Telegram Web Link
አል-አኒስ የኦን ላይን ት/ት ቤት`_

በዩቲዬብ ቻናሉ የተጅዊድ ትምህርቶችን ሲያቋድሰን እና በኦን ላይን ት/ት ቁርአንን በማስቀራት የሚታወቀው ናሲህ ሚዲያ መጭው ረመዷንን አስመልክቶ አዲስ ነገር እንካችሁ እያለ ይገኛል። ይሄውም 👇👇👇
ሙስሊሙን ማህበረሰብ በሚመቻቸው ሰአት እና ባሉበት ቦታ ሆነው ከቁርአን ጋር የሚተዋወቁበት እና የሚማሩበት *አል-አኒስ የኦን ላይን ት/ት* ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቆ በምዝገባ ላይ ይገኛል።

ከዚህ በፊት ያስቀራበት የነበረውን የአቀራር ስርአት በማዘመን መጭውን የተከበረ ወር ከ ቁርአን ጋር የምንከብርበት ይሁን ይለናል

💠ቂርአቱ የሚሰጠው በዙም አፕሊኬሽን በመሆኑ በኡስታዞች እና በተማሪወች መካከል ጥሩ በሆነ መስተጋብር የመማር ማስተማር ሂደቱ ይካሄዳል።
እንዲሁም በሌሎች አማራጮች:- ዋትሳፕ እና ኢሞ ቂርአቱ የሚካሄድ መሆኑ ለሁሉም ተደራሽ ይሆናል።
የሚሰጡ ትምህርቶች ♦️ለጀማሪ ተማሪወች ቃዒዳ
♦️ቁርአን በነዞር
♦️ቁርአን በተጅዊድ እና የተጅዊድ ኪታቦች
♦️የተውሂድ እና የአቂዳ ደርሶች
የምዝገባ ጊዜ ውስን በመሆኑ ቀድመው ይመዝገቡ።📲251 906443888
📲251 931800885
የዋትሳፕ ሊንክ......https://chat.whatsapp.com/L0udcLn0Zj4DyEc5qr5i1y
የቴሌግራም ሊንክ https://www.tg-me.com/+3js98as5D2tmN2M0

ከላይ ባሉት ስልክ ቁጥሮች በቴሌግራም ዋትሳፕ እና ኢሞ መመዝገብ ይችላሉ።
_አል-አኒስ ይለያል!_
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አል-አኒስ የኦን ላይን ት/ት ቤት`_

በዩቲዬብ ቻናሉ የተጅዊድ ትምህርቶችን ሲያቋድሰን እና በኦን ላይን ት/ት ቁርአንን በማስቀራት የሚታወቀው ናሲህ ሚዲያ መጭው ረመዷንን አስመልክቶ አዲስ ነገር እንካችሁ እያለ ይገኛል። ይሄውም 👇👇👇
ሙስሊሙን ማህበረሰብ በሚመቻቸው ሰአት እና ባሉበት ቦታ ሆነው ከቁርአን ጋር የሚተዋወቁበት እና የሚማሩበት *አል-አኒስ የኦን ላይን ት/ት* ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቆ በምዝገባ ላይ ይገኛል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አለማችን ላይ ካሉ ቢሊየነሮች መካከል አንዱ አንድቀን በሚዲያ ቀርቦ ጋዜጠኛዋ "እስኪ ስለስኬትህ ምንጭ ንገረን" ትለዋለች። ቢሊየነሩም ከኪሱ ባዶ ቼክ አውጥቶ ቀን ፅፎ ይፈርምና የምትፈልጊውን የገንዘብ መጠን ፃፊ ይላታል። ጋዜጠኛዋ ኮስተር ብላ "እኔ ስራ አለኝ ደሞዝ አለኝ ጥሩ ኑሮ አለኝ። ልለምን አይደለም ብላ ቼኩን ትመልስለታለች። እሱም "የስኬቴን ምንጭ አይደል የጠየቅሽኝ" አላት። አዎ አለች። ባለሀብቱም "አየሽ እኔ ያገኘሁትን እድልና አጋጣሚ ሁሉ ሀላል እስከሆነ ድረስ አላባክንም እጠቀማለሁ አንቺ ቼኩን ተቀብለሽ ቢሊየን ፅፈሽ ቢሆን ከቢሊየነሮች አንዷ ትሆኚ ነበር አላት

🌷ረመዳን የለውጥ ቼክ ነው። ለምሳሌ ሱና የፈርድ ያህል ይመዘገብልሀል። ፈርዱ ደግሞ በሰባ ይባዛልሀል። ስለዚህ ህይወትህ ላይ የምትፈልገውን ፅፈህ የመለወጥ እድሉን ፈጣሪ ሰቶሀል።

ፈጣሪ ዱአቸውን ከወደደላቸው ከተቀበላቸው ያድርገን ...ፁመዉ ተራቡት ከተባሉ ሚስኪን ባርያዎቹ ሳይሆን ለፆመኞች ለብቻ ለተዘጋጀዉ የጀነት በር የምንገባ ያድርገን
...ሴቱንም በረመዷን የምግብ ሙያ መለማማጃ ከማያደርጉት ያርጋችሁ😊

ወደ ከፍታ፣ ወደ ለውጥ ጎዳና፣ ወደ ክቡር ሰብዓዊነት፣ ወደ በረካ፣ ወደ እዝነት፣ ወደ ነፍስን መግርያ፣ ወደ እርቅ ማዕድ፣ ወደ ሰላም፣ ወደ ስክነት፣ ወደ አብሮነት፣ ወደ ተወዳጁና ተናፋቂው፣ የኸይር ወር ወደ ሆነው፣ የማይጠገበው ውድ የሆነው የረመዳን ፆም በአላህ ፍቃድ እንኳን አደረሰን።
መልካም ስራቸው ከሚበዛላቸው፣ ጊዜያቸውን ከሚጠቀሙት፣ በኸይር ከሚያሳልፉት፣ ለወንጀላቸው መሀርታን ከሚያገኙት፣ በጀነት ከሚበሰሩት ሰዎች መሀል አላህ እንዲያደርገን ዱዓዬ ነው።




ረመዳን ሙባረክ!!!


https://www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጎንደር ፒያሳ የሚገኘው እርግብ በር መስጅድ
||

ፍትሕ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ታፍነው የሽብር ጥቃት እየተፈጸመባቸው ለሚገኙት የጎንደር ሙስሊሞች


ሀገር አጥፊ የአክራሪዎች ትሩፋት!
እኛ ስናውቀው፣ አባ-ሼህ ከማል የክርስቲያኑም አባት ነበሩ። እርሳቸውን <አናስቀብርም> ያሉ አክራሪ ክርስቲያኖች ግና - ከሀጅ ኢልያስ መካነ-ቀብር ድረስ ተሰልፈው አይናችን እያየ በድንጋይ ጀምረው፣ ቦምብ ወረወሩ። መትረየስ ተኮሱ። የተደራጁ ሀይሎች መሣሪያ ታጥቀው ቀባሪውን ወገን ማጥቃት ጀመሩ። ከ10 ሠዎች በላይ ተመትተዋል። የሞቱም አልሉ። መስጅዶች እየተደበደቡ ነው። የሙስሊሞች ቤት፣ ሱቅ፣ ተንቀሳቃሽ መኪና በአሰሳ እና በጥናት እየተጠቁ ነው። ከተማው መንግሥት ያለው አይመስልም። በፍፁም ሀላፊነታቸውን እየተወጡ አይደሉም! የተቋማት አመራሮችን እንኳን ለማግኘት አልፈቀዱም። የሆነው ይኸው ነው። ስለሚሆነው ደግሞ እንመክራለን። ኢንሻአላህ ፅንፈኛን ሁሉ እንቃወማለን! በቆምንበት ለማለፍ አናመነታም!!!
Kedir taju

https://www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አቃጠሉት!

#update ጎንደር
~ እስካሁን በተገኘው መረጃ፣ አስራ-አንድ(11) ሠዎች ለህልፈት በቅተዋል።
~ አሁንም ድረስ ወደ ሆስፒታል እየገቡ ያልሉ ቁስለኞች መኖራቸው ታውቋል።
~ የተኩስ ድምፅ ረግቧል። የቃጠሎ ምልክቶች አሁንም ድረስ ይታያሉ።

~ አንድ ሚኒስተር፣ በቅርበት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛል።
~ የፀጥታ አካላት መሀል-ከተማ እና መስመር(መንገድ) አካባቢ በውስንነት ተሰማርተዋል።
~ ነጃሺ መስጅድ አካባቢ፣ ክርስቲያን ወጣቶች የማረጋጋት ሥራ እየሰሩ መሆኑ ተሰምቷል።
~ ገብርኤል መስጅድ ለከፍተኛ ቃጠሎ ተቃጥቷል።
~ አሁን ከመሼ ሠዎች እየተገደሉ መሆኑም ተነግሯል(ቀበሌ 06 አካባቢ/ቅዳሜገበያ አካባቢ)።
~ ሁሉም እንቅስቃሴ ተገትቷል።
....
Kedir taju

#Stop_Muslim_Genocide_in_Gondar
አስቸኳይ መልዕክት ነው። ሼር አድርጉት

በጎንደሩ ጥቃት ሌሎች አከባቢዎች ያሉ ክርስትያን ወንድሞቻችን ተጠያቂ አይደሉም፣ ልንጠብቃቸው ይገባል!

ጎንደር ለተፈጸመው ድርጊት ተጠያቂው ጥቂት የጎንደር አክራሪ እንጂ በሌሎች አከባቢ ያሉ ክርስትያን ወንድም እህቶቻችን አይደሉም።

ስለዚህም በየትኛውም ቦታ የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታይ ወንድም እህቶቻችን፣ ወገኖቻችንን ምንም አይነት ጥቃትም ይሁን ሌሎች ነገሮች እንዳይደርስባቸው ጥበቃ ልናደርግ ይገባል።

አንዳንድ አካላት ኃይማኖታዊ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ እየሰሩ በመሆኑ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ ሙስሊም ለሀገር ሠላምና መረጋጋት ሲል የራሱን ደህንነት እንዲጠበቅ፣ ሁከትና ብጥብጥ ከሚፈጥሩ ጉዳዮች እንዲርቅ፣ ከሌሎች ኃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ አጥፊዎችን እንዲያወግዝና መንግስት ጥፋተኞች ለሕግ እንዲያቀርብ በሰከነ ሁኔታ እንዲያግዝ አበክረን እንጠይቃለን።

ኃይማኖታችን አንዱ ባጠፋው ሌላውን የሚቀጣና እርምጃ የሚወስድ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ባለመሆኑ ሁላችንም ሙስሊሞች እንድንረጋጋ በአሏህ ስም እንጠይቃለን።

በጎንደር በአክራሪዎች ሕይወታቸው ለተቀጠፉ ሙስሊም ወንድሞቻችን አሏህ(ሱ.ወ) ማረፊያቸውን ጀነተልፊርዶውስ እንዲሰጣቸው እንለምነዋለን። አሏህ ሆይ! ማራቸው፤ ማረን

ሠላም፣ ፍቅር ፣ አንድነት ...ለሁላችንም!
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
======
የቤተ ክህነቷ ሰዎች እነ ዲያቆን አባይነህ ካሴ በዛሬው ዕለት በጎንደር ሙስሊሞች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የሽብር ጥቃት እንዲካሄድ ያደረጉት የጎንደር ሙስሊሞች ጎዳና ላይ እናፈጥራለን ብለው ዝግጅት መጀመራቸውን ተከትሎ ቀድሞ ለማክሸፍ መሆኑን በግልፅ አሳውቀዋል።

የሽብር ጥቃቱ አቀናባሪዎች ለኛ ባይጠፉንም በግልፅ «እኛ ነን!» ብለው መምጣታቸው መልካም ነው።

ለመሆኑ ቢታወቁስ የሚያግዛቸው እንጂ የሚቀጣቸው መንግስት መች አገኙና!
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
#Stop_Muslim_Genocide_in_Gondar
በሚዲያ profile በማድረግ ሌላ ማድረግ ባንችል በፆመኛ አንጀታቸዉ ለሚሰቃዩ የጎንደር ሙስሊሞች ድምፅ እንሁናቸዉ
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
" ንገሩ ለነዛ "
ወዲያ ወደ ጎንደር
ጥሰው ክብር ድንበር
ማን አለብኝ እብሪት
ለጫሩ እሳት ክብሪት
ንገሩ ለነዛ ..
የዝምታን ዋጋ በፍርሀት ላሰሉ
ንገሩ ለነዛ መስጊድ ላቃጠሉ

ታሪክ የማይረሳው ያፄ በደል አዝሎ
ታግሶ በኖረ ሀገር ትቁም ብሎ
ሰላም ይሻል ብሎ አንገት ስለደፋ
ተቻችሎ ሳይሆን ችሎ ቀን ቢገፋ
መስሎ ከታያችሁ ሙስሊም እንደፈሪ
መታደል ነው ለሱ ለዲን የሞት ጥሪ
ንገሩ ለነዛ .....
የዝምታን ዋጋ በፍራት ላሰሉ
ንገሩ ለነዛ ሙስሊሙን ለጠሉ

አዎ ንገሯቸው እምነት ላይ ላሴሩ
ንፁሀንን ገለው አጉል ለፎከሩ

ይሻል ተብሎ እንጂ መኖሩ ተዋዶ
ድንበር ለጣሰማ እሱው ወዶ ፈቅዶ

እንኳን ብርቱዉ አማኝ _ የኔ አይነቱም ሰነፍ
በእምነቱ ለመጣ _ ከፊት ለመሰለፍ
በጭራሽ አይሰጋም _ ከሞት ለመጋጨት
ክብሩ ነዋ ለሱ 💪
ለስልምናው ሙቶ _ ለጀነት መታጨት
.... ንገሩ ለነዛ .....❗️❗️❗️

#ሼን
https://www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
<<የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል>>
አሚር ሰይድ

‼️ራዕይ በተግባር የሚቀረፅ ህልም እንጂ በአእምሮ ብቻ የምናስበዉ መዳረሻ አይደለም፡፡


አንድ ልጅ እናቱ ጋር ይኖራል ከዛም እንቁላል ይሰርቃል እናቱ ዝም አለችዉ ከዛ በሂደት የሌላ ሰዉ ዶሮ ይሰርቃል ከዛም ሌባ ሲባል እናቱም ስትቆጦ
ልጁም"" እናቴ ምነዉ በእንቁላሉ በቀጣሽኝ ዶሮ ባልሰረኩ "" አላት..

ምን ለማለት ፈልጌ ነዉ ሞጣ ላይ ባደረጉት ድረጊት ስላልተቀጡ አሁንም በእነሱ አልፈረድም
የእኛ ዝምታ ጥግ ደረሰ
የእነሱ ጥጋብ ሞልቶ ፈሰሰ
ችግሩ ከራሳችን ነው ጠንካራ ሁኖ ማሳየት አቃተን ተጠራቅመን የአገሪቱ ከግማሽ በላይ ነን እያሉ ወሬ ስም ብቻ ...የአሁን ዘመን ሙስሊም እሰዉ ቤት የሄደ እንግዳ ይመስል መሽለጥለጥ ማሽቃበጥ ይወዳል፡፡ የሀይማኖት መሪ ተብየዎች በተለያየ ጊዜ ሙስሊሞች ሲገደሉ ሲፈናቀሉ ለሙስሊሙ ከመድረስ ድምፅ ከማሰማት ይልቅ ከመንግስት ሹመኛ ጋር ፎቶ መነሳት ይቀላቸዋል፡፡ጠና ቢል ቢሰሩ ሰላማዊ ሰልፍ ወይ በየመስጊዱ ተቃዉሞ ከዛ ቆፍጠን ያለ የአቋም መግለጫ አንብቦ ይበተናል ሙስሊሙ ቁጣዉን በሰልፍ በመስጊድ ባነር አሰርቶ ፎቶ ተነስቶ በሚዲያ ይለቃል ከዛ ይረሳል በዛዉ ተድበስቦሶ ያልፋል፡፡
ከመንግስት ጎን ይለጠፉና የእብድ ገላጋይ ዲንጋይ ያቀብላል ነዉና ነገሩ መንግስት የጠቀሙ መስለዉ ሙስሊሙን ግን እንዲጎዳ ያደርጋሉ፡፡


☞በሂደት የ ጎንደርን መስጅድ ለመገንባት እና ወንድሞቻችንን ለማቋቋም ተብሎ ገንዘብ ይሰበሰባል ....ዲኑን እየተጫወቱበት ያሉ የሴት ሊቀመንበር ሙነሺዶች ስለ ጎንደር ጥቃት ነሺዳ አዘጋጅተዉ ለአንድ ቀን ይለቀሳል....ከዛ በቲሸርትና በባነር የጎንደር ሙስሊሞች ህመም የኔም ህመም ነዉ ይባላል....ከዛስ .....ከዛማ ዝም ዝም ነዋ ሌላ ምን ይፈጠራል፡፡ ሙስሊሙ ልቡ በዱንያና በሴት ፍቅር ታዉሯል አዉርቶ ይቀራል ከዛ እነሱ እንደ ስለት በአመት አንዴ የሚፈልጉትን አጀንዳ ያስፈፅማሉ፡፡
☞የሚገርመዉ አሁን ድረስ ብሄርን ከእስልምና የሚያስበልጥ መኖሩ ነዉ ...የዛሬ 2 አመት በፊት በፁሁፍ ስለአማራ ክልል ሙስሊም ፅፌ የአማራ ክልል የሚኖሩ ሙስሊሞች ተችተዉኝ ከቻናል ፁሁፉን ለመሰረዝ ተገድጄ አጥፍቸዋለሁ ..የዛን ጊዜ የተናገርኩት በሁለት አመቱ በጎንደር ሙስሊሞች ላይ ደረሰ ...ምን ዋጋ አለዉ
በፊት ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ
አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ

እናም እኛ ሙስሊሞች የምናየዉ የዛሬን እና የነገን ብቻ ነዉ እንጂ ከትናንት ወዳ ምን ነበር? ከነገ ወዳስ የዛሬ አመትስ ምን ይፈጠራል?ብለን ማሰብ ስለማንችል እነሱ ግን ለወደፊት 50 ወይ 60 አመት ፕላን አዉጥተዉ ሲንቀሳቀሱ በእነሱ ወጥመድ እንወድቃለን፡፡
ስለ ኢትዮጲያ የምንሰማዉ የ13 ወር ፀጋ ነገር ግን የምናየዉ የ13 ወር ለሙስሊም ጥላቻ ነዉ፡፡

☞ግን የጎንደር ሙስሊሞች በረመዳኑ በጥይት ያስፈጠሯቸዉ በአደባይይ ኢፍጣር ላይ የታቀደ ነበር ..ግን በቀብሩ ጀመሩት እንጂ ..ግን ይሄ የአደባባይ ኢፍጣር እኔ ብዙም አልተዋጠልኝ ጉዳቱ ግን አንደ ጎንደር ያሉ ሙስሊሞችን ዋጋ አስከፍሏል፡፡
እኛ ሙስሊሞች የምንዋረደዉ በሱና በኸይር ስራ መሸቀዳደም ትተን ከሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች ጋር ፉክክር ስንገባ ነዉ ዉድቀታችን መታወቅ አለበት፡፡ አሏህ በተከበረ ቅዱስ ቁርአኑ በዱንያ እነሱ እንደሚደሰቱ ግን በአኼራ እንደሚቀጡ ነግሮናል እነሱ በስኳር መንፈስ መንገዱን አደባባዩን እንደፈለጉ ሲጠቀሙበት እኛ ሙስሊሞች እነሱ ጋር ምን አፎካከረን?? የነብዩ ሱና ይበልጣል ወይስ ከአነሱ ጋር ፉክክር??
☞በደሴ በነበረዉ ኢፍጣር አይቻለሁ ሴቶች እንደ ኢድ ልብስ ለብሰዉ ተኳኩለዉ ፊታቸዉን በቡርሽ ቦርሸዉ ነበር የመጡት እናም በዛን ጊዜ ታዳ በዛ የአይን ዚና የእጅ ዚና የአፍ ዚና ወዘተ ወንጀል መሰራቱ ይቀራል ወይ?? በአደባባይ ኢፍጣር ወንድ ሴት ፊት ለፊት እየሆነ ሲያፈጥሩ አይተናል ይሄ የነብዩ ሱና ነዉ ወይ??
☞የኢፍጣሩ ብር ከተለያዩ ባንኮች እስፓንሰር ተደርጓል ..በወለድ የሚሰሩ ባንኮች ለዚህ ኢፍጣር ሰጥተዋል ...ግን ይበቃል ወይ?? ይሄ ጥያቄዉ ለአሊሞቻችን ነዉ

☞ በተለይ ሴቶች በTik tok በfb youtube ለመልቀቅ ነበር አመጣጣቸዉ...ብዙ ሰዉ የሄደዉ ማለት ይቻላል ብዙዉ ኢንተርኔት ላይ ተጥዶ tik tok እና fb ላይ ነበር
☞ ከፍጥሪያዉ ቡሀላ አንዳንድ ጀመአዎች በተለይ የአህባሽ አቂዳ የሚከተሉ ለብቻቸዉ ተገንጥለዉ ወንድ ከሴት ተቀላቅለዉ መንዙማ ከፍተዉ ሲጨፍሩ አይቻለሁ ...
ይሄ ሁሉ ማስረጃ በስልኬ video አለኝ ግን ሁሉም በሚዲያ ግልፅ ማድረግ አግባብ አይደለም፡፡
መዉሊድ የተጀመረዉ ቀስ በቀስ ነዉ ወደ ሰዉ ልብ የሰረፀዉ ..የኛም ህዝብ ይሄ የአደባባይ ኢፍጣር በአመት አንዴ በሆነ ቁጥር የሚመጣዉ ትዉልድ ሱና ነዉ ብሎ እንዳይዘዉ☺️ ያሰጋል
እናም አላህ ካደረሰኝ ለሚመጣዉ አመት ረመዳን ከአደባባይ ኢፍጣር ተብየ አዲስ የመጣ አንድነትን ለማሳየት ተብሎ ብዙ መዘዝ ይዞ ለሚመጣ እኔ አልሳተፍም...መታወቅ ያለበት ይሄ የራሴ ብቻ አመለካከት ነዉ፡፡

☞ በፊት ከዛሬ 3 አመት በፊት ጀምሬ ሙነሺዶች የያዙት አቋም ከባድ ነዉ ነቢይ እያሉ ሌላ ነዉ እቅዳቸዉ እል ነበር...በዚህ የተነሳ ብዙ ሰዉ ይወቅሰኝ ነበር...ይሄዉ ዛሬ አሊም የሚሰማ ጠፍቶ ፈተዋዉም ደአዋዉም ከሙነሺዶች ሆነ ...እኔ የሚገርመኝ በተለያዩ tv ቻናሎች ስለኢስላም ሀይማኖት ሲባል እነሱ ይቀርባሉ ..ግን የክርስቲያን ዘማሪዎች ክርስትናን ወክለዉ ቀርበዉ አያቁም እነሱ አምላክ ነዉ ብለዉ ለያዙት ጥርት ያለ ስራ እየሰሩ ነዉ በtv program ወሬ የለም...የኛ ሙነሺዶች ግን በተለያየ Tv ቀርበዉ ሲበጠረቁ እያየን ነዉ ...ነሺዳና ሙዚቃ መለየት የማንችልበት ዘመን ደርሰናል...አሁንም ስለጎንደር ሙስሊሞች ነሺዳ አዉጥተዉ አንድ ደቂቃ አስለቅሰዉ ያስረሱናል፡፡

ራዕይ በተግባር የሚቀረፅ ህልም እንጂ በአእምሮ ብቻ የምናስበዉ መዳረሻ አይደለም፡፡

ብቻ ከባድ ነዉ ብዙ ማለት ይቻል ነበር መፃፍ ሳልፈልግ ጊዜ አስገድዶኝ ነዉ ..ትናንት ዛሬም ጎንደር ደዉየ ነበር የሚሰማዉ ወላሂ በጣም ከባድ የሚያስለቅስ ነዉ😔 ...

ዛሬ የረመዳን 27 ለይል ነዉ ሌላ ማድረግ ቢያቅተን ሳንተኛ በዱአ እንገዛቸዉ ...አላህ ይሰማን ይሆናል ኢንሻ አሏህ
በዱአ የጎንደር ሙስሊሞችን እንዳንረሳ

አዉፍ በሉኝ በችኮላ በ30 ደቂቃ ዉስጥ ያለዝግጅት የተፃፈ ነዉ....አደራ አደራ ለጎንደር ሙስሊሞች ዱአ እንድናደርግ

https://www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
#ሙስሊም_ማለት_እንደ_አንድ_ስጋ_ነው

ያኔ ለፍልስጤም እንደዛ ስንጮህ ምን አገባችሁ? ይመለከታችኀል? ስትሉን የነበራችሁ ያው ዛሬ እነሱም ፍልስጤሞች የኛ መነካት አስጨንቋቸው እየጮሁልን ነው ስለ መስጅዶች መደፈር ስለ ሸሂዶች እያወሩልን ነው ...ኢስላም ላኢልሀኢሏህ የሚል አካል ከተነካ አንድ አካል ነዉ...ምን ትሉ ይሆን??🤔
🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔

💙ኢስላም ማለት፦ ጦርነት ሲያውጁበት
የሚጠነክርና ሲተውት ደግሞ የሚስፋፋ
ቀደውትም አቃጥለውትም የማይበረዝ
ጠንካራ መመሪያ ያለው ትልቅ ሐይማኖት ነው ።


https://www.tg-me.com/Islam_and_Science
Audio
የደሴው የኹጥባ
=============
የስልጣኔ ማማ የአሸናፊነት ተምሳሌት ጥንታዊቷ የደሴ ከተማ ዛሬ ኮስተር ብላ ውላለች።
በዚህ መልኩ ሹራዋን አድርጋ ደምድማለች። «ለሃገር ሰላም ብለን እንጂ ሙተንም ገድለንም አሸናፊዎች ነን!» ብለዋል።

ዝምታችን ለሃገር ህልውና ብለን ነው። ነገር ግን በሸሪዓችን የአንድ ሙስሊም ነፍስ ከዱንያና በውስጧ ካለው ሁሉ ይበልጣል። ስለዚህ የ1 ሙስሊም ነፍስ እንኳን ከኢትዮጵያ ከዓለምም ይበልጣል። የ40 ሙስሊሞች ነፍስ ሲሆን ደግሞ…!


እስኪ ይህን ድንቅ የጁሙዓህ ኹጥባቸውን ተጋበዙልኝ።

ረመዳን 28, 1443 E.C

https://www.tg-me.com/Islam_and_Science
የ13 ዓመት ልጅ ከመደብር ዳቦ ሰረቀ ዘበኛው ይዞት ነበርና ሊያመልጥ ሲል የመደብሩ መደርደሪያ ወድቆ ተሰበረ።
ከዛ ልጁ ተይዞ እንደሌባ ተደብዶቦ ወደ ፍርድ ቤት ሄደ
ዳኛው የወንጀሉን ክስ ሰማና ልጁን እንዲህ ሲል ጠየቀው!
ዳቦ ሰርቀህ ነበር?"
ልጁ - እያፈረ "አዎን ሰርቂያለሁ"
ዳኛው - "ለምን?"
ልጁ - "አስፈልጎኝ"
ዳኛው - "መግዛት አትችልም ነበር?"
ልጁ - "ገንዘብ አልነበረኝም"
ዳኛው - "ከቤተሰብህ ለምን አትወስድም?"
ልጁ - "እናት ብቻ ናት ያለችኝ፥ እሷም በጠና ታምማ እቤት ተኝታለች"
ዳኛው - "ምንም ስራ የለህም?"
ልጁ - "መኪና እጥበት እሰራ ነበር፥ ነገር ግን እናቴን ለማስታመም አንድ ቀን ከስራ ስቀር አባረሩኝ" 
ዳኛው - "ሌሎች እንዲረዱ አልጠየቅኽም?"
ልጁ - "በጧት ነው ከቤት የወጣሁ፥ እንዲረዱኝ 50 የሚሆኑ ሰዎች ጋ ሄጄ ነበር፤ አንድም የሚረዳኝ ሰው ግን አላገኘሁም፤ በቃ መጨረሻ ላይ ይህንን
መጥፎ ውሳኔ ወሰንሁ" 

ጥያቄው ሲጠናቀቅ #ዳኛው ውሳኔ ማስተላለፍ ጀመረ።
እንዲህም አለ
"ዳቦ መስረቅ፥ በተለይ የተራበ ልጅ ዳቦ መስረቅ እጅግ በጣም አሳፋሪ ወንጀል ነው፤ እናም እኛ ሁላችንም የዚህ ወንጀል ተጠያቂ ነን። እኔን ጨምሮ በዚህ ቤት ውስጥ ያላችሁ በሙሉ ወንጀለኛና ተጠያቂ ነን። ስለዚህ እያንዳንዱ በዚህ ችሎት ላይ የታደመና እዚህ ቤት ውስጥ ያለ አስር (10) አስር ዶላር እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ማንም ሰው ሳይከፍል መውጣት አይችልም በማለት አስር ዶለር ከኪሱ አውጥቶ ወረቀት ላይ መመዝገብ ጀመረ።

በተጨማሪ ዳቦ ቤቱ የተራበ ልጅ ለፖሊስ አሳልፎ በመስጠቱ 1000 ዶላር እንዲከፍል ውሳኔ አስተላለፈ።
ይህ በ24 ሰአት ውስጥ ካልተፈጸመ ፍርድ ቤቱ ዳቦ መደብሩን ያሳሽጋል።

ፖሊስም የተራበ ልጅ ፍርድ ቤት በማቅረቡ 1000 ዶላር እንዲቀጣለት ወሰነ።

የተወሰነለትን ገንዘብ ለልጁ ካስረከበ በኋላ ፍርድ ቤቱ ልጁን ህዝብ ፊት ይቅርታ ጠየቀው! 
የዳኛውን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ በችሎቱ ላይ የነበሩ ታዳሚዎች ሁሉ በእንባ ተራጩ።
የልጁ እጅ ላይ የነበረው ሰንሰለት ተፈታለት። ዳኛው እንባ እየተናነቀው ሲያወራ ልጁ ያይ ነበር።
በኛ ማህበረሰብ ውስጥ ያለው የፍትህ ስርዓት ግን ምን ይመስላል? 

የተራበ ልጅ ዳቦ ሰርቆ ቢያዝ ወንጀሉም እፍረቱም ለህዝቡ ነው፡፡
ፅሁፉን ከዚህ ቀደም አንብባችሁት ይሆናል ነገር ግን በኢድ ቀን ብዙ የተራቡ የተቸገሩ ጎረቤቶች አሉ...ደግሞ ዘንድሮ ረመዳን የኑሮ ዉድነት ጣራ ነክቶ የተፆመ ረመዳን ስለሆነ ለኢድ በደስታ ቀን እነሱ ግን ደስታን በሌሎች ብቻ እያዩ የሚያከብሩ ስላሉ እነሱን በተቻለን አቅም መዘየር እንዳለብን እና ዘካተል ፊጥርን መስጠት እንዳንዘነጋ ፡፡


በተጨማሪ ደግሞ ብዙ ሰዉ በረመዳን ከተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ራሱን ያገላል በረመዳን ያልተጠቀመዉን ቀዷዉን ለማዉጣት ይመስል ከረመዳን ቡሀላ ማህበራዊ ሚዲያን ከልክ ባለፈ መልኩ ሲጠቀም እናያለን...መቼም ምክንያቱ ሸይጧን ተፈቷል ነዉ....
በረመዳን ላይ አንድ በሚዲያ ፍቅር ተብየ ሞንጨር ያደረገዉ...ሸህየዉን የሚያስቅ ፈትዋ ይጠይቃቸዋል....

ሼኺ በጣም ጥርጣሬ ዉስጥ እገኛለሁ..አንድ የማፈቅራት ልጅ ነበረች እሷም በርግጥ ታፈቅረኛለች የተዋወቅነዉ በFacebook ነዉ በአካል አንተዋወቅም፡፡ ፍቅር ከመሰረትን ለአመት 3 ወር ይጎለዋል ..ረመዳን ከመግባቱ በፊት በጣም እናወራ ነበር፡፡ነገር ግን ረመዳን ሊገባ አንድ ለሊት ከቀረዉ ለት ጀምሮ በፍፁም ሚዲያ ላይ በfacebook በtelegram በimo. የለችም ...ስደዉልም ቁጥሯ አይሰራም ከኢንተርኔት offline ነች
...እናም እኔም ጥርጣሬ የሆነብኝ ነገር እሷን እያሰብኩ በዉስጤ ሰዉ አይደለችም ሸይጧን ነበር ሲጀነጅንህ የነበረዉ እና ልጂቱ ታስራ ይሆናል😆😆😆😆 በማለት ዉዝግብ ላይ ነኝ ሼይህ ሲል
ሼይሁ በሳቅ .... 😁😁😁

እናም በሚዲያ ወሬ ብዙዉ በረመዳን ይቀንሳል የሚያቆምም አለ ...በዛዉ ሚዲያን ለመራቅ መሞከር እንጂ ረመዳን ተፈታ ተብሎ በረመዳን ያቆምንበትን የሚዲያ ቀዷን ከማዉጣት እንቆጠብ


ዉድ የቻናል ቤተሰቦች መልካም ኢድ አልፈጥር በአል ተመኘሁ፡፡ ለተጨቆኑ በግፍ የተገደሉ የጎንደር ሙስሊሞችን እንዳንረሳ የሶስት ቀን ሀዘን ብቻ ሆኖ እንዳይቀር....በተጨማሪ የደባርቅ ሙስሊሞች እና
በትግራይ ክልል የሚኖሩ የሁሉም እምነት ተከታዮችን በማስታወስ እናሳልፍ ..ደግሞ በትግራይ ክልል ያለዉን  አስባችሁታል?? ከሁለት አመት በላይ በጦርነት ላይ ናቸዉ የኑሮ ዉድነት አሁን ባለንበት እያየን ነዉ..ትግራይ ክልል እንዴት ፁመዉ እንዴት ኢድን ያከብሩ ይሆን??
በትግራይ ክልል ያሉ ሚስኪኖች እንዴት ይሆን በአልን የሚያከብሩት?? ይሄንን በማሰብ በአልን ብናከብር ኸይር ነዉ...ለምን አይታወቅም ነግ በኔ ነዉ ዱንያ  በደስታና ሀዘን ሀዲድ የምትረማመድ ነች ..ነገ ፈጣሪ የኛን በምን እንደፃፈዉ አናቅም...የጦርነትን ክፋት ችግር ጭንቀትና ስነልቦና ጉዳት እንዴት እንደሚያደርስ
የሚያቀዉ ጦርነትን ያየ ብቻ ነዉ...ጦርነት የከባድ መሳሪያ ድምፅን ያልሰማ ያላየ ከአየዉ ጋር  በጭራሽ ሊረዳ አይችልም ...በዛ ሰዉ ጫማ እስካልተራመድክ ድረስ የዛን ሰዉ ህመም ችግር መረዳት ይከብዳል፡፡
ትግራይ ወራሪ ሀይል መጥፎ ጎናቸዉ ቢበዛም ግን እንደሰበአዊነት እኛስ አላህ ዘራችንን ትግሬ አርጎት ቢሆንስ? አሁን በዚህ ሰአት እኛ ትግራይ ክልል ሁነን በነበረን ምን ይገጥመን ይሆን ?? ብለን ማሰብ መቻል አለብን...ኢትዮጲያ ዉስጥ ለፓለቲካ ጥቅም ተብሎ በዘር በሀይማኖት ዉስጥ ተሰግስገዉ ምንም የማያቀዉን የደሀ ልጅ ሞት አላህ በቃችሁ ይበለን...
አላህ ችግርና መከራን አንስቶ በደለኛን የሚቀጣበት ፣ሰላምና ፍትህን የሚያሰፍንበት ኢድ እንዲሆንል እመኛለሁ!
ሙስሊሞችን የበደሉ የጨቆኑ የገደሉትን አላህ ሂድያ ሰጥቶ ኢስላምን ይወፍቃቸዉ ካልሆነ አላህ በዱንያ የሚታይ የማያዳግም ቅጣት ያስጣቸዉ ያረብ

መልካም የኢድ አልፈጥር በአል ተመኘሁ ..ፁመዉ ተራቡት ከሚባሉት ባርያዎቹ ሳይሆን ለፆመኞች በተዘጋጀዉ በር ከሚገቡት ባርያዎቹ ያድርገን
      ኢድ ሙባረክ!!!


https://www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
ለጊወርጊስ ሲዘሉ የነበሩ የገራዶ #ፈረሶች ዛሬ ወደ ኢስላም ተመልሰዋል😊
#ማስታወሻ፦ እነዚህ ፈረሶች ለክርስቲያኖች በዓል ወሎ-ደሴ ላይ ለፈረሰኛው ጊዮርጊስ ማጀቢያ ከገራዶ #ሙስሊሞች በየ አመቱ የሚላኩ ነበሩ። ነገር ግን ከዚህ በሗላ ግን ብዙ ጥያቄ አለን

ባለፈዉ ጥምቀት ላይ አማራ Tv ሲያነጋግራቸዉ አልለምዱሊላህ ታቦታችን በሰላም ገቡ ያሉ ነበሩ፡፡ ዛሬ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ እነዚህ ባለፈረሰኞት የኢድን ሰጋጅ አጅበዉ አብረዉ ፉርቃን መስጊድ ሂደዋል፡፡
በዲን ከመጣ ጃሂልም አሊምም ሀብታም ደሀ ሴት ወንድ ልዩነት የለም


ደሴ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የነበረን ትንኮሳ በአሚሮች ትዕዛዝ በብልሀት ነበር ያሳለፈው ከሰላት በፊትም ቡኃላ ምንም አይነት ተቃውሞ ሳያሰማ ነበር የተመለሰው


ዛሬ ጎንደር ላይ በኢድ ቀን ሳይሰግዱ በቤታቸዉ ለሚያሳልፉና የትግራይ ሙስሊሞችን በማስታወስ በአልን እናሳልፍ

መልካም ኢድ ሙባረክ

https://www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
የኢድ ሶላት በመቀሌ

አላህ ሆይ አገራችንን ሰላም አርገህ ብሄር ዘር ሀይማኖት ከመከፋፈል ተላቀን ከሴረኞች ፓለቲካ ተላቀን....ከትግራይ ህዝብ ጋር አብረን እንደ በፊቱ አንድ የምንሆንበት ኢድ ያርግልን ያረብ ...ኢድን ለወደፊት ለአገራችን ሰላም አንድ ሁነን ዘር ሳንቆጥር ኢትዮጲያን ነን ብለን ለወደፊት የምናሳልፍ ያርገን በማለት የተጨቆኑን በማስታወስ ዱአ በማድረግ እናሳልፍ
ጥጋብ ደስታ ልክ አለዉ ብዙ የተጨቆኑ አሉና❗️❗️❗️

የትግራይና የጎንደር ወንድሞቻችን አብሽሩልን። ይህ ግፍ የቱንም ያክል የዒዱን ደስታና ድባብ ቢያደበዝዝባችሁም ግን ደግሞ በእርግጠኝነት ይወገዳል። ኢንሻ አላህ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዒድ ሰላት ወቅት የተከሰተው ክስተት በክርስቲያኑና በሙስሊሙም መካከል የተፈጠረ አይደለም።

አንዳንድ አካላት ችግሩን ከመንግስት ጋር ለመሰያያዝ መሞከራቸውም የተሳሰተ መሆኑን አረጋግጠናል።

በዒድ ሰላት ወቅት የተፈጠረው ችግር ምን እንደሆነ በስፍራው ከነበሩ በጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎቻችን ደርሶናል። በአንድ ፌደራል ፓሊስ ድንገት (ባርቆብኝ ነው ብሏል) በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስ ምክንያት የተፈጠረ ግርግር ነበር።የአስለቃሽ ጭሱ እንደተተኮሰ በቦታው የነበሩ የበአሉ ታዳሚዎች በከፍተኛ ደረጃ ተደናግጠዋል።ወደ ፌደራል ፓሊሱ በማቅናት ይዘውታል።ፓሊሱም ድንገት ባርቆበት እንደሆነ ተናግሯል ሆኖም ህዝቡ ከፍተኛ የሆነ መረበሽ ውስጥ ስለገባ ለመግባባት አልተቻለም።

በመጨረሻም የፌደራል ፓሊሱ በኤግዢቢሽን አካባቢ ወደ ሚገኘው የፌደራል ፓሊስ ካምፕ እዲገባ ተደርጎል።ይህን ተከትሎ ሌሎች ፓሊሶች ከካምፑ ሲወጡ ተኩሱ የፈጠረው ግርግር ባለመረጋጋቱ ችግሩ ሊባባስ ችሏል።

ከዚህ በተረፈ ከስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ኦርቶዶክስ እምነት ተለታዮች ጋር ችግሩን የሚያያይዘው ነገር አለመሆኑ ተረጋግጧል።በመንግስት በኩልም ሆነ ተብሎ የተፈጠረ ችግር አለመኖሩን አረጋግጠናል።በመሆኑም ህዝቡ እንዲረጋ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

የአዲስአበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት


‼️‼️ ይሄን video ይመልከቱ አስለቃስ ጭሱን ሲተኩሱ አንስቶ ወደ እነሱ
ወላሂ ጀግና ነዉ👌
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ወሎ_ደሴ

የኢድ ሶላት በደሴ
በዳና መልቲሚዲያ በድሮን ካሜራ የተቀረፀ

ምስጋና ዳና መልቲ ሚዲያ

#1443ተኛው_የኢድ_አል_ፊጥር_በአል

https://www.tg-me.com/Islam_and_Science
2024/09/27 11:25:18
Back to Top
HTML Embed Code: