Telegram Web Link
የህይወት ምስቅል ➋➐.mp3
19.4 MB
😔 #የሕይወት_ምስቅልቅል


ክፍል ☞
#ሀያ_ሰባት 2⃣7⃣
◉ አቅራቢ☞ አሚር ሰይድ
● የጊዜዉ ☞ ቆይታ 20 ደቂቃ
◎ Size ☞ 19 mb
> በislmic school ቻናል የቀረበ
#የሰብለ መጨረሻ በaudio ያዳምጡት😔
🔰ይህንን እዉነተኛ ታሪክ በአማረ መልኩ በAUDIO አቅርበናል
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

የመጨረሻዉ ክፍል ይቀጥላል.......
join

www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science

በYUOUTUBE 👇👇
https://youtu.be/i1c01__fehA
💧አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂
#SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
     
#ክፍል#አስራ_ስምንት 1⃣8⃣

ፀሀፊ ☞
#ዘቢባ_ሱልጣን


ተማሪዎቹ ከአቅማችን በላይ ሁነዋል። ፈቱዲን ያለው ንግግር ትዝ አለኝ። ጀመአው ፈርሷል ማለት ይቻላል ብሎ ነበር አምና።አሁን ግን የምር ፈርሷል ማለት ይቻላል። ሰአዳ እና መርየም ብዙ ጊዜ አንዋር እና ብሩክ ከሚባሉ ልጆች ጋር አብረው ሲንቀሳቀሱ እመለከታለው። እኔና ዘቦ ሰአዳን እና መርየምን ለማስተካከል በጣም እየጣርን ነው። ግን ሊሳካልን አልቻለም። እንዳውም እየሸሹን መተዋል። ዛሬ ፓርቲ አለ ብለው እቅድ ሲያወጡ መስማት የተለመደ ነው።

ሰአዳ ግልምጫዋ አያስቀርብም መርየም ግን ገር ናት ፈገግታዋ በራሱ ይስባል። አሰላሙ አለይኩም ስንላት ወአለይኩም ሰላም ሳትለን አታልፍም። ከዚህ ሱስ እንድትወጣ በምንጠይቃት ጊዜም በኔ አልተጀመረም እኮ ደሞም እንዴትም ብዬ መውጣት አልችልም ሞክሬ ያቃጠኝ ነገር ነው ትለናለች ፡፡ ሰይጣኗ የተነሳ ቀን ደሞ ምናገባቹ አቦ ፍቱኝ ቀኔን አታበላሹ ትለናለች።

እንደተለመደው የአሚሮች ሹራ ላይ ስለ ተማሪዎቹ መበላሸት አወራን እናም ቀጣይ የዳእዋ ፕሮግራም በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲሆን እና የንግግር ችሎታ ያለው ኡስታዝ እድዲጠራ ወሰንን። የኡስታዝ ምርጫ ላይም ትንሽ ከተከራከርን እና ከተመካከርን በኋላ ኡስታዝ ሙሀመድ ፈረጅ(አይ ዱንያ!) በሚለው ትምህርቱ አፍሪካ ቲቪ ላይ የምናውቀው ኡስታዝ እንዲጠራ ወሰንን እና ተለያየን ።ቀኑ ደረሰ ተማሪዎችም እንዳይቀሩ ብዙ እንቅስቃሴ ከልመና ጋር አደረግን። አልሀምዱሊላህ ፕሮግራሙ ላይ ሰአዳን እና መርየምንም ጨምሮ በርካታ ተማሪዎች ተገኝተዋል።


ኡስታዝ ሙሀመድ ፈረጅ ንግግሩ ድንቅ ነው ቀልብ ይስባል ሲናገር ቁጣ እና እልህ በተሞላበት ስለሆነ እንድናዳምጠው ያስገድዳል። ስለ ተማሪዎች አለባበስ እና ሁኔታንም ጨምሮ ስለ ሰላት አለመስገድ ብዙ ነገር አስተማረ። ግማሹ ተክዟል ግማሹም ያለቅሳል ሳናውቀው ሰአቱ ሄደ 10 ደቂቃ የቆየን ሳይመስለን በንግግሩ እንደተመሰጥን ፕሮግራሙ አለቀ።ተማሪዎቹ ሄዱ እኛ የተበላበትን ሰሀን ማጠብ እና ቦታውን ማፀዳዳት ጀመርን። ኡስታዝ ሙሀመድ ፈረጅም በርቱ በዚሁ ቀጥሎ ለትውልድ አሻራ ጣሉ እኔም በፈለጋችሁ ጊዜ እገኝላችሆለሁ ብሎን ሄደ። ከዛን ቀን የዳእዋ ፕሮግራም በኋላ ብዙ ተማሪዎች እንደ አዲስ መስገጃ ቤታችን መጉረፍ ጀመሩ። ትግስትም ስራዬ ብላ የጀመአችን ፕሮግራም ከኛ እኩል ትከታተላለች።ሰአዳ እና መርየም ግን የባሰ ስራቹ ላይ በርቱ የተባሉ ይመስል ብሶባቸዋል።


የጀመአው ፕሮግራም ላይም መገኘት አቆሙ።መርየም ከአንዋር ጋር ሰአዳ ደሞ ከብሩክ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምረዋል።ሰአዳ የምትኖረው ከአያትዋ ጋር ስለሆነ አያትዋን አታላ ለፓርቲ እና ለመጠጥ መውጣት ለስዋ ቀላል ነው። ዘይባ ጋር ላድር ነው ብላ በእኔ አሳባ ወጥታ ከ ብሩክ ጋር ታድራለች። መርየም የምትኖረው ብቻዋን ስለሆነ ቁጥጥር የለባትም። ቤተሰቦችዋ ያሉት ገጠር ሲሆን ያሳደገቻት አክስትዋ ናት።ሆኖም ዘጠነኛ ክፍል መጨረሻ አካባቢ በዚህ ባህሪዋ ከ አክስትዋ ጋር ስለተጣላች ከቤት ተባራ ሌላ ቤት ለብቻዋ ተከራይታ ነው የምትኖረው። ለዛም ነው 10 ኛ ክፍል እኛ ትምህርት ቤት የመጣችው። የቤት ክራይ የምትከፍለው አብራቸው ከምታድራቸው የተለያዩ ወንዶች ብር እየተቀበለች ነው።


ጀመአችን ተዳክሞአል ብር የሚያዋጣ ሰው እና እስፖንሰር በማጣታችን ምክንያት የምንረዳቸው የቲሞች ቁጥር 10 ደርሷል። አመቱ እየተገባደደ ነው። አንድ ቀን ለታ It (informastion tecnology) ትምህርት ልንማር ኮንፒተር ወዳለበት ክፍል አመራን። የ አይቲ ላብራቶሪያችን ካለንበት ፎቅ ወርደን ሌላኛው ፎቅ ገብተን ስለሆነ የምንማረው ርቀት አለው። አይቲ ላብ ገብተን ወንበራችንን ይዘን እንደተቀመጥን ነበር መፅሀፍ መርሳቴን ያስታወስኩት።

አስተማርያችንን እስማኢልን አስፈቅጄ መፅሀፌን ላመጣ ወደ ክፍላችን አመራሁ። ክፍላችን 2ተኛ ፎቅ ላይ ነው ሚገኘው። በሩ አልተዘጋም ገርበብ እንዳለ ነው። ክፍት አድርጌው ወደ ቦታዬ አመራሁ።መፅሀፉንም ከቦርሳዬ አውጥቼ በእጄ እንደያዝኩ የሆነ ድምፅ ተሰማኝ።

#Part 1⃣9⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

Join👇👇

www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
💧አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂ #SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
      #ክፍል ☞ አስራ ዘጠኝ 1⃣9⃣

ፀሀፊ ☞ #ዘቢባ_ሱልጣን


መፅሀፉንም ከቦርሳዬ አውጥቼ በእጄ እንደያዝኩ የሆነ ድምፅ ተሰማኝ
እእእእእእእ እእእእእ ቀስ.....ቀስ.... እእእእእእ የሚል የሴት ድምፅ።ፅው ፅው ፅው የሚለው ትቦ ውስጥ የሚኖሩት አይጦች ልፍያ ድምፅም መሰለኝ። ከክፍላችን ጣራ ላይ ያለው ክፍል ተማሪዎች እርግጫም መሰለኝ ብቻ አላወኩትም ወደ ኋላ ለመዞር አንገቴ አልዞር አለኝ ፈራሁ። አንዳች ነገር በ ፊልም እንደምናየው ሆረር የሚሉት ነገር የመጣብኝ መሰለኝ።

አንገቴን ሸርተት ባደረኩ ቁጥር ገና ከመዘሮ በጥፊ የሚደረግምብኝ ሰው ያለም መሰለኝ ብቻ እንደምንም ዞርኩ ዴስኩ ላይ ምንም አይታይም የሰው ዘር የለም።ሶስት ጊዜ አኡዙቢላህ አኡዙ ቢላህ አልኩ።ድምፁ ግን አሁንም አለ። የጥግ ወንበር ስር ወደ መሬት ስመለከት እንደ እንስሳ የሚንከባለሉ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ተማሪ ተመለከትኩ። ሰአዳ እና ብሩክ ...ያየሁትን ማመን አቃተኝ እውነት መሆኑን ላለማመን አይኔን ውሸት ነው ቅዠት ነው እያልኩ ልደልለው ሞከርኩ ግን አልቻልኩም እውነትን መደበቅ አይቻልማ!!! የእግሬ ኮቴን እንኳን መስማት እስኪሳናቸው በር ሰው ይመጣ ይሆናል ብለው እንኳን ማሰብ እስኪሳናቸው ድረስ በስሜት ጦዘዋል እንባዬ ከጎንጬ ተንቆረቆረ እያዞረኝ ከክፍሉ ድምፅ ሳላሰማ ወጣሁ።

በማግስቱም ለማንም ሳልናገር ሰአዳን ልመክራት ወሰንኩ እናም እፈልግሻለሁ ብያት ትናንት ስለሰራችዉ ስራ አናገርኳት
.... እስዋም ግን ምነው አንቺ ድንግል ነኝ ማለትሽ ነው? አታስቂኝ የኛ ገሀድ ስለወጣ ነው እንዴ ሁልሽም እናቅሻለን አንገት ደፊ ሀገር አጥፊ የናንተንስ ማን አየላቹ? ስንቱን የቤት ልጅ የተባሉ አይደል እንዴ እዛ ምናየው ብላኝ ሄደች

የሰአዲ እንዲህ መበላሸት በጣም ነው የገረመኝ አሳዝኖኛልም ጭምር። የስዋ ብቻ አይደለም የሁሉም ሙስሊም ተማሪዎች መበላሸትም እረፍት ነስቶኛል። አንድ ቀን ለት ጥዋት ሰልፍ ላይ ዳይሬክተራችን አጭር መልእክት አስተላለፈ እያንዳንዱን ጥጋበኛ ለቅመን እናባርራለን ሲል ፎከረ።ንግግሩ ከተማረ ሰው አይጠበቅም። ሁሌም ጋጠወጥ ንግግር ይናገራል።

ሳዲቅ የሚባል ልጅ ያለ ጥፍቱ አባሮታል።ምን ሆነ መሰላችሁ ሳዲቅ ሁሉም ተማሪ እንደሚያደርገው አስተማሪ እስኪመጣ ድረስ በርጋ ቆሞ እንዳለ ዳይሬክተራችን ደረሰበት ከዛም
ዳይሬክተሩ፦ አስተማሪ የለም?
ሳዲቅ፦-... አው
ዳይሬክተሩ፦...እና እንደሸሌ(ሴተኛ አዳሪ) በር ጋር ምን ትሰራለህ?
ሳዲቅ፦...ምነው ሄደህ ታውቃለህ እንዴ?

በማለቱ ነበር የተባረረው።ለ3 አመት የትኛውም ትምህርት ባት እንዳይማርም ታግዷል። በእርግጥ ሳዲቅም ጥፋት አለበት የዳይሬክተሩ ግን ይብሳል።

አንዲት ተማሪም ተኳኩላ ሊፒስቲክዋን ተቀብታ ሽቶዋን ነስንሳ ሲያያት ምነው ከሽርሙጥናው ቤት ነግቶብሽ ነው እንዴ የመጣሽው ብሎ አባሯት እናትዋ መታ ልጄን እንዴት እንዲ ትናገራታለህ?? ባለችው ጊዜ ሽርሙጥና እንድትሰራ መንገድ የከፈትሽላት አንቺ ነሽ ማለት ነው ብሎ ተናግሯት አገር ጉድ ብሏል።
ነገሩ የገባን በኋላ ላይ ነበር።ለካ የሴቶች ሽንት ቤት ኮርኒስ ውስጥ ተደብቀው የሚያጨሱት ተማሪዎች ተይዘው ተባረው ነው ሲደነፋ የነበረው።


የተያዙት ተማሪዎች ደግመው ድላችን ትምህርት ቤት መማር እንዳይችሉ ታግደው ተባረሩ። የሽንት ቤቱ ኮርኒስ እና የወንዶች እና የሴቶች ሽንት ቤት ማገናኛ ያደረጉት ያፈረሱት ግንብም እድሳት ተደረገለት። እኛም በጣም ቁጥጥር በዛብን። ለጥቂት ወራት እስኪረጋጋ ድረስ ምሳ ሰአታችንን ወደቤት ወይም ወደ መስጊድ እንዳንሄድ ተደረግን ሁሉም ተማሪ ትምህርት ቤት መዋል ጀመረ።በነዚህ ተማሪዎች ምክንያት ለብዙ ወራት ትምህርት ቤቱ መነጋገሪያ ርእስ ሆኖ ነበር።

በየተኬደበት የሚወራው ድላችን የሚባለው ትምህርት ቤት እኮ አሺሽ ሲያጨሱ ተማሪዎችን ያዘ የሚል ወሬ ነበር የሚሰማው።ብዙ ወላጆችም ልጆቻቸውን ከዛ ትምህርት ቤት አስወጥተው ወደ ሌላ ትምህርት ቤት አዘዋውረዋል...


#Part 2⃣0⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

Join👇
👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
💧አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂
#SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
     
#ክፍል ☞ ሀያ 2⃣0⃣

ፀሀፊ ☞
#ዘቢባ_ሱልጣን

ብዙ ወላጆችም ልጆቻቸውን ከዛ ትምህርት ቤት አስወጥተው ወደ ሌላ ትምህርት ቤት አዘዋውረዋል...


የመርየም እና ሰአዳ ጉዳይ አይምሮዬን አላሳርፍ ሲለው ዘቦን ለምን ከነሱጋር ተመሳስለን ቀስ በቀስ አንመልሳቸውም?? ስል ጠየኳት።
.....ዘቦም በፍፁም አላህ ከሀዲዎችን አትምሰሏቸው ብሏል እኮ አለች፡፡ እኔ ግን ሀሳቤን አልቀየርኩም ሰአዲን እና መርየምን የምትቅሙበት ቤት ማየት እፈልጋለሁ አልኳቸው ያለምንም ማቅማማት እሺ ብለው ወሰዱኝ።

ቤቱ በተማሪ ተሞልቷል ግን ከመርየም እና ከሰአዳ ውጪ ምንም ሙስሊም ተማሪ አላየሁም። ሄሄሄ.....ጨቅጫቃዋ መጣችችችች እያሉ ጮሁ።ይሄ ስም የተሰጠኝ እየዞርኩ አሰላሙ አለይኩም እያልኩ ሰላት እንዲሰግዱ በመጨቃጨቄ ነው።ሙስሊም ተማሪ ባለማየቴ ተደሰትኩ። ወደ ክፍሉ ከገባሁ 30 ደቂቃ ያክል አስቆጠርኩ እኔ ግን አንድ አመት ያክል የቆየሁ ነበር የመሰለኝ በጣም ይጨንቃል ሽታው ያቅለሸልሻል።ሁሉም እየመጣ እንቺ ንከሺ እያለ ጫት ይሰጠኛል።ተቀብዬ እግሬ ስር አስቀምጠዋለው። አንዳንዱ ሺሻ ይስባል።አንዳንዱ ደሞ ሀሺሽ ይስባል። ተማሪው አንድ አንድ እያለ ይመጣል። ክፍሉ ከገባሁ 1 ሰአት አካባቢ ሆነኝ።


አንዲት ጅልባቢስት መጣች።እጅዋ ላይ ጓንት አጥልቃለች እግርዋም እስከላይ ካልሲ (ስቶኪንግ) ስላደረገች አይታይም።አለባበስዋ ትክክለኛ ሙስሊምን ይገልፃል። ምን ልትሰራ መጥታ ነው? እንደኔ ለማየት ነው ብዬ እራሴን አሳመንኩ።ወደውስጥ ዘለቀች ሀይ ጋይስ...! ብላ ሰላምታዋን ሰጠቻቸው።አይኔ ከእሷ ጋር ይንከራተታል ስትቀመጥ ዝቅ ይላል ስትቆም ወደላይ ያፈጣል። ቅድምያ ቦርሳዋን አስቀመጠችው።ቀጥላም ጅልባብዋን አወለቀች ግራ ተጋባሁ።አሁንም ቀጥላ ሂጃብዋን አውልቃ ቁጭ አለች። ለካ ሙስሊም ተማሪ የሌለ የመሰለኝ ሁሉም ሂጃቡን አውልቆ ስለሚቅም ነው። እንባዬ መጣ ስሜቴን መቆጣጠር አቃተኝ።እራሴን አመመኝ።የሺሻው እና የሀሺሹ ሽታ ሆዴን አገለባበጠው።ተዝለፍልፌ ወደቅኩ እራሴን ሳትኩ።

ወንዶቹም ይሄንን ተጠቅመው ሊጫወቱብኝ ሲሉ መርየም ጓደኛዬን አሳልፌ አልሰጥም ብላ ታደገችኝ። እዛ ቦታ የሚታየው ነገር ይዘገንናል።ሁሉም ወንድ እና ሴት ጥንድ እና ጥንድ ሆነው ነው የሚቀመጡት።ሌላው የገረመኝ ወንዶቹ በአንድ እጃቸው የሺሻ ገመድ ይዘው በአንድ እጃቸው ደሞ እሴቱቹ አካል ላይ ነዉ.....። ሴቶቹም ዩኒፎርማችን ሸሚዝ እና ሹራብ ስለሆነ ሹራቡን አውልቀው ሸሚዙን ጡታቸው አካባቢ ከፍተው ያቀብሏቸዋል። ስሜት መቆጣጠር ሲያቅታቸው ለዚህ ጉዳይ መፈፀምያ ተብሎ ወደተዘጋጀው ክፍል ያመራሉ።

አንዱም መልከመልካም ወጣት ነይ እንመቻች አዲስ ትመስሊያለሽ ሲለኝ --------በእድሜ ዘመኔ ያጠራቀምኩትን ስድብ ሁላ አወረድኩበት።መርየምም አዲስ ስለሆበች ነው ሌላ ቀን ስትለምደው ብላ ጠቀሰችው።እዛች መባለጊያ ክፍል አንዱ ተረኛ ፈፅሞ ሲወጣ ሌላኛው ይቀጥላል።ስሜቱን መቆጣጠር ያልቻለም ተራውን ሳይጠብቅ ተደርቦ ይገባል። በጣም የገረመኝ ያሻቸውን ፈፅመው ስሜታቸውን ካበረዱ በኋላ ሴቶቹም ወንዶቹም ሌላ ወንድ ጋር ወይም ሌላ ሴት ጋር ሄደው የሚቀመጡት ነገር ነው በሄዱበት ቦታም ከሌላ ሰው ጋር ልክ እንደዛው ስሜት ቀስቅልሽ አስነዋሪ ነገር ካደረጉ በኋላ ስሜታቸው ሲመጣ በድጋሚ ተያይዘው ወደዛች ክፍል ይገባሉ።በቀን ውስጥ አንዲት ሴት ከተለያዩ ወንዶች ጋር ስትወጣ አይቻለው። ታዳ እነዚህ ተማሪዎች ለHIV ኤድስ ተጋላጭ አይደሉ እንዴ???


የማየዉ ነገር ዘገነነኝ ከዚህ በላይ እዛ መቆየት አልፈለኩም። ሙስሊሙንም ክርስትያኑንም የሚመለከት ንግግር ተናገርኩ።ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እኔ መፅሀፍ ቅዱስንም ቁርአንንም አንብቤያለው የትኛውም ሀይማኖት ይሄን ተግባር አይደግፍም ፈጣሪያቹን ፍሩ ከዚህ ዘግናኝ ሱስ እራሳቹን አርቁ ይሄ እኮ በቁም መሞት ነው። ለነጋቹ አስቡ......................ብዙ ነገር ተናገርኩ ግን አንድም የሰማኝ የለም።

ቀልድ ያወራሁ ይመስል ክትክት ብለው ሳቁ። በስተመጨረሻም መርየምንን እና ሰአዳን ቻው ብዬ ወጣሁ።ልብሴ ይሸታል መንገደኛው ሁሉ ያጨስኩ ይመስለዋል ብዬ ፈራሁ።አላህዬ ወደዚህ ቦታ በመምጣቴ ምህረትህን ለግሰኝ እያልኩ ተማፀንኩት።


በማግስቱም ለዘቦ እያንዳንዱን ነገር ነገርኳት።መጀመርያም አትሂጂ ብዬሽ ነበር ጥፋቱ የአንቺ ነዉ ብላ ወቀሰችኝ።

ከመሄዴ በላይ ያበሳጨኝ የጅልባቢስይዋ ጉዳይ ነው። ከኛ በፊት ከነበሩት አሚሮች መካከል አንድዋ እንደነበረች ሳውቅ ደግሞ ይበልጥ ተበሳጨሁ። ሰው እንዴት ለስሜቱ ይገዛል? እንዴት በስሜት ይነዳል? ራስን መቆጣጠር እንዴት ያቅታል?

የእየሩስ አብሮ አደጌ ወንድም ዳግም ትዳር መሰረተ።ከመሰረተም በኋላ ቤቱ እንድትለቅለት አላስቀምጥ ሲላት ቤቱን ለቃለት ከጎረቤቶቿ ጋር መኖር ጀመረች። ጎረቤቶችዋም ይሄን የማድረግ መብት የለውም አንቺም ሀቅ አለሽ ብለው በፍርድ ቤት ተከራክረው ቤቱን እንድትካፈል አድርገውላታል።

በሌላኛው ቀን ደሞ ሌላ አስደንጋጭ ዜና ተሰማ


Part 2⃣1⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል




Join👇👇

www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
የሕይወት ምስቅልቅል #የመጨረሻው ክፍል በወንድም #ማሜ,#ደስ የሚል #ፉፃሜ�
😔 #የሕይወት_ምስቅልቅል


#የመጨረሻዉ_ክፍል
አቅራቢ☞ ማሜ
● የጊዜዉ ☞ ቆይታ 13 ደቂቃ
◎ Size ☞ 12 mb
> በislmic school ቻናል የቀረበ


🔰ይህንን እዉነተኛ ታሪክ በአማረ መልኩ በAUDIO አቅርበናል
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢



በYUOUTUBE Subscribe ያድርጉ👇👇
https://youtu.be/p9nvP09Pfjs

🔷ታሪኩን በVOICE ጨርሰናል ፡፡ ለወደፊት የኔ የፃፍኳቸዉ ታሪኮች በVOICE ልንሰራ ስለሆነ መጨመር መቀነስ ያለበት እና ማስተካከል ያለብንን በዚህ BOT አድርሱን👇👇
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
💧አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂
#SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
     
#ክፍል ☞ ሀያ አንድ 2⃣1⃣

ፀሀፊ ☞
#ዘቢባ_ሱልጣን


በሌላኛው ቀን ደሞ ትምህርት ቤታችን ላይ ሌላ አስደንጋጭ ዜና ተሰማ
128 የድላችን ተማሪ ሺሻ ቤት እንደተያዘ ተሰማ። ከምንም በላይ የሚገርመው ከ 128ቱ 85ቱ ሙስሊም ተማሪዎች መሆናቸው ነው።ከ85ቱ ደግሞ 50ው ሴቶች ናቸው።
ከተያዙት መካከል መርየም አንዋር እና ሰአዳ እንዲሁም ብሩክ እንዲሆኑ ምኞቴ ነበር።ነገር ግን እነሱ የዛን ቀን ሌላ ቤት እንቀይር ብለው ወተው ስለነበር አልተያዙም።

ወላሂ በሙስሊሙ ተማሪ ብዛት ከልቤ አዘንኩ። የተማሪው ወላጆች እያነቡ የኔ ልጅ እንዲህ አያደርግም ልጄ ከሳምንት ሳምንት ትምህርት ቤት ነው(ናት) ቅዳሜና እሁድም ላይብረሪ ነው ሚያሳልፈው(ምታሳልፈው) እያሉ ወገባቸውን ይዘው ይከራከራሉ። አንዳንዱ ወላጅም በውንጀላ እንከስሀለን እያሉ ዳይሬክተራችን ላይ ይደነፋሉ።


ጁመአ ሳይደርስ አስቸኳይ ሹራ አደረግን ሁሉም አነባ መፍትሄው ምን እንደሆነ ተወያየን ግን የተሻለ ሀሳብ አላመጣንም። ሁሉም አሚር የጥሪ ስራ እንዲሰራ ተወሰነ ግን ለውጥ አልተገኘም። ትውልዱ ቀልቡ ደርቋል መሰለኝ በአንዱ ጆሮው ሰምቶ በአንዱ ጆሮው ያፈሰዋል። መርየምም ከ አንዋር ጋር የፍቅር ጨዋታዋን ቀጥላለች። አንዋር የሀብታም ልጅ ነው በእድሜውም ከኛ ተለቅ ይላል። ዲነኛ ቤተሰብ አለው እሱ ግን እንደምናውቀው። ማጨስ መጠጣት መቃም ስራው ነው


ሁኔታው ያላማራቸው ቤተሰቦቹም ማግባት አለብህ ብለው ወስነው ማትሪክ ሳይፈተን ያንተ መማር ትርጉም የለውም ብለው ትምህርት አስትተውታል። መርየምን እኔ ለማግባት ዝግጁ ነኝ እንጋባ ብትለውም ማግባት የምፈልገው ከነክብርዋ የተቀመጠችን ሴት ነው ንፁህ የሆነች ጋጠወጥ ያልሆነች ቤተሰቦቼ የመረጡልኝን ነው ማገባው ብሎ ቅስሟን ሰባብሮ ጢባጢቤ ተጫውቶ እንደ ሸንኮራ መጦ ቱቱቱ ብሎ ተፍቷቷል።

እስዋም በብስጭት ካገኘችው ወንድ ጋር እየተኛች እየተጃጃለች ትምህርቷን አቋረጠች። ሰአዳም እንደመርየም እንዳትሆን በመስጋት ግልምጫዋን ተጋፍቼ ልመክራት ወሰንኩ። ብሩክ ነገ ይተውሻል አላህ ግን መቼም አይተውሽም ተይ ተመለሺ ስል ተማፀንኳት። ሌላው ቢቀር እኮ እሱ ክርስትያን ነው ስላት... እሰልምልሻለሁ ብሎኛል ብላ አፍ አፌን አለችኝ። የፈለገውን እስኪያገኝ ነው እንደዛ ሚልሽ እንጂ እሱ አይሰልምልሽም ብላትም ልትሰማኝ አልቻለችም።


ማትሪክ ተፈተንን ስልጣንም አስረከብን። ውጤት መጠባበቅ ጀመርን ትግስት፤ ሰአዳ፣ አሚራ፣ብሩክ፣እየሩስ.......ሁሉም ጓደኞቼ ወደቁ እኔና ዘቦ ግን አለፍን

ትግስት ውጤት ባይመጣላትም ቀድሞውኑ እናቴን ማስደሰት አለብኝ የምትፈልገውን ማድረግ አለብኝ ወደ ከሚሴ እሄዳለው ብላ ወስና ስለነበር ውጤቱን እንደሰማች ከእናትዋ ጋር ወደ ከሚሴ ወደ ታላቅ ወንድምዋ አማር ቤት ተጓዙ። ከሚሴ እንደደረሱም ደውላ በእግዚአብሄር ፍቃድ በሰላም ገብተናል አትጨነቂ አለችኝ።


ትምህርት ቤታችን የሚመድበው አዲስ ከተማ የተባለ ትምህርት ቤት ቢሆንም በኛ ጊዜ እራሱ ትምህርት ቤቱ ወደ preparatory school ስለተቀየረ እዛው እንድንቀጥል ሆነ።እናም እኔ መሆን የምፈልገው አዋላጅ ዶክተር ስለነበር naturale science ገባሁ ዘቦ ጠበቃ መሆን ስለምትፈልግ social science ገባች።

ሰአዳ ጅልባብ ለብሳ አይቻታለው በዚህም ተደስቻለው መርየም በ አንዋር በደል ተጎሳቁላ እራስዋን መጠበቅ ባለመቻልዋ አብረዋት እያደሩ ብር የሚሰጡአት ወንዶችም ርቀዋት የቤት ኪራይ መክፈል አቅቷቷል ።አከራዮቹም ለብዙ ወራት ባለመክፈልዋ አባረዋት ጎዳና ወጥታለች።

Part 2⃣2⃣
ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል

Join👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💧አስተማሪ እዉነተኛ ታሪክ💧
 
የታሪኩ ርዕስ
💁‍♂
#SCHOOL_LIFE(የት/ቤት ሒወት )
     
#ክፍል ☞ ሀያ ሁለት 2⃣2⃣

ፀሀፊ ☞
#ዘቢባ_ሱልጣን


አከራዮቹም ለብዙ ወራት ባለመክፈልዋ አባረዋት ጎዳና ወጥታለች።
ጀመአችንም እውቀት ያለው አስተዳደር በማጣቱ ምክንያት ፈረሰ እኔም 11ኛ ክፍል በተዋወኳቸው ሁለት ሀያት ሀያት ከሚባሉ እና ዚነት ከምትባል ልጅ ጋር ጋደኝነት መስርቻለው።

ሶላት የምንሰግደውም ከትምህርት ቤታችን ፊት ለፊት ካለው ኮንዶሚኒየም ቤቶች መካከል አንዱ በሆነው በማዘር ቤት ነው. ማዘር የእውነት እናት ናቸው ውሀ ሲጠማን እና ሲርበን ፊታችንን አይተው ይረዳሉ። ልንሰግድ ቤታቸው ስንሄድ እንክብካቤያቸው አይለየንም። ጉዳይ ገጥሟቸው ሌላ ቦታ መሄድ ቢኖርባቸው እንኳን በራቸውን አይዘጉትም ልጆቼ ይመጣሉ አስተናግዱአቸው ብለው ለጎረቤት መልክት ያስቀምጣሉ። አብዛኛው የጊቢው ተማሪም የሚሰግደው ማዘር ጋር እየሄደ ነው።እነ ሀዩ ልክ እንደ ዘቦ የምወዳቸው ልዩ ጋደኞቼ ናቸው በምሳሳት ጊዜ ይመልሱኛል በየአንዳንዱ እንቅስቃሴዬም ይደግፉኛል።ጀመአችን በኛ ምክንያት ፈረሰ።

እኛ እውቀት ቢኖረን ባንሰለች ግልምጫቸውን እና ስድባቸውን መቋቋም ብንችል ምናልባትም ባልፈረሰ ነበር። ስልጣን ትልቅ አደራ ነው። ሰው ስልጣን ለመያዝ ይፍጃል ይገዳደላል ይተራረዳል። ሰው ስልጣን ለመያዝ አፈር ድሜ ይበላል ነገር ግን ስልጣን ትልቅ አደራ ነው ስልጣን ትልቅ ሸክም ነው። ስልጣንህን በአግባቡ ካልተጠቀምክ ትጠፋለህ አልያም ሌሎችን ታጠፍለህ። ያለ እውቀታችን ያለ ቦታችን የማይገባንን ስልጣን ተረክበን ከ 14 አመት በላይ የቆየውን ጀመአ አፈረስን።እኛ ያፈረስነው አንዲት ትንሽዬ የተማሪዎች ጀመአ ነው ነገር ግን ሌሎች ያለ ቦታቸው ስልጣን እየያዙ ሀገር እያፈረሱ ነው። ለስልጣኑ ብቁ ካልሆንክ ስልጣን አትያዝ ምክንያቱም ትጠየቅበታለህ!!!

11 ክፍል ልንጨርስ አካባቢ ሰአዳ ልጅ አቅፋ አንገትዋ ላይ መስቀል አድርጋ አየኋት። ያየሁት ህልም እንዲሆን ተመኘሁ ቀርቤ ላናግራት ስሞክር ዞር በይልኝ እያለች ሸሸችኝ።በጣም ተናደድኩ ጅልባብ ለብሳ ያየኋት ልጅ መስቀል አርጋ ሳያት በሸቅኩ።


በሌላ ቀን ቤትዋ ሄድኩ።ያረጁት አያትዋ ይንደፋደፋሉ።
.....አሰላሙ አለይኩም ማዘር ብዬ ገባሁ።
........ወአለይኩም ሰላም እንኳን ሳይሉኝ የጠፋ ልጃቸው የተገኘ በሚመስል ሁኔታ በደስታ ሰከሩ።አለሽ ልጄ ምነው ጠፍሽ? ወይ ዘይባ!! ሰአዳ እኮ ስላንቺ አውርታ አጠግብም ምነው ተቆራረጣቹሳ? አሉኝ በሀዘኔታ።
.....እኔም የትምህርቱ ጉዳይ እኮነው ማዘር አሁን የት ሄዳለች ??ብዬ ወደሄድኩበት አላማ አመራሁ።
....ማዘርም አሁንማ እኔጋር ምን ትሰራለች ባልዋ ጋር ናታ አሉኝ በቁጭት።
.....አገባች እንዴ? ብዬ ስጠይቃቸው
......አንቺም አታውቂም ልጄ?ጉድ አረገችኝ እኮ ጉድ ሰራችኝ።አሳድጌ አሳድጌ ረግጣኝ ሄደች። ከፍራ አገባች እኮ።እንደሌላው ሰው በወጉ እንኳን ብታገባ ጥሩ ነበር ነገር ግን ሳትነግረኝ ወንድጋ ኮበለለች አሉኝ። በጣም አሳዘኑኝ።
.....ኮበለለች ማለት ለምን አልነገረቾትም? ብዬ ጥያቄዬን ቀጠልኩ።ማወቁንስ አውቄያለው ከረፈደ ሆነ እንጂ። በጅልባብ ደልላኝ ራስዋን ደብቃ 6 ወር ከሆናት በኋላ ነው ማርገዟን ያወከት አሉኝ። ለካ ጅልባብ ለብሳ የነበረው እርግዝናዋን ለመደበቅ ነበር።የሰው አስተሳሰብ ይገርማል።

እኔ እኮ ጅልባል ያለበስኩት ለልብሱ ካለኝ ክብር የተነሳ ልብሱን ለብሼ እብድ እብድ ስል ያዩኝ ሰዎች እስልምናን በኔ እንዳይገምቱት እምነቴን በኔ እንዳይመስሉት ካለኝ ፍራቻ አንፃር ነው።እስዋ ያለምንም ማፈር ለእርግዝናዋ መሸፈኛ ስትል አንስታ ለብሳዋለች ሱብሀን አላህ።
......ማዘር ቀጠሉ ከዛም ልደግስልሽ ብላትም አልፈልግም ብላ ልብስዋን ይዛ ቤቱ ድረስ ሄደችለት አሁን ልጅ ወልደው እየኖሩ ነው እየመጣች ትዘይረኛለች።ውድዋ ልጄ ተጎሳቁላለች እኮ። ልጁም ያሰቃያታል መሰለኝ ብቻ አላውቅም አሉ በንዴት። ትንሽ ካቀረቀሩ በኋላም።ፍቺው እኔ አሳድገዋለው ብላትም አሻፈረኝ አለች ከልጅነትዋም ጀምሮ ደረቅ ግትር ናት።ግን ስላንቺ ሳታወራ አልፍ አታውቅም እስዋን ብሰማት ኖሮ ጓደኝነቴን ባጠናክር ኖሮ እዚህ ባልደረስኩ ነበር ትላለች አሉ ማዘር።


ብስጭታቸው እየጠነከረ ሲመጣ ንግግሬን አቁሜ እየመጣሁ እዘይራቹሀለሁ በሉ ቻው ወሰላሙ አለይኩም ብያቸው ወጣሁ።እስከ አስፓልቱ ጫፍ እስክደርስ ድረስ አትጥፊ እራስሽን ጠብቂ እንደስዋ እንዳትሆኚ እያሉ እየሸኙ አስጠነቀቁኝ።


አመቱ አለቀ 12ተኛ ክፍል ገባን።ትምህርት በጀመርንበት 15 ቀን ሰአዳን የትምህርት ቤታችን በር ጋር ነጠላ ለብሳ ቆማ እኔኑ ስትጠብቀኝ አየኋት።

#የመጨረሻዉ_ክፍል_

ይ.........ቀ.......
........ጥ.......ላ........ል


Join👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም School life የሚለዉን እዉነተኛ ታሪክ ጨርሰናል፡፡ ከታሪኩ ምን እንረዳለን ወንድማችሁ አሚር ሰይድ በኔ አመለካከት ትንሽ ልበል ..ከተሳሳኩ ይቅርታ አርጉልኝ

🔴 አሁን ላይ ትምህርት ቤት የሚማረዉ ብዙዉ ጊዜ ማሳለፊያ እና ላይፍ መቅጫ ሁኗል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ከአሁን በፊት የተመረቁት መቼ ስራ ያዙ ተምሮ ከመቀመጥ አሁኑኑ የትምህርት ቤት ላይፍ ብናሳልፍ ይሻለናል የተባባሉ ይመስላሉ ተማሪዎች ግን በዚህ ዉስጥ ብዙ ሰዉ ከፈጣሪ ከቤተሰብ ከማህበረሰብ የተሰጠዉን ሀላፊነት ዘንግተዋል ፡፡በዚህ school ife የሚያሳልፉ ቡሀላ ተፀፃች ሲሆኑ ለትዳር ሲቸገሩ እያየን ነዉ ፡፡ ታዳ ከኛ ምን ይጠበቃል?ካላችሁ ሁላችንም እህት ወንድሞቻችንን ልጆቻችንን በዲነል ኢስላም መርህ መሰረት ማሳደግ ግዴታ እና...በተለይ ሴት ተማሪዎችን መምከር የማህበረሰቡ ግዴታ ነዉ

🔵 በታሪኩ ዉስጥ ጓደኛዋ ለእሱ ለboyfrind ብላ ሀይማኖቷን ቀይራ ነበር ሀይማኖቷን ቀይራ እሱ ግን ሺሻ ቤት ይመላለሳል። መኖሪያ ቤታቸዉ ከሌላ ሴት ጋር ተኝቶ እጅ ከፍንጅ ይዘዋለች። ሺሻ ቤት ሲሄድ ሻሻ ቤት ምን ትሰራለህ?? እንዴት ይሄን ታደርጋለህ ??ስትለዉ
..... የእሱም መልስ አንቺን ያገኘሁሽ ይሄን ስትሰሪ ሺሻ ስታጨሺ አይደል እንዴ ምን እራስሽን እንደ ጨዋ ታያለሽ ብሎ እንዳሚያሸማቅቃት እና አንዳንዴም እዉጭ አድሮ እንደሚገባ ሴት ይዞ መቶ አልጋዋ ላይም እንደሚተኛ ከታሪኩ ላይ አይተናል፡፡...አንዲት ሴት የሌላ ሀይማኖት ተከታይ ለማግባት ብላ ኢስላምን ብቀይር ይሄ እንደሚገጥማት መረዳት አለባት ፡፡ አትሞኝ ይወደኛል ብትይ ይንከባከበኛል ብለሽ ብታስቢ ሀይማኖትሽን እስከምቀይሪ ብቻ ነዉ፡፡
☞ከእኛ የሚጠበቀዉ ብዙ ሰዉ ኢስላምን ሲቀበል ጥቂት ሰዉ ደግሞ ሀይማኖቱን ሲቀይር እያየን ነዉ ..ታዳ ይሄ የሚከሰተዉ በዲነል ኢስላም እዉቀት በሌላቸዉ ነዉ..ሀይማኖታቸዉን ሲቀይሩ ጓደኞቻችንም ቤተሰብ ዘመድ ቢሆኑም አንራቃቸዉ ለምን ብዙዎቹ ሀይማኖቱን አምንዉበት ሳይሆን እኛዉ ዲነል ኢስላምን የማስተማር ችግር እንደሆነ አዉቀን ሀላፊነት እንዳለብን እንወቅ...የዉመል ቂያማ ሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ለጀሀነም ሲዘጋጁ ጓደኛየ ሁኖ ወይም ሁና ሲለዲነል ኢስላም አላስተማረችኝም አብረህ ጀሀነም አስገባን የሚባልበት ጊዜ እንዳለ ማወቅ አለብን .ስለሆነም ክርስቲያን ጓደኛህ ካለ ነገ ጀነት ለመግባት ለራስህ ስትል ማስተማር አለብህ አለዛ ተያይዞ መክሰር ነዉ
☞ ስለዲነል ኢስላም አስተምረሀዉ መስገድ ከብዶት አላህ የሰጠዉ ትእዛዝ መተግበር ሲያቅተዉ ..እህቶቻችን ደግሞ ሀቁ ኢስላም እየሆነ እያወቀች በሌላ ሀይማኖት ተከታዮች የትዳር ወጥመድ ከገባች ግድ በኢስላም ቆይ ብለን አሻፈረን ካሉ በሀይማኖት ማስገደድ የለም የፈለጉትን መከተል መብት አላቸዉ...አንድ ሰዉ ታክሲ ሲሳፈር ከፍሎ የሚሄደዉ የሚወርድበት ቦታ ላይ ሲደርስ ሊወርድ እንጂ .ወደማሄድበት ቦታ አልፈህ ሂድ አይባልም..ታክሲ ላይ ሲወርድ የፈለገበት ቦታ ነዉ የሚወርደዉ
☞እንደዉም እኔ የምለዉ የሀይማኖት ነፃነት መከበር አለበት በዚህ 100% እስማማለሁ..ግን የኛ ማህበረሰብ ኢስላምን ሲቀበል ወይም ወደ ሌላ ሀይማኖት ሲሄድ ከቤተሰብ ከጓደኛ ከዘመድ ይገለላሉ ..በተለይ ጎንደር ጎጃም ያሉ ክርስቲያኖች ኢስላምን ከተቀበሉ ቤተሰቦቻቸዉ ሳይቀር አያስቀምጧቸዉም ይባራሉ..በወሎ በደሴ ደግሞ ማንም የሚናገረዉ የለም ተዋልዶ ተጋብቶ እናያለን ..ሰዉ መከበር ያለበት ሰዉ ስለሆነ እንጂ የአንተ ሀይማኖት ተከታይ ስለሆነ ብቻ አይደለም የፈለገዉን ሀይማኖት ሲከተል ኢስላምን በሌላ ሌላ ሀይማኖት ቀይረዉ እንደገና ሲያዩት የማይሆን ሲሆን መልሰዉ ወደ ኢስላም መጥተዉ ቀጥ ለጥ ብለዉ ሀይማኖቱን የሚተገብሩ አሉ ታዳ ይሄ የእመነት ነፃነት ካለ ጥቅሙ ለሁሉም ነዉ ፡፡ እኔ የማቃቸዉ ብዙ ሰዎች ከዘመዶቼ ጀምሮ ሲከሰት አይቻለሁ

🔴 ሴት ተማሪዎች ላይ በተለይ ፋየር ኤጅ ከ13አመት ጀምሮ እስከ 18አመት አለሁ አለሁ ከኔ በላይ ሴት የለም ብላ በመስተዋት ፊትሽን መመልከት ካበዛች ጥንቃቄ ያስፈልጋል ፡፡ ለምን በዚህ እድሚያቸዉ ገና ያዩትን ወንድ አካሄዱ መልኩ እያሉ ብዙ ሴቶች ያወራሉ ፡፡ ደግሞ አደጋዉ በዚህ እድሜ ያሉትን ሴቶች ወጥመድ የሚያዘጋጁላቸዉ ከ20አመት በላይ ያሉ ነፍስ ያወቁ ጨካኝ ወንዶች እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ በማለት እነዚህ ሴት ልጆች የስሜትን የድንግልናል ትርጉም ሳያቁት በተኩላ ወንዶች እየተሸወዱ የወደፊት ፕላናቸዉ ሲበላሹ እያየን ነዉ፡፡ ይሄ ሁሉ ችግር ወደ ቤተሰብ ሀላፊነት የሚወስደዉ ሲሆን ምክንያቱም ለትምህርት ከአቅም ጀምሮ በግል ካስተማረ ከ1000 ብር ጀሞሮ ደግሞ ባለጊዜ ደሀ የማይማርበት ክፍያዉ እኔ መጥቀስ የማልችለዉ እስከ ዉጭ ሀገር ድረስ እያስተማሩ ነዉ ፡፡ ነገር ግን ዲነል ኢስላም ለማስተማር በወር 100ብር በዛ ከተባለ 500 ብር ክፈል ሲባል የሚያንጠራራ የሚያፋሽግ ማህበረሰብ ሁነናል፡፡ ለትምህርት በከፈልከዉ ብር ዲነል ኢስላምን ካላወቁ በራስህ ብር አሳልፈህ ለተኩላ ሰጠህ ማለት ነዉ፡፡

🔵 ብዙ ተማሪዎች ቤተሰብ ቁርአን እንዲቀሩ የሚያመቻቹት ትምህርት ሲዘጋ በክረምት ነዉ ፡፡ ይሄ ታዳ ቁርአን እንዲቀሩ ሳይሆን በክረምት ቤት እንዳይቀመጡ ወይም እንዳይረብሹ ነዉ ብንል ይሻላል ፡፡ ቤተሰቦች እዚህ ላይ ከባድ ሀላፊነት አለባችሁ ቁርአን ቀርተዉ ሀዲስ መቅራት ጥቅሙ ለልጅህም ለቤተሰብ ነዉ ፡፡ ለምን ልጆችህ ዲነል ኢስላምን ቢያቁ ለአንተ ተዛዥ ለዲን ተቆርቋሪ ሀራምን የሚሸሹ ሀላልን የሚመርጡ በዲነል ኢስላም የሚታዘዙ ሲሆን፡፡ በተዘዋዋሪ ዲነል ኢስላምን ባታስተምር
☞ ከልጅህ ጋር ሁሌ ስትጣላ ስትጨቃጨቅ ትኖራለህ
☞ከመጥፎ ጓደኞች ጋር ስታያት ምን ታደርጋለህ?ጥፋቱ የአንተ ስለሆነ
☞ በዚህ የኑሮ ዉድነት ፋሽን ልብስ ግዛ እየተባልክ እዳህን ታያለህ፡፡ ዲነል ኢስላምን ብታቅ ኑሮ ሶስት ጅልባብ ካላት ለእሷ በቂዋ ነዉ..ግን ካላወቀች የቱርክ የዱባይ ልብስ ፋሽን በመጣ ቁጥር ግዛ በማለት እዳህን ታያለህ
☞ አላህ በሰጠን ዉበት አልሀምዱሊላህ ማለት ትታ ፡፡በመቀባባት መልኳን ለዉጣ የምትሄድበት ሜካፕ ግዛ በማለት ከአስቤዛ ዉጭ የእሷን ሜካፕ መግዣ በአንተ በቤተሰብ ይሸፈናል ማለት ነዉ፡፡ ደግሞ አንተ በገዘዉ ሜካፕ ተቀብቷ ስትሄድ በመንገድ ስትሄድ ብትሄድ አንተም ላታቃት ትችላለህ 😉ለምን መልኳን ስለሚቀይራት😆😆
☞በስተመጨረሻ ያዉ ለትዳር የሚፈለገዉ አደብ ያለዉ ምች እና አይንናስ ያልበላዉ በሰዉ አይን ያልበዛበት ስለሆነ ተንጓላ እቤት ስትቀር እሷ ማግባት ባለበት ሰአት ካላገባች ወጩ የአንተ መሆኑን አዘንጋ. ወንድም ሴትም በዲነል ኢስላም ማደግ አለባቸዉ ጥቅሙ ለቤተሰብ ነዉ ለማለት ያህል ነዉ

🔴 አሁን ላይ ሴቶች ገና ከ6ክፍል ጀምረዉ እስከ 12 ክፍል ባለዉ ጊዜ የድንግልናን ትርሩም ሳያቁት ትምህርት ሲዘጋ እንዝናና በማለት ምንም ሳያቁ እየተሸወዱ ነዉ፡፡
አንድ በቅርብ ቀን በፈረንሳይ ሀገር ጥናት አድርገዉ አንብቤ ነበር ሴቶች 18.አመት ሳይሞላቸዉ ከዛ በፊት ዚና ከሰሩ 95% ጥናት የተደረገ እርካቱ አላኙም: ለምን ገና ስላልደረሱ ፡፡ ዝም ብሎ ዲነል ኢስላምን ባለማወቅ እና በመቸኮል የሚሰራ ስራ ወንጀልና ደስታ የለዉም፡፡ በጥናቱ ላይ 18አመት ሳይደርሱ በጊዜ ክብራቸዉን ያስረከቡ ተቆጭተዋል ለምን ሲደርሱ መሆን የሚገባዉን ሳይደርሱ ስለሆነ ..ብቻ በሀራም የሆነ ነገር እስከ ዘላለም ደስታ የለዉም
በዚህ ጥናት ላይ በልጅነታችሁ ባለማወቅ ወይ👇👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ..SCHOOL LLFE በሚለዉ እዉነኛ ታሪክ እና በቻናሉ ዙሪያ የሰጣችሁትን አስተያየት ጠቅለል አርጌ ስመልስ

🔵 አሚር ሰይድ ለሴት ያለህ አመለካከት በጣም የወረደ የተጣመመ ነዉ ላላችሁኝ
☞ይሄ አስተያየት ቻናል ስከፍት ጀምሮ የተሰጠኝ የተነገረኝ ነዉ እኔም ሀፍዠዋለሁ😊 አሁንም እዉነት እሬት ቢሆንም መዋጡ ነዉ የሚሻለዉ..ብዙ ሴቶች በራሳችሁ እስከሚመጣ እንጂ በሌላ ሰዉ ለመማር ብዘም ቦታ ስለላችሁ ነዉ...አብሽሩ ትንሽ ቀን ነዉ የቀረኝ እኔም ከመፃፍም ከአስተያየትም አድባለሁ

🔴 ለምን የሰዉ አይብ ታወጣለህበታሪኩ ብናማርም ባለታሪኩ ከቶበተ ለምን ተፅፎ ይቀርባልአላህን ፍራ ለምትሉኝ
☞ዲነል ኢስላም ሁሉም በአቅሙ ነዉ ..የግጥም የፁሁፍ ፡የደአዋ ፡ መነባንብ፡ ችሎታ ያለዉ ሁሉም በቻለዉ ማገልገል አለበት ፡፡ ነገር ግን እኔም በሂደት ታሪክ ብቻ በቂ አይደለም ብየ ሀሳቡን አምኘበት በተለያዩ ቻናሎች የተለያዩ ዲነል ኢስላም ትምህርቶች ጀምሪያለሁ ፡፡ ከኔ ቻናሎች👇👇
➊የቁርአን ተፍሲር በታዋቂ ኡስታዝ አያተ ሰላም
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group

➋ስለ ክርስትና ኢስልምና ሀይማኖት ንፅፅር የፈለገ
☞www.tg-me.com/Loveyuolema

➌ ኢስላም እና የዘመናችን ስልጣኔ የሚያተኩር
☞www.tg-me.com/ne_siha_eslamik

☝️☝️☝️ ሶስቱንም ቻናል join በማድረግ በሚፈልጉት የተለያዩ ኢስላሚ እዉቀቶች ይሸምቱ ፡፡ በተጨማሪ ስለተዉሒድ አስተሞር ላላችሀኝ ..እኔ ኪታብ አልቀራሁም ሳላዉቅ ማሳወቅ አልችልም እገዙኝ የማፓሰት ላኩልኝ ብል አንድም ሰዉ ፍቃደኛ አላገኘሁም ፡፡ በዚህ ዙሪያ መስራት ስለምፈል telegram የምገባዉ ከሱብሂ ቡሀላ ስለሆነ በbot አማክሩኝ ፡፡

☞ታሪክ አቁም ለምትሉኝ መርሀባ ሀሳባችሁን 99% ተቀብያለሁ በችኮላ የሚወሰን አይደለም ..ግን እንደማቋረጥ ቃል እገባለሁ መቼ የሚለዉ ግን እኔ አንድ የተዘጋጀ ታሪክ አለ ከዛ ቡሀላ ኢንሻ አላህ

🔵በislamic university ቻናል👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
የሚፓሰተዉ ቁርአን ተፍሲር 23mb ነዉ በጣም በዛ ተፍሲር የሚሰጡት አያተ ሰላም እዉቀት አግኝተን ነበር ላላችሁ፡፡
☞የሚገርመዉ ከእናንተ በላይ እኔ አስባለሁ እኔም የምጠቀመዉ እኮ ካርድ ሞልቼ እንጂ በዉሀ አይደለም😊
ይሄ ተፍሲር record ሲደረግ በ100mb ነዉ እኔ ነኝ በaplication ወደ 23 mb የምቀይረዉ ደግሞ 50ደቂቃ ቆይታ አለዉ..ሪከርድ የሚያረጉልኝ ከልብ በማመስገን..እነሱም በYoutube ተፍሱሩ እየለቀቁት ነዉ.. ወሬ ሳይሆን ተግባር ነዉ የምንፈልገዉ..ለምን mb በዛ ከምትሉ ለስንት ሰዉ ሼር አርጊያለሁ ቢሉ ይቀላል

ግን ኢንሻ አላህ ይሄን ሰሞን በአዲስ aplicaton record ማረጊያ እኔዉ ሸዋበር መስጊድ እየሄድኩ በ10mb record እያረኩ ነዉ ፡፡ ኢንሻ አላህ ይሄዉ mb ቀንሰናል..ግን አስባችሁ record ለምታረጉልኝ ከልብ አመሰግናለሁ

🔰 በተጨማሪ ተግባር ሳይሆን ወሬ ብቻ ሁናችሁ ለተቸገራችሁ የቻናል ቤተሰቦች አንድ መፅሀፍ ልጋብዛችሁ የዶክተር ምህረት ደበበ #ሌላ_ሰዉ የሚለዉን መፅሀፍ አንብቡት የሳይኮሎጂ መፅሀፍ ነዉ 474 ገፅ ነዉ፡፡ አንተም አንቺም እሱም እሷም እነሱም ሁሉም በውስጡ ሌላ ሰዉ እንደሆነ ይገነዘባሉ😊 ስለሆነም ሰዉ የማይሰራዉን የማይሸከመዉን ለኔ ለመጫን መሞከር እና ለማራገፍ ማሰብ ..አንድ አይኑን ጨፍኖ በአንድ አይኑ እየተመለከተ ለምን ጨፈንከዉ ሲባል ለመቆጠብ ነዉ እንዳለዉ አስተሳሰብ ነዉ😉

🔵 አሁን አዲስ ታሪክ ትጀምራለህ ወይላላችሁ
☞እኔ የፃፍኩት እድሜ ጤና ከሰጠኝ ከረመዷን ቡሀላ ነዉ😊 ሌላ እንጃ ፅፈን እናደርሳለን ያሉት አልጨረሱም..ከትረካ ዉጭ ሌላ አንድ ተከታታይ አስቢያለሁ አብረን እናያለን

🔴 ኮሮራ በኢትዮ ከገባ ጀምሮ ስለኮረና መረጃ አልሰጠህምላላችሁ
☞ ሆነም ቀረ ሁሉም ሰምቷል የKg ተማሪ ለራሱ ሳይቀር..የሰዉ ሁኔታ ሳየዉ ሙቶ የቀመሰዉ ያለ ይመስል ተጨናንቋል..የሚገለዉ 1%ወይ 2% ነዉ ብቻ አላህ ያንሳልን በኛ መጠንቀቅ አይሆንም፡፡ ለዚህ በቀበሌ ስኳር እና ዘይት ለሆነ ኑሮ አንጨናነቅ😉
ግን አንዳንዴ ለኸይር ነዉ ያስብላል..እኔ ባለሁበት ከተማ መስጊዶች በሰጋጅ እየተጨናነቁ ነዉ የማይሰግደዉ የሚቀልደዉ ጠቅልሎ መስጊድ ገብቶ እየሰገደ ነዉ ቶብቼ ልጠብቀዉ የሚል ወጣት እየፈጠረ ነዉ😊 ስለሆነም በተቻለን አቅም ጥንቃቄ ከዛ ዉጭ ፍርሀት በልክ ይሁን መጀመሪያ ፈጣሪን እንፍራ

🔴አሁን ችግሩ ዩኒቨርስቲ ላይ ነዉ ፊርቃዉ በዝቶ ወደ ማን መሆን አቅቶን ከሙስሊሞች ጀመአ መግባት አልላችልንም ላላችሁ
☞ይሄ ሁሉም የዩኒቨርስቲ ተማሪ ተመካክራችሁ የማስተካከል ግዴታ ነዉ..በተቻላችሁ አቅም ፊርቃ አታብዙ እኛ የቸገረን አንዲት እፍኝ እዉቀት ይዞ ከtelegram record ሰምቶ እኛ ነን አዋቂ የሚል ነዉ የረበሸን😊፡፡ በቆርቆሮ ሽንቁር የምትገባ የፀሀይ ብርሀን አትበርድም አትሞቅም የአሁን አወቅን ባዮች ከዚች በቀዳዳ እንደምትገባ ፀሀይ ሳያዉቁ ብዙ የሚረብሹ አሉ ከመረበሽ ከአሊም ጎን ቁጭ ብሎ መቅራት

🔴 አንዳንድ ሰዎች ሀይማኖቱን እየቀየረ ነዉ ላላችሁ
☞ ኪሎ ቢቀነስ ኩንታል እየገባ ነዉ..ግን የሚወጡት ሰዎች የኛ ሙስሊሞች ደካማ ጎን እንደሆነ እወቁ ፡

🔰🔰 ዘቢባ ሱልጣን ከመለሰችዉ 👇👇
🔷እኔን ኢማነኛ ነሽ ማሻ አላህ ላላችሁኝ
☞በመጀመርያ እኔ እንደምታስቡኝ ኢማነኛ ሆኜ አይደለም ወላሂ ከ 2 ጊዜ በላይ ቁራንን አላከተምኩም ኪታብም ቢሆን ከአርባኢን እና ከ ኡስኑል ሰላሳ ውጪ አልቀራሁም ። አህላቅም ላይ ማሻ አላህ የምባል ሰው አይደለሁም በጣም ደካማ ነኝ ይሄን ሁሉ ሙገሳ አይገባኝም።

🔷በመቀጠል የሰው አይብ አወጣሽ ብላቹ ለተቆጣቹኝ እኔ ሙሉ ለሙሉ ማንነታቸውን አልገለፅኩም። ይሄ ታሪክ አልፎዋል ተረስቶዋል እናንተ ልትማሩበት ትችላላቹ ብዬ ነው የፃፍኩት።

🔷ታላላቆች ለታናናሾቻቹ አርአያ ሁኑ። እኔን የቀየረኝ ወንድሜ ነው። እናት አባቴ አንድም ቀን ቁርዐን ቅሪ ሂጂ መስጂድ ሂጂ እድሜሽ ደርሶዋል ሰላት ስገጂ ወይም ፁሚ ብለውኝ አያውቁም። ከስር ከመጀመርያው ጀምሮ ሰላት እንድሰግድ እየመከረኝ አልሰማ ስለው እየመታኝ እና እያስፈራራኝ ያስተማሪኝ ወንድሜ ነው። ቁርዐንም እንድቀራ ያደረገኝ እሱ እራሱ ነው። ፆም በ 11 አመቴ እንድጀምር ያደረገኝም እሱ ነው። ርሀቡን ባልቻልኩት ጊዜ በቃ ይበቃሻል ዛሬ ግማሽ ቀን ከፆምሽ ነገ ሙሉ ቀን ትፆሚያለሽ ብሎ ያስለመደኝ እርሱ ነው። ወንድሜ ለኔ መሰረቴ ነው ሁላችንም ታላላቆች አደራ አደራ ለታናናሾቻቹ መጥፎ ነገር አታስተምሩ።

🔷ሌላው ደግሞ መርየም እንደ ሰአዳ ሳትለውጡዋት ያላቹኝ ወላሂ መርየም ጎዳና መውጣትዋን ካወኩበት ቀን ጀምሮ ያለችበትን ማወቅ አልቻልኩም ላገኛትም አልቻልኩም አሁንም የት እንዳለች አላውቅም።እውነት ይሁን ውሸት ባላውቅም አንዳንድ ሰዎች መክፈርዋን ነግረዉኝ ያሉኝ ቦታም ፈልጌ አጥቻታለው

🔷ከድር የት ደረሰ ላላቹኝ መልስ፦ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ አላውቅም የደረሰው ዩኒቨርስቲ አንቦ ዩኒቨርስቲ ቢሆንም ረብሻ ሆኖ ተመልሶ አዲስ አበባ መቶ ኮሌጅ እየተማረ እንደሆነ የዛሬ አመት በራሱ አንደበት ሰምቻለው። አልፎ አልፎ በ አመትም በ 6 ወርም አንዴ ድንገት መንገድ ላይ ስንተላለፍ እንገናኛለን። ምንም እንደማይተዋወቅ ሙስሊም ወንድማማች እና እህትማማች አሰላሙ አለይኩም ተባብለን እንተላለፍለን።ትርፍ ንግግር የለንም።
"ፍቅር እንዲህ ነው ወይ"አስተማሪ ትርካ እንዳያመልጥወ ! በእህት ሰላም ካሳዬ
<unknown>
😥 #ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ??
(የደሀ ልጅ ፍቅር)


🔹 ክፍል ☞ አንድ 1⃣
🔸 አቅራቢ☞ ሰላም
🔹 የጊዜዉ ☞ 7 ደቂቃ
🔸 Size ☞ 7 mb

> በislmic school ቻናል የቀረበ

🔰ይህንን እዉነተኛ ታሪክ በአማረ መልኩ በAUDIO አቅርበናል
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢



join
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science

በYUOUTUBE 👇👇
https://youtu.be/Xj6xq9y4u-I
#ፍቅር #እንዲህ ነው ወይ !?ከባለፈው የቀጠለ ክፍል #ሁለት እህት #ሰላም ካሰ
😥 #ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ??
(የደሀ ልጅ ፍቅር)



🔹 ክፍል ☞ ሁለት 2⃣
🔸 አቅራቢ☞ ሰላም
🔹 የጊዜዉ ☞ 10 ደቂቃ
🔸 Size ☞ 9 mb
> በislmic school ቻናል የ
ተዘጋጀ

🔰ይህንን እዉነተኛ ታሪክ በአማረ መልኩ በAUDIO አቅርበናል
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢


join
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science

በYUOUTUBE 👇
https://youtu.be/xFMHyxxuDGU
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
‍ አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ ውድ ተከታዮቻችን ሰላም ብያለው ከታች የምታዩት ቪድዮ የሙስሊሞችን እንግልት ያሳያል ተመልከቱ👇

ኢንሻአላህ ነገ (የሙስሊሙ ደም የጠማቸው አውሬዎች) ወይም ታታር የተሰኘ አዲስ ተከታታይ እውነተኛ ታሪክ ይዘን ለመቅረብ ዝግጅታችንን ጨርሰናል።

☞ ወላሂ ታሪኩ በጣም ልብ የሚነካ ከመሆኑ ባሸገር አሁን እኛ ሙስሊሞች ያለንበትን ተጨባጭን ቁልጭ አድርጎ ያስቀምጣል።ምናልባት ታሪኩን ስታነቡት ፊልም ሊመስላችሁ ይችላል።ግን እውነተኛ የተፈፀመብን በደል ነው።


ታሪኩ ዘመን የማይሽረው የሆነውን የአላሁ ሱብሃነ ወተዓላ ቃል በሆነው ቁርዓን ካፊሮች ለሙስሊም ያላቸውን ጥላቻ ቁልጭ አድርጎ የተቀምጠውን የቁርዓን አንቀፅ አስረግጦ ያሳየናል👇

وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ ٱلْيَهُودُ وَلَا ٱلنَّصَٰرَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى ٱللَّهِ هُوَ ٱلْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ ٱتَّبَعْتَ أَهْوَآءَهُم بَعْدَ ٱلَّذِى جَآءَكَ مِنَ ٱلْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ ٱللَّهِ مِن وَلِىٍّۢ وَلَا نَصِيرٍ

"አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡"


በዘመናችን እራሱ መከፋፈላችን ያመጣብን ሙሲባ እጅግ ብዙ ነው።
☞ በበርማ
☞ በሶርያ
☞ በቻይና
☞ በየመን
☞ በፍልስጤም
☞ በአፍጋኒስታን
እሁን ደግሞ በህንድ.....

🔵ከላይ በተጠቀሱት ሃገራት የሙስሊም ደም ማፍሰስ የተበራከተባቸውና እየተበራከተባቸው ያሉ ሃገራት ናቸው።አንተ እዚህ ሱፊይ፣ሰለፊይ፣ወሃብይ፣መድህሊይ አረ ብዙ ነው! እየተባባልክ ስትነቋቆር እዛ ያሉት ሙስሊም ወንድሞችህ ያለ አግባብ ደማቸው መፍሰስ ከጀመረ ሰነባበተ።ነብያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ምን ነበር ያሉን➝የኔ ኡመቶች ልክ እንደ አንድ ጀሰድ(አካል) ናቸው ብለውናል።እስቲ የነብያችን ውቡን ምሳሌ አስተንትን! አንተ የእግርህን አውራ ጣት እንቅፋት ቢመታህ የትኛው አካልህ ነው ሚታመመው? ተለይቶ አንዱ አውራ ጣትህ ብቻ ነው ሚታመመው? አይደለም ይልቁንም መልሱን እኔ ልንገርህና ወላሂ ሙሉ ሰውነትህን ህመሙ ይወርሃል።
የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዑመት ምሳሌም ከዚህ የበለጠ አንድነት እንዳለው ውዱ ነብያችን ሙሃመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደ አንድ አካል ናቸው ሲሉ መስለውታል።ታድያ አንተ ሙስሊም ወንድሞችህን አስታውሰህ አልቅሰሃል።ዱዓ አድርገህላቸው ታቃለህ? እንዴታ! እንዴት እናልቅስ የኛ ጉዳይ ይሄ አይደለም😔

ካፊሮችን ባመረ ሰላምታ እና ፈገግታ እየተገናኘን ሙስሊም ወንድሞቻችንን መገላመጥ እየሆነ ነው።በመጨረሻም በፊርቃ ውስጥ ስምጥ ላሉት ወንድሞቼ የምነግራቸው ነገር ነገ አላህ ፊት እስልምናን ስትከፋፍል ነበር ተብለህ/ሽ መጠየቅህን/ሽን አትርሳ/ሺ!
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር

#ክፍል ☞ አንድ


ከርእሱ ልጀምርና እስኪ ስለ አደራ ምን ያህሎቻችን እናቃለን? ስንቶቻችንስ አደራችንን እየተወጣን ይሆን!!! ይቅርታ በጥያቄ ጀመርኩት መጀመሪያ ራሴን ሳላስተዋዉቅ........ ፊርዶስ ዩሱፍ እባላሁ ተወልጀ ያደኩት ጎጃም ደ/ማርቆስ አካባቢ ነዉ ሀገሩ፣ህዝቡ፣ አየሩ ብቻ ሁሉም ነገር ደስ ይላል። ሀገሩ ብቻ ሳይሆን እኔም ቆንጆና ደስ የሚል ፀባይ አለኝ ማለት ባልችልም..... ብዙዎቹ ግን ፀባይም ቁንጂናም አድሎሻል ይሉኛል። አልሀምዱሊላህ...... ከሰዉ ጋር ለመግባባት ቢሆን ብዙም አልቸገርም ቶሎ እግባባለሁ። ትምህርት የጀመርኩት በ 7 አመቴ ነዉ በትምህርቴም ጎበዝ ተማሪ ነኝ..... ደረጃም ቢሆን ከ1 እስከ3 አለቅም ሁሌም በየ አመቱ እሸለማለሁ። መምህሮች ሁሉ ይወዱኛል....... ምን መምህሮች ብቻ ተማሪዎችም በጣም ነዉ የሚወዱኝ። አንዳንዴ መምህሮች በተለያዪ ምክንያቶች ሊቀሩ ካሰቡ ለኔ ዳስተርና ቾክ እንዳስተምር ይሰጡኛል። እኔም ክፍለ ጊዜቸዉን ሸፍኘ አስተምራለሁ። ግን እኔን የሚበልጠኝ አንድ አብርሀም የሚባል ልጅ አለ እሱ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ አንደኛ ሲወጣ እኔ ደግሞ ሁለተኛ እየወጣሁ ይሄዉ ዘጠነኛ ክፍል ደረሰናል..... ግን ሁል ጊዜ እንዴት አብርሀም ይበልጠኛል አንድ ላይ እየተማርን ብየ እናደዳለሁ። መቸም ትምህርት ነዉና እንደየልፋቱ ደረጃዉም ይለያያል።
...... ከራሴ በላይ በጣም የምወዳት አያት አለችኝ አልሀምዱሊላህ........ አያቴ ለኔ እናቴ፣ አባቴ፣ እህቴ፣ ወንድሜ በአጠቃላይ ሁሉ ነገሬ ናት ደሞ የሚገርመዉ ፊርዶስ ብላ አትጠረኝም አደራየ ነዉ የምትለኝ። ወላሂ ምክንያቱን አላቅም ሁል ጊዜ እጠይቃታለሁ ግን አንች ገና ልጅ ነሽ ስታድጊ እነግርሻለሁ አሁን ብነግርሽ አትረጅኝም ትለኛለች። እኔም እንዴ..... አያቴ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ እኮ ነኝ እና እኔ ህፃን እባላለሁ ብየ አኮርፋታለሁ። እሷም ጠጋ ብላ ፀጉሬን እያሻሸች አደራየ የኔ ዉድ ቃል እገባልሻለሁ አንድ ቀን ሁሉንም ነገር አስረዳሻለሁ ትለኛለች በስስት አይኖቿ እየተመለከተችኝ። እኔም ፈገግ ብየ አይ! ዉዷ አያቴ ስለ ስሜ የማላቅ ይመስልሻል? አደራየ ምንድን ነዉ ስለ ስምሽ የምታዉቂዉ? አይ አያቴ ስለ አደራ ምንነት ብዙ አዉቃለሁ። እኮ ምን?......ስሜን ለማወቅ የተለያዪ ፁህፎችን አንብቤ ነበርና ለመግለፅ ብዙም አልተቸገርኩም አደራ ማለት ብየ መናገር ጀመርኩኝ.........
❖አደራ ማለት ለመግለፅ በጣም ከባድ ነዉ ከክብደቱ የተነሳ ተራራን ያንቀጠቀጠ ፣ሰማይን ያራደ፣ምድርን ያሳነ... ብቻ ምን ልበልሽ አያቴ አደራኮ ከመክበዱ የተነሳ አላህ(ሱ.ወ) አደራን ትሸከማት ዘንድ ወደ ሰማይ አቀረበ ሰማይም ጌታዋን አልችልም ይቅርታ አለች። በጣም ጠንካራ ወደ ሆነዉ ተራራም አቀረባት ተራራም ጌታየ ሆይ እኔ የመሸከም ለቅም የለኝም በማለት ደካማነቱን አሳወቀ ወደምድርም ይዟት ቀረበ ምድርም ጌታየ እኔ አልችልም ብላ ተመሳሳይ መልስ አቀረበች። ከዚህ ሁሉ በኋላ ወደ ሰዉ ልጅ ቀረበች የሰዉ ልጅም ምንም ሳይል እሽ ብሎ ተቀበላት።አላህም ይህን ክስተት እንዲህ ብሎ ነግሮናል።

እኛ አደራን በሰማያትና በምድር፣በተራራዎችም ላይ አቀረብናት። ሁሉም ግን እኛ ሀቅም የለንም አንችልም እንቢ አሉ። ሰዉም ተሸከማት። እርሱ በጣም በደለኛ ተሳሳች ነዉና።(አል አህዛብ.72)

እንግዲህ አያቴ ከዚህን ሰአት አንስቶ የሰዉ ልጅ ላይ አደራን እንዲጠብቅ ሀላፊነት የተሰጠዉ።
ዉዷ አያቴ ብዙ ሰዉ አደራን በመጠበቅ ይታወቅ ይሆናል ብዙ ነብዮችም አላህን ከፍጡራኖቹ ጋር ካስተዋወቁ፣ የአላህንም ሀቅ ከገለፁ በኋላ ቀጣይ ተግባራቸዉ የሚሆነዉ የፍጡራን ሀቅ የሆነዉን አማናን (አደራን) በመጠበቅ ላይ ማስተማር ነዉ። ከማንም በላይ ደግሞ የመጨረሻዉ ዉድ ነብይ የሆኑት ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ) በአደራ ጠባቂነታቸዉ የታወቁ ነበሩ። ለዛም ነዉ ነብይ ከመሆናቸዉ በፊት ጀምሮ ሙሀመዱል አሚን ታማኙ ሙሀመድ የሚባሉት።

አያቴም ታለቅስ ጀመር ግንኳ እኔ ብላ ማዉራት ስትጀምር... በጣም እያለቀሰች ነበርና አስቆምኳት ምንም ነገር መስማት አልፈልግም አሁን እንባሽን ታጠቢዉ ብየ ዉሀና በማስታጠቢያ ይዜላት መጣሁ...... አሷም ከታጠበች ቡሀላ ግን አደራየ የኔ ዉድ ልጂ አላህ አደራ ጠባቂዎችን ይወዳል አይደል?? ..... ዉዷ አያቴ ትጠራጠሪያለች እንዴ አወ አደራ ጠባቂወችን አላህ ይወዳል። ለዛም ነዉ የሱ ምርጥ ባሪያዎች መገለጫ ያረጋት። በዚህም ተግባራቸዉ የተነሳ ባሪያዎቹ ላይ የሚመፃደቅባቸዉ። አላህ በሁለት የቁርአን አንቀፆች ላይ እንዲህ ይላል......

👉እነዚያ እነርሱ አደራዎቻቸዉንና ቃል ኪዳናቸዉን ጠባቂዎች የኾኑት።(አል፡መዓሪጅ፡32)እና(አል ሙዕሚኑ፡8)

ደሞ ዉዷ አያቴ አደራ ቂያማ ለመቆሟና ላለመቆሟ ዋስትናም ምክንያት ናት። አደራ ጠባቂዎች በምድር ላይ እስካሉ ድረስ ቂያማ አትቆምም። ሰዎች እሷን ችላ ማለት ሲጀምሩና በምድር ላይ ለባለ አደራነት የሚበቃ ሰዉ የጠፋ ጊዜ የዛኔ ቂያማ ለመቆሟ ትልቅ ምልክት ትሆናለች። ነብያችን(ሰ.ዐ.ወ) ቂያማ መች እንደሆነች አንድ ሰዉ ሲጠይቃቸዉ እንዲህ አሉ.......
👉አደራ በጠፋች ጊዜ ቂያማን ተጠባበቅ ጠያቂዉም ደንገጥ ብሎ እንዴት ነዉ የምጠፋዉ? ሲል ጠየቀ
( ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ የአንድ ጉዳይ ሀላፊነት የማይገባዉ አካል ላይ ከተጣለ የዛኔ ቅያማን ተጠባበቅ ሲሉ ነገሩት።

አያቴም ይህንን ከሰማች ቡኋላ እነዛ ዉብ አይኖቿ በአንዴ ደም ለበሱ እኔም ምን ሁነሽ ነዉ የምታለቅሽ አስቀየምኩሽ እንዴ አያቴ? በአላህ አፉ በይኝ ሁለተኛ እንደዚህ አይነት ንግግር አይደገመኝም.። አደራየ የኔ ዉድ እኔኮ ብዙ አደራ አለብኝ። ግን አንድንም አልተወጣሁትም እያለች... ማልቀስ ጀመረች ኧረ በአላህ አያቴ ቆይ እሽ አደራሽ ምንድን ቢሆን ነዉ እንደዚህ የሚያስለቅስሽ?

አደራየ ዉዴ ለሁሉም ነገር ግዜና ቦታ አለዉ! አሁን አልነግርሽም። ግን አደራየ ወላሂ ዛሬ ኮርቸብሻለሁ። እንዴ አያቴ ምን አድርጌ ነዉ ደግሞ የኮራሽብኝ?....ስለ አደራ ምንነትና አደራ ሲጠፍም ዉመልቂያማ የመድረሱ ምልክቶች መካከል አንዱ እንደሆነ በደንብ ነግረሽኛል። አይ አያቴ የዉመልቂያማ የመድረሱ ምልክቶችኮ አደራን አለመወጣት ብቻ አይደለም ብዙ ምልክቶች አሉት። ለምሳሌ
👉 ፊትና በመብዛቱ ሳቢያ ሞትን መመኘት
👉 ሙስና፣ማጭበርበር እና የዋጋ ንብረት እያየለ መምጣት
👉 ስስት መስፋፋት
እያልኩ ከመሀል የቤቱ ስልክ ጠራ አያቴም በዚህ ለሊት ማን ይሆን የደወለ ብላ ስታነሳዉ.....

በአላህ ፍቃድ

#ክፍል 2⃣
...............ይ
...................ቀ
.......................ጥ
...........................ላ

................................ል



JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
2024/09/24 08:33:15
Back to Top
HTML Embed Code: