም ከአስር ሰዓት በኋላ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ
⚡️ለማጨት የሚፈልገዉን ሰዉ መልከ ጥፉ አድርጎ መመልከት
⚡️በብዛት በሀሳብ መወጠር (የሀሳብ መብዛት)
⚡️ በመኝታ ወቅት ፍርሃት ፍርሃት ማለት
⚡️ ይህ ዓይነት ድግምት በተደረገባቸዉ አንዳንድ ሰዎች ላይ የሆድ ህመም ይከሰታል
⚡️ የጀርባ የታችኛዉ ክፍል ህመም (የጀርባ ላይ ህመም መሰማት

📌📌  #ሰዉ_አንዳያገባ_ የተደረገበት_ ድግምት_ህክምና

✏️የሩቅያ አንቀፆችን ተቀራባታለህ እራሷን ከሳተች ከዚህ ቀደም በተማርነዉ መንገድ ጂኒዉን ታነጋግረዋለህ፡፡
✏️ እራሷን ሳትስት ነገር ግን በአካሏ ላይ የተለየ ስሜት የሚሰማት ከሆነ የሚከተለዉን እንድትከታተል ታደርጋለህ

➢ ሂጃብ መልበስ
➢ ሶላትን በወቅቱ ሳያቋርጡ መስገድ
ሙዚቃም ሆነ መዝሙር ከመስማት መታቀብ
➢ ከመኝታ በፊት ዉዱዕ ማድረግ እና አያት አል ኩርስይን መቅራት
➢ ለአንድ ሰዓት ያህል አያት አል ኩርሲሰይን በመደጋገም በስልክ ላይ በመጫን  በቀን አንድ ጊዜ እንድታዳምጠዉ ማድረግ፡፡
➢ አል ኢኽላስ፤ አል ፈለቅ፤ አል ናስ ለአንድ ሰዓት ያህል በካሴት ደጋግሞ በመቅዳት በቀን አንድ ጊዜ እንድታዳምጥ ማድረግ
➢ በዉሃ ላይ የአል ሩቅያ አንቀጾችን ትቀራለህ፡፡ ከዚያም ከዚህ ዉሃ ልጅቷ ትጠጣለች፣ በየሶስት ቀኑ ልዩነት ሰዉነቷን ትታጠብበት፡፡

➢ ላኢላሀ ኢለ አላህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሀምድ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ከስብሂ ሶላት በኋላ 100 ጊዜ ማለት
እነዚህን ለአንድ ወር ሙሉ መከታተል ይኖርባታል፡፡ ከዚህ በኋላ ከሚከተሉት አንዱ ይሆናል፡፡

➊ የህመሙ ምልክቶች ጠፍተዉ ህመሙ ድኖ ድግምቱ ይረክሳል።

አልሃምዱ ሊላህ ወይም

➋ ህመሙ ጠንቶባት የህመሙ ምልክቶች አይለዉ ሊሆን ይችላል። በዚህ ግዜ የአል ሩቅያ አንቀጾችን ትቀራባታለህ በአላህ ፈቃድ- እራሷን ትስታለች፡፡ ከዚያም ከዚህ ቀደም ባየነዉ መልኩ ጂኑን እንዲናገር እያረክ ታክማታለህ፡፡


#ክፍል 8⃣
ይቀጥላል....

Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ

            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
          

                 ⭐️
#ክፍል👉 ስምንት 8⃣


       🟢 #በሜካፕ_ላይ_የሚሰሩ_ሲህሮች
ኡስታዛህ ኡሙ ሩመይሳ ጥናት አድርጋ እንደተናገረችዉ

>>> በስጦታ ለተገኙ ቤት ውስጥ ለተገኙና በሚጠረጥሩት ሰው ለተሰጠ ሜካፖች ብቻ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ 
እቃው ከሚያመጣው ችግሮች በፊት ይህ ሲህር በቤት ውስጥ ተጥሎ ከተገኘ በሜካፕ ሲህር  የተጣለበት ቤት ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች፡፡ 

📌 #ሴቶች_ወይም_እቃውን_ያገኘው_ሰው በብዙ ሰው
አስቀያሚ ተብሎ የሚነገረው ይመስለዋል፡፡ ያገኘው ሰው ሁሉ በያዘው ነገር ላይ መጥፎ አስተያየት መስጠትን ይቀናዋል፡፡

📌 #በቤት_ውስጥ_በረካ_ይነሳል....ብዙውን ግዜ ይህ ሲህር ገላጣ ቦታ ሶፋ ላይ ጠረቤዛ ላይ ተጥሎ የሚሄድ አልያም ስጦታ የሚሰጥ ሲሆን
ያ ቤት አልያም የያዘው ሰው ሙሉ ለሙሉ በረካን የማጣት ችግሮች ይፈጠራሉ፡፡ የሚያገኙት ብር ብትን ብሎ የመጥፋት ለምን እዳዋሉት እስኪጠፋባቸው ድረስ፡፡ ረሀብ ጠኔ ቤት ውስጥ ሊፈጠር ይችላል፡፡

📌 #ቤት_ውስጥ_ተማሪዎች_ካሉ በጥናት ላይ መሳነፍ ሲያነቡ መታመም፡፡ ቤት ውስጥ ቁርአን የሚቀራ ሰው ካለ መሳነፍ ከሚቀራው ነገር መዘናጋትን ይጀምራሉ፡፡ 

📌 #ብዙውን_ግዜ_በባልና_ሚስት_መሀከል የሚፈጠሩ እርግዝናዎች እንዲጨናገፉ ያደርጋል፡፡ ይህም በሆስፒታል መውለድ ትችላላችሁ ተብለው እንኳ ቢወሰን እነርሱ ግን ልጅ ሊያገኙ አይቻላቸውም፡፡ ይህም የሩቅያህ ኡስታዞችን ተስፋ የሚያስቆርጥ ሲሆን ነገሮችን ሳይንቁ ጠለቅ ብሎ ማየቱ ውጤታማ ያደርጋል፡፡ 

📙 #ምልክቶቹ!!

➊ በመጀመርያ ሁለት ሳምንታት አስማታዊ የሆነ ለውጥ አለው፡፡ ሰው ሁሉ አማረብሽ/ አማረብህ ይልሀል ይልሻል፡፡ 
➋ ልክ ከሁለት ሳምንት አልያም ሜካፑን መጠቀም ስታቆሚ/ስታቆም ቡጉር በቡጉር አልያም የፊት መላላጥ ይኖራል፡፡ ይህም በአለርጂነት ወይም በእስቴሮይድ ኢፌክትነት የሚመጣ አይደለም ፡፡ ከዚህ በፊት ብዙ የሜካፕ ፕሮዳክት ተጠቃሚ ብትሆኚም ይህ ግን አደገኛ ነው፡፡

➌ ያለ ሜካፑ ካሳለፍሽ ፊት መቆጥቆጥ ፊት ማቃጠል ይመጣል፡፡ ይህም በቫዝሊን ብሎም በሎሽን አይጠፋም፡፡

➍ ንፋስ ፊት ላይ ይሰማናል፡፡ ሌላ ግዜ ፊታችን ፀሃይ እንኳን የማያቃጥለው አሁን ፊታችን በሙሉ ንፋስ የለ ፀሀይ ይሞክረናል ፡፡ ያሳክከናል ልክ ሲብስም እንደ ጥርስ ህመም ይጠዘጥዘናል፡፡

➎ ብጉር በብጉር ይሆናል ፊታችን...ይህን ልብ በሉት ሜካፑን እንኳን አንዴ ብንቀባው ከዛ ግዜ ጀምሮ ፊታችን ለምን 10 አመት አያልፈውም ቡግሩ የማያልቅ ይሆናል፡፡

➏ ማድያት ይፈጥራል.... ይህ ማድያት ቀን በቀን የሚላጥ የሚጠቁር የሚደማ የሚያቃጥል ነው፡፡ በዚህ ሰአት ብስጭት መናደድ ይከሰታል፡፡

➐ ውስጣችን ሰላም አያገኝም በተለይ ውዱእ ማድረግ ጀሀነም መግባት ይመስለናል፡፡ ውዱእም ስናደርግ ፊታችን በጣም ይታመማል፡፡

➑ ያለርሱ ከመውጣት ወኔ ሞራላችንን ይሰልበዋል፡፡ 
➒ አይናችን በባዶ ማልቀስ መቆጥቆጥ ይጀምረናል፡፡ ፊታችን የኛ አይመስለንም፡፡

➓ፊት ማበጥ ደባደቦ ከለር የሚያስጠላ የአፍ ሽታ ሳይቀር ይኖራል፡፡

   🟡 #በሊፒስቲክ_ላይ_የሚሰሩ_ሲህሮች

እነኚህ ምልክቶች በስጦታ ለተገኙ ቤት ውስጥ ለተገኙና በሚጠረጥሩት ሰው ከተሰጠ ብቻ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ 
እቃው ከሚያመጣው ችግሮች በፊት ይህ ሲህር በቤት ውስጥ ተጥሎ ከተገኘ ሊፒስቲክ የተጣለበት ቤት ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች፡፡ 

✏️ በቤት ውስጥ ፍቅር አይኖርም ይህም በተለይ ሴት ልጆች ላይ እጅግ ስነልቦናዊ ጫና እና ጭቆና ከዚህ ሰአት ኋላ ይፈጠራል፡፡

✏️ ሚስትም ትሁን የቤቱ ሴት ልጆች መልካቸው ብሎም አቋማቸው እጅግ ከሚስብ ምልከታ ወጥቶ ማስጠላት ያለ እድሜያቸው ማርጀት ይፈጠራል፡፡

✏️ በባልና ሚስት መካከል ያለ ፍቅ ወደ ጥላቻነት ይለወጣል፡፡ 
✏️ ሴቷ ውስጧ ጭንቀት ይነግሳል፡፡ ባሏን ላለማየት በርሱ ላለመታየት ብዙ ጥረቶችን ታደርጋለች፡፡ ባልም ትኩር ብሎ ሲያያት ህመሙ ይቀሰቀስባታል፡፡
✏️ እጅግ በጣም የሚያስጠላ ከንፈር ያለን ይመስለናል፡፡ 
✏️ ከንፈራችን በተደጋጋሚ ያብጣል ይሰነጣጠቃል፡፡ ማለስለሻ ነገሮችን ብንቀባ እንኳ፡፡
✏️ አፍ መሽተት ይጀምራል፡፡ ይህ የሲህር መነሻ ነውና፡፡
✏️ የምግብ ቃናዎቻችን ይለወጣሉ፡፡ የምንበላው አይጣፍጠንም ፡፡
✏️ ከንፈራችን መንፈሩ አልያም መቃጠሉን ሰዎች ባይረዱትም በሶፍት እንኳ መንካት ይከብዳል ከህመሙ የተነሳ፡፡
✏️ አፋችን ከተወሰነ ርቀት በላይ አይከፈትልንም፡፡ የበፊቱን የአፋችንን እቅስቃሴ ይገድበዋል፡፡
ለዚህ በሽታ ትኩስ ሽንት የሚያስነኩ አሉ ፡፡ ለግዜው ፍቱን ቢሆንላቸው እንኳ በንጋታው መድማት መላላጥ ይጀምራል፡፡
✏️ ሰው ሁሉ ከንፈራቸውን የሚያይ ይመስላቸዋል፡፡
እንዲያ እየታመሙ እንኳን ሊፒስቲክ ሳይቀቡ ወደ ውጭ መውጣት አይችሉም፡፡ 
✏️ውዱእ ሲያደርጉ ከንፈራቸውን አያስነኩም የሚሞቱ የሚመስላቸውም አሉ ፡፡

     📕📕 #ለህክምናው_የሚረዱ_ቁሳቁሶች፡፡ 
🔶 ማኡዘምዘም
🔷 ጥቁር አዝሙድ ፍሬ
🔶 ወይራ ዘይት
🔷 ዘይቱን ናቸዉ...



🟢 #ስለ_ድገምት_ሊታወቁ_የሚገባቸዉ_ቁልፍ_ሀቆች

⚡️ የድግምት ምልክቶች ከልክፍት ምልክቶች ጋር ሊመሳሰሉ ይችላሉ
⚡️የማይለቅ የሆድ ህመም መኖሩ ድግምቱ የተበላ ወይም የተጠጣ መሆኑን ይጠቁማል፡፡
⚡️ የቁርአን ህክምና ይሳካ ዘንድ የሚከተሉት ሁለት ሁኔታዎች ሊሟሉ የግድ ይላል።

➊ ሃኪሙ የአላህን ትዕዛዛት የጠበቀ ሊሆን ይገባል።
➋ ታካሚዉ በቁርዓን ህክምና ፈዋሽነትና ዉጤታማነት ሊተማመንና ሊያምን ይገባል።

⚡️ በርካታ የድግምት ዓይነቶች አንድ ተመሳሳይ ምልክት ያሳያሉ፡፡ ይኸዉም ምልክት በደረት ዉስጥ ጭንቅ የሚል ስሜት ሲሆን በተለይም እኩለ ሌሊት ገደማ በጣም ይስተዋላል፡፡
⚡️ በጥቁር አዝሙድ ዘይት _ ላይ የአል ሩቅያ አንቀጾችን ትቀራና ታካሚዉ የሚያመዉን ቦታ ጠዋትና ማታ እንዲቀባዉ ታደርጋለህ። ይህም ለማንኛዉም የድግምት ዓይነት ያገለግላል፡፡ በቡኻሪ እንደተዘገበዉ ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ)፡- “ጥቁር አዝሙድ ከሞት በቀር ለሁሉም ህመም መድሃኒት ናት” በማለት ተናግረዋል፡፡
⚡️ድግምቱ ያለበትን ቦታ በሚከተሉት ሁለት መንገዶች  ለማወቅ ይቻላል።

➊ የድግምቱ እንደራሴ ጂኒ ድግምቱ ያለበትን ቦታ ሊናገር ይችላል። ነገር ግን በተባለዉ ቦታ ፈልጎ የሚያመጣዉ ሰዉ ልከህ ሳታረጋግጥ አትመነዉ፡፡ የተላከዉ ሰዉ ካገኘዉ ጂኒዉ እዉነቱን ነዉ ማለት ነዉ፡
ካልሆነ ግን ጂኒዎች በጣም ይዋሻሉ፡፡

➋ ሌላኛዉ መንገድ ደግሞ ታካሚዉ ወይም ሃኪሙ በእምነት በእርጋታ፣ አላህን በመፍራት ሁለት ረከዓ ሶላት በሌሊት በመጨረሻዉ ክፍለ ጊዜ ዉስጥ ይሰግዳል፡፡ በዚህ ሶላት ዉስጥ ድግምቱ ያለበትን ቦታ እንዲያሳዉቀዉ አላህን ይለምናል፡፡ ከዚያማ በኋላ ድግምቱ ስላለበት ቦታ ህልም ልታይ ትችላለህ ወይም የድግምቱ ቦታ እዚህ ነዉ የሚል ስሜት በዉስጥህ ሊፈጠር ይችላል ወይም ደግሞ የድግምቱ ቦታ እዚህ ይሆናል ብሎ ዉስጥህ ሊያምን ይችላል፡፡ ከነዚህ አንዱ ሲከሰት አላህን አመስግን፡ ደግምቱንም ለማክሸፍ ተንቀሳቀስ

#ክፍል  9⃣
ይቀጥላል.......
👇👇
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ


            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ

          
                 ⭐️ #ክፍል👉 ዘጠኝ 9⃣


     🟢 #ስንፈተ_ወሲብ(መሰናክለ ወሲብ)


   መሰናክለ ወሲብ ማለት፡- ጤነኛ ሰዉ ሚስቱን መገናኘት አለመቻል ማለት ነዉ፡፡

መሰናክለ ወሲብ በወንዶች ላይ እንዴት ሊከሰት ይችላል?

በድግምት የተወከለዉ ጂኒ በወንዱ አእምሮ ዉስጥ ይቀመጣል፡፡

በተለይ ወሲባዊ መነሳሳትን በሚቆጣጠሩ እና ወሲባዊ መነሳሳትን በሚመለከት መልዕክት ወደ ወሲባዊ አካላት በሚልከዉ የአእምሮ ክፍል ዉስጥ ይቀመጣል፡፡

ጂኒዉ ይህ የአዕምሮ ክፍል መደበኛ ስራዉን እንዲያከናዉን ይተወዋል፡፡ ነገር ግን ሰዉዬዉ ሚስቱን ለመገናኘት ሲጠጋ ይህን የአእምሮ ክፍል ያሰናክለዋል። የወንዱን ብልት ዝግጁ ለማድረግ ደም እንዲረጭ የሚያደርጉትን የአእምሮ መልእክቶች አንዳይተላለፉ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህ ሳቢያ / ለግንኙነት ዝግጁ የሚያደርገዉ ደም ወደ ወንዱ ብልት አይደርስም፡፡ በወንዱ ብልት ዉስጥ ያለዉም ደም ይመለሳል፡፡ በዚህም ሳቢያ የወንዱ ብልት ጨርቅ ይሆናል፡፡

ለዚህም ነዉ አንድ ባል ከሚስቱ ጋር ቅድመ ወሲብ ልፍያ በሚያደርግበት ጊዜ ብልቱ ዝግጁ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ብልቱን ወደ ብልቷ ሲያስጠጋ ድንገት ይሟሽሽና ግንኙነቱ ሳይሳካ ይቀራል፡፡

እንዲህም ያጋጥማል፡- ባል ሁለት ሚስቶች ይኖሩትና ከአንደኛዋ ጋር ወሲባዊ ተራክቦ ሲፈጽም ደህና ይሆናል፡፡ ከሁለተኛዋ ጋር ግን መሰናክለ ወሲብ ያጋጥመዋል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ድግምት የተሰራበት ከሁለተኛዋ ሚስቱ ጋር እንዳይገናኝ ለማድረግ ነዉ ማለት ነዉ፡፡

ባል ሁለተኛ ሚስቱን ለመገናኘት ሲቀርባት የድግምቱ እንደራሴ ሰይጣን ጂን ያሰናክለዋል፡፡ ምክንያቱም ሰይጣኑ የታዘዘዉ ከሁለተኛ ሚስቱ ጋር እንደይገናኝ እንዲያሰናክለዉ በመሆኑ የታዘዘዉን ብቻ ይፈፅማል፡፡


    🟢 #የሴቶች_መሰናክለ_ወሲብ

በወንዶች ላይ የሚከሰተዉ የመሰናክለ ወሲብ ዓይነቱ ይለያይ እንጂ በሴቶች ላይም ይከሰታል፡፡ በሴቶች ላይ የሚከሰት መሰናከለ በአምስት ይከፈላል፡፡ እነሱም፡-

#መከልከል

ይህ የሚከሰተዉ ሴቷ ጭኖቿን እርስ በርሳቸዉ በማቆላለፍ እንዲይገናኛት ስታደርግ ነዉ። ይህም በሴቷ ፍላጎት የሚከሰት ሳይሆን ክፍላጎቷ ወጪ በዉጫዊ ሀይል የሚከሰት ነዉ። አንድ ወጣት በዚህ ዓይነት ድግምት መለከፏን ሳያዉቅ ሚስቱን ለምን እንዲህ ታደርጊያለሽ እያለ ሲጨቀጭቃት እንዲህ ትመልስለት ነበር እኔኮ ፈልጌ አይደለም የማደርገዉ ጭኖቼ እንዳይቆላለፉ ከፈለክ ግንኙነት ከማድረጋችን በፊት እግሮቼን በሰንሰለት ለያይተህ እሰራቸዉ" አለችዉ፡፡ እንዳለችዉም አደረገ ነገር ግን ምንም መፍትሄ ሊያመጣ አልቻለም፡፡ ሊገናኛት በሚፈልግበት ወቅት ማደንዘዣ መርፌ እንዲወጋት ጠቁማዉ አደረገዉ፡፡ መፍትሄ ቢገኝም አንደኛዉን ወገን ብቻ ነበር የጠቀመዉ፡፡ ከዚያም የቁርዓን ህክምና በመከታተል ተፈወሰች፡፡

#ወሲባዊ_ስሜት_ማጣት

በድግምት የተወከለዉ ጂኒ የሴቷን የወሲብ ስሜት በሚቆጣጠረዉ የአእምሮ ክፍል ዉስጥ ይቀመጣል፡፤ ባለቤቷ ሊገናኛት ሲቀርብ የወሲብ ስሜት እንድታጣ ያደርጋታል። በዚህም ሳቢያ ወሲባዊ እርካታ አታገኝም ለባሏ ፍቅር ምላሽ መስጠት ይሳናታል፡፡ ባለቤቷ የሻዉን ቢያደርጋት እንኳ የሞተ ገላ ትሆንበታለች፡፡ በተጨማሪም ለግንኙነት ብልት የሚያለሰልሰዉ ፈሳሽ አስፈላጊ የሆነዉ እና የሴቷን ብልት እይመነጭም፡፡ በዚህ ሳቢያ ወሲባዊ ተራክቦዉ ሳይሳካ ይቀራል።

#በወሲባዊ _ግንኙነት_ወቅት_ደም_መፍሰስ

ከተለመደዉ የወር አበባ ቀናት ዉጪ ደም መፍሰስን በተመለከተ በዚህ ቀደም አይተናል፡፡ በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ደም መፍሰስ ከዚህ አንድ ነገር ይለያል፡፡ ይኸዉም በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ደም መፍሰስ የሚከሰተዉ በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ብቻ ሲሆን ከተለመደዉ የወር አበባ ቀናት ዉጪ ደም መፍሰስ ደግሞ ከወሲባዊ ግንኙነት ጋር ተያያዥነት የለዉም እንዲያዉም ለበርካታ ቀናት ያለማቋረጥ የሚዘልቅ ነዉ፡፡

በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ደም መፍሰስ ማለት አንድ ባል ሚስቱን ሊገናኝ ሲል ሰይጣን ደም እንዲፈሳት ያደርጋታል፡፡ በዚህ የተነሳ ባል ለመገናኘት አይችልም፡፡
    አንድ ወታደር እንዲህ ብሏል፡- ለእረፍት ወደ ቤቴ መጥቼ ገና ከቤት ስደርስ ባለቤቴ ደም መፍሰስ ይጀምራታል፡፡ ደሙም ቤት ዉስጥ ባለሁባቸዉ የእረፍት ቀናት ሁሉ ይቆይባታል። የእረፍት ፈቃዴን ጨርሼ ወደ ጦሩ ስቀላቀል ግን ደሙ ይቋረጣል፡፡ እንዲያዉም ገና ቤቴን ሲለቅ ነዉ ደመ የሚቆመዉ፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ነዉ፡፡ ከዚያም ሴትየዋ የቁርአን ህክምና በመከታተል ተፈወሰች።

#የሴቷ_ብልት_በስጋ_መሸፈን

ባል ሚስቱን ለመገናኘት ሲጠጋ በብልቷ አካባቢ የሚያግደዉ እና ሊበጥሰዉ የማይችለዉ ስጋ ያጋጥመዋል። በዚህ ሳቢያ ወሲባዊ ተራክቦዉ ሳይሳካ ይቀራል፡፡

#ድንግልናን_ማድበስበስ

አንድ ባል ድንግል ያገባል፡፡ ነገር ግን በግንኙነት ወቅት ድንግልና የሌላት ሆና ያገኛታል፡፡ በዚህም ጥርጣሬ ላይ ይወድቃል፡፡ ነገር ግን ከቁርዓን ህክምና በኋላ ድግምቱ ሲከሽፍ ድንግልናዋ ይመለሳል።



   ⚫️ #የመሰናክለ_ወሲብ_ህክምና

መሰናክለ ወሲብን ለማከም በርካታ ዘዴዎች አሉ እነርሱም፡-

     🌙 #ዘዴ_አንድ 1⃣

የአል ሩቅያ አንቀፆችን በታማሚዉ ላይ ትቀራበታለህ፡፡ በዚህም ጂኒዉ ከለፈለፈ ድግምቱ ስለሚገኝበት ቦታ ትጠይቀዉና ድግምቱን አዉጥተህ እንዲከሽፍ ታደርገዋለህ፡፡ ከዚያም ጂኒዉ ከሰዉዬዉ አካል እንዲወጣ ትነግረዋለህ። ከወጣ ድግምቱ ከሸፈ ማለት ነዉ፡፡ ነገር ግን የአል ሩቅያ አንቀፆችን ስትቀራበት ጂኒዉ ካልተናገረ ከዚህ በታች ከምናያቸዉ ዘዴዎች ዉስጥ ትጠቀማለህ፡፡

    🌙 #ዘዴ_ሁለት 2⃣

ሱረቱል አእራፍ 117-122 የቁርአን አንቀፅን በዉሃ ላይ ሰባት ጊዜ ደጋግመህ ትቀራለህ፡፡ ከዚያም ታካሚዉ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ከዚህ ዉሃ ይጠጣለታል ይታጠብበታልም፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ድግምቱ ይረክሳል።


    🌙  #ዘዴ_ሶስት 3⃣

ሰባት አረንጓዴ የቁርቁራ ቅጠሎችን ታመጣና በሁለት ድንጋይ መሃል ትጨቀጭቃቸዋለህ፡፡ ከዚያም በዉሃ ዉስጥ ትጨምራቸዉና ዉሀዉን ወደ አፍህ አስጠግተህ ቅጠሎቹን በእጅህ እያገላበጥ አያት አል ኩርስይ፤ አል ኢኽላስ አል ፈለቅ እና አል ናስን ሰባት ጊዜ በመደጋገም ትቀራበታለህ፡፡ - ከዚያም ታካሚዉን ለሰባት ቀናት አንዲጠጣና እንዲታጠብበት ታደርጋለህ፡፡ ይህንንም ሲያደርግ በዚህ ዉሀ ላይ ሌላ ዉሃ መጨመርም ሆነ በእሳት ማሞቅ የለበትም... በፀሀይ ማሞቅ ግን ይችላል። ከታጠበ በኋላም አጣቢዉን በቆሻሻ ቦታ ላይ ማፍሰስ የለበትም፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ድግምቱ ከሽፎ መሰናክሉ ወሲቡ ይድናል፡፡

    🌙  #ዘዴ_አራት 4⃣

የአል ሩቅያ አንቀጾችን በታማሚዉ ጆሮ ላይ ትቀራለህ፡፡ ከዚያም በእጆቹና በእግሮቹ ጫፎች የመደንዘዝ ስሜት እስኪሰማዉ ድረስ ከዚህ በታች የተጠቀሰዉን የቁርአን አንቀጽ መቶና ከዚያ በላይ ደጋግመህ በጆሮዉ ላይ ትቀራበታለህ፡፡ ይህንንም ጤንነት እስኪሰማዉ ድረስ ለበርካታ ቀናት ትደጋግምለታለህ፡፡ ችግሩ ከተወገደለት ድግምቱ በአላህ ፈቃድ መክሸፉን ታረጋግጣለህ፡፡ ይህም አንቀጽ የሚከተለዉ ነዉ።👇👇👇
‎{ وَقَدِمۡنَاۤ إِلَىٰ مَا عَمِلُوا۟ مِنۡ عَمَلࣲ فَجَعَلۡنَـٰهُ هَبَاۤءࣰ مَّنثُورًا }
[Surah Al-Furqân: 23]

   🌙 #ዘዴ_አምስት 5⃣

አል ሃፊን እንዲህ ይላሉ - እብዱል ረዛቅ በአል ሻህ በኩል የሚከተለዉን ዘግበዋል : የአረቦችን አል ኑሽራ መጠቀም ክልክል አይደለም፡፡

አል ኑሽራ ማለት እሾሃማ ተክሎች ወዳሉበት ስፍራ ሄዶ ከግራ እና ከቀኙ ቅሎችን እየቆረጠ ይይዝና ይጨቀጭቃቸዋል። ከዚያም በዉሀ አድርጎ ይቀራባቸዉና ሰዉነቱን ይታጠብባቸዋል። የሚቀሪዉም የሚከተሉትን የቁርአን ምእራፎች ነዉ፡፡ አያተ አል ኩርስይ፣ አል-ኢኽላስ፤ አል-ፈለቅ፣ አል-ናስ።


   🌙  #ዘዴ_ስድስት 6⃣

ታማሚዉ በፀደይ ወራት ከጫካና ከጓሮ አበቦች የቻለዉን ያህል ሰብስቦ በንፁህ እቃ አድርጎ ከንፁህ ዉሀ ጋር በመጠኑ ያፈላቸዋል፡፡ ዉሃዉ ፈልቶ ሲሰክን አል-ኢኽላስ፤ አል-ፈለቅ እና አል-ናስ ይቀራበታል። ከዚያም ይታጠብበታል። በአላህ ፈቃድ ይድናል፡፡

   🌙  #ዘዴ_ሰባት 7⃣

በንጹህ እቃ ዉሃ ታቀርብና፣ አል ኢኽላስ፤ አል ፈለቅ፣ አል ናስ እና የሚከተሉትን ዱዓዎች ሰባት ግዜ በዉሀዉ ላይ ትቀራለህ፡፡ ከዚያም በዚህ ዉሃ ታማሚዉ ለሶስት ቀናት ይታጠብበታል፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ድግምቱ ይረክሳል ከመሰናክለ ወሲቡም ይድናል፡፡

  🌙  #ዘዴ_ስምንት 8⃣

አል ፋቲሃን ሰባ ጊዜ ወይም ከሰባ በላይ መቅራት
ኢያት አል ኩርሲይን ሰባ ጊዜ ወይም ከሰባ በላይ መቅራት
☞ አል ኢኽላስ፣ አል ፈለቅ እና አል ናስን ሰባ ጊዜ ወይም ከሰባ በላይ ለሶስት ወይም ለሰባት ተከታታይ ቀናት በታማሚው ጆሮ ላይ ትቀራለህ። በዚህም በአላህ ፈቃድ ድግምቱ እና መስናክለ ወሲቡ ይፈታል፡፡


   🌙  #ዘዴ_ዘጠኝ 9⃣

ከዚህ በታች የተጠቀሰዉን የቁርአን አንቀፅ በጡሃራ ቀለም በንጹህ እቃ ላይ ትፅፋለህ፡፡ ከዚያም ይህን የቁርአን ጽሁፍ በጥቁር አዝሙድ ዘይት ታጥበዋለህ፡፡ ይህንን ቁርአኑ የታጠበበትን የጥቁር አዝሙድ ዘይት ታማሚዉ ለሶስት ቀናት ይጠጣለታል ደረቱን እና ግንባሩን ያሽበታል። በዚህም በአላህ ፈቃድ ድግምቱ ይፈታል፡፡ መሰናክለ ወሲቡም ይወገዳል፡፡

{ فَلَمَّاۤ أَلۡقَوۡا۟ قَالَ مُوسَىٰ مَا جِئۡتُم بِهِ ٱلسِّحۡرُۖ إِنَّ ٱللَّهَ سَیُبۡطِلُهُۥۤ إِنَّ ٱللَّهَ لَا یُصۡلِحُ عَمَلَ ٱلۡمُفۡسِدِینَ }
{ وَیُحِقُّ ٱللَّهُ ٱلۡحَقَّ بِكَلِمَـٰتِهِۦ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡمُجۡرِمُونَ }
[Surah Yûnus:81- 82]


ኢብን ተይሚያህ ቁርአን እና አዝካር ጽፎ እና አጥቦ ለታማ ማጠጣት የተፈቀደ ስለመሆኑ ፈትዋ ሰጥተዉበታል፡፡

  🔰🔰 #በመሰናክስ_ወሲብ#በስንፈተ_ወሲብ እና #በወሲብ_መሳን #መካከል_ያለ_ልዩነት

📌 #መሰናክለ_ወሲብ፡- በዚህ ድግምት የተያዘ ሰዉ ከሚስቱ ጋር ወሲብ ለመፈጸም ከፍተኛ ፍላጎት እና ስሜት ይኖረዋል። ወደ ሚስቱ እስካልተጠጋ ድረስ ብልቱ ለወሲብ ዝግጁ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ለግንኙነት ወደ ሚስቱ ሲጠጋ ብልቱ ይደክማል በዚህም ሳቢያ መገናኘት ሳይችል ይቀራል፡፡

📌 #የወሲብ_መሳን፡- ወንድ ከሚስቱ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ አለመቻል ማለት ነዉ፡፡ በመሰረቱ ከሚስቱ እርቆም ሆነ ቀርቦ ብልቱ ለግንኙነት ዝግጁ አይሆንም፡፡

📌 #ስንፈተ_ወሲብ፡- ባል ከሚስቱ ጋር ግንኙነት ማድረግ የሚችለዉ በተራራቀ ጊዜያት ነዉ፡፡ ይህም ሆኖ እንኳ ወሲባዊ ግንኙነቱ ለአጭር ጊዜ ብቻ ነዉ የሚቆየዉ፡ ብልቱ ከትንሽ ግንኙነት በኋላ ይቀዘቅዛል፡፡

           ⚡️⚡️  #ህክምናዉ

የመሰናክለ ወሲብ ህክምናን በተመለከተ 10 ዓይነት ዘዴዎችን ከላይ ተመልክተናል፡፡ የወሲብ መሳን ደግሞ በዶክተሮች ሊታከም ይችላል፡፡ የስንፈተ ወሲብ ህክምና እንደሚከተለዉ ነዉ፡፡

➊  1 ኪሎ ንፁህ ማር እና 200 ግራም በንግስት ንብ የተመረተ ማር ማቅረብ
➋  ከዚያም አል ፋቲሃህ፣ አል ሸርህ አል ኢኽላስ፤ አል ፈለቅ፣ አል ናስ የተሰኙትን የቁርአን ምዕራፎች ሰባት ጊዜ ደጋግሞ በማሮቹ ላይ መቅራት
➌ ጠዋት ከምግብ በፊት 1 ማንኪያ፣ በምሳ ሰዓት ምግብ ከመብላቱ አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ 1 ማንኪያ አራት ከመብላቱ አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ አንድ ማንኪያ ይወስዳል
➍ እንደ ስንፈተ ወሲቡ መጠን ይህን ህክምና ሰወር ወይም ለሁለት


ወራት ያህል መከታተል፡፡ ህመሙ በአላህ ፈቃድ ይድናል፡፡

  🌟 #በወንዶች_ላይ_የሚከሰት _ወሲብን_ቶሎ_የመጨረስ_ችግር_ህክምና

ወሲብን ቶሎ የመጨረስ ችግር በወንዶች ላይ አካላዊ (ተፈጥሯዊ) ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን እንግዲህ ዶክተሮች በተለያዩ ዘዴዎች ሊያክሙት ይችላሉ፡፡ ከነዚህም ዘዴዎች፡-
➊ ስሜትን የሚያቀዘቅዙ ቅባቶችን በመጠቀም
➋ በግንኙነት ወቅት ሌሎች ነገሮችን በማሰብ
➌  በግንኙነት ወቅት ከባድ የሂሳብ ስሌቶችን በማስላት


በሌላ በኩል ደግሞ ቶሎ የመጨረስ ችግር በጂኒ ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህም የሚሆነዉ ጂኒዉ በወንዱ የብልት ፍሬዎች ዉስጥ ፈጣን የስሜት መነሳሳት በመፍጠር ወንዱ ቶሎ እንዲጨርስ ያደርገዋል፡፡ ይህ እንግዲህ በሚከተሉት ዘዴዎች በአላህ ፈቃድ ይታከማል፡፡

🔶 የአል ሙልክ ምዕራፍን ከመኝታ በፊት መቅራት ወይም ማዳመጥ
🔶 ኢያት አል ኩርሲይን በቀን ስባ ወይም ከሰባ በላይ መቅራት
🔶 የሚከተሉትን ዱዓዎች ጠዋትና ማታ ማለት

"ላኢላሀ ኢላ አላህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁ አል ሙልክ ወ ለሁ አል ሀምድ ወ ሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ከሱቢህ ሶላት በኋላ 100 ጊዜ ለአንድ ወር ያህል ማለት

‎ أعُوذُ بِكَلِمَاتِ اللهِ التَّامَّاتِ مِنْ شَرِّ مَا خَلَقَ ‎

‎ اسم الله الذي لا يَضُرُّ مَعَ الشيهِ شَيْءٌ فِي الْأَرْضِ وَلَا ‎ ‎ في السَّمَاءِ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ ‎


☞ አ ዑምሩ በከሊማቲላሂ አል ታማህ ሚን ኩሊ ሸይጣንን ወሃማህ ወሚን ኩሊ ዓይኒን ላማህ

እነዚህን ዱዓዎች ጠዋትና ማታ ሶስት ግዜ ለተከታታይ ሶስት ወራት ማለት፡፡

✏️✏️ በሚቀጣለዉ ክፍል ➓ የሰዉ አይን ቡዳ ምን እንደሆነና ህክምናዉ እንዳስሳለን
#ክፍል  🔟

ይቀጥላል......


4any cmt👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ


            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
          
                 ⭐️ #ክፍል👉 አስር 🔟



    🔰🔰 #የሰዉ_ዓይን (ቡዳ) 🔰🔰


   ⚡️⚡️#የሰዉ_ዓይን (ቡዳ) ምልክቶችን አስመልክቶ ሸይኽ አብዱ አል ረዛቅ እንዲህ ይላሉ፡- በቡዳ የተበላዉ የሰዉዬዉ ነፍስ ከሆነ በዚህ ሰዉ ላይ ሳኮሎጂያዊ የህመም ምልክቶች ይታዩበታል፡ ለምሳሌ፡-
☞ ወደ ትምህርት ቤት፣ ኮሌጅ ወይም ወደ ስራ ለመሄድ ይደብረዋል፡፡
☞ትምህርት ለመማር እና ለማጥናት ይከብደዋል ይጫጫነዋል፡፡
☞ነገሮችን ለመረዳትና ለማስታወስ የነበረዉ ችሎታ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡
☞ ብችኝነትን ምርጫዉ ያደርጋል ከቤተሰቦቹ ይርቃል። የቅርብ ቤተሰቦቹ እንኳን የማይወዱትና የማያስቡለት ይመስለዋል፡፡
☞ሰዎችን ተተናኮል ተተናኮል የሚል ስሜት ያድርበታል፡፡
☞ መቃወም እና መቃረን ባህሪዉ ይሆናል፡
☞ ንፅህናዉን አይጠበቅም፡፡
☞ ከቤተሰቦቹ፤ ከወዳጆቹ እንዲሁም ከጓደኞቹ ጋር መግባባት አይሆንለትም፡፡ በጭንቀት ይወረራል፡፡
☞ በፀባዩ በአመለካከቱ እና በንግገሩ ግራ የሚያጋባና የማይገመት ይሆናል፡፡
☞ መክሳት
☞ በቤተሰብ የሌለ የፊት ቡጉር የራስ ቁስለት
☞ የቆዳ መላላጥ
☞ የፊትና ሰውነት መቁሰል
☞ የትዳር አለመሳካት ። ወንድ ከሆነ ማግባት መፍራት ሴት ከሆነች ትዳር መራቅ ወይም ትዳር ይርቃቸዋል።
☞ ሰው ፊት ማውራትና መናገር መፍራት። ነገሮችን እንደ ከዚህ ቀደም በድፍረት ማድረግ አለመቻል።
☞ በተዋወቁት ሰው ሁሉ መጠላት። ጥሩ ስራ ሰርቶ ምስጋና ቢስ መሆን።
☞ የብብት የ ፊንጢጣ መቁሰል መላላጥ።
☞ ሰውን አለማመን መጠራጠር።
☞ ቁጡና ያለ ምክንያት ተናዳጅ መሆን።
☞ የልብ ምት ድንገት መጨመር።
☞ የሰውነት መጋል።
☞ ቶሎ ተሎሎ ማዛጋት፡፡ ይህም በሰላት ላይ አልያም ቁርአን በሚቀሩበት ወቅት ይፈጠራል፡፡
☞ ከሰዎች መገለልና ሰዎችን ያለምንም ምክንያት መጥላት፡፡
☞ ድንገተኛ የሆኑ በብዙ አይነት በሽታዎች መያዝ መጠቃት፡፡
☞ መስነፍና ቶሎ ቶሎ ተስፋ መቁረጥ፡፡
☞ የሰውነት ልክ አንቀጥቅጥ እንዳለበት ሰው መንቀጥቀጥ መራድ፡፡
☞ ያለ ምንም ምክንያት ማልቀስ ማዘን፡፡
☞ የሰውነት መገርጣት፡፡ ማድያት ማውጣት ፊት መቁሰል ብጉሮች መብዛት ፡፡
☞ የምግብ ፍላጎት ማጣት፡፡ ምግብ ሲበሉ መታመም፡፡ መቃጠል ማስታወክ፡፡ 
☞ እሞታለው ብሎ ከመጠን በላይ ፍራቻ በተለይም ከመግሪብ ኋላ ፡፡
☞ የማይለቅ ራስ ምታት በአንድ ጎን ብቻ ከፍሎ መታመም(ማይግሬን)
☞ እራስን ማጥፋት መመኘት 
☞ ቁርአን በሚሰሙበት ግዜ ማላብ ማስታወክ እና አይን እያዛጉ ማልቀስ፡፡
☞ የከንፈር መንከስ። ደም ቢደማም አለማቆም።
ወዘተ

   እነዚህ ምልክቶች አንድ ሰዉ ላይ በሙሉ ባይታዩም የተወሰነት ከታዩበት የሰዉ ዓይን (በቡዳ) ለመለከፉ አመላካች ስለሚሆኑ የቁርዓን ህክምና እንዲከታተል ያስፈልጋል፡፡

   🟢  #በቡዳ_የተበላዉ_የሰዉዬዉ ንብረት (ንግዱ፣ ስራዉ …..) ከሆነ ደግሞ
✏️ በገንዘብ ዙሪያ ከሰዎች ጋር ለመስራት ይጨንቀዋል፡፡
✏️የንግድ እቃዎችን ለማቅረብ እና ለማዘጋጀት ሲያስብና ሲንቀሳቀስ ይጫጫነዋል፡፡
✏️ የንግድ እቃዎቹ ለብልሽት የተጋለጡ ይሆናሉ፡፡
✏️ ገዢ ወደ እርሱ ለመደራደር ሲቀርብ የሆነ ነገር ገፍቶ ይመልሰዋል።


🟢  በቡዳ የተበላዉ የሰዉዬዉ አካል ከሆነ ደግሞ
✏️ሰዉነቱ ሙትት ድክምክም ይላል፡፡
✏️ ሰዉነቱ ይዝላል፡፡
✏️ ሲተነፍስ የማለክለክ እና ቶሎ ቶሎ አየር የማስገባት እና የማስወጣት ስሜት ይስተዋልበታል፡፡
✏️ጭንቅ ጭንቅ ይላወል፡፡ አንዳንድ ህመሞችም ይከሰቱበታል፡፡


   📚📚 አንዳንድ ሰዎች በሰዉ አይን ቡዳ የለም ብለዉ የሚያምኑ አሉ ስለ ሰዉ ዓይን ማስረጃዎች ከቁርአን

#ልጆቼ_ሆይ በአንድ በር አትግቡ ግን በተለያዩ በሮች ግቡ፣ ከአላህም (ዉሳኔ) በምንም አልጠቅማችሁም (አልመልስላችሁም፡፡) ፍርዱ የአላህ እንጂ የኔ አይደለም፡፡ በእርሱ ላይ ተመካሁ ተመከዎችም ሁሉ በእርሱ ብቻ ይመኩ

አባታቸዉ ካዘዛቸዉ ስፍራ በገቡ ግዜ ከአላህ (ዉሳኔ) ምንም ነገር ከእነርሱ የሚከላከልላቸዉ አልነበረም፡፡ ግን በያዕቆብ ነፍስ ዉስጥ የነበረች ጉዳይ ናት ፈፀማት፡፡ እርሱም ስላሳወቅነዉ የእዉቀት ባለቤት ነዉ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያዉቁም፡ (ዩሱፍ ፡ 67-68)
🔰🔰 ኢብን ከሲር እነዚህን ሁለት የቁርእን እንቀጾች ሲተነትኑ እንዲህ ይላሉ ..አላህ ስለ ያዕቆብ የሚከተለዉን አስተምሮናል ፡- ያዕቆብ ልጆቻቸዉን   ከቢንያሚን ጋር ወደ ግብጽ ሲልካቸው  ሁላቸዉም በአንድ በር በኩል እንዳይገቡ ይልቁንም በተለያዩ በሮች እንዲገቡ አዘዛቸዉ ይህን ያደረገበት ምክንያት ልጆቻቸዉ በጣም ቆንጆዎችና መልከ መልካም ስለነበሩ የሰዉ ዓይን እንዳያገኛቸዉ በመስጋት ነበር፡፡ የሰዉ ዓይን ደግሞ እዉነት ነዉ። ፈረሰኛን ከፈረሱ ላይ አሽቀንጥራ ትጥላለች፡፡
ከአላህም (ዉሳኔ) በምንም አልጠቅማችሁም አልመልስላችሁም ማለት፡- እንዲህ ዓይነት ጥንቃቄ ማድረግ ከአላህ  ዉሳኔ ሊያድን እንደማይችል ያስረዳል፤፤

አላህ ከወሰነ ማንም የእርሱን ዉሳኔ ሊሽር አይቻለዉምና፡፡ አባታቸዉ ካዘዛቸዉ ስፍራ በገቡ ጊዜ  ከአላህ ዉሳኔ ምንም ነገር ከእነርሱ የሚከላከልላቸዉ አልነበረም፡፡ ግን በያዕቆብ ነፍስ ዉስጥ የነበረች ጉዳይ ናት ፈፀማት፡፡ ከለዉ ዓይን መጠበቅ ማለት ነዉ ብለዋል፡፡

እነሆ እነዚያ የካዱት ሰዎች ቁርአንን በሰሙ ግዜ በዓይናታቸዉ ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቃረባሉ፤ እርሱም በእርግጥ አብድ ነዉ ይላሉ” (አል ቀለም፡ 5)


🌐🌐  ኢብን ዓባስ፡ ሙጃሂድ እንዲሁም ሌሎች ሊቃዉንት ይህን የቁርአን አንቀፅ በማስመልከት እንዲህ ብለዋል፡- በዓይኖቻቸዉ ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቃረባሉ” ማለት፡- አንተን ከመጥላታቸዉ የተነሳ ይመቀኙሃል የአላህ ጥበቃ ባይኖር ኖሮ (በጎዱህ ነበር)፡፡ ከነዚህ የቁርአን አንቀጾች የሰዉ ዓይን እዉነት መሆኑን እንገነዘባለን፡

  🔰 #ስለ_ሰዉ_ዓይን_ማስረጃዎች_ከሃዲስ 🔰

➊ አቡ ሁረይራህ የሚከተለዉን ሃዲስ አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ እሉ የሰዉ ዓይን (ቡዳ) እዉነት ነዉ” (ቡኻሪ እና ሙስሊም)

➋ ዓዒሻ የሚከተለዉን ሃዲስ እስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ ይላሉ ...ከሰዉ .አይን በአላህ ተጠበቁ አላህ እንዲጠብቃችሁ ፀልዩ ምክንያቱም የሰዉ አይን እዉነት ነዉ።” (ኢብን ማጀህ ዘግበዉታል። አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)

➌ ኢብን ዓባስ የሚከተለዉን ሃዲስ አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ ይላሉ
.... የሰዉ ዓይን እዉነት ነዉ። ቀደርን እጣ ፈንታን  የሚሽቀዳደም ቢኖር የሰዉ ዓይን ትቀድመዉ ነበር። እጣቢያችሁን ስትጠየቁ ታጠቡ፡፡ (ሙስሊም ዘግበዉታል) አንድ ሰዉ ወንድሙን በዓይኑ አግኝቶት እጣቢዉን ሲጠየቅ ታጥቦ ይስጥ ማለት ነዉ።

➍ አስማእ ቢንት ዑመይስ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!!! የጃዕፈርን ልጆች የሰዉ ዓይን ታገኛቸዋለች። ህክምና ባደርግላቸዉስ? ስትል ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ጠየቀች፡፡ ነብዩም እንዲህ በማለት መለሱላት አዎን .....ህክምና አድርጊላቸዉ፡፡ ቀደርን እጣ ፈንታን የሚሽቀዳደም ቢኖር ኖሮ የሰዉ ዓይን ትቀድመዉ ነበር (አህመድ ዘግበዉታል። አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)👇👇👇
➎ አቡ ዘር የሚከተለዉን ሃዲስ አስተሳልፈዋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ>>> የሰዉ ዓይን በአላህ ፈቃድ አንድን ሰዉ ከፍታ ላይ ወጥቶ እስኪፈጠፈጥ ድረስ ታጠቃዋለች” (አህመድ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)
  ይህም ማለት የሰዉ ዓይን አንድን ሰዉ ስታገኘዉ ከፍ ያለ ስፍራ ላይ ወጥቶ እንዲፈጠፈጥ ልታደርገዉ ትችላለች።

➏ ኢብን ዓባስ የሚከተለዉን አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ አሉ የሰዉ ዓይን አይነት እዉነት ነው ፡፡ ከፍታ ቦታ (ከተራራ ላይ) ትወረራለች (አህመድ ዘግበዉታል አልባኒ ሃሰን ነዉ ብለዋል)

➐  ጃቢር የሚከተለዉን ሃዲስ አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ አሉ>>>  የሰዉ ዓይን ሰዉን ቀብር ዉስጥ፤ ግመልን ድስት ዉስጥ ትከታለች (አቡ ነዒም ዘግበዉታል። አልባኒ ሃሰን ነዉ ብለዋል)

የዚህ ሀዲስ መልዕክት፡- የሰዉ ዓይን አንድን ሰዉ ታገኘዉና እንዲሞት አድርጋ ቀብር ዉስጥ ይገባ፡፡ ግመልንም ታገኝና ሊሞት ሲል ይታረዳል ድስት ዉስጥ ገብቶ ይቀቀላል፡፡

➑ ጃቢር የሚከተለዉን ሀዲስ አስተላልፈዋል። ነብዩ እንዲህ አሉ ፡- ከአላህ ቀዷዕ እና ቀድር በሆላ አብዛኛዉ ኡመቴ(ህዝቦቼ) የሚሞቱት በሰዉ አይን ሳቢያ ነዉ፡፡(ቡኻሪ ዘግበዉታል)

➒ ዐዒሻ እንዲህ አሉ >>ከሰዉ ዓይን በሩቅያ እንድታከም ነብዩ አዘዉኛል(ቡኻሪ ዘግበዉታል)

➓ አነስ አብኑ ማሊክ የሚከተለዉን ብለዋል "ከሰዉ ዓይን፣ ከአል ሁማ (መርዛማ የእባብ ጊንጥ መነደፍ) እና ከአል ነመነህ (በጀርባ ላይ የሚከሰት የቁስል አይነት ነዉ)  ህመሞች በ አል ሩቅያ መታከምን ነብዩ ፈቅደዋል  (ሙስሊም ዘግበዉታል)

➊➊ ኡሙ ሰለማህ የሚከተለዉን ሀዲስ አስተላልፈዋል፡፡ እኔ ቤት የነበረች ልጅን ፊቷ ላይ ጥቁር ወይም ዳልቻ ነገር ተመልክተዉ ነብዩ "ይህች ልጅ የሰዉ ዓይን አባት፡፡ ስሊዚህ በአል ሩቅያ አክሟት” አሉን፡
(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበዉታል)


🔰🔰 #ስለ_ስዉ_ዓይን(ቡዳ) የሙስሊም  ሊቃዉንት አስተያየት

☑️ አል ሃፊዝ ኢብን ከሲር እንዲህ ይላሉ....የሰዉ ዓይን በአላህ ፈቃድ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ይህም እዉነት ነዉ፡፡ አልሃፊዝ ኢብን ሃጀር እንዲህ ይላሉ

እርኩስ ባህሪ የተጠናወተዉ ሰዉ ከምቀኝነት ጋር በተቀራኜ አድናቆት ወደ አንድ ሰዉ ሲመለከትና በዚህ ሰዉ ላይ ጉዳት ሲደርስበት ይህ ነዉ እንግዲህ የሰዉ ዓይን ማለት፡:

☑️ ኢብን አሰር እንዲህ ይላሉ “ጠላት ወይም ምቀኛ አንድን ሰዉ ሊያየዉ እና በዚህም ሳቢያ ሰዉዬዉ ከታመመ የሰዉ ዓይን አገኘዉ ይባላል

☑️ አል ሃፊዝ ኢብን ቀዩም እንዲህ ይላሉ “ከፍተኛ የእዉቀት እጥረት ያለባቸዉ አንዳንድ ሰዎች የሰዉ ዓይን ስለመኖሩ ይክዳሉ። የሰዉ ዓይን ተጨባጭነት የሌለዉ ተረት ነዉ በማለት ይከራከራሉ፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች ከእዉነት እና ከእዉቀት የራቁ ስለ ነፍስ እና መንፈሳዊ ጉዳዮች ስለባህሪያቶቻቸዉ፣ ሊያደርሱት ስለሚችሉት ዉጤት እና ሊያስከትሉት ስለሚችሉት ተፅእኖ አንዳች ግንዛቤ የሌላቸዉ ናቸዉ፡፡

🔸🔸🔸  የተለያዩ ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ ጠቢባን የሰዉ ዓይን ስለመኖሩ አይክዱም፡፡ ምንም እንኳን ስለ መንስኤዎቹና ሊያስከትል ስለሚችለዉ ጉዳት የተለያየ አመለካከት ቢኖራቸዉም፡፡

አላህ የሰዉ ልጆችን አካላትና ነፍሶቻቸዉን በዉስጣቸዉ የተለያየ ሀይላት እና ስብዕና አድርጎ እንደፈጠራቸዉ አያከራክርም፡፡ በአንዳንድ በርከት ባሉት ላይ ደግሞ ልዩ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባህሪያት አድርጎባቸዋል። ነፍስ በአካል ላይ ልታደርስ የምትችለዉን ተጽዕኖ ማንም አስተዋይ ሰዉ አይክድም፡፡ ምክንያቱም ተጨባጭ ነገር ነዉና፡፡

#ለምሳሌ፡- የሚወደዉና የሚያከበረዉ ሰዉ የአንድን ሰዉ ፊት ሲመለከት ሲፈካ፣ በተቃራኒዉ ደግሞ የሚፈራዉ (በቁጣ) ሲያየዉ ፍም ሲመስል ይስተዋላል፡፡ ሰዉ ስላያቸዉ ብቻ የታመሙ የተዝለፈለፉ ሰዎች ማየታቸዉን ብዙዎች መስክረዋል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነዉ እንግዲህ በሰዉ ልጆች ነፍስ ተፅዕኖ ሳቢያ ነዉ። በሰዎች ነፍሶች እና በአይኖቻቸዉ መካከል ከፍተኛ ቁርኝት ስላለ ነዉ.... ይህ በነፍሶቻቸዉ የደረሰዉ ጉዳት በዓይን እንደደረሰ ተደርጎ ይቆጠራል። እዉነታዉ ግን ይህን ጉዳት የሚያስከትሉት የሰዉ ልጅ ዓይኖች ሳይሆኑ ነፍሶቻቸዉ ናቸዉ፡፡ ነፍሶች ደግም ባላቸዉ ሃይል፣ ባህሪያት እና በሌሎች ልዩ ልዩ ገጽታዎች ከሰዉ ሰዉ የተለያዩ ናቸዉ።

የምቀኛ ነፍስ ለምትመቀኘዉ ሰዉ ጎጂ ናት። ለዚህም ነዉ ነብዩን ከምቀኛ ተንኮል እንዲጠብቃቸዉ እንዲፀልዩ አላህ ያዘዛቸዉ፡፡ ምቀኛ በሚመቀኘዉ ሰዉ ላይ ስለሚያስከትለዉ ጉዳት ስለ ሰዎች አዉቀት የሌለዉ ካልሆነ በቀር ማንም አይክድም፡፡

🔹🔹🔹 .የሰዉ ዓይን ልክፍት መሰረቱ እንዲህ ነዉ፡፡ እርኩስ የሆነች ነፍስ በእርኩስ ባህሪይ ተገልጣ የምትመቀኘዉን ሰዉ ስታገኘዉ በዚህ ልዩ በሆነዉ እርኩስ ባህሪዋ ጉዳት ታደርስበታለች፡፡


ለዚህ ደግሞ ኮብራ እባብን በንፅፅር መዉሰድ ይቻላል። በኮብራ ዉስጥ መርዝ ከሃይል ጋር ይገኛል፡፡ ኮብራዉ ጠላቶቹን ሲያይ በሃይል እና በቁጣ ይነሳሳል። መጥፎና ጎጂ በሆነዉ ባህሪዉ ይገለጣል፡፡ ይህ መጥፎ የሃይልና የቁጣ ባህሪዉ ሲብስ ጽንስ እስከማስወረድ እና ዓይን እስከ ማጥፋት ይደርሳል፡፡

አብተር እና ዙጡፍየተይን ስለሚባሉ የእባብ ዓይነቶች እነዚህ ዓይን ያጠፋሉ ፅንስ ያስወርዳሉ፡፡ በማለት ነብዩ አስተምረዉናል፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)

🔻በመገናኘት!
🔻ድንገት በማግኘት፣
🔸በማየት፣ በነፍስ በማሰብ፣
🔺ድግምት በማነብነብ፤ በማማተብ፣
🔺 በምናብ በመሳል ቡዳ በሰዉ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡


🟡🔴 የቡዳ ነፍስ በማየት ብቻ አይደለም ጉዳት የምታደርሰዉ፡፡ ቡዳዉ ማየት የተሳነዉ ቢሆንም እንኳ ስለ ሆነ ነገር በሚነገረዉ ወይም በሚሰማዉ ብቻ ተመስርቶ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። በርካታ ቡዳዎች ሰዉየዉን ሳያዩት ስለ እርሱ በተነገራቸዉ ላይ ብቻ ተመስርተዉ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ቡዳ ከቡዳዉ ሰዉ በዓይኑ በኩል ውጥታ እንደ ቀስት ትወረወራለች። ዒላማዋን ልትስት ወይም ልታገኝ ትችላለች። ዒላማዉ
>> የጠዋት የማታ አዝካር የሚል
>> ሶላት የሚሰግድ
>> ቁርአን የሚቀራ ከሆን ቡዳዉ ሊጎዳዉ አይችልም።

# ባጭሩ የቡዳ ጉዳት የተመሰረተዉ እንዲህ ነዉ፡- ቡዳዉን አንድ ነገር ያስደንቀዋል፡፡ በዚህ ግዜ እርኩስ ነፍሱ  ወደ  አስደነቃት ነገር በዓይን በኩል መርዟን ትረጫለች፡፡ አንዳንዴም ቡዳ እራሱን በራሱ ሊበላ ይችላል። ሌሎችንም ቢሆን ያለፍላጎቱ ይበላል።

ክፍል 1⃣1⃣
ይቀጥላል....


4any cmt 🔽
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ

            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ

          
               ⭐️ #ክፍል👉 #አስራ_አንድ1


   🟢 #በምቀኝነትና_በቡዳ_መካከል_ያለ_ልዩነት

➊ ምቀኛ ሲባል ቡዳን ይጨምራል።
>> ቡዳ ማለት ልዩ የሆነ ምቀኛ ማለት ነዉ፡፡
>> ቡዳ ሁሉ ምቀኛ ነዉ፡፡
>> ምቀኛ ሁሉ ግን ቡዳ አይደለም፡፡ ከምቀኛ አላህ እንዲጠብቀን ዱዓ ማድረግ እንዳለብን ከአል ፈለቅ ምዕራፍ እንማራለን፡፡

☑️ አንድ ሙስሊም አላህ ከምቀኛ እንዲጠብቀዉ ዱዓ (ጾለት) ሲያደርግ ከቡዳም ጭምር እንዲጠብቀዉ ዱዓ አድርጓል ማለት ነዉ። ምክንያቱም ምቀኛ የሚለዉ ቃል ቡዳንም ምቀኛንም ሁለቱን ያጣመረ አገላለፅ በመሆኑ፡፡ ይህ እንግዲህ የቁርአን ታዓምራዊነት መገለጫ ነዉ።

➋  ምቀኝነት ከመመቅኘት፣ ከጥላቻ ወይም ሰዉ እንዲያጣ ከመፈለግ የሚመነጭ ሲሆን በተቃራነዉ ደግሞ የቡዳ መንስኤ ማድነቅና መገረም ነዉ፡፡

➌ ምቀኝነትና ቡዳ በሰዉ ላይ ጉዳት በማድረስ በዉጤት ሲመሳሰሉ በመንስኤዎቻቸዉ ደግሞ ይለያያሉ፡፡
>> የምቀኝነት መንስኤ የሰዉን ፀጋ መመቅኘት፣ በሰዉ ነገር መንገብገብ እና መቃጠል፣ እንዲያጣ መፈለግ ሲሆን በተቃራኒዉ
>>  የቡዳ መንስኤ ማየት እና መመልከት ነዉ። በዚህም ምክንያት ቡዳ ያልተመቀኘዉን ሰብል፣ ግዑዝ እቃ ወይም ንብረት ሊበላ ይቻላል፡፡ እንዲያዉም ቡዳ እራሱን በራሱ ሊበላ ይችላል፡፡ ቡዳ አንድን ነገር በአድናቆትና በአግርሞት በመመልከቱ ምክንያት ነፍሱ ወደ ዚህ ሁኔታ ትለውጥና በምታየዉ ነገር ላይ ጉዳት ታደርሳለች፡፡

➍ ምቀኛ ያልተከስተንና ገና ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅን ነገር ሊመቀኝ እና ሊጎዳ ይችላል፡፡
>> ቡዳ ግን በተግባር የሌለን ነገር ሊበላ አይችልም፡፡

➎ ሰዉ እራሱን ወይም ንብረቱን አይመቀኝም፡፡ ነገር ግን እራሱን ወይም ንብረቱን በቡዳ ሊበላ ይችላል፡፡

➏ ምቀኝነት ከምቀኛና ተንኮለኛ ብቻ የሚከሰት ሲሆን
>>  ቡዳ ግን ከመልካም እና ደጋግ ሰዎች ጭምር ሊከሰት ይችላል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ያስደነቃቸዉ ነገር እንዲጠፋ ባይፈልጉም በመደነቃቸዉ ብቻ ጉዳት ሊደርስ ይችላልና፡፡

➐ አንድ ሰዉ የሚያስደንቀዉ ነገር ሲያይ አላህ በረካ (ረድኤት) እንዲያደርግበት ዱዓ (ፆለት) ማድረግ አለበት፡፡ ያስደነቀዉ ነገር የራሱ ይሁን የሌላ ለዉጥ አያመጣም፡፡ ይህ ዱዓዕ አስደናቂዉን ነገር በቡዳ እንዳይጎዳ ያደርገዋል፡፡

     🔴 #ጂኒዎች_ሰዎችን_በቡዳ_ይበላሉ

➊ አቡ ሰዒድ አልኹድሪ እንዲህ ይላሉ>>> ነብዩ ከጂኒ ዓይንና ከሰዉ ዓይን አላህ እንዲጠብቃቸዉ ዱዓዕ ያደርጉ ነበር፡፡ የእል ፈለቅ እና የአል ናስ ምዕራፎች ሲወርዱ በእነዚህ በመጠቀም ሌሎችን (ዱዓዎች) ትተዋል” (ቲርሚዚ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብላዋል)፡፡

📌 የአል ፈለቅ እና የአል ናስ ምዕራፎችን በመቅራት ከጂኒ እና ከሰዉ ቡዳ መከላከል እና መጠበቅ እንደሚቻል ከዚህ ሃዲስ እንማራለን


➋ እናታችን ኡሙ ሰለማ እንዲህ ይላሉ፡ በቤቱ ዉስጥ በፊቷ ላይ ጥቁረት ያለባትን ልጅ ነብዩ ተመለከቱና እንዲህ አሉ የጂኒ ቡዳ ስላለባት ሩቅያ አድርጉላት” (ቡኻሪ ዘግበዉታል)

📌 ቡዳ ከ ከሰዉ ብቻ ሳይሆን  ከጂኒዎችም : (ከሰይጣናትም) ሊከስት እንደሚችል ከእነዚህ ሁለት ሀዲሶች እንገነዘባለን፡፡

ስለዚህ ማንኛዉም ሙስሊም
>> ልብሱን ሲያወልቅ፧
>> መስታዎት ሲያይ ማንኛዉንምስራ ሲጀምር ቢስሚላህ (በአላህ ስም) ማለት ይኖርበታል፡፡ ይህም ከጂኒ ቡዳ፣ ከሰዎች ቡዳ እና ከሌሎች ጉዳቶችም ይከላከልለታል፡፡


   🟡 #የሰዉ_ዓይን (የቡዳ) #ህክምና

የሰዉ ዓይን (ቡዳን) ለማከም የሚያገለግሉ በርካታ ዘዴዎች አሉ። የተወሰኑትን እንደሚከተለዉ እንመለከታለን፡፡


       🔸🔸  #መታጠብ 🔸🔸

በዓይነ ጉዳት ያደረሰዉ ሰዉ _ የሚታወቅ ከሆነ እንዲታጠብ ይደረጋል፡፡ ከዚያም የታጠበበትን ዉሀ በመዉሰድ በታመመዉ ሰዉ ገላ ላይ በጀርባዉ በኩል ማፍሰስ፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ይድናል፡፡


የትጥበቱ አፈፃፀም

ኢብን ሺሀብ አል ዙህሪ እንዲህ አሉ "ኡለማዎች ትጥበቱን በሚከተለዉ መልኩ ሲገልጹት አስተዉያለሁ፡፡ ይኸዉም በዓይኑ ጉዳት ላደረሰዉ ሰዉ በሳፋ ዉሃ ይቀርብለታል፤ ይህም ስዉ ከዉሃዉ በመዝገን ተጉመጥምጦ መልሶ ሳፋዉ ዉስጥ ይተፋዋል፡፡ ከዚያም ፊቱን ሳፋዉ ዉስጥ ያጥባል፡፡ ከዚያም ቀኝ እጁን በግራ እጁ ያጥባል። ከዚያም ግራ እጅን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ እጁን ክርን በግራ እጁ የግራ እጁን ከርን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ እግሩን በቀኝ እጁ የግራ እግሩን በግራ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ ጉልበቱን በግራ እጁ የግራ ጉልበቱን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም በሽርጡ የተሸፈነዉን የአካሉን ክፍል ሳፋዉ ዉስጥ ያጥባል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሳፋዉ መሬት ላይ መቀመጥ የለበትም፡፡ ከዚያም ዉሃዉን በታመመዉ ሰዉ ላይ በጀርባዉ በኩል ባንድ ግዜ ማፍሰስ፡፡"

ከዚህ በተረፈ በተማሚዉ ራስ እጅን አኑሮ የተለያዩ የሩቃ ምዕራፎችንና ቁርአንን መቅራት ነዉ፡፡




🔵🔵   🟠🟠🟠   #ከድግሞት_ከሲህር_ከአይንናስ_ከስንፈተ_ወሲብ_መከላከያ_መንገዶች


✏️✏️ #ዉዱዕ_አድርጎ_መንቀሳቀስ
በዉዱዕ የሚንቀሳቀስ ሙስሊምን ድግምት ሊነካዉ አይችልም፡፡ ምክንያቱም በዉዱዕ የሚንቀሳቀስ ሙስሊም ከአላህ በተላኩ መላእክት ስለሚጠበቅ ነዉ፡፡ ይህን በማስመልከት ነብዩ እንዲህ ይላሉ “የአካላችሁን ንጽህና ጠብቁ! አላህ ንፁሀ ያድርጋችሁ፡፡ ማንኛዉም ሰዉ ዉዱዕ አድርጎ ሲያድር መላኢካ ከጎኑ ያድራል፡፡ ይህ ስዉ በመኝታዉ ዉስጥ ሲንቀሳቀስ መላኢካዉ እንዲህ እያለ ጸሎት ያደርግለታል “አላህ ሆይ! ይህን አገልጋይህን  ይቅር በለው ዉዱዕ አድርጎ ነዉ ያደረዉና።" (ሳራኒ ዘግበዉታል ኢስናዱ ጀይድ ነዉ ብለዋል)


✏️✏️ ሶላት አል ጀማዓህ (የህብረት ስግደትን) መከታተል

የህብረት ስግደትን መከታተል ለሙስሊም ከሰይጣናት ተንኮል ሰላምን ታመጣለታለች፡፡ አንድ ሰዉ ሶላትን  በጀምዓ ከመስገድ ከተዘናጋ የሰይጣናት መፈንጫ ይሆናል፡፡ በልክፍት፣ በድግምት፣ በቡዳ እና በመሳሰሉት ሰይጣናት ይዘባበቱበታል፡፡ በዚህ ዙሪያ ነብዩ እንዲህ ይላሉ፡- ሶስት ሰዎች የጀምዓ ስገደት በማይሰገድባት ከተማ ወይም የገጠር መንደር ዉስጥ ከኖሩ ሰይጣን ይሰለጥንባቸዋል፡፡ ህብረትን (ጀማዓን) አደራ!! ተኩላ የሚያድነዉ እኮ ከመንጋ ያፈነገጠን በግ ነው” (አቡ ዳዉድ በኢስናዲን ሀሰን ዘግበዉታል)


✏️✏️ የሌሊት ሶላት (ስግደት)

እራሱን ከድግምት ለመከላከል የፈለገ የሌሊት ሶላት ይሰገድ፡ ከዚህም ሊዘናጋ አይገባም፤ የሌሊት ሰላትን አለመስገድ ሰይጣን በሰዎች ላይ እንዲሰለጥን በር ይከፍትለታል፤ ሰይጣን ከሰለጠነብህ ደግሞ ለድግምት ምቹ ሆንክ ማለት ነዉ ፡፡ ይህን በተመለከተ አንድ ቀን ነብዩ ዘንድ የሌሊት ሰላት ሳይሰግድ ስላደረ ሰዉ ጥያቄ ተነስቶ ነብዩ እንዲህ አሉ፡
“ይህ ሰዉ በጆሮዎቹ ሰይጣን ሸንተታል" (ኻሪ ዘግበታል)

ኢብን ዑመር እንዲህ ይላሉ - “ማንም ሰዉ የዊትር ሰላት ሳይሰገድ ካደረ ሰባ ክንድ ሰንሰስት ባንገቱ ላይ ታስሮበት ያህል " (አል ሃፈዝ.ፈትሁል ባሪ ዉስጥ ኢስናዱ ጀይድ ነዉ ብለዋል)👇👇👇
✏️✏️ ወደ መፀዳጃ ቤት ከመገባት በፊት ከሰይጣናት በአላህ መጠበቅ

ቢስሚላህ አሏሁመ ኢኒ አኡዙቢከ ሚነል ኹቡሲ ወል ኸባኢስ ማለት ..

   መፀዳጃ ቤቶች የሰይጣናት መኖሪያዎች ናቸዉ፡ የሙስሊምን እነዚህ ቦታዎች ላይ መገኘት እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅሞ ሰይጣን ሊገባበት ይችላል፤ በሩቃ  ጊዜ አንዳንዴ ጂኖቹ  ከሰይጣናት ሳይጠበቅ ወደ መፀዳጃ ቤት በመግባቱ ምክንያት ነዉ ልገባበት የቻልኩት" በማለት ይናገራሉ

(ዉዳሴዎች) ናቸዉ” በማለት መለሰልኝ፡ ነብዩ ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገቡ የሚከተለዉን ዚክር (ጸሎት) ይሉ ነበር፡-

‎ (بسم الله اللهم إني أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْحُبْثِ وَالْخَالِيث ‎ ቢስሚ አላህ አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚነ አል ኹቡሲ ወ አል ኸባኢስ” (ቡኻሪ ዘግበዉታል) ትርጉም፡- በአላህ ስም፤ አላህ ሆይ! ከወንድና ከሴት ሰይጣናት በአንተ

እጠበቃለሁ፡፡

✏️✏️ የሶላት መከፈቻ ዚክር

የሚከተለዉን ጾለት በሶላት መክፈቻ ወቅት ማለት፡፡ ጁበይር ኢብን አል ሙጥዒም የሚከተለዉን ሃዲስ ሲያስተላልፉ እንዲህ አሉ፡- ነብዩ ሲሰግዱ አየሁዋቸዉ እንዲህም ሲሉ ሰማሁ፡-


“አሏሁ አክበር ከቢራ፤ ወል ሃምዱ ሊላሂ ከሲራ፣ ወሱብሃነ አልሏሂ ቡክረተን ወአሲላ (ሶስት ግዜ)።
☞ አዑዙ ቢላሂ ሚነ ሸይጧን ረጂም ሚን ነፍኺኽ ወነፍሲኺ ወሀምዚሂ

ትርጉም፡- አላህ ታላቅ ነዉ፡፡ አላህ በብዙ የተመሰገነ ይሁን፡፡ በጠዋት በማታ አላህ ፍፁም ነዉ፡፡ ከተረገመዉ ስይጣን ከትምክህቱ፤ ከግጥሙ እና ከእብደቱ በአላህ እጠበቃለሁ፡

✏️✏️ የጋብቻ ህይወትን በሶላት መጀመር

ዓብደላህ ኢብን አል መስዑድ የሚከተለዉን አስተምረዋል። “ከመጀመሪያዉ የጫጉላ ግንኙነታችሁ በፊት ሚስትህ ሁለት ረክዓ ሶላት እንድትሰግድ አድርግ፡፡ አንተም ስገድ፡፡ ከዚያም የሚከተለዉን ፀሎት አድርግ፡-


አሏሁመ ባሪክ ሊ ፊ አኽሊ ወባሪክ ለኁም ፊዬ፣አሏሁመ ኢጅመዕ በይነና ማ ጀመዕተ በኸይሪን.. ወፈሪቅ በይነና ኢዛ ፈረቀተ ኢለ አል ኸይር” (ጦበራኒ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)

ትርጉም፡- አላህ ሆይ በረካ ያላት ሚስት አድርግልኝ፣ በእኔ ላይም በረካ አድርግ ለበጎ እስከተስበለብን ድረስ አንድ አድርገን፡፡ ወደ መልካም በምትለያየን ጊዜ ለያየን፡፡

✏️✏️ በግንኙነት ወቅት የሚባል ዱዓዕ

ነብዩ የሚከተለዉን አስተምረዉናል “ማንኛዉም ሰዉ ከባለቤቱ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ሊፈፅም ሲል የሚከተለዉን ዱዓዕ ካለ በዚህ ግንኙነታቸዉ ልጀ ቢፈጠር ልጁን ሰይጣን በፍጹም ሊጎዳዉ አይችልም ::

‎ بِسْمِ اللهِ اللَّهُمَّ جَنِّبْنَا الشَّيْطَانَ፣ وَجَنْبِ الشَّيْطَانَ مَا رَزَقْتَنا ‎ ቢስሚላህ። አሏሁመ ጀኒብና አል ሸይጣን፤ ወ ጀኒብ አል ሸይጣን ማ ረዘቅተና

ትርጉም፡- አላህ ሆይ! ከኛ ሰይጣንን አርቅልን፡፡ ከሰጠኸን ሲሳይ ላይም ሰይጣንን አርቅልን፡፡

📌📌 በአንድ ወቅት በጂኒ የተለከፈን ሰዉ ሩቃ ሲቀራበት፡፡ ጂኒዉ እስልምናን ከተቀበለ እና ንስሃ ከገባ በኋላ ታካሚዉ ይህን ፀሎት ሳይል ሚስቱን ይገናኛት ስለነበረ ሚስቱን በወሲብ እጋራዉ ነበር ብሏል፡፡

ሱብሃን አላህ! ስንት እና ስንት እንቁ ስጦታዎች እያሉን ዋጋቸዉን ዘነጋናቸዉ!




✏️✏️ ከመኝታ በፊት ዉዱዕ አድርጎ እና አያት አል ኩርሲይን ቀርቶ መተኛት፡፡


ከዚያም እንቅልፍ እንስከሚያሸንፍህ ድረስ ዚክር  ማለት፡፡ ከመተኛቱ በፊት አያት አል ኩርሲይን የቀራ ከአላህ የተላከ ጠባቂ : አይለየዉም፡፡ እስከሚነጋ ድረስም ሰይጣን አይቀርበዉም የሚለዉን ሀዲስ አቡ ሁረይራ አስተላልፈዉልናል፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)


✏️✏️ በየቀኑ ከመገሪብ ሶላት በኋላ የሚከተሱትን የቁርአን አንቀጾች መቅራት።
የአል በቀራ ምዕራፍን ከቁጥር 1 - 5 ያለዉን
➋  አያት አል ኩርስይን እና ቀጥለዉ ያሉትን ሁለት አንቀጾች
➌ አል በቀራ ምዕራፍ የመጨረሻዎችን ሶስት አንቀፆች
   እነዚህን አንቀፆች በቀራህባቸዉ ቀናት ሌሊቱንና ቀኑን ከድግምትና ከጂኒ ልክፍት በአላህ ፈቃድ ትጠበቃለህ፡፡


✏️✏️ ላኢላሀ ኢላ አላህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁ አል ሙልክ ወ ለሁ አል ሀምድ ወ ሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ከሱቢህ ሶላት በኋላ 100 ጊዜ ማለት፡፡


ይህንን በማስመልከት የሚከተለዉ ሃዲስ ተላልፎልናል። ይህን ፀሎት በቀን መቶ ጊዜ ያለ አስር ባሪያዎችን ነፃ እንዳወጣ ይቆጠርለታል፡፡ መቶ ምንዳ ይፃፍለታል። መቶ ሀጢያቶችን ይማራል። በዚያ ቀን እስከሚመሽ ድረስ ከሰይጣን መከላከያ ይሆነዋል፤ ይህ ሰዉ ከስራዉ ሥራ የሚበልጥ ማንም አያመጣም ከመቶ በላይ ያለ ካልሆነ በስተቀር፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)

✏️✏️ ወደ መስጊድ ስትገባ የሚከተለዉን ዱአ ማለት፡-

‎አኡዙቢላሂል አዚም፣ ወቢወጂብ አል ከሪም ወ ሱልጣኒሂ አል ቀዲም ሚነ አል ሸይጧን አል ረጅም (አቡ ዳዉድ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)

✏️✏️ ከቤትህ ስትወጣ የሚከተለው ዱዓዕ ማለት
‎ بسم الله توكلت عَلى اللهِ፣ وَلا حول ولا قوة إلا بِاللَّهِ ‎

ይህን ዱዓዕ በምትልበት ግዜ ሰይጣን እንዲህ ይላል “ተጠበክ ተመራህ፤ ተብቃቃህ እንግዲህማ ሰይጣን ይሸሽሃል ....ሌላ ሰይጣንም ሲያገኝ እንዲህ ይለዋል የተጠበቀን የተመራን የተብቃቃን ሰዉ ምንስ ልታደርገዉ ትችላለህ? ምንም ልታደርገዉ አትችልም” (አቡ ዳዉድ እና ቲርሚዚ ዘግበዉታል)


#ክፍል 1⃣2⃣
ይቀጥላል....


አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
30 አመት ወደ ኋላ የዘመን ቀመሩ ሲፈተል በ1992

  በተሞሸረች በ3 ቀኗ የሠርጉ ድባብ በቅጡ ሳይቀዘቅዝ ፍቺው ፀድቆ ወደወላጆቿ ቤት ተመለሰች። ያለምንም ምክንያት ተፋተው ወደ እናቷ ቤት ተሸኘች። ያ አምስት ዓመታትን ያስቆጠረው ውብ የፍቅራቸው ጊዜ በድንገት አከተመ። ሚስት የስቃይ ህይወትን መግፋት ጀመረች። እሱም ከሷ በኋላ ሳያገባ ድፍን ሰላሳ ዓመታት አለፈ። ሲህር ነበር ያለያያቸው የሠርግ ቬሎዋን ጠቅልለው ከሞተ ሰው አስክሬን አፍ ላይ ፎቷቸውን አስረው ቆፍረው ከመቃብር ስፍራው ቀበረው በስቃያቸው ተደሰቱ።

ሲህሩ ተገኝቶ ከተቀበረበት እንደወጣ ሚስቱ ድና ወደመልካም የጤንነት ሁኔታዋ ተመለሰች። ባል ወደ ቤተሰቦቿ አቀና። ሚስቱን በድጋሜ ተንበርክኮ ጠየቀ። አዲስ ፍቅር ቤታቸው ገባ። ጤንነት ከደጃፋቸው ደረሰ። ፍቅራቸውም አገረሸ። በ2022 ዳግም በእልልታ ተሞሸሩ።

የአክስቷ ልጅ ነበረች ሲህሩን ያሰራችባት። ቬሎዋን ቀዳ ለደጋሚው የሰጠች። ሳሂሩ ጥቁር ዶሮ አሽከርክሮ አንገቱን በጠሰና ደሙን ከፎቷቸው ጋር ለውሶ ከጀናዛ አፍ ጋር አስሮ ህይወታቸውን በስቃይ እንዲገፉ አደረጋቸው። አላህ ከሰባት ሰማያት በላይ ሆኖ አዘነላቸው ከድፍን ሰላሳ አመታት በኋላ ከአፊያው ዳብሶ ዳግም አገናኛቸው።
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ
             
          
                 ⭐️
#ክፍል👉 አስራ ሁለት 1⃣2⃣


  🔰🔰በተከታታይ ➊➊ ፓርቶች ድግሞትና ሲህር ከሚለዉ መፅሀፍ 70% በራሴ ካነበብኳቸዉ ከማቃቸዉ 30% ጨምሬ ከሰዎች ታሪክ በመጨመር በምሳሌ አቅርቢያለሁ ..ከpart ➊➋ ጀምሬ እስኪ ከሰማሁት ከማቀዉና መረጃዎችን በማጣቀስ ለእናንተ አቀርባለሁ፡፡


መጀመሪያ ብዙሀን ሰዉ አናምንም እኛን አይነካንም እንላለን ...ግን በራስ ሲደርስ ነዉ የሚታወቀዉ  የኢማን የመጠንከር የመላላት ጉዳይ አይደለም የሆነ የምንዘናጋበት ቀን አለ በዛ ቀን በሰዉ ምቀኛ በተለይ በቅርብ ጓደኛ በቅርብ ዘመዶች ሊያነጣጥሩብን ይችላሉ ....የት ይሰራል ብላችሁ ካሰባችሁ ...ብዙዎች እነሸህ እነ ወልይ የወደፊት ያቃሉ እያሉ እየሄዱ እየሰገዱ ቁርአን እየቀሩ ጀለብያ ጥምጣም ለብሰዉ ሳሂር ደጋሚ የሆኑ እንዳሉ አንዘንጋ በተጨማሪ ደግሞ በጣም ብዙ ሰዉ ከሙስሊሙም ሌላም ሀይማኖት ተከታዮች የሚሄዱት ደብተራዎች ጋር ነዉ፡፡ 
ደብተራዎች face book እና tg ቻናል አላቸዉ ለምሳሌ ሁለት የማቀዉን ከtg ያገኘሁትን ከታች ተመልከቱ

⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
መርጌታ ገብረ መድን በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ለማይችሉ ባሉበት እንሰራለን የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል   ☎️  09 ... 03 ....☎️ ስልኩን ያጠፋሁት ደግሞ እንዳደዉሉ ብየ ነዉ☺️
ለገበያ>>ለሀብት>>ለስንፈተ ወሲብ (ለቁመት:ለውፍረት: ቶሎ ለሚያበቃ) >> ለመስተፋቅር >>ጥይት ለማያስመታ >> ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ >> ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)>> ለፀር (ለጠላት)>>ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)>> ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)>>ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)>>ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)>> #መስተፋቅር>> ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
>> ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ>> ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)>> የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ>>ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)>> መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)>> መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)>> ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)>>ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)>> ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ>> ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ>> ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)>> ለሙግት>> ለሰላቢ>> ለስንፈት ወሲብ>> ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)>> ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)>> ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)>> ለዱላ( ዱላ የማያስመታ)>> መንስኤ_እስኪት (ለወንድ የመራቢያ አካሉ ለደከመ ላነሰ)>> ህገ_ጠብቅ (የትዳር አጋራችን ወደሌላ እንዳይሄድ የሚያስር
እንዳይዘሙት የሚከለክል)>> ለአይነ_ሰብእ (ከሰው አይን የሚጠብቅ)>> በመኝታ ሽንት ለሚያመልጠው >> እንቅልፍ መብዛት>> የእንቅልፍ ማነስ >> የወር አበባ ችግር ካለ

09...  03 ....
ይደውሉልን

✏️✏️በተጨማሪ የሌላዉን በtg የሚፓስተዉን ልላክላችሁ👇👇👇👇

☎️📞09 4............5  የባህል መድህኒት  ጥበብ አስማት ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
መፍትሄ ሀብት መስተፋቅር = የገበያ  ለቀለም= ትምህርት ለአይነ ጥላ= ለመፍትሔ ስራይ= ለህማም = ጋኔን ለያዘው ሰው = ቡዳ ለበላው = የዛር ውላጅ ለተዋረሰው = ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር) =  ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ) =  ለቀለም(ለትምህርት) = ሰላቢ የማያስጠጋ =  ለመፍትሔ ሀብት =ለመስተፋቅር =  ለገብያ =  ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ) = ለመድፍነ ፀር =  ሌባ የማያስነካ = ለበረከት
= ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ) = አፍዝዝ አደንግዝ = ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ) = ለግርማ ሞገስ =  ለዓይነ ጥላ
=  ለሁሉ መስተፋቅር =  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ = ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) = ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ =  ለድምፅ =  ለብልት እንደመቆም =  ለኤች አይቪ መድሀኒት
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት

ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል

ለጥያቄወ 📞☎️09 4........5 ይደውሉልን በአካል መቅረብ ለማትችሉ በሙሉ ወደ አሉበት ቦታ ድረስ ይደርሶዎታል

ይላል በTelegram በfacebook በጣም ብዙ አሉ ይሄን የላኩላችሁ ሲህር ድግምት ለእናንተ መጥፎ የሚስቡ መጥፎ ሰዎች እነዚህ ቦታ ቢሄዱ አስባችሁታል?? እነዚህ ቦታ ሂደዉ መስተፋቅር ወይ ገበያ እንድንከሰር ወይ ሌላ ነገር ቢያሰሩበን በእኛ ኢማን ድክመት በጣም ከባድ ነዉ ፡፡ እናም ብዙ ሰዉ የለም የሚል ካለ ራስን ማሞኘት ነዉ ደጋሚዎች ደብተራዎች በየሀገሩ በየመንደሩ አሉ፡፡


📌📌ማወቅ ያለብን የደብተራ ብቻ አይደለም ..በጣም በዙ ሙስሊም ተብለዉ በየገጠሩ የሚሰሩ አሉ ዱአ ላስደርግ ምናምን ጫት የሚቃምበት በጣም የሚበዛ ከሆነ ..ወይም በጫት እናስለቅቃለን ካሉ ዛር አለባቸዉ በጫት የሚያስለቅቀዉ ለትልቅ ጅን ይገብራል ማለት ነዉ እንወቅ እባካችሁሁሁሁ  ....

ወልዮች ሸሆች ጋር እያልን ጫት የሚቅሙ ጋር እየሄድን ባንዘናጋ ኸይር ነዉ፡፡በነገራችን ላይ እንደዚህ እያለ የሚሄድን ወጣትም ሆነ ትልቅ ሰዉ ሰዉየዉን ባንቀርብ ወይ ሰዉየዉን ከቀረቡ እራቅ ብሎ በዉዲዕ ቢሆን አሪፍ ነዉ፡፡

የሚገርመዉ ነገር አንድ የገጠር ሰዉ የማምነዉ ለጅን ማረድ ከተወ ቡሀላ ሲያወራኝ ለጅን የሚያርድልን ሰዉ የመስጊድ ኢማማችን ነዉ ብሎኛል ...

አሏሁ የስቱርና


--------- ------ ------ ------ -----
   📚📚ግን አንዳንድ ፍቅሮች እንዴት ነዉ ???🙄

አሁን ላይ ግራ የገባኝ ነገር አለ ፍቅር እንዴት ነዉ???
ፍቅር አለ ወይስ የለም ማለት ለማለት እየከበደ ነዉ ..ፍቅር አንዳንዴ የሲህር በሽታም ሊሆንም ይችላል ብቻ እኔ አሁን ግራ እየገባኝ ያለ ፍቅርን እንዴት መገለፅ ይቻላል መልስ የሌለዉ ጥያቄ...

ግን እስኪ ከዚህ በታች አይነት ታሪክ የደረሰባችሁ ካለ በአስተያየት መስጫ ላይ አስቀምጡልኝ...ግን በፊት እወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ ወይም እወዳታለሁ አፈቅራታለሁ ብለዉ በፍቅር ሲያለቅሱ ሲሰቃዩ የነበሩ..እንደ አጋጣሚ ወይም በሌላ ምክንያትም ቢሆን ታመዉ ሩቃ ሲገባ እወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ ያሉትን ሰዎች 80% እሱ ጋር ቢኖሩም ባይኖሩም ምንም አይመስላቸዉም...ከሩቃ ቡሀላ አፍቃሪዉ ሲህር ወይ ጂን ከነበረበት ከለቀቀ አፍቅረዋለሁ የሚለዉ ሰዉ ረጋ ማለት እና መረጋጋት ይታይበታል፡፡👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/24 22:27:36
Back to Top
HTML Embed Code: