Telegram Web Link
ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ብለህ ጀምር እርግጠኛ ሁን አላህ አያሳፍርህም ፡፡ ችግሩ የኛ ኢማን ጥንካሬ መድከምና ተስፋ መቁረጥ ነዉ....ንብ አንድ ኪሎ ማር ለመስራት 400 km ትንቀሳቀሳለች ተስፋ አትቁርጥም ታሳካለች ታዳ አንቺ አንተ እናንተ ምን የሚያስፈራ አለ???ምን ተስፋ የሚያስቆርጥ አለ??
ለምን እህትህን ለአጂ ነብይ ወንድ አሳልፈህ ትሰጣለህ??? ለምን እኔ አልችልም ትላለህ/ትያለሽ⁉️

ሀስቡነሏህ ብለህ መጀመር አቅቶህ ነዉ ወይስ አላህ በኔ ተማመን እያለህ በአሏህ መተማመን ፈርተህ ነዉ⁉️
የጀአለሁ መኽረጃ የወሙጫ መንገድ አዘጋጃለሁ ያለህ ጀሊሉን እንዴት መተማመን አቃተህ⁉️
ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል አላህን ይዘህ ሁሉም ነገር ቀላል ነዉ....አላህን ይዘን መፍራት አያስፈልግም


♻️♻️ ብዙ ሩቃ ቤቶች ሩቃን ለቢዚነስ አርገዉታል ከ3,000 እስከ 20,000 ከዛም በላይ እየጠየቁ እኔ መጀመሪያ ላይ ብር ላይ ፎከስ የሚያደርጉ ሰዎች ንያቸዉ ብር እንጂ ከአላህ አጅር እናገኛለን ብለዉ ስለማይሆን እንደነዚህ ሩቃ ቦታዎች እንጃ ብቻ ምን እንደምል አላቅም...በሀዲስ ይበቃል አይበቃም ፊርቃ ስላለዉ የሚሻለዉ ወላሁ አዕለም ግን ብዙም አይዋጡልኝ

የሚሻለዉ በራስ ኮንፊደስ ተወከልቱ አለሏህ ብሎ መጀመር ነዉ አሏህ ቁርአኑን መፍትሄዉን ነግሮናል ነብዩ ሰዐወ አስተምረዉናል እናም በራሳችን መታገሉ ኸይር ነዉ፡፡

ማወቅ ያለብን ጂን በደም ስር በመርፌ ቀዳዳ መሹለክ የሚችል ዉሸታም ሰላቢ የማይጨበጥ ነዉ ፡፡ #ግን_ቁርአን_በሚቀራበት_ጊዜ_መላኢካ_ከታማሚዉ_ሰዉነት_እንዳይወጣ_ጠፍሮ_ይይዘዋል፡፡
ከዛ ቁርአን በሚቀራበት ጊዜ ለእሱ ቁርአኑ ሰይፍ ነዉ የሚሆንበት ይቆራርጠዋል ...ወላሂ ቶሎ ብለዉ ነዉ የሚወጡት ለምን ካልወጣም ሊገለዉ ይችላል ፡፡

🔰🔰ቁርአን ለሰዉ ልጅም ለጂንም ካመንበት መድሀኒት እርጋታ ከፈጣሪ ጋር ያለን ግንኙነት መጨመሪያ ነዉ....ጂኖች ያቃሉ ግን ተገደዉ ወደ ሰዉ ገላ ስለሚገቡ ለመዉጣት የላካቸዉ ሸይጧን ወይም ትልቁ ጂን ወይ የጎሳ አለቃ ጂኑ ቅጣቱ ከባድ ስለሚሆንባቸዉ ላለመዉጣት ይታገላሉ ግን የሚያሸንፈዉ ቁርአን ነዉ ተቃጥለዉ ተንገብግበዉ አይናቸዉ ጠፍቶ እግራቸዉ ተቆርጦ ድረስ ይለቃሉ ሲናገሩ ከሰማችሁ አይኔ ጠፋ እግሬ እጄ ተቆረጠ ይላሉ ቁርአን ሀይል ነዉ ...አልሀምዱሊላህ ጀሊሉ ለሰጠን መድሀኒት ሀይል ብርታት ቁርአን

#ቁርአን 77430 ቃላት እና 430740 ፊደላት አለዉ አሏህ ፈጣሪያችን በቁርአን በአንድ ፊደል 10 ሀሰና አለዉ ብሎናል እናም 430740 ብናሰላዉ
🔶 በወር ሶስቴ ብናከትም 12,922,200 ሀሰና ሲኖረዉ
🔶 በወር ሁለቴ ብናከትም 8,614,800 ሀሰና እናገኛለን
🔶 በወር አንዴ ብናከትም 4,307,400 ሀሰና እናገኛለን

ቁርኣን አጠቃላይ ገፁ 604 ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር በመጠኑ በግማሽ ያንሳል። ነገርግን ላለፉት 1,400 ዓመታት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙፈሲሮች ማብራሪያውን ቢፅፉትም ፈፅሞ ሊጨርሱት አልቻሉም።
ለአብነት
♦️ ቁርጢቢ ➨ 21 ቅፅ 👉 5509 ገፅ
♦️ ኢብን ከሲር ➨ 10 ቅፅ 👉 6608 ገፅ
♦️ ጠበሪይ ➨ 12 ቅፅ 👉 3000 ገፅ
♦️ በገዊ ➨ 4 ቅፅ 👉 1487 ገፅ
♦️ ጀላለይን ➨ 1 ቅፅ 👉 1378 ገፅ
♦️ ሰዕዲ ➨ 10 ቅፅ 👉 6600 ገፅ
♦️ ቁጥብ ➨ 30 ቅፅ 👉 4018 ገፅ

ይህ ሁሉ ተፍሲር ለ604 ገፅ መጽሐፍ የተፃፈ ቢሆንም ሁሉም የሚችሉትን ያህል አብራሩት እንጅ አንዳቸውም አሟልተው ፅፈው አልጨረሱትም።

ከዚህ በተጨማሪ ቁርኣን በታሪክ፣ በህክምና፣ በጂኦግራፊ፣ በጠፈር ምርምርና በተለያዩ ዝርፎች የተጠና ሲሆን የተወሰነውን ቢያረጋግጡትም ገና ብዙ ያልተደረሱባቸው ምርምሮችን ይዟል።

ይህ ለሚያስተነትን ሰው በእርግጥ ተዓምር ነው።
«ይህ ቁርአን አንቀፆቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው። ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ የተወረደ ነው።»
(ሑድ 1)
እናም እኛ እንደ ቀልድ የያዝነዉ የአላህ ቃል ቁርአን ማስተንተን አልቻልንም እንጂ ሀይላችን ቅዋችን ከህመም መሻሪያችን ነዉ እናም ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ብለን እንጀምር

⚠️⚠️⚠️ ማስጠንቀቂያ
በፊት ለጅን የሚገብሩ በግ ፍየል ዶሮ በሬ ላም ወዘተ የሚያርዱ.... የሚገበረዉ ለብዙ ጃሂል ጂን ስለሆነ መጀመሪያ ማስቶበት ወደ አላህ እንዲመለሱ ማድረግ አለብን፡፡  ማድማቱን ማረዱን ሲያቆሙ ሀይለኛ ህመም ጂኑ ይልካል  ሀኪም ቤት ሲሄዱ ጂኑ አዉቆ እንደ ካንሰር ኩላሊት ምናምን ያስብላል

የዛን ጊዜ ካንሰር ኩላሊት ደም ግፊት ምናምን ከተባለ አደራ መድሀኒት አይጀሞሩ የካንሰርም በጨረር የሚሰራ አለ ባይሰሩ ጥሩ ነዉ  ለምን ጅኑ ደም ሲቆምበት እንዲሞቱ ይፈልግና ወደ ልጅ ወይ ልጅ ልጅ ይተላለፋል...የዚህ ጊዜ ጥሩ ሩቃ የሚቀራ ተፈልጎ ማስለቀቅ ነዉ መፍትሄው፡፡ግን ይሄን ጂን ለማስለቀቅ ቢያንስ 2ወር ሊፈጅ ይችላል፡፡ ነጬ በላ/ጥቁር በላ/ራሄሎ/አንበሴ/ወንዘኛዉ/ወዘተ ለጂን በሚያርዱበት ጊዜ ያለማካበድ ከ30 በላይ የሚሆኑ ናቸዉ የሚገበርላቸዉ እናም ማረድ ሲያቆሙ ያሁሉ ነዉ ቂም ይዞ እስከ ሞት የሚደርሽ ህመም ካንሰር ደም ግፊት የሚያስብሉት  ...ግን ለመሻር እንደ ታማሜዉ ቀልብ ይወሰናል፡፡ ትክክለኛ ተዉበት ከሆነ 3ቀን ለራሱ በቂ ነዉ፡፡
ነገር ግን አደራ አደራ!!! ሳይቶብቱ ሩቃ እንዳይጀምሩ ለምን ዋናዉ ቀልብ ነዉ ቀልባቸዉ ማድማት ለጂን ማረድ ከሆነ  ሩቃዉ በጣጣም አድካሚ ነዉ የሚሆነዉ ካልቶበቱ ሰዉነታቸዉን በጣም የሚያስጠላ ሽታ ሊሸቱ ይችላሉ፡፡ እናም ማስቶበቱ ላይ ትኩረት ማድረጉ ነዉ ...
አንዲት ሴትየ ሲታመሙ ካንሰር ተብለዉ ልጆቻቸዉ ቁርአን በተከታታይ ቀን ሲያስቀሩ የዛር ጂኖቹ ይለቃሉ መልሰዉ ከሁለት ከሶስት ቀን ቡሀላ ይመለሳሉ ከዛ ለምን ትመለሳላችሁ⁉️ብሎ ሲጠየቅ
ወላሂ እኛ እንወጣለን መጀመሪያ እሷን አስቶብታት ስንወጣ መልሳ እየጠራችን ተቸገርን ለምን እሷን ሳታስቶብት በቁርአን ታቃጥለናለህብሎ ነበር የመለሰዉ ጂኑ

🟢 አንዷ እናታችን በፊት ለጂን ያርዱ ነበር ሁለት ወር ያህል ታመዉ በአላህ ፍቃድ በሩቃ ጅኖቹ ለቀቁ.,,ሴትየዋ ግን አልሀምዱሊላህ በአላህ ቃል ተሻለኝ አላሉም....እኔን ያመመኝ እኮ ባለማድማቴ ነዉ የሚደማበት ቦታ ልሂድ ብለዉ ሲሄዱ የአሏህ ስራ የሚሄዱበት መኪና ሌላ መኪና ጋር ተጋጭቶ ከተሳፋሪዉ ሌሎቹ ሲተርፉ እሳቸዉ ግን ሞቱ😔😔 ኢናሊላህ ወኢኒ ኢለይሂ ራጂኡን አሟሟታቸዉ አላማረም....አላህ የመቶበቻ ጊዜ ሰጥቷቸዉ አልተጠቀሙበትም

   ትክክለኛ ተዉበት አድርገዉ ማድማቱን ሲያቆሙ ህመሙ ቁስለቱና ጂኑ ደማቸዉን ስለሚመጣቸዉ ደማቸዉ ይወርዳል ደም ግፊት ወይም ደም ብዛት ይባላሉ፡፡  በተጨማሪም የማህፀን ካንሰር ነዉ የመባል ቻንሱ ሰፊ ነዉ..ሰዉነታቸዉ ከበፊቱ በበለጠ መወፈር ወይም መክሳት ...ሆዳቸዉ እጃቸዉ አካባቢ ለብቻዉ ማበጥ ምልክት ያሳያል


⚠️ የምናቃቸዉ ደም የሚያደሙ ለጅን የሚገብሩ እናት አባቶች ካሉን በተጨማሪ አያቶቻችን ካሉ ብዙ የዲነል ኢስላም እዉቀት ስለሌላቸዉ በህይወት ካሉ  ይሄን ጊዜ እንዲቶቡ ማድረጉ ኸይር ጥሩ ነዉ ካልሆነ አሟሟታቸዉ እንደማያምር እወቁ ካንሰር ምናምን ሆነ ተብሎ ነዉ ህይወታቸዉ የሚያልፈዉ፡፡

ህመሙ በሽታዉ በሩቃ ለጅን ከሚገብረዉ አካል ካልተወገደ የዛር ጂን ቂመኛ ነዉ ወደ ልጅ ወይም ወደ ልጅ ልጅ ይተላለፋል ስለሆነም እንደ ቀላል ባናየዉ ጥሩ ነዉ፡፡



#የመጨረሻዉ_ክፍል_ይቀጥላል.....
4any cmt 🔽
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ጁምአ ነዉ የሆነ ችግር ሲበዛ ወይ ነይተን ለሰዉ ነግረን ያልተሳካ ካለ እንደዚህ ልጅ ሁኔታ ለጀሊሉ ነግረዉን ያሳፍረን ይሆን??
እስኪ ለጀሊሉ እንደዚህ ልጅ ሁኔታ አድርገን እንገረዉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ


            
#የመጨረሻዉ_ክፍል



  🔰 #ራስን_በራስ_ማከም_ከዛም_ለሌላ_መትረፍ


🌙🌙
ከpart ➊➍ ቀጥታ የቀጠለ.....
  ከዛር ዉጭ ያለን ሩቃን ለማድረግ ባንፈራ ጥሩ ነዉ ብቻ መጀመሪያ አላህን ይዘን ነይተን ሀስበነሏህ ብለህ መጀመር  ነዉ ፡፡

📚📚 ከተሞክሮ እስኪ ጀባ ልበላችሁ ወላሂ ይሄን የምነግራችሁ ጀሊሉ ያቅብኛል ለጉራ አይደለም ባልፅፈዉ ደስ ይለኛል ግን እንድትደፍሩ እንዳትፈሩ ለመጠቆም ነዉ፡፡ እኔ የዲን እዉቀት የለኝም በማንበብ እና የሰሙትን በመተግበር ላይ አተከለራለሁ ...እና ማንኛዉም ነገር አንድ እርምጃ ያስፈልገዋል የብዙ ሰዉ ችግር ሶስት አራት እርምጃ ይራመዳል ሳያጣራ ከዛ ግብ ሳይመታ ይመለሳል ...እኔ የማምነዉ አንድ እርምጃ ካልሆነ ወደፊት ሳይሄዱ መለስ እርምጃዉ የተሳካ ከሆነ ቀኝን እግርህን ካስቀደሙ ግራህን አስተከትለህ ሁለት እርምጃ ላይ ትቆማለህ ከዛ ነገሮችን እያገናዘቡ መሄድ ነዉ...
#ከተሞክሮ

✍🏼 አንዲት ክርስቲያን ጎረቤታችን  የ7 አመት ልጇ አላት ለሊት አይተኛ ቀን ታዝሎ ይዉላል ስራዉ ማልቀስ ምግብ የሚበላዉ ትንሽ ለዛዉም ያስመልሰዋል እንደ እድሜ እኩየቹ አይጫወትም ብቸኛ ነዉ ... ይሄ ህመም የጀመረዉ ገና በ4 አመቱ ነዉ 3 አመት ያህል ተሰቃይቷል  ያልሄደችበት ፀበል የለም ሌላም ሀገር ሂዳለች ፡፡በፀበል መፍትሄ ሲያጡ ሌላ ሀገር ጠንቋይ ቤት ሄዱ አረንጓዴ እስስት አምጡ ብሏቸዉ አረንጓዴ እስስት ለማግኘት አራት ወር ፈጀ በግድ ተገኘ ጠንቋዩ በአረንጓዴ እስስት ሌላም  ጨምሮ አንገት ላይ የሚንጠለጠል ሰጠው ምንም ለዉጥ የለም...ከ3አመት ስቃይ ቡሀላ ሲጨንቃት ቁርአን ቅሩልኝ አለች...

#አላህ_ሆይ እንዳታስፍረኝ የቁርአንን ሀይልን ለነዚህ ክርስቲያኖች አሳያቸዉ ብየ ዱአ አደረኩ ...ከዛማ በስፒከር ሩቃ ከፈትኩ ሁለት ሁነን በቻልነዉ ቀራን ወላሂ 45 ደቂቃ ባልሞላ እንቅልፍ ወስዶት ላብ በላብ ሆነ ቁርአኑን ስንጨርስ ጩኾ ተነሳ በዛዉ ለቀቀዉ ከዛ ቀን ቡሀላ ታሞ አያቅም ይሄዉ እንቅልፍም ይወስደዋል እናቱም አታዝለዉ ምግብም መመገብ ጀመረ የሚያስመልሰዉ ቀረለት  ትምህርትም ተመዘገበ አልሀምዱሊላህ....እናት አባቱ አጥባቂ ክርስቲያን ነበሩ አሁን ግን ከምነግራችሁ በላይ ለሙስሊም ያለቸዉ አመለካከት ደስ የሚል ነዉ አላህ ሂድያ ይስጣቸዉ የቁርአንን ሀይል ቤተሰብ ዘመድ ልጁን ተሽሎ ሲያዩት ይገርማቸዉ ይደንቃቸዉ ይዟል፡፡

✍🏼 አክስቴ ክርስቲያን ነች ታማ ፀበል ብትመላለስ ምን ብትል ያልተሻላትን በ30 ደቂቃ ሩቃ በመቅራት በአላህ ፍቃድ እንዲሻላት አድርጊያለሁ

✍🏼 ከነዚህ ዉጭ  3 ሰዎች ጎረቤት ምናምን ሲታመሙ በአላህ እገዛ ተሳክቶሎኛል እናም እንደዚህ ልላችሁ ያሰብኩት ሩቃ ማድረግ ከባድ አይደለም መጀመሪያ ጀሊሉን አላህየን ከያዙ ምንም የሚያስቸግር የለም እናም እህት ወንድምህን እናት አባትህን ...እናት አባትሽን እህት ወንድምሽን ለሌላ ባዳ አሳልፋችሁ አትስጡ

----- ጂን ሲናገር  ሊዋሽም ላይዋሽም ስለሚቾል አንዳንዴ ሲናገር እዉነት ነዉ ብለን ከተናገረዉ ሰዉ ጋር ሂደን መጣላት አያስፈልግም፡፡

🌟 ከዚህ ርዕሱ ጋር ባይሄድም በፊት ክፍል ላይ ዘንግቼ ሳላስገባ የቀሁት ጉዳይ አሁን ያለቦታዉም ቢሆን ስለዚህ ጉዳይ ትንሽ ልበል...
በቅርብ አመታት በተለያየ ማህበራዊ ሚዲያ ወንድና ሴት ዚና ሲሰሩ ወይ በባል ወይ በሚስቱ ላይ ሲማግጥ  ተጣብቀዉ እያየን ነዉ፡፡ ይሄ ባልየዉ ሚስቱን ካላመናት ወይም ሚስት ባሏን ካላመነችዉ ጠንቋዮች ጋር ሂደዉ ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች ወይም ሌላ ሴት ጋር ከተኛ እዛዉ እንዲጣበቅ ሰዉ እንዲያዋርደዉ ይሁን ብለዉ አስደግመዉ ሊሆን እንደሚችል አንዘንጋ...ካልሆነም ደግሞ ፈጣሪ እኛን ለማስተማር እነሱን ምሳሌም እያረገ ሊሆን ይችላል፡፡እናም ለትዳራቸዉ ታማኝ ያልሆኑ ሰዎች መጀመሪያ  ባለመተማመን ይጋባሉ ከዛ ይሄ ይፈጠራል፡፡
እናም ወይ የአላህ ቁጣ ነዉ ካልሆነ ድግምት ነዉ ...
ግን በተለይ በትዳር ላይ የሚሰሩ ሲህሮች በአሁን ዘመን ላይ በሰፊዉ ተንሰራፍቷል፡፡


 ⚡️⚡️⚡️ #በጂን_የተያዘ_ወይም_ሲህር_ወይ #በአይነጥላ_የተያዘ_ሰዉ_ወይም_አስታማሚዉ      
         
#ምን_ማድረግ_አለበት⁉️⁉️

      ኩን ፈየኩን ...አላህ ኩን ብሎት አላህ ሱወ በሲህር በጂን በአይነጥላ ሊፈትነን ይችላል ፡፡  ዱንያ የፈተና አለም ነች ለአላህ የትንኝ ክንፍ ያህል ቦታ የላትም ላለን ዱንያ ደስታን እናጣጥማለን ማለት አይደለም፡፡  ዱንያ በሀዘን ማቅ የተተበተበች ደስታ እንደመብረቅ ብልጭ ብሎ የሚጠፋበት የኑሮ መድረክ የፈተና መሸጋገሪያ ድልድይ ነች የጀነት መግቢያ የኸይር መሸመቻ የፈተና ማለፊያና መዉደቂያ የቁጥጥር ጣቢያ ነች፡፡  

  በርዚቃችን ትዳር እንዳናገባ ነገሮች እንዳይሳኩ ወዘተ ሲህር ድግምት  ከተደረገብን የአላህ ዉሳኔ ነዉ ፅናት ብርታት ጥንካሬ ያስፈልጋል ፡፡

♻️♻️ አላህ (ሱ.ወ) የወሰነውን ነገር መደው የተቀበሉ  ነብዩ ሰዐወ ናቸዉ በሲህር ተሰቃይተዋል.....በተጨማሪ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ኢብራሂም የሚባል ልጅ በተወለደላቸው ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የደስታ ስሜት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ተሸክመውት ወደተለያዩ ሰሐቦች ቤት ይዘውት ይሄዳሉ፡፡ ለሰዎችም ልጇን ኢብራሂምን ተመልከቱት፡፡› ይሉ ነበር፡፡ ትንሹ ኢብራሂም አባት ለልጅ በእጅጉ በሚጓጓበት የህፃንነት ዕድሜ ጡት መጣያው አካባቢ ሞተ፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) አለቀሱ😢፡፡ እንባ የልብ እዝነት ውጤት ነውና የአላህን ውሳኔ ካለመውደድ አይቆጠርም፡፡ እርሳቸውም ዐይን ያለቅሳል፣ ቀልብ ያዝናል፣ ጌታችን የሚወደውን ነገር እንጂ አንልም፡፡

#ኢብራሂም_ሆይ!!!! ከኛ በመለየትህ አዝነናል፡፡” አሉ፡፡ ከዚያም ወደቤታችው በመግባት ለአላህ (ሱወ) እንዲህ አሉ፡- ‹‹ጥሪህ ሰምተን በደስታ ወዳንተ መጣን፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ነው፡፡ መጥፎ ካንተ አይደለም፡፡” ብለዉ የጌታቸዉን ዉሳኔ ተቀበሉ...

መቼም የሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ ታሪክ ታቃላችሁ
💚በእናታቸዉ ሆድ ውስጥ ሳለ ወላጅ አባቱን በሞት ተነጠቁ
💛ዕድሜያቸዉ ስድስት ሲሞላ ወላጅ እናታቸዉን ቀበሩ።
❤️ በስምንት ዓመታቸዉ በፍቅር ተንከባክበው ያሳደጓቸዉ አያቱን አይቀሬው ሞት ነጠቀው።

💚 እንደ አይን ብሌናቸው የሚሳሱለት በማራኪ ስብዕናው ተረታ የትዳር አጋሩ ለመሆን የበቃችው ውድ ሚስቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ተከታትለው ተለዩት።
💛  ከሁለት ዓመታት ዕድሜ በላይ ያልቆዩ ሁለት ወንድ ልጆቹን ሞት ቀጠፋቸው። በህፃናቱ ፈገግታ ደምቆ የነበረው ቤት የሀዘን ጥላ አጠላበት።
❤️ከእርሱ ህልፈት በኋላ በስድስተኛው ወር በሞት ከተከተለችው ተናፋቂ ልጁ በስተቀር ሁሉም ሴቶች ልጆቹ ወደ መጪው ዓለም ተጓዙ።

💚 የአባቱ ጥሪት የነበሩት አጎቱ ተገደሉ። መገደል ብቻ አይደለም የሰው ልጅ ያደርገዋል ተብሎ የማይታሰብ ጭራቃዊ ተግባር በአካላቸው ላይ ተፈፀመ። ሂንድ አስክሬኑን አስቀድዳ ጉበቱን በላችው።👇👇👇
💛 ጧኢፍ ነዋሪዎቿን በነቂስ አውጥታ የስድብ እና የድንጋይ ናዳ እንዲወርድበት ፈቀደች። ምድር ከሰውነቱ የሚፈሰውን ደም መጠጠች።
❤️በመርዝ የተለወሰ ምግብ ሲሱጠት፣ ከሚናፍቅው የትውልድ ቀዬ ሲባረር ይቅር ባይነት የዘወትር ስንቁ ነበር። ስቃይ በተሸከመው አካልና መንፈሱ ታግዞ እግሮቹ አስከሚያብጡ ድረስ ለሊቱን በመቆም አመስጋኝ ባሪያ ለመሆን ከአምላኩ ጋር ያወጋል ሰዎችን ይቅር ይሉ ነበር ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ 
እናም ፈተና  መብዛት ችግር መደራረብ ባይኖር ዱንያ የደስታ ሀገር ብትሆን ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ ባልተፈተኑ ነበር እናም አንተም አንቺም እሱም እሷም እናንተም ፈተና ላይ ናቸሁ ፈተና ጨርሳችሁ ትንሽ ከተደሰታችሁ ቡሀላ ሌላ የከበደ ፈተና እንደሚጠብቀን እርግጠኛ ሁን የዛን ጊዜ ነዉ ኢማንህ የሚለካዉ፡፡
ኢማናችን መለካት እንጂ መነካት የለብንም ወገን


📌 እጅግ አምልኮ በማብዛት የሚታወቀው ታላቁ ታቢዒይ አልፉደይል ኢብኑ ዒያድ ረሒመሁላህ ፈገግታ አያበዙም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ግን ልጅ ሲሞትባቸው ፈገግ አሉ፡፡ ለምን ፈገግ እንዳሉ በተጠየቁ ጊዜ “አላህ የወደደው ነገር ነውና እኔም ወድጄ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የወደደውን እንድትወድ ነፍሴ ፈገግ እንድትል አስገደድኳት” አሉ፡፡

ዑለማዎች ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያለቀሱበትንና አልፉደይል ግን ፈገግ ያሉበትን ሁኔታ በማንሳት ለመተንተን ሞክረዋል፡፡ በመታገስ ደረጃ አፉደይል ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይበልጣሉ ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ትርጉሙም፡- ሞት በሚመጣበት ቅፅበት ቀልብን በሁለት ሰሜት ውስጥ ይከታል፡፡ እዝነትና ውዴታ፡፡ ማንም ሰው ሁለቱን ስሜቶች በአንድ ጊዜ ማስተናገድ አይችልም፡፡ አልፉደይል ሁለቱን ማሳካት አልቻሉምና በውዴታ ስሜት አንድም ፈገግ ማለት አለባቸው አሊያም አብዝተው ማልቀስ ነበረባቸው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ግን ሁለቱን ማሳካት ችለዋል፡፡ አላህ የወደደውን ወደዋል በሌላ በኩል ደግሞ አልቅሰው እዝነት ስሜት አሳይተዋል

📌 የነቢያችን አክስት የሆነችው : እመት ሶፊያ በኡሑድ ጦርነት ወቅት ቁስለኞችን ውሃ ታጠጣ ነበር፡፡ ታላቁ ጀግና ሐምዛ (ረ.ዐ) ተገደሉና አካላቸውም እንዲቆራረጥ ሆዳቸው እንዲቀደድ ተደረገ፡፡ ሒንድ በበቀል ስሜት ጉበታቸውን እስከማኘክ ደረሰች። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለልጇ ዙበይር ኢብኑ አልዐዋም ዝበይር ሆይ! ሶፊያን ወደ መዲና ይዘሀት ሂድ ሐምዛን ማየት የለባትም፡፡” አሉት። ልጇም ሄደና “እናቴ ሆይ! ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና ተመለሽ ብለውሻል፡፡” አላት፡፡

ልጄ ሆይ! ይህን የምታደርጉት ሐምዛን እንዳላይ ብላችሁ ነው አይደል? አለችው፡፡
....“አዎን” አላት፡፡
....እሷም “ልጄ ሆይ! አላህ ከዋለልን ፀጋ አንፃር በሐምዛ ላይ የደረሰው በጣም ቀላል ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በሐምዛ የፈተነን ሥራውን መውደድ አለመውደዳችንን ለማየት ነው፡፡ ወደ አላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሂድና የአላህ መልዕክተኛ ሆይ አላህ በሐምዛ የፈተነን ሥራውን መውደዳችንን ለመፈተን ነው ብላለች ሶፊያ በላቸው ፡፡ ልጁም ወደ ነብዩ (ሲዐወ) በመመለስ ነገራቸው፡፡
... ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) “እንግዲያውስ ማየት ትችላለች፡፡” አሉ፡፡ ሄደችና አይታው አለቀሰች፡፡ ኢንና ሊላህ ወኢንና ኢለይሂ ራጂኡን የኛዑን እኛ የአላህ ነን ወደ አላህም ተመላሾች ነን፡ በማለትም ዱዓእ አደረገችለት፡፡
እናም አላህ በሚያመጣብን ፈተና የዱንያም ሆነ የጂን የሲህርም አላህ ወዶን እየፈተነን እንደሆነ አንዘንጋ

ጅን ሲህር ሳሂር ደጋሚ ጠንቋይ ደብተራ እንደማይጎዳ አሏህ ብቻ ጎጂ እንደሆነ ማወቅን ከኢማኖች ውስጥ ጠንካራ ኢማን ሁኖ እናገኘዋለን!! በአሏህ ላይ የቂን እጅግ የምንፈልገው መሳርያ ነው!! ሌቦች ቤትን ሊዘርፉ ሲመጡ አለሁ ብሎ ድምፅን ማሰማት ሲቀጥልም የመሳርያን ድምፅ ማሰማት እነርሱን እንደሚያስበረግጋቸው ሁሉ የቂን ልክ እንደዛው ጅኖችን ያስፈራቸዋል እንዳይቀርቡን!! ይሁንና ያለ እውቀት ያለ መጠበቅያ የቁርአን አያዎች እና ዚክሮቸች ማለት ያለ መሳርያ መሳርያ ታጥቀው የመጡ ሌቦችን ማስፈራራት ብቻ ነው፡፡ ለኛ መሳርያችን ለጅኖች ሊያውም ከባለጌዎች ለመጠበቅ የምንታጠቀው መሳርያ ዚክርና ቁርአን እንዲሁም ዱአእ ነው፡፡ ሌላውን አይነት የመሀይማን መሳርያ የሆነውን ጥንቆላ መተት ፀበል እና አንጃ ግራንጃዎች ልክ ሌቦችን እንደመማፀን እንደመደራደር ነው የምንቆጥረው፡፡ ከሌባ ጋር ድርድር የለም ባንተ ንብረት ላይ መጥቷልና ፡፡ ከጅን ጋርም እያጠቃህ መደራደር የለም በቁርአን በዚክር ልኩን አሳይተሀው  መከባበር እንጂ፡፡


🖍🖍 እናም ፈጣሪ ይሁን ብሎ ተፅፎብን ከሆነ ትዕግስት ጥንካሬ ፅናት ያስፈልጋል፡፡ በሲህር በጂን የሚፈተን ሰዉ በዛዉም የፀና የጠነከረ አላህ ወዶን ይሆናል ዱአ ላይ መበርታት ግዴታ ነዉ...ከዱአ በጭራሽ ተስፋ ልንቆርጥ አይገባም
{ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِی عَنِّی فَإِنِّی قَرِیبٌۖ أُجِیبُ دَعۡوَةَ ٱلدَّاعِ إِذَا دَعَانِۖ فَلۡیَسۡتَجِیبُوا۟ لِی وَلۡیُؤۡمِنُوا۟ بِی لَعَلَّهُمۡ یَرۡشُدُونَ }
ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡[አል በቀራህ: 186]


🟢  አንድ ድንቅ የሆነ ሐዲስ አልቁድስይ ላካፍላችሁ፡፡ ነቢዩ ባስተላለፉት ሐዲስ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- “የአደም ልጅ ሆይ! እኔም እፈልጋለሁ አንተም ትፈልጋለህ፡፡ እኔ ለምፈልገው ነገር እጅ የሰጠህ እንደሆነ የምትፈልገውን አመጣልሃለሁ እኔ ለምፈልገው ነገር እጅ የማትሰጥ ከሆነ በምትፈልገው ነገር ላይ  እንድትደከም አደርግሃለሁ፡፡ በመጨረሻ እኔ የምፈልገው ነገር ብቻ እንጂ የሚሆን የለም፡፡” ይለናል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በተከበረ ቃሉ “አላህ ካሻ በስተቀር አናንተ አትሹም (አል-ኢንሳን ፡3) ብሏል፡፡

🟢 ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) ዱዓዬ መቼ ተቀባይነት እንደሚያገኝ አውቃለሁ፡፡ አሉ፡፡ “እንዴት ልታውቅ ትችላለህ? ተባሉ፡፡፡ “ቀልቤ በጥልቀት የአላህ ፍራቻ ካደረበት፣ መላ አካላቴ ከተንቀጠቀጠ፣ ዐይኔ ካነባች፣ ይህች ሰዓት ዱዓዬ ምላሽ የሚያገኝበት ነው፡፡ በማለት በዱዓዬ እጠናከራለሁ፡፡ ብለዋል፡፡

ለዱአ መቸኮል አያስፈልግም
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “እስካልቸኮላችሁ ድረስ ምላሽ ይሰጣችኋል፡፡” አሉ፡፡ መቸኮል ሲባል እንዴት ነው? ሲሏቸው አንዳችሁ “ዱዓእ አደረግኩ፤ ዱዓእ አደረግኩ ምላሽ አላገኘሁም፡፡ ይላል፡፡ (ተስፋ መቁረጥ) ዱዓእ ይተውን ይተዉና በዚያው ምላሽ ያጣል፡፡” ብለዋል፡፡
ሲህር ከተደረገብን ወደ አላህ የማይቋረጥ ቀጣይ የሆነ ዱአ ያስፈልጋል፡፡

🟢 ኢብኑ አልቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡ ብትባረርም እንኳን ከአላህ በር ላይ ከመቆም ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ቢመልስህም እንኳን ምክንያት ከማቅረብ አትውረድ፡፡ በሩ ተቀባይነትን ላገኙት የተከፈተ እንደሆነ ቀስ ብለህ በስርአቱ ግባ፡፡ ድሀ ነኝ ምፅዋት እፈልጋለሁ፡፡ በለው፡፡ ምፅዋት የሚሰጠው ለድሆችና ለችግረኞች ነው፡፡ እኔም ምስኪን ደሃ ነኝ፡፡ በለው፡፡👇👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ንጉስ ፈይሰል አሸዋ ላይ በተዘረጋው ምንጣፍ ላይ ተቀምጦ የአሜሪካ ቴፕላይን ካምፓኒ ሃላፊን አስጠራ
"አንዲት የነዳጅ ጠብታ ወደ እስራኤል እንዳይላክ" ሲልም አዘዘ።

አሜሪካ ትዕዛዙን ጥሳ ለእስራኤል እርዳታ እንደላከች ሲሰማ ከአሜሪካ ጋር የነበረውን የነዳጅ ሽያጭ ውሉን አቋረጠ።
በሀገረ አሜሪካ ሰላማዊ ሰልፍ ነገሰ
ሰዎች በነዳጅ ማደያዎች ፊት ተሰልፈው
ነዳጅ እንጂ እስራኤልን አንፈልግም የሚለውን መፈክር አስተጋቡ።
በዚህ ጊዜ ንጉስ ፋይሰል ታዋቂ ንግግሩን አደረገ
"ነዳጅ ከቁድስ ክብር አይበልጥብንም። አያቶቻችን በተምርና በወተት ኖረዋል እኛም ወደዛው ህይወት እንመለሳለን"
አላህ ይዘንልህ

ዛሬስ አረቦች
ዛሬስ የአለም ሙስለሞች??
በቀን ይሄን ያህል ንፁሀን ሞቱ ቆጣሪ ሁነናል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➊

#የነብዩ ሰዐወ መቃብር ቁፈራ የተጋለጠበት!!
አዘጋጅ ☞አሚር ሰይድ
የታሪክ መጻሕፍት በ557 ዓ.ሂ የተከሰተን አንድ አስገራሚ ጉዳይ ሳይጠቅሱ አያልፉም፡፡ ያ ዘመን የዐብባሳውያን ሥርወ-መንግሥት በመንኮታኮት ላይ የነበረበት ዘመን ነበር፡፡ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በአጐራባች አገራት ይኖሩ የነበሩ ክርስቲያን መንግሥታት አንድ ከባድ ሴራ ጠነሰሱ። ሴራቸው የሙስሊሞችን መዳከም ተገን አድርገው የነቢዩን አስከሬን ከነበረበት በመስረቅ ወደ ራሳቸው ግዛት መውሰድ ነበር፡፡ ይህን በማድረግም በሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ሞራላዊ ጉዳት ለማድረስ
አሰቡ::

ስለዚህ ይህን ረቂቅ ተንኮል ለማስፈፀም ሁለት የተመረጡ ሰላዮችን የሞሮኮ ኢስላማዊ አለባበስ በማልበስ ወደ መዲና ከተማ ሰደዱ ሰዎቹም ለነዋሪዎቿ ለፀሎት ወደ ቅድስቲቷ ከተማ የመጡ ሐጃጆች መሆናቸውን እንዲናገሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጣቸው፡፡ ሁለቱ ሰዎች ተልዕኮኣቸውን ለመወጣት እንዲችሉ መስጂደል ነበዊ (የነቢዩ መስጂድ) አጠገብ ባለ ቤት ውስጥ መኖር ጀመሩ፡፡ በጐረቤቶቻቸውም ዘንድ ለመታመን ሲሉ መስጂድ ማዘውተርና የዒባዳ ተግባራትን በጥልቀት ማከናወን የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ሆነ፡፡ ዋናው ጉዳያቸው ግን የተላኩበትን ዓላማ ማስፈፀም እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ይህን ተልዕኮ ለማከናወን የመጀመሪያ ሥራቸውንም ከነበሩበት ቤት አንስተው ወደ ነቢዩ መቃብር ለመድረስ ውስጥ ለውስጥ በመቆፈር መሿለኪያ ለማበጀት ቁፋሮ ጀመሩ፡፡ እንዳይነቃባቸውም በየቀኑ ትንሽ ትንሽ ብቻ እየቆፈሩ የሚያወጡትን አፈር በትናንሽ መያዣዎች አድርገው ጀለቢያቸው ሥር በማንጠልጠል አል-በቂፅ ወደሚባለው የመዲና
   የቀብር ስፍራ እየወሰዱ ይደፉ ነበር። ሌሎቹ ነዋሪዎች ሰዎቹ በየዕለቱ ወደ ቀብር ሥፍራ የሚሄዱት የሞቱትን በመዘየር ሞትና አኼራን ለማሰብ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡ ሰዎቹ አንዳንዴ ሲደክማቸው መሿለኪያ ለማበጀት የሚቆፍሩትን አፈር ከሚኖሩበት ቤት አጠገብ ወዳለ ጉድጓድም ይደፉ ነበር። እንዲህ እያደረጉ በመጨረሻ መሿለኪያውን ከነቢዩ ሰዐወ ቀብር ጋር ሊያገናኙ ደረሱ፡፡ እዚህ ደረጃ ሲደርሱ ተልዕኮኣቸው ለመሳካቱ እርግጠኛ ስለነበሩ የትኩረት አቅጣጫቸው የነቢዩን አስከሬን ካወጡ በኋላ በምን መንገድ ወደ መጡበት ግዛት እንደሚያጓጉዙ ማቀድ ነበር፡ የተለያዩ ዘዴዎችን አውጥተው አወረዱ፡፡ በዚያው ወቅት አላህ የራሱን ሴራ እያሴረባቸው እንደሆነ ግን አላወቁም፡፡

የዘመኑ የሙስሊሞች መሪ የነበሩትና ከመዲና ብዙ ርቀው የሚኖሩት ኑረዲን ሙሐመድ ኢብኑ ዘንጂ በዚያው ሰሞን አንድ ለየት ያለ ሕልም እዩ፡፡ በሕልማቸው ውስጥ ነቢዩ ሰዐወ ነበር የታዩዋቸው፡ ነቢዩ ወደ ሁለት ቀያይ ፀጉረ ልውጥ ሰዎች እያመለከቱ ከእነርሱ እንዲያድኗቸው ኑረዲንን ይማፀናሉ ይህን ከባድ ሕልም ሲመለከቱ ኑረዲን በድንጋጤ እየተንቀጠቀጡ ከእንቅልፋቸው ነቁ። ራሳቸውንም ለማረጋጋት ሶላት ከሰገዱ በኋላ ተመልሰው ወደ መኝታቸው ቢሄዳም አሁንም ያው ሕልም ተመልሶ መጣባቸው:: ሕልሙ ለሦስተኛ ጊዜ ሊመጣባቸው ከእንቅልፋቸው በመነሣት ከሚንስትሮቻቸው መካከል ሷሊሕና ብልህ የነበረውን ጀማሉዲን አል ሙሲሊ የተባለውን አስጠሩ፡፡ ያዩትን ሕልም ለጀማሉዲን ሲነግሩት ሕልማቸው በመዲና ውስጥ የሆነ እንግዳ ነገር እየተከናወነ መሆኑን እንደሚጠቁም አስረዳቸው፡፡ በአስቸኳይም ወደ ነቢዩ ከተማ በመሄድ ስለ ሕልሙ ለማንም ሳይናገሩ ሁኔታዎችን እንዲከታተሉ አሳሰባቸው፡፡ ኑረዲን ከለሊቱ የቀረውን ክፍል ለጉዞው ዝግጅት ሲያደርጉ አደሩ፡፡ ጀማሉዲንን ጨምሮ ሃያ ጭነት ከሃያ ሰዎች ጋር እንዲዘጋጅ አዘዙ፡ ከሻም(ሶሪያ) ተነስተው መዲና ለመድረስ የፈጀባቸው ዐሥራ ስድስት ቀናት ብቻ ነበር። መዲና ሲደርሱ በፍጥነት የሄዱት በመስጂደል ነበዊ ውስጥ ወደሚገኘው አልረውዳ ልዩ የሶላት ስፍራ ነበር፡፡ እዚያ በመሄድም ዱዓ አደረጉ:: ይሁን እንጂ ሕልሙን በተመለከተ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሊያውቁ አልቻሉም፡፡ አማካሪያቸው ጃማሉዲን በሕልማቸው ውስጥ ያዩዋቸው ሁለት ሰዎች ምን ዓይነት እንደሆኑ እንዲነግሩት ሲጠይቃቸው ኑረዲን የሰዎቹን መልክና አለባበስ እንደሚያስታውሱና ቢያገኙዋቸው መለየት እንደሚችሉ ነገሩት፡፡ ጀማሉዲን ሰዎቹን ለመያዝና ሴራቸውን ለማክሸፍ ቆርጠው በመነሳታቸው ፈጣን እርምጃዎችን መውሰድ ጀመሩ፡፡ የመዲና ነዋሪዎች በመስጂዱ ውስጥ ሲሰበሰቡም እንዲህ የሚል ማስታወቂያ አስነገሩ፡፡ 'መሪያችን በሶደቃ ለመስጠት ነይተው ያመጡት ብዙ ሃብት አለ፡፡ ሶደቃውን ለማከፋፈል እንዲመቸን በችግር ውስጥ ያላችሁ ሰዎች ሁሉ እየመጣችሁ ስሞቻችሁን እንድታስመዘግቡ እንጠይቃለን የሚል፡፡ ይህን ማሳሰቢያ እንዳስነገሩ ሰዎች ሶደቃውን ፍለጋ ተንጋግተው መምጣት ሲጀምሩ ኑረዲን በሕልማቸው ውስጥ ያዩዋቸውን ሰዎች ለመለየት ዳር ቆመው እያንዳንዱን ሰው ይቃኙ ነበር። ብዙ ሰዎች መጥተው የድርሻቸውን እያነሱ ቢሄዱም ኑረዲን ተፈላጊዎቹን ሁለት ሰዎች ሊያገኙ አልቻሉም፡፡

በመጨረሻም ከሶደቃው ድርሻውን ያልወሰደ ሰው እንዳለ ሲጠይቁ የሆነ ሰው ·ከሞሮኮ የመጡ ሁለት ሰዎች አሉ፡፡ ሰዎቹ በጣም ሷሊሕ ሰዎች ስለሆኑ ሶደቃውን ለመቀበል አልፈለጉም አላቸው፡፡ ኑረዲን ይህን እንደሰሙ ሁለቱን ሰዎች በአስቸኳይ እንዲያመጧቸው አዘዙ፡፡ ኑረዲን ሁለቱ ሰዎች እፊታቸው እንደቀረቡ ሰዎቹ ነቢዩ ሰዐወ በሕልማቸው ያመለከቷቸው ሰዎች መሆናቸውን በቀላሉ አወቁ። ሰዎቹንም “ለመሆኑ ከየት ነው የመጣችሁት? በማለት ጠየቁ፡፡ እነርሱም የመጣነው ከመግሪብ ነው፣ አመጣጣችን ለሐጅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ዓመት እዚሁ ለማሳለፍ ወስነናል' አሏቸው:: ኑረዲን ሰዎቹ የሆነ ያቀዱት ሴራ መኖሩን ቢጠረጥሩም ምን እንደሆነ በእርግጠኝነት ለመለየት ስላልቻሉ ድብቅ ሴራቸውን ይፋ እንዲያወጡ በማሰብ የተለያዩ ጥያቄዎችን አከታትለው ቢጠይቁም ምንም ፍንጭ ሳያገኙ ቀሩ፡፡ በዚህም የተነሣ ምንም እርምጃ ሊወስዱባቸው አልተቻላቸውም:: ኑረዲን ቀጥለው ያዘዙት ቤታቸው ይፈተሽ የሚል ነበር፡፡ ቤታቸው ሲፈተሽም በቤቱ ውስጥ ካስቀመጡት በርካታ ገንዘብ ውጭ ሊያስጠረጥራቸውና ሊያስወነጅላቸው የሚችል ምንም ነገር ሳይገኝ ቀረ፡፡ ለፍተሻ ወደ ቤታቸው የገባ ሰው አንድ በአንድ መውጣት ሲጀምር ኑረዲንም ምንም ምልክት በማጣታቸው ቤቱን ለቀው ሊወጡ ሆነ: በዚያች ቅፅበት ነበር አላህ የሙስሊሞቹ መሪ አንዳች ነገር አትኩረው እንዲመለከቱ ያደረገው ኑረዲን ወለሉን ሲቃኙ በወለሉ ላይ ከተነጠፉት ጣውላዎች ው አጥብቆ እንዳልያዘ አስተዋሉ፡፡ ይህን እንዳዩ ጐንበስ በማለት ጣውላውን ሲያነሱ የመዲናን ነዋሪዎች ጉድ ያሰኘ ክስተት ተስተዋለ። በወለሉ መሿለኪያ መቆፈሩን ነዋሪዎቹ ግን ይበልጥ የተደናገጡት መሿለኪያው ወዴት እንደሚያመራ ሲረዱ ነበር፨ መሿለኪያውን የቆፈሩት በከተማይቷ ውስጥ በሷሊሕነታቸው ይታወቁ የነበሩት ሁለቱ የሩቅ አገር እንግዶች መሆናቸው ሌላው ግርምታ የፈጠረ ጉዳይ ሆነ፡ እስከዚያን ጊዜ ድረስ ሁለቱ ሞሮኮኣውያን የሚታወቁት በጥልቅ ዒባዳቸውና በላቀ ኢስላማዊ ሥነ-ምግባራቸው ነበር፡፡ እጅግ የተናደዱት መሪ ኑረዲን ሁለቱን ሰዎች መግረፍ ሲጀምሩ ሰዎቹ በርግጥ ከመግሪብ (ሞሮኮ) አንዳልመጡና በመሪያቸው ከፍተኛ ገንዘብ ተከፍሏቸው የተላኩ ክርስቲያኖች መሆናቸውን የመጡትም የነቢዩን አጽም ቆፍረው በማውጣት በድብቅ ወደ አገራቸው ለመውሰድ መሆኑን አመኑ፡፡ ኑረዲን ሁለቱ ሰዎች በሞት እንዲቀጡ አዝዘው የተቆፈረው መተላለፈያም በአስተማማኝ መልኩ በአለት እንዲደፈን አደረጉ፡፡ ሴራውንም እንዳከሸፉ ወደ ሻም (ሶሪያ) ተመለሱ፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➋

#ነፍስያውን_ያሸነፈው_ወጣት
አሚር ሰይድ

ኢብን ሐዝም በጣም ይዋደዱ ስለነበሩ ሁለት ጓደኛሞች ታሪክ አስተላልፈውልናል፡፡ ሁለቱ ጓደኛሞች ከመዋደዳቸው የተነሣ በመካከላቸው ምንም ገደብ አልነበራቸውም። ከዕለታት አንድ ቀን ጓደኛሞቹ በአንደኛው ቤት ተቀምጠው ሳለ መሸ። ከጓደኛው ጋር ሲጫወት የነበረውና የቤቱ ባለቤት የሆነው በድንገት ለአስቸኳይ ሥራ ወጥቶ ለመመለስ ባለመቻሉ በቤቱ የቀረው ጓደኛው እዚያው የማደሩ ነገር እርግጥ ሆነ። በቤቱ ውስጥ እሱና የጓደኛው ሚስት ብቻ ቀሩ፡፡የሁለቱን ጥብቅ ጓደኝነት የማታውቀው ሚስት እኩለ ለሊት ሲደርስ ከባሏ ጓደኛ ጋር የመተኛት ፍላጐት ስላየለባት እሱ ወደተኛበት ክፍል ዘልቃ በመግባት እንዲገናኛት ወተወተችው፡ በመጀመሪያ ላይ የጠየቀችውን ለማድረግ ልቡ ቢነሣሣም የጓደኛው አመኔታ ሲታወሰው ስሜቱን ለመግታት ያልተለመደ እርምጃ ለመውሰድ ተነሣ፡፡ የጓደኛው ሚስት ስታስቸግረውና የእሱም ስሜት ሲነሣሣ አንደኛውን የእጁን ጣት አጠገቡ በነበረው ኩራዝ ላይ እያስቀመጠ “ከጀሃነም እሳት ይህ ይሻልሃል' ይል ጀመር፡፡ ሴትየዋ ይህንንም እያየች ወጣቱን ለወሲብ መፈለጓን አልተወችም፡፡ እሱም እሷ ባስቸገረችውና ስሜቱ በተቀሰቀሰበት ቅፅበት የእጆቹን ጣቶች በኩራዝ መለብለቡን ቀጠለ። ሲነጋ ከእጆቹ ጣቶች አንደኛው ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኖ ነበር፡፡

ጓደኝነት ይህ ነው


join👇👇👇

www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➌
#የዱዓ_ዕምቅ_ኃይል
  አሚር ሰይድ

ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት አንዲት ሴት የኢማም ማሊክ ደረሳ የነበሩ ኢስማዒል የሚባሉ ዓሊም ታገባለች የዚህ የተቀደሰ ጋብቻ ትሩፋት ሙሐመድ የሚባል ልጅ ማግኘታቸው ነበር ኢስማዒል ብዙም ሳይቆዩ አረፉ። ከበስተኋላቸው ግን ለሚስታቸውና ለሕፃን ልጃቸው ማሳደጊያ የሚሆን ብዙ ሃብት ትተው ነበር፨ እናት ልጇን ሙሐመድን በጥሩ ኢስላማዊ ሥነ-ምግባር ኮትኩታ አሳደገች በቂ የዲን ዕውቀትም እንዲቀስም አደረገችው ልጃ, አድጐና በዕውቀት ፋፍቶ ታላቅ ዓሊም እንዲሆንላት ምኞት ቢኖራትም ይህ ልጅ አንድ ችግር ነበረበት ዓይነስውርነት። በዘመኑ ደግሞ ለዓይነስውር ታዳጊ በዕዉቀት ለመግፋት ምቹ ሁኔታ አልነበረም፨ የዲን ዕውቀት የሚፈልጉ ሰዎች ከአገር አገር፣ ከዓሊም ዓሊም መሄድ የግድ ስለነበር ይህ ልጅ ይህን ለማድረግ ዕድል አልነበረውም፡፡እናቱ ግን ተስፋ አልቆረጠችም በየዕለቱ ዱዓ ማድረግ ጀመረች በዚህ ሁኔታ እያለች ከዕለታት አንድ ቀን በእንቅልፋ ለየት ያለ ህልም አየች። በህልሙ ውስጥ ነቢዩላህ ኢብራሂም  ወደ እሷ መጥተው “ከዱዓዎችሽ ብዛት የተነሣ አላህ ሰምቶሽ ለልጅሽ የአይኑን ብርሀን መልሶለታል አሏት

እናት እስኪነጋ ለመጠበቅ አልቻለችም፨ ተነስታ ልጁ, ወደተኛበት ክፍል ገብታ ከእንቅልፉ ስትቀሰቅሰው የሙሐመድ ዓይኖቹ በርግጥም በርተዋል አላህ የሚሳነው ነገር የለም፡፡

በታላቅ ጭንቀት ላይ ያሉና ለእርዳታ ወደርሱ የተመለሱትን ባሮች ከመርዳት ወደኋላ አይልምና አላህ የልጇን ዓይነስውርነት በመፈወሱ እጅግ የተደሰተችው እናት ልጇ ለትምህርት ያለውን ጉጉት ያብልጥ እንዲገፋበት በርትታ አዝዘችው በዚህ የዒልም ዘርፍ ከፍተኛ የተባለ ዕውቀቶችንም እንዲቀስም ረዳችው፡፡ በሕይወት ዘመኑ አጋማሽ ላይ ይህ ልጅ ከቁርኣን ቀጥሉ ታላቅ ተቀባይነት ያለውን መጽሐፍ ለማዘጋጀት የበቃው የሶሒሕ ቡኻሪ አጠናቃሪ –በሙሉ ስማቸው ሙሐመድ ኢብኑ ኢስማኢል አል- ቡኻሪ ናቸው፡፡

ቡኻሪ አላህ በዲናዊ ዕውቀት ያበለፀጋቸው እጅግ ብሩህ አስተዋይና አስታዋሽ አዕምሮ የሰጣቸው ታላቅ ዓሊም ነበሩ።

join👇👇👇

www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➍
#አላህ_እንዲህም_ያድናል!
አሚር ሰይድ

ከምዕተ ዓመታት በፊት የኖረው መሪ ሱልጣን ሱቀይላ እንቅልፍ ቶሎ የሚጥለው ሰው ነበር። ከምሽቶቹ በአንዱ ግን እንቅልፍ ሸሸው፡፡ ቢገላበጥ ሊወስደው አልቻለም። እንቅልፍ እንደሸሸው የተረዳው ሱቀይላህ 'መንቃቴ ካልቀረ ሥራ ልሥራ በማለት የባሕር ኃይሉን ጀነራል በመቀስቀስ “ከመርከቦቻችን አንዱን ወደ አፍሪካ ላክ፡፡ ምን እየተከናወነ እንደሆነም መልዕክት እንዲልኩ አድርግ የሚል ትዕዛዝ ሰጠው፡፡ ጄነራሱም እንደታዘዘው አደረገ፡ እንቅልፍ በማጣቱ በለሊት የሚንሸራሸረው ሱልጣን ቆየት ብሎ ወደ ባሕር ዳርቻው ወርዶ መርከቦቹን ሲቃኝ ወደብ የለቀቀ አንድም መርከብ አለመኖሩን ስላየ ጀነራሉን ተቆጣዉ:: ጀነራሉ የታዘዘዉን መፈፀሙን እሱ በማያቀዉ ምክንያት ተመልሶ መልህቅ መጣሉን ነገረዉ፡፡

መርከቡ ከጉዞው ለምን እንደተመለሰ የመርከቡን ካፒቴን ለመጠየቅ ተያይዘው ወደ ካፒቴኑ ሄዱ፡፡ ካፒቴኑም ለምን ከጉዞው እንደተገታ እንዲህ ሲል ነገራቸው፡፡ 'የባሕር ጉዞውን ስንጀምር ድቅድቅ ጨለማ ስለነበር ምንም ነገር ለመመልከት አልቻልንም፡፡ ትንሽ እንደተጓዝን ግን ከጭለማው ውስጥ ከባሕር ላይ “አላህ ሆይ አንተ ለእርዳታ ሲጠሩት ለጠሪው የምትደርስለት አምላክ እርዳኝ" የሚል የሰው ድምፅ ስለሰማን ድምፁን ወደሰማንበት አቅጣጫ አመራን፡፡ ስንደርስ የሆነ ሰው ከመስመጥ ለመዳን የሞት ሽረት ትግል ላይ ነበር፡፡ ከባሕሩ ውስጥ ጐትተን ካወጣነው በኋላ የገጠመውን ስንጠይቀው ይቀዝፍበት የነበረው ጀልባ እንደሰጠመችበትና እኛ እስከደረስንለት ጊዜ ድረስ እርዳታ ፍለጋ ሲጮህ ውሉ እንዳመሸ ነገረን

ከዚህ ታሪክ አላህ የአንድ ግለሰብ ሕይወት ለማዳን ሲል የአገሩን መሪ እንቅልፍ መንሳቱን እንገነዘባለን፡፡ አላህ ሱወ ጥበቡ የላቀ አሠራሩ የረቀቀ እርዳታው ከማይጠበቅበት አቅጣጫ የሚደርስ አምላክ ነው፡፡


join👇👇👇

www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➎
#ሙእሚን_ከአንድ_ጉድጓድ_ሁለቴ_አይነደፍም
አሚር ሰይድ


የበድር ጦርነት ወቅት አቡ ዐዝዛህ አል-ጁመሂ የተባለ ባለቅኔ በምርኮነት ሙስሊሞች እጅ ወደቀ፡፡ አቡ ዐዝዛህ የግጥም ተሰጥኦውን ተጠቅሞ በሙስሊሞች ላይ ቁረይሾችን ሲያነሣሣ የነበረ ሰው ነበር። ከተማረክ በኋላ ወደ ነቢዩ ሙሐመድ ሰዐወ ዘንድ ቀርቦ “እኔ ብዙ የቤተሰብ አባላትን የማስተዳድር ደሃ ስለሆንኩ ምሕረት አድርገውልኝ ይልቀቁኝ, ይዘኑልኝ• በማለት ተማፀናቸው፡፡

ነቢዩም ሰዐወ አዝነውለት እንዲለቀቅ አዘዙ፡፡ ሌላ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ግን ከቁረይሽ መሪዎች አንዱ የሆኑት ሶፍዋን ኢብኑ ኡመያህ ለአቡ ዐዝዛህ 'ያ አቡ ዐዝዛህ አንተ ትልቅ የግጥም ችሎታ አለህ  ይህን ችሎታህን ተጠቅመህ ተከታዮቻችን ሙስሊሞችን በመውጋት ላይ ጽናት እንዲኖራቸው ቀስቅስልን∶ በማለት ተማፀነው፡፡ አቡ ዐዝዛህ ነቢዩ ሰዐወ እሱን በመልቀቅ የዋሉለት ውለታ ስላለ ውለታቸውን ውድቅ በማድረግ የሚጐዳቸው ነገር ላይ ለመሳተፍ እንደማይፈልግ ቢነግረውም ሶፍዋን ኢብኑ ኡመያህ አቡ ዐዝዛህ በቅስቀሣው ዘመቻ የሚረዳቸው ከሆነ- “ከጦርነቱ በሰላም ከተመለስክ ከሃብቴ አካፍዬህ ሃብታም አደርገሃለሁ፡፡ በጦርነቱ ላይ ከተገደልክ ሴቶች ልጆችህን ከእኔ ሴቶች ልጆች ጋር የተቀማጠለ ኑሮ እንደማኖራቸው ቃል እገባልሃለሁ ብሎት አሳመነው፡ በተገባለት ቃል የጓጓው አቡ ዐዝዛህ ወደተባለው ጦርነት ሄደ። ለሁለተኛ ጊዜም የሙስሊሞች ምርኮ ሆነ፡፡ እንደ በፊቱም ነቢዩ ሰዐወ ፊት ቀርቦ ምሕረት እንዲያደርጉለት ጠየቃቸው፡፡ ነቢዩ  ግን “በአላህ ይሁንብኝ ከእንግዲህ ጉንጮችህ ዳግም መካን አይነኩም። በርግጥ ሙሐመድን ሁለቴ አታለሃል፡፡ አንድ ሙእሚን ደግሞ ከአንድ ጉድጓድ ሁለቴ አይነደፍም፡ ካሉት በኋላ ወደ ዙበይር ዞር ብለው ዝብይር ሆይ! ይህን ሰው ሰይፈው አሉት፡፡ ሁለቴ ለማታለል የሞከረው አቡ ዐዝዛህ በገዛ ቅጥፈቱ ምክንያት ሕይወቱን አጣ፡፡


http://www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከመፅሀፍ ገፅ ➏
#ስግብግብነት_ሲበዛ
አሚር ሰይድ

ሙሐመድ አደ-ዳሪ የሚከተለውን አስተላልፈዋል- “ከእኛ መሃከል አንድ ስግብግብ ሰው ነበር። ይህ ሰው ያለውን ዐሥር አህዮች እየነዳ የዳር ከተማን ለቅቆ ወጣ፡ በመጓዝ ላይ እያለም አንደኛይቷን አህያ ተቀመጠባት፡፡ አህያዋ ላይ ተቀምጦ እያለ የተቀሩትን አህዮች ሲቆጥር ዘጠኝ አህዮች ብቻ ሆኑበት፨ አህዮቹን ደጋግሞ ቢቆጥርም ቁጥራቸው ያው ዘጠኝ ሆነ። ከዚያ ከተቀመጠው አህያ በመውረድ ·ተቀምጨያት ከማገኘው ጥቅም ከአንዲት አህያ ቁጥር የማገኘው ትርፍ እመርጣለሁ🙄 በማለት በእግር መጓዙን መረጠ። መኖሪያ ቀየው ሲደርስ ረጅም ርቀት በእግሩ ተጉዞ ስለነበር ተዝለፍልፎ ሊወድቅ ደርሶ ነበር፡፡

join👇👇👇

www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
2024/09/28 13:20:22
Back to Top
HTML Embed Code: