Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሁሉም_ሴት_አንድ_ነው 🤔

ሰው ተርቤ ሳለሁ በቀድሞው ጉዳቴ
ድንገት ቀርባኝ እሷ ባዋያት ካንጀቴ
ታጋርታ ጭንቀቴን ሁና ልክ እንደኔ
ከናለ ስጋቴ መሆን ሽታ ጎኔ
የትናንት ብሶቴን ከውስጤ ለመፋቅ ፣
ባጋጣሚው ሁሉ እኔኑ ለማሳቅ ፣
ሁሉን ረስቼ እንድኖር እንዳዲስ ፣
አንካሳውን ልቤን በተስፋ ልታድስ ፣
መንገድ ስጠቁመኝ ስትነግረኝ ደጋግማ ፣
ስለኔው ስትነግረኝ በምሳሌ ቃና ፣
አንተኮ ቆንጆ ነህ ለዛውም ጠንካራ፣
በፍፁም የማትቆም በትናንት ሰበራ ፣
በዚህ ጯሂ አለም ሰሚ በሌለበት፣
ለሌላ ማይገባን የራስ ቅኔ ብሶት፣
አምቀህ ደብቀህ ካንተነትህ ጓዳ ፣
ችለህ የተጋፈጥክ የመኖርን ፋዳ ፣
*ተምሳሌት ነህኮ*
ሰው ወድቆ እንደማይቀር የቱንም ቢጓዳ፣
ደግሞ አንተም ታውቃለህ አለህ ዕልፍ ነገር፣
ምክኒያት የሚሆንህ በደስታ ለመኖር፣
•••• እናም አየውልህ ••••
ይህ የዛሬው ፅልመት ነገህን ሊጋርድ ፣
ከመንገድህ ቁሞ ሊያነቅፍህ በግድ ፣
በትዝታ አሳቦ የዃሊት ቢያሳይህ፣
ናፍቆት ተመርኩዞ ያለፈን ቢነግርህ፣
ደርሶ ቢያንሾካሹክ ፍቅር መውደድ ብሎ፣
ጭራሽ እንዳትፈቅድ እንዲያቆምህ ችሎ
በቃ ከዚህ ወዲያ ማንባትም መተከዝ ፣
በሀሳብ ተውጦ ፊትህን ማደብዘዝ ፣
አንተ ላይ እንዳላይ ከፈገግታህ በቀር
እያለች ደጋግሞ በመምከር በመዝከር
በ መጥፎ ቀኖቼ ተመስላ በ ደግ
ምኞት አሰቀጥላኝ ያዲስ መኖር ሀረግ
ወጌሻዬ ሆና ሰበብ ለመቆሜ፣
መዳኒቴ ሆና ለቀድሞ ህመሜ ፣
ዳግም ጥርሴ ሳቀ ሀሴትን ተላብሶ፣
አይኖቼም እረሱ ማደር በእንባ ርሶ፣
ጠውላጋ እኔነቴ ፈካ ተመልሶ፣
በሴት ልጅ ቢጎዳም በሴቷ ተክሶ ••

በዚህ አጋጣሚ ላአንዳንድ ሰዎች
ማለት እወዳለሁ ለጭፍን ፈራጆች
*
*
ደግም ክፉም አዝላ በምትኖር አለም
ባንዷ ጥፋት ጥለት ሌላን በመቀለም
ሁሉም ሴት አንድ ነው ማለት ልክ አይደለም
#ሼን


Join👇👇

https://www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከሰሞኑ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል EMS ከተሰኘ ሚዲያ ጋር በወቅታዊ የሙስሊሙ ጉዳይ ላይ ቆይታ አድርጓል። በዚህ ቆይታው በርካታ ነጥቦች የተነሱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በተለይም የሰሞኑን የመጅሊስ ምርጫ አስመልክቶ ጠቃሚ ጥያቄዎች ቀርበው ኡስታዝ አህመዲን አብራርቷል። ከተነሱ ጥያቄዎች ውስጥ የመጅሊሱን መርጫ ፍትሀዊ አይደለም በሚል ያልተቀበሉ ወገኖች አሉ ከዚህም በተጨማሪ ምርጫው የመንግስት ጣልቃ ገብነት ነበረው የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው። ምርጫው የብሔር መልክ የያዘ ነበር የሚለውን ሌላው ጥያቄ ነበር። እነዚህን ጥያቄዎች ያብራራበትን ክፍል ሀሩን ሚዲያ ለተመልካቾች በሚከተለው መልኩ አዘጋጅቷቸዋል። ይመልከቱት!
..
ከ ሀሩን ሚዲያ የተወሰደ

https://www.tg-me.com/Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ክረምት ነዉ...ትንሽ ሞቅ ሞቅ የሚያደርግ ነገር ያስፈልጋል፡፡በግጥምም በቀልዱም ያስፈልጋል😊

እቴዋ መርሀባ በይ ለበይክ በይ የሚለዉን በጦቢያ...በተስፋሁን ከበደ (ፍራሽ አዳሽ) የተዘጋጀ የወሎ የዱአ አደራረግ ጋር የተያያዘ አስቂኝ አስተማሪ video


😍መርሀባ በይ
😍ለበይክ በይ
መርሀባ ስትይ ለበይክ ስትይ ኸይር ይሆናል ነገሩ🥰

ይመልከቱት ከዛም በዚህ ክረምት ለደበረዉ ለበረደዉ መርጣችሁ ሼር ያድርጉት

https://www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Audio
ከችግር ቡሀላ..መፍትሄ አለ

https://www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንዲህ ያለ የሚያስቀና ትዳር አለ..በሞት ተለያይተዉ ሊረሱ የማይችሉ😔


https://www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ
እንዴት ናችሁ

ብዙ የሌላ ቻናል Admin እና አንዳንድ ዩቲዩበሮች ሳትወጋ ንገስ በሚለዉ ታሪክ መሀል የቀረበ የመራም ማስታወሻ የሚለዉን ለብቻዉ በyoutube እና በቻናል እናቅርበዉ ፍቀድልን ላላችሁ ይሄዉ የመራም ማስታወሻ የሚለዉን ለብቻዉ ከነገ ጀምሬ እፓስተዋለሁ፡፡ ቻናል ያላችሁና በyoutube ለመጀመር የፈለጋችሁ በጠየቃችሁኝ መሰረት አመቻችቻለሁ፡፡

☝️ በአስተያየት ለምን ፁሁፋ ማዘጋጀት አትጀምርም ላላችሁ ...ሌላ ፁሀፍ ላዘጋጅ ይቅርና እኔ ለራሱ 95% የፃፍኳቸዉን ፁሁፎች ረስቸዋለሁ፡፡ ወላሂ አሁን በአንዳንድ ቻናል የኔ ፁሁፍ ሲፓሰት ግን እኔ ነኝ የፃፍኩት ወይ ብየ ግራ እየገባኝ ነዉ፡፡እናም እንኳን ፁሁፍ አዘጋጅቶ ለሌላ ወገን ለመትረፍ ይቅርና ራስን ወደ በፊቱ ማንነት መመለስ ከባድ ነዉ...

ኢማን ይጨምራል ይቀንሳል....እኔም በሆነ ምክንያት ከበፊቱ አቋም እንደወረድኩ አቃለሁ..ብቻ ወሳኙ ዱአና ዱአ ብቻ ነዉ


በፊት ሳትዋጋ ንገስ በሚለዉ ታሪክ ላይ በመሀል የገባዉ የመራም ማስታወሻ ታሪክ ነገ ከጠዋት ይጀምራል፡፡
በድጋሜም ቢሆን መልካም ንባብ

አሚር ሰይድ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📖 #የመራም_ማስታወሻ
           ክፍል ~ ➊
ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ


      ሁሉም ነገር አላህ ሁን ባለው ጊዜ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
በህይወት ዉስጥ ስቃይ የማይቀር ከሆነ ..የህይወት ችግሮች ልናስቀራቸዉ የምንችላቸዉ ካልሆኑ ጥያቄዉ መሆን ያለበት ""መሰቃየታችንን እንዴት ማቆም አለብን???""ሳይሆን ለምንድን ነዉ የምንሰቃየዉ???ለምን አላማ ??መሆን አለበት፡፡

ሁሌም ቢሆን ከችግሬ መላቀቅ እችላለሁ
የሰዉ ልጅ የማሰብ አቅም ሲመክን አይቻልም የምትለዉ ቃል ባንደበቱ ይዘወትርና ፡የአነጋገር ለዛዉ ይሆናል..ቀላልም ይሁን ከባድ ነገሮች ሲጠየቅ ወደ መፍትሄዉ ሳይሆን አልችልም የሚለዉ ሚዛን ያቃጭልበታል፡፡

የማሰብ አቅሜን ተጠቅሜ በያዝኩት ነገር ላይ ልዩነት መፍጠር እችላለሁ ማለት ካልቻልን አፋችን ቃሉን ባይጠራዉም ሁሉንም ነገር የጀመርነዉ አይቻልም እያልን ነዉ ማለት ነዉ ፡፡ በመጀመሪያ የሚቻልበትን መንገድ ለይተን እንወቅ እንጂ የምንከተለዉን መንገድ አይቻልም ብለን አንጀምር ፡፡ አይቻልም የሚሉት ቃል የሽንፈት ማረጋገጫ ማህተም ነዉ
ሰዉ ነኝ እስካልን ድረስ የማሰብ አቅማችንን አለመጠቀም ይቅርታ የሌለዉ የሒወት ከባዱ ስህተት ነዉ ፡፡ ድንቁርና የሰዉን ተፈጥሮ የማሰብ አቅም በማዳከም ላለመሆንና ላለመቻል አጋልጦ ይሰጣል፡፡
ለሁሉም ነገር የሚባክኑ ጊዜያቶች ሰከንዶች ደቂቃዎች ለዱንያ ወደ አኼራ ለመሸጋገሪያ ድልድይ ለመስራት እንቅፋቶች ናቸዉ፡፡ አሁን ዘመን ላይ ጊዜ እንደ ወራጅ ወንዝ ሰዉ ሳይጠቀምበት እየፈሰሰ ነዉ፡፡ ኸይር ለመስራት በዲነል ኢስላም ላይ ለመሳተፍ ኪታብ ለመቅራት የሁላችንም መልስ ጊዜ አጣን ጊዜ የለንም ሁኗል፡፡እኛ ያነሰን ጊዜ ትርጉም ግን ምን ይሆን??ብለን እራሳችንን ጠይቀን እናዉቃለን ???

ማንኛችንም የማንክደዉ ሀቅ አለ ..መጀመሪያ የማንሻማበትን መስመር ሳንለይ እዛም እዛም እየረገጥን -ጊዜ አጠረን- ብንል ጊዜ የምንለዉ ነገር የሰበብ ቀበቶ ብቻ ነዉ፡፡
አሁን ብለን የምንጠራዉ ወቅት ብቻ ነዉ በእጃችን ያለዉ ጊዜ..... ከቆምንበት ሳንነቃነቅ ወደ ሆላ እያልን የምንጠራዉ ጊዜ እጃችን ላይ ያገማነዉ የፋይዳህ እንቁላል መጣያ ቅርጫት ብቻ ነዉ፡፡ የገማ እንቁላል መልሶ ተፈልፍሎ ጫጬት መስጠት አይችልምና.....
ወጣትነት ጉልበት ብርታት ወኔ ሞራል ነዉ....የአአምሮህን እግር ንቀለዉና ተገትሮ የቀረዉን ራስህን ቅደመዉ.....ዛሬ በከንቱ የሚፈሱ ጊዜያቶች ነገ ለአንተ ተመልሰዉ አታገኛቸዉና....
ሂወትም የምትወሰነዉ በራሳችን የአስተሳሰብ ምርጫ እና በምትጠቀማቸዉና በምታባክናቸዉ ጊዜያቶች ላይ የተወሰኑ ናቸዉ ፡፡ ሂወት የምርጫ አይደለችም! ብትሆንማ ኑሮ ማን ችግርን ይመርጥ ነበር!? አላህ ቀድሞ የፃፈውን ነገር በፍላጎት መቀየር አንችልምና ከሚያጋጥመን የሂወት ውጣ ውረድ ጋር ራሳችንን አጣጥመን፣ ዱንያ አጭር መሆኗን አውቀን ለዛኛው ለዘላለማዊ ሂይወታችን የምንሰንቅባት ሀገር መሆኗን እና የሚያጋጥሙንን ሙሲባ በሶብር ነገ የተሻለ እንደሚሆን በአላህ ማመን እንዳለብን ያስተማረችኝ እማ ነች፡፡

እናቴ የተወለደችው ሀረር ነው፡፡ ሀረር ትወለድ እንጂ የእማ እናቷ የደሴ ልጅ ነች፡፡ ስለዚህ እማ በደም ወለየ በአፈር ደግሞ ሀረሪ ነች፡፡ እናቴ ለቤተሰቦቿ ሁለተኛ ልጅ ነች ታላቅ ወንድሟ ፈይሰል ይባላል፡፡ እናቴ ደግሞ ለይላ ትባላለች፡፡ ደስተኛ ቤተሰብ እንደነበሯት እማ ሁሌ ነግራኛለች፡፡ መተሳሰብና መከባበር የሞላበት ፍቅር የሰፈነበት ቤተሰብ ነበራት፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው እማ ገና የ 12 አመት ልጅ እያለች እናቷ በምጥ ምክንያት ሞተችባት፣ በሰአቱ ፈይሰል የ15 አመት ልጅ ነበር፡፡ በእናቷ ሞት ምክንያት ቤተሰብ የማስተዳደር ሀላፊነት እናቴ ላይ ወደቀ፡፡ እናቴ በእናቷ ሞት ምክንያት ቅስሟ ተሰብሮ ልቧ መድማቱን አላቆመም፡፡ የእናት ናፍቆት ሲደመር ቤተሰብ ማስተዳደር ከእማ አቅም በላይ ሆነ፡፡ ሰውነቷ መመንመን ጀመረ፡፡ ይሄን የተመለከቱ የቅርብ ሰው ጎረቤቶች አባቷ ሌላ ሴት አግብቶ ልጆቹን እንድትንከባከብ መከረቱ፡፡ አቧቷም የጎረቤቶቹን ምክር ሰምቶ ልጆቹን ትንከባከብለት ዘንድ ሌላ ሚስት አገባ፡፡

ከዚህ በኃላ ግን ሂወት ይበልጥ ከብዳ ፈተነቻቸው፡፡ፈይሰል በእንጀራ እናታቸው የሚደርስባቸውን ግፍና መከራ መቻል አቅቶታል፤ አባታቸው እንደወትሮው ለነሱ መጨነቁን ቀነሰ፡፡ ይባስ ብሎ " አታናዷት የምትላችሁን ሰሙ" እያለ እነሱን መቆጣት ጀመረ፡፡ እማ ግን ችግሯን በውስጧ አፍና ይዛ ኑሮን ተያያዘችው፡፡ ከወንድሟ የምታገኘው ፍቅር ለሷ ምግብና ውሀ ሁኖ ያኖራታል፡፡ ፈይሰል ለእህቱ ችሎ የማይሆንላት ምንም ነገር የለም! እህቱን እጅግ በጣም ይወዳታል፤ አንዳቸው ለአንዳቸው እየተሳሰቡ መኖር ተያያዙ፡፡ ፋይሰል ከሱ ይልቅ እህቱ ላይ የሚደርሰው በደል እና እንግልት ያንገበግበዋል!አባታቸው ስለነሱ ማሰብ ማቆሙ ደግሞ ይበልጥ ያበሳጨዋል፡፡

እማ በጧት ወፍ ከመንጫጫቱ በፊት ነው የምትነሳው የቤቱን ስራ ስትጨርስ አርፍዳ ነው ወደ ትምህርት ቤት የምትሄደው፤ ከትምህርት ቤት ስትመለስም የማያልቀው የቤት ስራ ተከማችቶ ይጠብቃታል፡፡ የምትተኛው ከሰው ኃላ የምትነሳው ከሰው በፊት ነው፡፡ ግን አንድም ቀን አማራ አታውቅም ነበር፡፡ ይሄን እንግልቷን ማየት ያላስቻለው ፈይሰል " ቀን መቶልኝ አንችን ከዚህ ስቃይ ማውጣት ስችል እመለሳለሁ፡፡ ከማዘን ውጭ ምንም ልረዳሽ ስላልቻልኩ አዝናለሁ እህቴ ሂጃለሁ የምሄድበትን አላውቅም እና እንዳትፈልጊኝ፡፡ ያንችው ፈይሰል ነኝ" ብሎ ደብዳቤ ፅፎ አስቀምጦላት የት ገባ ሳይባል ጠፋ ፡፡
እማ ከወትሮው በበለጠ ሂወት ከበዳት፡፡ አንድ ብርታት የነበራት ወንድሟ ጥሏት ጠፋ፡፡ "የት ገብቶ ይሆን??" ብሎ የሚጨነቅለት ጠፍቶ " ጎርምሶ ጠፋ" መባሉን ስትሰማ፡፡ ብዙ የሀዘን እንባ ከአይኗ ፈሰሰ ልቧ ደጋግሞ ቆሰለ፤ ላይሽር ላያገግም ተሰበረ፡፡ የወንድሟ ትዝታ ረፍት ነሳት በስራ እያገዘ ያዝናናት ነበር፡፡ አሁን ግን ብቻዋን ቀርታለች ግን በእያንዳንዱ የስራ እንቅስቃሴ ፈይሰል ይታያታል፡፡ ትዝታው ረፍት ነስቶ አቅም አሳጣት፡፡ እናቴም ልክ እንደወንድሟ መጥፍት አሰበች፤ እናም አንድ ሀሳብ መጣላት፡፡
እማ አባቷን እንኩዋን በቅጡ ሳትሰናበተው የእናቷ ትውልድ ሀገር ወደሆነችው የወሎ መዲና ደሴ አያቶቿ ጋር ለመኖር መጣች፡፡ እማየ ደሴ ስትመጣ ለመላመድ አገሩን ለመልመድ ቀናት ወራት አልፈጀባትም..ወሎ ላይ ከየት መጣህ ሳይሆን እንኳን ሰዉ ሁነህ መጣህ ነዉ የሚባለዉና፡፡  ምን ይደረጋል ወሎ ገራገሩ እየተባለ ታሪኩን የተቀማ ህዝብ ነዉ... ትክክለኛ ታሪክ ቢሆንማ ወሎ ከኢትዮጲያ ታሪክ 70% በላይ ይዛ የቆየች ናት

በወሎ ምድር ታይተው የማይታወቁ፣ ተነግረው የማያልቁ፣ለልብ ደስታ ለአዕምሮ እረፍት የሚሰጡና የማይጠገቡ ድንቅ ድንቅ ሚስጥራዊ ክዋኔዎችና ባሕሎች ይገኛሉ።ወሎዬ ሲወድ በአፉ አይደለም፤በልቡ ነው።ፈትፍቶ  እያጎረሰ፣አውልቆ እያለበሰ፣ፀጉርን በፍቅር እየዳበሰ አቀማጥሎ የሚወድ ነዉ።
ከጫፍ እስከ ጫፍ በወሎ ምድር በተንቀሳቀሱ‹አብሽር አቦ› እያለ በፍቅር የሚቀበል ደግ ሕዝብ አለ።
የቆነጃጅቱ ውበት፣ የጎበዛዝቱ ልበ ሙሉነት ወሎን የረገጠ ሁሉ ልብ ያቀልጣል።👇👇
        ይህ ሁሉ መኳኳል ምን ያደርግልሻል
        ወሎየ ነኝ ብትይ ስሙ ይበቃሻል፡፡
        በጥብጬ ልቀባዉ የወሎን አፈር
        በጥብጬ ልቀባዉ የደሴን አፈር
        እኔም እንደነሱ ምን አልባት ባምር
ብለዉ የወሎን ዉበት ዘፍነዉ መስክረዋል
ወሎ ላይ ሲመጡ ወሎን ሲመለከቱ ወሎዬ ላልሆነ ወሎዬነትን ያስመኛል።
ወሎዬ በሠላም ቀን በደግነት በክፉ ቀን ደግሞ በጀግንነት ሺህ ጀግና ስለጣለ ከየትኛውም ሰው ልብ አይወጣም። ወሎዬዎች ኢትዮጵያውነትን አይናገሩትም፤ ይኖሩታል እንጂ፡፡ ወሎዬዎች ኢትዮጵያዊነትን በባሕላቸው፣በፍቅራቸው እና በጀግንነታቸው ተላብሰውታል።የወሎ ልጅ ሁኖ ኢትዮጲያን በፍትህ ያስተዳደረ ልጅ እያሱ ሚካኤል መቼም ከልብ ታሪኩ ሊጠፋ አይችልምና ፣ ከአይጠየፍ አዳራሽ ግርጌ፣ በጦሳና በአዘዋ ተራሮች ታጅባ ከደመቀችው ደሴ ከተማ ሲመጡ ዘረኝነት ትዝም አይለዎት፡ ወሎ ዘር አይቆጥርም፣ ሃይማኖትም አይለይም፣ለወሎዬ መለኪያው ሰውና ባሕሪው ብቻ ነው።መቻቻል፣ ፍቅር፣ አንድነትና አብሮነት መለያዎቹ ናቸው። በፍቅራቸው ተደሞ በወሎ ጭስ መልካም መዓዛ ታውጀዉ አመስግኖ መመለስ የሌላዉ ሀገር ወጉ ነዉ።
 ወሎዬዎች የመጀመሪያ ውበታቸዉና ደግነት ሁለተኛ የዋህነት ሶስተኛ ገራገርነት አራተኛ ሰውን በሰውነቱ እንጂ በሚታይ ቁሳዊ ነገር ልዪ ቦታን የማይሰጡ ንፁህ ሰውን እንጂ በገንዘብ በእውቀት እና በዘረኝነት የማይኮፈሱ ስስት ያልፈጠረባቸዉ የተቃራኒ እምነቶችን የሚያከብሩ ውበትን ከዘራቸዉ የሚወራረስ ፍቅርን በነፍስ የምታገኘው ወሎዬዎች ጋር ነው ።

ወሎየ ስትሆን ከሙስሊሙ ጋር ቀጠሮ ስትይዝ ሶላት ሰግደህ ስትመለስ እንገናኝ ትለዋለህ፡፡
ሙስሊም እንዲሁ ቤተ ክርስትያን ተሳልመህ ስትመለስ እንገናኝ ይለሀል፡፡
ክርስትያን ጓደኛህ ቤት ስትጫወት የሶላት ሰአት ሲደርስ የዉዱእ ውሀ ከጡሀራ መስገጃ ጋር ያቀርብልሀል፡፡
ከዚህ በላይ በሰውነት መጣመር ከየት ይመጣል?? ከወሎየነት እንጂ




አያቶቿ በእርጅና ተበሳቁለዋል፡፡ ከሁለቱ ውጭ ቤት ውስጥ የሚንከባከባቸው ሰው አልነበረም፡፡ ሴት አያቷ በልጃቸው ሞት ምክንያት ብዙ ከማልቀሷ ምክንያት አይኗ ተዳክሟል፡፡ የልጃቸው የስም መጠሪያ የልጃቸው ሽታ የሆነችውን እናቴን ሲያዩ የደስታ እንባ ማንባት ጀመሩ፡፡ ልጅ ወልዶ የሞተ ሰው መቸም አይረሳም በልጅ ሰሙ ሲጠራ ይኖራል ይባላል፡፡ለዛም ነበር አያቶቿ እናቴን ሲያዩ ልጃችን አልሞተችም ያሉት፡፡ እማ ለቀዘቀዘው ቤታቸው የፍቅርን ሙቀት ለጨለመው ቤታቸው ብርሀን እና ድምቀት ሆነች፤ በአመታት በፊት ያጣችውን ፍቅር አሁን በአያቶቿ ዳግም ተመለሰላት፤ እነሱን መንከባከብ እና ማስደሰት ስራዋ አድርጋ ያዘችው፡፡ሂወታቸው በእጅጉ ተቀየረ፡፡ አያቷ አሁን እንደበፊቱ ማልቀስ አቁማለች፡፡ ወንድ አያቷም በጣም ደስተኛ ሆኗል፡፡ ግን ከእድሜው ጋር በተያያዘ የተወሰነ የመስማት ችግር አለበት፡፡ እማየም ትምህርቷን ቀጥላለች፡፡ ከትምህርት ቤት መልስ ደግሞ ወደ መርከዝ በመሄድ ቂርአት ትቀራለች፡፡ እማ ሂወቷ መስመር ይዟል የሚያስብላት የሚንከባከቧት ቤተሰብ አላት፤ ሁሌ የወንድሟ ጉዳይ ረፍት ይነሳታል እሷ ስትስቅ እሱ ሲያለቅስ ይሰማታል፡፡ እሷ ጠግባ ስትበላ እሱን  ሲርበው ይታያታል፡፡" ወንድሜ የት ነህ!? የትስ ብየ ልፈልግህ? እዚህ ነኝ በለኝ ወንድሜ" እያለች ሁሌም ታስባለች፤ ግን የውሀ ሽታ ሆነና ቀረ፡፡

እማ እድሜዋ እየጨመረ ሲመጣና ራሷን መጠበቅ ስትጀምር የአደምን ልጅ ልብ አስደንጋጭ እና የልብ ቀማኛ ሆነች፡፡ እዚህ ቀረሽ የማይባልላት ሁሉን አሟልቶ የፈጠራት የጥበቡ ማሳያ ተምሳሌት እማ እንደሆነች ይመሰከርላታል፡፡ ፀባየ ሰናይ ሰናይ መሆኗ ደግሞ ከሰፈር እስከ ትምህርት ቤት እስከ መድረሳ ያሉ ሰወች በጠቅላላ ይወዷታል ያከብሯታልም፡፡ እማ ገና 18 አመት ሲሞላት ለትዳር የሚፈልጓት ወንዶች በዙና የአያቶቿን ደጅ የሚጠና ሰው ብዙ ነበር፡፡ አያቶቿ አግብታ በትዳሯ እንድትኖርና ዘር እንድታበረክትላቸው ተመኙ፡፡ እማ ግን አላማዋ ሌላ ነበር ተምራ ስራ ይዛ እነሱን መጦር ነው ህልሟ፡፡ እናም የሚቀርብላትን የትዳር ጥያቄ ወደ ጎን በመተው በትምህርቷ ፀናች፡፡ የ12ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ግን ያልጠበቀችው ነገር ድንገት ተከሰተ፡፡.....

#ክፍል
ይቀጥላል.......

Join👇👇

https://www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📖 #የመራም_ማስታወሻ
           ክፍል ~ ➋
ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ




            የ12ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ግን ያልጠበቀችው ነገር ድንገት ተከሰተ፡፡......
ወንድ አያቷ እርጅናን ለመከላከል ያህል ሁሌም የእግር ጉዞ የማድረግ ልምድ አለው፡፡ ቤታቸው አራዳ ቢሆንም በተለያየ ጊዜና ሰአት የተለያዩ ሰፈሮችን ያካልላል፡፡ እማ ቤት መዋሉ እሱን እንደሚያዳክመው ሰለምታስብ አትሂድ አትንቀሳቀስ ብላ አትከለክለውም ግን ጆሮው የመስማት ችግር ስላለበት መኪና እንዳይገጨው ትፈራ ነበር፡፡ የፈራችውም አልቀረም፡፡የፒያሳን አስፓልት አቆርጦ በላይኛው መስመር የዳውዶን መንገድ ይዞ በሚወስደው መንገድ ተጉዞ በአገር ግዛት ቁልቁል ወርዶ ወደ ሸል የሚያደርሰውን መንገድ ይዞ ወደ ቤቱ ለመመለስ ያሰበው አባቷ ሲከንፍ ከወልዲያ የሚመጣ መኪና ገጨው፡፡

አሁንም በድጋሚ ሂወት አሳማሚ የሆነውን ቅጣት አያቷን በሞት በመንጠቅ ቀጣቻት፡፡ መሪር ሀዘን ጥልቅ የሆነ የልብ ስብራት አያቷን ማስደሰት ባልቻለችበት ሁኔታ ሞት መጥቶ ቀደማት፡፡ ልቧ ደጋግሞ ቢደማም የሀዘን ድር ልቧ ላይ ቢያደራባትም ..እሷ በርትታ ሴት አያቷን ማበርታት እንዳለባት አስባ በአያቷ ተፅናናች፡፡

እማ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ለመፈተንና በጥሩ ውጤት ለማለፍ ግብግብ ይዛለች፡፡ ሆጤ ትምህርት ቤት ተማሪወቿን ለማብቃት ላይብረሪዋን ክፍት አድርጋለች፡፡ ከዛም ባሻገር ከመማሪያ ክፍሎቹ መጨረሻ በጀርባ የሚገኘው ጫካ ፍፁም ሰላምና ፀጥታ የሰፈነበት በመሆኑም ከዛም ባሻገር በቅርብ ርቀት የሚገኘዉ ቦርከና ወንዝ ወደ ገረቦት ሀገር ኮምቦልቻ ጉዞዉን ሲያደርግ በሚያሰማዉ ድምፅ እየመሰጡ ጫካው በተፈታኝ ተማሪወች ይሞላል፡፡

እናቴም ቀንም ለሊት ለፈተናዉ በመዘጋጀት ፈተናዉ ላይ ተቀምጣ ተፈነች እኔ ስበቡን አድርሻለሁ ቀሪዉ የፈጣሪ ነዉ ብላ አላህ ዉጤቷን ጥሩ እንዲያደርግላት ተማፀነች፡፡ እማ ብሄራዊ ፈተና እንደጨረሰች ክረምቱን ሰፈር ለሚገኙ ተማሪዎች ማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት እና የተለያዩ ኪታቦችን በመቅራት አሳለፈች፡፡


ዉጤት መጣ እማ ማትሪክን ሰቃይ ተማሪዎች ከሚባሉት ተርታ ተሰልፋ ጥሩ ዉጤት አመጣች፡፡ በጥሩ ውጤት አልፋ ዩኒቨርሲቲ የመግባት አቅሙ ቢኖራትም አያቷን ብቻቸውን ትታ መሄድ አልፈለገችም፡፡ አያቷም እንድትለያት አልፈለገችም፡፡ እማ ካለ አያቷ አያቷ ደግሞ ካለ እማ ማንም የላቸውም፡፡ አንዳቸው በአንዳቸው የፍቅር ድጋፍ ይቆማሉ፡፡ የአንዳቸው ድክመት ለሌላው ውድቀት ይሆናል፤ ስለዚህ እንዳይወድቁ አለመለያየት መፍትሄ ነው ተደጋግፎ መቆም፡፡ ለዛም ነው እማ ዩኒቨርስቲ መሄድን ትታ ለአያቷ ቅርብ ሁና ደሴ በሚገኘዉ በወይዘሮ ስህን ኮሌጅ የአካውንቲንግ ትምህርቷን የጀመረችው፡፡ እማ አያቷንም እየካደመች ትምህርቷንም ቂርአቷንም ሰአቷን በመከፍፈል ትጠቀምበታለች፡፡ የኮሌጅ ትምህርቷን በከፍተኛ ውጤት ተመረቀች፡፡ ስራ ለማግኘት ምንም ያህል ጊዜ አልፈጀባትም፡፡ የኢንዱስትሪ መንደር ወደ ሆነችም የደሴ ቅርብ ጎረቤት ሀገር ወደሆነችዉ ኮምቦልቻ ጎራ አለች፡፡

ኮምቦልቻ ከደሴ 21ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ የኮምቦልቻ የድሮ ስሟ ቦርቸሌ ይባል ነበር፡፡ በጣሊያን ጊዜ አንቻሮ ላይ ሆነው ቁልቁል ኮምቦልቻን ሲመለከቱ ያኔ ገና ስልጣኔ ባልነበረበት ወቅት ኮምቦልቻ ላይ መብራት ይታይ ነበር፡፡ ይሄን የተመለከቱ ጣሊያኖች የሁለት የጣሊያን ቃል ጥምረት ስያሜን አገኘች፡፡ " ኮምቦ " " ሎችያ" ብለው ሰየሟት " ኮምቦ" ማለት መንደር ማለት ሲሆን "ሎችያ" ደግሞ መብራት ማለት ነው፡፡ በአንድ ላይ ሲነበብ "የመብራት መንደር" ማለት ነው ይሄ የሚያሳየው ኮምቦልቻ በስልጣኔ ቀደምት መሆኗን ታሪክ ይናገራል፡፡ ኮምቦልቻ በውስጧ ኮስፒ ቆርቆሮ ፍብሪካ፣ ቆዳ ፍብሪካ፣ ስጋ ፍብሪካ፣ሁለት ጨርቃ ጨርቅ ፍብሪካ፣ 2 ከረጢት ፍብሪካ፣ ብረታ ብረት ፍብሪካ፣ ቆርኪ ፍብሪካ እነዚህን ሁሉ አምራች ድርጅት እና ከአገልግሎት ሰጭ ደግሞ ጥቁር አባይ መንገድ ትራንስፖርት፣ደረቅ ወደብ፣ ጉምሩክ፣ አ.ው.ስ.ኮ.ዶ፣ አውራ ጎዳና ይገኘበታል፡: እነዚህን ሁሉ ድርጅት አቅፏ በመያዟ የኢንደስትሪ መንደር የሚለውን ስያሜ አገኘች፡፡ የኢንደስትሪ መንደር ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የብዙ ሀገር ተወላጆችና የብሄር ብሄረሰብ ስብስብ መኖሪያ የሆነችው ወሎ ኮምቦልቻ ህዝቦቿ በፍቅር ተቻችለውና ተከባብረው የሚኖሩባት ሀገር ፍፁም ዘረኝነትን የማታንፀባርቀው የሁሉ መጠጊያ የሆነች ውብ ሀገር ናት፡፡

ማንም ለሀገሩ እንግዳ የሆነ ሰው ባይተዋርነት ሳይሰማው ሀገሩን ተላምዶ በፍቅር እጅ ይሰጣል፡፡ ከዛ በኃላ የትም ቦታ ቢሄድ ኮምቦልቻን ላይረሳ በደማቁ ፅፎ በልቡ ያኖራታል፡፡ እማየም ወደ ዚች ውብ ሀገር የመምጣቷ ሰበብ ይሄው ነው፡፡ እማ አውራ ጎዳና ውስጥ በኦዲተርነት ተቀጠረች፡፡ ከአያቷ ጋር ደስተኛ ሁና መኖር ጀመረች፡፡ አያቷ የልጇ ልጅ ለቁም ነገር በቅታ ማየቷ ደስታዋን አሻቀበው፡፡ እማ ስታልመው የነበረው ነገር አሁን ተሳክቶላት አያቷን እያስደሰተቻት ነበር፡፡

መቼም ዱንያ ነዉ የፈተናዉ አዳራሽ በየቦታዉ ነዉ.... እማ ስራ በጀመረች በሶስተኛ ወሯ ያላሰበችው ነገር ከፊት ለፊቷ ተጋረጠባት፡፡.....
እማን ምን ገጥሟት ይሆን???


#ክፍል ➌ ይቀጥላል

Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📖 #የመራም_ማስታወሻ
           ክፍል ~ ➌
ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ



እማ ስራ በጀመረች በሶስተኛ ወሯ ያላሰበችው ነገር ከፊት ለፊቷ ተጋረጠባት፡፡
እማ ከአያቷ ጋር ቁርስ በልታ ወደ ስራ ለመሄድ ስትዘጋጅ አያቷ አስሟ ተነሳባትና አፈናት፡፡ አስም እንዳለባት ብታውቅም ከደሴ ወደ ኮምቦልቻ ከመጡ በኃላ ግን አሟት አያውቅም ነበር፡፡ እማ በድንጋጤ ደርቃ ቀረች አይኗ እያየ ሞት መቶ አያቷንም ወሰደባት፡፡ ሰማይ እላይዋ ላይ የተደፍባት መሰላት፡፡ የእማ ድርብርብ ሀዘን በቅደም ተከተል እየመጣ ጠነከርኩ ስትል ጥንካሬዋን የሚፈታተን ሙሲባ እግር በእግር ይከተላት ይዟል፡፡
ሂወት እጅጉን ከበዳት... በብቸኝነት ለመኖር ተገደደች፤ ሰው እንዳትቀርብ የኔ የምትላቸውን ሰወች የሞት ጥላ በላይዋ እያንዣበበ የሚነጥቃት እሰኪመስላት ድረስ ሰው መቅረብ አስፈራት፡፡ እማ በብቸኝነቷ ታዋቂ ሆነች ..የአንጀቷን የምትነግረዉ የሀሳብ ማዕበሏን የሚገድብ የሴት ጓደኛ እንኳ ምንም የላትም ብቸኝነት ጌጤ ነዉ ብላ እራሷን ያሳመነችዉ ይመስለኛል.....ወደ ስራ ስትሄድም ሆነ ስትመጣ ብቻዋን ነዉ... ከስራ ባልደረቦቿ ጋርም ከሰላምታ በዘለለ የጠበቀ ግንኙነት አልነበራትም፡፡

ይሄን ብቸኝነቷን የታዘበው ዩሱፍ ሊቀርባት ወሰነ፡፡ ዩሱፍ እማ የመሰራበት መስሪያ ቤት በሹፍርና ሙያ ነው የተቀጠረው፡፡ የድርጅቱን ሰርቪስ መኪና ስለሚይዝ የሁሉንም ሰራተኛ መውረጃ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ዩሱፍ በባህሪው ሰው አክባሪ የተቸገረን መርዳት የሚወድ አይነት ሰው ነው፡፡ ከጥበቃ እስከ ስራ አስኪያጅ ድረስ ተወዳጅነትን ያተረፈ ምስጉን በጣም ጥሩ ሰው ነው፡፡ ሰወች ሁሉ በመልካም ያነሱታል ተጫዋችና ቀልደኛ ነው፡፡ ዩሱፍ ሁሌም እማን ይከታተላታል የምትወርድበትን ቦታ ስለማያውቅ ሰፈሯንም አወቀ በስራ ሰአት አልፎ አልፎ ቢሮ እየሄደ ያወራታል፡፡ የሻይ ሰአት ቢኖራቸውም እማ ያን ሰአት አትጠቀምበትም በአንድፊቱ ለምሳ ነው የምትወጣው፡፡ አሁን ግን የሱፍ በተለያየ ዘዴ እየፈጠረ ይዟት ይወጣል፡፡ ቅርርባቸው እየጠነከረ ሲመጣ እማ ያሳለፈችዉ ብቸኝነት ስለሆነ እማ የመጀመሪያ ያወቀችዉ ሰዉ ስለሆነ ለየሱፍ የልቧን አንድ ክፍል ለእሱ የሰጠችዉ ይመስል የሱፍን ሳታወራ ስቀር ይናፍቃት ጀመር...የሱፍም እነደዚሁ እማን ካላወራት ትናፍቀዉ ጀመረ.... ሁለቱም የመሀባዉ ስፍራ ተገጣጠመና ይነፋፈቁ ጀመር፡፡


ዩሱፍ ቀድሞ እማን የቀረባት ለትዳር አስቧት መሆኑን አይክድም፤ ኡሚ ስትቀርበው ለመልካምነቱ እጅ ሰጠች እሷም አፈቀረችው፡፡ እናም ይሄን ግንኙነት ወደሌላ ሳይሄድ ከትዳር በፊት ከአላህ ድንበር ዉጭ ሳያልፉ ፈጣሪ የከለከለዉን ተከልክለዉ በመቀራረብ ብዛት መሳሳት መኖሩን ሳላወቁ ይሄን ያማረ ፍቅር ወደ ትዳር ቀይረው በፍቅር ደስተኛ ሁነው አንድ ጎጆ ቀልሰዉ አብረዉ መኖር ጀመሩ፡፡

ዩሱፍ ማን ነዉ? ብላችሁ እያሰባችሁ መሰለኝ...ዩሱፍ ማለት የኔ አባቴ ነው፡፡ አባቢ ብየ እጠራዋለሁ በጣም መልከመልካም ጥሩ የሚያስብ በሰፈር በስራ ቦታ በጥሩነቱ የተመሰከረለት ነዉ አባቢ ..... ተጋብተው መኖር ከጀመሩ 6 ወራትን እንዳስቆጠሩ እኔ ተፀነስኩ፡፡

እማ ዘመድ ስለሌላት ብዙ ልጅ ወልዳ ዘር እንዲበዛላት ትፈልጋለች የሁሌም ዱአዋ አላህዋ ዘር የለኝም ዘሬን አብዛልኝ ነዉ ፡፡ አባቢ ኡሚ በማርገዟ ምክንያት ደስታዎ ወደር አልነበረውም መሬት አይንካሽ ማለት ነው የቀረው በጣም ይንከባከባታል፡፡ ኡሚም ትቀብጥበታለች የአባቢና የኡሚ ፍቅራቸው ጎረቤትን ያስቀናል፡፡ እማ ምንም የኔ የምትለው ዘመድ አልነበራትም እኔን ስትወልድ ማን እንደሚያርሳት ስታስብ ይጨንቃት ነበር፡፡

አሁን ግን ጎረቤቶቿ ጋር ስለተቀራረበች እና ማህበራዊ ኑሮ የሚችሉ ስለሆነ አይዞሽ አለንልሽ በየተራ እናርስሻለን ብለው አበሸሯት፡፡ እናትና አባቴ የሚኖሩት የመንግስት ቤት ተከራይተው ነው፡፡ ሁለት ክፍል ቤት ሰርቪስ እና የጋራ ውሀ እና የጋራ መፀዳጃ ያለው የመንግስት ቤት ነዉ ፡፡


መቼም እርግዝና ላይ ሴቶች የሚያምራቸዉ ነገር አለ...እናም አንድ ቀን እማ የበቆሎ ቂጣ አማረኝ አለችና ጎረቤቷ አሚናየ የሚባሉ አሮጊት አሉ መሀን ናቸው የቀን ስራ እየሰሩ ሂወትን ይገፋሉ፡፡ ለአላህ ብሎ የነየተ ሸህ ይማም በነፃ ሰርቪስ ውስጥ እዲኖሩ ፈቅዶላቸው ነው የሚኖሩት፡፡ ኡሚ በሆዷ ያሰበችዉ የበቆሎ ዱቄት ማግኘትን እንጂ በሆዷ መጥፎ ነገር አስባ አይደለም እናም አሚናየ ቤት ሂዳ
......የጤፍ ዱቄት በበቆሎ ቀይሩኝ ስትላቸው በጣም ተቆጡ በድህነታቸው እየቀለደችባቸው መሰላቸውና" ከመቸ ጀምሮ ነው ዩሱፍ በቆሎ የሚበላው?? ምነው የኔ በቆሎ መብላት ላንች ደነቀሽ??" አሏት፡፡ እንደዚህ ሲቆጡ ስታይ ኡሚ ደነገጠችና" እሽ ይቅርታ" ብላ ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ እሳቸው ግን ተናደው ስለነበር " እንዴት በድህነቴ ትቀልዳለች??" ብለው ለጎረቤት ሲነግሩ " አረ እርጉዝ ናት አምሯት ይሆናል" ብለው ነገሯቸው፡፡

እሳቸውም ምጣድ ሙሉ ቂጣ ጋግረው " ልጄ ይቅር በይኝ ሳላውቅ አስደነገጥኩሽ" ብለው ቂጣውን ሰጧት፡፡ ከሰጧት ቡሀላ እማማ አሚናት አዉፍ በይኝ ሲሏት
...አረ እማማ እኔ ቂም አልያዝኩም አለቻቸዉ፡፡ ከዛ ጊዜ በኃላ ግንኙነታቸው የእናትና ልጅ ሆነ "የሚያምርሽን ንገሪኝ እንዳትደብቂኝ እቀየምሻለሁ" ይሏታል፡፡ እማም እንደ እናቷ ነበር የምታያቸው የሚያምራትን ደስ ያላትን ምንም ሳትፈራ እንደ እናት ትጠይቃቸዋለች
....አሚናየም እሺ እያሉ በደስታ እያረጉላት እንደ ልጅ ይንከባከቧታል

መቼም ጊዜዉ ደረሰና አልሀምዱሊላህ ወደዚህ ምድር ተቀላቀልኩ....እኔ ስወለድ ኡሚ "ኒእማ" ብላ ስም አወጣችልኝ፡፡ አባቢ ደግሞ ትርጉሙ ምን እንደሆነ ባላውቅም "መራም" ብሎ ስም አወጣልኝ፡፡ እናም ስሜ "መራም" ሆኖ ፀደቀ፡፡

እኔ ከተወለድኩ በኃላ እኔን የሚንከባከበኝ ስላልነበረ እማ ስራዋን ለማቆም ተገደደች፡፡ ለኔ ስትል ስራዋን ትታ ከስራዋ ሁሉ በላጭ እኔን አድርጋ መረጠች፡፡ አባቢ እኔን ተንከባክባ ለማሳደግ ስትል ስራ በማቆሟ በጣም ተደሰተ፡፡ ቤት ሲገባ ሚስቱና ልጁ ቤቱን በፍቅር አሙቀው ይጠብቁታል፡፡ አባቢ ከስራ ወደ ቤቱ እስኪመለስ በጣም እንናፍቀዋለን፡፡ ከስራ እንደወጣ ቀጥታ ወደ ቤት መጥቶ ያጫውተናል ሽር ሽር ይወስደናል፡፡ ቤታችን በፍቅር የተሞላና ደስተኛ ቤተሰቦች ሆነን መኖር ጀመርን፡፡

እማ ስራ ትታ ቤት መዋል ስለጀመረች በአንድ ልጅ መድከሜ ካልቀረ ብላ ሁለተኛ አረገዘች፡፡ እኔም አመት ሞልቶኝ ቁሜ ለመሄድ በአቅሜ መፍጨርጨር ጀምሬያለሁ፡፡ ለማዳ በመሆኔ የያዘ ቢይዘኝ ያቀፈ ቢያቅፈኝ ለቅሶ አላውቅም፡፡ በዚህ ባህሪየ ሁሉም ጎረቤቶቻችን ይወዱኛል፡፡ እንዳገኘ አንጠልጥለውኝ ይዞራሉ፡፡ከዛ ሁሉ ሰው ግን አሚናየን በጣም እወዳቸዋለሁ፡፡ ገና በልጅ አንደበቴ እየተኮላተፍኩ አሚናየ ብለው ሲጠሩዋቸው እኔም " እማማዬ" ብየ ጠራኃቸው ከዛ ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ሰው እማማዬ ብሎ መጥራት ጀመረ፡፡ እሳቸውም በጣም ነው የሚወዱኝ ከሳቸው ቤት ምግብ ውጭ ሌላ አልበላም ብየ ሳስቸግራት ኡሚ በሳቸው ምግብ እየሰራች በሳቸው ሰሀን አድርጋ እማማየ ቤት ታስቀምጥልኝ ነበር፡፡

እኔም የእማማዬ ምግብ እየመሰለኝ ግጥም አድርጌ እበላለሁ፡፡እማማዬ ወደ ቤታቸው እስኪመጡ ድረስ በርበር እያየሁ እጠብቃለሁ፡፡ ከመጡ በኃላ ግን ኡሚን ትቻት እሳቸው ጋር ልጫወት እሄዳለሁ፡፡ኡሚ" ደክሟቸዋል ነይ ከኔ ጋር ተጫወች" ብትለኝም አልሰማትም፡፡ እማማዬም ሲመጡ እኔን ካላዩ ቤታቸው ሳይገቡ ወደኛ ቤት መተው ደህንነቴን ያረጋግጣሉ፡፡👇👇
እኔ አንድ አመት ከ8 ወር ሲሆነኝ ሪም ተወለደች፡፡ አሁን የቤተሰባችን ቁጥር ከ3 ወደ 4 ከፍ ብሏል፡፡ እኔና ሪም የቤቱ ድምቀት ሆንን፡፡ ኡሚ ሁለታችንም ሴት በመሆናችን ደስተኛ ሆነች ዘሯ የበዛላት መሰላት ሴት ዘር ታበዛለች ይባላል፡፡ እኔና ሪም እንደተከታታይ አንጣላም፡፡ ራሴን እንደትልቅ ልጅ ቆጥሬ ስንከባከባት እና ስጠብቃት የሚያየኝ ሰው ይደነቅብኛል፡፡ ሪምም ልክ እንደኔ ትወደኛለች የምላትን ነገር ትሰማለች፡፡ ገና በልጅ እድሜያችን እንደልጅ ትንቅንቅ ያለመግጠማችን መከባበር እና መተዛዘናችንን ያየ ሰው "ማሻአላህ" ሳይለን አያልፍም፡፡ እኛን እንደዚህ እንድንሆን ያደረገን ግን አንድ ሚስጥር አለ...

ክፍል ➍
ይቀጥላል........

Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
2024/09/25 20:20:37
Back to Top
HTML Embed Code: