Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሴትነት ምንድን ነዉ?

ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ
እንዴት ናችሁ
             አሚር ሰይድ

    ከተወሰኑ ቀናቶች በፊት በተፓሰተዉ በHiv positive ያለባቸዉ ችግሮች እና እነሱ ትዳር እርስ በራሳቸዉ ለመገናኘት ከባድ ፈታኝ ችግር ስለሆነ በቻናል ላይ የጤና ባለሙያዎች እና ማንኛዉም ያነበበዉ ሙስሊም የራሱ ሀሳብ ካለዉ እና Hiv positive የሆናችሁ በአስተያየት መስጫ bot እንዲያሳዉቁኝ ሰፋ ያለ ፁሁፍ ፓስቼ ነበር
ከሞላ ጎደል ከአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ አንፃር Data ስለተዘጋ በpisphon ብቻ ስለምንጠቀም በpisphon የማይጠቀምም ስላለ በተጨማሪም የተፓሰተዉ ረመዳን ሊገባ 10 ቀን ሲቀረዉ ስለሆነ በዚህ ቀናቶች ደግሞ አንዳንድ ወገኖች ረመዳንን ብቻ ሚዲያ አልጠቀምም ብለዉ የሚቶብቱ ስላሉ አላህ በዛዉ ከሚዲያ የሚጠፉ ያድርጋቸዉና😊 እንደታሰበዉ ፁሁፉ ለብዙ ሰዉ ተደራሽ ባይሆንም ግን ከታሰበዉ እቅድ 55% ግብ ላይ ዉሏል

☞በአስተያየት ላይ ሰዉ በጣም ሰፊ ልዩነት ያለዉ እንደዉ ስለ Hiv አያቁም ወይ ያስብላል የሚሰጡት comment ደባሪ የሰጡ አሉ ምን ይባላል ጀሊሉ እዉቀትን ጨምርላቸዉ ከማለት ዉጭ.. ስድብም የሰደቡኝ ነበሩ እነሱ የማይጠቅም የማይጎዱ ስለሆኑ
ከቻናል ተጭረዋል መቀመጣቸዉ ቻናል ከማሞቅ ዉጭ ጥቅም የላቸዉም

☞ የተወሰኑ ወደ 5 comment ደግሞ Hiv ይለቃል የሚሉም አየሁ ይሄን እያዩ አንዳንድ ከተሞች ሰፈሮች የፈጣሪ ቁጣ እንጂ በሽታ አይደለም ብለዉ ራሳቸዉን ያሳመኑም አሉ ....
የለቀቀዉ ሰዉ ብሎ የነገሩኝ ግራ ገብቶኝ የጤና ባለሙያ ስጠይቅ አይለቅም ግን በሽታዉ ስለሚዳከም ስትመረመር ላያሳይ ይችላል ብለዉኛል እናም ይለቃል ብላችሁ ባይዳከሙ ባይ ነኝ፡፡ ግን አንድ አዲስ አበባ የተፈጠረ የማቃት ልጅ የነገረችኝ ገርሞኛል ግን መንገሩ ጥሩ ስለማይሆን በደንብ ማሰቡ ይሻላል

☞ በቻናል Hiv positive ራሳቸዉን ይፋ ያደረጉት ሴቶች ብቻ ሲሆኑ ..ግን ተማሪዎችም ስራ ላይ ያሉም የወለዱም አሉ ግን ፈጣሪ ይድረስላቸዉ 95% ተስፋ የቆረጡ ሁነዉ አግኝቻቸዋለሁ :: የተወሰኑትም ተስፋ ቆርጠዉ መድሀኒት እስከማቆም የደረሱ ነበሩ እነሱን በሶይኮ ማከምና እነሱን የስነልቦና ምክርን በመስጠት መድሀኒት በማስጀመርና ለወደፊት ህልም ሰንቀዉ ተማሪዎችም ተምረዉ እንደነሱ hiv+ የሆኑትን መርዳት እንዳለባቸዉ የተለያዩ ምክሮች ልምዶች በመስጠት እነሱን በፊት ካሉበት ዲፕሬሽን በማዉጣትና መድሀኒት ያቋረጡትን ደግሞ እንዲጀምሩ በማድረግ በቅርብ በመከታል 97% ተሳክቷል አልሀምዱሊላህ ለወደፊትም ከጎናቸዉ ሁኜ እከታተላቸዋለሁ

☞አንድ እንኳ ወንድ ማግኘት አልቻልንም..ይሄ ማለት
ብዙዎች ደብቀዋል ወይም ከኑሮ ዉድነት አንፃር አሁን ላይ ትዳር ለመመስረት ስለከበደ ሊሆንም ይችላል እናም ለማገናኘት የተለባለዉ ወንድ ማግኘት አልቻልንም....
የHiv+ group አለ እዛ ወደ 20 ወንዶች ነበሩ ግን ከወሬ የዘለለ ቁም ነገር የላቸዉም...እነዚህን አግቡ ማለት ስስ የሆነ የሴት ልብን መጉዳት ነዉ፡፡ ለምን ብዙ ሴቶች በዚህ ኬዝ ያሉ እዉነት ስለሚመስላቸዉ የትዳር ፕሮሰስ ተጀምሮ ቢያፈገፍጉ የሴቱ ልብ ይጎዳል ከዚህ አንፃር ለማግባት የነየተን እንጂ እኔም የዚህ ኬዝ ካላት ጋር ወሬ ብቻ የሚወራን ማገናኘቱ ለሴቶቹ ጉዳት መጨመር እንጂ ጥቅም ስላልታየ ትተነዋል

☞ አዲስ አበባ ላይ መድሀኒቱን የሚሰጠዉ የጤና ባለሙያዉን ለማማከር በየጊዜዉ ይቀያየራሉ ብለዉኛል ይሄ ትንሽ ለማማከር ይከብዳል ግን ከአዲስ አበባ ዉጭ ያሉ ከተሞች መድሀኒቱን የሚሰጠዉ  አንድ የጤና ባለሙያ የተወሰኑ ወራቶች እስከ አመታትም ስለሚቆይ ብታማክሩ አሪፍ ነዉ መፍትሄ ግብ ላይ መድረስ ግዴታ ስበብ ማድረስ ስለሚያስፈልግ፡፡ Hiv+ ስለትዳር ሲታሰብ የመጀመሪያ ዉሳኔ መሆን ያለባቸዉ የጤና ባለሙያ ማማከር መሆኑን አንዘጋ...ግን የወሰኑ ሴቶች የጤና ባለሙያ ስናማክር የምናገኘዉ እድሜዉ ከ40 በላይ የሆነ ነዉ ያሉኝ አሉ በዚህ በእድሜ የተነሳ እንዳላገቡ ነግረዉኛል፡፡ይሄ በኔ የሚወሰን አይደለም ትዳር የፍላጎት ምርጫ ስለሆነ ገብቶ ከመጨቃጨቅ ከመናናቅ የሚወዱትን መስፈርታቸዉን የሚያሟሉ  ማግባት የራሳቸዉ ምርጫ ስለሆነ በእድሜ የገፋ አግቡ ብየ ማስገደድ አልችልም....
ፈጣሪ ያሰባችሁትን ያሳካለችሁ ከማለት ዉጭ


☞ አዲስ አበባ AHF Addis clinic /kolfe clinic የሚባል ለም ሆቴል አካባቢ አለ HIV positive ለሆኑ ሰዎች ትዳር ያገናኛሉ ብለዉኛል ይሄ የኮሚሽን ግን ይቀበላሉ ብለዉኛል እንደ አማራጭ ይያዛል


☞ለታዋቂ ሰዎች ማድረስ በሚለዉ ደግሞ ለተለያዩ ፀሀፊዎች ለተለያዩ ኡስታዞች የትላልቅ ሚዲያ ባለሙያዎች በማድረስ ከአንድ በኔ ሀሳብ በምትሄደዉ የዲን እህቴ ጋር በመናበብ 80% ያሳወቀን በዚህ ዙሪያ የቻሉትን እንዲሰሩ ታገለን ነበር ያዉ የዘንድሮ ሙስሊም ከኢንሻ አላህ ዉጭ የሚሰራ የለም ኢንሻ አላህ ብለዉ ዘግተዉናል😊
የአሁን ብዙዉ ሙስሊም ኢንሻ አላህ ብሎ ወደ ግራ የሚሄድ ነዉ ምንም ማድረግ አልችልም በተቻለን አላህን ይዘን መታገል ብቻ ..አሁን ላይ ከዳኢዎች ከኡስታዞች ጥሩ ምላሽ መጠበቅ ከብዷል አላህ ለዚህ የዋህ ሙስሊም ኡማ ይድረስልን

☞ አንድ ብቻ ሙስሊም ወንድም የጤና ባለሙያ ሙስሊሞችን Hiv+ የሚያገናኝ አለ ግን አሁን ረመዳን ነዉ ከረመዳን ቡሀላ ብሎኛል ፡፡ ግን ከአገናኘሁ ቡሀላ እየተጣሉ እየተፋቱ ተቸግሪያለሁ ለምን ይሁን ይሁን ችግር የለም በሚል ከተጋቡ ቡሀላ ብዙዉ ሳይግባቡ ስለሚጋቡ ሲግባቡ ችግር እየመጣ በጣም ተቸግሪያለሁ አለኝ...እናም ከረመዳን ቡሀላ ብሎኛል እናም እዚህ ያላችሁ
Hiv + የሆናችሁ የቻናል ቤተሰቦች ፈርታችሁ ያልተናገራችሁ በዚህ bot አሳዉቂኝ የእሱን ስልክ ቁጥር እሰጣችሆለሁ በዚህ bot ያሳዉቁኝ
👇👇👇
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot

☞  የተቸገሩን ኸይር መስራት የፈለገ Hiv+ ሆነ ከዛ ዉጭ ያሉ መርዳት የሚፈልግ ካለ እኔ ችግረኞችን በስልክ ወይ በtg acount አገናኛችሆለሁ ራሳችሁ መርዳት የምችሉበትን አመቻችላችሆለሁ ...እኔ ሚዲያ ላይ የማቃቸዉ በጣም ብዙ የተቸገሩ አሉ በራሴ አቅም የቻልኩትን ባደርግም ግን ብዙ ከአንድ ሰዉ አቅም በላይ ነዉ እናም ኸይር መስራት የሚፈልግ የተቸገረዉን እኔ ላገናኛችሁ ችግሩን ሁኔታ ራሱ ያስረዳችሆል የምረዱትን ቀጥታ እነሱ ጋር ማገናኘት እችላለሁ የመርዳት ንያዉ ያለዉ በዚህ bot ያሳዉቀኝ
👇👇👇
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot

☞ደግሞ በተሻለ መልኩ የክርስቲያን ሀይማኖት የሰጡት ገንቢ አስተያየት ነበር እነሱን ሳላደንቅ አላልፍም...አሁን ላይ እነሱ ይሰራሉ ለሀይማኖታቸዉ ደስ ይላሉ እኛ ግን እነሱ ሰሩ ቦታ ተቀበሉ ብሎ ጫጫታ ነዉ ለእምነታቸዉ የመስራት ፈጣሪ ብለዉ ከያዙት ግዴታ ስለተሰጣቸዉ ይሰራሉ ሰሩ ብሎ እርይ አያዋጣም ይልቅ እኛ ኢንሻ አላህ እያሉ ከመሹለክ እንደ እነሱ ተናቦ መስራት ያዋጣል፡፡ እናም ከልምድ አንፃር ለሰጣችሁኝ አስተያየት ጥቆማ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡👇👇
በነገራችን ላይ እንደ ወሎየ እያሰብኩም ሊሆን ይችላል... የኔ ሁለት አያቶቼ ክርስቲያን ናቸዉ ..አጎት የአጎት ልጅ ምናምን እንደ ወሎ አንድ ላይ በልተን ጠጥተን አድገናል ከዛ አንፃር እያሰብኩም ሊሆን ይችላል....ግን የኛ ሙስሊም ችግር ዲነል ኢስላምን እንኳን ለሌሎች ሀይማኖት ማዳረስ ይቅርና ለሙስሊሙ ለማስተማር ኡስታዞች ሸይሆች ከወጣት እስከ ትልቅ ሙስሊሙ በዱንያ ቢዚ ሁኗል የዚህ ችግር እንጂ
ሞክሩ እነሱን ኢስላምን በማስተማር ቀላል ነበር የኔ ቤተሰቦች 20% የሚሆኑት መልሰዉ ሰልመዋል
የኛ ችግር እነሱ ቦታ ተቀበሉ እንደዚህ አረጉ እርይ ኡኡኡኡ በቃ አለቀ የጮሀዉ ሁሉ 1% ሲሰራ አይታይም ጥጉን ይይዛል.... የሌሎችን ሀይማኖት ተከታዮችን ኢስላምን ለማስተማር እስከ ጥግ ድረስ ጥረት ሲደረግ አላየሁም...

ማወቅ ያለብን ለሌላ ሀይማኖት ኢስላምን ማስተማር ግዴታ እንዲሰልም አይደለም
ለኢስላም መጥፎ አመለካከት እንዳይኖረዉ ለማድረግ ጭምር መሆን መታሰብ አለበት ኢስላም የሚሰጠዉ አላህ ብቻ ነዉና...ከልምድ አንፃር አንድ ሰዉ ማስለም የፈለገ በጥረት የ5-7 አመት ትግል ያስፈልጋል
ሀይማኖት እኮ እንደ ስም በፍርድ ቤት ሂደህ በአንድ ወይ በሁለት ቀን የምትቀይረዉ ነገር አይደለም
ሀይማኖት መቀየር የህሊና ጦርተን ያለበት..ከቤተሰብ ከዘመድ ከወዳጅ የሚያራርቅ ከባድ ዉሳኔ ነዉ ስለሆነም የአሁን ሙስሊም በአንድ ወይ በሶስት ቀን የሚቀይሩ ስለሚመስለዉ አካሄድ አይችልም..እነሱን ከመወንጀል ከመከታተል ዉጭ እናም ይሄ መታረም አለበት በዚህ ቻናል ብዙ የማቃቸዉ የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ጋር ስለማቅ ስለምግባባ ጭምር ነዉ ፡፡
እናም መጀመሪያ ሁሉም ሙስሊም የኛ ጥርት ያለ ነዉ ማለት አንችልም የኑሮ ዉድነት እየመጣብን ያለዉ በተለይ በብዙ ስግብግብ ሙስሊም ነጋዴዎች መሆኑ አንዘጋ ይሄዉ ዘንድሮ ተምር 3000 ከዛም በላይ ገብቶ በካርቶን የለመድነዉ በኪሎ አፁመዉናል እኮ 😊መታሰብ ያለበት ተምር የሚሸጡት 90% በላይ ሙስሊም ነጋዴዎች መሆኑን አንዘንጋ

እያየነዉ ባለዉ ተጨባጭ ከሌላ ሀይማኖት ሰልመዉ ወደ ኢስላም የገቡ ናቸዉ ለኢስላም እየሰሩ ያሉት...ሙስሊሙ የኢስላምን ፀጋ ስጦታ አላስተነተነዉም ግን የሰለሙ ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጠዉ ቆርጠዉ ወደ ኢስላም ስለገቡ ቁርአን ቀርተዉ ሀዲስ ተፍሲር ቀርተዉ ሙስሊም ሁኖ የተወለደን እያስተማሩና ሌሎች ለመስለም ያልታደሉትን ወደ ኢስላም እየጠሩ እያስተማሩ እያሰለሙ እያየን ነዉ እናም አሁን ላይ በጣም ጭፍን ጥላቻ እነሱ ጋር ያለዉ አያስፈልግም ማስተማር እንጂ

እኛም ማወቅ ያለብን ነብዩ ሰዐወ አንድ ሰዉ እናንተን በባህሪ በሁሉ ነገር አይተዉ ለመስለም ጉጉት ካላደረጉ ኢማናችሁ ድክመት አለበት ብለዋል...የኛ ባህሪ ኢስላምን ይጣራል ወይ??



አሁንም በዚህ HIV+ ዙሪያ ገንቢ አስተያየት ካለ እቀበላሁ፡፡ሙሉ በሙሉ ችግሩን መቅረፍ ባንችል አንድ ወይ ሁለትም ቢሆን ትዳር ቢያገኙ ትልቅ ነዉና በተቻለን እንታገል እንረባረብ ...የነገን ማን ያቃል በጣም ከባድ ኬዝ ነዉ እናም  እስኪ HIV+ የሆኑትን ቀረብ ብላችሁ የተወሰነ ለመረዳት ሞክሩ እየሳቁ ብዙ የሚደብቁት ችግር የሙራል የሳይኮ ጉዳት ብቸኝነት ተስፋ መቁረጥ ተሸክመዉ ነዉ የሚዞሩት ወላሂ ብዙዎች ተስፋ የቆረጡ ናቸዉ

ከጎናቸዉ ልንሆን በሀሳብ ልንረዳቸዉ ይገባል ..ብዙዎች ሲወለዱ ከቤተሰብ ነዉ የሚይዛቸዉ ወደዉ ያልተቀበሉት በሽታ ነዉ እናም በሀሳብ ያለንን በመርዳት ትዳር በማፈላለግ ጭምር ከጎናቸዉ እንሁን

አስተያየት ለመስጠት👇👇👇
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጎዳና ላይ ኢፍጣር ደረሰ
        አሚር ሰይድ
     
አሰላሙ አለይኩም እንዴት ናችሁ
በፊት በልጅነታችን መድረሳ ቁርአን በምንቀራበት ጊዜ ከኢድ አልፈጥርና ከኢደል አድሀ በላይ ለልጆች የምንወደዉ የሚበላበት የሚጠጣበት
መድረሳ መስጂድ ዉስጥ ነሺዳ ፕሮግራም አዘጋጅተን የምንማማርበት በአል የመዉሊድ በአል ነበር...በልጅነታችን ለብዙ አመታት መዉሊድ በአልን በደስታ እናከብር ነበር...እድሜያችን በሰለ ዲነል ኢስላምን ሰዉ ማወቅ ሲያስተነትን ወደ ቁርአን ሀዲስ ስናዳምጥ ለስልጣን ብለዉ ሳይሆን ለአላህ ለዲነል ኢስላም ብለዉ የሚያቀሩ የሚያስተምሩ ዳኢዎች ኡስታዞች መውሊድ ሀራም መሆኑን በማስረጃ በማስደገፍ ሲነግሩን ትክክል ይሄ ቢድአ ነዉ በመዉሊድ ምክንያት ወደ ተለያየ ሀገር እየተሄደ ፈሳድ ዚና ይበዛል ሺርክ ይሰራል ተብሎ በማስረጃ አስተማሩን ሰሚዕና ወአጦዕና ብለን ብዙ ሰዉ መዉሊድን ቤተሰቦቻችን ሳይቀር ማክበር አቆምን አልሀምዱሊላህ

ዛሬስ?? የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተብሎ ከመዉሊድ የማይተናነስ ችግር ይዞ መጥቷል፡፡

መቼም አሁን ላይ ስንት አሊም መሻይሆች ባሉበት ሀገር እንደኔ ያለዉ ጃሂል መናገር መፃፍ አቅሜ ባይፈቅድም ግን እያዩ ማለፉ ብዙም አልተዋጠልኝ ይህ ትዉልድ ለወደፊት በረመዳን አንድ ቀን በየአመት የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተብሎ በዲን በኢስላም የሌለ ቢድዓ አይታወቅም እኛም ሙተን የሚቀጥል የዉመል ቂያማ ድረስ ሊደርስ ይችላል መቼም ዲነል ኢስላምን አላህ ይጠበቀዋል ግን
ለብዙ አስርት ወይ መቶ አመታት ሊቀጥል ይችላል...
ግን በኛ ዘመን መጀመር አሳፋሪ መሆኑን ልናዉቅ ይገባል👌👌

ብዙ ሰዎች የጎዳና ኢፍጣርን በሁለት ምክንያት ይደግፋሉ
➊ የሙስሊሙን አንድነት ለማጠናከር በሚል
➋ የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች መንገዱን አደባባዩን እነሱ ብቻ ለምን ይጠቀማሉ እኛም እንጠቀም አይነት ነዉ፡፡

☞ብዙ ሰዎች አንድነትን ለማጠናከር ሲባል የቱ አንድነት?? ሀብሀብ ተምር በመንገድ ላይ ተበልቶ ነዉ እንዴ ስንት አሊም በተለያዩ የዲነል ኢስላም ነገሮች ያልተስማማበትን በጎዳና ኢፍጣር ላይ አንድነት የሚመጣዉ??? ወይስ የአደም ዘር ወንዱም ሴቶም በአደባባይ ሲያፈጥር ነው እንዴ አንድነት የሚባለዉ??
☞ የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች መንገዱን አደባባዩን እደተጠቀሙበት ነዉ የሚሉ አሉ...አዎ ይጠቀሙ እኛ ከእነሱ ይሄን መዉረስ የለብንም ...አላህም በቅዱስ ቁርአኑ በዱንያ እንደሚደሰቱ ነግሮናል እንደፈለጉ ይደሰቱ ይጨፍሩበት... ይልቅ እኛ በእነሱ ከምንቀና ስንት ቁርአን ሀፊዞች ዳኢዎችን ኸይር ስራ የሚሰሩን በንከተል ይሻላል እንጂ ሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች እግር በእግር መከታተል ትርፉ ቡሀላ ጥፋት ነዉ፡፡

⚡️⚡️ በ2013  የሌላ ሀይማኖቶች ሙስሊሙን ለመጨቆን ትንሽ ተንቀሳቅሰዉ ስለነበር በጎዳና ማፍጠሩን እኛም በሀገራችን ይመለከተናል ኸይር ሆነ ጎዳና ላይ ማፍጠሩ
አምና 2014 ተደገመ በየሀገሩ በአደባባይ ተፈጠረ
ዘንድሮ 2015 ደግሞ ይሄዉ ለሶስተኛ ዙር በአደባባይ ይፈጠራል፡፡ እኔ በ2013 በ2014 አብሬ የዚህ አደባባይ ኢፍጣር ተሳታፊ አጅር ያለዉ ይመስል ስራም ሰርቻለሁ ግን ዘንድሮ በዚህ የጎዳና ኢፍጣር አልሳተፍም፡፡ ለምን አምና የጎንደር ሙስሊሞችን አንርሳ በዚህ የጎዳና ኢፍጣር መዘዝ ብዙ ሙስሊም ወንድም እህት እናት አባቶቻችን ተገለዋል ቆስለዋል የአካል ጉዳተኛ ሁነዋል ንብረታቸወ ተዘርፏል ክብራቸዉ ተነክቷል እናም ዘንድሮ የጎዳና ኢፍጣር በነዛ የጎንደር ሙስሊሞች በሞቱት በተጎዱት ላይ በደል መፈፀም ነዉ፡፡ በዚህ በጎዳና ኢፍጣር ላይ በአይኔ ያየሁት ችግር
☞ወንድና ሴት ይቀላቀል ፊት ለፊትም አብሮ ብዙ ሰዉ ያፈጥራል ከአጂ ነቢይ ጋር
☞በዚህ ጊዜ ሴቶች እንደ በአል አርገዉ ነዉ ከቤት የሚወጡት ኑሮ ተወዶ ለራሱ ያልተዉትን ኮስሞቲክስ
ፌር ተቀብተዉ በቃ ለትዳር ፍለጋ ለመጀናጀን ነዉ የሚወጣዉ 70%ሴቱ
☞ በዚህ ጊዜ ዚናም የሚሰራ ሊኖር ይችላል..ወይም በዚህ ቀን ስልክ የሚቀያየረዉ ብዙ ስለሆነ በትዳር ስበብ የዚና መስመር ሊጀምሩ ይችላሉ
☞በtiktok በfacebook በማህበራዊ ሚዲያ የሴቶች የወንዶች ፎቶ ጥልቅልቅ ብሎ ሚዲያ ሲያጨናንቅ አይተናል ..ሴቱ የሚያደርገዉን የሚይዘዉን የሚጨብጠዉን አጥቶ ነበር ሴትነት ትርጉሙ እስከሚጠፋቸዉ
☞ ጎዳና ኢፍጣሩ ሰዉ ሲበተን በዘንድሮ ዘመናይ ዘፋኞች ይቅርታ ሙነሺዶች ለማለት ነዉ በእነሱ ወንድ ሴት ተደባልቆ ሲጨፍሩ አምና የታዘብነዉ ነዉ..አሁን የአምናዉ የአደባባይ ኢፍጣር video በእጄ አለ ...በጣም አሳፋሪ ነዉ ከምር

📕የሙስሊም አንድነት የሚባለዉ ወንድ ሴት አብሮ በመንገድ ሲያፈጥር ሲጋፋ ነዉ እንዴ?? ጎበዝ

📘 አሁን ይሄ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ከመዉሊድ በምን ተለየ????

ዘንድሮ ስንት ሙስሊም በኑሮ ዉድነት በርሀብ በሚፆሞበት በአገሪቱ ወቅታዊ ችግር ምክንያት ስንቶች ከአገራቸዉ ከመኖሪያቸዉ ተፈናቅለዉ መጠለያ ዉስጥ የሚበላ የሚጠጣ ከእርዳታ ብቻ እየተቀበሉ ረመዳን በሚያሳልፉበት ጊዜ እነሱን መርዳት ሲገባን እንዴት በዚህ አደባባይ ኢፍጣር ሰዉ ጠግቦ ላይበላ ፈሳድ ወንጀል ይሰራል???

የሚገርመዉ አምና ለጎዳና ኢፍጣሩ ላይ የአህባሽ አመለካከትን የሚያራምዱ አቂዳ ተከታዮች በብዛት መጥተዉ አይቻቸዋለሁ...አህባሾች ለደአዋ ለዲነል ኢስላም ለመመካከር ሲጠሯቸዉ አይመጡም ነገር ግን ለእዚህ ለጎዳና ኢፍጣር መጡ እነሱ የተሻለ ኸይር ነገር የሚሰራ ቢሆን እንደማይመጡ እርግጥ ነዉ ግን ኢፍጣሩ ሲያበቃ ለብቻቸዉ ሁነዉ በራሳቸዉ አመለካከት አቂዳቸዉን በነሽዳ ወንድና ሴት ተደባልቀዉ  ሲያስተላልፉ ነበር ...ለደአዋ ለኢስላም እንወያይ ሲሏቸዉ የማይመጡ እንዴት ለአደባባይ ኢፍጣሩ መጡ???
⚡️⚡️ አንዳንዶች አይታወቅም አዲስ አበባ ከአፍሪካ ወይ ከአለም አንደኛ አደባባይ ኢፍጣር ክብረ ወሰን ለመበጠስ ልትሉ ትችላለሁ እሺ እንደ ተልካሻ ዲነል ኢስላም የማያቀዉ የሚያሳምን የሚመስል መልስ ልታመጡ ትችላላችሁ ግን በአደባባይ ኢፍጣር ነዉ ወይስ በቁርአን ሀፊዞች ቁጥር ብዛት በተዉሂድ ክብረ ወሰን በጠስን ተብሎ ቢወራ አይሻልም???
እሺ አዲስ አበባ እንደዚህ ከተባለ ሌሎች ከተማ ለምን ምክንያት ማድረግ አስፈለገ???
ከምር ግን ሊታሰብበት ይገባል...እኛ ለልጃቻችን ለትዉልድ ይሄን ማዉረስ የለብንም....የኛ ልጆች የልጅ ልጆች ይሄ የአደባባይ ኢፍጣር በነብዩ ሰዐወ በሱሀቦች በአራቱ ኸሊፋ ጊዜ የሌለ መቼ ተጀመረ ሲባል በኛ ዘመን በእኛ ትዉልድ ነዉ ብሎ መነገሩ ታሪክ ላይ መፃፉ አግባብ አይደለም


⚡️⚡️ መዉሊድን ሀራም ነዉ ለማለት ስንት ኡስታዞች ኡለሞች መዉሊድ በዚህ ዘመን የተጀመረ ነዉ ብለዉ እንዳላስተማሩ ዛሬ ገና በ2013 የተጀመረን አንድነት የሚመስል ፈሳድ ለምን መከልከል ተሳናቸዉ???
የዚህ በጎዳና ኢፍጣር ሰበብ የሚፈጠር ወንጀል ማዕሲያ እስከ ቆየበት ዘመን ድረስ የኛ አስተዋፆኦ እንዳለበት ለትዉልድ መጥፎ ነገር እንዳላስተላለፍን ልናወቅ ይገባል👌👌


አሁን ላይ አሊሞች መሻይሆች የመስጊድ ኢማሞች  አሊሞችም መሻይሆችን ስልጣንን ላለማጣት ፍራቻ
የመስጊድ ኢማሞችም ይቺኑ የወር ደመወዛቸዉን ላለማጣት ፍርቻ ቢድአ ወንጀል መሆኑን እያወቁ ዝም ብለዋል የሚከለክል ስለሌለ ይሄን ፁሁፍ ያነበበ ሰዉ ቁርአን ሀዲስ አንፃር አስበን ህሊናችንን ዳኛ አድርገን
እኛ ባለመሄድ የዚህ ለወደፊት ብዙ አመታት የሚቀጥል እንደ መዉሊድ ቢድአ የሆነን የዚህ የአደባባይ ኢፍጣር ባንሄድ ጥሩ ነዉ፡፡
ደግሞ ይሄን የሚያካሂደዉ 90% ወጣቱ ነዉ👇👇
እባካችሁ አሊሞች ሸይሆች  እኛን ወጣቶች በቁርአን በሀዲስ ኮትኩታችሁ ለነገ ትዉልድ ማስተላለፍ ቢያቅታችሁ እንደዚህ ፈሳድ የሆነን በየአመቱ ተከታይ አታድርጉን እባካችሁ ወጣቱን የማይጠቅም የማይጓዳ ጀነሬሽን ባለማድረግ ተባበሩን🙏🙏🙏


የተወሰነ ሰዉ ባይሄድ አሁን ባለቸዉ አቋም የሚቀር የሚቆም አይደለም
ግን አለመሄድ የባለቤቱ ወሳኔ ነዉ...አምና ታስታዉሱ ከሆነ ደሴ በተደረገዉ የጎዳና ኢፍጣር ከአየሁ ቡሀላ
በዛዉ በተደረገ ቀን ከአሁን ቡሁላ ላልሄድ ብየ ምያለሁ....ከዘንድሮ ጀምሬ አደባባይ ኢፍጣር አልሄድም
ይሄን ያነበበ አስተንትኖ ነገሮችን ከግራም ከቀኝም ከሆላም ከፊትም ከሁሉም አቅጣጫ ተመልክቶ በየአመቱ ለወደፊት ለሚካሄድ ኢፍጣር ራሳችሁን ብታገሉ ባይ ነኝ ...የአንድ የሁለት ሰዉ መቅረት ይሄን የአደባባይ ኢፍጣር ለማስቆም አቅም ባይኖረዉም ግን ለወደፊት በየአመቱ ለሚፈጠር ቢድአ ተባባሪ አለመሆን አንድ የሙስሊም ግዴታ ነዉ





ነገር ግን አንዳንድ ደጋግ የአላህ ባሮችና ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር በየጎዳናዉ የተቸገሩን ማፍጠሪያ የሌላቸዉን በየጎዳናዉ ያስፈጥራሉ እንደዚህ ያሉትን ደጋግ ባሮች ጀመአዎች ለአላህ ብለዉ የሚሰሩን አላህ ንያቸዉን አጅራቸዉን እጥፍ ድርብ ያርግላቸዉ ይሄ መበረታታት ያለበት ነዉ...ነገር ግን የአደባባይ ኢፍጣር ተብሎ ፆታ መለየት እስከሚያቅት  ወንድ ሴት ተደባልቆ ታላቁ በአይኑ የተለየ ይሄን ያህል ሜትር  ክብረ ወሰን በጠስን እያሉ በዲን ስበብ ፈሳድ ባይበዛ ኸይር ነዉ፡፡


ኸይር ፅፌ ከሆነ ከጀሊሉ ነዉ መጥፎ ወይ ስህተት ፅፌ ከሆነ ከሸይጧን ነዉ አዉፍ በሉኝ ስህተት ከሆነም አሳማኝ ምክንያት ከአገኘሁ ስህተት ነዉ ብየ ፁሁፉን ከቻናል እሰርዛለሁ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ዛሬ አንድ ነገር ላስቸግራችሁ ነዉ
ሙስሊም በጓንታናሞ እስር ቤት የሚለዉ መፅሀፍ የዛሬ አምስት ስድስት አመት በፊት ገበያ ላይ ነበር
እኔም ይህ መፅሀፍ ነበረኝ ግን አበድሬዉ ማን ወስዶ እንዳስቀረብኝ አላቅም ሆነም ቀረ አሁን ላይ ይሄን መፅሀፍ ገበያ ላይ ማግኘት አልቻልኩም፡፡

ደሴ ሁሉም መፅሀፍት መደብር አዲስ አበባም
ኮምቦልቻ ባቲ ሀርቡ ከሚሴ ሀረር አዋሳ አስፈለኩት መፅሀፉ አሁን አይታተምም ገበያ ላይ የለም ሆነ በየአቅጣጫዉ መልሱ፡፡

አሁን ያለዉ አማራጭ ከሙስሊም መፅሀፍ መሸጫ መደብር በፊት አምጥተዉ ያልሸጡት ካለ በአላችሁበት ከተማ አስታዉሳችሁ ፈልጉልኝ በተገኘዉ ዋጋ እገዛለሁ

ወይም የዛሬ አምስት ወይ ስድስት አመት በፊት ገዝታችሁ እቤት ያስቀመጣችሁ ካላችሁ  ለአንድ ወር ብቻ አበድሩኝ ወይም
በተመቻችሁ ዋጋ ሽጡልኝ
መፅሀፉን ፍለጋ 8ወር አለፈኝ
ከመፅሀፉ የሚዘጋጅ ቃል የገባሁት ነበር እናም
አዘጋጅልኝ ብለዉኝ ነዉ...ከዛ መፅሀፍ የሚዘጋጅ በቻናል ይፓሰታል..በሳምንት የሚበተን ወረቀት ላይም የሚዘጋጅ ነዉ ...የሚዘጋጀዉ በጣም ለሙስሊም ትዉልድ የሚጠቅም ራስችንን የምንፈትሽበት ነዉ፡፡መፅሀፉን እናንተ ባላችሁበት ከተማ ብቻ ጠቁሙኝ እኔ ራሴ አመቻችቼ ደሴ አስመጠዋለሁ፡፡ በቻላችሁት አቅም ይሄን መፅሀፍ በመፈለግ ተባበሩኝ በተባለዉ ዋጋ ለመግዛት ዝግጁ ነኝ ብቻ መፅሀፉ ይገኝ
መፅሀፉን በፊት ገዝቶ ያለዉ ካለ ወይም ገበያ ላይ ያገኘልኝ በዚህ Bot
አሳዉቁኝ
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
መፅሀፉን ገበያ ላይ ወይም ሰዉ ከሰዉ ተጠያይቆ ያገኘልኝ ወላሂ ባለዉለታየ ነዉ በዚህ bot አሳዉቁኝ
👇👇👇
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
አሚር ሰይድ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ???
      አሚር ሰይድ

       አሰላሙ አለይኩም እንዴት ናችሁ
ዛሬ ላማክራችሁ የፈለኩት አንድ ግራ የሚያጋባ ጥያቄ ከተወሰኑ ቀናታት በፊት በቻናል መጥቶልኝ ነዉ፡፡ እስከዛሬ በቻናል የሚመጡትን ጥያቄዎች ለብቻየ መፍትሄ መስጠት ችዬ ነበር ይሄ ግን ትንሽ ከበድ ብሎኝ ነዉ

እናንተ ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?? በጣም ከባድ ስለሆነ ነዉ ከምትሰጡት አስተያየት አንዱ ከአንዱ ስለሚሻል መፍትሄ ሀሳብ ልቀበልና ለባለታሪኳ እልከዋለሁ


✏️✏️ ምን መሰላችሁ እሷና እሱ ለአምስት አመት በላይ ይዋደዳሉ ግን በመሀላቸዉ እየተዋደዱ አንድ ላይ ለመሆን በጣም ሰፊ ክፈተት ነበር ያንን ሰፊ ክፍተት ትንሽ ጠበብ አድርገዉ የዛሬ 3 አመት በፊት ጀምሮ አንድ ላይ ለመሆን ጥረት ያደርጋሉ ግን ያበፊት የነበረ ሰፊ ክፍተት ግን የእሷ ቤተሰቦች ከተስማሙ ቡሀላ ወደ ትዳር ለመግባት 90% ፕሮሰስ ተጨርሶ በተለያዩ ምክንያቶች በእሷም በእሱም በዛ በበፊት ሰፊ ክፍተት ምክንያት አንድ ላይ ሳይሆኑ ቀሩ...ሁለቱም ግን ፍቅር አለባቸዉ 5 አመት ያህል ይዋደዳሉ ስሜቱን ተረድታችሁታል???ሁለቱም በመለያየታቸዉ በፍቅር በትዝታ ተጎዱ ብዙ ወራትን ሳያወሩ ቀሩ፡፡  ግን ህይወት ነዉ እሱ የሌላ ሆነ አጭቷል...እሷ ደግሞ ሌላ ትዳር ቢመጣላትም አይሆንም አሉ ቤተሰቦቿ ፡፡

ባለታሪኳ እንደነገረችኝ አሁን ዋናዉ ችግር እሱ አጭቶ የሌላ ሁኗል በቅርቡ ወይም 2016 ላይ ያገባል እሱ እንደ አጨና እንደሚያገባ አዉቃለሁ

..,ግን ማወቅ ያለብን እሱም ሌላ አጭቶ ሊያገባ ተዘጋጅቶ  ልቡ 5 አመት የሚወዳት እሷ ጋር ነዉ...

  የእሱ እንደልሆን  አዉቃለሁ ነግን ፍቅር የሚባል ህግ አስገድዶን  አሁንም ድረስ እያወራን ነዉ አለችኝ፡፡

መፍትሄዉ እኔም እሱም እናቀዋለን
☞የመጀመሪያዉ እሱ ጋር ማዉራት ማቆም ነዉ

እሱንም ወስኛለሁ....ከአሁን ጀምራችሁ ማዉራት አቁሙም ሊሆን ይችላል ግን አለማዉራቱ በብዙ ምክንያት ጉዳት አለዉ እንደምትሉ አቃለሁ ግን ለጊዜዉ በቴሌግራም ብቻ ማዉራታችን አይቀርም የምናወራዉም አልፎ አልፎ ነዉ እያወራን ለወደፊት ለሚያገባት ሚስቱ ነዉ የምጨነቀዉ የወደፊት ህይወቱን እንዲያስተካክል ጭምር እየታገልኩ ነዉ ሁሉን በሆዴ አምቄ ይዤ
ከአገባ ቡሀላ በአላህ ምያለሁ ላላወራዉ ለእሱም ለኔም ህይወት ስል ላያወራኝ ወስኗል ፡፡ በተጨማሪ
እሱ ከሚኖርበት ሀገር ለመቀየር ወስኛለሁ ...አገሩንም ለመቀየር አመቻችቼ ጨርሻለሁ 2016 መስከረም ላይ እሱ ከሚኖርበት ከተማ እለቃለሁ፡፡ግን እሱ የሚኖርበትን ከተማ ስለቅ ከጊዜ ብዛትም ቢሆን ማግባቴ እኔም የሌላ እሆናለሁ ይሄ ግዴታ ነዉ ህይወት እስከ ሆነ ድረስ

☞ሁለተኛዉ አለመገናኘት ነዉ ግን እሱ ጋር አንድ ሰፈር ነን መገናኘታችን አይቀርም ግን መንገድ ላይ ብንገናኝም ምንም እንዳልተፈጠረ ስቀን በአየር ላይ ሰላም ተባብበለን እንተላለፋለን፡፡

የሚገርመኝ እኔም የእሱ አይደለሁ እሱም የኔ አይደለም
ግን ሁለታችን ስናወራ የሆነ ደስ የሚል የተረጋጋን እንሆናለን የምናወራዉ ግን በቴሌግራም ብቻ ነዉ የኔ አለመሆኑን ከአወኩ በስልክም አዉርተን አናቅም፡፡
ይሄን ስላችሁ በቴሌግራምም ማዉራት አቁሙ ልትሉ ትችላላችሁ ግን እኔ ያማከርካችሁ እንደዚህ እንድትሉኝ አይደለም
ፍቅር ከባድ ነዉ ግን ከፍቅር በላይ የሚከብደዉ ትዝታዎቹና እሱ የሌላ ሁኖ ማየቱ ነዉ😔
መፍትሄ ሀሳቡ እኔና እሱም እናቀዋለን አለማዉራት ነዉ ግን ሞከርን ሞከርን ሞከርን አልቻልንም ቀን በቀን ባይሆንም በተወሰነ ቀናቶች ልዩነት በtg እናወራለን ያዉ እንደበፊቱ አይነት ወሬ አይደለም
ኖርማል ወሬ ነዉ፡፡


⚠️⚠️ አሁን ከእናንተ የምጠይቃችሁ ሀሳባችሁን እርዳቻችሁን የፈለኩት እነዚህ እታች በቅደም ተከተል በጥያቄ መልክ ካቀረብኳቸዉ ጥያቄዎች እላይ ካነበባችሁት ፁሁፍ ጋር አመዛዝናችሁ እንድትመልሱልኝ ነዉ ለወደፊት እሱ ከአገባ ቡሀላ እኔም ሀገር ከቀየርኩ ቡሀላ እሱም ለሚስቱ እኔም ለወደፊት ህይወቴ መስመር እንድናሲዝ በሀሳብ እንድትተባበሩን ነዉ፡፡


➊ በዚህ ቻናል ዉስጥ እየተዋደዳችሁ ግን በቤተሰብ አይሆንም ወይም በተለያዩ ምክንያት የምወዱትን ያጣችሁ...ግን ወይ የማይወዳችሁን በቤተሰብ ያገባችሁ ሴቶች ካላችሁ የትዳር ህይወት እንዴት ነዉ??የሌላ ሁኖ መልመድ ይቻላል ወይ?? ትዳር ላይ ሁኖ የበፊት ፍቅር ያስቸግራል አያስቸግርም??
የሌላ የሆናችሁ ወንዶች የምወዳት ልጅ ሚስትህ ጋር ሁነህ በሀሳብህ በህልምህ እየመጣች አላስቸገረችህም?? ከረሰሀት ጥሩ ግን ሳትረሳት በሀሳብህ እየመጣች ትዳርህን እንዴት እያስሄዳችሁ ነዉ??
አስተያየታችሁን በዚህ ይላኩልኝ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

➋ እንደዚህ አፍቅራችሁ ያጣችሁ የዚህ አምስት አመት ነዉ...ከአምስት አመት ወይ ከአምስት አመት በታችም ይሁን የምወዱትን ሌላ ሲያገባ ስሜቱን ታቁታላችሁ ከዛ ስሜት ወጥታችሆል??አሁን እሱ የሌላ ሲሆን ወልዶም ሊሆን ይችላል ላይወልድም ይችላል ምን ተሰማችሁ???
አስተያየታችሁን በዚህ ይላኩልኝ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot


➌ አሁን እሱ የሌላ ለመሆን ጨርሷል ሽማግሌ ልኮ የሰርጉን ቀን ቆርጧል...እሱ ለወደፊት እንዳይቸገር ራቂዉ እንደምትሉኝ አቃለሁ እኔም ያሰብኩት ነዉ ግን እሱ እሷ ጋር ጥሩ የተረጋጋ ህይወት እሷ ጋር ተዋደዉ ልጅ የልጅ ልጅ እንዲኖረዉ የዘወትር ዱአየ ነዉ
እሱም ለኔ የሚያስብልኝ ለወደፊት ጥሩ ህይወት እኔ የሚወደኝን አግብቼ የተሻለ ኑሮ እንድኖር ይፈልጋል ኢንሻ አላህ ፈጣሪም ያገዝናል ከአላህ ተስፋ አንቆርጥም...ግን በዚህ ላይ ሁለት ጥያቄ ለአእምሯችሁ ልስጣችሁ በተለይ አግብታችሁ ያላላችሁ ወይም የሰዉ ታሪክ ከሰማችሁት አንፃር
☞አንተ ትዳር ነዉ ብለህ ሌላ የምወዳት እያለች አግብተህ ከእሷ ዉጭ ሌላ ሴት አይታይህም ነበር ግን የአገባሀት ሚስት በፍቅር በእንክብኬቤ የድሮ ፍቅረኛህን አስረስተሀለች??? አልሀምዱሊላህ እሷ ቀርታ ፈጣሪ እሷን የሰጠኝ ብለህ አመስግነሀለል??ከአመሰገንክ ማሻ አላህ ግን እንዴት ልታስረሳህ ቻለች??

⚡️እሺ በተቃራኒዉ እንየዉ የአገበሆት ሚስት በፊት ቤተሰቦቿን ጠይቀህ እምቢ የተባልከዉ ጋር ስታወዳድራት የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት አላት ያንን ሁሉ ሸፍነህ እንዴት እሷ ጋር አብረህ  እየኖርክ ነዉ??? ልጅም ወልደህ ይሆናል ግን እንዴት ሳትወዳት አብረህ ወልደህ እየኖርክ ነዉ??
ፍቅር ከትዳር ቡሀላ ነዉ ይባላል ግን ከትዳር በፊት የነበረ ፍቅር ያስቸግራል እንዴት በአዲሷ ሚስትህ በፍቅር የተጎዳዉን ልብህን አከምክ??
በዚህ አስተያየትዎን ይፃፉ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

☞እሺ አንቺስ አሁን አግብተሽ ልጅ ወልደሽም ይሆናል....የምወጅዉን ቤተሰብ በሚያሳምንም በማያሳምን ምክንያት አጣሽዉ..ግን እሱ የትዳር ስበብ
ሲያደርስ ከጎኑ ሁነሽ በነበር የመሳካቱ ቻንሱ ሰፊ ነበር እንበል ...እናም ይሄ ምነዉ ሰበቡን አድርሼ በነበር ብለሽ ከአጣሽዉ ቡሀላ ልትቆጭ ትችያለሽ ግን ህይወት ነዉ እኔም ሌላ አገባለሁ በቅርቡ ኢንሻ አላህ ግን የአገባሽዉ ባል እንክብካቤ ሁኔታ በፊት የምወጂዉን አስረስቶሻል??አልሀምዱሊላህ እሱ ቀረብኝ ለኸይር ነዉ እሱን የሰጠኝ ብለሻል???👇👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሙነሺዶች

ዘንቦል ዘንጠል ዘንፈል ዘንፈልፈል ወዝወዝ ሲሉ 🙃 አጃቢዎቹንም ተመልከቱ ፌመስ ለመሆን ጥረትና ዉጥረት...

ቆይ ግን እሽክምክም እሽክምክም እያለች ከምዘፍነዉ ዘፋኝ በምን ተለዩ🙄



የሚገርመዉ ዘንድሮ ሙነሺዶች ብዙዎቹ በረመዳን መካ ኡምራ አድርገዋል...በአዳማጩ በyoutube ብር አግኝተዉ መካ አሳለፉ...
አዳማጩ ግን ቁርአን መሸምደድ መቅራት ዚክር ማድረገዉ ትተዉ በተለይ ሴቱ ወይኔ ድምፁ ሲያምር የእሱን ድምፅ ሳልሰማ መዋል ከብዶኛል😇 ብለዉ የእነሱን ድምፅ ካልሰሙ ራሳቸዉን የሚያማቸዉ የሚያቃዣቸዉም አሉ... አንዳንድም የምታለቅስ አለች

ሀያቴን ለርሶ ብያለሁ ጀባ ይሉሀል ይሄ ጀመአ🙂
ተመልከቱ ካሜራ ማን

የሙስሊም ሴቶች ለእስልምና መስራት አለባቸዉ በሁሉም ነገር ሴት መጨቆን የለባትም ይሉሀል
ድንበር ያለፈ ለሴት ልጅ መቆርቆር መምሰል መጨረሻዉ ዉጤቱ ይሄ ነዉ......

አጂ ነብይ ጋር በዲን ስም አብሮ መሆን...
በአላህ መንገድ ሲታገል ከርሞ ወደ አንደሉስ ምድር መናገሻ ከተማ ኮርዶቫ ሲዘልቅ ዕለቱ ዒድ ጠዋት ነበር። ሰራዊቱ በፈረሶቻቸው ላይ ተፈናጠው በድካም የሚንጠፈጠፈውን ላባቸውን ከግንባራቸው ላይ እየጠራረጉ አቧራ ባጨማለቀው ልብሳቸው ኢድ ወደ ሚሰገድበት ሜዳ በማቅናት ላይ ሳሉ ነበር አንዲት እድሜዋ የገፋ አዛውንት ከሡልጣን መንሱር ፊት ቆማ የፈረሱን ልጓም ይዛ ከመንገዱ በማስተጓጎል እንዲህ ያለችው:-


"በዛሬው የዒድ ቀን ከእኔ በቀር ሁሉም ሙስሊሞች ደስተኞች ናቸው"
ሐጂብ መንሱር ንግግሯን ሲሰማ ደነገጠ "ለምን?" ሲልም ጠየቀ።
ዕንባ ባቀረረው ዓይኗ እየተመለከተችው እንዲህ አለችው "በረባህ ምሽግ ከመስቀል ጦረኞች ጋር ሲፋለም የተማረከ አንድ ፍሬ ሙጃሂድ ልጅ አለኝ እሱ በጠላት እስር ቤት ውስጥ ሆኖ እንዴት መደሰት ይቻለኛል?"

ዘመኑ 380 ዓመተ ሂጅራ ግዛቶች በሐጂብ አል መንሱር ይተዳደሩ ነበር። የአንደሉስ ኢስላማዊ መንግስት በጥንካሬና በከፍታ ማማ ላይ የደረሰበት ወርቃማ ዘመን! የፉቱሐትና የዘመቻ የፍትህና የእኩልነት ጊዜ!

   ሐጂብ ንግግሯን ሲሰማ በፍጥነት ፊቱን ወደሠራዊቱ አዞረ። የፈረሱን ልጓም አጥብቆ ያዘና በጂሃድ ሜዳ የአፈር ትቢያውን ገና ላላራገፈው ሙጃሂድ፣ ከድካም ጀርባውን ላላሳረፈው ሠራዊት እንዲህ ሲል ትዕዛዙን አስተላለፈ "ከፈረሳችሁ ጀርባ እንዳትወርዱ" አለ።

   የፈረሱን ልጓም እየጎተተ ጀርባው ላይ እንደተፈናጠጠ ወደ ረባህ ምሽግ ሰራዊቱን ይዞ ገሰገሰ። የአሮጊቷን ልጅ ጨምሮ ሙስሊም እስረኞችን አስፈትቶ ከተማዋን በድል ከፍቶ ወደ አንደሉስ ምድር ተመለሰ።

ይህ ስለኢስላም መስራት በማንደክምበት ዕለት የተከሰተ የጀግንነት ታሪካችን ነው።


ለሁላችሁም ኢድ ሙባረክ ብያለሁ
ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን ሩሕ እስኪወጣ ጌታችንን የምንታዘዝ ያድርገን....ከረመዷን በፊት ወደነበርንበት አመፅና ወንጀል የማንመለስ ያርገን
....ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን  ሩሀችን   እስኪወጣ ጌታችንን የምንታዘዝ ያድርገን ያረብ

የቻናል ቤተሰቦች መልካም በአል ተመኘሁ❤️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልብሽን ምክንያት እየሰጠሽ አታድክሚዉ
ዩምና ሙሀመድ

እራስሽን ልክ እንደ ሙሳ ቀይ ባህር መሀል ላይ አኑሪው ከጀርባሽ ፊርአውንን እሚያክል ጠላት ወይ ችግር አለብሽ ከበላይሽ የተሰነጠቀ ባህር እሚያክል አንቺ ላይ ሊደርስ እሚችል ችግሮች ተከምረው ታይተውሻል ወደ ጎን አትይም መካከል ላይ ነሽ ብቻሽን አይደለሽም በአንቺ ስር ያሉ የብዙዎችን ህይወት ከአላህ በታች ይዘሻል ....ልክ ሙሳ ተከታዮቹን እንደያዘው ነፍሴን ብቻ አይልም ነፍሳችንን እንጂ ከእራሱ ሩህ በላይ እሚያስጨንቀው የተከታዮቹን ነገር ነው ምናልባትም አንቺ የብዙ ሀላፊነት ባለቤት ሆነሽ ይሆናል፡፡

ታዲያ ሙሳ ከባህሩ አልወጡምን? በየትኛው መንገድ? ከፊት ለፊታቸው በምትታያቸው አንድ መንገድ ያቺን መንገድ እስኪያገኟት ድረስ ወደ ሗላ አልዞሩም ወደ ሗላ ችግራቸው ነው ያለው ፊት ለፊታቸው ግን ነፃነት ከብዙ የነፍሶች ሀላፊነት ማረፍ ሀቀኝነትን ብቻ ቡዙ ተአምሮችን ይዟል ያቺ የታየቻቸውን መንገድ በጀሊሉ ፍቃድ ደረሱባት ዞር ብለው ወደ ችግሮቻቸው ሲያዩ ግን ቢወርድ ሊያጠፋቸው እሚችለው ባህር ሲከተላቸው የነበረውን ችግር ድምጥማጡን አጠፋላቸው

አንቺም ያሉብሽን ችግር እስክታልፊያቸው ዞረሽ አትመልከቻቸው ይደርሱብኛል እምትያቸው ችግሮችሽ ምናልባት የደረሱብሽን ችግሮች ማጥፊያ ናቸው ፡፡ መውጫሽን ተመልከቺ ግን ስለሁሉም ጌታሽን አጥብቀሽ ያዢው በእሱ ያለሽ እምነት ከልብሽ አድርጊው የተፃፈልሽ ሙሲባ በሙሉ ሊስትሽ አልነበረም የሳተሽ በሙሉ ሊያገኝሽ አልነበረም ልብሽን ምክኒያት እየሰጠሽ አታድክሚው

☞ አንቺ ማለት ሳትጠይቂው ለእሱ ባሪያው እንድትሆኚ የፈጠረሽ ባሪያው ነሽ
☞አንቺ ማለት ከስንት ሚሊዮን እህት እና ወንድሞችሽ ተመርጠሽ የተፈጠርሽ ፍጡር ነሽ
☞አንቺ ማለት በዱንያው እሳት ፈትኖሽ እንደ ወርቅ ሊያስከብርሽ ሊያስወድድሽ እሚያደርግ ጌታ ነው ያለሽ

>>> እናም ያኡኽታ ረህማኑን አጥብቂው የተጣበቀብሽ ይለቅሻል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሁንስ አትገረሚም???
ዩምና ሙሀመድ

ምን ያስገርመኛል መሰለሽ ሁሌ የረህማኑን አዛኝነት እኔ የእሱ ባሪያው እንድሆን የመሻቱ ስፋት በእኔ  መታወስ የፍላጎቱን ጥግ አስተውለሽው ይሁን?
እኔ ባላስታውሰው እኮ ሚጎድልበት ነገር የለም እሱ እኮ ስንት እሚዋደቁለት ባሪያዎች አሉት እሱ እኮ ምድር ላይ ያለች ትንሿ ጠጠር ሳትቀር የፈጠረ ጌታ እኔን ማስታወሱ አይገርምሽም?

^ ቢተወኝስ ቆይ ሲጀመር ባይፈጥረኝስ ስንት እህት እና ወንድሞቼን እናቴ ሆድ ውስጥ ባክነው እኔ መፈጠሬ ስለወደደኝም አይደለምን?
ታዲያ አይደለም የወደደኝ ጌታ የወደደኝ ሰው እኔ ላይ መብት የለውም እንዴ?
ምሳሌ ላንሳልሽ ምድር ላይ በጣም በጣም ከሚሳሱልኝ ሰዎች ውስጥ ከእናቴ ወይ ከአባቴ በላይ ፍጥረት የለም እኮ አይደል!! 
እስኪ ልጅኘታችንን ዞረሽ እይው ልጅ ናቸው በሚል ሀላፊነት የሚባል አልነበረብንም ሀላፊነት መውሰድን በትንሽ በትንሹ እንድንማር አደረጉን
አላሄዋም እስከ 15 አመት ወይም እራሳችንን እስክናውቅ ነፃነት ሰጠን ምንም ቅጣት እንደሌለብን አሳወቀን ለቤተሰቦቻችን ግን የኛን የመኮትኮት ሀላፊነት ሰጣቸው  አትገረሚም!!


.....ቡሗላ እንዳንደክም ግራ እንዳንጋባ እኮ ነው ከዛማ ልክ ስናድግ ቤተሰቦቻችን ለማስደሰት ውለታቸውን ለመመለስ እያልን ሀላፊነት እንዳለብን ሁላ ከእልጅነት እስከእውቀት  የለፉብንን  ለመመለስ ስንል እኛ ላይ መብት አላቸው እያልን እነሱን ለማስደሰት መብታቸውን ለመጠበቅ ደፋ ቀና እንላለን ታዲያ ያኡኽታ ይሄንን ሁላ ነገር አንቺ ካለነበርሽበት አስገኝቶ ጭራሽ እማያውቁሽ እማታውቂያቸውን ፍጡሮች እናት እና አባት ያውም ከእዝነት ጋር የለገሰሽ ጌታ አንቺ ላይ መብት የለውምን?

>>>>> ብርጭቆ ስትሰብሪ ሁላ እኮ እናትሽ ወይ ትቆጣሻለች ወይ ትመታሻለች እና ስለምን ሲባል የፈጠረሽ ጌታ በነገሮች ሲቆነጥጥሽ ቢጠላኝ ነው አስባለሽ?ምን ባደርገው ነው እያልሽ ከእሱ ጋር ግብግብ አስፈጠረሽ?

^^ደሞ እኮ በተከበረው ቃሉ ሲፈትንሽ እያላቀሽ  ስለመሆኑ አማኝ ስለመሆንሽ እንዲህ እያለ ነግሮሻል "አሊፍ ላም ሚም አሀሲበናሱ አዩትረኩ አመና ፈሁም ላዩፍተኑን"
^የሰው ልጆች አምነናል ካሉ ቡሗላ እንፈተናለን ብለው አላሰቡንም አልገመቱምን^ ይለናል አየሽልኝ ኡኽታ በእሱ ስለማመኔ ማመልከቻው ወይ ደሞ መለያው በሚያመጣልኝ ነገር መታገሴ ነው::
* ለትምህርት ፈተና ስል ስንቴ አነባለው ለሊት አዳር እያነጋሁኝ  እየተጨነኩኝ ካለፋሁኝ እንደምወድቅ አውቃለዋ ከወደኩኝ ደሞ ያኔ ለቤተሰቦቼ ተገቢውን ምላሽ አልሰጠሁም ማለት ነው የት ት ፈተናውን ማለፌ
ከእኔ በላይ ቤተሰቦቼ ያስደስታቸዋል አላሄዋም ሲሞክረኝ ወደእሱ እንድቀርብ አጥብቆ ይሻብኛል::

>>>>>አስተውዪማ የሆነ መስሪያ ቤት እራስሽን አስቀጥረሽ ሳዩው ከዛማ አሰሪሽ አንቺን ይወድሻል ሊያጣሽ አይፈልግም እንድትቀርቢው ይፈልጋል ምን እሚያደርግሽ ይመስልሻል?
በጣም ከምትፈልጊው እሱ ጋር ካለ ነገር ይቀንስብሻል ወይም ያስቀርብሻል ለምሳሌ ደሞዝሽን ግማሹን ወይም እሩቡን እሱ ጋር አስቀርቶ ቀሪውን ቢሰጥሽ እመኚኝ ቀሪውን ደሞዝሽ ፍለጋ አሰሪሽ ቢሮ ትመላለሻለሽ አሰሪሽም እሱ እሚፈልጋትን ሴት እስክትሆኚለት በመመላለስሽ እርካታን አግኝቶ ይቀመጣል::
____አላሄዋም ከአሰሪሽ በላይ ላንቺ እሚያስፈልግሽን ነገር ሲነጥቅሽ መርጦሽ ነው ወደእሱ እራስሽን እንድታዞሪ እየጠየቀሽ ነው ግን እኛ መመረጥን እምናውቀው ሁላ አይመስለኝም::
*ደሞ እኮ አያቆምም በቃ ተስፋ ቆርጫለው የፈጠረኝንም አስከፍቻለው ብለን ስናስብ እንዲህም አይደል የሚለን
"ቁል ያኢባዲየለዚነ አስረፋ አላ አንፉሲሂም ላተቅነጡ ሚን ራህመቲላህ ኢነላሀ ገፉሩን ረሂም"
(እናንተ በነፍሶቻቹ ላይ ድንበር ያለፋቹ ባሪያዎቼ ሆይ በአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ አላህኮ አዛኝና ማሀሪ ነው)
  ይለናል እሺ አሁንስ አትገረሚም?



አምፀነውም ወዶን በሞከረን ነገር ላይም እንዴት ብለን የእሱን መብት ለእራሳችን ሰጥተንበትም አሁንም ኑኑኑኑ ቅረቡኝ እያለን እኮ ነው::  ከእዝነቱ እንዳንሸሽ ይነግረናል ምን ያክል ለእኛ ቅርብ እንደሆነ ያሳውቀናል የእሱ እዝነት ትልቅ ስለመሆኑ ከእዝነቱ ያሻንን እንደምንወስድ እየወስድንም እንደሆነ
"ወኢን ተኡዱ ኒእመላሂ ፈላቱአዱሀ"
(የአላህን ፀጋ ብትቆጥሩት አትዘልቁትም)እያለ ያበስረናል በሰፊው እዝነቱ እንደምንኖር ስለምን በእዝነቱ እና በፀጋው ተከበን ተስፋን እንቆርጣለን አንቺዬ?
^መለስ አድርጎ ደሞ ፈተናዎቹ ብቻቸውን እንዳልመጡ ነገራቶች ሁላ መሞከሪያዎች ከእዛም ብርሀናዊ ፀጋዎች ስለመሆናተው እንዲህ ይለናል አይደል "ፈኢነማአል ኡስሪ ዩስራ" (በእርግጥም ከችግር ቡሓላ ምቾት አለ)
ብሎ ከፀጋዎቹ ውስጥ የሆነኛውን ይገልፅልናል እናም ኡኽታ ጨንቆሻል ከፍቶሻል ወይ የሆነ ይሳካልኛል ያልሽው ነገር አለመሳካቱ አዘንብሎብሻል ተሳሰቢውማ ተነሺና ውዱእ አድርገሽ መስገጃሽ ላይ ተደፍተሽ ማድረግ እየፈለግሽ ይቺን ትልቋን ነፍሲያሽን አሸንፈሽ ለአላሄዋ ብለሽ በተወሽው ነገር ተሳሰቢው ያኔ ግን ለእሱ ብለሽ የተወሽው ነገር ካጣሽ ቀድመሽ ነፍስሽን ተሳሰቢያት
2024/09/25 04:24:41
Back to Top
HTML Embed Code: