Telegram Web Link
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሀያ ስምንት 2⃣8⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL



🌹የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ለአባወራዉ
🔟
#ተከታተላት

ሴት ስሜታዊ ፍጡር ናት ።ከምክንያታዊነት ይልቅ
◇ ስሜታዊነት ያሸንፋታል ።
◇ ከወንድ ይልቅ ይበልጥ ተቆጭ ናት ።
◇ በቀላሉ ትታለላለች ።
◇ ስሜታዊ ፍላጎቶቿን መቆጣጠር አትችልም ።
◇ በትንሽ ነገር ትናደዳለች ።
◇ በትንሽ ነገር ትደሰታለች ።ስለሆነም ባል የሚስቱን ባህሪና ተግባር መግራት መቻል አለበት ።ይህ ሲሆን ችግሮች አይከሰቱም።ባል ከሚስቱ ተግባራት ላይ ግዴለሽ ሊሆን አይገባም ።እሷን ማማከርና ተግባራቷን መቆጣጠር ፣ከመጥፎና ጠማማ ሰዎች ጋር አለመቅረቧን ማረጋገጥ አለበት ።

~~~ መጥፎ ጓደኛ መያዝ የሚያመጣውን ጣጣ ሊያሰረዳት ይገባል ።
✔የወሲብ ፍላጎትን የሚያነሳሳ ወጣ ያለ አለባበስ ለብሳ እንድትወጣ ፣
✔እንደ ጭፈራና መቃሚያ ቤት ባሉ ስብስቦች ላይ እንድትሳተፍ መፍቀድ የለበትም ።

~~~ ሴት ልጅ በምታደርጋቸው ድርጊቶችም ሆነ በምትይዛቸው ጓደኞች ችላ የምትባል ከሆነ ከመጥፎ ሰዎች ወጥመድ ውሰጥ ትገባለች ።በባሎቻቸው ቸልተኝነት ለተበላሸ ህይወት የተዳረጉና በመጥፎ ሰዎች የተታለሉ ብዙ ሴቶች አሉ ።በዚህ ችግር የተነሳ ብዙ ቤተሰብ ፈርሷል ።ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆችም ብዙ ናቸው ።

♦ ተገቢ ያልሆነ አለባበስ ለብሳ ከቤት የምትወጣ ሚስቱን የማይከላከል ባል ከተለያዩ አይነት ሰዎች ጋር እንድትጎዳኝ እየጋበዛት ነው ።

♦ ከመጥፎ ስብሰብ ውሰጥ እንድትቀላቀል የሚፈቅድ ከሆነ በራሱ ፣በሚሰቱና በልጆቹ ላይ ትልቅ ጉዳት ሊያደርሰ የሚችል ተግባር እየፈጸመ ነው ።ይህ አመለካከቱ ሚሰቱን በመቶዎች ወደሚቆጠሩ በቀላሉ ለመውጣት ከማይቻልባቸው የአደጋ ቀጠናዎች ያመራታል።

ጋዝ ተቀጣጣይ ነው ።እሳት በቀላሉ ያነደዋል ።ጋዝን ከእሳት አጠገብ አስቀምጦ አያቃጥለውም ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው ።ይህ አይነቱ ነፃነት ውጤቱ የከፋ ነው ።

♦ አንዲት ሴት ህገወጥ እንቅስቃሴ እያሳየች ባሏ ዝም የሚላት ከሆነ የፍላጎቷን አድማስ ታሰፋና በሁሉም ነገር ራሷን ከባሏ ነፃ አድርጋ ታሰባለች ።ይህ ደግሞ በትዳር ላይ መጥፎ ክስተቶች እንዲፈጠሩ ያደርጋል ።ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ሁለት ነጥቦች አስታውሰው ፦


➊ / አንድ ባል ሚስቱን መከታተል ትክክለኛ ተግባር ነው ።ነገር ግን በጥንቃቄና በብልሀት መሆን ይኖርበታል ።እንደሚከታተላት ካወቀች ምላሸ መጥፎ ሊሆን ይችላል ።ጥሩው መንገድ ቁጣና ብጥብጥን ማሰወገድ ልክ እንደ አንድ ተቆርቋሪ ጓደኛ ለሚሰቱ የመጥፎ ተግባራትን ጉዳት ማብራራትና በራሷ ተነሳሽነት ትክክለኛውን መንገድ እንድትመረጥ ማድረጉ ነው ።

➋ / ሚዛናዊ መሆን አለበት ።በጣም ወግ አጥባቂና እንዲሁም ደግሞ ግዴለሽ መሆን አያስፈልግም ።ሴት ልጅ እንደ ወንድ ሁሉ ነፃነት ትፈልጋለች ።
◇ ከጥሩ ጓደኞቿ
◇ ከወላጆቿ ፣
◇ ከወንድሞቿና
◇ ከእህቶቿ ጋር ያላትን ግንኙነት ከማጥበቅ መከልከል የለባትም ።የምትከለከላቸው አንዳንድ ነገሮች ቢኖሩም በነዚህ ሁኔታዎች ላይ እንኳን ቢሆን ከወሰን ማለፍ አሰፈላጊ አይደለም ።

✔ ማክረር አደገኛ ነው ።ለጥል ይጋብዛል ።የባሏ ወግ አጥባቂነት ያማረራት ሴት መጥፎ ነገር ውሰጥ ልትገባና ፍቺም ልትጠይቅ ትችላለች ።


~~~ አንዲት ወጣት ወ/ሮ ፍርድ ቤት ውሰጥ ለአንድ ጋዜጠኛ ስትናገር ፦"ከባለቤቴ ጋር ከአምስት ዓመት በፊት ነው የተጋባነው ።አንድ ወንድና አንዲት ሴት ልጆች አሉን ባለቤቴ ለሰው ያለው አመለካከት በጣም መጥፎ ነው ።ከማንም ጋር እንድንገናኝ አይፈልግም ።ከቤት ሲወጣ በሩን ከውጪ ቆልፎብኝ ይሄዳል ።የእስረኛ ኑሮ ነው የምኖረው ።ወደ ወላጆቼ ቤት እንኳ መሄድ አልችልም ።በሱ የተነሳ ቤተሰቦቼም ወደኔ ቤት አይመጡም ።ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም ።በአንድ በኩል ከሱ ጋር መኖር እንደሌለብኝ አስባለሁ ።በሌላ በኩል ደግሞ የልጆቼ የወደፊት እጣ ያስጨንቀኛል ።ግራ ስለገባኝ ሁኔታውን ለፍርድ ቤት ለማሳወቅ ተገደድኩ ።እንደ ውሳኔ ያስተላልፋሉ የሚል እምነት አለኝ "ተብላለች ።
.....እንዲህ አይነት ወግ አጥብቆ የሆኑና ችግር ያለባቸው ባሎች ሚስቶቻቸው ሳይፈልጉ ፍቺ እንዲጠይቁ ያደርጋሉ ።

~~~ ሚስትህ ከቅርብ ዘመዶች ጋር እንዳትገናኝ መከልከል ምን ይባላል ?
ይህ ተግባርህ ሚስትህ ታማኝ እንዳትሆን ሊያደርጋት እንደሚችል ታውቃለህ ? ያንተን ወግ አጥባቂነት ችላ ብትቀመጥ እንኳ ቤታችሁ ውሰጥ የሞቀ የትዳር ህይወት ሊኖር አይችልም ።እሰር ቤት ውሰጥ የገባች ሴት እንዴት ለባሏ የፍቅርና የደስታ ምንጭ ልትሆን ትችላለች ።?

ክፍል ➋➒
ይቀጥላል....
ምንጭ ☞ፍቅርና
ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሀያ ዘጠኝ 2⃣9⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL



💐 የትዳር ማጣፈጫ ቅመም
➊➒
#ተጠራጣሪ_አትሁኚ

ሚሰት ባሏን መከታተሏ ተገቢ ቢሆንም ከጥርጣሬና ከእምነት ማጣት ደረጃ መድረስ የለበትም ።ይህ የማይድንና ውጤቱ አስከፊ የሆነ የመጠራጠር በሸታ በብዙ ሴቶች ላይ ይስተዋላል ።

~~~ ተጠራጣሪ ሴት ባሏ አምሽቶ ከመጣ ወይም ከሆነች ሴት ጋር ሲያወራ ካየችው በሱ ላይ እምነት ታጣለች ።ከፀሐፊው ወይም ከሌላ ሴት ጋር ግኑኝነት አለው ብላ ትጠረጥራለች ።
✔ ችግረኛ ሴትንና ልጆቿን ሲረዳ ካየች እሷን ሰለፈለጋት እንጂ ሊረዳት ስለፈለገ ነው ብላ አታስብም
✔ስለ ባሏ ቁንጅናና መልካም ባህሪ የምታወራ ሴት ካለች ግንኙነት አላቸው ማለት ነው ።
✔ቢሮው ውሰጥ የሆነች ሴት ካየች ይቺን ሴት ይዟል ማለት ነው ብላ ታሰባለች ።በቂ ማረጋገጫ ሳትይዝ ቀሰ በቀሰ ባሌ ታማኝ አይደለም የሚል ድምዳሜ ላይ ትደርሳለች ።ጧት ማታ የምታስበው ይሄንኑ ብቻ ይሆናል ።ወዳጅና ጠላት ሳትለይ ላገኘችው ሰው ሁሉ ባሌ እንዲህ አደረገኝ እያለች ታወራለች ።ይህንን የሰሙት ሴቶች ደግሞ ያዘኑ በመምሰል "ወንዶች አያደርጉም አይባልም ።እንዳትለቂው የታባቱንሰ ! የእከሌ ባልም አያደርግም ጨዋ ነው እየተባለ ነው መጨረሻ ላይ እንዲህ አድርጎ ጉድ የሰራት "እያሉ የመጥፎ ወንዶችን ታሪክ ይነግሯታል ።

~~~ ቤት ውሰጥ ንዝንዝና ጭቅጭቅ ይጀመራል ።ትከታተለዋለች ።ስልኩን በመጎርጎር ፣በርሳውንና ኪሱን በመፈተሽ አለመታመኑን የሚጠቁም መረጃ ትፈልጋለች ።ለቤቷና ለልጆቿ ትኩረት ትነፍጋለች ።ለገንዘብ አወጣጧ ግድ አይኖራትም ።ቤቱ ሰላም ያጣል ።እሷም ትሰቃያለች ።ሲብሰም ቤቱን ጥላ ትወጣለች ።

ባልየው ጥፋተኛ ላለመሆኑ ማሰረጃ ቢያቀርብ ፣ይህን መጥፎ ተግባር እንዳልፈፀመ በሚል ቢገዘት በፍፁም አትቀበለውም ።



♦ አንዲት ሴት ለቤተሰብ ሸንጎ ስትናገር ፦"እንዴት ብላችሁ አትነገረሙ ።ከአስራ ሁለት ዓመት የትዳር ቆይታና ሶሰት ልጆችን ካፈራን በኋላ ከባሌ ጋር ለመፋታት ወሰኛለሁ ።

ባለቤት ታማኝ አይደለም ።ከጥቂት ቀናት በፊት ከእንዲት ቆንጆ ሴት ጋር መንገድ ላይ አየሁት ።የኮከብ ነጋሪ አምድ ያለው አንድ ሳምንታዊ መፅሄት አነብባለሁ ።በየሳምንቱ ባለቤቴ በወርሀ ስኔ ከተወለዱ ሴቶች ጋር ጥሩ ጊዜ እንደሚያሳልፍ ይገልፃል ።እኔ የተወለድኩት በየካቲት ወር ሰሀለሆነ እዚያ ላይ ከተጠቀሱት ሴቶች አንዷ አይደለሁም ።ከዚህም በተጨማሪ ባለቤቴ ለእኔ ያለው ፍቅር እንደድሮው አለመሆኑ ጥርጣሬዬ ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጦልኛል " ብላለች ።
......ባልየው ሲመልስም "እባክሽን ምን ማድረግ እንዳለብኝ ንገሪኝ ?እንዚህ መፅሔቶች የኔ ሚስት አይነቶቹን አንባቢዎች ግምት ውሰጥ ቢያሰገቡና መዋሸታቸውን ቢያቆሙ ምናለ ? አውነት ነው የምላችሁ እነዚህ ፅሑፎች የእኔና የልጆቼን ህይወት አመሰቃቅለውታል ።ከመፅሔቶቹ አንዱ በዚህ ወር በርካታ ገንዘብ ያገኛል ብሎ ቢፅፍ ያን ሁሉ ገንዘብ የት አደረሰከው እንደምትለኝ አትጠራጠሩ ።እሱ ይጠብቀኝ እንጂ ደብዳቤ ተቀብሏል ተብሎ ቢፅፍም ነገር ተበላሸ ።ለሁለታችንም መለያየት ሳይሻል አይቀርም ።ምክንያቱም ሚስቴ ምክንያት ለመቀበል በፍፁም ዝግጁ አይደለችም "ብሏል ።

♦ አንድ ወንድ ለፍርድ ቤት ሲናገር የሚከተለውን ተብሏል ፦ "ከአንድ ወር በፊት ነው ።ከአንድ ግብዣ ስመለስ ጓደኛየንና ሚስቱን መንገድ ላይ አገኘኋቸው ።መኪና ይዤ ስለነበር እግረ መንገዴን ወደ ቤታቸው አደረሰኳቸው ።በሚቀጥለው ቀን ባለቤቴ ወላጆቿ ቤት እንዳደረሳት ጠየቀችኝ ።መንገድ ላይ እያለን ኋላ ወንበር ላይ አንድ ረጂም የፀጉር ዘለላ ተመለከተች ።"ይህ የማን ፀጉር ነው ?"ብላ ጠየቀችኝ ።ጥርጣሬዋ ሰላበሳጨኝ መልስ ልሰጣት አልፈቀድኩም ።ቤተሰቦቿ ቤት አድርሻት ወደ ስራ ሄድኩ ።
....ከስራ እንደወጣሁ ልወስዳት ስሄድ ወደ ቤት ለመሄድ ፈቃደኛ አልነበረችም ።ምክንያትሸ ምንድን ነው? ብዬ ስጠይቃት ከባለ ፀጉሯ ጋር ብትኖር ይሻልሀል አለችኝ ።

♦ ሌላዋ ወጣት ፍርድ ቤት ቀርባ እንዲህ ስትል በማማረር ባሏን ከሳለች ።
..."ባለቤቴ የትርፍ ሰዓት ስራ እሰራለሁ በማለት ሁሌ እያመሸ ይመጣል ።ጎረቤቶቻችን የሚያወሩትን ስሰማ ጭንቀቴና ጥርጣሬዬ እየጨመረ መጣ ።የትርፍ ሰዓት ስራ እየሰራ ሳይሆን ከሴት ጋር ሲዝናና ነው የሚያመሸው እያሉ ያወራሉ ።እሱ ግን ይዋሸኛል ።እኔ ደግሞ ከውሸታም ሰው ጋር ለመኖር ዝግጁ አይደለሁም ።በዚህ ጊዜ ባልዮው ከክሱ ነፃ መሆኑን የሚያረጋግጡ ደብዳቤዎችን ከኪሱ በማውጣት ለዳኛው ሰጣቸው ።ዳኛውን ጮህ ብለው ደብዳቤዎቹን ማንበብ ጀመሩ ።

አንደኛው ደብዳቤ ከምሽቱ ሁለት እሰከ ስድሰት ሰዓት የትርፍ ሰዓት ሥራ እንደሚሰራ የሚያመለክት ነበር ።



ሌሎቹ ደብዳቤዎች ደግሞ ሴሚናር ላይ መሳተፉን ይገልጻሉ ።ሚስት ደብዳቤዎቹን ካየች በኋላ "ዘወትር ማታ ላይ ኪሶቹን እፈትሸ ነበር ።ነገር ግን አንድም ደብዳቤ አላገኘሁም "አለች ።ዳኛው "ቢሮ ውሰጥ አስቀምጧቸው ሊሆን ይችላል "አሉ ።
...ባልዮውም "ሚስቴ በኔ ላይ ያላት ጥርጣሬ እየጨመረ ሲሄድ እኔም እሷን መጠራጠር ጀመርኩ ።እንቅልፍ ሰተኛ ያቃዠኛል ።እኔን ፈትታ ልታገባው ያሰበችው ሰው ሳይኖር አይቀርም ብዬ እሰከማሰብም ደርሻለሁ "አለ ።በዚህ ጊዜ ሚሰት ወደ ባሏ በመጠጋት የደስታ እንባ እያነባች ይቅርታ ጠየቀችው ።ተያይዘው ወደ ቤታቸው ሄዱ ።


♦ አንድ የጥርስ ሐኪም ፍርድ ቤት ቀርቦ "ሚስቴ በጣም ቀናተኛ ሴት ነች ።ብዙ ሴቶች ለህክምና ወደኔ ይመጣሉ ።ይህ ደግሞ የሚስቴን ቅናት ይጨምረዋል ።ዘወትር በዚህ ጉዳይ ላይ እንጨቃጨቃለን ።ሴቶችን ማከም የለብህም የሚል እምነት አላት ።እኔ ግን ደንበኛቼን ማባረር አልፈልግም ።ሚስቴን በጣም እወዳታለሁ ።እሷም ትወደኛለች ።ይህ ከንቱ ጥርጣሬዋ ግን ትዳራችንን እየበጠበጠው ነው ።ከጥቂት ቀናት በፊት ቢሮዬ መጣችና ካልመጣህ ብላ አመናጭቃ አሰወጣችኝ ።ወጣሁና ወደ ቤት ሄድን ።ችግሯ ምን እንደሆነ ስጠይቃት
፦"ቢሮህ መጥቼ እንግዳ መቀበያ ክፍል ውሰጥ ከአንዲት ወጣት ጎን ተቀመጥኩ ።ስላንተ ማውራት ጀመርን ።ሚስትህ መሆኔን አላወቀችም ።ሐኪሙ ቆንጆና ጥሩ ባህሪ ያለው ሰው ነው አለችኝ ።ማንም ሰው የፈለገውን አሰተያየት ሊሰጥ ይችላል።ሴትዮዋ በሰጠችው አሰተያየት እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ ? ሲል አማሯል ።


♦ ሌላዋ ሴት ደግሞ ለፍርድ ቤት ስትናገር ፦"ባለቤቴ አንዲት ሴትዮ ቤት ሲገባ እንዳየችው ጓደኛዬ ነገረችኝ ።አንድ ቀን ከቤት ሲወጣ ተከተልኩትና እውነት መሆኑን አረጋገጥኩ ።አሁን ፍርድ ቤቱን የምጠይቀው እዚያ ቤት ለምን እንደሚገባ አጣርቶ በሱ ላይ ቅጣት እንዲጥልልኝ ነው"አለች ።
ባልዮውም ሚሰቱ የተናገረችውን በመመርኮዝ ፦"አንድ ቀን መድኃኒት ለመግዛት ወደ አንድ ፋርማሲ ጎራ አልኩ ።ፋርማሲው ውሰጥ መድኃኒቱ በመግዛት ላይ የነበረች አንዲት ሴት ነበረች ።ለመድኃኒቱ መግዣ የሚሆን በቂ ገንዘብ አልነበራትም ።ቀሪውን ገንዘብ ሞላሁላት ።

ሴትዮዋ ባሏ የሞተባት ችግረኛ ሴት መሆኗን ተረዳሁ ።ስለዚህ እሷን መርዳቴን መቀጠል እንዳለብኝ ወሰንኩ "ብሏል።ዳኛውም ጉዳዩን በጥሞና ከመረመረ በኋላ ባል እውነተኛ መሆኑን አረጋግጥ ጥንዶቹን አስታረቀ ።


~~~ እንዲዚህ አይነት ችግሮች በብዙ ትዳሮች ላይ ይከሰታሉ ።
◇ በቤተሰብ መካከል ጥርጣሬና ጥል ይነግሳል ።
◇ ልጆች ይሰቃያሉ ።
◇ የወላጆቻቸው ጭቅጭቅ አዕምሯዉ👇👇
ውሰጥ
◇ የሚጥለው ጠባሳም ቀላል አይሆንም ።

》》ጥንዶቹ በዚህ መልኩ የሚቀጥሉ ከሆነና አንዱ ነገሩን ችላ የማይል ከሆነ በርግጠኝነት ወደ ፍቺ ያመራል ።ፍቺ ደግሞ ለሁለቱም አይጠቅምም ።
■ ልጆችንም ለእንግልት ይዳርጋል ።
■ ወላጆቻቸው የተፋቱ ልጆች ጤናማ ህይወት ሊኖሩ አይችሉም ።
■ ለእንጀራ እናት ወይም ለእንጀራ አባት ችግር ይጋለጣል ።

ባል ሚስቱን በመፍታት በሰላም አብራኝ የምትኖር ሌላ "ፍፁም የሆነች ሴት አገኛለሁ ብሎ ሊያሰብ ይችላል ።ነገር ግን ይህ ብዙ ጊዜ ህልም ሆኖ ነው የሚቀረው ።ምክንያቱም ከአዲሷ ሴት ሌላ አዲስ ችግር ይገጥመዋል ።

ፍቺ ለሴቷም ቢሆን የደስታ ጎዳና አይሆንም ።ለጊዜው ባሏን በመበቀሏ ደስ ይበላት እንጂ እንደገና ማግባት ቀላል ሆኖ አታገኘውም ።ምናልባትም ቀሪ ህይወቷን በብቸኛነት ለመኖር ልትገደድ ትችላለች ።ሌላ ባል ብታገባ እንኳን አዲሱ ባሏ ከሷ ፍላጎት ጋር ለመጣጣሙ እርግጠኛ መሆን አይቻልም ።
◇◇ ሚሰቱ የሞተችበትን ወንድ በማግባት ልጆቹን ለማሳደግም ትገደድ ይሆናል ።ስለዚህ ጥልም ሆነ ፍቺ ለጥንዶቹ አይጠቅማቸውም ።


~~~ ነገር ግን ሁሌም ሰላም ለመፍጠር የሚያሰችል እድል አለ ።ሴቷም ሆነች ወንዱ ምክንያታዊ ለመሆን መሞከር ይኖርባቸዋል ።ወንዶች በዚህ ዙሪያ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው ።የመፍትሄው ቁልፍም በእጃቸው ነው ።ራሳቸውን መጠበቅና ሚስቶችን ሊያጠራጥሩ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ አለባቸው ።

#ክፍል ➌ዐ
ይቀጥላል.....
ምንጭ ☞ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ



👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሰላሳ 3⃣0⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL



#ጥቂት_ምክር_ለሴቶች ፦

#እመቤት_ሆይ !

#በመጀመሪያ ባልሽን አለማመንሸ
እንደማንኛውም ነገር ሁሉ ማረጋገጫ ሊኖረው ይገባል ።ድርጊቱን ለመፈፀም ማረጋገጫ አሰካላገኘሸ ድረስ ልትወነጅይው መብት የለሽም ።የሰው ልጅ ህሊናም ሆነ ህግ አንድ ሰው ቢሆንም እንዲወነጀሉ አይፈቅዱም ።አንቺ ባልሰራሸው ሰራ ብትታሚ ደስ ይልሻል ? ታድያ በሱ ላይ ለምን ትፈፅሚዋለሸ ? ያንቺ ተራና መሰረት ቢስ ጥርጣሬ ባልሽን ዝሙትን በመሰለ ከባድ ወንጀል ሊያሰከሰሰው አይገባም ።


#እመቤት_ሆይ ! ለድምዳሜ ከመቸኮልሸ በፊት ጊዜ ወስደሽ ባልሽን እንድትጠረጥሪው ያደረጉሸን ነገሮች ሁሉ ቁጭ ብለሸ ፃፊያቸው ።ከእያንንዳንዱ ነጥብ ፊት ለፊትም ይህ ሊሆን ይችላል ....ሊሆን ይችላል ....እያለሽ ለድርጊቱ መፈፀም ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ አጋጣሚዎችን ሁሉ ፃፊ ።

~~~ ቀጥለሸም ራስሸን እንደ ፍትኃዊ ዳኛ በመቁጠር ሰለፃፍሻቸው ነገሮች በጥልቀት አሰቢ በትክክል ጥፋተኛነቱን የሚያረጋግጡልሸ ከሆነ ጉዳዩን እርግፍ አድርገሽ ተይ ።አለበለዚያ ደግሞ ሌላ ምርምር አድርጊ ።ለምሳሌ የፀጉር ዘለላ ባለቤትሽ መኪና ውሰጥ መገኘቱ ከሚከተሉት ባንዱ ሊተነተን ይችላል ፦

➊ የእህቱ ፦የእናቱ ፣የአክስቱ ወይም የልጆቻቸው ፀጉር ሊሆን ይችላል ።

➋ የአንቺ ፀጉር ሊሆን ይችላል ።

➌ ጓደኛውን ወይም ዘመዱን ከነሚስቱ አሳፍሮ ሊሆን ይችላል ።

➍ ችግረኛና ደካማ ሴትን አሳፍሮ ሊሆን ይችላል ።

➎ የመሳሪያ ቤት ባልደረባው አሳፍሮ ሊሆን ይችላል ።

➏ ያንችን ጥርጣሬ ለማጉላት የሚፈልጉ ሰዎች ሆን በለው ፀጉሩን አስቀምጠውት አሳፍሮ ሊሆን ይችላል ።

➐ ፍቅረኛውን አሳፍሮ ሊሆን ይችላል ።ፍቅረኛውን አሳፍሮ ሊሆን ይችላል የሚለው ነጥብ በመጨረሻ ሊመጣ የሚችል አማራጭ በመሆኑ ትኩረት ሊደረግበት አይገባም ።

~~~ ሌሎቹን አጋጣሚዎች ሁሉ ችላ ብሎ ይህ ስለሆነ ብቻ ነው ብሎ መደምደም ተገቢ አይደለም ።

◇ ባለቤትሽ ዘግይቶ ቤት ከገባ
◇ የትርፍ ሰዓት ስራ እየሰራ ይሆናል ።
◇ ታክሲ አጥቶ ይሆናል ።
◇ መንገድ ተዘጋግቶበት ይሆናል ።
◇ ጓደኛኞቹ ቤት ሄዶ ይሆናል .....ብለሽ አሰቢ ።ሌላ ሴት ሰለባልሸ ጥሩ ሰው መባልም ወንጀል አይደለም ።ባለቤትሽ ሁሉም ሰው የሚጠላው መጥፎ ሰው ቢሆን ይሻልሻል ? ባሏ የሞትባትን ድሃ ሴትና ልጆቿን የሚረዳ ከሆነ ባልሽ ምፅዋት የሚሰጥ ለጋስ በመሆኑ ልትደሰቺ ይገባል ።

ባለቤትሽ
☞ ስልኩን በሚስጥር ቁጥር የሚዘጋ ፤
☞ቁም ሳጥኑን የሚቆልፍ ፦
☞ ወይም ዶክመንቶችን እንዳታነቢበት የሚፈልግ ከሆነ የሆነ ነገር አለ ማለት ነው ብለሸ አታሰቢ ።ወንዶች በአጠቃላይ የሚሰጥራዊነትና የቁጥብነት ባህሪ አላቸው ።የግል ጉዳዮቻቸውን ሌሎች እንዲያውቁባቸው አይፈልጉም ።ምናልባት ከሰራው ጋር በተያያዘ ሚስጥራዊ ነገሮች ሊይዝ ይችላል ።ላንቺ ያልነገረሸ ወይም የደበቀሸ ደግሞ ባጋጣሚ ሚሰጥሬን ባትጠብቅልኝሰ የሚል ፍራቻ አድሮበት ሊሆን ይችላል ።


#ሁለተኛ ☞ ጥርጣሬ በሚያድርብሸ ጊዜ ከባለቤትሽ ጋር ውይይት በማድረግ እውነታውን ለመፈተሽ ሞክሪ ።


አዕምሮሸ ንፁህ እንዲሆንና ሰላም ታገኚ ዘንድ በቁጣ ሳይሆን በትዕግስት ግልፅ ሆነሽ የጥርጣሬሸ ምንጭ የሆነውን ነገር በመንገር እንዲያብራራልሸ ጠይቂው ።ማብራሪያውን በጥሞና አድምጪ ።በዚህ ጥርጣሬሸ ከተወገደ ችግሩ ተፈታ ።አሁንም ጥርጣሬው ካለሽ ግን እውነቱ እሰከሚገለፅልሸ ድረሰ ጉዳዩን መርምሪ ።

♦ በማጣራት ላይ እያለሽ ባልሽ እንደዋሸሸ የሚያመላክት ነገር ብታገኚ የጥፋቱ ማረጋገጫ አድርገሽ አትውሰጂው ።በእርግጥ ውሸት ተገቢ ባይሆንም የዋሸሽ ሁሉንም እውነት ቢነግርሸ ጥርጣሬሸ ሊጨምር ይችላል ብሎ በመፍራቱ ሊሆን ይችላል ።

~~~ ስለዚህ ለምን እውነቱን እንዳልነገረሸና አሁንም እውነቱን እንዲነግርሸ ደግመሸ ጠይቀው ።ነገሩን በደንብ ለማስረዳት ባይችል ጥፋተኛ ስለሆነ ነው ብለሸ አትደምድሚ ።የሆነ ነገር ረስቶ ወይም ፈርቶ አለያም ጥሩ ሰሜት ውሰጥ ስላልሆነ ሊሆን ይችላል ።ስለዚህ እዚያ ላይ ችክ አትበይ ።ጉዳዩን ለሌላ ጊዜ አቆይው ።የሆነ ነገር ረሳሁ ካለሽ ተቀበይው ።አሁንም ጥርጣሬው ካለሸ በሌሎች መንገዶች ለማጣራት ሞክር ።

#ሶስተኛ ☞ ጥርጣሬሸን ላገኘሸው ሰው ሁሉ አታውሪ ።ምክንያቱም ሁሉም ሰው ወዳጅ ሊሆን አይችልም ።ጠላቶችሸን ያንቺን ህይወት ለማበላሸት ሲሉ ነገሩን የሚያባብሱ ወሬዎችንና ውሸቶችን ሊያመጡልሸ ይችላሉ ።የግድ ጠላት ባይሆኑም አንዳንድ ሞኝና አርቆ ማሰብ የተሳናቸው የቅርብ ዘመዶችሸ ወይም ጓደኞችሸ ይህን ሊያደርጉ ይችላሉ ።

ምክር ጠቃሚ የሚሆነው
☞ከብልህ ፣
☞አስተዋይና
☞ሀቀኛ ሰዎች ጋር ሲሆን ነው ።ስለዚህ ጉዳይሽን ለሰው ከማማከርሸ በፊት የምታማክሪያቸውን ሰዎች ምረጪ ።

#አራተኛ☞ ለባልሸ ጥፋተኝነት ትክከለኛ ማሰረጃ ካልተገኘ ፤ጓደኛችሸና ቤተሰቦችሸ ማረጋገጫው በቂ አይደለም ብለው ካሰቡ ፣ባልሸም ድርጊቱን አልፈፀምኩም ካለ ፣አንቺ ግን አሁንም የምትጠራጠሪ ከሆነ በአንድ ነገር ላይ እርግጠኛ ሁኚ....ታመሻል ።ካንቺ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ የጥርጣሬ ምንጮች እያደጉ የአዕምሮ መዛባት አስከትለውብሻል ።ስለዚህ ተገቢውን እርዳታ ታገኚ ዘንድ ወደ ስነልቦና አማካሪ ሂጂ ።

#አምስተኛ ☞ ከባልሽ ጋር ጥል ለመፍጠር ወይም ጉዳዩን ለፍርድ ቤት ለማቅረብ መሞከር የለብሽም ።ሰለ ፍቺ አታውሪ ።ሰለ ፍቺ ማውራት ፍቺን ሊያሰከትል ይችላል ።
✔ ሞኛሞኝ ድርጊቶችን ከመፈፀም ወይም ራሰን ለማጥፋት ከመነሳሳት ተቆጠቢ ።
✔ በትዕግስትና በብልሃት ችግርን መፍታት እየተቻለ መሰረት በሌለው ነገር ተነሳስቶ ህይውትን ያህል ከባድ ነገር ማጣት ተገቢ አይደልምና ።

#ስድስተኛ ☞ ባልሽ ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት እንዳለው በበቂ መረጃ ከተረጋገጠ አንቺ ላይ ችግር አለ ማለት ነው ።ምክንያቱም በሱ ላይ ለሌላ ሴት መግቢያ ሊሆን የሚችል ክፍተት ባይኖር ኖሮ ባልሽ አንቺን ትቶ ወደ ሌላ ሴት ባልሄደ ነበር ።ስለዚህ አንቺንም ልትወቀሸ ይገባል ።ነገር ግን ተሰፋ መቁረጥ የለብሽም ።አሁንም ጊዜ አለሽ ።ባልሽን ወደ አንቺ ለመሳብ ትችይ ዘንድ ያለብሸን ችግሮች በማስተካከል ባልሽ ካንቺ ያጣቸውን ነገሮች ለማሟላትና ልቡን ለማሸነፍ ጥረት አድርጊ ።


♦♦ ብዙ ወንዶች ሚስቶቻቸውን ትተው ወደ ሌላ ሴት የሚሄዱት ሚስቶቻቸው ራሳቸውን ካገቡ በኋላ ግን ራሳቸውን ይጥላሉ ።ልጅ ሲወልዱ ደግሞ ትኩረታቸውን ሁሉ ወደ ልጆቻቸው ብቻ ያደርጉና የባሎቻቸውን ፍላጎት ለማሟላት አይጨነቁም ።

እነዚህ ነገሮች የወንዶችን ልብ ሰለሚያሸፍቱ
☞ራስሸን መጠበቅ ፣
☞ቤት ውሰጥ በምትሆኚበት ጊዜ የሚያማምሩ ልብሶችን መልበስ ፣
☞መኳኳልና ማጌጥ ይኖርብሻል ።ይህ ከሆነ የባልሸን ስሜት መግዛት ትችያለሽ ።


ክፍል ➌➊
ይቀጥላል.....
ምንጭ ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሰላሳ አንድ 3⃣1⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANAL


💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም
➋O
#ለአሉባልታ_ወሬ ትኩረት_አትስጪ

አንዳንድ ሰዎች እርስ በርስ የመተማማት ባህሪ አላቸው ።ይህ መንስኤም ይሆናል ።
✔በሰዎች መካከል ጥርጣሬ እና ግጭትን ያስከትላል
✔ጓደኝነትን ያበላሻል ።
✔ባልና ሚስትን ያለያያል ።
✔ቤተሰብን ይበትናል ።
✔ለወንጀል ተግባር ይዳርጋል ።

>>>> ይህ ባህሪ መጥፎ መሆኑ እሰኪረሳ ድረስ በሰዎች ዘንድ ተስፋፍቶ ይገኛል ።ሴቶች በሚሰባሰቡባቸው ቦታዎች ሁሉ በተለይ ደግሞ ቡና ላይ ሀሜት የተለመደ ተግባር ነው ።በየቤቱ በመዞር ውድድር እስኪመስል ድረስ በተራ ሰለ ሰዎች የሆነ ያልሆነውን ያወራሉ ።
☞ ስለ ባሎቻቸው መልክ ፣
☞ ስለ ስራቸው ፣
☞ በሌሎች ወንዶች ላይ ስለሚታየው ጉድለት ወዘተ ይዘባርቃሉ ።ወሬው የሚቆመው ሲለያዩ ብቻ ነው ።አንዷ ሴት የሌላዋ ሴት ባል ጫማ ሱሪ ወይም መካኒክ በመሆኑ ሚሰትየውን ታንቋሸሻለች ።ለምሳሌ ባሏ ሾፌር ከሆነ

✿ ባልሽ ሁልጊዜ ጉዞ ላይ ነው ።ይህን ነገር እንዴት ትንቋቋሚዋለሸ ?

✿ የስጋ ቤት ሰራተኛ ከሆነ ባልሽ ሁልጊዜ ስጋ ስጋ ይሸታል ።

✿ ደመወዙ ትንሽ ከሆነ በዚህ ደመወዝ እንዴት መኖር ትችያለሽ ?

✿ መልከኛ ካልሆነ ይህን ቁንጅና ይዘሽ ይህን አጭርና አስቀያሚ ሰው እንዴት አገባሽዉ? ቤተሰቦችሸ እንዴት ለሱ ይድሩሻል ? መታገስ አቃታቸው ? የፈለግሸውን መርጠሸ ማግባት ትችይ ነበር ።

ራሷ መርጣ ያገባቸው ከሆነ ደግሞ ይህን ሰውዬ እንዴት መረጥሸው ? ወይ መልኩ የለው ወይ ፀባይ የለው ።በዚያ ላይ ከቤት ሲወጣ ይዞሸ አይወጣም ።የትም ቦታ ይዞሸ አይሄድም ።እንዴት ነው ከሱ ጋር መኖር የምትችይው ?

✿ ያልተማረ ከሆነ አንቺ የተማርሸ ነሽ እንዴት ይህን መሐይም ታገቢያለሽ ?

ይህ አይነቱ ወሬ በብዙ ሴቶች የተለመደ ነገር ነው ።
ወሬያቸው ነገ ምን እንደሚያስከትል አያስቡም ።የነሱ ሐሜትና ጉድለት ፍለጋም ለፍቺ ከፍ ሲልም እንደ ነፍስ ግድያ ላሉ ታላላቅ ወንጀሎች ሊዳርግ እንደሚችል አይገነዘቡም ።እንዚህ ሰዎች በሰው ምስል የተሰሩ ሰይጣኖችና በባልና ሚሰት መካከል ግጭት በመፍጠር ሰላማዊ የትዳር ህይወትን ወደ ጨለማና አስፈሪ አዘቅት የሚለውጡ የትዳር ቀበኞች ናቸው ።ይህ የሁሉም ህብረተሰብ ሴቶች ባህሪ ነው ።


ይህ ባህሪ ያላቸው ሴቶች የተለያዩ ዓላማዎች ይኖሯቸዋል ።
☞ ቤተሰብን በመበተን ለመበቀል ፣
☞ በቅናት ተነሳስተው ራሳቸውን ከፍ ከፍ ለማድረግና ☞ የራሳቸውን ጉድለት ለመሸፈን ፣
☞ ተቆርቋሪ በመምሰል በቀላሉ የሚሞኙ ሴቶችን ለማታለል ይጠቀሙበታል ።አንዳንዴም ለማዳበሪያ ሲሉ ብቻ ሀሜት ይፈፅማሉ ።ከዚህ ውጪ ግን ሰዎችን ለመርዳት ወይም ለበጎ ነገር ተብሎ የሚፈፀም ሐሜት አለመኖሩ መታወቅ አለበት ።

~~~ የሐሜት ውጤት የከፋ መሆኑን ይገነዘቡ ዘንድ የሚከተሉትን ምሳሌዎች ይመልከቱ ።

♦አንዲት ሴት ለፍርድ ቤት ስትናገር ፦"ከባለቤቴ ጋር በሰላም እንኖር ነበር ።ሆኖም አቶ እከሌ በእኔና በባሌ መካከል ግጭት የሚፈጥሩ ነገሮችን ያወራልኝ ጀመረ ።ባሌ ለኔ ጥሩ እንዳልሆነ ፣ፍላጎቴን እንደማይረዳና ለኔ ምንም አይነት ፍቅር እንደሌለው ይነግረኛል ።ፈትቼው እሱን እንዳገባውም ይመክረኛል ።በመሆኑም በዚህ ነገር ተታልዬ ከሱ ጋር በመተባበር ባሌን ገደልኩት "ብላለች ።

#እመቤት_ሆይ ! ልጆችሸና ባልሽን የምትወጂ ከሆነ የሀሜትን መጥፎ ውጤት ተረድተሸ ከሰው መሰል ሰይጣኖች ምላስ ተጠንቀቂ ።ለነሱ የውሸት ጓደኝነት እጅ አትሰጪ ።እነዚህ ሰዎች ከትዳርሸ ሰትፈናቀይ ማየት የሚፈልጉ ጣላቶችሸ እንጂ ወዳጆችሸ አይደሉም ።በቶሎና በቀላሉ አትመኛቸው ።ድብቅ ዓላማ ሊኖራቸው እንደሚችል እወቂ ።

✿ ባለቤትሸን ማንቋሸሽ ሲጀምሩ ፈጥነሸ አሰቁሚያቸው ።መፍራት የለብሽም ።ከኔ ጋር በወዳጅነት መቀጠል የምትፈልጉ ከሆነ ሰለ ባለቤት መጥፎ ነገር ማውራታችሁን አቁሙ ።እኔ ስለሱ ምንም አይነት መጥፎ ነገር መሰማት አልፈልግም ።ባለቤቴን ሰታንቋሸሹ እኔንም እያንቋሸሻችሁኝ እንድሆነ ነው የሚሰማኝ ።እሱ ለኔ በጣም የምወደውና እንከን የማይወጣለት ሰው ነው በያቸው ።

ለባለቤትሸ እና ለትዳርሸ ያለሽን ፅኑ ፍቅር እንዴ ከአንደበትሸ ከተገነዘቡ ይደነግጡና መጥተው አንቺን ከመረበሸ ይቆጠባሉ ።ይቀየሙኝና ይርቁኛል ብለሸ አታሰቢ ።እውነተኛ ጓደኞችሸ ከሆኑ አይቀየሙሸም ።እንደውም ከጥፋታቸው ሰላረምሻቸው ሊያመሰግኑሸ ይገባል ።

♦ ጣላቶችሸ ከሆኑ ደግሞ ጠላትን ከመራቅ ሌላ የሚሻል ነገር የለም ።ከመጥፎ ተግባራቸው የማይመለሱ ሰዎች ሲያጋጥሙሸ ከነሱ ጋር ያለሽን ግንኙነት አቋርጪ ።


#ክፍል ➌➋
ይቀጥላል.....
ምንጭ ☞ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ



👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሰላሳ ሁለት 3⃣2⃣

በISLAMIC UNIVERSITY CHANNA
L


💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም
➋➊
#የባልሸን_ፍላጎት_አሰቀድሚ

ሴት ልጅ ከወላጆቿ ጋር በምትኖርበት ወቅት ተግባሯ የነሱን ፍላጎት በማሟላት ላይ ይወሰናል ።ስታገባ ግን ሚናዋ ይቀይራል ።በባሏ ቤት ውሰጥ ሚስት ለባሏ ፍላጎት ቅድሚያ መሰጠት ይጠበቅበታል ።በወላጆቿና በባሏ መካከል ግጭት ቢፈጠር ከባሏ ጎን መቆም አለበት ።ወላጆቿን የሚያስከፋ ቢሆንም ።ምክንያቱም ከባሏ ጎን አለመቆሟ የትዳር ህይወቷን አደጋ ውሰጥ ይጥለዋል ።ትዳር ከፈረሰ ደግሞ መመለስ አሰቸጋሪ ነው ።ከቤተሰብ ጋር ግን በሂደት መስማማት ይቻላል ።

♦ አንዳንድ እናቶች ልጆቻቸው ከባሎቻቸው ጋር ተስማምተው እንዲኖሩ መተው እንዳለባቸው አይገነዘቡም ።ጥንዶቹ በራሳቸው ጉዳዮች ላይ ራሳቸው እንዲወሰኑና ችግር ሲያጋጥማቸውም በራሳቸው እንዲፈቱ መተው ያሰፈልጋል ።ነገር ግን ይህን ነገር በአዕምሯቸው ሰለማያሰቀምጡ የልጃቸው ባል በነሱ ፍላጎት መሰረት እንዲንቀሳቀስ ይፈልጋሉ ።

ከዚያም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ትዳር ውሰጥ ጣልቃ በመግባት ምንም የማታውቅ ልጃቸው በባሏ ላይ ተፅዕኖ እንታደርግና ከሱ ተቃራኒ እንድትሆን ያደርጋሉ ።
>ይህን አድርጊ
>ይህን አታድርጊ ፣
>ይህን በይ ፣
>ይህን አትበይ እያሉ ይመክሯታል ።ደካማ ሚስትም እናቷን እንደ ተቆርቋሪና ልምድ ያላቸው አድርጋ ሰለምትቆጥር የተባለችውን ሁሉ አለበለዚያ ግን ጭቅጭቅ ይፈጠራል ።በእናት ጦስም የልጅ የትዳር ህይወት ይበጠበጣል ።


♦ ለምሳሌ እናት ለልጇ ፦
"ህይወትሸን በገዛ እጅሽ አበላሸሸው ።እኔ እንዲህ አይነት ባል አይቼ አላውቅም ።በእርግጥ ችግሩ የሱ አይደለም ።ያንቺ ነው ።ወንድ ልጅ ኮስተር ሲሉበት ይወዳል ።እንደፈለገ ሲሆን ዝም ሰለምትይው ነው ጭንቅላትሸ ላይ የወጣው ።የአክሰትሸን ልጅ እንኳ አታይም ? እንዴት አይነት ህይወት እንዳላት !እህትሸም ብትሆን ተከብራ ነው የምትኖረው ! ኑሯቸው ካንቺ ጋር የሚወዳደር አይደለም ።ለምን ህይወትሸን አታሰተካክይም ? ባንቺ ተቃጥዬ ልሙት !"ትላታለች ።ይህን መሰሎ ምክራቸው እንደተቆርቋሪ የተቆጠረ እናት በልጃቸውና በባሏ መካከል ግጭት እንዲፈጠር መንሰኤ ይሆናሉ ።ሚሰት ከባሏ ጋር አተካራ ውሰጥ ትገባለች ።ቤተሰቦቿም ከሷ ጎን ይሰለፉና በትፋታ እንደሚሻል ያላቸውን ፍላጎት ይገልፃሉ ።


♦ ከትዳሬ አፈናቅላኛለች በሚል አንዲት የሰላሳ ዓመት ሴት የአምሳ ዓመት እድሜ ያላቸውን እናቷን ደበደበች ።ሰትጠየቅም "እናቴ ሰለ ባሌ ብዙ መጥፎ ነግሮችን ታወራልኛለች ።በዚህ የተነሳ በእኔና በባሌ መካከል ቅራኔ ተፈጠረ ።በመጨረሻም ተፈታን ።ፍቺው ከተፈፀመ በኋላ ተፀፀትኩ ።

ነገር ግን ልመልሰው አልቻልኩም ።ባለቤቴ የገዛ ዘመዴን አገባ ።በዚህ ተበሳጨሁና እናቴን ለመደብደብ ወሰንኩ "ብላለች ።

♦ አንድ የሰላሳ ዘጠኝ ዓመት አባወራ የሚከተለውን ደብዳቤ በመፃፍ ሚስቱንና የሚስቱን እናት ጥሎ ይጠፋል ።"ሚስቴ ለኔ ያላት አመለካከት እየተበላሸ በመምጣቱ ስራ ተቀይሬያለሁና ወደ ሌላ እገር እንሂድ ስላት ለመሄድ ፈቃደኛ አልሆነችም ።በእኔ የሚጨክን አንጀት ይኖራታል የሚል ሃሳብ ስላልነበረኝ ስሜቴ በጣም ተጎዳ ።በመሆኑም ይህንን ዓለም ለመሰናበት ወሰንኩ ።ሚሰቴና እናቷ ለኔ ሞት ተጠያቂ ናቸው " በማለት በሚስቱ እናት ጣልቃ ገብነት የተማረረው ባል ራሱን አጠፋ ።


♦ "ተመሳሳይ ችግር የገጠመው ሌላው ሰው አማቱን ከታክሲ ገፍትሮ ጣላቸው ።"የእንደዚህ አይነት እናቶቻቸውን ፍላጎት ለማሟላት የሚጥሩ ልጆች በራሳቸው ላይ ከባድ ችግር ይፈጥራሉ ።ስለዚህ ለትዳራቸው ደህንነት የሚያስቡ ሴቶች በእናቶቻቸው ፍላጎት ተፅዕኖ ስር መውድቅና እነሱን ሙሉ በሙሉ ትክክለኛ አድርገው መቁጠር የለባቸውም ።

~~~ ብልህና ጠንካራ ሴት ሁልጊዜም ቢሆን እናቷ ያሏትን ነገር በትዳር ህይወቷ ላይ ተግባራዊ ከማድረጓ በፊት ጉዳዩን ትመረምራለች ።ተግባራዊ ማድረግ ያለባት በትዳሯ ላይ ችግር የማያመጣ ከሆነ ብቻ ነው ።ጠቃሚ ከሆነ ሚሰት ለእናቷ ትዕዛዝ ተገዥ መሆኗ ተገቢ ነው ።ለችግር እንደሚያጋልጣት እርግጠኛ ከሆነች ግን መቃወም ትችላለች ።የዚህን አይነት ችግር የገጠማት ሚሰት ሁለት አማራጮች አሏት ፦

➊ / የእናቷን ትዕዛዝ መፈፀምና ትዳሯን አደጋ ውሰጥ መክተት ወይም ፣
➋ / የእናቷን ምክር ወደ ኋላ ትታ ከባሏ ጋር ተስማምታ መኖር ።

የመጀመሪያውን አማራጭ መውሰድ አሰቸጋሪ ነው ።ምክንያቱም ሚስት ከባሏ ጋር ያላት ህይወት የተበላሸ እንዲሆን አለያም ለፍቺ እንድትጋለጥ ያደርጋታል ።ከባሏ ጋር አብራ መቀጠል ብትችል እንኳ ሰላም አይኖራቸውም ።ልጆች ይሰቃያሉ ።ከተፋታች ደግሞ ወደ ቤተሰቦቿ መሄድ ሊኖርባት ይችላል ።

--------- ቤተሰቦቿም መጀመሪያ ላይ አለንልሸ ይበሉ እንጂ እየቆየ ሲሄድ እንደ ቤተሰብ አባል አይቆጥሯትም ።ይንቋታል ።ከቤት እንድትወጣላቸውም ይፈልጋሉ ።ለብቻዬ ልኑር ብትልም ኑሮ ይከብዳታል ።ሌላ ባል ማግኘት ቀላል አይሆንላትም ።
☞ የሚቀጥለው ትዳርሰ የተሻለ እንደሚሆን እንዴት እርግጠኛ መሆን ይቻላል?
☞የልጆቿ ህይወትሰ ?
☞ከአዲሱ ባል የሚወለዱ ልጆችስ ? እነዚህ ነገሮች ሊያጨናንቋትና ራሷን አሰከመሳት ሊያደርሷት ይችላሉ ።ሌላ ባል ብታገባ እንኳ ይህ ጭንቀቷ ባሏ ከሷ ጋር ተስማምቶ መኖር አሰቸጋሪ እንዲሆንበት ስለሚያደርገው እንደገና ሊፈታት ይችላል ።በመሆኑም የእናትሸ ወይም የሌሎች ሰዎች ምክር ትዳርሸን የሚጎዳ መሰሎ ከታየሸ ተግባራዊ ማድረግ የለብሽም ።


♦♦ ለእናትሸ ፦
"እማዬ በአሁኑ ወቅት እኔ ባለትዳር ነኝ ።ባሌን ማስደሰትና ትዳሬን መጠበቅ ነው የሚሻለኝ ።እሱን በጥሩ ሁኔታ መያዝ አለብኝ ።የእኔና የልጆቼን ኑሮ ለማስተካከል ቀኑን ሙሉ በስራ ሲደክም የሚውል የህይወት አጋሬ ነው ።ሁሉንም የኑሮ ውጣ ውረዶች ከእኔ ጋር ይካፈላል ።ችግር ካጋጠመን እኛው ራሳችን ለመፍታትና ኑሯችንን ለማስተካከል ጥረት እናደርጋለን ።ያንቺ ጣልቃ ገብነት ችግሩን ወደባሰ ሁኔታ ሊለውጠው ይችላል ።ስለዚህ ሁለታችንም ካንቺ ጋር ያለን ግንኙነት መልካም እንደሆነ እንዲቀጥል የምትፈልጊ ከሆነ በኛ ህይወት ውሰጥ ጣልቃ አትግቢ ።ባለቤቴን አትሚ ።አለበለዚያ ካንቺ ጋር ያለኝን ግንኙነት አቋርጣለሁ "ማለት ትችያለሽ ።ፈ

☞ እናትሽ አሰተያየትሸን ተቀብሎ ጣልቃ መግባት ካቆሙ አሰዬው ።ያንቺን ፍላጎት ለመረዳት ዝግጁ ካልሆኑ ግን ከሳቸው መራቁ ይመረጣል ።ይህን ካደረግሸ ደስተኛ የትዳር ህይወት ይኖርሻል ።ከወላጆችሸ ጋር ያለሽ ግንኙነት በሚቋረጥበት ጊዜ በቤተሰብሸ ዘንድ ያለሽን ክቡር ልታጭ ትችያለሽ ።ይሁን እንጂ ከባልሽ ከዚያ በብዙ እጥፍ የበለጠ ክብር ታገኛለሸ ።

#ክፍል ➌➌
ይቀጥላል
ምንጭ ☞ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ


👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ታላቅ_ወርሀዊ_ደመወዝ_ማንም_ያላስተዋለዉ
✍ አሚር ሰይድ

🎁 አስራ ሁለት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ ሀያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ የፈለገ ሰዉ ብቻ ያንብበዉ

ምን መሰላችሁ ወዳጆቼ
ከመቅሪብ እስኪ ኢሻ ባለዉ ሰአት ብቻ ቁርአን ከቀራን ፈጣን ሰዉ በወር ሶስቴ መካከለኛ ሰዉ ደግሞ በወር ሁለቴ ..ደካማ ሰዉ ደግሞ በወር ዉስጥ አንዴ አክትሞ በተጨማሪ የቁርአን ግማሽ መቅራት ይችላል ብቻ የራስ ተነሳሽነት ይጠይቃል፡፡

#ቁርአን 77430 ቃላት እና 430740 ፊደላት አለዉ አሏህ ፈጣሪያችን በቁርአን በአንድ ፊደል 10 ሀሰና አለዉ ብሎናል እናም 430740 ብናሰላዉ
🔰 በወር ሶስቴ ብናከትም 12,922,200 ሀሰና ሲኖረዉ
🔰 በወር ሁለቴ ብናከትም 8,614,800 ሀሰና እናገኛለን
🔰 በወር አንዴ ብናከትም 4,307,400 ሀሰና እናገኛለን

መታገል ይሄን ጊዜ ነዉ ..አሁን ይሄ በብር ቢሆን ስንቶቻችን ነበር የምንሰራዉ ሁሉም የአለም ህዝብ ማለት ይቻላል ዉሎዉና አዳራ በቁርአን ላይ ይሆን ነበር...ግን ብርና አላህ በሀሳና የሚሰጠን የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት እንዳለዉ ዘንግተናል፡፡ የዚህ ሀሰና ተቋዳሽ መሆን ጥቅሙ ነገ የዉመል ቂያማ እናት አባት ወንድም እህት ዘመድ .ቦይ ፍሬንድ ገርልንድ ፍሬድ በማይጠቅምበት ጊዜ ይጠቅመናል👌

ከመቅሪብ እስከ ኢሻ ባለዉ ሰአት ..አንድ ሰአት ያህል አለ ወንዱ መስጊድ ቢያመሽ..ሴቶች እቤታቸዉ ከወሬ ከtv ከተለያየ ሚዲያ ርቀዉ ቁርአን ቢቀሩ በወር ሶስቴ ወይም ሁለቴ ከመግሪብ እስከ ኢሻ ባለዉ ብቻ ማክተም ይችላሉ
➊ በአቀራሩ ፈጣን የሆነ ☞ የቁርአን ገፁ 604 ነዉ ከመቅሪብ እስከ ኢሻ 60 ፊት ብንቀራ በወር ሶስቴ እናከትማለን ማለት ነዉ
➋ በአቀራሩ መካከለኛ የሆነ ☞ ከመግሪብ እስከ ኢሻ 50 ሶፍ ቢቀራ በአንድ ወር ዉስጥ ሁለቴ አክትመዉ እንደገና የቁርአን ግማሽ መድረስ ይቻላል፡፡
➌ በአቀራሩ ዝቅተኛ ከሆነ ☞ ከመግሪብ እስከ ኢሻ 40 ሶፍ ቢቀራ በአንድ ወር ዉስጥ ሁለቴ ማክተም ይችላሉ ማለት ነዉ፡፡
✔ ይሄን ለማሳካት ከሞከርን ቀላል ነዉ ፡፡ ከመቅሪብ እስከ ኢሻ ካልተመቸን በቀን በተመቻችሁ ወቅት ጊዜ ..አንድ ሰአት ቁርአን ለመቅራት ብንሰጠዉ ተጠቃሚ መሆን እንችላለን፡፡ ግን ወንዶች ከመቅራብ እስከ ኢሻ ቢሆን መስጊድ የማምሸት ስበብ ይሆናችሆል ባይ ነኝ ፡፡
✔ ደግሞ ስንጀምር የጀመርንበት ቀን ብንፅፍ ለኛ ጥንካሬ ወሳኝ ነዉ፡፡ ነገር ግን አልፎ አልፎ አንዳንድ ቀናት የተለያዩ ችግሮች ከገጠሙን ካልቀራን ተስፋ መቁረጥ በዛዉ ማቋረጥ የለብንም....አላህ በንያችን ይመዘግብልናል እናም ማቋረጥ በጭራሽ የለብንም ለሰይጣን እጅ መስጠት የለብንም ..አደራ ካልተመቸን አልፎ አልፎ ካልቀራን በዛዉ ማቆም የለብንም ማክተም አለብን አደራ!!!!

♦♦ ቁርአን የምንቀራዉ ደግሞ ኢንሻ አላህ በእጃችን ባለዉ ስልክ ሳይሆን ..በቁርአን ቢሆን ይመረጣል፡፡
ግን እስኪ ዛሬ ላይ ቁርአንን ዘንግተናል የዛሬ አራት ወይ አምስት አመት በፊት እናስታዉስ ሰዉ የቁርአን ፍቅር ነበረበት በየመስጊዱ በየቤቱ በየስራ ቦታዉ ሰዉ ቁርአን ይቀራ ነበር...ነገር በሞባይል ስልካችን መቅራት ከጀመርን ቡሀላ ለቁርአን ያለዉ ፍቅራችን እየቀነሰ የመጣ አይመስላችሁም???
☞ግን በያዝነዉ ሞባይል የጫነዉ ቁርአን እኛ ቁርአን እንድንቀራ አበረታቶናል ወይስ ከቁርአን በሂደት እንድንርቅ አርጎናል?
☞ቁርአን የተከበረ የአላህ ቃል ነዉ፡፡ ይሄን የተከበረ ቁርአን ዉዱዕ የሌለዉ፣በጀናባ ጊዜ፣ ሴቶች በኒፋስ በኻይድ ወዘተ ባለቡበት ወይም ጡሀራ ባልሆኑበት ጊዜ ቁርአን መንካት የተከለ ነዉ፡፡ ግን እኛ በያዝነዉ ስልክ ስንቶቻችን ነን ለቁርአን ያለንን ክብር እንዳንጠብቅ የሆነዉ ??

♦ ግን እስኪ በደንብ ብናስብ የተሻለ ነዉ ብየ አስባለሁ፡፡ ለምን ብንል አመቱ ጠፋኝ በጀርጂቡሽ ጊዜ ይሆናል የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚነስተር እናንተ ሙስሊሞች ከኛ መቼም ልትደበቁ ትሸሹ አትችሉም በየቤታችሁ ነዉ የምንከታተላችሁ ..ለምን ሽንት ቤት ለምን መኝታ ቤታችሁ ብትሆኑ ለራሱ ከኛ ማምለጥ አትቹሉም እንዳለች የሆነ መፅሀፍ ላይ አንብቢያለሁ፡፡ ታዳ ይሄ በስልካችን የጫነዉ ቁርአን ቢሆንስ?? ቁርአን በስልክ መጫኑ ሳይሆን ይሄን Aplication የፈጠረዉ የማን ሀገር ዜጋ ነዉ ? የየት ሀገር ልጅ ነዉ ? ሙስሊም ነዉ ወይስ አይደለም ? ብለን አጣርተን እናዉቃለን ግን ??? ግን ይሄን ነገር የኢትዮ ብቻ ሳንሆን የአለም ሙስሊም አጥብቆ ቢጠይቅ እና የተለያዩ የቁርአን Aplication ቢመረመሩ ጥሩ ነዉ ባይ ነኝ፡፡
እንደዚህ እንድል ያስገደደኝ
➊ የዛሬ ሁለት አመት በፊት በሞባይሉ የቂብላ Aplication ያለዉ ሰዉ የምዕራባዉያን ስለላ ላይ ነዉ የሚል ወሬ ተነዝቶ ነበር ...እዉነት ይሁን ዉሸት ግን አጣርቶ የደረሰ የለም...ለምን የአሁን ዘመን ሙስሊም ለወሬ እንጂ ለቁምነገር ጥግ ድረስ የሚሄድ ስለሌለ

➋ በቅርቡ ከአንድ ወር በፊት ስሙ ጠፋኝ.. የሞባይ ኬብል ነዉ ፡፡ በዛ ኬብል ቻርጅ ያደረገ የስልኩ መረጃ ለምዕራባዉያን ይደርሳል ማለት ነዉ፡፡ ይሄ ደግሞ ሙስሊሞች በስልካቸዉ ምን እንደሚሰሩ ማወቅ ይችላሉ ማለት ነዉ...

እናም ምን ለማለት ያህል ነዉ የቁርአን Aplication በሙስሊም ሀገሮች መሪዎች የተዘጋጁ ከሆነ በጣም ኸይር ለኡማዉ ጠቃሚ ነዉ ፡፡ ነገር ግን የምዕራባዉያን እቅድ ከሆነ ይሄ aplication እቅዳቸዉ የሉሲፈር 666 እቅድ ሊሆን ይችላል ለምን 666 እቅዳቸዉ ሰዎችን ከቁርአን ማራቅ የሚል ሰፊ እቅድ አላቸዉ እኛ የተጠቀምን መስሎን aplication ቁርአን ከመንካት ..እያስተነተን መቅራት ካቃተን የምዕራባዉያን ተንኮል ቢሆንስ? እናም መጠርጠር መቻል አለብን ባይ ነኝ

♦እስኪ እናንተ አስተያየት ስጡ በፊት ቁርአን ይዛችሁ ስቀሩ እና አሁን በሞባይል ብቻ ስትቀሩ የትኛዉ ተሽሏችሆል?
ቁርአን በስልካችሁ ስትቀሩ እና የተዘጋጀ የተጠረዘ ቅዱስ ቁርአኑን ስትቀሩ ለእናንተ የቱ ስሜት ይሰጣችሆል ??አስተያየታችሁን በዚህ ያቀብሉኝ
👇👇
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot

እናም የተወደዳችሁ የቻናል ቤተሰቦች ዋናዉ እቅዳችን ቁርአን በአንድ ወር በቀን አላህ ከሰጠን እድሜ አንድ ሰአት በመመደብ በወር ሁለቴ ወይም ሶስቴ ለማክተም ነዉ እቅዳችን ሆነም ቀረ ከቻልን ራሱን በቻለ በተጠረዘ ቁርአን ካልሆነ ደግሞ በያዝነዉ ሞባይል ቀርተን ማክተም እንችላለን..በሞባይል app ቁርአን መቅራት መንቀፌ መቃወሜ አይደለም ግን አንዳንድ ነገሮች ለኛ የጠቀሙ መስለዉ ጎጂ ቢሆኑስ የሚል ጥርጣሬ ነዉ


⚠️⚠️ አደራ ደግሞ በወር አስሬ ወይም ከዛ በላይ ሀያ ወይ ሀያ አምሰት ድረስ ሊሆንም ይችላል ቀንም ማታም ቁርአን ቀርታችሁ የምታከትሙ ደግሞ ይሄን አንብባችሁ በወር ሶስቴ ነዉ የማከትዉ ብላችሁ እንዳትቀንሱ☺️ እኔ በወር ሁለቴ ሶስቴ ያልኩት እንደኔ ከቁርአን ጋር ለተራራቅን ወንድም እህቶቼ ለማስተላለፍ ነዉ፡፡


ዉድ ያቻናል ቤተሰቦች ከዛሬ ጀምረን ከመቅሪብ እስከ ኢሻ ወይም በቀን አንድ ሰአት በመመደብ በወር በቻልነዉ አቅም ሶስቴም ወይም ሁለቴ ካልተቻለም አንዴ ለማክተም የነየተ ..በአላህ ምሎ ንያዉን አስተካክሎ ዛሬ መጀመር የፈለገ Like ይግጭ..አደራ የማይጀምር በምላስ የኢንሻአላህ ለወሬ ብቻ ወይም ይሄን message ሲያይ ከሌቡ ሳይሆን በምላሱ የመረቀነም Like🤙 እንዳይጫን Like🤙 የተጫነ መቅራቱን ይጀምራል፡፡ ስታከትሙ በዚህ bot አሳዉቁኝ
👇👇👇👇
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዉድና የተከበራችሁ የቻናል ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ፡፡ ምን ብየ እንደማመሰግናችሁ ቃላት ያጠረኛል ምንም ማለት ስለማችል በሀሳብ በተለያየ ገጠመኝ በሒወታችሁ የደረሰባችሁን የማይረሳ ጠባሳ ነግራችሁ ሁለት በፍቅር የተጎዱትን የመፍትህ አቅጣጫ ያስቀመጣችሁ ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ🙏 አሏህ በልባችሁ አስባችሁ ለሰዉ ያልነገራችሁትን ሁሉ እንዲያሳካላችሁ ልባዊ ምኞቴ ነዉ .....

ብዙዎች ሶላተል ኢስቲሀራ እሷም እሱም ይስገዱ የሚል ከአስተያየታቸዉ ጎን ለጎን አስቀምጣችሆል ....ሶላተል ኢስቲሀራ ሁለቱም ቢያንስ 6 ቀናቶች በላይ ለሊት እየተነሱ ሰግደዉ ዱአም አድርገዋል፡፡

♦ ዉድ የቻናል ቤተሰብ ከእናንተ በሰጣችሁት ሀሳብ ተሞክሮ ነገሮችን በማስተዋል ልጁ ጋር ተመካክረን ትናንት ቅዳሜ መግሪብ ሶላት ላይ ያልታሰበ ኸይር ነገር ተፈጥሯል ብቻ ወላሂ ብዙዎች ዱአ እናደርጋለን ብላችሁ ዱአ አድርገናል ያላችሁ የእናንተ ዱአም ደርሶ ሊሆን ስለሚችል አሁንም ዉስጣዊ በመነጨ መልኩ በዱአ እገዙት.....የዚህ ዱአ እና የልጁ እቅድ የተዘራዉ ፍሬ እሸቱ ሲደርስ የማሳዉቃችሁ ይሆናል😊

ገንቢ አስተያየት ካለም በአስተያየት መስጫ Bot ያሳዉቁኝ


ከዉስጣዌ ከመነጨ መዉደድና አክብሮት ጋር ከልብ አመሰግናለሁ
✍ አሚር ሰይድ
#የኤልሳቤጥ ታላቅ ወኔና ራዐይ
✍ አሚር ሰይድ

ኤልሳቤጥን ምን ያህል ታቋታላችሁ???

ኤልሳቤጥ የስፔንና የፊሽታላህ መሪ ነበረች፡፡ይህች ሴት ከ30 ዓመት በላይ የሚሆነዉን ዕድሜዋን ያጠፋችዉ ለካቶሊክ እምነት በመስራት ነበር፡፡ለስፔን ሀገሯና ሀይማኖቷ ብዙ ስራዎች የሰራችና መስዋት የከፈለች ናት፡፡ኤልሳቤጥ ሴት መሆኗንም ረሳች፡፡ስፔንን በእጇ እስክታደርግ ድረስ የዉስጥ ልብሷን ላትቀይር ለራሷ ቃልኪዳን ገብታ ማለች፡፡ ይህን ያለችዉ ስፔንን ከመቋጣጠሯ ከረጂም አመት በፊት ነበር፡፡

ቤክርስቲያን የኤልሳቤጥን ማንነት በማነፁ ላይ ትኩረት አድርጋ ሰርታለች፣ተንከባክባታለች፣ጠብቃታለች፣መንግስት እስከ መመስረት እንድትደርስም አድርጋታለች፡፡የሰዉ ሀይልና የገንዘብ ሀይል በገፍ በመለገስ አጠናክራታለች፡፡

ታዋቂዉ የታሪክ ፀሀፊ ፊርናንድ ፊስካይኑ በታህሳስ እ.ኤ.አ1987 ኤልሳቤጥና ጥንታዊ ቀሚስ በሚል ርዕስ መፅሀፍ ፅፏል፡፡ መፅሀፉ በዛ አመት ብቻ አራት ጊዜ የታተመ ሲሆን ፀሀፊዉ በመፅሀፉ ላይ ኤልሳቤጥ ወደ ቅዱስነት ደረጃ ከፍ እንድትደረግ ጠይቋል፡፡
☞በአንደሉስና በገርናጣ ያለዉን የሙስሊሞች ግዛት ለመጨረሻ ጊዜ እንዲወድቅ ያደረገችዉ ኤልሳቤጥ ናት፡፡
☞ኤልሳቤጥ ሙስሊሞችን ለማጥፋት የተለያዩ ሀገሮች ያሉ ክርስትያን አመራሮች በአንድነት እንዲቆሙ ያደረገችዉ እሷ ነች፡፡
☞ኤልሳቤጥ ሙስሊምችን ለማጥፋት በሚደረገዉ ዘመቻ ጦርሜዳ ድረስ በመሄድ ጦርነቱን ትመለከትና ታበረታታ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ገንዘብ እጥረት አጋጥሞ ጌጣጌጦቿን በማስያዝ ሰራዊቱ ደመወዝ እንዲከፈለዉ አድርጋለች፡፡
☞በገርናጣ የመጨረሻ መሪ የነበረዉን አብደላህን ያንበረከከችዉ ኤልሳቤጥ ነች፡፡
☞ኤልሳቤጥ አብደላህን 10ሺ ወርቅ ዓመታዊ ግብር እንዲከፍል አድርገዋለች፡፡አብየላህ ገርናጧን እስኪያስረክብ ድረስ ትንሹን ልጁን በማስያዣነት ይዛበታለች፡፡
☞በመጨረሻዉ እኤአ ጥር 1492 የክርስቲያን ሰራዊቷን ይዛ ገርናጧ ገባች፡፡ ገርናጧን ከተቆጣጠረች ቡሀላ
◇ ሙስሊሞችን በህይወት እያሉ አቃጠለቻቸዉ፡፡😔
◇ ከዚህም በላይ ሙታን ሙስሊሞችን ከመቃብራቸዉ አዉጥታ አቃጠለች፡፡😔
◇ በህይወት ያሉትን በግድ ክርስቲያን እንዲሆኑ አደረገች፡
◇ የሙስሊም አጠቃላይ ንብረታቸዉን ቀምታለች ፡ ዘርፋለች፡፡
◇ በአንደሉስ አዛን ማድረጊያ እስኪጠፋ አዛንም እስከማይደረግ ምንም ሙስሊም እስከማይኖር ድረስ የማጥፋት ዘመቻ አድርጋለች፡፡


✔ ኤልሳቤጥ ኮሎምበስን የአሜሪካን አህጉር ለማግኘት ላደረገዉ አሰሳ በጀት የመደበች ናት፡፡ የአዲሲቱን አሜሪካ ድልብ ሀብት ወስዳ ከስፔን ካዝና ዉስጥ ጨምራለች፡፡ የአሜሪካን ህዝብ አንበርክካ ለመግዛትና ክርስቲያን ለማድረግ የሀይማኖት ሰባኪዎች ሚሺነሪዎች ልካለች፡፡
ኤልሳቤጥ በአዉሮፓና በአሜሪካ ታሪክ ታላቅ ራዕይና ወኔ የነበራት ሴት ተደርጋ በካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ ትታያለች፡፡ኤልሳቤጥ ናት ሙስሊሞችን ከአንደሉስ(ስፔን)ጠራርጋ ያስወጣችዉ ፡፡

✔ ኤልሳቤጥ የሰራችዉ ስራ ለኛ ለሙስሊሞች ክፉኛ የሚያበሳጭ ዉስጥን የሚያደማ ቢሆንም ከፍተኛ ወኔ የነበራት መሆኑን መካድ አንችልም፡፡ሙስሊሞችን ለማጥፋት በፊትም አሁንም የሚደረገዉ ዘመቻ ምን ያህል የከፋና የጠነከረ ለመሆኑ ኤልሳቤጥ ማሳያ ናት

~~~~~~ ዉድ የቻናል ቤተሰቦች ይሄን ስታነቡ ከንፈር ለመንከስ ለመምጠጥ አይደለም ሰዉ ላመነበት ነገር በተለይ ለሀይማኖቱ እንደሷ መሆን አለብን ለማለት ያህል ነዉ ....በኤልሳቤጥ ዘመን ከዛስ ቡሀላ ያለዉ ሙስሊም ማህበረሰብ የኤልሳቤትን ያህል 5% ሰርቷል ወይ?? ኤልሳቤጥ ግን ላመነችበት ሀይማኖት ይሄን ሰርታለች ...መገንዘብ ያለብን ኤልሳቤጥ ሙስሊም ሁና ቢሆን ኑሮ አለም የሙስሊሞች እንደምትሆን ምንም ጥርጥር የለዉም ለምን ስፔን ከ600 አመት በላይ በሙስሊሞች እጅ ነበረች ..እንደ ኤልሳቤጥ ባሉ ለአላማቸዉ ጠንካራ በሆኑ ሴቶች ነዉ የተነጠቅነዉ፡፡


#ሴቶች_ሆይ እራስሽን ዝቅ አታድርጊ ሴትነት ማለት ማንነትን ፈልጎ ለማግኘት ሲባል ተወጥቶ ተሂዶ የማያልቅ ድካም ያለዉ ረጅም ተራራነት ነዉ፡፡ ኤልሳቤጥ ለያዘችዉ አቋም ሀይማኖቷን ለመርዳት የለበሰችዉን ዉስጥ ልብስ ፓንት ሳትቀይር ከ30 አመት በላይ ታግላለች እናንተ ግን በቀን አስሬ ፊትሽን እየታጠብሽ ኮስሞቲክስ እየተቀባችሁ የወንድ ምላስ ተጠባባቂ አድናቂ አትሁኝ፡፡

>> እጅሽን በኮስሞቲክስ ያገረጣሽዉን ለኢስላም ፃፊበት ቁርአን ይዘሽ ቅራበት...
>> እግርሽን ፈግፍገሽ ተቀብተሽ የምትሄጅበትን መድረሳ መስጊድ ሂደሽ ኢስላምን ሸምችበት፡፡

አንቺ የተፈጠርሽዉ ለወንድ ሁነሽ አግብተሽ ወልደሽ ማሳደግ ብቻ ፕላንሽን አታድርጊ፡፡ አግብተሽ ለዲነል ኢስላም ብዙ መስራት እንደምትችይ ብቻ እርግጠኛ ሁኝ፡፡ ለምን ብትይ እንደ ኤልሳቤጥ ወኔ ካለሽ እሷ ትዳር ሳትመኝ ሀይማኖቷን አስከብራለች አንቺም ያገባ ግማሽ ኢማንሽ ስለሚሞላ በተቀረዉ አላህን እየፈራሽ ለሀይማኖትሽ ብዙ መስራት ትችያለሽ፡፡ የህይወት ግብሽን ትዳር ብቻ ነዉ ብለሽ አትሰቢ ..ለምን ብትይ በዚህ ሀሳብ ትዳር ሲጠፋ ስንት ሴቶች እንደ ከፈሩ የምናቀዉ እዉነታ ነዉ፡፡ ነገር ግን ኤልሳቤጥ ካቶሊክ ሀይማኖቴ ይበልጥብኛል ከትዳሬ ብላ ዛሬ ድረስ ላሉት ካቶሊኮች ታሪክ ሰርታ አልፋለች

እናም በዚህ ዘመን ያላችሁ ሴቶች መቼም እንደ ኤልሳቤጥ ጠንካራ ወኔ ያለዉ ለሀይማኖቱ የሚታገል ሴትም ወንድም የለም .ለምን ሁሉም በዱንያ በምዕራባዉያን ፋሽን ኢስላምን አስረክቧል ...በኢስላም ስራ የማይጠቅም የማይጎዳ ሁኖ የሚኖር እንጂ ለወደፊት ለሙስሊም ማህበረሰብ አሻራ የሚያስቀምጥ ለወደፊት ለሚፈጠረዉ ሙስሊም ትዉልድ አሻራ የሚያስቀምጥ እንኳን ሊኖር ትዝ የሚለዉ የለም ፡፡ ሌላዉ ይቅር ሁሉም ከኢስላም ስም ዉጭ በጎን ሌላ ስም ለጥፎ ሌላን አላስቆም አላስቀምጥ ብለዉ ሲጣሉ ለዲነል ኢስላም ሰፊ እዉቀት የሌለዉ ጃሂል ተደናግሮ መንታ መንገድ ላይ ቁሟል፡፡

♦ እንደዉም አሁን ያለዉ ሙስሊም ለወደፊት ለሚመጣዉ ኡማ የሚያስቀምጠዉ ወንዱ ለሴት ለመታየት ብሎ ሙነሺድ መሆን ምኞቱ ሆነ፡፡ ከዛም ነሽዳ ያወጣል አዳራሽ ይከራያል 80% ሴት ይገባል ስታጨበጭብለት ደስ ይለዋል አበቃ ከዛ ቡሀላ ስንት ይሰራል ታሪኩ ብዙ ነዉ....ይሄም አልበቃ ብሎ ባወጣዉ ነሺዳ ህፃናት ቁርአን እየቀሩ እንዳያድጉ ሀፊዝ እንዳይሆኑ የተለያዩ ኪታብ ቀርተዉ ለወገን እንዳይሆኑ ነሺዳ አዳማጭ ሁነዉ ኢስላምን በሂክማ እናስተምር ብለዉ ይነሳሉ...ሴቱም የእከሌ ሙነሺድ ድምፅ ያምራል እሱ ልጅ ይመቸኛል ባይ እንጂ ዲነል ኢስላምን ተምራ ጠንካራ ወኔ ያላት እንደ ኤልሳቤጥ ጠንካራ አቋም አትይዝ በነሺዳ ነብዩን እወዳለሁ ስትል ትዉላለች፡፡

♦ በፊት ሱሀቦች ስለሀይማኖታቸዉ ሲመካከሩ እኔ አሸንፋለሁ ሳይሆን የእሱ ሀቅ ቢሆንስ ነበር ብለዉ መወያየት የሚጀምሩት...ዛሬ ዘመን እንደምናየዉ ሀቅ ሲነገር የማይሰማ ሁሉ ተፈጠረ...ከዛም በተዘዋዋሪ ሀቅ የሚናገረዉ ሰዉ የሚሄድበት አካሄድ ጥፋት ላይ ያለን ከማስተካከል በጥፋቱ ላይ ምን አገባዉ በሚል የብስ ጥፋት እየጨመሩ መጥተዋል..ግን ጥፋቱ ከጥፋተኛዉ ነዉ ወይስ ጥፋትህን አስተካክል ከሚለዉ አካል❓❓
ግን የወደፊት ትዉልድ የማይጠቅም የማይጎዳ መሆኑን የምታቁት በፊት አጂ ነብይ ጋር እደተደባለቁ ሰርግ አስጨፋሪ ስም ይዘዉ ነቢይ ዉዴ ..መርሀባ ሲሉ የነበሩ ሁሉ ዛሬ በስመ ታዋቂ ሙነሺድ ስም እህህህ ወዳጄ..ነቢይ ናፈኩኝ....ናፍቆቱህ በረታ..ልሂድ መካ ሊሂድ መዲና...ልሂድ እነአንይ ሾንክይ ጋር...የነቢይ መዉሊድ ናፈቀኝ....እያሉ👇👇👇
ፀጉራቸዉን በምዕራባዉያን እስታይል ተቆረጠዉ ነብዩ ሰዐወ እንወዳለን እያሉ በነቢይ ስም ሴት ማጥመጃ...ሴት ቁርአን እንዳቀራ ኪታብ እንዳቀራ ነሺዳ አዳማጭ እንድትሆን ....
በተዘዋዋሪ ደግሞ የአህባሽ አቂዳን በነሺዳ አላህ ባለቦታ ይገኛል እያሉ እያስተማሩ ነዉ‼️‼️‼️
እህት አለም ሆይ እና አንቺ የዚህ ዘመን ሙነሺዶች አድናቂ ሁነሽ ነዉ እንዴ ለካቶሊክ እምነቷ ብዙ ገድል የሰራችዉ ኤልሳቤጥ አይነት ለዲነል ኢስላም የምትሰሪዉ???

♦አሁን ዘመን ያሉ ሴቶች እንደ ኤልሳቤጥ የመሆኑ ሞራል እቅድ ስለሌላቸዉ አላማቸዉ ሁሉ አላህ እንዲያቸዉ ሳይሆን የሚሰሩት ጀዝባ ወንድ እንዲያቸዉ ሆነ፡፡ በተለያዩ ሙስሊም ተብየዎች tv program ዜና አቅራቢ ፕሮግራም መሪ ..በተጨማሪ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ በYoutube በtiktok በቴሌግራም ወዘተ እናስተምራለን ብላችሁ ፋሽን ልብስ ለብሳችሁ ብቅ ብቅ ያላችሁ ሁሉ
አለፍ ሲልም ሀይማኖት አስተማሪ ነን ብለዉ ተነስተዉ አፏን ከምስራቅ ወደ ምዕራብ እያጣመመች ሀዲስ ቁርአን አስተማሪ ሁነዉ እያየን ነዉ....ግራ የገባኝ ወንድ እንዲመለከታት ነዉ ወይስ እሷ አፏን እያጣመመች ስታስተምር ትዉልድ እቀርፃለሁ ብለሽ አስበሽ ይሆን??🤔
#ሴቶች_ሆይ!!! እዩኝ እዩኝ ያለ መልሶ ደብቁኝ ደቡቁኝ ማለቱ አይቀርም...የአንቺን ሚዲያ ላይ መዉጣት የተመለከተ ጉድ ሰርቶሽ መልሰሽ ከሚዲያ ደቡቁኝ እንዳትይ ....ለዚህ መድሀኒቱ ..በስሜትሽና በስሜት ከሚፈርዱ አንቺን እንደሚመችሽ የፈቀዱልሽ ኡለማ ተብየዎች ፈትዋ እራስሽን አግለሽ ...አንቺ ለምሰሪዉ ስራ ምንችግር አለዉ ? ዘመኑ ነዉ ከማለት ቁርአንና ሀዲስ እኔ ለምሰራዉ ስራ ምን ይላል የሚለዉን አስተንትኝ፡፡

#አላህ ጠንካራ ወኔ ካለቸዉ ብዙ ገድል ከሰሩ እንደነ አኢሻ እንደ ኸዲጃ አይነት ሴቶች ስብዕና ይወፍቃችሁ...ኤልሳቤጥ ለካቶሊክ ሀይማኖቷ ለሰራችዉ ታሪክ መቼም አይረሳትም ነገር ግን ቅጣቱን የሚሰጠዉ አላህ ነዉ፡፡ የእሷን ፈጣሪ ይወሰነዋል...

እኔ ትኩረት እንድታደርጉ የምፈልገዉ የእኛ ሙስሊም ሴቶች በሚዲያ ወሬ ሳይሆን እንደ ኤልሳቤጥ ላመነችበት አላማ ሟች በተግባር ጠንካራ የሙስሊም መከታ የምትሆኑ ያርጋችሁ ለምን እናንተ ጠንካራ ብትሆኑ የእናትነት ደረጃ ስደርሱ የሚወለደዉ ልጅ እሰቡት እንዴት የሙስሊም ቀኝ እጅ እንደ ሰልሀዲን አልአዩብ ያለ ወጣት በዘመናችን ከእናንተ ማህፀን መፈጠር ይችላልና፡፡

☝️ ነገር ግን አሁን ላይ ልጅ ሲወልድ አዩብ ብሎ አዩብን በተርቢያ በዲነል ኢስላም አሳድጎ አንተ የምወልደዉን ልጅ ሰልሀዲን በለዉ ..የሚል እናትና አባት አለ ግን??? በጭራሽ የለም...እስኪ ያገባችሁ ወይ ትዳር ያሰባችሁ የምወልዱትን ልጅ አዩብ ብላችሁ በአለም ቁጥር አንድ ጀግና ሁሉም የሀይማኖት ተከታይ ስለጀግንነቱ ጥሩ ባህሪዉ ስለሚመሰክሩለት ስለሰልሀዲን አዩብ ታሪክ ሲያድግ አሳዉቁት የወለዳችሁት ልጅ አዩብ ሲወልድ ሰልሀዲን ብሎ አዩብ ለሰለሀዲን የዛን ጀግና ታሪክ ነግሮት እንደሱ ለዲነል ኢስላም እንዲታገል ማድረግ ይቻላል...ግን ለዚህ እቅድ ስራዉ የሚጀምረዉ አሁን አንብባችሁ ዛሬዉኑ ነዉ👌 ከአላህ ጋር ንፁህ ንያ እና ወኔ ያለዉ ትግል ካረግን ስለሀዲን አልአዩብ በዘመናችን መተካት እንችላለን፡፡

♦♦ አሁን ከኛ የሚጠበቀዉ በኤልሳቤጥ ከንፈር መንከስ ሳይሆን የምናደርገዉ ፊልሚያ ኢስላምን መሉ በሙሉ ከምድረገፅ ለማጥፋት ከምዕራባወያንም ከአገር ዉስጥም ቆርጠዉ ከተነሱ ሰዎች ማህበረሰቦች ጋር መሆኑን በደንብ ተረድተን ዲናችንን ለመጠበቅ ከእነሱ በላይ ቆራጥ ሁነን መነሳት አለብን ኢንሻ አላህ


#ሴቶች_ሆይ!!!
አንዳንድ ወንዶች ሴቶች ተናደዉ ሲከፋቸዉ መፍትሄዉ አዲስ ልብስና ክሪም ሲሰጣቸዉ ይረሳሉ ይባላል😉 አሁን ዲነል ኢስላም ተደፍሯል
...ዲነል ኢስላም የተደፈረዉ በጦርነት ብቻ አርገዉ የሚይዙ አሉ ፡፡ ወላሂ በጦርነት ኢስላምን ማጥፋት እንደማይመች አዉቀዉ
☞በሊፒስቲክ ጦርነት
☞በኮስሞቲክስ ጥርነት
☞በሸሪአ ክሪም ሳይሆን በፋሽን ክሪም ጦርነት
☞በትክክለኛዉ ሂጃብና ጅልባብ ሳይሆን በእነሱ ተመሳሳይ በሆነ ጦርነት...ሴቶችና ምዕራባዉያን መፋለም ከጀመሩ ቆዩ...አሸናፊዉ ግን እስከ አሁን ምዕራባዉያን ኢስላም ጠሎች ናቸዉ....ታዳ አሁን ካላችሁ ሙስሊም ሴቶችና ላመነችበት ለካቶሊክ እመነቷ የሰራችዉ ኤልሳቤጥ ማን በለጠ???
ወይስ ኢስላምን በስጦታ ክሪምና አዲስ ልብስ ቀይራችሁት ይሆን እንዴ🙄


✿ እዉነት ተናግሬ ከዛም አልፎ ከትቤ ከሆነ ከአሏህ ነዉ...ስህተት ተናግሬ ከሆነ ከሸይጧን ነዉ አላህ ራህመቱን ያዉርድልኝ እናንተም አንብባችሁ አዉፍ በሉኝ ...እናንተንም ባነበባችሁት የኤልሳቤጥ ታሪክ ከእናንተ ጋር አመዛዝናችሁ...እኔስ ምን ይጎለኛል እኔም መሆን እችላለሁ ብላችሁ ወኔ ሰናቂ ያርጋችሁ

አብሽሩ አልችልም ማለት የሸይጧን የስንፍና መረማመጃ ድልድይ ነዉ...

እንችላለን !!! እንጀምራለን!!! አላህ ደግሞ ያግዘናል!!!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ግድ_እስከምንታመም_አንጠብቅ
✍ አሚር ሰይድ
28/01/2014

ቻርለስ ዳርዊን


ቻርለስ ዳርዊንን ምን ያህል ያቁታል??እስኪ ስለቻርልስ ዳርዊን አንዳንድ ነገር ልበላችሁ
ቻርለስ ዳርዊን 40 አመት ያህል በከባድ ህመም እየተሰቃየ በሽተኛ ሁኖ ኑሯል፡፡

እንዴት አርባ አመት ያህል ሊታመም ቻለ??ብላችሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ ..ግን ብቸኛ መልስ አለዉ መልሱም ድንበር ማለፍ ይሆናል፡፡


ቻርለስ ዳርዊን ህይወት ያላቸዉ ነገሮች ከዝቅተኛ ደረጃ ተነስተዉ ደረጃ በደረጃ እየተለወጡና እየተሻሻሉ በመምጣቱ ዛሬ በተለያዩ መንገድ ሄደዉ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰዋል..በዚህ መሰረት ጦጣና ዝንጆሮ አሁን በዕድገት ሂደት ከሰዉ የተለዩ ቢሆኑም ጥንት አንድ የጋራ መነሻ ሳይኖራቸዉ አይቀርም በማለት ፈጣሪ ነዉ የፈጠራቸዉ ማለትን ትቶ ተከራክሯል፡፡

በወቅቱ በዚህ አስተሳሰብ በሰዎች መካከል ትልቅ ንትርክ ክርክርና ዉዝግብ አስከተለ ፡፡ በተማሪዎች ላይ ችግር ፈጠረ...አንዱ የሚለዉን ሌላዉ አይቀበለዉም ..ለፈተና ብለዉ የሚያጠኑት መልስ ለአካባቢዉ ህዝብ አመለካከት ተለየባቸዉና ዉዥንብር ሆነ፡፡

ይሄን የሚያከፍር አስተሳሰብ ይዞ የመጣዉን የቻርለስ ዳርዊን አመለካከት ይሄዉ ዛሬ ድረስ አለምን በዚህ አስተሳሰብ ቀርፆ ኢትዮጲያ በእስልምናም በክርስትናም ሀይማኖት ጥርት ያለ እምነት አለን ብለን የምናስብ ይሄን ከዝንጆሮ መጣችሁ እየተባልን እየተማርን አድገናል ነገ ከነገ ወዳ ልንሞት እየተዘጋጀን ነዉ ግን እስከ መቼ???

ግን ይሄን ሀሳብ ያመጣዉ ዳርዊን የአእምሮና የጤና እክል ችግር ያለበት ሰዉ ነዉ...እና እንዴት በዚህ ታማሚ የታመመ አስተሳሰብ በታመመ አመለካከት ለትዉልድን ህመሙን ማካፈል ለምን አስፈለገ???መቼ ድረስ ይቀጥል ይሆን ??? አይታወቅም

☝️ እስኪ ስለዳርዊን ሰዉ የመጣዉ ከዝንጆሮ ነዉ ብሎ የሚያከፍር ከእስልምና የሚያወጣ አመለካከት ያመጣዉን ግለሰብ አንዳንድ ነገሮች ጀባ ልበላችሁ

ዳርዊን
☞ገና የስምንት አመት ህፃን እያለ እናቱ ሞተችበት ፡፡
☞ እሱን ያሳደገችዉ ታላቅ እህቱ ነበረች..
☞የዳርዊን አባት በፀባዩ ሰዎችን የመጫን ባህሪ የነበረዉ በጣም አስቸጋሪ ሀይለኛና ግዙፍ 150 ኪግ የሚመዝን ሰዉ ነበር፡፡ በአባቱ ባህሪ ዳርዊን ይበሳጭ ይናደድ ነበር፡፡
☞ ዳርዊን በትምህርት በኩል አልተሳካለትም ስለህክምና እንዲያጠና ወደ አንድ ዩኒቨርስቲ ቢላክም ከዚያ ወድቆ ተባረረ፡፡ ከዚያም ወደ ዝነኛዉ ኬምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ተልኮ ስለመንፈሳዊ ትምህርት እንዲከታተል ተደረገ በዚህም ቢሆን አልተሳካም፡፡


የዳርዊን ዝንባሌ ሁልጊዜም ፈረስ መጋለብ ተራራ መዉጣትና ወዘተ እርባና ቢስ ነገሮች ላይ ስለነበር አባትየዉ ይበሳጭበት ነበር፡፡ቤተሰብ አሰዳቢ ከንቱ ልጅ እያለ ይሰድበዉ ነበር ...በትምህርቱ ሰነፍ ስለሆነ አልሳካለት ሲል አንድ መርከብ ላይ ተቀጥሮ ሊሄድ ወሰነ...ይህም የመርከብ ጉዞ ዓለምን በከፊል እንዲዞር ያስቻለዉ ነዉ፡፡

ከመርከብ ጉዞዉ ሲመለስ ሰዉ በዝግመተ ለዉጥ ከጦጣና ዝንጆሮ ነዉ የመጣዉ ማለት ጀመረ
ዳርዊን በሀይማኖት በኩል ለሚሰነዘርበት ነቀፋ የራሱ ጥርጣሬ ነበረዉ፡፡

#ለምሳሌ እግዚአብሄር እዉነት ደግና ኑህሩህ ከሆነ ጌታ ሰዉ ባህሪዉን እየገረፈ ሲገዛ ወይም ሚስኪን እንስሳትን እንደዚያ ሲያሰቃይ ወይም ተዉሳክ የሰዉን ልጅ በተለይም የታዳጊ አገሮችን ህፃናትን እንደዚያ እያሰቃየ ሲፈጅና ሲያረግፍ እያየ እንዴት አስችሎት ዝም ይላል??ወዘተ እያለ በማሰብ ግራ ይጋባ እንደነበር ተመዝግቧል፡፡


♦ በዳርዊን አስተሳሰብ ነገሮች በሳይንሳዊ መረጃዎች እየታዩ መጠናት አለባቸዉ የሚል ነዉ፡፡ ሆኖም ዳርዊን ይሄን አመለካከት ለሰዎች ማስረፅ ሲጀምር ህይወቱን በሰላምና በጤንነት እንዲመራ አልታደለም ከባድ የጤና ጉድለት ነበረበት፡፡
የዳርዊን ህመምና የመጨረሻ ዘመን ታሪኩ የሚያስገርምና ዛሬም ትምህርት ሰጪ ነዉ፡፡ይላሉ ሳይንቲስቶች

ዳርዊን ከአምስት አመት የባህር ጉዞዉ ሲመለስ በአመቱ ጤናዉ መታወክ ጀመረ ..ይህ በሽታ ለአርባ አመት ያህል አሰቃይቶት ኖረ ፡፡ ለመሆኑ የታመመዉ በሽታ ምን አይነት ነዉ??ስም ለመስጠት የሚከብድ በሽታ ነበር

#ለምሳሌ:- ሆዱን ይቆርጠዋል፣አንጀቱን ክፉኛ ያመዋል፣ጋዝ ያበዛበታል፣ያስታዉከዋል፣አልፎ አልፎም ልቡ እጅግ በጥድፊያ ይመታል፣ ድካምና አቅመቢስነት ይሰማዋል ፣አንዳንዴም እንደማንቀጥቀጥ ይለዋል ..በአጭሩ ህመሙ ይሄ ይሄ ነዉ ማለት አይቻልም ሁሉም አይነት ህመም ያሰቃየዉ ነበር ፡፡


ህመሙ በጣም ሲጠናበት ከከተማ ወጥቶ ወደ ሀገር ቤት ገጠር ገብቶ መኖር ጀመረ...

☞ አንዳንድ ሀኪሞች እንደተናገሩት በሰዉነቱ ዉስጥ ምንም በሽታ ስላላገኙበት የዳርዊን ችግር የራሱ የመንፈስ ጭንቀት ወይም የአእምሮ ድክመት ያስከተለበት ቀዉስ መሆኑ ያስታዉቃል ይሄ ደግሞ ህመሙ አካላዊ በሽታ ሳይሆን ህሊናዊ ነዉ፡፡
በዘራቸዉ ለራሱ የዳርዊን እናትና አባት ወገን አልፎ አልፎ የአእምሮ መታወክ የነበረባቸዉ ሰዎች እንደነበሩ የዳርዊንም ችግር የዚሁ የዘር ችግር ሊሆን ይችላል

ብዙዎች የዳርዊን የመታመም ምክንያት በፈጣሪ ስራ ገብቶ የሰዉ ልጅ ከዝንጆሮ ነዉ የመጣዉ ማለቱ ይህ ከአንድ ሀይማኖት አለዉ ተብሎ የማይጠበቅ ስለሆነ ፈጣሪ ለሰዉ ማስተማሪያ በህመም እንዲኖር አድርጎት ነዉ ይላሉ
በዚሁ በሽታ ቀን ማታ ለአርባ አመት ያህል እንደተሰቃየ በሞት ተለይቷል...ታዳ አርባ አመት ታሞ መሞቱ የፈጣሪ ቁጣ አይደል??

በአጠቃላይ በአላህ ህግ ላይ ጭማሪ የሚጨምር እንደ ቻርለስ ዳርዊን አይነት ህይወት ለመኖር ሊገደድ ይችላል...አሁን ዘመን ላይ ስንት ከዲን ያፈነገጠ አስተሳሰብ እየሰማን ነዉ፡፡
ዛሬ ዘመን ላይ ተራዉ ጃሂል ብድግ ብሎ ያልበላዉን እያከከ በማያገባዉ ፈትዋ ሲሰጥ ይታያል...ለምሳሌ ሙስሊሞች ብዙ ስራ መስራት ሲጠበቅባቸዉ መዉሊድ እናክብር ፣ አረ በጭራሽ አታክብር፣ አያገባህም እኔ ላክብር እየተባባሉ በሚዲያ የስድብ ናዳ ከአንዱ ወገን ወደአንዱ ወገን ሲንከባለል እያየን ነዉ... አንዱ ሙነሺድ ተብየ በFb page >>> መዉሊድ የሚያከብርን ሰዉ አታክብር አይባልም፣የማያከብርን ሰዉ በግድ አክብር አይባልም፣የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን መዉሊድን ለማክበር ከአላህ መመረጥን ይጠይቃል፡፡<<<
ብሎ ሲለጥፍ ገረመኝ....
☞ዛሬ ደግሞ እኔዉ የማቀዉ የሰፈሬ ልጅ አብሮ አደጌ አጂ ነብይ ሴት ጋር ሲያወራ ሲጋተት ሌላም ሲሰራ የነበረ በሙዚቃ መሳሪያ የተቀናበረ ነሺዳ አዉጥቶ ክሊፑን ሳይ አይኔን ማመን አቅቶት በጣም ገረመኝ ....ቆይ ግን ሙነሺዶች የሚሰሩት ስራ ምንድን ነዉ ?? ነብይን እወዳለሁ እያሉ በTv መስኮት ለኒሳዖች እኛን የሚወደን ማን ነዉ የሚሉ አይመስሉም?? ነሺዳ ሲመረቅ የሚገቡት ሴቶችስ ግን ለምን ይሆን ገብተዉ ሙነሺዶችን ልባቸዉ ፍስስ እስከሚል ድረስ የሚመለከቷቸዉ???

አሊሞች ግን ለምን በዚህ ዙሪያ ፈትዋ ለመስጠት ፈሩ??? አሁን ላይ እኮ ፈትዋ በራስ ዝንባሌና በሞቀ ስሜት ዝና በሚፈልጉ አስመሳይ ዲን ጠቃሚ መስለዉ ሌላ አላማ ባላቸዉ ሙነሺዶች ፈትዋ እደተሰጠ ዲነል ኢስላም ያለመሪ መኪና እየተሾፈረ አሊም ደግሞ ያንን መሪ የሌለዉ መኪና ከሆላ ሁነዉ በሄደበት ሲገፉ እየተመለከትን ነዉ፡፡

ሌላዉ አልበቃ ብሎ የወንድ ሙነሺዶች ሲገርመኝ ደግሞ ሴት ነሺዳ አዉጥታለች ሲሉኝ አላመንኩም ...እኔ ለማመን ግድ መስማት አለብኝ ብየ ሴት ሙነሺድ መምጣቷን አረጋገጥኩ...ምን ይባላል አሊም ተብየዎች መሪ የሌለዉን መኪና ከሆላ እየተከተሉ በሄደበት እየገፉ እንጂ ....👇👇👇
መሪ የሌለዉን መኪና እየሄደ ንብረት ህይወት እንዳያጠፋ መላ እንበል የሚል መጥፋቱ አሳዛኝ ነዉ፡፡

ምን ለማለት ነዉ ቻርለስ ዳርዊን በቀጥታ ፀቡ ከአላህ ጋር በይፋ ነበር ፈጣሪ የፈጠረዉን ከዝንጅሮ ነዉ የሰዉ ልጅ የመጣዉ ብሎ አርባ አመት ያህል ታሞ አሟሟቱ አስጠልቷል....


ዛሬ ደግሞ መዉሊድ አንድ ሰዉ በጀመረዉ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ በቅብብሎሽ መጥቷል፡፡ እኛ ልጅ እንደነብርን መዉሊድ ሲከበር ዳቦዉ ሰደቃዉ ለሚስኪኖች ይደርስ ነበር...የመዉሊድ ዝግጅቱ ደግሞ ጥሩ የሚያስተምሩ ከቢድአ የፀዱ ነበሩ፡፡


ነገር ግን አሁን ላይ መሪዉ አሊም ሳይሆን ወጣት ሙነሺዶች ሁነዋል .... በመዉሊድ ስም አጂ ነብይ ሴቶች ጋር ፊት ለፊት እየተያያችሁ ደግሞ ምርቃናዉ ሲጨምር ደግሞ አንድ ላይ የምጨፍሩ...አላማ በሌላቸዉ ለሴት የማሻ አላህ ድምፅህ ያምራል😌 comment ተጠባባቂ ከሆኑ ሙነሺዶች ነሺዳ እናዳምጣለን እያላችሁ የምታሳልፉ
በመዉሊድ ስም ወደ ሌላ ሀገር እየሄደ ዚና የምሰሩ ...በአጠቃላይ በቢድአ ተጨማልቃችሁ መዉሊድ የምታከብሩ ሆይ!!!

ማንኛዉም ከሀዲስ ከቁርአን ዉጭ የሆነ ነገር ፈጠራ ነዉ ፈጠራ ደግሞ ጥመት ነዉ...ጥመት ደግሞ ወደ ጀሀነም እሳት ነዉ ግድ እንደ ቻርለስ ዳርዊን 40 አመት እስከምትታመሙ አትጠብቁ..የዱንያ ፈተና የሚበዛዉ ያሰብካቸዉ የማይሳኩት በዚህ ሊሆን ይችላልና፡፡

♥ ነብዩ ሰዐወ ለአንድ ቀን ብቻ የሚወደዱ አይደሉም..
ነብዩን ከወደድን ሱናቸዉን እንከተል...ፀጉር አበላልጦ ተቆርጦ ነሺዳ ከማለት ዱቤ ከመቆርቆር...የቱርክ ልብስ ለብሰሽ ፊትሽን በድል ቀለም ሳምፕል አስመስሎ ከንፈርሽን ትኩስ የበግ ሳንባ አስመስለሽ ነቢይ ናፈኩኝ መዉሊድ መዉሊድ ከማለት
✔ሰኞና ሀሙስ መፆም
✔ለተለያየ ሰዉ ሰራሽ ዉበት የምትጠቀሚበትን አሁን ላይ ተፈናቅለዉ ስንት የሚያለቅሱ ልብሳቸዉን መቀየር ያቃታቸዉ እህቶችሽ አድርጊ
✔ቁርአን መቅራት አንዴ ቢከተም 4,307,400 ሀሰናት መሸመት
✔አጂ ነብይ ጋር የምትደባለቂበትን አድበሽ እቤትሽ ብትቀመጭ ..ነገ ባልሽ ድንግል ነሽ ?ሲልሽ አይንሽ 360 ዲግሪ ከሚዞር ይሄን ጊዜ እግርሽ የሚሽከረከርበትን ቢድአ ቦታ የመሄድ ቀንሺ
✔የማይጠቅሙ ግን የሚጎዱ ሙነሺዶች ስታዳምጭ ጆሮሽ የደነቆረዉና ተሰምቶሽ በነሺዳ የምታለቅሺ ከሆነ ...ለቅሶ ለሴት ልጅ እንደሳቋ ቀላል ነዉ የሞኝ ለቅሶ ትተሽ በነሺዳ የደነቆረ ጆሮሽን በቁርአን በአዲስ መልክ አደራጂዉ ..የነሺዳ ፍቅር ልብሽ ገብቶ ለማልቀስ የገፋፋሽን በዚክር አርጥቢዉ ..ይሄ ነዉ ነብዩን መዉደድ

#ወንድሜ_ሆይ!!! ነብዩን መዉደድህ በመዉሊድ ከሆነ ተሸዉደሀል
✔ጫት እየቃምክ ..የጎመን ወጥ ብረድስት ከመምሰል እንደ ሰለሀዲን አዩብ ጀግና ሁን ..ጫት ቅሞ አይደለም እየሩስ አሌምን ነፃ ያወጣዉ ተዉሂድን ይዞ እንጂ
✔መዉሊድ ላክብር አላክብር እያልክ ከመጨቃጨቅ ስንት ሙስሊም እህቶችህ በካፊሮች ወጥመድ ገብተዉ ሀይማኖታቸዉን ከሚቀይሩ ..እንደ ወንድ ቆላ ደጋ በሰሜን ወይ በደቡብ ተንቀሳቅሰህ አግብተህ ዘርህን ተካ ...አየህ አንተ መዉሊድ እያልክ ሌላ ሀገር ሂደህ ጫት ከምትቅም አገር ቀይረህ ስራ ብትሰራ አላህ ያግዘሀል አንድ እህትህን ሀይማኖቷን ከመቀየር ከተከላከልክ ..አየህ እስልምና የሰዉ ልጅ ወደ መጥፎ እንዳይሄድ መከላከል ስለሆነ የአንተ ማግባት ብዙ ለዉጥ እንዳለዉ ተረዳ...ለምን አሁን ላይ ወንዱ ማስተዳደር አቅቶት ለወደፊት ሴቶች እንዳያስተዳድሩ እየተፈራ ስለሆነ😉 ወንድ ሁነህ ለሴት ብቃትህን አሳይ


እናም ወገን ሆይ !!!! በግርግር በአጣልፍኝ ወቅት መጨፈር የሚወድ..ቡና መጠጣት ጫት መቃም ስጋ መብላት አጂ ነብይ ጋር መጨፈር የሚወድ መዉሊድ መዉሊድ ከሚል ሰዉ እራስን ማግለል ጥቅሙ ለራስ ነዉ ...ግድ እንደቻርልስ ዳርዊን 40 አመት እስከምንታመም አንጠብቅ ...

ኸይር ተናግሬ ከሆነ ከአላህ ነዉ...ስህተት ከሆነ ከሸይጧን ነዉ አላህ ይቅር ይበለኝ
✋ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሁ ወበረካትሁ

Join👇👇
@IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
╔═══════════════╗
ማጄላንና ታላቁ ሙጃሂድ ላቡ ላቡ
╚═══════════════╝

ልጅ ሳለን ስለማጄላን ጥሩ ጥሩው ተነግሮናል። በየትምህርት ቤታችን አስተማሪዎቻችን ስለእርሱ መልካም መልካሙን አውግተውናል። ዓለምን የዞረ የጂኦግራፊ ሊቅ ተብሎ የሚወሳው ማጄላን ማን ነው? እውነተኛ ታሪኩን ላውጋችሁ።
ሙስሊሞች የፊሊፒንን ደሴቶች ማሃራጅ ብለው ይጠሯቸዋል። ከቻይና እና ከሱማትራ በመጡ ነጋዴዎችና ዳዒዎች እስልምና በአካባቢው ተስፋፍቷል። ለ“ማኒላ” ድንበር ነዋሪዎች በሙስሊም ነጋዴዎች አማካኝነት የኢስላም ጥሪ ደርሷቸዋል። የእስልምና ብርሃን ከ7000 በላይ ነዋሪዎች ዘንድም ፈንጥቋል። ይህ የእግር እሳት የሆነበት ማጄላን ሙስሊሞች እንዳይስፋፉ እስልምናን ማምከን ይቻለው ዘንድ ከፖርቹጋል ተነስቶ ምስራቅ አፍሪካን እስከ ህንድ አዳርሶ ሙስሊሞችን በገፍ ብትሩ ቀጥቷል።
ሙስሊሞችን በእጅጉ ይጠላል። በ1502 ለሐጅ ጉዞ 700 ሙስሊሞችን ጭኖ የሚጓዝ መርከብን አገተ። መንገደኞቹ ወዴት እንደሚሄዱም ጠየቀ። የአላህን ቤት ለመጎብኘት ወደ መካ እየተጓዙ መሆኑ ሲነገረው ለግብረ አበር ወታደሮቹ ትዕዛዝን አስተላለፈ። ንብረታቸውን ከተዘረፉ በኋላ በመርከቡ ላይ ሰብስበው ከነህይወታቸው አቃጠሏቸው። በዘመታቸው የመስቀል ጦርነቶች ከ300 በላይ መስጂዶችን አፍርሷል።
ሙስሊሞችን ማርኮ አፍንጫቸውንና ጆሮዎቻቸውን ቆራርጧል። ጥርሶቻቸውን እየሰበረ በድዳቸው አስቀርቷቸዋል። እጅና እግራቸው ተጠፍሮ በክፍል ውስጥ ታጭቀው ከነህይወታቸው በእሳት ነደዋል።
ማጄላን የምድር አሳሽ አለምን የዞረ ጆግራፊስት መሆኑን አስተምረውናል። ግና ለሙስሊሞች የነበረውን ጥላቻ ያደረሰባቸውን ግፍና መከራ አልነገሩንም።
እ.ኤ.አ. በ1521 በ“ፈርዲናንድ ማጂላን” የሚመራው የስፔን ጦር ፊሊፒን ደረሰ። የጎረቤት ደሴቶች በስፔን አክሊል ሥር እንዲተዳደሩና ክርስትናን የበላይ ለማድረግ በሚል ስምምነት ላይ ተደረሰ። አመጣጡም የእስልምናን መስፋፋት ለመግታትና ሙስሊሞችን አይቅጡ ቅጣት ለመቅጣት የታሰበበት ነበር።
በመስቀል ዘመቻው “ማክታን” የተሰኘች አንዲት ትንሽዬ ደሴትን ለመቆጣጠር ጉዞ ጀመረ። በወቅቱ ደሴቷ “ላቡ ላቡ” በሚባል ሙስሊም ሡልጣን ትተዳደር ነበር። በማጄላን የሚመሩት የስፔን ወታደሮች ከደሴቷ ጠረፍ መሽገው ከነዋሪዎቿ ምግብ እየነጠቁና ሐብት ንብረታቸውን እየዘረፉ ሲያስቸግሩ ሕዝቡ ተቃውሞውን አሰማ። ላቡ ላቡ እጅግ ጠንካራ ሙጃሂድ ነበርና ለማጄላን ወረራ እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማጄላን የአጎራባች ደሴት ነዋሪዎችን አነሳሳበት። ጥንካሬውን እና ዘመናዊ መሣሪያዎቹን ለማሳየት እድሉን ስላገኘ ደብዳቤ አስይዞ ወደ ላቡ ላቡ መልዕክተኛን ላከ።
"ከማጄላን ለማክታን ደሴት ገዢ ላቡ ላቡ በእየሱስ ስም እጀምራለሁ እኛ የነጭ ዘሮች የስልጣኔ ቀዳሚዎች ይህንን ሀገር የመግዛት ስልጣን ከእናንተ የበለጠ ይገባናልና ስልጣንህን አስረክብ"
ላቡ ላቡ ደብዳቤውን አንብቦ እንዳበቃ በግልባጩ አጭር ምላሽን ፅፎ ሰደደ "ኃይማኖት የአላህ ነው። የምናመልከው አምላክ ቀለማቸው ምንም ይሁን ምን የሰው ልጆች ሁሉ አምላክ ነው" ሲል መለሰ።
በዕለቱ ፀሐይ በሰማይ መሃል አናት ላይ ነበረች። የማጄላን መርከቦች በፊሊፒን ከሚገኙት የሙስሊም ደሴቶች በአንዱ ላቡ ላቡ በሚያስተዳድረው የማክታን ደሴት ዳርቻ እየተቃረቡ ነው። ዓመቱ 1521 ነው። ፊሊፒናዊያን በወጣት መሪያቸው “ላቡ ላቡ” መሪነት ተሰብስበው ለጂሃድ ተዘጋጅተዋል። ትናንሽ ጀልባዎች ላይ አድፍጠው የወቅቱን ዘመናዊ መሳርያ ታጥቀዋል። የራስ ቁር በአናታቸው አጥልቀው ሰይፍና ጋሻን ይዘዋል። በተንጣለለው ደሴት ላይ ከቀርከሃ በተሠሩ ቀስቶችንና አጫጭር ሰይፎችን ሸክፈዋል። የማጄላን ወታደሮች ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሲጠጉ ካደፈጡት ሙጃሂዶች ጥቃት ተሰነዘረባቸው። ሁለቱ ጭፍሮች ተገናኙ። የማጄላን ወታደሮች እንደለመዱት የሙስሊሞች አንገት ከራሳቸው ሊያበሩ ተዘጋጁ። በሹል ሰይፎቻቸው ሰውነቶችን ሊቀዳድዱ ቋመጡ። ግና ስላደፈጡት ሙጃሂዶችና ስለቀርከሃ ቀስቶች መረጃው አልነበራቸውም። የራስ ቁር እና ጋሻ ይዘው ያፌዙባቸው ጀመር። ጎራዴ ከጎራዴ ጋር ተፋጨ። ​ በ“ላቡ ላቡ” እና “ማጄላን” መካከል እጅግ ጠንካራ ፍልሚያ ተደረገ።
የብረት ጡሩር ደረቱ ላይ ያጠለቀው ማጄላን በባዶ ራቁቱ በሚዋጋው ሙጃሂድ በላቡ ላቡ ሠይፍ ተመቶ ወደቀ። ጉዳቱ ለሞት የሚዳርግ አልነበረም። ወጣት መሪ ላቡ ላቡ ለሁለተኛ ጊዜ የማጄላን አንገት ላይ ሰነዘረ። የማጄላን ጭንቅላት በደም ተጨማለቀ። የመሪያቸውን መገደል ያዩት ወታደሮች ከመሸሽ በቀር ሌላ አማራጭ አልነበራቸውምና አስክሬኑን ጥለው ወደ መርከባቸው መፈርጠጥ ጀመሩ።
ፊሊፒናዉ ሙስሊም ጀግና የተዋጣለት ተዋጊ ሙጃሂድ ‹ላቡ ላቡ› ማጄላን በሙስሊሞች ላይ የሰራውን ግፍና እየፈፀመ የነበረውን ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ሰምቶ በእጅጉ ተቆጥቶ ነበርና እነሆ ዛሬ እስከወዲያኛውም ወደ ቀብር ሸኘው።
ፊሊፒናውያን አሁንም ላቡ-ላቡን ብሔራዊ ጀግናቸው አድርገው ይመለከቱታል።
እንደ አለመታደል ሆኖ የእስልምና ጠላቶች የማጄላንን የሐሰት ታሪክ አስውበው ፃፉልን። እኛም በምዕራባውያን መስቀለኞች ዓይን እንድናነበው ተደረግን። በልባችን ውስጥ እንደጀግናና ተአምረኛም ይዘከር ይዟል።



═════════════════
ምንጭ:-
كتاب قبسات من نور
2024/09/27 09:38:16
Back to Top
HTML Embed Code: