Telegram Web Link
page ➋
ለመልቀም የማይመች ገደል አለ ወደ ግራ ስመለከት የሰፈሩ ሰዎች ቆሻሻ የሚደፉበት የቆሻሻ የአመድ ጥርቅም ተመለከትኩ ..መኪናዉም ደረሰብኝ ወደ ግራ ጥምዝዝ አድርጌ በዛ በፍጥንት አካሄድ ቆሻሻዉ ዉስጥ ሂጄ በአናቴ ተተከልኩ ..ብድግ እላለሁ ሰዉነቴ ልብሴ አመድ በአመድ ሁኛለሁ ፊቴ የኔ መሆኑ አያስታዉቅም ☹️..በብዙ ደቂቃ ትግል የተወሰነ አራግፌ ጓደኛየን በሩቄ ጠርቼ ሳይክሉን አድርስ ጓደኞቼ እንዳይስቁብኝ ሂጄ እቤቴ ልብሴን ልቀይር ብየ ከሰፈር ልጆች ተሰወርኩ...ሰገዳዉ ላይ ጀለብያ ለብሼ ቱቦ ገባሁ...ከሰአት ደግሞ ፍሬን የሌለዉ ሳይክል ሳሽከረክር ቆሻሻ መጠያ እኔም እንደቆሻሻ ወደኩ...ከዛ ቀን ቡሀላ ሳይክል ላልነዳ ብየ ቃል ገባሁ ይሄዉ ዛሬ ድረስ ልነዳ ስል ያአጋጣሚ ትዝ እያለኝ ሳይክል መንዳት አቁሜ ቀረሁ፡፡


አንዳንዴ ክርስቲያን ጓደኞቼ ጋር በሀይማኖት ስንከራከር እነሱም የኛ እኔም የኔ ይበልጣል እያልን አንግባባ ስንል...ሰፈራችን አንድ ቄስ አሉ እነሱን እንጠይቅ ብለን እንሄዳለን ..ከዛም አባባ ከእስልምናና ከክርስትና የቱ ይበልጣል? ስንላቸዉ ልዩነት የለዉም አንኮ አብራችሁ እየተጫወታችሁ እየበላችሁ አይደል ይሉናል
...አንድ የቸኮለ ልጅ አበባ እሺ ማንነዉ ገነት ማን ነዉ እሳት የሚገባዉ ክርስትያን ነዉ ወይስ ሙስሊም??ብሎ ሲጠይቃቸዉ
...ልጆቼ ከሁለት አንዱ ይቀጣል በእሳት አሩን ይበላል ፈጣሪ ነዉ የሚያቀዉ በሉ ሂዳችሁ ተጨዋቱ ብለዉን ጨዋታችንን እንቀጥላለን

ደሴ ላይ በልጅነት ረመዷን ይሄን ይመስል ነበር መገን ረመዷን ዘንድሮስ ??? እኔ የምለዉ ስልክ ከመጣ ቡሀላ የተፈጠረ ልጅ ላይፍ የለዉም ከስልክ ዉጭ ሌላ የሚያቀዉ የለም ..እኛ በልጅነት ስልክ ሳይኖር ጓደኞቻችን ጋር መገናኛ ቦታ አለ እንገናኝ ነበር አሁን ስልክ ዉሸት አስተምሮን መገናኛችን እርቋል.

አንድ ገጣሚ እንዲህ ብሏል
ታምሜ ተኛሁኝ፥ ካልጋው ከፍራሹ
ሀኪም አትጥሩልኝ፥ መድሀኒት አትሹ
ደባብሶ 'ሚያድነኝ፥ ጊዜ ነው ፈዋሹ።

መገን ጊዜ ብዙ አልፏል ለሁሉም ጊዜ አለዉ.. ጣፋጭ ጊዜያቶች አልፈዋል ..አሁንም ያለዉ ገና ያልፋል....

እስኪ ሙሀመድ አወል ከመንዙማዉ ስለረመዷን አሁን ሳይሆን ያዳመኩት ልጅ ሁነን መንዙማ ሀላል የዲነል ኢስላም ክፍል እየመሰለን በአመት ረመዳን ሲመጣ ሙሀመድ አወል መንዙማ ያወጣዉን ለማዳመጥ እንጓጓ ነበር ..ዛሬ ደግሞ መንዙማዉ ቀርቶ አስተካክለዉ ቁርአን ቀርተዉ ኪታብ ሳይቀሩ የነብዩ ሰዐወ ታሪክን ሳያቁ ብር መሰብሰቢያ እና ሴትን ልጅ ማዳከሚያ ማጃጃያ ነሺዳ እያወጡ ኡማዉን እያጠመሙ ነዉ...አረ ጎበዝ ከማጥመም አልፎ ሴቶች ልጆች በሙነሺዶች ከዉጭ የነቢይ ወዳጅ በዉስጥ ስራቸዉ ሌላ ሁኖ ብዙ ሴት ተሸዉዷል..በሂደት በትክክለኛ ማስረጃ ይፋ ይሆናል ኢንሻ አላህ

ግን ይቺ የሙሀመድ አወል ግጥምን ጀባ ልበላችሁ

ረመዳን ደጉ ቀን ኸይረኛዉ ወራት
ነፍሲቱን ደበቃት ሀራም ከመስራት
ምላሳችንንም ሰዉን ከማማት
መለአይኑ ሁሉ ወሬ ከማዉራት
ደግሞ የሚገርመዉ የአንዳንዱ ሰዉ ኢማን
አንድ ወር ብቻ ነዉ ሲገባ ረመዳን
ረመዳን ከወጣ አላህን አያቅም
አሊም ወደአለበት በጭራሽ አይዘልቅም
ሀላልና ሀራም አይጠባበቅም
ይበቃል አይበቃም ኪታብ አይጠይቅም
ሙራዳቸዉ ሞላ በእጅግ ተጠቀሙ
ሀቁን በሚገባ ጠብቀዉ የፆሙ
ፆመኛ አይባልም የኔ ቢጤ ደሀ
ተከልክሎ ቢዉል እህልና ዉሀ

ጌታችን ይመስገን ደረሰን ለኢዱ
ነገር ግን አዝነናል ፆሙ በመሄዱ
ረመዳን የአንተኮ ጓዳን መሄድህ
ነፍስያ እንደ ልባ ትፈንጥዝ እንግዲህ
ረመዷን ሊሄድ ነዉ የቲም አድርጎን
ባንፆመዉ እንኳ ሀቁን አድርሰን
አንሸኘዉም ወይ ምነዉ ተላቅሰን?
ለከርሞ አላህ ቢሻ እንዲሁ እንዳለን
ደህና እንቀበለዉ አመት አድርሶን

ረመዷኑ ሄደ ብዙ ሰዉን ጠቅሞ
በዟሂር በባጢል ሸልሞ ሸላልሞ
ረመዳን ተነሳ ጓዙን ጠቀለለ
የድንኳኑን አዉታር ካስማዉን ነቀለ
ረመዷኑ ሄደ ጠቀለለ ጓዙን
ለሚገባዉ ሁሉ ሰጥቶ ደመወዙን
ረመዷኑ ሄደ ጓዙን ሰላለፈ
ገምና በመሀከል ገብይቶ አተረፈ

👐👐እስኪ ወሎ በዱአ ነዉ ዱአዉን እናቧቧዉ
ቢስሚላሂ አልሀምዱሊላሂ ወሰላቱ ወሰላሙ አላ ረሱሊላህ ሰዐወ .አላህ ለመሚጣዉ ረመዳን አድርሰን ዙር ገጣሚ ያርገን ..የፆመኛ ምንዳን የምናገኝ ያድርገን ..ቀልብ ጀሰዳቸዉ ከጠራዉ ባርያዎቹ አላህ ያድርገን፣ አለማችንን...አህጉራችንን..አገራችንን..ከተማችንን..ቀበሌያችንን..ሰፈራችንን..መንደራችንን..ጎረቤታችንን..ዘመዶቻችንን..ቤተሰባችንን..ኸሊቁን እንዳለ በኒአደሙን በሙሉ አላህ ሰላም ያርገዉ አላህ ያዋደዉ የሚተዛዘን ያርገዉ አላህ ይጠብቅልን ፣በዘር በጎሳ በቀለም በዘር ሳይሆን በላኢለሀ ኢለላህ የምንተሳሰር ያድርገን፣እኛ አላማችን እቅዳችን ጀነት መግባት ነዉና በእኛ ኸይር ስራ ሳይሆን በአንተዉ እዝነት ጀነት የምንገባ አድርገን..አላህ ሆይ ክርስቲያኖችን ሌላ ሀይማኖት ተከታዮችንም አንተዉ በቁርአን እንዳለከዉ እኔ የፈለኩትን እመረዋለሁ እንዳልክ አንተዉ እንደሻህ አድርገህ ቀጥተኛዉን ምንገድ ምርቻዉ ልቦናቸዉን ክፈትላቸዉ፣ተናግሮ አናጋሪን አብሎ መስካሪን ከወዲህ መስሎ ከወዳ ዟሪን አቃፊ መስሎ ገፍታሪን ሳሚ መስሎ ነካሽን የሚያይ መስሎ ጠቃሽን አራጋፊ መስሎን አቆሻሻንን መካሪ መስሎ ተሳዳቢን ተራማጅ መስሎ አደናቃፊን መካሪ መስሎ ነካሪን አሳሪ መስሎ ቆራጭን አንተዉ ያዝልን፣አገር አማን ይሁን በላዉ ተብሪድ ይሁን ፣ እሷ የምታዘን ሳይሆን እኛ የምናዛት ዱንያ ሰደቃ የምንሰድቅበት የቲም የምንረዳበት ዲነል ኢስላምን የምንካድምበት መስጊድ መድረሳ የምንገነባበት የማታሳሳ ዱንያ ያረቢ ስጠን፣ ላላገባነዉ ደግሞ ሷሊህ የሆነችዉን አንተን ቤተሰቦችህን የምወድልህን የታሸገች የተሸሸገችዉን ከተቻለ Red blood cell(ቀይ የደም ሴል) 😉ያላትን..ባይኖራትም ፀባይ ባህሪ የዲነል ኢስላም ፍቅር ያላትን
በቃ ፍቅር በፍቅር የሆነችዉን ሁሌ ስታዛት መርሀባ መርሀባ ለዛም ነገር መርሀባ የምትለዉን በቃ በጠቅላላ ቅጥል ስሟ መርሀባ የሆነችዉን 😋አላህ ይወፍቅህ ይወፍቀን ለኔም ይወፍቀኝ አቦ.አላህዋ አደራህን ጅልባብ ለብሰዉ የጅልባብን ትርጉም ሳያቁት ለብሰዉ ዲነል ኢስላምን ከሚያሰደቡ በተለያየ ማህበሪያዊ ሚዲያ ትዳር ሲያጠምዱ ከሚዉሉ ጠቅለል ሲደረግ ጅልባል ለመግኘት ጅልባብ ከለበሱ ሴቶች አላህ ይጠብቀን(አዉፍ በሉኝ በኔም በጓደኞቼም ስለገጠመኝ ነዉ)

👐👐እህቴ ሆይ ለአንቺም ቢሆን ዱአዉ አለን ...ከዱአዉ በፊት ብዙዎቹ ሴቶች ዲነኛ ወንድ አይወዱም ኪታብ የቀራችዉም ቢሆን የምፈልገዉ ምላስ ያለዉ ዱርየ ነዉ..ኪታብ ቀርታ ቁርአን ሀፍዛ ዱርየ እያገቡ እያየን ነዉ ..አንዷ ለምን አገባሽ ተብላ ተጠይቃ ኪታብ አቅርቼ ቁርአን እንዲሀፍዝ አረገዋለሁ ፍላጎት አለዉ ብላ እሷም ባሏ ጋር አብራ ጫት ቃሚ ሁና አይቻት የቅርብ ቀን ትዝታየ ነዉ፡፡ አንዱ ኡስታዝ ደአዋ ሲያደርግ ሰምቸዉ አሁን ድረስ ይገርመኛል ደአዋዉ ሴት ማለት እንደ ብረትድስት ናት ብረትድስት እሳት ላይ ሲያረጉት ይሞቃል ሲያወጡት ይቀዘቅዛል ሴትም እንዲሁ ናት ኪታብ ቀርታ ዱርየ ከወደደች ዱርየ ትሆናለች ክርስቲያንም ከወደደች እንደሱ ትሆናለች እናም ጠንከር በይ ብሏል..እስኪ ደአዋዉ እዉነት ይሆን???
ቢስሚላሂ በዲኑ ጠንካራ የሆነ አይኑን የሰበረ የሚስቱን ሀቅ የሚወጣ ባል ይግጠምሽ፣ ቀበሮ ሁኖ የዘነጋን ሞኝ ፍየል ሲያሯሩጥ የኖረዉን ሳይሆን አንበሳ ሁኖ ክብሩን ጠብቆ የቆየዉን አላህ ይወፍቅሽ፣የብዙዉ ጥያቄ ጥሩ ባል ስጠን ነዉ አላህ ያሰብሽዉን ትዳር በመስኮት ብቅ እልም👇👇
Page ➌
የሚል ሳይሆን በተጨማሪም እንደ ክረምት ፀሀይ ጥፍት ምጥት የሚል ሳይሆን እንደ በጋ ፀሀይ ሁሉም የሚያየዉ እንደ ምሽት ጨረቃ ሳይፈራ የሚፈካ ሀላል ፈላጊ ስለሆነ በአንቺ ቤተሰቦች ለመታየት የማይፈራ በዋናዉ በር መጥቶ በግቢዉ በር ይዞሽ የሚወጣ ጥሩ ትዳር አላህ ይግጠምሽ፣ሴት ልጅ ከእናትነት ዉጭ ትምህርት ቤት ማህበረሰብ ነሽ..የዛሬዉ በብሄር በዘር የሚያጋጨን ከአንቺ ወጥቶ ያደገ ማህበረሰብ ስለሆነ አግብተሽ ወልደሽ ብሄር ዘሩን የሚቆጥር ሳይሆን የአላህን 99 ስሞች የሚቆጥር የነብዩ ሀዲሶችን ሸምድዶ ይሄን ያህል ሀፈዝኩ እያለ የሚቆጥር ..ቁርአን ከነተፍሲሩ ከነገፁ በቃሉ ሸምድዶ የሚቆጥር..በሳምንት ይሄን ያህል ቁርአን ሀፈዝኩ እያለ የሚቆጥር .. የሱሀባ ታሪኮችን የሚዘክር የሚያስታዉስ ልጅ ሰጥቶሽ በዲነል ኢስላም ኮትኩተሽ የምታሳድጊ አላህ ያርግሽ፣
ክብርሽን ጠብቀሽ ቀይ የደም ሴልሽን ለሀላሉ ባልሽ የምታስከብሪ አላህ ያድርግሽ፣አላህ የሰጠሽም ባል ቀይ የደም ሴል ያለዉን ያድርግልሽ😊
አንተም እንደ አጋጣሚ ሴት ናትና በተለያየ ምክንያት ቀይ የደም ሴል ከሌለ የምትረዳ ህሊናህ የምፈርድ አላህ ያርግህ ዋናዉ ትዳሩ ነዉ ሀቢቢ👌
በቃኝ እንግዲህ በፁሁፍ ዱአ የልብን ለማድረስ ይከብዳል..ሆነም ቀረ የቀልድ ሳይሆን ከልቤ ነዉ ዱአ ያረኩት ከልባችሁ አሚን በሉ...አሚን ካላችሁ ቡሀላ ለኔም አድርጉ

#ማጠቃለያ:- በፁሁፉ ላይ ያሉት ግጥሞች ከሙሀመድ አወል መንዙማ የተወሰዱ ናቸዉ ፡፡ ማወቅ ያለባችሁ መንዙማን ደግፌ ሳይሆን ረመዷን የምትለዉ የመንዙማ ክፍሉ ከሽርክ የፀዳችና አስተማሪ ሁኖ ስላገኘሁት ነዉ እንጂ መንዙማ ደግፌ እንዳልሆነ በትልቁ ከተቻለም በወፍራሙ ይሰመርልኝ🤙


ዉድና የተከበራችሁ የቻናል ቤተሰቦች ለምወዱት ለወዳጅዎ ለቤተሰብዎ ለጓደኛ ለዘመድ የእንኳን አደረሰህ መልዕክት ካለዎ ከዛሬ እሁድ ቀን ጀምሮ እስከ ኢድ አንድ ቀን እስከሚቀረዉ በዚህ bot ይላኩ
👇👇👇👇👇👇👇
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot
☝️☝️☝️☝️
እኔም ኢዱ ሲደርስ በቻናል የሁላችሁንም የላካችሁልኝን አስተላልፋለሁ፡፡
🎁 በተለይ የእንኳን አደረሳችሁ የላካችሁለት እዚሁ ቻናል ተከታታይ ከሆነ እንደምታከብሩት ጥሩ ምኞት እንደተመኛችሁለት ጓደኛነታችሁን ማጠናከሪያ እያሰባችሁ እንደሆነ አዘንጉ፡፡ ከተቻለ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱ ለሶስት ሰዉ ተፈቅዷል...እንደዉ አንድ ሰዉ መነጠል አልችልም ካላችሁ አራተኛዉ ይሁን ግድ የለም ..ግን ላስቸግርህ አምስተኛም ላላችሁ ግድ እየከፋኝም ቢሆን እቸገራለሁ ነገር ግን ስድስተኛ በጭራሽ አይቻልም ለምን Message ይበዛል፡፡
ስትልኩ መርሳት የሌለባችሁ
የእናንተን ስም እና የምትኖሩበትን ከተማ
እንኳን አደረሰህ የምትሉን ስም እና የሚኖርበትን ከተማ
እናንተም ደስ ካላችሁ እስከ ሰፈሩ መግለፅ ይቻላል ፡፡ በተለይ አዲስ አበባ በጣም ሰፊ ስለሆነ ሰፈሩን ብገልፁ የላካችሁለት ማወቅ ይችላል ብየ አስባለሁ የሌላ ከተማም ነዋሪዎች
በዚህ Bot ይላኩ
👇👇👇👇👇👇👇
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
እኔም በቻናል ኢዱ አንድ ቀን ሲቀረዉ እፓስተዋለሁ
መልካም ኢድ ሙባረክ ተመኘሁ
(አሚር ሰይድ)
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
አገራራሚው የደሴ ኢፍጣር ኘሮግራም// በደሴ ሙስሊም ወጣቶች ተዘጋጅቶ በአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች የቀረበ
አይተዉ ሰብስክራይብ ሼር ማድረግ አይዘንጉ👇👇
https://youtu.be/sr6Ndfeahvw
እንኳን አደረሳችሁ ከተላኩ የተወሰኑትን እነሆ
📥 መጀመሪያ እኔ #አሚር_ሰይድ እንኳን አደረሳችሁ የምለዉ
➊ ለመላዉ አለም ላይ ላሉ ሙስሊም ማህበረሰቦች እና ዉድ ለሆናችሁ የቻናል ቤተሰቦች
➋ ደሴ ከተማ ለምትገኙ የአረብ ገንዳ ወጣቶች ጀመአ ለሆናችሁ ለብቻህ ደግሞ ለአሚራችን ሁሴን
➌ ዉድ አብሮ አደጌ ጓደኛየ አረ አብሮ አደጌ ብየ አራኩህ ከዉልደት እስከ አሁኑ ሰአት ድረስ ጓደኛየ ክርስቲያን ሁነህ እንኳ ሀይማኖታችን ተለያይቶ ልባችን ሳይለያይ አብረን አድገን ዛሬ ደግሞ አላህ ልቦናህን ከፍቶልህ ዲነል ኢስላምን ተቀብለህ የዘንድሮዉ ረመዳን ለመጀመሪያ ጊዜ ከእኛ ጋር እየፆምክና ቁርአንን ለማክተም ጥረት እያረክ ላለሀዉ ዉድ ጓደኛየ በአዳማ ዩኒቨርስቲ የማስትሬት ትምህርትህን የምትማረዉ አሌክስ ብርሀን(ካሊድ) ለመጀመራያ ጊዜ ከእኛ ሙስሊም ወንድም እህቶችህ ጋር ሁነህ ለምታከብረዉ በአል እንኳን ለኢድ ሙባረክ በአል አደረሰህ
በዲነል ኢስላም ጠንክረህ
ሰልመዉ ጠንካራ እንደሆኑት እንደ ኡስታዝ ካሊድ ክብሮም
በአሜሪካን ቴክሳስ በሚገኝ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ቄስ የነበሩት ጆሴፍ ኢስተስ
የአሁኑ የእስልምና ዳኢ የሱፍ ኢስተስ
ለብዙ ክርስትና ተከታዮች የእስልምና ጥሪ በማቅረብ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ለመግባት ምክንያት የሆኑ ናቸዉ፡፡ አንተም እንደነሱ ሁነህ ቤተሰቦችህን ዘመዶችህን ወደ ቀጥተኛዉ መንገድ የምትመራ ያርግህ፡፡ ወሎ ነኝ ግማሹ ዘራችን ሙስሊም ነዉ እንዳትለኝ😉 እኔም አንተ የምናቃቸዉ አንዱ ዘራችሁ አለ
➍የተለያዩ እዉነተኛ ታሪክ ሲዘጋጅ አንብባችሁ ሼር ለምታደርጉ ሁሉ
ነጥየ ኢድ ሙባረክ ብል እኔ የማቀዉ በጣም ብዙ ስለሆናችሁ ወላሂ ፁሁፉ ጭራሽ አይበቃኝም ብቻ የማቃችሁ የማታቁኝ ሁሉ ኢድ ሙባረክ ብያለሁ

💠 #አሌክስ_ብርሀኑ (ካሊድ)☞የትዉልድ ቦታ ደሴ አሁን አዳማ ዩኒቨርስቲ
➊ ለእናቴ ቤተሰብች
➋ ለከሪማ ሁሴንና ቤተሰቦቿ
➌ ለአንተ አሚር ሰይድ ቤተሰቦች
➍ ለመላዉ ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ

📥 #ሠይድ_ሙሐመድ የምኖረዉ ጅቡቲ
➊ አዲስ አበባ ቃሊቲ ለመገኙት እህቶቼ ዘሐራ መሐመድ እና
➋ ሞእሚና መሐመድ

💠 #ፉአድ_ሙሀመድ_ያሲን ☞ከከሚሴ
☞ደሴ ለሚገኘዉ ጓደኛየ ለኢምራን ኑሩ

📥 #አህመድ_ቃሲም ☞ ከሀዋሳ
➊ ለመላው ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም
ተማሪዎች ጀመዓ
➋ አዲስ አበባ ለምትገኙ ቤተሰቦቼ
➌ ደባርቅ ለምትገኘዉ ወዳጄ ኢክራም

💠 #ራህመት_ሰይድ☞ ከወልቂጤ
ደሴ ለሚገኙት እህቶቼ
➊ለሰሚራ
➋ለመዲና
➌ለሉባባ

📥 #ሰአዳ_ሙሀመድ ☞ ከደሴ
➊ መላዉ ለሙስሊም ማህበረሰብ እና
➋ ለአንተ አሚር ሰይድ

💠 #አንዋር ☞ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦቴ( አለምጤና) ከተማ
➊በአለም ላይ ለሚገኙ ሙስሊሞች በሙሉ
➋ ለቤተሰቦቼ በሙሉ
➌አዳማ ከተማ ለምትኖረው ለተስሊማ ሙስጠፋ ከነቤተሰቦችሽ
➍ቡሌሆራ ላለኸው ውድ ወንድሜ አብዱልፈታህ ከነ ቤተሰቦችህ
➎ለኡስታዝ ሳዳት ከማልና ለሌሎች ኡስታዞቻችን
➏ ደሴ ለምትገኘዉ ለአንተ አሚር ሰይድ

📥 #ሳራ_ጀማል☞ ከቡታጅራ
➊ ለመላው ሙስሊም በሙሉ
➋ ለእናቴ ዙልፋ ጀማል እና ለ አባቴ ጀማል ሳሊሃ
➌ በጣም ለምወዳቹ እህቴና ወንድሜ ሙና ጀማል እና ጃዕፈር ጅማል
➍ ለሁሉም የቡታጅ ሙስሊም እና ለምወዳቹ ለጓደኞቼ
➎ ለአንተ አሚር ሰይድ

💠 #አህመድ☞ ከአዲስ አበባ
➊ደሴ ለሚገኙት ለአይሻና ለሶፊያ
➋ ኮምቦልቻ ለምትኖሪዉ ፊታ እና ይማም

📥 #ሮዛ_ሸሪፍ ☞ ከሀረር
➊ ለእናቴ ሰአድያ በድሩ
➋ ለአባቴ ሸሪፍ ቃሲም
➌ ኳታር ላለችዉ እህቴ ካሚያ ሸሪፍS እና ዘሂዳ ሸሪፍ እና ረሂማ ሸሪፍ

💠 #ለይላ_አብድልሽኩር☞አዲስ አበባ ኮልፌ ➊ ለእናቴ ለቤተሰቦቼ ለጓደኞቼ
➋ ለወለጋ ዩኒቨርሲቲ ጊምቢ ካምፖስ ተማሪዎች
➌ ለሁሉም ሙስሊም ኢድ ሙባረክ

📥 #ኢክራም_ከድር ☞ ከደሴ
➊ ሳዉዲ ለምትኖሪዉ በጣም ለምወድሽ ለምሳሳልሽ እናቴ መዲና ሰይድ በአለሽበት ይድረስልኝ

💠 #ኢነብ_ሚፍታህ☞ ከአዲስ አበባ ቤቴል አካባቢ
➊ ለእናቴ ሩቅያ ሙሀመድ
➋ ለአባቴ ሚፍታህ ሀሰንena le wendeme
➌ ለወንድሜ ሀሩን ሚፍታህ

📥 #ፋጡማ_በሽር☞ ከአዲስ አበባ ሰሚት ኮኖዶሚኒየም
➊ ደ/ወሎ ለጋምቦ ወረዳ ( መቅደላ አባ ዩኒቨርሲቲ) ለሚገኙት እጅግ በጣም ለምወዳቸው ቤተሰቦቼ
➋ ለእናቴ ለሉባባ ዳምጠው
➌ለወንድሜ ለጀውሀር በሽር፣
➍ለእህቴ ለከሪማ በሽር ከነቤተሰቧ
➎ አ/አ አያት ለሚኖረው በጣም ለማከብረው ጓደኛዬ ለመኮነን ዳውድ ከነቤተሰቦቹ

💠 #ሱመያ_አስፋዉ ☞ከሳዉዲ አረብያ
➊ለመላው የእስልምና ተከታዎች በሙሉ
➋ ለውድ ቤተሰቦቼ ወሎ አባሰል ለሚገኙት
➌ከኪያም ለውድ ሱመዩች ለኢቅራ ተማሪዎች እንካን አደረሳችሁ
➍ በመጨረሻም ለውድ ጓደኞቼ ሀገር ውስጥም ከውጭም ያላችሁ
➎ ለዚህ ቻናል አዘጋጅ ለሆናችሁት በሙሉ ለአሚር ሰይድና ለጓደኞችህ

📥 #ኢልሀም_ሙሀመድ ☞ከደሴ
➊ከሚሴ ኡቀጢቅ ሰፈር ለሚገኘዉ አብዱ ሰመድ

💠 #አቢ ☞ከዱከም
➊ለከሪም አስራር ዱከም ላለሀዉ
➋ለመላዉ እስልምና ሀይማኖት ተከታይ ለሆናችሁ በሙሉ

📥 #ፈሪዳ_ናስር ☞ ከአጋሮ
➊ለቤተሰቦቼ ና ለዘመዶቼ
➋ ዉጭ ሀገር ላለቸ እህቴ ዛሀራ ናስር ለወንድሜ አማር ናስር
➌በጣም ምወዳት ጓደኛዬ ነጃት አባስ

💠 #አብደሽኩር_ሀሰን ☞አዲስ አበባ ፒያሳ
➊ ለእናቴ ለወድሞቼና ለእህቶቼ
➋ ለመላው አለም ለሚገኘው ሙሥሊም
➌በመጨረሻ ለራሴ

📥 #ሀኒያ☞ ከአዲስ አበባ አለም ባንክ አካባቢ
➊ ለቤተሰቦቼ በሙሉ
➋ ለጓደኞቼ በሙሉ
➌ ለአንተ አሚር ሰይድ

💠 #ሀፍሷ_ሙሀመድ ☞ ከፉሪ
➊ለአባቴ ሙሀመድ ሁሴን
➋ ለእናቴ ረምላ ደሊል
➌ ለአክስቴ ሰሚራ ደሊል
➍ ለጓደኛየ ሀምዲያ ሙሀመድ አሚን

📥 #ጌታሁን_ጌትዮ☞ እኔ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ ነኝ ..
➊ ለእስልምና ሀይማኖት ተከታዮችና
➋ ለሙስሊም ጓደኞቼ
➌ አርሲ ለምትገኘዉ ጓደኛየ አቡሽ ሀይሌ
➌ ኮርያ ለምትገኘዉ ሸምስያ አህመድ እንኳን አደረሳችሁ

💠 #ትርሲት ☞ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
ሰላም አሚራችን እንዴት ነህ.... ለዱአው እኔም አሜን ብያለሁ ለአንተም ፈጣሪ ያሰብከውን ያሳካልህ። ከፆሙ አትራፊ ያድርግህ። እርሱ ጾምህንም ዱአህንም ይቀበልህ።
ለአንተም ቤተሰቦችህም አጠቃላይ ለደሴ ሙስሊም ደስ የሚል፣ ያማረ፣ የደመቀ ኢድ ተመኘሁ።
☝️☝️ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አይነስዉር የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነችዉ ትርሲት ትባላለች ሁሌም በአስተያየት በሀሳብ ከጎኔ ነች ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ብዙ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ጋር በዚህ ቻናል ተዋዉቀን አንድ ላይ ሁነን ብዙ ስራ እየሰራን ነዉ ግድ ለእናንተ መንገር አይጠበቅብኝም😊

ለማንኛዉም በህጉ መሰረት ያላካችሁ የላኪ ስም የረሳችሁ ወደ 40 message በቻናል አልተላለፈም አዉፍ በሉኝ
☞በተጨማሪ ይሄ post ከተዘጋጀ ቡሀላ የላካችሁ አላችሁ በጊዜ ማጣት እሱንም አላካተትኩም አዉፍ በሉኝ፡፡በተጨማሪ በጣም ለምወዳት እናቴ ጓደኛየ ምናምን ያላችሁት message እንዳይበዛ edit ተደርጌ አቅርቢያለሁ

⚠️ አደራ ሴቶች ወደ ኢድ ሶላት ስትሄዱ ኢስላማዊ አደብ በጠበቀ መልኩ ይሁን ከለሊቱ 6 ጀምራችሁ ስትካካሉ ስትበጃጁ 10 አይነት የሚቀባ የድል ቀለም አዲስ የተጀመረ ህንፃ የሚቀባ የዲዛይን ምርጫ መስላችሁ መስገጃ ቦታ እንዳትሄዱ😊
⚠️ ወንድ ሆይ አንተም ጀለብያ በጥምጣም እንጂ ሲኪኒ ሱሪ ጠቦ በፈስታል የሚወጣ ለብሰህ እንዳመጣ😉


ለሁላችንም መልካም በአል ተመኘሁ 🎁🎁🎁
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
ለፍልስጤም ወገኖቻችን ከቻልን ድምፃችንን ካልሆነ በዱአችን እንገዛቸዉ

ፎቶ አሚር ሰይድ ዛሬ እኔን ማወቅ የፈለገ ይሄዉ ፎቶዉ😊
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✋🏻 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ የተከበራችሀና የተወደዳችሁ የቻናል ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ

ከረመዳን በፊት #ሳትዋጋ_ንገስ የሚለዉን እዉነተኛ ታሪክ ሁሌ ተስፋ እንዳይሆን መፃፌን ለማሳወቅ እስከ part ➓ ድረስ ተፓስቶ ከረመዳን ቡሀላ ከአንድ ጀምረን እንጨርሳለን ብየ ከቻናል ታሪኩን ሰርዠዉ ነበር፡፡

አሁን ከረመዳን ቡሀላ ኢብሊስ ገና ከመፈታቱ😊 በአስተያየት መስጫ bot ከረመዳን ቡሀላ የተባለዉ ታሪክ ለምን አጀምረዉ??አንዳንዴም ምነዉ ቃልህን በላህ የሚልም በተደጋጋሚ ቀን በቀን ከተለያዩ የቻናል ቤተሰቦች አስተያየት እየሰጣችሁ እያየሁት ነዉ

ግድ ነዉ ቃሌን እጠብቃለሁ ቃሌን አላጠፍኩም ግን ባለፈዉም ስጀምር ምነዉ እጀምራለሁ ብለህ ጠፋህ ስትሉኝ ነዉ የጀመርኩት ታሪኩ ሙሉ በሙሉ አላለቀም ነበር ..አሁን ከረመዳን ቡሀላ በስራ ሰአት ሳይቀር ማታ እንቅልፍ ቀንሼ አሁን ላይ 98% ደርሷል ፡፡ ግጥሞችና በመሀል የሚገቡ ፁሁፎች ብቻ ማስገባት ነዉ የቀረኝ ፡፡ ኢንሻ አላህ የአሁኑ ሳምንት ቅዳሜ ጀምሮ ታሪኩ በቀን አንድ ፓርት ይፓሰታል

እናንተም ሼር ለማድረግ ተዘጋጁ፡፡
☞ታሪኩ እስኪጀመር ሁለት ቀን የምንወያይበት ሀሳብ አለን ዛሬ ማታ ጀምሮ ሀሳቡ በቻናል ይፓሰታል ፡፡


🌀 በተጨማሪ ቻናል ያላችሁ ፀሀፊ አሚር ሰይድ የሚለዉን እና የታሪኩን ርዕስ ሳታጠፉ ከሚፓሰተዉ ታሪክ አንድ ፊደል እንኳ ሳትጨምሩ ሳቀንሱ መጀመር ትችላላችሁ ..አላህ የባሰ ችግር ካላመጣብኝ በቀር መችም ቢሆን ከተጀመረ ታሪኩ አይቋርጥም

⚠️ ዛሬ ማታ ከመግረብ ቡሀላ የምንወያይበት ጊዜዉን ያማከለ ጉዳይ አለ ማታ Online መንደር እንገናኝ አንገብጋቢ ጉዳይ አለ


የቻናል ቤተሰቦች የሚጀምረዉን ታሪክ ቢያንስ ለ10 ሰዉ ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ

ይህን እዉነተኛ ታሪክ ኢንሻ አላህ ቅዳሜ እንጀምራለን..
ግን ቋሚ የሆነ የመፓሰቻ ሰአት የለም ፡፡ ሳስበዉ የሚፓሰተዉ ከዙሁር ቡሀላ ይመስለኛል ቅዳሜ ሲደርስ እናየዋለን

መልካም ንባብ ተመኘሁ
አሚር ሰይድ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ
የቻናል ቤተሶሶች እንዴት ናችሁ
(አሚር ሰይድ)

ዛሬ አንድ የሀገራችን ባህል ላወጋችሁ ወደድኩ መቼም የኛ ማህበረሰብ በተለይ የገጠሩ ነዋሪ ከቁርአን ከሀዲስ መመሪያ የሚይዘዉ ሶላት ስገድ ረመዳንን ፁም ብቻ ይመስል ሌላዉን በሀገር ሽማግሌና በባህል መመራት የእለት ከእለት ኑሮዉ ነዉ...ግን አንዳንድ ባህሎች ጠቃሚም ጎጂም አላቸዉ ፡፡ ግን አሁን አንድ ሰዉ ያጨወተኝን እኔም አላምን ብየ ከአምስት ሰዎች ትክክለኛ መረጃ አጣርቼ ይሄ ባህል ግን ከተማ ላይ ቢመጣ አዋጭነት አለዉ የለዉም ብየ ብቻየን አሰብ አረኩና ግን መጀመሪያ እናንተ የቻናል ቤተሰቦች ማመካር አለብኝ ብየ እኔ በጆሮየ ስሰማ እየገረመኝም እያሳቀኝም😁 ማመን እያቃተኝም ብቻየን ማስተንን ከጀመርኩ ሶስት ወር አለፈኝ ..ምን ይሆን ነገሩ??
እነሆ እስኪ ልንገራችሁ

በወሎ ገጠራማ አካባቢ ቦረና የሚባል ቦታ ሴት ልጅ የራሳቸዉ የሆነ አስተዳደግ አላቸዉ ፡፡ አስተዳደጉም ሴት ልጅ የሚጣፍጥና ሆሮጠም ያለ ነገር ከበላች ታስቸግራለች ወላጅ ታስጠቃለች በመባል ስታድግ ሌላዉ እንክብካቤ እንዳለ ሁኖ ብዙ ጣፋጭ ነገርና ጨዉ የበዛበት ወጥ አትበላም ለምን ቶሎ ይግባችሁ ማገዶ አትፍጁ ..ተግባባን😉

ከዛም ለትዳር ስትደርስ ወንድየዉ ያጫል ግን ገና ስትታጭ ድንግል ነች ወይስ አይደለችም ተብሎ አይጠየቅም የአገሩ ባህል ሴት ልጅን ከነክብሯ ነዉ የምትቀመጠዉ ለባሏ ብቻ ነዉ ያንን ነገር መስጠት ያለበት ተብሎ የሀገሩ ባህል ነዉ፡፡
ከዛ ሰርጉ ይደርሳል ይበላል ይጠጣል ይጨፈራል ማታ አባወራ ያዉ በመፈተሻዉ ይፈትሻል 😊..ከተገኘባት የጨዋ ቤተሰብ ልጅ ቆንጥጣ ያደገች ተብሎ ከነቤተሰቡ ይከበራል በሳምንቱ ምላሽ ሲኖር በደንብ ተደግሶ ለቤተሰቦቿ ሽልማት ድረስ ይኖረዋል

ነገር ግን ድንግል ካልሆነችሽ🤔 ??ከባዱ የዘመናችን ጥያቄ ነዉ...
ግን ይሄ የገጠር ባህል በ21 ክፍለ ዘመን መልስ ያልሰጠዉን ባህሉ መልስ አለዉ፡፡ በሰርጓ በሶስተኛ ቀን ማን ወንድ ነዉ የወሰደዉ ተብላ ትጠየቃለች..ከተናገረች ጥሩ ካልተናገረች ግን በሳማ በጅራፍ ተናገሪ እየተባለች ትገረፋለችከዛም ድንግልናዋን በሀራም የወሰደዉን ትናገራለች
..ሙሽራዉ ታዳ ከነሚዜዎቹ ይሄድና የእሷን ድንግልና በሀራም የወሰደዉን ሰዉ ዉሀ በማያስጠጣ ዱላ እንዳይሆን አድርገዉ እንዳይቆም እንዳይራመድ እንዳይሞት እንዳይድን ከ10 ፌደራል ዱላ የማይተናነስ😊 ቢያንስ ለ6ወር ያህል የሚስተኛ ብትር ተደብድቦ እቤት የአልጋ ቁራኛ ይሆናል፡፡ ከዛም እሷ በሰላም ከባሏ ጋር መኖር ትጀምራለች፡፡ ድንግል አይደለሽም እየተባለች ተሸማቃ አትኖርንም ለምን ጥፋቱ እሷን አባብሎ ሸዉዶ የወሰደዉ አጅሬዉ ነዉና እሱ ደግሞ ቢያንስ የ6ወር አልጋ ላይ የሚያስተኛ በሽታ ከሙሽራዉ ተሰጥቶታልና፡፡ የተመታዉ ልጅ ቤተሰቦች ለምን ልጄን መታህ ብለዉ ሙሽራዉን አይጠይቁም እንደዉም አንተ ልክስክስ አንተን ነዉ ወልጄ ያሳደኩህ አሳፈርከኝ ብለዉ ታሞ እንኳ የህሊና እርፍት አያገኝም

ታዳ ይሄ የገጠር ባህል በኔ አመለካከት 70% ጠቃሚ ነዉ ብየ አስባለሁ፡፡ ግን በኔ አንድ ተራ ግለሰብ አስተሳሰብ ነዉ፡፡ ግን ጉዳት ሊኖረዉ ይችላል ለምሳሌ
☞ በፊት የተጣላችዉ ወንድ ካለ አዉቃ እሱ ነዉ የወሰደዉ ብላ በዉሸት ያልወሰደዉን ሰዉ ብታስገርፈዉስ?
☞በተፈጥሮ ድንግልና የሌላቸዉና በተለያየ ምክንያት የሄደባቸዉ የዛን ጊዜ የባልየዉን ግርፋት ይቋቋሙ ይሆን? ግን እነዚህ ሴቶችስ መልሳቸዉ ምን ይሆን?

👌የዚህ ባህል ጥቅም
☞የወንድል ልጅ ድንግልና መመርመሪያ መሳሪያ ባለመኖሩ ዉሸታሙና እዉነታሙ ወንድም መለየት በተቸገረበት ዘመን ይሄ ባህል ግን የመለያ የመቆጣጠሪያ መሳሪያ ነዉ፡፡ ማግባት ከፈለገ ቀጥታ ወደ ትዳር ይገባል ማንም ሴት አያጀዝብም ለምን ሙሽራዉ ከነሚዜዉ ከነዘመድ መጥተዉ እንደ ደረሰ እህል ወቅተዉ መሬት ላይ ያሰጡታላ☺️


😔 የዚህ ባህል አሳዛኝ ገፅታ
ብዙዉ የዛ ማህበረሰብ ወደ ከተማ ሲገባ አሁን ወቅት ላይ 70% ተዳክሟል እየቀረ ነዉ አሉኝ፡፡ ሰዉ ሰለጠነ አሉኝ..ግን ይሄ ባህል ከገጠር ወደ ከተማ መዉረስ የነበረብን ነበር😉


አሁን ማስተላለፍ የምፈልገዉ መልዕክት
ማወቅ ያለባችሁ አሁንም ቢሆን መቼም ቢሆን ድንግልና የትዳር መስፈርት ሊሆን አይችልም፡፡ አንተ በኒ አደም ሆይ እባካችሁ አረ እባካችሁ ለአላህ ብላችሁ ትዳር ስትፈልጉ ዲኗን ቤተሰቧን የመጀመሪያ መስፈርት እናድርግ ..ለምሳሌ የኔ መስፈርት ወላሂ ብየ ልንገራችሁ ዲንና ቤተሰብ ነዉ፡፡ ሁሌ በፁሁፍ ላይ የማንፀባርቀዉ ሀሳብ ሴቶች የዘነጉ ስለሆነ ትንሽ ፈራ እንዲሉ ነዉ እንጂ ምላሴ ስለተናገረ መስፈርት ሊሆን አይችልምና... ጀሊሉ የሚሰጥህ በልክህ ነዉ አንተ እንደኖርከዉ አኗኗር የወደፊት አኗኗሪህን ታገኛለህ፡፡
☞ግን ሙስሊም ወንዶች የመጀመሪያ መስፈርት ድንግል ነሽ እያልን ሙስሊም ሴቶቻችን ሀይማኖታቸዉን እየቀየሩ ነዉ እባካችሁ የኢስላምን ጎዳና የምናሰፋ ባንሆን እንኳ እንዲጠብ በኛ ምክንያት አባራሪ አንሁን፡፡
እኔ ደሴ ከተማ ላይ እያየሁ ነዉ ነዋሪዉ ክርስቲያን ሙስሊሙ ተዋልዶ የኖረ ቢሆንም ግን ይሄ ቀርቶ ነበር ግን ሙስሊም ሴቶች ክርስቲያን እያገቡ እያየሁ ነዉ እናም ይቺ ልጅ መቼም ከሙስሊም ወገኗ መቶላት መስፈርትህ ቢክራ ሁኖ እሷ ሰዉነችና ተሳስታ ግን ጥርት ያለተዉበት ቶብታ አንተ ግን አንቋሸህ አዋርደህ ለሰድቦ ሰዳቢ ሰጥተህ ትተሀት በዚህም ይሁን በሌላ ምክንያት ሀይማኖቷን ብቀይር አንተም እሷም አላህ ፊት ተጠያቂ ነህ ሀቢቢ...

💠እኔ በአስተያየት መስጫ bot ብዙ ነገሮች ይደርሰኛል የሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች መስፈርታቸዉ ድንግልና አይደለም ባህሪ እንጂ..
ከቻልሽ አንቺም እህቴ ከተኩላ ምላስ እራስሽን ጠብቂ ፡፡

ወላሂ ይሄን ፁሁፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ ከረመዳን ቡሀላ በአስተያየት መስጫ Bot ላይ እርዳን የሚሉ እና ሀሳባቸዉን ስቀበል በጣም ግራ ገባኝ ፡፡ አራቱም ገና ድንግልናን ትርጉም ሳያቁት ትምህርት ቤት ተሸዉደዋል ቶብተዋል ወደ አላህ ተመልሰዋል..ምነዉ የአንተን ታሪክ የዛሬ አምስት ስድስት ሰባት አመት በፊት አግኝተነዉ በነበር ግን አራቱም ተስፋ የላቸዉም ሁለቱ 10 ክፍል ተማሪ አንዷ 11 አንዷ ደግሞ ኮሌጅ
ግን ለምን ተስፋ ቆረጣችሁ ስላቸዉ..የሙስሊም ወንድ ልጅ መስፈርቱ ድንግልና ነዉ አሉኝ፡፡

እንደነዚህ ያሉ ሴቶች ሰዉ ጋር አብረዉ ስቀቁ እየኖሩ ነዉ ግን አሁን ባለዉ የሙስሊም ወንድ አቋም ለወደፊት ብዙዎች ተስፋ አጥተዉ ተቀምጠዋል

እዉነት ነዉ ግን ወንድ ሆይ ምን እናድርግ? በኛ መስፈርት ምክንያት ሀይማኖት ይቀይሩ ተስማምተሀል ማለት ነዉ?ሰድበን ለሰዳቢ ስንሰጣቸዉ ምን ተሰማህ?

እኔ በበኩሌ ወላሂ ጓደኞቼ ጋር ያላገቡት ጋር በሰፊዉ አዉርተን በተቻለኝ አቅም አሳምኛለሁ፡፡ እነንተም ወንዶች ሆይ በስራ ቦታ በትምህርት ቤት በሰፈር በቤት ወንድምህ ሳይቀር መመካከር አለብን ቢያንስ ይሄን ሀሳብ ያነበበ ያመነበት 300 ሰዉ ቢገኝ 10 ሰዉ ቢያካፍል 3000 ሰዉ ይወያይበታል ማለት ነዉ ከ3000 ሰዉ 1000 እንኳ ሀሳቡን ቢቀይር ወላሂ ትልቅ ለዉጥ የሀሳብ ለዉጥ ማምጣት ይቻላል፡፡

☞የሚያስዘነዉ ደግሞ ለትዳር ብላ ሀይማኖት ብቀይር በደስታ አለመኖራቸዉ ደግሞ ሌላዉ ጠባሳ ነዉ፡፡ የአላህን ሀቅ የማያቅ እንዴት የአላህን ሀቅ አዉቃ የካደች ጋር አብሮ ተስማምቶ ሊኖር ይችላል?? ሴቶች ሆይ እናንተም እሰቡ ግባችሁ ትዳር ላይ ብቻ አታድርጉ ከፍረዉ የገቡ ወላሂ 95% ልጅ ወልደዉ ሂወት መስርተዉ መዉጫ 👇👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዉድና የተከበራችሁ የቻናል ቤተሰቦች
ወላሂ ዝምታ መጥፎ መሆኑን ዛሬ ተረዳሁ ብዙ ሀሳብ ማህበረሰቡ ላይ ያለ ለማመን የሚከብድ ነገሮች በሀሳብ አካፍላችሁኛል፡፡ ቢያንስ ከ500 በላይ አስተያየት ተቀቦያለሁ

እስኪ አራት comment እስኪ ጀባ ልበላችሁ የተሻሉ ሁሉንም ያማከሉ ሌላዉ ነገ 10 የተሻለ comment ይፓሰታል

መጀመሪያ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ የሆነችዉን ትርሲት የሰጠችኝ ከሁሉም ተመቸኝ
Comment ➊

💠ይሄ ባህል ወደ ከተማ ይምጣ!!! ኧረ አሚር ምን አስበህ ነው?
ወይስ መንግስት በሌለው በጀት ለተደበደቡ ማገገሚያ መስቀል አደባባይና ጃንሜዳ ሆስፒታል ሊገነባ ነው ሀሀሀ..

ግን አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ አስታወስከኝ 'ፈሪሳውያን አንዲትን አመንዝራ ሴት ሊከሷት ወደ እየሱስ አቀረቧትና "ይህች ሴት አመንዝራ ማለትም ዝሙተኛ ስለሆነች በሙሴ ህግ መሰረት በድንጋይ ትወገር" አሉት። እየሱስም "ከእናንተ መሀል ሀጢያት የሌለበት ይውገራት አላቸው። እነርሱም ትተዋት ከአካባቢው ሄዱ። እርሱም ቀና ብሎ አንቺ ሴት ከሳሾችሽ የታሉ? ሲላት " አላውቅም ጌታዬ ብላ መለሰች። እሷም ከልቧ ተፀፅታ ነበርና "አንቺ ሴት ሂጂ ሀጢያትሽ ተሰርዮልሻል ድጋሚ እንዳታደርጊው ብሎ ሸኛት።

እና አሁን ላይ የሚስቱን ድንግልና የወሰደውን ሰው ለመቅጣት የሚያስደፍር ስብእናና ንፅህና ያለው ምንያህል ወንድ ነው? ቢሆን እንኳን አስገድዶ የደፈረ ካልሆነ በቀር ሴቷ ወዳና ፈቅዳ ላደረገችው በምን እዳው ይደብደብ? ለነገሩ እኛ ሴቶች እኮ አናፍርም" እየጠጣን እናምሽ ሲለኝ እሺ አልኩ እንጂ ሌላ ነገር መች አልኩ" እንል ይሆናል። ወይም ደግሞ አልነካሽም ብሎኝ ቤቱ ሄድኩ የሚልም ይኖራል።
ዞሮ ዞሮ ግን አንተ እንዳልከው ድንግልና ለትዳር የግዴታ ባይሆን እንደመስፈርት ወይም እንደአንድ ክሬዲት ቢያዝ ጥሩ ይመስለኛል
ምክኒያቱም ድንግልና የክብር፣ የታማኝነት፣ የታጋሽነት፣ እንዲሁም የታዛዥነት መገለጫ ሊሆን ይችላልና ነው። ምክንያቱም በእስልምናም ሆነ በክርስትና ከጋብቻ በፊት ግንኙነት እንዳይኖር ያዛልና። በሌላ በኩል ወንድ ሞልቷል ሴት ሞልቷል እየተባለ የሚደረግ ፍቺን ሊቀንስ ይችላል።። ከዚህም በላይ ክብራቸውን ጠብቀው ለቆዩ የሚገባትን ክብር ሰቶ ሌሎችንም ማበረታቻም ነው።
ያው ይሄንን ስል ታዲያ ምክንያታዊ ፣ሰውን የሚረዱ ፣ከሁሉ በፊት መልካም ስብእናን የሚያስቀድሙ ፣እራሳቸውም መልካምና ታማኝ የሆኑ ወንዶች መኖር ሲችሉ ይመስለኛል።

የትርሲት ሀሳብ ትክክል ነዉ መስቀል አደባባይ እና ጃንሜዳ ለተመቱት ሆስፒታል ሊሰራ ነዉ ወይ ያለችኝ ብቻየን እያሳቀኝ ነዉ😁

💠 Comment ➋
እናልህ የፅሁፉ መደምደሚያ ላይ አሁን አንተ የለቀቅከውን አይነት ፅሁም አለው ማለት በድንግልና ምክንያት እህቶቻችን ከፍረው እያገቡ እንደሆነ እና ሙስሊም ወንሶች እባካቹ ለደም አትሩጡ ደም ከሆነ ፍላጎታቹ ዶሮ እረዱ ምናምን ይላል እና አንብቤ ስጨርስ አመሰግናለው ብዬ መለስኩ ከዛልህ ልጄ መልሶ አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው አይነት ነገር አለ ይሄን ፅሁፍ አላምንበትም አለኝ እንዴት አልኩት ይሄ ቢክራ ያሎኑ ሴቶች የፈጠሩት ውሸት ነው አላህ ሁሉንም ሴት ቢክራ አድርጎ ነው የፈጠረው እነዚህ ሲግማሙ ከርመው የፈጠሩት ማስተባበያ ነው አለኝ ወላሂ ነው ምልህ ጠላሁት።በርግጥ የሚያወራው ወሬ እኔን አይመለከትም አስተሳሰቡ እንዴትም ሆነ እንዴት እኔ ድንግል እስከሆንኩ ድረስ አይመለከተኝም ነበር ግን አልቻልኩም ወላሂ ጥያቄ ማከታተል ጀመርኩ ቆይ እነዚህ ችግሮች ተጋብተው አንዱ እኔላይ ቢፈጠር አታምነኝም ማለት ነው አልኩት በፍፁም አለኝ አሁንም ቀጠልኩ እሺ ዚና ሰራሁ ይባል እና ተፀፀትኩ ተውበት አደረኩ እንኳን አንተ አላህም ይምረኛል እና ያኔም እሺ አትልም አልኩት በፍፁም አለ።እሺ እኔን ተወኝና ሌላ ሴት ብታገባ ያቺ ሴት በህፃንነትዋም ይሁን ትልቅ ሆና ተደፍራ ቢሆንስ አልኩት እስዋን አላህ ይድረስላት እኔ ግን አላህን ተጠብቄ እንደቆየሁት የተጠበቀችዋን እንዲሰጠኝ ነው አለኝ ወላሂ ስበብ ፈልጌ ተውኩት ተምሮ እንሳልተማረ ድፍን ቅል ሰው ምን ያደርግልኛል ብዬ ተውኩት ብዙ ለመነኝ አሁንም ድረስ ለደቂቃ ሊያጣኝ ባይፈልግም ግን በቃ እኔ ወጣልኝ

💠 comment ➌

አሰላሙአለይኩም
የተነሳው ሀሳብ እጅግ ጠቃሚ ግን በጣም የተረሳ ወሳኝ መወያያ አጀንዳ ነው።ብዙዎቻችን እራሳችንን ከመውቀስ (self criticim) ይልቅ ወደ ሰዎች ጣታችንን መቀሰሩ ልማድ አድርገነዋል ለህቶች መበላሸት ዋናው ወንዶች ነን።ከሴቶችም ጋር ጥፋት የለም እያልኩ አይደለም አለባበሳቸው እንኳ ፋሽን ሾው ያለባቸው መስለው ነው የሚወጡት ሌላው ቀርቶ በኢድ ቀን ያውም ለሰላት ያንዳንዶች አለባበስ አዑዙቢላህ
ሌላው high school ሲገቡ new life የነሱ ሙድ ነው ከሳቀላቸው ጋር መገልፈጥ
ዩኒቨርስቲ ላይ ደግሞ ከዚህ የባሰ ማመን የሚከብድ ነገር ታያለህ ለዚህ ም ስክር ግቢ የተማረ ያውቀዋል
ዩኒቨርስቲ እንኳን ለጃሂሉ ለቀራውም ከባድ ቦታ በሁለት ሸይጧን የሚያስከብብ.............
የራሴም ተሞክሮ ስላለኝ ነው የጤና ባለሙያ ነኝ ግቢ እያለሁ ሆስፒታል አፓረንት ስንወጣ የግቢ ልጆች ለማስወረድ ሆስፒታል ይመጡ ነበር አንዳንዶችማ ግቢ ሲያዩን አፍረው አንገት የሚደፉ ነበሩ።
ወሬ አላብዛ በሀሳብህ ተስማምቻለሁ።
እራሳችንን እንሁን


በሀሳብህ ስስማማ አንድ ውሳኔ ወሰንኩ
ለመተዳደሪያ የመንግስት ሰራተኛ ነኝ
ምሳሌ አድርገህ ካቀረብካቸው የእውነት ቶብተው ከሆነና የማግባት ፍላጎት ካላቸው አንዷን ለማግባት ዝግጁ ነኝ
አብዱረህማን ነኝ ከደሴ ከተማ

ያጀሊሉ እንደ አብደረህማን ያለ ወንድ አብዛልን😍

💠 Comment ➍
አሰላሙአለይኩም
አሚር ከአድናቂዎችህ ውስጥ ነኝ ያው በብዙ ሀሳቦችህም አልስማማባቸውም ቢሆንም ግን ያው አድናቆቴን መደበቅ ግን አልችልም፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ ቢክር ያልሆነች ሴት ስታወራ የሚደርሱህን commentየኔም ችምር ናቸው፡፡ጥሩ ከመመኘት ይመስለኛል ይህን ምትናገረው፡፡ሀሳባችሁን አጋሩኝ በማለትህ ደስ ብሎኛል፡፡ ስለ ባህሉ ያልከው ወላሂ መጥፎ ባህል ነው ከኢስላም መራቃችንም ማሳያ ነው ምክንያቱም መምታት የግል መብታቸው አረጉት ሀዲሱ ቀጥቅጡ አይልም ብዬ አስባለው እስከ ማውቀው የለም፡፡ሲጀመር ከወላጅ ጀምሮ ሴት የወንዶች አሻንጉሊት እንደሆነች እንድታስብ ተደርጎ ነው ምታድገው፡፡ሲቀጥል ደግሞ አብዛኛው አሊም የሚባሉ ሰዎች ሴሰኞች ናቸው(ይቅርታ ግንእውነቱ ይሄ ስለሆነ ነው) ፡፡ እኔ በምኖርበት አካባቢ አንድ ሀፊዝ አለ እና ቁርአን ያስቀራናል እና ጅልባብ እንድንለብስ ይነግረናል እኛ ደግሞ እያሰብንበት ነበር በመሀል ግን ኡስታዙ ያልሆኑ ነገሮችን ማድረግ ጀመረ ለምሳሌ ከወንዶች ፈረቃ መቀየር ጥሩ አስቦ እንዳይመስልህ😜ሚያወራው ሁሉስለ አራት ሚስት ነው ፡፡ አስበው ባለትዳርና የልጅ አባት ነው፡፡ለአስራ ምናምን ልጆች ነው እንዲ ሚለው አስበው ተምራ ምንም አትፈጥርም እያለ ነው፡፡ በመጨረሻ ለየብቻ ላስቀራቹ 😳ምን ለመሆን?ገብቶሀል አ በስልክ መጀናጀን ምናምን normalነው፡፡ እኛ ደግሞ አንሄድም ስንል ቁርአን አትወዱም ምናምን ተባልንግን ተውን አመት ሳይሞላ ሚስቱን አባሮ ሌላ ሴት አመጣ ሲቀጥል ከሌላ ሴት ደግሞ(ከካፊር)በሀራም ወለደ፡፡አስበው ኡስታዝ ነው ካፊር ወንዶች ብቻ አይደለም ሙስሊሞችም አሉበት፡፡
ደግሞ ሙስሊሞች ብቻ አይደሉም ቢክራሚፈልጉት፡፡በቃ በሴቶች ብቻ አድፍረዱ መጀመርያ አለምን መቀየር እንደሚችሉ እንዲያስቡ ማድረግ ቢቻል ሀሳባቸውን መበተን👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አይኩም ወላሂ ተመልከቱ ብዙ አስተያየት ተቀብያለሁ የዚህን ግን መቋቋም አቋተኝ😭


ወንድሜ አሚር የአላህ ሰላምና እዝነት ባንተ ላይ ይስፈን....
ቢክራ ከምን መጀመር እንዳለብኝ አላዉቅም ወላሂ እልሀለዉ ወንድሜ በዚህ ምክንያት 5 ሙስሊም እህቶቼን አጥቻለሁ 5 ከፈሩብኝ

ነገሩ እንዲህ ነዉ 5ቱም በአንድ መንገድ ግን በተለያየ ምክንያት ቢክራቸዉን አጡ.. የሀራም መንገድ አይዘልቅምና በሙስሊሙ ማህበረሰብ አንዲት ሴት ከአንድ ወንድ ጋር ከታየች ያቺን ሴት ለትዳር የሚፈልጋት የለም.... እናም አንድ እህት የጀመረችዉ መንገድ ልክ እንዳልሆነ ገባት ልጁም ከቆይታ በሗላ አገባሻለሁ ብሎ ቃል የገባላትን አፈረሰ ..እሷም ራሷን ተፀየፈች ለወራት ከሰዎች ተገለለች ነደም ፀፀት ምሬት... ጌታየ ዚናን አትቅረቡ ብለህ እኔ ግን ድንበርህን አለፍኩ ይቅር በለኝ አለች ይቅር ባዩ አላህ ነዉ ፀፀት ከልብ ከሆነ ዳግም ካልተመለሰችበት ወንጀልን በሀሰናት ቀያሪ ነዉ...

ከአመት ቡሀላ የትዳር ጥያቄ መጣ ግን ቢክራ ነሽ?
እሷም ሳትዋሽ አይደለሁም አለች ግን አሁን ሀላል ነዉ የምፈልገው አለችዉ
....... ሀሀሀሀ ማንም የተጫወተብሽን እኔ ምን እዳዬ ሲል ፎከረ....
እሷም ለካ አላህ ነዉ ይቅር የሚለዉ አላህ ነዉ ለካ የረሳላት ሰዉ ለካ አይረሳም ነዉርን አይሸፍንም......
ሌላም የትዳር ጥያቄ በተደጋጋሚ መጣ ሁሉም ቢክራ ነዉ ጥያቄያቸዉ፡፡
በዚህ ምክንያት ብዙ ትዳር ተመለሰ

እድሜዋ ሲሄድ ቆሞ ቀር መባልም አለ...በስራ አጋጠሚ ከአንድ ካፊር ወንድ ተዋወቀች ተቀራረቡ ወደዳት አከበራትም በሒደት ለትዳር ጠየቃት
.... እሺ አለች ግንድንግል አይደለሁም አለችዉ አቅፎ ሳማት እኔ የምፈልገዉ አንቺን ነዉ ያንቺን ደም አይደለም ያለፈዉ አልፏል አላት
እሷም የትዳሩን ጥያቄ ተቀብላ ከፍራ አገባችዉ..😭...

ወንድም እህቶች ከዚህ በላይ ምን የሚያም ነገር አለ??? የ5ቱም እህቶቼ መጨረሻ ይህ ነበር... ምናለ ሴት ሆኜ ባልተፈጠርኩ ብዬ አማረርኩ😭


አንተ ወንድሜ ሆይ ተዉ አላህን ፍራ ባንተ አስተሳሰብ ምክንያት ብዙ ሙስሊም እህቶቼን እያጣሗቸዉ ነዉ... አንዴ ለሄደ ቢክራ አሁን ከየት ታምጣዉ...? ተዉ እንጂ ወንድሜ ሁላችንም እኮ ከወንጀል የፀዳን አይደለንም ጌታችን አላህ የባሮቹን ነዉር ደባቂ ነዉና ደበቀልን እንጂ....

ወንድሜ አሚር ይህንን መልዕክት እንድታስተላልፍልኝ አማና እልሀለዉ ወሬ ስላበዛሁ አፍወን
ወላሂ ዉሽቴን አይደለም ከወሊሶ ከተማ ነኝ

አስተያየቱን አነበባችሁ? በጣም አሳዛኝ ነዉ እኔ አዉርቼ እቀራለሁ የተጣመመ አመለካከት አለህ ተብያለሁ ..ግን የዲን እዉቀት ጠልቆ ያልገባበት ቤት ከአንድ ቤት አምስት ሴት በዚህ ምክንያት ሀይማኖታቸዉን ቀይረዋል

አሁን ጥፋቱ የወንዶች ነዉ ወይስ ቁርአን ኪታብ ቀርቶ ዲነል ኢስላምን ያላስተማረ ነዉ? ወይስ ፋሽን ተከታይ ሁነን ዲነል ኢስላምን የረሳን ይሆን ? ወይስ ለሙስሊም የማይጠቅመዉ መጅሊስ ይሆን? ወይስ የሰፈሩ ነዋሪ እና በሰፈሩ ያለ ጀመአ ይሆን?
አንቺ ዲንሽን ለመማር በሄድሽበት ባመንሻቸው ሰዎች ክብርሽን የጣሽው እህቴ እንዲሁም ደግሞ ኑሮ ፈተና ሆኖብሽ እሱን ለማሸነፍ ደፋ ቀና ስትይ በግድ የታደፈርሽው እህቴ አሁን የለሽው በትክክለኛው በእስላም ጎዳና ከሆና ወለሂ ቢላሂ ብዬ መነገር እችላለሁ ለኔ ድንግል ነሽ አተስቢ።
☝️ ወላሂ ብዙ ወንዶች ጋር ተመካከረን በሀሳብ ተግባብተን ቢያንስ 98% ተማምነናል ወንድም ሴቶች በመወያየት እመኑ ሀሳቡን ተደራሽ አርጉት ፡፡ አስተያየት እንዳይበዛ ብየ ነዉ እንጂ ብዙ የቻናል ቤተሰቦች ወንዶቹ አላህ ይዉደዳችሁ በሀሳቤ ተስማተዉ ሴቶችን ለመረዳት ዝግጁ ናቸዉ

⭕️ ይህ ሀሳብ ሁሉም ሰው ተወያይቶበት መፍትሄ ሊያበጅለት የሚገባ ሀሳብ ነው ከላይ የጠቀስከው ሀሳብ ግን በአሁን ሰአት ውጤት ያመጣል ብዬ አላስብም ምክንያቱም እነዛ በአከሌ ነው የተደፈረኩት የሚሉ ሴቶች እንዴት ይታመናሉ? በረግጥ በተጨባጭ እየተደፈሩ ያሉ ብዙ ሴቶች አሉ ነገረ ግን እየደፈሩ ያሉ ሴቶች መኖራቸውም የማይካድ እውነት ነው 🙈🙈 ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ የአበዛኞችን ሴቶች አለባበስ ብናይ ከቤት ሲወጡ ተቀባብተው ተውጣጥረው መሄድና ወንዶችን መፈታተን እንደ ትልቅ ነገረ እየታየ ነው ስለዚ አላህ ይጠብቀንና በተቻለን አቅም ራሳችንን መጠበቅና አለባበሳችንን ማስተካከል አለብን ይህን ካደረግን በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ማለት ነው .ደግሞም ታሞ ከመሳቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ ይላል የሀገሬ ሰው!!! ለዚሁሉ ደሞ መፈትሄ ሊሆን የሚችለው አንድ ነገረ ብቻነው እሱም ሁሉም ሰው ሀይማኖቱን ካወቀና መመሪያውን ከተገበረ ብቻና ብቻ ነው b/c ሁሉም ሰው ፈጣሪውን ፈርቶ መተው ካልነ በስተቀረ ሰው ምን ይለኛል ብሎ እኳን ወንጀልን መራቅ almost ቀርቶአል ማለት ይቻላል በተለይ ደሞ ከተማ ላይ 🤦‍♀🤦‍♀
በተርፈ አላህ እንደ ወንድም አብድራህማን ያሉትን ጨምሮ ጨማምሮ ያብዛልን
☝️አሁን ወንድ ብቻ ሳይሆን ሴቶችም እየደፈለ ነዉ ያለችዉ ወላሂ ትክክል ናት ሴቶች ሆይ ደጋግማችሁ አንብቡት

⭕️ አሰላሙአለይኩም አሚር እንዴት ነህ በባህሉ ዙሪያ አስተያየት ለመስጠት ፈልጌ ነው እና ባህሉ በጣም ጥሩ ነው እኔም የገጠር ልጅ ነኝ የተወሰነውን አቀዋለህ በተፈጥሮዋ ድንግል ባትሆን ላልከው ቤተሰቦቿ ድንግል አለመሆኗን ገና ህፃን እያለች ያውቃሉ የቤተሰብ በግልፅ አለመቀራረብ/አለመወያየት በልጆች ላይ ትልቅ ችግር እየፈጠረ ነው ሴቶች ስለድንግልና ሳናቅ ድንግልናችንን ወደማጣት እየሄድን ነው ሌላ ችግር የምለው ስልጣኔ/ድሞክራሲ የሚባል ነገር የገጠሩን ማህበረሰብ በጣም እየጐዳን ነው ም/ም ድሞክራሲ/መብት እየተባለ አባት ልጆቹን መቆጣጠር/መቆጣት እስከማይችልበት ደረጃ ደርሷል

ሁሌም የምትለቀውን ታሪክ አነባለሁ በጣም አስተማሪ ነው
☝️ አያችሁት የገጠሩ ባህል ቤተሰብ ጋር ሴት ልጅ በነፃነት ታወራለች ማለት ነዉ፡፡ ይሄዉ ባህሉን የምታቀዉ አስተያየት ሰጠችን

⭕️ ስም : ኢልሀም ☞ ኮምቦልቻ ከተማ

በመጀመሪያ ያነሳኸው ሀሳብ በጣም ጥሩ ነው እናም ያንተን ሀሳብ እጋራለሁ
1. ያልተመቸኝ ነገር ሴትም ሆነች ወንድ የሚመቱበት ነገር ምክንያቱም ሴቷ ለምሳሌ በተፈጥሮ ያጣችው ነገር ሊሆን ይችላል እና ስትጠየቅ ግርፊያውን ፈርታ ወይ ቢክራዋን ያልወሰደውን ሰው ልትናገር ትችላለች ይህ ማለት ግን የማታቀውን ሰው ሳይሆን ወይ የድሮ ጓደኛዋ ሊሆን ይችላል ወይ ደሞ እንዳልከው የተጣላችው ሰው ሊኖር ይችላል በዚ ሰአት የማያቀውን ሰው አስመታች ይህንንም ከፈራች ደሞ ራሷ ልትገረፍ ትችላለች እና ይሄ አልተመቸኝም ።
2. ደሞ ወንዶች ይሄን ጥያቄ አቁሙ ይደብራል ቢክራ መስፈርት ይሆናል ብየ አላስብ ምክንያቱም ሴትን ልጅ ቢክራ ብትሆንም ባትሆንም እንደዚ ብሎ መጠየቅ ያሳቅቃታል የሚያሳቅቀው ደሞ ለምን እንደሆነ ታቃለህ ልጅቷ ብትሆን እንኳ ነኝ ማለት ያስፈራታል ምክንያቱም በኋላ ላይ ድንገት በተፈጥሮ ላይኖር ይችላልና ለመመለስ ያሳቅቃታል
3.ትምህርት ጠቃሚም ነው ለ አንዳንድ ሴቶች ደሞ ጎጂ ነው እኔ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ ብዙ ልጆችን ሳይ ግን እኔም ትምህርት ሴትና ወንድ ተቀላቅሎ መማር የለበት ብያለሁ እንደውም ከጓደኞቼ ጋር ነበር ያወራነው በዚ በጣም የሚደብር ነገር ነው የሚመጡት እኩል ከተማሪ ጋር ሊማሩ ግን የሚውሉት...... እና ለአንዳንዶች ጉዳቱ ይህ ነው ነገር ግን ራሳቸውን አውቀው እና ጥንቁቅ ሆነው ለሚማሩ ደሞ መጠቀሚያ ነው ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበዛል
እና ደሞ ከሀራም ለመራቅ ዲናችንን እናጥብቅ ጓደኛም እንምረጥ እላለሁ አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን
☝️ ኢልሀምን ጠይቂያት ነበር ኮምቦልቻ አህባሽ ሴት ወንዱን አጃጅሎታል አንቺ እነሱ ቀጥተኛ መንገድ እንዲጓዙ ምን ስራ ሰራሽ ብየ ጥያቄየ ነበር እንዲህ አለችኝ
☞ተስፋ ቆርጩ ትቸዋለሁ ጀምአ መስርተን ገና ግቡ ስለኢቂዳ ሳይሆን ስለአጂ ነብይ ግኖኙነት እንመካከር ብላቸዉ መዉሊድ አክባሪ ነሽ አይደለሽም ሲሉኝ አይደለሁም ብያቸዉ ሀሳቤን ሊስማሙ አልቻለሉም ሴት ወንዱ ትምህርት እያለ ሲጃጃል ነዉ የሚዉለዉ ፡፡ አህባሾቹ ከኒካህ በፊት እንደፈለጉ ይገናኛሉ የወደፊት ባሌ ሚስቴ እየተባባሉ ..እባካችሁ ለዲነል ኢስላም የምታስቡ ዳኢዎች ኮምቦልቻ ላይ ብዙ መሰራት ይቀራል፡፡
አላህ እድሜዉን ያርዝመዉ የነሳዳት ጀመአ ኮምቦልቻ ላይ እየተንቀሳቀሱ የተወሰነ ለዉጥ እያመጡ ነዉ

⭕️ As wr wb....ene malet emifelgew neger red blood cell ende mesfert mekemetun kewendoch antsar bicha mayeth new, ene gn gdeta mehon alebet by negn miknyatum Allah yaskemetew mesfert kehone setochu enditebku bemetazezu yewendochm bicha syhon setuam yetdar mesfert new bla mamen alebat yihen demo yalkut hulum setoch sijajalu new yatut eyalkugn syhon tetalew yesetu or tegedew or besra chana atewut yhonal yihenen demo meredat ena mekebel wendochm ly gdeta new gn Allah yaskemetewun ena enditebkut yetekemeten neger mesfert atargut malet eko setochye feta blachu zemutu keza tetalye new tlalachu so yehone mamlecha ber lezina ykefetal malet new....demo endalkew tetalye new yatahut lemilew neger ewunet eski set lijn aydelem 10, 11, ena college dres yetemarut ykrna tach edme ly hunew sledinachew yaweku enkuan tetalelku Emil neger endemknyat aykebeluhm, eski asbew hajnebiy mechebet emikelekln himanot yzew, film ly yewend lijn bahry eyaweku, libweled eyanebebu, yesewun temokro eyesemu byans byans enatachew mitmekrachewun mastawes eyakatachew mekuakual ena me wend ga melalatn ende zemenawinet emikotru setoch👇👇
kegize buhala endemyders ena endemyfelgut eka ashkentrew ketalu buhala tetalye new zimut wust yegebahut mn yahil yasamnhal anten erasu....alga yzo, abrew condom sigezu, abra metet bet sitgeba kalnekach engdi yaw awuko yetegna bikeseksut aysemam new mihonew....mn malet felge new "tetalew new yatut and neger new gn demo mesfert atargut malet keallah kal wutu endemalet new , metsetsetm demo and neger new keza buhala betdar wust mn yahil metemamen ynoral lela guday new. Kezi beterefe gn Allah endalew tiruwoch setoch letruwochu wendoch yetegebu nachew wendochum endezaw, slezih ewunet ketetsetsetech ena tru set lehonech emiyasasbat neger aynorm "
☝️እንደዚህም ያሉ አስተያየቶች አሉ ..ግን እስኪ ሚዛናዊ የሆነ አስተያየት በሚል ይያዝ

⭕️ :-bahlu tkkl bayhonm gn tru gon alew wendoch zina endayseru yadergachewal biyans dula lemifera wend😁 mknyatum beahun seat bzu setochn kabelashu buhala dngl kalagebaw yemilut enesu mknyatu yenesu dnglna slemayastawk😏 gn dnglana yetdar mesfert aydelem resulachn (aleyhi selam) erasu ke 11 mistochachew wst bikr yagebut 1 bcha nat 10 seyb(agbtew yefetu) neberu wendoch bikrawan yatachbet mknyat kalat lireduat aliyam tewbet adrga kehone likebelat ygebal
Setochn betemelekete gn bemejemeriya lewendoch egna fit banasayachew bansklachew banawarachew yann dereja aydersum allahm yalew zinan atsru sayhon zinan atkrebu new mengedun kamechachenlachew buhala ya mefeteru midenek aydelem hijabuan tebka yemthed set yetgnawm wend aydaferatm hijab sidenegnn allah subhanehu wetealam bluan nikab endilebsu ezezachew kalabuhala asketlo tbuk mehonachew enditawekna aza endaydergu sibal new ylal gudletu kegna new egna setoch erasachnn enfetsh wendochm endewza
Afwen bzu aweraw
☝️ለወንድ ዱላ በመፍራት ያልሽዉ አዎ ሀቅ ነዉ፡፡ ነብዩ ሰዐወ ከሚስቶቻቸዉ ቢክራዋ አንድ ብቻ ናት ላልሽዉም ትክክል ግን ሌሎቹ ሚስቶቻዉ ባሎቻቸዉ የሞቱ ወዘተ ናቸዉ በሀላል የሄደ ነዉ እናም ይህን ብለን ሴቶች እንዳንዘናጋ ያህል ነዉ

⭕️ አሰላሙ አላይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ ወንድም አሚር አላህ ከይር ጀዘአን ይክፈልህ
በጣም ወሳኝና አስታማሪ ፁሁፍ ነው የሚትፁፈቸው አሪፍ ነው፡፡ብዙ እህቶች አስተያየት እየሰጡክ ነው ስለ ቢኪር ደም ብቻ አይደለም ክብረ ንፅና ነው እንደ ቀለል መተያት የለበትም
አላህ ስለ ክብራቸው በቡዙ ቁርአን አያዎች ለይ አውስቷል፡፡ እንደ እኔ የልቀራ ጃሂል ሰው በእስልምና ምንም ቦታ የሌላ እንደይመስለቸው ሴት እህቶች በዚህ ዙርያም የተወሰና ነገር በለቸው

ወንዶችም አንድ ነገር ማወቅ የለብን ነገር ቢኖር
ባለማቅ የተሰሳቱ እህቶች ጥርት የለ ተዉባ ከደረጉ አህላቀቸው ጥሩ ከሆነ ከወደዷት ቡሀላ
ለቢክሯ ብቻ ብሎ መራቅ የለበትም፡፡ እህቶቻችን ላሌላ አሰልፈን መስጣት የለብንም
እህቶቻችህም ክብራቸውን መጠበቅ ግዴታቸው ነው ፡፡

አሚር ሀሳቤን ትረደኛለህ ብየ ተሰፋ አደርጋለሁ
ሴት እህቶቸችን በዙጊዜ አህለቀቸው አለበባሳቸወ
አንገጋራቸው ላይ አይነአፋርነት ጠፋ።

ከወንዶችም በላይ ወዳ ዚና እየሩጡ ስለሆነ
የዚና በር በሴቶች ምክንያት ብቻ እንዳይከፈት በጣም እሰጋለሁ
ከዚህ አስተየያት ተነስተን እረሳቸውን እንዴት መጠቅ እንደለበቸው ምክር ለግሳቸው
አፉወን ወንድሜ
ለአላህ ብዬ በጣም እወደለው።
ከይር ጀዘአን አላህ ይክፈልህ
☝️ ይሄ አስተያየት ትክክል ነዉ ለምን አሁን ላይ ሴቱ ነዉ እየጀነጀነ የራሷን ስጋ በሀላፊነት ቆርጣ ለዉሻ የምሰጠዉ ዉሻ ስጋ ቀለቡ ነዉ ታዳ ምን ይደረግ ግን ለዚህ ሁሉ ጥንቃቄ 90% ሴቶች የራሳችሁ ጥረት ያስፈልጋል

⭕️ የመጨረሻ መደምደሚያ comment
አላህን ፍራ ወላሒ ድንበር እያለፍክ ነው‼️ ትናንት እና ዛሬ በፃፍከው ፅሁፍ ምክንያት በዚህ ሳምንት ስንት እህቶች ቢክራነታቸውን እንደሚያጡ ብታውቅ ራስህን ትጠላ ነበር። በዚህ ከጩልሌ የፈጠኑ አፈቅቤ ወንዶች በበዙበት ሰአት ሰሞኑን የለጠፍካቸው አስተያየቶች ጧት ማታ በነዚህ ጩልሌ ለሚጨቀጨቁ ሴቶች "ቢክራ አለመሆን normal" ስለሆነ የልብየልብ እየሰጣሀቸው ነው። dop ለሚባሉት ኢማንም እውቀትም ለሌላቸው ባለአጭር ጉርዶቹን ለትዳር ሲሉ የመክፈር አማራጭ እንዳላቸው እየነገርካቸው ነው። አንተ እንደምትለው ያክል አሁን ላይ ያሉ ሴቶች ለቢክራነት ስለማይጨነቁ በጣም እንዲጠነቀቁ ነበር መስራት ያለብህ ። " ጤፍ አትቆጥሪበትም ስጪው" እያሉ የሚመክሩ ሙስሊም ሴት እህቶች እያሉ....
በሰርጎ ለት ማታ "ድንግል አይደለሽምሳ" ሲላት "እስኪ በባትሪ ፈልገው!" የሚሉ ሴቶች ባሉበት ጊዜ አንተ "እንደ መስፈርት መታየት የለበትም" የሚሉ ሴቶችን ሀሳብ ትለጥፋለህ!? አላህን ፍራ‼️
እኔ ግን ምናልባትም የተፈታች ሊሆን ይችላል የማገባው አንተ አሁን እንዳሰብከኝ አይደለሁም...
From AASTU
☝️የኔም ጥያቄ
መርሀባ ወንድሜ አላህን ፍራ ስትለኝ ቀጥ ብያለሁ
ግን ሀሳቦችን ከላይ ጀምሮ አይተሀቸዋል?
እንዴት ይሰራል ዚና ብለህ እርግጠኛ ሆንክ?
የእሱም መልስ👇

ወላሒ መሀል ላይ ሁኜ ለማየት ሞክሪያለሁ። ሌላም ሠው አስገምግመው እና ትነግረኛለህ። አሁን ላይ ከማገኛቸው informationoch አቦዘሀኞቹ ማለት ይቻላል ወደፊት ምን ሊደርስባቸው እነደሚችል እያወቁ አንዳንዶቹ አራዳነት እየመሰላቸው የሚያስወስዱ ናቸው። ስለዚህ "ተውበት ካደረገች....ወደአላህ ከተመለሰች...ደም ምን ይሰራለታል...ይሄንን ነገር እንደቅድመ ሁኔታ የሚጠይቁ ወንዶችን ከካፊር ወንዶች እንደማይሻሉ ..."እና ሌሎችንም የሸይጧን ሽንገላወችን የምናቀርብላቸው ከሆነ ከሸይጧን በምን ተሻልን! ሀራም ላይ የመውደቅ እድላቸውን እያሰፋንላቸው ነው ምክንያቱም "ብዙዎቹ" የሀራም ጫፍ ላይ ሁነው ልስራው አልስራው ብለው እየተወዛገቡ ነው የሚሠሩት።

ምን ይባላል ለሁሉ ፈትዋ አይሰጥ 😊 በሉ comment በቂ ነዉ

🙏🙏 ዉድ የተከበራችሁ የቻናል ቤተሰቦች ከ1000 በላይ አስተያየት ተቀብያለሁ ዋናዉ በቻናል መፓሰቱ አይደለም በሀሳብ ተግባብተን ሁላችንም አስተምራችሁኛል እኔም በማቃት ትንሽ አስተምሪያለሁ እና ለወደፊት ብዙ መስራት እንዳለብን ያሳያል፡፡አዉፍ በሉኝ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም የተከበራችሁና የተወደጃችሁ የቻናል ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ

በዚህ ሰሞን በምንወያይበት አጀንዳ ላይ የሚገርም ነገር ገጠመኝ ፡፡ ትናንት ያዉ ተወያይተን ሴቶች ከቶበቱ ቢክራ መስፈርት አናድርግ በሚል ብዙ ተጨቃጨቅጨን ተወያይተን ተግባብተንም ሳንግባባም ግን በሀሳብ ማዕበል አዝንበን ነበር
ግን የሚገርመዉ ዛሬና ትናንት ያልጠበኳቸዉ አስተያየት ከሴቶች በዛብኝ..ቢክራ መስፈርት መሆን መቻል አለበት ብለዉ ብዙ ሴቶች ምክንያታቸዉን ደርድረዋል፡፡
መስፈርት አይሁን እያልክ ብዙ ሰዉ አታጥም የሚልም በዝቶ ነበር፡፡ ሀሳቤን በደንብ ያለመረዳት ችግር ይሆናል እንጂ እኔ ቢክራ መስፈርት አይሁን ብየ ሙሉ በሙሉ አልሰጠሁም፡፡ እኔ ያልኩት ጠቅለል ሲደረግ
☞በልጅነታቸዉ ለተደፈሩ
☞ በድህነት ተሰቃይተዉ ላደጉ
☞ለገጠር ልጆች ለምን የዲነል ኢስላም አስተምሮ ስለሌለ
☞ ሰለምቴዎች
☞ የከተማ ልጅ ሁኖ የዲኑል ኢስላም እዉቀት ለሌለዉ ግን ከተማ ተወልዶ ያደገ 90% ዲነል ኢስላምን ያቃል አዉቆ አጥፊ ነዉ👌

☞ አሳማኝ ምክንያት ላለዉ ወንዶች መጀመሪያ በመረዳት እንዚህን የተከበሩ እንስቶች እንጠብቃቸዉ ነዉ፡፡

💠ግን ከሁሉም የአጀበኝ የዚች እህቴ አስተያየት ነዉ👇
አሰላም አለይኩም አሚር እንዴት ነህ
ብዙ የምትለቃቸዉን ፀሁፎች አነባለዉ በብዙ እስማማለዉ በተለይ ወንድ እና ሴት አብረዉ አይማሩ በሚለዉ ጎበዝ ተማሪ ካልሆነች ትዳር እስክታገኝ እናቷን ታግዝ ያልከዉ በአሁን ሰአት ቤተሰቦች ልጄ ጎበዝ ተማሪ ናት ሜካብ አይቀራት እያሉ ሲያወረዉ ይሰማል ግን እቺ ልጅ ሜካብ ብላ ወጥታ ትምህርት ቤት ምንን እንደምታደርግ ማየት ያሰጠላል በፈተና ሰአት ከጎበዝ ተማሪ ኮርጃ አሪፍ የሚባል ዉጤት ታመጣለች ለቤተሰቦቿ ትሸዉዳለች አይህ አሚር ጎበዝ የምትባለዎ ሴት ተማሪ በመትፎ ጓደኛ ምክኛት ትበላሻለች ላይበረሪ ስትል ባክሽ አንቺ ደሞ ቡሃላ እናነባለን እያላት እንዳታነብ በሌላ ወሬ ለምሳሌ
ስለፍቅር አላፈቅርም አላማዬ መማር ነዉ ስትል ፋራ ትባላች፡፡ ባይገርምህ እኛ ትምህርት ቤት ሶላት ልስገድ ስትላቸወ እራሱ ምን ኡስታዝ ኡስታዝ ያጫዉትሻል እኛም እኮ ሙሰሊም ነን እያሉ የሰላትን ጣአም የሚያጠፋ ልጆች አሉ
ሂጃብ አያምርብሽም አጭር ቀሚስ ነዉ ሚያምርብሽ እያሉ ከዲነል ኢስላም የሚያወጡ ሙስሊሞች አሉ
ከአጂ ነቢ ምንም አይነት ግኑኝነት አልፈልግም ስትል አታካብጂ ቀለል አርጊ ተዝናኚ አትጨናነቂ በጊዜሽ ተጫወቺ መች ልትጫወቺ ነዉ ትምህርት ሰላት ቁርአን እያለሽ እያሉ ከዛ ከአንድ አጂነቢ ገር ጓደኛ እንድትን አራዳ ሁኚ ፋራ እያሉ ወደ ዚና የጠራሉ ከዛ እቺ ልጅ እርድና ይመስላትና ዚና ላይ ትወድቃለች
ወንዱ ደግሞ በተራዉ ፍቅር እስኪይዛት ይለምናትና ፈቅር እንደያዛት ሲያዉቅ የምትወጂኝ ከሆነ ድንግልሽን ስጪኝ ይላታል እና እሱን የምታገኝ መስሏት ስህተት ትሰራለች
በአሁን ሰአት ሀይስኩል ላይ ድንግል መሆን ብልግና ነዉ እያሉ ነዉ ያሉት

ወላሂ ነዉ ምልህ በጓደኛ ምክኛት ሂወታቸዉ የተበላሸ ብዙ ልጆች አቃለዉ በዲናቸዉ በትምህርታቸዉ ጠንካራ የነበሩ አሁን ዱርዬ ተብለዉ በየመንገዱ ከአጂ ነቢ የሚላላጡ ብዙ አሉ

ድንግል መሆን ለትዳር መስፈርት ሊሆን አይገባም ነገር ግን አንተ አሚር ሴቶች ዚና ለይ እንዲወድቁ እየረዳሀቸዉ ነዉ፡፡ በጊዜዬ ተዝናንቼ ለማገባዉ ባሌ እዋሽዋለሁ ለምሳሌ ተደፍሬ .ተታልዬ ምንምን እያሉ መዋሽት ይችላሉ

ያንተ ምክር ሊሆን የምገባዉ እንዲጠነቀቁ እና ደንግለቸዉን እንዲጠብቁ ከመትፎ ጓደኛ እንዲርቁ ከተሳሳቱ ወደ አላህ እንዲፀፀቱ ዳግመኛ እንዳይመለሱ መሆን አለበት ባይ ነኝ
☝️☝️ሌሎችም አስተያየቶች አሉ ከሴቶች ወላሂ ማመዛዘን ነዉ የከበደኝ

ደግሞ አንድ ወንድሜ የላከዉን ጀባ ልበላችሁ

አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ።
~የሰሞኑ ፖስቶችህና ኮሜንቶቹ ከማንበቤ በፊት፦
ኢንሻላህ ለማግባት ባሰብኩ ጊዜ ዒማንዋን አይቼ ቤተሰቦችዋንና ጓደኛችዋን አጥንቼ እንዲሁም እውቀትዋ ገምግሜ 2ረከዓ የኢስቲኻራ ሰላት ሰግጄ ከተመቸችኝ፣ በቃ ማናገር then ሽማግሌ መላክ።ጭራሽ ስለ ቢክራ ጥያቄ ውል ብሎብኝ አያውቅም ነበር።እውነት ለመናገር የቢክር መመርመሪያ መሳሪያዬ ተጠቅሜ መርምሬው resulቱ ማንበብ ምችል አይመስለኝም፤ዝም ብሎ Rblood ማየት ከሆነ ቀላል ነው። ግን ከስራና ድካም በኃላ ሌላ ስራ አይከብድም☺️
~ከፖስቶችህ በኃላ ግን ስለቢክራ ብዙ አሰብኩ prerequisitነቱ ጥቅምም ጉዳትም እንዳለው አመንኩ፤ግን ይህ ጥሩ ነው፣ያ መጥፎ... ማለት አልፈልግም። ምክንያቱም መጀመሪያ እስልምና ምንድነው ያለው ማለትን ማስቀደም ትክክለኛነት ነው። ነገራቶች የምናይበት መነፅር እስልምና(ቁርአንና ሀዲስ በደጋግ ቀደምቶች አረዳድ) ይሁን።አድርጉ ተብለን ከሆነ በቃ ምን አለፋን ለኛ በጣም ጠቃሚ ነው፤አታድርጉም ከሆነ አለማድረግ ነው።የአላህ ድንጋጌ አቅርቦ እስቲ ጥሩ ወይስ መጥፎ ተወያዩበት እስኪ ማለት ከባድ ጥፋት!!(አንተ አልክ ማለቴ አይደለም) አላህ ያልደነገገውን ነገር ደንግጎ ደሞ ጥሩ ነው ወይስ መጥፎ ማለትም ሌላ ጥፋት!! የእስልምና አስተምሮ ተከታዮቹ በስህተት ተረድተውት ከሆነም በማስረጃ ተሳስታችኃል እንደዚህ ነው መረዳት ያለባችሁ ብሎ ማስረዳት ነው እንጂ ውይይት አያስፈልገውም ምክንያቱም ሀቅ 1ድ ብቻ ነው። ተቃራኒ commenቶች አንብበን የማን አቋም እንያዝ?
ብቻ እኔ በሁለቱም መካከል ነኝ መወሰን አልቻልኩም ሌሎችም የተወዛገቡ ወይም የተሳሳተ አቋም የያዙ ስለሚኖሩ #ከቻልክ #በአላህ ይሁንብህ እንደ conclusion የሆነ ኡስታዝ ሰው በዚህ ዙርያ ሰፋ ያለ ትንተና እንዲፅፍ ጋብዝ፣ ከዛም ልቀቅልን pls. ጨረስኩ!!

ማሳሰብያ: ብዙ ሰዎች ቢክርዋ ሰጥታ የተፀፀተች ሲሉ አንዴ ቶብታ ፋይሉ የተዘጋ እያስመሰሉት ነው። የተውበቱ ተቀባይነት በምን እርግጠኛ ሆኑ? የሆነ ወንጀል ከሰራን እስክንሞት ወንጀሉ ባስታወስን ቁጥር መፀፀት አለብን እላለሁ።የሆነ ጊዜ ተሳስቼ ቢክራ ተብላ ከዛም ተፀፀትኩ አሁን ኖርማን ንፁህ ነኝ እንዳትይ፤አሁንም ተጸጸች።ኢንሻላህ ተቀባይነትም አጅርም ታገኛለሽ።



ወንድሜ በጣም እወድሃለሁ ብዙ ጊዜ ሃሳቦችህ ልኬ ናቸው፤ እንደውም ለወደፊት ሚስት አንተ ትፈልግልኛለህ ብዬ ነበር፤ አሁን ግን ሀሳቤ ቀየርኩ። ለራስህም ያልመረጥክ(ማለቴ finishing ላይ)😂 ደሞ ቢክር ያልሆነች መርጠህ ብታመጣልኝስ🙈
☝️☝️☝️ ይሄም ወንድሜ 360 ዲግሪ ነዉ የዞረበት😊 ፡፡ትክክል ነዉ በቁርአን በሀዲስ አንድ ዳኢ ቢያዘጋጀዉ የተሻለ ነዉ
በተጨማሪ ብዙ comment አሉ መጀመሪያ ተዉሂድ አስተምር ሌላዉ መወያያ ይደርሳል ያላችሁኝም አለ መርሀባ ተቀብያለሁ፡፡

እስኪ በራሴ አንድ ነገር ልበል ግን ይሄ ሁሉ ግፍ ሰዉ ወንጀልን ለምን አተንሾ ማየት ቻለብዙዉ ቁርአን ቀርቶ ኪታብ ቀርቷል ከጆሮዉ ሳያልፍ እንዴት ልቡ ላይ ጠብ ሳይል ቀረብለን እራሳችንን ስንፈትሽ
የዲነል ኢስላም እዉቀት ማነስ እና ባለዉ አመተግበር መልስ ይሆናል

💠የዲነል ኢስላም እዉቀት ማነስ ከምን መጣ ስንል ሰዉ ሙሉ በሙሉ ለዱንያ ለብልጭልጭ ነገር ጊዜ መፍጀቱ ነዉ፡፡ቀደምት ሱሀቦች ታብእዮች ዲነል ኢስላም አሁን ላለበት እንዲደርስ ሲታገሉ አልጋ በአልጋ ሳይሆን ብዙ ስቃይ አልፈዋል፡፡አቡ ሁረይራ ረዐ ብዙ ሀዲስ እንደዘገበ እናቃለን እንዴት ግን ከሱሀቦቹ በላይ ዘገበ ??ብለን ስንጠይቅ..አቡ ሁረይራ እዉቀትን ለመፈለግ ከነብዩ ሰዐወ ስር እየሄደ የእርሀቡ ብዛት ሆዱ ላይ በዲንጋይ ያስር ነበር👇👇
የእርሀቡ ብዛት ፌንት ድረስ ይጥለዉ ነበር
✿ኢማሙ ማሊክ ሲማሩ ብር አጥተዉ ደህይተዉ የቤታቸዉን ጣራ ሽጠዉ ነበር
✿አንድ ሰለፍ ስሙ ጠፋኝ አባቱ ግን ማህሙድ ይባላል እዉቀት ለመፈለግ የተጓዘበት ከመንገዱ መብዛት እግሩ ሺባ ሁኗል
✿አንዱ ሱሀባ ሲናገር እዉቀት ለመፈለግ በአሁኑ በkm 4000 km ተጉዟል፡፡ ኢትዮጲያ ከጫፍ እስከ ጫፋ 4000km ይሆናል ግን??
ኢማሙ አህመድ እዉቀት እስከየት ድረስ ነዉ ተብለዉ ተጠይቀዉ ከእናትህ ሆድ ወጥተህ እስከ ምትሞት ድረስ ነዉ ያሉት..
✿እነ አቡበር ስዲቅ ኡመር ወዘተ ዲነል ኢስላምን ሲማሩ ፀጉራቸዉ ሸብቶ ትልቅ ሁነዉ ነዉ ቢያንስ ከ38 አመት በላይ ሁነዉ ነዉ
✿ሸህ ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ አላገቡም ለምን አታገቡም ሲባሉ ቀንም አዳርም ዲነል ኢስላምን ስለሚማሩ የሚስቴን ሀቅ ላልወጣ እችላለሁ ብለዉ ሳያገቡ ነዉ የኖሩት፡፡አላህ ጀነተል ፊርዶስ ይወፍቃቸዉ
እኛስ ለዚህ ሁሉ እርስ በራሳችን ከምንወቃቀስ በእዉቀት ላይ ብናሳልፍ ይሄ ሁሉ ጣጣ ይመጣ ነበር ወይ??
አሁን ላይ ኪታብ ቀርተናል ብላችሁ የምታስቡ ሰዎች
☞የቀራችሁት ኪታብ ከሀራም ከለከላችሁ ወይ?
☞ኪታብ ሴቱም ወንዱም የቀራዉ ባለበት በሚኖርበት ከተማ ነዉ ፡፡የተመቸ ሀልጋ ላይ ተኝቶ የፈለገዉን በልቶ ጠጥቶ እሷም ቢሆን በልታ ጠጥታ የሀብታም ልጅ አቅሪ ተይዞለት ኡስታዙን ተሳድቦ ያከትማል ወላጅ ሆይ ቁርአን አቀራሁ ብለህ ታስባለህ?
በጭራሽ ዲነል ኢስላምን ለልጆችህ እንዳላወረስክ እወቀዉ፡፡ በተለይ የሸህ ቀርተዋል የተባሉ ሰዎች ልጆች ሲበላሹ እያየን ነዉ ቃልቻ ጡሌ እንጂ ልጅ አይወጣለትም😊 ተብሏል...ኡስታዞች ሸሆች የራሳችሁን ልጅ መቀየር ያልቻሉ እንዴት የማህበረሰብ ልጅ መቀየር ይችላሉ?

💠 በተማርነዉ አለመተግበር ደግሞ አሁን ላይ ያለንበት ነዉ ሚዲያዉ ቴሌቪዥኑ ወዘተ እያስተማረ ነዉ ግን ባዳና ቁንጫ በልቶ ሩጫ ሆነና ነገሩ ሁሉም አዳምጦ ከድጡ ወደ ማጡ ሆነ ታዳ መፍትሄዉ ምን ይሆን ? እኔም ግራ ገብቶኛል ጎበዝ

😎😎ወንድ ሆይ አላማህ ግድ ቀይ የደም ሴል ከሆነ አላህ የሁላቾንንም ዉሳጣዊም ዉጫዊም ቢያዉቅ .ግን አይተህ የሆነ የምትገነዘበዉ አለህ
የኢስላም አደብ አለባበስ የጠበቀች
ከያዘችዉ የሴት ጓደኛ
ከወላጆቿ የዲን አቋም
ከምትኖርበት ሰፈር
የኢልም ደረጃዋን ..በትርፍ ሰአቷ የት እንደምታዘወትር ማን ጋር ኪታብ እንደምቀራ
ጓደኞቿም የእሷ አይነት አቋም ካላቸዉ ለዲን ፍቅር ካየህባቸዉ፡፡
ወላጅ ጎረቤት ዘመድ ስትንከባከብ ካየህ
ይቺ ልጅ ከአላህ ጋር ይኖራታል፡፡ ካልሆነም መቼም ሸይጧን እንደ አጋጣሚ ከአሳሳታት ከተግባሯ አንፃር ወደ አላህ የተመለሰች ናት ማለት ነዉ፡፡ እነዚህ መስፈርት ከገኘህባት ቢክራም ሆነች አልሆነች ለአንተ መስፈርትህ ሊሆን አይገባም
መርሀባ ብሎ ጎጆ መቀለስ ነዉ😊

በተዘዋዋሪ ደግሞ አይተህ ቀይ የደም ሴል ያለመኖራቸዉ የማረጋገጫ ምልክቶች እነሆ፡፡ ግን ከነዚህ ከጠቀስኳቸዉ 10% ፐርሰንቱ ሊኖሬቸዉ ይችላል፡፡

ከ1000 ቲማቲም 900 ቢበላሽ ያዉ ሁሉ ተበላሸ ነዉ፡፡ ወይም እንደ ምሳሌ አባባሉ ከ100 ቲማትም 90ቢገማ ሁሉም ገማ ነዉ🙃 ነገሩ ፡፡ እስኪ ምልክቱን በከፊል አንተም ስታይ ልብህ ይነግርሀል
❖ ከኢስላም አለባበስ አደብ ዉጭ የሆነች እስከምትቀባዉ ኮስሞቲክስ የምትቀያይር አንተም ስታያት ዛሬ አመድ ነገ ጨዉ ከነገ ወዳ አሞሌ ጨዉ ምን አደከመህ 30 ቀን 30 መልክ ያላት 😊
አመት በሙሉ የተለያየ መልክ የሚፈራረቅባት
❖ የያዘቻቸዉ ጓደኞች ልክ እሷን የሚመስሉ ሁሉም ያዉ የስዕል መለማመጃ ደፍተር የመሰሉ ማለቴ ነዉ☺️
❖ የወላጆቿ የዲን አቋም ለዚሁ የቱርክ ልብስ ለኮስማቲክስ ብር የሚሰጡ ስለአለባበሷ የማይከታተሉ ከሆነ
❖የምትኖርበት ሰፈር ስትሄድ ሙሉቀን ሲጠጣ ሲጨፈር ሲወራ የሚዉል አጂነብይ ጋር ያለ ግንኙነቶች የላላ ከሆነ
❖የኢልም ደረጃዋ ደግሞ በቤተሰብ ተገዳ ኪታብ ቅሪ ተብላ አንዲት ኪታብ ይዛ ስታሾፍ ሙድ ስትይዝ ዉላ የምመጣ፡፡ በኪታብ መቅሪያ ሰአት የፈለገችበት የምዞር
❖ኪታብ አብረን እንቀራለን ብለዉ የሚሄዱ ጓደኞቾ እንደሷ አይነት ከሆኑ
❖እናቷ እቤት ስራ እየሰራች ደፋ ቀና ስትል እሷ መስተዋት ላይ ሙጥኝ የምትል ፡፡ በየመንገዱ ሲፎግራት የምትስቅ ፣ እንደሷ ያልሆኑ ስቶችን ፋራ አድርጋ የምትይዝ ከሆነ
❖የመኪና ሹፌር የባጃጅ ሹፌር ጋር አጉል ቅርርብ ሲሸኛት በተደጋጋሚ የምታይ ከሆነ
❖እማንም ወንድ ጋር በየመንገዱ የምትጋተት ከሆነ ፡፡
❖ እንደ ትራፊክ መብራት ቀይ አረንጓዴ ቢጫ እንደሚታዘዘዉ እሷም ያወራትን የሸኛትን የምትከተል ወይም በወንድ ምላስ Soft ware ተጭና በእሱ ስሜት ነበልባል ቁጥጥር ስር ከሆነች

አላማህ ቀይ የደም ሴል ከሆነ ከየት ታገኘዋለህ ወዳጄ😊 ያገበሀት ለትዳር ነዉ ከወደድካት ከነጎደሎዋ ማግባት መብትክ ነዉ፡፡ ግን ግድ ያ ነገር ይኑር ማለት በቆሎ ዘርተህ ጤፍ አጭዳለሁ ብሎ እንደመጠበቅ ነዉ😉
ሳር የሚገኘዉ ከመሬት ነዉ ከሰማይ አይወርድ ..ወርቅ አልማዝ የሚገኘዉ ከዉሀ ቆፍረህ ነዉ ከሰማይ አይወርድ ፡፡ ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል..ወይም ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ነዉ የሚሆነዉ እቅድህ ትዳር ከሆነ አግባት ግን ለምን ቀይ የደም ሴል የለሽም እያልክ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል፡፡ እንደ አንተ ያለ ሰዉ .መኖሪያ ቤት ለመግዛት እንደሄደ ምሳሌ ይሁን ...ከዛም ቤቱን አየዉ ጭራሽ አልተዋጠለትም አረ ብሬን እዚህ ላይ አዉጥቼ ከምከስር ባዶ ቦታ ገዝቼ ብሰራ ይሻላል ብሎ ወስኖ ባዶ ቦታዉ ላይ የፈለገዉን ቤት በተመቸዉ ዲዛይን እንደሰራ ይቆጠራል፡፡
ስለሆነም ከማግባትህ በፊት ምርጫ አለህ
➊ ዲን ያላት ?
➋ ዲን የሌላት የሆነችዉ ትሁን
ሁለቱ ነዉ ምርጫ ዲን የሌላት ከሆነች ከአገባሀት ቡሀላ ለምን ያነገር የለም ብለህ እኝኝኝ ብትል ቅድሚያዉኑ አይተህ ነዉ ያገበሀዉ ጥፋቱ የአንተ ነዉ ፡፡በአንተ ምርጫህ እንዝላልነት የተነሳ ዲነል ኢስላምን አታሰድብ 😏ወደ ሌላ ሀይማኖት እንዲሄዱ በር እየከፈክ እንደሆነ አትርሳ፡፡

☝️☝️ዩኒቨርስቲ ላይ ወንድ የወንድ አቅሪ ሴትም የሴት አቅሪ ብቻ ቢያቀራቸዉ ብቸኛ መፍትሄ ነዉ፡፡ የጀመአ አሚር ነን ተብሎ የሴቱን ቁጥር የሁሉንም ይዞ የወንድ አሚር እየደወለ መከታተል ይቅር፡፡ይሄን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የጀመአ አባሎች አስተካክሉ

☝️በሰፈር በመድረሳ ወጣት ኡስታዞች ለአቅመ አዳም የደረሱ ሴቶችን ማቅራት ባይኖርባቸዉ ባይ ነኝ፡፡ በተለይ የሀብታም ልጆች ከቤት እንዳይወጡ እየተባለ እቤቱ ቁርአን ትቅራ በሚል ሽፋን በወጣት የወንድ አቅሪዎች ሴቶች ልጆች ሁሉም እየተሸወዱ ነዉ ፡፡እዚህ ላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡

መቼም ቢሆን በአእምሯችን መዝግበን መያዝ ያለብን ነገር ኡስታዝም ሆነ ቁርአን አቅሪም ሆነ ሌላ በሴት ጉዳይ ላይ በጣም ይፈተናል፡፡ ሸይጧንም ያሳስተዋል ነብዩ ሰዐወ እዚች ዱንያ አንደ ሀብትና ሴት ፈተና አልተውኩላቸውም ብለዋል፡፡
ኢማሙ ሻፍእይ እንዲህ ብለዋል አንዲት ሴት እግሯን ተመልክቼ የመሀፈዝ ችሎታዬ ቀነሰ ብለዉ ተናግረዋል፡፡ሴቷን ሴት ኡስታዛህ ብታስቀራ ይህን ነገር ማስቆም ይቻላል ከዚህ ዉጭ እሳትና ጭድ አብራችሁ ተቀምጣችሁ እዚህ አካባቢ የእሳት አደጋ እንዳይፈጠር ሀላፊነት ተሰጥቷችሆል ጠብቁ😊 ተብሎ ስልጣን እንደመስጠት ነዉ

⭕️⭕️ አሁን መፍትሄ ብሎ የታየኝ ስለድንግልና ጉዳይ ከኔ ለተሻሉ ሰዎች ኡማዉ ጋር ቦታ ያላቸዉ መግባባት ለሚችሉ አቅርቡላቸዉና በሰፊዉ እነሱ ይሄን አጀንዳ ቢይዙት በfacebook በtg በtv መስኮት ድረስ የማድረስ👇👇
አቅም አላቸዉ
ከሁሉም ቁጥር አንድ ፀሀፊ #ፉአድ_ሙናን ሀሳቡን አንሱለት እሱ አዲስ አበባ ላይ ተፅእኖ መፍጠር ከሚችሉ ሰዎች ነዉ ፡፡ ፀሀፊ #ፉአድ_ሙናን ብታማክሩት አሪፍ ነዉ..እኔ ጋር እስከ አሁን አያቀኝም እኔ ፁሁፉን ስለምከታተል አቀዋለሁ በጣም ጎበዝ ለአሁን ማህበረሰብ መድረስ የሚችል ልጅ ነዉ፡፡ እንደምንም ብላችሁ ለፉአድ ሙና ሀሳቡን ሼር አድርጉለት እሱ ሊላህ ብሎ ከተነሳ ተፅእኖ መፍጠር ይችላል፡፡
☞ፀሀፊ አብደል ሀኪም ሰፋ እና ነጃት ሀሰን የVenu ቻናል Admin ይሄን ጉዳይ ቢይዙት ለኡማዉ ለዉጥ ማምጣት ይችላሉ፡፡

💠ከኡስታዞች ደግሞ..ኡስታዝ ሳዳት ከማል ቢሆን የተሻለ ነዉ እሱ ጋር የምቀሩ አማክሩት፡፡ በቻናሉ ስለዚህ ጉዳይ በተደጋጋሚ ቢያስተምር ለዉጥ ማምጣት ይችላል፡፡

💠 ከtv ቻናሎች ነሲሀ ቲቪ ለዉጥ ማምጣት ይችላል፡፡ ሌላዉ Minber እና bst ሌላ እራሱን የቻለ ፍትንያ ናቸዉ፡፡ አንዷ ዘመዴ ለወደፊት መሆን የምፈልገዉ ብየ ብጠይቃት Minber tv ዝግጆት አቅራቢ ነዉ😏
አለችኝ የሆነች ቅራቅንቦ ነገር...ሴቶች ለሁሉም ልክ አለዉ ግን የሴት ልጅ ከልክ በላይ መሆን በMinber እና Bst tv እያየን ነዉ፡፡ እነዚህ አጀማመራቸዉ ከሸሪአ አንፃር ዶኢፍ ስለሆኑ ዶኢፍ ደግሞ ያዉ ሀቅን መበጥበጡ አይቀርም😊

💠 ዩቲዩበሮች በሚጠቅም በማይጠቀም ነገር ቢዚ ከምትሆኑ በዚህ ዙሪያ ብሰሩ ለዉጥ ማምጣት ትችላላችሁ፡፡ እስኪ የምግባባቸዉ ዩቲዩበሮችን አማክራቸዋለሁ

💠 Tik tok የሚባል መጥቷል ..እኔ Tik tok aplication የለኝ ምን እንደሆነ ለራሱ አላቀዉም ለወደፊትም ማወቅ አልፈልግም😊 ለምን ጊዜ የሚፈጅብኝን ነገር አልፈልግም በዛ ቢዚ ሁኜ ብዙ መስራት ያለብኝን እንዳልዘነጋ ፡፡ ከተቻለ ማህበራዊ ሚዲያን በprogram ማረግ፡፡ እኔ የምጠቀዉ Imo እና telegram ብቻ ነዉ ፡፡ Imo የምጠቀመዉ ለስራ ነዉ ከዛ ዉጭ ያለዉን ማህበራዊ ሚዲያ ለኔ አይመለከተኝምእናም ማህበራዊ ሚዲያን ቀንሶ ኪታብ መቅራት እና መፅሀፎችን ማንበብ ላይ ብናተኩር የተሻለ ነዉ ብየ አስባለሁ፡፡


📥📥📥 ዉድና የተከበራችሁ የቻናል ቤተሰቦች ዛሬ ሳትዋጋ ንገስ የሚለዉን ታሪክ ለመጀመር ተናግሬ ነበር ..ዛሬም ይሄን የዉይይት ሀሳብ ጨረስኩ ነገ እሁድ በተከታታይ ከዙሁር ቡሀላ ባለዉ ሰአት እንጀምራለን፡፡
ይህ ታሪክ ከአራተኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12 ክፍል ድረስ ትምህርት ቤት ምን እንደሚካሄድ ይዳስሳል ፡፡ እዉነተኛ ታሪክ ነዉ...
☞ሴት ልጅ ጎበዝ ተማሪ ካልሆነች መማር የለባትም ማንበብ መፃፍ ይበቃታል😊 ብያለሁ በታሪኩ የሰነፍ ተማሪዎች School life እናንተዉ ታነባላችሁ
☞ቀይ የደም ሴል ይሄዳል ተብሎ የሚፈራዉ በፊት ሀይ እስኩል ነበር ፡፡ ይሄ ታሪክ ደግሞ አምስተኛ ክፍል ላይ አምስት ጣት ቆጥረዉ☺️ አስግቷል ታነቡታላችሁ
☞ወንድ ነዉ የማይታመነዉ ሴት?የሁላችንም ያልተግባባንበት ጥያቄ ነዉ ታሪኩ ግን ሁሉም እንደማይታመን በሰፊዉ ያትታል
☞ታሪኩ ላይ ሙስሊሞች አህባሽ አቂዳ ከመጣ ቡሀላ ለኢስላም የማይጠቅም የማይጎዳ ማህበረሰብ መፍጠር ችለዋል፡፡ ለዚህም ማሳያ ታሪኩ መልስ አለዉ
☞የዱንያ መዥገር መጥፎ ጓደኛ እንዴት እንደሚጎዳ እናያለን
☞በታሪኩ መራም ወንድም እህቶቻን ለማሳደግ ያደረገችዉ እልህ አስጨራሽ ዉጤት እና የቤተሰብ ሰላም አለመሆን ጉዳቱን ያሳያል
☞በታሪኩ ማብቂያ አካባቢ አንዲት ሰሚራ የምትባል ወፍ ዘራሽ አንድን የባለታሪኩን ጓደኛ በሌላ ሰዉ ፎቶ ተዋዉቃ በፍቅር ሁለት አመት ያጠመደችበት ይዳስሳል
☞ሆነም ቀረ ፍቅር የሚባል በጠፋበት አለም ሰዉ ፍቅር አለ እያለ ጊዜያቸዉን ፈጅተዉ ያስረጁ የወጣት ሽማግሌ የሆኑትን ተማሪ ታሪኮች እንኮመክማለን

ምን አደከማችሁ 100% እንኳ ባወዱት 1% እንኳ ትወዱታላችሁ😊
መልካም ንባብ ተመኘሁ እናንተም ሼር ለማድረግ ተዘጋጁ

ከአሁን ቡሀላ የመወያያ አጀንዳዉን ፋይል ዘግተናል 😊 ሀሳብ ካለ ላኩ እቀበላለሁ በቻናል ግን ለመወያየት Time is up

አሚር ሰይድ
2024/09/27 17:26:56
Back to Top
HTML Embed Code: