Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም እንዴት ናችሁ፡፡

☞በጂን
☞ በሲህር(ድግምት)
☞ አይነ ጥላ(ቡዳ)
ላይ ያተኮሩ ፁሁፎች ከቁርአንና ከሀዲስ በማስረጃ
ምልክቶች እና ሁሉም በቤቱ ያሉ መፍትሄዎች መከለከያዉ ያተኮረ ፁሁፍ ኢንሻ አላህ ቅዳሜ ሀምሌ ➊ ባልተንዛዛ ክፍል እጥር ምጥን ያለ የሚጠቅም ፁሁፍ ይቀርባል፡፡

የተዘጋጀዉ ፁሁፍ 70% መፅሀፍ ሲሆን
የመፅሀፉም ርዕስ
#ድግምት_ሲህር_ምንነቱና_ፈዉሱ  ከሚለወዉ መፅሀፍ ወሂድ አብዱሰላም ፅፎት ሰይድ አሸንፍ ወደ አማረኛ ተርጉሞት ገበያ ላይ ካለ መፅሀፍ የተዘጋጀ ነዉ፡፡
እናንተም ገዝታችሁ መፅሀፉን ሙሉዉን ብታነቡት ተጠቃሚ ትሆናላችሁ፡፡

30% ደግሞ  የዲን እዉቀት ያላቸዉን በመጠየቅና ...ሩቃ ለአላህ ብሎ የሚሰሩትን ከሚነግሩኝ ገጠመኝ አንፃር አተኩሮ የተፃፈ ነዉ፡፡

📌 በዚህ ፁሁፍ 70% ከመፅሀፍ የተዘጋጀ ነዉ ከመፅሀፍ ማዘጋጀት በጣም ከባድ ነዉ ጊዜ ይፈጃል ..አይንንም ይፈታተናል በዛዉ አሁን ትምህርት የተጠናቀቀበት ጊዜ ስለሆነ በማህበራዊ ሚዲያ ርቀን ማንበብ ላይ ብናተኩር የማንበብ ባህላችን ይጨምራል እናም ይሄን ስለሲህር ድግምት ከጨረስኩ ጊዜ እንደምንም ከተመቻቸልኝ ሌላ ርዕስ ተይዞ ከመፅሀፍ እና ከሚያቁ በመጠየቅ አዘጋጃለሁ፡፡
እናም በማቀርባቸዉ ፁሁፎች መፅሀፍ ማንበብ ማቆማችን ምን ያህል እዉቀት እያነሰን እንደሆነ
ሁላችንም ራሳችንን ፈትሸን ....
ከተስማማን በጀመአ መፅሀፍ ማንበብ program
እንጀምር ይሆናል፡፡


📌 ይህን ስለሲህር ጂን ቡዳ የሚያተኩር ፁሁፍ በቻላችሁት አቅም ለዘመድ ጓደኛ ቤተሰብ ሼር በማድረግ ራሳችንን ፈትሸን ሌሎች እንዲፈትሹ እናድርግ፡፡

ፁሁፍ ማቅረብ ታሪክ ማቅረብ ስላቆምኩ ከግማሽ በላይ የሚሆነዉ  የቻናል ቤተሰብ ከቻናል አምልጧል...ለወደፊት ያለዉ በቂ ነዉ ፡፡ ግን ይጠቀማሉ ብላችሁ ካሰባችሁ አዲስ እንዲገቡ  የምፈልጉ ካለ ሼር በማድረግ ለሚመቻችሁ ቤተሰብ ይጋብዙ

መልካም ንባብ ...አንብበን የምናስተነትን ራሳችንን የምንፈትሽ ፈጣሪ ያድርገን

አሚር ሰይድ


Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#የኤልሳቤጥ ታላቅ ወኔና ራዐይ
አሚር ሰይድ

ኤልሳቤጥን ምን ያህል ታቋታላችሁ???

ኤልሳቤጥ የስፔንና የፊሽታላህ መሪ ነበረች፡፡ይህች ሴት ከ30 ዓመት በላይ የሚሆነዉን ዕድሜዋን ያጠፋችዉ ለካቶሊክ እምነት በመስራት ነበር፡፡ለስፔን ሀገሯና ሀይማኖቷ ብዙ ስራዎች የሰራችና መስዋት የከፈለች ናት፡፡ኤልሳቤጥ ሴት መሆኗንም ረሳች፡፡ስፔንን በእጇ እስክታደርግ ድረስ የዉስጥ ልብሷን ላትቀይር ለራሷ ቃልኪዳን ገብታ ማለች፡፡ ይህን ያለችዉ ስፔንን ከመቋጣጠሯ ከረጂም አመት በፊት ነበር፡፡

ቤክርስቲያን የኤልሳቤጥን ማንነት በማነፁ ላይ ትኩረት አድርጋ ሰርታለች፣ተንከባክባታለች፣ጠብቃታለች፣መንግስት እስከ መመስረት እንድትደርስም አድርጋታለች፡፡የሰዉ ሀይልና የገንዘብ ሀይል በገፍ በመለገስ አጠናክራታለች፡፡

ታዋቂዉ የታሪክ ፀሀፊ ፊርናንድ ፊስካይኑ በታህሳስ እ.ኤ.አ1987 ኤልሳቤጥና ጥንታዊ ቀሚስ በሚል ርዕስ መፅሀፍ ፅፏል፡፡ መፅሀፉ በዛ አመት ብቻ አራት ጊዜ የታተመ ሲሆን ፀሀፊዉ በመፅሀፉ ላይ ኤልሳቤጥ ወደ ቅዱስነት ደረጃ ከፍ እንድትደረግ ጠይቋል፡፡
☞በአንደሉስና በገርናጣ ያለዉን የሙስሊሞች ግዛት ለመጨረሻ ጊዜ እንዲወድቅ ያደረገችዉ ኤልሳቤጥ ናት፡፡
☞ኤልሳቤጥ ሙስሊሞችን ለማጥፋት የተለያዩ ሀገሮች ያሉ ክርስትያን አመራሮች በአንድነት እንዲቆሙ ያደረገችዉ እሷ ነች፡፡
☞ኤልሳቤጥ ሙስሊምችን ለማጥፋት በሚደረገዉ ዘመቻ ጦርሜዳ ድረስ በመሄድ ጦርነቱን ትመለከትና ታበረታታ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ገንዘብ እጥረት አጋጥሞ ጌጣጌጦቿን በማስያዝ ሰራዊቱ ደመወዝ እንዲከፈለዉ አድርጋለች፡፡
☞በገርናጣ የመጨረሻ መሪ የነበረዉን አብደላህን ያንበረከከችዉ ኤልሳቤጥ ነች፡፡
☞ኤልሳቤጥ አብደላህን 10ሺ ወርቅ ዓመታዊ ግብር እንዲከፍል አድርገዋለች፡፡አብየላህ ገርናጧን እስኪያስረክብ ድረስ ትንሹን ልጁን በማስያዣነት ይዛበታለች፡፡
☞በመጨረሻዉ እኤአ ጥር 1492 የክርስቲያን ሰራዊቷን ይዛ ገርናጧ ገባች፡፡ ገርናጧን ከተቆጣጠረች ቡሀላ
◇ ሙስሊሞችን በህይወት እያሉ አቃጠለቻቸዉ፡፡😔
◇ ከዚህም በላይ ሙታን ሙስሊሞችን ከመቃብራቸዉ አዉጥታ አቃጠለች፡፡😔
◇ በህይወት ያሉትን በግድ ክርስቲያን እንዲሆኑ አደረገች፡
◇ የሙስሊም አጠቃላይ ንብረታቸዉን ቀምታለች ፡ ዘርፋለች፡፡
◇ በአንደሉስ አዛን ማድረጊያ እስኪጠፋ አዛንም እስከማይደረግ ምንም ሙስሊም እስከማይኖር ድረስ የማጥፋት ዘመቻ አድርጋለች፡፡


ኤልሳቤጥ ኮሎምበስን የአሜሪካን አህጉር ለማግኘት ላደረገዉ አሰሳ በጀት የመደበች ናት፡፡ የአዲሲቱን አሜሪካ ድልብ ሀብት ወስዳ ከስፔን ካዝና ዉስጥ ጨምራለች፡፡ የአሜሪካን ህዝብ አንበርክካ ለመግዛትና ክርስቲያን ለማድረግ የሀይማኖት ሰባኪዎች ሚሺነሪዎች ልካለች፡፡
ኤልሳቤጥ በአዉሮፓና በአሜሪካ ታሪክ ታላቅ ራዕይና ወኔ የነበራት ሴት ተደርጋ በካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ ትታያለች፡፡ኤልሳቤጥ ናት ሙስሊሞችን ከአንደሉስ(ስፔን)ጠራርጋ ያስወጣችዉ ፡፡

ኤልሳቤጥ የሰራችዉ ስራ ለኛ ለሙስሊሞች ክፉኛ የሚያበሳጭ ዉስጥን የሚያደማ ቢሆንም ከፍተኛ ወኔ የነበራት መሆኑን መካድ አንችልም፡፡ሙስሊሞችን ለማጥፋት በፊትም አሁንም የሚደረገዉ ዘመቻ ምን ያህል የከፋና የጠነከረ ለመሆኑ ኤልሳቤጥ ማሳያ ናት

~~~~~~ ዉድ የቻናል ቤተሰቦች ይሄን ስታነቡ ከንፈር ለመንከስ ለመምጠጥ አይደለም ሰዉ ላመነበት ነገር በተለይ ለሀይማኖቱ እንደሷ መሆን አለብን ለማለት ያህል ነዉ ....በኤልሳቤጥ ዘመን ከዛስ ቡሀላ ያለዉ ሙስሊም ማህበረሰብ የኤልሳቤትን ያህል 5% ሰርቷል ወይ?? ኤልሳቤጥ ግን ላመነችበት ሀይማኖት ይሄን ሰርታለች ...መገንዘብ ያለብን ኤልሳቤጥ ሙስሊም ሁና ቢሆን ኑሮ አለም የሙስሊሞች እንደምትሆን ምንም ጥርጥር የለዉም ለምን ስፔን ከ600 አመት በላይ በሙስሊሞች እጅ ነበረች ..እንደ ኤልሳቤጥ ባሉ ለአላማቸዉ ጠንካራ በሆኑ ሴቶች ነዉ የተነጠቅነዉ፡፡


#ሴቶች_ሆይ እራስሽን ዝቅ አታድርጊ ሴትነት ማለት ማንነትን ፈልጎ ለማግኘት ሲባል ተወጥቶ ተሂዶ የማያልቅ ድካም ያለዉ ረጅም ተራራነት ነዉ፡፡ ኤልሳቤጥ ለያዘችዉ አቋም ሀይማኖቷን ለመርዳት የለበሰችዉን ዉስጥ ልብስ ፓንት ሳትቀይር ከ30 አመት በላይ ታግላለች እናንተ ግን በቀን አስሬ ፊትሽን እየታጠብሽ ኮስሞቲክስ እየተቀባችሁ የወንድ ምላስ ተጠባባቂ አድናቂ አትሁኝ፡፡

>> እጅሽን በኮስሞቲክስ ያገረጣሽዉን ለኢስላም ፃፊበት ቁርአን ይዘሽ ቅራበት...
>> እግርሽን ፈግፍገሽ ተቀብተሽ የምትሄጅበትን መድረሳ መስጊድ ሂደሽ ኢስላምን ሸምችበት፡፡

አንቺ የተፈጠርሽዉ ለወንድ ሁነሽ አግብተሽ ወልደሽ ማሳደግ ብቻ ፕላንሽን አታድርጊ፡፡ አግብተሽ ለዲነል ኢስላም ብዙ መስራት እንደምትችይ ብቻ እርግጠኛ ሁኝ፡፡ ለምን ብትይ እንደ ኤልሳቤጥ ወኔ ካለሽ እሷ ትዳር ሳትመኝ ሀይማኖቷን አስከብራለች አንቺም ያገባ ግማሽ ኢማንሽ ስለሚሞላ በተቀረዉ አላህን እየፈራሽ ለሀይማኖትሽ ብዙ መስራት ትችያለሽ፡፡ የህይወት ግብሽን ትዳር ብቻ ነዉ ብለሽ አትሰቢ ..ለምን ብትይ በዚህ ሀሳብ ትዳር ሲጠፋ ስንት ሴቶች እንደ ከፈሩ የምናቀዉ እዉነታ ነዉ፡፡ ነገር ግን ኤልሳቤጥ ካቶሊክ ሀይማኖቴ ይበልጥብኛል ከትዳሬ ብላ ዛሬ ድረስ ላሉት ካቶሊኮች ታሪክ ሰርታ አልፋለች

እናም በዚህ ዘመን ያላችሁ ሴቶች መቼም እንደ ኤልሳቤጥ ጠንካራ ወኔ ያለዉ ለሀይማኖቱ የሚታገል ሴትም ወንድም የለም .ለምን ሁሉም በዱንያ በምዕራባዉያን ፋሽን ኢስላምን አስረክቧል ...በኢስላም ስራ የማይጠቅም የማይጎዳ ሁኖ የሚኖር እንጂ ለወደፊት ለሙስሊም ማህበረሰብ አሻራ የሚያስቀምጥ ለወደፊት ለሚፈጠረዉ ሙስሊም ትዉልድ አሻራ የሚያስቀምጥ እንኳን ሊኖር ትዝ የሚለዉ የለም ፡፡ ሌላዉ ይቅር ሁሉም ከኢስላም ስም ዉጭ በጎን ሌላ ስም ለጥፎ ሌላን አላስቆም አላስቀምጥ ብለዉ ሲጣሉ ለዲነል ኢስላም ሰፊ እዉቀት የሌለዉ ጃሂል ተደናግሮ መንታ መንገድ ላይ ቁሟል፡፡

እንደዉም አሁን ያለዉ ሙስሊም ለወደፊት ለሚመጣዉ ኡማ የሚያስቀምጠዉ ወንዱ ለሴት ለመታየት ብሎ ሙነሺድ መሆን ምኞቱ ሆነ፡፡ ከዛም ነሽዳ ያወጣል አዳራሽ ይከራያል 80% ሴት ይገባል ስታጨበጭብለት ደስ ይለዋል አበቃ ከዛ ቡሀላ ስንት ይሰራል ታሪኩ ብዙ ነዉ....ይሄም አልበቃ ብሎ ባወጣዉ ነሺዳ ህፃናት ቁርአን እየቀሩ እንዳያድጉ ሀፊዝ እንዳይሆኑ የተለያዩ ኪታብ ቀርተዉ ለወገን እንዳይሆኑ ነሺዳ አዳማጭ ሁነዉ ኢስላምን በሂክማ እናስተምር ብለዉ ይነሳሉ...ሴቱም የእከሌ ሙነሺድ ድምፅ ያምራል እሱ ልጅ ይመቸኛል ባይ እንጂ ዲነል ኢስላምን ተምራ ጠንካራ ወኔ ያላት እንደ ኤልሳቤጥ ጠንካራ አቋም አትይዝ በነሺዳ ነብዩን እወዳለሁ ስትል ትዉላለች፡፡

በፊት ሱሀቦች ስለሀይማኖታቸዉ ሲመካከሩ እኔ አሸንፋለሁ ሳይሆን የእሱ ሀቅ ቢሆንስ ነበር ብለዉ መወያየት የሚጀምሩት...ዛሬ ዘመን እንደምናየዉ ሀቅ ሲነገር የማይሰማ ሁሉ ተፈጠረ...ከዛም በተዘዋዋሪ ሀቅ የሚናገረዉ ሰዉ የሚሄድበት አካሄድ ጥፋት ላይ ያለን ከማስተካከል በጥፋቱ ላይ ምን አገባዉ በሚል የብስ ጥፋት እየጨመሩ መጥተዋል..ግን ጥፋቱ ከጥፋተኛዉ ነዉ ወይስ ጥፋትህን አስተካክል ከሚለዉ አካል
ግን የወደፊት ትዉልድ የማይጠቅም የማይጎዳ መሆኑን የምታቁት በፊት አጂ ነብይ ጋር እደተደባለቁ ሰርግ አስጨፋሪ ስም ይዘዉ ነቢይ ዉዴ ..መርሀባ ሲሉ የነበሩ ሁሉ ዛሬ በስመ ታዋቂ ሙነሺድ ስም እህህህ ወዳጄ..ነቢይ ናፈኩኝ....ናፍቆቱህ በረታ..ልሂድ መካ ሊሂድ መዲና...ልሂድ እነአንይ ሾንክይ ጋር...የነቢይ መዉሊድ ናፈቀኝ....እያሉ👇👇👇
ፀጉራቸዉን በምዕራባዉያን እስታይል ተቆረጠዉ ነብዩ ሰዐወ እንወዳለን እያሉ በነቢይ ስም ሴት ማጥመጃ...ሴት ቁርአን እንዳቀራ ኪታብ እንዳቀራ ነሺዳ አዳማጭ እንድትሆን ....
በተዘዋዋሪ ደግሞ የአህባሽ አቂዳን በነሺዳ አላህ ባለቦታ ይገኛል እያሉ  እያስተማሩ ነዉ‼️‼️‼️
እህት አለም ሆይ እና አንቺ የዚህ ዘመን ሙነሺዶች አድናቂ ሁነሽ ነዉ እንዴ ለካቶሊክ እምነቷ ብዙ ገድል የሰራችዉ ኤልሳቤጥ አይነት ለዲነል ኢስላም የምትሰሪዉ???

አሁን ዘመን ያሉ ሴቶች እንደ ኤልሳቤጥ የመሆኑ ሞራል እቅድ ስለሌላቸዉ አላማቸዉ ሁሉ አላህ እንዲያቸዉ ሳይሆን የሚሰሩት ጀዝባ ወንድ እንዲያቸዉ ሆነ፡፡ በተለያዩ ሙስሊም ተብየዎች tv program ዜና አቅራቢ ፕሮግራም መሪ ..በተጨማሪ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ በYoutube በtiktok በቴሌግራም ወዘተ እናስተምራለን ብላችሁ ፋሽን ልብስ ለብሳችሁ ብቅ ብቅ ያላችሁ ሁሉ
አለፍ ሲልም ሀይማኖት አስተማሪ ነን ብለዉ ተነስተዉ አፏን ከምስራቅ ወደ ምዕራብ እያጣመመች ሀዲስ ቁርአን አስተማሪ ሁነዉ እያየን ነዉ....ግራ የገባኝ ወንድ እንዲመለከታት ነዉ ወይስ እሷ አፏን እያጣመመች ስታስተምር ትዉልድ እቀርፃለሁ ብለሽ አስበሽ ይሆን??🤔
#ሴቶች_ሆይ!!! እዩኝ እዩኝ ያለ መልሶ ደብቁኝ ደቡቁኝ ማለቱ አይቀርም...የአንቺን ሚዲያ ላይ መዉጣት የተመለከተ ጉድ ሰርቶሽ መልሰሽ ከሚዲያ ደቡቁኝ እንዳትይ ....ለዚህ መድሀኒቱ ..በስሜትሽና በስሜት ከሚፈርዱ አንቺን እንደሚመችሽ የፈቀዱልሽ ኡለማ ተብየዎች ፈትዋ እራስሽን አግለሽ ...አንቺ ለምሰሪዉ ስራ ምንችግር አለዉ ? ዘመኑ ነዉ ከማለት ቁርአንና ሀዲስ እኔ ለምሰራዉ ስራ ምን ይላል የሚለዉን አስተንትኝ፡፡

#አላህ ጠንካራ ወኔ ካለቸዉ ብዙ ገድል ከሰሩ እንደነ አኢሻ እንደ ኸዲጃ አይነት ሴቶች ስብዕና ይወፍቃችሁ...ኤልሳቤጥ ለካቶሊክ ሀይማኖቷ ለሰራችዉ ታሪክ መቼም አይረሳትም ነገር  ግን  ቅጣቱን የሚሰጠዉ አላህ ነዉ፡፡ የእሷን ፈጣሪ ይወሰነዋል...

እኔ ትኩረት እንድታደርጉ የምፈልገዉ የእኛ ሙስሊም ሴቶች በሚዲያ ወሬ ሳይሆን እንደ ኤልሳቤጥ ላመነችበት አላማ ሟች በተግባር ጠንካራ የሙስሊም መከታ የምትሆኑ ያርጋችሁ ለምን እናንተ ጠንካራ ብትሆኑ የእናትነት ደረጃ ስደርሱ የሚወለደዉ ልጅ እሰቡት እንዴት የሙስሊም ቀኝ እጅ እንደ ሰልሀዲን አልአዩብ ያለ ወጣት በዘመናችን ከእናንተ ማህፀን መፈጠር ይችላልና፡፡

☝️ ነገር ግን አሁን ላይ ልጅ ሲወልድ አዩብ ብሎ አዩብን በተርቢያ በዲነል ኢስላም አሳድጎ አንተ የምወልደዉን ልጅ ሰልሀዲን በለዉ ..የሚል እናትና አባት አለ ግን??? በጭራሽ የለም...እስኪ ያገባችሁ ወይ ትዳር ያሰባችሁ የምወልዱትን ልጅ አዩብ ብላችሁ በአለም ቁጥር አንድ ጀግና ሁሉም የሀይማኖት ተከታይ ስለጀግንነቱ ጥሩ ባህሪዉ ስለሚመሰክሩለት ስለሰልሀዲን አዩብ ታሪክ ሲያድግ አሳዉቁት የወለዳችሁት ልጅ አዩብ ሲወልድ ሰልሀዲን ብሎ አዩብ ለሰለሀዲን የዛን ጀግና ታሪክ ነግሮት እንደሱ ለዲነል ኢስላም እንዲታገል ማድረግ ይቻላል...ግን ለዚህ እቅድ ስራዉ የሚጀምረዉ አሁን አንብባችሁ ዛሬዉኑ ነዉ👌  ከአላህ ጋር ንፁህ ንያ እና ወኔ ያለዉ ትግል ካረግን ስለሀዲን አልአዩብ በዘመናችን መተካት እንችላለን፡፡

አሁን ከኛ የሚጠበቀዉ በኤልሳቤጥ ከንፈር መንከስ ሳይሆን የምናደርገዉ ፊልሚያ ኢስላምን መሉ በሙሉ ከምድረገፅ ለማጥፋት ከምዕራባወያንም ከአገር ዉስጥም ቆርጠዉ ከተነሱ ሰዎች ማህበረሰቦች ጋር መሆኑን በደንብ ተረድተን ዲናችንን ለመጠበቅ ከእነሱ በላይ ቆራጥ ሁነን መነሳት አለብን ኢንሻ አላህ


#ሴቶች_ሆይ!!!
አንዳንድ ወንዶች ሴቶች ተናደዉ ሲከፋቸዉ መፍትሄዉ አዲስ ልብስና ክሪም ሲሰጣቸዉ ይረሳሉ ይባላል😉 አሁን ዲነል ኢስላም ተደፍሯል
...ዲነል ኢስላም የተደፈረዉ በጦርነት ብቻ አርገዉ የሚይዙ አሉ ፡፡ ወላሂ በጦርነት ኢስላምን ማጥፋት እንደማይመች አዉቀዉ
☞በሊፒስቲክ ጦርነት
☞በኮስሞቲክስ ጥርነት
☞በሸሪአ ክሪም ሳይሆን በፋሽን ክሪም ጦርነት
☞በትክክለኛዉ ሂጃብና ጅልባብ ሳይሆን በእነሱ ተመሳሳይ በሆነ ጦርነት...ሴቶችና ምዕራባዉያን መፋለም ከጀመሩ ቆዩ...አሸናፊዉ ግን እስከ አሁን ምዕራባዉያን ኢስላም ጠሎች ናቸዉ....ታዳ አሁን ካላችሁ ሙስሊም ሴቶችና ላመነችበት ለካቶሊክ እመነቷ የሰራችዉ ኤልሳቤጥ ማን በለጠ???
ወይስ ኢስላምን በስጦታ ክሪምና አዲስ ልብስ ቀይራችሁት ይሆን እንዴ🙄


✿ እዉነት ተናግሬ ከዛም አልፎ ከትቤ ከሆነ ከአሏህ ነዉ...ስህተት ተናግሬ ከሆነ ከሸይጧን ነዉ አላህ ራህመቱን ያዉርድልኝ እናንተም አንብባችሁ አዉፍ በሉኝ ...እናንተንም ባነበባችሁት የኤልሳቤጥ ታሪክ ከእናንተ ጋር አመዛዝናችሁ...እኔስ ምን ይጎለኛል እኔም መሆን እችላለሁ ብላችሁ ወኔ ሰናቂ ያርጋችሁ

አብሽሩ አልችልም ማለት የሸይጧን የስንፍና መረማመጃ ድልድይ ነዉ...

እንችላለን !!! እንጀምራለን!!! አላህ ደግሞ ያግዘናል!!!

⚡️መስከረም 15/2014 ተዘጋጅቶ በቻናል ተፓስቶ አሁን በድጋሜ የቀረበ


Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ


            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
          

                 ⭐️ #ክፍል👉 አንድ 1⃣


⚡️አንዳንድ ሰዎች የጂኒዎችን መኖር ክደዋል በዚህም ምክንያት መተት የለም ይለሉ፡፡
ግን በመተትና በጂኒዎች መካከል ጥብቅ ቁርኝነት አለ ..ጂኒዎችና ሰይጣናት የመተተኛ አይነተኛ ተዋናያን ናቸዉ፡፡

  ጂኒዎች ከሰዎች እና ከመላኢካዎች የተለዩ ዓለም አላቸዉ፡፡ ማሰብ የሚችሉ አዋቂ ፍጡራን ናቸው ፡፡
በመርፌ ቀዳዳ መሹለክ የሚችሉ በሰዉ ደም ዝዉዉር ዉስጥ መንቀሳቀስ የሚችሉ ፍጥረት ናቸዉ፡፡

የሰዉ ልጅ ትክክለኛዉን እምነት መርጦ የመከተል ነፃ ፈቃድ እንዳለዉ ሁሉ ጂኒዎችም አላቸዉ፡፡ከሰዉ የሚለዩበት ዓይነተኛዉ መለያ የተፈጠሩት ከእሳት መሆኑና እነርሱ የሚያዩን እኛ የማናያቸዉ የመሆኑ ጉዳይ ነዉ፡፡

🔰 ከጂኒዎች ዉስጥ ተንኮለኛና ሰዎችን ወደተሳሳተ መንገድ የሚመሩት ሸይጧን ተብለዉ ይጠራሉ፡፡ ስለሆነም ሸይጧን ሁሉ ጂኒ ነዉ ነገር ግን ጂኒ ሁሉ ሸይጧን አይደለም፡፡
እናም ጂኖች መኖራቸዉን ከቁርአን ማስረጃ
☞ከጋኔን የኾኑን ጭፍሮች ቀርአንን የሚያዳምጡ ሲሆኑ ወደ አንተ ባዞርን ጊዜ አስታዉስ (አል-አህቃፍ 29)
በተጨማሪ
☞ አል-ረህማን 33
☞ አል-ጂን 1
☞አል-ማኢዳህ 91
☞ አል-ኑር 21
እንዲሁም በቁርአን ጂኒ የሚለዉ 22 ቃል ጊዜ...ጂኒዎች የሚለዉ ቃል 7 ጊዜ...ሰይጣን የሚለዉ ቃል 68 ጊዜ ...ሰይጣናት የሚለዉ ቃል 17 ጊዜ ተጠቅሰዋል፡፡



አላህ በቁርአኑ እንደተናገረዉ 
>>> ሰወች በነቢዩ  ሱለይማን አለይሂ ሰላም የስልጣን  ዙፋን  በነበረው ነገር ተከተሉ ሱለይማን ደጋሚ አልነበረምና አልካደም ሰይጣኖች ግን ደጋሚ በመሆን በአላህ ክደዋል ይለናል
ነቢዩ ሱለይማን በምድር ላይ ስልጣንን በሰፊ እንዲቆናጠጡ ፈቅዶላቸው ነበረና ሰውን እንሰሳውን ጅኑን ተቆጣጥረው ያስተዳድሩ ነበር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን በጅኖች አለም ድግምትን በመስራት ለሰወች በማስተማር እጅግ የተጠመዱበት ዘመን ነበረና ይህንን ተንኮል ለማስቆም ነቢዩ ሱለይማን የድግምትን መዛግብት በሙሉ ከጅንም ከሰውም ያለውን አሰባስበው በማይደፈረው ሱልጣናቸው ወንበር ስር ቀበሩት፡፡ ምክንያቱም የእምነት መፅሀፍ የተቀላቀሉ ቃላቶች ስለነበሩ ምናልባት በዚያ ዘመን ማቃጠል የማይቻልበት ዘመን ይሆናል ተብሎ ይታሰባል፡፡  ዙፋናቸውን ማንም አይደፈረውም ጅኖች ከተጠጉት ያቃጥላቸዋል በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ነቢዩ ሱለይማን ህይወታቸው አለፈ፡፡

አመታት ተተካኩ ተንኮል ተንሰራፋ የሰይጣን ውስወሳ ጀመረ ...ሰወች ዳግም ሲህር ስለሚባለው ነገር ማሰብ ጀመሩ በዘመኑ የነበሩ የጅን ገባሪ ሰዎች በቂ የድግምት መረጃ በማጣታቸው ጅኖችን አማከሩ ጅኖች ደግሞ እኛ ብንነካው የሚያቃጥለን የድግምት እውቀት ታሽጎ የተቀመጠው የነቢዩ ሱለይማን ዙፋን ስር እንደተቀበረና ከሰዎች ውጭ ሌላ አካል ሊነካው እንደማይችል ለሰወች በመንገር ከነቢዩ ሱለይማን ዙፋን ስር የተቀበረውን የድግምት መፅሀፍ ሰወች አውጥተው ለጅኖች እንዲሰጧቸውና.... ጅኖች እዚያ ላይ ያለውን ነገር በማየት የተሻለ ድግምት ሊያደርጉላቸው እንድሚችሉ ለሰወች አሳምነው መፅሀፉን አስወጡት ይባላል፡፡

በሰወች የወጣውን የድግምት  መፅሀፍ ጅኖች ተቀብለው የተለያዩ ድግምትን እንደ አዲስ አንሰራፍተው ማስተማር ማድረግ ጀመሩ፡፡

    ለዚያም ነው በቁርአኑ ውስጥ ሱለይማን አልካደም ሰይጣኖች ግን ክደዋል ምክንያቱም ሰወችን ድግምት ያስተምራሉ የሚያስተምሩት ድግምት ደግሞ በሁለት ማላኢካዎች አማካኝነት ባቢሎን በሚባለው ምድር ሀሩትና ማሩት የተባሉ መላኢኮች ሰወችን ለመፈተን በማስተማር ሲመጡ ሰወች ተማሩ እነዚያ ማላኢኮች አንድንም ሰዉ አያስተምሩም ከማስተማራቸው በፊት እኛኮ ይሄንን የምናስተምራችሁ ለፈተና ነው አልማርም ይሄንን ተግባር ያለ አማኝ  ነጃ ወጣ የተማረ ግን በፈተና ውስጥ ወደቀ በማለት ይብራሩላቸው ነበር፡፡

  በነወዊ ተፍሲር ደግሞ ሀሩትና ማሩት መላኢካዎች ሳይሆኑ ሁለት ንጉሶች ናቸው በማለት ይፈስሩታል ግን አብላጫዉ ለፈተና የተላኩ መላኢኮች ናቸው የሚል ያመዝናል... አሏሁ አዕለም.... እናም ከማስተማራቸው በፊት እኛ ፈተናዎች ነን ይህን ተምረህ አትካድ በማለት ይናገራሉ ፡፡ ሰዎችም ከሁለቱ የሚማሩት ነገር ባልና ሚስትን አጣልቶ ትዳርን የሚበትን ድግምትን ነው ግን ይሄንን ማድረጋቸው አላህ ካልፈቀደ በስተቀር ማንንም መጉዳት አይችሉም ይለናል አላህ በቁርዐኑ....
አላህ የሚወደዉንም የማይወደዉን ይፈትነዋል...
ሲህር ድግምት እንኳን በሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ  አሰርተዉባቸዋል እናም ነብዩ የተፈተኑበትን  እኛም ተራ ሰዎች በየደረጃዉ ሊፈትነን ይችላል፡፡
ግን ድግምቱ ቢሰራ ቢላክ አላህ ኩን ካለለዉ  የፈለገዉ ጠንቋይ  ምንም እኛ ጋር ቢሰራ ቢልክ ምንም አያደርገን....
ማወቅ ያለብን ነብዩላህ ኢብራሂም የተቀጣጠለዉ እሳት ለብዙ ቀናት ማቀጣጠያ ተሰብስቦ ሲቀጣጠል የተቀጣጠለዉ እሳት በሰማይ የምሄድን  በራሪ ያስቀር ነበር እናም ነብዩላህ ኢብራሂምን በሩቅ በወስፈንጠር ላካቸዉና እሳቱ ሙሀል ቢገቡም አላህ ግን እሳቱን በርደን ወሰላማ አላ ኢብራሂም ብሎ እሳትን አዘዛት እናም እሳቱ ነብዩላህ ኢብራሂም እሳቱ ምንም ሳያደርጋቸዉ ቀረ...በርደን ብሎ ወሰላማን ባይጨምር ኑሮ ብርዱን አይችሉትም ነበር ብለዋል፡፡
☞ ነብዩላህ የኑስ አሳ ሆድ ዉስጥ ኑረዋል እናም አላህ የወሰነዉ ነዉ የሚሆነዉ....
በነብዩላህ ኢብራሂም ታሪክ ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ ... ሰዎች አንተን አንቺን ለመጉዳት ብለዉ ጠንቋይ ቤት ቢሄዱ ቢያሴሩ ቢጠቋቆሙ በመቶዎች በሺዎች ሁነዉ ክፋትን ቢያስቡ አላህ ከጎንህ ካለ በእሱ ተወከል ካለህ ስታገኝም ስታጣም ሲከፋህ ስትደሰትም ሚስጠራኛህ መመኪያህ አላህ ከሆነ ለምን ትንኮላቸዉ የተራራ ያህል ቢሆን አንተን አንቺን አይጎዳም ግን ከአላህ ጋር  ያለንን ግንኙነት መፈተሽ አለብን

🌀 በተዘዋዋሪ አላህ የሚወደዉን ባሪያ ይፈትነዋል ለምን ዱንያ የትንኝ ያህል ክንፍ ቦታ ስለሌላት አንዳንድ በደጋሚዎች በጂኖች ተልከዉ ሲመጡ በእኛም መዘናጋት ተጠቅመዉ አላህም እስኪ ባርያየን በዚህ ሙሲባ ይሸነፋል ወይስ እኔን ይዞ በኔ ተወክሎ በኔ ቃል ቃርአንን ይዞ ታግሎ የጠንቋይን የሳሂርን ትብትብ  ያሸንፍ ወይም ታሸንፍ ይሆን?? ብሎ ሊፈትነን ይችላል፡፡ ይሄን ጊዜ ወደ ቁርአን ወደ ዚክር እንድንመልስ አላህ ጋር ያለንን ግንኙነት ጠበቅ አድርገን እንድንይዝ ሊያስታዉሰን ኢማናችን እንዲጨምር መልሶ እድሉን እየሰጠን ሊሆን ይችላል፡፡

ነብዩ ሰዐወ በሀዲሳቸዉ አላህ በጠረጠራችሁኝ ቦታ ታገኙኛላችሁ ብሏል እናም
🔸 ነገሮች አልሳካ ሲሉ በስራ ስንፍና ምክንያት ስንከስር👇👇
🔹 ትዳር ሲመጣ ከእሱ የተሻለ ሀብታም ወይ ቆንጆ አገባለሁ ብለሽ አስበሽ ስታማርጭ እድሜሽ 27 ሲያልፍ ጠያቂ ሲጠፋ የኔ ሲህር አይንናስ ነዉ ከማለት ይሄን ጊዜ እረጋ ብሎ መወሰን
🔸 አንተም ከእሷ የተሻለ ቆንጆ የተሻለች አገባለሁ ብለህ እሷ ስታገባ ወንድ የሚቀናዉ የሚወዳት ለትዳር የናቃት ስታገባ ይቆጫል እናም ስታምርጥ እያሳለፍ ቡሀላ የትዳር ጡር ሲመጣብህ አይንስ ሲህር ነዉ ከማለት አሁኑኑ ሸርጥ ሳያደርጉ ማግባት
🔹 የራስ ባህሪን ችግር ሳያስተካክሉ ነገር ይገንብኛል እያሉ ከመሻከክ
🔸 መጀመሪያ ላይ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒን ተቅሞ ወይም የሚቀበረዉን ካስቀበሩ ቡሀላ ልጅ ሲፈለግ ክኒን መዋጥ አቁመሽ የሚቀበረዉንም አስወጥተዉ ልጅ ቢጠበቅ እንቢ ሲል ዘመድ ጓደኛ ጎረቤት ሲህር አሰርተዉብኝ ይሆናል ከማለት
🔹 ትምህርት በፊት ጎበዝ ሁና ወይም ሁኖ በራሱ ችግር ወይም ፍቅር ይዞት(ይዟት) የሰነፈችዉን አስነክተዉኝ ወ.ዘ.ተ እያሉ አጉል ጥርጣሬ ከማብዛት በራስ ችግር አንዳንዴ ራሳችንን በዚህ ጉዳይ ባናሳምን ጥሩ ነዉ፡፡

☑️ ብዙ የመፅሀፍ ሰወች ድግምትን በሰፊው ተምረውታል አብዛሀኛው ያውቁታል ድግምት ለፈተና የመጣ ሰወችን ከአላማቸው የሚያስት ህመም የሚያወርስ ብሎም ሲከፋ እስከሞት የሚወስድ ከባድ ስቃይ ነው፡፡  የድግምት አድራጊወች የማድረጋቸው ምክንያት ደግሞ አላህ እንደሚለው{ {ከሰወች ከራሳቸው የመነጨ ምቀኝነት ነው ይለናል}}

ያ ማለት ሰወች
☞ለምን ተፈጠርክ ጀምሮ
☞ ለምን አማረብህ ለምን አገኝህ
☞ለምን አወክ
☞ለምን ከኔ በለጥክ
በማለት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በመመለከት ሌላኛው አካል እንዳይበልጠን በማለት በንፁህ ሰው ላይ የሚተበትቡት ከአላህ በስተቀር ማንም የማያውቀውና የማይፈታው ሰይጣናዊ ወይንም ጅናዊ ኮድ ነው

☑️ ድግምት በተለያዩ ነገር እንደደረጃው ሊደረግ ይችላል
>>  በምግብ
>>  በመጠጥ
>>በመንካት
>> ቋጠሮ በማስቀመጥ
>> በማየት
እና በተለያዩ ነገሮች ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡


ሰውየው ድግምቱን ሲያስደርገው ለደጋሚው እንደሚያቀርበው ክፍያና የድግምት ደረጃ አድራጊው ከአስደራጊ በመቀበል ለጅኑ በሚያቀርብለት የሽርክ መስዋት ግብር ልክ ነው ፡፡ በአመቱ ሲያሳድሱት ከመጀመሪያው የተሻለ  ሌላ ግብር ያስቀምጣሉ፡፡
ማወቅ ያለብን አንዴ በእኛ ላይ ካደረጉብን ማሳደሱ ቀላል ነዉ ...በመንካት / የምትሄድበት ላይ በማድረግ/ ስራ ቦታ ወይም ትቤት ላይ/ የምበላዉ ምግብ/ወይም በተቀመክበት ወይ በልብስህ/ message በመላክ በፁሁፍ መልክ/ ስልክ በመደወል/ ስጦታ የሰጡ በማስመሰል ወዘተ ሊያድሱ ይችላሉ ማሳደሱ ቀላል ነዉ....ከባዱ መጀመሪያ ሳሂሩ ጠንቋየ ጂኑን ወደ ሚደረገበት ሰዉ ሲላክ በሰዉነቱ ዉስጥ ለመግባት የሚያደርገዉ ጥረት ነዉ የሚከብደዉ...ሰዉየዉ በዚክር በቁርአን በዉዱዕ የሚንቀሳቀስ ከሆነ የተላከዉ ጂን በጣጣም ከባድ ይሆንበታል እናም አሁንም አደራ!!! ከአላህየ ጋር ያለን ግንኙነት እንዳይላላ፡፡

➡️ ሰወች ሰው እንዳይበልጠን በማለት
➡️ ሴት ልጅን ለመቆጣጠር ወይም
➡️ ለሪዝቅና ለተተለያዩ ነገሮች ይሄን የፈተና መንገድ ልጅን ግብር በማቅረብ በአላህ በመካድ ሰይጣናዊን ተግባር ረክሰው ጠንቋይ ቤት ሂደዉ በማስደረግ ንፁሀኖችን ይጎዱበታ ያሰቃዩበታል ቶሎ ካልታወቀ እስከ እብደት ሞት ድረስ ሊዳርግ ይችላል፡፡

  ግፋ ሲል የሰውየውን ነሲብ ትከሻ በኮኮብ ቆጠራ በተወለደበት ወር ጨረቃ በማገናኝት የንፁሁን ሰው እድል ወደ ድግምት አስደራጊው እንገለብጣለን የሚል ሀሳብ አላቸው

🟢  አንዳንዱ ደግሞ ከዚህም ሲከፋ ሰውየውን በመግደል የሱን እድሜ እኔ እኖራለሁ በማለት ትልቅ የሽርክ አዘቅት ወንጀል ውስጥ ይዘፈቃሉ


☞ ድግምት ማስደረግም ማድረግም ደጋሚን ሄዶ መጠየቅም ያከፍራል ምክንያቱ ነቢዩ ሰ ዐ ወ አዋቂ ነኝ ብሎ የሚልን ደጋሚ አካል ጋር እሱ ዘንድ የሄደ ሰው በእርግጥ ክዷል ከፍሯል ብለዋል።

የተለያዩ ደግሚወች እንደሚናገሩት ደጋሚወች ማንንም አካል በድግምት ማጥቃት ይችላሉ የሚያቅታቸው ለሀይማኖቱ ቅርብ የሆነን ሰው ብቻ ነው

ሀይማኖተኛ ሰው ላይ ለማድረግ ሲሞክሩ አላህ ድግምታቸውን በሰውየው ተቅዋ ልክ ያስቀይሳቸዋል  ያፈስድለታል ፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ድግምቱ ይዞት በእሩቃ ይለቃል፡፡ ይሄንን ያልባነኑ ሰዎች ስሙ አዲስ በተሰየመ ህመም በህክምና ቆይተው ህይወታቸዉ ያልፋል፡፡ አንዳንዴ ደም ግፊት / የማህፀን ካንሰር /ኩሊሊት ጉበት /ደም ማዘል ፓላራይዝ ማድረግ ወዘተ በሰዉየዉ ላይ የተደረገበት ድግምት ሊሆን ይችላል...ለምሳሌ እኔ በቅርቡ የገጠመኝ የጓደኛየ እናት የማህፀን ካንሰር ተብለዉ በአስቸኳይ በ10ቀን ዉስጥ መሰራት አለባቸዉ ይሞታሉ ተብለዉ አረ ይሄ ነገር ብለን ወደ ሩቃ ወሰድናቸዉ ሲቀራ በሶስተኛዉ ቀን ሲህር ጂን እና የታመመችዉ ሴትዮ ከልጆቻቸዉ እየተደበቁ ገጠር ዘመድ ልጠይቅ እያሉ ለጂን በየአመቱ ያርዱ ነበር ዘንድሮ ስላላረዱ ማህፀናቸዉን እየወጉ ካንሰር እንዳስባሉ ጂነዉ ተናገረ ከዛ በ2ወር ሩቃ ክትትል የሚገበርላቸዉ ራሄሎ ጨገር አንበሴ ነጬ በላ ጥቁር በላ አረ በጣም ብዙ ናቸዉ
በቁርአን ሀይል ሁሉም ለቀቁ ከለቀቃቸዉ ቡሀላ ቸክ ሲደረጉ የማህፀን ካንሰር እንደማያሳይ አረጋግጠናል በአይኔ ያየሁት ነዉ፡፡

ደም ግፊት መድሀኒት የምትወስድ ሴት ታማ ሩቃ ገባች መድሀኒቱን አቆመች ከዛ በሩቃ ክትትል ጂኑ ሲለቅ ሀኪም ቤት ቼክ ስትደረግ ደም ግፊት አለመኖሩን አረጋግጣለች፡፡
እኛ ስንታመም ኢማናችን የቀጠነ ስለሆነ የምንሄደዉ ሀኪም ቤት ነዉ ግን በቁርአን በእጃችን መፍትሄ እንዳለ ዘንግተናል፡፡ ወላሂ ጂኖቹ ሲናገሩ ሀኪም ቤት እኛ ነን ያለነዉ የምናስታምማቸዉ ይላሉ...
ግን እንደዚህ ስል ሀኪም ቤት አትሂዱ ሳይሆን የምንሄድበትን ህክምና መለየት አለብን፡፡ ሀኪም ቤት ብዙ አመታት ተመላልሶ ግን በሩቃ ህመማቸዉን ሲፈወሱ እያየን ነዉ፡፡
ብዙ ማለት ይቻል ነበር ለማመን የሚከብዱ ነገሮች
ግን ለማመን የሚከብዱ ነገሮችን ብናገር ሰዉ ይዘናጋል
መልሶ ሸክ እንዳይፈጥር አለመናገሩ ኸይር ነዉ እንጂ
ብዙ ከባድ በሽታዎች ሀኪም ቤት በተወሰኑ ቀናት በየወሩ የሚያመላልሱ እስከ መተኛት የሚያደርሱ...አንዳንድ ከባድ ለሞት ያደርሳል የሚባሉ በሽታዎች ጂን ሲህር ጋር የተያያዙ ሊሆኑ ይችላሉና ቁርአንን በንጠቀምበት መፍትሄ እንደሆነ ባንዘነጋ ኸይር ነዉ፡፡

#ክፍል 2⃣
ይቀጥላል.....


አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇

T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ

            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
          
                 ⭐️ #ክፍል👉 ሁለት 2⃣


  አሁን ባለዉ ተጨባጭ ብዙሀኑ ሰው በሚባል መልኩ አሁን ላይ ድግምትን እንድ normal አድርገው ነው የሚጠቀሙት...እነሸህ ጋር ትልቅ ሰዉ ጋር ወልዮች ጋር እንሂድ እየተባለ ሳያቁት በማወቅም ባለማወቅም እየሄዱ ነዉ ..በማወቅም ባለማወቅም ጤነኛን ሰዉ እያጀዘቡ ይገኛሉ

#ለምሳሌ :- በጀመርኩት ጓደኝነት የፍቅር  ጥያቄየን አትቀበለኝ ይሆናል እንዳታሳፍረኝ  ብለው የፈሩ ወንዶች ድግምት አሰርተዉ ሴቶችን በድግምት እሱን እንድትወደዉ አድርገዉ የፈለጉት የብልግና ስራ ሲሰሩ ይታያሉ፡፡  የጨዋ ሰው ባህሪ በድንምት ይቀየራል ያ ሰው ምን ነካው?? ጥሩ አልነበረንዴ?? እስከሚባል ድረስ
☞የክፋት ጥግ የሚያሳይ ወንድ
☞ የብልግና ጥግ የምታሳይ ሴት ልጅ
☞ራሳቸዉን ስተዉ ለእብደት የሚጋለጡ ሰወች
☞አላህ የሰጣቸውን ሪዝቅ የተበታተነባቸው
☞ ራስን ለመቻል ሲጥሩ ስኬት የራቃቸው
የድግምት(ሲህር) ተጎጅዎች ብዙ ናቸው ብንል ማጋነን አይሆንም

   ታዲያ ይሄ ድግምት ለዚህም ለወዳኛው አለም ታላቁ ሰው ነብዩ ሙሀመድ ካልቀረላቸው በእኛ በኖርማሎቹ ሰወችማ እንዴት ነፃ ልንሆን እንችላለን ??ነቢዩ ሙሀመድንኮ ያዛቸውና እርሳና ላከባቸው ነገሮችን እየደጋገሙ ሲሰሩት ማስታወስ እስከማይችሉ ድረስ በየሁዳ ድግምት ተሰቃዩ መቸም የነሱ ችግር  ይዞ የሚመጣው እስከ ኡመቶቻቸው ሁሉ ነው፡፡ አላህ በህማቸው ድግምቱ የተደረገባቸውን ቦታ በመላኢኮች አማካኝነት የ ጠቆሟቸው... የነቢይ ህልም እውን ነውና እዚያ ቦታ ሂደዉ  ቆፍረው አወጡት ውሀ አፈሰሱበት ከዚያ መፈወሻ ይሆን ዘንድ የቁርአን አንቀፆችን አወረደላቸው  እንደዋናነት ለሩቃ ከሚቀሩ አንቀጾች መክቅክል ሱረሩ ኢኽላስና ሙአወዘተይ ናቸው  ለዚህም ነው አላህ

በሱረቱሩል ኢክላስ  ውስጥ እንዲህ የሚለው
{{ በል እርሱ አላህ አንድ ነው  እርሱ አላህ የሁሉ መጠጊያ ነው  አልወለደም አልተወለደም  ለእርሱ ለአላህ አንድም ቢጤ አምሳያ የለውም።  ይለናል

    በዚህ የቁርዐን አንቀፅ ውስጥ ጅኖች በብዙ መልዕክት ተብትበው እና ቋጥረው ገብረው ሰውን አስገብረው ያደረጉትን ድግምት በብቸኛውን አንዱ አላህ ስም ሊፈታ ዘንድ ይህ የቁርዐን አንቀጽ የወረደው
እንዲሁም በሱርውረቱል ፈለቅ ላይ እንዲህ ይለናል

#በል በፈለቅ ጌታ ጠበቃለሁ ንጋትን ከጨለማ ፈልቅቆ የሚያወጣ ማለት ነው
ከፈጠረው ተንኮል ሁሉ( ተንኮልና ድግምት አጠቃላይ መጥፎ ነገር የተፈጠረው ለፈተና ነው)
ለይሉ ድቅድቅ ብሎ በጨለመ ጊዜ የሚመጣን ተንኮል በአንተ ጠበቃለሁ በል

በክር የቆጣጠሩና የተፋፉ ከሚደግሙ ሴት ድግምተኞች በአንተ እጠበቃለሁ በል
የሚመቀኝው በተመቀኝ ጊዜም ያለን ተንኮል በአንተ እጠበቃለሁ በል ።

#የሰው_ልጅ ወደዚህ አለም ሲመጣ ብዙ አይነት ባህሪ አመንጭ ሆርሞኖች ይኖሩታል
🔸 የሚቀና መንፈስ
🔹 የሚመቀኝ መንፈስ
🔸 የሚወሰውስ መንፈስ
🔹መልካም የሚያስብበት መንፈስ
🔸 መጥፎ የሚያስብ መንፈስ እና ሌሎችም መንፈሶች አሉት፡፡ ታዲያ ሰወች የተንኮል አስተሳሰባቸውን መቆጣጠር ሲያቅታቸው
☞ሸራቸውን ተንኮላቸዉን መርጨት ይጀምራሉ
☞ይመቀኛሉ ይቀናሉ
☞ ጉዳትን ያደርሳሉ
☞ ድግምትን ይሰራሉ የነዚያን ተንኮል ሁሉ እንድንጠበቅ ዘንድ አላህ ይሄንን አያት አውርዶልናል

ሶስተኛዉ አንቀፅ አናስ ነው የሰወች ምዕራፍ ማለት ሲሆን

በሰወች ተንከባካቢ በሆነው አምላካቸው(አላህ) እጠበቃለሁ በል
የሰወች ንጉስ በሆነው አላህ ጠበቃለሁ በል
ሰወች የሚያመልኩት አምላክ በሆነው አላህ ጠበቃለሁ በል (ከምን) ?
☞ ብቅ ጥልቅ በማለት የተመላለሰ ከሚወሰውስ ጎትጓች ተንኮል

ያ በሰወች ልብ ውስጥ ጎትጓች ኮሆነ ተንኮል ። ማነው ጎትጓቹ አካል ካልን?
☞ ከሰወችና ከጅኖች ወስዋሽ ጎትጓች አሳሳቾች።

    ይህኛው አንቀፅ ደግሞ መግቢያውን ሀያል በሆነ የአላህ ስራና ባህሪ ከገለፀ በኋላ ከሰወች እና ከጅኖች ውስወሳ ተንኮል ብእሱ እንድንጠበቅ ይነግረናል የአላህ መልዕክተኛም እነዚህን አንቀፆች ደጋግመው ሲቀሩ ነበር የድግምቱ ስሜት ሙሉ በሙሉ የለቀቃቸው

እንደዚሁም ሌላው ትልቁ የሲህርና ጅኖች መጠበቂያ የሆነው አንቀፅ አያተል ኩርሲ ነው አያተል ኩርሲ የአላህን ፍፁምነት የሚገልፅ አንቀፅ ስለሆነ አንድ ሰው እሱን ቀርቶ ከቻለ ውዱዕ አድርጎ( ባያደርግም )ከተንቀሳቀሰ ምንም አይነት ነገር አይጎዳውም
ማታ ሲተኛ ቢያነበው ሰይጣንም ይሁን ጅን አይቀርቡትም ቢቀርቡትም እንኳን እሱን የመጉዳት አቅም ይነፈጋሉ በዚያው አጀሉ ደርሶ ቢሞት ደግሞ አላህ ጀነትን ይወፍቀዋል

       ሌላው ራስን ከእንደዚህ አይነት አደጋ ሊጠብቅ ሰበብ የሚሆነው ውዱዕ አድርጎ መንቀሳቀስ ነው ውዱዕ ማድረግ ሰይፍን ስሎ ወይንም በጣም ተጠንቅቆ እንደመሄድ ስለሚቆጠር ማንም ድግምት አድራጊ ለማድረግ ቢሞክር የውዱዑ በረካ ሰውየውን እንዳይጎዳው አላህ ሰበብ ያደርግለታል

🟢 እንዲሁም ሰወች መጥፎ ስሜት ሲሰማቸው ፍዘት ድብርትና የተለያዩ ነገሮች ድንገት ሲመጡባቸው ውዱዕ እንዲያደርጉ ይመከራል በቶሎ ከዚያ ስሜት ያወጣቸዋል፡፡ ከውዱኡ ጋር ሳይለያይ የሚመጣው ጉዳይ ደግሞ ሲዋክን ማዘውተር ነው ሲዋክ መጠቀም ጅንና ሰይጣንን ያርቃል ንፅህናውን ጠብቆ ንፁህ አፍ የያዘ ሰው በሲህር ተንኮል የመጠቃት ሀይል የለውም

መተት ሲህር መኖሩን ማረጋገጫ ከነብዩ ሰዐወ ህይወት ጀባ ልበላችሁ፡፡
    ዓኢሻ (ረዐ) እንዲህ ብለዋል፡- በኒ ዘረይዎ ከሚባል ጎሳ የተወለደ ለቢድ ኢብን አል አሪሶም የተባለ ሰው በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ደገመባቸው፡፡ በመተቱ ሳቢያ አንድን ነገር ሳይሰሩት የሰሩት ይመስላቸው ነበር
አንድ ቀን እኔ ቤት ሆነው ሳለ አላህን (ሱ.ወ) በጣም ለመነና እንዲህ አሉኝ፡ ዓኢሻ ሆይ! ስለለመንኩት ጉዳይ አላህ ልመናዬን እንደተቀበለኝ ታውቂያለሽን? ሁለት መላኢኮች ወደ እኔ መጡ፤ እንዱ በራሴ በኩል ተቀመጠ፡፡ ሌላኛዉ በእግሬ በኩል ተቀመጠ፡፡ ከዚያም አንዱ ለሌላኛው እንዲህ አሉ፡- "የዚህ ሰውዬ : ህመም ምንድን ነዉ? ሌላኛውም፦ “ተደግሞበት ነው አለ፡፡ የመጀመሪያዉም፡-ማን ነዉ የደገመበት?' ሲል ጠየቀ:: ያኛዉም፡- ለቢድ ኢብን አዕሶም የተባለ ሰው ነው መለሰለት፡፡ የመጀመሪያዉም፡- ሲል "በምንድን ነዉ (መተቱ) የተሰራዉ? ሲል ጠየቀ፡፡ ያኛዉም፡- በማበጠሪያ፣ ማበጠሪያው ላይ ባለዉ ጸጉራቸዉ እና በወንዴ የተምር ፍሬ ገለባ' ሲል መለሰ::

የመጀመሪያዉም (መተቱ) የት ነዉ ያለዉ?' ሲል ጠየቀ፡፡ ሌላኛዉም፡- ዝርዋን በምትባል  የውሀ ጉድጓድ ዉስጥ ሲል መለሰለት፡፡ ከዚያም ነቢዩ (ሲዐ.ወ) ከጥቂት ባልደረቦቻቸዉ ጋር ሆነዉ ወደ ጉድጓዳ ሄደው ሲመለሱ እንዲህ አሉኝ “የጉድጓዱ ውሀ ልክ እንደተዘፈዘፈ የሂና ቅጠል (ደም) የመሰለ ነው። የቴምር ዛፏ አናቶች ደግሞ የሰይጣናት ራስ መስለዋል አስቀያሚ ናቸው:: እኔም፡- “(ድግምቱን) አታስወጡትም ነበር? አሰኳቸው፡፡ እሳቸዉም፤- በርግጥም አላህ አድኖኛል፡፡ በሰዎች ዉስጥ ተንኮል አንዲስሩሩ አልፈልግም አሉ ፡፡›› (ቡኻሪ ዘግበዉታል)👇👇
🔰 #ከሀዲሱ_የምንረዳዉ
ይሁዲዎች ለቢድ ከሚባል የመተተኞች ቁንጮ ከሆነ ሰው ጋር ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ እንዲደግምባቸው እና ለዚህም ተግባሩ ሶስት ዲናር ሊከፍሉት ይስማሙሉ፡፡ ከዚያም ይህ መተተኛ በነቢዩ (ሰዐወ) የፀጉር ቁራጭ ላይ ድግምት ደገመ፡፡ ይህንን ፀጉር ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቤት ትመላለስ ከነበረች አንዲት ትንሽ ልጅ እንዳገኘዉ ይነገራል፡፡ ከዚያም በፀጉሩ ላይ መተት በመቋጠር ዘርዋን በምትባል የዉሀ ጉድጓድ ዉስጥ ቀበረ።

#ከሐዲሱ_የምንገነዘበው አይሁዶች በጣም አደገኛ የሆነ ድግምት በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ እንዳሰሩባቸዉ ነው፡፡ ዓላማቸውም ነቢዩን ሰዐወ ለመግደል ነበር፡፡ የሚገድል ድግምት እንዳለ የሚታወቅ ነው፡፡ ነገር ግን ከአይሁዶች ተንኮል አላህ ስለጠበቃቸው ይህን ገዳይ ድግምት ቀላል ወደ ሆነው የድግምት ዓይነት አቀለለላቸው፡፡


📚📚 ዒምራን ኢብን ሁሰይን (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል። ‹‹ድግምት የተነበየ ወይም ያስተነበያ የጠነቆለ ወይም ያስጠነቆለ : ድግምት የሠራ ወይም ያሠራ ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ የሚስቡን ያመነ በነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ በወረደው  ቁርአን ክዷል፡፡›› (አል በዛር ዘግበውታል፡፡)

በሸሪአዉ ደጋሚ ጠንቋይ ሰዉ ለተዉበት ጊዜ ሳይሰጠዉ  ፍርዱ ሞት ብቻ ነዉ፡፡ እናም ፍርዱ ሞት የሆነ ጋር እንዴት ሂደን የሰዉ ህይወት እናበላሻለን፡፡

📚📚 አቡ ሙሳ አል አሽዐሪይ ረዐ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ሰዐወ እንደዚህ ብለዋል
➊የመጠጥ ሱሰኛ
➋በድግምት (በመተት) የሚያምን እና
➌ ዘምድናን ቀራጭ እነዚህ ሶስቱ ጀነት አይገቡም፡፡ (ኢብን ሃባን ዘገበዉታል)

📚📚 ኢብን መስዑድ (ረዐ) እንዲህ ብለዋል፡- “ትንቢት ተናጋሪ፣ ጠንቋይ ወይም ደብተራ ዘንድ ሄዶ የሚለዉን ያመነ በሙሀመድ ላይ በወረደዉ በቁርአን በርግጥ ክዷል። (አል-በዛር እና አቡ-የዕላ ዘግበዉታል)

📒 ኢብን ቀዳማ የኢስላም ሙህራን እንዲህ ብለዋል፦ አስማት (መተት) ተጨባጭነት አለው፡፡
☞ ሊገድል የሚችል፤
☞የሚያሳምም፣
☞ ባል ሚስቱን እንዳይገናኝ የሚያደርግ፣
☞ተጋቢዎችን የሚለያይ የአስማት (መተት) ዓይነት አለ። ለዚህም አንድ በሰፊው የታወቀን ሀቅ መጥቀስ ይቻላል። ይኸውም አንድ ሰዉ 'ድግምት ስለተደረገበት በጋብቻው እለት ሙሽራይቱን መገናኘት ይሳነዋል፡፡ ከዚያም ድግምቱ እንዲፈታ ሲደረግ መገነት ይችላል፡፡ ይህ ዓይነት ክስተት ደግሞ በየትውልዱ የታወቀና ሊካድ የማይችል ሀቅ ነው። ብለዋል
   እናም መተት የለም ማለት ስህተት የሆነ አስተሳሰብ ነዉ፡፡

📚📚📚 አንዳንዴ ግን ሲህርና ጂንን መለየት አለብን፡፡ ጂን ራሱ በኛ መዘናጋት በኛ በመቅናት በተዘናጋንበት ጊዜ ሊይዘን ይችላል፡፡
ለምሳሌ
☞ ሽንት ቤት ስንገባ ሽንት ቤት የመግቢያ ዚክር ካላደረግን
☞ሴቶች በሀይድ ወይም በኒፋስ ጊዜ ከሶላት ከፆም ስለሚከለከሉ በዛ ጊዜ ያለዉን የመዘናጊያ ክፍተት ተጠቅሞ
☞ በቆሻሻ ቦታ ስንሂድ
☞ ብቻችንን ሁነን ሀሳብ መናደድ ስናበዛ
☞ በአንተ ባህሪ መልክ ፀባይ ጂኑ ሲቀና ወይም ከቀናብሽ
☞ በቃ አይታወቀም ጂን የሚይዝበት ምክንያት  ሊይዘን ይችላል

ጂን በተለያየ ምክንያት ይይዘናል፡፡ በተጨማሪ ደግሞ በድግምተኞች በሳሂሮች በመተተኞች በጠንቋዮች በደብተራዎች ወደ ሰዉ ልጅ ይላካሉ፡፡
ከላይ በጠቀስናቸዉ የሚላከዉ ጂን ተገብሮለት ደም ተደምቶለት ታዞ ስለሆነ በጣም ከባድ ነዉ፡፡
⚠️ማወቅ ያለብን ጠንቋይ ወይ ደብተራ ወይ ሳሂር ቤት ሂደን ግብር ወይ ብር ከፍለን በሰዉ ልጅ የምንፈልገዉ እንዲሆን ብለን ብናስደግም የተደገመበት ሰዉ በኢማኑ ጠንካራ ሁኖ በሩቃ በራስም በሌላም ታክሞ ቢሻለዉ ወደ አደረገዉ ሰዉ ጅኑ ይመለስና
ሰላም ይነሰዋል
እንቅልፍ ያሳጠዋል
ወይ በእሱ ወይ በልጁ ወይ በሚስቱ ህመም
ወይ በሚሰራዉ ስራ እርዚቁ ሲበላሽ
ወይ ከቤተሰብ አንዱ በከባድ ይታመማል እስከ ፓላራይዝ ድረስ ያደርጋል
ወዘተ 100% እርግጥ ነዉ ግልባጩ ከባድ ነዉ ለምን ጂን ሳሂሩ ሰዉየዉን እንዲጎዳ ሲልከዉ ሳይስማማ ነዉ በግድ በስንት ድካም ወደ ሰዉየዉ የሚገባዉ ሲወጣ እልክ ይይዘዋል ጂኑ ያደረገዉን ያጠቀዋል፡፡



✏️✏️ #የጅን_ጥቃት_በሴቶች_ላይ_ምልክቶቹ

ብቻሽን መሆን የምትፈልጊ ከሆነና ሀሳብሽ በሙሉ ከሰው ለመገለል ከሆነ እራስሽን ጠይቂ፡፡

የወሲብ ፍላጎት ከፍተኛ መሆን እና እራስን መንካት፡፡ በተቃራኒው ከባለቤትሽ ጋር ግንኙነትን እጅግ በጣም መጥላት

ምሽትና ቀን ማልቀስ ምክንያቱን በቅጡ በማታውቂው ምክንያቶች እምባ በእምባ መሆን ሆድ መባስ፡፡ ይከፋሻል ምክንያቱን ግን አታውቂውም።

ድብርት መሰማት ይህ ድብርት ጥዋት ላይ ይከፋል ሰው ወገግ እያየለለት ሲሄድ ባንቺ ላይ እየጨለመ ይመጣል።

የፔሬድ መብዛት:-ፔሬድ ከ5-8 ቀን በኖርማል ሁኔታ ሊፈስ ይችላል ፡፡ በጂን ልክፍት ግን 30 እና 45 ቀን የፔሬድ ደም ሶስት ቀን እረፍት ሊኖር ይችላል፡፡ ይህም እንደ ጥቃቱ ይለያያል፡፡ የጥቃቱ ሀይለኝነት የፔሬዱን ብዛት ይወስናል፡፡ ዝቅተኛ ጥቃት መጠነኛ የፔሬድ መብዛት ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ ከፍተኛ የፔሬድ መብዛት ይኖረዋል፡፡

ፍራቻ መሰማት፡- ማታ ሲመሽ ከመጠን በላይ መፍራትና የልብ ምት መጨመር፡፡ የሚሞቱ ያክል ፍራቻ መሰማት፡፡ መተንፈስ እንኳ እስኪጨንቅሽ።

ለሰው የማይታየው ለሷ ብቻ የሚታያት ምልክቶች መኖር፡፡ እነኛም 100 በ100 ልክ ናቸው፡፡ ከሰፈር ውስጥ ማን እንደሚሞት እንደሚታመም እንዲሁም የሚደረጉ ሁናቴዎች ለርሷ ግልፅ ባለ መልኩ ይታያታል፡፡ ይህ ግን ፈፅሞ በእውነታ ላይ የተመሰረተ ውሸት ነው፡፡ ይህን ሸይጧንም ያመሳስላል፡፡

ከጓደኞችሽ ጋር በሆነው ባልሆነው መጣላት... ሰላም ማጣት ብሎም ሳምንቱን ሙሉ መጥፎ ወሬዎችን መስማት፡፡ 

እጅግ በጣም ተናዳጅ መሆን ሰው ጥሩ እያወራሽ አንቺ ቱግ ማለት። ጥሩ እያሰቡልሽ እንደ ጠላት መቁጠር ሰው አለማመን አደለም ይሁንና እስከመንቀጥቀጥ የሚያደርስ ንዴት።

ውሸታምነት :- አዎ እጅግ ሲበዛ ውሸታም ነገር አሳባቂ መሆን ። ውሸቱን ወደሽ አደለም ምትዋሺው የሚያስገድድሽ ነገር አለ።

➊➊ ከልክ ያለፈ ቅናት ምቀኝነት፡- የምታውቂያቸው ሰዎች ካንቺ በታች ሁነው እንዲንፈራፈሩ ትሻለሽ። የነገራቶች ፈጣሪ ሰው ስላንቺ እንዲያወራ ብቻ ትፈልግያለሽ። ያ ሰው ጥቅም እንዲያገኝ አትፈልጊም ቢያገኝም ካንቺ ካልሆነ ያንገበግብሻል።

➊➋ ሙእሚኖችን በአሏህ መንገድ ላይ የሚሰሩ ሰዎችን መጥላት :-  ይህም ከልብሽ ብትበቀያቸው ደስታሽ ነው። ሲያወሩ ወሬያቸው አይጥምሽም ቢመክሩ ምክራቸው አይዋጥልሽም። ሳታውቂያቸው መጥላት።

➊➌ ሰላት ላይ መቆም ሞት መስሎ ይታይሻል። ረመዳን ካልመጣ በቀርም ሰላት የለም።

➊➍ አስመሳይ ገፀ ባህሪ እንዲኖርሽ ያደርጋል:- የማትወጂውን መውደድ መምሰል የምትወጂውን ጠይ መምሰል በጥቅሉ የሰውን ህሳቤ ወዳንቺ መጎተት ትፈልግያለሽ። ይህ ከዚህ በፊት የሌለ ባህሪ ነው።

በዚህ ግዜ የሚደረግ ሩቃ እጅግ ጥበብ በተሞላባቸውና ከላይ የተጠቀሱት አንድ ሴት ልጅ ጂን ሲይዛት ከሚታይባት ባህሪ ናቸዉ

#መተት_አስማት በቀጣይ ክፍል 3⃣
ይቀጥላል.....

4 any Comment👇👇

T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ

            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
          
                 ⭐️ #ክፍል 👉 ሶስት 3⃣

🔰🔰 #መተትና_አስማት ምንድን ነዉ


መተት መተት አስማት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸዉ ናቸዉ፡፡

ሻሚር እመት አኢሻን ጠቅሰዉ እንደተናገሩት ዓረቦች መተት... መተት ያሉበት ምክንያት ጤናን ከልክሎ ህመም በማስከተሉ ነዉ፡፡
   
መተት በእስልምና ህግ ኢብን ቁዳማ አል ሚቅዲስ የተባሉ ሙሁር እንዲህ ብለዋል፡፡
#መተት ማለት
✏️የሚቋጠር
✏️ የሚደገም ወይም የሚነበብ
✏️ የሚፃፍ ትብተባ
✏️ በተሰራበት ሰዉ ሰዉነት ልብ ወይም አእምሮ ላይ ያለ አንዳች ንክኪ ተፅእኖ እንዲፈጥር ጉዳት እንዲያስከትል የሚሰራ ስራ ነው

መተት ተጨባጭ እዉነታ አለዉ ይህም
☞የሚገድል
☞ህመም የሚያስከትል
☞በባል ላይ ስንፈተ ወሲብ በመፍጠር ሚስቱን ከመገናኘት የሚያግድ
☞ባልና ሚስትን በፍች የሚለያይ
☞ወይም እርስ በርሳቸዉ እንዳይስማሙ የሚያደርግ
☞ሁለት ሰዎችን የሚያፋቅር ሊሆን ይችላል፡፡

📚📚#የሲህር_የመተት_ምልክቶች

🔻የገዛ ማንነትን መጥላት
🔺 በሰውነት ውስጥ የሚሄድ የሚርመሰመስ ነገር መሰማት።
🔻 ከመግሪብ ቡሀላ ወይም ከአሱር ቡሀላ እጅግ ፍርሀት ስሜት መሰማት
🔺 ቁርአን ሲቀሩ የአይን ማቃጠል የራስ ምታት ጩህ ጩህ ማለት።
🔻 ከመጠን ያለፈ ድብርት በተለይ ጥዋት ላይ።
🔺 ሚስት ባልን ባል ሚስትን መጥላት.. ሲገናኙ መጣላት ሲለያዩ መነፋፈቅ።
🔻 የእንቅልው ማጣት .. ለሊት ሰው ሲተኛ አለመተኛት ቀን ላይ አጉል ሰአት ተኝቶ መነሳት።
🔺 ሽንትቤት ብዙ ሰአት መቀመጥ።
🔻 ከሰው መራቅ..ለመራቅ መሞከር
🔺 ስንፈተ ወሲብ... ለወንድ የብልት አለመቆም... ከቆመም ቶሎ የመርጨት ችግር።
🔻 የጨጓራ ህመም ምልክት ሶስት ቀን ሰላም ከሆኑ በቀጣይ ቀን መታመም።
🔺 ገንዘብ ደሞዝ ሀብት አለመበርከት ..ብኩን መሆን።
🔻 ስራና ትምህርት ላይ መስነፍ
🔺 ከሰው ጋር አለመግባባት እና ሁሉም ሰው ስለኔ ነው የሚያወራው ብሎ ማሰብ።
🔻 ለነገራቶች ሰነፍ መሆን
🔺 ከአልጋ መነሳት መጥላት
🔻 የሰውነት አለመታዘዝ ፓራላይዝ
🔺 ትውከት  በጣም የሚሸት ግኡዝ ነገር ማስታወክ።
🔻 ፔሬድ መብዛት
🔺 ከአግባብ ያለፈ ድፍረት አልያም ከአግባብ በላይ የሆነ ፍርሀት መኖር እነኚህ ጠቋሚ ምልከታዎች ናቸው
🔻 ትሰራለህ ትደክማለህ ያስቀመጥከው ገንዘብ ያልቃል እንጂ የሚጨምር ነገር የለም፡፡ በህይወትህ ውስጥ ደስታም የለም፡፡
🔺 የምትወደውን ለመቅረብ ትቸገራለህ ብዙውን ግዜ ከጠላቶችህ ጋር ትወዳጃለህ፡፡ ኋላም በያንዳንዳቸው ጉዳት መጎዳት ይኖራል፡፡
🔻 የፀጉር መመለጥ:- ይህ ከሌሎች ምክንያቶች ጋር ሊያያዙ ይችላሉ ይሁንና እነኚህ የሲህር ምልክቶች ውስጥ የሚያዝበት ዋነኛ ምክንያት አንድ ሰው በሲህር ሲጠቃ ወንድም ይሁን ሴት የፀጉር መነጨት ይገጥማል፡፡ በቶሎም ራሰበርሀ ወይም መመለጥ ይኖራል፡፡

🔺 አዛን በሚሰማበት ወቅት ይጨናነቃል ይፈራል፡፡ ጩህ ጩህ የሚለው ከሆነ ደግሞ የጅኑን መዳበር አመላካች

  🟢 አስጨናቂና አጣብቂኝ ሲህሮች መለያ ምልክቶቸቸው!!
ከዶ/ር አቡ ፈርሃን ጥናታዊ መጣጥፍ ላይ የተወሰደ፡፡ 


#የፀጉር_መነቃቀል_መላጣ_እስከመሆን፡- ይህ በቀልድ ነው የሚጀምረው፡፡ በተለይ ወንዶች ላይ እጃቸውን ወደ ፀጉራቸው ልከው መዘዝ ሲያደርጉ አሸን የሆኑ ፀጉሮችን ይዘው ይወጣሉ፡፡ ይሁንና ይህ የራሰበራነት እድሜ ላይ ከደረስክ አልያም እድሜ ከ 32-45 ቶች ውስጥ ከሆንክ ይህ ሌላ ትርጓሜ ሊኖረው ይችላል፡፡ ሴቶች ደግሞ ገና ፀጉራቸውን ከመንካታቸው ተሰባብሮ ያልቃል፡፡ ብን ብሎ ይነሳል፡፡ አሻንጉሊት ላይ እዳሉ ፀጉሮች በጣም ስስና ባዶ እስኪሆኑ ድረስ ከሲህሩ ጋር አብሮ ይጓዛል፡፡ 

#ከሰገራ_ጋር_የትሎች_መብዛት፡- ይህ የኮሶ ትልን ይጨምራል፡፡ እነኚህ ታማሚዎች ምንም እንኳ ከጥሬ ስጋና ኮሶን ከሚያመጡ ነገሮች  እራሳቸውን ቢጠብቁ እንኳ በኮሶ ትል መጠቃታቸው አይቀሬ ነው፡፡ በወስፋት ትልም እንዲሁ፡፡ ብቻ ከሆዳቸው ስር በሳምንት ውስጥ ትል ሳይወጣ አይቀርም፡፡ ምንም ያህል መድሃኒት ቢጠቀሙ ምንም ያህል ህክምና ቢያደርጉ ጅኑ እስካለቀቀ ድረስ ንፁህ አይሆኑም፡፡

#በአላህ_ላይ_አማራሪ_መሆን፡- አላህ ሀብት ሰጥቷቸዋል ግና የሰውን ተመልክተው ያማርራሉ፡፡ አላህ ልጅ ሰጥቷቸዋል ግና በልጆቻቸው አማራሪ ናቸው፡፡ አሏህ አመለሸጋ ሚስት ሰጥቷቸዋል፡፡ በሚስቶቻቸው ላይ አለቃቃሽ ናቸው፡፡ ምንም ነገር አያረካቸውም፡፡ ሰማይ የተፈጠረው እነርሱን ለማጨናነቅ እስኪመስላቸው ድረስ ውሀ ቀጠነ ብለው ማማረር ስራቸው ነው፡፡

#አስቸጋሪ_የፊት_ላይ_ብጉር፡- ይህ ቡጉር በመድሃኒት በኮስሞቲክስ ነገሮች የመጣ ወይም የሚሸፈን አይደለም፡፡ በቤተሰብ ላይ የሌለ ግና በፊት ላይ ፈፅሚ የሚያስፈራ ብጉር ይኖራል፡፡ አሁን ሰላም ተኩኖ በሌላ ግዜ ፊት ብልሽትሽት ይላል፡፡ ወዲያውኑ ሩቅያህ ካልጀመሩ እነኚህ ሰዎች ፊታቸው በማይለቁ ጠባሳዎች የሚበላሹ ይሆናሉ፡፡ አላህም ይጠብቃን፡፡ 

#የእግር_ስር_እና_የጀርባ_መንደድ፡-ብዙውን ግዜ ታማሚዎች በዚህ ሲህር ተጠቂዎች ምሽት ላይ የሚያቀርቡት ስሞታ ይህ ነው፡፡ የውስጠኛው እግሬ ይሞቃል ይግላል፡፡ በቀስታ ጀምሮ አሁን አላራምድ ብሎኛል፡፡ ጀርባዬን ቀስፎ ይዞኛል ሲሉ ያማርራሉ፡፡ እውነታው ይህ ነው፡፡ ጅኖች ሰውነትን ሊቆጣጠሩ የሚሹት በውድቅት ምሽቶች ነው፡፡ አሏህም ይጠብቀን፡፡ 

#ሰውነት_ውስጥ_የሚርመሰመስ_ነገር_ያለ_መምሰል፡፡

እኛ በአይናችን የማናያቸው ነገራት ለነርሱ ይታያሉ፡፡ በእውነት ደምስራቸው ስር የሚርመሰመስ ትል አልያም የሆነ ነብሳት ያለ ይመስላቸዋል፡፡ አዎን ስሜቱ አለ፡፡ ይህም የጅኑ ስራ ነው፡፡ ሲህሩም መጥፎነቱ የሚለካው እዚህ እስቴጅ ላይ ከደረሰ ነው፡፡አነኚህ ታማሚዎች ልባቸው ውስጥ ገብቶ በየደምስሮቻቸው የሚበተነው ደም ይታወቃቸዋል፡፡ ባእድ ነገርም ሲሄድ ይሰማሉ፡፡

#ብቻ_ማውራት  ይህ ከባዱ የሲህር መገለጫ ነው፡፡ ብቻቸውን ማውራት ይጣፍጣቸዋል፡፡ ሰው ዞር ሲል ከራሳቸው ጋር ይመክራሉ፡፡ ግና እያወሩ ያሉት ከጅኑ ጋር ነው፡፡ አላህም ይጠብቀንና ይህ አይነቱ ህመም ከባሰ ወደ እብደት የሚያመራና ሰው ወደ ማይታየው አለም ያመራሉ፡፡ 
====== ===== ===== ==== ===== ===== ===

🔴 #ድግምት በመተተኛዉና(በድግምተኛዉ) በሰይጣን መካከል የሚደረግ ስምምነት ነዉ

ይህም መተተኛዉ ሰይጣንን ለመሳብ
☞ቁርአን ያረክሳሉ
☞ቁርአን በእግራቸዉ በመጫመት ሽንት ቤት ይገባሉ
☞የቁርአን አንቀፅ በቆሻሻ ወይም በወር አበባ ደም በመፃፍ ያረክሳሉ
☞ዉዱዕ ሳያደርጉ ሶላት ይሰግዳሉ
☞ጀናባ ሁነዉ ለበርካታ ቀናት ሳይታጠቡ ይቆያሉ
☞የአላህ ሱ.ወ ስም ሳይጠሩ ለሰይጣን ያርዳሉ
☞ያረዱትን ሰይጣኑ በፈለገዉ ቦታ ላይ ይጥላሉ
☞ከዋክብትን በመለማመን ለከዋክብት ይሰግዳሉ
☞ከእናቶቻቸዉ ከልጆቻቸዉ ወይም ትዳር ከመሰረቱ አጂነቢያህ ሴቶች ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ይፈፅማሉ
☞ሽርክና ክህደት ያዘሉ የጥንቆላ ቃላትን ይፅፋሉ👇👇
ድግምተኛ እና ሰይጣን አላህ ሱ.ወ በማመፅ ላይ የተሰማሩ ሁለት ጥንዶች ናቸው ማለት ነዉ
ሁልጊዜም ማለት ይቻላል በሰይጣንና በአስማተኛ(በድግምተኛ) መካከል የጋራ ስምምነት ይኖራል፡፡ በዚህ ስምምነት ድግምተኛዉ የክህደትና የሽርክ ሀጢያቶችን በግልፅ ወይም በድብቅ ሊፈፅም እና ሰይጣኑ በበኩሉ ድግምተኛዉን ሊያገለግለው ወይም የሚያገለግለው ሌላ ሰይጣን ሊሰጠው ይስማማሉ።

🔰 የዚህ ዓይነት ስምምነት (ውል) አብዛኛዉን ጊዜ የሚደረገው በደጋሚዉና በሰይጣናት የጎሳ አለቃ መካከል ነው።
የጎሳ አለቃ በሚመራዉ ጎሳ ውስጥ ዝቅተኛ ማዕረግ ያለውን ሰይጣን ከእርሱ ጋር ውል የገባውን ደጋሚ እንዲታዘዘዉ እና እንዲያገለግለዉ ያደርጋል፡፡

↪️ ለምሳሌ
>> የተከሰቱ ድርጊቶችን በመንገር፣
>> ሰዎችን በማጣላት፤
>> መስተፋቅር በመስራት፣
>> ባል ሚስቱን ከመገናኘት በማሰናከል እና ሌሎች ችግሮችን ወዘተ ጉዳዮችን እንዲፈፅምለት ያዘዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ደጋሚዉ ይህንን ሰይጣን ለሚፈልጋቸው የመተት ሥራዎች ማስፈፀሚያነት ያውለዋል። ሰይጣኑ አልታዘዝ ካለው ክህደት ያዘሉ እና የሰይጣናት የጎሳ አለቃን የሚያወድሱ የድግምት ቃላት በመድገም ወደ ሰይጣናት የጎሳ አለቃ ይቀርባል። ይህም የጎሳ አለቃ አስማተኛውን አልታዘዝ ያለወን ሰይጣን እየቀጣ እንዲታዘዘው ዳግመኛ ያዘዋል : ወይም ሊታዘዘዉና ሊያገለግለው  የሚችል  ሌላ ሰይጣን ይሰጠዋል፡፡

ሰይጣኑ ደጋሚዉን የሚያገለግለዉ ተገዶ በመሆኑ ስራውንም ሆነ ደጋሚዉን በእጅጉ ይጠላል፡፡ በዚህም ሳቢ በደጋሚዉና በአገልጋዩ ሰይጣን መካከል ያለዉ ግንኙነት በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡ ሰይጣኑ በደጋሚዉ ወይም በጠንቋዩ ሚስት፣ ልጆች፤ ንብረት እና ሌሎች ነገሮቹ ላይ ጉዳት ከማድረስ ወደ ኋላ አይልም፡፡
እንዲያዉም አስማተኛዉ አያዉቀዉም እንጂ በራሱ ላይ ሳይቀር ጉዳት ያደርስበታል፡፡
☞ የማይለቅ የራስ ምታት፣
☞ከፍተኛ የእንቅልፍ እጦት፣
☞በአስፈሪ ሁኔታ እና በድንጋጤ ከእንቅልፍ መባነን እና በመሳሰሉ አንግልቶች ያሰቃየዋል
☞ አንዳንድ ድግምተኞች ልጅ መዉለድ የማይችሉ መሀኖች ናቸዉ ይህም የሚሆነዉ ፅንሱ ገና ከማደጉ በፊት ሰይጣኑ ስለሚገድለዉ ነዉ። ይህ ነገር በድግምተኞች ዘንድ በጣም ከመታወቁ የተነሳ አንዳንድ ደጋሚዎች ልጅ ለመዉለድ ሲሉ የድግምት ስራቸዉን አርግፍ አድርገዉ የተዉ አሉ፡፡

#ክፍል 4⃣
ይቀጥላል....

አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇

T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ

            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
          
                 ⭐️ #ክፍል👉 አራት 4⃣


🔰🔰 #ደጋሚዎች_ጂኒ_የሚስቡባቸዉ_የተለያዩ_ዘደዎች

💠 #ዘዴ አንድ፡- እርግማን

ድግምተኛው ጨለማ ክፍል ዉስጥ ገብቶ እሳት ያቀጣጥላል፡፡ ሊሰራዉ ለፈለገዉ የድግምት ዓይነት ተስማሚ የሆነ እጣን ያጨሳል፡፡ ሰዎችን የሚያጣላ፣ የሚያለያይ…….. ድግምት ለመስራት ሲፈልግ መጥፎ ጠረን ያላቸዉን እጣኖች ይጠቀማል።
☞ በተቃራኒዉ መስተፋቅር ለመስራት፤ ድግምት ለመፍታት... ሲፈልግ ጥሩ መዓዛ ያላቸዉን እጣኖች ይጠቀማል፡፡ ከዚያ በኋላ በክህደት የተሞሉ የድግምት ቃላትን ማማተብ ይጀምራል፡፡ እነዚህ የድግምት ቃላት ደግሞ በጂኒዎች አለቃ መማል በአለቃችሁ ይሁንባችሁ ... የሚሉትን የክህደት ቃላት ያዘሉ ናቸዉ፡፡ እነዚህን በማማተብ ጂኒዎችን ይለማመናል ለእነርሱም ይፀልያል እርዳታ ይጠይቃቸዋል ታላላቅ የጂኒ መሪዎችን ያወድሳል። ይህን ሁሉ በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ ድግምተኛው የቆሸሹ እና የተነጀሱ ልብሶችን መልበስ አለበት፡፡

ድግምቱን ተብትቦ ሲጨርስ ሰይጣን በዉሻ ወይም በእባብ ወይም በሌላ ማንኛዉም ቅርፅ ተመስሎ ይገለጥለታል፡፡ ከዚህ በኋላ የሚፈልገዉን እንዲፈፅምለት ይጠይቀዋል፡፡ ወይም ሰይጣኑ ሳይገለጥ ድምፁን ብቻ ያሰማዋል ወይም ድምፅ ላያሰማም ይችላል። በዚህ ጊዜ ድግምተኛው ወይም ደብተራው መተት ሊሰራበት ያሰበዉን ሰዉ ላብ የያዙ ቁራጭ ጨርቆችን ወይም ፀጉሩን በመቋጠር ይህ ሰዉ እንዲሆን የፈለገዉን አድርግ በማለት ሰይጣኑን ያዘዋል።


#ከዚህ_ዘዴ_የሚከተሉትን_እንገነዘባለን

➊ ሰይጣናት ጨለማ ክፍልን ይመርጣሉ
➋ የአላህ ስም ያልተጠራባቸዉን ጭሳጭሶች ይመገባሉ
➌ በዚህ ዘዴ ዉስጥ ያለዉ በጂኒዎች መማልና እርዳታ መለማመን ግልፅ የሆነ ሽርክ ነዉ
➍ ጂኒዎች ቆሻሻን ይመርጣሉ፡፡ ሰይጣናት ወደ ቆሻሻ ይቀርባሉ

💠 #ሁለተኛዉ_ዘዴ፡- እርድ

ድግምተኛው ጂኒዉ በሚፈለገዉ ዓይነት ልዩ የሆነ ወፍ ወይም ዶሮ ወይም እርግብ ወይም ሌላ እንስሳ ያቀርባል፡፡ (አብዛኛዉን ጊዜ ጥቁር ቀለምን ይመርጣሉ፡፡ ምክንያቱም ጂኖዎች ምርጫቸዉ ጥቁር ስለሆነ ከዚያም የአላህን ስም ሳይጠራ ያርደዋል፡፡ አልፎ አልፎ በታረደዉ ደም የታመመዉን ሰዉ አካል ሊቀቡም፣ ላይቀቡም ይችላሉ። የታረደዉ እንሰሳ የጂኒዎች መኖሪያዎች ናቸዉ በሚባሉ በፍርስራሽ ቦታዎች ጉድጓዶች ወይም ሰዉ በማይደርስባቸዉ አካባቢዎች የአላህን (ሱ.ወ) ስም ሳይጠራ ይወረዉረዋል፡፡ ከወረወረ በኋላ ወደ ቤቱ በመመለስ የክህደት ድግምቶችን ያነበንባሉ፡፡ ከዚያም እንዲሆንለት የሚፈልገዉን ጂኒዉ አንዲያደርግለት ይነግረዋል ወይም ያዘዋል፡፡

በዚህ ዘዴ ዉስጥ ሁለት ዓይነት ሽርኮችን እናያለን፡፡ እነርሱም፡-

➊ ለጂኒ ማረድ☞ ከአላህ በቀር ለሌላ ማረድ ሀራም በመሆኑ ከሀራምም አልፎ  እንዲያዉም ሽርክ ነዉ፡፡ እንኳንስ ለጂኒ ማረድ ለጂኒ የታረደን መብላት ሀራም (ክልክል) ነዉ፡፡ የሚያሳዝነዉ ነገር በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች መሀይማን እንዲህ ያለ ፀያፍ ድርጊት መስራታቸዉ ነዉ፡:

➋ እርዱን ከፈፀመ በኋላ ጠንቋዩ ወደ ቤቱ ተመልሶ የሚላቸዉ ድግምቶች ግልፅ ሽርክ እና ክህደት ያዘሉ ናቸዉ፡፡ ይህንንም ኢብን ተይሚያህ ገልፀዉታል፡፡

💠 #ሶስተኛዉ_ዘዴ፡ ወራዳዉ ዘዴ

ይህ ዘዴ ወራዳ ዘዴ በሚል መጠሪያ በድግምተኛው ዘንድ ይታወቃል፡፡ በዚህ ዘዴ የሚጠቀም ድግምተኛ የሚያገለግሉትና ትዕዛዛቱን የሚፈፅሙለት እጅግ ብዙ ሰይጣናት ይኖሩታል፡፡ ምክንያቱም በክህደቱና በሽርኩ ወደር ስለማይገኝለት ነዉ፡፡ ይህ ዘዴ ባጭሩ እንደሚከተለዉ ነዉ፡፡

📌📌📌 ድግምተኛው ወይ ጠንቋዩ (የማያቋርጥ የአላህ እርግማን ይዉረድበትና) ቁርአንን በእግሮቹ በመጫማት ሽንት ቤት ገብቶ የክህደት ድግምቶችን ያነበንባል፡፡ አነብንቦ  ሲያበቃ አንድ ክፍል ዉስጥ በመቀመጥ የሚፈልገዉን እንዲያደርጉለት ሰይጣናትን ያዛቸዋል፡ ሰይጣናትም ትዕዛዙን ለመፈፀም ይጣደፋሉ ምክንያቱም በአላህ በመካድ ወደር የለሽ በመሆን ባልእንጀራቸዉ ሆኗልና፡፡ ይህን በማድረጉ ከፍተኛ ክስረት ዉስጥ ወድቋል። ይህን ወራዳ ዘዴ የሚጠቀም ድግምተኛ ወይም ደብተራ ከላይ ካየናቸዉ ድርጊቶች በተጨማሪ
>> ከባለ ትዳሮች ጋር ወሲብ ማድረግ፣
>> ግብረ ሰዶም መፈጸም፤
>> እስልምናን መሳደብ እና የመሳሰሉትን በርካታ ተደራራቢ ሀጢያቶችንና ወንጀሎችን እንዲፈፅም ሰይጣናት ሊተባበሩት ዘንድ እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀምጡበታል።

💠 #አራተኛዉ_ዘዴ፦ ቆሻሻ

ይህን ዘዴ የሚጠቀም ድግምተኛ የአላህን ቃል በወር አበባ ደም ወይም በማንኛዉም ቆሻሻ ነገር ይፅፋል፡፡ እንደዚህ አድርጎ በመፃፉ ሰይጣን ይገለጥለታል፡፡ ከዚያም የሚፈልገዉን እንዲፈፅምለት ያዘዋል። በዚህ ዘዴ ዉስጥ ያለዉ ክህደት ለማንም ሰዉ የተሸሸገ አይደለም። አንዲትን የአላህን ቃል ማቃለል ክህደት (ኩፍር) ነዉ አይደለም በቆሻሻ መፃፍ፡፡ ከእንዲህ ዓይነቱ እርክስት አላህ እንዲጠብቀን እንማፀናለን፡፡

ጌታችን አላህ ሆይ! ልቦናችንን በኢማን አፅናልን ሞታችንን በእስልምና አድርግለን ከሞትም በኋላ መልካም ከሰሩት ጋር ሰብስበን።

💠 #አምስተኛ_ዘዴ፡- ማዞር

ድግምተኛው ጠንቋዩ (የአላህ እርግማን ይዝነብበት) ከቁርአን አንድ አንቀፅ በመዉሰድ የፊቱን ኋላ የኋላዉን ፊት አድርጎ ገልብጦ እና ፊደላቱን ነጣጥሎ ይፅፋል። በዚህም ምክንያት ሰይጣን ይገለጥለታል፡፡ ከዚያም ሰይጣኑን የሚፈልገዉን እንዲፈፅምለት ያዘዋል፡፡ ይህ ዘዴ እንደሚታወቀዉ ግልፅ ክህደት ነዉ።

💠 #ስድስተኛ_ዘዴ፦ ኮኮብ ቆጠራ

ይህ ዘዴ በሌላ አጠራር መጠባበቅ _ ይባላል፡፡ ምክንያቱም ድግምተኞች አንድ የተለየ ኮኮብ እስኪወጣ ስለሚጠባበቁ : ነጢር የሚጠበቀዉ ኮከብ ሲወጣ ድግምተኛዉ የድግምት ንባባትን እያማተበ ኮከቡን ይማፀናል። በተጨማሪም ልዩ የሆነ በሽርክና በክህደት የተሞላ ድግምት ይደግማል። ከዚያም  ልዩ የሆነ እንቅስቃሴ ያደርጋል፡፡ ይህንንም የሚያደርገዉ ድግምተኞች እንዲህ ዓይነት እንቅስቃሴ ስናደርግ የኮከቡ መንፈስ ይወርድልናል ብለዉ ስለሚያምኑ ነዉ፡፡ ነገር ግን ድግምተኛዉ አያዉቅም እንጂ ኮኮቡን እያመለከዉ ነዉ" በዚህ ግዜ ሰይጣናት የድግምተኛውን ጉዳይ ይፈፅማሉ ለድግምተኛው ኮከቡ ያደረገለት ይመስለዋል እንጂ ኮከቡ የሚያዉቀዉ ነገር የለም፡፡

በዚህ ዓይነት ዘዴ የተሰራ ድግምት ኮከቡ ተመልሶ ካልወጣ በቀር ሊፈታ አይችልም ይላሉ ድግምተኞች፤ ነገር ግን በቁርአን ወዲያዉኑ ይፈታል፡፡ አንዳንድ ኮከቦች ደግሞ በአመት አንድ ግዜ ብቻ ስለሚወጡ ድግምተኞች የነዚህን ኮከቦች መዉጣት በመጠባበቅ የተሰራ ድግምት ካለ ለመፍታት ጥረት ያደርጋሉ። 👇👇
💠 #ሰባተኛዉ ዘዴ:-የእጅ መዳፍ

ድግምተኛው ለአቅመ አዳም ያልደረሰ ልጅ ያመጣል፡፡ ልጁም ዉዱዕ ማድረግ የለበትም፡፡ በልጁ የግራ እጅ
አራት ማዓዘን ይስላል። ከዚያም ክህደት ያዘሉ ድግምቶችን በመዕዘኑ ዙሪያ ይፅፋል። በማዕዘኑ መሀል ላይ ሰማያዊ ፅጌረዳ እና ዘይት ወይም ስማያዊ ቀለም ያስቀምጣል፡፡ ሬክታንግል ቅርፅ ባለዉ ወረቀት ላይ ደግሞ ክህደት ያዘሉ ድግምቶችን ይፅፍና በልጁ ፊት ላይ ጣል በማድረግ እንዳትንሸራተት ደግሞ ቆብ ይጭንባታል፡፡ ከዚያም ልጁን በወፍራም ልብስ ይሸፋፍነዋል። ተሸፋፍኖ ጨለማ ዉስጥ ስለሆነ ባይታየዉም እንኳ ይህ ሁሉ ሲደረግ እጁ ላይ ማፍጠጥ አለበት፡፡ ከዚያ በኋላ ድግምተኛው ከፍተኛ ክህደት የያዙ ድግምቶችን ማንበልበል ይጀምራል። በዚህ ጊዜ አካባቢዉ በብርሃን የተሞላ መስሎ ለልጁ ይታየዋል በመዳፉ ላይ የምትሽከረከር ምስልም ያያል፡፡

ምን ይታይሃል ሲል ድግምተኛው ልጁን ይጠይቀዋል፡፡ ልጁም ሰዉ የሚመስል ነገር ይታየኛል” ይላል፡፡ ድግምተኛዉም ለምታየዉ ምስል  እንዲህ እንዲህ ይልሀል ብለህ ንገረዉ ይለዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ምስሉ በተባለዉ መሰረት ይንቀሳቀሳል፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ ይህን የሚጠቀሙት የጠፋን ነገር ለመፈለግ ነዉ፡፡ ይህ ዘዴ የያዘዉ የሚሉ እና የሽርክ ድግምት ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡

💠 #ስምንተኛዉ_ዘዴ፦ የሰዉን ላብ የያዘ ቁራጭ መጠቀም

ድግምተኛዉ ከታማሚዉ ልብስ ወይም ከሌላ ከማንኛዉም ነገር  የላቡን ሽታ የያዘ ቁራጭ ይወስዳል፡፡ ከዚያም ቁራጩን ከጫፉ ላይ ይቋጥረዉና አራት ጣት በሚያህል መጠን ለክቶ ይቆርጠዋል። ከዚያም ይህን ቁራጭ ጨርቅ በጣም ጭብጥ አድርጎ ይይዛል። ከዚያም ሱረቱል ተካሱር ምዕራፍን ወይም ሌላ አጭር ምዕራፍ ድምፁን ከፍ አድርጋ ያነባል። በመቀጠል ድምፁን ዝቅ አድርጎ የክህደት ድግምት ይደግማ ከዚያም ጂኒዎችን እየተጣራ እንዲህ ይላል፡-

የዚህ ሰዉ ህመም መንስኤዉ ልክፍት ከሆነ የጨርቅ ቁራጩን አሳጥሩት፤ ቡዳ ካለበት አስረዝሙት፣ አካላዊ ከሆነ ጨርቁን እንዳለ ተዉት፡፡ ይህን ካደረገ በኋላ ቁራጩን ጨርቅ ዳግመኛ ይለካዋል፡፡ ከአራት ጣት እረዝሞ ካገኛዉ ቡዳ ነዉ የታመምከዉ ይለዋል፡፡ አጥሮ ካገኘዉ ደግሞ ልክፍት አሉ ይለዋል። ሳያጥር ወይም ሳይረዝም እንዳለ አራት ጣት ሆኖ ካገኘ ምንም የለብህም ዘመናዊ ዶክተሮች ዘንድ ሂድ ይለዋል።

ማወቅ ያለብን
☞ ድግምተኛው ቁርአን ሲያነብ ድምፁን ከፍ በማድረግ ድግምቱን ሲያማትብ ደግሞ ድምፁን ዝቅ በማድረግ ታማሚን ያታልላል። ታማሚዉ ድግምቱ ስለማይሰማዉ እና ቁርአኑን ብቻ ስለሚሰማ ይህ ሰዉ በቁርአን ነዉ የሚያክመዉ ብሎ እንዲያስብ ያደርገዋል። ችግሩ ያለዉ በማይሰማ ድምፅ በሚያማትበዉ ድግምት ዉስጥ ነዉ፡፡

☞ በዚህ ዘዴ ዉስጥ ከጂኒዎች ጋር መተባበር አነሱን መጥራትና መለማመን ይገኝበታል፡፡ ይህ እንግዲህ ክህደትና ሽርክ ነዉ፡
☞ ጂኒዎች እጅግ በጣም ዉሸታሞች ስለመሆናቸዉ ነብያችን አስተምረዉናል፡፡ ታዲያ ይህ ጂኒ ስለተናገረዉ ነገር እዉነቱን ይሁን ዉሽቱን በምን ይታወቃል??

🟢 #ድግምተኛ_የሚለይባቸዉ_ምልክቶች

ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ምልክቶች አንዱ የተገኘበት ከመንፈሳዊ ህመሞች አድናለሁ የሚል ሰዉ ያለ ጥርጥር ድግምተኛ ነዉ፡፡ እነዚህም ምልክቶች እንደሚከተለዉ ተዘርዝረዋል፡፡

➊ የህመምተኛዉንና የእናቱን ስም ይጠይቃል

➋ ህመምተኛው ላቡ ያለበትን የልብሱ ቁራጭ፣ ኮፍያ፣ ማህረብ ካልሲ) ይወስዳል።

➌ በዓይነቱ የተለየ እንስሳ (ቀይ በግ ጥቁር ዶሮ) ህመምተኛው እንዲያቀርብ ያዛል። የሚያርደው ከሆነም የአላህን ስም ሳይጠራ (ቢስሚላህ) ሳይል ያርዳል። የታመመውን አካል በታረደው በክት ደም ይለቀልቀዋል። ወይም ያረደውን በክት ወደ ፍርስራሽ ቦታ ይወረውረዋል።

➍ ድግምት ይፅፋል።
➎ ግልጽ ያልሆኑ ድግምቶችን ማማተብ

➏ ቁጥሮችንና ፊደላትን የያዘ ባለ አራት ማዕዘን ፁሁፍ ይጠብቅሀል በማለት ለህመምተኛው ይሰጣል፡፡

➐ የፀሐይ ብርሃን በማይገባበት ክፍል ውስጥ ለዚህን ያህል ቀናት ቆይ በማለት ህመምተኛውን ያዘዋል፡፡

➑ ለዚህን ያህል ቀናት ገላህን አትታጠብ በማለት ህመምተኛውን ያዘዋል። አብዛኛውን ጊዜ ለአርባ ቀናት ነው ገላህን አትታጠብ በማለት የሚያዙት፡፡ ይህች ምልክት ይህን ድግምተኛ እና ጠንቋይ የሚያገለግለው ሰይጣን ክርስቲያን መሆኑን ታስገነዝበናለች፡፡

➒ ለህመምተኛው በመሬት ውስጥ የሚቀብራቸው ነገሮችን ይሰጣል።

➓ ለህመምተኛው የሚታጠናቸው ወረቀቶች ይሰጣል፡፡

➊➊ ግልፅ ባልሆነ ቋንቋ ያማትባል፡፡

➊➋ አንዳንድ አስማተኞች የህመምተኛውን ስም፤ መንደር እና ለምን ጉዳይ እንደመጣ አስቀድመው ይናገራሉ፡፡ (ይህም የሚሆነው ለአስማተኛው ሰይጣናት አስቀድመው ነግረውታል ወይም ስለ ታማሚው ማንነት እና ሁኔታ በሰላይ አማካኝነት ደርሶበታል ማለት ነው)

➊➌ በወረቀት ወይም በነጭ የሸክላ ሳህን ላይ የተቆራረጡ ፊደላትን በመጻፍ በውሀ አጥቦ እንዲጠጣው ለህመምተኛው ይሰጣል፡

ከነዚህ ምልክቶች አንዱን ያገኘህበት ያየህበት ሰዉ ጠንቋይ ደብተራ ድግሞተኛ ስለሆነ፣ አደራ አደራ በፍፁም ወደእሱ አትሂድ፡፡ ከሄድክ ግን የሚከተለዉ የነቢዩ ሀዲስ ተፈፃሚ ይሆንብሃል፡፡

“ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ የተናገረዉን የተቀበስ ሰዉ፡ ወደ ነቢዩ ሙሀመድ በወረደዉ (ቁርአን) በርግጥ ክዷል” (አል-በዛር ዘግበዉታል)


➊➍ በቤቱ ውሻ ያስራል
☞አስካሪ መጠጥ ይጠጣል።
☞ቁርአን ለመቅራትና ለመስማት አይወድም፡፡
☞ሙዚቃ ይሰማል፡፡
☞ሶላት አይሰግድም ከሰገደም  ጥራ ጥሬ እንደ ምትለቅም ዶሮ ጠቅ ጠቅ ነው፡፡
☞ የእጅ መዳፍ ያነባል።
☞ ከተለያዩ ሴቶች ጋር ዝሙት ይፈጽማል፣
☞የተከበረውን ቁርአንን ያላአግባብ በመቅራትና በመጠቀም ያረክሳል።

በጠንቋዮች (በደብተራዎች) በቄሶች የሚፈታ ድግምት ለጊዜዉ የተፋታ ይምሰል እንጂ ሙሉ በሙሉ አይድንም፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ዳግም ያንሰራራል፡፡ ምክንያቱም ሰይጣናት በጎሳ የተከፋፈሉ ናቸዉ፡፡

☑️ ድግምቱን የሰራዉን ደብተራ የሚያገለግሉት ሰያጣናት ድግምቱን የሚፈታዉን ደብተራ ከሚያገለግሉት ሰይጣናት በጎሳ የተለዩ ስለሚሆኑ የአንዱ ጎሳ ሰይጣን የሰራዉን መተት የሌላ ጎሳ ሰይጣን መፍታት ወይም በመተት የተወከለዉን ጂኒ ማስወጣት አይችልም፡፡ ምክንያቱም ይህን ማድረግ በጎሳዎች መካከል ጦርነት ይቀሰቅሳል።

#ስለሆነም ብዙ ጊዜ ጠንቋይ የሚያገለግሉ ሰይጣናት የሚያደርጉት ነገር ቢኖር በታማሚዉ ዉስጥ ከገባዉ ስይጣን ጋር መስማማት ነዉ፡፡ ይህም ስምምነት ሰይጣኑ ታማሚዉን ለጥቂት ወራት ወይም ሳምንታት ላያንገላታዉ እና ታማሚዉ ደግሞ ሰይጣኑ የሚፈልገዉን ሊያሟላ ይስማማሉ፡፡

ለምሳሌ፡-ጥቁር ዶሮ እንዲታረድለት ፈልጎ ከሆነ ታማሚዉ ይህንኑ ያቀርባል ወይም ለምስሎች እንዲሰግድ ያታዘዛል፡፡ በዚህም ታማሚዉ ለተወሰነ ጊዜያት ተሸሎት ይከርምና ያ የተስማሙበት የጊዜ ገደብ ሲያበቃ ህመሙ ዳግም ይቀሰቀሳል፡፡ ከዚያም ሌላ ስምምነት ... ሙሉ ፈዉስ ማግኘት የሚቻለዉ በዓለማት ፈጣሪ በአላህ ቃል በቁርአን ብቻ ነዉ፡፡

#ክፍል 5⃣
ይቀጥላል.....


አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ

            

#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ

          
                 ⭐️ #ክፍል👉 አምስት 5⃣



🟢
#የሚለያይ_የሚያጣላ_መተት_ሲህር_ምንነት

ባልና ሚስትን ለማለያየት፣ በጓደኞች ወይም በንግድ ሸሪኮች መካከል  ጠብ እና ጥላቻ እንዲፈጠር ለማድረግ የሚሠራ መተት ነዉ።

🔶 #የሚለያይ_መተት _ዓይነቶች

➊ እናትና ልጅን የሚያጣላ
➋ አባትና ልጅን የሚያጣላ
➌ ወንድማማቾችን የሚያጣላ
➍ ጓደኛሞችን የሚያጠላ
➎ የንግድ ወይም በሌላ መስክ የተሰማሩ ሽሪኮችን የሚያጣላ
➏ባለትዳሮችን የሚያለያይ (የሚያጣላ) ይህ ዓይነቱ አስከፊዉና እጅግ በጣም ተንሰራፍቶ ይገኛል፡፡


🔷 #የሚለያይ_የሚያጣላ_መተት_ሲህር_በተስከፈ_ሰዉ_ላይ_የሚታዩ _ምልክቶች

☞ከመዉደድ ወደ መጥላት ያልተጠበቀ የፀባይ ለዉጥ
☞መጠራጠር ማብዛት
☞አንዱ ሲያጠፋ ሌላኛዉ ያለማለፍ (ይቅር አለመባባል)
☞ በጣም ቀላልና ትንሽ ብትሆንም የፀባቸዉን መንስኤ ማግዘፍ
☞በትንሽ በትልቁ መጋጨት
☞ሚስት ለባሏ ያላት ባል ለሚስቱ ያለዉ እይታ መለወጥ፡፡ ምንም ዉብ ቆንጆ ብትሆንም እንኳን ባል ሚስቱ መልከ ጥፉ ትመስለዋለች አስቀያሚ መስላ ትታየዋለች። በተመሳሳይ መልኩ ሚስት ባሏ አስፈሪ መስሎ ይታያታል፡ በተጨባጭ ግን በሚስቲቱ ወይም በባል ፊት በአስቀያሚ ምስል የሚመሰለዉ የድግምቱ እንደራሴ ሰይጣን ነዉ።
☞ ድግምት የተደረገበት ወገን ሌላኛዉ የሚሰራዉን ሥራ መጥላት
☞ ድግምት የተደረገበት ወገን ሌላኛዉ የሚቀመጥበትን ቦታ መጥላት (ከፊቱ ዞር እንዲልለት ይፈልጋል)
#ለምሳሌ፡- ድግምት የተደረገበት ሰዉ ከከቤቱ ዉጭ ሲሆን በጥሩ ሁኔታና ፀባይ ይታያል ወደ ቤቱ ሲገባ የጭንቀትና የድብርት ስሜት ይሰማዋል።

☑️ ይህን በማስመልከት አል ሃፊዝ ኢብን ከሲር እንዲህ ይላሉ... ባለትዳሮች በድግምት የተነሳ የሚጣሉትና የሚለያዩት መጥፎ ወይ አስቃያሚ መልክ፣ እና ሌሎች የሚያጣሉ ነገሮችን አንዱ በሌላዉ ላይ ያየ ስለሚመስለዉ ነዉ፡፡


🟡 #የሚያለያይ_ድግምት_ሲህር_አንዴት_ሲከሰት_ይችላል?

አንድ በአላህ የተረገመ ሰው ወደ ጠንቋይ ዘንድ ይሄድና እገሌ እና ሚስቱን እንዲያለያይለት ይጠይቀዋል፡፡ ጠንቋዩም ድግምት የሚደረግበትን ሰዉዬ ስምና የእናቱን ስም ንገረኝ ይለዋል።
ከዚያም የዚህን ሰዉዬ
>> የላብ ፋና
>> የፀጉሩን
>> የልብሱን
>> የኮፍያዉን፣ የካልሲዉን ቁራጭ ይቀበለዋል፣

የላቡን ፋና ማግኘት የማይችል ከሆነ፣ በፈሳሽ ነገር ላይ ድግምት ይሰራና በስዉዬዉ መንገድ ላይ እንዲረጨዉ ያዘዋል፡፡ ሰዉዬዉ በሚረግጠዉ ጊዜ በድግምቱ ይለከፋል (እስላማዊ የድግምት መከላከያዎችን የሚከታተል ከሆነ ግን በድግምቱ አይለክፍም)፡፡


🟣 #የሚለያይ_የሚያጣላ_ድግምት_ህክምና


☑️ ደረጃ አንድ ቅድመ ህክምና ተገባራት

ህክምናዉ ከመጀመሩ በፊት የሚከተሉትን አድርግ-

➊ የኢማን አካባቢ መፍጠር :-  ይህም ማለት ህክምናዉ በሚሰጥበት ክፍል ዉስጥ መላኢኮች መግባት እንዲችሉ ፎቶዎች እና ምስሎች ካሉ ማንሳት እና ንጽህናዉ የተጠበቀ ክፍል ሊሆን ይገባል፡፡

➋  ሂርዝ፣ ክታብ የመሳሰሉ ታካሚዉ የያዛቸዉ ነገሮች ካሉ ማስወገድ እና ማቃጠል
➌ ህክምና በሚደረግበት ክፍል ዉስጥ ሙዚቃ እና የመሳሰሉት ነገሮች መኖር የለባቸዉም
➍ በሸሪዓ ከተከለከሉ ነገሮች ቦታዉ የፀዳ መሆን አለበት ፡፡
ለምሳሌ
>> ወርቅ ያደረገ ወንድ
>> ሂጃብ ያልለበሰች ሴት
>> ሲጋራ የሚያጨስ መኖር የለበትም

➎ ለታካሚዉና ለቤተሰቦቹ በእስልምና እምነት (በአቂዳ) ዙሪያ ትምህርት መስጠት፡፡ ይህም በአላህ ላይ ያላቸዉን እምነት ያፀናላቸዋል፡፡
በአላህ ላይ ብቻ ተስፋ እንዲኖራቸዉ ያደርጋል።
ጠንቋዮች የሚያክመት ከስይጣን ጋር በመተባበር መሆኑን አንተ ግን የምታክመዉ በአላህ ቃል በቁርአን ብቻ መሆኑን ለታዳሚዎች በሚገባ ልታባራራላቸዉ ይገባል።
እንዲሁም የቁርአንን ፈዋሽነት ልታረጋግጥላቸዉ ይገባል፡፡

➏ የህመሙን ሁኔታ በመጠየቅ መመርመር
የህመሙ ምልክቶች በሙሉ ወይም በአብዛኛዉ መኖራቸዉን ለማረጋገጥ ታካሚዉን አንዳንድ ጥያቄዎችን መጠየቅ፡- ለምሳሌ
አልፎ አልፎ እንኳን ቢሆን ባለቤትህ(ሽ) አስቀያሚ መስላ(ሎ) ትታይሃለች (ይታይሻል)?
  ከባለቤትህ (ሽ) ጋር በትንሽ በትልቁ ትጋጫላችሁን
ቤት በደህና ዉለህ (ሽ) - ወደ ቤት ስትገንቢ የመጨናነቅና የድብርት ስሜት ይሰማሃል (ይሰማሻል?)
ከባለቤትህ (ሽ) ጋር በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ጭንቀት ይሰማሀል (ሻል)?
አንተ ወይም ሚስትህ በእንቅልፍ ማጣት ተቸግራችኋልን?
አስፈሪ ህልሞች ይታዩሃል?

>>>>እንደዚህ እያልክ ጥያቄህን ትቀጥላለህ፡፡ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሚሆኑ የድግምት ምልክቶች በታካሚዉ ላይ ከተገኙበት ህክምናን ትቀጥላለህ፡፡

1⃣ ህክምና ከመጀመርህ በፊት ዉዱእ አድርግ፡፡ ታካሚዉ እና አብረዉህ የታደሙት ዉዱዕ እንዲያደርጉ አድርግ

2⃣ ታካሚዋ ሴት ከሆነች በሚገባ ትሸፋፈን በህክምና ወቅት እንዳትገለጥ ልብሶቿ ጠበቅ ተደርገዉ ይታሰሩ

3⃣ ከሸሪዓ ዉጭ የለበሰች (ምሳሌ፡- ፊቷን የገለጠች፣የጥፍር ቀለም የተቀባች ሴት አታክም

4⃣ ሙህሪሟ በሌለበት ሴትን አታከም

5⃣ በህክምና ክፍሉ ዉስጥ ከሙሀሪሟ በስተቀር ማንንም አታስገባ
6⃣ ሃይልም ሆነ ብልሃት የአላህ እንጂ አንተ እንደሌለህ አምነህ በአላህ ብቻ ታገዝ

       🟠 #ህክምናዉ_በደንብ_እናስተዉል
እጅህን በታካሚዉ ራስ ላይ ታደርግና የሚከተሉትን የቁርአን አንቀጾች በጥሩ አቀራርና ከፍ ባለ ድምፅ በጆሮዎቹ በኩል ትቀራበታለህ፡፡ እነዚህ የቁርአን አንቀጾች የሩቅያ አንቀጾች በመባል ይታወቃሉ፡፡ እነዚህ የሩቅያ አንቀጾች ጂኒዉ ከሰዉየዉ አካል ወጥቶ እንዲሄድ ወይም ቀርቦ እንዲናገር (እንዲለፈልፍ) ያደርጉታል፡፡
መቅራት የማትችል ከሆነ እነዚህን የሩቃ አንቀፆች በሞባይል ወይም በFLASH አድርጎ በጂፓስ ከፍቶ እንዲያዳምጥ ማድረግ ይቻላል፡፡

🔶 #የቁርአን_አንቀፆቹ
➊ ሱረቱል ፋቲሀ
➋ አል በቀራህ 1-5
➌ አል በቀራህ 101-102
➍ አል በቀራህ 163-164
➎ አል በቀራህ 255
➏ አል በቀራህ 285-286
➐ አል ኢምራን 18-19
➑ አል አዕራፍ 54-56
➒ አል አዕራፍ 117-122
➓ ዩኑስ 81-82
➊➊ አል ሙእሚኑን 115-118
➊➋ አስ ሷፍፋቲ 1-10
➊➌ አል አህቃፍ 29-32
➊➍ አር ረህማን 33-36
➊➎ አል ሃሽር 21-24
➊➏ አል ጂን 1-9
➊➐ አል ኢኸላስ
➊➑ አል ፈለቅ
➊➒ አል ናስ
በነዚህ የቁርአን አንቀፆች በጥሩ አቀራር ከቀራህበት በሆላ ታካሚዉ ከሚከተሉት ሶስት ሁኔታዎች ዉስጥ
በአንዱ ሁኔታ ላይ ይሆናል፡፡

1⃣ #አንደኛዉ_ሁኔታ

ታካሚዉ እራሱን ይስታል የድግምቱ እንደራሴ ጅኒዉ መናገር (መለፍለፍ) ይጀምራል፡፡ በዚህ ግዜ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጂኑን ትጠይቃለህ።

➊ ስምህ ማን ነዉ? ሀይማኖትህ ምንድን ነዉ? ሀይማኖቱን ሲነግርህ እንደ ሀይማኖቱ ሁኔታ ታነጋግረዋለህ፡፡ ይህም ማለት ሙስሊም ካልሆነ እስልምናን እንዲቀበል ጥሪ ታቀርብለታለሁ፡፡ ሙስሊም ከሆነ ደግሞ የሚሰራዉ ሥራ ማለትም ጠንቋይን ማገልገሉና መተባበሩ እስልምናን የሚቃረን እና የተከለከለ መሆኑን አስረዳዉ፡፡👇👇
➋ ድግምቱ ያለበትን ቦታ ትጠይቀዋለህ፡፡ ነገር ግን የነገረህን እስከምታረጋግጥ ድረስ አትመነዉ። ድግምቱ እዚህ ቦታ ይገኛል ካለህ የሚያመጣዉ ሰዉ ትልካለህ፡፡ የተላከዉም ሰዉ ድግምቱን በተባለበት ቦታ ካገኘዉ መልካም፡፡ ካላገኘዉ ግን ጅኑ ዋሽቷል ማለት ነዉ፡፡ ጂኒዎች ደግሞ በጣም ዉሸታሞች ናቸዉ፡፡

➌  የድግምቱ እንደራሴ እሱ ብቻ እንደሆነ ወይም ሌላ ጅን ከሱ ጋር አብሮት እንዳለ ጠይቀዉ፡፡ ሌላ ጅን አብሮት ካለ አቅርበዉ በለዉ፡፡

➍ አንዳንዴ ጂኒዎች ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ድግምቱን ያሰራዉ አገሌ ነዉ በማለት ይናገራሉ። እንዲህ ካለህ ጀኒዉን አትመነዉ፡፡ ምክንያቱም ሰዎች መካከል ጠብ እንዲፈጠር ስለሚፈልጉ ነዉ ይህን የሚናገሩት፡፡ ዚህም በላይ ጂኒዉ ጠንቋይ በማገልገሉ ሳቢያ ፋሲቅ ስለሆነ ምስክርነቱ በሸሪዓ ህግ መሠረት ዉድቅ ነዉ፡፡

#እናንተ_ያመናችሁ_ሆይ ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናች ህዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተፀፃቾች እንዳትሆኑ አረጋግጡ፡፡(አል ሁጁራት፡ 6)

🔶 #ድግምቱን_ካገኘኸዉ_እነዚህን_ሁለት_የቁርአን_አንቀፅ_ትቀራለህ
☞ አል አእራፍ 117-122 እና
☞ ዩኑስ 8

እነዚህን የቁርአን አንቀጾች በዉሀ ላይ ስትቀራ ካፍህ የሚወጣዉ ትንፋሽህ በምትቀራበት ዉሀ ላይ እንዲያርፍ አድርገህ ቅራ ፡፡ ከዚያም ድግምቱን በሩቃ ዉሀ ዉስጥ ረዘም ላለ ጊዜያት በመዘፍዘፍ ታማሟዋለህ። ከዚያም ከሰዉ ርቆ በሚገኝ ቦታ ላይ ይደፋል።

#ድግምቱን_ጠጥቶት_በልቶት_ነዉ ካለህ ታካሚዉን ብዙ ጊዜ የሆድ ህመም ይሰማዉ እንደሆነ ትጠይቀዋለህ፡፡ ህመም የሚሰማዉ ከሆነ ድግምቱን በልቶታል ወይም ጠጥቶታል ማለት ነዉ፡፡ ጂኒዉ የነገረህ እዉነት መሆኑን ስትረዳ እንዲወጣና ዳግመኛ እንዳይመለስ ለስለስ ባለ አነጋገር ትነግረዋለህ፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ድግምቱን ትፈታዋለህ፡፡ በመቀጠል ከላይ የተጠቀሱትን የቁርአን አንቀጾች እና የአል በቀራህ ምዕራፍ አንቀፅ 102 በዉሀ ላይ ደግመህ ትቀራለህ ከዚህ ዉሀም ታካሚዉ ለተወሰኑ ቀናት መጠጣትና መታጠብ አለበት፡፡

#ድግምቱን_ረግጦት  ወይም በላቡ ፋና በፀጉሩ፣ በልብሱ ቁራጭ ነዉ ድግምት የተደረገበት ካለህ..... ከላይ የተጠቀሱትን የቁርአን አንቀፆች በዉሀ ላይ ትቀራለህ ከዚያም ታካሚዉ ለተወሰኑ ቀናት እንዲጠጣ እና  እንዲታጠብበት ታደርጋለህ፡፡ ታካሚዉ የሚታጠበዉ ከባኞ ቤት ዉጭ መሆን ይኖርበታል፡፡ የታጠበበትን ዉሀ ከመታጠቢያ ቤት ዉጭ በጡሀራ ቦታ ላይ ይድፋዉ፡፡ ይህንንም ህመሙ እስከሚቆም ድረስ መከታተልና መደጋገም አለበት፡፡ ከዚህ በኋላ ጂኒዉ እንዲወጣ እና ዳግመኛ እንዳይመለስ ቃል ኪዳን አስገብተህ እንዲወጣ እዘዘዉ፡፡

ከተወሰነ ቀን ቡሀላ  የሩቅያ አንቀፆችን ትቀራበታለህ፡፡ በምትቀራበት ወቅት ምንም ዓይነት ስሜት ካልተሰማዉ ምስጋና ለአላህ ነዉ ድግምቱ አብቅቷል (ተፈትቷል) ማለት ነዉ፡፡ ነገር ግን ስትቀራበት እራሱን ከሳተ ጂኒዉ ዋሽቷል አልወጣም ተመልሶ ሰዉየዉ ጋር መጥቷል ማለት ነዉ፡፡ ስለዚህ ያልወጣበትን ምክንያት ጠይቀዉ ለስለስ ባለ መልኩ አነጋግረዉ። በዚህ ሁኔታ ለመዉጣት ከተስማማ ምስጋና ለአላህ ነዉ፡፡ ለመዉጣት ካልተስማማ ግን ቁርአን መቅራት በቅቶት እስኪጠግብ ድረስ በቁርአን እየቀሩ መልሶ እንዳይመለስ ማድረግ ነዉ

☑️ የሩቅያ አንቀፆችን ስትቀራበት ታካሚዉ እራሱን ላይስት ይችላል. ነገር ግን
🔸መንቀጥቀጥ
🔹መንዘርዘር፤
🔸ጭንቀት
🔹 በሰዉነቱ ዉስጥ ንዝረት ወይም የሚወር ስሜት የሚሰማዉ ከሆነ
አያት አል ኩርሲ ለ አንድ ሰዓት ያህል በመደጋገም ተቀርቶ የተቀመጠ በስልኩ በመጫን በኤርፎን አድርጎ በቀን ሶስት ጊዜ በተከታታይ ለአንድ ወር ያዳምጣል፡፡

#በዚህ_ካልዳነ_ግን
>> አል ሷፋት፤
>>  አል ዱኻን፣
>> አል ጂን የተሰኙትን የቁርአን : ምዕራፎች አሁንም በስልኩ በቀን ሶስት ጊዜ ለተከታታይ ሶስት ሳምንታት ያዳምጣል። በዚህም በአላህ ፈቃድ ይድናል፡፡ ምን አልባት ያልዳነ እንደሆነ የሚያዳምጥበትን ቀን  ማራዘም አለብት

      2⃣ #ሁለተኛ_ዘዴ_ህክምና

የሩቅያ አንቀፆች በሚቀሩበት ጊዜ መንቀጠቀጥ ጭንቀት ከፍተኛ የራስ ምታት እና ሰዉነቱን ሲነዝረዉ ይሰማዋል (ሰዉነቱን እንደ ኤሌክትሪክ ያለ ንዝረት ይነዝረዋል) ነገር ግን እራሱን አይስትም፣ ይህ ከሆነ የሩቅያ አንቀፆችን ሶስት ጊዜ በመደጋገም ትቀራበታለህ፡፡ ይሄኔ እራሱን ከሳተ መጀመሪያ ላይ በተገለፀዉ መልኩ ታነጋግረዋለህ።

ነገር ግን ታካሚዉ እራሱን አልሳተም ብቻ የሚያንቀጠቅጠዉ የሚነዝረዉ ጭንቀቱ እና የራስ ምታቱ ቀለል እያለዉ ከሆነ ለተወሱ ቀናት የሩቅያ አንቀፆችን ቅራበት በአላህ ፈቃድ ይድናል፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ ካልዳነ የሚከተለዉን ማድረግ ይኖርበታል፡፡

➊ ሙሉዉን የአል ሷፋት ምዕራፍ አንድ ጊዜ እና አያት አል ኩርሲን በመደጋገም የተቀራበትን በስልኩ ይጫን  ታካሚዉ በቀን ሶስት ጊዜ ያዳምጣል፡፡
➋ ሶላት በጀመዓ መስገድ አለበት


‎ لا إله إلا اللَّهُ وَحْدَهُ لا شَرِيكَ لَهُ፣ لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قدِي ‎
ከሱብሂ ሶላት ቡሀላ 100 ጊዜ ለአንድ ወር ያህል ማለት

ይህን ህክምና በሚከታተልበት በመጀመሪያዎቹ 10 እና 15 ቀናት ዉስጥ ህመሙ ሊባባስ እንደሚችል እና ቀስ በቀስ እየቀለለ እንደሚሄድ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ በወሩ መጨረሻ በአላህ ፈቃድ ከህመሙ ሙሉ በሙሉ ይድናል፡፡ ከዚያም ሲቀራበት በአላህ ፈቃድ ምንም ዓይነት ህመም አይሰማዉም፡፡

      3⃣  #ሶስተኛዉ_ዘዴ_ህክምና

ሩቅያ በሚቀራበት ጊዜ ታካሚዉ ምንም ዓይነት ህመም አይሰማም፡፡ በዚህ ጊዜ  ከላይ ያየናቸዉን የድግምት ምልክቶችን ትጠይቀዋለህ፡፡ ምንም ዓይነት ምልክት ካላገኘህበት አልተደረገበትም ማለት ነዉ። ይበልጥ እርግጠኛ ለመሆን ሩቅያ ሶስት ጊዜ ደጋጋመህ ቅራበት፡፡ የድግምት ምልክቶች ታይተዉበት ሩቅያ ተደጋግሞ ተቀርቶበት ምንም ሊሰማዉ ካልቻለ (ይህ ዓይነት ሁኔታ እጅግ በጣም አልፎ አልፎ የሚከሰት ነዉ) የሚከተለዉን እንዲፈጽም ታደርጋለህ፡፡ ድግምት

➊) ‎ استغفر الله ‎
“አስተግፊሩላህ” በቀን 100 ጊዜ እና ከዚያ በላይ ማለት

➋) ከቁርአን ዉስጥ የያሲን፣ የአል ዱኻን፣ የእል ጂን ምዕራፎችን በስልክ ጭነህ በቀን ሶስት ጊዜ እንዲያዳምጥ ማድረግ

➌) ‎ لاحَولَ أَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللَّهِ ‎
ላ ሃዉለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ¨ በቀን 100 ጊዜ እና ከዚያ በላይ ማለት

እነዚህ የተጠቀሱትን ታካሚዉ ለአንድ ወር በተከታታይ ይተገብርል

#ክፍል 6⃣
ይቀጥላል.........


አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

⚡️ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
2024/09/25 04:19:47
Back to Top
HTML Embed Code: