Telegram Web Link
በፈረንጆቹ በ1950ዎቹና በ1960ዎቹ አካባቢ የሴት ፍላጎት፣ መብትና ነፃነት አይደለም ሊከበር ቀርቶ አልታሰበም ነበር፡፡ ሴት ልጅ ያገባች ከሆነ የባሏ አገልጋይ፤ ለትዳር ካልደረሰች ደግሞ የእናቷ ረዳት፤  ወግ ሳይደርሳትና ዕድል ሳይገጥማት ሳታገባ ከቆየች ወይም ፈት ከሆነች ደግሞ በማህበረሰቡ የስድብ ናዳ ይወርድባታል፣ ትናቃለች፣ ትገለላች፡፡ ሴት ሆኖ መፈጠር ምን ያህል ከባድ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው፡፡ በአሜሪካ እንኳን እ.ኤ.አ. በ1950 ዓ.ም. የነበረው ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተዘጋጀውን የኑሮ በዘዴ መማሪያ መፅሐፍ (Home Economics text book) ብናይ ያገባች ሴት የባሏን ፍላጎት እንዴት ማሟላት እንዳለባት የሚያስተምርና የሚተነትን ነበር፡፡ ሴት ግዴታዋና ሃላፊነቷ የበዛ ነገር ግን መብትና ነጻነቷ ያነሰ፤ ምንም ምርጫ ያልነበራት እንደነበረች እናቶቻችንን ማየት በቂ ነው፡፡

ያም ሆነ ይህ በዘመናችን ያለችው ሴት በእናቶቻችን ዘመን ከነበሩት ሴት በብዙ መልኩ ትለያለች፡፡ ትናንት ፍላጎቷ የማይከበርላት፤ ዛሬ በአንድም በሌላም መንገድ ፍላጎቷ ይከበርላት ዘንድ አቅምና ጊዜ አግኝታለች፡፡ የዘመናችን አንገብጋቢውና አሳሳቢው ጉዳይ ግን ሴቶቹ ራሳችን የምንፈልገውን ነገር አለማወቃችን ነው፡፡ ራሳችንን አለማወቃችን የወንዶች ብያኔ ተጠቂ እንድንሆን አድርጎናል፡፡ ለጉብዝናችን ወይም ለቁንጅናችን የምስክር ወረቀት የምናገኘው ከወንዶቹ ነው፡፡ በዛም አለ በዚህ የወንዶች ስነልቦና ተጠቂ ሆነናል፡፡ በኢኮኖሚ ራሳችንን እየቻልን ብንመጣም በአስተሳሰብ ግን አሁንም የወንዶች ጥገኛ ነን፡፡ ራሳችንን በምግብ ብቻ ሳይሆን በሃሳብም ካልቻልን ከወንዶች ጭቆና አንተርፍም፡፡

መቼስ ሴትን እንደ እንደስነልቦና ምሁሩ ሲግመንድ ፍሮይድ ያጠናት የለም፡፡ ሰውየው ሴት ልጅ ገና ከልጅነቷ ጀምሮ ምን ዓይነት አስተሳሰብና ባህሪ ሊኖራት እንደሚችል፤ እንዲሁም ትክክለኛ ፍላጎቷ ምን እንደሆነ ለማወቅ የተመራመረ ነው፡፡ ለዚህ ነው ‹‹ሴት የምትፈልገው ምንድነው? What do women want›› በሚለው ጥያቄው የሚታወቀው፡፡

ሴት በሴት መቀናናት ያለ ነው፡፡ የማታስቀናም የማትቀናም ሴት የለችም፡፡ ሴት በወንድ ስትቀና ግን ሊያስገርም ይችላል፡፡ ፍሮይድ ይሄን በተመለከተ አንድ ጥናት ነበረዉ፡፡ ይሄ ጥናት ሴት ገና ከአፍላ እድሜዋ ጀምሮ አጎጠጎጤዎች ስታወጣ፣ የመራቢያ አካሏ እየዳበረ ሲመጣ፣ ለአቅመ ሔዋን ስትደርስና እንደ ወንድ አለመሆኗን ስታውቅ በወንዱ መቅናት ትጀምራለች ይለናል፡፡ መቅናት ከሴት ተፈጥሮ ጋር የተዋሃደ ይመስላል፡፡ ይሄ የስነልቦና ተመራማሪ ስለሴቶች ባህሪ ለማወቅ ብዙ ጥናቶችን ቢያከናውንም ሴቶች ግን እንቆቅልሽ እንደሆኑበት ነው ህይወቱ ያለፈው፡፡ የሚገርመው ሴት ልጅ አይደለም ለወንዱ ለገዛ ራሷ ግራ አጋቢ ፍጥረት መሆኗ ነው፡፡ ኤቭሊን ሌት (Evelyn Leite) የተባለች ታዋቂ የስነልቦና አማካሪ “Women” በተባለ መፅሐፏ ‹‹ፍሮይድ -- ሴት ምንድነው የምትፈልገው? -- የሚለው ጥያቄው ወንዱን ብቻ ሳይሆን ሴቷ ራሷ መልስ ያጣችለት ነው፡፡ (Freud’s question – What do women want – frustrates men, It also frustrates women)›› በማለት ትገልጻለች፡፡

ብዙዎቻችን ሴቶች ባላችን ወይም ምን እንዲያደርግልን ከመፈለጋችን በፊት እኛ የምንፈልገውን ቀድመን ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡ ሚስቶች ከባሎቻችን የምንፈልገው ነገር ብዙ ነው፡፡ ነገር ግን የምንፈልገውን ነገር በግልጽ አናውቀውም፡፡ ባሎችም ሚስቶቻቸው ምን እንደሚፈልጉ አለማወቅ ብቻ ሳይሆን የሚስቶቻቸው ፍላጎት በየጊዜው የሚለዋወጥ በመሆኑ ግራ ተጋብተዋል፡፡ ሴት የራሷን አካላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ስሜታዊ እና ሌላም ፍላጎቷን ለይታ ካላወቀች እንዴት ብሎ ነው ባሏ ፍላጎቷን ሊያሟላ የሚችለው? ብዙዎቻችን ሴቶች ለይተን ባላወቅነው ፍላጎታችን ወንዶችን ተጠያቂ እናደርጋለን፡፡

ግራ የሚያጋባ ነዉ.....
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለአንዲት ሴት በተለይ “ቆንጆ ሴት” ነን ብለን ለምናስብ ሴቶች ፣ አቅማችንን እንዳንጠቀም እስር ቤት የሚሆንብን የራሳችን ቁንጅና ነው፡፡ የራሳችን ቆዳ የራሳችን እስር ቤት ነው፡፡
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ  ‘ሴትነት እና ቁንጅና’ የሚባል እስር ቤት ፍርግርጋችንን እያስዋብን ተሟሙቀን የወንዶችን ጭብጨባና አድናቆት እየጠበቅን እንድንኖር ሆነናል፡፡ ሁሉም እስር ሰንሰለቱ ፈጦ አይታይም….. እንደውም አንዳንዱ እስራት ለታሳሪው ለራሱ ጭምር አይታይም፡፡ ማኅበረሰቡ አንዲትን ሴት “የብረት መዝጊያ የሚሆን አማች የምታመጣ እንጂ፣ የብረት መዝጊያ መሆን የምትችል አድርጎ አያስብም፡፡ ስለዚህ የእነሱን የምኞት በር የሚዘጋ የብረት መዝጊያ ለማምጣት፣ አንዲት ሴት ዓይኗንም አእምሯዋንም ሳይሆን እግሯን እንድትከፍት ከሕፃንነቷ  ጀምሮ ሲያዘጋጃት ይኖራል ”
”እግር የተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማው መራመድ ነው፤ ለሴት ልጅ ግን ከመራመድ በላይ እግር ውበት እንደሆነ እንድታስብ በሥነጽሑፉ፣ በፊለሙ አእምሮዋ ውስጥ ሲታጨቅባት ኖሯል፡፡ ከመራመዷ በላይ የአረማመዷን እና የእግሯን ውበት እንድታስብ ስትሰበክ ኖራልች፡፡ ለዚያም ነው ከፊታቸው የተነጠፈውን እሾህም ይሁን ጠጠር ረግጠውና ዋጋ ከፍለው ወዳሰቡበት ከሚራመዱ ሴቶች ይልቅ፤ ከየትም ባገኙአት ሳንቲም በየውበት ሳሎኑ ተጎልተው፣ እግራቸውን የጥፍር ቀለም ሲያስቀቡና ተረከዛቸውን ሲያስፈገፍጉ የሚውሉ ዘመነኞች የሚበዙት፡፡ እግራቸውን ከለሰለሰ በኃላ፣ አዝሎ የሚያሻግር ወንድ ሲጠብቁ ቁጭ ብለው ይኖራሉ፡፡
እጅ የተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማው መሥራት ነው፡፡ ብዙ የፋሽን እና ዘመናዊውን የውበት ሚዛን የሚደፉ ’ዘመናዊ’ ሴቶች፣ እጃቸው ከሚበላሽ ስማቸውም ሕይወታቸውም ቢበላሽ እና እጃቸው እንደለሰለሰ ቢኖር ይመርጣሉ፡፡ በልስላሴ ሳይሆን በንጽሕናና ራስን ችሎ በመቆም እንጨባበጥ ከተባለ ማን ናት ደፍራ እጇን የምትዘረጋ?! ለብዙኃኑ ወንዶች ጠንካራ የሴት እጅ ሀገርን ያቆመ ሳይሆን፣ ሴትነትን የገፋ መስሎ ነው የሚታያቸው፡፡ ለዚያ ነው በሥራ ስለደደረ የሴት መዳፍ፣ ዘፋኙም መዝፈን፣ ገጣሚውም መግጠመ የማይወደው፡፡ ድንጋይ ፈልፍሎ እና እምነበረድ ጠርቦ ውብ የእጅ ጣት ያላት ሴት ሐውልት የሚያቆመውን ቀራጺ እጅ ግን ተመልከተው፣ በሥራ የጎለደፈ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ሴት በሆነበት አገር፣ ሴቶች እጃቸውን አስውበው መደርደሪያ ላይ እንዲያስቀምጡ በማድረግ፣ ለውጥ ጠብ አይልም፤ እንዲሰሩ….. ማደፋፈር….እጅ ወደተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማ እንዲመለስ መሰበክ አለበት፡፡
                                                                                                                                                                                            
ከእለታት ግማሽ ቀን; ገጽ 182-183
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አዎ ! እሱ ጋ ያመኛል መጽሐፍን ዉስጥ አንዳንድ ሀሳቦች ፦
___

➫ ሁልጊዜ እሮሮ የሚዘበዝቡ፣ ሁልጊዜ ሰው ማጣጣል ላይ የተመሰጡ ሰዎች፣ ሁልጊዜም አልተሳካልን ዓይነት ደረት የሚመቱ፤ ለውድቀታቸው ሰው የሚወቅሱ ሰዎች፣ ለመውደቃቸው ኃላፊነት ከማይወስዱ ጋ አትወዳጅ ” ( ገጽ 17 )

➫ ደካማነት ምቹ ስፍራ ሲያገኝ እና ጊዜ ሲደላደልለት የሚያብብ ደዌ ነው። ( ገጽ 25 )

➫ መልካም አድራጎት የሚገዝፈው መልካም አድራጊው በየሰበቡ ካልፎከረበት ነው። ( ገጽ 28 )

➫ ወደ በጎ መለወጥ ብዙ ጠመዝማዛ መንገድ አለው። እንደ መበላሸት ቀላል አይደለም። ( 31 )

➫ አንዳንድ ትናንት ትናንት ላይ ብቻ አይቆምም። ዛሬያችንን የፈለገ ከትናንት አርቀን ሰቅለነዋል ብንል ፣ ጥለነው ብዙ መጥተናል ያልነው ትንናት ነጋችን ላይ በሁለት እግሩ ቆሞ እናገኘዋለን። ( ገጽ 49 )

ፍቅር ማለት ለሚያፈቅሩት ሲሉ ከማይችሉት ጋ መታገል እንጂ የሚያሸንፉትን ማሸማቀቅ አይደለም። ( ገጽ 59 )

➫ ከአማኝ ጥቅማጥቅማችን አንደኛው ከአቅማችን በላይ የሆነ ሁነት ሲጋረጥብን ፈጣሪ ላይ ሙጥኝ ማለት አይደል ?” ( ገጽ 65 )


➫ ለራስ ሰው አለመድረስን ያህል አርፋጅነት የለም። ( ገጽ 70 )

➫ ሴት ልጅ ትታለልልሃለች እንጂ አታታልላትም። ( 72 )


➫ ፍቅራችን ለምናፈቅራቸው እንድንጠነቀቅ ካላደረገን ፍቅራችን የእውነት ላለመሆኑ ምስክር ነው። ( 95 )

➫ ሰው በዕድሜ ብዛት ማስተዋል ከቻለ የሚማረው ነገር አለመፍረድን ነው። ( 96 )

➫ የበዳይን ምክንያት ሳንጠይቅ በደልን ከምንጩ ማድረቅ እንዴት ይቻላል ?” ( 99 )

➫ ችግራችንን የምናይበት መንገድ የገዘፈ ስለሆነ ነው ከችግራችን በታች የምንሆነው። ( 104 )

➫ በአለም ላይ ስሜቱን እንደሚከተል ሰነፍ የለም፤ ስሜቱን ብቻ መከተል የሰው ባሕሪ አይደለም፡፡ ከስሜት እውነት ይበልጣል ፣ እውነት ነው በጊዜ ብዛት የማይደበዝዘው ፣ ስሜት ዘለቄታዊ ደስታን አይፈጥርም። ማደግ ማለት ደግሞ እውነትን እየመረረንም ቢሆን የመዋጥ ክህሎትን የማዳበር ሂደት ነው። ( 118 )

➫ አሸናፊነት የሚመጣው ተጋጣሚ የሚፈልገውን ባለመስጠት ነው። የምንፈልገውን የምናገኘው እራሳችንን ከምንፈልገው ነገር ባለማሳነስ ነው። ( ገጽ 130 )

➫ ራስን የመሆን እና ራስን የማወቅ ጥግ ራስን መቀበል ነው። በዙሪያችን ያሉ ሰዎች እንዲቀበሉን እኛ ቀድመን ራሳችን መቀበል አለብን። ደካማ ሰው ነው ድክመት ላይ የሚመሰጠው ፣ በራሱ የማይተማመን ፣ እንከኑ የሚያሳቅቀው ነው ጉድለት የሚያስሰው። የማይለወጥ ነገርን መቀበል ከራስ ጋ ያዋሕዳል። ያየነውን ጥሩ ነገር በትክክለኛው ሰዓት ማንፀባረቅ በራስ መተማመን ይባላል። በራሳቸው የማይተማመኑ ሰው ማሳነስ ላይ ሲረማመዱ የሚውሉ ናቸው። ( ገጽ 130 )

➫ ማደጋችን የሚለካው የምንፈልገውን ሁሉ ባለማድረግ ነው። ( ገጽ 155 )

➫ ሕመማችን የሚባባሰው የበሽታችን ምክንያቶች እናክምህ ሲሉን አይደል ?” ወዳጃችን ሲያቆስለን ሕመማችን የሚበረታው እንደሚያስብልን ማስመሰሉ ስለማይቀር ነው። ( 155 )

➫ ባልተሳተፍንበት ነገር መስዋዕት የመሆን ያህል ከንቱነት የለም !! ( ገጽ 157 )

➫ ተገማች አለመሆን ዓላማን ለማሳካት ምቹ ነው። ( 162 )

➫ ከተበደለ የበለጠ ፣ መበደሉ የገባው በዳይ ኑሮው ሲኦል ነው !! ( 165 )
_



⚡️ሁሉ
ም አሪፎች ናቸዉ ይቺ ግን ከሁሉም ትለያለች 👇

➫ ሕመማ
ችን የሚባባሰው የበሽታችን ምክንያቶች እናክምህ ሲሉን አይደል ?” ወዳጃችን ሲያቆስለን ሕመማችን የሚበረታው እንደሚያስብልን ማስመሰሉ ስለማይቀር ነው። ( 155 )

ለእናንተስ???
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቆይ ግን ምንድን ነዉ ነገሩ??🙄
       አሚር ሰይድ

   በቃ መፃፍ መናገር አስጠልቶኝ ሰልችቶኝ ነገሮችን እያየሁ ከአቅም በላይ ሁነዉ ዉስጤ እየተቃጠለ ብዙ ነገሮችን እያለፍኩ እና በቻልኩት አቅም ከሚዲያ ርቄ በተቻለኝ  አቅም በቻልኩት ብቻየን እየሰራሁ ነዉ ግን አንድ እጅ አያጨበጭብም ግን አሁን ዘመን ካለ ሙስሊሞች ጋር የኢንሻ አላህና የአላሁ አክበር ከማለት ዉጭ ወደ ተግባር የማይሄዱ ጋር ከመስራት ብቻ መስራት ይሻላል፡፡

በቃ ለሴት የተጣመመ መጥፎ አመለካከት አለህ ምናምን ስድብ ወቀሳ ሲበዛ ከሚዲያ ራሴን አራኩ ግን በቃ ነገሮች አያስችሉም

ዛሬ ወረረኝ በቃ አለ አይደል በጣም ልቤን የነካኝ በጣም ያሳዘነኝ ነገር ገጠመኝና ለመፃፍ ተገደድኩ፡፡
በጂልባብና በኒቃብ ዙሪያ ከምር ከባድ ነዉ ..ጅልባብ ኒቃብ የሸፈናቸዉ ነገሮች እየከበዱ ትክክለኛ ለባሾችን በኛም በሙስሊሙ ለሌላም ሀይማኖት አያጋለጥናቸዉ ነዉ  እያዮቸዉም ነዉ ፡፡

!!!ሴቶች ሆይ እባካችሁ ከአረብ ሀገር ስትመጡ አትልበሱ በቃ ኢትዮ ኤርፓርት ስደርሱ አዉልቁትና ስታምኑበት ልበሱ...ሴቶች ሆይ ኢማን ይጨምራል ይቀንሳል ኢማናችሁ ሲጨምር ወይም አንድ ሁለት ኪታብ ስትቀሩ ዲኑ የገባችሁ መስሏችሁ ኒቃብ ጅልባብ ለብሳችሁ አላህን የማይፈራ ሴት ጓደኛ ይዛችሁ ወይም የቱርክ ልብስ ወይም በራሳችሁ ሳይዝ አሰፍታችሁ መልበስ ስትፈልጉ ኒቃብን ጅልባብን አታሰድቡ እባካችሁ፡፡ ከለበሱ ቡሀላ ኢስላም ከሚሰደብ እባካችሁ በቃ አዉልቁትና እንደገና የጂልባብ የኒቃብ ትርጉሙ ጥቅሙ ሲገባችሁ ልበሱት፡፡
..,አላህን ፍሩ ማለቱ ከቃላት ማባከን ዉጭ ለዉጥ አላመጣም በቃ አላህን አታስቆጡ ዲነል ኢስላምን አታሰድቡ...ኢስላምን መጥቀም  ባንችል በኛ እንዲሰደብ ለምን እናደርጋለን???

ዛሬ ጁምአ የገጠመኝን ልንገራችሁ
እኔ የምኖርበት ሰፈር ቤተክርስቲያን በቅርብ አለ ጠዋት ስወጣ ብዙ ሙስሊም ሴቶች ፀበል ሲያስጠቅሙ ሲገቡ እኔ ለስራ በጠዋት ነዉ ከቤት የምወጣዉ መቼም መንገድ የማያሳየዉ የለም አያቸዋለሁ፡፡ ጠዋት ጠዋት እየመጡ ሳገኛቸዉ እኔ አረ አላህን ፍሩ በቁርአን መጀመሪያ ሞክሩ የሚሰማ የለም ኢንሻ አላህ ብሎ ከማለፍ ዉጭ.. ግዴታ ማድረስ ስላለብኝ አይቶ ማለፍ ወንጀል ነዉ በቻልነዉ አቅም እናገራለሁ...

ዛሬ ያየሁት ግን በቃ ለአቅል ከበደኝ ሁለት ኒቃብ የለበሱ ሴቶች እኛ ሰፈር ያለ ቤተክርስቲያን እናታቸዉ ወይ ዘመዷን ይሆናል ይዘዉ ሲገቡ አየሁ ደነገጥኩ😧😧...ግን ወደ ቤተክርስቲያኑ ሲገቡ እዛ የነበሩ ሰዎች ስልካቸዉን አዉጥተዉ ፎቶ ሲያነሷቸዉ አየሁ   .. ወደ ቤተክርስቲያኑ አልገባ ጁምአ ነበር ጀለብያ ለብሻለሁ ጀለብያ ለብሼ ብገባ የነዛ ሰዎች ካሜራ ዉስጥ እገባለሁ ምን እንደሚያደርጉ ስለማይታወቅ...እስከምትወጣ ወደ 1 ሰአት ያክል ጠበኩ አልወጡም እኔም ከዛ አካባቢ ተንቀሳቀስኩ ... ዛሬ በአይኔ አየሁ ግን ከአሁን በፊትም ይገባሉ አላገጠምኝ ማለት ነዉ፡፡

እና ምንድን ነዉ ነገሩ???ሊታወቅልኝ የሚገባዉ ጅልባብ ኒቃብን ተቃዉሜ አይደለም ግን በጅልባብና በኒቃብ ጀርባ ብዙ ከኢስላም ያፈነገጡ ነገሮች አሉ... ትክክለኛ ኒቃብ ጅልባብ ለባሽ በነዚህ ፎርጅድ ለባሾች አብረዉ እየተወቀሱ አንገታቸዉን እየደፉ ነዉ፡፡


ከምር ጊዜዉ ከባድ ነዉ ብዙ የማቃቸዉ ወንዶች ኒቃቢስት ጅልባቢስት ነች ብየ አግብቻት እንዲህ እንዲህ ሆን እያሉ ብዙ ነገሮች እየሰማን አሁን ዘመን ላይም እያየን ነው...ያኒቃምን የጅልባብን  ትርጉሙን ሳያቁት የሚለብሱትም ግራ እየተጋባን ነዉ፡፡

አሁን ላይ እሷ ሷሊህ ነች ኢማን አላት ወይም ኢማን አለዉ ማለት ይከብዳል .. አፍ ሞልቶ የኔ ልጅ ወይ የኔ እህት እተማመንባታለሁ ማለት ከባድ ነዉ....እኔ እንደሚመስለኝ
ኢማን የሴት ልጅ..ሷሊህ የወንድ ስም ነዉ ወዳጄ🙄..እከሌ ኢማነኛ እሱ ሷሊህ ነዉ ማለት የማይቻልበት ዘመን ላይ ነን ..
ሷሊሀ ነች ሳይሆን በግልባጩ ጧሊሀ የሆነበት ተጨባጭ እያየን ነዉ፡፡


አሁን ሴቱ እሁድ ተጋብቶ ከወር ቡሀላ ብትፈታ ችግር የለባትም
ሀሳባቸዉ ብራይድ ሰርግ እንጂ ነገን ከነገ ወዳስ ትዳር ላይ እንዴት ነዉ ብለዉ ብዙዎች አያስቡም በተለይ ከ22 አመት በታች የሆነች ሴት፡፡
የሴት ኢማኗ የሚለካዉ ሰርጓ አካባቢ ነዉ በፊት ጅልባብ ለባሽ ኒቃብ ናቸዉ የተባሉት ለሰርጋቸዉ ኢማናቸዉ እንደ ወራጅ ወንዝ ወደ ታች ይፈሳል ልባቸዉ ላይ አይረጋም፡፡

የአማረኛ የቱርክ ፊልም እያዩ  በኑሮ ዉድነት እዳዉን ያየ ወንድ ሰርፕራይዝ ምናምን ነዉ ሀሳባቸዉ እንጂ ትዳሬ የምትል ሴት እንጃ እየጠፋች ነዉ፡፡ ወንዱም በሴቱ ባህሪ ማግባት ባለመቻሉ ዝሙት ላይ እየወደቀ ነዉ

⚡️ አንድ ነገር ሴቶች ላስታዉሳችሁ ነገሮች አሁን ወንድን ልትረዱ አልቻላችሁም  የኑሮ ዉድነት
የክርስቲያን ወንድ በ6000 ደመወዙ ማግባት ይችላል፡፡ የሙስሊም ወንድ ግን ከሴቱ ፍላጎት አንፃር 12,000 ደመወዝ ይዞ ማግባት አይችልም፡፡
በነገራችን ላይ ፍቅር ወንድም ሴትም እወዳታለሁ እወደዋለሁ እንጂ ይወደኛል ትወደኛለች ማለት ራስን ማሞኘት ነዉ፡፡ብዙ ያፈቀረ ሰዉ በህይወትህ ምን ተሳስተሀል ቢባል ማፍቀሬ ነዉ የሚለዉ ፍቅር እወዳታለሁ እወደዋለሁ በሉ እንጂ ይወደኛል ትወደኛለች ብላችሁ ራሳችሁን አታሳምኑ በራሳችሁ ብቻ እርግጠኛ ሁኑ....

⚡️⚡️ በተጨማሪ በዚህ 3ወር ዉስጥ Hiv positive የሆኑትን ትዳር ለማገናኘት በሚል ከእነሱ ጋር እየሰራሁ ወላሂ ከባድ ጊዜ ላይ ነዉ ያለነዉ...
አዲስ አበባ,ደሴ,ባህርዳር,ጎንደር,ጅማ,ድሬድዋ,አፋር ክልል,ኦሮሚያ ክልል
ወዘተ ከተማ ላይ ከተለያዩ ሙስሊሞች ነርሶች ጋር ለማገናኘት ጥረን ነበር፡፡
ከባድ ነዉ የሰማሁት ለአቅል የሚከብድ ነዉ
አዲስ አበባ ሆስፒታሎች ደሴ የተለያዩ ከተሞች ላይ ያሉት በብዛት ከወንድ ብዙ እጥፍ ሴቶች ናቸዉ፡፡

አዲስ አበባ የሚያገናኝ ጀመአ ነበሩ እነሱን ስጠይቅ እንኳን Hiv pos ወንድ ኖርማል ወንድ ሴቶችን ለማገናኘት ጀምረን ለትዳር ዝግጁ የሆነ ወንድ አጣን ነዉ ያሉኝ...አሁን አቋም ያለዉ ወንድ የለም የሚያጮልቅ የሚያደባ እንጂ ሴቱ በምላስ ፍቅር ተተብትቧል ግን መቼ ድረስ???

አሁን በተለይ ሴቶች hiv pos የሆኑ እኔ እንኳ አሁን ለማገናኘት የማቃቸዉ ብዛትና ከተለያዩ ሆስፒታሎች ያገኘሁት መረጃ አለቅል ስለሚከብድ ዝምታ ይሻላል..አሏህ ለነዚህ ሴት እህቶች ይድረስላቸዉ፡፡ የሚገርመዉ ብዙ hiv pos ወንድ ወጣት ገና ከ16-25 እድሜ ያለዉ ይበዛል እነሱ የሚሉት አቅም የለንም ነዉ፡፡ ደግሞ አቅም አለን የሚሉት ስናገናኝ 1ሳምንት አዉርተዉ  ስልካቸዉን ጥፍት በቃ ለምን በሴት ልብ እንጫወታለን???
Hiv pos የሆኖት ብቻ ሳይሆን ወንድ ሆይ!!! የትዳር process አገባሻለሁ እያልክ እድሜ ህልሟን ተስፋዋን አታጨልምባት ተስፋ አትስጥ ቶሎ ወስኑ ቀልብ አንስበር

ነገሮችን ስናጠና ወንዶች hiv ሲገኝባቸዉ ራሳቸዉን እየደበቁ በዚና ሴቶችን እያስያዙ እያገቡ እንደሆነ 90% እርግጥ ሁኗል፡፡👇👇
አሁን እኔ በምኖርበት ከተማ ደሴ ከባድ ሁኗል፡፡ ወሎየ የቆንጆ ሀገር እየተባለ Hiv ተስፋፍቷል፡፡
በዚህ ሰሞን አንዲት ልጅ ብቻ ተረድታኝ ደሴ ላይ ትልቅ ስራ እየሰራን ነዉ ፡፡የሚገርማችሁ ከ9 እስከ 12 ክፍል ተማሪዎች hiv ያለባቸዉ በጣም ብዙ ናቸዉ ግን ራሳቸዉን የለብንም ብለዉ አሳምነዋል  እነሱን በምክር
መድሀኒት እንዲጀምሩ እያረገች ነዉ ያለችዉ አላህ እድሜዋን ይጨምርላት፡፡ የአዲስ አበባን አላቅም ሰፊ ስለሆነ ወሎ ጠቅላላ ከተሞች በተለይ ደሴ በጣም ልቅ ተሁኗል፡፡ የአሊሞች ሀገር ወሎ በፊት ድሮ ቀረ አሁን ወሎ የቆንጆ ሀገር እየተባለ ብዙ ሴቶች hiv እየተገኘባቸዉ ነዉ፡፡ በነገረችን ላይ አላህ ተዉበቱን ይስጣችሁ ሸይጧን አሳስቷችሁ ዚና ላይ የወደቃችሁ ወንድም ሴቶች ራሷችሁን ተመርምራችሁ ብታቁ ጥሩ ነዉ...ለወደፊት ሚዲያ ላይ መፃፍ ከቻልኩ የማሳዉቃችሁ ይሆናል ጊዜዉ ከብዷል...እኔ ለራሱ ደንግጬ ሂጄ ተመረመርኩ ..እናም hiv በመመርመር ራሳችንን ብናቅ ጥሩ ነው፡፡

💫💫 እኔም ለወደፊት መስጊድ ኢማሞች ጋር መጅሊስ ድረስ ደርሶ ቋሚ የሆነ Hiv pos የሆኑትን የማገናኘት ስራ ወንዱ ራሱን እንዲያጋልጥ የማድረግ ጥረት እያረኩ ነዉ ኢንሻ አላህ ጫፍ ላይ ደርሻለሁ አላህ ያሳካዉ

ልላችሁ የፈለኩት አሁን በhiv pos ሰሞኑን ለማገናኘት ጥረት ስናደርግ ያወኩትን ትዳር ማማረጥ ያበዛችሁ ሀሳባችሁ ለብራይድ ለሰርግ ብቻ የሆናችሁ ሴቶች በተለይ ከ22 አመት የሆናችሁ ሴቶች በምሳሌ በእዉነታ ላስረዳችሁ ብየ ነዉ ሰከን በሉ ..

እኔ የማቃቸዉ ብዙ ወንዶች አሉ ትዳር ይፈልጋሉ ግን የወር ገቢያቸዉ ከ4,000 እስከ 6,000 የሆነ ግን እንዴት ብለን እናግባ ?? የቤት ኪራይ አስቤዛ ወጥቶ  እንዴት ይበቃል ነዉ የሚሉት ወላሂ ከባድ ጊዜ ነዉ፡፡


⚡️⚡️⚡️የሚገርመኝ ሴቱ ሷሊሁን ኢማን ያለዉን ትዳር ስጠን ብሎ ዱአ ያረጋሉ አንዳንዴም ሰምታችሁ ከሆነ በመስጊድ መዋጮ ጥሩ ትዳር እንዲሰጠኝ ወርቄን ብሬን ሰጠሁ ይላሉ ..ግን በስንት ዱአ ባሉን ሲያገኙ የሰጡትን ወርቅና ብር በ10 አባዝተዉ ባላቸዉ እንዲሰጣቸዉ ይመኛሉ🙄

የህንድ የቱርክ አማረኛ ፊልም ላይ ያለዉን ትዳር እርሱትና በኪራይ ቤት በአንድ ክላስ በ5000 ብር የወር ገቢ ያለዉ ጋር ለመኖር ራሳችሁን ብታዘጋጁ ይሻላል፡፡ካልሆነ ይሄ የኖሮ ዉድነት ወንዱ ትዳርን እየሸሸ ነዉ ያለዉ...
ለሚመጣዉ አመት የመንግስት ስራ ቅጥር የለም ተብሏል፡፡ በጣም ከባድ ነዉ ዩኒቨርስቲ ላይ ስራ ስንይዝ እንጋባለን የተባለ ቃል ኪዳን ፈረሰ ማለት ነዉ ጎበዝ....በተጨማሪ ወንድ 2016 የመንግስት ስራ ባገኝ አገባለሁ ያለ አያገባም ማለት ነዉ፡፡እናም ሴቶች በtiktok በyoutube በህንድ ፊልም በአማረኛ ፊልም ያያችሁትን ትዳር አትመኙ ሰከን ማለት ያስፈልጋል፡፡

ሴቶች እባካችሁ ባህሪያችሁ አቋማችሁ አንድ ይሁን እቤት ጨዋ አደበኛ ..ትቤት እዉጭ ደግሞ ሌላ ..ለትዳር የሚፈልጋችሁ ሌላ አይነት ባህሪ አታሳዩ ..እንደ እስስት የራስህን ባህሪ ሌላዉ ጋር መመሳሰል ለህሊና ከባድ ነዉ በቃ አንድ ባህሪ የማይቀየር ያዙ ይጠቅማችሆል ወንዱንም አታወዛግቡ


⚠️⚠️ እዚህ ቻናል ያላችሁ  ከ6እስከ10 ክፍል ያሉ ሴቶች ልጆች እህት ያላችሁ በጣም ተከታተሉ ስለዚና ቦይ ፍሬንድ ሀራም መሆኑን አስተምሩ፡፡ምን ገጠመኝ መሰላችሁ የአክስቴ ልጅ 7ክፍል ተማሪ ነች ከክላሳ ልጆች ጋር ትግባባለች ጠይቂያት ስትነግረኝ እነሱ ክፍል 42 ሴቶችአሉ ከእነዚህ ዉስጥ 37 የሚወዱት ደብቀዉ የሚያወሩት boyfrind አላቸዉ፡፡
የሚገርመዉ የወንድ ቁጥር አናሳ ሁኖ እንዴት ብየ ሳስበዉ ሴቶች እወቂ አንቺን እወድሻለሁ እያለሽ የሚያወራሽ 5 ወይ 4 ሴት እወድሻለሁ ሊል ይችላል ተብሎ ይገመታል፡፡ እናም ከ7-10 ያሉ ልጆች ጋር ይሰራ
ለምን የጉርምስና ምልክት የሚጀመርበት ስለሆነ፡፡
ማወቅ ያለብን ሴት ልጅ በ9 አመቷ የወር አበባ ታያለች ወንድ ደግሞ በ15 አመቱ ነዉ የዘፈር ፈሳሽ ማየት የሚጀመርዉ.. ተረዱኝ ይሄ ማለት በአመለካከት በአስተሳሰብ በስሜት ደረጃ የ6 አመት ሴት ልጅ ከ12 አመት ወንድ ልጅ ጋር እኩል ነች ማለት ነዉ፡፡ የ18 አመት ሴት ልጅ ከ24 አመት ወንድ ልጅ ጋር እኩል አስተሳሰብ አላት ማለት ነዉ...እናም ሴትን ልጅ 9 አመቷ ነዉ ወይም ገና 14 ወይ 15 አመቷ ነዉ ህፃን ነች ማለት ዋጋ ያስከፍላል፡፡ አኢሻ ረዐ ነብዩ ሰዐወ በስንት አመቷ እንዳገባች የምናቀዉ ነዉ እናም ሴቶች በእናታችን አኢሻ ረዐ እድሜ ከደረሰች ልጅ ነች ማለት ራስን ማሞኘት ነዉ ለአቅመ ሂዋን ደርሳለች በኢትዮ ህግ 18 አመቷ በ2ተባዝቶ መሆኑን አንዘንጋ😊


አንድ ቤተሰብ አለ 10 ክፍል እግል ትቤት የሚማር እኔ የማቃት ጅልባቢስት ነች የምላቸዉ ስናያቸዉ ልብሱን ለብሰዉታል አንገታቸዉን ደፍተዋል ግን በቃ ስልካቸዉን ከፍታችሁ ብታዩት ሞዴላቸዉ ቲክቶከሮች ናቸዉ ..እነሱ እንደ ቲኩተከሮች ሰርተዉ አስቀምጠዉታል በቲክቶክ አይለቁት አላህን ሳይፈሩ ቤተሰብ ፈርተዉ ትተዉታል ግን ቤተሰብ ባይኖር እንደ ለቀቁት ነዉ የሚቆጠረዉ እናም እባካችሁ ሴትን ልጅ ስታሳድጉ  እንደ እህት ሁናችሁ ቢሆን አሪፍ ነዉ፡፡

⚡️⚡️⚡️⚡️ ደግሞ አሁን ለሴቶች ትልቅ አደጋ የዚና መስፋፊያ
የሆኑት ጀመአ ,በጎ አድራጎት ማህበር, የቲም እንከባከብ, አሮጋዉያን እንደጉም,የተቸገረ እንርዳ የሚል ብዙ ኢስላማዊ ጀመአዎች በሁሉም ከተማ አሉ
..እኔ ስማቸዉን መጥራት አልፈልግም የአደባባይ ሀቅ ነዉ በየመስጊዱ በሁሉም ቦታ ከተሞች አሉ ሴቱ ወንዱ አንፀባራቂ ለብሰዉ ሴቱ የዉበት ዉድድር የወጣ ይመስል ተበጃጅቶ ..ጀመአችንን ለማጠናከር እየተባለ
☞ በየመንገዱ ሲዋክ መሸጥ
☞ ቡና እያፈሉ መሸጥ
☞ሴቶች የወንድ ጫማ እስከመጥረግ
☞ ወንድ ሂዶ ሴቷን..ሴቷ ደግሞ ወንዱን የሆነ ነገር ይዞ ግዛኝ ማለት
☞ ወንድ ባለበት ሱቅ 4ሴት ወይ ከዛ በላይ ሴት ያለበት ሱቅ ሰበብ ብሎ ወንድ እየሄዱ በይሉኝታ ብር መቀበል
☞ በየአዳራሹ ተቀላቅሎ መሰብሰብ
☞ የአረጋዉንያ ቤት ማፅዳት እየተባለ 6ሴት 3ወንድ እየሆኑ አብሮ መስራት መሳቅ ምን ይሉታል??
እኔ የሚገርመኝ የሴቶቹ አይደለም ወላሂ እናት አባት እህት ወንድም መንገድ ለመንገድ ስትገራፈጥ ስታሽካካ እያየ መፍቀዱ ነዉ..,
ቆይ እስኪ መንገድ ለመንገድ ለጀመአ ማጠናከሪያ እየተባለ ሲዋክ ወዘተ ከመሸጥ መጀመሪያ የእናት የአባት የጎረቤት የዘመድ ሀቅ ጠብቀሻል

ግልፁን ከተነጋገርን ይሄ ጀመአ አጅር የሌለዉ ንያዉ ሙሀላጣን የሚያስፋፋ የማወራትን ልጅ በምን መንገድ ላግኛት ካፌ ይሻላል ሌላ ቦታ?? ተብሎ ይታሰብ ነበር በፊት ዛሬ ግን በጀመአችን ወርሀዊ ስብሰባ የገቢ ማሰባሰቢያ ስም መገናኘት ነዉ ወዳጄ 😉😉😉 በኢስላም ስም ብዙ ካባ የለበሱ ስራዎች በዝተዋል፡፡ እኔ ጀመአ መቃወሜ አይደለም ግን የትኛዉ ነዉ ከሙሀላጣ የፀዳ ወንድና ሴት የማይቀላቀልበት አላህ ብለዉ የሚሰሩ??
ለአንድ ኪሎ ሩዝ የ10 ቤተሰብ ፎቶ ማንሳት ካሜራ ካልያዙ አይሰጡም..ለአላህ ብለዉ ያለካሜራ አይንቀሳቀሱ በቃ አለ አይደል የሆነ እስልምና በነዚህ ጀመአዎች ሲመዘን እንጃ ነገን ያስፈራል፡፡ እህቴ ሆይ በደንብ እሰቢበት ካለሽበትም አባል ከሆንሽም በደንብ እሰቡበት👇👇
እናም ከሁሉም አቀላቀልኩት ከሚዲያ ጠፋ ስላልኩ ነዉ በቃ የማየዉ የምሰማዉ ልቤን ነክቶኝ ልተንፍሰዉ ብየ ነዉ...ወደዋናዉ አጀንዳ ስመለስ ለወደፊት ደሴ ላይ ስለHIV positive ትዳር የማገናኘቱን እና ያለባቸዉ መድሀኒት እንዲወስዱ ለማድረግ እና ከታይታ የፀዳ ለአላህ ብለዉ ብቻ የሚሰረትን ተኮር ያደረገ በተለይ የተቸገሩና Hiv pos ጋር ያተኮረ የሆነ ተቋም ለመመስረት በስልክ እየተወያየን ነዉ እስካሁን ሂደቱ ጥሩ ላይ ነዉ እናሳዉቃለን...ከብር ማሰባሰብ ምናምን የሌለበት ነዉ ...ሰዉነት ግንባታ ጋር የተያያዘ ነዉ ....እናም ከደሴ ከተማ  ዉጭ ያላችሁ  ወይም በደሴ ያላችሁ እንደዚህ ወገን ለመርዳት በተለይ hiv pos የሆኑት ጋር ትኩረት ያደረገ ንያ ካላችሁ በዚህ bot 👇👇👇

T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

አሳዉቁኝ በጣም ከባድ ነዉ ግን እኔ ባለሙያዎች በስልክ ስለማገኛቸዉ  ሂደቱን እንዴት እንደሆነ አስረዳችሆለሁ መስጊዶች ላይ ያተኮረ ስለሚሆን ሀሳብ አካፍላችሆለሁ በዚህ bot አሳዉቁኝ
👇👇👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot


ለማንኛዉም ገንቢ አስተያየት በዚህ bot ይቻላል
ግን ስድብ ነቆራ አልፈልግም ምክር እቀበላለሁ፡፡ከምር ስድቡ ምኑ ነዉ ከሚዲያ ያራቀኝ ብቻ በማስረጃ አስተያየት መላክ ይቻላል👇👇👇

T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
Audio
የጁሙአ ስጦታ❤️🌟🌻🌻⭐️⭐️

#ቢስሚከ_ነህያ አልገፉር
🌙🌙🌙🌙🌙🌙⚡️⚡️⚡️🌟🌟🌟☀️☀️☀️

#ገፋር #ገፊር #ጋፊር ያለው ልዪነት ምንድነው
ምን ያክልስ ከአሏህ ስሞች ጋር እየኖርን ነው??!!!
https://www.tg-me.com/+-zHkXQeSZdc4MjY0
Audio
የጁሙአ ስጦታ 2 ❤️🌟🌻🌻⭐️⭐️
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

#ቢስሚከ_ነህያ_አል_ወዱድ

🌙🌙🌙🌙🌙🌙⚡️⚡️⚡️🌟🌟🌟☀️☀️☀️

#ዉድ እና #ሁብ  ያለው ልዪነት ምንድነው
ምን ያክልስ ከአሏህ ስሞች ጋር እየኖርን ነው??!!!
وَذِكۡرَىٰ لِلۡمُؤۡمِنِینَ

https://www.tg-me.com/+-zHkXQeSZdc4MjY0
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም እንዴት ናችሁ፡፡

☞በጂን
☞ በሲህር(ድግምት)
☞ አይነ ጥላ(ቡዳ)
ላይ ያተኮሩ ፁሁፎች ከቁርአንና ከሀዲስ በማስረጃ
ምልክቶች እና ሁሉም በቤቱ ያሉ መፍትሄዎች መከለከያዉ ያተኮረ ፁሁፍ ኢንሻ አላህ ቅዳሜ ሀምሌ ➊ ባልተንዛዛ ክፍል እጥር ምጥን ያለ የሚጠቅም ፁሁፍ ይቀርባል፡፡

የተዘጋጀዉ ፁሁፍ 70% መፅሀፍ ሲሆን
የመፅሀፉም ርዕስ
#ድግምት_ሲህር_ምንነቱና_ፈዉሱ  ከሚለወዉ መፅሀፍ ወሂድ አብዱሰላም ፅፎት ሰይድ አሸንፍ ወደ አማረኛ ተርጉሞት ገበያ ላይ ካለ መፅሀፍ የተዘጋጀ ነዉ፡፡
እናንተም ገዝታችሁ መፅሀፉን ሙሉዉን ብታነቡት ተጠቃሚ ትሆናላችሁ፡፡

30% ደግሞ  የዲን እዉቀት ያላቸዉን በመጠየቅና ...ሩቃ ለአላህ ብሎ የሚሰሩትን ከሚነግሩኝ ገጠመኝ አንፃር አተኩሮ የተፃፈ ነዉ፡፡

📌 በዚህ ፁሁፍ 70% ከመፅሀፍ የተዘጋጀ ነዉ ከመፅሀፍ ማዘጋጀት በጣም ከባድ ነዉ ጊዜ ይፈጃል ..አይንንም ይፈታተናል በዛዉ አሁን ትምህርት የተጠናቀቀበት ጊዜ ስለሆነ በማህበራዊ ሚዲያ ርቀን ማንበብ ላይ ብናተኩር የማንበብ ባህላችን ይጨምራል እናም ይሄን ስለሲህር ድግምት ከጨረስኩ ጊዜ እንደምንም ከተመቻቸልኝ ሌላ ርዕስ ተይዞ ከመፅሀፍ እና ከሚያቁ በመጠየቅ አዘጋጃለሁ፡፡
እናም በማቀርባቸዉ ፁሁፎች መፅሀፍ ማንበብ ማቆማችን ምን ያህል እዉቀት እያነሰን እንደሆነ
ሁላችንም ራሳችንን ፈትሸን ....
ከተስማማን በጀመአ መፅሀፍ ማንበብ program
እንጀምር ይሆናል፡፡


📌 ይህን ስለሲህር ጂን ቡዳ የሚያተኩር ፁሁፍ በቻላችሁት አቅም ለዘመድ ጓደኛ ቤተሰብ ሼር በማድረግ ራሳችንን ፈትሸን ሌሎች እንዲፈትሹ እናድርግ፡፡

ፁሁፍ ማቅረብ ታሪክ ማቅረብ ስላቆምኩ ከግማሽ በላይ የሚሆነዉ  የቻናል ቤተሰብ ከቻናል አምልጧል...ለወደፊት ያለዉ በቂ ነዉ ፡፡ ግን ይጠቀማሉ ብላችሁ ካሰባችሁ አዲስ እንዲገቡ  የምፈልጉ ካለ ሼር በማድረግ ለሚመቻችሁ ቤተሰብ ይጋብዙ

መልካም ንባብ ...አንብበን የምናስተነትን ራሳችንን የምንፈትሽ ፈጣሪ ያድርገን

አሚር ሰይድ


Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#የኤልሳቤጥ ታላቅ ወኔና ራዐይ
አሚር ሰይድ

ኤልሳቤጥን ምን ያህል ታቋታላችሁ???

ኤልሳቤጥ የስፔንና የፊሽታላህ መሪ ነበረች፡፡ይህች ሴት ከ30 ዓመት በላይ የሚሆነዉን ዕድሜዋን ያጠፋችዉ ለካቶሊክ እምነት በመስራት ነበር፡፡ለስፔን ሀገሯና ሀይማኖቷ ብዙ ስራዎች የሰራችና መስዋት የከፈለች ናት፡፡ኤልሳቤጥ ሴት መሆኗንም ረሳች፡፡ስፔንን በእጇ እስክታደርግ ድረስ የዉስጥ ልብሷን ላትቀይር ለራሷ ቃልኪዳን ገብታ ማለች፡፡ ይህን ያለችዉ ስፔንን ከመቋጣጠሯ ከረጂም አመት በፊት ነበር፡፡

ቤክርስቲያን የኤልሳቤጥን ማንነት በማነፁ ላይ ትኩረት አድርጋ ሰርታለች፣ተንከባክባታለች፣ጠብቃታለች፣መንግስት እስከ መመስረት እንድትደርስም አድርጋታለች፡፡የሰዉ ሀይልና የገንዘብ ሀይል በገፍ በመለገስ አጠናክራታለች፡፡

ታዋቂዉ የታሪክ ፀሀፊ ፊርናንድ ፊስካይኑ በታህሳስ እ.ኤ.አ1987 ኤልሳቤጥና ጥንታዊ ቀሚስ በሚል ርዕስ መፅሀፍ ፅፏል፡፡ መፅሀፉ በዛ አመት ብቻ አራት ጊዜ የታተመ ሲሆን ፀሀፊዉ በመፅሀፉ ላይ ኤልሳቤጥ ወደ ቅዱስነት ደረጃ ከፍ እንድትደረግ ጠይቋል፡፡
☞በአንደሉስና በገርናጣ ያለዉን የሙስሊሞች ግዛት ለመጨረሻ ጊዜ እንዲወድቅ ያደረገችዉ ኤልሳቤጥ ናት፡፡
☞ኤልሳቤጥ ሙስሊሞችን ለማጥፋት የተለያዩ ሀገሮች ያሉ ክርስትያን አመራሮች በአንድነት እንዲቆሙ ያደረገችዉ እሷ ነች፡፡
☞ኤልሳቤጥ ሙስሊምችን ለማጥፋት በሚደረገዉ ዘመቻ ጦርሜዳ ድረስ በመሄድ ጦርነቱን ትመለከትና ታበረታታ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ገንዘብ እጥረት አጋጥሞ ጌጣጌጦቿን በማስያዝ ሰራዊቱ ደመወዝ እንዲከፈለዉ አድርጋለች፡፡
☞በገርናጣ የመጨረሻ መሪ የነበረዉን አብደላህን ያንበረከከችዉ ኤልሳቤጥ ነች፡፡
☞ኤልሳቤጥ አብደላህን 10ሺ ወርቅ ዓመታዊ ግብር እንዲከፍል አድርገዋለች፡፡አብየላህ ገርናጧን እስኪያስረክብ ድረስ ትንሹን ልጁን በማስያዣነት ይዛበታለች፡፡
☞በመጨረሻዉ እኤአ ጥር 1492 የክርስቲያን ሰራዊቷን ይዛ ገርናጧ ገባች፡፡ ገርናጧን ከተቆጣጠረች ቡሀላ
◇ ሙስሊሞችን በህይወት እያሉ አቃጠለቻቸዉ፡፡😔
◇ ከዚህም በላይ ሙታን ሙስሊሞችን ከመቃብራቸዉ አዉጥታ አቃጠለች፡፡😔
◇ በህይወት ያሉትን በግድ ክርስቲያን እንዲሆኑ አደረገች፡
◇ የሙስሊም አጠቃላይ ንብረታቸዉን ቀምታለች ፡ ዘርፋለች፡፡
◇ በአንደሉስ አዛን ማድረጊያ እስኪጠፋ አዛንም እስከማይደረግ ምንም ሙስሊም እስከማይኖር ድረስ የማጥፋት ዘመቻ አድርጋለች፡፡


ኤልሳቤጥ ኮሎምበስን የአሜሪካን አህጉር ለማግኘት ላደረገዉ አሰሳ በጀት የመደበች ናት፡፡ የአዲሲቱን አሜሪካ ድልብ ሀብት ወስዳ ከስፔን ካዝና ዉስጥ ጨምራለች፡፡ የአሜሪካን ህዝብ አንበርክካ ለመግዛትና ክርስቲያን ለማድረግ የሀይማኖት ሰባኪዎች ሚሺነሪዎች ልካለች፡፡
ኤልሳቤጥ በአዉሮፓና በአሜሪካ ታሪክ ታላቅ ራዕይና ወኔ የነበራት ሴት ተደርጋ በካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ ትታያለች፡፡ኤልሳቤጥ ናት ሙስሊሞችን ከአንደሉስ(ስፔን)ጠራርጋ ያስወጣችዉ ፡፡

ኤልሳቤጥ የሰራችዉ ስራ ለኛ ለሙስሊሞች ክፉኛ የሚያበሳጭ ዉስጥን የሚያደማ ቢሆንም ከፍተኛ ወኔ የነበራት መሆኑን መካድ አንችልም፡፡ሙስሊሞችን ለማጥፋት በፊትም አሁንም የሚደረገዉ ዘመቻ ምን ያህል የከፋና የጠነከረ ለመሆኑ ኤልሳቤጥ ማሳያ ናት

~~~~~~ ዉድ የቻናል ቤተሰቦች ይሄን ስታነቡ ከንፈር ለመንከስ ለመምጠጥ አይደለም ሰዉ ላመነበት ነገር በተለይ ለሀይማኖቱ እንደሷ መሆን አለብን ለማለት ያህል ነዉ ....በኤልሳቤጥ ዘመን ከዛስ ቡሀላ ያለዉ ሙስሊም ማህበረሰብ የኤልሳቤትን ያህል 5% ሰርቷል ወይ?? ኤልሳቤጥ ግን ላመነችበት ሀይማኖት ይሄን ሰርታለች ...መገንዘብ ያለብን ኤልሳቤጥ ሙስሊም ሁና ቢሆን ኑሮ አለም የሙስሊሞች እንደምትሆን ምንም ጥርጥር የለዉም ለምን ስፔን ከ600 አመት በላይ በሙስሊሞች እጅ ነበረች ..እንደ ኤልሳቤጥ ባሉ ለአላማቸዉ ጠንካራ በሆኑ ሴቶች ነዉ የተነጠቅነዉ፡፡


#ሴቶች_ሆይ እራስሽን ዝቅ አታድርጊ ሴትነት ማለት ማንነትን ፈልጎ ለማግኘት ሲባል ተወጥቶ ተሂዶ የማያልቅ ድካም ያለዉ ረጅም ተራራነት ነዉ፡፡ ኤልሳቤጥ ለያዘችዉ አቋም ሀይማኖቷን ለመርዳት የለበሰችዉን ዉስጥ ልብስ ፓንት ሳትቀይር ከ30 አመት በላይ ታግላለች እናንተ ግን በቀን አስሬ ፊትሽን እየታጠብሽ ኮስሞቲክስ እየተቀባችሁ የወንድ ምላስ ተጠባባቂ አድናቂ አትሁኝ፡፡

>> እጅሽን በኮስሞቲክስ ያገረጣሽዉን ለኢስላም ፃፊበት ቁርአን ይዘሽ ቅራበት...
>> እግርሽን ፈግፍገሽ ተቀብተሽ የምትሄጅበትን መድረሳ መስጊድ ሂደሽ ኢስላምን ሸምችበት፡፡

አንቺ የተፈጠርሽዉ ለወንድ ሁነሽ አግብተሽ ወልደሽ ማሳደግ ብቻ ፕላንሽን አታድርጊ፡፡ አግብተሽ ለዲነል ኢስላም ብዙ መስራት እንደምትችይ ብቻ እርግጠኛ ሁኝ፡፡ ለምን ብትይ እንደ ኤልሳቤጥ ወኔ ካለሽ እሷ ትዳር ሳትመኝ ሀይማኖቷን አስከብራለች አንቺም ያገባ ግማሽ ኢማንሽ ስለሚሞላ በተቀረዉ አላህን እየፈራሽ ለሀይማኖትሽ ብዙ መስራት ትችያለሽ፡፡ የህይወት ግብሽን ትዳር ብቻ ነዉ ብለሽ አትሰቢ ..ለምን ብትይ በዚህ ሀሳብ ትዳር ሲጠፋ ስንት ሴቶች እንደ ከፈሩ የምናቀዉ እዉነታ ነዉ፡፡ ነገር ግን ኤልሳቤጥ ካቶሊክ ሀይማኖቴ ይበልጥብኛል ከትዳሬ ብላ ዛሬ ድረስ ላሉት ካቶሊኮች ታሪክ ሰርታ አልፋለች

እናም በዚህ ዘመን ያላችሁ ሴቶች መቼም እንደ ኤልሳቤጥ ጠንካራ ወኔ ያለዉ ለሀይማኖቱ የሚታገል ሴትም ወንድም የለም .ለምን ሁሉም በዱንያ በምዕራባዉያን ፋሽን ኢስላምን አስረክቧል ...በኢስላም ስራ የማይጠቅም የማይጎዳ ሁኖ የሚኖር እንጂ ለወደፊት ለሙስሊም ማህበረሰብ አሻራ የሚያስቀምጥ ለወደፊት ለሚፈጠረዉ ሙስሊም ትዉልድ አሻራ የሚያስቀምጥ እንኳን ሊኖር ትዝ የሚለዉ የለም ፡፡ ሌላዉ ይቅር ሁሉም ከኢስላም ስም ዉጭ በጎን ሌላ ስም ለጥፎ ሌላን አላስቆም አላስቀምጥ ብለዉ ሲጣሉ ለዲነል ኢስላም ሰፊ እዉቀት የሌለዉ ጃሂል ተደናግሮ መንታ መንገድ ላይ ቁሟል፡፡

እንደዉም አሁን ያለዉ ሙስሊም ለወደፊት ለሚመጣዉ ኡማ የሚያስቀምጠዉ ወንዱ ለሴት ለመታየት ብሎ ሙነሺድ መሆን ምኞቱ ሆነ፡፡ ከዛም ነሽዳ ያወጣል አዳራሽ ይከራያል 80% ሴት ይገባል ስታጨበጭብለት ደስ ይለዋል አበቃ ከዛ ቡሀላ ስንት ይሰራል ታሪኩ ብዙ ነዉ....ይሄም አልበቃ ብሎ ባወጣዉ ነሺዳ ህፃናት ቁርአን እየቀሩ እንዳያድጉ ሀፊዝ እንዳይሆኑ የተለያዩ ኪታብ ቀርተዉ ለወገን እንዳይሆኑ ነሺዳ አዳማጭ ሁነዉ ኢስላምን በሂክማ እናስተምር ብለዉ ይነሳሉ...ሴቱም የእከሌ ሙነሺድ ድምፅ ያምራል እሱ ልጅ ይመቸኛል ባይ እንጂ ዲነል ኢስላምን ተምራ ጠንካራ ወኔ ያላት እንደ ኤልሳቤጥ ጠንካራ አቋም አትይዝ በነሺዳ ነብዩን እወዳለሁ ስትል ትዉላለች፡፡

በፊት ሱሀቦች ስለሀይማኖታቸዉ ሲመካከሩ እኔ አሸንፋለሁ ሳይሆን የእሱ ሀቅ ቢሆንስ ነበር ብለዉ መወያየት የሚጀምሩት...ዛሬ ዘመን እንደምናየዉ ሀቅ ሲነገር የማይሰማ ሁሉ ተፈጠረ...ከዛም በተዘዋዋሪ ሀቅ የሚናገረዉ ሰዉ የሚሄድበት አካሄድ ጥፋት ላይ ያለን ከማስተካከል በጥፋቱ ላይ ምን አገባዉ በሚል የብስ ጥፋት እየጨመሩ መጥተዋል..ግን ጥፋቱ ከጥፋተኛዉ ነዉ ወይስ ጥፋትህን አስተካክል ከሚለዉ አካል
ግን የወደፊት ትዉልድ የማይጠቅም የማይጎዳ መሆኑን የምታቁት በፊት አጂ ነብይ ጋር እደተደባለቁ ሰርግ አስጨፋሪ ስም ይዘዉ ነቢይ ዉዴ ..መርሀባ ሲሉ የነበሩ ሁሉ ዛሬ በስመ ታዋቂ ሙነሺድ ስም እህህህ ወዳጄ..ነቢይ ናፈኩኝ....ናፍቆቱህ በረታ..ልሂድ መካ ሊሂድ መዲና...ልሂድ እነአንይ ሾንክይ ጋር...የነቢይ መዉሊድ ናፈቀኝ....እያሉ👇👇👇
ፀጉራቸዉን በምዕራባዉያን እስታይል ተቆረጠዉ ነብዩ ሰዐወ እንወዳለን እያሉ በነቢይ ስም ሴት ማጥመጃ...ሴት ቁርአን እንዳቀራ ኪታብ እንዳቀራ ነሺዳ አዳማጭ እንድትሆን ....
በተዘዋዋሪ ደግሞ የአህባሽ አቂዳን በነሺዳ አላህ ባለቦታ ይገኛል እያሉ  እያስተማሩ ነዉ‼️‼️‼️
እህት አለም ሆይ እና አንቺ የዚህ ዘመን ሙነሺዶች አድናቂ ሁነሽ ነዉ እንዴ ለካቶሊክ እምነቷ ብዙ ገድል የሰራችዉ ኤልሳቤጥ አይነት ለዲነል ኢስላም የምትሰሪዉ???

አሁን ዘመን ያሉ ሴቶች እንደ ኤልሳቤጥ የመሆኑ ሞራል እቅድ ስለሌላቸዉ አላማቸዉ ሁሉ አላህ እንዲያቸዉ ሳይሆን የሚሰሩት ጀዝባ ወንድ እንዲያቸዉ ሆነ፡፡ በተለያዩ ሙስሊም ተብየዎች tv program ዜና አቅራቢ ፕሮግራም መሪ ..በተጨማሪ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ በYoutube በtiktok በቴሌግራም ወዘተ እናስተምራለን ብላችሁ ፋሽን ልብስ ለብሳችሁ ብቅ ብቅ ያላችሁ ሁሉ
አለፍ ሲልም ሀይማኖት አስተማሪ ነን ብለዉ ተነስተዉ አፏን ከምስራቅ ወደ ምዕራብ እያጣመመች ሀዲስ ቁርአን አስተማሪ ሁነዉ እያየን ነዉ....ግራ የገባኝ ወንድ እንዲመለከታት ነዉ ወይስ እሷ አፏን እያጣመመች ስታስተምር ትዉልድ እቀርፃለሁ ብለሽ አስበሽ ይሆን??🤔
#ሴቶች_ሆይ!!! እዩኝ እዩኝ ያለ መልሶ ደብቁኝ ደቡቁኝ ማለቱ አይቀርም...የአንቺን ሚዲያ ላይ መዉጣት የተመለከተ ጉድ ሰርቶሽ መልሰሽ ከሚዲያ ደቡቁኝ እንዳትይ ....ለዚህ መድሀኒቱ ..በስሜትሽና በስሜት ከሚፈርዱ አንቺን እንደሚመችሽ የፈቀዱልሽ ኡለማ ተብየዎች ፈትዋ እራስሽን አግለሽ ...አንቺ ለምሰሪዉ ስራ ምንችግር አለዉ ? ዘመኑ ነዉ ከማለት ቁርአንና ሀዲስ እኔ ለምሰራዉ ስራ ምን ይላል የሚለዉን አስተንትኝ፡፡

#አላህ ጠንካራ ወኔ ካለቸዉ ብዙ ገድል ከሰሩ እንደነ አኢሻ እንደ ኸዲጃ አይነት ሴቶች ስብዕና ይወፍቃችሁ...ኤልሳቤጥ ለካቶሊክ ሀይማኖቷ ለሰራችዉ ታሪክ መቼም አይረሳትም ነገር  ግን  ቅጣቱን የሚሰጠዉ አላህ ነዉ፡፡ የእሷን ፈጣሪ ይወሰነዋል...

እኔ ትኩረት እንድታደርጉ የምፈልገዉ የእኛ ሙስሊም ሴቶች በሚዲያ ወሬ ሳይሆን እንደ ኤልሳቤጥ ላመነችበት አላማ ሟች በተግባር ጠንካራ የሙስሊም መከታ የምትሆኑ ያርጋችሁ ለምን እናንተ ጠንካራ ብትሆኑ የእናትነት ደረጃ ስደርሱ የሚወለደዉ ልጅ እሰቡት እንዴት የሙስሊም ቀኝ እጅ እንደ ሰልሀዲን አልአዩብ ያለ ወጣት በዘመናችን ከእናንተ ማህፀን መፈጠር ይችላልና፡፡

☝️ ነገር ግን አሁን ላይ ልጅ ሲወልድ አዩብ ብሎ አዩብን በተርቢያ በዲነል ኢስላም አሳድጎ አንተ የምወልደዉን ልጅ ሰልሀዲን በለዉ ..የሚል እናትና አባት አለ ግን??? በጭራሽ የለም...እስኪ ያገባችሁ ወይ ትዳር ያሰባችሁ የምወልዱትን ልጅ አዩብ ብላችሁ በአለም ቁጥር አንድ ጀግና ሁሉም የሀይማኖት ተከታይ ስለጀግንነቱ ጥሩ ባህሪዉ ስለሚመሰክሩለት ስለሰልሀዲን አዩብ ታሪክ ሲያድግ አሳዉቁት የወለዳችሁት ልጅ አዩብ ሲወልድ ሰልሀዲን ብሎ አዩብ ለሰለሀዲን የዛን ጀግና ታሪክ ነግሮት እንደሱ ለዲነል ኢስላም እንዲታገል ማድረግ ይቻላል...ግን ለዚህ እቅድ ስራዉ የሚጀምረዉ አሁን አንብባችሁ ዛሬዉኑ ነዉ👌  ከአላህ ጋር ንፁህ ንያ እና ወኔ ያለዉ ትግል ካረግን ስለሀዲን አልአዩብ በዘመናችን መተካት እንችላለን፡፡

አሁን ከኛ የሚጠበቀዉ በኤልሳቤጥ ከንፈር መንከስ ሳይሆን የምናደርገዉ ፊልሚያ ኢስላምን መሉ በሙሉ ከምድረገፅ ለማጥፋት ከምዕራባወያንም ከአገር ዉስጥም ቆርጠዉ ከተነሱ ሰዎች ማህበረሰቦች ጋር መሆኑን በደንብ ተረድተን ዲናችንን ለመጠበቅ ከእነሱ በላይ ቆራጥ ሁነን መነሳት አለብን ኢንሻ አላህ


#ሴቶች_ሆይ!!!
አንዳንድ ወንዶች ሴቶች ተናደዉ ሲከፋቸዉ መፍትሄዉ አዲስ ልብስና ክሪም ሲሰጣቸዉ ይረሳሉ ይባላል😉 አሁን ዲነል ኢስላም ተደፍሯል
...ዲነል ኢስላም የተደፈረዉ በጦርነት ብቻ አርገዉ የሚይዙ አሉ ፡፡ ወላሂ በጦርነት ኢስላምን ማጥፋት እንደማይመች አዉቀዉ
☞በሊፒስቲክ ጦርነት
☞በኮስሞቲክስ ጥርነት
☞በሸሪአ ክሪም ሳይሆን በፋሽን ክሪም ጦርነት
☞በትክክለኛዉ ሂጃብና ጅልባብ ሳይሆን በእነሱ ተመሳሳይ በሆነ ጦርነት...ሴቶችና ምዕራባዉያን መፋለም ከጀመሩ ቆዩ...አሸናፊዉ ግን እስከ አሁን ምዕራባዉያን ኢስላም ጠሎች ናቸዉ....ታዳ አሁን ካላችሁ ሙስሊም ሴቶችና ላመነችበት ለካቶሊክ እመነቷ የሰራችዉ ኤልሳቤጥ ማን በለጠ???
ወይስ ኢስላምን በስጦታ ክሪምና አዲስ ልብስ ቀይራችሁት ይሆን እንዴ🙄


✿ እዉነት ተናግሬ ከዛም አልፎ ከትቤ ከሆነ ከአሏህ ነዉ...ስህተት ተናግሬ ከሆነ ከሸይጧን ነዉ አላህ ራህመቱን ያዉርድልኝ እናንተም አንብባችሁ አዉፍ በሉኝ ...እናንተንም ባነበባችሁት የኤልሳቤጥ ታሪክ ከእናንተ ጋር አመዛዝናችሁ...እኔስ ምን ይጎለኛል እኔም መሆን እችላለሁ ብላችሁ ወኔ ሰናቂ ያርጋችሁ

አብሽሩ አልችልም ማለት የሸይጧን የስንፍና መረማመጃ ድልድይ ነዉ...

እንችላለን !!! እንጀምራለን!!! አላህ ደግሞ ያግዘናል!!!

⚡️መስከረም 15/2014 ተዘጋጅቶ በቻናል ተፓስቶ አሁን በድጋሜ የቀረበ


Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
                  አሚር ሰይድ


            
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
               መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
              ☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
          

                 ⭐️ #ክፍል👉 አንድ 1⃣


⚡️አንዳንድ ሰዎች የጂኒዎችን መኖር ክደዋል በዚህም ምክንያት መተት የለም ይለሉ፡፡
ግን በመተትና በጂኒዎች መካከል ጥብቅ ቁርኝነት አለ ..ጂኒዎችና ሰይጣናት የመተተኛ አይነተኛ ተዋናያን ናቸዉ፡፡

  ጂኒዎች ከሰዎች እና ከመላኢካዎች የተለዩ ዓለም አላቸዉ፡፡ ማሰብ የሚችሉ አዋቂ ፍጡራን ናቸው ፡፡
በመርፌ ቀዳዳ መሹለክ የሚችሉ በሰዉ ደም ዝዉዉር ዉስጥ መንቀሳቀስ የሚችሉ ፍጥረት ናቸዉ፡፡

የሰዉ ልጅ ትክክለኛዉን እምነት መርጦ የመከተል ነፃ ፈቃድ እንዳለዉ ሁሉ ጂኒዎችም አላቸዉ፡፡ከሰዉ የሚለዩበት ዓይነተኛዉ መለያ የተፈጠሩት ከእሳት መሆኑና እነርሱ የሚያዩን እኛ የማናያቸዉ የመሆኑ ጉዳይ ነዉ፡፡

🔰 ከጂኒዎች ዉስጥ ተንኮለኛና ሰዎችን ወደተሳሳተ መንገድ የሚመሩት ሸይጧን ተብለዉ ይጠራሉ፡፡ ስለሆነም ሸይጧን ሁሉ ጂኒ ነዉ ነገር ግን ጂኒ ሁሉ ሸይጧን አይደለም፡፡
እናም ጂኖች መኖራቸዉን ከቁርአን ማስረጃ
☞ከጋኔን የኾኑን ጭፍሮች ቀርአንን የሚያዳምጡ ሲሆኑ ወደ አንተ ባዞርን ጊዜ አስታዉስ (አል-አህቃፍ 29)
በተጨማሪ
☞ አል-ረህማን 33
☞ አል-ጂን 1
☞አል-ማኢዳህ 91
☞ አል-ኑር 21
እንዲሁም በቁርአን ጂኒ የሚለዉ 22 ቃል ጊዜ...ጂኒዎች የሚለዉ ቃል 7 ጊዜ...ሰይጣን የሚለዉ ቃል 68 ጊዜ ...ሰይጣናት የሚለዉ ቃል 17 ጊዜ ተጠቅሰዋል፡፡



አላህ በቁርአኑ እንደተናገረዉ 
>>> ሰወች በነቢዩ  ሱለይማን አለይሂ ሰላም የስልጣን  ዙፋን  በነበረው ነገር ተከተሉ ሱለይማን ደጋሚ አልነበረምና አልካደም ሰይጣኖች ግን ደጋሚ በመሆን በአላህ ክደዋል ይለናል
ነቢዩ ሱለይማን በምድር ላይ ስልጣንን በሰፊ እንዲቆናጠጡ ፈቅዶላቸው ነበረና ሰውን እንሰሳውን ጅኑን ተቆጣጥረው ያስተዳድሩ ነበር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን በጅኖች አለም ድግምትን በመስራት ለሰወች በማስተማር እጅግ የተጠመዱበት ዘመን ነበረና ይህንን ተንኮል ለማስቆም ነቢዩ ሱለይማን የድግምትን መዛግብት በሙሉ ከጅንም ከሰውም ያለውን አሰባስበው በማይደፈረው ሱልጣናቸው ወንበር ስር ቀበሩት፡፡ ምክንያቱም የእምነት መፅሀፍ የተቀላቀሉ ቃላቶች ስለነበሩ ምናልባት በዚያ ዘመን ማቃጠል የማይቻልበት ዘመን ይሆናል ተብሎ ይታሰባል፡፡  ዙፋናቸውን ማንም አይደፈረውም ጅኖች ከተጠጉት ያቃጥላቸዋል በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ነቢዩ ሱለይማን ህይወታቸው አለፈ፡፡

አመታት ተተካኩ ተንኮል ተንሰራፋ የሰይጣን ውስወሳ ጀመረ ...ሰወች ዳግም ሲህር ስለሚባለው ነገር ማሰብ ጀመሩ በዘመኑ የነበሩ የጅን ገባሪ ሰዎች በቂ የድግምት መረጃ በማጣታቸው ጅኖችን አማከሩ ጅኖች ደግሞ እኛ ብንነካው የሚያቃጥለን የድግምት እውቀት ታሽጎ የተቀመጠው የነቢዩ ሱለይማን ዙፋን ስር እንደተቀበረና ከሰዎች ውጭ ሌላ አካል ሊነካው እንደማይችል ለሰወች በመንገር ከነቢዩ ሱለይማን ዙፋን ስር የተቀበረውን የድግምት መፅሀፍ ሰወች አውጥተው ለጅኖች እንዲሰጧቸውና.... ጅኖች እዚያ ላይ ያለውን ነገር በማየት የተሻለ ድግምት ሊያደርጉላቸው እንድሚችሉ ለሰወች አሳምነው መፅሀፉን አስወጡት ይባላል፡፡

በሰወች የወጣውን የድግምት  መፅሀፍ ጅኖች ተቀብለው የተለያዩ ድግምትን እንደ አዲስ አንሰራፍተው ማስተማር ማድረግ ጀመሩ፡፡

    ለዚያም ነው በቁርአኑ ውስጥ ሱለይማን አልካደም ሰይጣኖች ግን ክደዋል ምክንያቱም ሰወችን ድግምት ያስተምራሉ የሚያስተምሩት ድግምት ደግሞ በሁለት ማላኢካዎች አማካኝነት ባቢሎን በሚባለው ምድር ሀሩትና ማሩት የተባሉ መላኢኮች ሰወችን ለመፈተን በማስተማር ሲመጡ ሰወች ተማሩ እነዚያ ማላኢኮች አንድንም ሰዉ አያስተምሩም ከማስተማራቸው በፊት እኛኮ ይሄንን የምናስተምራችሁ ለፈተና ነው አልማርም ይሄንን ተግባር ያለ አማኝ  ነጃ ወጣ የተማረ ግን በፈተና ውስጥ ወደቀ በማለት ይብራሩላቸው ነበር፡፡

  በነወዊ ተፍሲር ደግሞ ሀሩትና ማሩት መላኢካዎች ሳይሆኑ ሁለት ንጉሶች ናቸው በማለት ይፈስሩታል ግን አብላጫዉ ለፈተና የተላኩ መላኢኮች ናቸው የሚል ያመዝናል... አሏሁ አዕለም.... እናም ከማስተማራቸው በፊት እኛ ፈተናዎች ነን ይህን ተምረህ አትካድ በማለት ይናገራሉ ፡፡ ሰዎችም ከሁለቱ የሚማሩት ነገር ባልና ሚስትን አጣልቶ ትዳርን የሚበትን ድግምትን ነው ግን ይሄንን ማድረጋቸው አላህ ካልፈቀደ በስተቀር ማንንም መጉዳት አይችሉም ይለናል አላህ በቁርዐኑ....
አላህ የሚወደዉንም የማይወደዉን ይፈትነዋል...
ሲህር ድግምት እንኳን በሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ  አሰርተዉባቸዋል እናም ነብዩ የተፈተኑበትን  እኛም ተራ ሰዎች በየደረጃዉ ሊፈትነን ይችላል፡፡
ግን ድግምቱ ቢሰራ ቢላክ አላህ ኩን ካለለዉ  የፈለገዉ ጠንቋይ  ምንም እኛ ጋር ቢሰራ ቢልክ ምንም አያደርገን....
ማወቅ ያለብን ነብዩላህ ኢብራሂም የተቀጣጠለዉ እሳት ለብዙ ቀናት ማቀጣጠያ ተሰብስቦ ሲቀጣጠል የተቀጣጠለዉ እሳት በሰማይ የምሄድን  በራሪ ያስቀር ነበር እናም ነብዩላህ ኢብራሂምን በሩቅ በወስፈንጠር ላካቸዉና እሳቱ ሙሀል ቢገቡም አላህ ግን እሳቱን በርደን ወሰላማ አላ ኢብራሂም ብሎ እሳትን አዘዛት እናም እሳቱ ነብዩላህ ኢብራሂም እሳቱ ምንም ሳያደርጋቸዉ ቀረ...በርደን ብሎ ወሰላማን ባይጨምር ኑሮ ብርዱን አይችሉትም ነበር ብለዋል፡፡
☞ ነብዩላህ የኑስ አሳ ሆድ ዉስጥ ኑረዋል እናም አላህ የወሰነዉ ነዉ የሚሆነዉ....
በነብዩላህ ኢብራሂም ታሪክ ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ ... ሰዎች አንተን አንቺን ለመጉዳት ብለዉ ጠንቋይ ቤት ቢሄዱ ቢያሴሩ ቢጠቋቆሙ በመቶዎች በሺዎች ሁነዉ ክፋትን ቢያስቡ አላህ ከጎንህ ካለ በእሱ ተወከል ካለህ ስታገኝም ስታጣም ሲከፋህ ስትደሰትም ሚስጠራኛህ መመኪያህ አላህ ከሆነ ለምን ትንኮላቸዉ የተራራ ያህል ቢሆን አንተን አንቺን አይጎዳም ግን ከአላህ ጋር  ያለንን ግንኙነት መፈተሽ አለብን

🌀 በተዘዋዋሪ አላህ የሚወደዉን ባሪያ ይፈትነዋል ለምን ዱንያ የትንኝ ያህል ክንፍ ቦታ ስለሌላት አንዳንድ በደጋሚዎች በጂኖች ተልከዉ ሲመጡ በእኛም መዘናጋት ተጠቅመዉ አላህም እስኪ ባርያየን በዚህ ሙሲባ ይሸነፋል ወይስ እኔን ይዞ በኔ ተወክሎ በኔ ቃል ቃርአንን ይዞ ታግሎ የጠንቋይን የሳሂርን ትብትብ  ያሸንፍ ወይም ታሸንፍ ይሆን?? ብሎ ሊፈትነን ይችላል፡፡ ይሄን ጊዜ ወደ ቁርአን ወደ ዚክር እንድንመልስ አላህ ጋር ያለንን ግንኙነት ጠበቅ አድርገን እንድንይዝ ሊያስታዉሰን ኢማናችን እንዲጨምር መልሶ እድሉን እየሰጠን ሊሆን ይችላል፡፡

ነብዩ ሰዐወ በሀዲሳቸዉ አላህ በጠረጠራችሁኝ ቦታ ታገኙኛላችሁ ብሏል እናም
🔸 ነገሮች አልሳካ ሲሉ በስራ ስንፍና ምክንያት ስንከስር👇👇
🔹 ትዳር ሲመጣ ከእሱ የተሻለ ሀብታም ወይ ቆንጆ አገባለሁ ብለሽ አስበሽ ስታማርጭ እድሜሽ 27 ሲያልፍ ጠያቂ ሲጠፋ የኔ ሲህር አይንናስ ነዉ ከማለት ይሄን ጊዜ እረጋ ብሎ መወሰን
🔸 አንተም ከእሷ የተሻለ ቆንጆ የተሻለች አገባለሁ ብለህ እሷ ስታገባ ወንድ የሚቀናዉ የሚወዳት ለትዳር የናቃት ስታገባ ይቆጫል እናም ስታምርጥ እያሳለፍ ቡሀላ የትዳር ጡር ሲመጣብህ አይንስ ሲህር ነዉ ከማለት አሁኑኑ ሸርጥ ሳያደርጉ ማግባት
🔹 የራስ ባህሪን ችግር ሳያስተካክሉ ነገር ይገንብኛል እያሉ ከመሻከክ
🔸 መጀመሪያ ላይ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒን ተቅሞ ወይም የሚቀበረዉን ካስቀበሩ ቡሀላ ልጅ ሲፈለግ ክኒን መዋጥ አቁመሽ የሚቀበረዉንም አስወጥተዉ ልጅ ቢጠበቅ እንቢ ሲል ዘመድ ጓደኛ ጎረቤት ሲህር አሰርተዉብኝ ይሆናል ከማለት
🔹 ትምህርት በፊት ጎበዝ ሁና ወይም ሁኖ በራሱ ችግር ወይም ፍቅር ይዞት(ይዟት) የሰነፈችዉን አስነክተዉኝ ወ.ዘ.ተ እያሉ አጉል ጥርጣሬ ከማብዛት በራስ ችግር አንዳንዴ ራሳችንን በዚህ ጉዳይ ባናሳምን ጥሩ ነዉ፡፡

☑️ ብዙ የመፅሀፍ ሰወች ድግምትን በሰፊው ተምረውታል አብዛሀኛው ያውቁታል ድግምት ለፈተና የመጣ ሰወችን ከአላማቸው የሚያስት ህመም የሚያወርስ ብሎም ሲከፋ እስከሞት የሚወስድ ከባድ ስቃይ ነው፡፡  የድግምት አድራጊወች የማድረጋቸው ምክንያት ደግሞ አላህ እንደሚለው{ {ከሰወች ከራሳቸው የመነጨ ምቀኝነት ነው ይለናል}}

ያ ማለት ሰወች
☞ለምን ተፈጠርክ ጀምሮ
☞ ለምን አማረብህ ለምን አገኝህ
☞ለምን አወክ
☞ለምን ከኔ በለጥክ
በማለት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በመመለከት ሌላኛው አካል እንዳይበልጠን በማለት በንፁህ ሰው ላይ የሚተበትቡት ከአላህ በስተቀር ማንም የማያውቀውና የማይፈታው ሰይጣናዊ ወይንም ጅናዊ ኮድ ነው

☑️ ድግምት በተለያዩ ነገር እንደደረጃው ሊደረግ ይችላል
>>  በምግብ
>>  በመጠጥ
>>በመንካት
>> ቋጠሮ በማስቀመጥ
>> በማየት
እና በተለያዩ ነገሮች ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡


ሰውየው ድግምቱን ሲያስደርገው ለደጋሚው እንደሚያቀርበው ክፍያና የድግምት ደረጃ አድራጊው ከአስደራጊ በመቀበል ለጅኑ በሚያቀርብለት የሽርክ መስዋት ግብር ልክ ነው ፡፡ በአመቱ ሲያሳድሱት ከመጀመሪያው የተሻለ  ሌላ ግብር ያስቀምጣሉ፡፡
ማወቅ ያለብን አንዴ በእኛ ላይ ካደረጉብን ማሳደሱ ቀላል ነዉ ...በመንካት / የምትሄድበት ላይ በማድረግ/ ስራ ቦታ ወይም ትቤት ላይ/ የምበላዉ ምግብ/ወይም በተቀመክበት ወይ በልብስህ/ message በመላክ በፁሁፍ መልክ/ ስልክ በመደወል/ ስጦታ የሰጡ በማስመሰል ወዘተ ሊያድሱ ይችላሉ ማሳደሱ ቀላል ነዉ....ከባዱ መጀመሪያ ሳሂሩ ጠንቋየ ጂኑን ወደ ሚደረገበት ሰዉ ሲላክ በሰዉነቱ ዉስጥ ለመግባት የሚያደርገዉ ጥረት ነዉ የሚከብደዉ...ሰዉየዉ በዚክር በቁርአን በዉዱዕ የሚንቀሳቀስ ከሆነ የተላከዉ ጂን በጣጣም ከባድ ይሆንበታል እናም አሁንም አደራ!!! ከአላህየ ጋር ያለን ግንኙነት እንዳይላላ፡፡

➡️ ሰወች ሰው እንዳይበልጠን በማለት
➡️ ሴት ልጅን ለመቆጣጠር ወይም
➡️ ለሪዝቅና ለተተለያዩ ነገሮች ይሄን የፈተና መንገድ ልጅን ግብር በማቅረብ በአላህ በመካድ ሰይጣናዊን ተግባር ረክሰው ጠንቋይ ቤት ሂደዉ በማስደረግ ንፁሀኖችን ይጎዱበታ ያሰቃዩበታል ቶሎ ካልታወቀ እስከ እብደት ሞት ድረስ ሊዳርግ ይችላል፡፡

  ግፋ ሲል የሰውየውን ነሲብ ትከሻ በኮኮብ ቆጠራ በተወለደበት ወር ጨረቃ በማገናኝት የንፁሁን ሰው እድል ወደ ድግምት አስደራጊው እንገለብጣለን የሚል ሀሳብ አላቸው

🟢  አንዳንዱ ደግሞ ከዚህም ሲከፋ ሰውየውን በመግደል የሱን እድሜ እኔ እኖራለሁ በማለት ትልቅ የሽርክ አዘቅት ወንጀል ውስጥ ይዘፈቃሉ


☞ ድግምት ማስደረግም ማድረግም ደጋሚን ሄዶ መጠየቅም ያከፍራል ምክንያቱ ነቢዩ ሰ ዐ ወ አዋቂ ነኝ ብሎ የሚልን ደጋሚ አካል ጋር እሱ ዘንድ የሄደ ሰው በእርግጥ ክዷል ከፍሯል ብለዋል።

የተለያዩ ደግሚወች እንደሚናገሩት ደጋሚወች ማንንም አካል በድግምት ማጥቃት ይችላሉ የሚያቅታቸው ለሀይማኖቱ ቅርብ የሆነን ሰው ብቻ ነው

ሀይማኖተኛ ሰው ላይ ለማድረግ ሲሞክሩ አላህ ድግምታቸውን በሰውየው ተቅዋ ልክ ያስቀይሳቸዋል  ያፈስድለታል ፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ድግምቱ ይዞት በእሩቃ ይለቃል፡፡ ይሄንን ያልባነኑ ሰዎች ስሙ አዲስ በተሰየመ ህመም በህክምና ቆይተው ህይወታቸዉ ያልፋል፡፡ አንዳንዴ ደም ግፊት / የማህፀን ካንሰር /ኩሊሊት ጉበት /ደም ማዘል ፓላራይዝ ማድረግ ወዘተ በሰዉየዉ ላይ የተደረገበት ድግምት ሊሆን ይችላል...ለምሳሌ እኔ በቅርቡ የገጠመኝ የጓደኛየ እናት የማህፀን ካንሰር ተብለዉ በአስቸኳይ በ10ቀን ዉስጥ መሰራት አለባቸዉ ይሞታሉ ተብለዉ አረ ይሄ ነገር ብለን ወደ ሩቃ ወሰድናቸዉ ሲቀራ በሶስተኛዉ ቀን ሲህር ጂን እና የታመመችዉ ሴትዮ ከልጆቻቸዉ እየተደበቁ ገጠር ዘመድ ልጠይቅ እያሉ ለጂን በየአመቱ ያርዱ ነበር ዘንድሮ ስላላረዱ ማህፀናቸዉን እየወጉ ካንሰር እንዳስባሉ ጂነዉ ተናገረ ከዛ በ2ወር ሩቃ ክትትል የሚገበርላቸዉ ራሄሎ ጨገር አንበሴ ነጬ በላ ጥቁር በላ አረ በጣም ብዙ ናቸዉ
በቁርአን ሀይል ሁሉም ለቀቁ ከለቀቃቸዉ ቡሀላ ቸክ ሲደረጉ የማህፀን ካንሰር እንደማያሳይ አረጋግጠናል በአይኔ ያየሁት ነዉ፡፡

ደም ግፊት መድሀኒት የምትወስድ ሴት ታማ ሩቃ ገባች መድሀኒቱን አቆመች ከዛ በሩቃ ክትትል ጂኑ ሲለቅ ሀኪም ቤት ቼክ ስትደረግ ደም ግፊት አለመኖሩን አረጋግጣለች፡፡
እኛ ስንታመም ኢማናችን የቀጠነ ስለሆነ የምንሄደዉ ሀኪም ቤት ነዉ ግን በቁርአን በእጃችን መፍትሄ እንዳለ ዘንግተናል፡፡ ወላሂ ጂኖቹ ሲናገሩ ሀኪም ቤት እኛ ነን ያለነዉ የምናስታምማቸዉ ይላሉ...
ግን እንደዚህ ስል ሀኪም ቤት አትሂዱ ሳይሆን የምንሄድበትን ህክምና መለየት አለብን፡፡ ሀኪም ቤት ብዙ አመታት ተመላልሶ ግን በሩቃ ህመማቸዉን ሲፈወሱ እያየን ነዉ፡፡
ብዙ ማለት ይቻል ነበር ለማመን የሚከብዱ ነገሮች
ግን ለማመን የሚከብዱ ነገሮችን ብናገር ሰዉ ይዘናጋል
መልሶ ሸክ እንዳይፈጥር አለመናገሩ ኸይር ነዉ እንጂ
ብዙ ከባድ በሽታዎች ሀኪም ቤት በተወሰኑ ቀናት በየወሩ የሚያመላልሱ እስከ መተኛት የሚያደርሱ...አንዳንድ ከባድ ለሞት ያደርሳል የሚባሉ በሽታዎች ጂን ሲህር ጋር የተያያዙ ሊሆኑ ይችላሉና ቁርአንን በንጠቀምበት መፍትሄ እንደሆነ ባንዘነጋ ኸይር ነዉ፡፡

#ክፍል 2⃣
ይቀጥላል.....


አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇

T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/10/02 08:24:00
Back to Top
HTML Embed Code: