Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም የተከበራችሁና የተወደጃችሁ የቻናል ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ

በዚህ ሰሞን በምንወያይበት አጀንዳ ላይ የሚገርም ነገር ገጠመኝ ፡፡ ትናንት ያዉ ተወያይተን ሴቶች ከቶበቱ ቢክራ መስፈርት አናድርግ በሚል ብዙ ተጨቃጨቅጨን ተወያይተን ተግባብተንም ሳንግባባም ግን በሀሳብ ማዕበል አዝንበን ነበር
ግን የሚገርመዉ ዛሬና ትናንት ያልጠበኳቸዉ አስተያየት ከሴቶች በዛብኝ..ቢክራ መስፈርት መሆን መቻል አለበት ብለዉ ብዙ ሴቶች ምክንያታቸዉን ደርድረዋል፡፡
መስፈርት አይሁን እያልክ ብዙ ሰዉ አታጥም የሚልም በዝቶ ነበር፡፡ ሀሳቤን በደንብ ያለመረዳት ችግር ይሆናል እንጂ እኔ ቢክራ መስፈርት አይሁን ብየ ሙሉ በሙሉ አልሰጠሁም፡፡ እኔ ያልኩት ጠቅለል ሲደረግ
☞በልጅነታቸዉ ለተደፈሩ
☞ በድህነት ተሰቃይተዉ ላደጉ
☞ለገጠር ልጆች ለምን የዲነል ኢስላም አስተምሮ ስለሌለ
☞ ሰለምቴዎች
☞ የከተማ ልጅ ሁኖ የዲኑል ኢስላም እዉቀት ለሌለዉ ግን ከተማ ተወልዶ ያደገ 90% ዲነል ኢስላምን ያቃል አዉቆ አጥፊ ነዉ👌

☞ አሳማኝ ምክንያት ላለዉ ወንዶች መጀመሪያ በመረዳት እንዚህን የተከበሩ እንስቶች እንጠብቃቸዉ ነዉ፡፡

💠ግን ከሁሉም የአጀበኝ የዚች እህቴ አስተያየት ነዉ👇
አሰላም አለይኩም አሚር እንዴት ነህ
ብዙ የምትለቃቸዉን ፀሁፎች አነባለዉ በብዙ እስማማለዉ በተለይ ወንድ እና ሴት አብረዉ አይማሩ በሚለዉ ጎበዝ ተማሪ ካልሆነች ትዳር እስክታገኝ እናቷን ታግዝ ያልከዉ በአሁን ሰአት ቤተሰቦች ልጄ ጎበዝ ተማሪ ናት ሜካብ አይቀራት እያሉ ሲያወረዉ ይሰማል ግን እቺ ልጅ ሜካብ ብላ ወጥታ ትምህርት ቤት ምንን እንደምታደርግ ማየት ያሰጠላል በፈተና ሰአት ከጎበዝ ተማሪ ኮርጃ አሪፍ የሚባል ዉጤት ታመጣለች ለቤተሰቦቿ ትሸዉዳለች አይህ አሚር ጎበዝ የምትባለዎ ሴት ተማሪ በመትፎ ጓደኛ ምክኛት ትበላሻለች ላይበረሪ ስትል ባክሽ አንቺ ደሞ ቡሃላ እናነባለን እያላት እንዳታነብ በሌላ ወሬ ለምሳሌ
ስለፍቅር አላፈቅርም አላማዬ መማር ነዉ ስትል ፋራ ትባላች፡፡ ባይገርምህ እኛ ትምህርት ቤት ሶላት ልስገድ ስትላቸወ እራሱ ምን ኡስታዝ ኡስታዝ ያጫዉትሻል እኛም እኮ ሙሰሊም ነን እያሉ የሰላትን ጣአም የሚያጠፋ ልጆች አሉ
ሂጃብ አያምርብሽም አጭር ቀሚስ ነዉ ሚያምርብሽ እያሉ ከዲነል ኢስላም የሚያወጡ ሙስሊሞች አሉ
ከአጂ ነቢ ምንም አይነት ግኑኝነት አልፈልግም ስትል አታካብጂ ቀለል አርጊ ተዝናኚ አትጨናነቂ በጊዜሽ ተጫወቺ መች ልትጫወቺ ነዉ ትምህርት ሰላት ቁርአን እያለሽ እያሉ ከዛ ከአንድ አጂነቢ ገር ጓደኛ እንድትን አራዳ ሁኚ ፋራ እያሉ ወደ ዚና የጠራሉ ከዛ እቺ ልጅ እርድና ይመስላትና ዚና ላይ ትወድቃለች
ወንዱ ደግሞ በተራዉ ፍቅር እስኪይዛት ይለምናትና ፈቅር እንደያዛት ሲያዉቅ የምትወጂኝ ከሆነ ድንግልሽን ስጪኝ ይላታል እና እሱን የምታገኝ መስሏት ስህተት ትሰራለች
በአሁን ሰአት ሀይስኩል ላይ ድንግል መሆን ብልግና ነዉ እያሉ ነዉ ያሉት

ወላሂ ነዉ ምልህ በጓደኛ ምክኛት ሂወታቸዉ የተበላሸ ብዙ ልጆች አቃለዉ በዲናቸዉ በትምህርታቸዉ ጠንካራ የነበሩ አሁን ዱርዬ ተብለዉ በየመንገዱ ከአጂ ነቢ የሚላላጡ ብዙ አሉ

ድንግል መሆን ለትዳር መስፈርት ሊሆን አይገባም ነገር ግን አንተ አሚር ሴቶች ዚና ለይ እንዲወድቁ እየረዳሀቸዉ ነዉ፡፡ በጊዜዬ ተዝናንቼ ለማገባዉ ባሌ እዋሽዋለሁ ለምሳሌ ተደፍሬ .ተታልዬ ምንምን እያሉ መዋሽት ይችላሉ

ያንተ ምክር ሊሆን የምገባዉ እንዲጠነቀቁ እና ደንግለቸዉን እንዲጠብቁ ከመትፎ ጓደኛ እንዲርቁ ከተሳሳቱ ወደ አላህ እንዲፀፀቱ ዳግመኛ እንዳይመለሱ መሆን አለበት ባይ ነኝ
☝️☝️ሌሎችም አስተያየቶች አሉ ከሴቶች ወላሂ ማመዛዘን ነዉ የከበደኝ

ደግሞ አንድ ወንድሜ የላከዉን ጀባ ልበላችሁ

አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ።
~የሰሞኑ ፖስቶችህና ኮሜንቶቹ ከማንበቤ በፊት፦
ኢንሻላህ ለማግባት ባሰብኩ ጊዜ ዒማንዋን አይቼ ቤተሰቦችዋንና ጓደኛችዋን አጥንቼ እንዲሁም እውቀትዋ ገምግሜ 2ረከዓ የኢስቲኻራ ሰላት ሰግጄ ከተመቸችኝ፣ በቃ ማናገር then ሽማግሌ መላክ።ጭራሽ ስለ ቢክራ ጥያቄ ውል ብሎብኝ አያውቅም ነበር።እውነት ለመናገር የቢክር መመርመሪያ መሳሪያዬ ተጠቅሜ መርምሬው resulቱ ማንበብ ምችል አይመስለኝም፤ዝም ብሎ Rblood ማየት ከሆነ ቀላል ነው። ግን ከስራና ድካም በኃላ ሌላ ስራ አይከብድም☺️
~ከፖስቶችህ በኃላ ግን ስለቢክራ ብዙ አሰብኩ prerequisitነቱ ጥቅምም ጉዳትም እንዳለው አመንኩ፤ግን ይህ ጥሩ ነው፣ያ መጥፎ... ማለት አልፈልግም። ምክንያቱም መጀመሪያ እስልምና ምንድነው ያለው ማለትን ማስቀደም ትክክለኛነት ነው። ነገራቶች የምናይበት መነፅር እስልምና(ቁርአንና ሀዲስ በደጋግ ቀደምቶች አረዳድ) ይሁን።አድርጉ ተብለን ከሆነ በቃ ምን አለፋን ለኛ በጣም ጠቃሚ ነው፤አታድርጉም ከሆነ አለማድረግ ነው።የአላህ ድንጋጌ አቅርቦ እስቲ ጥሩ ወይስ መጥፎ ተወያዩበት እስኪ ማለት ከባድ ጥፋት!!(አንተ አልክ ማለቴ አይደለም) አላህ ያልደነገገውን ነገር ደንግጎ ደሞ ጥሩ ነው ወይስ መጥፎ ማለትም ሌላ ጥፋት!! የእስልምና አስተምሮ ተከታዮቹ በስህተት ተረድተውት ከሆነም በማስረጃ ተሳስታችኃል እንደዚህ ነው መረዳት ያለባችሁ ብሎ ማስረዳት ነው እንጂ ውይይት አያስፈልገውም ምክንያቱም ሀቅ 1ድ ብቻ ነው። ተቃራኒ commenቶች አንብበን የማን አቋም እንያዝ?
ብቻ እኔ በሁለቱም መካከል ነኝ መወሰን አልቻልኩም ሌሎችም የተወዛገቡ ወይም የተሳሳተ አቋም የያዙ ስለሚኖሩ #ከቻልክ #በአላህ ይሁንብህ እንደ conclusion የሆነ ኡስታዝ ሰው በዚህ ዙርያ ሰፋ ያለ ትንተና እንዲፅፍ ጋብዝ፣ ከዛም ልቀቅልን pls. ጨረስኩ!!

ማሳሰብያ: ብዙ ሰዎች ቢክርዋ ሰጥታ የተፀፀተች ሲሉ አንዴ ቶብታ ፋይሉ የተዘጋ እያስመሰሉት ነው። የተውበቱ ተቀባይነት በምን እርግጠኛ ሆኑ? የሆነ ወንጀል ከሰራን እስክንሞት ወንጀሉ ባስታወስን ቁጥር መፀፀት አለብን እላለሁ።የሆነ ጊዜ ተሳስቼ ቢክራ ተብላ ከዛም ተፀፀትኩ አሁን ኖርማን ንፁህ ነኝ እንዳትይ፤አሁንም ተጸጸች።ኢንሻላህ ተቀባይነትም አጅርም ታገኛለሽ።



ወንድሜ በጣም እወድሃለሁ ብዙ ጊዜ ሃሳቦችህ ልኬ ናቸው፤ እንደውም ለወደፊት ሚስት አንተ ትፈልግልኛለህ ብዬ ነበር፤ አሁን ግን ሀሳቤ ቀየርኩ። ለራስህም ያልመረጥክ(ማለቴ finishing ላይ)😂 ደሞ ቢክር ያልሆነች መርጠህ ብታመጣልኝስ🙈
☝️☝️☝️ ይሄም ወንድሜ 360 ዲግሪ ነዉ የዞረበት😊 ፡፡ትክክል ነዉ በቁርአን በሀዲስ አንድ ዳኢ ቢያዘጋጀዉ የተሻለ ነዉ
በተጨማሪ ብዙ comment አሉ መጀመሪያ ተዉሂድ አስተምር ሌላዉ መወያያ ይደርሳል ያላችሁኝም አለ መርሀባ ተቀብያለሁ፡፡

እስኪ በራሴ አንድ ነገር ልበል ግን ይሄ ሁሉ ግፍ ሰዉ ወንጀልን ለምን አተንሾ ማየት ቻለብዙዉ ቁርአን ቀርቶ ኪታብ ቀርቷል ከጆሮዉ ሳያልፍ እንዴት ልቡ ላይ ጠብ ሳይል ቀረብለን እራሳችንን ስንፈትሽ
የዲነል ኢስላም እዉቀት ማነስ እና ባለዉ አመተግበር መልስ ይሆናል

💠የዲነል ኢስላም እዉቀት ማነስ ከምን መጣ ስንል ሰዉ ሙሉ በሙሉ ለዱንያ ለብልጭልጭ ነገር ጊዜ መፍጀቱ ነዉ፡፡ቀደምት ሱሀቦች ታብእዮች ዲነል ኢስላም አሁን ላለበት እንዲደርስ ሲታገሉ አልጋ በአልጋ ሳይሆን ብዙ ስቃይ አልፈዋል፡፡አቡ ሁረይራ ረዐ ብዙ ሀዲስ እንደዘገበ እናቃለን እንዴት ግን ከሱሀቦቹ በላይ ዘገበ ??ብለን ስንጠይቅ..አቡ ሁረይራ እዉቀትን ለመፈለግ ከነብዩ ሰዐወ ስር እየሄደ የእርሀቡ ብዛት ሆዱ ላይ በዲንጋይ ያስር ነበር👇👇
የእርሀቡ ብዛት ፌንት ድረስ ይጥለዉ ነበር
✿ኢማሙ ማሊክ ሲማሩ ብር አጥተዉ ደህይተዉ የቤታቸዉን ጣራ ሽጠዉ ነበር
✿አንድ ሰለፍ ስሙ ጠፋኝ አባቱ ግን ማህሙድ ይባላል እዉቀት ለመፈለግ የተጓዘበት ከመንገዱ መብዛት እግሩ ሺባ ሁኗል
✿አንዱ ሱሀባ ሲናገር እዉቀት ለመፈለግ በአሁኑ በkm 4000 km ተጉዟል፡፡ ኢትዮጲያ ከጫፍ እስከ ጫፋ 4000km ይሆናል ግን??
ኢማሙ አህመድ እዉቀት እስከየት ድረስ ነዉ ተብለዉ ተጠይቀዉ ከእናትህ ሆድ ወጥተህ እስከ ምትሞት ድረስ ነዉ ያሉት..
✿እነ አቡበር ስዲቅ ኡመር ወዘተ ዲነል ኢስላምን ሲማሩ ፀጉራቸዉ ሸብቶ ትልቅ ሁነዉ ነዉ ቢያንስ ከ38 አመት በላይ ሁነዉ ነዉ
✿ሸህ ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ አላገቡም ለምን አታገቡም ሲባሉ ቀንም አዳርም ዲነል ኢስላምን ስለሚማሩ የሚስቴን ሀቅ ላልወጣ እችላለሁ ብለዉ ሳያገቡ ነዉ የኖሩት፡፡አላህ ጀነተል ፊርዶስ ይወፍቃቸዉ
እኛስ ለዚህ ሁሉ እርስ በራሳችን ከምንወቃቀስ በእዉቀት ላይ ብናሳልፍ ይሄ ሁሉ ጣጣ ይመጣ ነበር ወይ??
አሁን ላይ ኪታብ ቀርተናል ብላችሁ የምታስቡ ሰዎች
☞የቀራችሁት ኪታብ ከሀራም ከለከላችሁ ወይ?
☞ኪታብ ሴቱም ወንዱም የቀራዉ ባለበት በሚኖርበት ከተማ ነዉ ፡፡የተመቸ ሀልጋ ላይ ተኝቶ የፈለገዉን በልቶ ጠጥቶ እሷም ቢሆን በልታ ጠጥታ የሀብታም ልጅ አቅሪ ተይዞለት ኡስታዙን ተሳድቦ ያከትማል ወላጅ ሆይ ቁርአን አቀራሁ ብለህ ታስባለህ?
በጭራሽ ዲነል ኢስላምን ለልጆችህ እንዳላወረስክ እወቀዉ፡፡ በተለይ የሸህ ቀርተዋል የተባሉ ሰዎች ልጆች ሲበላሹ እያየን ነዉ ቃልቻ ጡሌ እንጂ ልጅ አይወጣለትም😊 ተብሏል...ኡስታዞች ሸሆች የራሳችሁን ልጅ መቀየር ያልቻሉ እንዴት የማህበረሰብ ልጅ መቀየር ይችላሉ?

💠 በተማርነዉ አለመተግበር ደግሞ አሁን ላይ ያለንበት ነዉ ሚዲያዉ ቴሌቪዥኑ ወዘተ እያስተማረ ነዉ ግን ባዳና ቁንጫ በልቶ ሩጫ ሆነና ነገሩ ሁሉም አዳምጦ ከድጡ ወደ ማጡ ሆነ ታዳ መፍትሄዉ ምን ይሆን ? እኔም ግራ ገብቶኛል ጎበዝ

😎😎ወንድ ሆይ አላማህ ግድ ቀይ የደም ሴል ከሆነ አላህ የሁላቾንንም ዉሳጣዊም ዉጫዊም ቢያዉቅ .ግን አይተህ የሆነ የምትገነዘበዉ አለህ
የኢስላም አደብ አለባበስ የጠበቀች
ከያዘችዉ የሴት ጓደኛ
ከወላጆቿ የዲን አቋም
ከምትኖርበት ሰፈር
የኢልም ደረጃዋን ..በትርፍ ሰአቷ የት እንደምታዘወትር ማን ጋር ኪታብ እንደምቀራ
ጓደኞቿም የእሷ አይነት አቋም ካላቸዉ ለዲን ፍቅር ካየህባቸዉ፡፡
ወላጅ ጎረቤት ዘመድ ስትንከባከብ ካየህ
ይቺ ልጅ ከአላህ ጋር ይኖራታል፡፡ ካልሆነም መቼም ሸይጧን እንደ አጋጣሚ ከአሳሳታት ከተግባሯ አንፃር ወደ አላህ የተመለሰች ናት ማለት ነዉ፡፡ እነዚህ መስፈርት ከገኘህባት ቢክራም ሆነች አልሆነች ለአንተ መስፈርትህ ሊሆን አይገባም
መርሀባ ብሎ ጎጆ መቀለስ ነዉ😊

በተዘዋዋሪ ደግሞ አይተህ ቀይ የደም ሴል ያለመኖራቸዉ የማረጋገጫ ምልክቶች እነሆ፡፡ ግን ከነዚህ ከጠቀስኳቸዉ 10% ፐርሰንቱ ሊኖሬቸዉ ይችላል፡፡

ከ1000 ቲማቲም 900 ቢበላሽ ያዉ ሁሉ ተበላሸ ነዉ፡፡ ወይም እንደ ምሳሌ አባባሉ ከ100 ቲማትም 90ቢገማ ሁሉም ገማ ነዉ🙃 ነገሩ ፡፡ እስኪ ምልክቱን በከፊል አንተም ስታይ ልብህ ይነግርሀል
❖ ከኢስላም አለባበስ አደብ ዉጭ የሆነች እስከምትቀባዉ ኮስሞቲክስ የምትቀያይር አንተም ስታያት ዛሬ አመድ ነገ ጨዉ ከነገ ወዳ አሞሌ ጨዉ ምን አደከመህ 30 ቀን 30 መልክ ያላት 😊
አመት በሙሉ የተለያየ መልክ የሚፈራረቅባት
❖ የያዘቻቸዉ ጓደኞች ልክ እሷን የሚመስሉ ሁሉም ያዉ የስዕል መለማመጃ ደፍተር የመሰሉ ማለቴ ነዉ☺️
❖ የወላጆቿ የዲን አቋም ለዚሁ የቱርክ ልብስ ለኮስማቲክስ ብር የሚሰጡ ስለአለባበሷ የማይከታተሉ ከሆነ
❖የምትኖርበት ሰፈር ስትሄድ ሙሉቀን ሲጠጣ ሲጨፈር ሲወራ የሚዉል አጂነብይ ጋር ያለ ግንኙነቶች የላላ ከሆነ
❖የኢልም ደረጃዋ ደግሞ በቤተሰብ ተገዳ ኪታብ ቅሪ ተብላ አንዲት ኪታብ ይዛ ስታሾፍ ሙድ ስትይዝ ዉላ የምመጣ፡፡ በኪታብ መቅሪያ ሰአት የፈለገችበት የምዞር
❖ኪታብ አብረን እንቀራለን ብለዉ የሚሄዱ ጓደኞቾ እንደሷ አይነት ከሆኑ
❖እናቷ እቤት ስራ እየሰራች ደፋ ቀና ስትል እሷ መስተዋት ላይ ሙጥኝ የምትል ፡፡ በየመንገዱ ሲፎግራት የምትስቅ ፣ እንደሷ ያልሆኑ ስቶችን ፋራ አድርጋ የምትይዝ ከሆነ
❖የመኪና ሹፌር የባጃጅ ሹፌር ጋር አጉል ቅርርብ ሲሸኛት በተደጋጋሚ የምታይ ከሆነ
❖እማንም ወንድ ጋር በየመንገዱ የምትጋተት ከሆነ ፡፡
❖ እንደ ትራፊክ መብራት ቀይ አረንጓዴ ቢጫ እንደሚታዘዘዉ እሷም ያወራትን የሸኛትን የምትከተል ወይም በወንድ ምላስ Soft ware ተጭና በእሱ ስሜት ነበልባል ቁጥጥር ስር ከሆነች

አላማህ ቀይ የደም ሴል ከሆነ ከየት ታገኘዋለህ ወዳጄ😊 ያገበሀት ለትዳር ነዉ ከወደድካት ከነጎደሎዋ ማግባት መብትክ ነዉ፡፡ ግን ግድ ያ ነገር ይኑር ማለት በቆሎ ዘርተህ ጤፍ አጭዳለሁ ብሎ እንደመጠበቅ ነዉ😉
ሳር የሚገኘዉ ከመሬት ነዉ ከሰማይ አይወርድ ..ወርቅ አልማዝ የሚገኘዉ ከዉሀ ቆፍረህ ነዉ ከሰማይ አይወርድ ፡፡ ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል..ወይም ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ነዉ የሚሆነዉ እቅድህ ትዳር ከሆነ አግባት ግን ለምን ቀይ የደም ሴል የለሽም እያልክ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል፡፡ እንደ አንተ ያለ ሰዉ .መኖሪያ ቤት ለመግዛት እንደሄደ ምሳሌ ይሁን ...ከዛም ቤቱን አየዉ ጭራሽ አልተዋጠለትም አረ ብሬን እዚህ ላይ አዉጥቼ ከምከስር ባዶ ቦታ ገዝቼ ብሰራ ይሻላል ብሎ ወስኖ ባዶ ቦታዉ ላይ የፈለገዉን ቤት በተመቸዉ ዲዛይን እንደሰራ ይቆጠራል፡፡
ስለሆነም ከማግባትህ በፊት ምርጫ አለህ
➊ ዲን ያላት ?
➋ ዲን የሌላት የሆነችዉ ትሁን
ሁለቱ ነዉ ምርጫ ዲን የሌላት ከሆነች ከአገባሀት ቡሀላ ለምን ያነገር የለም ብለህ እኝኝኝ ብትል ቅድሚያዉኑ አይተህ ነዉ ያገበሀዉ ጥፋቱ የአንተ ነዉ ፡፡በአንተ ምርጫህ እንዝላልነት የተነሳ ዲነል ኢስላምን አታሰድብ 😏ወደ ሌላ ሀይማኖት እንዲሄዱ በር እየከፈክ እንደሆነ አትርሳ፡፡

☝️☝️ዩኒቨርስቲ ላይ ወንድ የወንድ አቅሪ ሴትም የሴት አቅሪ ብቻ ቢያቀራቸዉ ብቸኛ መፍትሄ ነዉ፡፡ የጀመአ አሚር ነን ተብሎ የሴቱን ቁጥር የሁሉንም ይዞ የወንድ አሚር እየደወለ መከታተል ይቅር፡፡ይሄን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የጀመአ አባሎች አስተካክሉ

☝️በሰፈር በመድረሳ ወጣት ኡስታዞች ለአቅመ አዳም የደረሱ ሴቶችን ማቅራት ባይኖርባቸዉ ባይ ነኝ፡፡ በተለይ የሀብታም ልጆች ከቤት እንዳይወጡ እየተባለ እቤቱ ቁርአን ትቅራ በሚል ሽፋን በወጣት የወንድ አቅሪዎች ሴቶች ልጆች ሁሉም እየተሸወዱ ነዉ ፡፡እዚህ ላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡

መቼም ቢሆን በአእምሯችን መዝግበን መያዝ ያለብን ነገር ኡስታዝም ሆነ ቁርአን አቅሪም ሆነ ሌላ በሴት ጉዳይ ላይ በጣም ይፈተናል፡፡ ሸይጧንም ያሳስተዋል ነብዩ ሰዐወ እዚች ዱንያ አንደ ሀብትና ሴት ፈተና አልተውኩላቸውም ብለዋል፡፡
ኢማሙ ሻፍእይ እንዲህ ብለዋል አንዲት ሴት እግሯን ተመልክቼ የመሀፈዝ ችሎታዬ ቀነሰ ብለዉ ተናግረዋል፡፡ሴቷን ሴት ኡስታዛህ ብታስቀራ ይህን ነገር ማስቆም ይቻላል ከዚህ ዉጭ እሳትና ጭድ አብራችሁ ተቀምጣችሁ እዚህ አካባቢ የእሳት አደጋ እንዳይፈጠር ሀላፊነት ተሰጥቷችሆል ጠብቁ😊 ተብሎ ስልጣን እንደመስጠት ነዉ

⭕️⭕️ አሁን መፍትሄ ብሎ የታየኝ ስለድንግልና ጉዳይ ከኔ ለተሻሉ ሰዎች ኡማዉ ጋር ቦታ ያላቸዉ መግባባት ለሚችሉ አቅርቡላቸዉና በሰፊዉ እነሱ ይሄን አጀንዳ ቢይዙት በfacebook በtg በtv መስኮት ድረስ የማድረስ👇👇
አቅም አላቸዉ
ከሁሉም ቁጥር አንድ ፀሀፊ #ፉአድ_ሙናን ሀሳቡን አንሱለት እሱ አዲስ አበባ ላይ ተፅእኖ መፍጠር ከሚችሉ ሰዎች ነዉ ፡፡ ፀሀፊ #ፉአድ_ሙናን ብታማክሩት አሪፍ ነዉ..እኔ ጋር እስከ አሁን አያቀኝም እኔ ፁሁፉን ስለምከታተል አቀዋለሁ በጣም ጎበዝ ለአሁን ማህበረሰብ መድረስ የሚችል ልጅ ነዉ፡፡ እንደምንም ብላችሁ ለፉአድ ሙና ሀሳቡን ሼር አድርጉለት እሱ ሊላህ ብሎ ከተነሳ ተፅእኖ መፍጠር ይችላል፡፡
☞ፀሀፊ አብደል ሀኪም ሰፋ እና ነጃት ሀሰን የVenu ቻናል Admin ይሄን ጉዳይ ቢይዙት ለኡማዉ ለዉጥ ማምጣት ይችላሉ፡፡

💠ከኡስታዞች ደግሞ..ኡስታዝ ሳዳት ከማል ቢሆን የተሻለ ነዉ እሱ ጋር የምቀሩ አማክሩት፡፡ በቻናሉ ስለዚህ ጉዳይ በተደጋጋሚ ቢያስተምር ለዉጥ ማምጣት ይችላል፡፡

💠 ከtv ቻናሎች ነሲሀ ቲቪ ለዉጥ ማምጣት ይችላል፡፡ ሌላዉ Minber እና bst ሌላ እራሱን የቻለ ፍትንያ ናቸዉ፡፡ አንዷ ዘመዴ ለወደፊት መሆን የምፈልገዉ ብየ ብጠይቃት Minber tv ዝግጆት አቅራቢ ነዉ😏
አለችኝ የሆነች ቅራቅንቦ ነገር...ሴቶች ለሁሉም ልክ አለዉ ግን የሴት ልጅ ከልክ በላይ መሆን በMinber እና Bst tv እያየን ነዉ፡፡ እነዚህ አጀማመራቸዉ ከሸሪአ አንፃር ዶኢፍ ስለሆኑ ዶኢፍ ደግሞ ያዉ ሀቅን መበጥበጡ አይቀርም😊

💠 ዩቲዩበሮች በሚጠቅም በማይጠቀም ነገር ቢዚ ከምትሆኑ በዚህ ዙሪያ ብሰሩ ለዉጥ ማምጣት ትችላላችሁ፡፡ እስኪ የምግባባቸዉ ዩቲዩበሮችን አማክራቸዋለሁ

💠 Tik tok የሚባል መጥቷል ..እኔ Tik tok aplication የለኝ ምን እንደሆነ ለራሱ አላቀዉም ለወደፊትም ማወቅ አልፈልግም😊 ለምን ጊዜ የሚፈጅብኝን ነገር አልፈልግም በዛ ቢዚ ሁኜ ብዙ መስራት ያለብኝን እንዳልዘነጋ ፡፡ ከተቻለ ማህበራዊ ሚዲያን በprogram ማረግ፡፡ እኔ የምጠቀዉ Imo እና telegram ብቻ ነዉ ፡፡ Imo የምጠቀመዉ ለስራ ነዉ ከዛ ዉጭ ያለዉን ማህበራዊ ሚዲያ ለኔ አይመለከተኝምእናም ማህበራዊ ሚዲያን ቀንሶ ኪታብ መቅራት እና መፅሀፎችን ማንበብ ላይ ብናተኩር የተሻለ ነዉ ብየ አስባለሁ፡፡


📥📥📥 ዉድና የተከበራችሁ የቻናል ቤተሰቦች ዛሬ ሳትዋጋ ንገስ የሚለዉን ታሪክ ለመጀመር ተናግሬ ነበር ..ዛሬም ይሄን የዉይይት ሀሳብ ጨረስኩ ነገ እሁድ በተከታታይ ከዙሁር ቡሀላ ባለዉ ሰአት እንጀምራለን፡፡
ይህ ታሪክ ከአራተኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12 ክፍል ድረስ ትምህርት ቤት ምን እንደሚካሄድ ይዳስሳል ፡፡ እዉነተኛ ታሪክ ነዉ...
☞ሴት ልጅ ጎበዝ ተማሪ ካልሆነች መማር የለባትም ማንበብ መፃፍ ይበቃታል😊 ብያለሁ በታሪኩ የሰነፍ ተማሪዎች School life እናንተዉ ታነባላችሁ
☞ቀይ የደም ሴል ይሄዳል ተብሎ የሚፈራዉ በፊት ሀይ እስኩል ነበር ፡፡ ይሄ ታሪክ ደግሞ አምስተኛ ክፍል ላይ አምስት ጣት ቆጥረዉ☺️ አስግቷል ታነቡታላችሁ
☞ወንድ ነዉ የማይታመነዉ ሴት?የሁላችንም ያልተግባባንበት ጥያቄ ነዉ ታሪኩ ግን ሁሉም እንደማይታመን በሰፊዉ ያትታል
☞ታሪኩ ላይ ሙስሊሞች አህባሽ አቂዳ ከመጣ ቡሀላ ለኢስላም የማይጠቅም የማይጎዳ ማህበረሰብ መፍጠር ችለዋል፡፡ ለዚህም ማሳያ ታሪኩ መልስ አለዉ
☞የዱንያ መዥገር መጥፎ ጓደኛ እንዴት እንደሚጎዳ እናያለን
☞በታሪኩ መራም ወንድም እህቶቻን ለማሳደግ ያደረገችዉ እልህ አስጨራሽ ዉጤት እና የቤተሰብ ሰላም አለመሆን ጉዳቱን ያሳያል
☞በታሪኩ ማብቂያ አካባቢ አንዲት ሰሚራ የምትባል ወፍ ዘራሽ አንድን የባለታሪኩን ጓደኛ በሌላ ሰዉ ፎቶ ተዋዉቃ በፍቅር ሁለት አመት ያጠመደችበት ይዳስሳል
☞ሆነም ቀረ ፍቅር የሚባል በጠፋበት አለም ሰዉ ፍቅር አለ እያለ ጊዜያቸዉን ፈጅተዉ ያስረጁ የወጣት ሽማግሌ የሆኑትን ተማሪ ታሪኮች እንኮመክማለን

ምን አደከማችሁ 100% እንኳ ባወዱት 1% እንኳ ትወዱታላችሁ😊
መልካም ንባብ ተመኘሁ እናንተም ሼር ለማድረግ ተዘጋጁ

ከአሁን ቡሀላ የመወያያ አጀንዳዉን ፋይል ዘግተናል 😊 ሀሳብ ካለ ላኩ እቀበላለሁ በቻናል ግን ለመወያየት Time is up

አሚር ሰይድ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Watch "#ድሀ ልጅ ፍቅር አስተማሪ እና ቀልብን አንጠልጣይ መሳጭ እውነተኛ ታሪክ #part 1" on YouTube
https://youtu.be/xdA-e6sfkks
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎁🎁🎁 እጅግ አስቸጋሪ የሆነውን የውጭ አገርና የአገር ውስጥ ከበባድ ተፅዕዎችን በጽናት ተቋቁመን ሁለተኛውን ዙር የታላቁ የህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት በድል ተከናውኗል፡፡ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳ ደስ አለን፡፡
ደግሞ በጣም ደስ የሚለዉ ነገ አረፋ በአል ዛሬ በአረፋ ፆም ባለንበት ሰአት 2ኛዉ ዙር መሙላቱ የብስ ደስታን ይጨምራል፡፡
አማራ ኦሮሞ ትግሬ አፋር ሱማሌ ወዘተ የሚለዉን ትተን ኢትዮጲያ ነን ካልን ገና ብዙ ስራ መስራት እንችላለን🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ሀምሌ 12፣ 2013 ዓ.ም ይሄ ቀን ለታሪክ ይቀመጥ

#ይሄን_ያቃሉ ??
አባይ ግድቡ ተገንብቶ አልቆ ውሀ ሙሌቱ ሲጠናቀቅ ከግድቡ ጀርባ በሚንጣለለው ውሀ ስፋት በአለማችን ላይ ጨዋማ ያልሆነ ቁጥር አንድ ትልቁ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ይሆናል።
# GERD # ItsMyDam🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

የአረፋ በአልን ዝባዝንኬ ከሆነ ነሺዳ መንዙማ ዉጭ ባሉ ተግባራት እናሳልፍ፡፡ ነገር ግን ነገ የተለያዩ የቴሌቪዥን የበአል ፕሮግራሞች የዘንድሮ ሙነሺድ ተብየዎች ይበዛሉ በተጨማሪ Bst tv እናም ሙነሺዶች በተዘጋጀዉ ፕሮግራም ላይ አይታችሁ ለዲን የሚጠቅሙ ናቸዉ ወይስ የማይጠቅሙ ሰዉን ወደ ጥመት ነዉ የሚመሩት ወይስ አይደለምየሚለዉን እናንተዉ አይታችሁ ፍረዱ👌👌

ዉድ የተከበራችሁ የቻናል ምርጥ ቤተሰቦች መልካም ኢደል አድሀ በአል ለሁላችሁም ተመኘሁ
አሚር ሰይድ

@IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ

ሳትዋጋ ንገስ በሚለዉ ታሪክ አሁን ድረስ አስተያየት በመስጠት ደካማ ጎኔን እንደ አስተካክል እናም ደግሞ ብዙ የስድብ ናዳም ተቀብያለሁ ለሁሉም አመሰግናለሁ ግን ብዙ Comment ላይ የሚደጋገም አለ

ሴት ልጅ ከ1እስከ 7 ድረስ ካልወጣች መማር የለባትም ኪታብ ብትቀራ ይሻላል ብየ በራሴ አመለካከት አንዴ ተናግሬ የአስተያየት መስጫዉ bot በስድብም አንተ ሆላ ቀር ለዘመኑ የማትመጥን ነህ የሚል ብዙ አይቻለሁ
ግራ የሚገባኝ በኔ የተነሳ የሚያቆም የለ ምን አስጨነቃችሁ🙄 እኔ አንድ ተራ ሰዉ ነኝ ደአዋ አድራጊ አይደለሁ ታዋቂ ሰዉ አይደለሁ ምንም የሚያሳስብ አልነበረም ፡፡ አንተ ለዚህ ዘመን አመጥንም ሙስሊም ሴቶች ወደ ሆላ ለማስቀረት ተነስተሀል ላላችሁኝ ..አዎ ይሄ ዘመን ትዉልድ ባለንበት ባልመጥን የሚቆጨኝ ነገር አይደለም ለምን ትዉልድ እየከሰረ ያለበት ዘመን ነዉ፡፡ ሙስሊም ሴቶች ወደ ሆላ የቀሩት ሰነፍ ሁነዉ ተምረዉ ዩኒቨርስቲ ገብተዉ በዛ በዚህ ብለዉ ዲግሪ ይዘዉ መስሪያ ቤት ስራ ፍለጋ ስትዞር በ3000 እስከ 5000 ባለዉ ደመወዝ እየተከፈላት ከዩኒቨርስቲ ጀምሮ እስከ መስሪያ ቤት የፆታ ትንኮሳን አሳልፋ ትዳር በምፈልግበት ጊዜ እድሜዋን አሳልፋ ማጣቷ ነዉ የሚያሳዝነዉ፡፡
ዋናዉ ነገር በትምህርታቸዉ ሰነፍ የሆኑ ብዙ ሴቶች የወደፊት የሚኖሩበት መሆን የሚፈልጉት እቅድ አላቸዉ ወይ??? 95% እቅድ ፕላን የላቸዉም
እሺ ብዙዎቹ ጎበዝ ባይሆኑም ጎበዝ የመሆን አላማዉ አላቸዉ ያላችሁም አላችሁ በተዘዋዋሪ ኮርጀዉም ደረጃ የሚይዙ ሴቶች ስላሉ ኮርጀዉ ደረጃ ከያዙት ሰነፍ ሁነዉ የሚማሩት ይሻላሉ የሚልም አስተያየት አይቻለሁ ፡፡ ኮርጀዉ ደረጃ የያዙ ሴቶች በሰዉ ሀሳብ አዳሪና በሙቅ ዉሀ ታጣቢ አንድ ነዉ ነገ የማይደገም ነዉ እኔ በሂወቴ የማልረሳዉ ገጠመኝ አለኝ ስድስተኛ ክፍል ስማር በአንደኛ ሲሚስተር ከእኛ ክፍል አንደኛ ከወጣዉ ከ40ዉም ከ60 ኮርጄ ሶስተኛ ደረጃ ወጥቼ ደስ ብሎኝ በሁለተኛ ሲሚስተር ግን ከእሱጎን የመሆን እድል አልገጠመኝም ነበር 42 ነበር የወጣሁት☹️ እናም በጓደኛ በዘመድ በትምህርት ቤት ተማሪ በሰፈር ሳይቀር መሳቂያ ሁኛለሁ ስድስተኛ ክፍል ላይ የሰዉ አእምሮ መጠቀም እንደ እኔ አንድ ቀን ዉርደት ይሸከማል
ሰነፍ ሁነዉ ይማሩ ለምትሉ ደግሞ እየተማሩ የወደፊት የህይወት ግብ ከሌላቸዉ ከተወሰነ አመታት ቡሀላ አወዳደቃቸዉ እንደ ህዉሀት ነዉ የሚሆነዉ🤗
ወንድ ሰነፍ ከሆነ ለምን ይማራልም የሚል አለ.. .አዎ ሰነፍ ከሆነ ዲነል ኢስላምን ይማር ግን ትምህርት ቤት ሴቶችን አላማ ያስታል፡፡ ወንድ የህይወት አዙሪቱን በሂደትም ቢሆን ማስተካከል ይችላል፡፡ የሴት ግን በጥንቃቄ ካልሆነ አንዴ ከተበላሸ ለማስተካከል ከባድ ነዉ ምን አልባት እስከ ሞት አፋፍ ድረስ ሳይተካከል ይችላልና.. ከ5እስከ 8 ክፍል ያሉ ሴት ህፃናትን ተመልክታችሁ፡ፍረዱ ...ሴት ጠንካራ ናት አጋዥ ከጎና የሚሆን የሚረዳት ወንድምና እህት ካገኘች ባይሆን ወንድም ስል የእናት አባት ወንድም😊 ካገኘች መቀየር ትትላለች ብያለሁ ..እህት ያለዉ እህት ያለሽ ሰበቡን አድርሱ በከባድ ትግል ማስተካከል ይቻላል በአላህ ፍቃድ

አሁን ስላሉ ሙነሺዶች ስታነሳ እዚህ ቻናል ብዙ የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች አሉ ለምን በአደባባይ ታነሳለህ ለእነሱ አጋልጠህ ሰጠህ ማለት ነዉ የሚል አስተያየት አይቻለሁ....አዎ አቃለሁ ብዙ የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ይከታተላሉ ግን ሂዲያ የሚሰጠዉ አላህ ነዉ እነሱ ትክክለኛ የኢስላም መስመር ላይ አለመሆናቸዉን ማወቅ አለበት ምን አልባት ነገ ከነገ ወዳ ወይም ከተወሰኑ አመታት ቡሀላ ኢስላም በልባቸዉ ከገባ የሙነሺዶችን አካሄድ ከሄዱ አደጋ ይኖረዋል...እንደዉም ብዙ እዚህ ቻናል ያሉ በአሁን ሙነሺዶች ስራ ተገርመዉ በሚሰሩት ስራ እስልምና ላይ አለ ወይ? እያሉ የሚጠይቁኝም አሉ
ከአሁን ቡሀላ እኔም ስለእነሱ ማንሳት አልፈልግም...የሆነ ነገር ስል ገና ከእጄ ተፅፎ በቻናል ፓስቼ አስጠንቅቂያለሁ መረዳት ያለመረዳት አእምሮን ተጠቅሞ ማስተንተን የባለጭንቅላቱ ሰዉ ዉሳኔ ነዉ❗️❗️

❇️ በተለያዩ ታሪኮች ሲፓሰት አንዴ ወንድ በሴት ሲከዳ ደግሞ በሌላ በማዘጋጀዉ ታሪክ ሴት በወንድ ስትሸወድ ስትከዳ ታሪኩን ያነበበዉ ወንድ ከሆነ እንዴ ሴቶችም እንደዚህ ያረጋሉ መቼ ይታመናሉ ሲለኝ ሴቷ ደግሞ አንተ ለሴት ጥሩ አመለካከት የለህም ወንዶች ናቸዉ እንዲህ ያደረጉኝ የማላገባዉ ወንድን ከማምን ዉሻ ባምን ይሻላል እያሉ በፊት ባለማወቅ ይሁን አዉቀዉም ይሁን የተሳሳቱ ማህበረሰቦች ታሪክ ባነበቡ ቁጥር ጥርስ ነካሽ ሁነዋል እናም አሁን አንድ መፍትሄ ሀሳብ ይዘን ብቅ ብለናል😊
☞ወንዱም ሴት አይታመንም እያለ ግራ ተጋባ
☞ሴቷም ወንድ አይታመንም እያለች ትዳር መላሽ ሆነች
☞ትዳር ያሰቡ የትዳርን የሚያበላሸዉን ፍቅር የሚጨምረዉን ሳያቁ ገብተዉ ..ዋና ሳይችሉ መዋኛ ገንዳዉ ገብተዉ በዋናተኛ እየወጡ ነዉ
☞ትዳር ላይ ያሉ ደግሞ ይሄን የሚያምር ቁርኝት ኒዕማዉን ሳያቁት እያባከኑት ነዉ

ይሄን ሁሉ የማህበረሰቡን ችግር ምክንያት በማድረግ እስኪ ለዚህ ሁሉ ችግር ትዳር ለመግባት ዳር ላይ ለቆመዉ .ወንድ ለሴት ወይም ሴት ለወንድ መጥፎ አመለካከት ላለዉ ትንሽም ቢሆን ከልብ ያለዉን ኒፋቅ የሚያጠፋ ፁሁፍ እህታችን መህባቡ ቢንት አቡሀ ፍቅርና ትዳር ከሚለዉ መፅሀፍ ስለትዳርና ፍቅር ምርጥ ፁሁፎችን አዘጋጅታለች..እኔም የቃላት ስህተቱን በማስተካከልና ክፍሎቹን ኦርደር አድርጌ በቅርቡ የምንጀምር ይሆናል፡፡

❇️ የካንሰር በሽታ አይነቱ ብዙ ነዉ ሰዉ የሚያቀዉ የሆድ የጭንቅላት የጡት ወዘተ ካንሰር ነዉ ..ግን የትዳር ካንሰር አለዉ የትዳር ካንሰር የሚጀምረዉ በዘንድሮ ከምላስ አልፎ ጉሮሮ ከማይደርሰዉ ፍቅር ከትዳር በፊት የሚጀምር የሞኛሞኞች ፍቅር ነዉ ..በዚህ ካንሰር ብዙዎች ተጠቅተዋል
ብዙ የሚታከሙ ልቦች አካሚ አጥተዉ ከስመዋል
ብዙዎች ካንሰር መድሀኒት እንደለለዉ አዉቀዉ እንሙት ብለዉ ገብተዋል
እንሙት ብለዉ የገቡትም ሳይገላቸዉ ቀርተዉ ይሄዉ የቁም ቀባሪ ስለሌለ ሞትን እየተመኙ ሞት ጠባቂ ሁነዋል
ስንት የት ይደርሳሉ የተባሉ ትዉልዶች በራሳቸዉ ጥፋት እድል ቆዛሚ ቀዷና ቀድር ጋር እየተጋጩ የጋን ዉስጥ መብራት ሁነዉ ቀርተዋል
የወደፊት የኡማዉ ተረካቢ ትዉልድን 9ወር አርግዘዉ አምጠዉ ተሰቃይተዉ ወልደዉ ግን የተሰቃዩበት የማጡበት ትርጉምን ሳያቁ የሚወለደዉ ልጅ ለማህበረሰብ እንዴት አድርገዉ በተርቢያ አሳድገዉ ለማስረከብ የማይችሉ እንስቶች በየመንገዱ በየቤቱ በዝተዋል፡፡ እናቱ አምጣ አልቅሳ ወልዳ ወደ ዱንያ መምጣቱን ዘንግቶ በእናቱ በእህቱ ላይ እንዲሆን የማይፈልገዉን በሌሎች ሴቶች ላይ ከምጥ በላይ ስቃይ አሸክሞ የሚሄድ ሞራል የሌለዉ ወንድ ተሰራጭቷል፡፡ ታዳ ይሄ የትዳር ካንሰር አይደል?

የትዳር ካንሰርን ለማከም ጊዜ ቢፈጅም ግን መፍትሄዉ ጥሩ ትዳር መሆኑን በቻልነዉ አቅም በመህባቡ ፁሁፍ እንዳስሳለን

ባለማወቅና ባልታመኑ ነበልባል ምላሶች ምክንያት የተሸወደች ልብን መልሶ አድሶ ለመቆም ይጠቅማል ብየ አስባለሁ

📥ስለትዳር የዘጋጀሆቸዉ ፁሁፎች አሉ በቻናል ቢፓሰቱ ይጠቅማሉ ብላችሁ ያዘጋጃችሁት ፁሁፍ ካለ በዚህ bot አሳዉቁኝ 👇👇
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot

❇️ መህባቡ ቢንት አቡሀ ያዘጋጀችዉ ፁሁፍ በቅርቡ ይጠብቁኝ እንጀምራለን መልካም ንባብ
ወንድማችሁ አሚር ሰይድ ነኝ

#COMING SOON ..
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አብሀ
ክፍል :- አንድ 1⃣


#መቅደም

ማህበረሰብ የሚዋቀረው ከቤተሰብ ሲሆን የቤተሰብ መሰረቱ ደግሞ ጋብቻ ነው ።ጋብቻ አምሮና ደምቆ እሰከ ህይወት መጨረሻ ሲቆይ ለጥሩ ዜጎች ግንባታ ከፍተኛ አሰተዋፅኦ የሚያበረክተውን ያህል በፍቺ ሲጠናቀቅ የተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶችን ያስከትላል ።በተለይ ደግሞ ከዓመታት ቆይታ በኋላ የሚፈርስ ትዳር በጥንዶቹና በዙሪያቸው ባሉ ሰዎች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም ።ፍቺ ሲፈፀም ሳይፈልግ ተገዶ ወደ ፍቺው የገባው አካል ከባድ ሀዘን ውሰጥ ይወድቃል ።ይህ ሀዘን አጋርን በሞት ከማጣት ቀጥሎ ከባዱ ሀዘን እንደሆነ አጥኝዎች ይናገራሉ ::
ለአዕምሮ ህመምም ሊዳርግ ይችላል ።ፍቺ የሀብት ክፍፍልን ስለሚያስከትል ጥንዶች የኢኮኖሚ ውድቀት ይደርስባቸዋል ።
☞ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከነበሩና ሚሰት ስራ ከሌላት የሚበላ እስከማጣት ትደርሳለች ።
☞ልጆች ካሏቸው ደግሞ ችግሩ ተደራራቢ ነው ።
☞ልጆች የአባት ወይም የእናታቸውን ፍቅር ያጣሉ ።
☞ለእንጀራ አባት ወይም ለእንጀራ እናት ይጋለጣሉ ።
☞የኢኮኖሚ ችግር ያገኛቸዋል ።
☞በትምህርታቸው ይሰንፋሉ ።
☞ለተለያዩ የስነ ልቦና ችግሮችም ይጋለጣሉ ።
☞በግቢ ተሳስሮ የቆዬ ዘመድ አዝማድም ይበታተናል ።

በአገራችን ኢትዮጵያ የፍቺ አሀዝ ከግዜ ወደ ግዜ እያሻቀበ መምጣቱ ወጣቶች ትዳርን እንዲፈሩ እያደረጋቸው ነው ።የማግባታቸው ዜና ተሰምቶ ብዙም ሳይቆይ ተፋቱ የሚባልላቸው ብዙዎች ናቸው ።በሰርጋቸው ቀን የዛሬ ዓመት የማሙሸ እናት /የዛሬ ዓመት የማሙሸ አባት ።"ተብሎ የተሸኙ ጥንዶች ዓመት ሳይሞላ ለፍቺ ወደ ፍርድ ቤት የሚሄዱ በመሆኑ የዛሬ ዓመት ወደ ፍርድ ቤት "ወደሚል መቀየር አለበት እስከመባል ተደርሷል ።


ወንድ የተፈጠረው ለሴት ነው ሴትም ለወንድ ነዉ...ሁለቱ አንደ ማግኔት ናቸው ።አርሰ በርስ ይሳሳባሉ ።አንዱ ካንዱ ተለይቶ ቢኖር ህይወት ጣዕም አይኖራትም፣ጎደሎም ትሆናለች ።የሰው ልጅ ጋብቻን በመመስረት ለተፈጥሯዊ አሰፈልጎቶቹ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል ።ለዚህም ነው ለአቅመ አዳምና ለአቅመ ሄዋን የደረሱ ወንዶችና ሴቶች ትልቁ ፍላጎት ትዳር ሲሆን የሚስተዋለው ።ወጣቶች ቅዱሱን የጋብቻ ውል በመፈፀም የደስታ ህይወት ሀሁን ይጀመራሉ ።

#ትዳር
☞ በክፉም በደጉም ግዜ አብሯቸው የሚሆን ተቆርቋሪና ታማኝ አጋር ይሰጣቸዋል ።
☞በተረበሹበት ወቅት ያረጋጋቸዋል ።
☞የተዘበራረቁ ህልሞቻቸውን ወደ አንድ ስኬታማ ግብ ያመጣላቸዋል ።ይህ ቤተሰብ የመመስረት ህልም ወጣቶችን ከአላስፈላጊ ድርጊቶች ያቅባቸዋል ወጣቱ ከታማኝ የቤተሰብ አካል የተሻለ መጠለያ ሊያገኝ አይችልም ።

#ትዳር ተዝናንቶና ተመቻችቶ ለመኖር የሚያስችል የፍቅር ፣የርህራሄና የጓደኝነት ማዕከል ነው ።ሆኖም ብዙ ተጋቢዎች ይህን ነገር በአግባቡ ሲጠቀሙበት አይታይም ።ባለማወቅና ባለማስተዋል ይህን የሞቀና የተቀደሰ አንድነት ወደ ጨለማና ሲኦል ይቀይሩታል ።ወይም ደግሞ ከነጭራሹ ያፈርሱታል ።ጥንዶች እያንዳንዳቸው ከኔ ምን ይጠበቃል?? የሚለውን ነገር በደንብ ካውቁና ያን ተግባራዊ ለማድረግ ከጣሩ ያማረ የትዳር ህይወት እንደሚኖራቸው ጥርጥር የለውም ።

አለበለዚያ ሰላም የራቀው ትዳር ለመግፋት ይገደዳሉ ።በትዳር መካከል ግጭት እንዲፈጠር የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም አንደዚህ መፅሐፍ አዘጋጅ አሰተያየት ትልቁ ችግር ያለው ተጋቢዎች ምን እንደሚጠበቅባቸው አለማወቃቸውና ለጋብቻ ህይወታቸው ዝግጁ አለመሆናቸው ላይ ነው ።

እውቀትና ዝግጁነት ወሳኝ ነገሮች መሆናቸው ልብ ሊባል ይገባል ።ምክንያቱም አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ ተገቢው እውቀትና ዝግጁነት ከሌለው ስኬታማ ሆኖ የሚፈልገው ግብ ላይ ሊደርሰ አይችልም ።ልምድ ፣ዝግጁነትና እውቀት ለጋብቻ ህይወት አስፈላጊ ነግሮች ናቸው ።አንድ ወጣት ስለ ሚስቱ የህይወት መመሪያዎችና ውስጣዊ ፍላጎቶች አንዲሁም በትዳር ውሰጥ ስለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው በቂ እውቀት ሊኖረው ግድ ነው ።

#ጋብቻ በሁለት የህይወት ዘመን አጋሮች መካከል የሚፈፀም የፍቅር ፣የታማኝነት ፣የርህራሄ ፣የአጋርነትና የመተጋገዝ ውል አንጂ ሱቅ ገብተው አንደሚሸምቱት ሸቀጥ አይደለም ።ሴትም አንዲሁ የባሏን የህይወት ፍልስፍናና ፍላጎት ለይታ ማወቅ አለበት ።

#ጋብቻ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይህን ስራ ሲባል የሚሰራ የቤት ሰራተኛ አንደ መቅጠር አይደለም ።ነገር ግን ህይወትን በአግባቡ ለመምራት ለሚደረግ ጥረት አጋርና አጋዥ ማግኛ ዘዴ ነው ።

ስኬታማ አጋር ለማግኘት ደግሞ መግባባት ፣መተጋገዝና መሰዋዕት መክፈል ያሰፈልጋል ።ምንም እንኳ የወጣት ወንዶችና ሴቶች የወደፊት ሁኔታ ትልቅ እውቀት አንዲሁም ዝግጁነት በሚጠይቀው የትዳር ህይወት ላይ የሚመሰረት ቢሆንም ህብረተሰቡ የነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች አስፈላጊነት ችላ ሲል ይታያል ።

ወላጆች ስለ ልጃቸው የትዳር ጓደኛ ስራ ፣እድሜ ፣መልክ ፣ሐብትና መሰል ነገሮች የሚጨነቁትን ያህል ልጆቻቸው በትዳር ህይወታቸው ስኬታማ ሆነው ይቆዩ ዘንድ ማዘጋጀት እንዳለባቸው አይገነዘቡም ።
በመሆኑም ስለ ትዳር ህይወት በቂ መረጃ ሳይሰጡ ልጆቻቸውን ያጋባሉ ።ከዚያም ሁለት ልምድ የሌላቸው አፍላ ወጣቶች በአዲስ ህይወት ውሰጥ ይገናኙና ብዙ ችግሮችን ይጋፈጣሉ ። እሷ ምን ማድረግ አንዳለበት እሱም ምን ማድረግ አንዳለበት አያውቅም አለመግባባቱና ጥል ከፍ ሲልም ድብደብ የተለመደ ነገር እየሆነ ይመጣል ።ይህን ግጭት ለመፍታት ወላጆች ጣልቃ ይገባሉ ።ብዙ ግዜ ደገሞ ጣልቃ ገብነታቸው ለአንድ ወገን የሚያደላ በመሆኑ አለመግባባቱ ይሰፋና ችግሩ እየተባባሰ ይሄዳል ።

የመጀመሪያዎቹ የጋብቻ ዓመታት በክሰተቶች የተሞሉ ወሳኝ ጊዜያት ናቸው ።ብዙ ባለትዳሮች በፍቺና በመሰነጣጠቅ አደጋ ውሰጥ የሚገቡት በዚህ ወቅት ነው ።አንዳንዶቹ ይህን የተበላሸ የትዳር ህይውት አፍርሰን ሲመርጡ ሌሎች ደግሞ አርሰ በርስ ይበልጥ በመተዋወቅ አንፃራዊ ምቾት ያለው የትዳር ህይወት ይፈጥራሉ ።ይህን ችግር ለመፍታት ወላጆች ትልቁን ሀላፊነት መውሰድ ያለባቸው ቢሆንም ከነሱ በተጨማሪ የጋብቻ ዝግጅት "በሚል ርዕሰ ሰለ ጋብቻ መሰረቶችና ማጠናከሪያዎች ዝግጁ እንዲሆኑና ስኬታማ የትዳር ህይወት እንዲመሩ ያስችላቸዋል ።

ወደፊት እንድህ አይነት የማሰልጠኛ ተቋማት ይከፈታሉ የሚል ተሰፋ አለኝ ኢንሻ አሏህ ።


#የፁሁፉ_ምንጭ ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ

✿ በክፍል ሁለት የሴት ልጅ ተግባራት በአላህ ፍቃድ አቀርባለሁ

ክፍል ➋
ይቀጥላል.....


👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሁለት
2⃣


🌙🌙 #የሴት_ልጅ_ተግባራት

💐የትዳር ማጣፈጫ ቅመም አንድ
#ኑሮ_ከባል_ጋር......

የሚስት ተግባር ባሏን መጠብቅና መንከባከብ ነው ። ይህ ከባድ ሀላፈነት ነው ።የዚህን ሀላፊነት ትክክለኛ ገፅታ ያልተረዱ ሴቶች በትዳራቸው ላይ ችግር ይገጥማቸዋል ።ምንነቱን ለተረዳች ሴት የሴትነት አርቆ ማሰብና ብልሀትን የሚጠይቅ ተግባር ነው ።አንዲት ሴት ስኬታማ ሚስት ለመሆን የባሏን ልብ ማሸነፍና ለባሏ የደስታ ምንጭ መሆን አለባት ።ጥሩ ነገሮችን እንዲሰራ ልታበረታታው ከመጥፎ ነገር ልትከለክለው ይገባል ።ለደህንነቱና ለጤንነቱ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅበታል ።ጥረቷ ባሏ ለቤተሰቡ ጠንካራ መከታና ለልጆቹ ጥሩ አባት አንዲሆን ያደርገዋል ።በዚህ ረገድ ሴት ልጅ ልዩ ችሎታን ተጎናፅፋለች ።የቤተሰቧ ደስታና እድገት አንዲሁም ሀዘንና ውድቀት በመዳፏ ነው ያለው ።ሴት ልጅ ከውድቀት ዳርቻ ማድረስ ትችላለች ።በቤቷ ውሰጥ ያላትን ደረጃ ያወቀች ሴት ባሏ ከሰዎች ሁሉ ያነሰ ቢሆን አንኳ የተከበረ ሰው የማድረግ ኃይል አላት ።አንድ ምሁር "ሴቶች የፈለጉትን ነገር የማግኘት ታላቅ ኃይል አላቸው "ሲል ፅፏል ።

💐 የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ሁለት
#ሩህሩህ_ሁኚ

እያንዳንዱ ሰው አዛኝ የልብ ጓደኛ እንዲኖረውና በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ይፈልጋል ።በሰዎች ዘንድ የማይወደድ ሰው ራሱን አንደ ብቸኛና ባዶ አድርጎ ይቆጠራል ።እመቤት ሆይ !ባልሸም ከዚህ የተለየ አይደለም ።ፍቅርና እንክብካቤን ይፈልጋል ።ከማግባቱ በፊት ይህን ፍላጎቱን የሚያሟሉለት ቤተሰቦቹ ነበሩ ።አሁን ግን አንቺ ነሸ ልታሟይለት የምትችይው ።አሱ አንችን ለማስደሰት ይጥራል ።ምናልባትም ከወላጆችሸ በላይ ለደሰታሸ ይጨነቃል ።ሁሉንም የህይወት መሰናክሎች ካንቺ ጋር ይካፈላል ።ስለዚህ ሩህሩህ ሁኚለት ።ፍቅር ሰጪው ።እሱም ያፈቅርሻል ።ፍቅር ሁለት ሌቦችን አንድ የሚያደርግ የሁለትዮሽ ቁርኝት ነው ። "የቴህራን ዩንቨርሲቲ ተማሪ የሆነ አንድ የሀያ ዓመት ወጣት የአገሩ ልጅ የሆነችውን የሰላሳ ዘጠኝ ዓመቷን ባሏ የሞተባትን ሴት አፈቀረ ።ይህም የሆነው ይህች ሴት ያደረገችለት እንክብካቤ ከእናቱ ያጣውን ፍቅር ሰላሟላለት ነው ።የፍቅር የጋራ ሲሆን የጋብቻ መሰረት ይጠናከራል ።የመለያየት አደጋ አይኖርም ።

ባሌ መጀመሪያ ላይ አንዳየኝ ነው በፍቅሬ የወደቀው ብለሸ አትኩራሪ ።ምክንያቱም ይህን መሰሉ ፍቅር ዘለቄታ የለውም ።

#ዘላቂ_ፍቅር_የሚመነጨው
☞ከመቀራረብ ፣
☞ከመተዛዘንና
☞ከመተሳስብ ነው ።

ባልሽን ካፈቀርሸውና ከሱ ጋር መልካም ግንኘነት ካለሸ ደስተኛ ይሆንና ላንቺ ደህንነት ራሱን አሳልፎ እስከመስጠት ይደርሳል ።

የሚስቱን ፍቅር የሚያገኝ ባል የጤንነት መጓደልና ስነልቦናዊ ችግሮች አያጋጥሙትም ።

ከሚስቱ ጋር መልካም ግንኘነት የሌለው ወንድ
☞ ደሰታ ይርቀዋል
☞ቤቱ ያሰጠላዋል
☞ችግሩን የሚረዳው ጓደኛ በመፈለግ በርካታ ሰዓታትን ከቤቱ ውጪ ያሳልፋል ።
"የማይወዱኝንና የማያዝኑልኝን ሰዎች ለማስተዳደር ለምን አልፋለሁ ? ራሴን መዝናናትና የልብ ጓደኛችን ለማግኘት መሞከር አለብኝ የሚል ሰሜት ያድርበታል ።

ሴት ልጅ ባሏን ከልቧ ልትወደዉ ነገር ግን ፍቅሯን ላትገልፅለት ትችላለች ።ፍቅርን በተግባር ማሳየት በራሱ በቂ አይደለም ።አልፎ አልፎ በቃላት መግለፅም ያሰፈልጋል ።

ለምሳሌ "አወድሀለሁ "አፈቅርሀለሁ "የሚሉና መሰል ነገሮች ግንኙነትን በማጎልበት ረገድ ትልቅ አሰተዋጽኦ አላቸው ።

ባል ወደ ሌላ ቦታ በሄደበት ወቅት ሚስት አንደናፈቀችው በመግለፅ ስልክ መደወልና መልዕክት መፃፍ አለበት ።በሌለበት ወቅት ለጓዶኞቹና ለዘመዶቹ እሱን ማድነቅ አሱን የሚቃወም ሰው ካለ መከራከር ይኖርባታል ።

💐 የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ሶስት
#ባልሽን_አክብሪ !

የሰው ልጅ በተፈጥሮው መከበርን ይፈልጋል ።ነገር ግን ሰዎች በቀላሉ ክብር ለመሰጠት ፍቃደኞች አይደሉም ።
ባለቤትሽ ከቤት ውጪ በሚሆንበት ጊዜ ከብዙ ሰዎች ጋር ይገናኛል ።ትህትና የጎደላቸው ሰዎች ሊያሰቀይሙትና ሊያናድዱት ይችላሉ ።ስለዚህ አንድ ሚሰት ቤት ውሰጥ ክብርና ድጋፍ አንድትሰጪውና ውጪ የተጎዳ ስሜቱን አንድትጠግኚለት ይፈልጋል ።

ባልሽን ማክበርሸ አንቺን ዝቅ አያደርግሸም ።ነገር ግን ወርቃማ የትዳር ህይወት ትጎናፀፊ ዘንድ ኃይልና ጥንካሬ ይሆንሻል ።
☞ሁልጊዜ ሰላምታ ስጪው ።ሰላምታሸም ፍቅርን የተላበሰ ይሁን ።
☞በትህትና አናግሪው አትጬሂበት
☞በሚያወራበት ጊዜ አታቋርጪው
☞አብራችሁ ወደ ማህበራዊ ስብስቦች በምትሄድበት ወቅት ቀድሞ እንዲገባ ጋብዢው
☞ከሌሎች ፊት አድንቂው ልጆችሽ አባታቸውን እንዲያከብሩ ምከሪያቸው
☞ለሱ ጥሩ አመለካከት ከሌላቸው አመለካከታቸውን እንዲያስተካክሉ አድርጊ
☞በእንግዶች መሀል አክብሪው ።ለሱም ሆነ ለእንግዶች ፍላጎት እኩል ትኩረት ሰጪ
☞በር በሚያንኳኳበት ወቅት በፈገግታና በደስታ ስሜት ክፈቺ ።ሞቅ ያለ ሰላምታ አቅርቢለት ።

ይህ ቀላል ተግባር የባልሸን የድካም መንፈስ የማደስ ትልቅ ኃይል አለው ።
አንድአንድ ሴቶች ይህ ተግባር ሲከብዳቸው ይስተዋላል
ለባላቸው ሰላምታ ካቀረቡ አንደ ውጪ ሰው የቆጠሩትም ይመስላቸዋል ።ይህ ትክክል አይደለም ።ቀኑን ሙሉ ለቤተሰቡ ደህንነት ሲለፋ አንደመዋሉ መጠን ወደ ቤት ሲመለሰ ክብርና አትኩሮት ይገባዋል ።ለውጪ ሰው ጥሩ የሆነው ሰላምታሰ ለባል ሲሆን ምን ይለዋል ?

ባልሽን ከማዋረድ ተቆጠቢ ።
ሲናገር በጥሞና አድምጪው ።
መጥፎ በሆኑ ቅፅል ስሞች አትጥሪው ።
ስሜቱን የሚጎዳ ንግግር ከተናገርሸው እሱም በተራው ያሰቀይምሻል ።ይህ ደግሞ የፍቅርና የመከባበር መንፈሳችሁን ይሸረሸረዋል ።በመጨረሻም ለፍቺ ሊዳርጉ የሚችሉ ተደጋጋሚ ግጭቶች ይፈጠራሉ ።ባትፋቱ እንኳ ህይወታችሁ በተዘበራረቁ አጋጣሚዎች የተሞላ ይሆናል ።በጥንዶች መካከል የጥላቻ ስሜትና ስነልቦናዊ ቀውስ ከተፈጠረ ደግሞ ወደ ወንጀል መገፋፋት ሊመጣ ይችላል ።

ቀጣዮቹ ታሪኮች ይህን ሀሳብ የሚያጠናክሩ ናቸው ።አንድ የሃያ ሁለት ዓመት ወጣት የአስራ ዘጠኝ ዓመት ሚስቱን በስለት ወግቶ ይገድላል ።ፍርድ ቤት ቀርቦ ድርጊቱን ለምን እንደፈጸመ ሲጠየቅ የሚከተለውን ተናግሯል ፦"ይህቺን ሚስቴን ከአንድ ዓመት በፊት ነበር ያገባሆት ።መጀመሪያ አካባቢ በጣም ትወደኝና ትንከባከበኝ ነበር ።ነገር ግን ያ ሁኔታ ሊቆይ አልቻለም ትዘልፈኝና ታዋርደኝ ጀመር ።በየአጋጣሚው ሁሉና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር መጥፎ ንግግር ትናገረኛለች ይህ ነገር ግራ አያጋባኝ መጣ ።ይባስ ብላ ግራ አይኔ ላይ ችግር በመኖሩ "አውር "አህያ "እያለች ትሰድበኝ ጀመርች ።አንድ ቀን "እውር አህያ "ስትለኝ ቦግ አለብኝ ።ንዴቴን መቆጣጠር አልቻልኩም ።በቢላዋ አሰራ አምስት ጊዜ ወግቼ ገደልኳት

ሚስቱን የገደለው ሌላው አባወራ ደግሞ ለምን እንደገደላት ሲያብራራ "ሚሰቴ"በድንገት ባህሪዋ ተቀያየረ ።ታንቋሸሸኝ ጀመረች ።አንድ ቀን "አውነቱን ልንገርህ ከአንተ ጋር መኖር አልፈልግም !አለችኝ ።ንግግሯ አበሳጨኝ ።ሁለት ጊዜ በመጥረቢያ መትቼ ገደልኳት "ብሏል ።

በክፍል ➌ ወቀሳና ምሬትን እንዴት ማስወገድ እንዳለብሽ እንዳስሳለን

#ምንጭ ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ
ይቀጥላል.....

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- ሶስት 3⃣

በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL




💐 የትዳር ማጣፈጫ ቅመም አራት
#ወቀሳና_ምሬትን_አሰወግጂ

ችግር የማያጋጥመው ሰው የለም ።ችግርን ለሰው ማዋየት ደግሞ እፎይታና መፍትሄ ያስገኛል ።እያንዳንዱ ሰው ችግሩን የሚያዳምጠውና የሚቆረቆርለት ሰው እንዲኖረው ይፈልጋል ።ነገር ግን ለሁሉም ነገር ጊዜና ቦታ አለው ።ለወቀሳም ቢሆን ጊዜና ቦታ ሊመረጥ ይገባል ።አንዳንድ ሞኞች ራስ ወዳድ ሴቶች ባሎቻቸው ቀኑን ሙሉ በሰራ ሲደክሙ መዋላቸውን በመዘንጋት የድካም መንፈሳቸውን እሰኪያድሱ ትንሽ በመታገስ ፋንታ ገና እንደገቡ የምሬት ዶፍ ያወርዱባቸዋል ።
☞"አንተ ምን አለብህ ?ከነዚህ አሰቸጋሪ ልጆች ጋር ትተኸኝ ትሄዳለህ ።
☞አንዱ ልጅ የፊቱን በር መስታወት ሰበረው ።ይሄ ደግሞ ጥናቱን እርግፍ አድርጎ ትቶታል ።ውጤቱም አሽቆልቁሏል ።
☞ሴቶቹ ስርዓት የሚባል ነገር የላቸውም ።ጩኸታቸው ሊያሳብደኝ ነው
☞በቤት ስራ አያግዙኝም ።
☞ቀኑን ሙሉ ብቻየን ስደክም ነው የዋልኩት
☞ሰዋከብ እጄን በቢላዋ ቆረጥኩት ።
☞ችግሬን የሚረዳልኝ ሰው የለም
☞ልጅ ባልወልድ ኖሮ ይህ ሁሉ ችግር አይደርሰብኝም ነበር ።
☞በነገራችን ላይ እህትህ መጥታ ነበር ።ምን ሆና ነው ግን አንደሆነ ነገር ያደርጋታል ።ሆ! የአባቷን ሀብት የቀማሆትኮ ነው የመሰላት
እናትህንማ ተዋቸው ።ከበሰተጀርባዬ ብዙ ነገር ያወራሉ ።ፈጣሪ ለምን ከእንዲህ አይነት ሴት ጋር አንዳገናኘኝ አላውቅም ።በሁሉም ነገር ተማርሬያለሁ ።

☞ትናንት ከሳራ ሰርግ ምነው ባልሄድኩ ነው ያልኩት
☞የጓደኛህ ሚስት ብታያት !ምን አለ አኔም እንደሷ እድለኛ ሴት ብሆን ?የለበሰችው ልብስ ፣ያረገችው ጫማ ፣ወርቋ !አንዳንድ ወንዶች ሚስቶቻቸውን በጣም ስለሚወዱ ቆንጆ ቆንጆ ነገሮችን ይገዙላቸዋል ።ትክክለኛ ባል ማለት አንዲህ አይነቶች ናቸው ።እሷ ስትገባ ሁሉም ሰው በአድናቆት ተቀበላት ።ሰዎች የለበሰከውን ነው የሚያዩት ።አኔንማ አንዴት በንቀት ዓይን አንዳየችኝ ልክ ናት አኔ እንደሷ እድለኛ ሴት አይደለሁም ።እሷ የሚወዳት ባል አላት ። #ትሰማለህ አይደል ከዚህ በኋላ አንተንና ልጆችህን በመንከባከብ አዚህ ቤት ውሰጥ ህይወቴን መጨረስ አልፈልግም ።
ስለዚህ የምታደርገውን ነገር አድርግ !

ይህን መሰሉ አካሄድ ስህተት ነው ።አንዲህ ዓይነት አመል ያላቸው ሴቶች ባሎቻቸው በየዕለቱ ለሽርሽርና ለመዝናናት የሚወጡ ነው የሚመስላቸው ።

ወንዶች በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ችግሮች ያጋጥማቸዋል ።እመቤት ሆይ ! ባልሽ በሰራ ላይ ምን እንደሚያጋጥመው አታውቅም ።ቀኑን ሙሉ ክፉና አሰቸጋሪ ሰዎች ጋር ሊሆን ይችላል የሚውለው ።ስለዚህ ቤት በሚገባበት ወቅት ወቀሳዎችሸን በሙሉ በእንዴ በማዥጎድጎድ ባል መሆኑን እንዲጠላ ማድረግ የለብሽም ።

በመጨቅጨቅና በመነዝነዝ ለጭንቀት የምትዳርጊው ከሆነ ከአንቺ ጭቅጭቅ ለመራቅ ሲል አዲስ ባህሪ ይጀመራል ።ወደ ቤት ከመግባት ይልቅ
ወደ መጠጥ ቤት ፣ጫት ቤት ወዘተ ለመሄድ አለያም አንዲሁ በየጎዳናው ለመዞር ይገደዳል ።

ስለዚህ እመቤት !በፈጠረሽ ይህን በየመጥፎ አጋጣሚዎች መጨቃጨቅሸን ተይ ።ለወቀሳ ተስማሚ ወቅቶችን ምረጪ ።ከዚያም በመውቀስ ሳይሆን በማማከር አይነት ዋነኞቹ ችገሮችሸን በእርጋታ ለባልሸ አሳውቂ ።በዚህ መልኩ ችግሮችሸን ማቅረብሸ መፍትሄ የሚያስገኝ ከመሆኑም ባሸገር በባልሸ ላይ የጥላቻ ስሜት አይፈጥርበትም ።በቤተሰቡ መካከል ያለው ፍቅርም እንደተጠበቀ ይቆያል ።

ጨቅጫቃ ሴቶች በጭቅጭቅ ምን ማትረፍ እንደሚፈልጉ አይታወቅም ።የባሎቻቸውን ትኩረት ለማሰብ ከሆነ በርግጠኝነት ውጤቱ ተቃራኒ ነው የሚሆነው ።ለማበሳጨት ፣በሱ ላይ ስነልቦናዊ ችግር ለመፍጠር አለያም ህይወቱን ለማበላሸት አስበው ከሆነ ግን በአርግጥም ይሳካላቸዋል ።

ውድ ሴቶች ! ለባሎቻችሁና ለቤተሰባችሁ የምታስቡ ከሆነ ይህን መጥፎ አካሄድ ማቆም አለባችሁ ።ይህ ባህሪ የቤተሰባችሁን ህይወት በአደገኛ ሁኔታ ሊጎዳ አንደሚችል ተረዱ ።አንድ ዶክተር ለፍርድ ቤት ቃሉን ሲሰጥ ፦"በጋብቻ ህይወታችን ውሰጥ ሚስቴ አንድም ቀን ጥሩ ሴት ሆና አይቻት አላውቅም ።ቤታችን ሁሌ አንደተረበሸ ነው ።ጧት
ማታ ጭቅጭቅ ።በሷ በጣም ተማርሬያለሁ ።በርካታ ገንዘብ ከሰጣት በኋላ ፍቺ ፀደቀለት ።ከዚያም እፎይ በሚል አይነት ሰሜት " ከዚህም በላይ ብትጠይቀኝ ኖሮ ከሷ ለመገላገል ስል ያለኝን አጠቃላይ ሀብትና የህክምና ዲግሪዬን ሳይቀር እሰጣት ነበር "ብሏል ።



#ምንጭ ☞ ፍቅርና እና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ

#ክፍል ➍ ይቀጥላል.........

👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- አራት 4⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL

እስኪ ብቃት ያላት ሴት ለብቁ ወንድ ነዉና አንተም ወንድነህና እስኪ ከአንተ የሚጠበቀዉንም እንዳስ

#የቤተሰብ_ኃላፊ

የቤተሰብ ሀላፊ መሆንህን አትዘንጋ
ወንድና ሴት ሁሉቱም የቤተሰብ መሰረቶች ናቸው ።ነገር ግን ወንዶች በምክንያታዊነት የተሻሉ ስለሆኑ የቤተሰብ መሪ ሊሆኑ ችለዋል ።ስለዚህ ወንዶች ቤተሰባቸውን በመደገፍ ረገድ ትልቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል ።

#ወንድ
☞በብልሀት ቤተሰቡን ማስተዳደር
☞ለቤተሰቡ ደሰታ
☞ቤቱን ሰላም የሰነፈነበትና
☞ሚስቱን የቤቱ ዘውድ ማድረግ ይችላል ።ሴትም ልክ አንደ ወንድ ሁሉ የሰው ፍጡር መሆኗንና እሷም ፍላጎቶቿን የማሟላትና በነፃነት የመኖር መብት እንዳላት ማወቅ አለበት ።

ሚስት ማግባት ሰራተኛ መቅጠር አይደለም ።ቀሪ ህይወትን አብራ የምታሳልፍ አጋርና ጓደኛ መምረጥ እንጂ ።ወንድ ለሚስቱና ለፍላጎቶቿ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ።ሚሰት ባል እንደፈለገው የሚያደርጋት ንብረቱ አይደለችም ።ከሱ ላይ የምታገኛቸው በርካታ መብቶችም አሏት ።

🌹የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ለአባወራዉ
1⃣
#ሚስትህን_ተንከባከብ

የአንድ ቤተሰብ የስኬት ሚስጥረ ባል ሚስቱን ከሚንከባከብበት ዘዴ የሚመነጭ ነው ።ሴት ልጅ ባሏን በጥሩ ሁኔታ መንከባከቧ ወሳኝ እንደሆነው ሁሉ ወንድም ሚስቱን መንከባከቡ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ተግባር ነው ።ነገር ግን አንድ ባል ሚስቱን መልካም ሚስት ለማድረግ ምን ማድረግ አንዳለበት ማወቅ ይኖርበታል ።

~~~ለዚህም ሚስቱ ምን አይነት ባህሪና ፍላጎት እንዳላት ጠንቅቆ ማወቅ አለበት ።ህይወቱን በሚስቱ ፍላጎትና አግባብነት ያላቸው ጥያቄዎቿ መሰረት ማስተካከል ይኖርበታል ።በሚያሳየው መልካም ባህሪ ሚሰቱ እሱንና ቤተሰቧን አንድትወድ ማድረግ ይችላል ።ይህ ርዕሰ ጉዳይ በቀጣዮቹ ምዕራፎች በደንብ ይብራራል ።

🌹 የትዳር ማጣፈጫ ቅመም ለአባወራዉ
2⃣
#አፍቃሪ_ሁን

ሴት ልጅ የእዝነት ማዕከል ናት ።ህይወቷ በፍቅርና በእዝነት የተሞላ ነው ።በሌሎች መወደድን ትፈልጋለች ።በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ስትል ራሷን አሳልፋ እስከመስጠት ትደርሳለች ።

~~~ማንም ሰው አይወደኝም ብላ ካሰበች እንድ ውድቀት ትቆጥረዋለች ።ደሰታ የራቃትና የተገለለች ትሆናለች ።በጋብቻ ህይወት ውሰጥ የአንድ ባል ስኬት ለሚስቱ በሚያሳየው ፍቅር ይወሰናል ማለት ይቻላል ።

#ውድ_ወንድም_ሆይ!
ሚስትህ አንተን ከማግባቷ በፊት የቤተሰቦቿን ፍቅርና እንክብካቤ ታገኝ ነበር ።አሁን ግን ቀሪ ህይወቷን ከአንተ ጋር ለማሳለፍ የጋብቻ ውል ፈፅማ ወዳንተ መጥታለች ።ስለዚህ የምትፈልገውን ፍቅርና እንክብካቤ አንተ እንድታሟላላት ተሻለች ።

☆ ቤተሰቦቿና ጓደኞቿ ይሰጧት ከነበረው የበለጠ ፍቅር ከአንተ ማግኘት ትፈልጋለች ።ከምንም በላይ ሰላመነችህ ነው ቀሪ ህይወቷን ከአንተ ጋር ለማሰለፍ የወሰነችው ።

☆ ሚስቱን ማፍቀር የደሰተኛ ትዳር ሚስጥር ነው ።የሚስትህን ልብ ለማግኘትና ፍላጎትህን የምታሟላልህ ታዛዠ ፣አፍቃሪና ታማኝ ሚሰት አንድትሆንልህ ከፈለግህ ፣ጠንካራ መሰረት ያለው ትዳር እንዲኖርህ የምትሻ ከሆነ ሁልጊዜም ለሷ ያለህን ፍቅር ማሳየትና መግለፅ አለብህ ።

☆ እዝነትህን ከነፈግካት ለቤቷ ፣ለልጆቿ ከሁሉም በላይ ደግሞ ላንተ ያላት ፍቅር ይቀዘቅዛል ።ካንተ ያጣችውን ፍቅር ከሌሎች ለማግኘት ጥረት ልታደርግ ትችላለች ።ቤትህ ሰላም ደርቀዋል ።ፍቅር የሌለበት ቤት የቱንም ያህል ውብና በማራኪ እቃዎች ያሸበረቀ ቢሆንም ሲኦል ነው ።

☆ሚስትህ በአንተና በትዳሯ ላይ ያላት ጥላቻ ሊበረታና ፍቺ እስከመጠየቅ ልትደርስ ትችላለች ።ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው አንተ ነህ ።ምክንያቱም ከአንተ ማግኘት ያለባትን እንክብካቤ አልሰጠሀትም ።

ብዙ ፍቺዎች የሚፈፀሙትም ከእንክብካቤ ጉድለት ነው ።
እ.ኤ.አ 1969 ከተፈፀሙ አጠቃላይ 10,372 ፍቺዎች መካከል 1,203 ሴቶች ለፍቺ የዳረጋቸው ባሎቻቸው ለፍላጎታቸውና ስሜታቸው ትኩረት ሊሰጡ አለመቻላቸው የትዳር ትርጉም አንዲያጡና በህይወት ተሰፋ እንዲቆርጡ ስላደረጋቸው አንደሆነ ገልፀዋል ።

~~~ አንዲት ሴት ፍርድ ቤት ቀርባ ባለቤቷ የሰጣትን ጥሎሽ ጨምሮ ሌላም ገንዘብ ጨምራ ሰጥታው ለፍቺ እንዲስማማ ታግባባዋለች ።ምክንያቷ ምን አንደሆነ ስትጠየቅ "ባለቤት ትርፍ ጊዜውን ከኔ ይልቅ ከጓደኞቹ ጋር ማሳለፍን ይመርጣል ።ስለዚህ ከሱ ጋር መቀጠል አልፈልግም "ብላለች ።

ፍቅርና ውዴታ በሌሎች ልብ ውሰጥ ይገባ ዘንድ እውነተኛ መሆን አለበት ።በልብ ብቻ መውደድ በቂ አይደለም ።በቃላት መግለፅም ያሰፈልጋል ።ግልጽ ሁን ለሚስትህ ያለህን ፍቅር በቃላትና በተግባር ከመግለጽ አትቆጠብ ።

ይህ የፍቅር ቁርኝትን ያጠነክራል ።
☞ባለችበትም ሆነ በሌለችበት እሷ ለአንተ ልዩ ሰው እንደሆነች ተናገር ።
☞በጉዞ ወቅት ደውልላት አንደናፈቅካትም ግለፅላት
☞አልፎ አልፎ አንዳንድ ነገሮችን ግዛላት ።
☞በስራ ላይ በሆንክበት ወቅት ደውልና ሰላምታ አቅርብላት ይህን መሰሉ ተግባር በሴት ልጅ ልብ ውሰጥ ታላቅ ቦታ ይሰጠዋል ።

■ አንዲት ሴት ስትናገር "ከባለቤት ጋር በደሳሳ ጎጆ ውሰጥ ለስድስት ዓመታት ያህል በሰላም ኖረናል ።በዚህም በዓለም ላይ ራሴን የመጀመሪያዋ እድለኛ ሴት አድርጌ ነበር የምቆጥረው ።ማርገዜን ሳውቅ ደስታዬ ወደር አልነበረውም ።ሁኔታውን ለባለቤቱ ስነግረው አቅፍ አድርጎኝ ራሱን መቆጣጠር እስኪያቅተው ድረስ የደስታ እንባ አነባ ።ወዲያውኑ ወጣና ከወር ገቢው እየቀነሰ የሚያጠራቅመውን ገንዘብ አንሰቶ ትልቅ የወርቅ ሐብል ገዛልኝ ።"ይህን ሐብል የምሰጠው ከሁሉም በላይ ለሆነቸውና በዓለም ላይ አምሳያ ላላገኘሁላት ውድ ባለቤቱ ነው "በማለት አንገቴ ላይ አጠለቀልኝ ።ነገር ግን አብረን ብዙ አልቆዬንም ።በመኪና አደጋ ሞተ "ብላለች በሐዘን በተሰበረ ሰሜት ።


እናም ለሚስቶቻቸዉ አልፎ አልፎ ስጦታ መስጠት ሚስቶችን ደስተኛ መቼም የማይረሱት ዉለታ መሆኑን አትዘንጋ

በክፍል ➎ ለዉዷ እህቴ መልካም ስነምግባር መኖር እንዳለባት እንዳስሳለን...
ምንጭ ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ

ሼር ያድርጉ
👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
💚💛❤️ #ፍቅር_እና_ጋብቻ 💐🌹💐

#አዘጋጅ ☞ መህቡባ ቢንት አቡሀ
ክፍል :- አምስት 5⃣


በISLAMIC UNIVERSITY CHANNAL


💐 የትዳር ማጣፈጫ ቅመም አምስት
#መልካም_ፀባይ_ይኑርሽ !

አንዳንድ ጥሩ ተፈጥሮና መልካም ፀባይ ያላቸው ሰዎች አሉ ።ይህ አይነቱ ስብዕና በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትና ከማስገኘቱም በላይ ለስነልቦና ችግር ከማጋለጥ ያድናል ።

ጥሩ ሰዎች ለህይወት ያላቸው አመለካከት ጥሩ ስለሚሆን ችግር ቢግጥማቸው እንኳ ሁሉንም ነገር እንዳመጣጡ ለመሸኘት አይቸገሩም ።መጥፎ ባህሪ ላላቸው ሰዎች ህይወት አሰቸጋሪ ናት ።የነገሮች ሁሉ መጥፎ ጎን ብቻ ነው የሚታያቸው ።ተመስገንን አያውቁትም ።ሁሌም ህይወትን ሲያማርሩ ይደመጣሉ ።

■ ይህ አይነት ባህሪ ደግሞ በሰዎች ዘንድ ስለሚጠላ በጥሩ መንፈስ የሚቀርባቸው ጓደኛ አያገኙም ።ምክንያቱም ሁሌ እሮሮ መሰማት የሚፈልግ ሰው የለም ።ይህ የልብ ጓደኛ ማጣታቸው ደግሞ ለተለያዩ የሰነ ልቦና ችግሮች እና ሌሎች በሽታዎች እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል ።

#እመቤት_ሆይ !
ከልጆችሸና ከባለቤትሽ ጋር በደስታ ለመኖር ከፈለግሽ
ባህሪሸን አስተካካይ
ፀባይሸ ጥሩ ይሁን
ጠብ ጫሪ አትሁኚ

☞ቤትሸን ንትርክ ወይም ሰላም የሰፈነበት የማድረጉ ችሎታ በእጅሽ ነው ያለው ።
☞ፍላጎቱ ካለሸ ልጆችሸና ባለቤትሽ ሰላም የሚያገኙብሸ የደግነት አውራ መሆን ትችያለሽ ።
☞በፈገግታሸና በአነጋገር ለዛሸ ልባችው ወስጥ ጥሩ ስሜት ማሳደር አንደምትችይ አውቂ ።

ያንቺ መልካም ባህሪ ልጆችሽ በትምህርት ቤት ፣ባለቤትሽ በሰራ ቦታ ቀኑን ሙሉ ደስተኞች ሆነው እንዲውሉ ያደርጋቸዋል ።ስለዚህ ጥሩ ህይወት አንዲኖርሸና ከባለቤትሽ ጋር ያለሽ ግንኙነት ጤናማ ይሆን ዘንድ ቅንነት አይለይሸ ።ትዳርን አንደ ምሶሶ ደግፎ የሚያቆየው መልካም ሰነ ምግባር ነው ።ብዙ ጊዜ ፍቺ የሚከሰተው በባልና ሚስት መካከል የባህሪ አለመጣጣም ሲኖር ነው ።

● መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ብዙዎች ፍቺ የፈፀሙ ጥንዶች ተመሳሳይ አመለካከት ፣የሞራል እሴቶችንና ስነምግባር አይታይባቸውም ።

ለቤተሰብ ግጭት ዋናው መንስኤ የጥንዶች ባህሪ አለመጣጣም ነው ።የሚከተሉት መረጃዎች ይህን እውነታ የሚያረጋግጡ ናቸው ።
"ከሰባ በመቶ ባላይ የሚሆኑት የቤተሰብ ግጭቶች የሚከሰቱት በዚህ ጉዳይ ነው ።አንዲት ሴት "ባሏ ሁልጊዜ ምሳውና ራቱን ቤቱ አንደማይበላ ለፍርድ ቤት በማማረር ትገልፃለች ።ባልዮውም ምከንያቱ ምን አንደሆነ ሲጠየቅ "ሚስቴ በፍፁም በውስጧ ጥሩ ነገር የለም ።በዓለም ላይ ካሉ መጥፎ ሴቶች ሁሉ የከፋች ናት"በማለት መልሷል ።ይህን ሲናገርሞ የሴትዮዋ በፍጥነት ተነስታ ከዳኞች ፊት እሱን መሳደብና መማታት ጀመረች ።

ይቺ ሞኝ ሴት በመሳደብና በመማታት ባሏን ወደ ቤት የምትመልስ መሰሏታል ።ነገር ግን ቀላልና በሳል የሆነውን መልካም ባህሪን የማሳየት የመሳብ ዘዴን መጠቀም ትችል ነበር ።

ሌላዋ ሴት ባለቤቷ ለአስራ አምስት ወራት ያህል ሳያናግራት እንደቆየና የቤት ወጪም የሚልከው በእናቱ በኩል አንደሆነ ለፍርድ ቤት ሪፖርት አድርጋለች ።
ባልዮው ሲመልሰም "ሚስቴ የምታሳየኝ መጥፎ ባህሪ ልታገሰ ከምችለው በላይ ስለሆነብኝ ለረዥም ጊዜ ላላናግራት ወሰንኩ "ብሏል ።


ጥንዶች አዲስ ቤት ሰርተው ገብተዋል ።የቤት ምርቃት አድርገን ደስታችንን ከወዳጅ ዘመድ ጋር እንካፈል በሚል ደግሰ ይደግሳሉ ።ዘመድ ወዳጅ ተጠራ ።ቤት በሰው ተሞልቶ ይበላል ፣ይጠጣል ።በመሀል ሚስት ለባሏ ለቡና ቁርሰ የሚሆን ኬክ ካልገዛህ ትለዋለች ።ባል "ብር የለኝም ዳቦ አለ እሱ ከተቆረሰ ይበቃል "ይላል
.....ሚስት ልትረዳው አልቻለችም ።"ብርማ አለህ የለኝም ማለት ስለምትወድ ነው አንጂ "እያለች ትሳደብ ጀመር ።አሱም መልስ ይሰጣታል ።እንግዶች አሰኪያውቁባቸው ድረስ ።እንግዶቹ አንተም ተው አንችም ተይ ይሉ ጀመር ።እነሱ ግን ንትርካቸውን ሊያቆሙ አልቻሉም ።አንድ አባት ይነሱና "ዛሬ የደሰታችን ቀን ነው ።ኑ ቤታችንን መርቁልን "ተብሎ ጠርቶ ሲያበቁ ጠብ መፍጠር በየትም አገር ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ነውር ነው ....አንቺም ለእንግዶችሸ ክብር ይኑርሽ ።አንተስ ብትሆን ወንድ አይደለህም አንዴ ምንድነው ነው ከሴት ጋር እሰጣ ገባ ?"አሉ ።

ሚስት ትነሳና "አይ አባባ እሱኮ ወንድ አይደለም .... ብላ ፀያፍ ቃል ወረወረች ።ሸማግሌው ሞቅ ብሏቸው ነበርና "ተዲያ ወንድ ካልሆነ አነዚህን ልጆች ከማን ወለድሻቸው እባክሽ ?ይሄ ንግግርሸ እኮ ብዙ መዘዝ ሊያመጣብሸ ነው "አሉ ።ብዙዎች ሰዎች ሲያዝኑ የተወሰኑት ሳቁ ።

ባል ይህ አይነቱ ውርደት የደረሰበት በጓደኞቹና በዘመዶቹ ፊት ነው ።ሮጦ ያዛትና ይደበድባት ጀመር ።ኡኡታዋን አቀለጠችው የሰፈር ሰው ተሰበሰቡ ።ፖሊስ መጣ ።ይታሰርልኝ አለች ።ወሰደው አሰሩት በቀጣዩ ቀን ፖሊስ ጣብያ ሄዳ ከእስር ይፈታልኝ አለች ...ተፈታ ወደ ቤቱ ግን አልተመለሰም ።ሸማግሌዎች ሄደው "እሷ ጥፋቷን አምና ይቀርታ አድርግልኝ ወደ ቤትህ ግባና ትዳራችን እንቀጥል "ብላሃለች ሲሉት "እኔኮ ወንድ አይደለሁም ።ወንድ ፈልጉና አጋቧት አለ ።አቋሙን ሊቀይር ባለመቻሉም ፍቺ ተፈፀመ ።

ብዙዎቹ ቤተሰባዊ ግጭቶች በመተዛዘን ፣በመቻቻልና ጥሩ ስነምግባርን በማሳየት ሊፈቱ የሚችሉ ናቸው ።

ባለቤትሽ ለአንቺ አዝነትና ክብር የሚጎድለው ፣ተሳዳቢ ፣ጯሂ ሊሆንና ሌሎች ትዳር ላይ ግጭት ሊያሰከትሉ የሚችሉ ባህሪያት ሊኖሩበት ይችላል ።ይህን ችግር ለመፍታት አንድ ብቸኛ ዘዴ አለ ።ይሄውም ለሱ አዛኝና ደግ ሆኖ መቅረብ ።ደግ ሆነሽ ቅረቢውና ውጤቱን ጠብቂ ።አስገራሚ ለውጥ ታያለሸ ።ምክንያቱም ደግነት የማያሸንፈው ነገር የለም ።

》》》በሚቀጥለዉ ክፍል ለዉዱ ወንድሜ ሚስትህን ማክበር እንዳለብህና መልካም ባህሪ መላበስ እንዳለብህ እንዳስሳለን

#ምንጭ ☞ ፍቅርና ጋብቻ ከሚለዉ መፅሀፍ የተዘጋጀ

ክፍል ➏
ይቀጥላል....



👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/23 04:34:48
Back to Top
HTML Embed Code: