Telegram Web Link
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ


            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
          
                 ⭐️ #ክፍል👉 አስር 🔟



    🔰🔰 #የሰዉ_ዓይን (ቡዳ) 🔰🔰


   ⚡️⚡️#የሰዉ_ዓይን (ቡዳ) ምልክቶችን አስመልክቶ ሸይኽ አብዱ አል ረዛቅ እንዲህ ይላሉ፡- በቡዳ የተበላዉ የሰዉዬዉ ነፍስ ከሆነ በዚህ ሰዉ ላይ ሳኮሎጂያዊ የህመም ምልክቶች ይታዩበታል፡ ለምሳሌ፡-
☞ ወደ ትምህርት ቤት፣ ኮሌጅ ወይም ወደ ስራ ለመሄድ ይደብረዋል፡፡
☞ትምህርት ለመማር እና ለማጥናት ይከብደዋል ይጫጫነዋል፡፡
☞ነገሮችን ለመረዳትና ለማስታወስ የነበረዉ ችሎታ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡
☞ ብችኝነትን ምርጫዉ ያደርጋል ከቤተሰቦቹ ይርቃል። የቅርብ ቤተሰቦቹ እንኳን የማይወዱትና የማያስቡለት ይመስለዋል፡፡
☞ሰዎችን ተተናኮል ተተናኮል የሚል ስሜት ያድርበታል፡፡
☞ መቃወም እና መቃረን ባህሪዉ ይሆናል፡
☞ ንፅህናዉን አይጠበቅም፡፡
☞ ከቤተሰቦቹ፤ ከወዳጆቹ እንዲሁም ከጓደኞቹ ጋር መግባባት አይሆንለትም፡፡ በጭንቀት ይወረራል፡፡
☞ በፀባዩ በአመለካከቱ እና በንግገሩ ግራ የሚያጋባና የማይገመት ይሆናል፡፡
☞ መክሳት
☞ በቤተሰብ የሌለ የፊት ቡጉር የራስ ቁስለት
☞ የቆዳ መላላጥ
☞ የፊትና ሰውነት መቁሰል
☞ የትዳር አለመሳካት ። ወንድ ከሆነ ማግባት መፍራት ሴት ከሆነች ትዳር መራቅ ወይም ትዳር ይርቃቸዋል።
☞ ሰው ፊት ማውራትና መናገር መፍራት። ነገሮችን እንደ ከዚህ ቀደም በድፍረት ማድረግ አለመቻል።
☞ በተዋወቁት ሰው ሁሉ መጠላት። ጥሩ ስራ ሰርቶ ምስጋና ቢስ መሆን።
☞ የብብት የ ፊንጢጣ መቁሰል መላላጥ።
☞ ሰውን አለማመን መጠራጠር።
☞ ቁጡና ያለ ምክንያት ተናዳጅ መሆን።
☞ የልብ ምት ድንገት መጨመር።
☞ የሰውነት መጋል።
☞ ቶሎ ተሎሎ ማዛጋት፡፡ ይህም በሰላት ላይ አልያም ቁርአን በሚቀሩበት ወቅት ይፈጠራል፡፡
☞ ከሰዎች መገለልና ሰዎችን ያለምንም ምክንያት መጥላት፡፡
☞ ድንገተኛ የሆኑ በብዙ አይነት በሽታዎች መያዝ መጠቃት፡፡
☞ መስነፍና ቶሎ ቶሎ ተስፋ መቁረጥ፡፡
☞ የሰውነት ልክ አንቀጥቅጥ እንዳለበት ሰው መንቀጥቀጥ መራድ፡፡
☞ ያለ ምንም ምክንያት ማልቀስ ማዘን፡፡
☞ የሰውነት መገርጣት፡፡ ማድያት ማውጣት ፊት መቁሰል ብጉሮች መብዛት ፡፡
☞ የምግብ ፍላጎት ማጣት፡፡ ምግብ ሲበሉ መታመም፡፡ መቃጠል ማስታወክ፡፡ 
☞ እሞታለው ብሎ ከመጠን በላይ ፍራቻ በተለይም ከመግሪብ ኋላ ፡፡
☞ የማይለቅ ራስ ምታት በአንድ ጎን ብቻ ከፍሎ መታመም(ማይግሬን)
☞ እራስን ማጥፋት መመኘት 
☞ ቁርአን በሚሰሙበት ግዜ ማላብ ማስታወክ እና አይን እያዛጉ ማልቀስ፡፡
☞ የከንፈር መንከስ። ደም ቢደማም አለማቆም።
ወዘተ

   እነዚህ ምልክቶች አንድ ሰዉ ላይ በሙሉ ባይታዩም የተወሰነት ከታዩበት የሰዉ ዓይን (በቡዳ) ለመለከፉ አመላካች ስለሚሆኑ የቁርዓን ህክምና እንዲከታተል ያስፈልጋል፡፡

   🟢  #በቡዳ_የተበላዉ_የሰዉዬዉ ንብረት (ንግዱ፣ ስራዉ …..) ከሆነ ደግሞ
✏️ በገንዘብ ዙሪያ ከሰዎች ጋር ለመስራት ይጨንቀዋል፡፡
✏️የንግድ እቃዎችን ለማቅረብ እና ለማዘጋጀት ሲያስብና ሲንቀሳቀስ ይጫጫነዋል፡፡
✏️ የንግድ እቃዎቹ ለብልሽት የተጋለጡ ይሆናሉ፡፡
✏️ ገዢ ወደ እርሱ ለመደራደር ሲቀርብ የሆነ ነገር ገፍቶ ይመልሰዋል።


🟢  በቡዳ የተበላዉ የሰዉዬዉ አካል ከሆነ ደግሞ
✏️ሰዉነቱ ሙትት ድክምክም ይላል፡፡
✏️ ሰዉነቱ ይዝላል፡፡
✏️ ሲተነፍስ የማለክለክ እና ቶሎ ቶሎ አየር የማስገባት እና የማስወጣት ስሜት ይስተዋልበታል፡፡
✏️ጭንቅ ጭንቅ ይላወል፡፡ አንዳንድ ህመሞችም ይከሰቱበታል፡፡


   📚📚 አንዳንድ ሰዎች በሰዉ አይን ቡዳ የለም ብለዉ የሚያምኑ አሉ ስለ ሰዉ ዓይን ማስረጃዎች ከቁርአን

#ልጆቼ_ሆይ በአንድ በር አትግቡ ግን በተለያዩ በሮች ግቡ፣ ከአላህም (ዉሳኔ) በምንም አልጠቅማችሁም (አልመልስላችሁም፡፡) ፍርዱ የአላህ እንጂ የኔ አይደለም፡፡ በእርሱ ላይ ተመካሁ ተመከዎችም ሁሉ በእርሱ ብቻ ይመኩ

አባታቸዉ ካዘዛቸዉ ስፍራ በገቡ ግዜ ከአላህ (ዉሳኔ) ምንም ነገር ከእነርሱ የሚከላከልላቸዉ አልነበረም፡፡ ግን በያዕቆብ ነፍስ ዉስጥ የነበረች ጉዳይ ናት ፈፀማት፡፡ እርሱም ስላሳወቅነዉ የእዉቀት ባለቤት ነዉ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያዉቁም፡ (ዩሱፍ ፡ 67-68)
🔰🔰 ኢብን ከሲር እነዚህን ሁለት የቁርእን እንቀጾች ሲተነትኑ እንዲህ ይላሉ ..አላህ ስለ ያዕቆብ የሚከተለዉን አስተምሮናል ፡- ያዕቆብ ልጆቻቸዉን   ከቢንያሚን ጋር ወደ ግብጽ ሲልካቸው  ሁላቸዉም በአንድ በር በኩል እንዳይገቡ ይልቁንም በተለያዩ በሮች እንዲገቡ አዘዛቸዉ ይህን ያደረገበት ምክንያት ልጆቻቸዉ በጣም ቆንጆዎችና መልከ መልካም ስለነበሩ የሰዉ ዓይን እንዳያገኛቸዉ በመስጋት ነበር፡፡ የሰዉ ዓይን ደግሞ እዉነት ነዉ። ፈረሰኛን ከፈረሱ ላይ አሽቀንጥራ ትጥላለች፡፡
ከአላህም (ዉሳኔ) በምንም አልጠቅማችሁም አልመልስላችሁም ማለት፡- እንዲህ ዓይነት ጥንቃቄ ማድረግ ከአላህ  ዉሳኔ ሊያድን እንደማይችል ያስረዳል፤፤

አላህ ከወሰነ ማንም የእርሱን ዉሳኔ ሊሽር አይቻለዉምና፡፡ አባታቸዉ ካዘዛቸዉ ስፍራ በገቡ ጊዜ  ከአላህ ዉሳኔ ምንም ነገር ከእነርሱ የሚከላከልላቸዉ አልነበረም፡፡ ግን በያዕቆብ ነፍስ ዉስጥ የነበረች ጉዳይ ናት ፈፀማት፡፡ ከለዉ ዓይን መጠበቅ ማለት ነዉ ብለዋል፡፡

እነሆ እነዚያ የካዱት ሰዎች ቁርአንን በሰሙ ግዜ በዓይናታቸዉ ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቃረባሉ፤ እርሱም በእርግጥ አብድ ነዉ ይላሉ” (አል ቀለም፡ 5)


🌐🌐  ኢብን ዓባስ፡ ሙጃሂድ እንዲሁም ሌሎች ሊቃዉንት ይህን የቁርአን አንቀፅ በማስመልከት እንዲህ ብለዋል፡- በዓይኖቻቸዉ ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቃረባሉ” ማለት፡- አንተን ከመጥላታቸዉ የተነሳ ይመቀኙሃል የአላህ ጥበቃ ባይኖር ኖሮ (በጎዱህ ነበር)፡፡ ከነዚህ የቁርአን አንቀጾች የሰዉ ዓይን እዉነት መሆኑን እንገነዘባለን፡

  🔰 #ስለ_ሰዉ_ዓይን_ማስረጃዎች_ከሃዲስ 🔰

➊ አቡ ሁረይራህ የሚከተለዉን ሃዲስ አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ እሉ የሰዉ ዓይን (ቡዳ) እዉነት ነዉ” (ቡኻሪ እና ሙስሊም)

➋ ዓዒሻ የሚከተለዉን ሃዲስ እስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ ይላሉ ...ከሰዉ .አይን በአላህ ተጠበቁ አላህ እንዲጠብቃችሁ ፀልዩ ምክንያቱም የሰዉ አይን እዉነት ነዉ።” (ኢብን ማጀህ ዘግበዉታል። አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)

➌ ኢብን ዓባስ የሚከተለዉን ሃዲስ አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ ይላሉ
.... የሰዉ ዓይን እዉነት ነዉ። ቀደርን እጣ ፈንታን  የሚሽቀዳደም ቢኖር የሰዉ ዓይን ትቀድመዉ ነበር። እጣቢያችሁን ስትጠየቁ ታጠቡ፡፡ (ሙስሊም ዘግበዉታል) አንድ ሰዉ ወንድሙን በዓይኑ አግኝቶት እጣቢዉን ሲጠየቅ ታጥቦ ይስጥ ማለት ነዉ።

➍ አስማእ ቢንት ዑመይስ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!!! የጃዕፈርን ልጆች የሰዉ ዓይን ታገኛቸዋለች። ህክምና ባደርግላቸዉስ? ስትል ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ጠየቀች፡፡ ነብዩም እንዲህ በማለት መለሱላት አዎን .....ህክምና አድርጊላቸዉ፡፡ ቀደርን እጣ ፈንታን የሚሽቀዳደም ቢኖር ኖሮ የሰዉ ዓይን ትቀድመዉ ነበር (አህመድ ዘግበዉታል። አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)👇👇👇
➎ አቡ ዘር የሚከተለዉን ሃዲስ አስተሳልፈዋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ>>> የሰዉ ዓይን በአላህ ፈቃድ አንድን ሰዉ ከፍታ ላይ ወጥቶ እስኪፈጠፈጥ ድረስ ታጠቃዋለች” (አህመድ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)
  ይህም ማለት የሰዉ ዓይን አንድን ሰዉ ስታገኘዉ ከፍ ያለ ስፍራ ላይ ወጥቶ እንዲፈጠፈጥ ልታደርገዉ ትችላለች።

➏ ኢብን ዓባስ የሚከተለዉን አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ አሉ የሰዉ ዓይን አይነት እዉነት ነው ፡፡ ከፍታ ቦታ (ከተራራ ላይ) ትወረራለች (አህመድ ዘግበዉታል አልባኒ ሃሰን ነዉ ብለዋል)

➐  ጃቢር የሚከተለዉን ሃዲስ አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ አሉ>>>  የሰዉ ዓይን ሰዉን ቀብር ዉስጥ፤ ግመልን ድስት ዉስጥ ትከታለች (አቡ ነዒም ዘግበዉታል። አልባኒ ሃሰን ነዉ ብለዋል)

የዚህ ሀዲስ መልዕክት፡- የሰዉ ዓይን አንድን ሰዉ ታገኘዉና እንዲሞት አድርጋ ቀብር ዉስጥ ይገባ፡፡ ግመልንም ታገኝና ሊሞት ሲል ይታረዳል ድስት ዉስጥ ገብቶ ይቀቀላል፡፡

➑ ጃቢር የሚከተለዉን ሀዲስ አስተላልፈዋል። ነብዩ እንዲህ አሉ ፡- ከአላህ ቀዷዕ እና ቀድር በሆላ አብዛኛዉ ኡመቴ(ህዝቦቼ) የሚሞቱት በሰዉ አይን ሳቢያ ነዉ፡፡(ቡኻሪ ዘግበዉታል)

➒ ዐዒሻ እንዲህ አሉ >>ከሰዉ ዓይን በሩቅያ እንድታከም ነብዩ አዘዉኛል(ቡኻሪ ዘግበዉታል)

➓ አነስ አብኑ ማሊክ የሚከተለዉን ብለዋል "ከሰዉ ዓይን፣ ከአል ሁማ (መርዛማ የእባብ ጊንጥ መነደፍ) እና ከአል ነመነህ (በጀርባ ላይ የሚከሰት የቁስል አይነት ነዉ)  ህመሞች በ አል ሩቅያ መታከምን ነብዩ ፈቅደዋል  (ሙስሊም ዘግበዉታል)

➊➊ ኡሙ ሰለማህ የሚከተለዉን ሀዲስ አስተላልፈዋል፡፡ እኔ ቤት የነበረች ልጅን ፊቷ ላይ ጥቁር ወይም ዳልቻ ነገር ተመልክተዉ ነብዩ "ይህች ልጅ የሰዉ ዓይን አባት፡፡ ስሊዚህ በአል ሩቅያ አክሟት” አሉን፡
(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበዉታል)


🔰🔰 #ስለ_ስዉ_ዓይን(ቡዳ) የሙስሊም  ሊቃዉንት አስተያየት

☑️ አል ሃፊዝ ኢብን ከሲር እንዲህ ይላሉ....የሰዉ ዓይን በአላህ ፈቃድ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ይህም እዉነት ነዉ፡፡ አልሃፊዝ ኢብን ሃጀር እንዲህ ይላሉ

እርኩስ ባህሪ የተጠናወተዉ ሰዉ ከምቀኝነት ጋር በተቀራኜ አድናቆት ወደ አንድ ሰዉ ሲመለከትና በዚህ ሰዉ ላይ ጉዳት ሲደርስበት ይህ ነዉ እንግዲህ የሰዉ ዓይን ማለት፡:

☑️ ኢብን አሰር እንዲህ ይላሉ “ጠላት ወይም ምቀኛ አንድን ሰዉ ሊያየዉ እና በዚህም ሳቢያ ሰዉዬዉ ከታመመ የሰዉ ዓይን አገኘዉ ይባላል

☑️ አል ሃፊዝ ኢብን ቀዩም እንዲህ ይላሉ “ከፍተኛ የእዉቀት እጥረት ያለባቸዉ አንዳንድ ሰዎች የሰዉ ዓይን ስለመኖሩ ይክዳሉ። የሰዉ ዓይን ተጨባጭነት የሌለዉ ተረት ነዉ በማለት ይከራከራሉ፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች ከእዉነት እና ከእዉቀት የራቁ ስለ ነፍስ እና መንፈሳዊ ጉዳዮች ስለባህሪያቶቻቸዉ፣ ሊያደርሱት ስለሚችሉት ዉጤት እና ሊያስከትሉት ስለሚችሉት ተፅእኖ አንዳች ግንዛቤ የሌላቸዉ ናቸዉ፡፡

🔸🔸🔸  የተለያዩ ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ ጠቢባን የሰዉ ዓይን ስለመኖሩ አይክዱም፡፡ ምንም እንኳን ስለ መንስኤዎቹና ሊያስከትል ስለሚችለዉ ጉዳት የተለያየ አመለካከት ቢኖራቸዉም፡፡

አላህ የሰዉ ልጆችን አካላትና ነፍሶቻቸዉን በዉስጣቸዉ የተለያየ ሀይላት እና ስብዕና አድርጎ እንደፈጠራቸዉ አያከራክርም፡፡ በአንዳንድ በርከት ባሉት ላይ ደግሞ ልዩ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባህሪያት አድርጎባቸዋል። ነፍስ በአካል ላይ ልታደርስ የምትችለዉን ተጽዕኖ ማንም አስተዋይ ሰዉ አይክድም፡፡ ምክንያቱም ተጨባጭ ነገር ነዉና፡፡

#ለምሳሌ፡- የሚወደዉና የሚያከበረዉ ሰዉ የአንድን ሰዉ ፊት ሲመለከት ሲፈካ፣ በተቃራኒዉ ደግሞ የሚፈራዉ (በቁጣ) ሲያየዉ ፍም ሲመስል ይስተዋላል፡፡ ሰዉ ስላያቸዉ ብቻ የታመሙ የተዝለፈለፉ ሰዎች ማየታቸዉን ብዙዎች መስክረዋል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነዉ እንግዲህ በሰዉ ልጆች ነፍስ ተፅዕኖ ሳቢያ ነዉ። በሰዎች ነፍሶች እና በአይኖቻቸዉ መካከል ከፍተኛ ቁርኝት ስላለ ነዉ.... ይህ በነፍሶቻቸዉ የደረሰዉ ጉዳት በዓይን እንደደረሰ ተደርጎ ይቆጠራል። እዉነታዉ ግን ይህን ጉዳት የሚያስከትሉት የሰዉ ልጅ ዓይኖች ሳይሆኑ ነፍሶቻቸዉ ናቸዉ፡፡ ነፍሶች ደግም ባላቸዉ ሃይል፣ ባህሪያት እና በሌሎች ልዩ ልዩ ገጽታዎች ከሰዉ ሰዉ የተለያዩ ናቸዉ።

የምቀኛ ነፍስ ለምትመቀኘዉ ሰዉ ጎጂ ናት። ለዚህም ነዉ ነብዩን ከምቀኛ ተንኮል እንዲጠብቃቸዉ እንዲፀልዩ አላህ ያዘዛቸዉ፡፡ ምቀኛ በሚመቀኘዉ ሰዉ ላይ ስለሚያስከትለዉ ጉዳት ስለ ሰዎች አዉቀት የሌለዉ ካልሆነ በቀር ማንም አይክድም፡፡

🔹🔹🔹 .የሰዉ ዓይን ልክፍት መሰረቱ እንዲህ ነዉ፡፡ እርኩስ የሆነች ነፍስ በእርኩስ ባህሪይ ተገልጣ የምትመቀኘዉን ሰዉ ስታገኘዉ በዚህ ልዩ በሆነዉ እርኩስ ባህሪዋ ጉዳት ታደርስበታለች፡፡


ለዚህ ደግሞ ኮብራ እባብን በንፅፅር መዉሰድ ይቻላል። በኮብራ ዉስጥ መርዝ ከሃይል ጋር ይገኛል፡፡ ኮብራዉ ጠላቶቹን ሲያይ በሃይል እና በቁጣ ይነሳሳል። መጥፎና ጎጂ በሆነዉ ባህሪዉ ይገለጣል፡፡ ይህ መጥፎ የሃይልና የቁጣ ባህሪዉ ሲብስ ጽንስ እስከማስወረድ እና ዓይን እስከ ማጥፋት ይደርሳል፡፡

አብተር እና ዙጡፍየተይን ስለሚባሉ የእባብ ዓይነቶች እነዚህ ዓይን ያጠፋሉ ፅንስ ያስወርዳሉ፡፡ በማለት ነብዩ አስተምረዉናል፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)

🔻በመገናኘት!
🔻ድንገት በማግኘት፣
🔸በማየት፣ በነፍስ በማሰብ፣
🔺ድግምት በማነብነብ፤ በማማተብ፣
🔺 በምናብ በመሳል ቡዳ በሰዉ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡


🟡🔴 የቡዳ ነፍስ በማየት ብቻ አይደለም ጉዳት የምታደርሰዉ፡፡ ቡዳዉ ማየት የተሳነዉ ቢሆንም እንኳ ስለ ሆነ ነገር በሚነገረዉ ወይም በሚሰማዉ ብቻ ተመስርቶ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። በርካታ ቡዳዎች ሰዉየዉን ሳያዩት ስለ እርሱ በተነገራቸዉ ላይ ብቻ ተመስርተዉ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ቡዳ ከቡዳዉ ሰዉ በዓይኑ በኩል ውጥታ እንደ ቀስት ትወረወራለች። ዒላማዋን ልትስት ወይም ልታገኝ ትችላለች። ዒላማዉ
>> የጠዋት የማታ አዝካር የሚል
>> ሶላት የሚሰግድ
>> ቁርአን የሚቀራ ከሆን ቡዳዉ ሊጎዳዉ አይችልም።

# ባጭሩ የቡዳ ጉዳት የተመሰረተዉ እንዲህ ነዉ፡- ቡዳዉን አንድ ነገር ያስደንቀዋል፡፡ በዚህ ግዜ እርኩስ ነፍሱ  ወደ  አስደነቃት ነገር በዓይን በኩል መርዟን ትረጫለች፡፡ አንዳንዴም ቡዳ እራሱን በራሱ ሊበላ ይችላል። ሌሎችንም ቢሆን ያለፍላጎቱ ይበላል።

ክፍል 1⃣1⃣
ይቀጥላል....


4any cmt 🔽
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ

            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ

          
               ⭐️ #ክፍል👉 #አስራ_አንድ1


   🟢 #በምቀኝነትና_በቡዳ_መካከል_ያለ_ልዩነት

➊ ምቀኛ ሲባል ቡዳን ይጨምራል።
>> ቡዳ ማለት ልዩ የሆነ ምቀኛ ማለት ነዉ፡፡
>> ቡዳ ሁሉ ምቀኛ ነዉ፡፡
>> ምቀኛ ሁሉ ግን ቡዳ አይደለም፡፡ ከምቀኛ አላህ እንዲጠብቀን ዱዓ ማድረግ እንዳለብን ከአል ፈለቅ ምዕራፍ እንማራለን፡፡

☑️ አንድ ሙስሊም አላህ ከምቀኛ እንዲጠብቀዉ ዱዓ (ጾለት) ሲያደርግ ከቡዳም ጭምር እንዲጠብቀዉ ዱዓ አድርጓል ማለት ነዉ። ምክንያቱም ምቀኛ የሚለዉ ቃል ቡዳንም ምቀኛንም ሁለቱን ያጣመረ አገላለፅ በመሆኑ፡፡ ይህ እንግዲህ የቁርአን ታዓምራዊነት መገለጫ ነዉ።

➋  ምቀኝነት ከመመቅኘት፣ ከጥላቻ ወይም ሰዉ እንዲያጣ ከመፈለግ የሚመነጭ ሲሆን በተቃራነዉ ደግሞ የቡዳ መንስኤ ማድነቅና መገረም ነዉ፡፡

➌ ምቀኝነትና ቡዳ በሰዉ ላይ ጉዳት በማድረስ በዉጤት ሲመሳሰሉ በመንስኤዎቻቸዉ ደግሞ ይለያያሉ፡፡
>> የምቀኝነት መንስኤ የሰዉን ፀጋ መመቅኘት፣ በሰዉ ነገር መንገብገብ እና መቃጠል፣ እንዲያጣ መፈለግ ሲሆን በተቃራኒዉ
>>  የቡዳ መንስኤ ማየት እና መመልከት ነዉ። በዚህም ምክንያት ቡዳ ያልተመቀኘዉን ሰብል፣ ግዑዝ እቃ ወይም ንብረት ሊበላ ይቻላል፡፡ እንዲያዉም ቡዳ እራሱን በራሱ ሊበላ ይችላል፡፡ ቡዳ አንድን ነገር በአድናቆትና በአግርሞት በመመልከቱ ምክንያት ነፍሱ ወደ ዚህ ሁኔታ ትለውጥና በምታየዉ ነገር ላይ ጉዳት ታደርሳለች፡፡

➍ ምቀኛ ያልተከስተንና ገና ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅን ነገር ሊመቀኝ እና ሊጎዳ ይችላል፡፡
>> ቡዳ ግን በተግባር የሌለን ነገር ሊበላ አይችልም፡፡

➎ ሰዉ እራሱን ወይም ንብረቱን አይመቀኝም፡፡ ነገር ግን እራሱን ወይም ንብረቱን በቡዳ ሊበላ ይችላል፡፡

➏ ምቀኝነት ከምቀኛና ተንኮለኛ ብቻ የሚከሰት ሲሆን
>>  ቡዳ ግን ከመልካም እና ደጋግ ሰዎች ጭምር ሊከሰት ይችላል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ያስደነቃቸዉ ነገር እንዲጠፋ ባይፈልጉም በመደነቃቸዉ ብቻ ጉዳት ሊደርስ ይችላልና፡፡

➐ አንድ ሰዉ የሚያስደንቀዉ ነገር ሲያይ አላህ በረካ (ረድኤት) እንዲያደርግበት ዱዓ (ፆለት) ማድረግ አለበት፡፡ ያስደነቀዉ ነገር የራሱ ይሁን የሌላ ለዉጥ አያመጣም፡፡ ይህ ዱዓዕ አስደናቂዉን ነገር በቡዳ እንዳይጎዳ ያደርገዋል፡፡

     🔴 #ጂኒዎች_ሰዎችን_በቡዳ_ይበላሉ

➊ አቡ ሰዒድ አልኹድሪ እንዲህ ይላሉ>>> ነብዩ ከጂኒ ዓይንና ከሰዉ ዓይን አላህ እንዲጠብቃቸዉ ዱዓዕ ያደርጉ ነበር፡፡ የእል ፈለቅ እና የአል ናስ ምዕራፎች ሲወርዱ በእነዚህ በመጠቀም ሌሎችን (ዱዓዎች) ትተዋል” (ቲርሚዚ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብላዋል)፡፡

📌 የአል ፈለቅ እና የአል ናስ ምዕራፎችን በመቅራት ከጂኒ እና ከሰዉ ቡዳ መከላከል እና መጠበቅ እንደሚቻል ከዚህ ሃዲስ እንማራለን


➋ እናታችን ኡሙ ሰለማ እንዲህ ይላሉ፡ በቤቱ ዉስጥ በፊቷ ላይ ጥቁረት ያለባትን ልጅ ነብዩ ተመለከቱና እንዲህ አሉ የጂኒ ቡዳ ስላለባት ሩቅያ አድርጉላት” (ቡኻሪ ዘግበዉታል)

📌 ቡዳ ከ ከሰዉ ብቻ ሳይሆን  ከጂኒዎችም : (ከሰይጣናትም) ሊከስት እንደሚችል ከእነዚህ ሁለት ሀዲሶች እንገነዘባለን፡፡

ስለዚህ ማንኛዉም ሙስሊም
>> ልብሱን ሲያወልቅ፧
>> መስታዎት ሲያይ ማንኛዉንምስራ ሲጀምር ቢስሚላህ (በአላህ ስም) ማለት ይኖርበታል፡፡ ይህም ከጂኒ ቡዳ፣ ከሰዎች ቡዳ እና ከሌሎች ጉዳቶችም ይከላከልለታል፡፡


   🟡 #የሰዉ_ዓይን (የቡዳ) #ህክምና

የሰዉ ዓይን (ቡዳን) ለማከም የሚያገለግሉ በርካታ ዘዴዎች አሉ። የተወሰኑትን እንደሚከተለዉ እንመለከታለን፡፡


       🔸🔸  #መታጠብ 🔸🔸

በዓይነ ጉዳት ያደረሰዉ ሰዉ _ የሚታወቅ ከሆነ እንዲታጠብ ይደረጋል፡፡ ከዚያም የታጠበበትን ዉሀ በመዉሰድ በታመመዉ ሰዉ ገላ ላይ በጀርባዉ በኩል ማፍሰስ፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ይድናል፡፡


የትጥበቱ አፈፃፀም

ኢብን ሺሀብ አል ዙህሪ እንዲህ አሉ "ኡለማዎች ትጥበቱን በሚከተለዉ መልኩ ሲገልጹት አስተዉያለሁ፡፡ ይኸዉም በዓይኑ ጉዳት ላደረሰዉ ሰዉ በሳፋ ዉሃ ይቀርብለታል፤ ይህም ስዉ ከዉሃዉ በመዝገን ተጉመጥምጦ መልሶ ሳፋዉ ዉስጥ ይተፋዋል፡፡ ከዚያም ፊቱን ሳፋዉ ዉስጥ ያጥባል፡፡ ከዚያም ቀኝ እጁን በግራ እጁ ያጥባል። ከዚያም ግራ እጅን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ እጁን ክርን በግራ እጁ የግራ እጁን ከርን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ እግሩን በቀኝ እጁ የግራ እግሩን በግራ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ ጉልበቱን በግራ እጁ የግራ ጉልበቱን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም በሽርጡ የተሸፈነዉን የአካሉን ክፍል ሳፋዉ ዉስጥ ያጥባል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሳፋዉ መሬት ላይ መቀመጥ የለበትም፡፡ ከዚያም ዉሃዉን በታመመዉ ሰዉ ላይ በጀርባዉ በኩል ባንድ ግዜ ማፍሰስ፡፡"

ከዚህ በተረፈ በተማሚዉ ራስ እጅን አኑሮ የተለያዩ የሩቃ ምዕራፎችንና ቁርአንን መቅራት ነዉ፡፡




🔵🔵   🟠🟠🟠   #ከድግሞት_ከሲህር_ከአይንናስ_ከስንፈተ_ወሲብ_መከላከያ_መንገዶች


✏️✏️ #ዉዱዕ_አድርጎ_መንቀሳቀስ
በዉዱዕ የሚንቀሳቀስ ሙስሊምን ድግምት ሊነካዉ አይችልም፡፡ ምክንያቱም በዉዱዕ የሚንቀሳቀስ ሙስሊም ከአላህ በተላኩ መላእክት ስለሚጠበቅ ነዉ፡፡ ይህን በማስመልከት ነብዩ እንዲህ ይላሉ “የአካላችሁን ንጽህና ጠብቁ! አላህ ንፁሀ ያድርጋችሁ፡፡ ማንኛዉም ሰዉ ዉዱዕ አድርጎ ሲያድር መላኢካ ከጎኑ ያድራል፡፡ ይህ ስዉ በመኝታዉ ዉስጥ ሲንቀሳቀስ መላኢካዉ እንዲህ እያለ ጸሎት ያደርግለታል “አላህ ሆይ! ይህን አገልጋይህን  ይቅር በለው ዉዱዕ አድርጎ ነዉ ያደረዉና።" (ሳራኒ ዘግበዉታል ኢስናዱ ጀይድ ነዉ ብለዋል)


✏️✏️ ሶላት አል ጀማዓህ (የህብረት ስግደትን) መከታተል

የህብረት ስግደትን መከታተል ለሙስሊም ከሰይጣናት ተንኮል ሰላምን ታመጣለታለች፡፡ አንድ ሰዉ ሶላትን  በጀምዓ ከመስገድ ከተዘናጋ የሰይጣናት መፈንጫ ይሆናል፡፡ በልክፍት፣ በድግምት፣ በቡዳ እና በመሳሰሉት ሰይጣናት ይዘባበቱበታል፡፡ በዚህ ዙሪያ ነብዩ እንዲህ ይላሉ፡- ሶስት ሰዎች የጀምዓ ስገደት በማይሰገድባት ከተማ ወይም የገጠር መንደር ዉስጥ ከኖሩ ሰይጣን ይሰለጥንባቸዋል፡፡ ህብረትን (ጀማዓን) አደራ!! ተኩላ የሚያድነዉ እኮ ከመንጋ ያፈነገጠን በግ ነው” (አቡ ዳዉድ በኢስናዲን ሀሰን ዘግበዉታል)


✏️✏️ የሌሊት ሶላት (ስግደት)

እራሱን ከድግምት ለመከላከል የፈለገ የሌሊት ሶላት ይሰገድ፡ ከዚህም ሊዘናጋ አይገባም፤ የሌሊት ሰላትን አለመስገድ ሰይጣን በሰዎች ላይ እንዲሰለጥን በር ይከፍትለታል፤ ሰይጣን ከሰለጠነብህ ደግሞ ለድግምት ምቹ ሆንክ ማለት ነዉ ፡፡ ይህን በተመለከተ አንድ ቀን ነብዩ ዘንድ የሌሊት ሰላት ሳይሰግድ ስላደረ ሰዉ ጥያቄ ተነስቶ ነብዩ እንዲህ አሉ፡
“ይህ ሰዉ በጆሮዎቹ ሰይጣን ሸንተታል" (ኻሪ ዘግበታል)

ኢብን ዑመር እንዲህ ይላሉ - “ማንም ሰዉ የዊትር ሰላት ሳይሰገድ ካደረ ሰባ ክንድ ሰንሰስት ባንገቱ ላይ ታስሮበት ያህል " (አል ሃፈዝ.ፈትሁል ባሪ ዉስጥ ኢስናዱ ጀይድ ነዉ ብለዋል)👇👇👇
✏️✏️ ወደ መፀዳጃ ቤት ከመገባት በፊት ከሰይጣናት በአላህ መጠበቅ

ቢስሚላህ አሏሁመ ኢኒ አኡዙቢከ ሚነል ኹቡሲ ወል ኸባኢስ ማለት ..

   መፀዳጃ ቤቶች የሰይጣናት መኖሪያዎች ናቸዉ፡ የሙስሊምን እነዚህ ቦታዎች ላይ መገኘት እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅሞ ሰይጣን ሊገባበት ይችላል፤ በሩቃ  ጊዜ አንዳንዴ ጂኖቹ  ከሰይጣናት ሳይጠበቅ ወደ መፀዳጃ ቤት በመግባቱ ምክንያት ነዉ ልገባበት የቻልኩት" በማለት ይናገራሉ

(ዉዳሴዎች) ናቸዉ” በማለት መለሰልኝ፡ ነብዩ ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገቡ የሚከተለዉን ዚክር (ጸሎት) ይሉ ነበር፡-

‎ (بسم الله اللهم إني أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْحُبْثِ وَالْخَالِيث ‎ ቢስሚ አላህ አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚነ አል ኹቡሲ ወ አል ኸባኢስ” (ቡኻሪ ዘግበዉታል) ትርጉም፡- በአላህ ስም፤ አላህ ሆይ! ከወንድና ከሴት ሰይጣናት በአንተ

እጠበቃለሁ፡፡

✏️✏️ የሶላት መከፈቻ ዚክር

የሚከተለዉን ጾለት በሶላት መክፈቻ ወቅት ማለት፡፡ ጁበይር ኢብን አል ሙጥዒም የሚከተለዉን ሃዲስ ሲያስተላልፉ እንዲህ አሉ፡- ነብዩ ሲሰግዱ አየሁዋቸዉ እንዲህም ሲሉ ሰማሁ፡-


“አሏሁ አክበር ከቢራ፤ ወል ሃምዱ ሊላሂ ከሲራ፣ ወሱብሃነ አልሏሂ ቡክረተን ወአሲላ (ሶስት ግዜ)።
☞ አዑዙ ቢላሂ ሚነ ሸይጧን ረጂም ሚን ነፍኺኽ ወነፍሲኺ ወሀምዚሂ

ትርጉም፡- አላህ ታላቅ ነዉ፡፡ አላህ በብዙ የተመሰገነ ይሁን፡፡ በጠዋት በማታ አላህ ፍፁም ነዉ፡፡ ከተረገመዉ ስይጣን ከትምክህቱ፤ ከግጥሙ እና ከእብደቱ በአላህ እጠበቃለሁ፡

✏️✏️ የጋብቻ ህይወትን በሶላት መጀመር

ዓብደላህ ኢብን አል መስዑድ የሚከተለዉን አስተምረዋል። “ከመጀመሪያዉ የጫጉላ ግንኙነታችሁ በፊት ሚስትህ ሁለት ረክዓ ሶላት እንድትሰግድ አድርግ፡፡ አንተም ስገድ፡፡ ከዚያም የሚከተለዉን ፀሎት አድርግ፡-


አሏሁመ ባሪክ ሊ ፊ አኽሊ ወባሪክ ለኁም ፊዬ፣አሏሁመ ኢጅመዕ በይነና ማ ጀመዕተ በኸይሪን.. ወፈሪቅ በይነና ኢዛ ፈረቀተ ኢለ አል ኸይር” (ጦበራኒ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)

ትርጉም፡- አላህ ሆይ በረካ ያላት ሚስት አድርግልኝ፣ በእኔ ላይም በረካ አድርግ ለበጎ እስከተስበለብን ድረስ አንድ አድርገን፡፡ ወደ መልካም በምትለያየን ጊዜ ለያየን፡፡

✏️✏️ በግንኙነት ወቅት የሚባል ዱዓዕ

ነብዩ የሚከተለዉን አስተምረዉናል “ማንኛዉም ሰዉ ከባለቤቱ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ሊፈፅም ሲል የሚከተለዉን ዱዓዕ ካለ በዚህ ግንኙነታቸዉ ልጀ ቢፈጠር ልጁን ሰይጣን በፍጹም ሊጎዳዉ አይችልም ::

‎ بِسْمِ اللهِ اللَّهُمَّ جَنِّبْنَا الشَّيْطَانَ፣ وَجَنْبِ الشَّيْطَانَ مَا رَزَقْتَنا ‎ ቢስሚላህ። አሏሁመ ጀኒብና አል ሸይጣን፤ ወ ጀኒብ አል ሸይጣን ማ ረዘቅተና

ትርጉም፡- አላህ ሆይ! ከኛ ሰይጣንን አርቅልን፡፡ ከሰጠኸን ሲሳይ ላይም ሰይጣንን አርቅልን፡፡

📌📌 በአንድ ወቅት በጂኒ የተለከፈን ሰዉ ሩቃ ሲቀራበት፡፡ ጂኒዉ እስልምናን ከተቀበለ እና ንስሃ ከገባ በኋላ ታካሚዉ ይህን ፀሎት ሳይል ሚስቱን ይገናኛት ስለነበረ ሚስቱን በወሲብ እጋራዉ ነበር ብሏል፡፡

ሱብሃን አላህ! ስንት እና ስንት እንቁ ስጦታዎች እያሉን ዋጋቸዉን ዘነጋናቸዉ!




✏️✏️ ከመኝታ በፊት ዉዱዕ አድርጎ እና አያት አል ኩርሲይን ቀርቶ መተኛት፡፡


ከዚያም እንቅልፍ እንስከሚያሸንፍህ ድረስ ዚክር  ማለት፡፡ ከመተኛቱ በፊት አያት አል ኩርሲይን የቀራ ከአላህ የተላከ ጠባቂ : አይለየዉም፡፡ እስከሚነጋ ድረስም ሰይጣን አይቀርበዉም የሚለዉን ሀዲስ አቡ ሁረይራ አስተላልፈዉልናል፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)


✏️✏️ በየቀኑ ከመገሪብ ሶላት በኋላ የሚከተሱትን የቁርአን አንቀጾች መቅራት።
የአል በቀራ ምዕራፍን ከቁጥር 1 - 5 ያለዉን
➋  አያት አል ኩርስይን እና ቀጥለዉ ያሉትን ሁለት አንቀጾች
➌ አል በቀራ ምዕራፍ የመጨረሻዎችን ሶስት አንቀፆች
   እነዚህን አንቀፆች በቀራህባቸዉ ቀናት ሌሊቱንና ቀኑን ከድግምትና ከጂኒ ልክፍት በአላህ ፈቃድ ትጠበቃለህ፡፡


✏️✏️ ላኢላሀ ኢላ አላህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁ አል ሙልክ ወ ለሁ አል ሀምድ ወ ሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ከሱቢህ ሶላት በኋላ 100 ጊዜ ማለት፡፡


ይህንን በማስመልከት የሚከተለዉ ሃዲስ ተላልፎልናል። ይህን ፀሎት በቀን መቶ ጊዜ ያለ አስር ባሪያዎችን ነፃ እንዳወጣ ይቆጠርለታል፡፡ መቶ ምንዳ ይፃፍለታል። መቶ ሀጢያቶችን ይማራል። በዚያ ቀን እስከሚመሽ ድረስ ከሰይጣን መከላከያ ይሆነዋል፤ ይህ ሰዉ ከስራዉ ሥራ የሚበልጥ ማንም አያመጣም ከመቶ በላይ ያለ ካልሆነ በስተቀር፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)

✏️✏️ ወደ መስጊድ ስትገባ የሚከተለዉን ዱአ ማለት፡-

‎አኡዙቢላሂል አዚም፣ ወቢወጂብ አል ከሪም ወ ሱልጣኒሂ አል ቀዲም ሚነ አል ሸይጧን አል ረጅም (አቡ ዳዉድ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)

✏️✏️ ከቤትህ ስትወጣ የሚከተለው ዱዓዕ ማለት
‎ بسم الله توكلت عَلى اللهِ፣ وَلا حول ولا قوة إلا بِاللَّهِ ‎

ይህን ዱዓዕ በምትልበት ግዜ ሰይጣን እንዲህ ይላል “ተጠበክ ተመራህ፤ ተብቃቃህ እንግዲህማ ሰይጣን ይሸሽሃል ....ሌላ ሰይጣንም ሲያገኝ እንዲህ ይለዋል የተጠበቀን የተመራን የተብቃቃን ሰዉ ምንስ ልታደርገዉ ትችላለህ? ምንም ልታደርገዉ አትችልም” (አቡ ዳዉድ እና ቲርሚዚ ዘግበዉታል)


#ክፍል 1⃣2⃣
ይቀጥላል....


አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
30 አመት ወደ ኋላ የዘመን ቀመሩ ሲፈተል በ1992

  በተሞሸረች በ3 ቀኗ የሠርጉ ድባብ በቅጡ ሳይቀዘቅዝ ፍቺው ፀድቆ ወደወላጆቿ ቤት ተመለሰች። ያለምንም ምክንያት ተፋተው ወደ እናቷ ቤት ተሸኘች። ያ አምስት ዓመታትን ያስቆጠረው ውብ የፍቅራቸው ጊዜ በድንገት አከተመ። ሚስት የስቃይ ህይወትን መግፋት ጀመረች። እሱም ከሷ በኋላ ሳያገባ ድፍን ሰላሳ ዓመታት አለፈ። ሲህር ነበር ያለያያቸው የሠርግ ቬሎዋን ጠቅልለው ከሞተ ሰው አስክሬን አፍ ላይ ፎቷቸውን አስረው ቆፍረው ከመቃብር ስፍራው ቀበረው በስቃያቸው ተደሰቱ።

ሲህሩ ተገኝቶ ከተቀበረበት እንደወጣ ሚስቱ ድና ወደመልካም የጤንነት ሁኔታዋ ተመለሰች። ባል ወደ ቤተሰቦቿ አቀና። ሚስቱን በድጋሜ ተንበርክኮ ጠየቀ። አዲስ ፍቅር ቤታቸው ገባ። ጤንነት ከደጃፋቸው ደረሰ። ፍቅራቸውም አገረሸ። በ2022 ዳግም በእልልታ ተሞሸሩ።

የአክስቷ ልጅ ነበረች ሲህሩን ያሰራችባት። ቬሎዋን ቀዳ ለደጋሚው የሰጠች። ሳሂሩ ጥቁር ዶሮ አሽከርክሮ አንገቱን በጠሰና ደሙን ከፎቷቸው ጋር ለውሶ ከጀናዛ አፍ ጋር አስሮ ህይወታቸውን በስቃይ እንዲገፉ አደረጋቸው። አላህ ከሰባት ሰማያት በላይ ሆኖ አዘነላቸው ከድፍን ሰላሳ አመታት በኋላ ከአፊያው ዳብሶ ዳግም አገናኛቸው።
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ
             
          
                 ⭐️
#ክፍል👉 አስራ ሁለት 1⃣2⃣


  🔰🔰በተከታታይ ➊➊ ፓርቶች ድግሞትና ሲህር ከሚለዉ መፅሀፍ 70% በራሴ ካነበብኳቸዉ ከማቃቸዉ 30% ጨምሬ ከሰዎች ታሪክ በመጨመር በምሳሌ አቅርቢያለሁ ..ከpart ➊➋ ጀምሬ እስኪ ከሰማሁት ከማቀዉና መረጃዎችን በማጣቀስ ለእናንተ አቀርባለሁ፡፡


መጀመሪያ ብዙሀን ሰዉ አናምንም እኛን አይነካንም እንላለን ...ግን በራስ ሲደርስ ነዉ የሚታወቀዉ  የኢማን የመጠንከር የመላላት ጉዳይ አይደለም የሆነ የምንዘናጋበት ቀን አለ በዛ ቀን በሰዉ ምቀኛ በተለይ በቅርብ ጓደኛ በቅርብ ዘመዶች ሊያነጣጥሩብን ይችላሉ ....የት ይሰራል ብላችሁ ካሰባችሁ ...ብዙዎች እነሸህ እነ ወልይ የወደፊት ያቃሉ እያሉ እየሄዱ እየሰገዱ ቁርአን እየቀሩ ጀለብያ ጥምጣም ለብሰዉ ሳሂር ደጋሚ የሆኑ እንዳሉ አንዘንጋ በተጨማሪ ደግሞ በጣም ብዙ ሰዉ ከሙስሊሙም ሌላም ሀይማኖት ተከታዮች የሚሄዱት ደብተራዎች ጋር ነዉ፡፡ 
ደብተራዎች face book እና tg ቻናል አላቸዉ ለምሳሌ ሁለት የማቀዉን ከtg ያገኘሁትን ከታች ተመልከቱ

⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
መርጌታ ገብረ መድን በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ለማይችሉ ባሉበት እንሰራለን የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል   ☎️  09 ... 03 ....☎️ ስልኩን ያጠፋሁት ደግሞ እንዳደዉሉ ብየ ነዉ☺️
ለገበያ>>ለሀብት>>ለስንፈተ ወሲብ (ለቁመት:ለውፍረት: ቶሎ ለሚያበቃ) >> ለመስተፋቅር >>ጥይት ለማያስመታ >> ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ >> ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)>> ለፀር (ለጠላት)>>ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)>> ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)>>ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)>>ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)>> #መስተፋቅር>> ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
>> ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ>> ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)>> የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ>>ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)>> መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)>> መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)>> ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)>>ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)>> ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ>> ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ>> ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)>> ለሙግት>> ለሰላቢ>> ለስንፈት ወሲብ>> ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)>> ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)>> ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)>> ለዱላ( ዱላ የማያስመታ)>> መንስኤ_እስኪት (ለወንድ የመራቢያ አካሉ ለደከመ ላነሰ)>> ህገ_ጠብቅ (የትዳር አጋራችን ወደሌላ እንዳይሄድ የሚያስር
እንዳይዘሙት የሚከለክል)>> ለአይነ_ሰብእ (ከሰው አይን የሚጠብቅ)>> በመኝታ ሽንት ለሚያመልጠው >> እንቅልፍ መብዛት>> የእንቅልፍ ማነስ >> የወር አበባ ችግር ካለ

09...  03 ....
ይደውሉልን

✏️✏️በተጨማሪ የሌላዉን በtg የሚፓስተዉን ልላክላችሁ👇👇👇👇

☎️📞09 4............5  የባህል መድህኒት  ጥበብ አስማት ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
መፍትሄ ሀብት መስተፋቅር = የገበያ  ለቀለም= ትምህርት ለአይነ ጥላ= ለመፍትሔ ስራይ= ለህማም = ጋኔን ለያዘው ሰው = ቡዳ ለበላው = የዛር ውላጅ ለተዋረሰው = ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር) =  ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ) =  ለቀለም(ለትምህርት) = ሰላቢ የማያስጠጋ =  ለመፍትሔ ሀብት =ለመስተፋቅር =  ለገብያ =  ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ) = ለመድፍነ ፀር =  ሌባ የማያስነካ = ለበረከት
= ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ) = አፍዝዝ አደንግዝ = ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ) = ለግርማ ሞገስ =  ለዓይነ ጥላ
=  ለሁሉ መስተፋቅር =  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ = ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) = ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ =  ለድምፅ =  ለብልት እንደመቆም =  ለኤች አይቪ መድሀኒት
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት

ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል

ለጥያቄወ 📞☎️09 4........5 ይደውሉልን በአካል መቅረብ ለማትችሉ በሙሉ ወደ አሉበት ቦታ ድረስ ይደርሶዎታል

ይላል በTelegram በfacebook በጣም ብዙ አሉ ይሄን የላኩላችሁ ሲህር ድግምት ለእናንተ መጥፎ የሚስቡ መጥፎ ሰዎች እነዚህ ቦታ ቢሄዱ አስባችሁታል?? እነዚህ ቦታ ሂደዉ መስተፋቅር ወይ ገበያ እንድንከሰር ወይ ሌላ ነገር ቢያሰሩበን በእኛ ኢማን ድክመት በጣም ከባድ ነዉ ፡፡ እናም ብዙ ሰዉ የለም የሚል ካለ ራስን ማሞኘት ነዉ ደጋሚዎች ደብተራዎች በየሀገሩ በየመንደሩ አሉ፡፡


📌📌ማወቅ ያለብን የደብተራ ብቻ አይደለም ..በጣም በዙ ሙስሊም ተብለዉ በየገጠሩ የሚሰሩ አሉ ዱአ ላስደርግ ምናምን ጫት የሚቃምበት በጣም የሚበዛ ከሆነ ..ወይም በጫት እናስለቅቃለን ካሉ ዛር አለባቸዉ በጫት የሚያስለቅቀዉ ለትልቅ ጅን ይገብራል ማለት ነዉ እንወቅ እባካችሁሁሁሁ  ....

ወልዮች ሸሆች ጋር እያልን ጫት የሚቅሙ ጋር እየሄድን ባንዘናጋ ኸይር ነዉ፡፡በነገራችን ላይ እንደዚህ እያለ የሚሄድን ወጣትም ሆነ ትልቅ ሰዉ ሰዉየዉን ባንቀርብ ወይ ሰዉየዉን ከቀረቡ እራቅ ብሎ በዉዲዕ ቢሆን አሪፍ ነዉ፡፡

የሚገርመዉ ነገር አንድ የገጠር ሰዉ የማምነዉ ለጅን ማረድ ከተወ ቡሀላ ሲያወራኝ ለጅን የሚያርድልን ሰዉ የመስጊድ ኢማማችን ነዉ ብሎኛል ...

አሏሁ የስቱርና


--------- ------ ------ ------ -----
   📚📚ግን አንዳንድ ፍቅሮች እንዴት ነዉ ???🙄

አሁን ላይ ግራ የገባኝ ነገር አለ ፍቅር እንዴት ነዉ???
ፍቅር አለ ወይስ የለም ማለት ለማለት እየከበደ ነዉ ..ፍቅር አንዳንዴ የሲህር በሽታም ሊሆንም ይችላል ብቻ እኔ አሁን ግራ እየገባኝ ያለ ፍቅርን እንዴት መገለፅ ይቻላል መልስ የሌለዉ ጥያቄ...

ግን እስኪ ከዚህ በታች አይነት ታሪክ የደረሰባችሁ ካለ በአስተያየት መስጫ ላይ አስቀምጡልኝ...ግን በፊት እወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ ወይም እወዳታለሁ አፈቅራታለሁ ብለዉ በፍቅር ሲያለቅሱ ሲሰቃዩ የነበሩ..እንደ አጋጣሚ ወይም በሌላ ምክንያትም ቢሆን ታመዉ ሩቃ ሲገባ እወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ ያሉትን ሰዎች 80% እሱ ጋር ቢኖሩም ባይኖሩም ምንም አይመስላቸዉም...ከሩቃ ቡሀላ አፍቃሪዉ ሲህር ወይ ጂን ከነበረበት ከለቀቀ አፍቅረዋለሁ የሚለዉ ሰዉ ረጋ ማለት እና መረጋጋት ይታይበታል፡፡👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ

          
           ⭐️
#ክፍል👉አስራ ሶስት 1⃣3⃣



🟢 ጊዜዉ ከባድ ነዉ ልንገራችሁ እስኪ ብዙ መንገር ይቻላል
ግን ለመስማት የሚዘገንን ነዉ ግን ይሄ ከሌላዉ አንፃር ይሻላል ብየ ነዉ፡፡


  አንዲት እህታችን 7 ልጅ አላት..ባሏ የከባድ መኪና ሹፌር ነዉ እናም ብዙ ቀን እቤት አያድርም፡፡ እቤት ስለማያድር ሚስቲቱን ሌላ ወንድ ጋር እኔ ሳልኖር ብትሄድ ወይ ብትተኛብኝስ??ብሎ ይጠረጥራታል ፡፡
ጊዜ የማያመጣዉ የለም የመጨረሻዉ ልጅ ይታመምና እኛ ሰፈር ያለ ሩቃ የሚያደርግ አንድ ብር የማይቀበል ለአላህ ብሎ የሚሰራ ነበር እሱ ጋር መጣች ልጁን በተወሰነ ደቂቃ በአላህ ፍቃድ በአፉ ብዙ ነገር ወጥቶ ሻረ....እናቲቱም እስኪ እኔም ለሊት ጭንቅ ጭንቅ ይለኛል ስትለዉ በቁርአን ገና ጀመር ሲያደርግ...ለማመን ይከብዳል እርይ ማለት ጀመረች...ጂኑ ተነቃብኝ ተጋለጥኩ ተጋለጥኩ ማለት ጀመረ...
ከዛ ልጁ ጂኑን መጠየቅ ጀመረ...ጂኑ ሲናገር...
ባሏ እሷን አያምናትም ሹፌር ስለሆነ ሌላ ጋር ብትማግጥስ ብሎ ስለሚያስብ ሶስት አይነት ሲህር(ድግምት) ጎጃም ሂዶ 10,000 ብር ከፍሎ አሰራ እሱ እያሰራ ለእሷ ግን የአስቤዛ የለኝም ይላታል፡፡ የተሰራዉ የተላክነዉ 3 ጂኖች ነን የተሰጠን ስራ
➊ ቤተሰብ ጋር እንዳትስማማ ልጆቿ እንዳይወዷት አንቺ ነገረኛ ነሽ አባታችን ነዉ ለኛ የሚያስብልን ብለዉ እሷን
እንዲጠሏት...የእሷም የእሱም ዘመዶች ነገረኛ ከፉ ነች ተብላ እንድትጠላ
➋ ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች ቀኝ አይኗን እንድናጠፋ
➌ ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች በአደባባይ እንድትጋለጥ በዛ እፍረት እብድ እንድትሆን ነዉ ያስደገመባት ...

ድግምቱን ይዘን መጥተናል የመጀመሪያ ከልጆቿ ከቤተሰቦች እንዳትስማማ አሳክተናል፡፡ ግን ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች ቀኝ አይኗን አጥፍተን እብድ ለማድረግ በሰከንድ ከእኛ እይታ ተደብቃ አታቅም በየሰከንዱ እንሰልላታለን እሷ ግን የዋህ ታማኝ ነች እንኳን ከሌላ ወንድ ጋር ልትተኛ ..ልጆቿ እሷን ባይወዷትም  በሰገደች ቁጥር ለልጆቿ ለባሏ  ዱአ ታደርግላቸዋለች...
ከዛ ትለቃላችሁ ሲባል አዎ እንለቃለን ግን እሱ መጥፎ ሰዉ ነዉ ይቺ ምንም የማታቅ ሚስኪን 7ልጅ ለማሳደግ እየተጨነቀች እሷን በዚና ጠርጥሮ እንደዚህ አድርጓታል አንለቀዉም ብለዉ ከእሷ ሰዉነት ጅኖቹ ወጡ

እናም ጊዜዉ ከብዷል ጎበዝ
ወላሂ እኔ ብዙ የማቀዉ ብነግራችሁ ጓደኞ ዘመድ ቤተሰብ ጋር ያለን ግንኙነት ትንሽ እንዳይሻክር በመፍራት ብዙዉን ከመፃፍ ተቆጥቢያለሁ
☞ እህት በእህት/እህት በወንድም/ወንድም በእህት
☞ሁለተኛ ወይ የመጀመሪያ ሚስት በባሏ
እስኪ አስተዉሉ ሸሪአዉ ፈቅዶ አቅም ኑሮት ሁለተኛ ሲያገባ በጣም ከባድ ፀብ ጭቅጭቅ በአንዷ ቤት ይኖራል ..ከአንዷ ጋር በጣም ፍቅር ከአንዷ ጋር ፀብ ምናምን በቃ ያገባዉ የተለያዩ ባህሪ ፀባይ እስከ ፍች ወይም ለሁለቱም ሚስቶቹ ሳይሆን የሚቀር ከሆነ እንጃ ወንዶች መጠርጠሩ አይጎዳም
☞ የዘመድ የጎረቤት ያለ ጉድ ከባድ ነዉ...ብቻ የሚሻለዉ #ከሰዉ_ጋር_ያለንን_ግንኙነት_በዉዱዕ_መሆን_ነዉ_ያለብን

🟢 በደንብ አዉቀን ልናሳዉቅ ለሌች ትምህርት ልንሰጥ የሚገባዉ አንዳንዴ በዲን እዉቀት ጠለቅ ብለን የማናቅ ሙስሊሞች ላይ ሸክ ጥርጣሬ የሚገባን ጉዳይ አለ እሱም ...ጂንን ሲህር ድግምትን
🔶 ክርስቲያኖቹ በፀበል እያስለቀቁት አይደል እንዴ
🔶ጴንጤዎች አሜን እያሉ እያተበተቡ ያስለቅቁ የለ እንዴ
🔶 አንዳንድ ሸሆች እየቃሙ ያስለቅቁ የለ እንዴ
🔶 ጠንቋዮችም ሲያስለቅቁ እያየን አይደል እንዴ

አንዳንዶቹ ሲሞግቱ ከባድ ጂን ወይም ብዙ ሲህር አይነጥላ ከሆነ ቀናቶች ይፈጃሉ በቁርአን ይሄን ያህል ቀን ይፈጃል በፀበል ጠንቋይ ቤት ግን በአንድ ቀን ይለቃል ታዳ ከቁርአን ዉጭ ፀበልም የጴንጤዎች ቦታ የታመዉ መሻሉ እንጂ ለምን አንወስድም?? እያሉ እየወሰዱም ነዉ...ግን ክርስቲያኖችም ጴንጤዎች  እንዴት ማስለቀቅ ቻሉ??የብዙ ሰዉ ጥያቄ ነዉ

🌀 #ለምሳሌ በቫቲካኖች (ካቶሊኮች)  ህክምና እነርሱ ዘንድ ሊታከም የመጣ ሰው በኮከብ ውስጥ አስረው እና ጥላሸት ቀብተው እነሱ ትልልቅ ጂኖችን እያዘዙ ሰዉየዉን የያዘዉን ትንሽ  ጂን ከቦታው ያስወጣሉ። አዎ ይህ ህክምና ይሰራል ምክንያቱም ለደካማ ጅን ሁሌም ቢሆን ጠንካራ ጅን አለ ። ይሁንና ይህ ታካሚ ኢፍሪት የያዘው ወቅት ላለመውጣት ታካሚውን ሙሉ ለሙሉ ገድሎና ሰውነቱን ቀጭቶ ይወጣል። ከ 100% 25%ድንገተኛ ሟቾች ናቸው።

ይህ አይነቱ ህክምናም በተለያዩ እምነቶች ያለ ሲሆን ህክምናቸውም ሲህርን በሲህር በጅን እያደረጉ አስማት ነው በማለት ሰዎችን ይሸነግላሉ ።

አስማትን በአስማት ማከም መታከም ለድንገተኛ ሞት ይጋልጣል።ለምን የሚያዟቸዉ ትልቅ ጅንን ነዉ ሰዉየዉ የያዘዉ ከሚታዘዘዉ ጅን በላይ አቅም ካለዉ ከባድ ነዉ ሰዉየዉን በሂደት እስከመግደል ይደርሳል፡፡

ለምሳሌ እስኪ እሰቡት እስኪ በወንዶች በፊት ስናድግ በሰፈራችን የሰፈር አለቃ አለ እንበል....እሱ የፈለገ ቦታ ይልከናል እምቢ ብንል ይመታናል ያለን አማራጭ መታዘዝ ነዉ፡፡ ወይም መንግስት ግዴታ ይሄን አድርግ ካለን ምን አማራጭ አለን??? ምንም ግዴታ ከማረግ ዉጭ..,,እናም ትልቅ ተፅእኖ ፈጣሪ ተፈሪ የሆኑ ጅንኖች ትናንሽ ደካማን ፈሪን ከሰዉየዉ ገላ  የማስወጣት አቅም አላቸዉ

በጠንቋዮች (በደብተራዎች) በቄሶች የሚፈታ ድግምት ለጊዜዉ የተፋታ ይምሰል እንጂ ሙሉ በሙሉ አይድንም፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ዳግም ያንሰራራል፡፡ ምክንያቱም ሰይጣናት በጎሳ የተከፋፈሉ ናቸዉ፡፡

☑️ ድግምቱን የሰራዉን ደብተራ የሚያገለግሉት ሰያጣናት ድግምቱን የሚፈታዉን ደብተራ ከሚያገለግሉት ሰይጣናት በጎሳ የተለዩ ስለሚሆኑ የአንዱ ጎሳ ሰይጣን የሰራዉን መተት የሌላ ጎሳ ሰይጣን መፍታት ወይም በመተት የተወከለዉን ጂኒ ማስወጣት አይችልም፡፡ ምክንያቱም ይህን ማድረግ በጎሳዎች መካከል ጦርነት ይቀሰቅሳል።
ጂኒዎች እንደኛዉ ናቸዉ እነሱ የሚያዩን እኛ የማናያቸዉ ስለሆን ነዉ እንጂ

#ስለሆነም ብዙ ጊዜ ጠንቋይ የሚያገለግሉ ሰይጣናት የሚያደርጉት ነገር ቢኖር በታማሚዉ ዉስጥ ከገባዉ ስይጣን ጋር መስማማት ነዉ፡፡ ይህም ስምምነት ሰይጣኑ ታማሚዉን ለጥቂት ወራት ወይም ሳምንታት ላያንገላታዉ እና ታማሚዉ ደግሞ ሰይጣኑ የሚፈልገዉን ሊያሟላ ይስማማሉ፡፡

ለምሳሌ፡-ጥቁር ዶሮ እንዲታረድለት ፈልጎ ከሆነ ታማሚዉ ይህንኑ ያቀርባል ወይም ለምስሎች እንዲሰግድ ያታዘዛል፡፡ በዚህም ታማሚዉ ለተወሰነ ጊዜያት ወራትም አመታትም ሊሆን ይችላል ጠንቋዩ ጋር ጅኑ እንደስምምነታቸዉ ነዉ ተሸሎት ይከርምና ያ የተስማሙበት የጊዜ ገደብ ሲያበቃ ህመሙ ዳግም ይቀሰቀሳል፡፡ ከዚያም ሌላ ስምምነት ማካሄድ አለባቸዉ መቼም አይለቅም  ... ሙሉ ፈዉስ ማግኘት የሚቻለዉ በዓለማት ፈጣሪ በአላህ ቃል በቁርአን ብቻ ነዉ፡፡

🌀 በፀበል ደግሞ ላላችሁት በሚዲያ ላይ ማዉጣት ይከብዳል የሆነ የሚሰማ የማቀዉ ስላለ ነዉ፡፡ወሎ ሲባል ቅልቅል ነን እኔም ብዙ ቤተሰቦቼ ክርስቲያን ናቸዉ👇👇
ከእነሱ አንዳንድ የምሰማዉም አለ....እስኪ በመጀመሪያ የራሳችንን እንወቅ ሙስሊም መስለዉ የሚሸዉዱት  ጥንቃቄ እናድርግ የሌላዉ ይደርሳል...ብቻ በፀበል
ይለቀናል ባላችሁ ሂዳችሁ የብስ ህመም ጨምራችሁ እንዳትመጡ ....
🌀 እነሸህ ተብየ ጫት ቅመዉ ወይ በዛር የሚያስለቅቁ ይሄ በቀላል ቋንቋ 90% እርግጠኛ ሁኑ ለጅን ይገብራሉ ትልቁ ጉልበተኛዉ ጂን ለትንሹ ቀላል ነዉ ...ሲያጎራ ሲጮሁ ሰምታችሁ ከሆነ በጣም ለአቅል ይከብዳል ሲለፈልፉ በእነሱ አድርጎ ይወጣል፡፡
አንዳንዴ ዛር ያለበት እያጨበጨበ እየጨፈረ ሲያስለቅቅ ያየሁት አሉ ጅኑ አጨብጭብ ጨፍር ብሎት ወላሂ በአይኔ ያየሁት ነዉ፡፡ ግን ይሄ ለጅን ግብር ነዉ ተመልሶ ይመጣል ወይ ሌላ የቤተሰብ አባል ወይም ልጅን ይይዛል፡፡
የሀሉም መፍትሄ ቁርአን ብቻ


 🟢  አይንናስ(ቡዳ) ..ሲህር..ጂን ብዙዎቻችን ላይ ያለ ይመስለኛል ለምን ብዙሀን ሙስሊሞች ከዲናችን  የተዘናጋን ስለሆነ ራሳችንን ቆም ብለን ብናይ  ጥሩ ነው.....ብዙዎቻችን
✏️ የጠዋት ማታ ዚክር ማድረግ አቁመናል
✏️ ቁርአን ስልክ ከመጣ ቡሀላ የምንቀራ በጣት የምንቆጠር ነን ሁሉም በስልኩ ቁርአን አዝካር አለ ያንን ለመቅራት ነይቶ ስልኩን ሲነካካ ወደ ማህበራዊ ሚዲያላይ ነዉ የሚወስደን፡፡ ግን አስተዉለናል?? በፊት ስልክ ሳይመጣ እኮ ለቁርአን ያለን ፍቅር ዚክር ለማድረግ ያለንን ጉጉት የተለየ ነበር ግን አሁን ማን ነዉ ቁርአንን አክብሮ ገልጦ የሚቀራዉ??የሚሻለዉ በስልክ ቁርአን መቅራት ብናቆም የተሻለ ነዉ እናም
የኛ ከቁርአን መዘናጋት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ማሳለፍ ከዲን የመዘናጋት ስለሆነ ራሳችንን ማኔጅ ብናደርግ ጥሩ ነዉ
✏️ በማህበራዊ ሚዲያ በTG..Whatsap..facebok..instgram ወዘተ የምናደርገዉ profile pictur ፎቶ ለአይን ናስ(ቡዳ) መበላት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
ለምን ጀሊሉ ሲፈጥር ማስጠሌ ብሎ የፈጠረዉ የለም ግን የሰዉ አይን የፈለገዉን ቆንጆ የፈለገዉን ማስጠሌ አድርጎ ይስላል፡፡ profile ስታደርጉ እራሱን ወይ እራሷን እንደ ማስጠሌ የምታይ ዉይ ሲያምር ወይም ዉይ ስታምር ሊሉ ይችላሉ እናም profile ከማድረግ እንጠንቀቅ

✏️ በtiktok ላይ video የምፓስቱም የሰዉ አይን ሰለባ ስለምትሆኑ መጠንቀቁ አይጎዳም...እስኪ እኔ ብዙም ግንዛቤዉ የለኝም በtiktok የሚታወቁ ሰዎች ትዳር አላቸዉ የላቸዉም? ካላገቡ መቼም የሚታዩት ቆንጆ ናቸዉ እንዴት አላገቡም?
መጀመሪያ በሚዲያን የቀረበ ራሱን ጨረታ ያወጣ በሀራጅ ተከስሮ ነዉ የሚሸጠዉ ጨረታ እቃ ያሸነፈ ነዉ በሀራጅ ይገዛል ኦዲት ሲደረግ ይወድቃል
በመቀጠል ግን የሰዉ አይንም(ቡዳ) ችግር ሊሆን ይችላል
✏️ ያለቅጥ የተካበደ ሰርግ ብራይድ ማድረግ በሰዉ አይን የመበላት አቅሙ ሰፊ ነዉ ለምን በዚህ በኑሮ ዉድነት ባለበት ዘመን የሚበላ የሚጠጣ ቤት ኪራይ መክፈል በአቃቃተበት ዘመን ያለቅጥ ደስታ በደሀ እምባ መቀለድ ነዉ የእናንተን ሰርግ ደሀ ሲያየዉ ወይ የበላችሁበት ወይ የጠጣችሁበት ምግብ ላይ ወይ የለበሳችሁት ልብስ ላይ አይኑ ያርፋል እናም የተቸገረ ሰዉ ቀልብ አይን ከባድ ነዉ ፡፡
በተጨማሪ በዚህ ወንዱ ብር ማስተዳደሪያ ሴት ደግሞ ባል ባጣችበት ዘመን በሚዲያ ሰርጋችሁ ተካብዶ ሲያዩት ወንዱም ወይኔ ትንሽ ኑሮኝ በነበር ሴቷም እድለኛ  ነች የሚያምር ባል አግብታለች ባይባል ጥሩ ነዉ የሰዉ አይን ከባድ ነው፡፡

የተወራለት በሚዲያ የታዩ ሰርጎች ብዙዎች ፍች ተፈጥሮ ደብቁኝ ደብቁኝ እያሉ ነዉ እናም ሁሉም በልክ ይሁን

✏️ ልጅ ሲወልዱ በደስታ prpfile pictur ማድረግ ይሄ ደግሞ በጣም ከባድ ነዉ ልጅ ያጣ ያላገባ ባለበት ዘመን ማሻ አላህ ሳይሆን አይኑ አፍንጫዉ መልኩ እናቱን ወይስ አባቱን በሚባልበት ዘመን profile ባይደረግ ባይ ነኝ፡፡

✏️ ከሰዎች የተለየ ልብሶችን መልበስ እና ቀን በቀን መቀያየር ይሄም ልብስ ያጡ አይኖች ላይ ትኩረት መግባት ነዉ ፡፡ ዱንያ ነዉ መብላት መጠጣት መልበስ ነዉ ማለት ቡሀላ ምነዉ ባልበላሁ ባልጠጣሁ ባለበስኩ ከማለት ሁሉን በልክ ማድረግ እና በዚክር በቁርአን መንቀሳቀስ ነዉ

⚡️⚡️⚡️   በሰዉ ህይወት ቀንታችሁ በማወቅም ባለማወቅም ያሰራችሁ ካላችሁ ጉዳቱ ለተደረገበትም ለእናንተም ጭምር መሆኑን አትዘንጉ የተዉበት ጊዜዉ ገና ነዉ ወደአላህ እንመለስ ...እኛ የምናምፀዉ በወንጀል ድንበር የምናልፍበት ጌታችን ቅርብ ሁኖ እያየን እንደሆነ አንዘንጋ....
ጌታችን አሏህ ሱወ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይለናል
“ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው) እኔ ቅርብ ነኝ፣ የለማኝን ፀሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፣ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፣ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ለምመሩ፡፡ ይከጀላልና፡፡” (አል-በቀራህ፡ 186)

ታዳ ለምን እኛ የሰዉንም የራሳችንን ህይወት ለማበላሸት ደጋሚዎች ደብተራዎች ጠንቋይ ቤቶች እንሄዳለን??
የምንመቀዉን ሰዉ የሰጠዉ አላህ ለምን ለእኛስ ስጠን ብለን ወደ ጠንቋይ ከመሄድ ወደ ጀሊሉ እጃችንን አንዘረጋም??

በሐዲሥ አልቁድሲይ እንደተዘገበው አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- የሰው ልጅና አጋንት በሚገርም ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት፡፡ እፈጥራለሁ  የሚመለከው ሌላ ነው፡፡ ሲሳይ እሰጣቸዋለሁ የሚመሰገነው ሌላ ነው:: መልካም ነገር ሁሉ ከኔ ወደ ባሮቼ ይወርዳል፤ የነሱ መጥፎ ነገር ወደኔ ይወጣል፡፡ ከነርሱ የተብቃቃሁ ሆኜ ሳለ በእዝነቴ ወደነርሱ እወደዳለሁ፡፡ እነርሱ ግን ከኔ ፈላጊ ድሆች ሆነው ሳሉ ወንጀል በመሥራት በኔ ለመጠላት ይሠራሉ፡፡ ለኔ ቅርብ የሆኑት እኔን የሚያወሱት ናቸው፡፡ እኔ   የምወዳቸው እኔን የሚታዘቡት ናቸው፡፡ ወንጀል የሚሠሩትን ከእዝነቱ ተስፋ እንዲቆርጡ አላደርጋቸውም፡፡ በተዉባ ወደኔ የሚመለሱትን እኔ ወዳጃቸው ነኝ፡፡ ቢያምፁም አካሚያቸው እኔ ነኝ፡፡ በችግርና መከራ የምፈትናቸው ከነውር ላፀዳቸው ነው፡፡ ተውባ አድርጎ ወደኔ የሚመለስን ሰው ገና ሩቅ እያለ እቀበለዋለሁ፡፡ ከኔ ዞር ብሎ የሄደውን በቅርብ ሆኜ እጠራዋለሁ፡፡ ከኔ ውጭ ሌላ አምላክ አለህ እንዴ ወዴት ነው የምትሄደው?› እለዋለሁ፡፡
በተጨማሪ

አላህ ለነብዩ ዳወድ እንዲህ አለ፡- ዳውድ ሆይ! ለኔ ጀርባቸውን የሰጡ ሰዎች (ወደኔ በመመለሳቸውና ተፀፅተው በመምጣታቸው) ለነርሱ ያለኝን ጉጉት ቢያውቁ ኖሮ ለኔ ከሚኖራቸው ጉጉት የተነሳ በቀለጡ ነበር፡፡ ዳውድ ሆይ! ይህ ለኔ ጀርባቸውን ለሰጡ ሰዎች ያለኝ ፍላጎት ነው፡፡ ፊታቸውን ወደኔ ላዞሩ ሰዎች እንዴት የሚሆን ይመስልሀል?
አላህ እንዲህ እያለ ይወቅሰናል
ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳፅና ከቁርአንም ለወረደዉ ልቦቻቸዉ ሊፈሩ ጊዜዉ አልቀረበምን??
አላህ እየወደደን ወደኔ ቅረቡ እያለ ይለምናል እኮ
እናም ያለፈዉ ስህተት ከነበርን ቶብተን ወደ አላህ እንመለስ ያስደረግንም ካለን በሰዉ ህይወት አንጫወት ላንጠቀም ነገር ሲህሩ ድግምቱ እንዲፈታ እንዲቆም ማድረግ አለብን፡፡
ህሊና ላለዉ ሰዉ  ሲህር አስደርጎ የተደረገበት ሰዉ ሲሰቃይ ሲቸገር ሲታመም እንዴት አቅላችን ይሸከመዋል??
እንዴት ሰዉ እንዳያገባ ተደርገ የእሱ ወይ እሷ አግብቶ መዉለድ እንዴት እኛን ሊያናድደን ይችላል??ብቻ አሁንም የተዉበት በሩ ክፍት ነዉ ወደ አላህ እንመለስ


#ክፍል 1⃣4⃣
ይቀጥላል.....


አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
 
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
አሚር ሰይድ

                 ⭐️ #ክፍል👉አስራ አራት 1⃣4⃣




🟢 የሲህር(ድግምት) የቡዳ(አይንናስ ጂን ህክምናዎች


ነብዩ ሰዐወ በሀዲሳቸዉ አላህ እኔን በጠረጠራችሁኝ በኩል ታገኙኛላችሁ ብሏል እናም ሲህር አለብን ብለን ባንጠራጠር ራሳችን ባናሳምን ጥሩ ነዉ ምልክቱ እስካልታየብን ድረስ
...በተጨማሪ በዉዱዕ የምንቀሳበቀስ ..የጠዋት ማታ ዚክር የምናደርግ...
>> አላህ የከከለልንን የምንከለከል ከሆነ 
>> ዚናን ሙዚቃን ዉሸትን ስርቆት የየቲም ሀቅ የሰዉ ሀቅ የሚዲያ አጠቃቀማችን ለሀላል ነገር ብቻ ከሆነ ..
>> ከትልቅም ከትንሽም ወንጀል የራቅን ከሆን በአላህ ፍቃድ ወደኛ ማንም መጥፎ ሰዉ ቢያስብ አይነካንም
ከነካንም በዲናችን ጠንካራ ከሆን ዚክር ቁርአን የምናበዛ ከሆነ እንደተያዝን ሳናቀዉ በራሱ ጊዜ ይለቀናል፡፡

🔻🔻 ግን ከላይ የጠቀስኳቸዉ በትልቅ ወይ በችንሽ ወንጀል በከፊልም በሙሉም የተዘፈቅን ከሆነ በተጨማሪ እስኪ ወደ ሆላ 3 ወይ 4አመታት አስታዉሱ የነበራችሁን ጥንካሬ
☞ አሁን ግን የኢማን መንሸራተት ካለባችሁ..
☞ ትዳር ሲመጣ ጭንቅጭ ጭንቅ የሚላችሁ
☞ከማግባት ይልቅ ለማበላሸት የሚቀናችሁ..ከዛ ካበላሻችሁ ቡሀላ የሚቆጫችሁ ከሆነ
☞ አጭቴችሁ ምነዉ አጭቼ ባልነበር ከአጨሁት ይሄኛዉ ይሻለኝ ነበር ወይም ያችኛዋ ትሻለኝ ነበር እያለ ሸይጧን ለማበላሸት የሚወሰዉሳችሁ ከሆነ
☞ ቁርአን ሂፍዝ እስከ መጥፋት..
☞ ቁርአን ስቀሩ ስታዳምጩ የሚጨንቃችሁ የሚያልባችሁ ካለ ሩቃ ቢደረግባችሁ ጥሩ ነዉ፡፡


🌐🌐 ሩቃ ሁለት ጥቅም አለዉ
#የመጀመሪያዉ በኛ ላይ ሲህር ወይ ድግምት ወይ አይነጥላ ጅን ካለ ይለቃል
#ሁለተኛ ጥቅሙ እኛ ሁሉም ከሌለብን ቀልባችን ይጀደዳል በቁርአን ጥንካሬ ያገኛል፡፡

  በራስ ሩቃ ማድረግ በጣም በላጩ ነዉ
ሩቃ ሲባል ከባድ አድርገን አንያዘዉ ..ሩቃ በቀላል ቋንቋ ከአላህ ጋር ያለን ግንኙነትን ማስተካከል በዚክር በቁርአን ልብን ማርጠብ ማለት ነዉ
✏️ የጠዋት የማታ ዚክሮችን ማለት
✏️ ሲተኙ ሱረቱል ናስ ፈለቅ አሀድን ሶስት ሶስቴ መቅራት አያተል ኩርሲን መቅራት እነዚህን ስንቀራ ዉሀ በሀይላንድ ይዘን ዉሀዉ ላይ መቅራት ከዛ የሩቃ ዉሀ ሆነ ማለት ነዉ...የሩቃ ዉሀ መጠጣት ከተቻለም የወይራ ዘይት ጥቁር አዝሙድ ዘይት ዉሀዉ ላይ ጠብ ጠብ አድርጎ መጨመር ነዉ
✏️ ቁርአንን በቻልነዉ አጋጣሚ በቁርአን መቅራት..
ዚክሮችን በስራ ቦታ በትምህርት ቤት ታክሲ ላይ ሲንቀሳቀሱ ዚክሮችን ማድረግ አላህን ማስታወስ ነዉ...
🔶 #ነብዩላህ_የኑስ ዐ.ሰ ብዙ መልካም ስራ አልነበራቸዉም ጥፋት ባጠፉ ጊዜ አላህ ሱ.ወ በዓሳ ሆድ ዉስጥ ጣላቸዉ ከዚያ ያወጣቸዉ ያደረጉት ተስቢህ የአላህ ዉዳሴ ነዉ፡፡
አላህ ሱወ እንዲህ ይላል
እርሱ ለጌታዉ ከአወዳሾች ባልሆነ ኑሮ እስከሚቀሰቀስበት ቀን ድረስ በሆዱ ዉስጥ በቆየ ነበር
(አል ሷፋት 143-144)

እናም አላህን ማዉሳት መቶበት ለሁሉም መፍትሄ ነዉ
✏️ በቁርአን ዉስጥ በደረጃ ትልቅ አንቀፅ አያተል ኩርሲይ ነዉ በአንድ አንቀፅ ዉስጥ ስድስት ያህል መልካም የአላህ ስሞች እናገኛለን...አያተል ኩርሲን ባገኝንበት አጋጣሚ መቅራት


✏️ ወንጀል ላይ ካለን ዚና የምንሰራ ሙዚቃ የምናዳምጥ ትንሽም ትልቅም ወንጀል ላይ ካለን ከዛ መታቀብ
✏️ የማይጠቅሙ የማይጎዱ ጓደኞችን መቀነስ
✏️ በtv በስፒከር ቁርአን መክፈት ጆሯችን ጎን አድርገን የተለያዩ የሩቃ አንቀፆችን ቁርአኖችን መቅራት ነዉ...በአላህ ፍቃድ ጂኑ ሳይናገር ሳይለፈልፍ በራሱ ጊዜ እየተወገደ ይሄዳል፡፡
ከበፊቱ ለዉጥ ካለን እንቅልፍ እምቢ የሚለን ከሆነ እንቅልፍ መዉሰድ ከጀመረን መጥፎ ህልሞች እያየን በፊት ከነበረ ከዛ ቡሀላ መጥፎ ህልሞች ከራቁልን ..ሙዚቃ ካስጠላን ከዚና ቱብት ካደረግን ወይም ከዉሸት ከመጥፎ ጓደኛ ከራቅን በራሳችን ሩቃ ተሳክቶልናል ማለት ነዉ ...በዚሁ ኢማንን እያጠነከሩ መሄድ ነዉ

🟢 ጂን መቷቾሁ ከሆነ ወይም በምቀኛ ሰዉ ሲህር ድግምት ተደርጎባችሁ ከሆነ እኔ ራሴን በራሴ ሩቃ ማድረግ አይሆንልኝም ብላችሁ ካሰባችሁ...ሩቃ የሚያደርግላችሁ ፈልጋችሁ በቁርአን ሀይል የዛን ጊዜ መናገር ይጀምራል በአላህ ፍቃድ ይለቃል፡፡

📚📚 ከሁሉም ግራ የሚገባዉ ነገር ማን ጋር ሩቃ እንጀምር የሚለዉ የብዙ ሰዉ ጥያቄ ነዉ ለምን ቢባል አንደንድ ሩቃ እናደርጋለን የሚል በሩቃ ስም ሀራም የሚሰሩ ሴቶች ጋር የሚተሻሹ በተጨማሪም ሳይታመሙ ታመምን የሚሉ አሉ እዛ ሂደዉ መተሻሸት የሚፈልጉም ሴቶች እንዳሉ ልናወቅ ይገባል ..እናም ትክክለኞቹ ማን ናቸዉ??ግራ የሚያጋባ ነዉ

♻️♻️  ግን እኔ የምለዉ ቆይ እስኪ እቤት እናት አባት እህት ወንድም ሲታመም ምን የሚያስፈራ አለ?? የአላህ ቃል በስፒከር ከፍቶ በተከታታይ ቀናቶች መቅራት ነዉ ብዙዉ በአንድ ቀን ይለቃል እናም እኔም አንተም አንቺም እሱም እሷም ማላቀቅ እንችላለን መጀመሪያ በአላህ መተማመን አንተን ይዤ በአንተዉ ቃል ቁርአን አድነዋለሁ ብሎ ነይቶ መነሳት ነዉ እናም ሩቃ ቤት ከመዉሰድ መጀመሪያ በራስ መታገል ይበልጣል፡፡

የተለያዩ የሩቃ እወቀቶች መቅሰምና መፅሀፎችን ማንበብ ለቤተሰብህ ለጓደኛህ መሆን ይቻላል

ሴት የዲን እህትሽ ስትታም ለምን ለአጂ ነቢይ ወንድ አሳልፈሽ ትሰጫለሽ?? ሀስቢየሏሁ ወኒዕመል ወኪል ብለሽ አንቺዉ ቁርአን ቂሪባት

እህትህ ስትታመም ለምን ወንድ ሩቃ የሚያደርግ ትፈልጋለህ??
ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ብለህ ጀምረዉ  ...ሀስቡነሏህ ብለህ ከጀመርክ ከጀመርሽ ሰበብ አድርስ አላህ ያግዘሀል ያግዝሻል ግን ያለስበብ ወደፊት ያለርምጃ የሚሆን አይደለም ሰበብ ግዴታ ነዉ

ሀስቡነላህ ወኒዕመል-ወኪል”
ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ወደ እሳት በተወረወሩ ጊዜ የተናገሯት ቃል ነች፡፡
ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ፊርአውንን በመሸሽ ላይ እያሉ በሱ ያመኑ ሰዎች “እነ ፊርዐውን ደረሱብን!” ባሏቸው ጊዜ ይህችኑ ቃል ተናግረዋል፡፡
የአላህ መልእክተኛም (ሰዐወ ሰዎች "በኡሀድ ጦርነት ሰዎች እናንተን ለማጥቃት ተሰባስበዋልና ፍሯቸው ባሏቸው ጊዜ ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ይህችን ቃል ብለዋል፡፡
እናም ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ብለን ጀምረን ፈጣሪ አያሳፍረንም እርግጠኛ ሁኑ
  እናታችን ሀጀር ብቻዋን በዛ በርሀ  ለኢስማኢል ዉሀ ጠምቶት ሲያለቅስ ቁማ አልተመለከተችም ሰባት ጊዜ ስትዞር ነዉ  ጂብሪል ከሰማይ በመውረድ  በክንፉ እግር ስር በመጫር ዘምዘም ዉሀ እንዲፈልቅ ያደረገዉ
መርየም በዛ በምጥ ተሰቃይታ ባለችበት ጊዜ አላህ የሚበላ የሰጣት እኮ በጅብሪል አማካኝነት የተምሩን ዛፍ አወዛዉዢዉ ሲላት ስታወዛዉዘዉ ነዉ የሚበላ ያገኘችዉ...እናም አላህ የሚያግዘን ከኛ ትንሽ ሰበብ ይፈልጋል ሀስቡነሏህ ብለን መጀመር ነዉ 👇
👇
ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ብለህ ጀምር እርግጠኛ ሁን አላህ አያሳፍርህም ፡፡ ችግሩ የኛ ኢማን ጥንካሬ መድከምና ተስፋ መቁረጥ ነዉ....ንብ አንድ ኪሎ ማር ለመስራት 400 km ትንቀሳቀሳለች ተስፋ አትቁርጥም ታሳካለች ታዳ አንቺ አንተ እናንተ ምን የሚያስፈራ አለ???ምን ተስፋ የሚያስቆርጥ አለ??
ለምን እህትህን ለአጂ ነብይ ወንድ አሳልፈህ ትሰጣለህ??? ለምን እኔ አልችልም ትላለህ/ትያለሽ⁉️

ሀስቡነሏህ ብለህ መጀመር አቅቶህ ነዉ ወይስ አላህ በኔ ተማመን እያለህ በአሏህ መተማመን ፈርተህ ነዉ⁉️
የጀአለሁ መኽረጃ የወሙጫ መንገድ አዘጋጃለሁ ያለህ ጀሊሉን እንዴት መተማመን አቃተህ⁉️
ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል አላህን ይዘህ ሁሉም ነገር ቀላል ነዉ....አላህን ይዘን መፍራት አያስፈልግም


♻️♻️ ብዙ ሩቃ ቤቶች ሩቃን ለቢዚነስ አርገዉታል ከ3,000 እስከ 20,000 ከዛም በላይ እየጠየቁ እኔ መጀመሪያ ላይ ብር ላይ ፎከስ የሚያደርጉ ሰዎች ንያቸዉ ብር እንጂ ከአላህ አጅር እናገኛለን ብለዉ ስለማይሆን እንደነዚህ ሩቃ ቦታዎች እንጃ ብቻ ምን እንደምል አላቅም...በሀዲስ ይበቃል አይበቃም ፊርቃ ስላለዉ የሚሻለዉ ወላሁ አዕለም ግን ብዙም አይዋጡልኝ

የሚሻለዉ በራስ ኮንፊደስ ተወከልቱ አለሏህ ብሎ መጀመር ነዉ አሏህ ቁርአኑን መፍትሄዉን ነግሮናል ነብዩ ሰዐወ አስተምረዉናል እናም በራሳችን መታገሉ ኸይር ነዉ፡፡

ማወቅ ያለብን ጂን በደም ስር በመርፌ ቀዳዳ መሹለክ የሚችል ዉሸታም ሰላቢ የማይጨበጥ ነዉ ፡፡ #ግን_ቁርአን_በሚቀራበት_ጊዜ_መላኢካ_ከታማሚዉ_ሰዉነት_እንዳይወጣ_ጠፍሮ_ይይዘዋል፡፡
ከዛ ቁርአን በሚቀራበት ጊዜ ለእሱ ቁርአኑ ሰይፍ ነዉ የሚሆንበት ይቆራርጠዋል ...ወላሂ ቶሎ ብለዉ ነዉ የሚወጡት ለምን ካልወጣም ሊገለዉ ይችላል ፡፡

🔰🔰ቁርአን ለሰዉ ልጅም ለጂንም ካመንበት መድሀኒት እርጋታ ከፈጣሪ ጋር ያለን ግንኙነት መጨመሪያ ነዉ....ጂኖች ያቃሉ ግን ተገደዉ ወደ ሰዉ ገላ ስለሚገቡ ለመዉጣት የላካቸዉ ሸይጧን ወይም ትልቁ ጂን ወይ የጎሳ አለቃ ጂኑ ቅጣቱ ከባድ ስለሚሆንባቸዉ ላለመዉጣት ይታገላሉ ግን የሚያሸንፈዉ ቁርአን ነዉ ተቃጥለዉ ተንገብግበዉ አይናቸዉ ጠፍቶ እግራቸዉ ተቆርጦ ድረስ ይለቃሉ ሲናገሩ ከሰማችሁ አይኔ ጠፋ እግሬ እጄ ተቆረጠ ይላሉ ቁርአን ሀይል ነዉ ...አልሀምዱሊላህ ጀሊሉ ለሰጠን መድሀኒት ሀይል ብርታት ቁርአን

#ቁርአን 77430 ቃላት እና 430740 ፊደላት አለዉ አሏህ ፈጣሪያችን በቁርአን በአንድ ፊደል 10 ሀሰና አለዉ ብሎናል እናም 430740 ብናሰላዉ
🔶 በወር ሶስቴ ብናከትም 12,922,200 ሀሰና ሲኖረዉ
🔶 በወር ሁለቴ ብናከትም 8,614,800 ሀሰና እናገኛለን
🔶 በወር አንዴ ብናከትም 4,307,400 ሀሰና እናገኛለን

ቁርኣን አጠቃላይ ገፁ 604 ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር በመጠኑ በግማሽ ያንሳል። ነገርግን ላለፉት 1,400 ዓመታት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙፈሲሮች ማብራሪያውን ቢፅፉትም ፈፅሞ ሊጨርሱት አልቻሉም።
ለአብነት
♦️ ቁርጢቢ ➨ 21 ቅፅ 👉 5509 ገፅ
♦️ ኢብን ከሲር ➨ 10 ቅፅ 👉 6608 ገፅ
♦️ ጠበሪይ ➨ 12 ቅፅ 👉 3000 ገፅ
♦️ በገዊ ➨ 4 ቅፅ 👉 1487 ገፅ
♦️ ጀላለይን ➨ 1 ቅፅ 👉 1378 ገፅ
♦️ ሰዕዲ ➨ 10 ቅፅ 👉 6600 ገፅ
♦️ ቁጥብ ➨ 30 ቅፅ 👉 4018 ገፅ

ይህ ሁሉ ተፍሲር ለ604 ገፅ መጽሐፍ የተፃፈ ቢሆንም ሁሉም የሚችሉትን ያህል አብራሩት እንጅ አንዳቸውም አሟልተው ፅፈው አልጨረሱትም።

ከዚህ በተጨማሪ ቁርኣን በታሪክ፣ በህክምና፣ በጂኦግራፊ፣ በጠፈር ምርምርና በተለያዩ ዝርፎች የተጠና ሲሆን የተወሰነውን ቢያረጋግጡትም ገና ብዙ ያልተደረሱባቸው ምርምሮችን ይዟል።

ይህ ለሚያስተነትን ሰው በእርግጥ ተዓምር ነው።
«ይህ ቁርአን አንቀፆቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው። ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ የተወረደ ነው።»
(ሑድ 1)
እናም እኛ እንደ ቀልድ የያዝነዉ የአላህ ቃል ቁርአን ማስተንተን አልቻልንም እንጂ ሀይላችን ቅዋችን ከህመም መሻሪያችን ነዉ እናም ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ብለን እንጀምር

⚠️⚠️⚠️ ማስጠንቀቂያ
በፊት ለጅን የሚገብሩ በግ ፍየል ዶሮ በሬ ላም ወዘተ የሚያርዱ.... የሚገበረዉ ለብዙ ጃሂል ጂን ስለሆነ መጀመሪያ ማስቶበት ወደ አላህ እንዲመለሱ ማድረግ አለብን፡፡  ማድማቱን ማረዱን ሲያቆሙ ሀይለኛ ህመም ጂኑ ይልካል  ሀኪም ቤት ሲሄዱ ጂኑ አዉቆ እንደ ካንሰር ኩላሊት ምናምን ያስብላል

የዛን ጊዜ ካንሰር ኩላሊት ደም ግፊት ምናምን ከተባለ አደራ መድሀኒት አይጀሞሩ የካንሰርም በጨረር የሚሰራ አለ ባይሰሩ ጥሩ ነዉ  ለምን ጅኑ ደም ሲቆምበት እንዲሞቱ ይፈልግና ወደ ልጅ ወይ ልጅ ልጅ ይተላለፋል...የዚህ ጊዜ ጥሩ ሩቃ የሚቀራ ተፈልጎ ማስለቀቅ ነዉ መፍትሄው፡፡ግን ይሄን ጂን ለማስለቀቅ ቢያንስ 2ወር ሊፈጅ ይችላል፡፡ ነጬ በላ/ጥቁር በላ/ራሄሎ/አንበሴ/ወንዘኛዉ/ወዘተ ለጂን በሚያርዱበት ጊዜ ያለማካበድ ከ30 በላይ የሚሆኑ ናቸዉ የሚገበርላቸዉ እናም ማረድ ሲያቆሙ ያሁሉ ነዉ ቂም ይዞ እስከ ሞት የሚደርሽ ህመም ካንሰር ደም ግፊት የሚያስብሉት  ...ግን ለመሻር እንደ ታማሜዉ ቀልብ ይወሰናል፡፡ ትክክለኛ ተዉበት ከሆነ 3ቀን ለራሱ በቂ ነዉ፡፡
ነገር ግን አደራ አደራ!!! ሳይቶብቱ ሩቃ እንዳይጀምሩ ለምን ዋናዉ ቀልብ ነዉ ቀልባቸዉ ማድማት ለጂን ማረድ ከሆነ  ሩቃዉ በጣጣም አድካሚ ነዉ የሚሆነዉ ካልቶበቱ ሰዉነታቸዉን በጣም የሚያስጠላ ሽታ ሊሸቱ ይችላሉ፡፡ እናም ማስቶበቱ ላይ ትኩረት ማድረጉ ነዉ ...
አንዲት ሴትየ ሲታመሙ ካንሰር ተብለዉ ልጆቻቸዉ ቁርአን በተከታታይ ቀን ሲያስቀሩ የዛር ጂኖቹ ይለቃሉ መልሰዉ ከሁለት ከሶስት ቀን ቡሀላ ይመለሳሉ ከዛ ለምን ትመለሳላችሁ⁉️ብሎ ሲጠየቅ
ወላሂ እኛ እንወጣለን መጀመሪያ እሷን አስቶብታት ስንወጣ መልሳ እየጠራችን ተቸገርን ለምን እሷን ሳታስቶብት በቁርአን ታቃጥለናለህብሎ ነበር የመለሰዉ ጂኑ

🟢 አንዷ እናታችን በፊት ለጂን ያርዱ ነበር ሁለት ወር ያህል ታመዉ በአላህ ፍቃድ በሩቃ ጅኖቹ ለቀቁ.,,ሴትየዋ ግን አልሀምዱሊላህ በአላህ ቃል ተሻለኝ አላሉም....እኔን ያመመኝ እኮ ባለማድማቴ ነዉ የሚደማበት ቦታ ልሂድ ብለዉ ሲሄዱ የአሏህ ስራ የሚሄዱበት መኪና ሌላ መኪና ጋር ተጋጭቶ ከተሳፋሪዉ ሌሎቹ ሲተርፉ እሳቸዉ ግን ሞቱ😔😔 ኢናሊላህ ወኢኒ ኢለይሂ ራጂኡን አሟሟታቸዉ አላማረም....አላህ የመቶበቻ ጊዜ ሰጥቷቸዉ አልተጠቀሙበትም

   ትክክለኛ ተዉበት አድርገዉ ማድማቱን ሲያቆሙ ህመሙ ቁስለቱና ጂኑ ደማቸዉን ስለሚመጣቸዉ ደማቸዉ ይወርዳል ደም ግፊት ወይም ደም ብዛት ይባላሉ፡፡  በተጨማሪም የማህፀን ካንሰር ነዉ የመባል ቻንሱ ሰፊ ነዉ..ሰዉነታቸዉ ከበፊቱ በበለጠ መወፈር ወይም መክሳት ...ሆዳቸዉ እጃቸዉ አካባቢ ለብቻዉ ማበጥ ምልክት ያሳያል


⚠️ የምናቃቸዉ ደም የሚያደሙ ለጅን የሚገብሩ እናት አባቶች ካሉን በተጨማሪ አያቶቻችን ካሉ ብዙ የዲነል ኢስላም እዉቀት ስለሌላቸዉ በህይወት ካሉ  ይሄን ጊዜ እንዲቶቡ ማድረጉ ኸይር ጥሩ ነዉ ካልሆነ አሟሟታቸዉ እንደማያምር እወቁ ካንሰር ምናምን ሆነ ተብሎ ነዉ ህይወታቸዉ የሚያልፈዉ፡፡

ህመሙ በሽታዉ በሩቃ ለጅን ከሚገብረዉ አካል ካልተወገደ የዛር ጂን ቂመኛ ነዉ ወደ ልጅ ወይም ወደ ልጅ ልጅ ይተላለፋል ስለሆነም እንደ ቀላል ባናየዉ ጥሩ ነዉ፡፡



#የመጨረሻዉ_ክፍል_ይቀጥላል.....
4any cmt 🔽
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ጁምአ ነዉ የሆነ ችግር ሲበዛ ወይ ነይተን ለሰዉ ነግረን ያልተሳካ ካለ እንደዚህ ልጅ ሁኔታ ለጀሊሉ ነግረዉን ያሳፍረን ይሆን??
እስኪ ለጀሊሉ እንደዚህ ልጅ ሁኔታ አድርገን እንገረዉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ


            
#የመጨረሻዉ_ክፍል



  🔰 #ራስን_በራስ_ማከም_ከዛም_ለሌላ_መትረፍ


🌙🌙
ከpart ➊➍ ቀጥታ የቀጠለ.....
  ከዛር ዉጭ ያለን ሩቃን ለማድረግ ባንፈራ ጥሩ ነዉ ብቻ መጀመሪያ አላህን ይዘን ነይተን ሀስበነሏህ ብለህ መጀመር  ነዉ ፡፡

📚📚 ከተሞክሮ እስኪ ጀባ ልበላችሁ ወላሂ ይሄን የምነግራችሁ ጀሊሉ ያቅብኛል ለጉራ አይደለም ባልፅፈዉ ደስ ይለኛል ግን እንድትደፍሩ እንዳትፈሩ ለመጠቆም ነዉ፡፡ እኔ የዲን እዉቀት የለኝም በማንበብ እና የሰሙትን በመተግበር ላይ አተከለራለሁ ...እና ማንኛዉም ነገር አንድ እርምጃ ያስፈልገዋል የብዙ ሰዉ ችግር ሶስት አራት እርምጃ ይራመዳል ሳያጣራ ከዛ ግብ ሳይመታ ይመለሳል ...እኔ የማምነዉ አንድ እርምጃ ካልሆነ ወደፊት ሳይሄዱ መለስ እርምጃዉ የተሳካ ከሆነ ቀኝን እግርህን ካስቀደሙ ግራህን አስተከትለህ ሁለት እርምጃ ላይ ትቆማለህ ከዛ ነገሮችን እያገናዘቡ መሄድ ነዉ...
#ከተሞክሮ

✍🏼 አንዲት ክርስቲያን ጎረቤታችን  የ7 አመት ልጇ አላት ለሊት አይተኛ ቀን ታዝሎ ይዉላል ስራዉ ማልቀስ ምግብ የሚበላዉ ትንሽ ለዛዉም ያስመልሰዋል እንደ እድሜ እኩየቹ አይጫወትም ብቸኛ ነዉ ... ይሄ ህመም የጀመረዉ ገና በ4 አመቱ ነዉ 3 አመት ያህል ተሰቃይቷል  ያልሄደችበት ፀበል የለም ሌላም ሀገር ሂዳለች ፡፡በፀበል መፍትሄ ሲያጡ ሌላ ሀገር ጠንቋይ ቤት ሄዱ አረንጓዴ እስስት አምጡ ብሏቸዉ አረንጓዴ እስስት ለማግኘት አራት ወር ፈጀ በግድ ተገኘ ጠንቋዩ በአረንጓዴ እስስት ሌላም  ጨምሮ አንገት ላይ የሚንጠለጠል ሰጠው ምንም ለዉጥ የለም...ከ3አመት ስቃይ ቡሀላ ሲጨንቃት ቁርአን ቅሩልኝ አለች...

#አላህ_ሆይ እንዳታስፍረኝ የቁርአንን ሀይልን ለነዚህ ክርስቲያኖች አሳያቸዉ ብየ ዱአ አደረኩ ...ከዛማ በስፒከር ሩቃ ከፈትኩ ሁለት ሁነን በቻልነዉ ቀራን ወላሂ 45 ደቂቃ ባልሞላ እንቅልፍ ወስዶት ላብ በላብ ሆነ ቁርአኑን ስንጨርስ ጩኾ ተነሳ በዛዉ ለቀቀዉ ከዛ ቀን ቡሀላ ታሞ አያቅም ይሄዉ እንቅልፍም ይወስደዋል እናቱም አታዝለዉ ምግብም መመገብ ጀመረ የሚያስመልሰዉ ቀረለት  ትምህርትም ተመዘገበ አልሀምዱሊላህ....እናት አባቱ አጥባቂ ክርስቲያን ነበሩ አሁን ግን ከምነግራችሁ በላይ ለሙስሊም ያለቸዉ አመለካከት ደስ የሚል ነዉ አላህ ሂድያ ይስጣቸዉ የቁርአንን ሀይል ቤተሰብ ዘመድ ልጁን ተሽሎ ሲያዩት ይገርማቸዉ ይደንቃቸዉ ይዟል፡፡

✍🏼 አክስቴ ክርስቲያን ነች ታማ ፀበል ብትመላለስ ምን ብትል ያልተሻላትን በ30 ደቂቃ ሩቃ በመቅራት በአላህ ፍቃድ እንዲሻላት አድርጊያለሁ

✍🏼 ከነዚህ ዉጭ  3 ሰዎች ጎረቤት ምናምን ሲታመሙ በአላህ እገዛ ተሳክቶሎኛል እናም እንደዚህ ልላችሁ ያሰብኩት ሩቃ ማድረግ ከባድ አይደለም መጀመሪያ ጀሊሉን አላህየን ከያዙ ምንም የሚያስቸግር የለም እናም እህት ወንድምህን እናት አባትህን ...እናት አባትሽን እህት ወንድምሽን ለሌላ ባዳ አሳልፋችሁ አትስጡ

----- ጂን ሲናገር  ሊዋሽም ላይዋሽም ስለሚቾል አንዳንዴ ሲናገር እዉነት ነዉ ብለን ከተናገረዉ ሰዉ ጋር ሂደን መጣላት አያስፈልግም፡፡

🌟 ከዚህ ርዕሱ ጋር ባይሄድም በፊት ክፍል ላይ ዘንግቼ ሳላስገባ የቀሁት ጉዳይ አሁን ያለቦታዉም ቢሆን ስለዚህ ጉዳይ ትንሽ ልበል...
በቅርብ አመታት በተለያየ ማህበራዊ ሚዲያ ወንድና ሴት ዚና ሲሰሩ ወይ በባል ወይ በሚስቱ ላይ ሲማግጥ  ተጣብቀዉ እያየን ነዉ፡፡ ይሄ ባልየዉ ሚስቱን ካላመናት ወይም ሚስት ባሏን ካላመነችዉ ጠንቋዮች ጋር ሂደዉ ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች ወይም ሌላ ሴት ጋር ከተኛ እዛዉ እንዲጣበቅ ሰዉ እንዲያዋርደዉ ይሁን ብለዉ አስደግመዉ ሊሆን እንደሚችል አንዘንጋ...ካልሆነም ደግሞ ፈጣሪ እኛን ለማስተማር እነሱን ምሳሌም እያረገ ሊሆን ይችላል፡፡እናም ለትዳራቸዉ ታማኝ ያልሆኑ ሰዎች መጀመሪያ  ባለመተማመን ይጋባሉ ከዛ ይሄ ይፈጠራል፡፡
እናም ወይ የአላህ ቁጣ ነዉ ካልሆነ ድግምት ነዉ ...
ግን በተለይ በትዳር ላይ የሚሰሩ ሲህሮች በአሁን ዘመን ላይ በሰፊዉ ተንሰራፍቷል፡፡


 ⚡️⚡️⚡️ #በጂን_የተያዘ_ወይም_ሲህር_ወይ #በአይነጥላ_የተያዘ_ሰዉ_ወይም_አስታማሚዉ      
         
#ምን_ማድረግ_አለበት⁉️⁉️

      ኩን ፈየኩን ...አላህ ኩን ብሎት አላህ ሱወ በሲህር በጂን በአይነጥላ ሊፈትነን ይችላል ፡፡  ዱንያ የፈተና አለም ነች ለአላህ የትንኝ ክንፍ ያህል ቦታ የላትም ላለን ዱንያ ደስታን እናጣጥማለን ማለት አይደለም፡፡  ዱንያ በሀዘን ማቅ የተተበተበች ደስታ እንደመብረቅ ብልጭ ብሎ የሚጠፋበት የኑሮ መድረክ የፈተና መሸጋገሪያ ድልድይ ነች የጀነት መግቢያ የኸይር መሸመቻ የፈተና ማለፊያና መዉደቂያ የቁጥጥር ጣቢያ ነች፡፡  

  በርዚቃችን ትዳር እንዳናገባ ነገሮች እንዳይሳኩ ወዘተ ሲህር ድግምት  ከተደረገብን የአላህ ዉሳኔ ነዉ ፅናት ብርታት ጥንካሬ ያስፈልጋል ፡፡

♻️♻️ አላህ (ሱ.ወ) የወሰነውን ነገር መደው የተቀበሉ  ነብዩ ሰዐወ ናቸዉ በሲህር ተሰቃይተዋል.....በተጨማሪ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ኢብራሂም የሚባል ልጅ በተወለደላቸው ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የደስታ ስሜት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ተሸክመውት ወደተለያዩ ሰሐቦች ቤት ይዘውት ይሄዳሉ፡፡ ለሰዎችም ልጇን ኢብራሂምን ተመልከቱት፡፡› ይሉ ነበር፡፡ ትንሹ ኢብራሂም አባት ለልጅ በእጅጉ በሚጓጓበት የህፃንነት ዕድሜ ጡት መጣያው አካባቢ ሞተ፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) አለቀሱ😢፡፡ እንባ የልብ እዝነት ውጤት ነውና የአላህን ውሳኔ ካለመውደድ አይቆጠርም፡፡ እርሳቸውም ዐይን ያለቅሳል፣ ቀልብ ያዝናል፣ ጌታችን የሚወደውን ነገር እንጂ አንልም፡፡

#ኢብራሂም_ሆይ!!!! ከኛ በመለየትህ አዝነናል፡፡” አሉ፡፡ ከዚያም ወደቤታችው በመግባት ለአላህ (ሱወ) እንዲህ አሉ፡- ‹‹ጥሪህ ሰምተን በደስታ ወዳንተ መጣን፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ነው፡፡ መጥፎ ካንተ አይደለም፡፡” ብለዉ የጌታቸዉን ዉሳኔ ተቀበሉ...

መቼም የሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ ታሪክ ታቃላችሁ
💚በእናታቸዉ ሆድ ውስጥ ሳለ ወላጅ አባቱን በሞት ተነጠቁ
💛ዕድሜያቸዉ ስድስት ሲሞላ ወላጅ እናታቸዉን ቀበሩ።
❤️ በስምንት ዓመታቸዉ በፍቅር ተንከባክበው ያሳደጓቸዉ አያቱን አይቀሬው ሞት ነጠቀው።

💚 እንደ አይን ብሌናቸው የሚሳሱለት በማራኪ ስብዕናው ተረታ የትዳር አጋሩ ለመሆን የበቃችው ውድ ሚስቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ተከታትለው ተለዩት።
💛  ከሁለት ዓመታት ዕድሜ በላይ ያልቆዩ ሁለት ወንድ ልጆቹን ሞት ቀጠፋቸው። በህፃናቱ ፈገግታ ደምቆ የነበረው ቤት የሀዘን ጥላ አጠላበት።
❤️ከእርሱ ህልፈት በኋላ በስድስተኛው ወር በሞት ከተከተለችው ተናፋቂ ልጁ በስተቀር ሁሉም ሴቶች ልጆቹ ወደ መጪው ዓለም ተጓዙ።

💚 የአባቱ ጥሪት የነበሩት አጎቱ ተገደሉ። መገደል ብቻ አይደለም የሰው ልጅ ያደርገዋል ተብሎ የማይታሰብ ጭራቃዊ ተግባር በአካላቸው ላይ ተፈፀመ። ሂንድ አስክሬኑን አስቀድዳ ጉበቱን በላችው።👇👇👇
💛 ጧኢፍ ነዋሪዎቿን በነቂስ አውጥታ የስድብ እና የድንጋይ ናዳ እንዲወርድበት ፈቀደች። ምድር ከሰውነቱ የሚፈሰውን ደም መጠጠች።
❤️በመርዝ የተለወሰ ምግብ ሲሱጠት፣ ከሚናፍቅው የትውልድ ቀዬ ሲባረር ይቅር ባይነት የዘወትር ስንቁ ነበር። ስቃይ በተሸከመው አካልና መንፈሱ ታግዞ እግሮቹ አስከሚያብጡ ድረስ ለሊቱን በመቆም አመስጋኝ ባሪያ ለመሆን ከአምላኩ ጋር ያወጋል ሰዎችን ይቅር ይሉ ነበር ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ 
እናም ፈተና  መብዛት ችግር መደራረብ ባይኖር ዱንያ የደስታ ሀገር ብትሆን ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ ባልተፈተኑ ነበር እናም አንተም አንቺም እሱም እሷም እናንተም ፈተና ላይ ናቸሁ ፈተና ጨርሳችሁ ትንሽ ከተደሰታችሁ ቡሀላ ሌላ የከበደ ፈተና እንደሚጠብቀን እርግጠኛ ሁን የዛን ጊዜ ነዉ ኢማንህ የሚለካዉ፡፡
ኢማናችን መለካት እንጂ መነካት የለብንም ወገን


📌 እጅግ አምልኮ በማብዛት የሚታወቀው ታላቁ ታቢዒይ አልፉደይል ኢብኑ ዒያድ ረሒመሁላህ ፈገግታ አያበዙም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ግን ልጅ ሲሞትባቸው ፈገግ አሉ፡፡ ለምን ፈገግ እንዳሉ በተጠየቁ ጊዜ “አላህ የወደደው ነገር ነውና እኔም ወድጄ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የወደደውን እንድትወድ ነፍሴ ፈገግ እንድትል አስገደድኳት” አሉ፡፡

ዑለማዎች ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያለቀሱበትንና አልፉደይል ግን ፈገግ ያሉበትን ሁኔታ በማንሳት ለመተንተን ሞክረዋል፡፡ በመታገስ ደረጃ አፉደይል ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይበልጣሉ ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ትርጉሙም፡- ሞት በሚመጣበት ቅፅበት ቀልብን በሁለት ሰሜት ውስጥ ይከታል፡፡ እዝነትና ውዴታ፡፡ ማንም ሰው ሁለቱን ስሜቶች በአንድ ጊዜ ማስተናገድ አይችልም፡፡ አልፉደይል ሁለቱን ማሳካት አልቻሉምና በውዴታ ስሜት አንድም ፈገግ ማለት አለባቸው አሊያም አብዝተው ማልቀስ ነበረባቸው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ግን ሁለቱን ማሳካት ችለዋል፡፡ አላህ የወደደውን ወደዋል በሌላ በኩል ደግሞ አልቅሰው እዝነት ስሜት አሳይተዋል

📌 የነቢያችን አክስት የሆነችው : እመት ሶፊያ በኡሑድ ጦርነት ወቅት ቁስለኞችን ውሃ ታጠጣ ነበር፡፡ ታላቁ ጀግና ሐምዛ (ረ.ዐ) ተገደሉና አካላቸውም እንዲቆራረጥ ሆዳቸው እንዲቀደድ ተደረገ፡፡ ሒንድ በበቀል ስሜት ጉበታቸውን እስከማኘክ ደረሰች። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለልጇ ዙበይር ኢብኑ አልዐዋም ዝበይር ሆይ! ሶፊያን ወደ መዲና ይዘሀት ሂድ ሐምዛን ማየት የለባትም፡፡” አሉት። ልጇም ሄደና “እናቴ ሆይ! ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና ተመለሽ ብለውሻል፡፡” አላት፡፡

ልጄ ሆይ! ይህን የምታደርጉት ሐምዛን እንዳላይ ብላችሁ ነው አይደል? አለችው፡፡
....“አዎን” አላት፡፡
....እሷም “ልጄ ሆይ! አላህ ከዋለልን ፀጋ አንፃር በሐምዛ ላይ የደረሰው በጣም ቀላል ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በሐምዛ የፈተነን ሥራውን መውደድ አለመውደዳችንን ለማየት ነው፡፡ ወደ አላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሂድና የአላህ መልዕክተኛ ሆይ አላህ በሐምዛ የፈተነን ሥራውን መውደዳችንን ለመፈተን ነው ብላለች ሶፊያ በላቸው ፡፡ ልጁም ወደ ነብዩ (ሲዐወ) በመመለስ ነገራቸው፡፡
... ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) “እንግዲያውስ ማየት ትችላለች፡፡” አሉ፡፡ ሄደችና አይታው አለቀሰች፡፡ ኢንና ሊላህ ወኢንና ኢለይሂ ራጂኡን የኛዑን እኛ የአላህ ነን ወደ አላህም ተመላሾች ነን፡ በማለትም ዱዓእ አደረገችለት፡፡
እናም አላህ በሚያመጣብን ፈተና የዱንያም ሆነ የጂን የሲህርም አላህ ወዶን እየፈተነን እንደሆነ አንዘንጋ

ጅን ሲህር ሳሂር ደጋሚ ጠንቋይ ደብተራ እንደማይጎዳ አሏህ ብቻ ጎጂ እንደሆነ ማወቅን ከኢማኖች ውስጥ ጠንካራ ኢማን ሁኖ እናገኘዋለን!! በአሏህ ላይ የቂን እጅግ የምንፈልገው መሳርያ ነው!! ሌቦች ቤትን ሊዘርፉ ሲመጡ አለሁ ብሎ ድምፅን ማሰማት ሲቀጥልም የመሳርያን ድምፅ ማሰማት እነርሱን እንደሚያስበረግጋቸው ሁሉ የቂን ልክ እንደዛው ጅኖችን ያስፈራቸዋል እንዳይቀርቡን!! ይሁንና ያለ እውቀት ያለ መጠበቅያ የቁርአን አያዎች እና ዚክሮቸች ማለት ያለ መሳርያ መሳርያ ታጥቀው የመጡ ሌቦችን ማስፈራራት ብቻ ነው፡፡ ለኛ መሳርያችን ለጅኖች ሊያውም ከባለጌዎች ለመጠበቅ የምንታጠቀው መሳርያ ዚክርና ቁርአን እንዲሁም ዱአእ ነው፡፡ ሌላውን አይነት የመሀይማን መሳርያ የሆነውን ጥንቆላ መተት ፀበል እና አንጃ ግራንጃዎች ልክ ሌቦችን እንደመማፀን እንደመደራደር ነው የምንቆጥረው፡፡ ከሌባ ጋር ድርድር የለም ባንተ ንብረት ላይ መጥቷልና ፡፡ ከጅን ጋርም እያጠቃህ መደራደር የለም በቁርአን በዚክር ልኩን አሳይተሀው  መከባበር እንጂ፡፡


🖍🖍 እናም ፈጣሪ ይሁን ብሎ ተፅፎብን ከሆነ ትዕግስት ጥንካሬ ፅናት ያስፈልጋል፡፡ በሲህር በጂን የሚፈተን ሰዉ በዛዉም የፀና የጠነከረ አላህ ወዶን ይሆናል ዱአ ላይ መበርታት ግዴታ ነዉ...ከዱአ በጭራሽ ተስፋ ልንቆርጥ አይገባም
{ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِی عَنِّی فَإِنِّی قَرِیبٌۖ أُجِیبُ دَعۡوَةَ ٱلدَّاعِ إِذَا دَعَانِۖ فَلۡیَسۡتَجِیبُوا۟ لِی وَلۡیُؤۡمِنُوا۟ بِی لَعَلَّهُمۡ یَرۡشُدُونَ }
ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡[አል በቀራህ: 186]


🟢  አንድ ድንቅ የሆነ ሐዲስ አልቁድስይ ላካፍላችሁ፡፡ ነቢዩ ባስተላለፉት ሐዲስ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- “የአደም ልጅ ሆይ! እኔም እፈልጋለሁ አንተም ትፈልጋለህ፡፡ እኔ ለምፈልገው ነገር እጅ የሰጠህ እንደሆነ የምትፈልገውን አመጣልሃለሁ እኔ ለምፈልገው ነገር እጅ የማትሰጥ ከሆነ በምትፈልገው ነገር ላይ  እንድትደከም አደርግሃለሁ፡፡ በመጨረሻ እኔ የምፈልገው ነገር ብቻ እንጂ የሚሆን የለም፡፡” ይለናል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በተከበረ ቃሉ “አላህ ካሻ በስተቀር አናንተ አትሹም (አል-ኢንሳን ፡3) ብሏል፡፡

🟢 ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) ዱዓዬ መቼ ተቀባይነት እንደሚያገኝ አውቃለሁ፡፡ አሉ፡፡ “እንዴት ልታውቅ ትችላለህ? ተባሉ፡፡፡ “ቀልቤ በጥልቀት የአላህ ፍራቻ ካደረበት፣ መላ አካላቴ ከተንቀጠቀጠ፣ ዐይኔ ካነባች፣ ይህች ሰዓት ዱዓዬ ምላሽ የሚያገኝበት ነው፡፡ በማለት በዱዓዬ እጠናከራለሁ፡፡ ብለዋል፡፡

ለዱአ መቸኮል አያስፈልግም
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “እስካልቸኮላችሁ ድረስ ምላሽ ይሰጣችኋል፡፡” አሉ፡፡ መቸኮል ሲባል እንዴት ነው? ሲሏቸው አንዳችሁ “ዱዓእ አደረግኩ፤ ዱዓእ አደረግኩ ምላሽ አላገኘሁም፡፡ ይላል፡፡ (ተስፋ መቁረጥ) ዱዓእ ይተውን ይተዉና በዚያው ምላሽ ያጣል፡፡” ብለዋል፡፡
ሲህር ከተደረገብን ወደ አላህ የማይቋረጥ ቀጣይ የሆነ ዱአ ያስፈልጋል፡፡

🟢 ኢብኑ አልቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡ ብትባረርም እንኳን ከአላህ በር ላይ ከመቆም ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ቢመልስህም እንኳን ምክንያት ከማቅረብ አትውረድ፡፡ በሩ ተቀባይነትን ላገኙት የተከፈተ እንደሆነ ቀስ ብለህ በስርአቱ ግባ፡፡ ድሀ ነኝ ምፅዋት እፈልጋለሁ፡፡ በለው፡፡ ምፅዋት የሚሰጠው ለድሆችና ለችግረኞች ነው፡፡ እኔም ምስኪን ደሃ ነኝ፡፡ በለው፡፡👇👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/10/02 18:28:26
Back to Top
HTML Embed Code: