Telegram Web Link
የመራም ማስታወሻ የሚለዉ ታሪክ አልቋል

አስተያየት አልቀበልም😊....ከትንሽ ቀን ቡሀላ የሆድ ዉስጥ ፉም እሳት የሚለዉን በ45 Part የቀረበዉን ለዩቲዩበሮች እና ለሌሎቻ ቻናሎች እንዲመች በመሀል የገቡ አባባሎች ሀዲሶች ተቀንሶ ወደ 25 part size አንሶ አቀርባለሁ...

መልካም ቆይታ

አሚር ሰይድ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ፡፡
አንዳንድ የቻናል admin እና ዩቲዩበሮች የሆድ ዉስጥ ፉም እሳት እዉተነኛ ታሪክ በ45 part የተቀረበዉን በአጭር part አርግልን ስላላችሁ በዉስጡ ያሉትን አባባሎች እና አጭር ምክሮች ተቀንሰዉ እና ሁለቱን part በአንድ በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ይቀርባል መልካም ንባብ፡፡

⚠️በአስተያየት መስጫ ማንኛዉንም ሀሳብ አስተያየት አልቀበልም

አሚር ሰይድ
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
🎖የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞  አንድ 1⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ



    በሰዎች ዉሳኔና ፍላጎት ምኞት እና ጉጉት ብቻ ተፈፃሚ የሚሆን ነገር የለም የአሏህ ፍቃድ እስካልታከለበት ድረስ.. አንዳንዴ በሰዉ በዘመድ ተከበህ ሰዉ ይናፍቃል. እዉነት ነዉ በአለም ላይ በቢሊየን የሚሆን ህዝብ እያለ የዉስጡን የሆዱን የታፈነ ነበልባል አንድ ሰዉ ላይረዳህ ይችላል...የዚህን ጊዜ ብቸኝነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት ይቻላል ፡፡

     ዉሀ ላይ ሁኜ ዉሀ ይጠማኛል
     እሰዉ ጋር ሁኜ ሰዉ ይናፍቀኛል
      የያዘኝ በሽታ ወንድም ያሰኘኛል
አንድ መንዙማ ላይ የሰማሁት ነዉ . እዉነት ነዉ ዉሀ ጠምቶህ ጠጥተሀዉ ሆድህ ቢገባም ዉሀዉ ጥምህን የማይቆርጥ ከሆነ
በሰዉ መሀል ተከበህ ሰዉ ሲያስፈልግህ ሰዉ ግን አንተን ለመረዳት ሳይፈልግ በአንተ ላይ የሚሳለቅ ከሆነ ሰዉ መሀል ተከበህ ጥቅሙ የሚሆነዉ የሰዉ ቆጠራ ጊዜ አብሮ ተቆጥሮ አለ ይሄን ያህል አለ ለማለት ያህል ካልሆነ በቀር ....

የተፈጠርንበት ማንነት ዲነል ኢስላም በወንድምነት በእህትነት አስተሳስሮን ነገር ግን ዛሬ ጓደኛ ነገ ደግሞ ጥላት እየሆነ የመጣ ይመስላል. ታዳ መቼ ይሆን ለሰዉ እዉነተኛ ሰዉ የምንሆነዉ???..ለሰዉ ልጅ በሽታዉም ህመሙም ያዉ አላህ እንደቀደረዉ ሁኖ ታንቆም መርዝ ጠጥቶም የሚሞተዉ ያዉ በሰዉ ምክንያት ነዉ ..ምክንያቱም ይህን ዉሳኔ የወሰነዉ መቼም ሰዉ ነዉ እና ጥፋት አይቀርም..አጥፍቶ መሄጃ ሲያጣ በአማከረዉ ሰዉ ወይም ለልብ ጓደኛዉ የልቡን ነግሮት ግን የተናገረዉን ከጆሮ ባልዘለለ ከልቡ ሳያስቀምጠዉ ሲቀር ያኔ ከሰዉ በላይ አላህ ይጠብቀን ሸይጧን ይቀርበዋል ይሳሳታል ይታነቃል ወይ መርዝ ይጠጣል ..ይሄን ዉሳኔ የሚወስነዉ ዱንያን መሮት እንጂ ተመቸቶኝ ብሎ ራሱን የሚያጠፋ የለምና...

በጥናት ዉጤት ስናየዉ አሜሪካ በአንድ አመት ብቻ 25,000 ሰዎች ራሳቸዉን ያጠፋሉ ቻይና በየዓመቱ 30,000 ሰዉ ራሱን ያጠፋል በአለም ላይ በየ20 ሰከንዱ ሰዎች ራሳቸዉን ያጠፋሉ ይህ ማለት በአለም ላይ ወደ በአንድ አመት ሁለት ሚሊየን ህዝብ እራሳቸዉን ያጠፋሉ ማለት ነዉ፡፡

ሁሉም ሰዉ ሊያወቀዉ የሚገባ የማይካድ ሀቅ ደስታ በዲነል ኢስላም አላህ ጋር ባለን ግንኙነት እንደሚወሰን መገንዘብ አለብን..የቁርአንን መመሪያ መከተል ለዚህ ያለእድሜዉ እራሱን ለሚያጠፋዉ እና በሂወት እያለ ሒወት እንደ ዥዋ ዥዌ ጨዋታ ለሆነችበት ቁርአን መፍትሄ እንደሆነ እርግጥ ነዉ .... አሁን ጊዜ ላይ ያለነዉ የሁላችንም ጥፋት የቁርአን መመሪያ እኛ መከተሉን ትተን በእኛ መስመር እንዲከተለን መፈለጋችን ነዉ፡፡

ታዳ ለዚህ ሁላ ራሱን ላጠፋዉ ተጠያቂዉ ሰዉ አይደለም ብላችሁ ታስባላችሁ??? ሰዉ ከሚሳሳትባቸዉ ምክንያቶች ዋናዉ እና አንደኛዉ ባለፈዉ ጊዜ ምን ምን ነገሮች ነበሩ??ዛሬ ምን ይደረጋል?ነገስ ምን ይመጣ ይሆን? የሚሉትን ጥያቄዎች ሳያስተዉሉ ሁሉንም ነገር ለዛሬ ብቻ ሲሰጡ ነዉ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ደስታ የሚገኘዉ በብር ብቻ ነዉ ብለዉ የሚያምኑ አሉ... ስህተት ነዉ ደስታ የሚገኘዉ በዲነል ኢስላም ነዉ :: ዲነል ኢስላምን አዉቆ ያልሰራበት ደስታ በጭራሽ አያገኝም..ለምሳሌ አሜሪካንን እንዉሰድ የአለም ኢኮኖሚ 50% በአሜሪካ እጅ ይገኛል ነገር ግን በአለም ላይ በደስታ የሚኖሩ አገሮች ቁጥር ተርታ ስትሰለፍ 116 ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡በተዘዋዋሪ ደግሞ በአለም ላይ በደስታ የሚኖሩ ሀገሮች የመሪዎችን ደረጃ የያዙት ሙስሊም ሀገራት ሲሆኑ.....ቁጥር 1 ናይጀሪያ ናት ..ናይጀሪያ እንደምናዉቀዉ የሙስሊም ሀገር ናት በኢኮኖሚዋ ዝቅተኛ ብትሆንም ግን የመጀመሪያ አላማቸዉ አላህን ማስደሰት ስለሆነ በአላቸዉ ተብቃቅተዉ በደስታ ይኖራሉ

የሰዉ ልጅ ብር ደስተኛ እንደማያረግ የጃፓኑን ትልቅ ድልድይ በቀን ከ300 መኪና በላይ የሚተላለፍበትን የገነባዉ ኢንጅነር በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ገቢ ያገኘ ቢሆንም ተመርቆ አገልግሎት በሚሰጥበት ቀን በትንሽ ቁራጭ ወረቀት ኑዛዜ አስቀምጦ ራሱን ከድልድይ ላይ በመጣል ራሱን አጥፍቷል...በኑዛዛዉ እንዳስቀመጠዉ """"እኔ የገንዘብ ችግር አላጋጠመኝም ደስታ በማጣቴ ብቻ ከዚህ አለም ለመሰናበት ፈልጊያለሁ"""" ነበር ያለዉ ፡፡

በአለም ላይ የሰዉ ልጅ ራሱን ለመቀየር 24ቢሊዮን ዶላር/ ሴቶች ለኮስሞቲክስ 18ቢሊዮን ዶላር /ፀጉርን ለመንከባከብ 38ቢሊየን ዶላር /ለሽቶ ደግሞ 15ቢሊዮን ዶላር በአመት ያወጣሉ... ታዳ ሰጥቶን ስጡ ለተባልነዉ ዱንያ የአላህ ወዴታን ለማግኘት ስንት አዉጥተናል?? ለተቸገረ ሰዉ ስንቶቻችን የችግሩ መፍትሄ ሁነናል??ስንቶቻችን ነን ደሀ እና ሀብታምን ሳንለያይ በአንድ አይን የምናየዉ???
ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ አንድ ሰዉ ጀሀነም እሳት ዉስጥ ለመግባት ሙስሊም ወንድሙን በዝቅተኛ አይን ማየቱ በቂ ነዉ ብለዋል..እስኪ ሆድ ይፍጀዉ

    የኔ ታሪክ ስለ ሁላችንም የሰዉ ማንነት ላይ ዱንያ የደስታ ህይወት አለመሆኗን  ያተኮረ ሲሆን እስኪ ሳይረፍድ ወደ ታሪኩ እንግባ
    ቅድሚያ መተዋወቅ ይቀድማል እንተዋወቅ የእናንተን ባለቅም የእኔ ስም ነዋል እባላለሁ አሁን ላይ የኔ እድሜ አስራ ዘጠኝ ሲሆን ፡፡ እኔ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ ከእኔ በታች በሶስት አመት የምበልጠዉ አንድ ታናሽ ወንድም እና በጣም ታናሽ እህት አለችኝ..በጠቅላላ ለቤተሰቦቻችን ሶስት ልጆች ነን፡፡
ተወልጄ ያደኩት የፍቅር የመከባበር ሀገር በሆነችዉ የአባጅፋር ሀገር ጅማ ከተማ በአጂፕ ሰፈር አዲሱ ገቢዎች ግምሩክ አካባቢ ነዉ፡፡

   አባቴ  ጅማ ከተማ ላይ ታዋቂ ኮንትራከተር ህንፃ ተቋራጭ ሲሆን በዚህም የተነሳ ዉብ የሆነ ቤት እና ወደ ሰባት የሚሆን መኪና ያለን ሲሆን ጅማ ላይ እስኪ ብር ያለዉ ባለሀብት ጥሩ ቢባል ቁጥር አንድ የሚጠራዉ የኔ አባት ነዉ፡፡ እንደ መጀመሪያ ልጅ በመሆኔ ምንም ሳይጎልብኝ የፈለኩትን በልቼ የፈለኩትን ጠጥቼ ነዉ ያደኩት ፡፡ አባቴ በጣም ተንከባክቦ ነዉ ያሳደገኝ ፡፡

መቼም ማንኛዉ ሰዉ እድሜዉ ከትምህርት ከደረሰ ትምህርት ቢያነስረዉ መመዝገቡ አይቀርም  ...እኔም ጅማ የሚገኘዉ ኮምዪኒቲ ትምህርት ቤት--KG1 ተመዘገብኩ፡፡ KG ትምህርቴን እንደ ጨርሼ አንደኛ ክፍልም እዛዉ ኮምዩኒቲ ትምህርት ቤት ተመዘገብኩ፡
  
የሰፈር ልጆች ጋር ከልጅነቴ ጀምረን ስጫወት እነሱ ግን እኔ ጋር መጨዋት አይፈልጉም ነበር
.....ለምን እኔ ጋር አትጫወቱም ስላቸዉ ??
....እናት አባቶቻችን አንቺ ጋር እንዳትጫወቱ ተብለናል ይሉኛል፡፡
እኔም ልጆቹ ያሉኝን ለአባቴ ሂጄ እነግረዋለሁ
...አባቴም አንጫወትም ካሉሽ አትጫወቺ ምን ያረጉልሻል እቤትሽ አድበሽ ተጫዋቺ ይለኛል


     አንደኛ ክፍል እየተማርኩ የኔ ጓደኛ ለመሆን የማይጥር የለም ... ትምህርት ቤት ስሄድም ስመጣም መኪናዉ የራሳችን ስለሆነ አባቴ በያዘልኝ ሹፌር ነዉ የምመላለሰዉ ፡፡ የሀብታም ልጅ ስለሆንኩ ነዉ መሰለኝ ብዙ ሴት ልጆች እኔን ጓደኛ እንድሆናቸዉ ይቀርቡኛል 👇👇👇
  ከአንደኛ ክፍል ጀምሬ አንዲት ጓደኛ ያዝኩኝ ልጅቱም ፌሩዛ ትባላለች ...ፌሩዛ በትምህርቷ ጎበዝ ነች እኔም እንደ እሷ ጎበዝ መሆን የኔም የአባቴም ምኞት ነዉ  ጓደኛየ ማድረግ ወሰንኩ ፡፡ ክፍላችን ዉስጥ ተሰሚነት ነበረኝ እኔ ከክላስ ልጅ አንድ ልጅ ጋር ከተጣላሁ የተጣላሇትን እሷን እንዳታወሩ ካልኩኝ የሚያወራት የለም ፡፡ እኔ የወደድኩትን ይወዳሉ የጠሉትን ይጠላሉ....እኔ የምጫወትዉን ይጫወታሉ እኔ የማይመቸኝን ጨዋታ አይጫወቱም ፡፡

   ቁርአን ደግሞ መቅራት የጀመርኩት KG ተማሪ በነበርኩበት ሰአት ሲሆን ቁርአን የገባሁትም ጅማ ኑር (አጅፕ)መስጊድ ያለዉ ቁርአን ቤት ነዉ ..ገና አፌ መናገር ሲጀምር አባቴ ቁርአን እንድቀራ በቁርአን ጎበዝ እንድሆን ይመክረኝ ያበረታታኛል..ግን ምን ዋጋ አለዉ በአንድ ሰዉ ጥረት አይሆን..ቁርአን እንድቀራ እናቴ ትኩረት ስላልሰጠችኝ መድረሳ ቁርአን ለመቅራት እመላለሳለሁ እንጂ አሊፍ ባታ ሳ ጂም ብሎ ሁሉንም ፊደል ለመለየት  ሶስት አመታት ፈጅቶብኛል፡፡
   
    ቀን ማታ መሽቶ ነግቶ ሁሌ ሀሳብ የሆነብኝ ነገር የሰፈር ልጆች ልጫወት እነሱ ጋር ስሔድ አንቺ ጋር አንጨዋትም እያሉ እኔን ለብቻየ የሚያገሉኝ ነገር ሚስጥሩን ምክንያቱን ላዉቀዉ አልቻልኩም  ..እንደ ልጅነቴ የሰፈር ልጆች ጋር የመጫወት እድል ላገኝ አልቻልኩም....እኔ ከእነሱ ጋር የማልጫወትበት ምክንያት ምንድን ነዉ ??? እያልኩ እራሴን ብጠይቅ መልስ ሊመጣልኝ አልቻለም..

    አባቴንም ሁሌ ቀን በቀን እኔ ጋር አልጫወትም አሉኝ እያልኩ እነግረዋለሁ የአባቴ መልስ ግን ምንም ሊቀየር አልቻለም ...
....ተያቸዉ ልጆቹ ጋር አትጫወች የምትለዉ መልስ ብቻ ነዉ የሚመልስልኝ...ተለዋጭ መልስ ሊሰጠኝ አልቻለም
   

    አንድ ቀን የሰፈር ልጆች ተሰብስበዉ ሲጫወቱ የሚጫወቱት ጨዋታ በጣም ደስ አለኝና ...እኔም  በግድም ቢሆን ሂጄባቸዉ የሰፈር ልጆች ጋር ጨዋታ ጀመርን ....ልጅነት መቼም ጨዋታዉ ፈረሰ ዶቦዉ ተቆረሰ ከተባለ መጣላታችን አይቀርም አይደል...አንዲት የጎረቤታችን ልጅ ጋር ተጣላን ...ከዛም ከልጅቱ ጋር ሲያገላግሉን መሰዳደብ ጀመርን ....
........ተጣልተን ስንሰዳደብ እኔ የልጅነት አንቺ ማስጠሌ አይጥ እያልኩ ስሳደብ እሷ ግን የሰፈር ሰዉ በተሰበሰበት መሀል ከአእምሮ የማይዋጥ የሚዘገንን በልጅ አቅሜ መሸከም የማልችለዉ ስድብ ሰደበችኝ
....እኔም ይሄን ስድብ እንደሰደበችኝ ደነገጥኩ ... እሷ ጋር ስድብ መመላለስ አፍ መካፈቴን አቁሜ ስድቡን እያብሰለሰልኩ እየተገረምኩ እንዴት እንዲህ ብላ ትሰድበኛለች???እያልኩ ወደ ቤቴ ሄድኩኝ..

እቤት ስገባ የአላህ ነገር አባቴ ቁጭ ብሎ አገኘሁት...
ፊቴ መቀያየሬ መናደዴን ያየዉ አባቴ ምን ሁነሽ ነዉ ልጄ ፊትሽ ተቀያይሯል ሰዉ ጋር ተጣልተሻል እንዴ???? አለኝ
......እኔም አባቴ የጎረቤታችን ልጅ""" ........."""ብላ ሰደበችኝ እኮ አልኩት ..
.......ወዳዉ አባቴ ፊቱ ተቀያየረ ተናደደ እና ቁጭ ካለበት በመነሳት መኝታ ክፍል ገብቶ ሽጉጡን ከአስቀመጠበት አንስቶ ወዳዉ አቀባብሎ ከመኖሪያ ቤት ወጥቶ የሰደበችኝን ህፃኒቱን የኔኑ እኩያ በሽጉጥ ሊገላት ይፈልጋት ጀመር፡፡ 


አባቴ በጣም ተናዷል ጅማቱ ዉጥርጥር ብሏል....ልጅቱ መኖሪያ ቤት ሂዶ ነይ ዉጪ የት ነሽ ዛሬ እገልሻለሁ እያለ እየፈለጋት ነዉ...

ሰፈሩ በአንድ እግሩ ቆመ ..የኛ ጎረቤቶች በኛ ቤት አቅራቢያ የሚገኙ ዘመድ አዝማዶች ተሰብስበዉ ንዴት አብርድ እያሉ እየለመኑት ነዉ ...

አባቴን ተረጋጋ እባክህ ተብሎ በጓደኞቹ በዘመድ አዝማዶች በስንት ጉድ ተለምኖ ተመልሶ እቤቱ ገባ፡፡ ግን አባቴ ልጅቱን አለቃትም ሌላም ቀን ቢሆን በዚህ ሽጉጥ አናቷን ብየ ነዉ የምገላት እያለ ይደነፋል............

  ማታ ተኝቼ ብቻየን ማሰብ ማሰላሰል ጀመርኩኝ አብረን የምንጫወት የሰፈራችን ልጅ እንዴት ልሰድበኝ ቻለች ???ይሄን ለጆሮ ለመስማት የሚዘገንን ስድብ እንዴት ሰደበችኝ ???አባቴስ ስነግረዉ ለምን እገላታለሁ ብሎ ደነፋ ???? እያልኩ ብቻየን ሳስብ አደርኩኝ....ግን ይሄን ስድብ እዉነት ነዉ ወይስ ዉሸት?? ማጣራት አለብኝ ብየ ወሰንኩ ...ግን ማንን ልጠይቅ ???
   
የምጠይቀዉ ሳጣ ሲጨንቀኝ አንድ ሀሳብ መጣልኝ ለምን የቤት ሰራተኛችንን አልጠይቃትም???ብየ አሰብኩኝ...እሷን ለመጠየቅ ወሰንኩ

የቤት ሰራተኛችንን ልጅቱ ለምን"""""""____"""""እንደዚህ ብላ እንደሰደበችኝ ጠየኳት ...ሰራተኛችን ለመንገር ፍቃደኛ አልሆነችም ... ግን እኔ ንገሪኝ እያልኩ አፋጥጬ ስይዛት የቤትሰራተኛችን እያለቀሰች ....,እንደዚህ አለችኝ.........


ልጅቱ የሰደበቻት ምን ብላ ነዉ ????  የተደበቀዉ ...ማንነት ምንድን ነዉ ???ለምን አባትየዉ ገና ነፍስ ያላወቀችን ልጅ አገላለሁ ብሎ ለምን ተነሳ ??? የተቆለፈዉ ሚስጥር ምንድን ነዉ ???
በሚቀጥለዉ ክፍል እናያለን


#ክፍል 2⃣
ይ....ቀ...ጥ.....ላ....ል

www.tg-me.com/Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
🎖የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ ሁለት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ



 የቤት ሰራተኛችን እያለቀሰች እንዲህ አለችኝ፡- ነዋል አሁን ለአንቺ መንገር አልችልም ገና ልጅ ነሽ ....የወር አበባ ማየት ስጀምሪ  የዛን ጊዜ እነግርሻለሁ እንድነግሪሽ አታጨናንቂኝ አለችኝ እያለቀሰች ፡፡
...እኔም መንገር ካልፈለክሽ አላስገድድሽም አትጨናነቂ አልኳት ፡፡

እሷን ማጨናነቅ አልፈለኩም.. በቤት ሰራተኛችንም አልፈረድም ለምን እኔ እና አባቴ በጣም እንቀራረባለን ይሄ ሚስጥር እሷ እንደነገረችኝ ከአወቀ አባቴ ጋር እንደሚጣሉ አቃለሁ .......
  
የሚገርማችሁ እኔ ሳድግ እቤት ጥሩ ኑሮ ብንኖርም ብር ብቻ ለሰዉ ልጅ ደስታን አይፈጥርም እናት እና አባቴ ሁሌ እንደተጣሉ እንደተጨቃጨቁ ነበር... በሰላም ሳይጣሉ ያደሩበትን ቀን መቁጠር ይቀላል፡፡ እኔ ታዳ ማታ ማታ በተጣሉ ቁጥር እኔ መጨነቅ መጠበብ ነዉ ስራየ..

    ሁሌ ታዳ እናቴ አባቴን በነገር ስትወጋዉ ከሳሎን ተነስቶ ሌላ ክላስ ገብቶ ብቻዉን ቁጭ ይላል.....እኔም ለአባቴ እራቱን ይዤ ያለበት ክላስ እሄዳለሁ ... አባቴም ፀጉሬን እያሻሸ እንዲህ ይለኛል  .....ነዋልየ የአይኔ ማረፊያ እናትሽ ጋር ብዙ ቀን ለመፋታት አስባለሁ ግን አንቺ ትዝ ትይኛለሽ እኔና እሷ ተፋተን አንቺ ስትሰቃይ አባቴን ወይ እናቴ ናፈቁኝ እያልሽ ስትሰቃይ በአይኔ እየታየኝ እንደገና እተወዋለሁ....እኛ ስንጣላ አትጨናነቂ መኝታ ክላስ ግቢ ብዙ ነዉ ሚስጥሩ ነዋል ይለኛል፡፡

_እናቴ ደግሞ እንዲህ ትለኛለች.......በሂወቴ አንቺን ካረገዝኩ ጊዜ ጀምሮ አሁን ድረስ የተረገመ ሒወት ዉስጥ ነዉ የገባሁት ምነዉ ተወልደሽ ባልነበር ትለኛለች እየተናደደች ...
.......እናቴ ከምነግራችሁ በላይ በጣም ሀይለኛ ቁጡ ዉሀ ለምን ቀጠነ ብላ የምትጨቃጨቅ ...ለሰዉ በቀላሉ የማትመለስ ናት ፡፡ እኔን ለራሱ ስትናገረኝ ሁሌም ቢሆን ለኔ ክብር የላትም ቃላቶችን መጥና ከአፏ መወርወር አትችልም ... በተዘዋዋሪ ደግሞ አባቴ አስተዋይ እረጋ ያለ ነገሮችን በትግስት የሚያልፍ ለቤተሰቡ ክብር ያለዉ እና በተናደደ ሰአት ደግሞ ፊቱ ለመቅረብ የሚፈራ ቁጡ ሀይለኛ ነዉ ግን ለነገሮች ሁሉ አይቸኩልም ፡፡ አባቴ ትዳሩ እንዳይበተን ተረጋግቶ ይዞት ነዉ እንጂ እንደ እናቴ ሀይለኝነት ትዳሩ ፈራሽ ነዉ ፡፡

ትዳር ማለት የአንዱን ጎዶሎ አንዱ ይሞላል ማለት ይህ ነዉ፡፡ አባቴ የእናቴን ጎዶሎ እየሞላ ትዳራቸዉ እንዲቀጥል አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡
እናቴ ይሄን የነብዩ ሀዲስ የረሳችዉ ይመስለኛል
★★★ተወዳጁ የአላህ መልዕክተኛ ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል ፡-በሚስት ላይ ያለባት ከባዱ ሀቅ የባሏ ሀቅ ነዉ..በወንድ ላይ ደግሞ ያለበት ከባዱ ሀቅ የእናትና አባቱ ሀቅ ነዉ..በማለት የባል ሀቅ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለማሳየት ሞክረዋል..

ነብዩ ሰ.ዐ.ወ በሌላ ዘገባቸዉ ማንኛዉም ሴት ባሏ እርሷን እየወደዳት በርሷ ላይ ተደስቶ ከሞተች ጀነት ትገባለች...ብለዋል፡፡ እናትሽ ፀባዯን አላህ ያስተካክልልኝ ብላችሁ እስኪ ዱአ አድርጉልኝ

  
    በትርፍ ሰአቱ ቁርአን ቤት እየሄድኩ ስቀራ  ኡስማን ከሚባል ልጅ በፍቅር ወደኩኝ........በፍቅር ስል የሌላ እንዳታደርጉት በልጅነት ስናድግ በጣም የምንቀራረብ ልጆች ነን፡፡ አንድ ቁርአን ቤትና ትምህርት ቤት ነን
  የኡስማን አባት እና እናት የመንግስት ሰራተኛ ናቸዉ .......ኡስማን አንድ እህት አለችዉ ... ቁርአን የሚያቀራን ሸህ ስለሚገርፉን መድረሳ እንገናኝና የኡስማን ቤተሰቦች እቤት ካሉ ቁርአን እንቀራለን ግን እቤት ከሌሉ ዛሬ የሉም ስራ ናቸዉ ከተባለ ቁርአናችንን መቅራት ትተን አሱር አዛን እስከሚል ድረስ እነ ኡስማን ቤት ሂደን ስንጫወት ስንደባደብ እንዉላለን ....አሱር አዛን ሲል እኔ ወደ ቤቴ ተመልሼ ቁርአን የቀራሁ መስየ እሄዳለሁ፡፡

ኡስማን ጋር ያዉ የልጅነት ነገር መጫወት መደባደብ እንጂ ሌላ ነገር የለም ግን የእቃቃ ባል ይባል የለ ....ኡስማን ጋር በልጅነታችን በጣምምም እንዋደዳለን፡፡
  
አባቴ ከትምህርት መልስ ቁርአን ቤት እንድቀራ የፈለገዉ የሰፈር ልጆች ጋር እንድቀራረብ ስለማይፈልግ ነዉ....ከሰፈር ልጅ ጋር አብሬ አላደኩም የወንድም የሴትም የሰፈር ልጅ ጓደኛ የለኝም፡፡ ለምን ያቺ ልጅ ከሰደበችኝ ቡሀላ ከሰፈር ልጆች ጋር እኔም መጫወት እየከበደኝ መጣ .....

አንዳንዴ ብቸኝነት ሊዉጠኝ ሲደርስ ልጆቹ ጋር ልጫወት ስቀርባቸዉ የሚጫወቱትን ጨዋታ ትተዉ ይነሱና እኔን ብቻየን ጥለዉኝ ይሄዳሉ
.....እኔም ስማቸዉን እየጠራሁ ለምን ትሄዳላችሁ??አብረን እንጫወት እንጂ ??? ስላቸዉ
..........እነሱም ቤተሰቦቻችን አንቺ ጋር እንዳንጫወት ከልክለዉናል አንቺ ጋር አንጫወትም እያሉኝ ጥለዉኝ ይሄዳሉ..........እኔ ለመጫወት ወደ ልጆቹ ሲሄድ እነሱም ይሸሹኛል ወይ ክፉ እድል.......
 
   ከአሱር ቡሀላ ከቁርአን ቤት ስመለስ እቤት እየመጣ ትምህርት የሚያስጠናኝ አንድ ልጅ አለ........ከዛ ዉጭ ግቢ ዉስጥ ታናሽ ወንድሜ እና እህቴ ጋር እየተጫወኩ ነዉ ጊዜየን የማሳልፈዉ፡፡


ጊዜዉ በቀልዱም በምሩም ቁሞ አይጠብቅም   ቁርአን ቤት ሄድኩኝ እያልኩ ስጫወት መዋል ከጀመርኩ ሶስት አመት ሆነኝ ፡፡ ኡስማን እና እህቱ ጋር ከሁለተኛ ክፍል ጀምረን ነበር ቁርአን ቀራሁ እያልኩ መኖሪያ ቤታቸዉ እየሄድኩ የምጫወተዉ
 
ጉድ እና ጅራት ከስተቡሀላ ነዉ አይደል የሚባለዉ መቼም ይሄ ጉድ ተደብቆ አልቀረም....አንድ ቀን አባቴ ቁርአን ቤት መጥቶ ሸህየዉን ስለእኔ ሲጠይቃቸዉ ብዙ ቀን እንደማልመጣ እና እነ ኡስማን ቤት ስጫወት እንደምዉል መረጃዉ ደረሰዉ
  
እቤት ስገባ------- አባቴ ተቆጥቶ ፊቱ የእሳት ፉም መስሎ ጠበቀኝ.........
   
.... ነዋል ነይ ቁጭ በይ አለኝ በንዴት
......እኔም እሺ ብየ ቁጭ አልኩኝ.
...... ለስንት ደረጃ ትደርሻለሽ እያልኩ አንቺ ቁርአን ቤት ነኝ እያልሽ ሶስት አመት ስቀልጂ መቆየትሽን ዛሬ ቁርአን የሚያቀራሽ ኡስታዝ ነገረኝ....እንዴት እንደዚህ ትሰሪያለሽ ??? አለኝ
....እኔም ደንግጬ አፌ ተያያዘ የምመልሰዉ ጠፋኝ

አባቴም የመኖሪያ ቤታችንን በር ቆልፎ ለመጀመሪያ ጊዜ ገረፈኝ ....ከቀበቶ አልፎም እጄን አስሮ በርበሬ አጠነኝ

...አባቴ ከተናደደ ተናደደ ነዉ ብጮህ ብጮህ የሚገላግለሉኝ ሰዎች ወደ ቤት መግባት አልቻሉም.. አባቴ ገርፎ በርበሬ ከአጠነኝ ቡሀላ በሩን ከፈተዉ እና ጥሎኝ ሄደ
    
እናቴ ጎረቤት እና የቤት ሰራተኛችን ተሰብስበዉ ቢያባብሉኝ ቢያባብሉኝ እምባየ ሊቋረጥ አልቻለም

.........ከዚህ ቀን ቡሀላ አድቤ ቁርአን ቤት እየሄድኩ መቅራቴን ቀጠልኩ ... ከነኡስማን እና እህቱ ጋር ለጊዜዉም ቢሆን ጓደኝነታችንን ሰረዝን...


አባቴ እኔን ወደ ሶሰት ቀን የሚሆን አኮረፈኝ ...እኔም መልሼ አይኑን ማየት ፈራሁ ፡ አባቴ ሲመጣ ተጠምጥሜ እንደማልስመዉ ..አሁን ግን የእሱ መምጫ ሰአት ሲደርስ አይኑን ማየት እየፈራሁ መኝታ ክፍሌ እገባለሁ፡፡
  
ከሶሰት ቀን ቡሀላ አባቴ ነዋል ነይ ዛሬ ይዠሽ የምሄድበት ቦታ አለ አለኝ
...እኔም እሺ ብየ  አባቴ ጋር መኪናዉን እየነዳ ከጅማ በ45Km በቅርብ እርቀት የምትገኘዉ ወደ አጋሮ ከተማ አባቦቃ መናፈሻ ወስዶ ሲያዝናናኝ ሲያስደስተኝ ዋለ👇👇
አባቴም ነዋልየ አትከፊብኝ እኔ እኮ ተናድጄ ነዉ የገረፍኩሽ በቁርአንሽ ጎበዝ እንድትሆኝልኝ ነዉ ሁሌም ምኜቱ ፡ብዙ ጊዜ ነግሬሻለሁ ለአንቺ ብየ ነዉ ከእናትሽ ጋር የምኖረዉ ደልቶኝ ተመችቶኝ ሳይሆን አንቺን ብየ እንደሆነ ..ነዋል መቼም ቢሆን አንቺን አልጠላሽም.... ከገረፍኩሽ ቡሀላ የዛኑ ቀን ተፀፅቻለሁ ማታ ወደ ቤት ስገባ እኔን ፍርቻ ብቻሸን መኝታ ክፍልሽ ስትገቢ ምነዉ ባልገረፍኳት እያልኩ እየፀፀተኝ ነዉ አለኝ
.......እኔም አባቴ አንተ ልክ ነህ ጠፋቱ የኔ ነዉ ይቅርታ አድርግልኝ......ከአሁን ቡሀላ ጨዋታ አያታልለኝም መጥፎ ጓደኞችንም አልይዝም የዛሬን ይቅር በለኝ አልኩት አንገቴን አቀርቅሬ
....አባቴም አረ ዛሬ እዚህ ላዝናናሽ የመጣሁት አንቺ ተሸማቀሽ አንገትሽን እንድትደፊ ሳይሆን እኔ የገረፍኩሽን ይቅርታ ልልሽ ነዉ አለኝ፡፡ ከዛም ሁለታችንም ታረቅን አንዴ ሳቅ በሳቅ ደስታ ሆነ ..ከዛም ወደ ጅማ ጥሩ ጊዜ አሳልፈን ተመለስን

  አምስተኛ ክፍል ተምረን ጨረስን እኔ በምማርበት ጊዜ ክረምት ላይ የረመዷን ፆም ያዝን ....እኛ ሰፈር የሚገኘዉ ኑር(አጅፕ) መስጂድ ተራዊህን ለመስገድ አንዲት የሰፈራችን ልጅ ጋር ተራዊህ አብረን ሂደን አብረን ወደ ቤት እንመለሳለን ፡፡

ረመዷን አጋምሰናል ኑር(አጅፕ) መስጂድ ኢሻን ልንሰግድ ተቀምጠን .....ልጅቶ እንደዚህ አለችኝ
.......ነዋል የሆነ ነገር ልንገርሽ አዳምጪኝ ?? አለችኝ
....እኔም ..ምንድን ነዉ??ንገሪኝ አልኳት እናቴ እኮ """ #ነዋል " ..........."ብላኛለች.. አለችኝ ...

ይሄንን ስትነግረኝ ፍዝዝ ድንዝዝ ብየ ቀረሁ መሬት የዋጠኝ ነዉ የመሰለኝ ላቤ በግንባሬ ችፍ ችፍ ሲል ይታወቀኛል......እራሴን መቋቋም አቃተኝ ..ጭንቅላቴ ፍልፍል ቋጥኝ ዲንጋይ ይመስል በጣም ከበደኝ...
መስጊድ እስከ መሆኔ ዘንግቸዋለሁ...

   ያቺ ልጅ በልጅነቴ የሰደበችኝ አባቴ በሽጉጥ እገላለሁ ያለዉ ሚስጥር ሙሉ በሙሉ እየተገለጠልኝ መጣ.....


  የተደበቀዉ ሚስጠር ምን ይሆን???

#ክፍል 3⃣
ይ......ቀ........
.....ጥ.......ላ..........ል



·¨: ❀ share
           `·.     www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
  •════•••🍃🌺🍃•••════•
  
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
🎖የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ ሶስት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ


     ያቺ ልጅ በልጅነቴ የሰደበችኝ አባቴ በሽጉጥ እገላለሁ ያለዉ ሚስጥር ሙሉ በሙሉ እየተገለጠልኝ መጣ.....
.....ኢሻ ሶላት እስከሚደርስ ደአዋ እየተደረገ ሶላቱን እየተጠባበቅን በነበርንበት ሰአት እምባየ እንደ ወራጅ ወንዝ ይወርድ ጀመር.... በአንዴ የለበስኩትን ሒጃብ በእምባ አራስኩት ....ግን የነገረችኝ እዉነት ነዉ እንዴ?እያልኩ በእድሌ ማዘን ጀመርኩ....

ልጅቱንም ከአሁን ቡሀላ አንቺ ጋር ወደ መስጊድ መሄድም መምጣትም ጓደኛም መሆን አልፈልግም ብየ ከመስጊዱ ዉጭ በመዉጣት እምባየን ጠርጌ ፊቴን ታጥቤ መልሼ መስጊድ ገብቼ ኢሻንም ተራዊህን ሰግጄ እቤቴ ብቻየን ተመለስኩኝ...........
    
በመነገታዉ ወደ መስጊድ ብቻየን ስሄድ የእሷ ቅርብ ጓደኞች መስጊድ መግቢያ በር ላይ አገኘሆቸዉና ነዋል በምን ተጣልታችሁ ነዉ ?? አብራችሁ መስጊድ እየሄዳችሁ አልነበር እንዴ ?? አንቺም ብቻሽን እሷም ብቻዋን ነዉ የምትሄደዉ ምን ሁናችሁ ነዉ ??ብለዉ ሰብሰብ ብለዉ ጠየቁኝ
......እኔም አይ ለጊዜዉ ተጣልተን ነዉ ቀላል ፀብ ነዉ እንታረቃለን ብየ ማለፉን ፈለኩኝ ለምን የተጣላንበትን ምክንያት መንገር ለኔ በጣም የሚቀፍ እና አሳፋሪ ነዉ ............
   እነሱም ነዋል ለምን ትዋሺናለሽ ?? አንቺ ባነግሪንም እኛ የተጣላችሁበትን ምክንያት አዉቀንዋል ፡፡ የተጣላችሁበትን ምክንያት እሷ የአንቺን የምታቀዉ ሚስጥር እናቷ ስለነገረቻት ስለምታዉቀዉ ነዉ አይደል አንቺ "..................." ስለሆንሽ በዚህ እዉነተኛ ወሬ አፍረሽ አይደል የተጣላሽዉ አሉኝ፡፡
.....እኔም በልጅቱ ነገረኛነት ሚስጥር አለመጠበቅ በማዘን ጥሩ ጓደኛ አለመሆኗን ታዝቤ ልጆቹን ትቻቸዉ ጥሩም መጥፎም ሳልመልስ ሄድኩኝ....አንዷ እየሄድኩ ከሆላየ እየተከተለች መጥታ """"""ነዋል አንቺ"" ............. ""ስለሆንሽ አታናግሯት ብላኛለች ስለሆነም እኛም ከአሁን ቡሀላ አናወራሽም አሉኝ፡፡
  
የዚች ልጅ መጥፎ ጓደኝነት ከነከነኝ በሰራችዉ ስራ በጣጣም አዘንኩ ...ለነገሩ ሰዉ አመሉ መጥፎ ከሆነ ጥሩ ለመሆን እድል ይጠይቃል ፡፡መጥፎ ጓደኛ በህይወት ላይ የራሱ የሆነ መጥፎ ጫና አለዉ ...
  ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ በሀዲሳቸዉ ሙዕሚንን እንጂ አትጎዳኝ ...እንዲሁም አንድ ሰዉ በጓደኛዉ እምነት ላይ ነዉ ;ከእናንተ አንዳችሁ ከማን ጋር እንደሚወዳጅ ይመልከት ..እንጂ ዝም ብሎ ወዳጅነት አይመስርት ሲሉ ይመክራሉ

አብደላ ቢን ኡመር ደግሞ አስገራሚ ምክር ለግሰዉናል ፡- "ጠላትህን ራቀዉ፡ወዳጅህን ተጠንቀቀዉ ሙዕሚን ሲቀር፡አላህን ከሚፈራ በቀር ታማኝ የለምና፡ጠማማን አትጎዳኝ ከጥመቱ ያስተምርሀል፡ሚስጥርህን ለእሱ አትንገር ፡ማማከር ስትፈልግ አላህን የሚፈሩ ግለሰቦችን አማክር...ብለዋል

ጓደኝነት በኢስላም ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸዉ ግንኙነቶች አንዱ ነዉ፡ሰዉ ዉሎዉን ይመስላል ይባላል ከመጥፎ ሰዎች የዋለ እንደዛዉ መጥፎ የመሆን እድል ይገጥመዋል ፡ ከጥሩ ሰዎች የዋለ እንደ እነሱ ጥሩ ሰዉ የመሆን እድሉ ሰፊ ነዉ፡፡

    በሰፈር ልጆች ወሬ ሒወት ገና በልጅነቴ አስጠላችኝ...ለወደፊት ለመኖር ተስፋ ቆረኩ በልጅነቴ ህይወት ጨለመችብኝ ..ኑሪ ኑሪ የሚል ተስፋ ከኔ ላይ ጥሎኝ ሲሄድ ታየኝ.... ብቻየን በየመንገዱ ማልቀስ ጀመርኩ ...ግን ፈጣሪ በልጅነቴ ጀምሮ ለምን ሊፈትነኝ ፈለገ እያልኩ ብቻየን አስባለሁ..... በኔ እኩያ ያሉ ልጆች ደስታ ጨዋታና ሳስታዉስ በተዘዋዋሪ ደግሞ እኔ በመደሰቻየ ስቄ ተጫዉቼ በማደጊያየ የሰቀቀን የለቅሶ ህይወት ለመኖር ተገደድኩ .....
ወሬዉ ትክክል መሆኑን ሲደጋገም አረጋገጥኩ......... ግን የበለጠ እርግጠኛ መሆን የፈለኩት ሰራተኛዋ ስነግረኝ መሆኑን እራሴን አሳመንኩኝ....

ረመዷን አልቆ ክረምቱም አልፎ ስደስተኛ ክፍል ገባሁ ....የቤት ሰራተኛችን የአላህ ነገር የአባቴ ጓደኛ እሷን አግብቶ ወደ ናዝሬት እንደሚወስዳት ከአባቴ ሰማሁኝ....

   ይህን ወሬ አባቴ እንደነገረኝ ማሻ አላህ አልኩ..ከዛም አባቴ ለስራ ከቤት ሲሄድ ...
የቤት ሰራተኛችንን ሚስጥሩን እንድነግረኝ ...እባክሽ ስሰቃይ አልኑር እዉነቱን ንገሪኝ እኔ የሰፈር ልጆች እየነገሩኝ ነዉ አንቺ እዉነት ነዉ በይኝ እና ቁርጤን ልወቀዉ ብየ እያለቀስኩ ለመንኳት
......እሷም እንባየን እያበሰች ነዋል እሺ እነግርሻለሁ እምባሽን ጥረጊ አለችኝ.....
...እኔም ሚስጥሩ እዉነት መሆኑን ለማረጋገጥ ወዳዉ እንባየን ጠረኩኝ
......, ሰራተኛችንም ለአባትሽ ላልናገር ብለሽ በአላህ ስም ማይልኝ አለችኝ
...........እኔም ወላሂ ለአባቴ በጭራሽ ላልናገር ብየ ማልኩኝ
....ሰራተኛችን ለስለስ ባለ ድምፅ ነዋል እኔ ባልወልድሽም የማይሽ እንደ ልጄ ነዉ እዚህ ቤት ሰራተኛ ሁኜ ማገልገል የጀመርኩት ገና አንቺ ሳትወለጅ እናት እና አባትሽ ከተጋቡበት ጊዜ ጀምሬ ነዉ.....በመንከባከብ ያሳደኩሽ እኔዉ ነኝ፡፡

ነዋል ግን በልጅነትሽ አንድ የተፈጠረ ነገር አለ.. ስነግርሽ መጨናነቅ አያስፈልግም ለወደፊት ጠንካራ እና ለሰዉ ወሬ የማትበገሪ መሆን አለብሽ ..ይሄ በአንቺ ቤተሰብ እና በኔ ቁጥጥር የሆነዉ ሚስጥር አገር ያወቀዉ ፀሀይ የሞቀዉ የአደባባይ ሀቅ ነዉ.... ከሰፈር ልጆች የምሰሚዉ ሚስጥሩ በሁሉም የሰፈር ሰዉ ትልቁም ትንሹም ያቀዋል .....

   ነዋል አንቺ ገና የልጅነት ሒወትሽን ሳታጣጥሚ ክፉ እና ደጉን በማትለይበት በለጋ እድሜሽ በአራት አመትሽ..........

#ክፍል 4⃣
ይ.......ቀ........
......ጥ.......ላ...........ል



JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
🎖የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ አራት 4⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




  ነዋል አንቺ ገና የልጅነት ሒወትሽን ሳታጣጥሚ ክፉ እና ደጉን በማትለይበት በለጋ እድሜሽ በአራት አመትሽ በጎረቤታችን ልጅ  አንቺም እኔም በምናቀዉ በቶፊቅ  ተደፍረሽ ነበር ..ለዛ ነዉ ልጅቱ ጋር ስትጣሉ #በቶፊቅ_የተደፈርሽዉ ያለችሽ ..መስጊድ ዉስጥ ያቺ ልጅ እናቷ ነግራት አንቺን የነገረችሽ የማይካድ ሀቅ ነዉ ነዋልየ  

አንቺ ልጅ ስለሆንሽ ስለማታስታዉሽ ነዉ  ብላኝ እንባዋን እየዘረገፈች  የቤት ሰራተኛችን ነገረችኝ፡፡

ሰራተኛችን ስነግረኝ ቁሜ ቀረሁ እንባየ በሁለት ጉንጮቼ ኩልል እያሉ ወረዱ ...እዉነት መሆኑን አረጋገጥኩ ... ወደድኩም ጠላሁም አምኖ መቀበል እንጂ መቀየር የማልችለዉ የተፈጠረ ሀቅ ነዉ፡፡
የኔ ሂወት ዉጣ ዉረድ ስቃይ ፈተና ከዚሁ ከአራት አመቴ ይጀምራል

       ሬቱን ከማር ለይቼ ሳላውቀው
       ሀራሙን ከሀላል ከቶ ሳለየው
       አፍረተ ገላዬን መሸፈን ሳለምድ
      ጣፍጭ የሚያታለኝ በግድም በውድ

     ብልጠት ያላበቀልኩ እንቡጥ ከረሜላ
     ገና ያልበሰልኩ ጥሬ እንቡቅላ
     እንኳንስ ቀበቶ ለኔ ሊፈቱ
     የስሜታቸውን ጥግ በኔ ላይ ሊያበርዱ

      ገና ሲያዩኝ ላይን የማሳሳ
     እንኳንስ ሊነኩኝ ሲያዩኝ የሚያሳሳ
    እንዴትስ ተችሎት ስቃይ አሸከመኝ??
     አካሌን ለአካሉ ለምኑ ተመኘኝ???
     

ሰራተኛችን ከነገረችኝ ቡሀላ ወደ ሆላ ማሰብ ጀመርኩ በዛ ጊዜ አባቴ ቶፊቅን በሽጉጥ እገላለሁ ሲል እና ገና በተደፈርኩኝ አካባቢ ሆስፒታል ስሄድ ፓሊስ ጣቢያ አባቴ ጋር ስሄድ ፍርድ ቤት አብረን እየሄድን አባቴ ሲከራከር ትንሽ ትዝታዎች ብልጭ ይልልኝ ጀመር ፡፡

ቶፊቅም እዛዉ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ታወሰኝ ነገር ግን አልታሰረም በብር ቅጣት ተቀጥቶ ክሱ የተቋረጠ ይመስለኛል...ግን ለመን አልታሰረም ህይወቴን ልጅነቴን አይደል የወሰደዉ????በአራት አመቴ ህፃን ልጅ ነኝ መደፈር የሚባለዉን አላቅም..ቶፊቅ ግን ትልቅ ልጅ ነዉ ቢያንስ ሀያ አመት ይሆነዋል፡፡ ገና እኔ ሰዉነቴ ሳይጠነክር ሳያዝንልኝ እንደ ደፈረኝ አስተወስኩኝ ፡፡  ሰራተኛችኝም ብዙ ነገሮችን እያረጋጋች ነገረችኝ ...

ቶፊቅ ጅማ የሚኖረዉ ከአያቱ ጋር ነዉ ፡፡ ከእኛ ቤት ጎን ነዉ ቤታቸዉ ፡፡ ሁሌ መጫወት ስፈልግ የእኛ ግቢ በጣም ሰፊ ቢሆንም ቤታችን ሙሉወን G2 የተሰራ ሲሆን  መኪና ማቆሚያ ብቻ ነዉ ያለዉ ...ስለሆነም እነ ቶፊቅ ቤት መጨዋት ለኔ ይመቸኛል ...የቶፊቅ አያቶቹ ነጋዴዎች ስለሆኑ እሱ ነዉ ቤት ሲጠብቅ የሚዉለዉ.....
    እዛ ግቢ እቃቃ ስንጫወት እንትና የኔ ልጅ ትሁን እንትና እየተባለ ቶፊቅ እኔን የኔ ልጅ ናት ብሎ ሁሌ እቃቃ ስንጫወት የቶፊቅ ልጅ ነበር የምባለዉ ፡፡ ቶፊቅ ለቤተሰቦቼ ጥሩ መስሎ የሚታይ ሁሌ እቤቴ ሲወስደኝ አቅፎ ተንከባክቦ ስለሆነ እናቴም አባቴም አይጠረጥሩትም ....እንደዉም አባቴ ልጄን የወደደ እኔን ወደደ ይባል የለ ..ቶፊቅን በጣም ይወደዋል..,

  አንድ ቀን እናቴ ድስት ከእነቶፊቅ ቤት አምጪ ብላ ላከችኝ.... እሱ ቤት ስሄድ ቶፊቅ ማንጎ እየበላ ነበር....ማንጎ ስጠኝ ???ስለዉ
ድስቱን ለእናትሽ አድርሰሽ ነይ እና እሰጥሻለሁ አለኝ
....እኔም ለእናቴ ድስቱን ሰጥቼ ወደ ቶፊቅ ቤት ተመለስኩኝ ...ከዛም ማንጎ ሰጥቶኝ የፈለገዉን የልጅነት ገላየን ሲጫወትበት ...እናቴም ልጄ ምን ሁና ቀረች ??መጣሁ ማንጎ ተቀብየ  ብላኝ ?? ከነቶፊቅ ቤት ዉጭ ሂዳ ይሆን እንዴ ??ብላ ...እነ ቶፊቅ ቤት መኖሬን አልመኖሬን ለማረጋገጥ ስትገባ ቶፊቅ እኔን ልብሴን አስወልቆ እንዳሻዉ ሲያደርገኝ በአራት አመቴ መቀበል የማልችለዉ በደል ሲያደርስብኝ እናቴ በአይኗ ተመለከተች
......እናቴም ያየችዉን ማመን አቃታት. ባለችበት ድርቅ ብላ ቀረች..
....,የምታወራዉ የምትለዉ አጣች አፏ ተያያዘ ..ምን ይደረጋል ይሄ እንኳን የወለደችኝ እናቴ ለኔ የምትሳሳስልኝ አድጌ ብዙ ደረጃ እንድደርስ የምጠበቅ ልጅ ..በልጅነቴ ተደፈርኩ ...እናቴ የኔን ክብር ማጣት በአይኗ አየችዉ፡፡
የምትለዉ ስታጣ ጩኸቷን አቀለጠችዉ.
  የእኛ ሰፈር የሚኖሩ ሰዉ አንድም ሳይቀር ልጅ ትልቁ ወጣቱ ሽማግሌዉ የኔን መደፈር በአንዴ ታወቀ...ቶፊቅም አፍሮ ለጊዜዉ ከአካባቢዉ ተሰወረ፡፡ ሰራተኛችን በሂደት ሁሉንም ነገረችኝ፡፡

   ከሁሉም ሰዉ የቤት  ሰራተኛችን ትሻለኛለች እሷ ትረዳኛለች፡፡ ቤተሰቦቼ ጋር ብር እርዚቅ ቤታችን ላይ ይኑር እንጂ ምንም ስምምነት የለም... ሁሌ መጣላት ነዉ ስራቸዉ፡፡ የመጨረሻ ልጅ እህቴ ከተወለደች ቡሀላ እናት እና አባቴ አንድ ላይ  ሲተኙ እንኳ አይቻቸዉ አላቅም፡፡
     የኔ ስነ ልቦና ጫና እያለብኝ ግን ቤተሰብ ባለመስማማታቸዉ እኔን ከጎኔ ሁኖ አብሽሪ እያለ የሚያፅናናኝ ቤተሰብ ዘመድ ጎረቤት ጓደኛ የለኝም ፡፡

   ቶፊቅ በኔ ላይ የሰራዉ በደል ትዝ ሲለኝ ብቻየን አልቅሼ እምባየን የሚጠርግልኝ የለ እኔዉ እራሴ በአስሩም የእጅ ጣቶቼ እያቀያርኩ ከፊቴ አብሰዉ ይዣለሁ፡፡ ለማን አልቅሼ ነግሬ አብሽሪ ይበለኝ ??? ማን ነዉ ከጎንሽ ነን የሚለኝ ???

አንዳንዴ ይሄ መደፈሬ ትዝ ሲለኝ ብቻየን ሁኜ ድብር ብሎኝ ስቀመጥ....አባቴ በከፋኝ በደበረኝ ቁጥር ከጎኔ ሁኖ ነዋል ምን ሆንሽብኝ?ደብሮሻል ፊትሽ ተቀያይሯል እኮ እያለ  ያፅናናኝ ነበር ....
ግን ይሄንን ወሬ ሰራተኛችን ስለነገረችኝ ለአባቴ መናገር አልችልም፡፡ ያለኝ አማራጭ አባቴ ጋር ስሆን ደስተኛ ምንም ቅር ያላለኝ በሒወቴ የተደሰትኩ እመስላለሁኝ..ብቻየን ስሆን ደግሞ ባለቅሰዉ ባለቅሰዉ ደግሜ ባለቅሰዉ ምንም ሊወጣልኝ አልቻለም ፡፡እምባየ አለማለቁ ለራሴ ይገርመኛል
   ደግሜ ከእኔ ቁስል በላይ የሚያመኝ እናት እና አባቴ ማታ ማታ በተጣሉ ቁጥር እኔ ሌላ ሀዘን ለቅሶ ጭንቀት ነዉ ፡፡ ለማን አግዛለሁ ?? ማን ጥፋተኛ እንደሆነ አላቅም ግን ሲመስለኝ እኔ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይታወቀኛል

ግን ብዙዉን ጥፋቱ እናቴ ትመስለኛለች..ሁሌም ቢሆን ነገር አፈንፍና ነዉ የምትጣላዉ

   እናት እና አባቴ ትዳራቸዉን አይፋቱ እኛ ሶስት ልጆች ተፈጥረናል ፡፡ ተስማምተዉ አይኖሩ መስማማት አልቻሉም ፡፡ ብር ሀብት ሳያንስ ግን መስማማት ባለመቻላቸዉ አላህ የሰጠንን ሀብት ንብረት በደስታ መጠቀም አልቻልንም ፡፡

  ከእናቴ በላይ አባቴ በጣም ይቀርበኛል የቶፊቅን በደል አብሽሪ አይዞሽ አይለኝም..ለምን እኔ የማቅ አይመስለዉም ፡፡ ይሄን ሚስጥር ማወቄን ቢሰማ ቀጥታ ሰራተኛችን ጋር እንደሚጣላ እርግጠኛ ነኝ
 
አባቴ ግን ሁሌ ባገኘኝ ቁጥር በዙ ቀን እየደጋጋመ ፀጉሬን እያሻሸ አንቺ ባትፈጠሪ ኑሮ እናትሽ ጋር መለያየታችን አይቀርም ነበር ...እናትሽ ጋር ለመፋታት አስብ እና አንቺ ትዝ ስትይኝ እንደገና እተወዋለሁ ይለኛል፡፡
ሁሌም ቢሆን የአይኔ ማረፊያየ ነሽ..አላህ ይጠብቅልኝ ብሎ ግንባሬን ሳም አርጎኝ ስሄድ የሆነ ደስ የሚል ስሜት ይፈጥርልኛል..ልቤም እንደመረጋጋት ይላል👇👇👇
   ከልጅነት ጀምሬ የምቀራረበዉ ኡስማን  ትምህርት ቤት አንድ ስለሆነ ቁርአን ቤትም እንገናኛለን እሱም ቁርአን ላይ ጠንክሯል፡፡ ቁርአናችንን እየተዉን እቤታቸዉ እየሄድን ባንጫወትም ግን እኔ እና እሱ የልጅነት ፍቅር ተብየ በሁለታችን ልብ ዉስጥ አለ
   ኡስማን ጋር ከአንደኛ ክፍል እስከ ሰባተኛ ክፍል ድረስ ስንማር አንድ ትምህርት ቤት ስለነበርን የፍቅር ይሁን የልጅነት ነገር ይሁን አላቅም ኡስማንን ሳየዉ ፍዝዝ የማለት ልቤ እንደመደንገጥ ሰዉነቴ አልታዘዝ አልታዘዝ እንደማለት ይሆናል ፡፡ ግን ፍቅር ማለት ምን ማለት ነዉ??
በነብዩ ጊዜ የነበሩ ሱሀቦች ፍቅርን እንዲህ ነበር የተረጎሙት

★★★በአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጊዜ በኡሁድ ዉጊያ ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ተገድለዋል የሚል ዜና መዲናን እየናጣት ነበር ..የመዲና ሰማይ በዚህ አሳዛኝ ወሬ በሀዘን አጥልሏል..መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ኡሁድ አቅጣጫ እየተመመ ነዉ
ከአንሶሮች መካከል የሆነችዉ ሱመይራ(ረ.ዐ) ሁለት ልጆቿ አባቷ ባለቤቷና ወንድሟ ሰማዕት መሆናቸዉን ተረዳች ..ሱመይራ እነዚህ ሁሉ ወገኖቿ ቢሞቱባትም በዚህ ሁሉ የሀዘን ዉርጅብኝ አልተናወፀችም ..እልቁንስ እሷን ያስጨነቃት በእዉነት የታወቀዉ የጓጓችለት አንድ ዜና አለ ይህም የነብዩ ሰ.ዐ.ወ በሒወት መኖር ነዉ
..በእርሳቸዉ ላይ የደረሰ አንዳች ክፉ ነገር አለ??በማለት ጠየቀች
...የነብዩ ባልደረባዎችም ለአላህ ምስጋና ይገባዉ እርሳቸዉ በሒወት ይገኛሉ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ አሏት
ሱመይራ እንዲህ አለች ፡-እሳቸዉን እስከማይ ድረስ እረፍት አላገኝም የአላህ መልዕክተኛን (ሰ.ዐ.ወ)አሳዩኝ አለች
እሳቸዉን እንዳሳዩዋትም በቀጥታ ወደ እርሳቸዉ በመሄድ የካባቸዉን ጫፍ ከያዘቼ ቡሀላ እንዲህ አለች
"""""እናቴና አባቴ መስዋት ይሁንለልዎ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!እርስዎ በሂወት እስካሉ ድረስ ሌላዉ ሁሉ ቀላል ነዉ ..ያ በነብዩ ዙሪያ የነበሩ የተባረከ ትዉልድ ለእርሳቸዉ ይህን የመሰለ ድካ የሌለዉ ፍቅር ይለግሳቸዉ ነበር ...እኛስ?? ፍቅርን በሰዉ አይደል የምናመሳስለዉ ???

  እኔ ስድስተኛ ክፍል በምማርበት ጊዜ ኡስማን ጋር ብዙ ጊዜ ቁርአን ቤት እና ትምህርት ቤት እንገናኛለን ቁርአን እቀራለሁ እንጂ ሶላት አልሰግድም ለዚህም ምክንያት ቤተሰቦቼ ስገጅ ብለዉ ስለማያበረታቱኝ ነዉ ...   ትምህርት ቤት ስሄድ ሱሪ እለብሳለሁ ..

ሱሪ በምለብስ ጊዜ ኡስማንም ቁርአን ቤት ስትመጪ ሒጃብ ትለብሻለሽ ትምህርት ቤት ደግሞ ሱሪ ትለብሻለሽ አንዴ ቃልቻ አንዴ ዱሪየ እስታይል አትከይ ከአሁን ቡሀላ ትምህርትም ስትመጪ ሱሪ ለብሰሽ እንዳትመጪ ብሎ ይቆጣኛል፡፡
....እኔም እሺ ከአሁን ቡሀላ አለብስም አልኩት

እኔ ከኡስማን ጋር ጊዜ ማሳለፍ እሱም እኔ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ደስ ይለዋል፡፡ ኡስማን ጋር ከትምህርት ቤት ስንመለስም ስንሄድም ተቃቅፈን ነዉ....የክላስ ልጆች ነዋል እና ኡስማን እኮ ይዋደዳሉ ተቃቅፈዉ ነዉ የሚሄዱት እያሉ ሁሌ ያወራሉ ፡፡ አዎ እዉነታቸዉን ነዉ የኡስማን ሰፈር ቆሎ በር አካባቢ ነዉ፡፡ አንዳንዴ እኔን አጂፕ ድረስ ይሸኘኛል
 
አሁን ድረስ የሚገርመኝ ሁሌ እቤቴ ስሄድ ሶላት ባልስግድም __ግን በዱአ አላህን በመለመን አምን ነበር፡፡ መስገጃ ቦታ ላይ ሱጁድ ወርጄ  ስቅስቅ ብየ እያለቀስኩ ያረቢ  ኡስማንን የኔ አድርግልኝ ኡስማን የኔ የወደፊት ባሌ አድርግልኝ አንዴ የፍቅር ጥያቄ ይጠይቀኝ እምቢ አልልም እንዲጠይቀኝ አርግልኝ  እያልኩ አላህን እለምናለሁ ፡፡
   ግን ቢጠይቀኝ ገና ልጅ ነኝ ምን እለዋለሁ??? እንዴ ሁለታችንም ልጆች ነን ትዳር የማይታሰብ ነዉ እንዴት ይሄንን ሀሳብ ልመኝ ቻልኩኝ??? ደግሞ ለኡስማን የተለየ አመለካከት ቢኖረኝም ወንድ ልጅ እንደ ቶፊቅ ጨካኝ ቢሆንስ እያልኩ ብቻየን የሀሳብ ማዕበል ወስዶ ይመልሰኛል ..ነገር ግን ኡስማንን መራቅ የማልችልበትም ደረጃ ላይ ነኝ፡፡

ትምህርት ቤቶች ላይ ጥንቃቄ ግድ ነዉ ትዉልዱ ገና ከአራተኛ ክፍል ጀምሮ ሌላ መስመር ይጀምራል...ቤተሰብ ልጄ ገና ህፃናት የሚለዉን የድሮ ተረት ትተዉ  ልጅን እንደልጅ ሳይሆን እንደ እህትነት አርገዉ ቢቀርቡ የተሻለ ነዉ..አንድ ሰዉ ሁሌ የሚናገራት ንግግር ትዝ ይለኛል የሴት እና የአር ትንሽ የለዉም ይላል እዉነቱን ነዉ ሴት ልጅ ገና ልጅ ናት ቢባል በወንድ ልጅ አፍ መሸወዳ አይቀርም..አርም ትንሽ ብትሆን መሽተቱ አፍንጫ መረብሹ ስለማይቀር ወላጅ የትምህርት ቤት አዋዋልን ልብ ሊል ይገባል ባይ ነኝ፡፡
  
ኡስሚ አንዳንዴ እየቀለደ ነዋል አፈቅርሻለሁ እኮ ምናምን ሲለኝ እዉነት እየመሰለኝ ልቤ ድንግጥ ይላል ወይ የልጅነት ፍቅር ...








#ክፍል 5⃣
ይ.......ቀ.......ጥ
......ላ........................ል


JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
   
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
🎖የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ አምስት 5⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ


ኡስሚ አንዳንዴ እየቀለደ ነዋል አፈቅርሻለሁ እኮ ምናምን ሲለኝ እዉነት እየመሰለኝ ልቤ ድንግጥ ይላል ወይ የልጅነት ፍቅር ...
ሴትን ልጅ ሁለት ቃላቶች ላይ ልባቸዉ ይንጠለጠላል አንደኛዉ፡-እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ የሚባለዉን ቃል ሲሰሙ እዉነትም ይሁን ዉሸት ልባቸዉ ይሰረቃል ሁለተኛዉ ደግሞ በመንገድ ላይ እየሄዱ ቅናሽ እቃ ይሄቃ በዚህ ዋጋ ነበር አሁን ቀንሶ በዚህ ዋጋ ሲባል ከሰሙ አሁንም ልባቸዉ ይንጠለጠላል....
 
..የክላስ ልጆች ኡስማንና ነዋል ይዋደዳሉ ሲባል ደስ ይለኛል...ግን ኡስማን ይሄን ወሬ ሲሰማ በጣጣጣም ይቆጣል ይናደዳል ..ነዋልን ወላሂ የማያት እንደ እህቴ ነዉ በሌላ አይን አትዩን እያለ የክፍል ልጆች ጋር ብዙ ቀን ተጣልቷል
 
ኡስማን ጥፋት ሳጠፋ በጣም ይቆጣኛል... በአለባበሴም ቀን በቀን ምን ልብስ እንደለበስኩ ይከታተለኛል ሱሪ ለብሼ ስመጣ ስለሚቆጣኝ ሒጃብ መልበስ ክሪም መልበስ ኡስሚ እንዳይቆጣኝ እያልኩ በዛዉ ሂጃብና ክሪም መልበሱን ጀመርኩኝ .... ከትምህርት እንደተለቀቅን እቤታችን ደርሰን ሁሌም ቁርአን ቤት እንሄዳለን ፡፡ ኡስማንን እኔ ብወደዉም እሱ ግን እንደ እህት እንጂ ሌላ አስቦ በጭራሽ አያቅም ልቡን አሳምኖታል፡፡

ቁርአን ቤት እየሄድን ...ነዋል ቁርአን ማን ጋር ደረሽ??? ልታከትሚ ስንት ጁዝ ቀረሽ ?? ትናንትና ስንት ፊት ቀራሽ?? እያለ ቀን በቀን ይቆጣጠረኛል ...........ነዋል ነግሬሻለሁ ቶሎ አክትሚ እና የቁርአን ክትሚያ በግ አርደሽ አብሊን እያለ በጣም ይከታተለኛል ...ኡስሚ በጣም ጥሩ ልጅ ነዉ..እሱ በቁርአን ይበልጠኛል ነገር ግን እኔ እንደአክትም ይቆጣጠረኛል...
   ሶላት መስገድ የጀመርኩት በኡስማን ነዉ በፊት የምሰግደዉ በረመዷን ብቻ ነበር..የረመዷን ቃልቻ ነኝ ማለት ነዉ..

የአሁኑ ዘመን ፋሽን ተከታይ ነን ባዯች የአሁን ዘመን
እኛዉ ትዉልዶች ለሶላት ያለን አመለካከት በጣም ዝቅተኛ ነዉ

በፊት የነበሩ ምርጥ ትዉልዶች ለሶላት ያላቸዉ አመለካከት ምን ይመስላል ???እስኪ ከዓሊ (ረ.ዐ) እንጀምር

★★★ዓሊ(ረ.ዐ)እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዉ ነበር ፡-የምእመናን አዛዥ ሆይ! የሶላት ሰአት ሲቃረብ የፊትዎ ቀለም የሚቀያየረዉና የሚንቀጠቀጡት ለምንድን ነዉ ??
ዓሊ (ረ.ዐ) እንዲህ በማለት መልስ ሰጡ """ይህ ሰአት ሰማያትና ምድር እንዲሁም ተራሮች ሊሸከሙት እንዳልቻሉ በመግለፅ ያልተቀበሉትን አደራ ወደ ባለቤቱ የመመለሻ ሰአት በመሆኑ ነዉ ፡፡እኔ በትክክል መቻሌን አለመቻሌን አላዉቅም

★★★የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የልጅ ልጅ የሆነዉ ሀሰን(ረ.ዐ) ምን ጊዜም ዉዱዕ ባደረገ ቁጥር ፊቱ ይገረጣ ነበር
አንድ ዕለት አንድ ሰዉ ሀሰን ሆይ!!! ዉዱዕ ባደረግክ ቁጥር ፊትህ የሚገረጣዉና ወደ ቢጫነት የሚቀየረዉ ለምንድን ነዉ ?? በማለት ጠየቀዉ
ሀሰን (ረ.ዐ) የሚከተለዉን መልስ ሰጠ፡- ብቸኛዉ የሀይል ባለቤት ታላቅና ባለግርማ ከሆነዉ አላህ ፊት የመቅረቢያ ሰአት  በመሆኑ ነዉ ""
ሀሰን(ረ.ዐ) ወደ መስጊድ ሲገባ የሚከተለዉን ዱአ ያደርግ ነበር፡-
ጠባቂየ ሆይ!!!! ባሪያህ በቤትህ ደጃፍ ላይ ደርሷል፡፡ምህረት ሁሉ በእጅህ የሆነዉ ሆይ!!! ሀጢያተኛዉ ባሪያህ ወደ አንተ መጥቷል ፡፡ ቅን ባሪያዎችህ ሌሎች ሰዎች የሰሩባቸዉን መጥፎ ነገር ይቅር እንዲሉ አዘሀል፡፡ ምክንያቱም አንተ ይቅር ባይና ቸር ነህ፡፡ አላህ ሆይ በተለመደዉ ይቅሬ ባይነትህና ምህረትህ በደሌን ይቅር በል .እዘንልኝም፡፡ ብለዉ ለሶላት ክብር ፍራቻ ነበራቸዉ እኛስ ??ብዙዎቻችን የመስጊድ ሙአዚን አዛን ሲል ሳንጠላዉ እንቀራለን ብላችሁ ነዉ?? ከኔ ጀምር ማን ነዉ አላህን ፈርቶ ሶላትን የሚሰግደዉ??? መልሱን ሁሉም በየቤቱ

       ትምህርት ቤት ሱሪ ለብሼ መምጣት ሙሉ በሙሉ አቁሚያለሁ .........ቤተሰቦቼ ሶላት ስገጅ አይሉኝም ፡፡ ኡስማን ግን ትምህርት ቤት እና ቁርአን ቤት ስንገናኝ ሶላት ሰገድሽ ወይ እያለ ይጠይቀኛል እኔም አንዳንዴ ሳልሰግድ ሰገድኩ እላለሁ ...ኡስማንም ወላሂ በይ እንዳትዋሺ ዉሸት ሀራም ነዉ ይለኛል...እኔም በቃ ሙሉ በሙሉ ሶላት መስገድ ጀመርኩኝ አልሀምዱሊላህ....... እንደዚህ ኡስማን ጋር አሳልፈን ስድስተኛ ክፍል ጨርሰን ክረምት ገባ
በክረምት ግን ኡስማን ጋር ቁርአን ቤት እንገናኛለን ፡፡ ግን ያዉ ቁጥጥሩ ቁርአን ቅሪ ሰገድሽ ወይ ነዉ......

ኡስሚም ቁርአን ሲከታተለኝ በእኔም ጥረት ቁርአኔን ስድስተኛ ክፍል እንዳለሁ አከተምኩኝ፡፡አልሀምዱሊላህ ቁርአን ሳከትም ቤታችን በግ ታርዶ ተሰድቆ ተበላ፡፡ ከዛም ምላሽ መቅራት ጀመርኩኝ፡፡

ክረምት አልቆ ለበጋ ለአዲስ አመት ጊዜዉ አስረከበ ሰባተኛ ክፍል ተመዘገብኩ ....የትምህርት ቤት ተማሪዎች ኡስማን እና ነዋል በጣም ይዋደዳሉ እየተባለ መወራቱ በሰፊዉ ሁኗል .......ፍቅር የጀመርን አስመስለዉታል ሁሉም ተማሪ ኡስማን እና ነዋል ይዋደዳሉ ነዉ የሚሉት እኔ እንደዚህ ሲወራ ደስ ይለኛል ....
........መቼም ሴት ነኝ እና ከብዙ ሴቶች ጋር ማዉራቴ አይቀርም ..አንድ ቀን ለትምህርት ቤት ጓጀኞቼ የሞቀ ወሬ ይዘን እያወራን ዉሸቴን ኡስማን እኮ የፍቅር ጥያቄ አቀረበልኝ እወድሻለሁ አለኝ ብየ ለሁሉም ነገርኳቸዉ....
....... ይሄ የዉሸት ወሬ ኡስማን ጆሮ ሳይዉል ሳያድር ደረሰ.....


ኡስማን ጋር ከትምህርት ቤት ተለቀን አብረን ስንሄድም ቁርአንቤትም ስንገናኝ የፍቅር ጥያቄ አቀረበልኝ ብለሻል እንዴ ??? ብሎ እንኳ አልጠየቀኝም ....እኔ ግን ዉሸት ስለሆነ በተናገርኩት ቃላት አፈርኩኝ ግን ኡስሚ ሰምቶ ባልሰማ አለፈዉ....
  
ኡስማን በልጅነቴ መደፈሬን ያቃል ..,የኛ ሰፈር ልጆች እኔ ጋርም የተጣሉት እሱ ጋር በጣም ይግባባሉ ፡ለምን እሱ ወንድም ሴትም ይቀርበዋል እንኳን ይሄን ብዙ ሚስጥር ይነግሩታል፡፡ የኔ በልጅነቴ መደፈር በትምህርት ቤት ሳይቀር የሚወራ ወሬ ነዉ፡፡ ለኔ ያለዉ አመለካከት ቀረቤታ ምንም ነገር አልቀነሰብኝም....ከወንድሜ በላይ አስበልጬ ነበር የምወደዉ ...የወደፊት የትዳር አጋሬ ቢሆን ዱአየ ነዉ፡፡ አላህ ያሳካልሽ በሉኝ

  
   ትምህርት እየተማርን አንድ ቀን የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ነዋል እኮ በልጅነቷ ተደፍራለች ድንግል አይደለችም እያሉ ወሬዉን እንደ አዲስ ሰበር ዜና አናፈሱት .....እኔም ይህን ወሬ በጆሮየ ስሰማ መናደድ ማልቀስ ሆነ ስራየ .............
ይሄን ሚስጥር ያልሰሙትም እየመጡ ይጠይቁኛል...ምን መልስ አለኝ ቀን በዝምታ ማታ ከማልቀስ ዉጭ... በዚህ ወሬ እየተደጋገመ ሲወራ የክፍል ጓደኞቼም የማቃቸዉ ልጆች ሳይቀር እየጠየቁኝ ስቸገር .. ክፍል ዉስጥ ተቀምጦ መማር  እያስጠላኝ ጥያቄዉን ሲጠይቁኝ በጣም ስናደድ ትምህሬን ቀጥቼ እወጣና እዛዉ ት/ቤት ግቢ ዉስጥ ብቻየን ቁጭ ብየ እንባየን በማፍሰስ መደፈሬን ለመርሳት እሞክራለሁ ግን የማይረሳ የማይፋቅ ክስተት መቀየር አይችል ምን ይደረጋል ወደ ሰማይ ቀጥ ብሎ አልቅሶ ወደ መሬት እምባ ከማፍሰስ በቀር..ትምህሬትንም በተረጋጋ መልኩ ልማር አልቻልኩም ..ትምህርት ቤት የምሄደዉ እቤት ለምን አትሄጂም እንዳልባል ብቻ ነዉ እንጂ ትምህርት ቤት ግቢዉ ክላስ እየቀጣሁ ብቻየን ማሳለፍ ከጀመርኩ ሰነባብቻለሁ👇👇
አንድ ቀን እረፍት ሰአት ላይ ቁጭ ብየ ብቻየን እያሰብኩ ናርዶስ የምትባል የክፍላችን ልጅ ...ወደ እኔ መጥታ ከጎኔ ቁጭ አለች.......
.....ናርዶስም ነዋል በሰላም ነዉ ብቻሽን ቁጭ ያልሽዉ ?? አለችኝ
.......እኔም አዎ በሰላም ነዉ ከይቅርታ ጋር ብቻየን መሆን ፈልጌ ነዉ ናርዶስ ብቻየን እንደሆን ፍቀጅልኝ ......የምፈልጊኝ ከሆነ ክፍል ስንገባ እንገናኛለን አልኳት
......እሺ ነዋል አንድ ነገር ብቻ እንድናገር ፍቀጅልኝ ብቸኝነት አታብዢ አትጨናነቂ የሰዉ ወሬ እንደሆነ መቼም አያልቅም የዘንድሮ ሰዉ እንዳያወራ አፉን ቢዘጉት በቂጡ ማዉራቱ አይቀርም.....ከአንቺ የባሰ ሒወት የሚኖሩ አሉ እኮ የኔ ተመስገን የተሻለ ነዉ ያስብላል አንቺም ልትይ ትችያለሽ......ስለሆነም አንቺ ስታለቅሺ ስትተክዢ ማየት አልፈልግም ...ለምን ብትይ አንቺ ለኔ ጥንካሬ ብርታት እንድትሆኚኝ እፈልጋለሁ ነዋል አለችኝ
........እኔም ግራ ገባኝ ከአሁን በፊት ናርዶስ ጋር ብዙም አንግባባም ከክፍል ጓደኝነት ዉጭ.....ሚስጥር አዉርታኝም አዉርቻትም አታቅም አላዉቅም ......ናርዶስ የክርስቲያን ሀይማኖት ተከታይ ናት """ምን ለማለት ፈልገሽ ነዉ?? አልገባኝም"""አልኳት
.......ናርዶስም፡- ቅዳሜ ከሰአት ብንገናኝ በሰፊዉ ላወራሽ እችላለሁ ይመችሻል ??? አለችኝ
........እኔም አዎ ይመቸኛል አልኳት......
ናርዶስም እሺ ቅዳሜ 10 ሰአት ላይ ዶሎሎ ሆቴል መናሀሪያ አካባቢ እንገናኝ አለችኝ
.....እኔም እሺ እንገናኛለን አልኳት፡፡ ከዛም እረፍት ሰአት አልቆ  ተደዉሎ ወደ ክላስ ገባን....

ናርዶስ ያለችኝ ነገር በጣም ግራ ገባኝ በአእምሮየ እየደጋገምኩ ማብሰልሰል ጀመርኩ""" ከአንቺ የባሰ ሒወት የሚኖሩ አሉ እኮ የኔ ተመስገን የተሻለ ነዉ ያስብላል አንቺም ልትይ ትችያለሽ......ስለሆነም አንቺ ስታለቅሺ ስትከዢ ማየት አልፈልግም ...""" እንዴት እንዲህ ልትለኝ ቻለች???? እያልኩ ብቻየን ማሰብ ይዣለሁ.........

የተቀጣጠርንበት ቀን ቅዳሜ ደረሰ በተባባልነዉ በ10 ሰአት ስሄድ ናርዶስ ጋር ጅማ የሚገኘዉ ዳሎል ሆቴል ተገናኘን ...ከዛም ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ወንበር ይዘን ተቀምጠን
የሚጠጣ አዘን አንዳንድ ወሬ ካወረን ቡሀላ ....>>>>>ምንድን ነበር የምነግሪኝ ናርዶስ??? አልኳት
.....ናርዶስም አደራ የምነግርሽ ቤተሰቦች ወንድሜም እህቴም እናት እና አባቴ የማያቁት ሚስጥር ነዉ......የምናቀዉ  ፈጣሪ  እኔ እና ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ አንቺ ነሽ...ስለሆነም ሚስጥራችን እዚሁ ይቅር አለችኝ
..........ከዛም እሺ ናርዶስ ለማንም አላወራም ብየ ቃል ገባሁ
>>>>>>>>_ናርዶስም ወደ መሬት አጎንብሳ የምታወጣቸዉን ቃላቶች ከየት ልጀምር እያለች እንደ ምጥ ከብዷታል.......ምን መሰለሽ ነዋል እኔ በልጅነቴ ....................___


#ክፍል 6⃣
ይ...........ቀ........
.........ጥ.........ላ.............ል


Join👇👇

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEOFXIlKIXVySUTDcA
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ ስድስት 6⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ


...ምን መሰለሽ ነዋል እኔ በልጅነቴ ... ገና የስድስት አመት ልጅ እያለሁ አጎቴ ጋር ከአባቴ በላይ በጣም እንቀራረብ ነበር ....ከመቀራረባችን የተነሳ አጎቴ ቤት እየሄድኩ አድር ነበር ..አንድ ቀን እንደተኛሁኝ አጎቴ ገና በስድስት አመቴ የልጅነት ህልሜን አበላሸዉ ...ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ የተኛሁበት አልጋ ደም በደም ሁኖ አገኘሁት... በህፃንነቴ በምወደዉ አጎቴ ተደፈርኩኝ....ከዚች ቀን ቡሀላ
አፈርኩኝ ደነገጥኩ አጎቴን ተዉ የምልበት ድፍረት እና ቃላት አጠረኝ... ወደ ቤቴ ከተመለስኩ ቡሀላ ይህንን ወሬ ለእናት እና አባቴ ሳልናገር ዝም አልኩኝ..........
.....አጎቴ በሰራዉ ስራ አፍሯል ከደፈረኝ ቀን ጀምሮ እሱ ቤት መሔድ አቆምኩኝ እሱም ወደ እኛ ቤት መምጣት አቆመ ....
እናት እና አባቴ ምን ሁነህ ጠፋህ??? ሲሉት የተለያየ ዉሸት እየደረደረ እኛ ቤት መምጣቱን አቆመ .....በልጅነቴ ይህን ጉድ ተሸክሜ ብቻየን ሳለቅስ ኖርኩኝ ፡፡
     ይሄዉ በደሌ ይሄዉ ግፍ ፈጣሪ አይበቃሽም ብሎኝ ደግሞ አጎቴ በደፈረኝ ከአንድ አመት ቡሀላ የአባቴ ጓደኛ እቤት መጥቶ አባቴም እናቴም የሉም ነበር ከዛም አባትሽ እስከሚመጣ እዚሁ ልጠብቀዉ አለኝ
...እኔም እሺ ብየ እቤት አሰገባሁት
ሳላወቀዉ ቁጭ ባልኩበት መጥቶ በጉልበት አስፈራርቶ የሚፈልገዉን በለጋ ሰዉነቴ የሚሰቀጥጥ ተግባር  ፈፀመብኝ ....በአባቴ ጓደኛ በእድሜዉ በገፋ ሰዉ ሁለተኛ በልጅነት የመደፈር ሰለባ ሆንኩኝ ......እግዚአብሔርን እስከ አሁን እናት እና አባቴ ይሄንን ሚስጥር አያቁም ...የምነግረዉ የለኝ የሚረዳኝ የለም ፡፡ ለአንቺ ስነግርሽ ትንሽ ቀለለኝ ብላ ...እምባዋን ቁልቁል ዘረገፈችዉ፡፡

ናርዶስ ስነግረኝ ጀምራ እምባየን መቋቋም አልቻልኩም ነበር ህመምህን መንገር ያለብህ ታሞ ለሚያቅ ሰዉ ነዉ ይባል የለ...እኔ ስነግረኝ እኔም በልጅነቴ የደረሰብኝ ትዝ እያለኝ አለቅስ ይዣለሁ፡፡ ሁለታችንም እያለቀስን ሁለታችንም ባለብሰተኞች ነን፡፡ በሆዳችን የፉም እሳት ነበልባል ተሸክመን ነዉ የምንሄደዉ ..ይሄ ነበልባል ሆድ ዉስጥ ይቀጣጠልና ቢተነፍሱት ለሰዉ ለመድረስ የሚከብድ ቀጥታ ወደ አይን ሂዶ አይንን ለብልቦ በእምባ የሚወጣ የማያባራ ጊዜ ቦታ የማይመርጥ እንደ ወራጅ ወንዝ መቆሚያ የሌለዉ ስቃይ ነዉ፡፡

ካፌዉ ዉስጥ ያሉ ሰዎች ትኩረታቸዉ ወደ እኛ ነዉ እኔ እንደምንም እምባየን ተቋቁሜ ናርዶስን እምባዋን እየጠረኩ አባበልኩኝ
   የዘንድሮ ሴቶች የሚያለቅሱት ወንጀል ሰርቻለሁ ሀራም ሰርቻለሁ ሳይሆን ጓደኛየ እወድሻለሁ ብሎኝ ተወኝ ሌላ አገባብኝ ሁኗል፡፡ እኛ ግን በህፃንነታችን በመደፈራችን ነዉ የእድል ነገር ሁኖብን ፈጣሪ ግፉን አሸከመን...

.......ናርዶስም እንደዚህ አለችኝ ነዋል የአንቺ የአደባባይ ሚስጥር ሁኖ ነዉ እንጂ ብዙ ሴቶች እኮ በጎረቤት በዘመድ በአባት ሳይቀር የልጅነት ህልማቸዉ የተበላሸባቸዉ ቤት ይቁጠረዉ ስለሆነም ከአሁን ቡሀላ ማንም ቢናገርሽ እንዳታለቅሺ ቆራጥ ጀግና ሁኚ...የበታችነት ሳይሰማን ተምረን ጥሩ ደረጃ ላይ ደርሰን እንደዚህ ያሉ እህቶቻችንን መርዳት አለብን አለችኝ፡፡
...እኔም እሺ ቃል ገብቻለሁ ለሰዉ ወሬ ትኩረት ላልሰጥ በትምህሬቴም ጠንክሬ ተምሬ በሴት ልጅ የሚደርስን በደል ግፍ ከእህቶቼ ጎን ለመቆም ወሰንኩኝ
....ከዛም ከካፌ ወጥተን ከአሁን ቡሀላ ሀይማኖታችን ላያግደን ጓደኛ ልንሆን ቃል ተገባብተን አንቺም ከጎኔ ሁኚ እኔም ከጎንሽ አለሁ ተባብለን ተለያየን፡፡

የኡስሚ ጓደኛነት እንዳለ ሁኖ ናርዶስ ጋር ምርጥ ጓደኞች ሁነናል ...ናርዶስ ጋር ስለ ድንግልና ስናወራ ለወደፊት ለሚያገባን ባላችን ስንጠየቅ ምንድን ነዉ ግን የምንለዉ ???ብየ ጠየኳት
>>>>>>>>> ነዋል እኛ እኮ ፈልገነዉ ስሜታችን አስቸግሮን ድንግልናችንን አጥተናል እንዴ ???አላጣንም እኮ...ሳንወድ በግዳችን ነፍስ ሳናቅ በልጅነታችን የድንግልና ትርጉሙን ሳናቅ  ነዉ  በማያስቡ ሰዉነት በማይሰማቸዉ በስሜታቸዉ ያደሩ ወንዶች የተነጠቅነዉ ስለሆነም እኛ ሁሌም ቢሆን ድንግል ነን ....>>>>እኔ ሁሌ እራሴን የማሳምነዉ ድንግል ነኝ ብየ ነዉ አለችኝ፡፡ እኔም ናርዶስ እንደዚህ ካለች ቡሀላ እኔ ድንግል ነኝ ብየ እራሴን አሳመንኩ ለምን ምንም የድንግል ጥቅም ሳላቅ በልጅነቴ ስላጣሁት እራሴ ድንግል ነኝ ብየ አሳመንኩኝ....
ከዛ ቡሀላ በልጅነትሽ ተደፍረሻል ቢሉኝም ወሬ ቢያወሩ ምንም አይመስለኝም ነበር ግን ጠባሳዉ ባይለቀኝም......እራሴን አሳመንኩኝ ለዘንድሮ ሰዉ ጆሮ ላልሰጥ ብየ ...... ሰዉ ቢያወራ ቢጠቋቆሙብኝ ምንም አይመስለኝም........

ለሁሉም ነገር የሰዉንም ትችት ለመቋቋም ትዕግስት ማድረግ እንዳለብኝ እራሴን አሳመንኩኝ ...
ግን የኛ ትዕግስት እስከ የት ነዉ??? ተወዳጁ ነብያችን ሀቢቡና ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ
ስድስት ልጆቻዉን በተለያየ ጊዚያት በራሳቸዉ እጅ ከመቃብራቸዉ ዉስጥ ካስገቡ ቡሀላ የህሊና ሚዛናቸዉ ሳይዛባ ሁሉንም ዋጥ አርገዉ በትዕግስት የሚኖር በዚህ አለም ግን እንደ ነብዩ ሙሀመድ
ሰ ዐ.ወ ይገኛልን ??ከልጅነት እስከ እዉቀት በዚህ ሁሉ መካራ እንደ አላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)የተፈተነ ይገኛልን??በዚህ አለም ይህ ሁሉ የመከራ መደራረብ የተፈራረቀበት ይህም ሁኖ ጌታዉን የሚያመሰግን ከነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ዉጭ ሌላ ሰዉ ፈፅሞ አይገኝም ...
አላህ ሆይ ለኔም ለዚህ ለተፈፀመብኝ ነገር ትዕግስቱን ስጠኝ እያልኩ የዘወትር ዱአየ ነዉ...እናንተም በዱአ እገዙኝ

   እኛ ክፍል አንድ ሙባረክ የሚባል ልጅ አለ ...ሁሌ ቀን በቀን ለኔ የፍቅር ደብዳቤ እየፃፈ እንደሚወደኝ ለጓደኞቼ ይልክልኛል .....ወደ ሆላ ታሪኬ ሙባረክ ጋር ያለዉን ስንመለስ ሙባረክ ደብዳቤ መላክ የጀረዉ አምስተኛ ክፍል ጀምሮ ነዉ ........እኔ ግን ለሙባረክ ምንም ጥሩ አመለካከት የለኝም ከነመፈጠሩም ትዝ አይለኝ....የኡስሚ ያለኝ አመለካከት ግን እኔም ግራ ይገባኛል፡፡ አልርቀዉ አልቀርበዉ ነገር ....

ወንድ ሲባል እንደ ቶፊቅ ተጠቅሞ የሚጥለኝ ነዉ የሚመስለኝ ....ሙባረክን ከአሁን ቡሀላ ደብዳቤ ብትልክ ብትረብሸኝ ለአባቴ ነዉ የምነግረዉ ተወኝ ብያለሁ ብየ በደብዳቤ ላኩለት ከዛ ቡሀላ ........ሙባረክ ደብዳቤ መላኩን አቆመልኝ፡፡

      የሚገርማችሁ ከአንድ እስከ ስድስት በምማርበት ጊዜ ከአንድ እስከ አምስት ነበር የምወጣዉ ....ሰባተኛ ክፍል ግን ለቤተሰብ ለመንገር የሚያሳፍር ደረጃ ወጣሁኝ...ከሀምሳ ተማሪ ሰላሳ አምስተኛ ነበር የወጣሁት.......በትምህርት ደረጃየ እኔ በጣም አዘንኩኝ ሰባተኛ ክፍል መቀለዴ ዋጋ አስከፈለኝ......ለአባቴ ካርዴን ሳሳየዉ ቢከፋዉም እኔን መጥፎ ቃል መናገር አልፈፍግም ..፡፡ ነዋል አብሽሪ ለሚመጣዉ አመት ዋና ፈተናዉ ሚኒስትሪ ላይ ታሻሽይዋለሽ አለኝ፡፡
....አባቴ አብሽሪ ቢለኝም እኔ ግን ዉጤቴ በመዉረዱ በጣም ተናደድኩኝ፡፡👇👇👇
ክረምት አልፎ ስምንተኛ ክፍል ተመዘገብኩ ..ስምንተኛ ክፍል እያለሁ እኛ ክፍል የሚገኙ ሴት ልጆች ኡስማንን ...ነዋልን እወድታለሁ ብልሀል ወይ ?? እሷ እኮ ሁሌ ኡስማን የፍቅር ደብዳቤ ሰጠኝ እወድሻለሁ እለኝ እያለች ትነግረናለች እዉነቷን ነዉ እንዴ ?? ብለዉ ይጠይቁታል
.....እሱ ግን መልሱ ዝምታ ብቻ ነበር
የኛ ክላስ ልጆች በዉሸት እኔ እና ኡስማንን በተለያየ በዉሸቱም በእዉነቱም ወሬ ለማጣላት የማይፈነቅሉት ዲንጋይ የላቸዉ ነበር ..

እነሱም ከእሷ ምን አለህ አንተ እኮ ብዙ ላይፍ ይጠብቅሀል ካልወደድካት ተዋት እያሉ ብዙ ነገር ካሳመኑት ቡሀላ በማላቀዉ ምክንያት በተለያዩ ወሬዎች ኡስማን እኔን ዘጋኝ......ኡስሚ በእኛ ክላስ የተቀነባበረ ወሬ ጆሮዉን ሞልቶ እኔን ጀርባዉን ሰጠኝ...



ኡስሚም በፊት ቁርአን ቤት እንገናኝ ነበር ከቁርአን ቤት ወጥቶ እቤቱ ሸህ ይዞ ኪታብ መቅራት ጀመረ....ትምህርት ቤት ስንሄድ አብረን ነበር የምንመለሰዉ ..አሁን ለብቻዉ በባጃጅ ሁኗል የሚመላለሰዉ ... በሁሉም አጋጣሚዎች እኔን እራቀኝ አንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ኡስማን ጋር ተጣላን...

እኔም ምን አጥፍቼ ነዉ የዘገሀኝ ምን አጥፍቼ ነዉ የተዉከኝ ??? ብየ አልጠየኩትም ዝም ሲለኝ ዝም አልኩት ሲዘጋኝ ዘጋሁት ........ልቤ ፍቅር እንደማይገዛዉ .. ማንንም ወንድ ወደ ልቤ እንደማይገባ አየሁት ..ለምን አንዴ ቶፊቅ ጉድ ሰርቶኛል ..ወንድ እንዳላምን አርጎኛል..........ኡስማን ጋር አብረን በሆንበት ጊዜ ለኔ ባለዉለታየ ብቸኝነት አይሰማኝም ነበር.... እወደዉ ነበር አልክድም ከመዉደዴ የተነሳ አልቅሼም ዱአ አድርጌያለሁ ኡስሚን ለኔ አርግልኝ ብየ ......ግን የኔ ልብ የፍቅር ልብ ማንንም መዉደድ እንደማይችል ተረዳሁኝ......አሁን አንድ ጓደኛ አለችኝ እንደ እኔዉ በልጅነቷ ክብሯን ያጣችዉ ናርዶስ ብቻ ናት.......

   የሰባተኛ ክፍል ዉጤቴ መዉረዱ በጣሞ ስላናደደኝ አሁን ሀሳቤ እና አላማየ አንድ እና አንድ፡ብቻ ነዉ ይሄዉም ለሚኒስትሪ ጥሩ ዉጤት ይዞ ማለፍ እና አባቴን ማስደሰት ነዉ የምፈልገዉ.....


  ሰምንተኛ ክፍል ላይ ትምህርቴ ላይ ብቻ ፎከስ ማድረግ ብቻ ሁኗል ትኩረቴ .....ከትምህርት ቤት ጓደኞቼም እንደበፊቱ የማይጠቀም የማይጎዳ የጊዜ ማሳለፊያ ወሬ ማዉራት ..አፍ መካፈት ዘመናይ ነኝ ከሚባሉት ከሁሉም ነገሮች እራኩኝ........ አልሀምዱሊላህ ሶላቴን ተከታትዪ ሰጋጅ ሁኛለሁ
ቁርአንም ምላሽ እየቀራሁ ነዉ፡፡
   
   በተጨማሪም ትምህርት ቤታችን ያሉት ጎበዝ ሴት ተማሪዎች ጋር ላይብረሪ እየገባሁ ማጥናት ጀምሪያለሁ፡፡ እራሴን ለመቀየር ወገቤን ጠበቅ አርጌ ተነስቻለሁ... ግራ የገባኝ ነገር ቢኖር እኔ ሳጠና ናርዶስ በጭራሽ አላጠናም አለችኝ ...ናርዶስን ቀን በቀን ተስፋ ሳልቆርጥ ላይብረሪ እንግባ እናጥና ብላት ሁሌም ከአፏ የሚወጣዉ መልስ እምቢታ ብቻ ነዉ፡፡


ናርዶስ የሀብታም ልጅ ናት ቤተሰቦቿ ጅማ ከተማ ላይ ህንፃ እና ታዋቂ ሆቴል አላቸዉ ፡፡

ትጋብዘኛለች ...ናርዶስ ብር በጣም ታባክናለች አባቷ የወጭ እያለ ይሰጣታል ብዙም አያካብድም፡፡ ብር እንደፈለገች ስለሚሰጣት አዳዲስ ልብስ መልበስና የፈለገችዉን ምግብ መብላት መጠጣት የዘወትር ተግባሯ ነዉ ...
ከትምህርት ስንለቀቅ ብዙ ጊዜ ካፌ ትጋብዘኛለች

ናርድስ ስለምታባክነዉ ብር ግራ እየገባኝ ..ተይ ብር መበተኑ ማባከኑን ቀንሽ እያልኩ ሁሌ ብመክራትም፡ የእሷ መልስ ግን እኔ በዚህ ጊዜ የምፈልገዉ እራሴን ዘና አድርጌ መኖር ነዉ የምፈልገዉ በስንቱ ልጨናናነቅ?? መጨናነቅ ይበቃኛል.....በትምህርት ጥናትም መጨናነቅ አልፈልግም ከመጣ ዉጤት ይምጣ ካልመጣም የራሱ ጉዳይ.....ትለኛለች፡፡

አንድ ቀን ናርዶስን ብቻዋን ቁጭ ብላ ጭልጥ ያለ አለም የሄደች ትመስላለች ከአጠገቧ ሂጄ ናርዶስ ናርዶስ እያልኩ ብጠራት ልትሰማኝ አልቻለችም ..ከጎኗ ሁኜ ናርዶስ ብየ ፊቷን ነካ ሳረጋት ከእንቅልፍ እንደባነነ ሰዉ ብንን ብላ ነቃች
...እኔም፡- ግን ለምን እንደዚህ በሀሳብ እርቅሽ እስከምትሄጅ ታስቢያለሽ?? ብቻሽን ተቀምጠሽ በሀሳብ ከምትበታተኝ አብረን ላይብረሪ ገብተን እናጥና ለወደፊት እኔ እና አንቺ በልጅነታችን ህልማችን ቢወሰድም ...ለወደፊት ህልም ያለን ህልማችንን መመለስ የምንችል ልጆች ነን ....ባለፈዉ ስንመካከር እኮ እኛ አርአያ መሆን አለብን ብለን ሁለታችን ቃል ገብተናል ለምን እንደዚህ ተስፋ ትቆርጫለሽ ??? ብዙ ጊዜ ብር በመበተን በመዝናናት በመልበስ መደሰት ምን ይሰራልሻል ??? አልኳት

ናርዶስም :- >>>>>>>እኔ በልጅነቴ በአጎቴ እና በአባቴ ጓደኛ የደረሰብኝ በደል አሁን ድረስ ከአእምሮየ አልጠፋም .,ቀን ቀን ስንገናኝ ደስተኛ እመስልሻለሁ ሰዉ ጋር ተጨዋች እመስላለሁ ግን ማታ መኝታየ ላይ ተኝቼ የተኛ ሰዉ ብመስልም ንፁህ እንቅልፍ ከወሰደኝ ብዙ አመታት አለፈኝ... ሁሌ ለሊት ለሊት ሳለቅስ ነዉ የማድረዉ ምንም መረጋጋት አልቻልኩም፡፡ እቤቴ ምንም አልጎደለብኝም ቤታችንም ዉስጥ የምንኖረዉ በደስታ ነዉ ምንም የማስብበት የምጨነቅበት ነገር የለኝም፡፡ ግን ይሄ የልጅነቴ በደል ምንም ሊረሳኝ ሊለቀኝ ከአእምሮየ ልሰርዘዉ አልቻልኩም፡፡
ማታ ስተኛ እያለቀስኩ እየኖርኩኝ በቀኑ ደስተኛ ልምሰል ብየ ነዉ ...ትምህርት ለማጥናት ሞከርኩኝ ግን አእምሮየ ምንም ሊቀበልልኝ አልቻለም ...መፅሀፉን ስገልጠዉ ካላነበብኩት እምባየ የምማርበት መፅሀፍ ላይ ቢያርፍ ምን ጥቅም አለዉ ??ብላ ጥያቄየን በጥያቄ መለሰችልኝ ...,
    በናርዶስ አነጋገር በጣም ተሰማኝ ምን ማረግ እችላለሁ ...እኔም የእሷ አይነት አደጋ በልጅነቴ ደርሶብኛል፡፡ አብሽሪ አላህ አለን ከማለት ዉጭ

    የማይደርስ የለም ሚኒስትሪ ፈተና ደረሰ ተፈተንኩኝ ...........ከተፈተንኩ ቡሀላ ናርዶስ ጋር በእናቴ ስልክ እንደዋወላለን በሳምንት አልፎ አልፎ አንገናኛለን ......

የሚኒስትሪ ዉጤት ሲመጣ አባቴ ዉጤቴን ለማየት ቸኩሎ መጀመሪያ እኔ ነኝ ማየት ያለብኝ ብሎኝ ወደ ትምህርት ቤት ካርዴን ሊያመጣ ሄደ

የሚኒስትሪ ዉጤቴ አባቴ ይዞት መጣ .....በሩን ሲከፍተዉ አባቴ ጋር ፊት ለፊት ተያየን ....ምን ይለኝ ይሆን??? ጥሩ ዉጤት ነዉ ወይስ አይደለም ??"እያልኩ በቆምኩበት ጨንቀት ያዘኝ.......






#ክፍል 7⃣
ይ........ቀ......
......ጥ.......ላ.......ል


JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/21 23:18:06
Back to Top
HTML Embed Code: