Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Watch "#ድሀ ልጅ ፍቅር አስተማሪ እና ቀልብን አንጠልጣይ መሳጭ እውነተኛ ታሪክ #part 1" on YouTube
https://youtu.be/xdA-e6sfkks
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎁🎁🎁 እጅግ አስቸጋሪ የሆነውን የውጭ አገርና የአገር ውስጥ ከበባድ ተፅዕዎችን በጽናት ተቋቁመን ሁለተኛውን ዙር የታላቁ የህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት በድል ተከናውኗል፡፡ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳ ደስ አለን፡፡
ደግሞ በጣም ደስ የሚለዉ ነገ አረፋ በአል ዛሬ በአረፋ ፆም ባለንበት ሰአት 2ኛዉ ዙር መሙላቱ የብስ ደስታን ይጨምራል፡፡
አማራ ኦሮሞ ትግሬ አፋር ሱማሌ ወዘተ የሚለዉን ትተን ኢትዮጲያ ነን ካልን ገና ብዙ ስራ መስራት እንችላለን🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ሀምሌ 12፣ 2013 ዓ.ም ይሄ ቀን ለታሪክ ይቀመጥ

#ይሄን_ያቃሉ ??
አባይ ግድቡ ተገንብቶ አልቆ ውሀ ሙሌቱ ሲጠናቀቅ ከግድቡ ጀርባ በሚንጣለለው ውሀ ስፋት በአለማችን ላይ ጨዋማ ያልሆነ ቁጥር አንድ ትልቁ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ይሆናል።
# GERD # ItsMyDam🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

የአረፋ በአልን ዝባዝንኬ ከሆነ ነሺዳ መንዙማ ዉጭ ባሉ ተግባራት እናሳልፍ፡፡ ነገር ግን ነገ የተለያዩ የቴሌቪዥን የበአል ፕሮግራሞች የዘንድሮ ሙነሺድ ተብየዎች ይበዛሉ በተጨማሪ Bst tv እናም ሙነሺዶች በተዘጋጀዉ ፕሮግራም ላይ አይታችሁ ለዲን የሚጠቅሙ ናቸዉ ወይስ የማይጠቅሙ ሰዉን ወደ ጥመት ነዉ የሚመሩት ወይስ አይደለምየሚለዉን እናንተዉ አይታችሁ ፍረዱ👌👌

ዉድ የተከበራችሁ የቻናል ምርጥ ቤተሰቦች መልካም ኢደል አድሀ በአል ለሁላችሁም ተመኘሁ
አሚር ሰይድ

@IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ

ሳትዋጋ ንገስ በሚለዉ ታሪክ አሁን ድረስ አስተያየት በመስጠት ደካማ ጎኔን እንደ አስተካክል እናም ደግሞ ብዙ የስድብ ናዳም ተቀብያለሁ ለሁሉም አመሰግናለሁ ግን ብዙ Comment ላይ የሚደጋገም አለ

ሴት ልጅ ከ1እስከ 7 ድረስ ካልወጣች መማር የለባትም ኪታብ ብትቀራ ይሻላል ብየ በራሴ አመለካከት አንዴ ተናግሬ የአስተያየት መስጫዉ bot በስድብም አንተ ሆላ ቀር ለዘመኑ የማትመጥን ነህ የሚል ብዙ አይቻለሁ
ግራ የሚገባኝ በኔ የተነሳ የሚያቆም የለ ምን አስጨነቃችሁ🙄 እኔ አንድ ተራ ሰዉ ነኝ ደአዋ አድራጊ አይደለሁ ታዋቂ ሰዉ አይደለሁ ምንም የሚያሳስብ አልነበረም ፡፡ አንተ ለዚህ ዘመን አመጥንም ሙስሊም ሴቶች ወደ ሆላ ለማስቀረት ተነስተሀል ላላችሁኝ ..አዎ ይሄ ዘመን ትዉልድ ባለንበት ባልመጥን የሚቆጨኝ ነገር አይደለም ለምን ትዉልድ እየከሰረ ያለበት ዘመን ነዉ፡፡ ሙስሊም ሴቶች ወደ ሆላ የቀሩት ሰነፍ ሁነዉ ተምረዉ ዩኒቨርስቲ ገብተዉ በዛ በዚህ ብለዉ ዲግሪ ይዘዉ መስሪያ ቤት ስራ ፍለጋ ስትዞር በ3000 እስከ 5000 ባለዉ ደመወዝ እየተከፈላት ከዩኒቨርስቲ ጀምሮ እስከ መስሪያ ቤት የፆታ ትንኮሳን አሳልፋ ትዳር በምፈልግበት ጊዜ እድሜዋን አሳልፋ ማጣቷ ነዉ የሚያሳዝነዉ፡፡
ዋናዉ ነገር በትምህርታቸዉ ሰነፍ የሆኑ ብዙ ሴቶች የወደፊት የሚኖሩበት መሆን የሚፈልጉት እቅድ አላቸዉ ወይ??? 95% እቅድ ፕላን የላቸዉም
እሺ ብዙዎቹ ጎበዝ ባይሆኑም ጎበዝ የመሆን አላማዉ አላቸዉ ያላችሁም አላችሁ በተዘዋዋሪ ኮርጀዉም ደረጃ የሚይዙ ሴቶች ስላሉ ኮርጀዉ ደረጃ ከያዙት ሰነፍ ሁነዉ የሚማሩት ይሻላሉ የሚልም አስተያየት አይቻለሁ ፡፡ ኮርጀዉ ደረጃ የያዙ ሴቶች በሰዉ ሀሳብ አዳሪና በሙቅ ዉሀ ታጣቢ አንድ ነዉ ነገ የማይደገም ነዉ እኔ በሂወቴ የማልረሳዉ ገጠመኝ አለኝ ስድስተኛ ክፍል ስማር በአንደኛ ሲሚስተር ከእኛ ክፍል አንደኛ ከወጣዉ ከ40ዉም ከ60 ኮርጄ ሶስተኛ ደረጃ ወጥቼ ደስ ብሎኝ በሁለተኛ ሲሚስተር ግን ከእሱጎን የመሆን እድል አልገጠመኝም ነበር 42 ነበር የወጣሁት☹️ እናም በጓደኛ በዘመድ በትምህርት ቤት ተማሪ በሰፈር ሳይቀር መሳቂያ ሁኛለሁ ስድስተኛ ክፍል ላይ የሰዉ አእምሮ መጠቀም እንደ እኔ አንድ ቀን ዉርደት ይሸከማል
ሰነፍ ሁነዉ ይማሩ ለምትሉ ደግሞ እየተማሩ የወደፊት የህይወት ግብ ከሌላቸዉ ከተወሰነ አመታት ቡሀላ አወዳደቃቸዉ እንደ ህዉሀት ነዉ የሚሆነዉ🤗
ወንድ ሰነፍ ከሆነ ለምን ይማራልም የሚል አለ.. .አዎ ሰነፍ ከሆነ ዲነል ኢስላምን ይማር ግን ትምህርት ቤት ሴቶችን አላማ ያስታል፡፡ ወንድ የህይወት አዙሪቱን በሂደትም ቢሆን ማስተካከል ይችላል፡፡ የሴት ግን በጥንቃቄ ካልሆነ አንዴ ከተበላሸ ለማስተካከል ከባድ ነዉ ምን አልባት እስከ ሞት አፋፍ ድረስ ሳይተካከል ይችላልና.. ከ5እስከ 8 ክፍል ያሉ ሴት ህፃናትን ተመልክታችሁ፡ፍረዱ ...ሴት ጠንካራ ናት አጋዥ ከጎና የሚሆን የሚረዳት ወንድምና እህት ካገኘች ባይሆን ወንድም ስል የእናት አባት ወንድም😊 ካገኘች መቀየር ትትላለች ብያለሁ ..እህት ያለዉ እህት ያለሽ ሰበቡን አድርሱ በከባድ ትግል ማስተካከል ይቻላል በአላህ ፍቃድ

አሁን ስላሉ ሙነሺዶች ስታነሳ እዚህ ቻናል ብዙ የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች አሉ ለምን በአደባባይ ታነሳለህ ለእነሱ አጋልጠህ ሰጠህ ማለት ነዉ የሚል አስተያየት አይቻለሁ....አዎ አቃለሁ ብዙ የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ይከታተላሉ ግን ሂዲያ የሚሰጠዉ አላህ ነዉ እነሱ ትክክለኛ የኢስላም መስመር ላይ አለመሆናቸዉን ማወቅ አለበት ምን አልባት ነገ ከነገ ወዳ ወይም ከተወሰኑ አመታት ቡሀላ ኢስላም በልባቸዉ ከገባ የሙነሺዶችን አካሄድ ከሄዱ አደጋ ይኖረዋል...እንደዉም ብዙ እዚህ ቻናል ያሉ በአሁን ሙነሺዶች ስራ ተገርመዉ በሚሰሩት ስራ እስልምና ላይ አለ ወይ? እያሉ የሚጠይቁኝም አሉ
ከአሁን ቡሀላ እኔም ስለእነሱ ማንሳት አልፈልግም...የሆነ ነገር ስል ገና ከእጄ ተፅፎ በቻናል ፓስቼ አስጠንቅቂያለሁ መረዳት ያለመረዳት አእምሮን ተጠቅሞ ማስተንተን የባለጭንቅላቱ ሰዉ ዉሳኔ ነዉ❗️❗️

❇️ በተለያዩ ታሪኮች ሲፓሰት አንዴ ወንድ በሴት ሲከዳ ደግሞ በሌላ በማዘጋጀዉ ታሪክ ሴት በወንድ ስትሸወድ ስትከዳ ታሪኩን ያነበበዉ ወንድ ከሆነ እንዴ ሴቶችም እንደዚህ ያረጋሉ መቼ ይታመናሉ ሲለኝ ሴቷ ደግሞ አንተ ለሴት ጥሩ አመለካከት የለህም ወንዶች ናቸዉ እንዲህ ያደረጉኝ የማላገባዉ ወንድን ከማምን ዉሻ ባምን ይሻላል እያሉ በፊት ባለማወቅ ይሁን አዉቀዉም ይሁን የተሳሳቱ ማህበረሰቦች ታሪክ ባነበቡ ቁጥር ጥርስ ነካሽ ሁነዋል እናም አሁን አንድ መፍትሄ ሀሳብ ይዘን ብቅ ብለናል😊
☞ወንዱም ሴት አይታመንም እያለ ግራ ተጋባ
☞ሴቷም ወንድ አይታመንም እያለች ትዳር መላሽ ሆነች
☞ትዳር ያሰቡ የትዳርን የሚያበላሸዉን ፍቅር የሚጨምረዉን ሳያቁ ገብተዉ ..ዋና ሳይችሉ መዋኛ ገንዳዉ ገብተዉ በዋናተኛ እየወጡ ነዉ
☞ትዳር ላይ ያሉ ደግሞ ይሄን የሚያምር ቁርኝት ኒዕማዉን ሳያቁት እያባከኑት ነዉ

ይሄን ሁሉ የማህበረሰቡን ችግር ምክንያት በማድረግ እስኪ ለዚህ ሁሉ ችግር ትዳር ለመግባት ዳር ላይ ለቆመዉ .ወንድ ለሴት ወይም ሴት ለወንድ መጥፎ አመለካከት ላለዉ ትንሽም ቢሆን ከልብ ያለዉን ኒፋቅ የሚያጠፋ ፁሁፍ እህታችን መህባቡ ቢንት አቡሀ ፍቅርና ትዳር ከሚለዉ መፅሀፍ ስለትዳርና ፍቅር ምርጥ ፁሁፎችን አዘጋጅታለች..እኔም የቃላት ስህተቱን በማስተካከልና ክፍሎቹን ኦርደር አድርጌ በቅርቡ የምንጀምር ይሆናል፡፡

❇️ የካንሰር በሽታ አይነቱ ብዙ ነዉ ሰዉ የሚያቀዉ የሆድ የጭንቅላት የጡት ወዘተ ካንሰር ነዉ ..ግን የትዳር ካንሰር አለዉ የትዳር ካንሰር የሚጀምረዉ በዘንድሮ ከምላስ አልፎ ጉሮሮ ከማይደርሰዉ ፍቅር ከትዳር በፊት የሚጀምር የሞኛሞኞች ፍቅር ነዉ ..በዚህ ካንሰር ብዙዎች ተጠቅተዋል
ብዙ የሚታከሙ ልቦች አካሚ አጥተዉ ከስመዋል
ብዙዎች ካንሰር መድሀኒት እንደለለዉ አዉቀዉ እንሙት ብለዉ ገብተዋል
እንሙት ብለዉ የገቡትም ሳይገላቸዉ ቀርተዉ ይሄዉ የቁም ቀባሪ ስለሌለ ሞትን እየተመኙ ሞት ጠባቂ ሁነዋል
ስንት የት ይደርሳሉ የተባሉ ትዉልዶች በራሳቸዉ ጥፋት እድል ቆዛሚ ቀዷና ቀድር ጋር እየተጋጩ የጋን ዉስጥ መብራት ሁነዉ ቀርተዋል
የወደፊት የኡማዉ ተረካቢ ትዉልድን 9ወር አርግዘዉ አምጠዉ ተሰቃይተዉ ወልደዉ ግን የተሰቃዩበት የማጡበት ትርጉምን ሳያቁ የሚወለደዉ ልጅ ለማህበረሰብ እንዴት አድርገዉ በተርቢያ አሳድገዉ ለማስረከብ የማይችሉ እንስቶች በየመንገዱ በየቤቱ በዝተዋል፡፡ እናቱ አምጣ አልቅሳ ወልዳ ወደ ዱንያ መምጣቱን ዘንግቶ በእናቱ በእህቱ ላይ እንዲሆን የማይፈልገዉን በሌሎች ሴቶች ላይ ከምጥ በላይ ስቃይ አሸክሞ የሚሄድ ሞራል የሌለዉ ወንድ ተሰራጭቷል፡፡ ታዳ ይሄ የትዳር ካንሰር አይደል?

የትዳር ካንሰርን ለማከም ጊዜ ቢፈጅም ግን መፍትሄዉ ጥሩ ትዳር መሆኑን በቻልነዉ አቅም በመህባቡ ፁሁፍ እንዳስሳለን

ባለማወቅና ባልታመኑ ነበልባል ምላሶች ምክንያት የተሸወደች ልብን መልሶ አድሶ ለመቆም ይጠቅማል ብየ አስባለሁ

📥ስለትዳር የዘጋጀሆቸዉ ፁሁፎች አሉ በቻናል ቢፓሰቱ ይጠቅማሉ ብላችሁ ያዘጋጃችሁት ፁሁፍ ካለ በዚህ bot አሳዉቁኝ 👇👇
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot

❇️ መህባቡ ቢንት አቡሀ ያዘጋጀችዉ ፁሁፍ በቅርቡ ይጠብቁኝ እንጀምራለን መልካም ንባብ
ወንድማችሁ አሚር ሰይድ ነኝ

#COMING SOON ..
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አብሀ
ክፍል :- አንድ 1⃣


#መቅደም

ማህበረሰብ የሚዋቀረው ከቤተሰብ ሲሆን የቤተሰብ መሰረቱ ደግሞ ጋብቻ ነው ።ጋብቻ አምሮና ደምቆ እሰከ ህይወት መጨረሻ ሲቆይ ለጥሩ ዜጎች ግንባታ ከፍተኛ አሰተዋፅኦ የሚያበረክተውን ያህል በፍቺ ሲጠናቀቅ የተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶችን ያስከትላል ።በተለይ ደግሞ ከዓመታት ቆይታ በኋላ የሚፈርስ ትዳር በጥንዶቹና በዙሪያቸው ባሉ ሰዎች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም ።ፍቺ ሲፈፀም ሳይፈልግ ተገዶ ወደ ፍቺው የገባው አካል ከባድ ሀዘን ውሰጥ ይወድቃል ።ይህ ሀዘን አጋርን በሞት ከማጣት ቀጥሎ ከባዱ ሀዘን እንደሆነ አጥኝዎች ይናገራሉ ::
ለአዕምሮ ህመምም ሊዳርግ ይችላል ።ፍቺ የሀብት ክፍፍልን ስለሚያስከትል ጥንዶች የኢኮኖሚ ውድቀት ይደርስባቸዋል ።
☞ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከነበሩና ሚሰት ስራ ከሌላት የሚበላ እስከማጣት ትደርሳለች ።
☞ልጆች ካሏቸው ደግሞ ችግሩ ተደራራቢ ነው ።
☞ልጆች የአባት ወይም የእናታቸውን ፍቅር ያጣሉ ።
☞ለእንጀራ አባት ወይም ለእንጀራ እናት ይጋለጣሉ ።
☞የኢኮኖሚ ችግር ያገኛቸዋል ።
☞በትምህርታቸው ይሰንፋሉ ።
☞ለተለያዩ የስነ ልቦና ችግሮችም ይጋለጣሉ ።
☞በግቢ ተሳስሮ የቆዬ ዘመድ አዝማድም ይበታተናል ።

በአገራችን ኢትዮጵያ የፍቺ አሀዝ ከግዜ ወደ ግዜ እያሻቀበ መምጣቱ ወጣቶች ትዳርን እንዲፈሩ እያደረጋቸው ነው ።የማግባታቸው ዜና ተሰምቶ ብዙም ሳይቆይ ተፋቱ የሚባልላቸው ብዙዎች ናቸው ።በሰርጋቸው ቀን የዛሬ ዓመት የማሙሸ እናት /የዛሬ ዓመት የማሙሸ አባት ።"ተብሎ የተሸኙ ጥንዶች ዓመት ሳይሞላ ለፍቺ ወደ ፍርድ ቤት የሚሄዱ በመሆኑ የዛሬ ዓመት ወደ ፍርድ ቤት "ወደሚል መቀየር አለበት እስከመባል ተደርሷል ።


ወንድ የተፈጠረው ለሴት ነው ሴትም ለወንድ ነዉ...ሁለቱ አንደ ማግኔት ናቸው ።አርሰ በርስ ይሳሳባሉ ።አንዱ ካንዱ ተለይቶ ቢኖር ህይወት ጣዕም አይኖራትም፣ጎደሎም ትሆናለች ።የሰው ልጅ ጋብቻን በመመስረት ለተፈጥሯዊ አሰፈልጎቶቹ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል ።ለዚህም ነው ለአቅመ አዳምና ለአቅመ ሄዋን የደረሱ ወንዶችና ሴቶች ትልቁ ፍላጎት ትዳር ሲሆን የሚስተዋለው ።ወጣቶች ቅዱሱን የጋብቻ ውል በመፈፀም የደስታ ህይወት ሀሁን ይጀመራሉ ።

#ትዳር
☞ በክፉም በደጉም ግዜ አብሯቸው የሚሆን ተቆርቋሪና ታማኝ አጋር ይሰጣቸዋል ።
☞በተረበሹበት ወቅት ያረጋጋቸዋል ።
☞የተዘበራረቁ ህልሞቻቸውን ወደ አንድ ስኬታማ ግብ ያመጣላቸዋል ።ይህ ቤተሰብ የመመስረት ህልም ወጣቶችን ከአላስፈላጊ ድርጊቶች ያቅባቸዋል ወጣቱ ከታማኝ የቤተሰብ አካል የተሻለ መጠለያ ሊያገኝ አይችልም ።

#ትዳር ተዝናንቶና ተመቻችቶ ለመኖር የሚያስችል የፍቅር ፣የርህራሄና የጓደኝነት ማዕከል ነው ።ሆኖም ብዙ ተጋቢዎች ይህን ነገር በአግባቡ ሲጠቀሙበት አይታይም ።ባለማወቅና ባለማስተዋል ይህን የሞቀና የተቀደሰ አንድነት ወደ ጨለማና ሲኦል ይቀይሩታል ።ወይም ደግሞ ከነጭራሹ ያፈርሱታል ።ጥንዶች እያንዳንዳቸው ከኔ ምን ይጠበቃል?? የሚለውን ነገር በደንብ ካውቁና ያን ተግባራዊ ለማድረግ ከጣሩ ያማረ የትዳር ህይወት እንደሚኖራቸው ጥርጥር የለውም ።

አለበለዚያ ሰላም የራቀው ትዳር ለመግፋት ይገደዳሉ ።በትዳር መካከል ግጭት እንዲፈጠር የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም አንደዚህ መፅሐፍ አዘጋጅ አሰተያየት ትልቁ ችግር ያለው ተጋቢዎች ምን እንደሚጠበቅባቸው አለማወቃቸውና ለጋብቻ ህይወታቸው ዝግጁ አለመሆናቸው ላይ ነው ።

እውቀትና ዝግጁነት ወሳኝ ነገሮች መሆናቸው ልብ ሊባል ይገባል ።ምክንያቱም አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ ተገቢው እውቀትና ዝግጁነት ከሌለው ስኬታማ ሆኖ የሚፈልገው ግብ ላይ ሊደርሰ አይችልም ።ልምድ ፣ዝግጁነትና እውቀት ለጋብቻ ህይወት አስፈላጊ ነግሮች ናቸው ።አንድ ወጣት ስለ ሚስቱ የህይወት መመሪያዎችና ውስጣዊ ፍላጎቶች አንዲሁም በትዳር ውሰጥ ስለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው በቂ እውቀት ሊኖረው ግድ ነው ።

#ጋብቻ በሁለት የህይወት ዘመን አጋሮች መካከል የሚፈፀም የፍቅር ፣የታማኝነት ፣የርህራሄ ፣የአጋርነትና የመተጋገዝ ውል አንጂ ሱቅ ገብተው አንደሚሸምቱት ሸቀጥ አይደለም ።ሴትም አንዲሁ የባሏን የህይወት ፍልስፍናና ፍላጎት ለይታ ማወቅ አለበት ።

#ጋብቻ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይህን ስራ ሲባል የሚሰራ የቤት ሰራተኛ አንደ መቅጠር አይደለም ።ነገር ግን ህይወትን በአግባቡ ለመምራት ለሚደረግ ጥረት አጋርና አጋዥ ማግኛ ዘዴ ነው ።

ስኬታማ አጋር ለማግኘት ደግሞ መግባባት ፣መተጋገዝና መሰዋዕት መክፈል ያሰፈልጋል ።ምንም እንኳ የወጣት ወንዶችና ሴቶች የወደፊት ሁኔታ ትልቅ እውቀት አንዲሁም ዝግጁነት በሚጠይቀው የትዳር ህይወት ላይ የሚመሰረት ቢሆንም ህብረተሰቡ የነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች አስፈላጊነት ችላ ሲል ይታያል ።

ወላጆች ስለ ልጃቸው የትዳር ጓደኛ ስራ ፣እድሜ ፣መልክ ፣ሐብትና መሰል ነገሮች የሚጨነቁትን ያህል ልጆቻቸው በትዳር ህይወታቸው ስኬታማ ሆነው ይቆዩ ዘንድ ማዘጋጀት እንዳለባቸው አይገነዘቡም ።
በመሆኑም ስለ ትዳር ህይወት በቂ መረጃ ሳይሰጡ ልጆቻቸውን ያጋባሉ ።ከዚያም ሁለት ልምድ የሌላቸው አፍላ ወጣቶች በአዲስ ህይወት ውሰጥ ይገናኙና ብዙ ችግሮችን ይጋፈጣሉ ። እሷ ምን ማድረግ አንዳለበት እሱም ምን ማድረግ አንዳለበት አያውቅም አለመግባባቱና ጥል ከፍ ሲልም ድብደብ የተለመደ ነገር እየሆነ ይመጣል ።ይህን ግጭት ለመፍታት ወላጆች ጣልቃ ይገባሉ ።ብዙ ግዜ ደገሞ ጣልቃ ገብነታቸው ለአንድ ወገን የሚያደላ በመሆኑ አለመግባባቱ ይሰፋና ችግሩ እየተባባሰ ይሄዳል ።

የመጀመሪያዎቹ የጋብቻ ዓመታት በክሰተቶች የተሞሉ ወሳኝ ጊዜያት ናቸው ።ብዙ ባለትዳሮች በፍቺና በመሰነጣጠቅ አደጋ ውሰጥ የሚገቡት በዚህ ወቅት ነው ።አንዳንዶቹ ይህን የተበላሸ የትዳር ህይውት አፍርሰን ሲመርጡ ሌሎች ደግሞ አርሰ በርስ ይበልጥ በመተዋወቅ አንፃራዊ ምቾት ያለው የትዳር ህይወት ይፈጥራሉ ።ይህን ችግር ለመፍታት ወላጆች ትልቁን ሀላፊነት መውሰድ ያለባቸው ቢሆንም ከነሱ በተጨማሪ የጋብቻ ዝግጅት "በሚል ርዕሰ ሰለ ጋብቻ መሰረቶችና ማጠናከሪያዎች ዝግጁ እንዲሆኑና ስኬታማ የትዳር ህይወት እንዲመሩ ያስችላቸዋል ።

ወደፊት እንድህ አይነት የማሰልጠኛ ተቋማት ይከፈታሉ የሚል ተሰፋ አለኝ ኢንሻ አሏህ ።


#የፁሁፉ_ምንጭ ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ

✿ በክፍል ሁለት የሴት ልጅ ተግባራት በአላህ ፍቃድ አቀርባለሁ

ክፍል ➋
ይቀጥላል.....


👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሁለት
2⃣


🌙🌙 #የሴት_ልጅ_ተግባራት

💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም አንድ
#ኑሮ_ከባል_ጋር......

የሚስት ተግባር ባሏን መጠብቅና መንከባከብ ነው ። ይህ ከባድ ሀላፈነት ነው ።የዚህን ሀላፊነት ትክክለኛ ገፅታ ያልተረዱ ሴቶች በትዳራቸው ላይ ችግር ይገጥማቸዋል ።ምንነቱን ለተረዳች ሴት የሴትነት አርቆ ማሰብና ብልሀትን የሚጠይቅ ተግባር ነው ።አንዲት ሴት ስኬታማ ሚስት ለመሆን የባሏን ልብ ማሸነፍና ለባሏ የደስታ ምንጭ መሆን አለባት ።ጥሩ ነገሮችን እንዲሰራ ልታበረታታው ከመጥፎ ነገር ልትከለክለው ይገባል ።ለደህንነቱና ለጤንነቱ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅበታል ።ጥረቷ ባሏ ለቤተሰቡ ጠንካራ መከታና ለልጆቹ ጥሩ አባት አንዲሆን ያደርገዋል ።በዚህ ረገድ ሴት ልጅ ልዩ ችሎታን ተጎናፅፋለች ።የቤተሰቧ ደስታና እድገት አንዲሁም ሀዘንና ውድቀት በመዳፏ ነው ያለው ።ሴት ልጅ ከውድቀት ዳርቻ ማድረስ ትችላለች ።በቤቷ ውሰጥ ያላትን ደረጃ ያወቀች ሴት ባሏ ከሰዎች ሁሉ ያነሰ ቢሆን አንኳ የተከበረ ሰው የማድረግ ኃይል አላት ።አንድ ምሁር "ሴቶች የፈለጉትን ነገር የማግኘት ታላቅ ኃይል አላቸው "ሲል ፅፏል ።

💐 የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ሁለት
#ሩህሩህ_ሁኚ

እያንዳንዱ ሰው አዛኝ የልብ ጓደኛ እንዲኖረውና በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ይፈልጋል ።በሰዎች ዘንድ የማይወደድ ሰው ራሱን አንደ ብቸኛና ባዶ አድርጎ ይቆጠራል ።እመቤት ሆይ !ባልሸም ከዚህ የተለየ አይደለም ።ፍቅርና እንክብካቤን ይፈልጋል ።ከማግባቱ በፊት ይህን ፍላጎቱን የሚያሟሉለት ቤተሰቦቹ ነበሩ ።አሁን ግን አንቺ ነሸ ልታሟይለት የምትችይው ።አሱ አንችን ለማስደሰት ይጥራል ።ምናልባትም ከወላጆችሸ በላይ ለደሰታሸ ይጨነቃል ።ሁሉንም የህይወት መሰናክሎች ካንቺ ጋር ይካፈላል ።ስለዚህ ሩህሩህ ሁኚለት ።ፍቅር ሰጪው ።እሱም ያፈቅርሻል ።ፍቅር ሁለት ሌቦችን አንድ የሚያደርግ የሁለትዮሽ ቁርኝት ነው ። "የቴህራን ዩንቨርሲቲ ተማሪ የሆነ አንድ የሀያ ዓመት ወጣት የአገሩ ልጅ የሆነችውን የሰላሳ ዘጠኝ ዓመቷን ባሏ የሞተባትን ሴት አፈቀረ ።ይህም የሆነው ይህች ሴት ያደረገችለት እንክብካቤ ከእናቱ ያጣውን ፍቅር ሰላሟላለት ነው ።የፍቅር የጋራ ሲሆን የጋብቻ መሰረት ይጠናከራል ።የመለያየት አደጋ አይኖርም ።

ባሌ መጀመሪያ ላይ አንዳየኝ ነው በፍቅሬ የወደቀው ብለሸ አትኩራሪ ።ምክንያቱም ይህን መሰሉ ፍቅር ዘለቄታ የለውም ።

#ዘላቂ_ፍቅር_የሚመነጨው
☞ከመቀራረብ ፣
☞ከመተዛዘንና
☞ከመተሳስብ ነው ።

ባልሽን ካፈቀርሸውና ከሱ ጋር መልካም ግንኘነት ካለሸ ደስተኛ ይሆንና ላንቺ ደህንነት ራሱን አሳልፎ እስከመስጠት ይደርሳል ።

የሚስቱን ፍቅር የሚያገኝ ባል የጤንነት መጓደልና ስነልቦናዊ ችግሮች አያጋጥሙትም ።

ከሚስቱ ጋር መልካም ግንኘነት የሌለው ወንድ
☞ ደሰታ ይርቀዋል
☞ቤቱ ያሰጠላዋል
☞ችግሩን የሚረዳው ጓደኛ በመፈለግ በርካታ ሰዓታትን ከቤቱ ውጪ ያሳልፋል ።
"የማይወዱኝንና የማያዝኑልኝን ሰዎች ለማስተዳደር ለምን አልፋለሁ ? ራሴን መዝናናትና የልብ ጓደኛችን ለማግኘት መሞከር አለብኝ የሚል ሰሜት ያድርበታል ።

ሴት ልጅ ባሏን ከልቧ ልትወደዉ ነገር ግን ፍቅሯን ላትገልፅለት ትችላለች ።ፍቅርን በተግባር ማሳየት በራሱ በቂ አይደለም ።አልፎ አልፎ በቃላት መግለፅም ያሰፈልጋል ።

ለምሳሌ "አወድሀለሁ "አፈቅርሀለሁ "የሚሉና መሰል ነገሮች ግንኙነትን በማጎልበት ረገድ ትልቅ አሰተዋጽኦ አላቸው ።

ባል ወደ ሌላ ቦታ በሄደበት ወቅት ሚስት አንደናፈቀችው በመግለፅ ስልክ መደወልና መልዕክት መፃፍ አለበት ።በሌለበት ወቅት ለጓዶኞቹና ለዘመዶቹ እሱን ማድነቅ አሱን የሚቃወም ሰው ካለ መከራከር ይኖርባታል ።

💐 የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ሶስት
#ባልሽን_አክብሪ !

የሰው ልጅ በተፈጥሮው መከበርን ይፈልጋል ።ነገር ግን ሰዎች በቀላሉ ክብር ለመሰጠት ፍቃደኞች አይደሉም ።
ባለቤትሽ ከቤት ውጪ በሚሆንበት ጊዜ ከብዙ ሰዎች ጋር ይገናኛል ።ትህትና የጎደላቸው ሰዎች ሊያሰቀይሙትና ሊያናድዱት ይችላሉ ።ስለዚህ አንድ ሚሰት ቤት ውሰጥ ክብርና ድጋፍ አንድትሰጪውና ውጪ የተጎዳ ስሜቱን አንድትጠግኚለት ይፈልጋል ።

ባልሽን ማክበርሸ አንቺን ዝቅ አያደርግሸም ።ነገር ግን ወርቃማ የትዳር ህይወት ትጎናፀፊ ዘንድ ኃይልና ጥንካሬ ይሆንሻል ።
☞ሁልጊዜ ሰላምታ ስጪው ።ሰላምታሸም ፍቅርን የተላበሰ ይሁን ።
☞በትህትና አናግሪው አትጬሂበት
☞በሚያወራበት ጊዜ አታቋርጪው
☞አብራችሁ ወደ ማህበራዊ ስብስቦች በምትሄድበት ወቅት ቀድሞ እንዲገባ ጋብዢው
☞ከሌሎች ፊት አድንቂው ልጆችሽ አባታቸውን እንዲያከብሩ ምከሪያቸው
☞ለሱ ጥሩ አመለካከት ከሌላቸው አመለካከታቸውን እንዲያስተካክሉ አድርጊ
☞በእንግዶች መሀል አክብሪው ።ለሱም ሆነ ለእንግዶች ፍላጎት እኩል ትኩረት ሰጪ
☞በር በሚያንኳኳበት ወቅት በፈገግታና በደስታ ስሜት ክፈቺ ።ሞቅ ያለ ሰላምታ አቅርቢለት ።

ይህ ቀላል ተግባር የባልሸን የድካም መንፈስ የማደስ ትልቅ ኃይል አለው ።
አንድአንድ ሴቶች ይህ ተግባር ሲከብዳቸው ይስተዋላል
ለባላቸው ሰላምታ ካቀረቡ አንደ ውጪ ሰው የቆጠሩትም ይመስላቸዋል ።ይህ ትክክል አይደለም ።ቀኑን ሙሉ ለቤተሰቡ ደህንነት ሲለፋ አንደመዋሉ መጠን ወደ ቤት ሲመለሰ ክብርና አትኩሮት ይገባዋል ።ለውጪ ሰው ጥሩ የሆነው ሰላምታሰ ለባል ሲሆን ምን ይለዋል ?

ባልሽን ከማዋረድ ተቆጠቢ ።
ሲናገር በጥሞና አድምጪው ።
መጥፎ በሆኑ ቅፅል ስሞች አትጥሪው ።
ስሜቱን የሚጎዳ ንግግር ከተናገርሸው እሱም በተራው ያሰቀይምሻል ።ይህ ደግሞ የፍቅርና የመከባበር መንፈሳችሁን ይሸረሸረዋል ።በመጨረሻም ለፍቺ ሊዳርጉ የሚችሉ ተደጋጋሚ ግጭቶች ይፈጠራሉ ።ባትፋቱ እንኳ ህይወታችሁ በተዘበራረቁ አጋጣሚዎች የተሞላ ይሆናል ።በጥንዶች መካከል የጥላቻ ስሜትና ስነልቦናዊ ቀውስ ከተፈጠረ ደግሞ ወደ ወንጀል መገፋፋት ሊመጣ ይችላል ።

ቀጣዮቹ ታሪኮች ይህን ሀሳብ የሚያጠናክሩ ናቸው ።አንድ የሃያ ሁለት ዓመት ወጣት የአስራ ዘጠኝ ዓመት ሚስቱን በስለት ወግቶ ይገድላል ።ፍርድ ቤት ቀርቦ ድርጊቱን ለምን እንደፈጸመ ሲጠየቅ የሚከተለውን ተናግሯል ፦"ይህቺን ሚስቴን ከአንድ ዓመት በፊት ነበር ያገባሆት ።መጀመሪያ አካባቢ በጣም ትወደኝና ትንከባከበኝ ነበር ።ነገር ግን ያ ሁኔታ ሊቆይ አልቻለም ትዘልፈኝና ታዋርደኝ ጀመር ።በየአጋጣሚው ሁሉና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር መጥፎ ንግግር ትናገረኛለች ይህ ነገር ግራ አያጋባኝ መጣ ።ይባስ ብላ ግራ አይኔ ላይ ችግር በመኖሩ "አውር "አህያ "እያለች ትሰድበኝ ጀመርች ።አንድ ቀን "እውር አህያ "ስትለኝ ቦግ አለብኝ ።ንዴቴን መቆጣጠር አልቻልኩም ።በቢላዋ አሰራ አምስት ጊዜ ወግቼ ገደልኳት

ሚስቱን የገደለው ሌላው አባወራ ደግሞ ለምን እንደገደላት ሲያብራራ "ሚሰቴ"በድንገት ባህሪዋ ተቀያየረ ።ታንቋሸሸኝ ጀመረች ።አንድ ቀን "አውነቱን ልንገርህ ከአንተ ጋር መኖር አልፈልግም !አለችኝ ።ንግግሯ አበሳጨኝ ።ሁለት ጊዜ በመጥረቢያ መትቼ ገደልኳት "ብሏል ።

በክፍል ➌ ወቀሳና ምሬትን እንዴት ማስወገድ እንዳለብሽ እንዳስሳለን

#ምንጭ ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ
ይቀጥላል.....

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሶስት 3⃣

በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL




💐 የትዳር ማጣፈጫ ቅመም አራት
#ወቀሳና_ምሬትን_አሰወግጂ

ችግር የማያጋጥመው ሰው የለም ።ችግርን ለሰው ማዋየት ደግሞ እፎይታና መፍትሄ ያስገኛል ።እያንዳንዱ ሰው ችግሩን የሚያዳምጠውና የሚቆረቆርለት ሰው እንዲኖረው ይፈልጋል ።ነገር ግን ለሁሉም ነገር ጊዜና ቦታ አለው ።ለወቀሳም ቢሆን ጊዜና ቦታ ሊመረጥ ይገባል ።አንዳንድ ሞኞች ራስ ወዳድ ሴቶች ባሎቻቸው ቀኑን ሙሉ በሰራ ሲደክሙ መዋላቸውን በመዘንጋት የድካም መንፈሳቸውን እሰኪያድሱ ትንሽ በመታገስ ፋንታ ገና እንደገቡ የምሬት ዶፍ ያወርዱባቸዋል ።
☞"አንተ ምን አለብህ ?ከነዚህ አሰቸጋሪ ልጆች ጋር ትተኸኝ ትሄዳለህ ።
☞አንዱ ልጅ የፊቱን በር መስታወት ሰበረው ።ይሄ ደግሞ ጥናቱን እርግፍ አድርጎ ትቶታል ።ውጤቱም አሽቆልቁሏል ።
☞ሴቶቹ ስርዓት የሚባል ነገር የላቸውም ።ጩኸታቸው ሊያሳብደኝ ነው
☞በቤት ስራ አያግዙኝም ።
☞ቀኑን ሙሉ ብቻየን ስደክም ነው የዋልኩት
☞ሰዋከብ እጄን በቢላዋ ቆረጥኩት ።
☞ችግሬን የሚረዳልኝ ሰው የለም
☞ልጅ ባልወልድ ኖሮ ይህ ሁሉ ችግር አይደርሰብኝም ነበር ።
☞በነገራችን ላይ እህትህ መጥታ ነበር ።ምን ሆና ነው ግን አንደሆነ ነገር ያደርጋታል ።ሆ! የአባቷን ሀብት የቀማሆትኮ ነው የመሰላት
እናትህንማ ተዋቸው ።ከበሰተጀርባዬ ብዙ ነገር ያወራሉ ።ፈጣሪ ለምን ከእንዲህ አይነት ሴት ጋር አንዳገናኘኝ አላውቅም ።በሁሉም ነገር ተማርሬያለሁ ።

☞ትናንት ከሳራ ሰርግ ምነው ባልሄድኩ ነው ያልኩት
☞የጓደኛህ ሚስት ብታያት !ምን አለ አኔም እንደሷ እድለኛ ሴት ብሆን ?የለበሰችው ልብስ ፣ያረገችው ጫማ ፣ወርቋ !አንዳንድ ወንዶች ሚስቶቻቸውን በጣም ስለሚወዱ ቆንጆ ቆንጆ ነገሮችን ይገዙላቸዋል ።ትክክለኛ ባል ማለት አንዲህ አይነቶች ናቸው ።እሷ ስትገባ ሁሉም ሰው በአድናቆት ተቀበላት ።ሰዎች የለበሰከውን ነው የሚያዩት ።አኔንማ አንዴት በንቀት ዓይን አንዳየችኝ ልክ ናት አኔ እንደሷ እድለኛ ሴት አይደለሁም ።እሷ የሚወዳት ባል አላት ። #ትሰማለህ አይደል ከዚህ በኋላ አንተንና ልጆችህን በመንከባከብ አዚህ ቤት ውሰጥ ህይወቴን መጨረስ አልፈልግም ።
ስለዚህ የምታደርገውን ነገር አድርግ !

ይህን መሰሉ አካሄድ ስህተት ነው ።አንዲህ ዓይነት አመል ያላቸው ሴቶች ባሎቻቸው በየዕለቱ ለሽርሽርና ለመዝናናት የሚወጡ ነው የሚመስላቸው ።

ወንዶች በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ችግሮች ያጋጥማቸዋል ።እመቤት ሆይ ! ባልሽ በሰራ ላይ ምን እንደሚያጋጥመው አታውቅም ።ቀኑን ሙሉ ክፉና አሰቸጋሪ ሰዎች ጋር ሊሆን ይችላል የሚውለው ።ስለዚህ ቤት በሚገባበት ወቅት ወቀሳዎችሸን በሙሉ በእንዴ በማዥጎድጎድ ባል መሆኑን እንዲጠላ ማድረግ የለብሽም ።

በመጨቅጨቅና በመነዝነዝ ለጭንቀት የምትዳርጊው ከሆነ ከአንቺ ጭቅጭቅ ለመራቅ ሲል አዲስ ባህሪ ይጀመራል ።ወደ ቤት ከመግባት ይልቅ
ወደ መጠጥ ቤት ፣ጫት ቤት ወዘተ ለመሄድ አለያም አንዲሁ በየጎዳናው ለመዞር ይገደዳል ።

ስለዚህ እመቤት !በፈጠረሽ ይህን በየመጥፎ አጋጣሚዎች መጨቃጨቅሸን ተይ ።ለወቀሳ ተስማሚ ወቅቶችን ምረጪ ።ከዚያም በመውቀስ ሳይሆን በማማከር አይነት ዋነኞቹ ችገሮችሸን በእርጋታ ለባልሸ አሳውቂ ።በዚህ መልኩ ችግሮችሸን ማቅረብሸ መፍትሄ የሚያስገኝ ከመሆኑም ባሸገር በባልሸ ላይ የጥላቻ ስሜት አይፈጥርበትም ።በቤተሰቡ መካከል ያለው ፍቅርም እንደተጠበቀ ይቆያል ።

ጨቅጫቃ ሴቶች በጭቅጭቅ ምን ማትረፍ እንደሚፈልጉ አይታወቅም ።የባሎቻቸውን ትኩረት ለማሰብ ከሆነ በርግጠኝነት ውጤቱ ተቃራኒ ነው የሚሆነው ።ለማበሳጨት ፣በሱ ላይ ስነልቦናዊ ችግር ለመፍጠር አለያም ህይወቱን ለማበላሸት አስበው ከሆነ ግን በአርግጥም ይሳካላቸዋል ።

ውድ ሴቶች ! ለባሎቻችሁና ለቤተሰባችሁ የምታስቡ ከሆነ ይህን መጥፎ አካሄድ ማቆም አለባችሁ ።ይህ ባህሪ የቤተሰባችሁን ህይወት በአደገኛ ሁኔታ ሊጎዳ አንደሚችል ተረዱ ።አንድ ዶክተር ለፍርድ ቤት ቃሉን ሲሰጥ ፦"በጋብቻ ህይወታችን ውሰጥ ሚስቴ አንድም ቀን ጥሩ ሴት ሆና አይቻት አላውቅም ።ቤታችን ሁሌ አንደተረበሸ ነው ።ጧት
ማታ ጭቅጭቅ ።በሷ በጣም ተማርሬያለሁ ።በርካታ ገንዘብ ከሰጣት በኋላ ፍቺ ፀደቀለት ።ከዚያም እፎይ በሚል አይነት ሰሜት " ከዚህም በላይ ብትጠይቀኝ ኖሮ ከሷ ለመገላገል ስል ያለኝን አጠቃላይ ሀብትና የህክምና ዲግሪዬን ሳይቀር እሰጣት ነበር "ብሏል ።



#ምንጭ ☞ ፍቅርና እና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ

#ክፍል ➍ ይቀጥላል.........

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- አራት 4⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL

እስኪ ብቃት ያላት ሴት ለብቁ ወንድ ነዉና አንተም ወንድነህና እስኪ ከአንተ የሚጠበቀዉንም እንዳስ

#የቤተሰብ_ኃላፊ

የቤተሰብ ሀላፊ መሆንህን አትዘንጋ
ወንድና ሴት ሁሉቱም የቤተሰብ መሰረቶች ናቸው ።ነገር ግን ወንዶች በምክንያታዊነት የተሻሉ ስለሆኑ የቤተሰብ መሪ ሊሆኑ ችለዋል ።ስለዚህ ወንዶች ቤተሰባቸውን በመደገፍ ረገድ ትልቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል ።

#ወንድ
☞በብልሀት ቤተሰቡን ማስተዳደር
☞ለቤተሰቡ ደሰታ
☞ቤቱን ሰላም የሰነፈነበትና
☞ሚስቱን የቤቱ ዘውድ ማድረግ ይችላል ።ሴትም ልክ አንደ ወንድ ሁሉ የሰው ፍጡር መሆኗንና እሷም ፍላጎቶቿን የማሟላትና በነፃነት የመኖር መብት እንዳላት ማወቅ አለበት ።

ሚስት ማግባት ሰራተኛ መቅጠር አይደለም ።ቀሪ ህይወትን አብራ የምታሳልፍ አጋርና ጓደኛ መምረጥ እንጂ ።ወንድ ለሚስቱና ለፍላጎቶቿ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ።ሚሰት ባል እንደፈለገው የሚያደርጋት ንብረቱ አይደለችም ።ከሱ ላይ የምታገኛቸው በርካታ መብቶችም አሏት ።

🌹የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ለአባወራዉ
1⃣
#ሚስትህን_ተንከባከብ

የአንድ ቤተሰብ የስኬት ሚስጥረ ባል ሚስቱን ከሚንከባከብበት ዘዴ የሚመነጭ ነው ።ሴት ልጅ ባሏን በጥሩ ሁኔታ መንከባከቧ ወሳኝ እንደሆነው ሁሉ ወንድም ሚስቱን መንከባከቡ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ተግባር ነው ።ነገር ግን አንድ ባል ሚስቱን መልካም ሚስት ለማድረግ ምን ማድረግ አንዳለበት ማወቅ ይኖርበታል ።

~~~ለዚህም ሚስቱ ምን አይነት ባህሪና ፍላጎት እንዳላት ጠንቅቆ ማወቅ አለበት ።ህይወቱን በሚስቱ ፍላጎትና አግባብነት ያላቸው ጥያቄዎቿ መሰረት ማስተካከል ይኖርበታል ።በሚያሳየው መልካም ባህሪ ሚሰቱ እሱንና ቤተሰቧን አንድትወድ ማድረግ ይችላል ።ይህ ርዕሰ ጉዳይ በቀጣዮቹ ምዕራፎች በደንብ ይብራራል ።

🌹 የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ለአባወራዉ
2⃣
#አፍቃሪ_ሁን

ሴት ልጅ የእዝነት ማዕከል ናት ።ህይወቷ በፍቅርና በእዝነት የተሞላ ነው ።በሌሎች መወደድን ትፈልጋለች ።በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ስትል ራሷን አሳልፋ እስከመስጠት ትደርሳለች ።

~~~ማንም ሰው አይወደኝም ብላ ካሰበች እንድ ውድቀት ትቆጥረዋለች ።ደሰታ የራቃትና የተገለለች ትሆናለች ።በጋብቻ ህይወት ውሰጥ የአንድ ባል ስኬት ለሚስቱ በሚያሳየው ፍቅር ይወሰናል ማለት ይቻላል ።

#ውድ_ወንድም_ሆይ!
ሚስትህ አንተን ከማግባቷ በፊት የቤተሰቦቿን ፍቅርና እንክብካቤ ታገኝ ነበር ።አሁን ግን ቀሪ ህይወቷን ከአንተ ጋር ለማሳለፍ የጋብቻ ውል ፈፅማ ወዳንተ መጥታለች ።ስለዚህ የምትፈልገውን ፍቅርና እንክብካቤ አንተ እንድታሟላላት ተሻለች ።

☆ ቤተሰቦቿና ጓደኞቿ ይሰጧት ከነበረው የበለጠ ፍቅር ከአንተ ማግኘት ትፈልጋለች ።ከምንም በላይ ሰላመነችህ ነው ቀሪ ህይወቷን ከአንተ ጋር ለማሰለፍ የወሰነችው ።

☆ ሚስቱን ማፍቀር የደሰተኛ ትዳር ሚስጥር ነው ።የሚስትህን ልብ ለማግኘትና ፍላጎትህን የምታሟላልህ ታዛዠ ፣አፍቃሪና ታማኝ ሚሰት አንድትሆንልህ ከፈለግህ ፣ጠንካራ መሰረት ያለው ትዳር እንዲኖርህ የምትሻ ከሆነ ሁልጊዜም ለሷ ያለህን ፍቅር ማሳየትና መግለፅ አለብህ ።

☆ እዝነትህን ከነፈግካት ለቤቷ ፣ለልጆቿ ከሁሉም በላይ ደግሞ ላንተ ያላት ፍቅር ይቀዘቅዛል ።ካንተ ያጣችውን ፍቅር ከሌሎች ለማግኘት ጥረት ልታደርግ ትችላለች ።ቤትህ ሰላም ደርቀዋል ።ፍቅር የሌለበት ቤት የቱንም ያህል ውብና በማራኪ እቃዎች ያሸበረቀ ቢሆንም ሲኦል ነው ።

☆ሚስትህ በአንተና በትዳሯ ላይ ያላት ጥላቻ ሊበረታና ፍቺ እስከመጠየቅ ልትደርስ ትችላለች ።ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው አንተ ነህ ።ምክንያቱም ከአንተ ማግኘት ያለባትን እንክብካቤ አልሰጠሀትም ።

ብዙ ፍቺዎች የሚፈፀሙትም ከእንክብካቤ ጉድለት ነው ።
እ.ኤ.አ 1969 ከተፈፀሙ አጠቃላይ 10,372 ፍቺዎች መካከል 1,203 ሴቶች ለፍቺ የዳረጋቸው ባሎቻቸው ለፍላጎታቸውና ስሜታቸው ትኩረት ሊሰጡ አለመቻላቸው የትዳር ትርጉም አንዲያጡና በህይወት ተሰፋ እንዲቆርጡ ስላደረጋቸው አንደሆነ ገልፀዋል ።

~~~ አንዲት ሴት ፍርድ ቤት ቀርባ ባለቤቷ የሰጣትን ጥሎሽ ጨምሮ ሌላም ገንዘብ ጨምራ ሰጥታው ለፍቺ እንዲስማማ ታግባባዋለች ።ምክንያቷ ምን አንደሆነ ስትጠየቅ "ባለቤት ትርፍ ጊዜውን ከኔ ይልቅ ከጓደኞቹ ጋር ማሳለፍን ይመርጣል ።ስለዚህ ከሱ ጋር መቀጠል አልፈልግም "ብላለች ።

ፍቅርና ውዴታ በሌሎች ልብ ውሰጥ ይገባ ዘንድ እውነተኛ መሆን አለበት ።በልብ ብቻ መውደድ በቂ አይደለም ።በቃላት መግለፅም ያሰፈልጋል ።ግልጽ ሁን ለሚስትህ ያለህን ፍቅር በቃላትና በተግባር ከመግለጽ አትቆጠብ ።

ይህ የፍቅር ቁርኝትን ያጠነክራል ።
☞ባለችበትም ሆነ በሌለችበት እሷ ለአንተ ልዩ ሰው እንደሆነች ተናገር ።
☞በጉዞ ወቅት ደውልላት አንደናፈቅካትም ግለፅላት
☞አልፎ አልፎ አንዳንድ ነገሮችን ግዛላት ።
☞በስራ ላይ በሆንክበት ወቅት ደውልና ሰላምታ አቅርብላት ይህን መሰሉ ተግባር በሴት ልጅ ልብ ውሰጥ ታላቅ ቦታ ይሰጠዋል ።

■ አንዲት ሴት ስትናገር "ከባለቤት ጋር በደሳሳ ጎጆ ውሰጥ ለስድስት ዓመታት ያህል በሰላም ኖረናል ።በዚህም በዓለም ላይ ራሴን የመጀመሪያዋ እድለኛ ሴት አድርጌ ነበር የምቆጥረው ።ማርገዜን ሳውቅ ደስታዬ ወደር አልነበረውም ።ሁኔታውን ለባለቤቱ ስነግረው አቅፍ አድርጎኝ ራሱን መቆጣጠር እስኪያቅተው ድረስ የደስታ እንባ አነባ ።ወዲያውኑ ወጣና ከወር ገቢው እየቀነሰ የሚያጠራቅመውን ገንዘብ አንሰቶ ትልቅ የወርቅ ሐብል ገዛልኝ ።"ይህን ሐብል የምሰጠው ከሁሉም በላይ ለሆነቸውና በዓለም ላይ አምሳያ ላላገኘሁላት ውድ ባለቤቱ ነው "በማለት አንገቴ ላይ አጠለቀልኝ ።ነገር ግን አብረን ብዙ አልቆዬንም ።በመኪና አደጋ ሞተ "ብላለች በሐዘን በተሰበረ ሰሜት ።


እናም ለሚስቶቻቸዉ አልፎ አልፎ ስጦታ መስጠት ሚስቶችን ደስተኛ መቼም የማይረሱት ዉለታ መሆኑን አትዘንጋ

በክፍል ➎ ለዉዷ እህቴ መልካም ስነምግባር መኖር እንዳለባት እንዳስሳለን...
ምንጭ ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ

ሼር ያድርጉ
👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- አምስት 5⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL


💐 የትዳር ማጣፈጫ ቅመም አምስት
#መልካም_ፀባይ_ይኑርሽ !

አንዳንድ ጥሩ ተፈጥሮና መልካም ፀባይ ያላቸው ሰዎች አሉ ።ይህ አይነቱ ስብዕና በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትና ከማስገኘቱም በላይ ለስነልቦና ችግር ከማጋለጥ ያድናል ።

ጥሩ ሰዎች ለህይወት ያላቸው አመለካከት ጥሩ ስለሚሆን ችግር ቢግጥማቸው እንኳ ሁሉንም ነገር እንዳመጣጡ ለመሸኘት አይቸገሩም ።መጥፎ ባህሪ ላላቸው ሰዎች ህይወት አሰቸጋሪ ናት ።የነገሮች ሁሉ መጥፎ ጎን ብቻ ነው የሚታያቸው ።ተመስገንን አያውቁትም ።ሁሌም ህይወትን ሲያማርሩ ይደመጣሉ ።

■ ይህ አይነት ባህሪ ደግሞ በሰዎች ዘንድ ስለሚጠላ በጥሩ መንፈስ የሚቀርባቸው ጓደኛ አያገኙም ።ምክንያቱም ሁሌ እሮሮ መሰማት የሚፈልግ ሰው የለም ።ይህ የልብ ጓደኛ ማጣታቸው ደግሞ ለተለያዩ የሰነ ልቦና ችግሮች እና ሌሎች በሽታዎች እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል ።

#እመቤት_ሆይ !
ከልጆችሸና ከባለቤትሽ ጋር በደስታ ለመኖር ከፈለግሽ
ባህሪሸን አስተካካይ
ፀባይሸ ጥሩ ይሁን
ጠብ ጫሪ አትሁኚ

☞ቤትሸን ንትርክ ወይም ሰላም የሰፈነበት የማድረጉ ችሎታ በእጅሽ ነው ያለው ።
☞ፍላጎቱ ካለሸ ልጆችሸና ባለቤትሽ ሰላም የሚያገኙብሸ የደግነት አውራ መሆን ትችያለሽ ።
☞በፈገግታሸና በአነጋገር ለዛሸ ልባችው ወስጥ ጥሩ ስሜት ማሳደር አንደምትችይ አውቂ ።

ያንቺ መልካም ባህሪ ልጆችሽ በትምህርት ቤት ፣ባለቤትሽ በሰራ ቦታ ቀኑን ሙሉ ደስተኞች ሆነው እንዲውሉ ያደርጋቸዋል ።ስለዚህ ጥሩ ህይወት አንዲኖርሸና ከባለቤትሽ ጋር ያለሽ ግንኙነት ጤናማ ይሆን ዘንድ ቅንነት አይለይሸ ።ትዳርን አንደ ምሶሶ ደግፎ የሚያቆየው መልካም ሰነ ምግባር ነው ።ብዙ ጊዜ ፍቺ የሚከሰተው በባልና ሚስት መካከል የባህሪ አለመጣጣም ሲኖር ነው ።

● መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ብዙዎች ፍቺ የፈፀሙ ጥንዶች ተመሳሳይ አመለካከት ፣የሞራል እሴቶችንና ስነምግባር አይታይባቸውም ።

ለቤተሰብ ግጭት ዋናው መንስኤ የጥንዶች ባህሪ አለመጣጣም ነው ።የሚከተሉት መረጃዎች ይህን እውነታ የሚያረጋግጡ ናቸው ።
"ከሰባ በመቶ ባላይ የሚሆኑት የቤተሰብ ግጭቶች የሚከሰቱት በዚህ ጉዳይ ነው ።አንዲት ሴት "ባሏ ሁልጊዜ ምሳውና ራቱን ቤቱ አንደማይበላ ለፍርድ ቤት በማማረር ትገልፃለች ።ባልዮውም ምከንያቱ ምን አንደሆነ ሲጠየቅ "ሚስቴ በፍፁም በውስጧ ጥሩ ነገር የለም ።በዓለም ላይ ካሉ መጥፎ ሴቶች ሁሉ የከፋች ናት"በማለት መልሷል ።ይህን ሲናገርሞ የሴትዮዋ በፍጥነት ተነስታ ከዳኞች ፊት እሱን መሳደብና መማታት ጀመረች ።

ይቺ ሞኝ ሴት በመሳደብና በመማታት ባሏን ወደ ቤት የምትመልስ መሰሏታል ።ነገር ግን ቀላልና በሳል የሆነውን መልካም ባህሪን የማሳየት የመሳብ ዘዴን መጠቀም ትችል ነበር ።

ሌላዋ ሴት ባለቤቷ ለአስራ አምስት ወራት ያህል ሳያናግራት እንደቆየና የቤት ወጪም የሚልከው በእናቱ በኩል አንደሆነ ለፍርድ ቤት ሪፖርት አድርጋለች ።
ባልዮው ሲመልሰም "ሚስቴ የምታሳየኝ መጥፎ ባህሪ ልታገሰ ከምችለው በላይ ስለሆነብኝ ለረዥም ጊዜ ላላናግራት ወሰንኩ "ብሏል ።


ጥንዶች አዲስ ቤት ሰርተው ገብተዋል ።የቤት ምርቃት አድርገን ደስታችንን ከወዳጅ ዘመድ ጋር እንካፈል በሚል ደግሰ ይደግሳሉ ።ዘመድ ወዳጅ ተጠራ ።ቤት በሰው ተሞልቶ ይበላል ፣ይጠጣል ።በመሀል ሚስት ለባሏ ለቡና ቁርሰ የሚሆን ኬክ ካልገዛህ ትለዋለች ።ባል "ብር የለኝም ዳቦ አለ እሱ ከተቆረሰ ይበቃል "ይላል
.....ሚስት ልትረዳው አልቻለችም ።"ብርማ አለህ የለኝም ማለት ስለምትወድ ነው አንጂ "እያለች ትሳደብ ጀመር ።አሱም መልስ ይሰጣታል ።እንግዶች አሰኪያውቁባቸው ድረስ ።እንግዶቹ አንተም ተው አንችም ተይ ይሉ ጀመር ።እነሱ ግን ንትርካቸውን ሊያቆሙ አልቻሉም ።አንድ አባት ይነሱና "ዛሬ የደሰታችን ቀን ነው ።ኑ ቤታችንን መርቁልን "ተብሎ ጠርቶ ሲያበቁ ጠብ መፍጠር በየትም አገር ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ነውር ነው ....አንቺም ለእንግዶችሸ ክብር ይኑርሽ ።አንተስ ብትሆን ወንድ አይደለህም አንዴ ምንድነው ነው ከሴት ጋር እሰጣ ገባ ?"አሉ ።

ሚስት ትነሳና "አይ አባባ እሱኮ ወንድ አይደለም .... ብላ ፀያፍ ቃል ወረወረች ።ሸማግሌው ሞቅ ብሏቸው ነበርና "ተዲያ ወንድ ካልሆነ አነዚህን ልጆች ከማን ወለድሻቸው እባክሽ ?ይሄ ንግግርሸ እኮ ብዙ መዘዝ ሊያመጣብሸ ነው "አሉ ።ብዙዎች ሰዎች ሲያዝኑ የተወሰኑት ሳቁ ።

ባል ይህ አይነቱ ውርደት የደረሰበት በጓደኞቹና በዘመዶቹ ፊት ነው ።ሮጦ ያዛትና ይደበድባት ጀመር ።ኡኡታዋን አቀለጠችው የሰፈር ሰው ተሰበሰቡ ።ፖሊስ መጣ ።ይታሰርልኝ አለች ።ወሰደው አሰሩት በቀጣዩ ቀን ፖሊስ ጣብያ ሄዳ ከእስር ይፈታልኝ አለች ...ተፈታ ወደ ቤቱ ግን አልተመለሰም ።ሸማግሌዎች ሄደው "እሷ ጥፋቷን አምና ይቀርታ አድርግልኝ ወደ ቤትህ ግባና ትዳራችን እንቀጥል "ብላሃለች ሲሉት "እኔኮ ወንድ አይደለሁም ።ወንድ ፈልጉና አጋቧት አለ ።አቋሙን ሊቀይር ባለመቻሉም ፍቺ ተፈፀመ ።

ብዙዎቹ ቤተሰባዊ ግጭቶች በመተዛዘን ፣በመቻቻልና ጥሩ ስነምግባርን በማሳየት ሊፈቱ የሚችሉ ናቸው ።

ባለቤትሽ ለአንቺ አዝነትና ክብር የሚጎድለው ፣ተሳዳቢ ፣ጯሂ ሊሆንና ሌሎች ትዳር ላይ ግጭት ሊያሰከትሉ የሚችሉ ባህሪያት ሊኖሩበት ይችላል ።ይህን ችግር ለመፍታት አንድ ብቸኛ ዘዴ አለ ።ይሄውም ለሱ አዛኝና ደግ ሆኖ መቅረብ ።ደግ ሆነሽ ቅረቢውና ውጤቱን ጠብቂ ።አስገራሚ ለውጥ ታያለሸ ።ምክንያቱም ደግነት የማያሸንፈው ነገር የለም ።

》》》በሚቀጥለዉ ክፍል ለዉዱ ወንድሜ ሚስትህን ማክበር እንዳለብህና መልካም ባህሪ መላበስ እንዳለብህ እንዳስሳለን

#ምንጭ ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ

ክፍል ➏
ይቀጥላል....



👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ስድስት 6⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL



🌹የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ለአባወራዉ
3⃣
#ሚስትህን_አክብር

ወንድ ልጅ በወንድነቱ አንደሚኮራው ሁሉ ሴት ልጅም በሴትነቷ ትኮራለች ። መከበርን ትፈልጋለች ፡፡የምትናቅና የምትዋረድ ከሆነ ስሜቷ ይጎዳል ።

> የሚያከብሯትን ሰዎች ሰትወድ ዝቅ አድርገው የሚያይዋትን ሰዎች ደግሞ ትጥላለች ።

#ውድ_ወንድም_ሆይ !
ከሌሎች በበለጠ ሁኔታ ሚስትህ የህይወት አጋሯን የቅርብ ጓደኛዋ በሆንከው ባንተ መከበር ትሻለች ።የመከበር መብትም አላት ።ለአንተና ለልጆችህ ድሎት የምታደርገውን ከፍተኛ ጥረት እንድታደንቅላትና ክብር እንድትሰጣት ትፈልጋለች ።እሷን ማክበርህ አንተን ዝቅ አያደርግህም ።ለሚስትህ ልዩ ፍቅር ያለህ ሰው መሆንህን ያረጋግጥልሃል አንጂ ።

~~~ስለዚህ ለሌሎች ከምትሰጠው ክብር በበለጠ ሁኔታ ሚስትህን አክብር ።
☆ በትህትና አናግራት ።
☆ ስትናገር አታቋርጣት ።
☆ አትጬህባት ።
☆ በቁልምጫ ስሞች ጥራት ።
☆ ወደ ቤት ስትገባ ሰላምታ አቅርብላት ።
☆ ስትወጣ ቻው በላት ።
☆ ራቅ ወዳለ ቦታ በምትሄድበት ወቅት በተለያዩ መንገዶች እሷን ከማግኘት አትቆጠብ ።ስልክ ደውልላት ።ደብዳቤ ፃፍላት ።
☆ ከሰዎች ጋር በምትሆንበት ጊዜ ክብር ስጣት ።
☆ እሷን ከመሳደብና ከማንቋሸሽ ተቆጠብ ።
☆ ለቀልድም ቢሆን አትሰደባት ።
☆ ለሷ ቅርብ በመሆንህ አትቀዬመኝም ብለህ አታስብ ።ይህን መሰሉን ድርጊት ላትወደው ነገር ግን በግልጽ ላትነግርህ ትችላለች ።

አንዲት የሰላሳ አምስት ዓመት ሴት ፍቺ ለምን እንደጠየቀች ሰታብራራ ፦"ካገባሁ አሰራ ሁለት ዓመቴ ነው ።ባሌ ጥሩ ሰው ነው ።በርካታ ጥሩ ባህሪያት አሉት ነገር ግን እኔ ሚስቱና የልጆቹ እናት መሆኔንና ክብር እንደሚገባኝ መረዳት አልቻለም ።እንድ ግብዣ ፣ሰርግና የሀዘን ቤት ባሉ ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ቦታዎች ላይ መገኘት ይወዳል ።ነገር ግን እኔን በመሳደብና በማዋረድ ነው የሚያሳልፈው ።ምን ያህል እንደተሰቃየሁ ልነግራችሁ አልችልም ።አዕምሮዬ በጣም ተጎድቷል ።ወደ ስነልቦና አማካሪ መሄድ ሳይኖርብኝ አይቀርም ።ንቀት በተሞላበት ሁኔታ እንዳያየኝ ፣ሚሰቱ እንደሆንኩ ፣ትልቅ ሰው እንደሆንኩ ፣ሊያከብረኝ እንደሚገባና የሰው መሳቂያና መሳለቂያ ሊያደርገኝ እንደማይገባ ነግሬዋለሁ ።ለምኜዋለሁ ።ሊሰማኝ ግን አልቻለም ።ስለዚህ ፍቺን መርጫለሁ ።ህይወት ለብቻዬ የተሳካ እንደሚይሆንልኝ አውቃለሁ ።ነገር ግን በሰው መሀል እየተዋረዱ ከመኖር የማይሻል ነገር የለም "ብላለች ።

~~~ ሁሉም ሴቶች ባሎቻቸው እንዲያከብሯቸው ይፈልጋሉ ።በተለይ ደግሞ ከሰው ፊት ።ባሎቻቸው ከሰው ፊት ሲሰድቧቸው ዝም የሚሉ ሴቶች ቢኖሩ እንኳ ውስጣቸው ደስ ብሎት አይደለም ዝም የሚሉት ።መናገር ስላልፈለጉ እንጂ ።
☞ሚስትህን ካከበርካት እሷም በተራዋ ታከብርሃለች ።ግንኙነታችሁ ይጠነክራል ።
☞ሚስትህን አክባሪ ሰው በመሆንህ ሌሎች ሰዎችም ያከብሩሃል ።ከናቅካት እሷም ትንቅሃለች ።

#ውድ_ወንድሜ_ሆይ !
ትዳር ባርያ እንደ መግዛት አይደለም ።ሚስትህን አንተን ያገባችህ ቀሪ ህይወቷን ከአንተ ከምትወደው ባሏ ጋር በሰላም ለማሰለፍ ነው ።ስለዚህ አንተ ሊደረግልህ የምትፈልገውን እንክብካቤ ለሷም አድርግላት ።

🌹የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ለአባወራዉ
4⃣
#መልካም_ባህሪ_ይኑርህ

የዚህ ዓለም እንቅስቃሴ በሰው ልጅ እጅ አይደለም ያለው ።የህይወት ገጠመኞችም እኛ በፈለግነው መልኩ አይከሰትም ።

~~~ አንድ ሰው ጠዋት ከቤቱ ከወጣበት ደቂቃ ጀምሮ ወደ ቤቱ እሰከሚመለሰባት ሰዓት ድረስ ብዙ ነገሮች ያጋጥሙታል ።
◇ከሰው ጋር ሊጣላ ፣
◇መጥፎ ጓደኛ ሊገጥመው ፣
◇ታክሲ ወይም አውቶብስ አጥቶ ብዙ ሰዓት ሊጉላላ ፣
◇በሰራ ቦታ ላይ በተፈጠረ ችግር ሊከሰሰ ፣
◇ገንዘብ ሊጥል ወይም ሊዘረፍ ይችላል
።እነዚህና መሰል ችግሮች በየትኛውም ቦታ በየትኛውም ሰዓት ይደርሳል ።
ነገር ግን አንዳንድ ወንዶች ለሚያጋጥሙ ችግሮች ሁሉ ሌሎችን ወይም ይህችን ዓለም ማማረር ተገቢ አለመሆኑን እያወቁ ወደ ቤት ሲመጡ ንዴታቸውን ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ላይ ለማብረድ ይሞክራሉ ።

ይህ መጥፎ ባህሪ ከላብህ ያንተ ወደ ቤት መግባት ለቤተሰቡ የሰይጣን መግባት ይሆናል ።
አንተ ስትመጣ ልጆችህ እንደ አይጥ አይናቸውን አፍጠው በየቦታው ይወተፋሉ ።ፀብ ለመጫር የሚያሰችል ስህተት ትፈልጋለህ ።
>ምግቡ ጨው ሊበዛበት ወይም ሊያንሰው ይችላል ።
>የለመድከው ቡና ላይፈላ ይችላል ።
>ቤቱ ላይፀዳ ይችላል ።
>ልጆቹ ሊረብሹ ይችላሉ ።...።ስለዚህ እነዚህ ነገሮች ቤትህን ቀውጢ እንድታደርገው በር ይከፍቱልሃል ።ትጮሃለህ ።ልጆችህን ትሳደባለህ ።ትመታለህ .. በዚህ ወቅት ቤትህ ሰላምና ፍቅር የሰፈነበት መሆኑ ቀርቶ ሲኦል ይሆናል ።

~~~ አንተ ቤት በገባህበት ወቅት ልጆችህ ወደ ውጭ መውጣት ከቻሉ በረው ይወጣሉ ።ካልቻሉ ደግሞ አንተ የምትወጣበትን ሰዓት በጉጉት ይጠባበቃሉ ።

በዚህ ዓይነት ቤተሰብ ውሰጥ
ግለኝነት እና አስፈሪ ሁኔታ ይነግሳል ።
ጭቅጭቅና ንዝንዝ ይበዛል ።
ቤቱ ይታመሳል ።
ሚስትህ ባንተ ትሳቀቃለች ።
ፊትህን ማየት ያስጠላታል ።
ደሰታ ይርቃታል ።

እናም እዉጭ በሚፈጠሩ የህይወት ዉጣ ዉረድ የእለት ተዕለት ተግባራት በመናደድ ንዴትህን ሚስትህ ጋር የምታበርድ ከሆነ ትዳርህ አደጋ ላይ እየወደቀ መሆኑን አትዘንጋ


በሚቀጥለዉ ክፍል እህቴ ሆይ የተሳሳተ አመለካከትን ማስወገድ እንዳለብሽ እንዳስሳለን
ምንጭ ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ

#ክፍል ➐ ይቀጥላል

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሰባት 7⃣

በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL




💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም
#የተሳሳቱ_አመለካከቶችን_አሰወግጂ !

እመቤት ሆይ! አንቺ የቤትሸ ዘውድ ነሽ ።ብልህና አስተዋይ ሁኚ ።ወጪሸ ከገቢሽ ጋር የተመጣጠነ ይሁን ።ከሰዎች ጋር በፍፁም አትፎካከሪ ።በሌሎች አትቅኚ ።የሌሎች ኑሮ ላንቺ አይሆንም ፡ያንቺ ኑሮም ለሌሎች አይሆንም ፡
☞ያየሸውን ሁሉ ልብስ ፣
☞ያየሸውን ሁሉ ጌጣጌጥ ፣
☞ያየሸውን ሁሉ እቃ ባልሽ ከአቅሙ በላይ የሆነ ገንዘብ አውጥቶ ወይም ተበድሮ እንዲገዛ አታድርጊው ይህ ሞኝነት ነው ።ይልቁንም ገቢያችሁ እስኪያድግ ድረስ በትዕግስት ጠብቂ ።ብዙ ጊዜ ለጉራ ሲሉ አላሰፈላጊ ብክነት የሚያደሰቱት አላዋቂና ራስ ወዳድ ሴቶች ናቸው ።ባሎቻቸው በእዳ አንዲዘፈቁና የሚሰቶቻቸውን የማያቋርጥ ፍላጎት ለማሟላት አንዲናውዙ ያደርጓቸዋል ።

አንደዚህ አይነት ሚስቶች ያሏቸው ወንዶች ያላቸው አማራጭ ፍቺ ነው ።ትዳርን ዓላማና ትርጉም ያልተረዱ ሴቶች ትዳር ባል የሚስቱን ህፃናዊና ቁሳዊ ፍላጎቶች የሚያሟላበት ካምፕ ይመስላቸዋል ።እንደፈለጉ ሲሆኑ ባሎቻቸው ዝም እንዳሏቸውና በገንዘብ አወጣጣቸው ላይ ጣልቃ እንዳይገቡ ይፈልጋሉ ።አንዳንዴ ከዚህም አልፈው ባላቸው ከአቅሙ በላይ ወጪ እንዲያወጣና ከዚያም ለኪሳራ ተዳርጎ ወደ ወንጀልና ሌሎች አልባሌ ተግባራት እንዲሰማራ ያደርጉታል ።

#ገደብ_የለሽ_ፍላጎቷ_ለፍቺ_ያጋላጣት_ሴት
በሰዎች ዘንድ ትናቃለች
ልጆቿም ይጠሏታል
ለብቸኝነት ኑሮም ትዳረጋለች
ሌላ ትዳር ውሰጥ የመግባት አድሏም የመነመነ ነው ።
ብታገባም ድጋሚ ተመሳሳይ ችግር ይገጥማታል ።

እመቤት ሆይ ! ያየሸውን ሁሉ መመኘትን ትተሽ ምክንያታዊ ለመሆን ሞክሪ ።ሌሎችን ለመምሰል ከመሞከር ይልቅ ብዙውን ጊዜሸን ለልጆችሸና ለባልሸ ደህንነት በመጣር አሳልፊ ።ባልሽ በከንቱ ገንዘብ የሚያወጣ ከሆነ እንዲቀንስ አድርጊ ።ለአላስፈላጊ ነገሮች ወጪ ከማውጣት ይልቅ የተወሰነ ገንዘብ እየቆጠቡ ለክፉ ቀን ማስቀመጥ ትልቅ ጠቃሜታ አለው ።


እስኪ አንድ ታሪክ ላጫዉትሽ
ባል ነዋሪነቱ ውጭ ነዉ ሚስት አግብቶ ሶስት ልጆችን ወልዷል ።ሚስቱና ልጆቹ አዲስ አበባ ነው የሚኖሩት ።አልፎ አልፎ እየመጣ ያያቸዋል ።ሚሰት ገንዘብ ማባከን ከጀመረች ውሎ አድሯል ።የሱስ ተገዥ ሆናለች ፡ ባሏ የሚልክላት ገንዘብ ሊበቃት አልቻለም ።አንዴ እኔን አመመኝ ሌላ ጊዜ ልጆቹ ታመሙብኝ እያለች ጭማሪ ገንዘብ ታስልካለች ።ከሰዎች ብር ትበደራለች ።የቤት እቃ ሳይቀር ትሸጣለች ።ባሏ የገንዘብ አወጣጧን እንድታስተካክል ቢመክራትም በያሰመክራትም ልታሻሸል አልቻለችም ።አንደውም ባሰባት ።ሌት ተቀን እየሰራ የሚያገኘው ገንዘብ አላግባብ መባከኑ ሰላማረረው በሷ ስም ብር ላለመላክ ወሰነ ።በጓደኛው በኩል እየላከ እሱ የቤት ኪራይና የልጆቹን ትምህርት ቤት ክፍያ የዓመቱን አንዴ እንዲከፍልና አንዲሁም ለወር የሚበቃውን የቤት አስቤዛ በርከት አድርጎ እየገዛ አንዲያቀርብላት አደረገ ።እሷም ሆነ ልጆቿ ህክምና ካደረጉ ደረሰኝ ትጠይቃለች ።

ሚስት ሱሷ አደብ አሳጣት ።ለወር ተብሎ የሚገዛውን የቤት አስቤዛ በርካሽ እያወጣች መሸጥ ጀመረች ።ሳምንት ሳይሞላው ያልቃል ሄዳ አለቀብኝ ትላለች ።አንደገና ተግዝቶ ይሰጣታል ።አሁንም ያልቃል ።መጠየቅ ሲያሳፍራት ልጆቿን ቁርሳቸውን ዳቦ በሻይ አያበላች ምሳቸውን እንጀራ ብቻ ትቋጥርላቸዋለች እራትም ያንኑ ...ልጆቹ ሊበላቸው አልቻለም ፡፡ ትልቁ ልጇ ለምን?? ይላት ጀመር ።"አንዲህ የሚያሰቃያችሁ አባታችሁ ነው ።አምስት ሳንቲም አይልክልኝም ።ታዲያ እኔ ከየት ላምጣ ?ልውለድ ?"ትለዋለች ።ሁኔታውን ለአባቱ ማሳወቅ ፈለገ ።ወረቀት አወጣና አንዲህ ሲል ፃፈ ።


"ዳድ እንዴት ነህ ?እኛስ ደህና አይደለንም ።ቤት ውሰጥ ምግብ የለም ።የሚቋጠርልን እንጀራ ብቻ ነው ።ዳድ አሰብ እስቲ ሁሌ እንጀራ መብላት አይሰለችም ?አኔ ግን ዳድ የሚቋጠርልኝን ምግብ አልበላውም እጥለዋለሁ ከዚያ ጓደኞቼ ያበሉኛል አንድ በጣም የሚወደኝ ጓደኛ አለኝ ።ለእናቱ ችግርተኛ ጓደኛ አለኝ ብሎ ሰለነገራት ለሁለታችንም የሚሆን የተለያየ ምግብ ትቋጥርልናለች ።እከሌ በጣም ጥሩ ሰው ናት /ሰራተኛቸው ።ባልወልዳችሁም ልጆቼ ናችሁ አሳዲያችኋለሁ ትለናለች ።እናታችንማ ክፉ ሆነች ።በሆነ ባልሆነው ትጮህብናለች ።ወንድሜን ለምን ምሳ እቃህን አልጨረሰክም እያለች ሁልጊዜ ትቀጠቅጠዋለች እሱ ዝም ይላታል ።እኔ ግን "ካልጣፈጠው አንዴት ይጨርሰ ?"ስላት "አፍህን ዝጋ አንተ ጥጋበኛ "ትለኛለች ።ብታያት ሁሌ ጫት ማኘክ ሽሻ ታጨሳለች ...መጠጥም ትጠጣለች ...ለጫት መግዣ ገንዘብ ከየት እንደምታመጣ ታውቃለህ ?ጋሼ የአንተ ጓደኛ የሚያመጣልንን የዱቄት ወተት ፣ዘይት ማርማላት ምናምን እየሸጠች ነዉ ።ይህንን የነገረችኝ ሰራተኛችን ነች

አንዳንዴ ደግሞ እቤት አታድርም ።ለሰራተኛችን ስልክ ትደውልና ዛሬ አልመጣም በጊዜ ዘጋጉና ተኙ ትላታለች ።እሷም ትልቁን ፍራሸ አውርዳ ሁላችንንም አቅፍ አደርጋን ትተኛለች ።አባዬ አንተ ጋ ውሰደን ።ሰራተኛችም ከኛ ጋር ትሂድ ።ማሚን ግን ከፈለግክ ውሰዳት ከፈለግክ አትውሰዳት ።አኔ አያገባኝም ።ቻው ።ደብዳቤ አንደፃፍኩልህ ለማሚ አንዳትነግራት ።በጣም ትቆጣኛለች ልትመታኝም ትችላለች ።ወረቀቱን አጣጥፎ በፖስታ ካሸገ በኋላ ለአባቱ ጓደኛ ሰጠው ።

እሱም ለአባቱ ላከለት ።ሚሰት እንደልማዷ ለሰራተኛዋ ደውላ "ዛሬ አልመጣም ልጆቹን በጊዜ አስተኛችው "አለቻት ።እሷም "ሴቷ ልጅኮ በጣም አሟታል ።ኃይለኛ ትኩሳት እላት ብትመጪ ይሻላል አለቻት ።"ተያት ባክሽ ።ጉንፋን ነው ።እንቅልፍ ሲወስዳት ይተዋታል "አለቻት ።

ልጅቷ ግን እንቅልፍ ሊወሰዳት አልቻለም ታቃስታለች ሰራተኛዋ ተጨነቀች ምግብ ልታበላት ብትሞክርም እሺ አላለቻትም ።ሙቀቱ ሲቀዘቅዝ ደግሞ ለማስተኛት አዝላ ወዲያ ወዲህ ትላለች ።በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ድንገት የግቢው በር ተንኳኳ ደነገጠች ...እኩለ ሌሊት ሆኗል ።ማን ሊሆን ይችላል ?እሷ አለመኖሯን ያወቀ ሌባ ሳይሆን አይቀርም አለች ።በድጋሚ በሩ በሃይል ተንኳኳ ።መጣችና የሞት ሞቷን "ማን ነው ?"አለች ።"አኔ ነኝ ክፈቺልኝ "አላት ።ባልየው ነበር ።ከፈተችለትና ገባ ።ሚስቱን "የታለች ?"ሲል ጠየቀ ።የለችም ።"

"የት ሄደች ?"
"የት እንደሄደች አላውቅም ።"
"ሌላ ጊዜም ውጪ ታድራለች ማለት ነው ?"
"አልፎ አልፎ ታድራለች ።"
"ታድያ ልጅቷን ለምን አዘልሻት ?"
"አሟታል ።"
"ምን ሆነች ?"
"ኃይለኛ ትኩሳት አለባት ።"
"እናቷ መታመሟን አላወቀችም ነበር አንዴ ?"
"ነግሪያት ነበር ።ጉንፋን ነው ይሻላታል አለች ::"ወዲያውኑ ጓደኛውን ጠራና ሀኪም ቤት ይዘዋት ሄዱ ።ጠዋት ላይ ልጆቹን ሲያያቸው በጣም አዘነ ...አመድ መስለዋል የቤቱ ዋና ዋና እቃ የለም ..ንዴቱን መቆጣጠር አቃተው ቤተሰቦቹንና ጓደኞቹን ጠራ አየሆነ ያለውን ነገርም አስረዳቸው ልጁ የፃፈለትን ደብዳቤም አነበበላቸው ።በጣም አዘኑ ይህ ሁሉ ሲሆን እሷ አልመጣችም ።ስልክ ተደወለላትና መጣች ። ፍቺ እንደሚፈልግ ነገራት እያለቀሰች "በፊት አንዲህ አይነት ባህሪ አልነበረኝም ኋላ ላይ ግን መጥፎ ጓደኞች አጋጠሙኝ ።በቀላሉ መውጣት የማልችለው አደገኛ ሱሰ ውስጥም አስገቡኝ ።ገንዘብ እጄ ላይ ሰለሌለ እነዚህን ነገሮች በቀላሉ ማግኘት እችል ዘንድ ውጭ ማደር ጀመርኩ እባክህን ይቅርታ አድርግልኝ ።ይህን ነገር ቀሰ በቀስ ለመተው እሞክራለሁ👇
አለች ፡፡ባል ጥላቻው ጫፍ ደርሶበታል ።"ትሰሚያለሸ አንቺን የማሰታምምበት ጊዜ የለኝም ።ምንም አይነት ዝባዝንኪም መሰማት አልፈልግም ።አሁኑኑ ፍቺው አንዲንፈፀም ነው የምፈልገው ?"ሲል አምባረቀ ።ሰዎቹም "መፍትሔዉ ፍቺ ብቻ ነው "አሉ ።ደነገጠች ከሆነም ልጆቼን ራሴ ነኝ የምይዘው አለች ።በሶስት ምክንያቶች ልጆቹን መያዝ አትችይም ።
አንደኛ የራስሽ የሆነ የገቢ ምንጭ የለሽም ።
ሁለተኛ ያለ ጥንቃቄ ቤት ውሰጥ በምታጫጭሻቸው ሱስ አምጪ ነገሮች ልጆች ተጠቂ ሆነው ሳያሰቡት ሱስ ውሰጥ ሊገቡ ይችላሉ ።
ሶስተኛ ውጪ ሰለምታድሪ ልጆቹ ብቻቸውን ለአደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ ተባለች ።ልጆችም ሲጠየቁ በጭራሽ እሷ ጋር መሆን አንፈልግም አሉ ።
....እሺ መግቢያ ሰለሌለኝ ቤት ይገዛልኝ አለች
.....ያጠፋሸው ገንዘብ አይደለም መኖሪያ ቤት አስፓልት ይሰራ ነበር ።አሁን ግን ላንቺ ቤት የምገዛበት አቅምም ሞራልም የለኝም አለ
....ሸማግሌዎች ብዙ ከተወያዩ በኋላ ያለውን የቤት እቃ አንድትወሰድና አንዳለችውም የምትገባበት ስለሌላት ቢያንስ የኮንዶሚኒየም ስቱዲዮ የምትገዛበት ገንዘብ እንዲሰጣት ወሰነው ፍቺው ተፈፀመ ።

ባል ቤት ተከራይቶ የቤት እቃዎችን ከሟላ በኋላ ክፈለ ሀገር የሚኖሩ እናቱን አምጥቶ ልጆቹንና ሰራተኛቸውን እሳቸው ጋር አስቀምጦ ወደ አገሩ ተመለሰ ።ከወራት በኋላ ተመልሶ በመምጣት ከሰራተኞችዋ ጋር ትዳር መሰረት ።

#በክፍል ➑ ለዉድ ወንድሜ ለወደፊት ስታገባ ወይም ትዳር ላይ ካለህ መልካም ባህሪ መላበስ እንዳለብህ እንዳስሳለን

ክፍል ➑ ይቀጥላል...............
ምንጭ ፍቅርና ትዳር ከሚለዉ መፅሀፍ

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
2024/09/27 19:20:36
Back to Top
HTML Embed Code: