Telegram Web Link
አሰላሙአለይኩም ያጀመአ
"መራራ እዉነት" ተብሎ የተሰየመዉን
በከፊል በእዉነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተፃፈዉን አዲስ ታሪክ የፊታችን ሰኞ ማስነበብ እንጀምራለን


#መራራ እዉነት ታሪኩ እየመከረ፤የዘነጋነዉን እያስታወሰ፤ እናንተንም እየጠየቀ በጥያቄዉ እየጋበዘ.... ብዙ ትምህርቶችን የምታገኙበት፤ የፍቅርን ጥግ የምታዩበት አሪፍ ታሪክ ነዉ ።


ኢንሻአላህ ታሪኩ 95% ተፅፎ ስላለቀ የኔቶርክና መሰል ችግሮች ካላጋጠሙን ቋሚ ሰአት ባይኖረዉም ቀን በቀን ይፓሰታል😊

☞ ወንድም አሚር ሰኢድ ቀን በቀን ታሪኩን መፓሰት ስለማይመቸዉ እኔን Admin ስላደረገኝ የምፖስተዉ ይሆናል


ዉዶቸ እናንተም ለወዳጂ ዘመድ በማጋራት፤አስተያየት በመስጠት ድጋፋቹህ አይለየን🙏

...... ሰሚራ ሽኩር

www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
ታህሳስ 19/04/2013 ዓ.ም

መራራ እዉነት
ክፍል 1⃣

.......ሰሚራ ሽኩር

ዉዶቸ በአላህ ፍቃድ ያስተምራል ብየ ለመፃፍ የሞከርኩትን (መራራ እዉነት) ዛሬ ጀመርነዉ
በታሪኩ ዉስጥም የተለያዩ ጥያቄዎችን አቀርብላቹሀለሁ በአካል ባንቀራረብም በሀሳብ ከኔ ጋር በመሆን ለራሳቹህ መልስ ስጡ ..... ሸር በማድረግ ድጋፋቹህ አይለየን!


ሂወት እኛ እንደምናስባት ጣፋጭ ተረት ሳትሆን መራራ እዉነት ናት!
በሂወታችን ዉስጥ ሰላማችንን አጥተን ከራሳችን ጋር ተጣልተን ሰላም እንደሆን እያስመሰልን የምንኖር ስንቶቻችን ነን???
በኑሯችንስ ተስፋ ቆርጠን በጭስ ተደብቀን በሱስ ተጠምደን፤ ልባችን ተሰብሮ፤ እብዶች እየተባልን በፍርሀት፤በብቸኝነት፤በጭንቀት.....የምንኖር ስንቶቻችን እንሆን!
ስንቶቻችንስ የፈለግነዉን የምንመኘዉን ሰዉ፤ገንዘብ፤ቤተሰብ፤ስራ.... አግኝተናል???
ስንቶቻችንስ ያላደረግነዉን አደረጋቹህ፤ያልሰራነዉን ሰራቹህ፤ያላወራነዉን አወራቹህ...ተብለን በማናቀዉ፤ባላሰብነዉ፤ባልሰራነዉ...የስቃይን ጥግ አይተናል
ስንቶቻችንስ በበሽታ ተይዘን፤ከቤተሰብ ርቀን ኑሮ አልሞላልን ብሎ መኖራችን ከመሞታችን አንሶ ታይቶን መሞታችንን ተመኝተናል???
ጥያቄዉን ለናንተዉ ተዉኩት



ዉይ! ለካ ከጥያቄ መተዋወቅ ይቀድም ነበር ይቅርታ ጥያቄየን ስላስቀደምኩኝ
ራሴን ላስተዋዉቅ ሀናን እባላለሁ የመጀመሪያ አመት የህክምና ተማሪ ነኝ እናቴ መርየም ትባላለች የቤት እመቤት ናት አባቴ ደግሞ ኡመር ይባላል በጣም የዋህ፤ለሰዉ ሲበዛ አዛኝ፤ዝምተኛ የሚወደድ ጥሩ ፀባይ ያለዉ ሀብታም ነጋዴ ነዉ። በቤተሰባችን ዉስጥ እኔ የመጀመሪያ ልጂ ስሆን ሪሀና ደግሞ የኔ ተከታይ የአስረኛ ክፍል ተማሪ ናት እናትና አባታችን ከሁለታችን ዉጭ ወንድም ሆነ ሴት ልጂ የላቸዉም ነገር ግን አንድ እንደልጃቸዉ የሚያዩት አማን የሚባል የአእምሮ በሽተኛ ወጣት ልጂ አለ።
በጊቢያችን ዉስጥም አንድ ክፍል ተሰጦት ከኛ ጋር መኖር ከጀመረ አንድ አመት ሁኖታል።
እነዚህን ጊዚያት ከአማን ጋር በጭንቀት፤በሀዘን....እንዴት እንዳሳለፍነዉ አላህ ብቻ ነዉ የሚያዉቀዉ
.....አባቢ አማንን እኛ ቤት ሲያመጣዉ መጮህ ፤ልሂድ ልቀቁኝ ማለት፤መቃም፤ማጨስ፤ መለፍለፍ.....ነበር ስራዉ አማን በጣም ነዉ የሚያሳዝነኝ ሁሌም መጮህ ፤ማልቀስ፤ብቸዉን ማዉራት፤ራስን ስቶ መዉደቅ.....የሁል ጊዜም ተግባሩ ነዉ።


ግን አማኔ ምን ሁኖ ይሆን ያበደ የሁል ጊዜም ጥያቄየ ነዉ!
...... መቸም የሰዉ ልጂ ምንም ሳይነካዉ አያብድም ካለ ምክንያት ሱስ ዉስጥ አይገባም፤ምንም ሳይሆን ራሱን አያጠፋም.......አይደል ዉዶቸ?

.... ታናሽ እህቴ አማንን በጣም ነዉ የምትጠላዉ እሱም እኛን አይወደንም እህቴ ሁሌም "" የሆነ ቀፋፊ ነገር ነዉ ልብሱ ቀለሙን ከቀየረ ሰነባብቷል እንደዉም ልብሷቹ ለተለያዩ ነፍሳቶች መኖሪያ ሁኗል፤ሰዉነቱ ከመቆሸሽም አልፎ መጥፎ ሽታን ተላብሷል፤ቅጥነቱ ከሳር ይበልጣል፤ከንፈሩ ደርቆ፤ጥርሱ ጠቁሮ ፤ፂሙ አድጎ፤ጥፍሮቹ አድገዉ ቆሽሸዉ፤ፀጉሩ እንደሴት ተንጨብሮ፤ፊቱ በቆሻሻ ተደብቆ ጥቁር ይሁን ቀይ ለመለየት ከባድ እስከሚሆን ድረስ ከሰዉነት ጎዳና ወጥቷል። እና ይሄ ጤነኛ ነዉ እብድ!""ትላለች

እኔንም ሆነ ሪሀናን ትምህርት ቤት ለመሄድም ሆነ ሌላ ቦታ ከጊቢዉ አያስወጣንም ለነገሩ ሪሀና ብቻ ሳትሆን የምትጠላዉ እሱም ከሷ በላይ ይጠላናል ሁሌም አባቢ እሱን እኛ ቤት ያመጣበትን ቀን ሪሀና ስትረግም፤ስታማርር ይሄዉ አንድ አመት አስቆጠርን እኔን፤ እማየንና ሪሀናን ሲያይ ምንም ሳናደርገዉ ካልመተኋቸዉ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል።
በቃ ምን አለፋቹህ ሴቶችን ሁሉንም ሲያይ በጣም ስለሚጠላቸዉ ልማታ ይላል።
ወንዶቹን ግን ፈርቷቸዉ ይሁን አላቅም ምንም አይላቸዉም ገና ልንወጣ የግቢዉን በር ስንከፍት ከሰማ ቶሎ ድንጋይ ይዞ ይመጣል።
ነገር ግን ከአባቢ ጋር ስለሚዋደዱ አባቢ ተዉ ካለዉ መተዉ ነዉ።
...... አሁን አሁን ግን የተወሰኑ ለዉጦች ይታዩበታል ከክላሱ ፈፅሞ አይወጣም በርግጥ መጀመሪያ አባቢ እኛ ቤት እንዳመጠዉ ካልወጣሁኝ እያለ ያስቸግረን ነበር ከዛ አባቢ በየቁርአን ቤት እየወሰደ ብዙ ለፋ ሲህር፤ቡዳ፤ጂን....ነዉ በማለት ቁርአን ተቀራበት ቢያንስ ለሊት ለሊት የሚጮኸዉን፤ራሱን ስቶ የሚወድቀዉን አቆመ ከዚህ ዉጭ ብቻዉን ማዉራቱ፤እንቅልፍ አለመተኛቱን ደግሞ አባቢ ሀኪም ቤት ወስዶት (ዳ.ር) የሰጠዉን መድሀኒት መዉሰድ ከጀመረ ጀምሮ በጣም ብዙ ለዉጦችን አሳይቷል ግን እኔንም እማየንም መማታት ፤አትወጡም ማለት፤አንዳንዴ ምግብ አልበላም ማለቱን አልተወዉም።አይ አባቢ በጣም ደግ አባትኮ ነዉ እንዴት እንደምወደዉ! ሳያዉቀዉ፤በስጋ ሳይዛመደዉ.... ለአእምሮ በሽተኛዉ (ለአማን) ብዙ ነገር ያደርግለታል እንደዉም ከኛ ይበልጥ እሱን ሳይወደዉ አይቀርም አባየ ሁሌም ገላህን ልጠብህ ይለዋል ነገር ግን ለመታጠብ ፍቃደኛ አይደለም ልብሱን ሰዉ ሲነካበት አይወድም።
አባቢ ሁሌም ምግቡን አብልቶ መድሀኒቱን በስአቱ ይሰጠዋል እረስቶት እንኳን ሳይሰጠዉ ከሄደ እማየ እንድትሰጠዉ ይደዉልላታል እማየም በስንት ስቃይ ትሰጠዋለች።
......ሁሌም ሪሀና "እባክህ ይሄን እብድ አስወጣልንና እንደድሮዉ በሰላም እንኑር " ብትለዉም አባቢ በጣም በመናደድ አይቻልም ሁለተኛ እንደዚህ አይነት ንግግር እንዳልሰማ! ሪሁየ የኔ ልጂ እኔ ልጆች አሉኝ ነገ ምን እንደሚፈጠር አላቅም ልጀ አንች ቁርአን የቀራሽ አይደለሽ አላህ በተከበረዉ ቁድስ ቁርአኑ "አንተ የአደም ልጂ ሆይ ጥሩም ስራ ስራ መጥፎም ስራ ስራ ትመነደዋለህ" የሚለዉን የአላህን ቃል አታስታዉሽም?" በማለት አፏን አዘግቷታል።
............እንዲህ ካላት ቡኋላ ሪሀና አንድም ቃል ስለ አማን ተናግራ አስወጣልን ብላዉ አታቅም።


ግን አባቢ አማንን(የአእምሮ በሽተኛዉን) ከየት አገኘዉ? እንዴትስ እኛ ቤት ሊያመጣዉ ቻለ?

ኢንሻአላህ በክፍል 2 አጫዉታቹሀለሁ።

join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 2⃣

....... ሰሚራ ሽኩር

አባቢ አማንን ያገኘዉ የዛሬ አንድ አመት አ.አ እቃ ሊያመጣ በሄደበት ጊዜ ነበር መቸም አባቢ ነጋዴ ነዉ ብያቹሀለሁ የተለያዪ እቃዎችን ከአዲስ አበባ እያመጣ እዚህ ያከፋፍላል ያመጣቸዉ እቃዎችም ሲያልቁ በድጋሚ ወደ አ.አ ይሄዳል ።

ትዝ ይለኛል በመጀመሪያ ቀን አማን እኛ ቤት ሲመጣ እንዳሁኑ ዝም ያለ ሳይሆን ሱመያና ሙሀመድ እያለ ቀንም ማታም ይጮህ ነበር ምግብም አይወስድም፤ልብሷቹ እንዳሁኑ አልቆሸሹም ፤መልኩ በጣም የሚያምር ወንዳወንድ ነበረ። ገና እንዳየነዉ ደንግጠን አባቢ ከየት ነዉ ያመጣኸዉ?ማንና ምናችን ነዉ?.... እያልን የጥያቄ ማእበል ነበር ሁላችንም ያወረድንበት አባቢ ግን መልስ ሊሰጠን ፍቃደኛ አልነበረም ለኛ መልስ ከመስጠት ይልቅ አማንን እጂና እግሩን በሰንሰለት አስሮ ካስቀመጠዉ ቡኋላ የተለያዩ ቁርአን የሚቀሩ ኡስታዞችን ሰብስቦ ቀንም ማታም ለተከታታይ ወራት አስቀራበት ነገር ግን ለዉጥ የለም ፀባዩ ይሄ ነዉ ለማለት ግራ ነበር የሚያጋባ መጮህ፤ማልቀስ"ሱመያ ሙሀመድ....እባካቹህ ልቀቁኝ ልሂድ "የሚሉ ቃላትን ነበር የሚደጋግም ነገሩ ሁላችንንም ግራ አጋብቶን አስፈርቶን ነበርና አባቢን ደጋግመን ስንጠይቀዉ አባቢም እንዲህ በማለት መልስ ሰጠን"ልጆቸ ያመጣሁት ልጂ ስሙ አማን ይባላል።
እኔና እሱ የተገናኘነዉ አ.አ በተደጋጋሚ እቃዎችን ላስጭን በሄድኩበት ሰአት ነዉ በቃ እዛ በረንዳ ሲያድር አየሁት ይዠዉ መጣሁ"ብሎ ዝም አለ እኔም ነገሩ ግራ ሲገባኝ አባቢ ግን በቃ በረንዳ ሲያድር ስላየኸዉ ብቻ ነዉ ያመጣሀዉ? ስል ጥያቄየን አነሳሁ ሪሀናም"አባቢ ተዉ አትዋሸን እንደዛ ከሆነማ በረንዳ የሚያድር እሱ ብቻ ነዉ እንዴ ብዙዎች አሉ አይደል ለምን እሱን ብቻ ለይተህ አመጣኸዉ"ስትል ቀጠለች እማየም "እንኳን ለማታዉቀዉ ለምታቀዉም ይሄን ያህል እንክብካቤ ስታደርግ አይቸህ አላቅም አይ!የሆነ የደበከን ነገርማ አለ" ብላ ፈገግ አለች አይ አማየ ፍቅር የሆነች እናትኮ ናት ለባሏ ደግሞ ታማኝ ሲበዛ ተወዳጂ ብቻ የነሱ ፍቅር በጣም ያስቀናል አንዳንዴ እማየና አባቢ በኛ ምክንያት ይጋጫሉ ነገር ግን ሲታረቁ አምስት ደቂቃ አይቆዩም ገና ከቤት ወጥተን ስንገባ እየተሰሳቁ ነዉ የምናገኛቸዉ ከባድ ፀብ ለራሱ ቤት ዉስጥ ሲፈጠር ማንም ከሱም ከሷም ቤተሰቦች ከጓረቢት እኛም ማንም ሰዉ መጣላታቸዉን ሳያቅ እነሱ ተወያይተዉ ይፈቱታል።

ግን ዉዶቸ በትዳር ዉስጥ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ሌላ የዉጭ ሰዉ እንዲሰማ ማድረግ ተገቢ ነዉ ትላላቹህ? ሚስት በሁለቶች መካከል ግጪት ሲፈጠር የባልን ሚስጥር ለቤተሰቦቿ፤ለጓደኞቿ አሳልፋ መናገር ተገቢ ነዉ? ባልስ የሚስቱን ሚስጥር ለማንም ቢሆን መናገር አለበት? መልሳቹህ አለበት ወይም የለበትም ሊሆን ይችላል ያዉ እንደግጭቱ ክብደት ይወሰናል ነገር ግን ማንኛዉንም ግጭትና ሚስጥር ለማንም አሳልፈን የምንናገር ከሆነ እመኑኝ እንዲህ አይነቱ ትዳር ጭቅጭቅ የበዛበት፤እምነት የሌለበትና እድሜዉ አጭር የሆነ ትዳር ነዉ አትጠራጠሩ። ምናልባት በትዳር ዉስጥ ስንገባ ስለ ትዳር ብዙ የማናቅ ከሆነ ምን ቢሆን ይሆናል! ካልሆነም ይቀራል! እንላለን ግን እንዲህ አይነቱ ንግግር ትክክል አይደለም። ልጂ ከተወለደ ቡኋላ መባል የለበትም ምናልባት እኛ አንጎዳም ይሆናል ሁለት በሬዎች ሲጣሉ የሚጎዳዉ ሳሩ ነዉ እንደሳሩ ሁሉ የሚጎዱ የተወለዱት ልጆች ናቸዉ። የአባት ወይም የእናት ፍቅር ሳያገኙ ሁሌም በፍቅር ተቃጥለዉ ነዉ የሚያድጉት ሁሌም ከጓደኞቻቸዉ በታች የሆነ የጎደላቸዉ ነገር እንዳለ ይሰማቸዋል ስለዚህ ዉዶቸ ጋብቻ ዉስጥ ከገባቹህ የማይሆን ከሆነ ልጂ ከመዉለዳቹህ በፊት በሰላም ተለያዩ ከወለዳቹህ ቡኋላ ግን ለመለያየት በጣም ከባድ ነዉ ቢቻል ባትለያዩ ደስ ይላል። አይ የኔ ነገር! አባቢ እንዴት አማንን እንዳገኘዉ እያወራ እኔ በሀሳብ ተጓዝኩ ።


አባቢ ንግግሩን ቀጠለ""እንግዲህ አማንን እንዴት እንዳገኘሁት ንገረኝ ካላቹህኝ ልንገራቹህ ልብ ብላቹህ ስሙኝ መቸም እኔ አባታቹህ በጣም ችኩል እንደሆንኩ ታቃላቹህ" ብሎ ወደኛ ዞር አለ አወ አባቢ ሲበዛ ችኩል ነዉ ይሄም ደካማ ጎኑ ነዉ ብዙ ጊዜ አሁን የያዛት አሮጌ መኪና አለች ታላቅ ወንድሙ ነዉ አዲስ መኪና ሲገዛ አሮጌዋን ለአባቢ በስጦታ መልክ የሰጠዉ
መቸም በዝች መኪና ያልተገጨ የሰፈር ዉሻና ድመት የለም ሁሌም አትቸኩል ተረጋጋ ብንለዉም አይሰማንም እሽ ይላል ገጪቶ ይመጣል።
.... አ.አ እቃ ሊያስጭንም ከሄደ በዝች መኪና ነዉ የሚሄድ። "ታስታዉሳላቹህ የዛሬ አመት ወይም ሁለት አመት አካባቢ እቃ ላስጭን ሂጀ እቃዉ ከዉጭ አልመጣም እቆያለሁ ብየ ወር የቆየሁበት ጊዜ"ሲል ጠየቀን እኛም በአንድነት አወ እንዴት የዛኔ እንደናፈከን ነበርኮ መቸም አንረሳዉም ።


...... አባቢ የግድ ካልሆነበት ከቤት ዉጭ የትም አያድርም ግድ እንኳን ከሆነ ሁለት ወይም ሶስት ቀናትን እንጂ ከዚህ በላይ ከኛ ተለያቶ አያድርም። አባቢ ንግግሩን ቀጠለ"ካስታወሳቹህ ጥሩ ያኔ እቃዉ ከዉጭ ስላልመጣ እቆያለሁ ያልኳቹህ እዉነቴን አልነበረም ያኔ ወር የቆየሁኝ የአስራ
አምስት አመት ልጂ ላይ የመኪና አደጋ አድርሸ ነዉ" በማለት አንገቱን ወደ መሬት ደፍቶ ያን ጊዜ በሀዘን ማስታወስ ጀመረ።ሁላችም ደንግጠን ኧረ አባቢ ምንድን ነዉ የምታወራ በማለት ተንጫጫን አባየም "ዝም ብላቹህ ስሙኝ ጥያቄቹህን ስጨርስ" ብሎ ያን ጊዜ በማስታወስ ንግግሩን ቀጠለ "ያኔ በጣም ከባድ ጊዜ ነበር ያሳለፍኩኝ ግን አልሀምዱሊላህ አላህ አማንን ጥሎልኝ ከዛ ጭንቀት ወጣሁኝ"አለ ሁላችንም ግራ ገብቶን እንዴት ይሄ ለራሱ ያልሆነ የአምሮ በሽተኛ አንተን ከጭንቅ ያወጣሀል ስንል ጠየቅነዉ አባቢም""ያኔ አስታዉሳለሁ እሁድ ቀን ወደ ስምንስ ሰአት አካባቢ ነበር ወንድሜ ሰግጀ ስጨርስ ደዉሎ ምሳ ቀርቦ እየጠበቀኝ እንደሆነ የነገረኝ እኔም አልቆይም መጣሁ ብየዉ ይህችን አሮጌ መኪና ይዠ ወደ ወንድሜ ቤት እየሄድኩኝ ከመሀል አንድ የአስራ አምስት አመት ልጂ ከፊት ለፊት ሳይክል ይዞ እየመጣ በቀኝ በኩል ደግሞ አማን እየመጣ ነበር።
....ሁለቱም ከፊት ለፊት ሲመጡ በመሀል ሊገቡብኝ ነዉ ቶሎ ብየ መኪናየን ላቆም ስል የመኪናየ ፊሬን እንቢ አለኝ ወደ ቀኝ እንዳልሄድ አማን ወደ ግራ እንዳልሄድ ህፃኑን ልጂ ልገጨዉ ነዉ ዞረብኝ እጀም ተንቀጠቀጠ አልታዘዝ አለኝ ትንፋሽ አጠረኝ ከዛ የህፃኑ ልጂ ሳይክል ከኔ የመኪና ጎማ ስር ገባ ልጁም ከሳይክሉ ወድቆ አጠገቡ የነበረ ድንጋይ ጋር ራሱ ተጋጭቶ ደሙ እንደጎርፍ መፍሰስ ጀመረ እኔም የተወሰነ ተጎዳሁኝ ነገር ግን የኔ ህመም ሳይሆን የልጁ ሂወት ነበር ያሳሰበኝ በጣም ደንግጨ አይኔ ለደቂቃዎች ከልጁ ደም አልተነቀለም ነበር ከመሀል አማን እየሮጠ መጦ የልጁን ራስ ቀና ሲያደርገዉ የለበሰዉ ነጭ ሸሚዝ በቀይ ደም ተጨማለቀ።

ልጁም ራሱን ትልቅ ድንጋይ ነበርና ያገኘዉ ራሱ ተተርትሮ ደሙ ይፈሳል ከዛ አማን....."" ሁላችንም ምስጥ ብለን እያዳመጥን ከመሀል የአባቢ ስል ጠራ ዉይ! በአሁኑ ሰአት ማን ይሆን የደወለ ብየ የአባቢን አፍ አፍ ማየት ጀመርኩ ጓደኞቹ ናቸዉ መሰል ቆይ መጠሁ ብሎን ስልክ እያወራ ከቤት ወጣ አባቢ ወደ ቤት መጦ ታሪኩን ሲቀጥል እኔም እቀጥላለሁ ግን አማን ምን ይሆን ከዛ ቡሀላ ያደረገ?



ኢንሻአላህ በቀጣይ ክፍል የምናየዉ ይሆናል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል3⃣
........ ሰሚራ ሽኩር

.............""ልጁ ራሱን ትልቅ ድንጋይ ነበረና ያገኘዉ ራሱን መቶት ደሙ ይፈሳል ከዛ አማን እየሮጠ መጣና "ራሱን የምጠቀልልበት ነገር ስጠኝ!"እያለ ይጮህ ጀመር እኔ ደንግጨ ቁሜ ማየት ጀመርኩ ነገር ግን አማን "አትሰማም! ደሙኮ እየፈሰሰ ነዉ የሆነ ልብስ ነገርም ቢሆን አቀብለኝ መጥፎ ቦታ ነዉ የጎዳሀዉ !"እያለ ሲጮህብኝ ብንን ብየ ልብስ ነገር መፈለግ ጀመርኩ አማንም "በቃ ተወዉና ና! የኔን ሸሚዝ ቀድጀ አስሬለታለሁ ቢያንስ የሚፈሰዉን ደም ይቀንሰዋል" አለኝ እኔም እሽ ብየ ለወንድሜ ደዉየ የተፈጠረዉን ነገር አስረዳሁት ወንድሜም መጣሁ እዘዉ ቦታ ቆየኝ ብሎኝ በፍጥነት መጣ ከዛ ከአማን ጋር ልጁን ይዘነዉ ወደ ሆስፒታል ከወንድሜ ጋር ሄድን""


ቀጣዩን ለማወቅ በጓጓ አንደበቷ ሪሀና ከመሀል ከዛስ ምን ተፈጠረ አባቢ! ስትል ጠየቀች አባቢም"ከዛ ሆስፒታል እንደደረስን አማን የተፈጠረዉን አደጋ ለዶክተሮቹ ነግሮቸዉ ለህክምና የተዘጋጀዉ ክላስ አብሮቸዉ ገባ።
ነገሩ በጣም ግራ ገባኝ ብዙም ስለህክምና ባላቅም ቀዶ ጥገና የሚደረግበት፤ ቁስሎች የሚሰፉበት ክፍል.... መግባት የሚችሉ ዶክተሮቹ ብቻ ነበሩ ነገር ግን ለምን አማን ከነሱ ጋር ሲያወራ ቆይቶ አብሯቸዉ ገባ??? አላቅም ነገር ግን ልጁ ቶሎ የህክምና እርዳታ ተደረጎለት ቤተሰቦቹም መጠዉ ከተረጋጉ ቡኋላ ለአንድ ወር ያህል ቤቱ እየተመላለስኩ ስለጤንነቱ ተከታትየ ስለ ጤናዉ እርግጠኛ ስሆን ወደዚህ ተመለስኩኝ "
እማየ በደነገጠ አንደበቷ" እና እዚህ ከመምጣትህ በፊት አማን እንደዛ አግዞህ ምን አልከዉ ማለቴ እንዴት አመሰገንከዉ"አለች የሷ ብቻ ሳይሆን የኔም ጥያቄ ነበር።

አባቢም"" ልጁ ከነቃ ቡሀላ አማንን ሆስፒታል በአይኔም በእግሬም ተዘዋዉሬ ብፈልገዉ አጣሁት። ከሆስፒታል ዉጭም እኔና ወንድሜ ለአንድ ወር ያህል ፈለግነዉ ነገር ግን ልናገኘዉ አልቻልንም። በመጨረሻም በመጀመሪያም አማንን ያገኘሁት ያች አደጋ ባደረስኩበት ቀን ነበር ከዛ ቡኋላ ማግኘት አልቻልኩም አፈላለጉት አፈላለኩት....አጣሁት።


ሁሌም በዱአየ አማንን አስታዉሰዋለሁ አንድም ቀን ረስቸዉ አላቅም "የዛኔ የልጁን ራስ ባይጠቀልልለትና ደሙን መቀነስ ባይችል ምናልባትም ብዙ ደም ፈሶት የልጁ ሂወት አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችል ነበር" በማለት ዶክተሮቹ አማንን አድንቀዉታል የምር አማን ባልኖረ የልጁ ሂወት አልፎ እኔም አሁን ከናንተ ጋር ባልነበርኩ"ብሎ በማዘን ለደቂቃዎች ዝም አለ።

ሪሀና ፈጠን ብላ "እንዴ! አባቢ ምንድን ነዉ የምታወራ እኔ አልገባኝም ቆይ አገኘኸዉ አገዘህ ከዛ ላመሰግነዉ ፈልጌዉ አጣሁት አልክ እሽ እንዴት በድጋሚ አግኝተኸዉ እዚህ እኛጋ ልታመጣዉ ቻልክ? ስሙንስ አማን እንደሆነ እንዴት ልታቅ ቻልክ? እንዴትስ ሊያብድ እንደዚህ ሊሆን ቻለ?"....... በማለት የጥያቄ ማእበል አወረደችበት
አባቢም"ሪሁየ መች ንግግሬን ጨረስኩ ገና እኮ ነኝ እይዉልሽ የኔ ልጂ ያኔ ለወር ፈልጌዉ ሳጠዉ በጣም አዝኜ ነበር እናንተም ትደነግጣላቹህ ብየ አደጋዉን አልነገርኳቹህም።
....... እዚህ ከመጣሁ ከአመት ቡሀላ ወንድሜ ደዉሎ "አማንን አንድ ቦታ አየሁት ነገር ግን እሱ መሆኑን እርግጠኛ አይደለሁም ሁሉ ነገሩ ተቀይሮል አብዶል! .....በቃ ስትመጣ ታየዋለህ ከቻልክ በፍጥነት ለመምጣት ሞክር!" አለኝ እኔም በጣም ደነገጥኩኝ በመገኘቱ ደስ አለኝ ነገር ግን ወንድሜ ያለዉን አላመንኩም ምናልባት ተመሳሳይ ሰዉ አይቶ ይሆናል .....ብቻ ሰሞኑን እቃም እያለቀብኝ ስለሆነ መሄዴ አይቀርም የዛኔ ማየትና ማረጋገጥ እችላለሁ ብየ ወንድሜ በነገረኝ በሶስተኛ ቀን ወደ አዲስ አበባ አቃ ላመጣ ነዉ ብያቹህ ሄድኩኝ ........


ከዛስ አማንን አገኘዉ?..... ኢንሻአላህ በቀጣይ ክፍል የምናየዉ ይሆናል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
ወራራ እዉነት
ክፍል 4⃣

..... ሰሚራ ሽኩር

........ከዛ እቃ ላመጣ ነዉ ብያቹህ ወደ አዲስ አበባ ሄድኩኝ። ወንድሜም የኔን መምጣት በጉጉት ይጠብቅ ነበርና ገና ከመሄዴ ፈጠን ብሎ "ና! አማንን ላሳይህ" በማለት ወደ አንድ የንግድ መካዘን በረንዳ ወሰደኝ አስታዉሳለሁ ያኔ ያየሁትን ማየት ነበር ያቃተኝ የራሴን አይን አላምን አልኩኝ አማን የመጀመሪያ ጊዜ ሳየዉ አለባበሱ ጥሩ የሚባል ፤ መልኩ በጣም የሚያምር ቀይ ነበር።
........ አሁን ግን የብርዱ ብዛት አጥቁሮታል እሱ መሆኑ እንኳን እስከማይለይ ድረስ ቀጥኖል፤ ፀጉሩ ተንጨብሮ ያስፈራራል፤የሚመገበዉ ከተለያዩ የቆሻሻ ገንዳዎች ዉስጥ የወዳደቁ ምግቦችን ነዉ። በዛ ላይ በአንድ እጁ ጫት በአንድ እጁ ሲጋራ ይዞ ያጨሳል ፤ይቅማል ..... ያየሁትን አላምን አልኩኝ በአንድ አመት ዉስጥ ምን አግኝቶት ይሆን ብየ አሰብኩ! ተጠግቸ አስታወስከኝ ምን ሁነህ ነዉ?ምንድን ነዉ የነካህ አልኩት ነገር ግን መልስ አልሰጠኝም ዝም ብሎ በፍቅር አይኑ እኔን መመልከት ጀመረ እኔም ትቸዉ ለመሄድ አልቻልኩም አሳዘነኝ።


.......ግን ማን ይሆን እንዲያብድ ያደረገዉ?ምን አደረጋቸዉ? ምን አይነት ዘመን ነዉ!....... እያልኩ ከራሴ ጋር መከራከር ጀመርኩ
..... እስከማታ ዝም ብየ ቁሜ ሁኔታዉን አየሁት በጣም አዘንኩ ከዛ ወንድሜ መጦ "ና እንጂ እዚህ አብረኸዉ ልታድር ነዉ እንዴ! ከመጣህኮ ምግብ አልበላህም ና!በል እንሂድ ቅድም እንሂድ ብልህ እንቢ አልከኝ እኔ ደርሸ መጣሁ ና! እየመሸ ነዉ መቅሪብም አዛን ሊል ነዉ " አለኝ እኔም በሁኔታዉ ተገርሜ አጃኢብ እያልኩ ወደ ወንድሜ ቤት ሄድኩኝ ነገር ግን ያን ቀን መተኛት አልቻልኩም ገና ልተኛ አይኔን ስጨፍን አማን ይመጣብኛል ነግቶም አማን ላይ ምግብ ይዤ ሂጀ ሳወራዉ፤ ሳበላዉ ቆይቸ እመጣለሁ ማታ ማታ ለሶስት ተከታታይ ቀናቶች ከአማን ጋር እየሆንኩ አንድ አይነት ህልም አንድ አይነት ቅዠት አላስተኛኝ አለ።


በአራተኛዉ ቀን እቃየን አስጭኔ አማንን ልሰናበተዉ ስሄድ አማን አጀን ጥቅጥቅ አርጎ ይዞ አለቀኝ አለ።እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም ቁጭ ብየ አማኔ ተመልሸኮ እመጣለሁ አልኩት ነገር ግን እጀን ለመልቀቅ ፍቃደኛ አልነበረም አዘንኩ ምን እንደማረግ ግራ ገባኝ ምናልባት በህክምና ብሞክር በሽታዉ ይለቀዉ ይሆን ብየ ሀኪም ቤት ይዠዉ ሄድኩኝ ራጂ ተነሳ ሙሉ ምርመራ ተደረገለትና ለሶስት ወር መድሀኒት ሰጡት።


........ አንድ ዶክተር ወደኔ መጣና "መድሀኒቱ በጣም ከባድ ነዉ ምግብ በደንብ መመገብ አለበት ደሞ ተከታትሎ የሚሰጠዉ ሰዉ ያስፈልገዋል።መድሀኒቱን ካላቋረጠ ጊዜ ይወስድብህ ይሆናል እንጂ ይዳናል እንዲህ አይነት በሽተኞች ብዙ ጊዜ ሀኪም ቤታችን መጠዋል ብዙዎቹም በጊዜ ሂደት ሊድኑ ችለዋል አይዞህ "አለኝ
........ግን ዳ.ር እንዲህ አይነት በሽታ እንዴት ሊከሰት ይችላል ብየ ጠየቁት.......
ዳክተሩም "እይዉልህ የኔ ወንድም ይሄ በሽታ በብዙ ምክንያቶች ይፈጠራል ሁሉም ሰዎች ሊያብዱ የሚችሉት አንድም ከጎደኛ፤ከቤተሰብ፤ከጎረቢት.....ከመሳሰሉ ሰዎች ለልጁ ባላቸዉ ጥላቻ/ምቀኝነት ማለትም በተለያዩ ነገሮች የበለጣቸዉ ሲመስላቸዉ ለምን በለጠን ብለዉ በተለያዩ ምግቦችም ሆነ በሌላ ነገሮች ሊያሳብዱ የሚችሉ መድሀኒቶችን ሰጠዉ ራሳቸዉን ስተዉ እንዲያብዱ ያደርጓቸዋል።
በሌላ በኩልም አዋቂ ነኝ የሚሉ ሰዎች(ጠንቋዮች) ጋር ሂደዉ በልጁ አስደግመዉ እንዲያብድ ያደርጋሉ።

ሁለተኛዉ ደግሞ ሰዎች እንዲያብዱ የሚያደርጋቸዉ ሂወት ብዙ ጊዜ መራራ ናት!የሰዉ ልጆች ስንባል ስሜቲዊ ነን ቶሎ እንናደዳለን በተለይ የለፋንበት ገንዘብም ሆነ ሌላ ነገር ሲከስር፤ባመናቸዉ ሰዎች ስንከዳ፤የምንወዳቸዉ ሰዎች ሲርቁን/ሲሞቱብን፤ኑሮ ምርርር ሲለን፤ ሁሉም ነገር ሲደብረን............ሊሆን ይችላል
ብቻ ራሱን እንዳያጠፋ ተከታተለዉ

የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ
. ራስን ማጥፋት (SUllDE)
ራስን ማጥፋት ሁል ጊዜ በሚባል ሁኔታ የአእምሮ ዉጤት ሲሆን ብዙዉን ጊዜ ድብርት ትልቁን ሚና ይጫወታል
አንዳንድ ሰዎች ራስን የመግደል ሀሳቦች አሏቸዉ በፍፁም እርምጃ አይወስዱም።አንዳንዶቹ ደግሞ እቅዶችን ለቀናት ለሳምንቶች ወይም ከአመታት በፊትም ያወጣሉ ከመተግበራቸዉ በፊት ሌሎች በድንገት ያለ ቅድመ ዝግጂት ያጠፋሉ።
በአለም ዙርያ በየሰአቱ 80ሰዎች ራሳቸዉን ያጠፋሉ። አብዛሀኛዉ ወጣቶች ሲሆኑ ከጠቅላላዉ የህዝብ ብዛት ወደ 40% የሚሆኑት በሂወት ዘመናቸዉ ቢያንስ አንድ ጊዜ የመሞት ምኞት ይኖራቸዋል።
የአለም የጤና ድርጂት እንደገመተዉ በየአመቱ በየ 40ሴኮንድ አንድ ሰዉ ራሱን ያጠፋል።
.

ስለዚህ ራሱን እንዳያጠፋ ክትትል ያስፈልገዋል።
....እኛ አካብደን እያየነዉ ነዉ እንጂ ቀላል በሽታ ነዉ በቁርአኑም፤በመድሀኒቱም ጥሩ ክትትል ከተደረገለት ባጭር ጊዜ ዉስጥ የመዳን እድሉ በጣም ከፍተኛ ነዉ"አለኝ።

.....እንዴት አድርጌ ግራ ገባኝ እዚህ አዲስ አበባ ብሆን ችግር የለዉም እየተከታተልኩ መድሀኒቱን እሰጠዉ ነበር በየኡስታዞችም እየወሰድኩ አስቀራበት ነበር።
...... ግን እዚህ አይደለሁም ግራ ገባኝ ምናልባት መድሀኒቱን እየተከታተለ ይሰጠዉ እንደሆነ ብየ ለወንድሜ አማከርኩት ወንድሜም በንቀት አይኑ እየተመለከተኝ "ያማሀል እንዴ ዘመዳችን አይደለም አናዉቀዉም ባለፈዉ በዋለልህ ዉለታ ብቻ እብድ ልይዝልህ ነዉ ኧረ አልችልም እኔ ስንት ስራ ያለብኝ ሰዉ ነኝ!"......አለኝ

ከአባቢ ንግግር ልመልሳቹህና
አንድ ጊዜ ቀስተኞች ሬሳ ተሸክመዉ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በተቀመጡበት ፊት ያልፋሉ ። የአላህ መልክተኛም(ሰ.ዐ.ወ) ተነስተዉ ይቆማሉ። ከአጠገባቸዉ የነበሩ ተከታዮቻቸዉ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የአይሁድ ሬሳ ነዉኮ" ይሏቸዋል። እርሳቸዉም ፦ የሰዉ ልጆች አይደለንምን?" ሲሉ መለሱ (ቡኻሪና ሙስሊም) እንግዲህ አስቡት በሂወት ለሌለ ሰዉ ይሄን ያህል ክብር ከተሰጠዉ ሂወት ላላዉ ሰዉስ ምን ያህል ክብር ይገባዋል???


አላህ በተከበረዉ ቁዱስ ቁርአኑ ላይ "የብናኝ ክብደት ያክል መልካምን የሰራ ሰዉ ያገኘዋል። የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሰራ ሰዉ ያገኘዋል"(አል-ዘልዘላ፦7-8) ብሎናል የአባቢ ወንድም በጣም ተሰስቷል አልችልም ማለት የለበትም ነበር ልጆች አሉት ነገ ምን እንደሚፈጠር አያቅም።
......ጥሩም ሰራ ሰራን መጥፎ ሁላችንም እንደየስራችን አላህ ይመነዳናል ትንሽ ናት ብለን የምንሰራት ጥሩ ስራ ምናልባትም ጀነት ለመግባት ሰበብ ትሆነን ይሆናል ትንሽ ናትም ብለን የምንሰራት ወንጀል ለጀሀነም ሰበብ ትሆነን ይሆናል ማን ያቃል!

አላህ እንዴት እንደፈጠረን ሲነግረን "ሰዉን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነዉ"(አጥ-ጢን፡4) ይላል
ሁላችንም ሰዉ ለመርዳት የግድ በደም፤በዘር፤በሀይማኖት ....የኛ ዘመድ መሆን አለበት ትላላቹህ?
ሁላችንም ሰዉ መሆናችን ዉብ ሁነን መፈጠራችን አያዛምደንም?
ሰዉን ለመርዳት ሰዉ መሆን ራሱ በቂ አይደለም?
ቆይ የትኛዉ ሰዉ ነዉ ወዶ የሚያብደዉ? የትኛዉ ሰዉ ነዉስ ከሚፈልገዉ ቤተሰብ የተፈጠረዉ?
የትኛዉ ሰዉ ነዉ የሚፈልገዉን መልክ፤ብሄር ፤ፆታ.....ይዞ የተፈጠረዉ......ሁላችንም አላህ በመረጠልን ፆታ፤ብሄር፤መልክ..... ዉብ አድርጎ ነዉ የተፈጠረን።
እዚጋ ከታሪኩ የመለስኳቹህ የአባቢ ወንድም ንግግሩ ስህተት ስለነበረበት ነዉ ።
ኢንሻአላህ በቀጣይ ክፍል የአባቢን ንግግር ካቆምንበት የምንቀጥል ይሆናል
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Isl
መራራ እዉነት
ክፍል 5⃣

...... ሰሚራ ሽኩር


..........."ያማሀል እንዴ ዘመዳችን አይደለም
አናዉቀዉም ባለፈዉ በዋለልህ ዉለታ ብቻ እብድ ልይዝልህ ነዉ ኧረ አልችልም እኔ ስንት ስራ ያለብኝ ሰዉ ነኝ.."አለኝ
የዛኔ የምለዉን አላቅም ብቻ ከወንድሜ ጋር ትንሽ ተጋጨን
..... የሰዉ ልጂ አይደል እንዴት እብድ ይላል ቢያንስ የአምሮ ታማሚ ይባላል! ደሞስ ጥሩም ሰራ መጥፎ አጂሩ ለራሱ ነዉ አይ የናት ሆድ ዝጉርጉር ይሉታል እንዲህ ነዉ። እያልኩ ብዙ አሰብኩኝ ከብዙ ሀሳብ ቡሀላም በቃ አማንን ይዜዉ መሄድ አለብኝ የነገን ማን ያቃል ሲሆን አላህ ብሎት ወደ ጤናዉ ይመለሳል ኢንሻአላህ
ካልሆነም አልጎዳም ከአላህ አጂር አገኝበታለሁ። ዉለታዉንም በትንሹም ቢሆን መክፈያ ይሆነኛል። ብየ ይዜዉ መጣሁ


ሁለተኛዉ ጥያቄሽ ደግሞ ስሙን እንዴት አወክ ነዉ
..... ስሙን ያወኩት የዛኔ ሀኪም ቤት እንዳለሁ አማንን ስፈልግ አጣሁት ከዛ ዳክተሮቹን ከኔ ጋር የመጣዉ ወጣት ከናንተ ጋር የገባዉ የት ሄደ? ስል ጠየቋቸዉ እነሱም ቶሎኮ ነዉ በታችኛዉ በር የወጣዉ ሲሉ መልስ ሰጡኝ እሽ ስልኩን ወይም አድራሻዉን ታዉቃላቹህ ስል ጥያቄየን ቀጠልኩ እነሱም ስሙ አማን እንደሚባል ነግሮናል ሌላ ነገር ግን ስለሱ አናቅም አሉኝ........ . .....ይሆዉ ነዉ እንግዲህ"

........ወላሂ እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም ቶሎ ከአባቢ አጠገብ ተነስቸ አማን ወዳለበት ክፍል ሮጥኩ....አማን አማን....ብየ መጣራት ጀመርኩ ወድያዉ አማን ተነስቶ የክፍሉን በር ከፈተልኝና በክፉ አይኑ ከፀጉሬ እስከ እግር ጥፍሬ ድረስ በትኩረት ተመለከተኝ።
ደነገጥኩ አይቸዉ እንደማላቅ አዲስ ሰዉ መሰለኝ....እንባዎቸ በጉንጮቸ እየወረዱ በተቆራረጠ ድምፅ አማን ይቅርታ አልኩት እሱ ግን መልስ አልሰጠኝም ጥሎኝ ወደ ዉስጥ ገብቶ ፍራሹ ላይ እግሩን ዘርግቶ ተቀመጠ እኔም ለመጀመሪያ ጊዜ ቀስ ብየ ለመግባት እየተንቀጠቀጥኩ ተከትየዉ ገብቸ አጠገቡ ቆምኩ ከዚህ በፊት ክፉሉ ገብቸ አይቸዉ አላቅም ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ገባሁ ።
...... ሁሌም ክፍሉን የሚያፀዳለት፤ምግቡን ፤መድሀኒቱን ሰአቱን ጠብቆ የሚሰጠዉ....... አባቢ ነዉ ።
ወላሂ ራሴን በጣም ጠላሁት እንዴት አንድ አመት ድረስ ጨቀንኩበት ሁሌም ሳየዉ ያሳዝነኛል በቃ!
አፌን ከመምጠጥ ዉጭ ምንም ያደረኩለት ነገር የለም እሱ ግን ለአባቢ ባለዉለታዉ ነዉ።
........እኔን ብሎ የህክምና ተማሪ!!!

እንዲሁ አጠገቡ ቁሜ ከራሴ ጋር ስከራከር ሪሀና መጣች።
እንባዋን በቀኝ እጇ እየጠረገች "አማኔ ወላሂ ይቅርታ እብዷ እኔ እንጂ አንተ አይደለህም ለአባቢ ባለዉለታዉ ነህ ያን ጊዜ አንተ ባትኖር የሚፈጠረዉን ማሰብ ይከብዳል .... እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ" አለችዉ እሱም በፍራት አይን አይናችንን እያየ አንገቱን ደፍቶ ዝም አለን።
ወድያዉኑ አባቢ መጥቶ "እናንተ ምንድን እያላቹህት ነዉ ኑ አታስጨንቁት" ብሎ ይዟን ወደ ቤት ገባና " እይዉላቹህ እንዲህ አይደለም ይቅርታ የምትጠይቁም" ብሎ ነገሩን ሳይጨርስ ሪሀና ባዘነ አንደበቷ "እና እንዴት ነዉ የምንጠይቀዉ?
....... ግንኮ አባቢ እኛ ሳንሆን አንተ ነህ ጥፋተኛዉ እስካሁን እንዴት እንዳገኘኸዉ ብትነግረን ምን አለበት ያን ያህል ጊዜ እባክህ እያልን ስንለምንህ"
........እሪሀና እዉነቷን ነዉ እኔ እንኳን ስንቴ ለምኘሀለሁ አባቢ ግን ለምን ዛሬ ነገርከን ስል ጠየቁት።
አባቢም ቆጣ ብሎ "ሁሉም ነገር ጊዜና ቦታ አለዉ ትዝ ይላቹሀል ያኔ አማኔን የመጀመሪያ ጊዜ እንዳመጣሁት ጓረቢቷቻችንና ጓደኞቸ ምን እያሉ እንደነበር ታስታዉሳላቹህ!?"

አወ እኔ በደንብ አስታዉሳለሁ ወላሂ ያኔ አባቢ ነግሮኝ በሆነ ከስንቱ ጋር እጣላ ነበር!።
.......አባቢ ያኔ አማንን እንዳመጠዉ ጓረቢቶቻችን "አይ!ወንዶች ሲባሉ አይታመኑም ይህኔ አማንን ካንዱ ወልዶት ይሆናል አሁን ቀን ሲጥለዉ ጉዱ ወጣ ምን ያድርግ ሲታመምበት ይዟት መጣ!" እያሉ ካለ ስሙ ስም ሲሰጡት......ጓደኞቹ ደግሞ እኛ ቤት ይመጡና አማንን ሲያዩት "ዉይ ግቢዉ በጣም ይሸታል ደሞ ከብት መሰለህ እንዴ የምታደልበዉ ሰዉኮ ነዉ ያዉም በሽተኛ!"እያሉ ያሾፉበት ነበር። እማየና አባቢ በትዳራቸዉ ተማምነዉ ተዋደዉ ስለሚኖሩ ማንም ምንም ቢል እማየ አባቢን ከሷ በላይ ታምነዋለች።ሁሌም "ምን አገባቹህ ልጁ ከሆነ የኔም ልጂ ነዉ"በማለት የጎረቢቶቿን አፍ ታዘጋቸዉ ነበር።
....እማየ በጣም ጠንካራ ሚስት ናት ይሄኔ ሌላ ሰዉ በሆነ ያሉትን ሰምቶ ትዳራቸዉ ፈርሶ እኛም በየቦታዉ በወደቅን ነበር ።

"ልጆቸ ያኔ ብነግራቹህ ምናልባትም ከብዙዎቹ ጋር ትጣሉ ነበር ደሞ በኔ ምን ያህል እምነት እንዳላቹህ ማወቅ እፈልግ ነበር .........ብቻ አላቅም ጥሩ ጊዜ ያልኩት አማን ወደ ጤናዉ ተመልሶ እሱ በአንደበቱ ይነግራቹሀል ብየ ነበር ወደ ጤናዉ ለመመለስ ዘገየ የናንተም ጥያቄ ቀን በቀን ሲሆንብኝ ነገርኳቹህ እንግዲህ ካጠፋሁኝም አዉፍ በሉኝ"
ሪሀና "ወይ አባቢ ምንም አላጠፋህም እንኳንም አባቴ ነህ!ወላሂ አስደሰትከኝ"ብላ ተጠመጠመችበት።
እኔም በሁኔታዉ አጃኢብ እያልኩ አባቢ ተንግዲህ የአማንን መድሀኒት እኔ እየተከታተልኩ እሰጠዋለሁ ምንም እንኳን እኔን ባይወደኝም እንዲቀርበኝና ይቅርታየን እንዲቀበለኝ እጥራለሁ አልኩት አባቢም
"እኔ አርፍጀም ቢሆን የተረዳሁት አንድ ሰዉ ብቻዉን ምንም ማድረግ እንደማይችል ነዉ አንድ እጂ ብቻዉን ማጨብጨብ እንደማይችለዉ!ብቻየን አመት ለፈሁ እንደሚድንም እርግጠኛ ነበርኩ ግን አልተሳካልኝም በርግጥ አላሀምዱሊላህ በጣም ብዙ ለዉጦችን አሳይቷል አሁን ዝምታዉን መስበር ነዉ ያቃተኝ እንዲያወራ ደግሞ ለማድረግ የናንተን እገዛ እሻለሁ" አለን
በደስታ እንዴ አባቢ ብቻ ይቅርታ ያድርግልንና ለመዳን አላህ ያብቃዉ እንጂ የፈለከዉን እናደርጋለን አልኩኝ
አባቢም ደስ በሚል ሞቅ ባለ ድምፅ "እሽ
በዛሬዋ ቀን ሁላቹህም ለራሳቹህ ቃል ግቡ ሁሌም ከአማን አጠገብ በመሆን በምችለዉ ሀቅም አግዘዋለሁ በሉ"አለን እኔም ፤እማየም፤ሪሀናም፤ ሁላችንም ቃል ገባን አማንን በምንችለዉ ሀቅም ልንከባከዉ።

የዛሬዋ ቀን ነበረች ሁላችንንም አማን ጥግ ያሰባሰበችን ሁላችንም አማን አጠገብ በፍራቻ ተቀመጥን አባቢ ከአማን በቀኝ በኩል ሲቀመጥ እማየ ከአማን ከግራ በኩል ተቀመጠች እኔ ከእማየ አጠገብ ሪሀና ደግሞ ከአባቢ አጠገብ ተቀመጥን።
አባቢ "አማን አብሽር!ትድናለህ እኛ ሁሌም ከአጠገብህ ነን!" ሲለዉ እኔ ደግሞ አማኔ እኔና ሪሀና እህቶችህ ነን አንተ ወንድማችን ነህ አባቢ አባትህ እማየ ደግሞ እናትህ ናት ከእንግዲህ እኛን በክፉ አይንህ እያየህ አትራቀን እኛ ያንተን ጤና እንጂ ሌላን አንፈልግም እባክህ አማን መልስ እንኳን ስጠን ዝም አትበል አታስጨንቀን የኛን ተወዉ አባቢ አመት ሙሉ ሲለፋ አያሳዝንህም አልኩት አማን ግን መልስ የለም ዝምታ ብቻ

ሁላችንንም ያስጨነቀን ይሄ ዝምታዉ ነዉ ዝምታዉን ደግሞ ልንሰብረዉ የምንችለዉ ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ስንችል ነዉ።

ምንድን ነዉ ድርሻችን ኢንሻአላህ በቀጣዩ ክፍል የምናየዉ ይሆናል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 6⃣

....... ሰሚራ ሽኩር

ዝምታዉን ለመስበር እኔ ሁሌም አጠገቡ ሁኜ መጽሀፎችን ለሱ ማንበብ ጀመርኩ የማነብለት መፀሀፍም ራሳቸዉን በተለያዩ ነገሮች ስተዉ /አብደዉ ወደራሳቸዉ የተመለሱ ሰዎች፤አነቃቂ ፁህፎች፤አስቂኝ ቀልዶች፤የሚገርሙ የቁርአን ምእራፎችን......ብቻ ቢሰማኝም ባይሰማኝም እለፈልፍለሁ ለሱ ብየ የማነበዉ ለኔ ብዙ ጠቀመኝ።

ሪሀና ደግሞ በትወና ላይ በጣም ጎበዝ ናት አንዴ ዶክተር ሁና አንዴ ተማሪ አንዴ አባት እናት ፤ሚስት......ሁና ትተዉናለች አንዳንዴ አማን ሁኔታዋን እያየ ፈገግ ይላል የዚህን ጊዜ ሪሀና 30ደቂቃ ልትተዉን ያለችዉን ወደ አንድ ሰአት ታራዝመዋለች።

አባቢ ደግሞ በስንት ስቃይ ሰዉነቱን አጥቦ ልብሱን ቀይሮለት የተለያዩ ዘና የሚያደርጉ ቦታዎች ላይ ይወስድና እንዲዝናና ያደርጋል።

እማየ ምግቡን በስርአት እያዘጋጀች ትሰጠዋለች የተለያዪ አስተማሪ ታሪኳችን ትነግረዋለች ትመክረዋች......ብቻ ሁላችንም ለአንድ አመት ለፋን እኛ ቤት ከመጣ ሁለተኛ አመቱን ያዘ አሁን ብዙ ለዉጥ አለዉ።

አማን በኛና በዶክተሮች ጥረት ብዙ ነገሩ ቢቀየርም አባቢ ግን የመድሀኒቱን ወጭ አልቻለዉም አሁን እንደሙም በጣም የሚወዳትን መኪና ለመሸጥ ተገዶ ሸጣት ንግዱም እንደድሮዉ ጥሩ አይደለም በጣም ቀዝቅዟል በዚህ ከቀጠለ ወደፊት የአማን መድሀኒትና የኛ የትምህርት ቤት ክፍያ ከየት እንደሚመጣ አላቅም እኔ ይሄን ሳስበዉ እፈራለሁ።
...... አባቢ ሁሌም በየሶስት ወሩ አ.አ እየሄደ መድሀኒቱን ገዝቶ የአማን ጤናዉ በምን ሁኔታ እንደሆነ ቸክ አድርጎ ይመጣል ዶክተሮቹ በትንሽ ጊዜ ወደ ጤናዉ እንደሚመለስ እርግጠኛ ሁነዉ ለአባቢ ነግረዉታል ብቻ የኛ ተስፋ በዶክተሮቹ ሳይሆን በአላህ ላይ
ነዉ አላህ ቶሎ ወደ ጤናዉ እንዲመልሰዉ የሁላችንም ዱአ ነዉ።


........ ጁመአ ቀን አማን በጠዋት ተነስቶ ፀሀዮ ላይ ተቀምጦል እኔ ደግሞ ከእንቅልፌ ተነስቸ አይኔን እያሻሸሁ በአንድ እጀ ዉሀ ይዜ ከቤት ስወጣ አማንን ደህናክ አደር አማን አልኩት ለምዶብኝ ነዉ እንጂ መልስ ይሰጠኛል ብየ አልነበረም ሁሌም ብጠይቀዉ ፤ባወራዉም ከዝምታ ዉጭ መልስ አይሰጠኝም ለነገሩ ዝምታም ባይገባኝ ነዉ እንጂ ለሱ መልስ ነዉ። አወ ዝምታ ላወቀዉ ጥሩ መልስ ነዉ እኔም ይሄን ስለማዉቅ ለጥያቄየ የቃል መልስ ሳልሰማ እንግባባለን ዛሬ ግን አማንን ደህና አደርክ አማን ስለዉ"አልሀምዱሊላህ"ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ተነፈሰ አላመንኩም ከኋላየ ሌላ ሰዉ መልስ የሰጠኝ መስሎኝ ዞርኩ ከአማን ዉጭ ሌላ ሰዉ የለም ጆሮየን ጭራሽ አላምን ብየ በድጋሚ ድምፄን ጮክ አድርጌ አማኔ ደህና አደርክ ስል ጠየቁት ለሰስ ባለ ድምፅ "ደህና" አለኝ የምሰማዉን አላምን ብየ በድጋሚ ጠየቁት አሁንም "ደህና" አለኝ የዚህን ጊዜ አፍጥጨ ተመለከትኩት ምንም አላምን አልኩኝ እሱ ነዉ ወይስ ጆሮየ ነዉ ብየ ግራ እንደተጋባሁ አባቢ መጦ ምን እየሰራሽ ነዉ ሀናኔ አለኝ እባቢ አባቢ አባቢ........አአአአአአአ አማን አማን እንትን አማን......መናገር አቃተኝ አማን አወራ ብሎ ማመን ከባድ ነዉ እንደ እብድ የመጣ አካባቢ ይለፈልፍል እንጂ በስረአት አንድ ቃል አዉርቶ አያቅም ይሄዉ ሁለት አመት ሆነዉ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ አልሀምዱሊላህ ሲል እንዴት ልመን ......

አባቢ ምንድን ነዉ የምታወሪ አማን ምን ሆነ ሲል ጠየቀኝ እኔም አማን አወራ አማን አወራ አባቢ አማን አወራ.....ቆይ ካላመንከኝ ከሱ አንደበት ስማ አማን ደህና አደርክ ስለዉ አልሀምዱሊላህ ሲለኝ ስማ ብየ አማን ደህና አደርክ አልኩት አማን ዝም አለኝ አሁንም በድጋሚ አማኔ ደህና አደርክ አልኩት አማን ግን ዝም ከማለት ዉጭ መልስ አልሰጠኝም እኔም ተስፋ ሳልቆርጥ ደጋግሜ አማን ደህና አደርክ አልኩት መልስ የለም አማኔ ቅድም አልሀምዱሊላህ ብለኸኝ አልነበር አሁን ለአባቢ አልሀምዱሊላህ በለዉ በአላህ አማኔ ስል ለመንኩት መልስ የለም አባቢ "ሀናኔ ሁሌም አማን የሚያወራበትን ቀን ስለምትናፍቂ ነዉ ያወራ የመሰለሽ ደሞ እንቅልፍሽን አልጨረሽም መሰል በይ ወደ ቤት ግቢ" አለኝ ቆይ አባቢ እኔን አታምነኝም ማለት ነዉ አወራኮ ነዉ የምልህ አማን አወራ አልኩት አባቢ ግን ጭራሽ አላመነኝም ራሴን ተጠራጠርኩ የምር አላወራም እንዴ!እያልኩ ከራሴ ጋር ማዉራት ጀመርኩ ከመሀል አባቢ "በይ መቃዠቱን ተይዉና እኔ ስራ እየረፈደብኝ ነዉ አማንም ቁርሱን አልበላም ቁርስ ስጭዉና መድሀኒቱን በስአቱ ይዉሰድ አደራ" ብሎኝ ሄደ።

.......ወላሂ አባቢ እየቃዠሁ አይደለም እዉነቴን ነዉ አማን አዉርቶል አልኩት አባቢ በማሾፍ አይነት እየሳቀ "እዉነት ያድርግልሽ በሉ ደህና ዋሉ" ብሎን ሄደ።
እንዴት አባቢ አያምነኝም ተናድጀ አማን ለምን ዝም አልክ አታወራም አዉራ አየህ አባቢ እየቃዠሽ ነዉ ሲለኝ ሰማህ! ኧረ በአላህ አማኔ ተዉ አዉራ ዝም!ሁሌ ዝም አይጨንቅህም በቃ እሽ እንዴት አደርክ ስልህ አንዴ ብቻ አልሀምዱሊላህ በለኝ ሌላ ምንም በል ብየ አለምንህም እሽ አማን እሽ አልሀምዱሊላህ በለኝ አልኩት ቢያንስ አልሀምዱሊላህ ብሎኛል አላለኝም የሚለዉን እርግጠኛ ለመሆን ነበረ ነገር ግን አማን አሁንም መልስ የለም ዝም አለኝ አይ አባቢ እዉነቱን ነዉ እየቃዠሁ እንጂ አማን አዉርቶ አይደለም ብየ ምግቡን ልሰጠዉ ወደ ቤት ስገባ የግቢዉ በር ተንኳኳ......

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 7⃣

....... ሰሚራ ሽኩር


......የጊቢዉ በር ተንኳኳ አንድ ሀሊማ የምትባል ጎረቢታችን ናት እዉነት ለመናገር እኔ አትመቸኝም የዛኔ አማኔ እኛ ቤት የመጣለት አባቢን "ከአንዱ ወልዶት ይሆናል" እያለች ካለስሙ ስም ስትሰጥ የነበረች ሰትዮ ነት።
ዛሬ ምን እግር ጥሎት እንደመጣች ባላቅም በሩን ከፍቸላት ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡኋላ ነይ ግቢ ወደ ቤት ብየ ይዣት ስገባ አማኔን ዉጭ ፀሀይ ላይ ተቀምጦ አየችዉና "እንደዉ ላይድን አባትሽ ዝም ብሎ ይለፍል በደህና ጊዜ ያገኘዉን መኪናም ሸጠዉ አሉ እንደዉ ልፋ ብሎት ነዉ እንጂ ለማይድን እብድ የሚለፋ...."ንግግሮን አላስጨረስኳትም በጣም አናደደችኝ የማይሆን ነገር ልናገር አልኩና ካፌ መለስኩት ሀሊማ ምን ፈልገሽ ነዉ የመጣሽ በደህና ነዉ ብየ ወሬዋን ቀየርኩባት እሷም "ምን ትሏለች! ጎረቢት አይደለሁም እንዴ የጎረቢት ሀቅ የለዉም ያለሽ ማን ነዉ እኔማ ልጠይቃቹህ ብየ ስራየን አቋርጨ ነዉ የመጣሁ ደሞ ልጀ/ጓደኛሽ ልታገባልኝ ነዉ ልጂ በልጂነቱን ነዉ" እያለች አፈጠጠችብኝና እናትሽ የለችም እንዴ ስትል ጠየቀችኝ ቀስ ብየ በጥዋቱ የመጣሽ ልትጠይቂንስ አይደለም የልጂሽን ማግባት ልትናገሪ ነዉ ባትመጭ ይሻል ነበር አልኩኝ "ምን አልሽ" አለችኝ የተናገርኩት አልተሰማትም ጀሮዋን ትንሽ ያከራክራታል ብዙም አትሰማም ምንም አላልኩም እናቴ አለች ነይ ወደቤት ግቢ እማየ ቁርስ እያዘጋጀች ነዉ ብየ ወደ ዉስጥ ይዦት ገባሁ እማየንም ጠርቻት አብረዉ መጫወት ሲጀምሩ እኔ እማየ እያዘጋጀች የነበረዉን ቁርስ ልሰራ ወደ ኩሽና ገባሁና አዘጋጂቸ ጨርሸ ሳቀራርብ ሀሊማ "እኔ አልበላም በልቸ ነዉ የመጣሁ" አለች እማየም ኧረ ተይ ትንሽ ቅመሽ ብላ ለመነቻት በልቻለሁ ሰትል ገገመች ።

...... እማየም "እንግዳዉስ አልበላም ካለች አማኔን ይዘሽዉ ነይና ለኛ አቅርቢ" አለችን እኔም እማኔን ከዉጭ ይዠዉ ወደቤት ገባሁና ምግብ በአንድ ሱፍራ አቀረብኩ አማኔ እኔ አጠገብ ሁኖ መመገብ ጀመረ ሀሊማም ቆጣ ብላ "ኧረ እናንተ ሰዎች ምን ነካቹህ ሰዉ እንዴት ከእብድ ጋር አንድ ላይ ተቀምጦ ይመገባል!ይሄንንም ተዉትና እንደዉ ለመሆኑ የሱን የመመገቢያ እቃዎቹን ማንኪያዉን፤ብርጭቆዉንና፤ሰሀኑን ለይታቹህታል ........?" አለችን


ሀሊማ አልበዛም ቆይ ምን ለማለት ፈልገሽ ነዉ አማኔኮ ለኔ ወንድሜ ነዉ ደሞ የሚባልና የማይባለዉን እወቂ ጥሩ ንግግር ሰደቃ ነዉ(ረ.ሰ.ዐ) ......ንግግሬን ሳልጨርስ እማየ ተነሳችና ከአማኔ አጠገብ ተቀምጣ ከአማኔ ጋር አብራ በአንድ ሰሀን መመገብ ጀመረች ሀሊማም በንቀት አይኖ እያየች "ጭራሽ አንድ ላይ መመገብ ኢጭ! ከዚህ ከቆሻሻ እብድ ጋር" ......ብላ ወደ አማን አፈጠጠች

አማኔ ከሀሊማ ንግግር የመረረዉ ይመስላል እዝን ብሎ አንገቱን ደፍቶ ወደ ክላሱ ሄደ እኔም ሀሊማ ስትናገር ጀምሮ በአይኔ የአማንን ሁኔታ እየተከታተልኩኝ ነበርና አዝኖ ሲሄድ አላስቻኝም መመገቤን ትቸ ተከትየዉ ክላሱ ገባሁ።
አማኔ ሁለት እግሩን አጥፎ ከሆዱ ጋር አጣብቆ ይዞ ኩርምት ብሎ ተቀምጦል።
አማኔ! ብየ ስጠራዉ ቀና አለ እናዛ ዉብ ከሆኑ ጎላ ጎላ ካሉ አይኖቹ እንባዎች ይረግፋሉ።

እንዴ እማኔ ሀሊማኮ ዝም ብላ ነዉ ዉይ በሷ ንግግር ነዉ የምታለቅስ አይ አማኔ ባህሪዋኮ ነዉ የምትናገረዉን አታዉቀዉም በአላህ አትቀየማት......እያልኩ ማፅናናት ጀመርኩ አማኔ ግን ማልቀሱን አላቋረጠም እንባዉ ዝም ብሎ ይፈሳል ምን ላርግ ጨነቀኝ መድሀኒቱን ደግሞ አልሰጠሁትም ምክንያቱም መድሀኒቱ በጣም ከባድ ስለሆነ በደንብ ካልተመገበ ጨንጎራዉን ይጎደዋል ምናለ ሀሊማ በሄደችና ሰአቱ ሳያልፍበት በልቶ መድሀኒቱን በወሰደ ስል አሰብኩ ለነገሩ ብትሄድም እሽ ብሎ አይመገብም ብቻ በሆነ ነገር ሀዘኑን አስረስቸ ፈገግ ማረግ ፈለኩና አንድ ታሪክ ልነግረዉ መጽሀፍ ይዜ መጠሁ መቸም መፅሀፍ ሳነብለት ምስጥ ብሎ ነዉ የሚሰማኝ አባቢ እንኳን ቢጠራዉ አይሰማም።


.....መጽሀፍ ይዜ መምጣቴን ሲያይ አጠገቤ ጠጋ ብሎ ተቀመጠ እኔም ፍላጎቱን ስለማቅ አማኔ ዛሬ አንብቤቸዉ ፈገግ ካሰኙኝ አስተማሪ ገጠመኞች አንዱን አነብላሀለሁ ብየ ጀመርኩ "አንድ የድህረ ምረቃ ተማሪ የመስክ ምርምር ለመስራት ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ይሄዳል የሰሜኑ ክፍል ደግሞ እንደምናቀዉ ደኖቹ የተራቋቱ ናቸዉ ይሁን እንጂ አንዳንድ የሀይማኖት ተቋማት ያሉበት ቦታ በደን የተከበበ ነዉ ሰዉየዉ ምርምሩን ማድረግ የፈለገ ዛፎቹ በተፈጥሮ ዘር የመስጠትና ዘሮቹም የብቅለት ችግር ሊያጋጥማቸዉ ይችላል ወይ? የሚለዉና የስር የተፈጥሮ ብቅለት ከምን ይመነጫል? የሚለዉን ለማወቅ የዛፎችን እድገት መከታተል ይጠይቅ ነበር በዚህም መሰረት አንድ ዛፍ ያብባል፤ ፍሬ ይሰጣል፤ፍሬዉም ወደ መሬት ይረግፋል መሬት ላይ ከረገፈ ቡኋላ ግማሹ ይበቅላል በቅሎ ችግኝ ሁኖ መልሶ ዞፍ ይሆናል የቀረዉ ደግሞ መሬት ዉስጥ ከአፈር ጋር ሁኖ ምቹ ጊዜን ይጠብቃል....እንግዲህ የብቅለትን ችግር ለማወቅ ይህን ኡደት እየተከታተሉ ማወቅ ያስፈልጋል ለዚህም የተለያዩ ቦታዎች እየተዘዋወረ ከዛፉ ላይ ከረጢቶችን ያስቀምጣል በየሳምንቱም ከረጢቱ ዉስጥ የገቡትን ፍሬዎች ወደ ላብራቶሪ እየወሰደ ምርምር ያደርጋል ይሄ ምርምርም ቢያንስ አንድ አመት ይፈጃል። አንዳንዴ አንዱ ከረጢት በሳምንት ምንም ፍሬ ሳይዝ ባዶዉን ሊገኝ ይቻላል ይሄ ደግሞ የምርምሩ አካል እንጂ ችግር አይደለም።
ከሪጢቱን ያስቀመጠበት ቦታ አንድ አባት መምህር አሉ ተማሪዎችን ሰብስበዉ በዛ አካባቢ ያሉትን ተማሪዎችን ያስተምራሉ ሰዉየዉም ያን መምህር ማንኛዉም ሰዉ መጦ ከረጢቱን እንዳይወስደዉ አደራ ብሎቸዉ ሄደ።........


........ስለምርምሩ ጠብቅልኝ ላለዉ መምህር ምንም አልነገረዉም ብቻ በየሳምንቱ ለወር ያህል እየተመላለሰ በከረጢቱ የገቡትን ፍሬዎች ይዞ ይሄዳል ይሄን መመላለሱን ያዩ መምህርም "እንደዉ ልጀ አመት ሙሉ ተመላልሰህ ትዘልቀዋለህ" አሉት በሀዘኔታ ......

ሰዉየዉም አወ አመት ሙሉ እመላለሳለሁ ከከረጢቱ ዉስጥ የገባዉን ዘር ስለምፈልግ ግድ ነዉ አመላለሳለሁ አላቸዉ። በዚህ ሁኔታ አንድ ሁለት ወር ከተመላለሰ ቡኋላ ስምንት ጊዜ ማለት ለዘጠነኛ ጊዜ ሲመጣ ሁሉም ከረጢቶቹ አፍ እስካፍቸዉ ሙልት ብለዉ ያገኛቸዋል ይደነግጣል እንዴት በአንድ ሳምንት ይሄን ያህል ዘር ያረግፋሉ!ተአምር ነዉ እያለ ከራሱ ጋር ድምፁን ከፍ አድርጎ ሲፋጠጥ መምህሩ ሰምተዉ ነበርና ተማሪዎችን አስከትለዉ ይመጣሉ ሰላምታ ከሰጡት ቡሀላ መገረዉን አይተዉ "ምነዉ ልጀ" አሉት ልጁም አይ እንደዉ ደንቆኝ ነዉ በሳምንት ይሄን ያህል ዘር ማርገፍቸዉ ሲላቸዉ መምህሩ "እ...ነዉ አሉና እኔማ እንደዉ በየሳምንቱ ስትመላለስ ስታዛዝነኝ ጊዜ ተማሪዎቸን ሰብስቤ ከመሬት ያለዉን እያፈስን ከዛፉ እያረገፍን ሞላንልህ" አሉት ።

እንግዲህ አማን አስበዉ የዛችን ሳምንት ምርምር በሚቀጥለዉ አመት ያችን ጊዜ መጠበቅ ሊኖርበት ነዉ ሰዉየዉ ተናዶ ዝም ሲል መምህሩ "እንግዲህ የኔ ልጂ የሚበቃህ ይመስለኛል ተንግዲህ አትመላለስም" አሉት።

አማን ፈገግ አለ ፈገግታዉ እንዴት ያምራል እልያልኩ ትንሽ ካፈጠጥኩበት ቡኋላ ግን አማኔ ማን ይመስልሀል ጥፍተኛዉ አልኩት እንደለመደዉ ዝም አለ።👇👇👇
.....እየዉልህ አማኔ ለኔ ጥፋተኞች ሁለቱም ናቸዉ።
ምርምሩን የሚያደርገዉ ሰዉየ ለመምህሩ መናገር ነበረበት መምህሩም ልጁን ለምን እንደሚፈልገዉ መጠየቅ ነበረበት አየህ አማኔ ይሄ ታሪክ የኛንም ሂወት ይዳስሳል ሩቅ ሳንሄድ ዛሬ እኛ ቤት የመጣችዉ ሀሊማን ብናይ

ምናልባትም ስላንተ በቂ ግንዛቤ ስለሌላት እኛም ስላላስረዳናት ይሆናል እንደዛ ያለችህ በሌላ በኩል ለሰዎች ጥሩ ነዉ ብለን የምንናገረዉ፤ የምናደርጋቸዉ...... ማንኛዉም ነገሮች ለኛ ጥሩ ይምሰለን እንጂ የሌሎች የአመት ብቻ ሳይሆን የእድሜ ልክ ሂወታቸዉን ልናበላሽ እንችላለን ስለዚህ የምንናገረዉን በተግባር የምናገረዉን እንጠንቀቅ በስሜት ሳይሆን አስበን እናድርግ።
ለምሳሌ አንድ ሴት አንድን ወንድ እየቀረበችዉ እሱም እህቴ ማለት ናት ብሎ እያቀረባት እያገዛት....በጊዜ ሂደት እየወደደችዉ እሱም ዉዴታዋን እያወቀ ዝም ካላትና ዉዴታዋ ዳር ደርሶ እንደምትወደዉ ስትነግረዉ አልወድሽም ብሏት ያልሆነ ነገር ብታደርግ ማን ነዉ ተጠያቂዉ እሱ ወይስ እሷ.....አየህ አማኔ እኛ ሰዎች ምንም ጥፋት የሌለብን ይመስለናል እንጂ ዙረን ብናይ ብዙ ጥፋቶች አሉብን የብዙ ሰዉ ሂወት የመበላሸትም ሆነ የመስተካከል ምክንያቶች እኛዉ ነን ለሰዉ ልጂ መድሀኒቱ ሰዉ ይሁንጂ ጠላቱም ራሱ የሰዉ ልጂ ነዉ።


......ስል አማኔ ራሱን መነቅነቅ ጀመረ ልክ ነሽ ለማለት ይመስላል ወይኔ! አማኔ ዛሬኮ ጁመአ ነዉ ትምህርት ቤት ስብሰባ አለን በትምህርት ቤት በወር አንድ ጊዜ ሴቶችም ወንዶችም የምንሰበሰብበት አንድ ጀመአ አለን እኔ ይሄን ጀመአ የተቀላለልኩ ከሶስት ወር በፊት የደረሰኝ ዩኒቭ ራቅ ያለ ስለነበርና ፀጥታዉም ጥሩ ስላልነበር አባቢ ካሎጂ አስገባኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ኮሎጂ እንደገባሁ የጀመአዉ አሚሮች ፉአድና አይሻ ነበሩ ጀመአዉን እንድቀላቀል አደረጉኝ ።እኔም በደስታ ተቀላቀልኩ በዲኔም ገንዘቦችን በማሰባሰብም የተሻልኩ ስለነበርኩ በገባሁ በወሬ እኔን በአሚርነት ሾሙኝ ከተሾሙኩኝ ጀምሮ የተዋጡ ገንዘቦች እኔ ጋር ነዉ የሚቀመጡት ጀመአዉ በዋናነት የተቋቋመ በትምህርት ቤትም ይሁን ከትምህርት ቤት ዉጭ እርዳታ ለሚሹ እህትና ወንድሞቻችንን ይዘይራል፤አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ያሟላል፤የቤት ክራይ፤የትምህርት ቤት ክፍያ....የመሳሰሉትን ይከፍላል።

ዛሬ ጀመአዉን ከተቀላቀልኩ ለሶስተኛ ጊዜ ልሄድ ነዉ የዛሬዉ ፕሮግራም አንድ የተመመ ሰዉ አለ ብለዉን እሱን የተለያዩ ነገሮችን ገዝተን እንዘይራለን ብለናል ባለፈዉ ወር የተዋጣዉ 5000 ብር እኔጋ ነዉ ዛሬ ይዘሽዉ ነዉ ተብያለሁ የግድ በሰአቱ መድረስ አለብኝ ግን ሰአቱ እየረፈደብኝ ነዉ የአማኔን ምግቡን እንደምንም ሰጥቸዉ እስከሚመገብ ልብሴን ቀየርኩ ከዛ መድሀኒት ሰጥቸዉ ብሩን ይዤ በፍጥነት ወጣሁ አላህ ሲያግዘኝ አንድ ታክሲ አግኝቸ እየሄድኩ እያለ ትዝ ሲለኝ መድሀኒቱን ሰጥቸ በጣም ቸኩየ ስለነበር ከአማን አጠገብ አላነሳሁትም ወይኔ! ዛሬ አባቢ ገደለኝ ሁሌም መድሀኒት፤ስል ነገሮችን..... አጠገብ አታስቀምጡ ይለናል እናምን ተሻለኝ እንዳልመለስ ሊረፍድ ነዉ እንዳልሄድ አማኔ መድሀኒቱን ወስዶ አንድ ነገር ቢሆንስ ገራ ገባኝ......


በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 8⃣

...... ሰሚራ ሽኩር

.....ወይኔ አባቢ ዛሬ ገደለኝ መድሀኒቶችን፤ስልነገሮችን....አማኔ አጠገብ አታስቀምጡ እያለ ብዙ ጊዜ አስጠንቅቆናል።
.......እና ምን ተሻለኝ እንዳልመለስ ሊረፍድ ነዉ እንዳልሄድ አማኔ መድሀኒቱን ወስዶ አንድ ነገር ቢሆንስ ግራ ገባኝ.....ወድያዉኑ አንድ ሀሳብ መጣልኝ እማየ ላይ ደዉየ መድሀኒቱን እንድታነሰዉ ማድረግ አወ ልደዉልላት ብየ ቦርሳየን ስፈትሽ ስልኬን ቻርቸር እያደረገ እረስቸዉ ነዉ የመጣሁ ያአላህ!ምን ይሻለኛል ግራ ገባኝ ..............አጠገቤ የተቀመጠ አንድ ወጣት በትኩረት ሲያፈጥብኝ ቆይቶ "ምን ጠፍቶሽ ነዉ የተናደድሽ ትመስያለሽ" አለኝ አወ በጣም ተናድጃለሁ ስልክ ልደዉል ብየ ስልኬን ቤት እረስቸዉ መጥቻለሁ አልኩት እሱም"እህ ለዚህ ነዉ እንዴ የተናደድሽ አኔ ስልክ ይዣለሁ ከፈለግሽ እንኪ እያለ ኪሱን መዳበስ ጀመረ እኔም አልሀምዱሊላህ ብየ ስልኩን ልቀበል እጂ እጁን ሳይ ፊቱ መቀያየር ጀመረ ከተቀመጠበት ተነሳና በኋላ ኪሱ ከፊት ኪሱ ጃኬቱን ፈተሸ ስልኩ የለም "እንዴ! ስልኬስ ስልኬስ....." እየለ መለፍለፍ ጀመረ ኧረ ወንድም ምንድን ነዉ የምታወራ ስልክህ ጠፍቶህ ነዉ "አወ ስልኬ ጠፋኝ"
..... አይ!እንደኔ ቤት እረስተኸዉ ይሆናል በቃ ተወዉ ከመኪና ስወርድ በአንዱ ስልክ እደዉላለሁ አልኩት እሱም እሽ ብሎ ተረጋግቶ ከተቀመጠ ቡኋላአስተያየቱና ሁኔታዉ አልተመቸኝም ወድያዉ ስልኬን አገኘሁት እንኪ ደዉይ ብሎ ሰጠኝ ከየት አገኘኸዉ ልለዉ ነበር ......ምን አገባኝ ብየ ለመደወል ተቀበልኩት ከዛ የእማየን ስልክ በቃሌ አዉቀዉ ነበር ስሞክር ስልኩ ባላንስ የለሙም ወንድም ስልክህ ብር የለዉም ለማንኛዉም አመሰግናለሁ ብየ ሰጠሁት እሱም "ኧረ ጣጣ የለዉም ባላንስ ያለዉ መስሎኝ ነበር ይቅርታ" አለኝ

......... ኧረ ችግር የለዉም ብየ ፈገግ ስል ዉይ ፈገግታሽ ያምራል ሲል በትኩረት ተመለከተኝ እኔም አመሰግናለሁ ብየ ወደ መስኮቱ ዞርኩ "መተዋወቅ ይቻላል ያሲን" እባላለሁ ብሎ እጁን ዘረጋ ድፍረቱ ሲጀመር ቦታ አጥቸ እንጂ አጠገቡ የተቀመጥኩ ለሌላ ነገር መስሎት ነዉ ይሄ ምን አይነቱ ጂል ነዉ አጂ ነብይ ሰላም ይባላል እንዴ! እያልኩ "መተዋወቅ አትፈልጊም" አለኝ እእእእ .......ሀናን እባላለሁ አልኩት የዘረጋዉን እጂ ሰበሰበና "ሀናን ደስ የሚል ስም አለሽ እና ስራ እንዴት ነዉ"ብሎ እጁን ትክሻየ ላይ አስቀመጠዉ ወላሂ የዛኔ ከእግር እስከፀጉሬ የሆነ ነገር ወረረኝ ቅፍፍ አለኝ ሰዉ ሳይሆን ሰይጣን የተገደፈኝ መሰለኝ ..... ቀስ ብየ ወደ መስኳቱ ሸሸት ሸሸት.....እልኩ ከጁ ለመራቅ ስቁነጠነጥ ይባስ ብሎ ጃኬቱን አዉልቆ ያዥዉ አለና ጭኔጋ አስቀመጠዉ ኧረ መነናቅ የኔ ሀሳብ አማኔ ምን ነክቶት ይሆን በስአቱ ትምህርት ቤት ስብሰባዉ ላይ እደርስ ይሆን እያልኩ በሀሳብ ተጉዣለሁ ለካ አጂሬዉ እኔ በሀሳብ እንደሆድኩ ስርቀዉ ሲጠጋ ከመኪናዉ መስኳት ጋር አጣብቆ በአንድ እጁ ወገቤን ይዞኛል ወይ ጉድ!ብዙ ቆይቸ ነዉ ከሀሳቤ የነቃሁኝ ለካ የልባችን አይን ካልነቃ የስጋችን አይን መፍጠጡ ትርጉም የለዉም ዝም ብለዉኮ ድንበር ይዘል ነበር!።

.......ከዛማ ከእንቅልፏ እንደተነሳች ሴት ብንን ብየ በአንድ እጀ ወገቤን የያዘበትን እጁን ወደዛ አሽቀንጥሬ በአንድ እጀ ደግሞ ጭኔ ላይ የነበረዉን ኮት ወረወርኩት ........


"አንች ያምሻል እንዴ ምን አጠፋሁ" ሲል አፈጠጠብኝ ምን አጠፋሁ .....አታፍርም ከዚህ በላይ ምን አስበህ ነዉ አንተ ጂል ዱርየ.... አሁን ከአጠገቤ ዞር በል! አልኩት ታክሲ ዉስጥ ከኋላችን ያሉ ሰዎች ጭቅጭቃችንን እየሰሙ ነበርና "ተዉ እንጂ አትጣሉ ተደማመጡ በትዳር ዉስጥ እንቅፋቶች አይጠፉም አንዳንዴ እያሳለፉ ነዉ ተስማሙ" አሉን ወይኔ ዛሬ ማበዴ ነዉ!። ጭራሽ ባልና ሚስት መስለናቸዋል እህ ምንድን ነዉ የምትሉት እኛኮ.....ያሲን ንግግሬን አላስጨረሰኝም "አወ እዉነታቸዉን ነዉ ከመጣላት መስማማቱ ነዉ ለኛ የሚሻለን"እያለ እጁን በድጋሚ ትክሻየ ላይ አደረገዉ ኧረ ድፍረት እንዴት ብትንቀኝ ነዉ አንተ ባለጌ የት አዉቀኸኝ የት አዉቄህ አንተ ብሽቅ....አልኩኝና አጠገቤ የሆነ እሱን የምመታበት ነገር በአይኔ ባይ አጣሁ ከዛም ጫማየን ወለቅ አድርጌ ራስ ራሱን ስለዉ ታክሲ ቆመና ታክሲዉ ዉስጥ የነበሩት ሰዎች ሁሎችም እኛን ከበቡን "ምንችግር ተፈጠረ ምንድን ነዉ"አሉ ከጀርባችን ተቀምጠዉ የነበሩት ሰዎችም "ባልና ሚስት ናቸዉ መሰለኝ እንዲሁ ሲጨቃጨቁ ነበር ጭራሽ አሁንማ ብሶባቸዉ መደባደብ ጀመሩ"
.....ቆይ ሰዉ በማያዉቀዉ ፤በማያገባዉ በመሰለኝ እንዴት ያወራል በመሰለኝ ባልና ሚስት አደረጉን፤በመሰለኝ የስንት ሰዉ ስም ጠፍቶል፤ በመሰለኝ ስንቶች ከትዳራቸዉ ተረረቀዋል፤ በመሰለኝ ስንቶች ተጣልተዋል፤ በመሰለኝ ስንቶች የወንጀል ሰለባ ሁነዋል፤ በመሰለኝ ስንቶች ታስረዋል፤ ስንቶች ተሰቃይተዋል........... በቃ እርግጠኛ ሳንሆን እንዲህ መሰለኝ እንላለን በመሰለኝ የማይመስል ነገር እናደርጋለን፤ እናወራለን፤ እንሰራለን......።


........."ኧረ ተዉ ተላቀቁ" እያሉ ለመገላገል በመሀላችን ገቡ "ቆይ ምንድን ነዉ የጣላቹህ" አሉ እኔ በንዴት የምናገረዉን አላቅም እሱ"ይች ነቻ ሌባ ስልኬንና ብሬን ወስዳ አልወሰድኩም ብላ ገገመች" ምን! ኢላሂ አንተ ቀፋፊ ዉሸታም ጂል እኔነኝ ያንተን ስልክ የሰረቁ!? ደግሞ ስልኬን ሰረቀችኝ ብሎ መከራከር ጀመር እኔ ምን ልበል ግራ ገባኝ ሰዎችም "ኧረ እህት ከወሰድሽ አትገግሚ ፓሊስ መጦ ሌላ ነገር ከመፈጠሩ በፊት ስጪዉ" ማለት ጀመሩ
........ኧረ ዛሬ ማበዴ ነዉ ምንድን ነዉ የምታወሩት እሱኮ..... አላስጨረሰኝም እፌን አዘጋኝ "በቃ እሽ አልወሰድኩም ካልሽ ቦርሳሽ ይፈተን"
......ኑ ይሄዉ ቦርሳየ ፈትሹ ብየ ቦርሳየን ሰጠኋቸዉ እነሱም ሲፈትሹ የተሰበሰበዉን ይዜዉ የወጣሁትን አምስት ሺ ብርና ስልኩን አገኙ ደነገጥኩ ኧረ እኔ እኔ አልወሰድኩም ብሩ የራሴ ነዉ ስልኩ የኔ አይደለም እንዴት እኔ ቦርሳ የሱ ስልክ ሊገባ ቻለ ግራ ገባኝ ትዝ ሲለኝ ስልኬ ጠፍቶ ቦርሳየን ስፈትሽ ብሩን አይቶታል ቦርሳየንም በሱና በእኔ መሀል ነበር ያስቀመጥኩት ፊቴም መደ መስኮቱ አዙሬዉ ነበር .......ብቻ አላቅም ሰዎቹ "ዉይ ሲያዮትስ ጥሩ ትመስል ነበር አይ!የዘመኑ ልቦች እንዲህ ጥሩ እየመሰሉ ነዉ ሰዉን የሚዘርፉት" እያሉ ማሽሟጠጥ ጀመሩ ንግግራቸዉ አናደደኝ ወላሂ አልወሰድኩም አልወሰድኩም.....ብልም የሚሰማኝ ጠፋ ወድያዉ ፓሊስ መጦ እኔንና እሱን ወደ ፓሊስ ጣቢያ ይዘዉን ሄዱ
......እዛ እንደደረስንም ተያዥ አምጭ አሉኝ ማን ተያዥ ይሆነኛል ለአባቢ ብደዉልም ይደነግጣል እማየም እንደዛዉ በዛ ላይ ትምህርት ቤት የተዋጣዉ ብር እኔጋ ስለሆነ ትምህርት ቤት የጠበቁኝ ይሆናል ግራ ገበኝ በቃ ከፓሊሶች ስልክ ተቀብየ እማየጋ ደዉየ እይድትመጣ ላድርግ ብየ ስደዉል ይጠራል አይነሳም አሁንም ደግሜ ሞከርኩ ይጠራል አይነሳም በተደጋጋሚ ወደ ስድስት ጊዜ ሞከርኩ ይጠራል አይነሳም ጨነቀኝ በዛ ላይ ጊዜዉም እየመሸ ሄደ በቃ አባቢ ይቆጠኛል ቢሆንም ግድ ነዉ ብየ አባቢጋ ሰደዉል እሱም እንደማየ ይጠራል አያነሳም 👇👇👇
ደጋግሜ ሞከርኩ በኔም ስልክ ብታነሰዉ ብየ ሞከርኩ ይጠራል አይነሳም የአላህ ምን ላርግ ለማን ልደዉል ማን ይድረስልኝ ፓሊሶቹ "ተያዥ ካላመጣሽ አትወጭም"ብለዉኛል የነማየ ስልክ አይነሳም በሰላምማ አይደለም የማያነሱት እማየም ሆነች አባቢ ስልክ ቶሎ ነበር የሚመልሱ ዛሬ ምን አግኝቷቸዉ

ይሆን ምን አልባት ከአማን አጠገብ መድሀኒቱን ስላላነሰሁት .......ማሰብም አልፈልግም አይሆንም! እሽ ምን ተሻለኝ እየመሸ ነዉ

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join👇👇👇

www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል9⃣

......ሰሚራ ሽኩር


.......እማየም ሆነች አባቢ ስልክ ቶሎ ነበረ የሚመልሱ ዛሬ ምን አግኝቷቸዉ ይሆን ምን አልባት ከአማን አጠገብ መድሀኒቱን ስላላነሰሁት አማን......ማሰብም አልፈልግም አይሆንም!እሽ ምን ተሻለኝ እየመሸ ነዉ ወይ!የዛሬዉን ቀን በሂወቴ መቸም አረሰዉም ደሞ የጎረቢት ስልክ አላቅ አልደዉል በቃ ዛሬ እዚሁ ፓሊስ ጣብያ ማደሬ ነዉ እያልኩ አንዱ አዛዥ ፓሊስ ማረፊያ ክፍል ዉሰዳት አለና ትዛዝ ሰጠ ታዛዡም እሽ ብሎ ወደማረፊያ ክፍል ወሰደኝ ወይኔ እማየ ትጨነቃለች አባየ በጣም ያስባል እንዴት አድርጌ ላግኛቸዉ አላቅም ነገር ግን ማረፊያ ክፍል የሚወስደኝን ፓሊስ የነማየን ስልክ ሰጥቸዉ ደጋግሞ እንዲሞክረዉና ያለሁበትን ሁኔታ እንዲያስረዳቸዉ ነገርኩት እሱም ጣጣ የለዉም አለኝ
...... አላህ ይስጥህ እያልኩ ወደ ማረፊያ ክፍል ሄድኩኝ ማረፊያ ክፍል ስገባ ከኔ ተለቅ ተለቅ ያሉ አምስት ሴቶች ተቀምጠዋል ዉይ እነዚህም እንደኔ ሰረቃቹህ ተብለዉ ይሆን አይ እንዴት ይባላሉ ትልልቅ ሴቶች ናቸዉ ለነገሩ ትልቅ ሴት አይሰርቅም ያለዉ የትኛዉ ሰዉና ህግ ነዉ እኔጃ ብቻ እንደኔ በዉሸት ይሆናል እዚህ የገቡት ለማንኛዉም ከድሚያቸዉ ተለቅ ያሉ ስለሆኑ አያስፈሩም እያልኩ ሰላም አልኳቸዉ እነሱም ሰላምታየን ከመለሱ ቡኋላ "አንች ደግሞ በዚህ እድሜሽ ምን አድርገሽ ነዉ" ብለዉ ጠየቁኝ እኔም ሁሉንም አንድ በአንድ ነገርኳቸዉ አምስቱም ሳቁብኝ ግራ ገባኝ ቆጣ ብየ ያስቃል እንዴ ካለጥፋቴ ያናድዳል እንጂ እያልኩ እነሱ በምን ምክንያት እዚህ እንደገቡ ጠየኳቸዉ

.....ከመሀል አንዷ በእድሜ ከነሱ እነስ የምትል ተነሳችና "ጩጨዋ የሳቅን የኛንና ያንችን ወንጀል ስናነፃፅረዉ ሰማይና ምድር ሁኖብን ነዉ ለማንኛዉም እኛ አምስታችንም የሰዉ ሂወት በማጥፋት ተጠርጥረን ነዉ የገባነዉ"
........ ደነገጥኩ ምንም አልተነፈስኩ ቀስ ብየ ከነሱ ራቅ ብየ ተቀመጥኩ ያረብ ምን አይነት ቦታ ነዉ የመጣሁ እያልኩ አምርሬ አነባሁ "ኧረ ፒስ ነይ አትፍሪን ይሄን ያህል እንኳን በሴት የሚጨክን አንጀት የለንም" በዉስጤ ስለአንጀት ያቃሉ ግን እያልኩ ቃሌ እየተቆራረጠ እና በወንዶች ነዉ የምትጨክኑት ስል ጠየኳቸዉ "ስሚ ጩጨዋ ሂወት መራራ ነች እኛ ሁላችንም የሰዉ ነፍስ አጥፍተናል"
........ምንድን ነዉ የምታወሪ የሰዉ ሂወት ማጥፍት እንደምትይዉ ቀላል ነዉ እንዴ!
......... ለምን እንዴት ማለቴ እኔጃ ብቻ ፈርቸ ይሁን ደንግጨ ተርበተበትኩ "አወ ቀላል ነዉ ጩጨዋ ሂወት ስትመርሽ ማድረግ የማትፈልጊዉን ወደሽም ሆነ ተገደሽ ታደርጊያለሽ የሄ ደግሞ የሂወት ህግ ነዉ እኔ የገደልኩት የእንጀራ አባቴን ነዉ የእንጀራ አባቴን ገደልኩት ትሰማላቹህ ! ያሳደገኝን የእንጀራ አባቴን ገደልኩት!" እያለች የብድ ሳቅ መሳቅ ጀመረች
.....ምን የእንጀራ አባቴን ምን አጠፋ ስል ከመሀል አንዷ "አንች ጨካኝ ያሳደገ የእንጀራ አባትሽን ገደልሽዉ የኔ ይሻላል ሲያሰቃየኝ የነበረ ባለቤቴን ነዉ የገደልኩት" ወይ ጉድ ሰዉ ወዶ አይስቅም ፈገግ አልኩ ቆይ ከእንጀራ አባትና ከባለቤት የቱ ይቀርባል ብቻ ሁለቱም እንደየ አቀራረባችን ሊሆን ይችላል አንዳንዴ ከወለደችን እናት ያሳደጉንን ፤ከአባት የእንጀራ አባትን፤ከእህት ጎደኛን፤ከአክስት ጎረቢትን....... እንቀርባለን

ልጂቷም ቀጠል አድርጋ "እስኪ ልጠይቃቹህ እግዚአብሄር ጨካኝ ነዉ አይደለም?"በማለት ጠየቀች አራቱም ክርስቲያን ናቸዉ ሁላችም አንች ያምሻል እንዴ እግዚአብሄርማ ጨካኝ አይደለም ብለዉ አፈጠጡባት።


..... ልጂቷ ወደኔ ዞር አለችና አንችስ አላህ ለማለት አለሀ ጨካኝ ነዉ አይደለም ስትል ጠየቀችኝ እኔም አላህማ የኛ ጌታ ጨካኝ አይደለም
እጂግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ
(አል ፋቲሀ 1፡3) ጌታ ነዉ አልኳት


......በቃ እሽ እግዚአብሄር የማርያም ልጇ ነዉ አይደለም ስትል ጠየቀች
ሌላኛዋ "አንች ያምሻል እንዴ ድንግል ማርያምማ የእግዚአብሄር እናት ነች!ተንከባክባ፤አብልታ፤አጠጥታ ......ያሳደገችዉ እናቱ ነች" ካለቻት ቡኋላ ጥያቄዉ ወደኔ ዞረ ጠየቁኝ እኔም እግዚአብሄር ፈጣሪያቹህ እንደሆነ አቃለዉ ሌላ ነገር ግን አላቅም የኛን ካላቹህኝ ግን ፈጣሪያችን አላህ (ሰ.ወ) አልወለደም አልተወለደምም (አል-ኢኽላስ112፡3)
የእርሱ አንድም ቢጤ የለዉም......



...ልጂቷም "ጨካኝ ነሽ አላቹህኝ!ስሙ የኔ የእንጀራ አባት ሲበዛ ጨካኝ ቆዳ ለበስ ሰይጣን ነበር " ለደቂቃዎች አዝና ዝም ካለች ቡኋላ እስኪ ልጠይቃቹህ አለች እኛም የልጂቷ ሁኔታ ግራ እያጋባን እሽ አልናት ልጂቷም "ማርያምን ማን የገደላት ይመስላቹሀል"አለች ሁሉም አምላኳ እግዚአብሄር ነዋ! በማለት መለሱ"አያቹህ አኔ የበደልን ጥግ ያሳየኝን ጨካኙ የእንጀራ አባቴን ስለገደልኩት ጨካኝ አላቹሁኝ እግዚአብሄር ግን እንደዛ ተንከባክባ ያሳደገችዉን ያዉም ከአባት የምትበልጠዋን እናቱን ሲገል ጨካኝ ነዉ አላቹህ እእእእ...... መልሱልኛ እኔ የእንጀራ አባቴን ስለገደልኩ የሰፈር ሰዎች ሁሉም ይች ጨካኝ ሱሉ ልቤን ያደሙታል አንገቴን እንድደፋ ያደርጉኛል ያዉም ለምንና እንዴት እንደሞተ ሳያቁ እግዚአብሄር እናቱን ስለገደለ ምን ተባለ? ምንም እኔ ሰዉ ስለሆንኩ እሱ ጌታ ስለሆነ....."


....ቆይ ምን ቢበድልሽ ነዉ የጨከኝሽበት?

....."በደሌ እንደማወራቹህ ቀላል አይደለም ህመሜ የሚያማቹህ በኔ ቦታ ስትሆኑ ብቻና ብቻ ነዉ ህመም ግን ታቃላቹህ!? ህመም የማታቁ ከሆነ መነገሬ ለኔ ህመምን እንጂ ሌላ ነገርን አይጨምርልኝም በቃ ተዉት ምኑን ትቸ ምን ብየ ላዉራቹህ አባቴ በጣም ጨካኝ እንደነበረ ፤ ይደፍረኝ ያሰቃየኝ እንደነበረ ወይስ ምግብ የሚሰጠኝ ሞት አፋፋ ላይ ስደርስ እንደነበረ ምኑን ልንገራቹህ እእእእ እናቴን አሰቃይቶ የገደላት እሱ እንደሆነ ተጫዉቶብኝ ሲያበቃ ጎዳና እንደወረወረኝ..... ምኑን ልንገራቹህ እእእእ መልሱልኝ ከየት ልጀምር እእእእእ.........ዝም አትበሉ መልሱልኝ!"
ሁላችንም ዝም አልን ማመን የሚከብድ ወሬ ምን ይባላል ግን እስኪ መልሱ እንዲህ አይነት የእንጀራ አባት አባት ነዉ እንዴ!እእእእ እኔም ልጠይቃቹህ ባይወልዳትም ልጁ ማለት ናት ልጁን የስቃይ ጥግ የሚያሳይ የእንጀራ አባት አባት ነዉ አላቅም ብቻ ሙሉ ሂወቷን ለማወቅ ጓጉተን እንድታጫዉተን ለመናት እሷም ትንሽ ካቅማማች ቡሀላ "እንግዲህ ታሪኬ መራራ እዉነት ነዉና ቢመራቹህም ዋጡት"ብላ ታሪኳን እንዲህ አጫወተችን

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 1⃣0⃣

......ሰሚራ ሽኩር

....."እንግዲህ ታሪኬ መራራ እዉነት ነዉና ቢመራቹህም ዋጡት" ብላ ታሪኳን እንዲህ አጫወተችን

....."በመጀመሪያ ስሜ ትእግስት ካሳ ይባላል ታሪኬን ከየት እንደምጀምርላቹህ ባላቅም

እናትና አባቴ በጣም ሀብታም ነጋዴ ፤ስራ ወዳድ ፤ሲበዛ ሰዉ አማኝ የዋህ፤ በሰፈሩም ተወዳጂ ነበሩ። እኔ በቤቱ በጣም ተወዳጂ ብቸና ልጃቸዉ ነኝ።
እናትና አባቴን በጣም እወዳቸዋለሁ እነሱም በጣም ይወዱኛል..... ወጥቸ እንኳን እስከምመለስ በስስትና በጭንቀት ይጠብቁኛል አስታዉሳለሁ ሁሌም እናቴ ከህፃንነቴ ጀምራ ሰዉነቴን ስታጥበኝ ትግስቴ የኔ ልጂ ማንም ሰዉነትሽን ከኔ ዉጭ እንዳይነካብሽ ማንም ቢሆን እያለች ደጋግማ ትነግረኛለች ነገሩ ባይገባኝም እሽ እማ ማንንም አላስነካም አላት ነበር።

.........አባየ በጣም የሚወደዉ ጓደኛ አለዉ እኔም እማየም እንወደዋለን አባየ ሁሌም እቤት ይዞት ይመጣል፤ያበለዋል ያጠጠዋል ......በጣም ይቀራረባሉ አንዳንዴ እማየ የአባየ ስልክ አልሰራ ሲላት በጓደኛዉ ትደዉልለታለች ሁሌም አንድ ላይ ናቸዉ አባየ ያለበት ቦታ ጓደኛዉም አይጠፋም ብቻ የነሱ ፍቅር እንዲህ እንደምነግራቹህ ቀላል አልነበረም።


ስሙ ታሪኩን እያለፍኩኝ ነዉ የማጫዉታችሁ ሁሉንም ለመናገር ስአት አይበቃም የኔ ታሪክ ተነግሮም፤ተፅፎም አያልቅም" አለችን እኛም ተመስጠን እያዳመጥን ስለነበረ እሺ ከዛስ አልናት ትግስትም
....."ሁላችንም በፍቅር እየኖርን ከለታት በአንድ ምሽት አባቢን ብንጠብቀዉ ብንጠብቀዉ ቀረብን በጓደኛዉ ስልክ በራሱም ሞከርን ይጠራል አይነሳም።

በጣም መሸ አሁንም ብንጠብቀዉ ብንጠብቀዉ ቀረ እኔ ወደ ዘጠኝ ሰአት አካባቢ ሲሆን አልቻልኩም ሶፋዉ ላይ እንደተቀመጥኩ እንቅልፍ ወሰደኝ እማየ ኧረ ጨነቀኝ ትግስቴ አይ እኔጃ በጤናዉ ይሆን እያለች ከሳሎን መኝታ ቤት ስትቀመጥ ስትነሳ ሰትደዉል ስትንጎራደድ ...... ቆይታ ኡኡኡኡኡኡኡኡ እያለች ጮኸች ከተኛሁበት ብንን ብየ እየተደናበርኩ እማ እማ ምንድን ነዉ እማ እማ ብላትም ጩኸቷን አላቋረጠችም የግቢዉ የቤቱም በር ተከፍቷል እማየ አንዴ ወደ ዉጭ አንዴ ወደ ዉስጥ ራሷን ይዛ ትወጣለች ትገባለች ወድያዉ ራሷን ስታ ወደቀች የግቢዉ በር ተከፍቷል የቤቱ በር ተከፍቷል እማየ መሬት ላይ ወደቀችብኝ ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ብቻየን ነኝ ምን ላርግ ወድያዉ ጓረቢታችን የእማየን ጩኸት ሰምተዉ ነበርና እናሱም እየሮጡ እግቢዉ በር ቁመዉ መጮህ ጀመሩ እኔም እየሮጥኩ ወደ በሩ ሄድኩና እማ እማ.... ብየ እጇን ይዠ ወደ ቤት ላስገባት ስል አይና መሬት ላይ አንድ በጩቤ የተወጋ በደም የተነከረ ሰዉየ ላይ አርፏል ማን ነዉ ? ማን ነዉ? ብየ በትኩረት ተመለከትኩት ልብሱ ጫማዉ ያባየን ይመስላል ምን ልሁን እማየ እቤት ወድቃለች አባቴ ዉጭ ወድቋል ዞረብኝ ከዛ ቡሀላ ለአመታት የአባየ ናፍቆት አላስተኛ አላስበላ አላስጠጣ አለኝ እማየም ከዛ ቡሀላ አታወራ አትንቀሳቀስ ምንም ማድረግ አልቻለችም


አስቡት በአስር አመቴ ምንም ነገር አላቅም አባየ ላይመለስ ጥሎኝ ሄደ/ሞተ እማየ አትነሳ ፤አትቀመጥ፤አታወራ....የአልጋ ቁረኛ ሆነችብኝ እህት የለኝ ወንድም የለኝ እናዛ እንኳን ወዳጅ የተባሉ ጓረቤቶቻችን ራቁን


............ትምህርቴን ከአራተኛ ክፍል ማቋረጥ ግዴታ ሆነብኝ ምክንያቱም እናቴ ከኔ ዉጭ አብሯት የሚሆን ማንም አልነበረም ሁሉም ዘመድ ጎረቢት የተባሉ ራቁን ወዳጂ ያልናቸዉ ቀን ሲጥለን ፊታቸዉን አዞሩ ምን ላርግ እማየ መራመድ አትችልም የምትፀዳዳ መኝተዋ ላይ ነዉ እኔ ማንሳት አይሆንልኝም አንዳንዴ ያ ዉብ የነበረዉ ቤታችን ሽታዉ አያስገባም ከሽታዉ የተነሳ የአስም በሽተኛ ሆንኩ!አንዳንዴ እንደምንም የአባቢን ጓደኛ ለምኘ በመከራ እናነሳትና በደንብ አፀዳላታለሁ።


.... ምግብ ማብሰል አልችልም ማለቴ እንጀራ መጋገር ወጡን እንደምንም ሰርቸ እንጀራ መግዣ ብር ሲኖረኝ እገዛለሁ ብሩ ሲያልቅብኝ ከሆቴል ፍርፋሪ አምጥቸ እየቀፈፈንም ቢሆን እንበላለን ፍርፋሪም ብርም ከሌለ ፆማችንን እናድራለን ብቻ ቤት የማፀዳ እኔ፤ እቃ የማጥብ እኔ ፤አለቀ አላለቀ የማስብ እኔ...... በቃ ሁሉንም የማረግ እኔ ብቻ ነኝ አንዳንዴ ስራ ጨርሸ የሚያወራኝ ሳጣ ብቻየን አወራለሁ አንዳንዴ እማየን እንዳይከፋት እያልኩ እያመመኝ እስቃለሁ አንዳንዴ አለቅሳለሁ አንዳንዴ አባየ ምን አለበት እኔንና እማየን ወደ አለህበት ጠርተህ ብትወስደን ብየ እማፀነዋለሁ ምን ብየ ልንገራቹህ በቃ ሂወት መረረችኝ ጓደኞቼን ሳይ ቦርሳ ይዘዉ ዘንጠዉ ይማራሉ እኔ ደግሞ .....ከባድ ነዉ" ብላ እንባዋን በቀኝ እጃ መጥረግ ጀመረች

አሳዘነችኝ ንግግሯን ሳትጨርስ በሀዘን ቃል እኔ ምለዉ ሀኪም ቤት አልወሰዳቹሀትም?? ስል ጠየኳት ምን አልባትም ትድን ይሆናል በሚል ተስፋ


..ልጂቷም " የአባቴ ጓደኛ ትላልቅ ዳክተሮች ላይ ወስዷት ነበር ትድናለች የሚል ተስፋ ይሰጡናል እንጂ ቀን ከቀን ህመሟ እየባሰ ነበር የሄደ የኔ ትምህርት ማቋረጥ፤ የአባየ መሞት ተደምሮ በሽታዋን አባሰባት የአባቴ ጓደኛ እንደዉ መፍትሄ ቢሆን ብሎ አንች ትምህርትሽን ጀምሪ ከእናትሽ ጋር እኔ እሆናለሁ አለኝ በጣም አምነዋለሁ እወደዋለሁ በቃ ልክ እንደአባቴ ነዉና የማየዉ እሽ ብየ ትምህርቴን መማር ጀመርኩ መሄድ መምጣት እንጂ ትኩረት ሰጥቶ መማር የማይታሰብ ነዉ ሁሌም ክላስ ሁኜ እማየ ምን ሁናብኝ ይሆን ምግብ ሰጧት ይሆን .....እያኩ አስባለሁ የቤት ስራ አልሰራ ክፍል ዉስጥ አልሳተፍ እንደ ድንጋይ ተቀምጨ ሲደወል እወጣለሁ

አንድ ቀን እየተማርኩኝ በጣም ጨነቀኝና ካለ ሰአቱ እቤት ስሄድ የአባየ ጓደኛ ትራስ ይዞ እማየ አጠገብ ወደሷ አጎንብሷል እኔም ደህና ዋላቹህ ብየ ገባሁ ወድያዉ የአባየ ጓደኛ ደህና ዋልሽ የኔ ልጂ አለና የያዘዉን ትራስ የእማየን አንገት አስደግፎ አስተኛት ይሄኔ በጣም ደስ አለኝ ከኔ ይበልጥ እሱ እንደሚከባከባት ሳቅ እረፍት ተሰማኝ ምን አለ እማየ ቶሎ ብትድንና ቢያገባት ብየ ተመኘሁ ግን መቸ ነዉ የምታገባዉ እስካሁን ብታገባኮ እህትና ወንድም ይኖረኝ ነበር አልኩት እሱም
" መቼ እንደምንጋባ አላቅም ገና እሷ ፍቃደኛ ትሆን አትሁን የማቀዉ ነገር የለም ብቻ ቶሎ ይሻላትና ብንጋባ".....አልጨረሰዉም እስኪ ፀልይልኝ የህፃን ፀሎት ይደርሳል አለኝ ግራ ገባኝ ....."ቶሎ ተሽሏት" ምን ለማለት ነዉ እእእእእ ታማለች ማለት ነዉ አልኩ እሱም ደንገጥ ብሎ ምን! ታማለች ማን አለሽ ሲል ገገመ ሰምቸሀለሁ ብለዉ አይ ተሰስተሽ ነዉ አላልኩም አለኝ እኔም ዉስጤን ደስ እያለዉ አንተ አላልኩም ብትል ሁሉ ነገርህ እማን እንደወደድካት ያስታዉቃል እያልኩ በፈገግታ ወደ እማየ ልስማት ጠጋ ስል የማየ ሁለቱም አይኖቿ እንባ ሞልተዉ ይፈሳሉ እማ እማ.....አመመሽ?
ምን ሆንሽብኝ! ስል የአባየ ጓደኛ "አይ ምንም አልሆነችም ሁሌም እኔን ለምን አታገባም ትለኝ ነበር እኔም ችግሬን አማክራታለሁ አየሽ አሁን ስለጋብቻ ስታወሪ የነገርኳት ችግር ትዝ ብሏት ነዉ"
....ወይኔ እማየ አላወቁም ብየ እንባዋን ስጠርግላት የአባየ ጓደኛ መጣሉ ቡሎ ወጣና ትንሽ ቆይቶ መጠጥ ይዞ መጣ ያየሁትን ማመን አቅቶኝ መጠጥ ነዉ ወይስ... አልኩት 👇👇👇
እሱም መጠጥ አይደለም አለኝና ይዞት ገብቶ መጠጣት ጀመረ እኔ እማየ የተኛችበትን አልጋ ተደግፌ መሬት ላይ ተቀምጫለሁ እሱ ከኔ ራቅ ብሎ ሶፋ ላይ ተቀምጦ መጠጣት ጀመረ በትኩረት እይን አይኔን ያየኛል የእማየ አይን እሱን እሱን ያያሉ ከመሀል ተነሳና የኔ ቆንጆ ብሎ ወደኔ
ተጠጋ እኔም ነገሩ አላማረኝምና ሸሸሁት


በአላህ ፍቃድ
ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል1⃣1⃣

...... ሰሚራ ሽኩር


....."የኔ ቆንጆ ብሎ ወደኔ ተጠጋ እኔም ሁኔታዉ አላማረኝምና ሸሸሁት ወደ እማየ ተጠጋሁ አሁንም የኔ ቆንጆ ብሎ ወደኔ ተጠጋ እኔም በጁ ያለዉን መጠጥ ልቀማዉ ወደሱ ስጠጋ መጠጡን መሬት አስቀመጠና ጠቅጥቆ ያዘኝ
..... ልቀቀኝ አሳመምከኝ አልኩት እሱም "ዛሬ ከኔ እጂ አታመልጭም" እያለ ልብሴን ሊያወልቅ መታገል ጀመረ እኔ ምንም የማዉቀዉ ነገር የለም እህ ምንድን ልታደርገኝ ነዉ ልቀቀኝ አልኩት እሱም ነይ እያለ ይጎትተኝ ጀመር እኔ ከሱ እጅ ለማምለጥ ስታገል እሱ ልብሴን ለማዉለቅ ሲታገል እማየ እያየች ታለቅሳለች መነሳት አይሆንላት ተነስታ አትመጣ መጮህ አትችል ጩሀ አትገላግለኝ ማልቀስ ብቻ!


..........ልቀቀኝ እያልኩ ብጮህ አለቅም እያለ መታገል ጀመረ አባክህ እባክህ.... ብለዉም ነይይይይይይ!..... እያለ ሲጎትተኝ ጉርዴ ወለቀ አሁንም ለመሄድ ስሮጥ ነይ እያለ ሲጎትተኝ ጃኬቴን አወለቀዉ ሱሪና ቲሸርት ለብሸ ከሱ ለማምለጥ መታገል ጀመርኩ እንዴት ላምልጥ እሱ በጣም ግዙፍ እኔ አንድ ፍሬ በመጨረሻም እኔን የያዘበትን እጁን ነከስኩና እያለቀስኩ እማየ እማየ እያልኩ ወደማየ ሂጀ ተሸጎጥኩ እሱም እናትሽ የምታስጥልሽ መስሎሽ ነዉ እያለ በንዴት መጣብኝ ምን ልሁን ከእማየ አጠገብ ሲጎትተኝ ከአንድ ግድግዳ ወደ አንድ ግድግዳ መሮጥ ጀመርኩ በሩን ከፍቸ እንዳልወጣ በሩን ቆልፎ ቁልፉን ይዞታል ምንም አማራጭ የለኝም አሱ እየተከተለ ሱሪየን ለማዉለቅ ሲታገል እኔ ሁለት እጆቸን በሁለት ጭኖቸ መሀል አስገብቸ እማ እማ የኔ እናት እናቴ አማየ
ገላየን ስታጥቢኝ ማንም እንዳይነካብሽ ያልሽኝን ሊነካብኝ ነዉ እማ ሊነካብኝ ነዉ እናቴ ሊነካብኝ ነዉ .....ብጮህ ብጮህ ማን ይድረስልኝ ቃሌ እየደከመ ቀስ ቀስ እያልኩ እማ እማ ማለት ጀመርኩ በመጨረሻ ታግሎ ልብሴን አዉልቆ ከጨረሰ ቡኋላ የሱን ልብስ ሲያወልቅ
በማርያም በማርያም.... እባክህ ልለምንህ ምንም አታድርገኝ እህት የለህም እሽ እናት እባክህ እማ ማንም እንዳይነካሽ ብለኛለች አትንከኝ በማርያም በእግዚአብሄር እሽ በናትህ በቃ እሽ በአባትህ ........እያለቀስኩ ብለምነዉ ብለምነዉ....... ሰዉ ያልሆነ ቆዳ ለበስ ሰይጣን ነዉና በአስር አመቴ ክብረ ንጽህናየን እማየ እያየች ወሰደዉ አልቻልኩም እማ አመመኝ ያማል እማ ያማል......እማማማማማማ ብየ ራሴን ሳትኩ ከዛ ቡኋላ ራሴን ሆስፒታል ዉስጥ ግልኮስ ተተክሎልኝ አገኘሁት ከአጠገቤ የአባየ ጓደኛ ተቀምጧል ራቅ ብሎ የኔን መንቃት ዳክተሩ ይጠባበቅ ነበረና ፈጠን ብሎ ነቃሽ ተረጋጊ አንዴ መጣሁ ብሎኝ ወጣ የአባቴ ጓደኛን ሳየዉ ቀፈፈኝ ሰይጣን እንጂ ሰዉ አልመስለኝ አለ ሌላ የማላቀዉ ሰዉ ሆነብኝ።


...... ጠጋ አለና "የተፈጠረዉን በሰአቱ አላቅም ሰክሬ ስለነበረ ነዉ አሁን ልብ ብለሽ ስሚ ለዶክተሩም ይሁን ለሌላ ሰዉ እኔ እንደደፈርኩሽ ብትናገሪ አንችንም ሆነ ያች ያልጋ ቁራኛ እናትሽን እንዳባትሽ እደፋቹሀለሁ!ሰማሽ እደፋቹሀለሁ! አለኝ ምን ላርግ አለቀስኩ በተለይ የአባቴ ገዳይ እንደዛ የሚወደዉ የገዛ ጓደኛዉ መሆኑን ሲነግረኝ አላመንኩም ሂወት መረረችን መኖሬን ጠለሁት ዳክተሩና የስነልቦና አማካሪ መጠዉ "ምንም የተፈጠረ ነገር የለም አታልቅሽ ይሄኮ ቀላል ነገር ነዉ ይከሰታል"....... እያሉ ሲያፅናኑኝ ቆይተዉ
... አባትሽ ትምህርት ቤት አምሽተሽ ስትመጪ እንደተደፈርሽ ነግሮናል እስኪ እንዴት አድርገዉ ስንት ሰአት? እነማን?.....እንደሆኑ የምታስታዉሹዉን ንገሪን አሉኝ ምን ብየ ልንገራቸዉ አለቅሳለሁ አይገባቸዉም በቃል አልችልም ዝም ብየ አለቅሳለሁ ንገሪን አይዞሽ አሉኝ ምን ልበል እማ እማየ አልኩ እናትሽ ደህና ናት አንች ብቻ የጠየቅንሽን ንገሪን ማን ነዉ የደፈረሽ አሉኝ ምን ልበል አባቴ በጣም የሚወደዉ ጓደኛዉ ወይስ የእማየ ባል ለኔ አባቴ እንዲሆን የምመኘዉ ሰዉ....... ምን ልበል እዉነቱን ብናገር ለኔ ችግር የለብኝም አንዴ ገድሎኛል ሙቻለሁ ህልሜ የለኝም ህልሜን ለደቂቃ ስሜቱ ሲል ገሎታል! የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ነዉ ሞትን አልፈራም ሞት ለኔ እረፍት ነዉ ተናግሬ ብሞት ምንም አይመስለኝም እማየ ግን ምን አጠፋች በኔ ሰበብ ልትሞት... አይሆንም ከራሴ ጋር ስሟገት ቆይቸ የደፈረኝን አላቅም ምሽት ስለነበረ አላየሁትም ብየ ዋሸሁ እንዲህ ሰል የአባየ ጓደኛ ፊቱ ላይ የደስታ ስሜት ይታይበት ነበር


የአባየ ጓደኛ በቃ እናቷን ለማየት የጓጓች ትመስላለች እንሂድ ብሎ ከሀኪም ቤት በመኪና ይዞኝ ወደ ቤት መጣን ወድያዉ እማ እማየ ብየ ተጠመጠምኩባት እሱም ይቅርታ ሰክሬ ስለነበረ ምንም የማስታዉሰዉ ነገር የለም ብሎን ሄደ እማየ ማልቀስ ጀመረች እእእእእእእእእ....ምን ልትለኝ እንደሆነ አላቅም የሆነ ልትነግረኝ ያለችዉ ነገር እንዳለ ትለያለች ምንድን ልትለኝ ይሆን ምንም የጠረጠርኩትም የማቀዉም ነገር የለም።
... ዝም ብላ ታለቅሳለች አለቅሳለሁ በመጨረሻ ዉስጤ እያለቀሰ ፈገግ ለማለት እየታገልኩ እማ እኔኮ ደህና ነኝ እማየ ደህና ነኝ አልኳት እሷ ግን ከማልቀስ ለደቂቃዎች አላረፈችም ታለቅሳለች ወድያዉ የአባየ ጓደኛ አንድ ቄስና ቀለበት ይዞ እማየን ሰማንያ/በሙስሊሞች ኒካህ አሰርኩኝ አለ ከዚች ቀን ጀምሮ ለኜ የደፈረኝ የእንጀራ አባቴ ለማየ ባሏ ሆነ ግን የኔ ደደብነት ግርም ያደርገኛል የዛኔ ለምን ሰማንያ እንዳሰረላት የማዉቀዉ ነገር የለም ብቻ አሰረላት አባየ ያፈራዉን ንብረት ሁሉ ወደሱ አካዉንት አስገባ ቤቱን የማየን እጂ ይዞ እንድትፈርም አስገደዳት ከዛ ቡኋላ ምግብ ልንሞት ሞት አፋፍ ላይ ስንደርስ በበላን በአራት ቀናችን ትንሽየ ዳቦና ዉሀ ይሰጠናል ቤት እንደከብት ቆልፎብን ይዉላል በቃ ይሄ ነበር ቀን ከቀን ሂወታችን ሲያስፈልገዉ እማየ ፊት ይደፍረኛል በአንድ ቤት እናትና ልጂ የሱ ሚስት ሆን።
ቀን ከቀን የማየ ህመም እየባሰባት ሄደ ምግብ በበላን በሶስተኛዉ ቀን ራቡን፤ የልጇን ስቃይ ማየት ሲመራት አልቅሳ አልቅሳ ላትመለስ አሸለበች።
...አባየ ወደ ሄደበት እሷም ሄደች እኔም አለቀስኩ........
አለቀስኩ በልቅሷ የሞተ ሰዉ የሚመለስ ቢሆን የኔ እንባ የአንድ ሀገርን ሰዉ ከሞት በመለሰ ነበር ብቻ እኔም እማየ ከሞተች ቡኋላ የእንጀራ አባቴ ማለቴ የአባየ ጓደኛ ልብሴን ይዜ እንድወጣ አዘዘኝ በገዛ ቤቴ ሲጫወትብኝ ኑሮ እንደቃ አዉጥቶ ጣለኝ ... የአባቴ ገዳይ የእናቴ የመሞቷ ስበብ የሆነዉ ቤታችንን ወርሰዉ ምን ላርግ ልብሴን ይዤ ወደ ጓዳና ወጣሁ እዛም ብዙ የጎዳና ልጆችን ተዋዉቄ አምስት አመቶችን አሳለፍኩ አንዴንዴ ይርበኛል፤ይበርደኛል፤ አለቅሳለሁ ፤እስቃለሁ አጨሳለሁ፤ እቅማለሁ ....በቃ ሂወቴ እንዲህ ሆነ ከጓደኞቸ ብዙዎቹ በሴተኛ አዳሪነት በየሆቴሉ ይሰራሉ አሪፍ ክፍያ ልከፈላሉ ሂወታቸዉም ጥሩ የሚባል መሆኑን ሳይ እኔም ቢያንስ አይርበኝም፤አይበርደኝም.... ተንግዲህ ሆዴ በምግብ ማጣት አይጫህም ብየ ገባሁበት ወደ አምስት አመት ሰራሁ ሂወቴ የሚያስጠላ ቀፋፊ ቢሆንም ሳልወድ ወደድኩት በቃ!


.......አንድ ቀን የአባየ ጓደኛ እኔ ተቀጥሬ የምሰራበት ሆቴል አልጋ ሊይዝ ሲመጣ አየሁት

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Scienc
ለማንኛዉም 👇👇👇 ሀሳብ አስተያየት
@Meh_Ani_bot
መራራ እዉነት
ክፍል 1⃣2⃣

..... ሰሚራ ሽኩር


.....አንድ ቀን የአባየ ጓደኛ እኔ ተቀጥሬ የምሰራበት ሆቴል አልጋ ሊይዝ ሲመጣ አየሁት በጣም ተቀይሯል ጎዳና ከወጣሁ ጀምሮ አይቸዉ አላቅም ደነገጥኩ የማረገዉ ጠፍብኝ ሂጀ ብጥስጥስ አድርጌ ብገለዉ ደስ ባለኝ ብቻ ከእግሬ እስከ ፀጉሬ ድረስ ወረረኝ ሁሉም ግፍ ትዝ አለኝ ራሴን አረጋጋሁና የናቴን፤ የአባቴንና የኔን ሂወት ምስቅልቅሉን ያወጣዉን የእንጀራ አባቴን እንዴት መበቀል እንዳለብኝ ማሰብ ጀመርኩ


........ አንድ ሀሳብ መጣልኝ ዛሬ ከሱ ጋር ማደር ከዛ የማረገዉን አቃለሁ።
...ከሱ ጋር ልታድር የነበረችዋ ሴት ጋር በጣም ስለምንቀራረብ ነገርኳት እሷም "ፒስ ይመችሽ" ብላ አሳልፋ ሰጠችኝ እኔም በጣም ቆንጆ ሁኘ እንዳይለየኝ ተጠንቅቄ አብሬዉ ስበላ፤ስዝናና ካመሸሁ ቡሀላ ወደ መኝታ ክፍል ቁጥር 22 ወሰደኝ እኔም እየሳኩ በዉስጤ ማንነቴን ባወቀ እያልኩ ተከተልኩት መብራት አብርተን በሩን ቆልፌ በተራየ ቁልፉን ራሴ ይዠ ገባን ልብሱን አዉልቆ ነይ ማሬ አለኝ መጠጥ በአንድ እጁ ይዟል እኔም እሽ አልኩና እንዳይለየኝ የተቀባሁትን ሜካብ ታጥቤ ዉዱ የእንጀራ አባቴ እንዴት ነህ እናቴን አግኝተሀት ታቃለህ? አባቴስ እንዴት ነዉ? እያልኩ ከመታጠቢያ ክፍል ወጣሁ
ለነገሩ ለምን እጠይቅሀለሁ ከሰአታት ቡኋላ ስለምታገኛቸዉ ሰላም እንድትልልኝ እሽ አልኩት
....በአንድ እጀ ስል ጩቤ ይዠ ቀረብኩት ደነገጠ ላቡ በፊቱ ተንጠፈጠፈ እጁ መንዘርዘር ጀመረ ማን ነሽ ማን ነሽ አንች ትግስት ነሽ አላምንም እያለ.......መርበትበት መሸሹን ተያያዘዉ



ሀሀሀሀሀ አረሰኸኝም ትግስት ነኝ
ያች በአስር አመቷ የደፈርካት
የምትወደዉ በጣም የምሳሳለትን አባቷን የገደልክባት
እናቷን ያሰቃየህባት
በጨቅላ እድሜዋ ህልሟን የቀበርክባት

ለደቂቃ ስሜት ብለህ ህወቷን ያጠለሸህባት
አስታወስካት ትግስት
ያች እንደዉም እማ እያለች ስትጮህ የደፈርካት
አስታዉስ ምግብ በአራት ቀን ልትሞት ስትል የምሰጣት
በረንዳ የወረወርካት
አታስታዉስምምምም?

"አስታዉሳለሁ አስታዉሳለሁ ......ትግስቴ የኔ ዉድ ልጂ የዛኔኮ እእእእእ ምንም የማስታዉሰዉ ነገር የለም እእእ አባትሽ የሰራሁበትን ብር አልሰጥም ሲለኝ ነዉ የየየየየገደልኩት አንችን የደደደፈፈፈርርርኩኩኩሽሽሽ ሰክሬ አላወኩም"....ምን ይበል

እ* ከቤት ያስወጣኸኝም ሰክረህ ነዉ አይደል!ስል ጠየቁት እሱም አአአወ መለሰ

ብገለዉ የናትና የአባቴን ደመኛ ተበቀልኩላቸዉ ደስ ይላቸዋል ጊዜ ማጥፋት አልፈለጉም ጓዳና ተዳዳሪ ጓደኞቸን ጠራሁና ይዘዉት ወደ ጫካ እንዲሄዱ አደረኩ ተባብረን ገደልነዉ!ገ*ደ*ል*ነ*ዉ ሰማቹህ የአባቴን፤ የናቴን ፤የህልሜን ገዳይ ገደልነዉ።
... ከዛ ወደ ቤቴ ስመጣ አንዳንድ የጓዳና ተዳዳሪዎች የእንጀራ አባቷን ገደለችዉ ጨካኝ! እያሉ ማዉራት ጀመሩ

.....ይሄን ስሰማ ቶሎ ፓሊስ ሳይዘኝ ሀገር ቀይሬ ሄድኩኝና ሌላ ሀገር አዲስ ሂወት መኖር ጀመርኩ ነገር ግን ህሌናየን ረፍት ነሳኝ አላስቀምጠኝ አለ በህልሜ እማየና አባየ ለምን! ለምን! ገደልሽዉ ትግስቴ ይሉኛል መተኛት አልቻልኩም ቅዠት አላስተኛ አለኝ አልበላ በጩቤ ስወጋዉ እየመጣብኝ አላስበላኝ አለ በዛ ላይ ሌባና ፓሊስ ድብብቆሽ መጫወት መረረኝ ምን ተሻለኝ ሰዉን ብሸሸዉ ህሊናየን እንዴት ልሽሸዉ አልቻልኩም!!!

....ፖሉሶችም እያፈላለጉኝ እንደሆነ ጓደኞቸ ነገሩኝ እስከመቸ ሀጥያት ሰርቸ እየተደበኩ እኖራለህ የላይኛዉ መግቢያየስ ምን ይሆን? ከፖሊስ ብደበቅ ከጌታ እደበቅ ይሆን?.....ገራ ሲገባኝ ፖሊሶችም ሊይዙኝ እንደሆነ ሳቅ ቢያንስ ወንጀሌ ቢቀል ብየ እጂ ሰጠሁ አሁን ወንጀሉን እያጣሩ ነዉ ታሪኬ እንግዲህ ይሄን ይመስላል! "

ዞር ብላ ሁላችንንም ካየች ቡኋላ "ኧረረረ የምን ማለቃቀስ ነዉ" አለችን እዉነትም ሂወት መራራ እዉነት እንጂ ጣፋጭ ተረት አይደለችም! አልኩ አሁን በትግስት ስንት አመት ይፈርዱባት ይሆን ስል አሰብኩ ምናልባት ወደ ሀያ ምናምን ወይም የድሜ ልክ ያስሯታል ይሄ የዱንያ ቁጣቷ ነዉ ነገር ግን የአሂራዉን ስናይ አላህ(ሱ.ወ)በቁዱስ ቁርአን ላይ የሰዉን ነፍስ ማጥፋት እንደሌለብን ሲገልፅ ፦
"ለምእመን በስህተት ካልሆነ በቀር ምእመንን መግደል አይገባዉም" (አን-ኒሳህ ፡92)


በሌላ የቁርአን አያ የሰዉን ልጂ ሂወት ያጠፋ ቅጣቱን ሲነግረን እንዲህ ይላል ፦ "ምእመንንም ሆነ ብሎ የሚገድል ቅጣቱ በዉስጧ ዘወታሪ ሲሆን ገሀነም ናት አላህም በእርሱ ላይ ተቆጣ።ረገመዉም ።ለእርሱም ከባድ ቅጣትን አዘጋጀ።(አን -ኒሳህ፡93) በበዙ አያዎች የሰዉን ልጂ ሂወት ማጥፋት እንደሌለብን ይነግረናል ምናልባትም በዱንያ ቅጣቱ ከበደ ቢባል የሞት ፍርድ ይሆናል የአሂራዉ ግን ጀሀነም እድሜ ልክ ሞት የሌለበት ከባድ ቅጣት ነዉ የሚጠብቀን።


ትእግስት የስቃይን ጥግ አይታለች ብንል እንደኛ እይታ ስነየዉ እሷ በአንደበቷ ስለነገረችን እንጂ ከዚህ የበለጠ በየቤቱ ቢፈተሽ ስንቱ ጉድ አለ? ስንት የታፈነ ሰሚ ያጣ ጩኸት አለ? ስንት ያልታየ ያልተሰማ ስቃይ አለ?።
አልሀምዱሊላህ ማለት ተስኖን ቀን በቀን እናማርራለን ሁሌም መጥፎ አጋጣሚዎች ሲፈጠሩ ለኸይር ነዉ ከማለት ዉጭ እድሌ ማለት ይቀናናል ዛሬ ባልሰረኩት ሰረቅሽ ተብየ ፓሊስ ጣቢያ ስገባ ያረብ ምን አረኩት እያልኩ አምርሬ አልቅሸ ነበር መች ለኸይሩ ይሄን ታሪክ ሊያሰማኝ እንደሆነ ገባኝ!አሁንማ እዚኸዉ ቆይቸ የአራቱንም ታሪክ መስማትን ተመኘሁ...


.......ትግስት ዝም ብላ ከቆየች ቡኋላ እንዴ! የናንተን ንገሩኝ እንጂ የኔ በአጭሩ የነገርኳቹህን ይመስላል አለች አንዷ ሂወት እባላሁ የኔን ታሪክ ላጫዉታቹህ ብላ ታሪኳን መናገር ጀመረች


በአላህ ፍቃድ
ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 1⃣3⃣

..... ሰሚራ ሽኩር

....ትግስት ዝም ብላ ከቆየች ቡኋላ "እንዴ! የናንተን ንገሩኝ እንጂ የኔ ባጭሩ የነገርኳቹህን ይመስላል " አለች አንዷ ሂወት እባላለሁ የኔን ታሪክ ልንገራቹህ ብላ መናገር ጀመረች "እለፍ እለፍ እያልኩ ታሪኬን በትንሹ ልንገራቹህ እንግዲህ መስማት ብቻ ትርጉም የለዉም ልብ ብላቹህ አዳምጡ! በመጨረሻም ፍርዱን ለናንተ እተዋለሁ።

........የዛሬ አስር አመት አካባቢ በጣም ቀይ ቆንጂየ ደስ የምል ለግላጋ ወጣት ነበርኩ።እድሜየም ለትዳር በደንብ ደርሶ ነበርና ብዙ ወንዶች ለትዳር መጠየቅ ጀመሩ አንዳንዶቹ ሀይማኖተኛ ፤አንዳንዶቹ ጥሩ ፀባይ ያላቸዉ ፤አንዳንዶቹ በጣም ሀብታም፣አንዴንዶቹ ደሀ.... ነበሩ ወላጆቸ ከሁሉም የተሻለ ሰዉ ሊድሩኝ መመካከር ጀመሩ ምርጫቸዉም በጣም ሀብታም ሰዉ ሁሉን ነገረ የሚያሟላልኝ በገንዘቡ ሁሉንም እያረገ የሚያስደስተኝ ሰዉ ሆነ ምክንያቱን ስጠይቃቸዉ ሀብታም ካገባሽ ሀብታም ትሆኛለሽ፤የፈለግሽዉን ማግኘት ትችያለሽ፤ ሰዉ ይወድሻል....በቃ ሀብታም ነዉ የምታገቢ ተባልኩ ማንና ምን እንደሆነ የማቀዉ ነገር የለም ብቻ ታገቢዋለሽ ሀብታም ነዉ መኪና አለዉ ፤ብዙ ብር አለዉ......ተባለ እኔ አላዝዝም በኔ ወላጆቸ ናቸዉ አዛዦች እኔ ፍቃደኛ ልሁን አልሁን ጉዳያቸዉ አይደለም በሰርጉ እኔ ባልስማማም እነሱ ተስማሙና ማግባት አለብሽ አሉኝ እኔም እሽ ብየ አገባሁት


.......ስሙ ሳሙኤል ይባላል እንዳሉትም የእዉቀት ድሀ ሁኖ የገንዘብ ሀብታም ነዉ !!! በገንዘቡ የፈለገዉን እንደሚያገኝ፤ የሚፈልገዉን እንደሚያደረግ ምንም የሚያቅተዉ ነገር እንደሌለ ደጋግሞ ይናገራል ይሄ ወሬዉ ሁሌም ያናድደኛል የሚያስብ ስለገንዘብ የሚያወራ ስለገንዘብ ሁሉ ነገሩ ገንዘብ ነዉ የታመመ ሰዉ እንኳን ሲያይ አየሽ ገንዘብ ቢኖረዉ ታክሞ ይድን ነበር ይላል ያጨሳል ፣ይቅማል ፤ዉጭ ያድራል.....ገንዘቡን ለሰዉ አይሰጥ ቆጥቋጣ ስግብግብ ነዉ እኔ አንዳንዴ ምግብ ለሌላቸዉ የሚበላ ነገር እየተደበኩ ለጎረቢቶቻችን እሰጣለሁ እናቱ ስሰጥ ታይና ልጁ ሲመጣ ገንዘብህን ለማንም እየሰጠች ጨረሰችልህ እያለች ታጣላን ነበር እሱም ገንዘቤን ለምን እያለ ይመተኝ፤ይሰድበኝ፤ያሰቃየኝ .....ነበር እኔ ግን ትዳሬ ይበልጣል ብየ ችየዉ ተቀመጥኩ።


....... አንዳንዴ እየተናደድኩ ገንዘብ ገንዘብ ስትል ምናለ ፈጣሪየ ባደኸየህ አለዋለዉ እሱም ሀሀሀሀ ብሎ እየሳቀ አንች ስላልሽ ነዉ እንኳን አንች ብለሽ እሱም ብሎ አልደኸይም በላቤ ደክሜ፤ ለፍቸ ጥሬ ግሬ ...... እንጂ እሱ አልሰጠኝም ሲል ያሾፋል ጌታም ይሄን ሰምቶ ነበርና ገንዘቡን የተወሰነዉን ወስዶ ጤና ነሳዉ ሙሉ አካሉ ፓራላይዝ ሆነ እንዳይነሳ፤ እንዳይቀመጥ፤ እንዳይንቀሳቀስ አድርጎ አስተኛዉ ።

....እኔም እእእእእ በገንዘቤ ታክሜ እድናለሁ ብለህ አልነበረ ሞክረዉ አልኩት ገንዘቡ አልቆ የሚበላ እስከሚጠፋ ድረስ በየሀኪሙ ገንዘቡን ጨፈጨፈ መዳን የለም።
አንዳንዴ ለዚህ ሁሉ ምክንያት አንች ነሽ ይላል እንዴት ስለዉ ባለፈዉ ምናለ ጌታየ የሰጠኸዉን ብትወስደዉ ብለሽ ነበር ይሄዉ ሰምቶሽ ገንዘቤንም ጤናየንም ነሳኝ እንኳን ደስ ያለሽ ይለኛል እኔም እህ ገንዘብም ሆነ ሌላ ነገር ሁሉንም በራስህ ማግኘት እንደምትችል እርግጠኛ ነበርክ እና ዛሬ ማን ይዞህ ነዉ ጤናህን መግዛት ያቃተህ ገንዘብህን መሰብሰብ የቸገረህ መብላት መጠጣት መምጣት መሄድ ለምን አልቻልክም መልስልኝ እለዋለሁ እሱም ዝምታን ይመርጣል እየህ ሁሉም ያለዉ በሱ በፈጣሪ እጂ እንጂ በኛ አይደለም እሱ ያለዉ ይሆናል እኛ ያልነዉ ሳይሆን
... በል ወደ ጌታህ ተመለስ ይቅርታ በለዉ አልኩት እሱም ጥጋቡ አልለዉም ጤናየንና ገንዘቤን ይመልስ አለ እኔ ምን አገበኝ የድርሻየን ተወጥቻለሁ።


......የባሌ የሳሙኤል ህመሙ አልሻል ሲለዉ ጨነቀኝ ምን ልሁን የምንበላዉ እንኳን ሳይኖረን ብሩ ሀብት ንብረቱ ሁሉም አለቀ
በሂወት ለመቆየት የግድ መመገብ አለብን ለመመገብ ገንዘብ ያስፈልጋል ለገንዘብ ደግሞ ስራን ሳይንቁ መስራት ነበረብኝና ተደራጂተን ደረቅ ቆሻሻ በየቤቱ እየሄድን ቆሻሻ ማዉጣት፤መንገዷችን ማፅዳት ...... ጀመርን የዚህ ብር ቢያንስ ለምግብ ይበቃናል ለሱ መድሀኒት ደግሞ ከጠዋት ፅዳት ስንሰራ ከቆየን ቡኋላ ከሰአት ደግሞ መንገድ ዳር በቆሎ እየጠበስኩ መሸጥ ጀመርኩ ሁሉም ሰዎች ተገረሙ እንደዛ ሀብታም የነበሩት እያሉ ስለኛ ያወሩ ጀመር ያሉትን ይበሉ ለተራ ወሬ ቦታ አልሰጥም ጊዜ የለኝም! ሂወት ተገለባባጭ ናት ያጠዉ ሲያገኝ፤ያገኘዉ ሲያጣ፤የታመመዉ ሲድን፤የዳነዉ ሲታመም፤የወደቀዉ ሲነሳ፤የተነሳዉ ሲወድቅ፤ያበደዉ ሲድን ጤነኛዉ ሲያብድ፤ ሲሞት ሲወለድ .......

...ብቻ የበቆሎየ ትርፍ ለመድሀኒቱ መግዣ ሆነኝ ሲለፋ አምሽቸ ደክሞኝ እንደመጠሁ ማታ ሰዉነቱን አጥቤ ልብሱን ቀይሬ ገላዉን በቫዝሊን አሽቸ እተኛለሁ ያልፍል እያልኩ ለሰባት አመት ስቃየን አየሁ ከዛሬ ነገ ይድናል በሚል ተስፋ ተሰቃየሁ ያልጋ ቁራኛ በሆነ በሰባት አመቱ ተሽሎት እንደድሮዉ መስራት ጀመረ ደስ አለኝ


ደስታየን አጠጥሜ ሳላበቃ እንች አሮጊት ባርያ፤በልቶ አይጠግብ ቀጫጫ ስታስጠይ .....እያለ መሳደብ ጀመረ ፀባዩ ሁሉ ተቀየረብኝ ሰባት አመት ሙሉ ልፋቴ ለዚህ ነበር እንዴ አልኩ የጠቆርኩ የሱን ሆድ ለመሙላት በየሰዉ ቤት በፀሀይ እየሄድኩ ቆሻሻ ሳፍስ ፤የከሳሁ በሱ አሳብ ካለ እንቅልፍ ሳድር፤ያረጀሁ በጨለማ በበቆሎ ጠበሳ የሱን የመድሀኒት ወጭ እሸፍናለሁ ስል......በቃ ነገሩ ሁሉ ገረመኝ አይ ሰዉ ለካ ምንም ብታደርጉለት ምስጋና ቢስ ነዉ ያኔ ሲታመም እንደሌሎች ሴቶች ብሆን ኖሮ ጠጥየዉ ሂጀ ነበር እኔ ግን አምላኬን እፈራሁ እንኳን የማዉቀዉ ባለቤቴን የማላዉቀዉ ምንገደኛም ቢሆን አያስችለኝም።



.......አንድ ቀን ከስራ መልስ ድክም ብሎኝ ቤት ስመጣ ቤቱ አልተቆለፈም ነበር ክፍት አድርጌዉ ገባሁ ከዉጭ የሴት ጫማ አለ ማን መጦ ነዉ ብየ ገባሁ ሳይ ባሌ ከአንድ ሴት ጋር አንሶላ ይጋፈፋል ያየሁትን ማመን አቃተኝ ሳሚ ብየ ጮሁኩ ወይ መደንገጥ አልደነገጠም እሷ አፍራ ምነዉ?ማነሽ?ስትል ጠየቀችኝ እኔም እእእእእእ....ስንተባተብ እሱ ሰራተኛየ ናት አለኝ እኔም በጣም ተናደድኩ ጭራሽ ሰራተኛየ ብየ ወደ እቃቤት ሂጀ የቡና የብረት ዘነዘና ነበር እንደተናደድኩ አምጥቸ ባሌ ላይ ብወረዉር አናቱን አልኩት


በአላህ ፍቃድ
ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 1⃣4⃣

....... ሰሚራ ሽኩር

እንደተናደድኩ ብወረዉር አናቱን አልኩት አንዳንዴ ንዴታችንን መቆጣጠር ካልቻልን የድሜ ልክ የሚፀፅተንን ነገር እንሰራለን የኔ የደቂቃ ንዴቴ ለድሜ ልክ ፀፀት ጋብዞኛል ምናልባትም ቤተሰቦቸ ምናለ ለሱ ባይድሩኝና ደሀም ቢሆን ጌታዉን ለሚፈራ ጥሩ ፀባይ ላለዉ ሰዉ በዳሩኝ ብየ አስባለሁ ምናልባት ለሀብታም የዳሩኝ ጥሩ ሂወት እንድኖር ካላቸዉ ጉጉት የተነሳ ሊሆን ይችላል።

........ለነገሩ ሀብታም ብቻ ነዉ እንዴ ጥሩ ኑሮ የሚኖር አይደለም! ደሀም ከሀብታም በበለጠ ጥሩ ሂወት ይኖራል ገንዘብ ቁስ ነገርን እንጂ ፍቅርን የት ሲገዛ አየን? እሽ እንደዉ በገንዘብ ፍቅር ይገዛል ብንል የተገዛዉ ፍቅር ፍቅር ነዉ አይደለም! ገንዘቡ ሲያልቅ ፍቅሩም ያልቃል ሁሌም ምርጫችን ለገንዘብ ሳይሆን ለማንነት ቅድሚያ እንስጥ ገንዘብ ይመጣል ይሄዳል ዛሬ ላንተ ነገ ለሌላ ነዉ። ገንዘብ ወረቀት እንጂ ሌላ አይደለም ለወረቀት ደግሞ ራሳችንን አሳልፈን መስጠት የሚያስጠላ ነገር ነዉ ገንዘብን ጠንክረን ከሰራን ሰዉ የቆጠረዉን መቁጠር አንችላለን .....ብቻ ታሪኬ በአጨራረስ ቢሆንም ብዙ ነገሮችን ተምሬበታለሁ"


.....የአላህ የሁለቶችም ታሪክ አስተማሪና አሳዛኝ ነበር ይሄዉ ታሪካቸዉን ስሰማ ነጋ የሶስተኛዋ ልጂ ታሪክን ለመስማት ጓጓሁ እስር ቤት ሳይሆን ሌላ ቦታ ያለሁ መሰለኝ አላህ ለኸይሩ ነዉ ያን ሙሲባ አምጥቶ የታሰርኩ እድሜ ልኬን የማረሰዉ ጥሩ ትምህርት በአንድ ቀን አስተማሩኝ።
አልሀምዱሊላህ ስል አላህን ደጋግሜ አመሰገንኩት ዛሬ አብረን ዉለን የሁሉንም ታሪክ ብሰማ ደስ ይለኛል ያረብ የዛሬን... ብየ ሳላበቃ ሀናን ሰዉ ይፈልግሻል ተብየ ተጠራሁ ማን ይሆን ብየ ስሄድ አባቢ ነዉ


...አባቢ ብየ በፍራት አየሁት እሱም "ሀናኔ ሰላም ነሽ ደህና ነሽልኝ" ብሎ አገላብጦ ከሳመኝ ቡኋላ ፈርሞ ሁሉን ነገር ጨርሶ ነይ እንሂድ አለኝ ለመሄድ ፍቃደኛ አልነበርኩም ስመጣ አማርሬ ስሄድም አማርሬ አይ የኔ ነገር! ...

ታሪካቸዉ በጣም ያሳዝናል የሌሎች ደግሞ ከሁለቶቹ ታሪክ የባሰ ይሆን ስል አሰብኩ እኔጃ ብቻ አባቢ ነይ ብሎ ሳልሰናበታቸዉም ቶሎ ወጣሁ
....ከአባቢ ጋር ወደ ቤት እየሄድን እያለ በምን ምክንያት እንደታሰርኩ ጠይቆኝ ነገርኩት በዛዉም ስለትግስትና ስለ ሂወት ታሪክ አጫወትኩት በታሪኩ ተገረመ

ወላሂ እረስቸዋለሁ አባቢ የዛኔኮ አማኔ መድሀኒቱን ከሰጠሁት ቡኋላ ከአጠገቡ አላነሳሁትም አነሳቹህት ስል በፍራቻ ጠየቁት
እሱም"ሀናኔ የዛኔ ስልካችን አልሰራ ያለሽ አማኔ መድሀኒቱን ሙሉዉን ወስዶት ታሞብን ሀኪም ቤት ስለነበርን ነዉ ስልክ ያላነሳነዉ አዉፍ በይን በኛ ምክንያት እስር ቤት አደርሽ"አለኝ

ደነገጥኩ አባቢ የምርህን ነዉ ወይኔ ጉዴ!አማኔ አሁን እንዴት ነዉ?
ተሻለዉ? የት ነዉ ? ሰል የጥያቄ ማእበል አዘነብኩበት

አባቢም"ሀናኔ ተረጋጊ ተረጋጊ አላህ ለኸይሩ ነዉ የዛኔ አባኔ ታመመ መድሀኒቱን ሙሉ ወሰደዉ ብለዉ
ደዉለዉልኝ ሀኪም ቤት በፍጥነት ነበር የወሰድነዉ ሀኪሞችም ከመረመሩት ቡኋላ ማስታወስ እየጀመረ ነዉ ጤናዉ ባንዴ ወደ ነበረበት ሊመለስ ነዉ አይዞህ አሁን የምናዝዝህ መድሀኒት አለ እሱን ትገዛለህ በትንሽ ቀናት ይድናል "አሉኝ


.....ግራ ገባኝ ማለት እንዴት መድሀኒቱን ለመግዛት መኪናህን ሽጠሀታል በዛ ላይ የአማኔን ሂወት አደጋ ላይ ጥየዉ ነበር እና ይሄ ለኸይሩ ነዉ ትለኛለህ!
"እይዉልሽ ሀናኔ በርግጥ ለመድሀኒቱ ብዙ ወጭ አዉጥቻለሁ ልክ ነሽ ነገር ግን ለኸይሩ ነዉ ያልኩሽ ያኔ አማኔ መድሀኒቱን የወሰደ ቀን ሀኪም ቤት ሁላችንም ደንግጠን ስንሄድ የዉጭ ጥሩ ጥሩ ዳክተሮች መጠዉ ነበር አማኔንም አዩት በለዉጡ በጣም ተገርመዉ አሁን ማስታስ፤ማዉራት ....ይጀምራል መድሀኒቱን መቀየር አለብህ አሉኝ ካወራ፤ካስታወሰ ...ደግሞ ልፋታችን ፍሬ አወጣ ማለት ነዉ "እያለ መሳቅ ጀመረ


......ለምን እንደሆነ ደስ ቢለኝም ከልቤ ደስ አላለኝም የበለጠ ጭንቀት ፤ችግር ዉስጥ የገባን መስሎ ታየኝ ምክንያቱም የባለፈዉን መድሀኒት አባቢ ሲገዛ መኪናዉን ሽጦ ነበር አሁንስ ምኑን ሽጦ ሊገዛዉ ይሆን በገንዘቡ አልል ገንዘብ እንደሌለዉ በደንብ አቃለሁ ንግዱ ቀዝቅዟል ባለፈዉ የትምህርት ቤት ክፍያም የከፈለልን ተበድሮ ነዉ እና አሁን የአማኔን መድሀኒት ከየት አምጥቶ ሊገዛዉ ይሆን ስል አሰብኩ



አባቢም "የኔ ልጂ ምን እያሰብሽ ነዉ"አለኝ
ለካ እናት ብቻ ሳትሆን አባትም ሲጨንቀን ሆነ ስንደሰት ፊታችንን ማንበብ፤ስሜታችንን ማወቅ መረዳት ይችላል ።
አባቢ ባለፈዉ የትምህርት ቤት ክፍያ ስትከፍል ተበድረህ ነዉ እሽ አሁንስ የአማንን መድሀኒት በየትኛዉ ገንዘብህ ልትገዛለት ነዉ ስል ጠየቁት አባቢም ትንሽ ካሰበ ቡኋላ"ወንድሜ ካበደረኝ እጠይቀዋለሁ እንቢ ካለኝ ወደ ጓደኞቸ እዞራለሁ እነሱም እንቢ ካሉኝ ቤቱን በባንክም ቢሆን አስይዘዋለሁ "አለ ምን ቤቱን እንዴት ማለቴ እኛስ የት ልንሄድ


"ሀናኔ እኛ መከራየት እንችላለን ብዙ አመት ለፍተን ትንሽ ሲቀረን እጂ አንሰጥም! ደሞ ሰዉ እያለ ይረዳዳ ከሞተ መቅበር እንጂ ለሱ ምን ይሰራለታል የኛ ኡኡታ ይልቅ በሂወት እያሉ መተጋገዝ፤መረዳዳት፣መዋደድ፤ይቅር መባባል ጠቃሚ ነዉ እኛም እማኔ እያለ እንልፍለት" አለኝ አባቢ እዉነቱን ነዉ በሂወት እያለ ይቅር ያላልነዉ፤በህመም ሲሰቃይ አይዞህ ያላልነዉ፤ ሲቸግረዉ እያየን ያለፍነዉ....ሲሞት ወየዉ ወየዉ ...ማለቱ መጮሁ፤ መዉደቅ መነሳቱ ለሱ ምን ሊጠቅመዉ።
እያልኩ ሳስብ እቤት ደርሰን የግቢዉን በር አንኳኳን ለመጀመሪያ ጊዜ አማኔ በሩን ከፈተልን




በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 1⃣5⃣

...... ሰሚራ ሽኩር


.......እቤት ደርሰን የግቢዉን በር አንኳኳነዉ ለመጀመሪያ ጊዜ አማኔ በሩን ከፈተልን ደነገጥኩ እማኔ አልኩ በዝነት አይኑ አፍጥጦ አያየን ዝም አለ አባቢ ከደስታዉ ብዛት አማን አማን.... እያለ አቀፈዉ ወድያዉ ሪሀና በፍጥነት መጣችና "እ ቁልፍ ይዛቹህ ነበር እንዴ ደሞ መሮጤ" ብላ ተጠመጠመችብኝ አባቢም "ሪሁየ ቁልፍ አልያዝንም የከፈተልን አማን ነዉ አማን ከፈተልን" እያለ ፈገግ ማለት ጀመረ እማየም ሀናኔ መጣሽልኝ የኔ ልጂ ደህና ነሽ ብላ አቀፈችኝ አባቢ አማንን አቅፎት ስታይ ምንድን ነዉ ስትል ጠየቀች አባቢም "አማን ነዉ በሩን የከፈተልን አማን ከፈተልን" እያለ አማንን በዝነትና በፍቅር አይኑ መመልከት ጀመረ።


....የዛሬዋ ቀን እኔ የተፈታሁበት አማኔ ተነስቶ በር የከፈተበት... ለኛ የደስታ ቀን ናበረች ሁላችንም ከአማኔ አጠገብ ተቀምጠን ስናወራ፤ስንስቅ...ከመሀል አባቢ ተጫወቱ መጣሁ ብሎን ሄደ እኔም የትሊሄድ ነዉ ብየ ተከተልኩት ስልክ ሊደዉል ነበር የሄደ ከማን ጋር እንደሚያወራ አላቅም ብቻ አማኔን መድሀኒት በዚህ ሳምንት መገዛት ስላለበት ብድር እየጠየቀ መሰለኝ "ኧረ በአላህ በፍጥነት እመልሳለሁ ለአንድ ወር ብቻ አበድረኛ እኔስ ስንቴ ነበር ያበደርኩህ".....እያለ ሰመሁት ሰዉየዉ እንቢ ብሎት እጁን ወደ ላይ ዘርግቷ እያለቀሰ "ያረብ! አሁን ከየት ላመጣ ነዉ በቃ ያበድሩኛል ብየ ተስፋ የጣልኩባቸዉ ሰዎች ከወንድሜ ጀምረዉ ፊታቸዉን አዞሩብኝ አሁን ምንድን ነዉ የማረግ የልጆቸ የትምህርት ቤት ክፍያ እየደረሰ ነዉ ከየት አምጥጨ እከፍላለሁ ያረብ አንተዉ አግዘኝ!" ሲል ከኋላ እየሰመሁት ነበር አባቢ ተዉ አትናደድ አላህ ለኸይሩ ነዉ በቃ ቤታችንም ቢሆን ይሸጣል ደሞ የትምህርት ቤት ክፍያም እየደረሰ ስለሆነ ብትበደርም አይበቃህም ስል ሀሳቤን ነገርኩት አባቢም እስኪ አበድሬዉ የነበረ አንድ ወዳጀ ነበረ ሁሌም ብሬን ስጠኝ ስለዉ ቆይ ዛሬ ነገ እያለ ከተበደረ አምስት አመት ሆነዉ እሱ አያሳፍረኝም ይሰጠኛል ካልሰጠኝ ደግሞ ቤቴንም ቢሆን እሸጠዋለሁ አንች አታስቢ እኔ አባትሽ እያለሁ ምንም የሚቸገረን ነገር አይኖርም አለና ተነስቶ ሄደ።


እማየ "ሀናኔ ምን እያደረጋቹህ ነዉ አትመጡም እንዴ ከአማኔ ጋር አትጫወቱ" ስትል ጠየቀችኝ አባቢ ተነስቶ መጣሁ ስመጣ እንጫወታለን ብሎ ሄደ አማየም የት ነዉ አባትሽ የሚሄድ አለችኝ ሁሉንም ነገርኳት አማየም ታቅ ነበር መጠሁ ብላ አባቢን ተከትላ ወጣችና ከአባቢ ጋር ሲያወሩ ቆይተዉ እሷ ወደ መኝታ ቤት ሂዳ ሲጋቡ ስጦታ የተሰጠችዉን ወርቆች ከቁም ሳጥኖ አወጣች እኔም እማ ምን ልታደርጊያቸዉ ነዉ ስል ጠየቋት እማየም እነዚህ ወርቆች ተሽጠዉ ለአማኔ መድሀኒት መግዣ ይሆናሉ እንጂ ቤታችንን አንሸጥም አለችኝ


......እኔም እየሮጡ መኝታ ቤቴ ገበሁና ከአስራ ሁለተኛ ክፍል ወደ ዩኒቭ ስገባ አባቢ የሰጠኝን የወርቅ የአንገት ሀብል ይዠ መጣሁ ከእማየ ወርቆች ጋር አደረኩት እማየም አይኗ እንባ ሞልቶ በሀዘን ሀናኔ "በጣም የምትወጂዉን የአንገት ጌጥሽን " አለችኝ
.... እማየ እዉነቷን ነዉ የሄን ያንገት ጌጤን በጣም ነበረ የምወደዉ ስለምሳሳለት ይጠፋብኛል እያልኩ አለብሰዉም ነበር ዛሬ ግን ሁለተኛ ላይመለስ ይሸጥ ብየ ከእማየ ወርቋች ጋር አደረጉት ሪሀናም አባቢ ለኔ የአንገት ጌጥ ሲገዛ ለሶ የጆሮ ወርቅ ገዝቶላት ነበር አዉልቃ ለእማየ ሰጠቻት እንግዲህ አንዳንዴ ሂወት እንደዚህ ናት የምትወደዉን ሰዉ ፤የምትወደዉን ቁስ.... ነገር አሳልፈህ መስጠት ግድ ይሆንብሀል ለነገሩ አላህስ በተከበረዉ ቁዱስ ቁርአኑ የምትወዱትን እስካልሰጣቹህ ድረስ አላመናቹህም ብሎን የለ እኛ በሀቅማችን ለአማኔ መድሀኒት መግዣ ሰጠናል።


.....በአንዴ አባቢ ተናዶ ፊቱ ቲማቲም መስሎ መጣ ያበደረዉ ሰዉየ አልሰጥም ብሎት ይሆናል እያልኩ ለምን እንደተናደደ ጠየቁት አባቢም"እኔ ለችግሩ ጊዜ ከጎኑ ነበርኩ ለኔ ችግር ጊዜ ግን ፊቱን አዦረብኝ ቆይ ያበደርኩትን መጠየቅ ጥፋት ሆኖ ነዉ አትጨቅጭቀኝ እንደዉም አልሰጥም ማለት አችላለሁ ብሎ የሚንጠራራብኝ እሱ ማን ስለሆነ ነዉ የሰጠሁትን የማይሰጠኝ እንደዉም በችግሩ አይዞህ በርታ ስለዉ እንደነበረ አሁን ከኔ ጎን ሁኖ አይዞህ ማለት ነበረበት "

.....አባቢ በቃ አትናደድ ሂወት መራራ ናት ከሰዉ ሳይሆን ከአላህ እርዳታን ጠይቅ አሱ አያሳፍርህም ...አልኩ አባቢ ግን መረጋጋት አልቻለም እየደጋገመ በጣም ነበረኮ የምወደዉ እኔ ለሱ ያደረጉለትን ብነግርሽኮ ሀናኔ ማለት ጀመረ
በቃ አባቢ ምንም አደረክለት ምን ከሰዉ ሳይሆን ከአላህ አጂሩን ታገኛለህ ተረጋጋ አልኩት መረጋጋት አልቻለም ትንሽ ቆይቶ ለሰዉ ከእንግዲህ አንድ ነገር አላረግም ወዳጂ ያልኳቸዉን ሰዎች ሁሉ አየኋቸዉ ለካ የሰዉን ምንነት የሚታወቀዉ በመከራ በችግር ጊዜ ነዉ በደስታማ ሳይጠራ አቤት ይላል
...... አይ ሰዉ! ሰዉ ማለት ትርጉም የለሽ ለማወቅ የሚያስቸግር ዉስብስብ ፍጡር ነዉ ብሎ ለደቂቃዎች ዝም ካለ ቡሀላ ....

ኢንሻአላህ ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
መራራ እዉነት
ክፍል 1⃣6⃣

..... ሰሚራ ሽኩር

.......አይ ሰዉ! ሰዉ ማለት ትርጉም የለሽ ለማወቅ የሚያስቸግር ዉስብስብ ፍጡር ነዉ ለካ ካለ ቡኋላ ለደቂቃዎች ዝም አለና ግን ሀናኔ ሰዉን ዉደጂዉ እንጂ ፍፁም አትመኝዉ አንች ለሱ ጥሩ ካደረግሽ እሱም ያደርግልኛል የጭንቅ ቀን ይደርስልኛል ብለሽ ተስፋ እንዳታደርጊ!"ብሎ ዝም አለ አሁን ንዴቱ እየበረደለት እየተረጋጋ የሄደ ሲመስለኝ እኔም የማቀዉን ለአማኔም ሁሌም የምነግረዉን ምክር እንዲህ ስል ጀመርኩ


አባቢ ሁሌም ምላሽ የማይጠብቅ ፍቅርና መልካም ስራ ልክ ጸሃይቱ ምድርን በብርሃን እንደምታበራ ሁሉ፤ የጨለማን ህይወት በብርሃን ይሞላል። ለሰው ግን ያለ_ምላሽ ማፍቀር፤ ያለ ምላሽ መስጠት አይከብደውም? ለምናደርገው ነገር ሁሉ ምላሽ ስለምንሻ ነገሮች እንዳሰብናቸው ካልሆኑ ደስታችንን ያጎድሉብናል አባቢ አንተ ለጓደኛህ ምላሽን ባትሻ ነሮ ዛሬ ይሄን ያህል ባልተነደድክ።

አባቢ አንተ ጓደኛህን በጣም ትወደዉ ታምነዉም ነበር እሱ ለምን አልወደደኝም ብለህ አትናደድ አንተ ዝም ብለህ ልክ እንፀሀዮ ለምድር ካለ ምላሽ ብርሀኖን እንደምትለግሳት ሁሉ አንተም ምላሽ ሳትሻ መዉደድህን፤መስጠትህን... ቀጥል።

እኛ ሰዎች ስንባል ሰዎች ሳይወዱን መውደዱ አናውቅበትም፤ ብናውቅበት እንኳን ሞኝነት ይመስለናል።

ሰዎች ይቅር ሳይሉን ይቅር ማለቱን አንችልበትም ፤ ብንችልበት እንኳን ገር የሆንን ይመስለናል።ሰዎች ሳያከብሩን ማክበሩን አንችልበትም፤ ብንችልበት እንኳን የተዋረድን ይመስለናል።

አባቢ ሰዎች ካልረዱን መርዳት አንችልበትም ፤ ብንችልበት እንኳን የዋህ የሆንን ይመስለናል።ለምናደርገው ነገር ሁሉ ምላሽ እንሻለን ፤ ለፍቅራችን፤ ለደግነታችን ፤ ለይቅርታችን ፤ ለክብራችን ምላሽ ካልተሰጠን ደስተኞች አይደለንም።

አንተ አበደርከዉ ማሻአላህ ፤የጭንቁ ቀን አጠገቡ ነበርክ፤ሲከፋዉ አይዞህ ባዩ ነበርህ ላንተ ችግር መከራ ጊዜ ግን ፊቱን አዞረብህ ለዚህም ይመስለኛል በጣም የተናደድክ

አባቢ ለሰዉ የምታደርገዉን ዉለታ ምላሹን ከጠበክ በትንሽ በትልቁ ኩርፊያ እና ቂም ብቅ ይላሉ። "እኔ እንዲህ አድርጌለት" "እኔ ለሱ ጊዜ እንዲህ ነበርኩኝ?" "ለእኔ የሚገባኝ ይህ ነው?"
እያልን የገዛ ደስታችንን የምናጠፋው እኮ
ያለ_ምላሽ_ማፍቀር፤ ያለ ምላሽ መስጠት፤ያለ_ምላሽ_ማድረግ ስላለመድን ነው።

ስንሰጥ ምላሽ ካልጠበቅን ሰዎች ክፉ ቢሆኑብን ግር አይለንም። ስንወድ ለመወደድ ብለን ካልሆነ ፤ ፍቅራችን ሲገፋ አይከፋንም።

አባቢ ስንረዳ ለክፉ ቀናችን ብለን ካልሆነ፤ ሰዎች እርዳታቸውን ሲነፍጉን አይደንቀንም። የምናደርገው ነገር ሁሉ ከልባችን ሲሆን፤ ደስታችን ሌሎች በሚሰጡን ምላሽ ላይ አይወሰንም።

እንደ ጸሃይ ማን ምላሽን ሳይጠብቅ ማን ይሰጣል?ማንስ ይወዳል ካልን? በመጀመሪያ ፈጣሪችንን አላህን እናስብ፤ ዝቅ ስንል
ወላጅን እንይ ፤ እውነትም ያለ_ምላሽ እንደሚወደድ ፤ ያለ_ምላሽ ይቅር እንደሚባል ፤ ያለ_ምላሽ እንደሚሰጥ መሆን እንደሚቻል ማስረጃዎች ናቸው።
እንደው ዝም ብለን መውደዱን ብንለምድ ና መስጠቱም ቢለምድብን ምነኛ ደስ ይል ነበር ፤ በቃ ያለምክንያት ጥሩ መሆን ፤ ያለ_ምላሽ መልካም መስራት ፤ ያለ_ፉክክር መረዳዳት ቢለምድብን እንዴት ደስ ይል ነበር?

አባቢ የሌላውን ምላሽ ሳንጠብቅ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ከቻልን ከራሳችን ላይ ትልቅ ቀንበር አነሳን ማለት ነው። ሰዎች ምንም አይነት ምላሽ ቢሰጡንም የኛን መልካምነት አያጎድፉትምና.......

ጸሃይ ለምድር የዋለችውን ውለታ አስልታ ክፈይ ብትል ምድርን ምን
ይውጣት ነበር ?? መልሱን ለናንተዉ ተዉኩት


አባቢ በዝምታ ከአዳመጠኝ ቡሀላ ከተቀመጠበት ወንበር ብድግ ብሎ ሀናኔ አለና ግንባሬን ሳመኝ አስደሰትሽኝ አልሀምዱሊላህ እናንተን የመሰለ ቤተሰብ የሰጠኝ አላህ ክብር ምስጋና ይገባዉ ሲል እማየ ከመኝታ ቤት ወደ ሳሎን በጨርቅ የተጠቀቀለ ነገር ይዛ መጣች የተጠቀለለዉን ለማወቅ ጊዜ አልፈጀብኝም ወርቅ ነዉ ለአባቢም "አይዞህ እኛ ሁሌም ከጎንህ ነን ይሄን ሽጥና የአማኔን መድሀኒት ግዛ አለችዉ አባቢ ግን አይቻልም አለ


በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join👇👇👇
www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
2024/09/23 12:26:17
Back to Top
HTML Embed Code: