Telegram Web Link
መፍቱሀ ቤት እንደ ደረስኩ ...እሷ የምልብሰዉ በጣም የሚያምር ጅልባብ አምጥታ ይሄን ልበሽ አለችኝ
....እኔም ሰርግ ነዉ እንዴ የምንሄደዉ?? አልኳት...
ብዙ ጊዜ ብዙ ሰዉ ይሄን ጅልባብ ስለብሺ ያምርብሻል ይሉኛል እኔም ሰርግ ሲኖረኝ የመፍቱሀን ጅልባብ ነዉ የምለብሰዉ
.....እሷም ጅልባቡን ልበሽ ከሰርግ በላይ ነዉ አለችኝ

ባጃጅ ገብተን እየሄድን...ካሊድ ደወለልኝ
..... የኔ ፍቅር እየመጣችሁ ነዉ ??? አለኝ
.........የት ነዉ የምንመጣዉ ?? አልኩት
....እሱም እኔ መኖሪያ ቤት አለኝ
ከዛም ተናድጄ ጆሮዉ ላይ ስልኩን ዘጋሁት


ከዛም መፍቱሀን እወንድ ቤት ነዉ እንዴ የምወስጂኝ ?? የሷሊህን ገጠመኝ ነግሬሽ እንዴት ትወስጂኛለሽ ??መፍቱሀ አሳልፈሽ ልሰጪኝ ነዉ እንዴ?? እያልኩ ባጃጅ ዉስጥ ሁኜ አለቀስኩኝ

መፍቱሀም ነዋል ተረጋጊ ምንም አትሆኝም ድብቅ ሚስጥር የለዉም ...እህቶቹ ምሳ አዘጋጅተዉ እየጠበቁን ከእነሱ ጋር ሊያስተዋውቅሽ ነዉ እንጂ ለሌላ አይደለም አለችኝ

ካሊድ የመጨረሻ ልጅ ነዉ ፡፡ ያገቡ ልጅ ያላቸዉ ታላቅ እህቶች አሉት ...ብዙ ጊዜ ስለእህቶቹ ስለነገረኝ እሺ ብየ ተረጋጋሁ እና እንባየን ጠረኩኝ ፡፡


ካሊድ መኖሪያ ቤት እንደደረስኩ ያየሁትን ማመን አቃተኝ ሰርፕራይዝ ነዉ የሆነብኝ ፡፡ የሒወቴ የመጀመሪያ የደስታ ጊዜ ይቺ ቀን ናት ብየ መናገር እችላለሁ የዚህን ቀን ደስታ ወላሂ መናገር አልችልም...አባቴ እኔን የተለያዩ ቦታ ወስዶ አዝናንቶኛል ...ግን የዚህን ቀን ደስታ እሩብ እንኳ አያክልም ...

ገና እቤቱ በር ላይ ስደርስ መፍቱሀ አይኔን አሰረችኝ
....እኔም ደነገጥኩኝ ምንድን ነዉ መፍቱሀ እየተፈጠረ ያለዉ ነገር አልገባኝም?? አልኳት
....መፍቱሀም በሂደት ይገባሻል አለችኝ...የካሊድ አንዱ እህቱ Video እየቀረፀችኝ ነዉ፡፡

መፍቱሀ እጄን ይዛኝ ፤ አይኔ እንደተጨፈነ ወደ ዉስጥ ገባሁኝ ...የቤቱ ሳሎኑ  በጣም ሰፊ ነዉ

ካሊድ እንዲህ አላት:- መፍቱሀ አሁን አይኗን ግለጫት አላት
-------መፍቱሀም አይኔን ገለጠችኝ .....ያየሁትን ማመን አቃተኝ እንደዚህ አይነት ሰሬፕራይዝ በፊልም ለራሱ አይቼዉ አላቅም እንኳን በኔ ሒወት ከፊልም በላይ ነዉ የሆነብኝ

ቤቱ በዲምላይት እና በዲኩሬሽን አሸብርቋል በየመሀሉም ILOVE YOU NEWAL የሚል ወረቀቶች ተለጥፈዋል፡፡ ኬኩ ላይ ለራሱ ነዋል ሁሌም እወድሻለሁ ልታገቢኝ ፍቃደኛ ነሽ ወይ?? የሚል አፅፎበታል...ቸኮሌቱ ፍራፍሬዉ ተሰናድቷል ...በየቦታዉ ሻማ ተደርጓል  ከምነግራችሁ በላይ ቤቱ አሸብርቋል

ቤቱ ዉስጥ ከገባሁ ቡሀላ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቁሜ ቤቱ ማሸብረቁ ድባቡ ለአይኔ አዲስ ሁኖበት ገርሞኝ እንደቆምኩኝ አየዉ ይዣለሁ ...ወላሂ ህልም ህልም ነዉ የመሰለኝ አይኔን ብገልጠዉ ብጨፍነዉ ነገሮች ሊቀየሩ አልቻሉም እዉነት ነዉ ብየ ከመቀበል ዉጭ.... ይሄ ሁሉ ለኔ ዝግጅት በጭራሽ ሊዋጥልኝ አልቻለም በጣም አጀበኝ እንዴት ቤቱ አምሯል በአላህ .....

ቁሜ እየተገረምኩኝ እየተአጀብኩኝ ካሊድ መጥቶ በጉልበቱ ተንበርክኮ
.....ነዋል የኔ ፍቅር በጣም እወድሻለሁ ግዙፍ  ሶስት አመት ያህል ታግሼ ጠብቄሻለሁ ...ወላሂ ብየ ነዉ የምነግርሽ ሶስት አመት ያህል ለሊት እየተሳሁ እየሰገድኩ ነዋልን ለኔ አድርጋት እያልኩ አልቅሻለሁ ከአሁን ቡሀላ አመታትን እንኳ ይቅር አንድ ሳምንት አንቺን አጥቼ መኖር አልፈልግም  .....ልታገቢኝ ፍቃደኛ ነሽ ወይ ???? አለኝ

......ካሊድ ተንበርክኮ እንደዚህ ሲለኝ ማመን አቃተኝ ተገረምኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ተንበርክኮ አግቢኝ ሲለኝ ____አረ ሌሎችም ወንዶች ብዙ የትዳር ጥያቄ ሲመጣ ማንም ተንበርክኮ ጠይቆኝም አያቅም የካሊድ ግን ገረመኝ

እኔ በጣም ደስ አለኝ እንደዚህ ያለ ፍቅር ወላሂ ምኞቴ ነዉ ግን በማንነቴ እፈራለሁ.....ምን እኔ ብቻ ብዙ ሴቶች እንደዚህ አይነት ምኞታቸዉ ነዉ ይሄን በህልማቸዉ የሚያዩትን የፍቅር ምኞታቸዉን ለማሳካት በሀራም መንገድ በር ሲከፍቱ ይስተዋላላሉ ....ካሊድ ተንበርክኮ ሲጠይቀኝ እምባየ ቀደመኝ

እምባየ በቆምኩበት ጭንቅ ጥብብ እያለኝ እየተወዛገብኩ በጉንጮቼ በሁለት ረድፍ ኮለል እያሉ እየወረዱ ነዉ ጭንቀቴም እኔን እስከማንነቴ ይቀበለኛል ወይ ??? ይሄን ሁሉ ሰርፕራይዝ ይሄ ሁሉ ፍቅር ለኔ እየገለፀልኝ እኔም እሺ ብል ቡሀላ ስነግረዉ ካሊድ ከነማንነቴ ባይቀበለኝስ ?? ግራ ተጋባሁ ...አሁን ዉሳኔዉ ለዛሬዉ ደስታ ሳይሆን የወደፊት ደስታየን አያደፈርስም ወይ ??ነዉ......
ማንነቴን ይቀበለኛል ወይስ አይቀበለኝም ??"

በሀሳብ ዉስጥ ሁኜ ለካሊድ ...እንዲህ አልኩት...

#ክፍል 3⃣8⃣
ይ..........ቀ..........
......ጥ..........ላ............ል




          `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
     
#ክፍል ☞ ሰላሳ ስምንት 3⃣8⃣

ፀሀፊ ☞
#አሚር_ሰይድ



በሀሳብ ዉስጥ ሁኜ ለካሊድ ...እንዲህ አልኩት...
.....
#ግን_እኔን_ከልብህ_ትወደኛለህ ??? አልኩት
.......ካሊድም:- ነዋል ወላሂ ከልቤ እወድሻለሁ በፊት እንደዛ ፊት ስትነሽኝ ስታስቀይሚኝ ለራሱ አልጠላሁሽም ..እንኳን ልጠላሽ ፍቅርሽ ጨመረብኝ እንኳን ዛሬ ከፊለፊቱ ሁነሽ አለኝ...

እኔም የምመልሰዉ የማወራዉ ግራ ገባኝ ከዝምታ ዉጭ መልስ አጣሁ
....ካሊድም ዝም ብለሽ ቆየሽ እኮ ዉሳኔዉን ንገሪኝ??? እምቢ ልትይ ነዉ እንዴ??? አረ ተንፍሺ በሀሳብ ጨረሽኝ እያለ ሲያወራ እምባ ተናንቆታል፡፡

.......እኔም እሺ ፍቃደኛ ነኝ እንጋባለን አልኩት፡፡
ካሊድ በጣም ደስ አለዉ እህቶቹም እልልታዉን አቀለጡት ፡፡ ቀለበት ገዝቶ ይዞታል ...አንድ ቀን እንኳ ከካሊድ ጋር እጅ ለእጅ ተነካክተን አናቅም  ..ካሊድ ጋር ቀጥ ብሎ አይን ለአይን ተያየን ፡፡ ለመፍቱሀ እንኪ ቀለበቱን አድርጊላት ብሎ ሰጣት....መፍቱሀም ቀለበቱን አደረገችልኝ እህቶቹ በእልልታ ቤቱን አደመቁት

ከዛም ካሊድ ቆይ መቼ ጨረስን ...ነዋል ለኔ ቀለበት አታረግልኝም እንዴ ??? አለ
......እኔም ደንግጬ ካሊድ እኔ እኮ ምንም አልገዛሁም እዚህ ስመጣ ይሄ ይሆናል ብየ አልገመትኩም አልኩት
.....ካሊድም እየሳቀ ችግር የለዉም እኔ ገዝቻለሁ ብሎ ሰጠኝ....ከዛም ቀለበቱን እጁ ላይ ሳንነካካ አስቀመኩለት እሱም ጣቱ ላይ አደረገ

እኔ እና ካሊድ አንድ አይነት ቀለበት አደረግን፡፡ እህቶቹ በየተራ እየመጡ በደስታ ተጠመጠሙብን እንደ ህፃን ልጅ ሳሙን፡፡ ምሳ ዝግጅት በየአይነት ምግብ ተዘጋጅቶ ነበር እህቶቹ እያጎረሱኝ እየተሳሳቅን እየተጨዋወትን ምሳ በላን

ከዛም ኬኩን እኔዉ ቆርሼ በላን.... ከጁምአ ሶላት ቡሀላ የጀመርን እስከ መቅሪብ ሊደርስ አካባቢ ድረስ እህቶቹ ጋር ሁላችንም ሰንጨዋወት ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍን፡፡

★★★ የሚሆነዉ አልገባኝም ለካሊድ ትክክለኛ ፍቅር ነዉ ወይስ የፍቅር ስሜት እየተሰማኝ ያለዉ?? ፍቅርና የፍቅር ስሜት ይለያል
የፍቅር ስሜት ከእዉነተኛ ፍቅር ጋር አንድ አይደለም ..የፍቅር ስሜት ጊዜያዊ አስደሳችና አስደናቂ ስሜትን ይፈጥራል፡ ይህ ማለት ደግሞ ትወደኛለች እንወዳታለን የምንለዉ ስሜት ማለት ነዉ...ለዚህ ጊዜያዊ ስሜት በፍቅር ስም ብዙ ተፃፈለት ተዘፈነለት ፊልም ወጣለት ብዙ ተባለለት ነገር ግን ስሜት እንጂ ከዛ የዘለለ ነገር የለዉም ..ስሜት ደግሞ ቋሚ አይደለም ይጨምራል ይቀንሳል..ይመጣል ይሄዳል ..አንድ ሰዉ ዛሬ ጠንካራ የፍቅር ስሜት ሊኖረዉ ይችላል...ይህ ስሜት ነገ ደግሞ ሊጠፋ ይችላል ..ምክንያቱም የፍቅር ስሜት ማለት ስሜት ብቻ ስለሆነ ነዉ ስሜት ደግሞ ይቀያየራል፡፡
ታዳ በዚህ የፍቅር ስሜት መቀያየር የሚፈጠር ህገወጥ የፍቅር ግንኙነት ሀራም ነዉ፡፡
ዲነል ኢስላም የተቃራኒ ፆታን ግንኙነት የራሱ የሆነ ገደብና ስርአት በማበጀት ነዉ አጂነብይ ግንኙነት እንዲፈፀም የሚፈቀደዉ ፡፡ይህን ኢስላማዊ ህግና ስርዓት በርካቶች አዉቀዉ መተግበር ባለመቻላቸዉ መድራችን በዚህ ዙሪያ በርካታ ችግሮችን መከራዎችን ለማስተናገድ ተገዳለች፡፡ተሰምተዉና ተነበዉ የማያልቁ በርካታ አሳዛኝና ዘግናኝ ታሪኮችን ስናነብና ስንሰማ ቆይተናል፡፡አሁንም እየተመለከትን እንገኛለን..ለወደፊትም እድሜ ከሰጠን ገና ብዙ እንሰማለን እናያለን፡፡
በዚህ ከትዳር በፊት የሚፈጠር ህገ-ወጥ የፍቅር ግንኙነት ምክንያት ከማይመጥናቸዉ .ከአቻቸዉ ዉጭ ከሆኑ በእምነትና አመለካከት ከማይመጥናቸዉ ጋር የትዳር ህይወት ለመኖር ተገደዋል፡፡ ዉስጣቸዉ ሁሌ እያዘነና ጉድለት እየተሰማቸዉ ሰላም የራቀዉን ህይወት በመምራት ላይ ይገኛሉ..የማይመለሰዉ ድንግልናቸዉን በሀራም ግንኙነት ሲያስረክቡ እና የሴትነት ወግ ማዕረጉ እየተረሳ የመጣ..የሴት ልጅ ክብሯ ሀያእ ነበር ይሄም እየቀረ እየመጣ ይመስላል....ከትዳር በፊት ቦይ ወይ ገርል ፍሬንድ በዲነል ኢስላም የተወገዘ ሀራም እኩይ ተግባር ስለሆነ ሁሉም ሊነቃ አላህን ሊፈራ ይገባል፡፡

ማፍቅር መልካም ነገር ነዉ አላህ በሰዎች መካከል የሚስቀምጠዉ ደስታን፣እርካታን የሚያጣጥሙት የሒወት ቅመም ነዉ ይህ ፍቅር ግን ያለቦታዉ ገብቶ የማይዋልበት ቦታ ሲገባ ስቃይና መከራ ይሆናል.
..
ከመፍትሄ ይልቅ ችግር ከእረፍት፣ ይልቅ ስቃይ ፣ከደስታ ይልቅ ሀዘንን ያበዛል .በተለይ በልጅነት ሂወት ላይ ሲከሰት መካራዉ ይደራረባል ሒወት አጭር ናት ከትደሰትክባት በሚል የተሳሳተ ተስፋ አጭሯን ሂወት ለስቃይና ለመከራ የሚያደርግ ጦሳ ሂዶ የማያልቅ ማዕበል ዉስጥ ይገባል
"
"
በጎደኛም ይሁን በአይን ስህተት* በጅንጀናም ይሁን በዉሸት ፍቅር የያዛቸዉ ይህንን ፍቅር የሚሉትን ስሜት ለማስታገስና ለማከም የማይገባዉ ጉድጓድ ዉስጥ ይገባሉ .ለመዉጣት ደግሞ መዉጫ ቀዳዳ ይጠፋል ..
ታሞ ከመሟቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ...አሻግረን መመልከት አቅቶን ሂወታችንን ግዜያችንን እያቃጠልን ስንቶች አለን በማይረቡ የሽንገላ ቃላቶች ተሽብበን ከቤተሰብ ከዘመድ የተራራቅን ?? ስንት ቦታ ወድቀን አለን ያለፈዉን መመለስ ብንችል ብለን የምንመኝ ስንትና ስንት ተስፋ የቆረጥን አለ??

ነብዩ ሰዐወ እንዲህ ብለዋል... ጣጣዉን የቻላ ያግባ ያልቻለ ሰዉ በፆም ይከላከል እንዳሉት ሀላፊነቱን ለመሸከም ተዘጋጅተን ማግባት ነዉ አለበለዚያ በማይመለከተን ግዜን የማይመለከተንን ነገር ጀምረን በጊዜ ከሂወት ጉዞ ዉጭ እንሆናለን ፡፡ በመቸኮል ቀድመን በስሜት በምናደርጋቸዉ ጥቃቅን ስህተቶች ዘላቂና እርጅም የሒወታችን መራራ እናድርግ
:
ለማናዉቃቸዉና ለማንተማመንባቸዉ ጊዜ አዊይ ስሜቶች የማናዉቀዉን የማንተማመንበት ጣፋጭ ሒወት እናበላሽ... ከሸይጧን ግፊት ለሚደረግበት ስህተት ፍቅር በሚል ሽንገላ ከአላህ ሽልማት የሚጠበቀዉን እድል እናፈርስ፡፡

ከካሊድ ቤት ወደ መኖሪያ ቤቴ ተመለስኩኝ.... እቤት ስመለስ ይሄዉ በሽታየ ጀመረኝ ብቻየን መጨናነቅ ለካሊድ እንዴት ነዉ በልጅነት መደፈሬን የምነግረዉ ??? እያልኩ ብቻየን ሳስብ ሳስብ የማልገፋዉን የተራራ ቁልል ሀሳብ ብቻየን በአእምሮየ ሳመላልሰዉ አደርኩ

ጭንቀት ሳበዛ ጨጓራየን ያመኛል ምግብም አልወስድም ሲያስታዉከኝ አደረ.....

የሚገርማችሁ ነገር እኔ ካሊድን እወደዋለሁ ግን ልቤ ሰፍ አይልለትም....በጣም እንደሚወደኝ እንደሚያፈቅረኝ አዉቃለሁ .....እኔ ደግሞ ይናፍቀኛል እወደዋለሁ ከእሱ የሆነ ነገር እጠብቃለሁ ግን አላፈቅረዉም ፡፡ እንዴት እንደምገልፀዉ ግራ ይገባኛል አንዳንድ ሴቶች ይሄን ልጅ ሳየዉ ልቤ ሰፍ ይላል ልቤ ይርገበገባል ይላሉ ..እኔ ደግሞ ለካሊድ እንደዚሁ ነኝ ሁሌም እወደዋለሁ ግን ለእሱ  ልቤ ሰፍ አይልም፡፡ እኔ ይሄን ፍቅር ስተረጉመዉ ካሊድን የወደድኩት በአእምሮየ ነዉ እንጂ በልቤ አይደለም ይመስለኛል፡፡እናንተ እንደዚሀ አይነት ፍቅር ገጥሟችሁ ያቃል ??? የገጠመዉ የሚያቀዉ ሊረዳኝ ይችላል

  ሁሌ ጁምአ ከአሱር ቡሀላ እዛ እገጠሩ ቦታ ሰዉ የሌለበት እየሄድን እናወራለን ይሄ ፕሮግራማችን ሆነ  ፡፡ እንደ ዘንድሮ ፍቅር ጎን ለጎን ሁኖ እወድሻለሁ አበድኩልሽ..ልሳምሽ ልንካሽ በጭራሽ የለም፡፡
 ቁም ነገር ነዉ የምናወራዉ ካሊድ ደስታዉ እኔን ማየቱ ብቻ ነዉ

    ቀለበት ካረገልኝ ቡሀላ ካሊድ ፍቅሩ ከበፊቱ ባሰበት፡፡ ጠዋት ማታ መደወል ስለትዳር ማዉራት ሁኗል ወሬዉ እስከምንገባ በጣም ቸኮለ 👇👇👇
..እኔ ደግሞ ማንነቴ አስጨነቀኝ በጣም በስቃይ በለቅሶ በዱአ ላይ ነኝ ...ካሊድ ሲደዉል እስቃለሁ ደህና ነኝ እላለሁ ..ግን ስልኩን ሲዘጋዉ የማይጠፋ እሳት ሆዴ ዉሴጥ ተለኩሶ በእንባየ የሚጠፋ ይመስል አለቅስ ይዣለሁ፡፡ ደግሞ ትምህርት ቤት እና በየመንገዱ ደስተኛ ነኝ ፊቴ ዘና ብሎ ጥርሴ መሳቅ አመሉ ነዉ....አይ ጥርሴ የልቤን ብታየዉ እንኳን መሳቅ ከነጭነት ወደ ጥቁርነት በተቀየርኩ ባልከኝ እንኳን እኔን ከፍቶኝ አይኔ ሲያለቅስ ጥርሴ ግን በልቤና በእምባየ እየቀለደ ይመስል ፈገግ ይለዋል፡፡

  ወላሂ ብየ ነዉ የምነግራችሁ ሰዉ ሁላ ዘመድ ጎረቤት ጓደኞቼ ቀለበቴን ሲያዩት በደስታ ፣ መቼ ነዉ ሰርግሽ ??? የማይለኝ የለም ፡፡ ታዋቂ መሆን አንዳንዴም አስቸጋሪ ነዉ....በየመንገዱ ያገኘኝ ሁሉ መቼ ነዉ ንገሪኝ የማይለኝ የለም....

የለበስኩትን ቀለበት ብቻ አይተዉ ነዋል ልታገባ ነዉ የሚል ወሬ በእኛ ሰፈርና በኮሌጅ ሳይቀር በአንዴ ተናፈሰ...


#ክፍል 3⃣9⃣
ይ..........ቀ...............,
.......ጥ.........ላ..............ል



     Join     `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
     
#ክፍል ☞ ሰላሳ ዘጠኝ 3⃣9⃣

ፀሀፊ ☞
#አሚር_ሰይድ




ነዋል ልታገባ ነዉ የሚል ወሬ በአንዴ ተናፈሰ....
በመንገድ ያገኘኝ ሰዉ ነዋል ልታገቢ ነዉ እንዴ?? ብሎ ሲጠይቁኝ.... አብሽሩ መቼም ሰርጉ ሲደርስ እናንተን ጥየ ያገባሁት ሰርግ... ሰርግ ሳይሆን ሀዘን ነዉ ዱአ አድርጉልኝ ኢንሻ አላህ በቅርብ ቀን አይቀርም እያልኩ ለሰዎች እመልስላቸዋለሁ፡፡

  ሁሌም ከካሊድ ጋር በሳምነት ጁምአ ከአሱር ቡሀላ ስንገናኝ ልንገረዉ አልንገረዉ እያልኩ ብቻየን አስባለሁ ..ግን ከምኑ እጀምራለሁ??አፍ አዉጥቶ ለመንገር አንደበቴን ይሳናል .....


አላህ ይርዳሽ በሉኝ ለሚመጣዉ ሳምንት ካሊድ በሚመቸዉ ቀን ቀጠሮ ይዤ ሁሉንም አፍረጥርጬ ልነግረዉ ወሰንኩኝ...

   ሰኞ ጠዋት ለካሊድ ደዉየ በጣም እፈልግሀለሁ የማወራህ አስቸኳይ ጉዳይ አለ  አልኩት
.....እሱም ስራ ላይ ነኝ ዛሬ አይመቸኝም ምን አልባት እሮብ እና ሀሙስ ልቀር እችላለሁ ...ለምን ጁምአ በሳምንት የምንገናኝበት ቀን ነዉ ጁምአ አነግሪኝም ወይ ?? አለኝ
.....,እኔም ጁምአ እኮ የደስታችን ቀን ነዉ አሁን የምነግርህ የተደበቀ ሚስጥር ለጁምአ የሚነገርበት ቀን አይደለም አልኩት
......የምነግሪኝ የሀዘን ነዉ ማለት ነዉ???? ...አታስጨንቂኝ አሁን ንገሪኝ አለኝ
.........እኔም ዝም አልኩት፡፡
....እሱም ሀሙስ ከሰአት ስራ አልገባም እንገናኛለን ትነግሪኛለሽ አለኝ.....
...እኔም ኢንሻ አላህ ብየ የስልክ ወሬያችንን ጨረስን

ከካሊድ የምወድለት ሶስት ባህሪዎች አሉት የመጀመሪያዉ ምንም ነገር ቢፈጠር በስራ ቀልድ አያቅም ስራ ስራ ነዉ የሚለዉ ደግሞም ስራ አይመርጥም ሁለተኛዉ በጭራሽ አይዋሽም ሶስተኛ አይደብቅም ለምሳሌ አንዳንድ ሰዉ ስታጠፋ መስመር ስታልፍ የሚደብቅልህ አለ እሱ ግን ሀቅ ከሆነ ከፈለገ ቅር ይበልህ እንጂ እሱ ነዉርን ካየ ፊለፊት ነዉ የሚናገረዉ ይሄ ባህሪዉ ይመቸኛል ፡፡

  ስልክ አዉርተን ብንጨርስም ካሊድ እየደወለ በጣም አስቸገረኝ ምንድን ነዉ የምነግሪኝ??? ነዋል እባክሽ ንገሪኝ በሀሳብ ልሞት ነዉ?? ስራ መስራት አልቻልኩም እያለ በየሰአቱ እየደወለ ነዉ፡፡ እኔም ተጨኔቄ እሱንም አስጨነኩት
....እኔም ይሄንን ሀሳብ ተረጋግቼ ማሰብ ስላለብኝ እሱም እየደወለ ሲያስቸግረኝ ...ካሊድ እኔም ለራሴ ሀሳብ ላይ ነኝ በአላህ አንድ ነገር ተባበረኝ???አልኩት
.....እሱም ምን ልተባበርሽ ??? አለኝ.....
....,እኔም ሀሙስ እስከሚደርስ በተደጋጋሚ አትደዉል በቀን አንዴ ከደወልክ ይበቃል በዚህ ተባበረኝ አልኩት
......እሱም ጭራሽ የማይሆን ነዉ እኔም ተጨንቂያለሁ..,የኔ በተደጋጋሚ አለመደወል አሁን ለአንቺ ሰላም የሚያረግሽ ከሆነ እሺ ሳልወድ በግዴ የተናገርሽዉን አከብራለሁ አለኝ
....በዚህ ሀሳብ ተስማማ

እኔ ይሄን ያልኩበት ምክንያት ካሊድ በኔ ፍቅር በጣም እየተጎዳ ስለሄደ ...በቀን አንዴ ከደወለ ይበቃል ..እኔ ስነግረዉ እንደማይቀበለኝ አቃለሁ በዚህ የተነሳ እኔን እየረሳኝ ይሄዳል ብየ አሰብኩኝ ፡፡ካሊድ በቃሉ መሰረት በቀን አንዴ መደወል ጀመረ....

   እኔም መደወል ሲያቆም ትንሽ ጊዜ አገኘሁ ወላሂ ቢላሂ ቀን ማታ ማልቀስ ሆነ ስራየ ፡፡ ለሊት እየተነሳሁ ሶላት እየሰገድኩ ወላሂ ዱአ እያረኩ አለቅሳለሁ፡፡ ሶላተል ሀጃ ሶለተል ኢስቲሀራ አየሰገድኩ በቂያምም በሩኩኡም በሱጁድም እያለቅሱ አላህን እጠይቀዉ እለምነዉ ይዣለሁ አላህ እርዳኝ ካሊድ ማንነቴን እንዲቀበለኝ እርዳኝ .... ሁሌ ደካማ አታርገኝ አሁንስ ደከመኝ ማን ማንነቴን ይረዳኝ ??ጌታየ እኔንም በማንነቴ ካሊድንም በፍቅር አታሰቃየን ፡፡ እያልኩ ዱአ ማድረግ ተያይዠዋለሁ...እናንተም በዱአችሁ አትርሱኝ

★★★ ዱአ
ዱአ በሀይማኖታችን ዉስጥ ትልቅ ጠቀሜታ ያለዉ ሲሆን እኛን የሰዉ ልጆች ደካማነትና ረዳት የለሽነት በመለኮታዊ ችሎታ ፊት የማቅረቢያ መንገድ ነዉ።

አንድ ባሪያ ጉዳዮቹን ይፈፅምለት ዘንድ ወደ ሀያሉ አላህ ፊት ይዞ ሲቀርብ ከቃላት ማነብነብ ባለፈ ልባዊ በመሆንና ፊትን ወደ አላህ በማዞር መሆን አለበት። ይህም ሲሆን ሁል ጊዜም ቢሆን አላህን በመፍራትና ምህረቱንም ተስፋ በማድረግ መካከል መሆን ግድ ነዉ። ለምሳሌ አንድ አማኝ አላህ ሀጥያቱን እንዲምረዉ ከፈለገ በዱአዉ ዉስጥ ሙሉ ትኩረት ማድረግና ጉዳዩን በሙሉ ልቡ ለፈጣሪዉ ማቅረቡን ማረጋገጥ ይኖርበታል። በፀፀት በተቃጠለ ልብና እንባ የሚያወርዱ አይኖች የፈጣሪን ትኩረት የማግኘት እድላቸዉ ሰፊ ነዉና።

በሁሉም አጋጣሚዎችና ሁኔታዎች አንድ አማኝ የአላህ ባሪያ መሆኑን ከሚያረጋግጥባቸዉ መስፈርቶች አንዱ ሁል ጊዜም እርሱን መለመን መቻሉ ነዉ። ባሪያ የመሆን ሚስጥሩና የእዉነተኛ አምልኮት አስኳል የሚገኘዉም አላህን በተከታታይና በዘዉታሪነት በመለመን ነዉ። ምክንያቱም ሶላትና ዱአ ወደ አላህ የሚወስድ ወሳኝ መንፈሳዊ መንገዶች ናቸዉና።

አላህ በተከበረ ቃሉ በቁርአን እንዲህ ብሏል
ባሮቼ ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ(እንዲህ በላቸዉ)""እኔ ቅርብ ነኝ የአማኝን ፀሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ።ስለዚህ በእኔ ይታዘዙ በእኔም ይመኑ እርሱ ሊመሩ ይከጂላልና""(አል በቀራህ186)

ተወዳጁ የአላህ መልክተኛ ሀቢቡና ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ከሰላታቸዉ በተጨማሪ እንባቸዉን እያፈሰሱና በመቆም ተረከዛቸዉ እስከሚያብጥ ድረስ አላህን በፅኑ ይማፀኑና ይለምኑ ነበር። አጭርና ልባዊ የሆነን ዱአ የመዉደዳቸዉን ያህል ከልብ ያልሆነን ማነብነብ ይጠሉ ነበር። ተከታዮቻቸዉም እንደሚከተለዉ በማለት ይመክራሉ።
""ባሪያዉ ወደ ጌታዉ ይበልጥ ቅርብ የሚሆነዉ ሱጁድ ላይ ሲሆን ነዉ። ስለዚህ ሱጁድ ባደረጋቹህበት ጊዜ ብዙ የምትፈልጉትን ነገር አላህ ያሳካላቹህ ዘንድ ለምኑት"" ብለዉናል፡፡

አንድ አማኝ ሁል ጊዜም በዱአ አላህን በመለመን መትጋት የሚገባዉ መሆኑ እንደተጠበቀ ሁኖ በእምነት ወንድሙ የሆነ ሰዉም ዱአ እንዲያደርግለት መጠየቅ ይኖርበታል። ይህ ሰዉ ምናልባትም ድሀ፤ደካማ፤ችግረኛ...ቢሆን እንኳን አላህ የእርሱን ልመና ሊሰማዉ ይችላል። ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ(ሰ.ሰ.ወ) እንዲህ ብለዋል።
"" አንድ ሙስሊም ለሌላዉ ወንድሙ በሌለበት ከሚያደርግለት የበለጠ በፍጥነት ተቀባይነትን የሚያገኝ ዱአ የለም።(ቲርሚዝ) እናንተም በዱአ አግዙኝ....
  

ከሰኞ ጀምሬ ሀሙስ ድረስ ትምህርት ሳልሄድ እቤቴ እየዋልኩ ከሶላት በፊትም ቡሀላም ዱአ ላይ ነኝ ፡፡ ወላሂ እነዚህ ቀናቶችን ዳግመኛ በሒወቴ ላይ ማሰብ አልፈልግም በጥላቴም ላይ በጭራሽ አልመኛቸዉም .ጠዋት ጀምሬ እስከ ማታ ይሄም አልበቃኝ ብሎ አዳሬን ማልቀስ ሆነ የኔ ነገር፡፡ እንቅልፍ አስተካክየ መተኛት እንኳን አልቻልኩም አይኔ አለመፍረጡም የጉድ ነዉ፡፡


የሚገርማችሁ እያለቀስኩ ዱአ ሳደርግ ምን ብየ ዱአ እንደማደርግ ታቃላችሁ?? ከሁሉም ሰዉ የተለየ ዱአ ነበር የማደርገዉ

ዱአየም......
>>>>>>>>> የፈጠርከኝ ጌታየ አላህ ሆይ!!!! እባክህ እርዳኝ ደካማህ ባሪያህ ነኝ ;ካሊድ ከሁሉም ወንድ የተሻለ ነዉ ለኔም የተሻለ ሰጥተህኛል አቃለሁ ...ማንም ከሚወደኝ በላይ ይወደኛል ..ማንም ሳያከብረኝ እሱ ግን አክብሮኛል ....የእኔ እና እሱን የመጨረሻዉን በሰላም አርገህ አሳየኝ...ማንነቴን ነግሬዉ ከተቀበለ አልሀምዱሊላህ እሰየዉ .ነገር ግን ማንነቴን የማይቀበለኝ ከሆነ በዱንያ መሬት መኖር አልፈልግም ;እኔም ታንቄ መርዝም ጠጥቼ መሞት አልፈልግም👇👇
አንተዉ እንደፈጠርከኝ ግደለኝ ... ጌታየ ሆይ ወድጄ አይደለም...ከዚህ በላይ መታገስ አልችልም፡፡ ስቃየ በዛ እኔም ተሳቅቄ በማንነቴ ተሸማቅቆ መኖር በቅቶኛል ፡፡ ሞትን የመረኩት ምክንያት አለኝ ------ ማንነቴን የሚቀበለኝ ከሌለ በዱንያ ላይ ወንድን አልፈልግም #አንተዉ_በጀነት_ላይ_አንተን_ሲገዛ_የኖረ_አንተ_ከምወደዉ_ባሪያህ_መርጠህ_ታጋባኛለህ ..የማገባዉ ጀነት ዉስጥ ብቻ እንዲሆን ነዉ የምፈልገዉ ...መቼም ይሄንን ሁላ ግፍ አሳልፌ ከልጅነቴ ጀምሬ ሳለቅስ ኑሬ ስጨናነቅ ኑሬ በዱንያ የሀሳብ እና በእንባ ጎርፍ በአንተዉ ዉሳኔ ተቀጥቼ....እራሴን አጥፍቼ አንተ ጋር ብመጣ  ይሄንን ሁላ ግፍ ለቅሶ አሳልፌ በአንተ ራህመተህ እዝነትህ የጀሀነም እንደማታደርገኝ እርግጠኛ ነኝ..... ለነገሩ ምን እርግጠኝነት አለ??? አንተዉ ፈጥረሀኝ ወደ አንተዉ ተመላሽ ነኝ ምን ዋስትና አለኝ??? የሰዉ ልጅ ለመሞት አንድ ስንዝር ስትቀረዉ በአላህ ሲያምፅ ኑሮ የጀነት ስራ ሰርቶ ጀነት የሚገባ እና በተዘዋዋሪ የጀነት የሚያስገባ ስራ ሰርቶ ለመሞት አንድ ስንዝር ስቀረዉ የጀሀነም የሚያስገባ ስራ ሰርቶ ጀሀነም የሚገባ አለ ....እራሱን ያጠፋም ጀነት እርም እንደሆነ አቃለሁ ብቻ አንተዉ ጠብቀኝ እኔም ግራ ገባኝ፡፡ #አላህዋ ካሊድ የኔን ማንነት የማይቀበል ከሆነ እዚሁ ሱጁድ ላይ እንዳለሁ ግደለኝ ..ሂወት በቃኝ ግደለኝኝኝኝ  መኖር አልፈልግም ይበቃኛል፡፡  እስከ አሁን ደስተኛ ሁኜ የኖርኩበት ቀን የለኝም...የኔ ደስታ አንተ ያዘጋጀህልኝ ጀነት ነዉ ጌታየ አንተዉ ሽማግሌ ሁነህኝ ደስታየን በጀነት ወንድ አርግልኝ ....,እየደጋገምኩ እየደጋገምኩ ካሊድ ማንነቴን የማይቀበለኝ ከሆነ ግደለኝ መኖር አልፈልግምምም እያልኩ ስጁድ ላይ እማባየን አፈስ😢😢 ይዣለሁ
 
ካሊድ በቀን አንዴ እየደወለ አረ አስጨነቅሽኝ ምን ሁነሽ ነዉ??? ንገሪኝ እያለ ይጠይቀኛል
.....እኔም ሀሙስ ተባብለናል ሀሙስ ሲደርስ እነግርሀለሁ እለዋለሁ፡፡


የማይደርስ የለም የፈራሁት ዱአ ያረኩበት ልነግረዉ የወሰንኩት ቀን ሀሙስ ደረሰ ..
....ካሊድ ጋር ተገናኘን ወሬዉን ለመስማት ቸኩሏል፡፡ሰንገናኝ የምንዝናናበት ቦታ እንሂድ እንዴ??? አለኝ
......እኔም አንተ መኖሪያ ቤት ይሻላል አልኩት..,ምክንያቱም በመንገድ ስመጣ ወይም እዛ ማልቀሴ የማይቀር ነዉ ሰዉ እይታ እንዳልገባ በማሰብ ነዉ መኖሪያ ቤቱን የመረጥኩት
....እሱም እስከዛሬ ወንድ ቤት አልሄድም ብየ ስላስቸገርኩት . ..እርግጠኛ ነሽ እኔ ቤት እንሂድ??? አለኝ
......እኔም አዎ አንተ ቤት ነዉ የምነግርህ አልኩት
..............እሺ መርሀባ ብሎኝ ወደ እሱ ቤት ጉዞ ጀመርኩኝ ፡፡ ግን ምን ሁነሽ ነዉ?? ንገሪኝ በጣም ተጨነኩኝ እቤት እስከምደርስ አላስቻለኝም አለኝ
.......እኔም ምንም አልሆንኩም ቤት ስንድረስ ብነግርህ ይሻላል አልኩት .
ከዛም በመኪናዉ መኖሪ ቤቱ ወሰደኝ
..... እቤት እንደገባሁ ብዙም የተካበደ ሳይሆን የወንደ ላጤ ግብዣ ጋበዘኝ እና...የኔ ፍቅር ምንሁነሽ ነዉ ???ንገሪኝ እኔም በጭንቀት አለኩኝ እኮ ስራ መስራት አልቻልኩም አለኝ

....እኔም ለመናገር ምራቄን ዋጥ አርጌ ምላሴ ለመንገር እየፈራ እየተንቀጠቀጠ መንገሬን ጀመርኩ....ካሊድ አንንተተ ምን ያህል እንደምወደኝ እንደ እንደደደ ምታፈቅረኝ  አቃለሁ ፡፡ አፈቅርሀለሁ ብየ ባልዋሽህም እወድሀለሁ አንተተተን ማማማጣት አልፈልግም ....አንድ ስለ እእእእኔ ማንነት የምነግርህ አለ ይሆናልልልል ብለህ የማጠብቀዉ ነዉ፡፡
  
ለካሊድ ባለፈዉ ያረገልኝን ቀለበት አዉጥቼ ሰጠሁት ፡፡አሁን የምነግርህን የማትቀበለኝ ከሆነ ቀለበቱን እንደያዝከዉ ለኔ አታድርግልኝ ዝም ብለኝ ...ምንም አስተያየት ጥያቄ አንዳታነሳብኝ ..እንዴት ለምን ሆነ ??እያልክ ታሪኩን  እንድጠይቀኝ አልፈልግም...ከቤት ዉጪ በለኝ ከቤት እወጣለሁ ደግሜ በሒወትህ በጭራሽ አልገባም ከአሁን ቡሀላ በጭራሽ አንገናኝም ..ብሞት ለራሱ ነዋል አላህ ይርሀማት ብለህ ለመቅበር እንዳትመጣ
....እሱም አረ ምንድን ነዉ ነገሩ?" አስጨነቅሽኝ አለኝ
.......,እኔም እስከማንነቴ ለመቀበል ለመወሰን ጊዜ እሰጥሀለሁ ይሄ ነገር ቀልድ አይደለም፡፡ አንድ ቀን ፈጣሪ ካለ አንድ ላይ ሁነን ትዝ ብሎህ ወይም ከተጋባን ቡሀላ ይሄ ነገር እንዴት እንደዚህ ሆነ ??ብለህም እንድትጠይቀኝ አልፈልግም...በጠቅላላ ዛሬ ከነገርኩህ ቡሀላ፡ዳግመኛ ይሄን ወሬ ማዉራት አልፈልግም አልኩት፡፡
ይሄን ወሬ ለመስማማት ወይም ለመተዉ 24ሰአት እሰጥሀለሁ ..አሁን 8:00ነዉ አይደል ??? አልኩት
.....እሱም አዎ አለኝ
.....እኔም ነገ ጁምአ 8:00 ላይ ደዉለህ ዉሳነኔህን ታሳዉቀኛለህ ፡፡ ከስምንት ሰአት አንድ ደቂቃ ካለፈ ሀሳብህ አልፈልግሽም ስለሆነ እንዳትደዉል መቼም ይቅር ልልህ አልችልም አልኩት
....እሱም ደነገጠ አረ ምን ሁነሽ ነዉ???ይለኛል
......በቃ ልነግረዉ ነዉ......የስንት አመት የታፈነዉን የሆድ ዉስጥ ፉም እሳቱን ልነግረዉ ማልቀስ ሆነ ስራየ... ልረጋጋ አልቻልኩም እምባየ እንደወራጅ ወንዝ ይጓዛል😢...ካሊድ አላስቻለዉም አብሮኝ ያለቅሳል አረ ንገሪኝ የአንቺን ሀዘን ማየት አልችልም እያለ መላቀስ ይዘናል

እኔም መናገር አቃተኝ እንዴት ብየ ቃላት አዉጥቼ ልንገረዉ ?? ሁለታችንም እየተያየን መላቀስ ሆነ ፡፡ አፌ ተያያዘ ልጅ ሁኜ ተደፍሬ ነበር ብየ እንዴት ብየ ልንገረዉ ???.ከዛም አንድ ሀሳብ መጣልኝ ስልክህን ያዝ text አሁን እልክልለሁ አንተ የምትለኝ እዉነትሽን ነዉ ...ብቻ በለኝ ጥያቄ እንዳታበዛብኝ  አልኩት
....እሱም እሺ አለኝ
.........እኔም ሳይበዛ በmessage በአራት አመቴ በጎረቤት ልጅ ተደፍሬ ነበር የነገረችኝ የቤት ሰራተኛችን ናት..አባቴ የጎረቤታችን ልጅ በልጅነትሽ የተደፈርሽዉ ብላኝ አባቴ በሽጉጥ ሊገላት ነበር ብየ በአጭሩ ፃፍኩለት
....ካሊድ እየደጋገመ የላኩለትን Message አነበበዉ አነበበዉ ...በአንዴ ፊቱ ተቀያየረ 😡መናደዱ ፊቱ ላይ ያስታዉቃል ከንፈሩን በፊት ጥርሱ ነክሶ ፍጥጥ ብሎ ያየኝ ጀመረ.... ..እንም የካሊድን ለኔ ያለዉን አመለካከት ስመለከት በጣም ደነገጥኩ፡፡ ከመደንጠጤ የተነሳ ልቤ ከቦታዉ ተነቅላ የሄደች ነዉ የመሰለኝ .... ምን ይደረጋል የፈራሁት ስጨነቅበት የነበረዉ ነገር ደረሰ😔


#ክፍል 4⃣0⃣
ይ.........ቀ........
.......ጥ .........ላ...........ል


ዉድና የተከበራችሁ የቻናል ቤተሰቦች ይህን እዉነተኛ ታሪክ ምን ያህል ሰዉ እንደሚከታተለዉ ለማወቅ እና #part 4⃣0⃣ ቶሎ እንዲፓሰት ከፈለጋችሁ አሁኑኑ Like 🤙🤙🤙 በማድረግ አሳዉቁ..... ታሪኩ ይቋረጥ የሚል በአስተያየት መስጫ እያነበብኩ ስለሆነ የሚከታተለዉን ሰዉ ለማወቅ 🤙🤙🤙 like በማድረግ አሁኑኑ አሳዉቁኝ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
     
#ክፍል ☞ አርባ 4⃣0⃣

ፀሀፊ ☞
#አሚር_ሰይድ




ካሊድ የላኩለትን message እየደጋገመ አነበበዉ አነበበዉ ፊቱ ተቀያየረ መናደዱ ፊቱ ላይ ያስታዉቃል ...የፈራሁት ስጨነቅበት የነበረዉ ደረሰ ብየ አሰብኩኝ
......... ካሊድ አብሽር አትደንግጥ አልፈልግሽም ማለትህ አይደል? በቃ ልነሳ እና ልሂድ አንተን ማስጨነቅ አልፈልግም ብየ ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ
......እሱም ነይ ተቀመጭ ምንድን ነዉ የምትይዉ?? አሁን ከአፌ ምን ሲወጣ ሰማሽ?? ብሎ ሲቆጣኝ መልሼ ተቀመጥኩኝ
......እሱም አንድ ጥያቄ ብቻ ልጠይቅሽ message በደንብ አልገባኝም እስኪ አብራሪልኝ የአራት አመት ልጅ ሁኜ ነዉ ያልሽዉ ወይስ ከአራት አመት በፊት ነዉ ??? ብለሽ የፃፍሽዉ?? አለኝ
.....የአራት አመት ልጅ ሁኜ ነዉ አልኩት
......ካሊድም ዝም ብሎ ቆየና... ያላሰብኩት ይለኛል ብየ ያልገመትኩት መልስ ሰጠኝ >>>>> #እንዴት_ሰዉ_የአራት_አመት_ልጅ_ጋር_ስሜቱ_ይታዘዝዋል ???<<<<<<< ግን የምርሽን ነዉ የኔ ፍቅር መቼም አፕሪል ዘፉል እያልሽ ሰዎቹ እንደሚጃጃሉት እየተጃጃልሽ አይደለም አይደል ?? አለኝ
.....እኔም አዎ እዉነቴን ነዉ አልኩት
........እኔን ለመፈተን አይደለም ???እንደዚህ ስለዉ ከተወኝ ልተወዉ ከተቀበለኝ ደግሞ የወደፊት የትዳር ምርጫየ ነዉ ብለሽ አስበሽ እኔን ለመፈተን..የአንቺ የፈተና መሰናክሉን ማለፍ አለማለፌን ለማረጋገጥ ብለሽ  አይደለም ??? አለኝ
.....አዎ አይደለም እዉነተኛ ነዉ የነገርኩህ አልኩት
..........እሱም ወላሂ በይ ??? አለኝ
..............ወላሂ ቢላሂ ብየ ማልኩለት
......እሱም እንዴት ሰዉ ገና ለጋ በሆነች የአራት አመት ልጅ ጋር ስሜቱ ይታዘዝዋል ???ምን አይነት ጨካኝ ቢሆን ነዉ ??? የኔ ፍቅር አለኝ
....እኔም ጥያቄ እያበዛህ አታጨናንቀኝ .....አልኩት
.......አንድ ነገር ልጠይቅሽ ፍቃደኛ ከሆንሽ ??አለኝ
.... እሺ ምን ነበር ጥያቄዉ??? አልኩት
.......እዚሁ ቁጭ እንዳልሽ የማስብበት ሀያ ደቂቃ ብቻ ስጭኝ አለኝ
......እሺ ቅድም እንዳልኩህ እንኳን ሀያ ደቂቃ አንድ ቀን እሰጥሀለሁ አልኩት
   
ካሊድ ለ20 ደቂቃ ያህል እየደጋገመ ቴክስቱን እያነበበዉ ነዉ ...የካሊድ ሁኔታ በጣም አስጨነቀኝ ወላሂ እምባዉ እያነበበ ዱብ ዱብ እያለ ይወርዳል ....

ከዛም ከ20ደቂቃ ቡሀላ እንደዚህ አለኝ ...ነዋል እኔ የምወደዉ አንቺን ነዉ ሁሌም ቢሆን እወድሻለሁ፡፡ ፍቅር ማለት ከነማንነት መቀበል ነዉ፡፡ እኔ የምፈልገዉ አንቺን ነዉ ...እኔ ምኞቴ አንቺ የኔ ስትሆኝ ዱአየ ደርሶ ማየቴ ነዉ ፡፡ እኔ አንቺን ምን ያህል እንደማፈቅርሽ አታዉቂም ማለት ነዉ ??? ፍቅር ማለት እንደ አሁን ዘመን ሰዎች ተገናኝተዉ ስሜታቸዉን ማብረድ ..መንገድ ለመንገድ ተገናኝተዉ መጋተት መገባበዝ ብቻ መሰለሽ እንዴ ???አለኝ
.......እኔም ካሊዶ አታስጨንቀኝ ነገሮችን አታወሳስብብኝ ግልፁን ንገረኝ አልኩት

....ነዋል አንቺ ምንም ሁኚ ምንም የምፈልገዉ ነዋል የኔ እንድትሆኝ ብቻ ነዉ ..አንቺን አግብቼ አቅፌሽ እንድተኛ...ከአንቺ ጋር ደስተኛ ሁኜ ልጅ መዉለድ ....ልብሽ ከልቤ ጋር እየመታ እንዲኖር ነዉ የምፈልገዉ ..ለኔ ሌላዉ ትርፍ ነዉ ምንም አልፈልግም ...ይሄ እኮ ቀላል ነገር ነዉ እኔ የተማርኩ ሰዉ ነኝ ብዙ ነገር አዉቃለሁ ..የግድ ድንግል አይደለሽም ብየ ሀገር የምበጠብጥ በረዶ ይቆላልኝ እያልኩ የምለፈልፍ መስሎሽ ነበር እንዴ ??? ድንግልና እኮ ለትዳር መስፈርት አይሆንም ...እንዴት ፍቅርን በዚህ ተራ መስፈርት የምተዉ መስሎሽ ነበር እንዴ??? ብሎ እንደመቆጣት አለኝ
.......እኔም ካሊድ የሚያወራዉ እዉነት እዉነት አልመሰለኝም... ከምርህ ነዉ ??? አልኩት
...........እሱም የሰዉ ልጅ ከወደደ እንኳን አንቺ በማታቂዉ በልጅነትሽ ክብርሽን የአጣሽዉን.....አንዴት ሴት አግብታ ልጅ ወልዳ ተፋታ ከአንዴም በላይ አራት የተለያዩ ባሎች ጋር ኑሮዉን አይታ መፋታት የምታበዛ ፀባይ የሌላት ጨቅጫቃ...... በዛም ላይ . ልጅ ኑሯት ይችን ሴት በፍቅር አምነዉ ወድቀዉ ተዋደዉ ....እያገቡ አይደል እንዴ ???  አለኝ
......እኔም ምን ለማለት ፈልገህ ነዉ ??ካሊድ አንድ ቃል ብቻ ንገረኝ ..ማንነቴን ተቀብልሀል አልተቀበልክም??? አልኩት
......የሰጠሁትን ቀለበት መልሶ እጄን ይዞ አስተካክሎ  በጣቴ አረገልኝ ፡፡ ስሜታዊ ስለሆነ አጂ ነብይ የሚለዉን ዘንግተንዋል
......እኔም በኔ ማንነት ተስማምተሀል ማለት ነዉ ???አልኩት..ጭራሽ የሚሆነዉን ነገር ማመን አልቻልኩም
............እሱም ምን ለማለት ፈልገሽ ነዉ ??ይሄ እኮ ቀላል ነገር ነዉ ቀለል አርገሽ እይዉ....የኔ ፍቅር እስከዛሬ ለዚህ ቀላል ነገር እንደዚህ ተጨንቀሽ ነበር ማለት ነዉ ?? አንቺስ ተጨንቀሽ እኔንም ያስጨነቅሽኝ ለዚህ ተራ ነገር ነዉ ??? ወላሂ እኔም ተጨንቄ ቀን ስራ መስራት ማታ መተኛት አልቻልኩም ነበር ..አለኝ
........እኔም ተቀብለህኛል ማለት ነዉ ??? አልኩት
እሱም አዎ ተቀብያለሁ ይሄ ተራ ነገር ነዉ ..ለወደፊት ስለዚህ ጉዳይ ማዉራትም አያስፈልግም ..በዚሁ እርሺዉ አለኝ
.....ግን አስበህበታል ??? ሁለት  ቀን ልስጥህ እና እሰብበት ቡሀላ እንዳይቆጭህ አልኩት
.....ሁለት ቀን አያስፈልገኝም አሁኑኑ ወስኛለሁ ብቻ አሁንም ለወደፊትም አንቺቺቺቺቺቺቺቺቺቺቺቺ የኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔኔ ብቻቻቻቻቻቻቻቻ  ሁኝልኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝ አለኝ፡፡

ከዛም ይሄን ያህል አመት ከልጅነትሽ ጀምሮ እንደዚህ ስታለቅሺ የኖርሽበት ገና በአራት አመትሽ ስሜቱ ታዞት ይሄንን በደል ፈፅሞብሽ ስታለቅሺ እንድቶኖሪ የፈረደብሽን ልጅ አሳየኝ  እገለዋለሁ አለኝ
......እኔ እሱን ለአላህ ብየ ትቸዋለሁ በቀል ጥቅም የለዉም ይቅርታ ያሸንፋል...ግን ፈጣሪ የስራዉን ወይ በዱንያ ወይ በአኼራ ይሰጠዋል አልኩት
....እሱም ማሻ አላህ.. እኔ ብሆን ለእምባየ ምክንያት የሆነዉን በአገኘሁት አጋጣሚ እበቀለዉ ነበር...አንቺ ይቅር የሚል ጥሩ ልብ አለሽ አለኝ ፡፡


ከዛም ካሊድ አሁን ሳይመሽ ወደ ቤትሽ ልዉሰድሽ ብሎኝ ከቤት ወጣን...መኪናዉ ወስጥ ሁነን ነዋል እንዴት ቅልል እንዳለኝ ልነግርሽ አልችልም ..ተረጋጋሁ በጣም እየተቀጨነኩ ነበር ምን ሁነሽ ይሆን እያልኩኝ ለወደፊት በእንደዚህ ያሉ የሒወት አጋጣሚዎች ተስፋ መቁረጥ የለብሽም ብሎ የተለያዩ ምክሮች መከረኝ...

እኔም ይሄ የተጨነኩበት ቀን እንደዚህ እኔ ባልጠበኩት ሁኔታ አለፈ....አልሀምዱሊላሂ ረቢል አለሚን አልቅሸም አልቀረሁም አላህ ዱአየን ተቀበለኝ፡፡
ወንድ ልጅን ሳስብ ትዳር ሲመጣ ድንግልና ብቻ ነዉ መስፈርታቸዉ ብየ አስቢያለሁ..ባስብም አይፈረድብኝም ከአንድ ሁለቴም ደርሶብኛልና ..ደግሞ በተዘዋዋሪ እንደ ካሊድ ያሉ አስተዋይ ለሴት ልጅ የሚያዝኑ ቅንጣት ሰዎች አሉ ...

★★★ ግን አሁን ድረስ ወንዱ ድንግልናን ደም ጋር ያያዙታል..ግን ደም ብቻ ነዉ የድንግልናዉ መገለጫዉ???
#ድንግልና_ወይም_ክብረ_ንፅህና_የምንለው_ምንድንነው?
አንዳንድ ወንዶች ግድ ደም ካላየን ድንግል አይደለችም እያሉ ያዙኝ ልቀቁኝ እያሉ ሲያቅራሩ ይስተወላሉ፡፡ ነገር ግን ስንት ጥብቅ አላህን ፈሪ የሆኑ ሴቶች ጌታቸዉን ትዕዛዝ ተቀብለዉ ከዚህ አስከፊ ዘመን ሙሲባዉ ሹብሀዉ በበዛበት ጊዜ👇👇👇
ከወንጀል ተከልክለዉ ኑረዉ... ትዳር ላይ ሲገቡ ምሽት ላይ በማታየዉ ምልክት አጅሬዉ ነብር ይመስል ደም ካላየ አንቺ ድንግል አይደለሽም እየተባለች ባልሰራቸዉ ስራ ባልሰራቸዉ ዚና በባሎች ተጠርጥራ በግራ አይን እንድትታይ .... ነገሩም ከከፋ እስከ መፋታት ድረስ የሚደርሱ ብዙ ትዳሮች እያየን ነዉ፡፡ ዉድ እንቁ እህቶች በዚህ ምክንያት ፈጣሪ በሰጣቸዉ ፀጋ ለምን ደም አላየንም አንቺ ዉሸታም ድንግል ነኝ ብለሽ ዋሸሽኝ እየተባለች በባሎች ማሸማቀቅ ምነዉ አግብቼ ባልነበር እያሉ ሲያለቅሱ የሚኖሩ ብዙ እህቶች እንዳሉ ቤት ይቁጠረዉ ፡፡ ወንድሜ ሆይ!!!!! ደም መድማት ብቻ ነዉ እንዴ የድንግልና መገለጫ ??? አትሳሳት ከአእምሮህ ላይ ደም ብቻ ነዉ የሚለዉን ፍቀህ አዉጣዉ....ደም ማየት ብቻ የድንግልና ማረጋገጫ አይደለም፡፡

መጀመሪያ ስለድንግልና ትርጉም እወቅ.. ድንግልና ለሴት ልጅ ብቻ አይደለም ለወንድም አለ...ነገር ግን ምን ይደረግ የወንድ በሴት ልጅ መታወቅ አይችልም..አንተ አወኩኝ ብለህ የምታሸማቅቅ ከሆነ ...የአንተን ማንነት የሚያቅ ፈጣሪ እንዳለ አደራ አንዳትዘነጋ ፡፡ #ድንግልና ማለት የወንዶችም ሆነ የሴቶችን የአካል መቆጠብ ለመግለፅ የምንጠቀምበት ቃል ሲሆን ይሄም ማለት ከግብረ ስጋ ግንኙነት (ከሩካቤ ስጋ) መቆጠብን ይመሰክራል ፡፡ ይህ የመቆጠብና የመጠበቅ ሒደትም ለሰውነት ክብር መስጠት ነውና የሰውነትን ንፅህና ለመግለፅ ስንጠቀምበት ክብረ ንፅህና(የንፅህና ክብር) ወይም ድንግልና ይባላል፡፡

‼️ #ድንግልና_በምን_ይገለፃል?
በእርግጥ ሁለቱም ፆታዎች መታቀብን ተከትሎ ቢያገለግልም በወንዶች ላይ መታቀቡንና መፅናቱን ተከትሎ የሚታይ የአካል ለውጥ የለም፡፡ በሴቶች በኩል ግን የተራክቦ አካላት ከሆኑት መሀል በብልት አካባቢ ይህን የድንግልና መገለጫ ምልክት ይሆን ዘንድ ተፈጥሮ አስቀምጦት ይገኛል።
ድንግልና በሴቶች ብልት በራፍ ላይ የተቀመጠ አነስተኛ መጠን ያለው በደም ስሮች የተሞላ ስስና ሴንሴቲቭ የሆነ የሰውነት ክፍል ነው።

ይሄ በጣም ስስ የሰዉነት ክፍል(አካል) በቀላሉ ሴት ልጅ ልታጣው ትችላለች፡፡ ለምሳሌ፡- ሳይክል በመንዳት ፣ ፈረስ በመጋለብ ፣ ጅምናስቲክ የመሳሰሉ እስፖርቶችን በመስራት...በሀይድ መደራረብ...በከባድ ህመም ወዘተ ያለምንም ፆታዊ ተራክቦ ታጣዋለች።

#የድንግልና_አይነቶች_ስንትናቸው?
አምስት አይነት የድንግልና አይነቶች አሉ። እነርሱም #አንደኛዉ ➊ ☞ ሙሉ የብልት አካል በራፍ ላይ እንደ መጋረጃ የዘጋው ሲሆን የእጃችን ቀዳዳ ምታክል ክፍተት አለው ለወር አበባ መፍሰሺያ ሆኖ የተፈጠረ ድንግልና አለ። ይሄ ቀዳዳ ሙሉ የድንግልናውን ቦታ አይሸፍንም የድንግልናውን መጋረጃ ሩብ ምታክለዋ ቀዳዳ ናት።

#ሁለተኛ ➋☞ ብዙ ጊዜ ባይሆንም አንዳንድ ሴቶች ላይ የወንፊት መልክ በተያዘ በርካታ የተበሳሱ ቀዳዳዎች የተሞላ ሆኖ የተፈጠረ ድንግልና አለ።

#ሶስተኛ ➌☞ በተፈጥሮዋ ምንም የተጋረደ ነገር የለዉም ፡፡ በመጀመሪያው ግንኙነትዋ ጊዜ የሚፈስ ደም የሌላት ሴት አለች ድንግል እንደሆነች የምታውቀው እርስዋ ብቻ ናት ምንም ድንግል እንደሆነች ምልክት አታሳይም ደም አይፈሳትም።

#አራተኛ ➍☞ ድንግልናው በተፈጥሮ የጠነከረና በወንዱ ብልት ሊበጠስ የማይችል ነው ፡፡ይሄ አይነት ድንግልና ያላቸው ሴቶች ድንግልናቸውን ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ በሰርጀሪ ወይም በቀዶ ጥገና ወቶላቸው ነው ግንኙነት የሚፈፅሙት።

#አምስተኛ ➎☞ ሴትዋ ምንም አይነት የድንግልና መጋረጃ ሳይኖራት በብልትዋ ግርግዳ በኩል ብቻ ትናንሽ ሄመኖች ሲገኙ እነሱም የሚወገዱት በወንዱ ብልት ፍትጊያ ነው።
የሴቶች ድንግልና እላይ በጠቀስኳቸዉ አምስቱ ምክንያት ከፈጣሪ የሚሰጣቸው የተፈጥሮ ፀጋ ነው፡፡
.ይህ ፀጋ ደሞ የሚገኘው በመወለድ አንድ ጊዜ ነዉ፡፡ እድል ነውና በህይወታቸው ውስጥ ሴቶች የማይረሳ አሻራን ጥሎ ሚያልፍ ነው። ብዙዎቻቹ የመጀመሪያ ግንኙነታቹን አይረሱትም ለዛ ነዉ ወንዱ ድንግል ምርጫዉ ያደረገዉ፡፡ እናም ወንድሞቼ ደም ካላየሁ ድንግል አይደለችም ብለህ ንፁህ እህትህን ሚስትህን ለተናግሮ ተናጋሪ እንዳትሰጥ በተጨማሪ ከእኔ በፊት ከሌላ ጋር ባልጋለች ብለህ እቺን ንፁህ እንስት እንዳታረክስ ፡፡ የለቅሶዋ ምክንያት እንዳትሆን፡፡


ከዛም ጁምአ ደረሰ እና ብቻችንን ሂደን የምናወራበት፡ቦታ በመኪናዉ ሄድን ... ከአሁን ቡሀላ ጊዜ አንፍጅ አንቺም እቤት አሳዉቂ እኔም አሳዉቃለሁ በቅርብ ቀን ሽማግሌ ልልክ አስቢያለሁ ..አንቺ ምን ሀሳብ አለሽ ?? አለኝ
.......ግን ካሊድ ቤተሰቦችህ ድንግል ናት ወይ ብለዉ ቢጠይቁህ ምን ትላቸዋለህ ?? ብየ ጠየኩት
.....ካሊድም እንዲህ አለኝ_____

#ክፍል 4⃣1⃣

ይ.............ቀ.................
........ጥ............ላ...................ል


join👇👇👇👇

        . www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
     
#ክፍል ☞ አርባ አንድ 4⃣1⃣

ፀሀፊ ☞
#አሚር_ሰይድ




.......ግን ካሊድ ቤተሰቦችህ ድንግል ናት ወይ ብለዉ ቢጠይቁህ ምን ትላቸዋለህ ?? አልኩት
......ካሊድም ቤተሰቦቼ በሌላዉ ሒወቴ እንጂ ጣልቃ የሚገቡት በዚህ የትዳር ሒወት የምወስነዉ እራሴ ነኝ ...ደግሞም ቤተሰቦቼ ስለፀባይ ስለዲን ነዉ የሚጠይቁኝ እንጂ አንቺ ስለምትይዉ በጭራሽ ትዝም አይላቸዉ አለኝ

  እኛ ሀገር አንድ ባህል አለ ..ሁለት ጥንዶች እንደተጋቡ ...አዳሩ ላይ በሩ ላይ ሁነዉ ዘመዶች ያዳምጣሉ የሴቷ የጩኸት የማቃሰት ድምፅ ካልሰሙ አይተኙም ...ከአዳራቸዉ ቡሀላ ጠዋት ላይ የወንዱ ዘመዶች በር ላይ ሁነዉ ይጠብቃሉ... አዲሱ ሙሽራ በቀይ ደም የተበከለዉን አንሶላ ካላሳያቸዉ ድንግል ናት ብለዉ አያምኑትም፡፡ ማታ የወንዱ ቤተሰብች ገብተዉ አንሶላዉን ያነጥፋሉ ጠዋት ደግሞ አንሶላዉን ማሳየት አለበት ፡፡ ሙሽራዉ ድንግል ናት ብሎ ሲናገር..የወንዱ ቤተሰቦች ደስታ በደስታ ነዉ የሚሆነት እልልታዉ ጭፈራዉ #ሰበታ_መቀነት ይባላል... ከሰርጉ ያልተናነሰ ጭፈራ ይጨፈራል የወንድ ቤተሰብ ቤት ይደምቃል ፡፡ ከዛም ሴቷ ቤተሰብ ቤት ተሂዶ ልጃችሁ ስነስርአት ያላት አደበኛ ጨዋ የሽማግሌ ልጅ ናት ተብሎ ስጦታ ይሰጣል ......

እኔም ይሄን ባህል ስለማቀዉ ካሊድ ለቤተሰቦችህ እንዴት ልታደርግ ነዉ አንተ ??? አልኩት
.....እሱም አብረን የምናድረዉ እኔ እና አንቺ ነን እነሱ ምን አገባቸዉ መቼም መኝታ ክፍላችን ገብተዉ አፍጥጠዉ አያድሩ ...እኔ እራሴ የምላቸዉን አቃለሁ ....ለምን እንደዚህ አይነት ሀሳብ ታስቢያለሽ ???  ብሎ እኔ በተናገርኩት እሱ ይናደዳል ...
ነዋል እኔ ብቸኛ አንድ መሆኔ ሰልችቶኛል ..ከአንድ ይልቅ ሁለት መሆን ስቃይ ደስታን ለመጋራት ይመቻል...እኔ የናፈቀኝ ሀሳብ የሆነብኝ መቼ ይሆን እኔ እና አንቺ እኔም የአንቺ አንቺም የኔ የምትሆኝዉ ነዉ ሀሳቤ ጭንቀቴ....እናም ትዳር ነዉ የናፈቀኝ አለኝ...
★★★ #ትዳር የሚያስብ ሰዉም ከወዲሁ ኒያዉን መሬት ማስያዝና ማስተካከል አለበት፡፡ ገና ወደ ትዳሩ ከመግባቱ በፊት ኒያው ማማር አለበት፡፡ በኒያው ዘላቂ ትዳርን አስቦ የገባ ይዘልቅለታል፡፡ ሀሳቡ ጊዜያዊ የሆነው ደግሞ መንገድ ላይ ይቀራል፡፡ አላህ የሰዎችን ሀሳብ አይሰርቅባቸዉም፡፡ አልመው የተነሱትን አይቆርጥባቸዉም፡፡ መውደቅ የፈለገ በመጥፎ ሀሳቡ ምክንያት ይወድቃል፡፡ ገብቼ ልውጣ ያለዉም ገብቶ አይቶ ይወጣል፡፡ አንድ እግሩን እዉጭ አኑሮ በአንድ እግሩ የገባም እንደ ሀሳቡ ያገኛል፡፡ ምክንያቱም አላህ (ሱ.ወ.) ለያንዳንዱ የሰው ልጅ እንደየ ሀሳቡ ይሰጣል፡፡ አላህ ለሰዎች እንደምርጫቸው ይሰጣቸዋል፡፡

ትዳር ሐላል አክሲዮን ነው፡፡ አክሲዮኑ በሁለት ተፈቃቃጅ በሆኑ ወንድ እና ሴት መካከል የሚመሰረት ግንኙነት ነዉና እንደዋዛ መታየት የለበትም፡፡ እንደዋዛ ከታየ እንደዋዛ ይፈርሳል፡፡ ትዳር መልካምነቱን አስበው፣ ወደዉና ፈቅደው በሙሉ ሀሳብ የሚጠቃለሉበት እንጂ በግማሽ ልብ የሚገቡበት ቤት አይደለም፡፡

ትዳር ከሐራም ኑሮ ወደ ሐላል ግቢ ሽሽት ነው፡፡ ከጉድለት ሕይወት ወደ ሙሉነት ቤት ሩጫ ነው፡፡ ጠፍቶ የቆየን ግራ ጎን ማሟያ ፍለጋ ፅድቅ ስደት ነው፡፡

ትዳር የንፅህና ሻወር ነው፡፡ ሲንከራተት ለኖረ ዐይን ማረፊያ ነው፡፡ ሲባዝን ለኖረ ልብ ማስከኛ ነው፡፡ ፍላጎትን ሐላል እና ነፍስ በምትወደው መልኩ ለማሳካት ምክንያት ነው፡፡

ትዳር ባልና ሚስት ተፈጥሯዊ ስሜታቸዉን ሐላል እና አላህ በፈቀደው መልኩ የሚያረኩበት ጥምረት ነው፡፡ ለዚህ ጥምረት ዘላቂነትና ስኬት ከወዲሁ ሀሳብን ማስተካከል ግድ ይላል፡፡ “ከሞቀኝ እቀጥላለሁ ከበረደኝ እወጣለሁ” በሚል ስሜት የተገባበት ቤት የመፍረስ ዕድሉ ከፍ ያለ ነው፡፡ ከሙቀቱ ይልቅ ብርዱ ሊበዛ ይችላልና፡፡ ሀብት ንብረት ለመካፈል ብለው የሚገቡበት ጥምረት ዕድሜው አጭር ነው፡፡ ሀብት ንብረቱ አልገኝ ሲል ያነጫንጫልና፡፡ “አለው” ብለው የተቀበሉት ኪዳን አይዘልቅም፡፡ ያጡ ቀን ባህሪን ያባላሻልና፡፡

ወደ ትዳርም ሆነ ወደማንኛዉም መልካም ነገር ስንገባ ንያችንን ማሳመሩ ግድ ነው፡፡ በበጎ ነገር ዉስጥ ሁሉ የአላህን ዉዴታ እናስብ፡፡ መልካም ነገሮችን ስንጀምር እሱን አስበን እንጀምር፡፡ በስራዎቻችን ዉስጥ ሁሉ አላህ ከጎናችን ስለመኖሩ እርግጠኛ እንሁን፡፡ በሁለመናችን ዉስጥ አላህን እናስገባ፡፡ በዕውቀታችን፣ በብልሀታችንና ብልጠታችን ከመተማመን ይልቅ ነገሮችን እሱ እንዲሰራልን እንፍቀድ፡፡ ምክንያቱም ነገሮች እኛ ስንሰራቸውና አላህ ሲሰራቸው የተለያዩ ናቸውና፡፡ የቱን ያህል ዕውቀትና ብልሃት ቢኖረንም ስራችን በአላህ ድጋፍ ካልታገዘ ከንቱ ነው፡፡ እሱ ከሌለበት የትኛዉም እንቅስቃሴያችን እንከኑ ብዙ ነው፡፡ ጉድለቱ የትየሌሌ ነው፡፡

ማንኛዉንም መልካም ነገር ስንጀምር በአላህ ስም ብለን እንጀምር፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) ከሌለበት አንድን ነገር እንስራ ብለን ብቻችንን ብንነሳ የሚበላሸው ይበዛል፡፡ የሚጠፋው ይበረክታል፡፡

ትዳር በሕይወት በምድር ላይ እስካሉ ድረስ ባልና ሚስት የሚኖሩበት ህንፃ ነው፡፡ በዚህ ህንፃ ግንባታ ላይ የአላህ እጅ እንዲኖርበት መፍቀድ ብልህነት ነው፡፡ ብቻችንን የምንሰራው ቤት.. ቤት አይሆንም፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) የሌለበት ቤት መሰረቱ ደካማ ነው፤ ጣሪያውም ያፈሳል፣ ግድግዳው በቀላሉ ይዘማል፣ ምሰሶው ያረገርጋል፣ ሁለመናው ስጢጥ ስጢጥ ይላል፡፡
ትዳርን ስናስብ ቁሳዊም ሆነ መንፈሳዊ ሰበቡን እናሟላ፡፡ አላህን በቤታችን ስናኖረው ያኔ የቤታችን መሰረት ፅኑ ይሆናል፣ ምሰሶው መሬት ይይዛል፣ ግድግዳው ቀጥ ይላል፡፡
ለአላህ ብለው ያሰቡት ነገር የሱ ጥበቃ አለበት፡፡ አላህ የሰራው ቤት አይፈርስም፣ እሱ ያነጸው ህንፃ አይዘምም፡፡ በዚህች ምድር ላይ የማያልፍ የለምና ላያልፍም የመጣ ነገር የለምና ስራችን ባያምር እንኳን ሀሳባችን አምሮ እንለፍ፡፡ ስለ አላህ እንኑር፡፡ ስለ አላህ እናድርግ፡፡ አላህን ከፊታችን እናድርገው፡፡ ትዳር ወሳኝ ነገር ነዉና ቤታችንን በበረከትና በፍቅር ይሞላልን ዘንድ እሱን እናስቀድመው፡፡ ዋናዉና መቅደም ያለበት እሱ ነዉና የሚቀድመውን በማስቀደም የሚከተለውን እናስከትል፡፡ ለባለትዳሩም የትዳር እድሜ ይስጣችሁ ..ላላገባንም አላህ ፈላጊ ከፈላጊ ያገናኝ አሚን...

ካሊድ ለኔ ያንን ሁሉ የሒወት ዉጣ ዉረድ አልፌ ለዚህ በቃሁኝ ....ደስተኛ ለመሆን መሞከር ረጅም ለመሆን የሞመከር ያህል ለኔ በጣም ከባድ ነበር የሆነብኝ
ዛሬ የምወደዉ የሚወደኝ ፍቅር ምን እንደሆነ በዱንያ ምድር ካሊድ አሳየኝ፡፡ ፍቅር ማለት ይሄ ነዉ ..ፍቅር ከሆነ ግድ መተማመን አለ .. ካሊድ ቢወደኝ ቢያመነኝ ነዉ ሒወቴን ያረጋጋዉ...ደግሞ ባለፈዉ ታሪኬ እንደ ዶክተር ሷሊህ ያለ ተስፋ እንድቆርጥ የስነልቦና ጫና አድሬሶብኝ...ወንድ እና ቁንጫ በልቶ እሩጫ ብየ ከትዳር አለም ተስፋ ቆርጬ ነበር........የብዙ አመት ጠባሳየ ሲያመኝ ሳለቅስ ከሰዉ በታች ነኝ ብየ ሁሌ እራሴን እንደ አሰብኩ እንደ ካሊድ አይነት ጥሩ አስተሳሰብ ያለዉ ሒወቴን ልቤን ማንነቴ ሳይቀር በእሱ መለሰልኝ ..እኔ ሁሌ ድንግል ነኝ ብየ እንዳስብ አረገኝ...አዎ ሁሌም እኔ ድንግል ነኝ... ለምን አስቤበት አምኜበት ስሜቴን መቆጣጠር አቅቶኝ አሳልፌ የሰጠሁት አይደለም... ገና በልጅነቴ እህሉን ከአፈር በማለይበት ጊዜ ተገድጄ የተቀበልኩት ነዉ፡፡👇👇👇
በሳምንቱ ጁምአ ደርሶ በተለመደዉ ሰአት ተገናኝተን...... ካሊዶ ጋር እያወራን ሁሌም ድንግል ባለመሆኔ ስቆጭ
.....እንደዚህ አለኝ ... ነዋል አትሰቢ አትጨናነቂ ይሄ ተራነገር ነዉ እኮ...አንቺ ግድ መሆን አለብኝ ብለሽ ካሰብሽ የአላህ ነገር አይታወቅም ተስፋ መቁረጥ አንችልም ..... ድንግልም ልትሆኝም ትችያለሽ እኮ.......ለምን ብትይኝ ገና በልጅነትሽ በ4 አመትሽ ነዉ ይሄ በደል የደረሰብሽ ..እና በዛ እድሜ ደግሞ ልጅ ስለሆንሽ የሚጠብቅሽ መላኢካ ነዉ ..እናም ሙሉ በሙሉ ተስፋ አትቁረጭ በአላህ ፍቃድ አንቺ የለኝም ብለሽ የምታስቢዉ ነገር ሊኖር ይችላል አለኝ......

#ክፍል 4⃣2⃣

ይ...............ቀ.............
..........ጥ...........ላ...............ል

Join👇👇👇
💐___⭐️______💐______⭐️____
_💐
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
     
#ክፍል ☞ አርባ ሁለት 4⃣2⃣

ፀሀፊ ☞
#አሚር_ሰይድ




እና በዛ እድሜ ደግሞ ልጅ ስለሆንሽ የሚጠብቅሽ መላኢካ ነዉ ..እናም ሙሉ በሙሉ ተስፋ አትቁረጭ በአላህ ፍቃድ አንቺ የለኝም ብለሽ የምታስቢዉ ነገር ሊኖር ይችላል አለኝ......
.....,እኔም የHealth ተማሪ እንደመሆኔ መጠን አንዴ ድንግልና ከሄደ እንደማይመለስ አቃለሁ ..ካሊድ በጭራሽ መሆን አልችልም አልኩት
..... ምነዉ ነዋል ከአላህ እኮ ተስፋ አይቆረጥም አለኝ፡፡ ካሊዶ እንደዚህ ሲለኝ እዉነቱን ነዉ ከአላህ ተስፋ አልቆርጥም ብየ እንደገና ሞራል ሰጠኝ፡፡

    አንድ ቀን የሞባይሌ ባትሪ ተበላሽቶ ለመግዛት ጂማ መርካቶ ሰፈር አካባቢ አንድ ኤሌክትሮኒክስ ሱቅ ስገባ  ...ያየሁትነ ማመን አቃተኝ ...በጣም ደነገጥኩኝ፡፡ ሚፍታህ ጋር ተገናኘን
.....እሱም ድንጋጤ ነዋል አሰላሙ አለይኩም አለኝ
........እኔም ወአለይኩም ሰላም ሰላም ነዉ አልኩት
....እሱም እንዴት ነሽ ሁሉ ሰላም ቤተሰብ ሰላም ናቸዉ?? አንቺስ እንዴት ነሽ ??አለኝ
....እኔም አልሀምዱሊላህ ደህና ነኝ አልኩት
.......እሱም ቀለበቴን እያየ ነዋል ልታገቢ ነዉ እንዴ ??? አለኝ
....እኔም...አዎ ኢንሻ አላህ በቅርብ ቀን አስቢያለሁ አልኩት
ሚፍታህም :- ሽማግሌ ተልኳል ወይስ አልተላከም??? አለኝ
....እኔም ገና አልተላከም በቅርብ ቀን ይልካል አልኩት
....... ነዋል ወላሂ ብየ ነዉ የምነግርሽ በጣም ነዉ የምወድሽ ..አንቺ የሌላ ስትሆኝ ማየት አልችልም... ወላሂ ሁሌም ህልሜ አንቺ ጋር ተጋብቶ መኖር ነዉ፡፡

አንድ ነገር እንድታቂልኝ እፈልጋለሁ ... አንቺ የሌላ ሰዉ ሁነሽ ..ትዳር ከሌላ ሰዉ ጋር ብትመሰርች ፀቤ ከአንቺ ወይም ከአገባሽ ሰዉ አይደለም..ፀቤ ከፈጣሪ ከአላህ ጋር ነዉ..... ለምን ብትይ ሀጅ ባደረኩበት ጊዜ አላህን ከሁሉም ሀጃየ አስበልጬ ስጠይቀዉ ስለምነዉ የነበረዉ....አንቺ የኔ እኔድትሆኝ ነበር... አላህን ስለምነዉ የነበረዉ ከአንቺ ልጅ መዉለድ እስከ እለተ ሞቴ አንቺ ጋር አብሮ መኖር ነዉ አለኝ
....ይሄን ሲለኝ አብረዉ ጓደኞቹ ነበሩ... ይሄን እየተናገረ ሚፍታህ እምባ ነዉ የቀረዉ፡፡
ቁርጤን ንገሪኝ ቁርጤን ንገሪኝ ..የልላ ስትሆኝ ማየት አልፈልግም የኔ ብቻ ሁኜ እባክሽ እያለ ይለምነኛል
........እኔም በጣም ተወዛገብኩ ግራ ገባኝ...ሚፍታህ ዉሳኔየን በስልክ ደዉየ አሳዉቅሀለሁ አልኩት

ከሱቁ ወጥቼ ወደ ቤቴ እየተመለስኩ ነዉ... ልቤ ተሸበረ ...ዉሳኔ መወሰን አልቻልኩም ...የማልክደዉ እዉነት ቢኖረዉ ሚፍታህ በጣም እወደዉ ነበር ለመጋባት ድረስ ደርሰን ቤተሰብ ለቤተሰብ ተጠይቆ እሺ ተብሎ ጨርሰን እንደነበር በአለፈዉ ታሪክ ላይ ታስታዉሳላችሁ...ሚፍታህ አንቺን ማግባት ነዉ የምፈልገዉ ሲለኝ የማላቀዉ ስሜት ከየት መጣ የማልለዉ ወረረኝ ...እሱ ጋር ያሳለፍኳቸዉ የፍቅር ገጠመኞች ጊዚያቶች ፊቴ ላይ እንደመስተዋት መልሶ ያሳየኛል

  ከዛ እንደዚህ እየተጨናነኩ የምወስነዉ ግራ ገብቶኝ ሁለት ልብ ሁኜ ለካሊድ ደወልኩለት፡፡
  ሰላምታ ከተለዋወጥን ----- ካሊድ እኔን ብታጣኝ የሌላ ብሆን ምን ይፈጠራል ብለህ ታስባለህ ? እኔን አጥተህ ብትኖር ምን ይሰማሀል ??? ብየ ጠየኩት
......ካሊዶ ለካ እንደሌሎቹ ወንዶች አይደለም የመለሰልኝ መልስ አስገራሚ ነበር እንደዚህ አለኝ ... #አንቺን_ማጣት_ምን_እንደሆነ_ነዋል_የኔ_ባትሆን_የሚለዉን_በጭራሽ_ማሰብም_መገመትም_አልፈልግም ፡፡ አንቺ የሌላ ስትሆኝ እንዲህ እሆናለሁ ብየ ምሳሌ እንኳ መስጠት አልፈልግም ... ነዋል እኔን ለመቀለድ ብለሽ እንኳን እንደዚህ አይነት ቃል ዳግመኛ እንዳትይኝ ....አለኝ

ወላሂ ጥፋቱ የኔ ነዉ.... ሶስት አመት በትዕግስት ጠብቆ ከነማንነቴ ተቀብሎኝ...ገና ሚፍታህ አንቻን ነዉ ማግባት የምፈልገዉ ሲለኝ ልቤ ወላዉሎ ካሊድን ይሄን ጥያቄ መጠየቄ ከመደወሌ ቡሀላ ብቻየን አፈርኩኝ..

ዉየ ሳላድር ወዳዉኑ ለሚፍታህ Text ላኩለት ...እንደዚህ አልኩት>>>>> ሚፍታህ ከአሁን ቡሀላ ወደ ሆላ መመለስ አንችልም ትናንት ከትናንትናዉ ጋር አብሮ አልፏል ..በርግጥ የማልዋሸህ በፊት እወድህ ነበር ያደግሞ በጊዜዉ አልፏል ...፡፡ አሁን ላይ መጉዳት የማልፈልገዉ የምወደዉ የሚወደኝ እሱን አጥቼ እሱም እኔን አጥቶ መኖር የማይችል እኔም እሱን አጥቼ መኖር አልችል ሁኜ ልቤ ዉስጥ ያስቀመኩት እሱም ያስቀመጠኝ ሰዉ አለ ብየ ላኩለት......
 

  ሚፍታህ ጋር በዚሁ message አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተለያየን...አንድ የወንድ ልጅ ድክመት አለች እየወደዱ ማግባት እየፈለጉ የተሻለ አገኛለሁ ብሎ ከኔ ዉጭ አታገባም ትጠብቀኛለች ብለዉ እያሰቡ ነገር ግን እሷን የሚወዳት አግኝታ ልታገባ ስትል ትጠብቀኛለች ብሎ ያሰበዉ እንደ አዲስ ከእንቅልፉ ሲባንን ይስተዋላል፡፡ ታዳ ሚፍታህም አገባሻለሁ ብሎ ሽማግሌ ልኮ አጭቶኝ ጥፋቴን ሳላቀዉ አመታት ያህል ረስቶኝ ነገር ግን ላገባ ነዉ ስለዉ እንደገና በቅናት ተንገብግቦ አንቺን ነዉ የማገባዉ ማለቱ አግባብ አይደለም..ሴትነት የእናት ነት የእህትነት ደረጃ እንጂ የምርጫ የቅርጫ ለትዳር መወዳደሪያ አይደለችምና፡፡


★★★ #መልካምን_ለማግኘት_ቅድሚያ_መልካም_መሆን_የመጀመሪያው_መስፈርት_ነው"
በአሁን ሰአት ብዙ እህቶችም ሆኑ ወንድሞች ወደ ትዳር አለም ለመግባት እጅጉን በፍርሃት ላይ ይገኛሉ እህቶች ስለ ትዳር ስንጠየቅ ባል የለም እንላለን ወንድሞችም እንዲሁ ሚስት የለም ይላሉ… በሌላ መልኩ ወንዶች የሴትን ገንዘብ ለመብላት እንጂ የትዳር አላማ ኖሯቸው አይደለም የሚያገቡት ይላሉ ሴቶች በሌላው በኩል ወንዶችም ሴት ልጅ ሀብታምን ወንድ ነው የምትወደው ስለዚህ መኸሯ ብቻ እንደ ጉሙሩክ እቃ እየጨመረ በመምጣቱ ከማግባት መቆጠቡ የተሻለ ነው ይላሉ………

#ለመሆኑ_ግን_የእኛ_የሙስሊሞች_የትዳር_መስፈርት_ምንድን_ነው??? ብዙ እህቶች በአሁን ሰአት ስለዲናችን አውቀናል እየተማርንም ነው እንላለን ግን የተማርነውን ጭራሽ ተግባራዊ እያደረግነው አይደለም ስለ ትዳር ስንጠየቅ ወላሂ የእኔ ምርጫ በዲኑ የታነፀ ኢማኑ የሞላ በቂየ ነው ሀብት በዲን ውስጥ አለ ፍቅር ካለ እንላለን በመሆኑም ብዙዎቻችን እየተታለልን ነው ማለቴ ለእኛ ዲን ያለው ብለን እየመረጥን ያለነው ..ግሩፕ ከፍቶ ቁርዓን የሚያቀራን,,በሶሻል ሚዲያ ብቅ ብሎ የሚታይን,, ከታዋቂ ሰዎች ጋር በፎቶ ያየነውን,, በጥሩ ምላሱ ታጅቦ በቃላት ቅንብር ቃለ ረሱለሏሂ ሱለሏሁ አለይሂ ወሰለም ብሎ ንግግር የጀመረውን,, አንድ የቁርአን አያ ድምፁን በማሳመር ቀርቶ በኤፍ ቢ ብቅ ያለውን,, ድምፃቸዉን አቀነባብረዉ ምንም ሳያቁ ብቅ ያሉ ተራ ሙነሺዶችን,,ሰርግ ላይ የሚጨፍሩትን ከልቡ መዉደድ የሌለዉን ነቢይ ነቢይ የሚል ተራ ወንዶችን ሁኗል ምርጫችን

የእኛ የሴቶች ችግር።አንድን ሰው ከወደድን ስለ እሱ ማንንም መጠየቅ አንፈልግም ልክ መለአክ አድርገን እሱኑ ብቻ እናምናለን የድምፁ፣የቃላቱ፣የፎቶው ውበቶች ተደማምረው እኛነታችንን ይገዙታል እኮ ለምን??
በተለይ ደግሞ እኛ ኒቃቢስቶች ነን፣ጀልባቢስቶች ነን የእኬሌ ተማሪዎች በሂጃባቸው ፅኑዎች ነን ብለን እንፎክራለን ግን የት አለ መፎክራችን?? እኮ የት ነው??
በጣም የሚያሳዝነው ገና ኒካህ ሳያርፍብን ያለ የሌለ ማንነታችን በግልፅ አሳልፈን እንሰጣለን አካላዊ ግንኙነት ሲቀር ብቻ ትንሽ የለበስነው ሂጃብ እንኳ ሳይገብደን👇👇👇
ሳያስፈራን
እህቴ ሂጃብሽ ፣ጅልባብሽ ትልቅ ክብር አለው አላማውን አውቀሽ ልትለብሽው ይገባል ወላሂ ለመመሳሰል ብለሽ ከለበሽው ነገ ጀዛሽን ከአሏህ ነው የምታገኚው ፅኑ የአሏህ ባሪያ ልትሆኚ ይገባል ፡፡
እህቴ ሆይ!!!! በሶሻል ሚዲያ የመጣ ወንድ ሁሉ ሊያታልልሽ አይገባም እርግጥ ነው ሴት ልጆች ብዙ ወንዶች ሊጠይቁን ይችላሉ ግን የጠየቁን ሁሉ ሊያገቡን አይችሉም #100 ወንዶች ሊጠይቁሽ ይችላሉ 99 ሲወድቁ 1 የአንቺ ባል ነው ታድያ ይህንን ሰው የምትመርጭው በምኑ ነው? ? በመልኩ?? በሀብቱ?? በአንደበተ ጣፋጭነቱ?? መልሱን ለራሳችን
ትክክለኛ የትዳር አጋር ገና ከአመጣጡ በኢህትራም የታጀበ ነው ስለ አንቺ ሀብት፣ስለ አንቺ ቁመና፣ስለ አንቺ የአለፈ ማንነት ፍፁም ግድ የለውም ግን ስለዲንሽ አጥብቆ ጠያቂ ነው አሁን ሰላለሽበት ማንነት አብጠርጥሮ እና ተንትኖ ማወቅን ይሻል ስለ እሱ እሱን አይደለም ስብሰባ አውጀሽ ስለ እሱ ማንነት ብጠይቂ ፍፁም አይሸማቀቅም፣አያፍርም፣ በመሆኑም ይህንን ትክክለኛ የትዳር አጋር ለማግኘት የቃላት፣የድምፅ፣የአለባበስ ምርጫ ማካሄድ አይጠበቅብሽም በጥሩ እና ኢኽላስ በተሞላበት አንደበት ሶላትሽን ሰግደሽ አሏህን ለምኚ ለምን ትዳር የዱዓ ውጤት ነው እና
ብዙ እህቶች በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ በእንባ እየታጠቡ አገባሻለሁ ብሎ ከዳኝ ..ከኔ የሚፈልገዉን አግኝቶ እንደ ማስቲካዉ ተፋኝ ..ከአሁን ቡሀላ ወንዶች በሙሉ በአንድ ጉድጓድ ይግቡ በማለት ሲራገሙ ይታያል እህቴ ወንድ እኮ አባትሽ ነው፣ወንድ እኮ ወድምሽ ነው፣ወንድ እኮ ባልሽ ነው፣ወንድ እኮ ልጅሽ ነው ታድያ ለምን የጅምላ ጭፍጨፋ አስፈለገ?? እርግጥ ብዙ ባለጌ እና ድንበር አላፊ ወንዶች አሉ የማይካድ ሃቅ ነው ይህ ደግሞ እንዳልኩሽ ችግሩ የአንቺ ምርጫ ነው ድሮም አመጣጡ በመስኮት ነው የሚፈልገውን ሲያገኝ በመጣበት መስኮት ሰብሮ ይወጣል አበቃ የእሱ አላማ ድሮም ይህ ነበር እና……

እህቴ ሆይ!!!!" እባካችሁ ሃያእ ይኑረን አሏህን እንፍራ የሂጃብ፣የኒቃብ ትርጉሙ ይገባን ካልገባን አንልበሰው፡፡
ጠንካራ ሴቶች በደካማ ሴቶች እየተሰደቡ ነው ትላንት ስለ ሂጃብ እና ስለ ኒቃብ ስትፎክር የነበረች ሴት አንዳንዶቹ መጥፎ ቦታ እየታዩ ነዉ . ለይምሰል ነው ጅልባብ እና ኒቃብ የለበሱት ተብሎ ጠንካሮች በደካሞች ስራ ይሰደባሉ ...የሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች ይህችን ክፍተት ተጠቅመው ኢስልምናን ይዘልፋሉ ፡፡እነሱም የሙስሊሞችን ልብስ እየለበሱ ወንጀል እየሰሩበት እኛንም እያሰደቡን ነዉ፡፡ ስለዚህ እባካችሁ ክብራችንን በመጠበቅ ክብራችንን ልናስጠብቅ ይገባል ምርጫችንንም ልናስተካክል ይገባል፡፡ #ለሂጃባችን_ለኒቃባችን_ክብር እንስጠው፡፡ ሂጃብ ስንለብስ አብሮ ዉስጣችንም ይልበስ

አሁን ዘመን ላይ ብዙዎቻችን የተፈጠርንበት አላማ ከእኔ ጀምሮ ረስተናል ..መሞትን ቀብር ገብቶ መጠየቅን አላህ ፊት መቆማችንን ዘንግተንዋል....የሚገርመዉ እንኳን የተፈጠርንበትን አላማ ልናስታዉስ የምንኖርበትን አላማ እረስተናል....እንዴት ብየ እራሴን መቀየር አለብኝ?እንዴት ቤተሰቦቼን መቀየር አለብኝ?ለወደፊት ትዳር መስርቼ ልጆች ወልጄ እንዴት ነዉ የምኖረዉ ? እንዴት ነዉ ጓደኞቼ ጋር ጎረቤቶቼ ጋር ማህበረሰቡ ጋር የምኖረዉ ? ለወደፊት ስኖር መተዳደሪያ ብር ያስፈልገኛል እንዴት ነዉ ብር ይዤ እኔንም ቤተሰቦችን ማስተዳደር የምችለዉ ወ.ዘ.ተ የሚያስፈልጉን የወደፊት ለመኖር የሚያስፈልጉን ነገሮች እንኳ ለይተን ማወቅ የማንችል ማህበረሰቦች ነን፡፡ የተፈጠርንበት አላማማ ሁላችንም እረስተንዋል አንዳንዶች ሲቀሩ...
ሴቱም የሚያወራዉ ስለ ጓደኛዋ እከሌን ጓደኛ ያዘች ተጣሉ ..አታምርም እኮ እየተቀባባች ነዉ እንጂ ..... አሁን እሱ ጓደኛየ ነዉ በጣም እረብሾኛል ሲደዉል አላነሳለትም block ነዉ የማረገዉ የሚወራዉ ስለወንድ ነዉ ግን ማዉራት አልፈልግም ለጓደኞቿ ብላ እሷ ግን እሱን ለማዉራት ከእሱ የበለጠ ብሳ ትገኛለች....ሴት ለሴት ከተገናኘ አለም እንዴት አደረች ነዉ ወሬ በወሬ ነዉ ፡፡ የማያወሩት ቢኖር ስለ እድሚያቸዉ ብቻ ነዉ፡፡😉
ወንዱ ሲገናኝ የሚያወራዉ ..ዛሬ ጫት አንቅምም ወይ ? ሽሻ ቤት አንገባም ወይ ? ኳስ አናይም ወይ ?እከሌን አወጣሇት  ... እከሌን እያወራሇት ነዉ ፎንቄ አስጭሪያታለሁ ወ.ዘ.ተ
ወጣት ወንዶች በሱስ በጫት በሽሻ በማይሆን ሱሶች ይበላሻሉ ወጣትነቷቸዉን ብቻ ተደስተዉ ለወደፊት ትዳር መመስረት አቅቷቸዉ ..በሱስ ተጨማልቀዉ እንኳን ማግባት ይቅር ቤተሰብ ሲያስቸግሩ ...ሰዉ ጋር ሲጣሉ ለመቃሚያ እየተባለ ሲሰርቁ ሲገረፉ እያየን ነዉ፡፡

#ስለሆነም የተፈጠርንበትም አላማ እረስተን የምንኖርበትንም አላማ እረሳን ማለት ይህ ነዉ ወይ ከዱንያ አልሆን ወይም ከአኼራዉ አልሆን... ወንዱም ሴቱም ከሁሉም ዉጭ ሆን ማለት ነዉ፡፡
ሁላችንም የምንሰራዉ ስራ ከአፀያፊነቱ  የጀነት ካርድ የተሰጠን ይመስላል፡፡ አላህን ፍራ ሲንባል አላህ አዛኝ ነዉ ማሀሪ ነዉ እንላለን እስኪ ቁጭ ብለን ምሳችንን ሳንበላ አላህ ምሳየን አብላኝ ብንለዉ ከሰማይ ምግብ ይልክልናል እንዴ ??? አንድ ፍሬ ስንዴም አይልክልህም😊... ምሳ ለመብላት መስራት እና ስበቡን ማድረስ አለብን፡፡ ጀነትም ለመግባት አላህ ባለዉ መንገድ ቀጥ ብሎ መታዘዝ ያስፈልጋል፡፡
አላህ ከሚታዘዙበት ባሪያዎቹ ያድርገን

ካሊድ አ15 ቀን ቡሀላ ቅዳሜ ሽማግሌ እልካለሁ አለኝ
....እኔም መርሀባ ብየ ተስማማሁኝ፡፡


እነዚህ አስራምስት ቀናት ለሁለታችንም እርቃልብናለች ቀን በቀን በተደዋወልን ቁጥር ይሄ ቀን ቀረን እያልን ሲቀርብ ሲቀርብ ..ሶስትም አልፎ ሁለት ቀናት ቀረን ፡ ነገ ቅዳሜ ሁኖ ዛሬ ጁምአ ላይ ደርሰናል  
......ከዛም ጁምአ ቀን የኔ ፈተና መቼም አይለቅ ...ያልተሳበ ይሆናል ብየ ያልገመትኩት በራልኝ ስል የጨለመብኝ የሒወት አዙሪት በባሰ መልኩ አይኑን አፍጥጦ መጣብኝ...እኔ ስፈጠር እንዳትደሰቺ የተባልኩ ይመስል....ያላሰብኩት ነገር ተፈጠረ የሸይጧን መሰናክል ሁሌም ቢሆን አይጠፋም  ነገሩም ...,

#ክፍል 4⃣3⃣
ይ...........ቀ.............
.......ጥ.........ላ.............ል



Join👇👇👇

          `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም እንዴት ናችሁ ...ሁለት ቀን ያልተፓሰተበት ምክንያት አለ እናንተን ልብ ለማንጠልጠል ብየ አይደለም..ያዉ እንደተለመደዉ ሙሳፊር ከሆንክ ታሪኩን edit ለማድረግ አይመችም..የዛሬዉም በእንቅልፍ በድካም ናዉዤ ነዉ 3ቀን እንዳይጨመር edit ያረኩት...እኔ እንደሌሎች ፀሀፊዎች የሚገመግም አስተያየት የሚሰጥ ሰዉ የለኝም ለዛ ነዉ እናንተም እኔም የተሰቃየነዉ😊

ሁለት ቀን ሳይፓሰት ተናዳችሁ በአስተያየት ስሰጡ ለስድቡ አዉፍ ብያለሁ..ምክንያቴን ለተረዳችሁ ደግሞ ይቅርታ አርጉልኝ


⚠️ ቅድመ ጥንቃቄ ነገ ሀሙስ part ➍➍ ይፓሰታል፡፡ የመጨረሻዉ part እና የተወሰነ የማጠቃለያ ፁሁፍ ስለሚያስፈልግ የመጨረሻዉ ክፍል ደግሞ በአላህ ፍቃድ እሁድ ጠዋት ጨርሼ እፓስታለሁ ...ጁምአ እና ቅዳሜ አይፓሰትም ከአሁኑ ይቅርታ ይደረግልኝ...ተሳዳቢዎችም ይሄዉ ቀኑ ሳይመጣ ተናግሪያለሁ ለአፋችሁ ዚብ ለእጃችሁ አደም አስተምሩ😊

መልካም ንባብ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
     
#ክፍል ☞ አርቦ ሶስት 4⃣3⃣

ፀሀፊ ☞
#አሚር_ሰይድ

ከዛም ጁምአ ቀን ያልተሳበ ይሆናል ብየ በራልኝ ስል የጨለመብኝ የሒወት አዙሪት በባሰ መልኩ አይኑን አፍጥጦ መጣብኝ...እኔ ስፈጠር እንዳትደሰቺ የተባልኩ ይመስል...ያላሰብኩት ነገር ተፈጠረ የሸይጧን መሰናክል ሁሌም ቢሆን አይጠፋም ፡፡
 
     ቅዳሜ ካሊድ ሽማግሌ ሊልክ ጁምአ እናቴ ከአባቴ ጋር ተጣልታ ዘመዶቿ ጋር ሄደች ፡፡ በእኛ ሰፈር የሚገኙ ሽማግሌ ተሰብስበዉ ሁለቱም እንዲታረቁ ቢለመኑ ..አንታረቅም የኛ መጨረሻዉ ፍች ብቻ ነዉ መፍትሄዉ ብለዉ በጭራሽ ሊስማማሙ አልቻሉም፡፡
...እኔም ለካሊድ ደዉየ ቤተሰቦቼ እንደተጣሉ እና ሽማግሌዎቹን እንዳይልክ ነገርኩት

ጊዜያቶች እየነገዱ ነዉ....አባቴ ሌላ ሴት ለማግባት እየፈለገ ነዉ...እናቴም ፍርድ ቤት ከሳ ንበረቱን ተካፍላ ከቤት ይዉጣልኝ እያለች ነዉ፡፡ ነገሩ በጣም ሲጠና ...አባቴ ለልጆቼ ብየ እታረቃለሁ ቢልም ..እናቴ ግን በጭራሽ አልታረቅም ብላ አሻፈረኝ አለች.... የሰፈር ታዋቂ ሸሆች... የመስጊድ ኢማማችን ሳይቀር ቢለምኗት እምቢ አለች፡፡


እኔ እና ካሊድ ለመጋባት 100% ጨርሰናል ሁለታችንም ለትዳር ልባችን ቢንጠለጠልም ግን እናት እና አባቴ ተለያይተዉ በሚኖሩበት ቤት በተበታተነ ቤተሰብ ለማን ሽምግልና ይላካል??? ዱአ ከማድረግ ዉጭ ምንም አማራጭ የለም...

   ደግሞ አዲስ ነገር የማይፈጠር የለም ...ሚፍታህ ደወለልኝ እና ...ነዋል አንቺን ማግባት ነዉ የምፈልገዉ ነዋል ከልቤ ነዉ እወድሻለሁ ሽማግሌ ልልክ ነዉ አለኝ
......እኔም ሚፍታህ አሁን መቼም ቢሆን የአንተ መሆን አልችልም ለሁሉም ጊዜ አለዉ አንተም በጊዜህ እኔን ትተህኛል...አሁን እኔም ልቤ የሌላ ነዉ ...ተስፋ ቁረጥ እንደፈለክ የምከፍተዉ የምዘጋዉ የቤትህ በር አይደለሁም አልኩት ቆጣ ብየ
 
ሚፍታህ ከመደወሉ ከአንድ ቀን በፊት ኮሌጅ ስሄድ አግኝቶኝ ልታገቢ ነዉ እንዴ ?ብሎ ጠይቆኝ
እኔም ቀለበት አድርጊያለሁ ቅርብ ቀን ሽማግሌ ይልካል ላገባ ነዉ ብየዉ ነበር..ለዛ ይሆናል የደወለዉ

አይጠቅምም ብለዉ የጣሉት እቃ ሌላ ሰዉ አንስቶ ሲጠቀምበት ምነዉ ባልጣልኩት ብለዉ ይቆጩ የለ... ..ሚፍታህ እኔን ትቶኝ ላገባ process ላይ መሆኔን ሲያቅ ..እንደገና ካላገባሁ ሙቼ እገኛለሁ..ሽማግሌ ልልክ ነዉ እያለ አሁንም ተስፋ ያልቆረኩ ይመስለዋል..ሴት ልጅ ስወድ ወደደች ነዉ ከጠላች ደግሞ በእሷ መስፈርት ሁሉንም አሟልተህ ብትገኝ ከጠላችህ መቼም በልባ መግባት እንደማችል እንደነ ሚፍታህ ያሉ ወንዶች ዘንግተዉታል... መቼም ካሊድን በማንም የማልቀይረዉ እዉነተኛ የትዳር አጋሬ ነዉ፡፡

✿✿✿ ምርጥ ጓደኛየ መፍቱሀም ተመርቃ የግል ሆስፒታል ዉስጥ ገብታ እየሰራች ነዉ..

✿✿✿ብሩክታይትም ቢላል የሚባል የወንዶች የጀመአ አባል ብሩክታይት ዲነል ኢስላምን አስተምራለሁ ቁርአን አቀራታለሁ ብሎ መፍቱሀን እና እኔን አማከረን ...እኛም ብሩክታይትን አማከርናት ... ቢላልን ታቀዋለች በትዳር ጥያቄዉ ተስማማች .. ስሟንም በራሷ ፍቃድ ብሩክ ታይት ሳይሆን ራዉዳ ነኝ ብላ ከቢላል ጋር እህል እና ዉሀቸዉ ገጥሞ በትዳር አለም አብረዉ መኖር ጀምረዋል፡፡

✿✿✿ ካስታወሳችሁ በአለፉት ክፍል ናርዶስ(በአጎቷ እና በአባቷ ጓደኛ በልጅነቷ የተደፈረችዉ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ተማሪ ነች ለሚመጣዉ አመት ትመረቃለች...ዩኒቨርስቲ ገብታም እንደዋወላለን.. የወደፊት እቅዷ በልጅነታቸዉ ለሚደፈሩ ሴቶች ምን ፕሮጀክት ብነድፍ ..ምን ስራ ብሰራ ይሄንን ጉዳይ በቸልተኝነት እንዳይታለፍ እና ይህን በደል በሴቶች ላይ የሚሰሩት ወንዶች እንዴት ማስቆም እንዳለባት የዘወትር እቅዷ እንደሆነ ብዙ ቀን ነግራኛለች፡፡

✿✿✿ የሱፍ (ለሚፍታህ ነዋልን ዳረኝ ብሎ ስልኩን የሰጠዉ) እሱ ደግሞ ሚፍታህ ጋር አንዴ ተጣልተዉ...ነገሩ ከብዶ ፓሊስ ጣቢያ ድረስ ሂደዉ ነበር በሽምግልና ታረቁ ቢባል የሱፍ በጭራሽ አልታረቂም እበቀለዋለሁ እንዳለ ቂም እንደያዘ .. በመጨረሻም የሱፍም ቤተሰቦች እነሱዉ አምጥተዉ እሱም ጎጆ ቀልሶ እየኖረ ነዉ፡፡

✿✿ ሚፍታህም በንዴት ይሁን አስቦበት አላቅም እኔ ላገባ ነዉ ከአሁን ቡሀላ አንተ እና እኔ አንድ ላይ መሆን አንችልም ካልኩት ቡሀላ ...ብዙም ሳይቆይ አንድ ወር ባልመላ ቀናት ዉስጥ እኔን አናዳታለሁ ብሎ አስቦ ይሁን ..ትዳሩን አምኖበት ይሆን...ነዋልን ልቀደማት ብል አስቦም ይሆን አላቅም እሱም የትዳር ጎጆዉን ቀልሷል

✿✿✿ ካሊድም የቤት እቃ እያማሏ ነዉ ፡፡ እኔም ነገሮች እስከሚስተካከሉ ብየ ጅማ የሚገኝ የመንግስት ሆስፒታል በተመረኩበት ፊልድ ማገልገል ጀመርኩኝ...አልሀምዱሊላህ አባቴ ያሰበዉ ደረጃ ደረስኩኝ ..

ሆስፒታል መቼም የብዙ ሰዉ ብሶት መቀበያ አይደል....እንደ እኔ በልጅነታቸዉ የተደፈሩ ሴቶች በጣም ብዙ ገጥመዉኛል ..ልጆችን በማፅናናት ከጎናቸዉ በመሆን እነሱን ማገዝ የአእምሮ ጭንቀት እንዳይዛቸዉ የስነልቦና አገልግሎት መስጠት የዘወትር ስራየ ነዉ. .በተጨማሪም በፍቅር ለተጎዱ ሴቶች ...እንደ እኔ በቤተሰብ ፍቅር ዉጭ ለአደጉ ልጆች..በተለያዩ ጉዳዮች ዲፕሬሽን(በአእምሮው ጭንቀት) የተጎዱ የዱንያ የአኼራ እህቶቼን ከጎናቸዉ በመሆን እነሱን መንከባከብ በሀሳባቸዉ ተረድቼ መፍትሄ ስሰጥ ለኔ የዉስጥ ደስታ ሰላም ይሰጠኛል፡፡ የሰዉ ልጅ ደስታዉ ብቻዉን መቀየሩ ደስታን ማግኘቱ ሳይሆን በእሱ የተነሳ ስንት ሰዉ መቀየሩ መደሰቱ ታላቅ ደስታ ነዉ..

የሚገርማችሁ እዛዉ ጤና ጣቢያ በሴት ልጆች ላይ የሚደርሰዉ በደል ሳይ የኔ ምን አለበት አልሀምዱሊላህ ያልኩባቸዉ ብዙ ቀናቶች አሉ..
እኔ ከገጠመኝ በታላቅ ወንድሞቻቸዉ የተደፈሩ ልጆች ገጥሞኛል..በተዘዋዋሪ ጭካኔ የበዛበት ዘመን መሆኑ ያሳዝናል ብዙ ህፃናት በአባቶቻቸዉ ተደፍረዉ የሚመጡ ብዙ ልጆች ገጥመዉኛል፡፡እኔ አንድ ሴት ነኝ ከጎኔ ማን አለ?? ሁሉም ከጎኔ ባይሆኔም ግን እንደ እኔ ተብድለዉ በሆዳቸዉ አፍነዉ የሚኖሩ ቤት ይቁጠረዉ,..... መቼ ድረስ ነዉ የሴት ልጅ እምባ መዉረድ የሚያቆመዉ ??? ሁሌም በልቤ ቁጭት አለ ታዳ ምን ያደርጋል አንድ ሰዉ አስቦ አንድ በሬ ስቦ አይሆንም...እኔ የራሴን ታሪክ በፁሁፍ ዘረገፍኩት እንጂ ብዙ ሴቶች አሁን ድረስ ዛሬ ከነገ ይሻላል ቢሉም ግን የብስ እየጨለመ የሚሰቃዩ ለቁጥር አይገባም. ... እንደ እኔ እንቅልፍ አጥተዉ የሚኖሩ ሴቶች አይናገሩ ሰሚ የለ ....ለማን ይነገር?? በእንባ ጎርፍ ለፈጣሪ አቤት ከማለት በቀር ፡፡ ስለሆነም ወንዶች እባካችሁ ለሴት ልጆች እዘኑ ይሄ ሁሉ ለቅሶየ ስቃየ በኔ በራሴ የመጣ አይደለም በጨካኝ ስሜቱን መቆጣጠር በአቃተዉ ወንድ የተፈጠረብኝ በልጅነት መደፈር ነዉ ፈጣሪ ሁላችንንም ልቦና ይስጠን

ቢያንስ ከ5 ወራት ቡሀላ በስንት ሽምግልና አልሀምዱሊላህ እናት እና አባቴ ተስማምተዉ መልሰዉ አብረዉ መኖር ጀመሩ ..

እናት እና አባቴ ታርቀዉ ብዙም ቀን ሳይቆዩ በቤተሰብ የትዳር ጥያቄ መጣ ...
ማታ ላይ ሳሎን ቁጭ ብለን አባቴም፡- ነዋል ይሄ መታለፍ መመለስ የሌለበት ትዳር ነዉ..እኛ እንተማመንበታለን ጥሩ ሰዉ አላህን ፈሪ ነዉ ፡፡ነዋል እኔ አባትሽ ለምወድሽ ልጄ መጥፎ ምርጫ እንደማልመርጥ ታቂያለሽ ..እኔም አንቺ አሁን የመጣዉን ትዳር እንድታገቢ ምርጫየ ነዉ እሺ በይኝ አለኝ

ክፍል 4⃣4⃣
ይ.......ቀ........
.......ጥ.......ላ.....ል
2024/09/23 16:34:00
Back to Top
HTML Embed Code: