Telegram Web Link
ለእናቴ ለማንም የማታወሪብኝ ከሆነ ሚስጥር ነበረኝ አልኳት። «ኸረ ልጄ ለማንም አልናገርብህም አብሽር እስኪ ንገረኝ» አለችኝ።

እኔም ከሆነች ቱርካዊት ጋር እንደተግባባን እና ለመጋባት እንደተስማማን ነገርኳት። ማሻአላህ አለችኝ።

በነገታው ሳሎን ቤት ቁርስ ልንበላ በተዘጋጀንበት አባቴ ወደ ሳሎን መጣ። አይን ለአይን ተያየን። እሱም፦ «ሱልጣን ኦግሎ እንዴት አደርክ?» በማለት ሰላምታ አቀረበልኝ

(ከዐረብኛ የተተረጎመ)

©ኢስማዒል ኑሩ
ስለ "Halal Jobs" ሰምተዋል?

ይህ ፕላትፎርም የተከፈተው ሐላል የሆኑ የስራ ማስታወቂያዎችን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ለማድረስ ሲሆን፥

አዲስ ስራ ለሚፈልጉ፣ ስራ መቀየር ላሰቡና እንዲሁም ቀጣሪዎች የስራ ማስታወቂያቸውን በነፃ እንዲለቁበት በማሰብ የተዘጋጀ ፕላትፎርም ነው!።

ይወዳጁን! ይከታተሉን! ወዳጅዎንም ይጋብዙ! ያተርፉበታል!

እርስዎም ለወዳጅዎ በማጋራት የአላማችን ተካፋይ ይሁኑ።
ቻናል👉 www.tg-me.com/HalalJobsEth
ቃላቸውን የሚሞሉና ታማኝ ሰዎችን በምን እንለይ⁉️

ቃላቸውን የሚሞሉና ታማኝ ሰው መሆናቸውን የምናውቅበትን መንገድ ዓሊሞች ሲናገሩ…… እነዚህ ሰዎች
ٱلَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ دَآئِمُونَ (المعارج - 23)
የተባለውን አንቀፅ በደምብ የሚተገብሩ ናቸው፡፡ እነሱ መስጂድ የሚሄዱት ኢቃም ሲል አይደለም፡፡ የሰላት ረከዓ አያመልጣቸውምም፣ ሁሌም መስጂድ አዘውትረውና በወቅቱ የሚገኙ ሰዎች ናቸው አሉ፡፡
እንደዚህ አይነት ሰዎች ለመታመንና ቃላቸውን ለመሙላት ቅርብ ናቸው ይላሉ፡፡

አሏህ ይወፍቀን
ዝምታም የሙእሚን ባህሪ ነው፡፡

ለተናገረው ሁሉ መልስ ቢሰጥ፣ የሰደበውን ሁሉ ቢሳደብማ ውረደት እንጂ አያተርፍም፡፡ ውሻኮ የተናቀው አላፊ አግዳሚው ላይ ሁሉ ስለሚጮህ ነው፡፡ እሱም ቢሆን ከአንድ ድንጋይ አላለፈም፡፡
ሙእሚን ዝምታን ይመርጣል፡፡ ከተናገረም ከመናገሩ በፊት ምን ማውራ እንዳለበት ያስባል፡፡ ክብሩንም ይጠብቃል፡፡ ከአፉ መልካም እንጂ ክፉ አይወጣም፡፡ ሙእሚን በዝምታው ውሰጥ ክብሩ አለ፡፡ አንበሳ ለምን ተፈራ? ለምንስ ተከበር? በዝምታው፡፡
ጨለማን ለምን አንደፍረውም? ለምንድነው የምንፈራው? ፀጥ ያለ ስለሆነ፡፡ ሬሳን ለምንድነው የምንፈራው?ስለማያወራ።
በቁርዓን ላይ የምናገኛቸው ምልክቶች እና የሚያስተላለፍት መልዕክት

ቁርዓን በምንቀራበት ወቅት እነዚህን ምልክቶች ሁል ጊዜ እናያቸዋለው፡፡ ግን አብዛኞው ሰው የምልክቶችን መልዕክት በአግባቡ አይረዳቸውም፡፡ ከዚህ በታች ያለው ምስል እያንዳንዱ ምልክት የሚያስታልፈውን መልዕክት ያስገንዝበናል

ይህን ጠቃሚ ማስታወሻ ያዘጋጀውን ወንድም አላህ ኸይር ስራውን ይቀበለው

ይህን ጠቃሚ ማስታወሻ ለሌሎችም እናዳርስ
2024/07/01 02:12:44
Back to Top
HTML Embed Code: