Telegram Web Link
★ዉድ አንባቢዎች ይሄን ታሪክ እንዲቀርብ የፈለኩት ለኔ ባይጠቅመኝም ግን እንደ እኔ ብዙ የተጎዱ ስላሉ ከኔ ትምህርት እንዲወስዱ እና ተስፋ መቁረጥ እንደሌለባቸዉ ለማስታወስ ያህል ነዉ
★ፀሀፊ አሚር ሰይድ ከደሴ ከተማ ከልብ አመሰግናለሁ በየaudio የላኩልህን እና በስልክ ያጫወኩህን ዉሸት ሳትጨምር እንደዚህ በሚያምሩ ቃላት አሳምረህ በማቅረብህ ከልብ አመሰግናሀለሁ፡፡


የኔ የአሚር ሰይድ ለማጠናቀቅ ያህል በዚህ እዉነተኛ ታሪክ የተወሰነ ልበል፡፡
በዚህ በነዋል ታሪክ ለእሷ ጥንቃቄ ሲባል የእሷ ስም የምትኖርበት ከተማ ተቀይሯል...
   ባለታሪኳ ነዋል ታሪኩን የነገረችኝ ለካሊድ መደፈሯን ከነገረችዉ ቡሀላ ሽማግሌ ሊልክ ሲል ነበር....ከዛ ቤተሰቦቿ ሲጣሉ ሚፍታህ መልሼ ልላክ ሲል እንደ አጋጣሚ እኔን ነበር የምታማክረዉ በሚዲያ ያገናኘን ምርጥ እህት ወንድም ሁነን ነበር ጠዋት ማታ ነበር የተፈጠረዉን እየደወለች እየነገረችኝ በመመካከር ነበር ለዚህ ትዳር  እንድትደርስ የሆነችዉ
☞ሚፍታህ መልሶ ልላክ ሲል የነዋል ሁብ የመጀመሪያ ፍቅር ከባድ ነዉና..ሚፍታህን ፊት እንዳትሰጥ ማግባት እንደሌለባት ያሳመንኳት እኔ ነበርኩ....እኔ ከሚፍታህ የካሊድ ደጋፊ ነበርኩ ሚፍታህን እንዳታገባ ካሊድን እንድታገባ ያደረኩት እሷ ጋር ስንመካከር በማሳመን ነበር መቼም ከታሪኩ ትረዳላችሁ፡ መቼም አላህም የፃፈዉ ነዉ ካሊድ ጋር በመሆኗ ምንም ቁጭት እንደሌለዉ  ትረዱኛላችሁ ብየ አስባለሁ...
ሚፍታህን ነዋል እንደምወደዉ ባቅም ግን የሴት ልጅ ፍቅር ለትዳር በቂ አይደለም እሷን ከ3 አመት በላይ የሚወዳት ብታገባ ይሻላል ብየ ነዉ፡፡ ሲጀመር ሚፍታህ ለሰዉ ልዳርሽ ብሎ ጀምሮ ነዉ በሰዉ እርዚቅ ገብቶ ነዋል ጋር የጀመሩት ካሊድ ግን ሁሌም ይወዳታል ነዋል ትገበዋለች ብየ እኔም በተደዋወልን ቁጥር በሚፍታህ ፍቅር ብትቸገርም ካሊድን እንድታገባ ተፅእኖ ፈጥሬበታለሁ፡፡ የነዋል ባህሪ ደስ የሚለዉ ሰዉ ትሰማለች ታገናዝባለች እንደአሁን ሴቶች ችኩል አይደለችም ..በፊት እሷ በዛ ችግሯ እኔን አማካሪዋ በማድረጓ ሁሌም ትዝ ባለኝ ቁጥር ደስተኛ ነኝ፡፡
ሚፍታህ ሌላ ሲያገባ ምንም እንዳይመስልሽ ነበር ብየ ከእሷ አግብቶ በመራቁ ሞራል ስሰጣት የነበረዉ..ሚፍታህም ጓደኛዉ የሱፍም ሲያገቡ አዉቅ ነበር ለምን ከነገረችኝ ቡሀላ ታሪኩ ላይ ያልተፃፈ ብዙ ፈተና ስለነበር..ይሄን ፈተና እኔ ከደሴ ሁኜ አብረን ነበር በመወያየት በመመካከር ለዚህ ደረጃ ነዋል የደረሰችዉ
☞እኔም ጋር ስታወራ ነዋል በኔ አመለካከት ድንግል ነሽ ብየ ነዉ የማስበዉ ብየ እነግራት ነበር...አራት አመትሽ ነዉ ወዳዉ እናትሽ ደርሳበታለች አንቺም በጊዜዉ ታመሽ አልተኛሽም እናም አትጨነቂ አንቺ ድንግል ነሽ አንቺን የሚያስቸግርሽ የሰዉ ወሬ ተደፍረሻል እያለ እንጂ አንቺ ድንግል ነሽ እላት ነበር፡፡
በነገራችን ላይ እሷ ስታገባ covid ባይሆን እንደ እቅዷ ሀይለኛ ሰርግ ብታዘጋጅ ሰርጉ ለመገኘት ቃል ገብቼ ነበር ግን covid ሁኖ ሰርግ ስለተከለከለ የተካበደ ሰርግ አላረገችም እኔም አልሄድኩም...በሰርጉ ማግስት ሰኞ ለት ጠዋት አሚር የሚገርም ነዉ ድንግል ነበርኩ ስትለኝ ወላሂ ያንን message ሳየዉ የደስታ ለቅሶ ነበር ያለቀስኩት...ለምን በስልክ ከ6ወር በላይ ተወያይተናል ሚስጥሯን ስለነገረችኝ የሆነ ሙሲባ ሲመጣባት ደዉላ አማክራኝ ተወያይተን ነበር የምንፈታዉና

#ይሄን_ታሪክ ከፃፍኩት ቡሀላ በተለያዩ ምክንያቶች በጊዜ ማጣት ላለማቅረብ ወስኜ ነበር ነገር ግን 2012 ረመዷን ሶስተኛዉ ቀን ላይ እሁድ ቀን እንደ አጋጣሚ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ቡሀላ በሪሞት እየቀያየርኩ prgram ሳይ 2012 ላይ ፋናtv ላይ የሆነ እዉነተኛ ዶክመንተሪ ፊልም አይኔ አረፈ
አንዲት ሴት ልጅ ከልጅነቷ ጀምሮ በአባቷ የወሲብ ጥቃት ይደርስባት ነበር ..አባቷ መጠጥ እየጠጣ ማታ ማታ ሁሌ ያስቸግራታል ..ሳትወድ በግዷ አባቷ ጋር ብዙ ቀን ታድራለች...ከዛም ወደ 18ቹ አመት ሲጠጋት ከአባቷ ታረግዛለች...ግን ለማን ታዉራ ለማን ትናገር
??ሁለት ታላቅ ወንድሞች አሏት ግን የየራሳቸዉ ስራ አላቸዉ እቤት አይኖሩም..አባቴ ይደፍረኛል ብላም ለመናገር ትፈራለች...ከዛም ሲቸግራት ለጓደኛዋ ትነግራታለች ..ጓደኛዋ እና ልጅቷ ሁነዉ ጓደኛ መኖሪያ ቤት ይሄዳሉ ..ጓደኛዋ ለእናቷ ነግራት እንርዳት ስትላት..ከአሁን ቡሀላ እሷ ጋር ጓደኛ እንዳትሆኝ ብላ የጓደኛዋ እናትም ከቤት አስወጣቻት...ከዛም ሲጨንቃት ለአባቷ እህት(አክስቷ)ታማክራታለች ..አክስቷም አመነጫጭቃ ከአሁን ቡሀላ ወንድሜን እንደዚህ ብለሽ ብታነሺ በእኔ እጅ ነዉ የምሞችዉ ብላ ከቤት አባረረቻት....ታዳ ይሄን በደሏን የሚረዳት ስታጣ ጓደኛዋ የምትፅፈዉን ደፍተር ብቻ አደረገች

ይቺ ሚስኪን ልጅ ከአባቷ አርግዛ ሆዷ ገፋ..አባትየዉ በሰፈር ልጄ ዱርየ ሆነች ዲቃላዋን ይዛብኝ መጣች እያለ ወሬዉን አናፈሰዉ...የልጅቱ ሁለቱ ወንድሞችም እርጉዝ በመሆኗ ዱርየ ሆነች ብለዉ ከማን አረገዝሽ ብለዉ እንኳ ሳይጠይቁ አኮረፏት... ይቺ ልጅ ለማን ተናግራ ማን ይረዳት??ሒወቷ ገና በልጅነቷ ተበላሸ ህልሟ በአባቷ ጨለመ...ይሄም ሳያንሰዉ በሰፈር ልጄ ዲቃላ አመጣችብኝ እያለ በዉሸት ወሬዉን ነዛዉ፡፡ ልጅቱ የወሰደችዉ እርምጃ መጠኑ ያልታወቀ ኪኒን ዉጣ እራሷን አጠፋች😔😢ከሞተች ቡሀላ ወንድሞቿ ቢያለቅሱ የጓደኛዋ እናት ብትቆጭ ለልጂቱ የጠቀማት ነገር የለም ..
ፓሊስ የሞተችበትን ሲያጣራ በደብተር ላይ የፃፈችዉን መኝታ ክፍሏ አግኝቶ አባቷን አስሮ .ስንት አመት እንደሆነ እረሳሁት እስር ተፈረደበት፡፡

ቆይ እስኪ እንደዚህ አይነት አባት....በልጅነታቸዉ የተደፈሩ ሴቶች ምክንያት የሆኑ ወንዶች የሞት ፍርድ ካልተፈረደበት የሴት ልጅ አስገድዶ መደፈር ያቆማል ወይ???በጭራሽ ወንድ ልጅ ሴትን ልጅ እየበደለ ታስሮ እስከተፈታ ድረስ በልጅነታቸዉ የሚደፈሩ ሴት ልጆች መቼም መቆም አይችልም

የሞተ ተጎዳ አባትየዉ ከእስር ይፈታል መልሶ መኖር ይጀምራል ...እራሷን ያጠፋችዉ ልጅ ግን ወላሂ አሳዘነችኝ አስለቀሰኝ የነዋል ታሪክ ጋር ሳመዛዝነዉ የዝች ልጅ ታሪክ አሁን ድረስ ከአእምሮየ ሊጠፋ አልቻለም.. ይሄን እዉነተኛ ዶክመንተሪ ፊልም ካየሁ ቡሀላ ነዉ የነዋልን ታሪክ ለማቅረብ ያነሰሳኝ፡፡

#የእኔ_አሚር_ሰይድ ልባዊ ምኞቴ ይሄን ታሪክ ያነበበዉ ሰዉ ...ወንድ ለሴት ወገኖቹ እንዲያስብ ..ሴቶችም የወደፊት ትዉልድ በእነሱ ማህፀን የተቋጠረ ስለሆነ በተርቢያ በዲን አሳድገዉ ለዲነል ኢስላም የሚያስረክቡ እንስቶች ካሉበት ተጨባጭ እራሳቸዉን እንዲፈትሹ ነዉ፡፡

እኔ የምፅፋቸዉን ያነበበ ሰዉ እራሱን ቀይሮ ወደ ፈጣሪዉ እንዲቃረብ እና ወደ ወንጀል መንደርደር የያዙ እንዲያፈገፍጉ እና በወንጀል የተዘፈቁ ጥርት ያለ ተዉበት ቶብተዉ ወደ ፈጣሪያቸዉ ያለዉን መንገዳቸዉን እንዲያስተካክሉ እና ማንኛዉም ሰዉ እራሱ ተቀይሮ ማንኛዉንም ሰዉ የመቀየር ተሰጥኦ ስላለዉ ይሄን ተሰጥኦ በተግባር እንዲያሳይ ብር ያለዉ በብር..ሀሳብ ያለዉ በሀሳቡ..እዉቀት ያለዉ በእዉቀቱ...ዲነል ኢስላምና ኢስላም ወንድም እህቶቹ ጎን እንዲሆን ልባዊ ምኞቴ ነዉ፡፡
#ተ............ #ፈ............ #ፀ...... #መ.....

ታሪኩ በ2013 ተነቦ በድጋሜ አሁን የቀረበ ነዉ
⚠️⚠️ከይቅርታ ጋር ጥሩም መጥፎም ማንኛዉንም አስተያየት አልቀበልም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዉድና የተከበራችሁ የቻናል ቤተሰቦች የሆድ ዉስጥ ፉም እሳት ታሪክ ጨርሰናል ፡፡እስኪ ስለታሪኩ ወንድሜችሁ አሚር ሰይድ የመሰለኝን ትንሽ ብቻ ልናገር ለምን አሁን ሰሚ የለም ሁሉም በራሱ አለም ላይ ነዉ ያለዉ

🔵በዚህ ታሪክ ላይ ከሙሉ ፁሁፉ ቢያንስ 20% በራሴ አመለካከት ስላስገባሁ ታሪኩ በመሀል ያሉት የራሴ አመለካከት ስለሆነ ያበቂ ነዉ ግን በተጨማሪ
☞በአሁን ጊዜ በህፃንነታቸዉ ወይም አድገዉ ተገደዉ ሴት ልጅ መደፈር የሴት ልጅ ጥቃት በየሰፈሩ በየመንደሩ የቡና መጠጫ ወሬ ሁኗል..ይሄ ታሪክ በዚህ ሰለባ የሆነች እህታችን እዉነተኛ ታሪኳን አቅርቢያለሁ ግን ማወቅ ያለብን ከዚች ልጅ የባሰ ብዙ የሒወት ተራራን ለመግፋት የተገደዱ እህቶች አሉ ታዳ እነዚህን እህቶቻችንን ማን ነዉ ተርድቶ ከአእምሮ መጨናነቅ ዲፕሬሽን ሊያላቅቃቸዉ የሚችለዉ?? ዘመድ ቤተሰብ ወይስ ጓደኛ??? ወይስ እንደዚሁ ሰዉ ሲያያቸዉ እየሳቁ ብቻቸዉን እንዳለቀሱ እንዲኑሩ የተፈረደባቸዉ እህቶቻችንን ለማን አቤት ብለን ድምፃችንን በሰማን?? ለመንግስት ወይስ ለሀይማኖት አባቶች ወይስ ለፓለቲካ ፓርቲዎች?? ሁሉም ይሄን ግፍ ያወቀዋል ግን ለምን አሁን ድረስ መፍትሄ ለምን ጠፋ?? መቼ ድረስ ነዉ የሴት ልጅ ጥቃት የሚቆመዉ?? ይሄ ጥያቄ የሁሉም ሰዉ ጥያቄ ነዉ መልሱ ግን እስከ አሁን ከሰዎች አንደበት ሲመለስ ሰምቼዉ አላቅም ፈጣሪ የተሻለዉን ያዉቃል ብለን እንለፈዉ ..ግን ለወደፊት ይሄ ነገር መቅረት የሚችለዉ እንዴት ይሆን??እስኪ ሁሉም ብቻዉን ሰአት ሰጥቶ ይሰብበት....

🔴 በታሪኩ ላይ ድንግል አይደለሁም ተደፍሪያለሁ ብላ አስባ ስንት ትዳር ሲመጣ በልጅነቴ ተደፍሪያለሁ ለማለት ስትጠበብ ስትጨነቅ ስንት ስቃይ እንዳሳለፈች አይተናል..ግን ወንድሞቼ ለትዳር ቢክራ መሆን መስፈርት ነዉ ወይ?? በልጅነታቸዉ ሳይወዱ በግዳቸዉ የተደፈሩ..በስራ ብዛት ..በምቾት..በወር አበባ ብዛት አብሮ ድንግልናቸዉ የሚሄድ እህቶች እኮ በጣም ብዙ ናቸዉ..ታዳ ለእነዚህ ንፁህ እህቶቻችን ንፁህ ልባችንን ከፍተን የምንረዳቸዉ መቼ ይሆን ??
በጣም ማሰብ አለብን ይሄ ነገር እኮ እኛ ካልተረዳናቸዉ ለሌላ ሀይማኖት አጋልጠን ሰጠናቸዉ ማለት ነዉ..ለምን ድንግልና ለትዳር መስፈርት ያልሆነ ሀይማኖት ተከታዮች አሉና...


🔴በዚህ ታሪክ ላይ የትምህርት ቤት ላይፍ አይተናል፡፡ የማይካድ ሀቅ ነዉ...አሁን ትምህርት ተዘግቶ ምነዉ ትምህርት በተከፈተ ብለዉ የሚናፍቁ ተማሪዎች ትምህርቱ ናፍቋቸዉ ሳይሆን ላይፉ ናፍቋቸዉ እንደሆነ ጥርጥር የለዉም፡፡ትምህርት ቤቶች ሴትና ወንድ አንድ ላይ እየተማሩ ይሄ ይቀራል ብሎ ማሰብ ቤንዚን ላይ እሳት ጨምሮ አይነድም እንደማለት ይቆጠራል ፡፡ ለምን ነዳጅ ለማስሞላት ገና ማደያ ስንገባ ስጋራ ማጨስ እና ተቀጣጣይ ነገሮች ይዞ መግባት ክልክል ነዉ የሚል በማንኛዉም ማደያ ቦታ ተለጥፏል ፡፡ታዳ ሁሉም ማደያዎች ቅድመ ጥንቃቄ ማስጠንቀቂያዉ ተለጥፏል እኛስ ይሄን የወንድና የሴት አብረዉ እየተማሩ ዱርየ ቢሆኑ ይፈረዳል ወይ??? ግን አንድና አንድ መፍትሄ አለ ይሄም መፍትሄዉ በሁላችንም አእምሮ እና ጥረት የሚስተካከል ነዉ ብየ አስባለሁ .

🔸🔸እስኪ እኔ በራሴ ያጣራሁትን ልንገራችሁ፡፡ ደሴ ከተማ አንድ ጓደኛየ ሳዳትን በደንብ ያቀዋል ከሱ ነዉ ቂርአት የቀራዉ ብሎ አስተዋወቀኝ ከዛም ስለሳዳት ጥርጥር ያለብኝን ነገር ሁሉ ጠየኩት ልጁ ጋር የሚገርማችሁ 99% ተግባባን በጥሩም በመጥፎም ጎኑም ብዙ ነገሮች ተመካከርን ግን ትምህርት ኢህቲላጥ እያላችሁ ለምንድን ነዉ የምከለክሉት?ብየ ጠየኩት..ልጁም ሳዳት አይከለክልም የሚከለክለዉ የደሴዉ ሙስጠፋ ነዉ አለኝ፡፡ እኔም በጣም ቅርብ 6አመት ሙስጠፋ ኪታብ ያቀራዉን ልጅ ጠየኩት
ለምንድን ነዉ ኢህቲላጥ እያላችሁ ትምህርትን የምከለክሉት?? ብየ ጠየኩት
እሱም እንዲህ ብሎ መለሰለኝ ወደ ቁርአን ሀዲስ ስንመልሰዉ መደባለቅ አላህ ከልክሏል ፡፡ እና ነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ እና አራቱ ኸሊፋዎች ዘመን ወንድና ሴት ተደባልቆ አልተማረም ..ደግሞ የበላዮች ህግ የሚለዉ ህገመንግስት እያልን ነዉ የምትማረዉ የበላዮች ህግ ግን ቁርአን ነዉ ..ይሄ ትምህርት ዱንያዊ እንጂ አኼራዊ አይደለም ብሎ መለሰልኝ
..እኔም መጀመሪያ እኮ ኢህቲላጥ ሀራም ነዉ ማለት ያለባችሁ ሴትና ወንድ የማይደባለቅበት ከፍታችሁ ነዉ መከልከል የምችሉት ስለዉ
እሱም ዱአ አድርግ በKGጀምረናል ለወደፊት አንደኛም ሁለተኛም ደረጃ እስከ ኮሌጅ ለመክፈት አስበናል:: በተጨማሪ የሙስሊም ሴቶች ሲወልዱ በሙስሊም ሴቶች እንዲወልዱ እስከ ሆስፒታል ድረስ በደሴ አስበናል አለኝ ፡፡ ከዚህ በላይ መጠየቅ አልፈለኩም አላህ ይገዛችሁ በአቅሜ የበኩሌን አደርጋለሁ አላህ ይገዛችሁ ብየ ጥያቄየን ጨረስኩ፡፡
☞አንድ ነገር ማወቅ ያለብን የሁሉንም የኢስላም ኡስታዞች ትምህርት ማዳመጥ ጠቃሚ ነዉ እኔ የሳዳትንም የሙስጠፋንም የነአቡበከር ያሲን ኑሩ ወዘተ በተመቸኝ አጋጣሚ አዳምጣለሁ ከሁሉም ኡስታዞች የሚጠቅመንን መያዝ እንጂ የአንድ ወገን አመለካከት ጨምድዶ መያዝ ሞኝነት እንደሆነ ይሰማኛል፡፡

ለማንኛዉ አሁን ተደነጋግረናል ፈጣሪ ከድንግርግር ይጠብቀን....
አንዱ ባለፈዉ በደርግ ጊዜ የተማረ ወይ በ19 ክፍለ ዘመን የተማረ መሰለኝ እኔ እስከ 12 ተምሬ እስከምጨርስ 1000 ብር አልጨረስኩም ዛሬ ልጅ ትምህርት ቤት ይዞት የሄደዉ ከ3000 ብር በላይ ሁኗል ብሏል፡፡ እዉነት ነዉ ፓርሳ 1500-1000 ደብተር 800 የትምህርት ክፍያዉ እስክርቢቶዉ ሁሉ ሲሰላ ከ3000 ይበልጣል እናም በኑሮ ዉድነት ወጭ ወጥቶ እየተማሩ ወላጅ ቢከታተል ጥሩ ነዉ፡፡



🔴 ማወቅ ያለብን ጓደኛ ወሳኝነት ነዉ በታሪኩ ላይ ስለ ጥሩ ጓደኛ ብዙ ቦታ አስገብቻለሁ...
☞ሚፍታህ ነዋልን የጀመረዉ የሱፍ ዳረኝ ብሎት እንደሆነ አንብበናል.ሁሌም ቢሆን አደራ ለሀላል ከሆነ የምፈልጋት በጓደኛችሁ አደራ እንዳትጀምሩ ለምን የቅርብ ጓደኛህ አይሆን...ሴትና ወንድ ሲያወሩ ምን እንደሚፈጠር አናቅምና👌 እሱ በአፉ በጣም ቀልጣፋ ከሆነ ሴት ልጅ ልቧ ያለዉ ጆሮዋ ላይ ነዉ ይባላል. እናም የሰማችዉን ሁሉ ስለምታምን አስታርቃለሁ ብሎ ገብቶ አፍኜ ብበላ ብሎ ከኳስ መጫወቻ ሜዳ ዉጭ ጠርዞ እንዳያወጣህ😊

እኔ ወላሂ ከዚህ ታሪክ ጋር የተያዘዘ እዉነተኛ ነዉ..
🔸አንድ በጣም የምቀርበዉ ጓደኛየ ሌላ የእሱ አብሮ አደጉ ጓደኛ አለዉ..ጓደኛዉ አንዲትን ልጅ ይወዳታል ለትዳር እያወራት በመሀል በቀላል ነገር አለመግባባት ይፈጠራል..ላስታርቃችሁ ብሎ ተለሳልሶ ገብቶ አጣልቷቸዋል..ከዛም ለራሱ አድርጎ ሊያገባት ጫፍ ደርሶ ደግሞ ተጣልተዋል፡፡ ግን አስታርቀኝ ያለዉ ልጅ ጓደኛዉ ነዉ እየደበረዉ እየገረመዉ ትችታለሁ ለአንተ ትሁን ብሎ አዝኖ መጥፎም ክፉም ሳይናገረዉ ጓደኝነቱን ሰረዘዉ ..እኔም ወላሂ ይሄን በማድረጉ ባልጣላዉም ግን ለወደፊት እንዳላምነዉ አድርጎኛል..ለምን ነገ የሚሆነዉ አይታወቅምና፡፡
☞ እናም የቻናል ቤተሰብ ምርጥ ወንድሞቼ ለትዳር የሰብካትን ከተጠላህ በሁለታችሁ ብቻ ይፈታ..በሀሳብ ማመን በመነጋገር ማመን አለባችሁ ሚስጥር ከሁለታችሁ ከወጣ ሶስተኛዉ ሰዉ ለምን ይደብቀዋል?? ለምን ከእናንተ አልፏላ... በሁለታችሁ ችግራችሁ  ካልተፈታ ገና ዉስጥ ለዉስጥ አልተናበባችሁም ማለት ነዉ፡፡ አላህ ያግባባችሁ 😊 ሌላ ካግባባችሁ በጣም ግራ ነዉ የሚገባችሁ. ችግርን ሁለታችሁ ተነጋግራችሁ መፍታት ካልቻላችሁ ነገ ስትጋቡ ብትጣሉ አስታራቂ ካልተገኘ አራተኛዉ የአለም ጦርነት ፈጠራችሁ ማለት ነዉ😉👇👇👇
እህቴ ሆይ አስተዉይ
☞መጀመሪያ በአንቺ በቤተሰቦችሽ የመጣ ትዳር ፈላጊ ነዉ ተብሎ 75% ይታሰባል
☞ነገር ግን በጓደኛሽ የመጣ ከሆነ ..አላህን የማፈራ የሙስሊምም ሆነ የሌላ ሀይማኖት ተከታይ ብትሆንም አንቺን ከእሱ በምታገኘዉ ጥቅማ ጥቅም  ልትሸጥሽ እንደሆነ 90% ይጠረጠራል፡፡ እናም ይሄ ልጅ ለአንቺ ያለዉ አመለካከት..ስለ አንቺ ጥሩ ነገር ያወራል ካለችሽ እባክሽ ተጠንቀቂያት ሴት ስትፈግ ሴትን በሴት እሾህን በእሾህ ነዉና..የአንቺ ጠቃሚሽም ጎጅሽም ሴት እህቶችሽ እንደሆኑ ሁሌ አትዘንጊ

🎖🎖ዉድና የተከበራችሁ ቤተሰቦች የማጠቃለያ ፁሁፍ በጊዜ ማነስ አስቤበት አላዘጋጀሁም ነገር ግን በታሪኩ ላይ ብዙዉን ጠቅሸዋለሁ...

መልካም ንባብ ተመኘሁ
አስተያየት አልቀበልም ለምን እራሴ ለራሴ መቋቋም የማይቻልበት አቅም ላይ ተሁኖ አስተያየት መቀበሉ ጥቅም የለዉም..ደግሞ በአስተያየት የሰዉ ልጅ መፅሀፍ ነዉ ብዙ የደበቀዉ አለ አንዳንዴ ስለምሰማ ራሴን መሆን እያቀተ የሰዉ ሀሲብ ሲጨመር ከባድ ነዉ የሚሆነዉ ፡፡ እናም በአስተያየት መስጫ bot ትችትም ጥሩ ሀሳብም ለወደፊት የሚስተካከል ብየ የምቀበለዉ የለኝም...መፃፍ አቁሚያለሁ ይሄም የሆድ ዉስጥ ፉም እሳት ለyoutuber እና ለቻናሎች በማሰብ ነዉ የበፊቱ 45 part ስለነበር ሳይዙን ቀንስልን ስላሉኝ ነዉ 2013 የተነበበ ታሪክ አሁን የተደገመዉ፡፡

ብዙ ቀን ለምን ታሪክ አታዘጋጅም ቻናልህ ሰዉ እየቀነሰ ነዉ ምናምን የሚል አስተያየት አያለሁ...እኔ አንድ ሰዉ ቻናል ላይ ቢቀር አይመለከተኝም እኔ እንደሙነሺዶች ዩቲዩብሮች በስሜ ነግጄ ብር ማግኘት አልፈልግም ሁሉም የራሱ አቋም አለዉ....እኔ የራሴ በጣም ቢዚ የሚያደርግ ስራ አለኝ ፁሁፍ በፊትም በትርፍ ሰአቴ ለሊት ነበር የማዘጋጀዉ እንደሙነሺዶች እንደ አንዳንድ ፀሀፊዎች ሚዲያ ለኔ ቀጥታ ስራየ ሳይሆን ትርፍ ሰአቴን ነዉ የተጠቀምኩበት፡፡ እናም ከቻናል መግባት መዉጣት የባለቤቱ ባለእጁ ዉሳኔ እንጂ ገና ቻናል ሰዉ ወጣ ብየ 100% ሁኜ ልንገራችሁ ለወደፊት የሚዘጋጅ ታሪክ የለም፡፡ብዙ እዉነተኛ ታሪክ በእጄ ነበር ግን ጥቅምና ጉዳቱን ሳነፃፅረዉ ለኔ ስላልተዋጠልኝ ላለመዘጋጀት ወስኜ ትቸዋለሁ፡፡ ይሄም የማይቀየር አቋሜ ነዉ፡፡

ብዙ ሀጃ አለኝ የሰዉ ልጅ ዱንያ ነዉ ይከፋል ይደሰታል..,የኔ መከፋቴ ማዘኔ ጨምሯልና ሙስሊም ወንድማችሁ ነኝ ዱአ አርጉልኝ..,,
እንደበፊቱ አሚር ሰይድ መሆን የማይቻልበት ላይ ነኝ ብቻ በዱአ እንደሚስተካከል አምናለሁ..ነብዩ ሰዐወ ኢማን ይጨምራል ይቀንሳል ብለዋል ኢላህ ኢማኔ እንዲጨምር እናንተም በዱአ አትርሱኝ
መአሰላም

ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሁ ወበረካትሁ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰላም ያለዉ ህይወት ለመኖር አላስፈላጊ ሰዎችን ከህይወትህ ማስወጣት ይኖርብናል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እስከዛሬ ሙነሺዶችን ተጠንቀቁ ስትል ለእነሱ ያለመረጃ ነዉ እነሱን የመዉቀስ ሞራል የለህም እያለች የምትከራከረኝ ልጅ ነበረች ከዛሬ 3 አመት በፊት...እኔም ንዝንዙ ሲሰለቸኝ የዛሬ ሶሰት አመት አካባቢ በሂደት በጊዜ ብዛት የእሱን ጉድ ትሰሚያለሽ እድሜ ይስጥሽ ብየ ክርክሩን አቁመን ነበር...

ይሄዉ ዛሬ ይሄን Video ላከችልኝ በፊት የተከራከርኩህን አዉፍ በለኝ ብላ......

Video ሳየዉ እኔም ገረመኝ😂 አራት አግቡ ምናምን የሚል ነዉ...ብለዉ ብለዉ በምላሳቸዉ
ነቢይ ነቢይ ብለዉ ሲጨርሱ ይሄዉ በኑሮ ዉድነት  አንድ ማግባት አቅቶት እዳዉን አይቶ ይሄዉ በነሺዳ አግቡ እያሉ መጡ ብለዉ ብለዉ በሰላም እየኖረ ያለ ቤተሰብን ሊበጠብጡ ነዉ☺️

በነገራችን ላይ ይሄ ከአንድ በላይ ማግባት የመቃወም የምፍቀድ ሳይሆን የኢስላም ህግ
ሸሪአ አላህ የፃፈዉ አለ ለሁሉም ድንበር ህግ አለዉ በነሺዳ ሶስት አሪት አግቡ ብሎ የሚወጣ አልነበረም..,,

ሴቶች ሆይ ልብ ይስጣችሁ ..አሁን ሙነሺዶች የያዙት አቋም ከባድ ነዉ በዚህ አካሄዳቸዉ ከሄዴ
ከሁለት ወይ ከሶስት አመት ቡሀላ ከባድ የማይፈታ ችግር በዲነል ኢስላም ላይ ሊያመጡ ይችላሉ..
የሙነሺዶች ችግር ስር ሰዷል ብቻ አሁንም እባካችሁ ሴቶች እየተሸወዱ ነውዉዉዉ....,


📚የዛሬ ሁለት ወይ ሶስት አመት በፊት ስለሙነሺዶች ያልኩትን እስኪ ዛሬም ደግሜ ልላክላችሁ ...አሁን ያለዉ ሁኔታ አንፃር አዉነት ነዉ ወይስ አይደለም??

👇👇👇👇
☞ ብዙ ጊዜ ሙነሺዶችን ተጠንቀቁ እያልክ አንዳንድ ሙነሺዶችንም ስም እየጠራህ በVideo እየፓሰትክ ነዉ ይሄ ለሌላ ሀይማኖት ተከታዮች እርስ በራሳችን ስንናቆር ክፍተት አይሆንም ወይ? አንተስ የመዉቀስ ሞራል አለህ ወይ ? የሚል ከበፊት ጀምሮ በተደጋጋሚ ይሰጠኛል አሁንም ታሪኩ ሲያበቃም ብዙ ሰዉ ፅፎት አንብቢያለሁ እስኪ የተወሰነ ልበል

አንተ ለመዉቀስ ሞራል አለህ ወይ ላላችሁኝ ትክክል ናችሁ ወላሂ ሞራሉ ብቃቱ የለኝም ግን የለኝም ብየ እጄን አጣጥፌ አልቀመጥም ብቻ በነዚህ የጊዜ ወጥመዶች የተዘናጋ ካለ እንዳይዘናጋ ማስጠንቀቅ አለብኝ ለምን እኔን በስመ ፀሀፊ አንድ እዉቀት የሌለኝ ሚስጥራቸዉን የሚነግሩት ሲያጡ ከማዘጋጃቸዉ ፁሁፎች ጋር እራሳቸዉን እየፈተሹ ብዙ ሚስጥር በማስረጃ የነገሩኝ እህቶቼ ጋር የብዙ ሙነሺዶች ገበና ለማወቅ ችያለሁ ..እሺ ማወቅ የለብኝም ነበር??? እና የአሁን ሙነሺድች አንድ ሰዉ ሁነዉ ሁለት ቅርፅ ያላቸዉ ናቸዉ ..እናም እኔ እንደማቀዉ በአደባባይ ወላሂ ከተናገርኩት 1% እንኳን የሚሰሩትን ስራ መች ገለፅኩና ..ብቻ ሙነሺዶች እያልኩ እተች ይሆናል፡፡
ወደዳችሁም ጠላችሁም የአሁን ጊዜ ሙነሺዶችና ሚንበር ቲቪ ይዘዉብን የመጡት ጉድ ከአህባሽ ዘመን ካለፈ የባሰ ፈተና እንደሆነ አንዘንጋ፡፡ ለምን አህባሽ ሲመጣ ብዙ ነገሮችን ከዲን የለቀቁ ይፋ አድርጎ ነዉ ሙነሺዶችና ሚንበር ቲቪ ግን በአህባሽ ዘመን የተጃጃለዉን ወጣት ልቦና ስለሚያቁ ወጣቱን ወደማንነቱ ከመመለስ በነሺዳ ስም ወንድ ሴት እየቀላቀሉ ትዉልድን የከሸፈ ቀለሀ እየሆነ ነዉ፡፡ ሙነሺድ ተብየዎች ደግሞ ታዋቂነት በመጠቀም ብዙ ስራ እየተሰራ ነዉ አላማ ኢላማ በሌላቸዉ በሴቶች ላይ

እሺ ሌላ ማረጋገጫ ልስጣችሁ
ዘንድሮ ኢድ ናሁtv ያየ ካለ አንድ ሙነሺድ(ስሙን መጥቀስ አልፈለኩም ያየ ያቀዋል) ቃለመጠይቅ እየተደረገለት..ነሺዳ የጀመርኩት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በArt ነበር የምማረዉ ሙዚቃ ማጥናቱን ትቼ በዛ መንገድ የኒሽዳን ተማርኩ ብሎ አረ ብዙ ሲያወራ ነበር
ከ15 ቀን በፊት ይመስለኛል በbst tv አንዱ ሙነሺድ ቀርቦ(ስሙን አልገልፅም ያየ ያቀዋል) ገና ነሺዳ ስራ በኢትዮ አልተሰራም በሂክማ ነዉ ሰዉ መማር ያለበት እያለ ሲበጠረቅ ነበር
ለወደፊት ምን ሀሳብ አለህ ሲባል..የነሺዳ መለማመጃ ትቤት መክፈት ነዉ ሀሳቤ ብሎ እርፍ ቁርአን ሂፍዝ መድረሳ ቀረ
አንተ በሂወት ዘመንህ የምታደንቀዉ የምትከተለዉ ሰዉ ሲባል ..ማሂር ዘይን ነዉ ያለዉ..ነቢይ እያለ የሚያቋላምጣቸዉ ቁጥር 1 ብሎ መቼ አደነቀ??
እኔ የሰዉ ትችት ነዉ ያጠነከረኝ እንደማሂር ዘይን በሙዚቃ መሳሪያ ስሰራ ሀራም ነዉ እያሉ ሲተቹኝ ለኔ ግን ብርታት ሆነኝ አለ
ከኒሻዳ ዉጭ ምን ስራ አለህ? ተብሎ ሲጠየቅ እኔ ነሺዳ ቋሚ ስራየ አይደለም ዩቲዱብ አለኝ ይከፈለኛል ብሎ እርፍ መገን ጊዜ
እኔ ብዙ የማቃቸዉ ሙነሺዶች አሉ ደሴ እናም የሚሰሩትን በfb በአካል በተመቸኝ አጋጣሚ እከታተላቸዋለሁ፡፡ ብዘ ነዉ ሚስጥሩ ወዳጆቼ
አንድ አብሮ አደግ ጓደኛየ ቁርአን አብረን የቀራነዉ አሁን ሙዚቀኛ ሁኗል..ግን አዲስ አበባ ሲገባ ነሺዳ አወጣለሁ ብሎ ነበር...ለምን ሙዚቃ አወጣህ ስለዉ ምን ልዩነት አለዉ ..እነ.......ሙዚቃ እንዳወጣ ገፋፉኝ አለኝ..ዛሬ ላይ ታዋቂ ወጣት ሙዚቀኛ ሁኗል ስሙ ግን ይቆይ ለምን ብዙ ሰዉ ያቀዋል
ስንት ወጣት ልጆች ቁርአን ሀፊዞች ነሺዳ እናወጣለን ብለዉ አላማቸዉን ስተዉ የቀሩት?ስንት ሰዉ በእነሱ ተሳነፈ ? ስንት ሰዉ ከቁርአን እራቀ?

ብቻ ሁሉም እራሱን ይፈትሽ
ግን አንዷ እህቴ አንዱን ጠይቃዉ የመለሰዉ መልስ ግን መቼም ቢሆን ሊረሳ አይችልም
.እኔ ተቸገርኩ ሙነሺድ ታዋቂ መሆን አስቸጋሪ ነዉ እራሳቸዉ ሴቶች እየደወሉ እያስቸገሩኝ ነዉ ..ምን ይሻለኛል እስከማለት የደረሰም አለ...
ግን ግራ የሚገባኝ መልስ አልባ ጥያቄዉ ጥፋቱ ከእነሱ ነዉ ወይስ አላማ ኢላማ በተቆረሰ ልብ የምትኖረዉ ሴቷ ትሆን? ብቻ አላህ እዉነተኛን የሙስሊሞች መንገድ ለሁላችንም ይምራን

የአሁን የሙነሺዶች አደረጃጀታቸዉን ተንኮላቸዉን ከፊል የአዲስ አበባ ሰዉ እና 80% የደሴ ከተማ ነዋሪ ያቃል ሁሉም ባለበት ከተማ እነሱ ከዞሩ መጠርጠር አይከፋም

📘 አሁን ላይ በተለይ ሴቱ ስንት ኡስታዝ ደአዋ ከማዳመጥ ስንት ታዋቂ ቃርዕ እያለ ቁርአን ከማዳመጥ የተለያዩ አላማ የሌላቸዉን ሙነሺዶች እያዳመጡ ከመስመር እየሳቱ ነዉ...ሌላዉ ይቅር የእነሱ ጠበቃዎች እነሱን ከተናገርክ አይኔን ግንባር ያርገዉ እያሉ ጠበቃ እየቆሙ እያስተዋልን ነዉ፡፡😊ቆይ ግን ሙነሺዶች እነማን ናቸዉ? ነቢይ እያሉ ፓንክ ባላቶሊ ተቆርጦ ፊዳከ ነቢይ ቢል ነብዩን እየወደደ ሳይሆን ሙድ እየያዘ ነዉ ይሄ ደግሞ በአዳማጩም ሙድ እየያዘ ነዉ
ግን ለምን ሴቶች ሙነሺዶችን ይወዳሉ ?? አንዱ አዲስ ነሽዳ የሚያወጣ አንድ ወጠጤ ያለዉን ስሜን ሳልፅፍ ያለዉን ቃል በቃል አንብቡት ማረጋገጥ የፈለገ ከFB በscreen shoot ስላነሳሁት ልኬለት ማረጋገጥ ይችላል

📥📥"""በቅርብ ቀን እንደ ሙነሺድ__ግጥምና ዜማዉ በኔ የተሰራ አንድ የነሺዳ ነጠላ ዜማ ልልቀቅና ሴቱን ሁላ ላሳብደዉ እያሰብኩ ነዉ ፡፡ ሴቶች ለሙነሺድ ያላቸዉን ፍቅር ካየሁ ቡሀላ የተመኘሁት ታላቅ ሙነሺድ መሆን ብቻ ነዉ ፡፡
መልካም እድል በሉኝ"""'
ይላል እና ነገሩ እንዴት ነዉ 🙄ነሺዳ የሚወጣዉ ለሴቶች ለመወደድ ከሆነስ ከዛስ...ከዛስ ከዛስ....ከዛ ቡሀላ ነገሩ ብዙ ነዉ የደረሰባቸዉ ያቃሉ
...የአሁን ሙነሺዶች አቋማቸዉ የዘነጋችን ሴት ማጥመጃ እንጂ የነቢይ ፍቅር ልባቸዉን ነክቷቸዉ አይደለምምምም....የነብዩ ሰዐወ ፍቅር ቢኖርባቸዉ በአደራሽ አጂ ነብይ ሴት ሰብስበዉ መድረክ ላይ ሁነዉ ጨፍረዉ አያስጨፍሩም ነበር.....
በእልክ የሚሄደዉ ሙስሊም በሙነሺዶች አንድ ቀን በየቤቱ ችግር ይዞ ሲመጣ ከረፈደ ስር ከሰደደ ቡሀላ ይረዳል...አረ ሴቶች የሴት ቤተሰቦች እናስተዉል

📘 ነሺዳ እንዲህ ማለት እንዲህ ሽርክ ነዉ ሀራም ነዉ ሲባሉ ሀራም ነዉ ካለማ የብስ እናናደዉ እየተባለ የባሰ ነሺዳ እያወጡ ሙስሊሙን የማይጠቅም የማይጎዳ ማህበረሰብ እያደረጉ ወደ ጀሀነም መንገድ እነሱ ከፊት ሁነዉ ሌላዉ አብሮ እያጨበጨበ እየሄደ ነዉ

📘 ይቅርታ አርጉልኝና እንኳን የአሁን ነሺዳ ተብየ የድሮዉ የየዋሆቹ ለራሱ ረድ ተሰጥቶበታል፡፡ የአሁንማ ለሴት ለመታወቅ ብለዉ አጨመላለቁት...እኔ አሁን ላይ በሙዚቃ መሳሪያ እያቀነባበሩ ሲያወጡ እነዚህ ሰዎች ምነዉ ፔንጤ ፔንጤ አጫወታቸዉ ነዉ ያልኩት ..ለምን ፔንጤዎች ከክርስትና ተገንጥለዉ ነዉ በሙዚቃ መሳሪያ የጀመሩት...አሁን ያሉት ሙነሺዶች እነደዚሁ በሙዚቃ መሳሪያ ጀምረዋል ነገ ደግሞ እንደ......የማይሁንበት ምን ምክንያት ይኖራል ብቻ አላህ ከነዚህ ሰዎች በላእ ይጠብቀን፡፡

👌አንዱ ክርስቲያን ዘመዴ ነዉ የእናንተም እስልምና በሙዚቃ መሳሪያ እንደ ፔንጤ ዘፈን ጀመራችሁ እንዴ ያለኝ..እነሱ በስሜት ሲጓዙ ክርስቲያኖቹ የሙስሊም ፔንጤ ብለዉ ታምፔላ እንደሰጡ መታወቅ አለበት

📘  እግር በእግር የካፊሮችን መንገድ የሚከተለዉ Member tv የነሺዳ ዉድድር አላቸዉ ቀኑን ባላስታዉስም እቤት እንደአጋጣሚ እዛ ላይ ነበር አንዱ የሆነ አልጫ ወንድ መጣና

   አንድ ነዉ አላህ አንድ ነዉ
አንድ ነዉ አንድ ነዉ አላህ አንድ ነዉ
አንድ ነዉ አላህ አንድ ነዉ
አንድ ነዉ አንድ ነዉ አላህ አንድ ነዉ👇👇
እያለ የፈጠረንን ጌታ በነሺዳ መሳለቂያ ማድረጋቸዉ በጣም አሳዛኝ ነዉ ..ይሄን ብዙ የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ይመለከቱታል ግን በጣም የሚያስጠላዉ ሰዉ ትንሽ ስለተዉሂድ ማወቅ ስንጀምር መልሰዉ ወደ ጠማማ መንገድ መዉሰዳቸዉ ዛሬ በስሜታቸዉ ቢጓዝም ነገ ከሞት ቡሀላ ለሁሉም መልስ አለ..ተጠያቂነት አለ

☞ አንዳንድ ሙነሺዶች አንዳንድ የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች Comment ላይ በጣም ደስ ይላል ስላሏቸዉ ለመከራከሪያነት ሌላም ሀይማኖት ይከታተለናል ይላሉ እስኪ እሰቡት አሁን ፔንጤዎች በሙዚቃ መሳሪያ ይዘምራሉ ነሽዳዉ በሙዚቃ ከሆነ ፔንጤ ቢያዳምጠዉ ለእሱ ምንም ልዩነት አይኖረዉምና ይከታተሉታል እነሱ comment ላይ ስለሰጡ ትክክለኛ መስመር መሆናቸዉን ሙነሺዶች ማረጋገጥ አይችሉም...

ብቻ የሆድን ቢያወሩት ሆድ ባዶ ይሆናል እስኪ ነገሩ ብዙ ነዉ ግን በዚሁ ይብቃኝ ሰዉ ያዉቃል የቸገረን የሚተገብረዉ ነዉ ፡፡ እናም የወሬ ሳይሆን የተግባር ሰዎች ያድርገን !!!
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የነቢይ ወዳጆች ተመልከቱ ..በጀመአ ነቢይ ሙሀመድ ሰዐወ ሲያወድሱ🙄

እነዚህ ናቸዉ ኡማዉን በሂክማ እናስተምራለን ብለዉ ራሳቸዉን ያሳመኑት ሙነሺዶች😒
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሸኽ ሙሀመድ ሀሚዲን መስክሩልኝ ብለዋል!
---------------------

በነሺዳ ስም ሙስሊሙን ማህበረሰብ ወደ ዘፈን እየወሰዱ ላሉ ሁሉ...

ዑለማዎቹ ቁርአኑ ሀዲሱ በሚያዘው ለኡማው እውነታውን አስተላልፈዋል።

አድርሰናል መስክሩ ሲሉም አስመስክረዋል።

ስሜት አሸንፎህ በዘመናዊው ነሺዳ የተለከፍክስ አብሽር!! አላህ ተውበቱን ይወፍቅህ እንልሀለን!!!

ከዛ አልፎ ሀላል ነው በሚል ከዑለማዎቹ በልጦ የሚከራከረውና በዲኑ ያለእውቀት የሚፈተፍተው አላህን ይፍራ!!!

#ኡለማዎቹ_መስክሩ_ብለዋል
#እኛም_አድርሳችኋል_ስንል_መስክረናል

ሌሎች ዑለማዎችም እውነታውን በዚህ መልኩ ለዑማው በማድረስ እውነታውን ማስገንዘብና ማህበረሰቡን መታደግ የግድ ሆኗል!!!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሙነሺዶች ሲያማቸዉ ተመልከቱ..ይሄ ጉንፋን ይዞት ነዉ...ወይ ታይፎይድ ወይ ሆድ ቁርጠት ቢይዘዉ ምን ሊል ነዉ☺️

ኢስላምን በሂክማ የሚያስተምሩን ተመልከቱ.... ጉንፋን ሲይዛችሁ እንደዚህ ብታንጎራጉሩበት ይለቅ ይሆናል😆

ኢስላምን በሂክማ የሚያስተምሩ እነዚህ ናቸዉ??? ሁሉም ለህሊናዉ ይፍረድ...የክርስቲያን ሀይማኖት መዝሙር የሚዘሞሩት እና የኛ ሙነሺድ ተብየዎች እስኪ አወዳድሯቸዉ...የክርሲቲያኖቹ በጭራሽ በሚዲያ ላይ አይቀልዱም ጌታ ብለዉ ለያዙት ለሀይማኖታቸዉ ክብር አላቸዉ፡፡

የኛ ሙነሺዶች ግን በቃ የሚፈልጉት ዝና እና የዘናገች ሴት ልብ ማድከም ነዉ....

ብቻ አሁን ሙነሺዶች የያዙት አቋም ከባድ ነዉ በጊዜ መባነን ያስፈልጋል⚠️
ሁሉም ያዳምጠዉ ሩቃ ነዉ ፡፡ downlod አርጋችሁ ሁሌም ጠዋትና ማታ ብታዳምጡት አሪፍ ነዉ

Watch "الرقية الشرعية رقية خروج المس وابطال السحر اقوي رقية شرعية شاملة للسحر والمس والعين والحسد" on YouTube
https://youtu.be/Bu8D2hhY_gk
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🛑 መቼም የማትረሳውን የህይወት ትምህርት የምትማረው ከትልቁ ስህተትህ ነው፤ ብዙም አትናደድ በቀሪው ዘመንህ እንዳትረሳው የተፈለገ ወሳኝ መልዕክት ደርሶሀል  ስለዚህ ሁለት ነገር አድርግ
1. አትድገመው
2. ተማርበት

ህይወትን በጥበብ የሚኖር ሰው ከዚህ የተለየ ምንም አያደርግም።

─━━━━❤️⊱✿⊰❤️━━━━━─


Join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
...... አላጋጠማችሁም.......

ድንገት ወደ ሂወታችን ይገቡና አርፎ የተኛ ልባችንን ይቀሰቅሱታል ፣ በተስፋ ይሞሉናል ፣በምኞት እሩቅ ያሳዩናል ፣ምርኩዝ የሆኑ መስለው እጃችንን አጥብቀው ይይዙታል ፣ያን ሰሞን ሆን ብለው ቀድሞ የማናውቀውን አለም ያሳዩናል  ያው ሰው አይደለን እኛም 🤔 ቀን ቀንን እየተካ ሲሄድ ያ አርፎ የተኛ ልባችን ዳግም ይቀሰቀሳል ፡ትናንትናውን ረስቶ አዲስ የሂዎት መንገድ ይጀምርና ፡ አሻግሮ ነገውን  ያልማል፡ አጥብቆ የያዘን እጃቸው የማይለቀን የማይተወን  መስሎን ሙሉ እኛነታችንን እነሱ ላይ እንጥላለን ፡ እነሱን እንደገፋለን .... ያን ጊዜ ድንገት እንደመጡት ድንገት ምስስ ብለው ከሂወታችን ይወጣሉ... ውረድ ብንለው በዋዛ የማይወርድ የትዝታ ጓዝ አሸክመውን ፡ የማይመለስ ጥያቄ ሰጥተውን እንዲህ ነው ብለው እንኳ ምክኒያታቸውን ሳይነግሩን  ድንገት እንደገቡት ድንገት ጥለውን ይወጣሉ ...🚶‍♀🚶

ሼን


Join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
በፊት ሴት ልጅ ሰነፍ ከሆነች አትማር ማንበብ መፃፍ ካወቀች ይበቃል እስከ 8 ከተማሩ በቂ ነዉ የትምህርት ቤት እና የቤት ዉስጥ ባህሪያቸዉ የተለያየ ነዉ ...ሰነፍ ከሆነች አትማር መማሯ ጉዳት ያመጣል በዲን አሳድጎ በልጅነቷ መዳር ይሻላል....
ወንድም ያዉ ነዉ ግን ጉዳቱ ለሴት በጣም ያመዝናል ስል..... በተደጋጋሚ አንተ የድሮ ሰዉ ነህ ለሴት መጥፎ የተጣመመ አመለካከት አለህ ተብየ ነበር

እድሜ ለትምህርት ሚኒስተራችን ለዶክተር ብርሀኑ ነጋ🙂 እንኳን ሰነፍ ሴት ተማሪ ወንድም ቢሆን ሰነፍ ከሆነ መማር እንደሌለበት ትክክል መሆኑን ዘንድሮ በ12 ክፍል ፈተና ዉጤት አሳይቶናል

በጣምም ብዙ ትምህርት ቤቶች አንድ እንኳ ተማሪ ያላሳለፉ እንዳሉ መቼም ሰሞታችሆል...ለወደፊት የትምህርት ጥራትን በአሁኑ አጀማመሩ ጥርት ያለ ትዉልድ እንደሚፈጥር ባለሙሉ ተስፋ ነኝ...

መቼም መምህሮቹ ማሰቢያቸዉ ከሰራ  ከአሁን ቡሀላ ትምህርት ቤቶች እንዳይወቀሱ እንዳይተቹ እየጓፈፉ የሚያሳልፉ አይመስለኝም ለምን በአሁኑ የትምህርት ሚኒስተር አያያዝ ስወድቁ ትምህርትቤቱን እንደሚገመግም ባለሙሉ ተስፋ ነኝ...
ለማንኛዉም በተለይ ለሴቶች ሰነፍ ተማሪ ከሆነች ይሄኔ በሀላሉ ጥግ ቢይዙ ኸይር ነዉ ባይ ነኝ😊

ለወደቃችሁ ተማሪዎች የስራ ዉጤት ነዉ ምንም ማለት አይቻልም ያለፋችሁ ግን ከእናንተ ጀምሮ ያለዉ ተማሪ ምርጥ ትዉልድ እንደሆነ አርጋችሁ አስባችሁ ጥሩ ደረጃ እንደምደርሱ ባለሙሉተስፋ ነኝ ለምን ዝምብሎ ግቢ ገብቶ ላይፍ እንቅጭ;boy frind ..girl frind እያለ ከሚያለቃቅስ ስራፈት እና
በዘር በፓለቲካ ዝባዝንኬ እያነሳ የሚበጠብጠዉን ቦዘኔ የማይጠቅም የማይጎዳን የአፈር ገንፎን ዶክተር ብርሀኑ ነጋ ደህና አድርጎ አበጥሮታልና😉 አሁን ዩኒቨርስቲ የሙህራን ህልም ያለዉ ለሀገር ለወገን የሚበቁ ትዉልዶች ማፍሪያ ይሆናል፡፡



ደግሞ በፊት ያልኳቸዉ ሙነሾዶች የያዙት አቋም ከባድ ነዉ ተጠንቀቁ ስል ነበር...የዛን ጊዜም እተች ነበር ግን ይሄዉ ሁሉም ነገር ይፋ እየወጣ ነዉ

የእነሱም ጉድ ሚዲያ ላይ እያያችሁ ነዉ ሲያገቡም ሲፈቱም☺️በአዳራሽ  ሰብስበዉ ሲጨፍሩ ሲያስጨፍሩ....
እኔ የምመኘዉ ቦዘኔ ተማሪን ዶክተር ብርሀኑ ነጋ አደብ እንዳሲያዘልን ..በዲን የሚያላግጡ ሙነሺዶችን ቁርአን መቅራት ሀዲስ ማዳመጥ ትተዉ አብረዉ እያንጎራገሩ የሚዉሉ የሙነሺድ ተከታይ አድናቂዎች 80% በላይ የሚሆን ሴቱን ከነሺዳ አዉጥቶ በቁርአን በተዉሂድ የሚያረጥብ አንድ ጀግና እንደሚፈጠር ኢንሻ አላህ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ጀሊሉ ሆይ ለሰነፍ ለቦዘኔ ተማሪ ዶክተር ብርሀኑ ነጋን እንደላክልን☺️ በዲን ለሚቀልዱና እነሱን ለሚከተሉ ሁሉ ቀጥተኛ መንገድ የሚመራን የማንም ፊርቃ አባል ያልሆነ ከዚህ ትዉልድ አዉጣልን ያረብ

ለማንኛዉም ለዶክተር ብርሀኑ ነጋ ትልቅ ክብር አለን🙏
ይህን ፁሁፍ ለመፃፍ የዘገየሁት ያዉ ከሚዲያ ራሴን ሳላገለልኩ ነዉ ያለፋችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ

የወደፊት የሚፈጠረዉን ደግሞ አብረን እናያለን
መልካም ጥሩ የህይወት ዘመን ተመኘሁ


⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
اسلام عليكم ورحمة الله وبركاته
Amir  seid dena neh?
Abshr hulum neger yalfal bcha ante tegstegna hun ALLAH kante ga new,ALLAH SUBHANEHU WETEALA ytebkh,enam bekrbu wede telegram alem endemtmeles  tesfa aregalehugn
ALLAH Imanh ychemrlh🤲...

ye mekelle lij negn

Channelhn befit awkow neber  abzagnawochu  tarikoch anbibyachaw nebere enam bzu tmrt kante Channel aggnichalow جزاك الله خيرا but 2 amet yakl  internet alneberem....
Be gugt yante channel etebk neber
Alhamdulilah ahun tekefto egna sngeba ante tefahbn ALLAH be kheyr ymelsh...

Yetefahbet mknyat balekewm انشاء الله tmelesaleh biye tesfa argalehugn...
Ende mitaweqew egnam betam bekebad chgr lay new yenebernew bihunm hulum neger alfo  negerochn be ALLAH fkad eyetestekakelu ygegnalu...
Slehonem yedunya musibawoch ena fetenawoch ayalkum ena hulum neger lekheyr new bleh dua arg انشاء الله
ALLAH SUBHANEHU WETEALA kalehbet chgrh yawtah...جزاك الله خيرا

ትግራይ ክልል ያሉ በፊት የኔን ቻናል ሲከታተሉ የነበሩ ብዙዎች በአስተያየት ከመቀሌ ከአድዋ ወዘተ እየላኩልኝ ነዉ ይሄ የአንዱ ቤተሰብ አስተያየት ነዉ፡፡ አልሀምዱሊላህ ያ ቀን አልፎ ለመገናኘት በቃን አልሀምዱሊላህ
ከትግራይ ክልል ኢንተርኔት እንደተከፈተ የኔ ደህንነት አስስቧችሁ ለጠየቃችሁኝ ከልብ አመሰግናለሁ🙏


አሚር ሰይድ
2024/09/21 17:20:41
Back to Top
HTML Embed Code: