Telegram Web Link
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ...

ሁለት ቀን ባለመፓሰቱ ይቅርታ በአላህ በአስተያየት መስጫ Bot እላፊ ቃላት አትናገሩ😒 ወላሂ ማንንም ልብ ለማንጠልጠል አይደለም..ልጀምር ስል ተናግሪያለሁ ገና ታሪኩ edit አልተደረገም ደግሞ ስራ ካልተመቸኝ አይፓሰትም ብያለሁ...ሁለት ቀን ለስራ ጉዳይ አዲስ አበባ ነበርኩ ..ለዛ ነዉ ያልተፓሰተዉ ..አንዳንድ እላፊ የምትናገሩ የቻናል ቤተሰቦች ለአፋችሁ ዚብ አሰሩ😷
ስድብም ሲበዛ ይደብራል
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
     
#ክፍል ☞ ሰላሳ አንድ 3⃣1⃣

ፀሀፊ ☞
#አሚር_ሰይድ



ሚፍታህን አሳማኝም በሆነ የማያሳምን የተለያዩ ለፀብ ለቁርሾ የሚሆን ስበብ ፈልጌ አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ልርቀዉ ወሰንኩኝ .........
በተለያዩ ዘዴዎች አዉቄ ሁለታችንን ሊያጣላን የሚችል ጥፋት እያጠፋሁ ነገር እየፈለኩት በራሴ ጥፋት ሚፍታህን መጣላት ጀመርኩኝ....ግን በተጣላን ማግስት ሚፍታህ ከቤቴ ስወጣ መንገድ ላይ እየጠበቀ በራሴ ጥፋት ይቅርታ አርጊልኝ  ይለኛል

በተለያዩ ዘዴዎች የዉሸት ምክንያቶች እየደረደርኩ ብዙ ጊዜ አስቀየምኩት ግን ሚፍታህ ይቅርታ አርጊልኝ እያለ ሊርቀኝ ከኔ ተስፋ ሊቆርጥ በጭራሽ አልቻለም.....

ከትንሽ ቀን ቡሀላ ሚፍታህ ለስራ ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ ፡፡ አሁን ሚፍታህን በአካል አላገኘዉም በስልክ ብቻ ነዉ የምንገናኘዉ...ለመለያየት ከኔ ተስፋ ለመቁረጥ ጥሩ ጊዜ ነዉ ብየ አሰብኩኝ ...ለእኔም ለሚፍታህም የሚጎዳ ከባድ ዉሳኔ ወሰንኩኝ....

ሚፍታህ ከልቡ ቆርጦ እንዲጠላኝ ስልኩን block አረኩት ... ምክንያቱም እሱን ባወራሁት ድምፁን በሰማሁት ቁጥር የበለጠ እየወደድኩት እያፈቀርኩት መሀባዉ እየጨመረብኝ ሄደ ፡፡ ደግሞ በዚህ ሁኔታ ሁኜ መለየት አቅቶኝ እያለቅሱኩኝ ከዚህ በላይ ደግሞ ብወደዉ አብጄ ልብሴን መቅደዴ አልቀረም.
ፍቅር ግን ምንድን ነዉ የበፊት ምርጥ ትወልዶች፡ፍቅርን እንዴት ነበር የገለፁት??? መጀመሪያ የፍጡራን ፈጣሪ የሆነዉን የአለማት ጌታ ለአላህ ነበር ፍቅራቸዉ..እስኪ የዚችን ንፁህ ልብ ያላት ወጣት የፍቅር ታሪክ ልጋብዛችሁ

★★★ ኡመር(ረ.ዐ)በመዲና ጎዳናዎች ላይ በጨለማ ሲዘዋወሩ አንድ ቤት አጠገብ ሲደርሱ እናት እና ልጅ ሲከራከሩ ይሰማሉ
እናት፡-ልጄ ሆይ ነገ ከምንሸጠዉ ወተት ላይ ጥቂት ዉሀ ጨምሪበት
ልጅ፡-እማዬ ኸሊፋዉ ኡመር ወተት ላይ ዉሀ እንዳንጨምር ከልክለዉናል ትላታለች እናቷን
እናትም፡-ኸሊፋዉ እኮ አሁን የምንሰራዉን አያየንም አለቻት
ልጅም፡ አላህን በመፍራት ለእርሱ ባላት ፍቅር ልቧ የተሳበዉ ወጣት እንዲህ አለቻት ..እናቴ ሆይ!!!ይህን ድርጊታችንን ኸሊፋዉ ባይመለከተንም ከአላህ ግን ልንደብቀዉ አንችልም አለቻት፡፡
ልጅቱ ለእናቷ የሰጠቻት መልስ ኡመርን በቆሙበት ቦታ በሲቃ ናጣቸዉ፡፡ ከዛም ሲነጋ ቤቱ የማን ቤት እንደሆነ አረጋግጠዉ ያቺን ልጃገረድ ልጃቸዉ እንዲያገባ ሁኔታዉን አመቻቹለት፡፡ ምክንያቱም ልጅቱ ለአላህ የነበራት ፍራቻ ከርሷ የሚጠበቅ አልነበረምና፡፡ ከእነዚህ ጥንዶች የተወለደዉ በኢስላም አምስተኛዉ በትክክል የመራ ኸሊፋ እንደሆነ የተመሰከረለት ኡመር ኢብኑ አብደል አዚዝ የተገኘዉ፡፡ እናቱ አላህን ፈሪ ስለሆነች በዛ ተርብያ ስላሳደገችዉ ለዲነል ኢስላም መሪ የሆነ ልጅ አበርክታለች....እንደዚህ ለአላህ የነበራቸዉ ፍቅር ላይ ያለፉ ትዉልዶች ስንት ስቃይ አሳልፈዉ እኔ ግን በሚፍታህ ፍቅር እርብሽብሽ ለቅሶ በለቅሶ ሁኛለሁ

... እኔም እንዲህ ብየ አሰብኩኝ>>>>>>>
#ትዳር_ለኔ_አልተፈጠረም_ቢክራ_ስላልሆንክ_የወደድኩትን_ሰዉ_ማግባት_አልችልም<<<<<<<ብየ ከሰዉ በታች እንደሆንኩ ሁሌ ይሰማኛል፡፡

 
.....ሚፍታህ በጭራሽ ከኔ ተስፋ ሊቆርጥ አልቻለም ፡፡ በተለያዩ የተለያዩ ሰልክ ቁጥር ቢደዉል ቢደዉል እኔ አላነሳ ስለዉ በእናቴ ስልክ ይደዉላል ፡፡
እናቴም፡- ሚፍታህ ነዉ ነዋልን ፈልጊያት ነዉ አገናኚኝ እያለ ነዉ በስልክ አግኝዉ ስትለኝ
እኔም፡- አሁን ማናገር አልፈልግም እላታለሁ......

በሌላ ስልክ ሲደዉል እንደ አጋጣሚ ካነሳሁት የእሱ ድምፅ መሆኑን ስሰማ አላናግረዉም......እንዲዚህ እያልን 3ወር ያህል የሚፍታህን ድምፅ ሳልሰማ block እንዳደረኩበት ጨከንኩበት፡፡


አንድ ቀን አባቴ ብር አሰግቢ ብሎኝ ብር ላስገባ ባንክ ቤት ሄድኩ.. የአላህ ነገር ሁኖ ሚፍታህ ጋር ባንክ ቤት ተገናኘን
.....ነዋል አሰላሙ አለይኩም አለኝ
....እኔም ያልጠበኩት ነገር ነዉ ደንግጬ ወአለይኩም ሰላም አልኩት
.........የሚገርም ነዉ ገና ትናንት ከአዲስ አበባ መጥቼ ነዉ .ከአዲስ አበባ የመጣሁበትም ምክንያት ለአንቺ ብየ ነዉ ምን ሁነሽ ነዉ ስልኬን block ያረክሽዉ ??
አሁኑኑ ስልኩን ከblock አንሺዉ አለኝ
....እኔም ዉሳኔየ ነዉ አሁን አላነሳዉም አልኩት
.......ሚፍታህም ባንክ ቤት ተገልጋዮች ባሉበት ሰዉ ፊት ነዋል ምን አድርጌሽ ነዉ Block ያረግሽኝ??ምን አርጌሽ ነዉ ??? ጥፋት ካለኝ እዚሁ ሰዉ በተሰበሰበበት ጥፋቴን ንገሪኝ ፡፡ እኔ ወላሂ በጣም ነዉ የዎወድሽ አንቺን አጥቼ መኖር አልፈልግም አንቺን ተለይቶ መኖር ልቤ መቼም አይፈቅድልኝም.. ለምንድን ነዉ ብሎክ ያረግሽኝ??? እያለ ሲጮህ
በጣም ደነገጥኩኝ
....ሚፍታህም ጥፋት የለብኝም ሰዉ ፊት ነዉ ጥፋቴን የጠየኩሽ አሁኑኑ አይኔ እያየ block አንሺዉ አለኝ
...እኔ ደንግጫለሁ ብሎኩን አንስቼለት ቶሎ ብየ ከባንክ ቤቱ ወጣሁ፡፡

ከዚህ ቀን ቡሀላ የሚፍታህ ፀባይ አስተሳሰብ የተቀየረ መሰለኝ..በጣም የሚወደኝ ያለኔ መኖር የማይችልም መሰለኝ.....እንደበፊቱ በስልክ ማዉራት ጀመርን ፡፡ እቤት አባቴ በትምህርትሽ እንዳትሳነፊ  ብዙ ስልክ ማዉራት ቀንሱ ተብሎ ተከልክለናል.....የማወራዉ ተደብቄ ነዉ ፡፡ እንደበፊቱ ብዙ ነገሮች ማዉራት ጀመርን ያዉ በወሬ በወሬ እኔ የምሸማቀቅበት አንገቴን የምደፋበት ስለትዳር እና ስለ ድንግልና እኔን በቀጥታ መጠየቅ ቢፈራኝም ግን በተዘዋዋሪ እንደበፊቱ የጓደኞቹን ታሪክ እያነሳ ያወራኛል
.....እኔም ይሄ ወሬ መደጋገም ሲበዛብኝ ..ምራቄን ዉጬ እንዲህ አልኩት
ሚፍታህ እኔ እንደምጠብቀኝ አይነት ልጅ አይደለሁም ከኔ የተሻሉ ብዙ ሴቶች አሉ ሌላ ሰዉ አግባ ...እኔ አንተ ላቀረብካቸዉ የትዳር መስፈርትህ ማሟላት አልችልም አልኩት...
....እሱም ነዋል እንደዚህ አትበይ ከአንቺ የተሻለ ሴት መቼም አላገኝም እወድሻለሁ እኮ ..አንቺ የኔን የትዳር ዉሳኔ አሁን መወሰን አትችይም እኔ አንቺን መርጫለሁ ወደ ሆላ አትመልሽኝ ፡፡ በፀባይ በዲን በአስተሳሰብ ከአንቺ የተሻለ አላገኝም ይለኛል፡፡

እኔ በልጅነቴ ልደፈር አልደፈር ይወቅ አይወቅ የማቀዉ ነገር የለኝም፡፡ ግን የሱፍ ያቃል ..የሱፍ ታስታዉሱ እንደሆነ ገና ታሪኩ እንደጀመረ ልጅ ሁኜ ተራዊህ ልንሰግድ ገብተን እናቴ ነዋል በልጅነቷ ተደፍራለች ብላ ነግራኛለች ብላ የተጣላሇት ልጅ እህቱ ናት( part ➎ላይ ያለችዉ ልጅ) ፡፡
የሱፍ የኔን ታሪክ ያዉቃል..ግን ለሚፍታህ ይንገረዉ አይንገረዉ የማቀዉ ነገር የለኝም...

ግን ሚፍታህ ጋር በአወራን ቁጥር የእኔ ባለቤት ድንግል ካልሆነች ቀልድ የለም ይለኛል ..እንደዚህ ሲል መደፈሬን አልሰማም ማለት ነዉ ብየ አሰብኩኝ... ግን አሁን ድረስ ግራ የሚገባኝ ለኔም ያልተመለሰልኝ መልስ ሚፍታህ ስለኔ ያቃል አያቅም??የሚለዉ የተወዛገባ ሀሳብ በጭራሽ መልስ ላገኝለት አልቻልኩም....ብቻየን በሀሳብ ማዕበል እጓዛለሁ ..ግን ምን ዉሳኔ እንደምወስን ይጨንቀኛል ..ደግሞም ልንገረዉ ብየ እወስንና እንዴት ብየ ልንገረዉ??እያልኩ ደግሞ ሀሳብ ይሆንብኛል ግን ያለኝ አንድና አንድ ብቻ ነዉ ...ካልደፈረሰ አይጠራም በልጅነቴ መደፈሬን ለመንገር ወሰንኩኝ

ሚፍታህ ሲደዉልልኝ ከዛሬ ነገ ልንገረዉ?? መቼ አልንገረዉ ???እያልኩ እኔዉ ለራሴ ሀሳብ ሆነኝ እንዴት ብየ ልንገረዉ???...ዉይ ሒወት የስቃይ ማዕበል

የሒወቴ ከባዱ ፈተና ይህ አመት ነዉ👇👇👇
ልጅ ሁኜ ትምህርት ቤት ያለዉ ተፅእኖ ያሳለፍኩት አሁን ካለሁበት ሳነፃፅረዉ በልጅነቴ ሲሰድቡኝ ሲጠቋቆሙብኝ የነበረዉ ቀላል ነዉ ...የኔን ማንነት ለማያቅ ሰዉ ነገ አብሬዉ ለምኖረዉ ለትዳር አጋሬ እንዴት ብየ ነዉ ድንግል አለመሆኔን የምነግረዉ ??
እኔ እወደዋለሁ እሱም ይወደኛል ለመጋባት በመሀከላችን ምንም የሚያጣላን የሚያለያየን ነገር የለም ..ነገር ግን የኔን ማንነት ይቀበለኛል ወይ ? ?? አግብቼ ከሚፍታህ ጋር በዚሁ ምክንያት ከትዳር መለያየት ቢመጣ ነዋል አግብታ ፈታች እየተባለ የቡና መጠጫ ወሬ እሆናለሁ ...

ደግሞ እኔን የሚያቁኝ ሰዎች ከሌሎች ሴቶች ለኔ ቦታ አላቸዉ በትምህርቷ ጎበዝ ናት፡ ዲን አላት ፡ጥሩ ፀባይ አላት ፡ ጅልባብ ለባሽ ናት ብሎ ማንኛዉም ሰዉ ይመሰክርልኛል....ነገር ግን ዉስጤ ያለዉ ቁስል ነዶ የማያልቅ የፉም እሷት ጨብጬ ይዣለሁ ...እንዴት አርጌ ልንገረዉ ??? እያልኩ ብቻየን መጨነቅ መኝታ ክፍል ሁኜ ማልቀስ ሁኗል ስራየ

ሚፍታህ ተወኝ ብለዉ አይተወኝም...,,ደግሞ ካልተወኝ ለወደፊት ግንኙነታችን ለመጋባት ስለጨረስን ይሄን ነገር ማወቅ አለበት ...ከተጋባን ቡሀላ ድንግል አለመሆኔን ያዉቃል ከዛ ምን ይፈጠር ይሆን ???እላለሁ 

ለሊት እየተነሳሁ ረከአተይን ሰግጄ ዱአ አደርጋለሁ ... ደግሞም በማንኛዉም ሰአት እና ከሶላት ቡሀላ ዱአ አደርጋለሁ...የሚገርማችሁ ነገር ይሄን ዱአ በመደጋገም አደርግ ነበር >>> #አላህዋ_መርየመን_ያለድንግል_ማንም_ሳይነካት እንድትወልድ ያረካት ጌታ ሆይ የመርየምን ድንግል ለኔ ስጠኝ<<<<<<<< ብየ ብዙ ጊዜ አልቅሼ😢😢😢 ዱአ አድርጌያለሁ በሒወቴ ከባዱ ገጠመኝ በማንነቴ ያለቀስኩበት የተጎዳሁበት አመት ይሄ አመት ነዉ ፡፡
አንዳንዴ ሳስበዉ ለዱንያ ይሄን ያህል መጨናነቅ ለቅሶ ይሄን ያህል እላለሁ ..
★★★አቡ አባስ ሰህል ኢብን ሰዓድ አስ ሳዒዲይ (ረ.ዐ)እንዲህ ብለዋል፡-፡
አንድ ቀን አንድ ሰዉ መጣና የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ አላቸዉ ፡- የአላህ መልዕክተኛ ሆይ !ብሰራዉ አላህ የሚወድልኝና ሰዎችም የሚወዱልኝ ነገር ይንገሩኝ ? አላቸዉ
ነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ እንዲህ በማለት መልስ ሰጡት ""የዚችን አለም መደሰቻዎች ችላ በል..ጉጉት አይኑሩህ..ይሄን ስታደርግ አላህ ይወድሀል፡፡ እንዲሁም በሰዎች እጅ ላይ ላሉ ነገሮች ትኩረት አትስጥ ሰዎች ይወዱሀል፡፡"""" ብለዉታል፡፡
..እኔ ታዳ ትኩረቴ ለሚፍታህ ሆነ አላህ ከኔ እንደራቀኝ ይሰማኛል

ኮሌጅ የሁለተኛ አመትን እንደዚህ ነበር ያሳለፍኩት....እናም አመት ዙሮ ረመዷን ቢደርስም የዚህ አመት ረመዷንን በመጨናነቅ በማሰብ አሰለፍኩኝ.....አስከትሎም ኢድም አልፎ ዛሬ ልንገረዉ አልንገረዉ እያልኩኝ ስወዛገብ ሳለቅስ ኑሬ ...... ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመንገር ተዘጋጀሁ...ለመንገር ለሚፍታህ ልደዉል ስልኬ ከተቀመጠበት ሳነሳ በእጄ እንዳለ ስልኬ ጠራ ..የደወለዉም ሚፍታህ ነዉ፡፡

ስልኩን አንስቼ ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ
.....ነዋል ልሄድ ነዉ አለኝ
.........,,እኔም ልቤ እየደነገጠ የት ነዉ የምትሄደዉ ??አልኩት

#ክፍል 3⃣2⃣
ይ..........ቀ.......
....ጥ..........ላ............ል


www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
     
#ክፍል ☞ ሰላሳ ሁለት 3⃣2⃣

ፀሀፊ ☞
#አሚር_ሰይድ



ስልኩን አንስቼ ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ
.....ነዋል ልሄድ ነዉ አለኝ
.........,,እኔም ልቤ እየደነገጠ የት ነዉ የምትሄደዉ ??አልኩት
...እሱም አረፋን የምዉለዉ ሀጃጆች ጋር ነዉ.. በዚህ አስር ቀን ዉስጥ ሳዉዲ አረቢያ ሀጅ ልሄድ ነዉ ከሀጅ ስመለሰ እናወራለን እዛ ሁኜ በimo እና telegram እንገናኛለን አለኝ......
...እኔም እሄዳለሁ ሲለኝ ደንጋጤም ጥርጣሬም አስቤ ነበር ..ተረጋግቼ መርሀባ አላህ ያሳካልህ ሀጅህንም ይቀበልህ እኔም ብዙ ሀጃ አለኝ በዱአህ አትርሳኝ አልኩት
....እሱም አልረሳሽም አለኝ

ሚፍታህ ለሀጅ ወደ ሳዉዲ አረብያ ሄደ ..ሳዉዲ ከገባበት ሰአት ጀምሮ እኔ እዛ የሄድኩ እስኪመስለኝ ሳዉዲን በየሄደበት በtelegram እና በimo video እየቀረፀ እየላከ ያሳየኛል፡፡ ጠዋፍ ሲያደርግ..ሶፋ እና መርዋ ላይ ሲወጣ..አረፋ ተራራ ..ስንቱን ላዉራዉ ሀጅ በሚያደርገበት ቀን በቀን ያለዉን ሁኔታ እስከሚመለስ ድረስ በimo እየላከ ያሳየኛል፡፡ አሁን ላይ ሁኜ ሳስበዉ ሀጅ የሚሰራዉ ሀጅ አደረገ ለመባል ነዉ ወይስ ግዴታ አላህ እንደአዘዘዉ ሰርቶ ወንጀሉን እንዲማር ነዉ ??
እስኪ እንደዚህ አድርጎ ያረገዉ ሀጅ ከአላህ ጋር ተቀባይነት ያገኝ ይሆን ??? እላለሁ፡፡ ታዳ ይሄ አይነት አላህን ይፈራል ብሎ መገመት ይቻላልን??

★★★ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ በማለት ጌታቸዉን ለምነዋል፡-አላህ ሆይ!!ከማይጠቅም እዉቀት ፡አንተን ከማትፈራ ቀልብ ከማትጠገብ ከማትረካ ነፍስ ፡ ተቀባይነት በሌለዉ ዱአ በአንተ እጠበቃለሁ ... ብለዋል

★★★በሌላ ሀዲሳቸዉ የአላህ መልዕክተኛ የሆኑት ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል
አማኝ የሆነ ሰዉ በእዉነቱ የአላህን ቅጣት ሀያልነት ቢያዉቅ ኖሮ ጀነተ እገባለሁ የሚል ተስፋ ፈፅሞ አይኖረዉም ነበር፡፡ እንዲሁም ከሀዲ የሆነ ሰዉ በእዉነቱ የአላህን እዝነት ልኩን ቢያዉቅ ኖሮ ጀነት ከመግባት ፈፅሞ ተስፋ አይቆርጥም ነበር ብለዋል..

አላህ በተከበራ ቅዱስ ቁርአኑ የይዩልኝ ስራ የሚሰሩትን አስጠንቅቋቸዋል...እንዲህም ብሏል
☞ እነዚያም ለሰዎች ይዉልኝ ሲሉ ገንዘቦቻቸዉን የሚሰጡ፥ በአላህና በመጨረሻዉ ቀን የማያምኑ ይቀጣሉ...(ሱረቱል ኒሳእ፡38)

በሌላ የቁርአን ቦታ ላይ ደግሞ እንዲህ ብሏል
☞ እናንተ ያመናቹህ ሆይ! እንደዚያ ገንዘቡን ለሰዎች ማሳየት ሲል፥ እንደሚሰጠዉና በአላህና በመጨረሻዉም ቀን እንደማያምነዉ ሰዉ፥ ምፅዋታቹሁን በመመፃደቅና በማስከፋት አታበላሹ፧ ምሳሌዉም በላዩ አፈር እንዳለበት ለንጣ ደንጊያ ሀይለኛም ዝናብ እንዳገኘዉና ምልጥ አድርጎ እንደተወዉ ቢጤ ነዉ። ከሰሩት ነገር በምንም ላይ(ሊጠቀሙ) አይችሉም.....(ሱረቱል በቀራ፡264)

ተወዳጁ ሀቢቡና የአላህ መልክተኛ የሆኑት ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል
በኡመቶቸ(ተከታዮቼ) ላይ በጣም የምፈራዉ ይዩልኝ(ሪያእን)ነዉ። ብለዋል
በሌላ ሀዲሳቸዉ ደግሞ --------- ካስፈሪ ነገሮች በጣም ለናንተም የምፈራላቹህ ትንሹን ሽርክ ነዉ ትንሹ ሽርክ ምንድን ነዉ ያአላህ መልክተኛ? አሏቸዉ እሳቸዉም ሪያህ የይዩልኝ ስራ ነዉ አሉ።
ታዳ እንደሚፍታህ ያሉ ሀጃጆች ስንት ስራቸዉን አበላሽተዋል??? ቤት ይቁጠረዉ ..አላህ ሆይ አንተ ያዘዝከንን ስንሰራ ከሰዉ ምስጋናን ሳይሆን የአንተን ሀቅ አሟልተን ከአንተ ሽልማት የምናገኝ አድርገን

ሚፍታህ ሀጅ አድርጎ ሲመጣ ጂማ የሚገኘዉ መርካቶ ሰፈር ኤሌክትሮኒስ ሱቅ ከፈተ ...ታላቅ ወንድሙ ከዉጭ ሀገር እቃ ይልካል አንድ ወንድሙ አዲስ አበባ ይሸጣል ለሚፍታህ ደግም ወደ ጅማ ይላክለታል.....ሚፍታህ ኑሮዉንም አዚሁ ጅማ አደረገ ፡፡ ለኔ በጣም ደስ አለኝ በስልክ ሳይሆን ሲናፍቀኝ አይኑን ማየት እችላለሁ ብየ አሰብኩ፡፡


አንድ ቀን እለቱ ቅዳሜ ቀን ነዉ የኔን ማንነት በልጅነቴ መደፈሬን ልንግረዉ ብየ እራሴን አሳምኜ ደወልኩለት
....... ስልኩን አነሳዉ
............ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ሚፍታህ ዛሬ ትልቅ ሚስጥር ነዉ የምነግርህ ..አደራህን የምነግርህን ተረዳኝ በነገርኩህ ነገር ተቀይመህ ወይም እኔን እንደአሰብከኝ አለመሆኔን ስታቅ ከአንተ አፍ የሚወጣዉ ቃላት እኔን አንተን የሚወደወለን ልቤን እንዳያደማዉ ተጠንቀቅ ..እኔ ለአንተ ያልነገርኩህ ብዙ የሚያስጨንቁ በሆዴ የታፈኑ ማንነቶች አሉኝ..አንተ እኔን እንደምታስበኝ ሴት አይደለሁም.. የአንተ የትዳር መስፈርትህ እኔ ካለኝ ማንነት ጋር በጣም ሰፊ ልዩነት አለ አልሆንህም . እያልኩ ወደ ዋናዉ ቁም ነገር መደፈሬን ልነግረዉ ከአፌ ላወጣዉ ስል...,ሚፍታህ ወሬየን አስቆመኝ
.....ነዋል ወሬዉን አቁሚዉ እና አሁኑኑ በአካል እፈልግሻለሁ እቤት ነይ አለኝ.....
.....እኔም እሺ ብየ ከጠየቀኝ አንድ ባንድ እነግረዋለሁ ብየ ወደ ቤቱ ሄድኩኝ

... እቤቱ እንደደረስኩ ያየሁት ነገር አይኔን ማመን አቃተኝ...እኔ ያሰብኩት ሌላ የሚሆነዉ ሌላ ነዉ
.......ሚፍታህ ቢያንስ ከ6 የሚበልጡ ጓደኞች ባሉበት ነዋል እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ አንቺን አጥቼ መኖር አልፈልግም  ይሄዉ በጓደኞቼ ፊት እመሰክርልሻለሁ ...,በተጨማሪም አንድ የማረሳዉ ንግግር እንዲህ አለኝ
>>>>>>እኔ ዲንጋይ እመስልሻለሁ እንዴ ???እንደፈለኩ እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ ስል ቆይቼ ተወኝ ስትይኝ የምተወዉ አንስተሽ የምትወረዉሪኝ ዲንጋይ እመስልሻለሁ እንዴ ???እኔ የፍቅር የመዉደድ ስሜት የለኝም እንዴ??" ...እኔ አልሆንህም ስትይኝ እኮ ልቤ እየደማ ነዉ ነዋል እባክሽ ሌላ ፈልግ አትበይኝ እንደዚህ ስትይኝ ፍቅርሽ ያሳደረብኝ ዉጋት እየጨመረብኝ ነዉ <<<<<<አለኝ፡፡

እኔም እንደዚህ ሲለኝ ሆዴ ባባ አሳዘነኝ እሺ ከአሁን ቡሀላ እንዲህ አልልህም አልኩት

..ከዛም የሴቶች ጀመአችን የምንገናኝበት ወደ አልይ መስጊድ ሄድኩ ...እዛ እንደደረስኩ መፍቱሀ የጀመአ ሴቶችን ጅልባብ ብዙዎቹን አልብሳቸዉ ደረስኩ...በፊት ጅልባብ መልበስ ፍቃደኛ ያልሆኑትን ሴቶች በእራሷ ወጭ ገዝታ ስጦታ እየሰጠች ጅልባብ እንዲለብሱ ጥረት ታደርጋለች..ደግሞ ይሄ ኸይር ስራዋ በአላህ እርዳታ ይሳካላታል...የጀመአ አባሎቻችን ጅልባብ ለባሽ ሲሆኑ እንዴት ደስ ይላል..ከዓሊ መስጊድ ስንወጣ ሁላችንም ጅልባብ ለብሰን ስንሄድ ለተመልካች የተለየ ዉበት አለን፡፡
★★★★ የኛ ድንቅ አርዓያዎች እነማን ናቸዉ??ምዕራባዉያን ፋሽን ተከታዮች ናቸዉን??

ሰዎች ለህይወታቸው መመሪያ ይሆኑ ዘንድ ብዙ አርዓያዎችን ያበጃሉ። እነኚህ አርዓያ ተደርገው የሚወሰዱ ግለሰቦች ጥቂቶቹ በትክክል የተመሩና ቅኖች መልካሞች ሲሆኑ ብዙዎቹ ግን ራሳቸው መንገድ የሳቱ አመላካች የሚሹ ደካሞች ናቸዉ.. እነሱ ተደናግረዉ ብዙ ሰዉን የሚያደናግሩ ናቸው።

ከአርዓያዎች ሁሉ በላጮቹ የሰዉ ልጆችን ካልነበሩበት ያስገኘውና ቀጥተኛውን መንገድ የተመሩትን ከጠመሙት ለይቶ የሚያውቀው አምላክ አርዓያ እንድናደርገቻው የመረጠልን ናቸው!!!!! ከነዚህም አሽረፈል ኸልቅ ሙሀመድ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ዋነኛው ሲሆኑ በማስከተልም የእርሳቸው ሱሀባዎችና እነሱን በመልካም የተከተሉ ሷሊሆች ናቸው።

ምዕመናን ሴቶችም በበኩላቸው አርዓያ ሊያደርጓቸው ከሚገቡ ድንቅ ስብዕናዎች መካከል ቅድሚያ የሚሰጣቸው የመልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሚስቶች ቀጥሎም ሰሃብያት ናቸው።
ከነሱም መካከል የሙዕሚኖች እናት👇👇👇
የሆነችው ተወዳጇ እናታችን ዓኢሻ (ረዱየላሁ አንሀ) አንዷና ዋነኛዋ ናት።
ይህች እንቁ እናት ዓኢሻ በሂጃብ ላይ የነበራት የፀና አቋም ዛሬ እናታቸው ከነበረችበት የፀና አቋም ወለም ዘለም እያሉ ግራ ቀኝ ለሚሉ ልጆቿ መንገዳቸውን በጊዜ እንዲያበጁና እንዲያስተካክሉ ይረዳልና ላስታውሳቸው ከጀልኩ።

እህቴ ተወዳጇ እናታችን ዓኢሻ ከሙታኖችን እንኳን ታፍር (ሀያዕ) ታደርግ ሂጃቧንም አስተካክላ በመልበስ ሰውነቷንና ፊቷን ትሸፍን እንደነበር ታዉቂያለሽን?
በሚያሳዝን ሁኔታ የአሁን ዘመን ሙስሊም ሴቶች አይደለም ሙታንን ይቅርና በህይወት ካለው ጋርም ያላቸውን መስተጋብር እያየነው ነው ።

ሀያዕ ከሙስሊም ሴቶች ተገፎ ጠፍቷል ጥቂቶች ጋር ሲቀር ! አደባባይ ለአደባባይ አጅነብይ ወንዶችን ከቁብ ሳይቆጥሩ የለባሽ እርቃን ሆነው ውድ እና ሸሪዓ ያከበረውን ገላቸውን አራቁተው ለአላፊ አግዳሚው በመታየት ፈታኝ መሆን ከጀማመሩ ሰነባብተዋል። ጥቂት አላህ ያዘነላቸው ሲቀሩ! አላህ ከጥቂቶቹ ሴቶች ያደርገሽ ዘንድ እማፀነዋለሁ።
አማኝ ሴት ልክ እንደ እናቷ አኢሻ በሂጇቧ ልትፅና ይገባታል።
«የአባይን ልጅ ውሀ ጠማው» እንደሚሉት ብሂል አርዓያ እንደሌለሸ ነገር ከእንስሳ በላይ ራሳቸውን መቆጣጠርና ማሰብ የተሳናቸውን ፈር የለቀቁትን ምዕራባውያን የፊልም አክተር ..ተዋናዮችን አርዓያ አድርገሽ ቁልቁል ልትወርጂ ክብርሽን ልታዋርጂ አይገባም።

ይልቁን የዓኢሻንና እነዛ ቁጥብና ጥንቁቅ እንደዚሁም ክብራቸውንና ራሳቸውን ከሀራም የሚጠብቁ የሆኑት ሰሃብያት ልትከተይ ይገባል።
በዚህ ትልቅ ሐዲስም እነዛ ጥብቅ ጥንቁቅ እንደዚሁም ራሳቸውን ከሀራም ነገር የሚጠብቁ የሆኑ ሴቶች በአቋማቸው እንዲፀኑ !በተቃራኒው ደግሞ ከቁጥብነት ፣ ለመሸፋፈን እንደሚታወቀው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተቀበሩት በቤታቸው ውስጥ ነበር እንዲሁም አባቷም አቡበከር (ረድየላሁ አንሁ) ከእርሳቸው ጋር አብሮ ነበር የተቀበረው። ማለትም በእናታችን ዓኢሻ ቤት ማለት ነው። እናታችን ዓኢሻ እንዲህ ትለናለች፦

« ሁለቱም ሞተው ከተቀበሩ በኋላ እዛ ቤት እገባ ነበር ስገባም ሂጃቤን ባልተሟላ መልኩ ሳልለብስ ነበር
«እዚህ ቤት ውስጥ የተቀበሩት አባቴና ባሌ ናቸው ሌላ ሰው የለም» እልም ነበር።
በአላህ ይሁንብኝ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ አብሯቸው ከነሱ ጋር ከተቀበረ በኋላ ግን እዛ ቦታ ላይ አንድም ቀን ሂጃቤን በትክክል ለብሼ ፊቴን ተሸፍኜ ቢሆን እንጂ ገብቼ አላውቅም። ምክንያቱም ዑመር ረድየላሁ አንሁ አጅነብይ በመሆኑ ሀያዕ አደርጋለው ። » ብላለች....እኛስ መንገድ ለመንገድ ስንት የለባሽ እርቃን እናያለን?? ትዳር በመቀባባት በመገላለጥ በሜካፕ ይመጣ ይመስል...ስንቱን የለባሽ እርቃን እና ከቄራ ዉሻ ስጋ ይዞ ያመለጠ የምመስል... አፍን የቀለም ፋብሪካ ሳምፕል የምመስል ለቅልቃ የምትሄድን እንስት ስንቱን ፈጣሪ አሳየን?? ምን ይባላል ሞት መካሪዉ ሳይመጣ እነሱን ልቦና ይስጣቸዉ፡፡ ኡመር ኢብኑ ኸጧብን አንድ ሰዉ መጣና ከአንቱ ምክር እፈልጋለሁ ምከሩኝ አላቸዉ ..ኡመርም አባትህ ሙቷል ወይስ በሂወት አለ??ብለዉ ጠየቁት
ሰዉየዉም:- አባቴ ሙቷል ብሎ መለሰላቸዉ
ኡመር:- አባትህ ከሞተ ምኑን እመክርሀለሁ አሉት ..እዉነታቸዉን ነዉ ሞት መካሪ ነዉ እኛ ግን ለመመከር ዝግጁ አይደለንም ነገም አባትሽ የገባበት አፈር አያቶችሽ የገቡበት አፈር መግባታችን አይቀርምና ..ችግሩ የሰዉ ሞት እኛን ካልመከረን የኛ ቀን ሲደርስ በደንቂቃ ልዩነት ከሰዉ ከተባለዉ ስም ጀናዛ (አስክሬን) ተብሎ ስም ይሰጠናል ..የዚህን ቀን የሚወዱሽ እናት አባትሽ..የሚወድሽ ባልሽ ..ተሰቃይተሽ ወልደሽ ያሳደግሻቸዉ ልጆች..ዘመድ ጎረቤት ጓደኛ እንወዳታለን አንድ ቀን ትደር የሚል የለም ለምን ጀነዛ ሲቆይ ሽታ ያመጣል...በሌላ ሰዉ ሞት ምክር ሳትወስጂ አንቺም ሄድሽ ማለት ነዉ፡፡ እናት አባት ካለሽ ለተወሰኑ አመታት ያዝናሉ...ባልሽ ሙተሻልና ግድ እንስት ያስፈልገዋል ሌላ ሴት ያገባል...ልጆችሽ በአንቺ እናት አባት ቤት ያድጋሉ ወይም በእንጀራ እናት ያድጋሉ..የሞተ ተጎዳ እህቴ አንቺ በመሞትሽ ጥቂት ሰዉ ለተወሰነ ቀን ሊጎዳ ይችላል በሂወት እያለሽ በሞቱ እናት አባትሽ ወይም ዘመድ ጓደኛ ምክር ዉሰጅ

አብዘሀኛዉ ሴቶች ጅልባብ..ኒቃብ ልበሱ ሲባሉ የሚያመጧት አሳማኝ መስሎ አስመሳይ ላለመልበስ የሚጠይቋት ጥያቄ አለች..ብዙዎቹ ሴቶች ኒቃብ ጅልባብ ለብሰዉ ወንጀል እየሰሩበት ዲናችንን እያሰደቡ ነዉ ለዛ ነዉ የማንለብሰዉ እያሉ ጥያቄን በጥያቄ እየጠየቁ ላለመልበስ ምክንያት ይደረድራሉ
..-------- እህቴ ይሄን ላለመልበስ የምትሰጭዉ ምክንያት በጭራሽ ምክንያት ሊሆን አይችልም..ዛሬ ለጠየቀሽ ሰዉ በዚህ ምክንያት አለብስም ብለሽ መልስ አግኝተሻል ይሄ መልስ ሙተሽ አላህ ሲጠይቅሽ ለመልስነት ይሆናል ወይ ??? የአንቺ ግዴታ በቁርአን ላይ አላህ እንዳዘዝሽ ልበሽ ተብለሻል መልበስ ነዉ..ለብሰዉ ልብሱን ያረከሱት ፀቡ የሚሆነዉ ከአላህ ዘንድ ነዉ...አላህ እኔ ልበሽ ባልኩሽ በተከበረ ልብስ ተገን አድርገሽ ወንጀል ሰርተሽ እኔንም አዋርደሽኛል የሚለብሱትንም የእኔን ትዕዛዝ የታዘዙትን በሌላ አይን እንዲታዩ አድርገሻል ለምን እንደዚህ አደረግሽ ብሎ የሚጠይቅባት ቀን አለ የዉመል ቂያማ..የዛን ጊዜ ለቀልድም የለበሰዉ ..አላህን ፈርቶም የለበሰዉ ሁሉንም የስራዉን ያገኛል፡፡ የአንቺ ግዴታ ለብሰዉ ወንጀል የሚሰሩትን መከታተል ማማት መቦጨቅ ሳይሆን ከቻልሽ መምከር ካልቻልሽም ሰድቦ ለሰዳቢ አሳልፈሽ አትስጭ....የአንቺ ግዴታ እራስሽን አሳምነሽ አላህ ግዴታ ያረገብሽን የራስችን መጠበቂያ ሂጃብሽን መልበስ ብቻ ነዉ፡፡ አላህ ሁሉም ሰዉ በሰራዉ ስራ ተጠያቂ ነዉ ብሎናል...አንቺ ለጥያቄዉ መልስ መፈለግ እንጂ ጥያቄዉን የተሳሳቱን እያየሽ እነሱ ተሳስተዉ ሌላ አሳስተዋል.. እነሱ ተሳስተዉ ሌላ ስላሳሳቱ ስለተሳሳቱም እኔም ብለብሰዉ ይሄ ይገጥመኛል ብለሽ አስበሽ ይሆን እንዴ?? እነሱ ለብሰዉ ወንጀል ሰሩበት ከማለት አንቺ ለብሰሽ ኸይር ስራ ስሪበት ዲነል ኢስላምን አስጠሪበት ..ሸይጧን ያጠመማቸዉን እህቶችሽን ድረሽላቸዉ የዛን ጊዜ ልብሱን አንቺም አከበርሽዉ .. አላማሽ አላህን ፈርተሽ ከለበሽ ጌታሽም ያከብርሻል .የዛን ጊዜ የህሊና ደስታ ታገኛለሽ፡፡



መቅሪብ ሊደርስ ሲል ከዓሊ መስጊድ ወደ ቤቴ ተመለስኩ ማታ ተኝቼ ዛሬ ሚፍታህ እቤቱ ሂጄ በነገረኝ ቃላቶች አስተነተንኩኝ እንደሚወደኝ እርግጠኛ ሆንኩ በጓደኞቼ ፊት ነዉ ቃል የገባልኝ... ሚፍታህ እንደዚህ ቢለኝም ግን ይሄ ማንነቴን መናገር አለብኝኝ ግዴታየ ነዉ ....በልጅነቴ መደፈሬን ተገናኝተን ሻይ ቡና እያልን ከአንድ ሳምንት ቡሀላ ልነግረዉ ወሰንኩኝ ፡፡ከአንድ ሳምንት ቡሀላ ልነግረዉ የወሰንኩት ዛሬ በተናገሩኝ ቃላቶች እኔ አልሆንህም ሁለተኛ እንዳትይኝ ስላለኝ ደስታዉን በዚህ ሳምንት ላለማደፍረስ በማሰብ ነዉ፡፡

ከአንድ ሳምንት ቡሀላ ይሄን ጉዳይ ለመንገር ... ስደዉልለት ስልኬን block አድርጎታል.....በጣም ግራ ገባኝ በጓደኞቼ እና በሌላ ሰዎች ስልክ ስደዉልም የኔ ድምፅ መሆኑን ሲሰማ ጆሮየ ላይ ይዘጋብኛል.. ስልክ ማንሳቱንም አቆመ ..
ምክንያቱን በማላቀዉ መልኩ ሚፍታህ የእኔን ስልክ block አረገዉ የጓደኞቼንም አያነሳም...በጣም ግራ ገባኝ ምን ይሆን ምክንያቱ ????

#ክፍል 3⃣3⃣
ይ............ቀ.........
.......ጥ...........ላ.......ል


          www.tg-me.com/Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
     
#ክፍል ☞ ሰላሳ ሶስት 3⃣3⃣

ፀሀፊ ☞
#አሚር_ሰይድ



ምክንያቱን በማላቀዉ መልኩ ሚፍታህ የእኔን ስልክ block አረገዉ የጓደኞቼንም አያነሳም....በጣም ግራ ገባኝ ምን ይሆን ምክንያቱ ????

ሚፍታህ ጋር ምክንያቱን ሳይነግረኝ ጥፋቴን ሳላዉቀዉ በዚህ መልኩ ተለያየን መደዋወል አቆምን ሒወት ማለት እንዲህ ናት እየወደዱ መለያየት እንዴት ከባድ ነዉ ፡፡ ሚፍታህን እያፈቀርኩት እየወደድኩት በማንነቴ  እኔ ተወኝ ስለዉ እምቢ ብሎኝ እንደገና በራሱ ጊዜ በማላቀዉ ጥፋት ሲተወኝ በጣምም ያማል፡፡  አላህ ፅናቱን ይስጠኝ

ከተለያየን ቡሀላ ብዙ ጊዜ መንገድ ላይ እንገናኛለን፡፡መንገድ ላይ ሲያየኝ እንደሚወደኝ ያስመስላል ከዛም እንደገና ወደ እሱ ለመጠጋት ሳስብ ደግሞ መልሶ ይርቀኛል...ሚፍታህ አሙለጭላጭ ሳሙና ሁኗል....በሒደት ከሚፍታህ ጋር መንገድ ላይ ስንገናኝ እንዴት ነህ----- እንዴት ነሽ ያለፈ ወሬ ማዉራት ካቆምን ቆየን ....እኔም ዲፕሬሽን ዉስጥ ወደኩ..ሚፍታህን ማጣቴ ጥፋቴን ሳይነግረኝ መጣላቴ በጣም ጎዳኝ እንቅልፍ አይወስደኝ...ብቸኝነት ማብዛት ሁኗል ስራየ...ንፋስ ይነፍሳል እንጂ ተራራን አይገፋም ይባል የለ እኔም ብናፍቅም ብወደዉም ባፈቅረዉም ሚፍታህ ለኔ ዉኔ መስሎ ብዙ አሳልፈን የማይረሳ የቅዠት ህልም መስሎ እኔን አእምሮ መጨነቅ እና መጥፎ የተለያዩ ሀሳበች ዉስጥ ከተተኝ.....ሁሌም ሚፍታህ መቼ ነዉ የሚደዉልልኝ? እያልኩ ዛሬ ወይ ነገ አልያም ከነገ ወዳ ይሆን?እያልኩ ስልኬን ይዤ የሱን ስልክ መጠበቅ ሁኗል ስራየ...ምግብ ለራሱ ቀንሻለሁ..ትምህርት ቤት ቀን በቀን መሄድ አቁሚያለሁ ..ሰዉን ማዉራት ለራሱ በጣም አስጠልቶኛል..አባቴ ጋር ለራሱ ቀርበን ማዉራት አቁመናል..የኔ ፀባይ መቀያየር አባቴን በጣም ግራ ገብቶታል...የጀመአ ልጆች ጋር ለራሱ መገናኘት አቆምኩ...ምን ልበላችሁ የሚያረገኝን ለመግለፅ ቃላት የለኝም ..ሚፍታህ ካልደወለልኝ ይሄ የተፈራረቀ እኔን የሚጎዳኝ የፍቅር ስሜት የሚለቀኝ አልመሰለኝም...አንዳንዴ በህልሜ ሚፍታህ ሌላ ሴት አግብቶ እያየሁ በድንጋጤ ህልም አይሉት ቅዠት ብንን እላለሁ ...ሀሳቤ ሚፍታህ ብቻ ሆነ...

አንዳንድ ባለሙያዎች እንደዚህ የሚያደርገዉ የፍቅር በሽታ (ላይመራንስ)የሚሉት ይሆን እንዴ እኔንም የያዘኝ???

ግን ላይመራንስ(የፍቅር በሽታ) ማለት ምን ማለት ነዉ???
በአሁኑ ሰአት በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን በየአጋጣሚዉ የምንሰማዉ ፍቅር ነዉ እየተባለ የምናየዉ የፍቅር ልክፍት በሽታ እንጂ ትክክለኛ ፍቅር አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ጎን ለጎን ቁጥራቸዉ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ግራ ተጋብተዉ ግራ ሲያጋቡ ይታያሉ ...እንዲሁም ፍቅር ምን እንደሆነ በፍፁም ያልገባቸዉ ግለሶቦች ፍቅር ጀምረዉ ሳይሳካላቸዉ ሲቀር ፍቅርን ሲረግሙት እና ሲያማርሩት ..አፍቅረዉና ተፋቅረዉ ለስሜታቸዉ ደስታን ያገኙበት ደግሞ ሲያሞግሱት እና ያለ እርሱ መኖር እንደማይቻል ሲገልፁ ይስታወላሉ፡፡

የሳይካሪስት ተመራማሪዎች ይህን የፍቅር አባዜ ወይም በፍቅር በሽታ የመነደፍ ልማድ ከነጭራሹ ፍቅር አይባልም እነሱ እንዳሉት #ላይመራንስ በማለት ይጠሩታል፡፡፡
ይህ የፍቅር በሽታ ወይም የፍቅር ልክፍት ላይመሪንስ ሳይመቱ ያስለቅሳል፡ማዘንና መተከዝን ያፈሩበታል፡ከፍ ብሎ ሲገኝ ራስን ወደ ማጥፋት ሊያመራ ይችላል፡፡ አፈቀርኩት ከሚሉት ግለሰብ ዉጭ ሌላ ግለሰብን ማፍቀርም ማግባትም እንደማይችሉ ይሰማቸዋል..ይህን ሀሳብ ለዉስጣዊዉ አእምሯችን ክፍል ይነግረዋል..እርሱም ሁሉንም ነገር ሊያከናዉን ወደሚችለዉና ነገሮችን ወደ ተግባር እንዲለወጡ የሚያደርገዉ የአእምሮችን ክፍል ያስተላልፈዋል ..ይሄኔ ነገራቶች ሁሉ በፅልመት አይን መታየት ይጀምራል ..አንዳንዶቹ ሌላ ተቃራኒ ፆታን ሲያዩ ተቀራኒ ፆታ እስከማይመስላቸዉ ይደርሳሉ..አልፎ አልፎም እስከ መጥላት ይደርሳሉ ..ለዚህ አይነት ጎጂ የተዛባ አስተሳሰብ ላይመራንስ ወይም የአፍላ ፍቅር ልክፍት ነዉ..

በዚህ ፍቅር በሽታ በርካቶች ተጎድተዋል..አሁንም እየተሰቃዩ ነዉ በጣም ብዙ ተሰቃይተዋል ..ጭንቀት መከራ ላይ ወድቀዋል .ለወደፊትም የሚሰቃዩ ብዙ ናቸዉ .. አሁን ላይ ያለነዉ ፍቅር ተብየ ጨዋታ የምንጫወት ከዚህ የዉሸት ፍቅር መላቀቅ ካልተቻለ ብዙ የከፋ ነገር እንደሚፈጠር ማሰብ አለብን፡፡ ይህን ፍቅር ተብሎ የተተበተበ የሳምንት ወይ የወር ወይም የአመታት የቃላት ጨዋታ በጊዜ የማይላቀቁ ከሆነ ከዚህም ሲከፋ ከሚወዱት አምላካዊ መመሪያ በመራቅ ህይወታቸዉን ለከፋ አደጋ አጋልጠን እንሰጣለን ፡፡

በዚህ ላይመራስ በሽታ በርካቶች ተምረዉ የት ይደርሳሉ የተባሉ በየመንገዱ ቀርተዋል..ሀብታቸዉን በማጣት ለከባድ ዉድቀት ተዳርገዋል..በዚህም ከሰዉነት ማዕረግ ወጥተዉ ተራና ርካሽ ተግባር ዉስጥ ተዘፍቀዋል .ልመና ስርቆት ሲጋራና መጠጥ ሱስ ዉስጥ በመግባት ስቃያቸዉን ለመርሳት ሲሞክሩ በተደጋጋሚ ተስተዉለዋል፡፡የላይመሪንስ በሽታዉን ለማስወገድ ስቃዩን ለመርሳት በየቡና ቤቶች. በጫት መሸጫ ተራ .የሺሻና የሀሺሽ መንደሮች . በየፊልምና በየካራንቡላ ቤቶች ገብቶ መደበቅ እንደ አማራጭ የሚጠቀሟቸዉ ስልቶች ናቸዉ፡፡ በተለይ ሴቶች የተለያዩ አማረኛ እንግሊዘኛ የፍቅር ፊልሞችን እያዩ የማልቀስ እና ሙዚቃ ማዳመጥ ለመርሳት እያሉ የሚያረጉት ተግባር ሁኗል፡፡
በጣም የሚገርመዉ በላይመራንስ በሽታ የተለከፈ ሰዉ ጤነኛ እንዳትሉት በነፃ የአእምሮዉ ክፍል እያሰበ ነፃ ምርጫዉን ተጠቅሞ መንቀሳቀስ መወሰን ይከብዳቸዋል ..በስሜትና በሞራል መጎዳታቸዉ ሳያንሳቸዉ ሌሎች የሰዉነት ክፍሎችን ጤና ሲያዉክና ስርዓታቸዉን ሲያዛባ ይስተዋላል፡፡

የላይመራስ በሽታ የምግብ መጠጥ ፍላጎት ይቀንሳል. ለእንቅልፍ እጦት ይዳርጋል. የአካል መድከም ድብርት .ከባድ የራስ ምታት. የስራ ፍላጎት መቀነስ .ብቸኝነት መምረጥ .የአእምሮ ነፃ ምርጫን ማጣትና እራሱን የመምራት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይስተዋላል ፡፡ሲበዛ እብደትን እስከማስከተል ይደርሳል...
ለላይመራንስ በሽታ መድሀኒቱ አንድ ብቸኛ መፍትሄ አለ ወደ አሏህ መንገድ መመለስ እና ቁርአንን መቅራት እንደሆነ ብዙ ደርሶባቸዉ ከዚህ የፍቅር ልክፍት የዳኑ ሰዎች ይናገራሉ..... ለሰዉ የሰጠሀዉን ፍቅር ሰዉን ለፈጠረዉ ፈጣሪ አሏህ መልሰህ ስትሰጠዉ ዱንያዉም አኼራዉም ያምራል፡፡



  በዚህ የስቃይ ጊዜ ዉስጥ ሁኜ ጊዜ ደጉ የማያሳየን የማይፈጠር የለም ሌላ አዲስ ነገር ተፈጠረ... ለትዳር እኔን ጠየቀኝ ስሙም ሷሊህ ይባላል፡፡ ሽማግሌም እቤት ላከ

    እስኪ ስለ  ሷሊህ አንዳንድ ነገር ልንገራችሁ ሷሊህ በጂማ ከተማ በእራሱ ህንፃ ላይ የግል ሆስፒታል ያለዉ ነዉ፡፡ ዶክተር ሷሊህ ጋር የተዋወቅነዉ እሱ ሆስፒታል አፓረንት ወጥቼ ነበር የዛን ጊዜ አየኝ ወደድኩሽ ካላገባሁ ሞቼ እገኛለሁ እያለ እርይ አለብኝ፡፡ ከአፓረንት ወጥቼ ለራሱ መግቢያ መዉጫ አሳጣኝ ...ከዛም ለቤተሰቦችሽ ሽማግሌ ልልክ ነዉ እያለ አስቸገረኝ
.....,እኔም እንደዚህ ሲያስቸግረኝ ካፌ ተቀምጠን የኔን ማንነቴን በልጅነቴ ስለተደፈርኩ ድንግል አይደለሁም ብየ አንድ ባንድ ነገርኩት
......ዶክተሬ ሷሊህም እሺ ማንነትሽን አምኜ ተቀብያለሁ ...እኔ የምፈልገዉ አንቺን አግብቶ ልጅ መዉለድ ነዉ አለኝ

በኔ ጓደኞች በስልክም በአካልም በአገኘኝ ቁጥር ጠዋት ማታ አንቺን ካላገባሁ ሙቼ እገኛለሁ እያለ አስቸገረኝ👇👇👇
እኔ ባልወደዉም እሱ ከወደደኝ በቂ ነዉ
ተጋብተን አብረን ስንኖር እወደዋለሁ ብየ አሰብኩኝ ...እኔም እሺ ሽማግሌ ላክ አልኩት
.......እሱም እሁድ ቀን ሽማግሌ ላከ የኔ ቤተሰቦች እና የተላኩት ሽማግሌዎች እኔን ለመስጠት ከተስማማሙ ቡሀላ ኒካሁን እና የሰርጉን ቀን እንወስናለን ተባብለዉ ሽማግሌዎቹ ተመለሱ

ዶክተር ሷሊህ የወደፊቱ ባሌ ጋር እየተደዋወልን ነዉ ...አልሀምዱሊላህ ሚፍታህን መርሻ ይሆንልኛል ብየ አሰብኩኝ..ሚፍታህ ቢተወኝም ማንነቴን የተረዳኝ እስከማንነቴ የሚያገባኝ አገኘሁኝ እያልኩ በአንድ ጎን ደስታ በአንድ ጎን የሚፍታህ ትዝታ ለሁለት ከፋፈለኝ....መቼም አላህ የተሻለ አለዉ፡፡

...ጊዜዉ ይሄዳል ረመዷን ወር ደርሰናል...ፆምም ላይ ነን፡፡ ረመዷን ፆም ጀምረን ከተወሰኑ ቀናት ቡሀላ ሷሊህ ደዉሎ ዛሬ ከሰአት መኖሪያ ቤቱ እንደሚፈልገኝ ነገረኝ
....,,እኔም ሌላ ምንም አልጠረጠርኩም ስለሰርጉ ሁኔታ ልንነጋገር ይሆናል ብየ መኖሪያ ቤቱ ሄድኩኝ

.....መኖሪያ ቤቱ እንደደረስኩ ትንሽ ተቀምጠን አንዳንድ ወሬ እያወራን ከቆየን ቡሀላ መጥቶ ከጎኔ ቁጭ አለ እና ይሄን የዉድ ከንፈሬን ጉንጬን እንደፈለገ ማረጉን ተያይዞታል...ከዚህም አልፎ የማይነኩ ቦታዎችን መነካካት ጀምሯል...
.....ከዛም እኔ አኡዙቢላሂ ብየ ብድግ ብየ ማልቀስ ጀመርኩኝ  ...ከዛም ሷሊህ ምነዉ ተነሳሽ እሳ ምን ያስለቅስሻል?? ነይ እንጂ ልብሰሽን አዉልቂ እንጂ ምን ታካብጃለሽ   ???አለኝ አፉን ሞልቶ
......እኔም አላህን አፈራም እንዴ ??? ኒካህ የለንም እንዴት የኔን ሰዉነት ለሰሜት ማብረጃ ልትጠቀምብኝ ነዉ እንዴ ?? እንዴት እንኳን እኔ ገና ኒካህ ያላሰርን ብናስርስ ረመዷን ፆም ይዘን አይቻልም እንዴት ይሄን ታስባለህ ??? አልኩት በመናደድ
.....ዶክተር ሷሊህም መቼም ቢሆን ከአእምሮየ የማይጠፋ የመርዝ ቃሉን ተፋብኝ.. ሷሊህን የመሰለ ስም ይዟል ግን ተግባር ዜሮ ነዉ...ስሙን ያወጡለት ጉቦ የበላ ቃልቻ መሆን አለበት
....እኔን እንደዚህ አለኝ አላህንማ የማፈሪዉ አንቺ ነሽ.......

#ክፍል 3⃣4⃣
ይ...............ቀ............
.........ጥ...........ላ........ል

❀ share
           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
 
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
     
#ክፍል ☞ ሰላሳ አራት 3⃣4⃣

ፀሀፊ ☞
#አሚር_ሰይድ




ሷሊህ እንደዚህ አለኝ>>>>> አላህንማ የማፈሪዉ አንቺ ነሽ....... የትም ስትልከሰከሺ ማንም ጋር ስትተኚ ስትማግጪ ላስወሰድሽዉ ድንግልና ምን ታካብጃለሽ... ባለፈዉ እኮ በልጅነቴ ተደፍሪያለሁ ብለሽ ስትነግሪኝ የተቀበልኩሽ በዉበትሽ ተማርኬ ነዉ እንጂ እዉነት እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ ... ዉበት ደግሞ ለማንኛችንም ወንድ ልጆች አስቸጋሪ ነዉ የፍቅር ሳይሆን የዉበት ፈላጊ ነን ....እኔ የወደፊት ባልሽ ነኝ እስከምንጋባ ድረስ አብረን አንዳንዴ ማሳለፍ አለብን ..አብሮ ለመተኛት አዲስ አትሁኚ የለመድሽዉ ነዉ አለኝ፡፡

የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም አይደል የሚባለዉ ሷሊህ ሆዱ ያለዉን በዚህ ቅፅበት ዘረገፈዉ....

.....,.እኔም ምንም አላልኩትም ከዶክተር ሷሊህ ቤት ወዳዉኑ ወጥቼ እቤቴ እስከምድርስ በጅማ ጥቁር አስባልት መንገድ ጥቁር እድሌን ይዤ ከለር በሌለዉ እምባ ልስልስ ባሉት ጉንጮቼ አዘንባቸዉ ይዣለሁ ፡፡
አይ ሷሊህ የተማረ ብዙ ነገር ያቃል ተብሎ ለዛዉም በዶክተርነት ዲግሪ ይዞ የብዙ ሰዎችን ሂወት ያተርፋል ተብሎ ተስፋ የተሰጠዉ ሰዉ ..ከአፋቸዉ ጤነኛ መስለዉ ዉስጣቸዉ ግን እንደ አባጨጓሬ የኮሰኮሰ ማንነት በነጭ ጋወናቸዉ ተሸክመዉ ይዞራሉ ፡፡በሷሊህ አነጋገር ልቤ እየደማ ከሚፍታህ መለየት በላይ ወደ ዉስጥ ብሶቴ ገብቶ ብዙ ግፍ ወደ ተሸከመዉ ወደ መኖሪያ ቤቴ በለቅሶ አይኔ ቅልት ብሎ ተመለስኩኝ......
 
እቤት ክላሴ ገብቼ -----የፈጠርከኝ አላህ ሆይ!!!!! አረ ምንድን ነዉ ወንጀሌ??? አላህ ሆይ ፈተናየ በዛ ፈተናዉ ይበቃሻል በለኝ... ፅናቱን ስጠኝ እያልኩ እያለቀስኩ ዱአ ሳደርግ ..ሶላትም ስሰግድ አደርኩ፡፡
አዳሬን ለሰከንድ እንኳ እንቅልፍ በአይኔ ሳላይ ጨለማ ለጀንበር አስረከበች .......,

★★★ ፅናት ማለት ቀልባችን ላይ የተዘራዉን የኢማን ችግኝ ተንከባክቦና ኮትኩቶ ለፋሬ እስከሚደርስ ድረስ ዋጋ መክፈል ነዉ። ሳይሞክሩ መፍራት፤ ሳይወዳደሩ ማሸነፍ፤ሳይደርሱ መጨነቅ፤ ሳይጠይቁ ማጣት..... ፅናት የሌላቸዉ ሰዎች የሚያሳዩት ባህሪ ነዉ። ለምን እንደወደቁ ለማስረዳት መከላከያ ማፈላለግ ፅናት የሌላቸዉ ሰዎች አዘወትረዉ የሚያንፀባርቁት ፀባይ ነዉ።

ፅናት ማለት በሁሉም ነገሮች ላይ አሸናፊ መሆን አይደለም። ነገር ግን ጥረትን አለማቋረጥ እንጂ። የኢማን ፅናት ያለዉ ሰዉ በህይወቱ ዉስጥ የሚያጋጥሙትን ፈተናዎች በቀላሉ ይቋቋማቸዋል። በኢስላም ላይ መጤ አመለካከቶች ጠባሳ አይፈጥሩበትም፤ አሉባልታዎች አይዳፈሩትም፤ ስጋቶች ከመስመር አያሶጡትም፤ ለዲኑ ሲል መስዋት መክፈል አይከብደዉም።

የኢማን ፅናት ቢላልን ለስኬት አብቅቶታል፤ሀምዛን በሸሂድነት ሸኝቷል፤ ሱመያ ዉድ ህይወቷን ሰዉታለች፤ አቡበከርን የሲድቅነት ማዕረግ አሰጥቷል፤ በበድር ላይ ሙሽሪኮችን ድል አሰጥቷል።

አላህ በተከበረ ቃሉ በቁርአን እንዲህ ብሏል
እነዚያ ጌታችን አላህ ነዉ ያሉ፥ ከዚያም ቀጥ ያሉ፥ በነሱ ላይ ፍርሀት የለባቸዉም። እነርሱም አያዝኑም(አሕቃፍ ፡13)
☞ እነዚያ ጌታችን አላህ ነዉ ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ አትፋሩ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላቹሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳል(ፋሲለት፡30)


ጠዋት እቤት መሆን ሲያስጠላኝ ተነስቼ ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ ፡፡ግን ምን ይደረጋል እራሴን በጣም ስላመመኝ መማር ስላልቻልኩ መልሼ ወደ ቤቴ ተመለስኩኝ

ሷሊህ የብስ የኔን ሞራል ለመጉዳት በሶስት ቀን በሳምንት  ይደዉልና ያንን ነገር አመቻቸሽ የኛ ጨዋ መቼ አብረን እንደር ?? ወይስ የመጀመሪያሽ ወንድ ከኔ ይሻልሻል?? እያለ ይቀልድብኛል

እኔ መልስም አልመልስለት ፈጣሪ የስራዉን ይስጠዉ ፡፡ግን ከእንደዚህ ያለ ሰዉ ለሰዉ አርአያ መሆን ከሚችል ሰዉ ለምን ይሄ መጥፎ ባህሪ ጎልቶ ይንፀባረቃል??? ሷሊህ ለህዝብ ተስፋ መሆን ሲገባዉ በተለይ እንደኔ ተቸግረዉ ተስፋ ላጡ የሚረዳቸዉ አጥተዉ የሚሰቃዩ ላሉ ወገኖቹ አብሽሩ ከጎናችሁ ነኝ ብሎ ማፅናናት ተስፋ መስጠት ሲገባዉ ...ነገር ግን እንደ እሱ የወረደ አስተሳሰብ ይዞ እንደዚህ እኔን ማሸማቀቅ መስደብ ምን ያደርጋል ?? ቢቻል ማግባቱ ቢቀር ለኔ ሒወት እንዲስተካከል የስነልቦና ጫና አለብሽ ብሎ መፍትሄ እንደመስጠት እየደወለ የሚያሳምም ንግግር በቃላት እየወረወረ የብስ ሒወትን ተራራ እንደመግፋት አደረገብኝ....ታዳ ምሁርነቱ ዶኮተርነቱ ምኑ ላይ ነዉ ??መማር ማለት ይሄን ካላገናዘበ ምኑ ላይ ነዉ መማሩ ??? ነጭ ጋወን መልበሱ እና ከስራዉ ጋር የማይሄድ ስም ሷሊህ ቢሉት ጥቅም የለዉም..
★★★የኢማሙ አህመድ ምክር-ትዳርን ላሰቡ ሰዎች
ትዳር ያሰባችሁ ጊዜ ባለ ዲኗን ምረጥ!" አሉ ውዱ ነብይﷺ።
በዲንህ ጥሩ አቋም ላይ ላለኸው ወንድሜ ሆይ ዲኗን፣ ፀባዩዋን አይተህ አግባ። መስፈርትህ ዲን ካልሆነ ግን
① ለነብያዊው ምክር ትኩረት ነፍገሀል፣
② በራስህ ህይወት ላይ ቀልደሀል፣
③ የመጪ ልጆችህን ሐቅ ገሸሽ አድርገሀል፣
④ ባለ ዲኗ እህትህን ካልሆነ ቦታ የመውደቅ እድሏን በአንድ ሰው ከፍ አድርገሀል፣
⑤ ለማህበረሰብህ ተምሳሌት የመሆን ፣ ጥሩ ነገር የማበርከት እድልህን በእጅጉ አመንምነሀል።
⇛ስለዚህ "ኋላ አስተካክላለሁ" እና መሰል ማመካኛ እየደረደርክ እራስክን እንዳትሸውድ። ዛሬውኑ ባለ ዲኗን ምረጥ። ካልሆነ ግን ወይ ስትነፍር ትኖራለክ። ወይ ትዳራችሁ ይነፍራል። ወይ ልጆችህ ንፍሮ ይሆናሉ።

አግብቻት የምትስተካከልስ የለችም ወይ?" እንዳይባል። ልትኖር ትችላለች። ግና የተስፋ ዳቦ ከማለም ከወዲሁ ለነብያዊ ምክር ዋጋ ሰጥቶ ሰበብ ማድረስ ይሻላል።

>>>>>ምርጥ ምክር ዱንያ አኼራውን ለሚያሳስበው በኒ አደም ሁሉ!!

አደራሽን የምትወጅውን ወንድ ሳይሆን የሚወድሽን ወንድ አግቢ፡፡ ቢክራ ቢክራ የሚል ወንድ ሲጀመር ለስሜቱ የሚጨነቅ እንጅ እዉነት አላህን ፈርቶ ትዳርን የፈለገ አይደለም።ምክኒያቱም ረሱልﷺ ባላጩ ለዲን ብሎ ያገባ ነዉ ስላሉ።

ትክክለኛ ትዳር ፈላጊ ወንድ ለዲኗ ሲል መርጦ ያገባ ነዉ። ከዛ ዉጭ ቢክራሽን ቅድሚያ የሚል ከሆነ አንችን ሳይሆን ቢክራሽን ብቻ ነዉ የሚፈልገዉ ማለት ነዉ። ስለዚህ ባጭሩ አይወድሽም ። ይሄን ሰዉ ትተሽ ሌላ አላህን የሚፈራ የሚወድሽን አግቢ።
ምክንያቱም የሚወድሽ ወንድ በደስታ ያኖርሻል; ፍቅርን ያስተምርሻል፣ አንችም ለሚወድሽ ወንድ ምንም ሳትሳሺ እስትንፋስሽን ስጭው ያኔ
ደስታ ምን ማለት እንደሆነ ታውቂያለሽ፡፡
አህቴ አደራሽን አንቺ ግን የምትወጂውን ወንድ ግድ ካላገባሀኝ ሙቼ እገኛለሁ እያልሽ እንደዉም ቤተሰቦችሽን አያገባችሁም እሱን አገባለሁ ካልሆነ እናት አባቴ መሆናቸዉን እክዳለሁ እያልሽ የምትወጅዉን ካገባሽ የሚወዳትን ሴት ሲያገኝ ጥሎሽ ይሄዳል። እንዲሁም ሌላ ቢክር ያላት ሴትም ካገኘ ጥሎሽ እንደሚሄድ አትጠራጠሪ። ግን አንቺ ምንም አማራጭ የለሽም ከመቀበል ዉጭ ለምን ወይ ልጅ ወልደሻል ወይም እሱን እንዳላገባ ከከለከላችሁኝ እናት አባቴ መሆናችሁን እክዳለሁ ብለሽ የወላጅ ሀቅን ዘንግተሽ ቤተሰቦችሽን ገፍትረሽ እሱን ብለሽ ስለሄድሽ ወደ ቤተሰብ ለመመለስ እፍረት ይሆንብሻልና፡፡


እህቴ ትዳር እንደ ልጆች ጨዋታ ...ጨዋታዉ ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ ተብሎ የሚቀለድበት አይደለም በትዳር ህይወት ዉስጥ ሰላም ከሌለሽ እራስሽን እንደኖርሽ አድርገሽ አትቁጠሪዉ። በጣም ከባድ ነዉ ስለዚህ ተጠንቀቂ ለቢክራ👇👇
ሳይሆን ለዲኑ የሚጨነቅ ወንድ አግቢ።

ማወቅ ያለብሽ ነገር የአላህን ሀቅ ያልጠበቀ ወንድ በፍፁም ያንችን ሀቅ አይጠብቅልሽም። ሊያገባሽ የመጣዉ ወንድ ቢክራ ብቻ ከሆነ መስፈርቱ እዉነት አላህን ቢፈራ ኑሮ የረሱልን ሰለላዋለሂ ወሰለም ተግባር ባስቀደመ ነበር።

አላህ ካዘነላቸው ወንድሞች ውጭ!
ወንዶች በአፍ ሌላ! በተግባር ሌላ ናቸው!
ለትዳር የሚያስቧት ሴት የመጀመሪያ መስፈርታቸው ዲኗ ሳይሆን መልኳ...በተጨማሪ ያላገባች( ቢክራ) የሆነች ብለው ሙጭጭ ይላሉ!
ታዳ በተግባር ይህ ከሆነ! በንግግር ብቻ ዲን ዓቂዳ ነው ትላለህን?
የአላህ መልዕክተኛ (صلى الله عليه وسلم) ሱና መልዕክት እኮ ይህ ነው:-

ከአቡ ሁረይራ በተወራው ሀዲስ ተወዳጁ ሀቢቡና ረሱል (ሰ.ዐ.ወ ) እንዲህ ብለዋል:
አንድ ወንድ ሴትን ልጂ ለ 4 ነገሮች ያገባታል!
ለዲና ለገንዘቧ ለዘሯ ለውበቷ
ከዚህ! በላጩ ግን! ለዲኗ ብሎ የሚያገባት ነው!
አለበለዛ ግን እጁ ዓመድ አፋሽ ነው የሚሆነው!!! ብለዋል፡፡
አላህ ሆይ በፈጣሪ ቃል እና በነብዩ ሰዐወ ንግግር ተመርተን እጃችን አመድ አፋሽ ከመሆን ጠብቀን፡፡

በኮሌጅ ሁለተኛ አመት ፍቅር በሚባል የሰዉ አላማ ፕላን ጋር የማይመጥን የሒወት አዙሪት ጊዜየን ፈጅቼ
የሁለተኛ አመት Coc ስፈተን ወደኩኝ...ደግሞ ከወደኩኝ ሶስተኛ አመት ኮርስ መቀጠል አልችልም

ከዛም ለCoc ለመፈተን ብየ መስከረም ወር ላይ የጅማ የቅርብ ጎረቤት ወደ ሆነችዉ አጋሮ ከተማ ሄድኩኝ ..

አጋሮ ፈተና በሄድኩበት ጊዜ ከነመፈጠሩ የረሳሁት ካሊድ እየደወለ በስልክ ማዉራት ጀመርን በጣም ተቀራረብን...ጠዋት ማታ እየደወለ አብሽሪ አላህ ያሳካልሽ ይለኛል፡፡ ካሊድ ጋር ማዉራቱን እንደ አዲሱን ተያይዘንዋል አጋሮ ሁኜ እሱ ጋር ማዉራት ሱስ እስከሚሆብኝ ድረስ ተቀራረብን....

ካሊድ ብዙ ጊዜ ሲደዉልልኝ እንደዚህ ይለኛል #ነዋል_ቆጣሪዉ_እየቆጠረ_ነዉ ፡፡ የምትለዉን ቃላት እየደጋገማት ነዉ
....,እኔ ደግሞ እኔ ጋር ስደዉል ነዉ ማለት ነዉ ካርድህ የሚያልቀዉ?? እለዋለሁ ..ቆጣሪ እየቆጠረ ነዉ የሚለዉን ቃላት በቀላል ማዕናዉን መረዳት አልቻልኩም

....,ለካ ይሄ ቆጣሪ መቁጠር ቡሀላ ማዕናዉ ትርጉሙን ሳቀዉ ፍቅርሽ እየጨመረብኝ ነዉ ማለት እንደሆነ በጊዜ ሳይገባኝ ከብዙ ቀን ቡሀላ ተረዳሁኝ

ካሊድ ጋር በስልክ በጣም መቃለድ ተያይዘነዋል....እሱም እንደበፊቱ አይደለም አሁን ፍርሀቱ ለቆታል.....ግን እኔ ካሊድ ጋር ስናወራ ለትዳር ይሆናል ብየ በጭራሽ አስቤዉም ትዝም ብሎኝ አያቅም ...ለምን በፊት ካሊድን እንደማልፈልገዉ ነግሬዉ እሱም ተስማምቷል ፡፡ አሁንም አጀማመራችን በእህትነትና በወንድምነት ተባብለን ነዉ፡፡ ግን ይቺ ወንድነትና እህትነት የምትለዉ ቃላት ይአጅበኛል እሱም እቤቱ ወንድም እህት እያለዉ እኔም እቤቴ ወንድም እህት እያለኝ ተጨማሪ የባዳ እህትና ወንድም ለምን አስፈለገ???ስንት በቁጥር ለመግለፅ የተጀመረ የሀላልም የሀራሙም ግንኙነት በእህትነትና በወንድምነት እየተጀመረ ከአንድ ማህፀን ዉስጥ ለወጣዉ ወንድሟ የማታወራዉን ሚስጥር እንደ ወንድምሽ እይኝ ላላት ስንቱን የቆጥ የማገሩን ስታወራ ትዉላለች??? እሱም ቢሆን እቤቱ የምታገለግለዉን አይቡን የምሸፍንለት እህቱ እያለች በሚዲያ ለተዋወቃት እህት ተብየ ምን አዲስ ነገር አለ ስትለዉ ዘጠኝ አህጉር የሰማዉን ወሬ ሲቀባጥር ይስተዋላል፡፡ በዚህ በእህት ወንድም ግንኙነት ስንት ሀራም ወንጀል እየተሰራ ነዉ??? መቼም እኔ እህት ሁኚኝ ወንድም ልሁንሽ ሲልሽ የአንቺ መልስ መሆን ያለበት እቤት ያሉት ወንድሞቼ በቂ ናቸዉ ካልሆነ ሒወትሽ አደጋ ላይ ነዉ እህቴ.,

coc ተፈተን አልሀምዱሊላህ አለፍኩኝ ..መልሼ ወደ ጂማ ተመለስኩኝ ፡፡ ትምህርቴን ሶስተኛ አመት ተመዘገብኩኝ፡፡ በዚህ ሶስተኛ አመት ትምህርት ግሬድ ለማሻሻል ፍቅር የሚባለዉን ከልቤ ፍቄ ለማጥናት ወሰንኩኝ፡፡
በዚህ አመት እቅድ ብየ ብዙ ሀሳቦችን ካሰብኩኝ ቡሀላ በጠረንፔዛ ዙሪያ ዉይይት በተረጋጋ መልኩ እኔዉ ብቻየን በብቻየ ክላስ ተቀምጬ ተወያይቼ ወሰንኩኝ፡፡ ዉሳኔየም ለአሁኑ አመት የመጨረሻ አመት ተመራቂ ተማሪ ነኝ  ቸክየ ተምሬ coc ካለፍኩኝ ስራ የማግኘት እድል አለኝ..በተጨማሪም በትምህርት ቤታችን ግሬድ ከፍተኛ ነጥብ አለኝ ዲግሪ በስኮላር ሺፕ እማራለሁ፡፡ ብየ ወሰንኩኝ


ወላሂ ቢላሂ ወንድ የሚባል ፍጡር በትምህርት ቤትም ሆነ ሰፈርም በየአየሁት አጋጣሚ እንኳን ለማዉራት በአይኔ ለማየት ጠላሁኝ ..ጭራሽ ከወንድ ልጅ ፍቅር ከመጠበቅ ጆንያ ሙሉ ቁንጫ ለቆ እነሱ ይመጣሉ ብሎ መጠበቅ ይሻላል የምትለዉን አባባል አያብሰለሰልኩ እራሴን አሳመንኩ...ፍቅር ስሙ እንጂ ተግባሩ ወንድ ልጅ ጋር የለም ብየ በአራት ነጥብ ደመደምኩ ፡፡

የሚገርማችሁ ብዙ ሴት ጓደኞቼ በትምህርት ቤትም በሰፈርም ነዋል ልናገባ አስበናል ስለትዳር ምን ትመክሪናለሽ ??ብለዉ ሲጠይቁኝ
...እኔም መልሴ ጥምም ያለ ተስፋ የሚያስቆርጥ እንጂ ተስፋ የሚዘራ ከአፌ በጭራሽ አይወጣም ..... የዘንድሮ ወንድን አምናችሁ አታግቡ እኔ ትዳር አለመክራችሁም...ወንድ ልጅ የሚያገባዉ ለስሜቱ እንጂ አንቺን አስደስቶ ለመኖር አይደለም እያልኩ የብዙ ሴት ጓደኞችን ሒወት በተጣመመ የትዳር እና የወንድ ልጅ አመለካከት በልቤ ቋጥሬ አበላሸሁ..

#ክፍል 3⃣5⃣

ይ........ቀ.........ጥ
...........ላ.........................ል


          `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
     
#ክፍል ☞ ሰላሳ አምስት 3⃣5⃣

ፀሀፊ ☞
#አሚር_ሰይድ


....እኔም የዘንድሮ ወንድን አምናችሁ አታግቡ እኔ ትዳር አለመክራችሁም ብየ የብዙ ሴት ጓደኞችን ሒወት በተጣመመ የትዳር እና የወንድ ልጅ አመለካከት በልቤ ቋጥሬ አበላሸሁ..
.የትምህርት ቤት ጓደኝቼ ነዋል ለምን አታገቢም?? ቆንጆ ነሽ ደግሞም ብዙ የትዳር ጥያቄ መጥቶልሻል ይሉኛል
....የአሁን ወንድ አምኜ ከማገባ እንደ መብራት ፓል ቁሜ ብቀር ይሻለኛል ሆነ የዘወትር መልሴ

ማንኛቸዉም እኔን የሚቀርቡኝ የሴት ጓደኞቼ ነዋል ላገባ ነበር ብላ ካማከረችኝ...አረ ወንድ አትመኝ ..ዛሬ አገባሽ ነገ አብረሽ እንደምትኖሪ እንደማትፋቺ እንዴት እርግጠኛ ሆንሽ ???የአሁን ወንድ እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ ቢልሽ ከአፉ ነዉ ከልቡ አይደለም አትመኝ እያልኩ ክፉ መካሪ ሆንኩ ፡፡ በሰፈር እና በሬፍት ቫሊ ኮሌጅ ተሰሚነት ተቀባይነት ስላለኝ አምነዉኝ ብዙ ጓደኞቼ ትዳር መልሰዋል፡፡ አላህ ይቅር ይበለኝ

እኔ ትዳር የሚባለዉ ጠላሁኝ በጭራሽ ስለትዳርም ማሰብ አልፈልግም..እኔ ለትዳር ያለኝ አመለካከት በጣም የወረደ ሆነ፡፡ደግሞ ትዳር አርአያ ያስፈልገዋል እኔ ሳድግ ከቤተሰቦቼ ያየሁት ሲጨቃጨቁ ሲጣሉ ነዉ እንጂ የቤተሰብ ፍቅር አላየሁም አሁን ድረስ የሚገርመኝ እናት እና አባቴ የመጨረሻ ሴት ልጅ ከወለዱ ቡሀላ አብረዉ እንኳ ሲተኙ አይቻቸዉ አላቅም፡፡የየራሳቸዉ ክፍል አላቸዉ፡፡
እናትና አባቴ ከመቀያየማቸዉ የተነሳ መኖሪያ ቤት ሲገቡ አሰላሙ አለይኩም ማለት ጎጂ ባህል ነዉ የተባሉ ይመስል አባቴ ሳሎን ከተቀመጠ እናቴ ሌላ ክላስ ነዉ የምትሆነዉ ...ዋ ሳትጣሉ ታድሩና የተባሉ ይመስል በተለያዩ ምክንያት ለምን ዉሀ ቀጠነ በሚል ስበብ ቤቱን በአንድ እግር ያቆሙታል ...
ይወደኛል ያለአንቺ መኖር አልችልም ሲለኝ ከዛም አልፎ እኔን ሊያገባ ሽማግሌ የላከዉም ሚፍታህ እስከ ነመፈጠሬም ረስቶኛል ፡፡ የተማረ ይግደለኝ በሚለዉ የዋህ ህዝብ ባህል አድጌ እንደ ዶክተር ሷሊህ ያለም ሙሁር እሱም ሊያገባኝ ሽማግሌ ልኮ ግን አላማዉ ሌላ ሁኖ እንደዉም የብስ ስለትዳር ተስፋ አስቆረጠኝ ፡፡ ታዳ ስለትዳር ማንን ጥሩ አርአያ ላድርግ??

በኔ በደረሰብኝ በደል ታማኝ ወንድ የለም...ይሄን ስታነቡ ሁሉም ሊያጉመተምት ይችላል እደግመዋለሁ ታማኝ ወንድ የለም ....ወንድ ልጅ ሴትን ህልም እንደሌላት የወንድ ልጅ መጠቀሚያ ብቻ አድርጎ ያስባል፡፡ ሴት ልጅ ስትፈጠር ጀምራ በእሾህ የተከበበች ናት እኛ ሴቶች ግዴታችን እሾሁን እየነቀልን መሄድ ነዉ ..ግን የሚያሳዝነዉ በሴት ዙሪያ የተሰከሰከዉ እሾህ ከሴት ማህፀን የወጣዉ ለሴት ልጅ እዝነት ክብር የሌለዉ አላማዉን የዘነጋ ወንድ ልጅ ነዉ፡፡ ሴት ልጅ በሒወቷ ብዙ ፈተና ችግር መሰናክል ብታሳልፍም ብዙ መስዋአትነት ለሱ ከፍላ አንድ ጎዶሎ ካገኘባት ምን ሁነሽ ነዉ?? በምን ምክንያት ይሆን የተሳሳትሽዉ?? ብሎ ሳይጠይቅ በራሱ አስተሳሰብ ብቻ የሚጓዝ ከሴት በላይ ነኝ ምን ታመጣለች ብሎ የሚያስብ ነዉ፡፡ ከዛም የፈለገዉን ካረገ ቡሀላ ወይም መወደዱን ካረጋገጠ በሴት ልጅ ንፁህ የዋህ ልብ ሞት አፋፍ እንደቀረበች ቁንጫ በእጁ እያፍተለተለ መጨዋት ይፈልጋል..ታዳ እኔ ንፁህ ልቤን ሰጥቼ ተጎዳሁ አይበቃኝም??

በቃ አላገባም ምን እሆናለሁ?? ባላገባ ምን የሚቀርብኝ አለ ?? ከስሜትና ከዘር ማስቀጠል ዉጭ ትዳር ለኔ ምን ይጠቅመኛል ??አግብቼ ማንነቴን የማይቀበል ወንድ ለኔ ምን ይጠቅመኛል??? የሰዉ ልጅ ለስሜት ብቻ ነዉ እንዴ የተፈጠረዉ??? እስኪ ንገሩኝ፡፡ አላማ አለኝ ተምሬ እመረቃለሁ Coc አልፌ ስኮላርሽፕ እማራለሁ ከዛም ...ትልቅ ሰዉ ስሆን ከጎን አንድ ልጅ ያስፈልገኛል.....ልጅ መዉለድ እንኳ ቢያምረኝ ከህፃናት ማሳደጊያ ጉድፈቻ አንዲት ሴት ልጅ ወስጄ አሳድጋለሁ ብየ እራሴን አሳመንኩኝ ይሄ የራሴ አስተሳሰብ ብቻ ነዉ ..ለኔ የምኖረዉ እኔ ነኝ ከዚህም ዉጭ ብዙ ማሰብ እችላለሁ

ለወንድ ልጅ የተጣመመ የተወላገደ አስተሳሰብ እያለኝ ከካሊድ ጋር በጣም መደዋወል ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ ተቀራርበን ማዉራት ተያይዘነዋል፡፡ ካሊድ ባጃጅ አለዉ ቀን በቀን ትምህርት ቤት በር ላይ እየጠበቀ ከትምህርት ስወጣ ባጃጁን ይዞ መጥቶ እቤቴ ድረስ ይሸኘኛል..

ካሊድን የማደንቀዉ ባህሪ አለ ስራዉን አክባሪ በጣም ጎበዝ ነዉ ሁለት ባጃጅ አሉት አንዱን እራሱ እየሰራ አንዱን ለሹፌር ሰጥቷል.....በጊዜ ብዛት በእነዚህ ባጃጆች ስራየን ሰርቼ ሀይሮፍ መኪና ገዛሁ ሲለኝ በጣምምምም ገረመኝ ፡፡
ስራ አክባሪዋን ታከብራለች ይባላል እዉነት ነዉ ደግሞ ሲኖር ከሰዉ በታች ሁኖ ነዉ እንጂ አለሁ አለሁ ልታይ ልታይ አይልም..ጉረኛም በጭራሽ አይደለም

ካሊድ በተፈጥሮዉ እንከን የሌለዉ ሰዉ ነዉ....መጥፎ አይናገር ሰዉ ጋር አይጣላ በስራ ቦታ ስለ እሱ ሁሉም በጥሩነቱ እንጂ በመጥፎ ማንም የሚያነሳዉ የሌለ ሁሉም ሰዉ ጋር ተግባቢ ነዉ፡፡
....ካሊድ ለኔ 1% እንኳ ባያስቀይመኝም ባያስከፋኝም እኔ ጥሩነቱን ልቤ መቀበል አልቻለም ምክንያቱም ወንድ ማመን ስልችቶኛል ..በተለያዩ ወንዶች የተወጋዉ ልቤ ቆስሏል ገና አላገገምኩም ....በተለይ ደግሞ አፍቅሮ ማጣት እንዴት እንደሚጎዳ ስሜቱን ስለማቀዉ ከካሊድ ለመራቅ ወሰንኩኝ

....ካሊድ ጋር የመጣያ መንገድ ማፈላለግ ጀመርኩ ..እሱ የሚሰራበት አካባቢ የባጃጅ ፌርማታ የሚቆምበት ቦታ እየሄድኩ..መቼም የባጃጅ ሹፌር ስራቸዉ ሴት ጋር መጃጃል ሶስት እግር ሲይዙ ከእነሱ በላይ ሰዉ ያለ አይመስላቸዉም ..ብዙዎቹ ከትርፉ ላይፉ እያሉ ነዉ ባጃጅ ገዝተዉ ስራ የሚጀምሩት፡፡ ታዳ የአሁን ዘመን ሴቶች ሁለት ወይ ሶስት ብር ትራንስፓርት ሸኘሁሽ አልቀበልሽም ሲላት በአዉሮፕላን በሌላ ሀገር የሸኛት ይመስል ተደስታ በዚህ ሶስት ብር ዉለታህን አረሳም ብላ ዉለታዋን ለባጃጅ ሹፌር የፈለገዉን ክብሯን አሳልፋ ስትሰጥ እያየን ነዉ..አይ ሴትነት በሁለት በሶስት ብር ብለሽ ሹፌር ያዝናናል ነጋዴ ጊዜ የለዉም እያልሽ በረከሱ ሹፌሮች ማንነትሽን አታርክሺ....እኔም ካሊድ እንደነዚህ አይነት የባጃጅ ሹፌሮች ቢሆን ብየ ለመጣላት ስለሚያመች የተለያዩ ሰዎችን ስለእሱ ባህሪ በተለያዩ ዘዴ ለማዉጣጣት ብሞክር የእሱን መጥፎ ጎን የሚነግረኝ አንድ ሰዉ እንኳን አጣሁ፡፡

ካሊድ መጥፎ ባህሪ አለበት ሴት ጋር ይሄዳል የሴት ጓደኛ አለዉ ወይ ጫት ይቅማል ወይ ሲጋራ ያጨሳል የሚል አጣሁ...በምን ምክንያት ልጣላዉ ???
ካሊድ ሲደዉልልኝም አዉቄ እንዲናገረኝ ተናግሬዉ እንዳስቀይመዉ እያልኩ መጥፎ ቃላቶች ስናገረዉ እሱ በኸይር ነዉ የሚመልስልኝ....ብዙ ከካሊድ መራራቂያ ዘዴ በተለያየ ምክንያት ከዉሸቱም ከእዉነቱም እየደባለኩ ብናገረዉ ካሊድ በጭራሽ ሊርቀኝ አልቻለም...እኔም እሱን የምጣላበት ምክንያት አጣሁኝ.... ወላሂ ሱመወላሂ ካሊድን አንድ ጥፋት እንከን ባገኝበት ልርቀዉ 100% ወስኛለሁ ግን በጭራሽ እንዴት ጥፋት ላግኝበት?? አልቻልኩም

ካሊድ በስልክ ደዉሎ እንደዚህ አለኝ
...ነዋል ከቤተሰቦቼ ወጥቼ #ቤት_ተከራይቼ_ብቻየን_መኖር_ጀመርኩኝ አለኝ

በሌላ ቀን ሲደዉልልኝ ለቤቱ የገዛዉን ይነግረኛል .አንድ ቀን ቡፌ ገዛሁ ሌላቀን ቴሌቪዢን አረ ብዙ ነገር እያሟላ እንደሆነ ይነግረኛል፡፡ እኔንም በተለያዩ ቅኔዎች እንደሚወደኝ ይነግረኛል..ለምሳሌ አንቺን የመሰለ ልጅ ፈልጊልኝ ይሄ ቤት ብርድ ብርድ አለኝ ሀላሌ ናፈቀችኝ...ወይም እቃዉ ቤቱ ተሟሏ ምሳ 👇👇👇
ቁርስ አዘጋጅታ እንብላ የምትል ጠፋች....ቤቱ ሙድ እየያዘብኝ ተቸገርኩ ብቻየን ሊወረኝ ነዉ...አንዳንዴም የገዛሇቸዉ የቤት እቃዎች ሳልጠቀምባቸዉ ሸረሪት ድር አደራበት እኮ ማን ይስራበት...እያለ በተለያየ ዘዴ እንደሚወደኝ እና በዘዴ እኔን ማግባት እንደሚፈልግ እየነገረኝ ይመስለኛል ባልሳሳት...ግን እንጃ ደግሞ የወንድ ፍቅር ከአፍ መች ያልፋል

ዘንድሮ መመረቂያ አይደል አፓረንት መዉጣት ግድ ነበር ከጂማ የሶስት ሰአታት መንገድ የሚሆን ሰካ የምትባል ገጠራማ ቦታ ጤና ጣቢያ ለሶስት ወር ጊዜ ወጣሁኝ እዛዉ ለ3ወር ቤት ጓደኞቼ እኔ መፍቱሀ እና ብሩክ ታይት ጋር አንድ ላይ ቤት ተከራይተን መኖር ጀመርን ፡፡ ላለመደዉ ሰዉ በጣም ይከብዳል በግድ አገሩን ተላመድኩት፡፡አይ ዱንያ
★★★ነብዩላህ ኑህ (ዐ.ሰ) ሊሞቱ በተቃረቡበት ጊዜ የሚከተለዉ ጥያቄ ቀርቦላቸዉ ነበር፡-እረጅም እድሜ የታደሉት ነብይ ሆይ!!!!ይህን አለም እንዴት ተመለከቷት??
ኑህ (ዐ.ሰ)ለዚህ ጥያቄ መልስ ሲመልሱ ""ሁለት በሮች እንዳሉት ቤትና በአንዱ በር ገብቼ በሌላዉ በር የወጣሁ ያክል ሆና ነዉ ያገኘሆት .የሚል ምላሽ ሰጥተዋል
★★★ነብዩላህ ኑህ (ዐ.ሰ)ለራሳቸዉ በቀርቀሀ አነስተኛ ጎጆ ቀልሰዉ ነበር የሚኖሩት
ከዚህ የተሻለ ጠንካራ ቤት መስራት እየቻሉ..ለምን በዚህ ደካማ ጎጆ ዉስጥ ይኖራሉ ? ተብለዉ ሲጠየቁ
ነገ በሞት ይችን አለም ለሚለቅ ሰዉ ይህ ራሱ ሲበዛበት ነዉ ብለዋል፡፡
ዱንያ የዚህን ያህል ጭንቀት ደስታ ይፈራረቅብናል እንጂ የዚህን ያህል የሚጓጓላት ለሚኖር የሚናፈቅባት አይደለችም.. አላህ ልቦና ይስጠን!!!!!


አፓረንት ላይ ሁኜ ከካሊድ ጋር እናወራለን
...ሆስፒታሉ አንድ ቀን አዳር አንድ ቀን ደግም በቀን ነበር ተመድቤ የምሰራዉ፡፡
እዛ ስንሰራ አዳር እንቅልፍ እንዳይዘኝ ካሊድ ይደዉልልኛል አኩለ ለሊት እስኪያልፍ ስናወራ እናመሻለን ...ጉድ ነዉ ካርዱ ተገዝቶ መሆኑን እረስተን ከምንጭ ተጠልቆ የተሞላ ይመስል ትዝ አይለንም ፡፡


ካሊድ በሶስት ቀን ልዩነት ከጂማ ምግብና የሚጠጡ የተለያዩ ነገሮች ይዞልኝ ይመጣ እና በሩቁ ሰላም ናችሁ አብሽሩ ብሎን ይመለሳል፡፡ ካሊድ በስልክ ነዉ እንጂ ዘና ብሎ የማያወራኝ በአካል ስንገናኝ እንደተደገመት ሰዉ አፉ ይያያዛል ቶሎ ለመሄድ ነዉ የሚቸኩለዉ . ነዋል አብሽሪ አትፍሪኝ የምፈልጊዉ ከጂማ የሚመጣ ነገር ካለ ንገሪኝ ..እኔም እየመጣሁ አያችሇለሁ በሉ ቻዉ ብሎን ይሄዳል፡፡

ካሊድ እነዚህን ሶስት ወራት እየመጣ ገጠር ድረስ አይቶኝ አንዳንድ ነገር ይዞልኝ ይመጣል...በስልክም ማታ እንቅልፌ እንዳይመጣ እዛዉ ጤና ጣቢያ ሁኜ አሱ ጋር እያወራን እኩለ ለሊት ያልፋል፡፡፡

በዚህ ሶሰት ወራት አዲስ ነገር ተፈጥሯል ጓደኛችን ብሩክ ታይት በመፍቱሀ ምክር ደአዋ በፊትም ልቧ ወደ ኢስላም ያዘነበለ ነበር እስልምናን ተቀበለች በጣም ደስ አለን፡፡ እሷም ሙስሊም መሆኔን ለቤተሰቦቼ ሳልዉል ሳላድር ማሳወቅ አለብኝ አለችን..
ቆይ ተረጋጊ በሒደት ትነግሪያቸዋለሽ አሁን እስልምናን በደንብ እወቂ ብንላት
..ብሩክታይት ልንገራቸዉ እና ይለይልኝ ቤተሰቦቼ ከኢስላም ሀይማኖት አይበልጡብኝም ብላ እኛ ተረጋጊ ብንላት ልትሰማን አልቻለችም ... ለእናት እና ለአባቷ ስትደዉል...የገጠማት የማይታመን ነበር ሙስሊም ከሆንሽ እቤት እንዳትመጪ ብለዉ የወለደ አንጀታቸዉ ቆራጥ አመራር ገጠማት.እኛም ጭንቅ ጥብብ አለን ፡፡መፍቱሀም አትሰቢ እኔ ጋር ትኖሪያለሽ አብሽሪ አለቻት

★★★★ አላህ(ሱ.ወ) ለሰዎች መልካሙንና ክፉዉን ያሳያቸዉ ቢሆንም ያሻቸዉን እንዲመርጡ ነፃ አድርጎ ፈጥሮቸዋል። በምርጫቸዉ አይገባም።ሁሉም ሰዉ ያሻዉን የመምረጥ መብት እንዳለዉ ሁሉ የምርጫዉን ዉጤት የመቀበል ሀላፊነትም አለበት።
አላህ በተከበረ ቁዱስ ቁርአን እንዲህ ይላል፦
""ጌታህም በሻ ኖሮ በምድር ያሉትን ሰዎች ሁሉም የተሰበሰቡ ሁነዉ ባመኑ ነበር።ታድያ አንተ ሰዎችን አማኖች እንዲኾኑ ታስገድዳለህን?""(ዮኑስ፡99)
ከዚህ የቁርአን አንቀጽ እንደሚነግረን ማንኛዉንም ሰዉ በሀይማኖቱ ማስገደድ እንደሌለብን ነዉ ሁሉም የፍላጎቱን መከተል ይችላል።

በሌላኛዉ የቁርአን አንቀጽም እንዲህ ይላል
""እዉነትም ከጌታቹህ ነዉ።የሻም ሰዉ ይመን፤የሻም ሰዉ ይካድ።(አል-ካህፍ፡29)
ብትክዱ አላህ ከእናንተ የተብቃቃ ነዉ። ለባሪያዎችም ክህደትን አይወድም...(አዝ-ዙመር፡7)
ስለሆነም ሀይማኖት የነፃነት ምርጫ ነዉ እንጂ በማስገደድ ወደ ኢስላም ማምጣት ለራሱ ወንጀል ነዉ ለምን ፈጣሪ የፈለገ ሰዉ ይመን የፈለገ ሰዉ ይካድ እያለን ..እኛ የምናስገድድ ከሆነ የፈጣሪን ቃል መቃረን ስለሆነ፡፡

በጃህልያ ዘመን ልጆቻቸዉ በጠና የታመሙ እናቶች""ልጀ በሂወት ከቆየልኝ አይሁድ አደርገዋለሁ""እያሉ ይሳሉ ነበር።በዚህም ምክንያት የበኒ ነድር የአይሁድ ነገዶች ከነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ጋር የተጋቡትን ቃል በማፍረሳቸዉ ከመዲና ሲባረሩ ከእነሱ ዉስጥ በዚህ ስለት ምክንያት አይሁዳዊ የሆኑ ልጆች ነበሩ። የነዚህ ልጆች ሙስሊም ዘመዶች""ልጆቻችንን አንሰጥም""በሀይል እናስቀራቸዋለን ሙስሊምም እናደርጋቸዋለን ብለዉ ነበር።አላህ ግን፦"" በሀይማኖት ማስገደድ የለም"" የምትለዋን የቁርአን አንቀፅ አወረደ።

በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡"
(በቀራ 256) .ስለሆነም ወገን የአንተም የአንቺም የእሱም የእነሱም የእነዛም ሙስሊም ሰዎች ግዴታ ማድረስ ነዉ ከዛም ለእነሱ በሕሊናቸዉ እንዲያስቡ ማድረግ ብቻ ነዉ፡፡ ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም...
.
ተወዳጁ የአላህ ነብይ ሀቢቡና ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) በሐዲሳቸው እንዲህ ብለዋል"
#ሶስት_ሰዎች_ኢስልምናቸው_ተቀባይነት_የለውም" ብለዋል።
➊"ተገዶ የሰለመ
➋ለሚስት ብሎ የሰለመና
➌ለገንዘብ ብሎ የሰለመ።" ብለዉናል፡፡
ታዳ ስንትና ስንት ለሴት ብሎ የሰለመ ስንት አለች ለወንድ ብላ ሳታምንበት የሰለመች??ስንት አለ ለብር ብሎ የሰለመ?? ቤት ይቁጠረዉ ..ለሚስትም ለባልም ብለዉ የሰለሙትን ፈጣሪ ቀጥተኛዉን መንገድ ይምራቸዉ፡፡
እናም ማንም ሰው ኢስልምናን አልቀበልም ቢል ማስገደድ አይቻልም። አላህ በልቡ ላይ ኢማንን ያልፃፈለትን ሰው በግድ ተቀበል ብንለውም ሊቀበለን አይችልም።
ኢስላም በግድ የሚቀበሉት ሀይማኖት አይደለም። ስለሆነም የትኛዉም አይነት እምነቱን ሰዎች ላይ የመጫን/የማስገደድ አካሄድን አይቀበልም። በራሱ ላይም በሀይማኖቱ እንዲገደድ አይፈልግም። አላህ ቁዱስ ቁርአንን የመጠበቁ አንደኛዉ መገለጫም ይሄዉ ነዉ። ሰዎች ሀይማኖቱን በጭንቅላታቸዉ አመዛዝነዉ መቀበል የራሳቸዉ ፍላጎት ነዉ።
ሰዎችን እንደማግኔት የሚስበዉም አዉነተኛነቱ በምክንያታዊነት በአሳማኝ መረጃዎችን ማቅረብ በመቻሉ ነዉ፡፡ አንዳንድ የፀሀይ ጭራ የምታክል የዲነል ኢስላም እዉቀት ይዛችሁ የሌሎች ሀይማኖት ተከታዮችን በመሳደብ በማስገደድ ኢስላምን እንዲቀበሉ የምትደርጉ ከሆነ ፀቡ ከአላህ እና ከነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) መሆኑን አትዘንጉ፡፡

አፓረንታችንን 3ወር ያህል ጨርሼ ተወልጄ ወደ አደኩበት አባጅፋር ሀገር ጂማ ከተማ ተመለስኩኝ ፡፡ ብሩክታይትም መፍቱሀ ቤተሰቦች ጋር አብራ መኖር ጀመረች
ከተመለስኩ ጀምሬ ካሊድ ጋር በስልክ እያወራን ነዉ....ሀሙስ ቀን እንደዚህ አለኝ

ነዋል ነገ ከጓደኛሽ መፍቱሀ ጋር አብራችሁ መጥታችሁ ችብስ ትወጅ የለ እንዴ ልጋብዛችሁ አለኝ
...እንደዚህ ሲለኝ የዶክተር ሷሊህ ትዝታ አእምሮየ ላይ ብልጭ አለብኝ

#ክፍል 3⃣6⃣

ይቀጥላል....
. www.tg-me.com/Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
     
#ክፍል ☞ ሰላሳ ስድስት 3⃣6⃣

ፀሀፊ ☞
#አሚር_ሰይድ




 ነዋል ነገ ከጓደኛሽ መፍቱሀ ጋር አብራችሁ ለምን አንገናኝም ?<<<??? ችብስ ትወጅ የለ እንዴ ልጋብዛችሁ አለኝ.........እንደዚህ ሲለኝ የዛ የዶክተር ሷሊህ ትዝታ አእምሮየ ላይ ብልጭ አለብኝ....
እሺ መልሼ እደዉልልሀለሁ ብየ ስልኩን ዘጋሁት..

ካሊድ ችብስ ልጋብዝሽ ያለኝ ችብስ በጣም እንደምወድ ስለሚያቅ ነዉ፡፡ አፓረንት ገጠር በወጣንበት ጊዜ ለራሱ ሲመጣ ይዞልኝ ይመጣ ነበር
..... .....ደዉየ መፍቱሀን ሳማክራት ምን ችግር አለዉ የምንሄደዉ አብረን ነዉ  እንሄዳለን አለችኝ

መፍቱሀ ሁሌም ቢሆን ካሊድ ጋር እንድቀራረብ ጥረት ታደርጋለች...ለኔ ጥሩ ነገር ነዉ የምታስብልኝ ..ሁሌም ቢሆን ሚፍታህ ጋር በምናወራ ጊዜ መፍቱሀ እንዲህ ትለኛለች....#ሚፍታህ_የጀመረሽ_ትዳር_ፈልጎ_ሳይሆን_ጓደኛዉ_አንቺን_ዳረኝ_ስላለዉ_አንቺን_ለማግባት_እልክ_ይዞት_ነዉ፡፡ ብላኝ ነበር ፡፡ መፍቱሀ እዉነቷን ነዉ...ብዙ ጊዜ ሚፍታህ ጋር የነበረንን ግንኙነት አልወደደችዉም ግን በፍቅር መሀል ጣልቃ አልገባም ብላ ትታን ነዉ፡፡ በፊት ጀምራ ታያለሽ አንቺ የካሊድ ነሽ እሱ ነዉ ባልሽ  ፡፡ አንቺን የሚወድሽን የሚጠቅምሽን እኔ ነኝ የማቀዉ ትለኛለች.... እኔ ግን ካሊድ ጋር ትዳር የማይታሰብ ነዉ ፡፡ ግን ለኔ በዚህ ጭንቀቴ መፍቱሀን የመሰለች ጓደኛ ፈጣሪ ባይሰጠኝ ምን ይዉጠኝ ነበር???

★★★★ ጥሩ ጓደኛ መያዝ ጥቅሙ በጣም ብዙ ነዉ:: ጓደኛ ለናንተ ምን ማለት ነው? ከናንተ ጋር ውሎ ማምሸት?
እሱ ሚመራንን መንገድ ሁሉ መመራት? ወይስ እሱ ያረገውን ሁሉ በማድረግ እሱን መምሰል? ከእሱ ጥሩውን ወስዶ መጥፎውን ማረም ወይስ ባበጁህ ምትሄድ በነዱህ ምትነዳ ነህ?

ኢማሙ አልገዛሊ እንዲህ ብለዋል ጓደኛ 3 አይነት ነው።
➊ የአኼራ ወንድምህ ከዲን በስተቀር ሌላ ነገር አትጠብቅ
➋ የዱንያ ወድምህ ከመልካም ስነ ምግባር በስተቀር ሌላ ነገር አትጠብቅ
➌ለመዝናናት የምትይዘው ወድምህ ከተንኮልና ከክፋቱ ሰላም መሆንህን እንጂ ሌላ ነገር አትጠብቅ ፡፡

ወደ ጓደኛ ስትገባ አትቸኩል። ከገባህ ደግሞ ሳታመነታና ሳታቋርጥ ቀጥልበት። ጓደኛ የዛሬውን ሆነ የነገ ማንነትህን ለመቅረፅ ትልቅ ድርሻ እንዳለው አትዘጋ። አንተ አወከውም አላወቅከውም ውጤቱ ዛሬም ይምጣ ነገ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከጓደኞችህ መልካም ወይም መጥፎ ተፅዕኖ አታመልጥም።
ኢማሙ አልገዛሊ ስለ ጥሩ ጓደኛ እንዲህ ብለዋል #ሰዎች_ሶስት_አይነት_ናቸው፦ አንደኛው (አይነት ሰው) እንደ ምግብ ዘወትር የሚያስፈልግህ ነው። ሁለተኛው ( አይነት ሰው) እንደ መድሀኒት ነው በአስፈላጊዜ መጠን ብቻ የሚያስፈልግህ ነው። ሶስተኛው (አይነት ሰው) እንደ በሽታው ፈፅሞ የማያስፈልግህ ነው። ብለዋል .... እናንተ ለጓደኛቹ ከየትኛው ውስጥ ናቹ? ጓደኛችሁስ ከየትኛው ውስጥ ነው?

ጓደኛ ከጓደኛው ላይ የሚመለከተውን፤ የሚሰማውን፤ ባህሉን፤ አመለካከቱን፤ ንግግሩን ወ.ዘ.ተ በራሱ ላይ ሳያውቀው ያንፀባርቀዋል። ይህን ለማድረግ ምንም አይነት ጥረትና ዝግጅት እንኳን አያስፈልገውም። በአካል ወይም በህሊና የዘወትር አብሮነት ብቻ በቂ ነው። በዛሬው ማንነትህ ላይ የሚታየው አውታዊውም ይሁን አሉታዊ ስሜትህ ሀሳብህና እንቅስቃሴህ የቅርብ ጓደኞችህ የቤተሰቦችህ እንዲሁም በአካል አብርሀቸው ባትችልም የምትወዳቸውንና የምታደንቃቸው ሰዎች ተፅዕኖ ነፀብራቅ ነህ። ተሳሳትኩ?

ክብርህንና መልካም ስኬትህን የምትፈልገው ከሆነ ካንተ የተሻለ አላማና ሥነ ምግባር ከሌላቸው ሰዎች ጋር የልብ ወዳጅነት አትፍጠር። ካልተሳካልህ ከመጥፎ ጓደኛ ብቸኝነት እንደሚሻል እወቅ። ጓደኞችህ ማግኘት በሚገባህ እውቀት ላይ በመጠኑ በአይነቱና በጥራቱ ልይም ቢሆን ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተረዳ። ወይ ለውጤት ለክስረት ያበቁሀል። በተለይም በግለ ባህሪህ በሳቡህ ቦታ የምትሳብ፤ በጎተቱህ አቅጣጫ የምትጎተት ተፅዕኖ ተቀባይ ሰው ከሆንክ ጥሩ ጓደኛ ቢያገኝህ የምትጠቅምህን ያህል መጥፎም ጓደኛ ከአገኘህ ይበድልሀል።

እነሆ የአንተም የአንቺም የእሱም የእሷም የሆነዉ የፈጣሪ ቃል በቅዱስ ቁርአን የመጥፎ ጓደኝነትን አደጋ ሲናገር እንዲህ ይላል፦
"በዳይም፦ <<ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በኾነ ዋ ምኞቴ!>> እያለ በፀፀት ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን አስታውስ።
<<ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ናሮ እመኛለው፤ የእምነት ቃልን ከመጣልኝ በኃላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ፤>> (ይላል)፤" (አል-ፋርቃን:27-29) እናም ሞት መጥቶ አላህ ፊት ስንቀርብ በጓደኞቻችን ከምንፀፀት ዛሬዉኑ ምርጫ አለን አስተዉለን የሚጠቅሙንን አጥብቀን ይዘን የማይጠቅም የማይጎዳን ብናስወግድ የተሻለ ብቸኛ አማራጭ ነዉ ፡፡

የሰው ልጅ ያየውንና የሰማውን በቀላሉ አምኖ ይቀበላል፤ ተግባሩን ይከተላል ፤ የሚያልመውን ያልማል፤ የሚመኘውን ይመኛል፤ የሚሆነውን ይሆናል፤ የሚጠላውን ይጠላል፤ የሚወደውን ይወዳል። ጥሩ ጓደኛ ከገጠመው እድለኛ ይሆናል። ክፉ ከገጠመው ቡሀላ ነገሮች ከአለቁ ቡሀላ በፀፀት ይቃጠላል። ዳሩ ግን ፀፀት ቅንጣት ውጤት አያመጣም። ስንቶቻችን ያልሆነ ጓደኛ ይዘን ተፀፅተን ይሆን??? ወይስ አሁንም እየቀጠልን ይሆን?

የሰዎች ተፅዕኖ በኛ ላይ ያለው የመወሰን ድርሻ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ የአካባቢያችን ሰዎች አልፎ አልፎም ቢሆንም ዘመዶቻችንና ቤተሰቦቻችንም ሳይቀሩ በእኛ ማንነት ላይ በአሉታዊ መልኩ ተዋናይ መሆን ሲፈልጉ ተጨማሪ ጥንቃቄ ማድረግና ፍቃድ ሊነፈጉ ይገባቸዋል።

ተወዳጁ የአላህ መልዕክተኛ ሀቢቡና ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ በአንድ ሰው ማንነት ክስረትና ውድቀትን ወይም መልካም ውጤትና ስኬትን የመወሰን አቅም ካላቸው ነገሮች ውስጥ ጓደኞቻችን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ሲገልፁ እንዲህ ብለዋል፦
<<አንድ ሰው በጓደኛው ዲን ላይ ነው። ስለሆነም አንዳችሁ ከማን መወዳጀት እንዳለበት ያስተውል>> ብለዉናል፡፡

መልካም ጓደኛ መልካም ጥላዉን ይጥልብሀል። አወከውም አላወቅከውም በዱንያ ላይ ይብዛም ይነስም ይጠቅምሀል። ክፋ ጓደኛ ሳትፈልግ በግድህ በዱንያህ ወይም በአኼራህ አለበለዚያ በሁለቱም ላይ አንተ ብታውቅም ባታውቅም ጉዳቱ ቢሰማህም ባይሰማህም ይጎድሀል። ከሁለት አንዱን እንድትሆን የሚያበቃህ ጉዳይ ደግሞ የራስህ ምርጫ ነው። ማንም ሰው ባንተ ላይ ተወቃሽ ሊሆን አይችልም። አንተ ልትበላሽ የምችለው በጓደኛህ፣ በማህበረሰብ፣ በቤተሰብ ነዉ፡፡ ማነው ተወቃሽ ጓደኛ?፣ ማህበረሰቡ?፣ ቤተሰብ ወይስ ራሱ ግለሰብ?
ደርሶ በራስ ችግር የአርባ ቀን እድሌ ነዉ እያሉ ከመቆዘምና ፈጣሪ ጋል ከመጣላት ዛሬዉና ጓደኛችንን እንምረጥ ካልሆነ ግን ይዞን ገደል መሆኑን አንዘንጋ፡፡


ካሊድ ደዉሎ ግብዣየን ተቀበልሽኝ ወይስ አልተቀበልሽኝም?? አለኝ
.....እኔም እሺ ተቀብያለሁ አልኩት
.....ካሊድ በጣም ደስ አለዉ

የማይደርስ የለም የሀሙስ ለሊት ለጁምአ ቀን አስረከበች ከዛም ከኡስር ቡሀላ ካሊድ መኪናዉን ይዞ እኔ እና መፍቱሀን ይዞን ሊጋብዘን ጉዞ ጀመርን....እየሄድን ማንም የሌለበት ሰዉ የማይበዛበት ቦታ ዉስጄ ልጋብዛችሁ አለኝ
.....እኛም እሺ አልነዉ

ከዛም እልም ያለ ገጠር ዉስጥ ዛፍ አዋፋት የበዛበት ማንም ሰዉ የሌለበት ቦታ ወሰደን፡፡ ከመኪናዉ ወረድን ተቀመጥን ....ያለነዉ ሶስታችን ነን ወሬ ማዉራቱን ተያያዝነዉ...👇👇👇
በወሬያችን መሀል ካሊድ እንደዚህ አለን፡......መፍቱሀ...እኔን ነዋል ብዙ ነገር በድላኛለች ..እሷ የበደለችኝን ነገር እሷ ባለችበት ለአንቺ ልንገርሽ እና ቅጣት እንድትቀጣልኝ እፈልጋለሁ አለ....
መፍቱሀም እሺ ተናገር አለችዉ
.....እኔም ካሊድ አንተን በድየህ አስቀይሜህ አቃለሁ እንዴ ???አልኩት
..... አዎ ብዙ በድለሽኛል ነዋል አለኝ
....,ምን ምን በድየሀለሁ ?? አልኩት

እሱም እንደዚህ አለኝ>>>>>>በሒወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ለትዳር ስጠይቅሽ አልፈልግህም አንተን ማግባት አልፈልግም ስትይኝ ለሁለት ወር ያህል አሞኝ ስራ መስራት አልቻልኩም ነበር አለኝ<<<<<<
.....እኔም መታመምህን   በምን አቃለሁ??? አልኩት

ካሊድም ቀጠለ ....እሺ ሌላኛዉ ደግሞ ስደዉል ብዙ ጊዜ ስልክ አታነሺም፡፡ አንስተሽም ቡሀላ እደዉላለሁ ነበር የምትይኝ ..ስፈልጊ ስልኬን block ታረጊኝ ነበር..text ስልክልሽ አመልሽም ... መንገድ ላይም ፊት ትነሺኝ ነበር ...እያለ በደሉን በአንዴ ዘረገፈዉ ኮሌጅ መማር ከጀመርኩ  ጀምሮ የሶስቱንም አመቱን ብሶቱን አንድ ባንድ ነገረኝ ...
ከዛም አንቺስ ይሄን አድርገህኛል ይሄ ጥፋት አለብህ የምትይኝ አለ ?<?<? ንገሪኝ አለኝ
.....,እኔም የምለዉ የምመልሰዉ ሳጣ ምንም አላረከኝም ላለማለት አንድ ቀን callme back ልኬልህ እንድደዉልልኝ ፈልጌ አልመለስክልኝም አልኩት
......እሱም ሳቀ

መፍቱሀም ጥፋተኛ እሷ ናት ምን እንድትቀጣ ነዉ የምፈልገዉ ??? አለችዉ
ካሊድም >>>እኔ ልቤን ሰጥቻት ልቤን ጣለችብኝ ልቤን ከጣለችበት አንስታ ትስጠኝ<<<አለ

በጣምምም ደነገጥኩ ካሊድ እንደዚህ ይላል ብየ አስቤም ትዝም ብሎኝ አያዉቅም
.....እኔም እንዳልገባኝ ለማስመሰል ምን ለማለት ፈልገህ ነዉ ??አልኩት
...መፍቱሀ ሰምተሻል በአንቺ ቤት ማደናቆርሽ ነዉ??.. ልቤን ሰጥቻት ጥለዋለች ብሏል ከጣልሽበት ሂደሽ ፈልገሽ አምጪ አለችኝ

....እኔም ወደ ካሊድ ዙሬ ምን ለማለት ፈልገህ ነዉ?? ንገረኝ ዙሪያ ጥምጥም አትሂድ እያልኩ ፍጥጥ አርጌ ያዝኩት
.....ካሊድም ነዋል ዛሬ ተረጂኝ እባክሽ ከልቤ እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ ፍቃደኛ ከሆንሽ ላገባሽ እፈልጋለሁ  ልትመረቂ ሁለት ወር ነዉ የቀረሽ...,ታስታዉሽ እንደሇነ ገና ኮሌጅ ሳትመዘገቢ ላግባሸ ስልሽ አሁን መማር እፈልጋለሁ ነዉ ያልሽኝ...አሁን ትምህርት ጨሬሰሻል የቀረሽ የምረቃን proces ብቻ ነዉ
.....ስለዚህ ላገባሽ እፈልጋለሁ እና ፍቅሬን ተቀበይኝ ...በዚህ ሁለት ወር ዉስጥ እንግባባ ስለ እኔ ማጣራት የምፈልገዉ ነገር ካለ ከማንኛዉም ሰዉ ማጣራት ትችያለሽ ..,እኔ ግን ስለአንቺ ምንም የማጣራዉ የምጠይቀዉም የለም ዛሬም ነገም ብትይኝ አንቺን ለማግባት ዝግጁ ነኝ..,አለኝ......

#ክፍል 3⃣7⃣
ይ ...........ቀ........
.......,ጥ...........ላ..............ል


JOIN

´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
•════•••🍃🌺🍃•••════•
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
     
#ክፍል ☞ ሰላሳ ሰባት 3⃣7⃣

ፀሀፊ ☞
#አሚር_ሰይድ


እኔ ግን ስለአንቺ ምንም የማጣራዉ የምጠይቀዉም የለም ዛሬም ነገም ብትይኝ አንቺን ለማግባት ዝግጁ ነኝ..,አለኝ......

....እኔም ከአነጋገሩ እምቢ የምልበት ድፍረት አጣሁኝ.... አስቤበት ይሁን በድንጋጤ አላወኩትም ከአፌ ግን እሺ የምትል ሁለት ቃላት ተነፈስኩኝ

ካሊድ በጣም ደስ አለዉ የዛን ጊዜ የተደሰተዉ ደስታ በቃላት መግለፅ አልችልም ቁጭ ብድግ ነዉ እያለ የሚያወራዉ ጠፍቶታል፡፡ የሚያወራዉ ሲያጣ በቃ የዛሬ ሳምንት ጁምአ ምሳ ሰአት እንገናኛለን አለኝ
.....እኔም ኢንሻ አላህ አልኩት
ወደ ጂማ ከተማዉ ሳይመሽ ተመለስን...እቤቴ ድረስ በመኪና ሸኝቶኝ ተመለሰ፡፡

★★★★#ትዳር የሚያስብ ሰዉ ከወዲሁ ኒያዉን መሬት ማስያዝና ማስተካከል አለበት፡፡ ገና ወደ ትዳሩ ከመግባቱ በፊት ኒያው ማማር አለበት፡፡ በኒያው ዘላቂ ትዳርን አስቦ የገባ ይዘልቅለታል፡፡ ሀሳቡ ጊዜያዊ የሆነው ደግሞ መንገድ ላይ ይቀራል፡፡ አላህ የሰዎችን ሀሳብ አይሰርቅባቸዉም፡፡ አልመው የተነሱትን አይቆርጥባቸዉም፡፡ መውደቅ የፈለገ በመጥፎ ሀሳቡ ምክንያት ይወድቃል፡፡ ገብቼ ልውጣ ያለዉም ገብቶ አይቶ ይወጣል፡፡ አንድ እግሩን እዉጭ አኑሮ በአንድ እግሩ የገባም እንደ ሀሳቡ ያገኛል፡፡ ምክንያቱም አላህ (ሱ.ወ.) ለያንዳንዱ የሰው ልጅ እንደየሀሳቡ ይሰጣል፡፡ አላህ ለሰዎች እንደምርጫቸው ይሰጣቸዋል፡፡

ትዳር ሐላል አክሲዮን ነው፡፡ አክሲዮኑ በሁለት ተፈቃቃጅ በሆኑ ወንድ እና ሴት መካከል የሚመሰረት ግንኙነት ነዉና እንደዋዛ መታየት የለበትም፡፡ እንደዋዛ ከታየ እንደዋዛ ይፈርሳል፡፡ ትዳር መልካምነቱን አስበው፣ ወደዉና ፈቅደው በሙሉ ሀሳብ የሚጠቃለሉበት እንጂ በግማሽ ልብ የሚገቡበት ቤት አይደለም፡፡

ትዳር ከሐራም ኑሮ ወደ ሐላል ግቢ ሽሽት ነው፡፡ ከጉድለት ሕይወት ወደ ሙሉነት ቤት ሩጫ ነው፡፡ ጠፍቶ የቆየን ግራ ጎን ማሟያ ፍለጋ ፅድቅ ስደት ነው፡፡

ትዳር የንፅህና ሻወር ነው፡፡ ሲንከራተት ለኖረ ዐይን ማረፊያ ነው፡፡ ሲባዝን ለኖረ ልብ ማስከኛ ነው፡፡ ፍላጎትን ሐላል እና ነፍስ በምትወደው መልኩ ለማሳካት ምክንያት ነው፡፡

#ትዳር ባልና ሚስት ተፈጥሯዊ ስሜታቸዉን ሐላል እና አላህ በፈቀደው መልኩ የሚያረኩበት ጥምረት ነው፡፡ ለዚህ ጥምረት ዘላቂነትና ስኬት ከወዲሁ ሀሳብን ማስተካከል ግድ ይላል፡፡ “ #ከሞቀኝ_እቀጥላለሁ_ከበረደኝ_እወጣለሁ” በሚል ስሜት የተገባበት ቤት የመፍረስ ዕድሉ ከፍ ያለ ነው፡፡ ከሙቀቱ ይልቅ ብርዱ ሊበዛ ይችላልና፡፡ ሀብት ንብረት ለመካፈል ብለው የሚገቡበት ጥምረት ዕድሜው አጭር ነው፡፡ ሀብት ንብረቱ አልገኝ ሲል ያነጫንጫልና፡፡ “አለው” ብለው የተቀበሉት ኪዳን አይዘልቅም፡፡ ያጡ ቀን ባህሪን ያባላሻልና፡፡

ወደ ትዳርም ሆነ ወደማንኛዉም መልካም ነገር ስንገባ ንያችንን ማሳመሩ ግድ ነው፡፡ በበጎ ነገር ዉስጥ ሁሉ የአላህን ዉዴታ እናስብ፡፡ መልካም ነገሮችን ስንጀምር እሱን አስበን እንጀምር፡፡ በስራዎቻችን ዉስጥ ሁሉ አላህ ከጎናችን ስለመኖሩ እርግጠኛ እንሁን፡፡ በሁለመናችን ዉስጥ አላህን እናስገባ፡፡ በዕውቀታችን፣ በብልሀታችንና ብልጠታችን ከመተማመን ይልቅ ነገሮችን እሱ እንዲሰራልን እንፍቀድ፡፡ ምክንያቱም ነገሮች እኛ ስንሰራቸውና አላህ ሲሰራቸው የተለያዩ ናቸውና፡፡ የቱን ያህል ዕውቀትና ብልሀት ቢኖረንም ስራችን በአላህ ድጋፍ ካልታገዘ ከንቱ ነው፡፡ እሱ ከሌለበት የትኛዉም እንቅስቃሴያችን እንከኑ ብዙ ነው፡፡ ጉድለቱ የትየሌሌ ነው፡፡

ማንኛዉንም መልካም ነገር ስንጀምር በአላህ ስም ብለን እንጀምር፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) ከሌለበት አንድን ነገር እንስራ ብለን ብቻችንን ብንነሳ የሚበላሸው ይበዛል፡፡ የሚጠፋው ይበረክታል፡፡

ትዳር በሕይወት በምድር ላይ እስካሉ ድረስ ባልና ሚስት የሚኖሩበት ህንፃ ነው፡፡ በዚህ ህንፃ ግንባታ ላይ የአላህ እጅ እንዲኖርበት መፍቀድ ብልህነት ነው፡፡ ብቻችንን የምንሰራው ቤት ቤት አይሆንም፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) የሌለበት ቤት መሰረቱ ደካማ ነው፤ ጣሪያውም ያፈሳል፣ ግድግዳው በቀላሉ ይዘማል፣ ምሰሶው ያረገርጋል፣ ሁለመናው ስጢጥ ስጢጥ ይላል፡፡

ትዳርን ስናስብ ቁሳዊም ሆነ መንፈሳዊ ሰበቡን እናሟላ፡፡ አላህን በቤታችን ስናኖረው ያኔ የቤታችን መሰረት ፅኑ ይሆናል፣ ምሰሶው መሬት ይይዛል፣ ግድግዳው ቀጥ ይላል፡፡
ለአላህ ብለው ያሰቡት ነገር የሱ ጥበቃ አለበት፡፡ አላህ የሰራው ቤት አይፈርስም፣ እሱ ያነጸው ህንፃ አይዘምም፡፡ በዚህች ምድር ላይ የማያልፍ የለምና ላያልፍም የመጣ ነገር የለምና ሰራችን ባያምር እንኳን ሀሳባችን አምሮ እንለፍ፡፡ ስለ አላህ እንኑር፡፡ ስለ አላህ እናድርግ፡፡ አላህን ከፊታችን እናድርገው፡፡ ትዳር
ወሳኝ ነገር ነዉና ቤታችንን በበረከትና በፍቅር ይሞላልን ዘንድ እሱን እናስቀድመው፡፡ ዋናዉና መቅደም ያለበት እሱ ነዉና የሚቀድመውን በማስቀደም የሚከተለውን እናስከትል፡፡ አላህ ሆይ ለተጋቡትም ፍቅር ደስታን ዲነል ኢስላምን የሚያስጠራ ልጅ ስጣቸዉ...ላላገባነዉም ከሸይጧንም ከሰዉም ዉስወሳ ወንጀል ጠብቀህ የዱአችን ዉጤት የሆነዉን ትዳር ስጠን...ዱአችንን እንደዚገይ አታድርገዉ ያረብ.... አሚን...


እቤቴ ከገባሁ ቡሀላ እንደገና የረሳሁትን ማሰብ የማልፈልገዉ የአእምሮ ጥያቄ እየመጣ ያቃጭልብኝ ይዟል... መጨነቅ መጠበብ ሆነ ካሊድ ድንግል ነሽ ወይስ አይደለሽም ?? ብሎ ቢጠይቀኝ ምንድን ነዉ መልሴ??...እንዴትስ ነዉ የማስረዳዉ ???እያልኩ ስጨናነቅ እንቅልፍ በአይኔ ሳላይ አደርኩኝ.....

የማይነጋ ለሊት የለም ጨለማ ለፀሀይ ቦታዋን አስረከበች ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ ዘንድሮ ተመራቂ ስለሆንኩ coc እንዳልወድቅ ዝግጅት እያረኩ ነዉ.... ግን ካሊድ ይደዉልልኛል፡፡ በነዚህ ቀናት ዉስጥ በቀን ዉሰጥ በትንሹ ደወለ ከተባለ ቢያንስ 5 ጊዜ ሳይደዉል ቀርቶ አያቅም ፡፡
......እኔ ካሊድ ጋር ስናወራ ከበፊቱ ጀምሬ የምፈራዉ በማንነቴ ነዉ ..ሁሌም ሀሳቤ በዚህ ማንነቴ መጣላታችን አይቀርም እያልኩ አስባለሁ ፡፡ እንዴት እኔን ሊረዳኝ ይችላል??

ካሊድን እሺ ካልኩ ቡሀላ እንደ በፊቱ መጨናነቅ ይዣለሁ ...ካሊድን እንዴት ልራቅ??? ማንነቴን ላይቀበለኝ ይችላል እያልኩ ሳስብ ጨጓራ አለብኝ በጣም አመመኝ በሁለት ቀን ልዩነት ሀኪም ቤት እስከ መሄድ ደርሻለሁ.... ካሊድም ምን ሁነሽ ነዉ ያመመሽ ??ተሻለሽ ወይ ??እያለ በየሰአቱ ነበር የሚደዉለዉ....መልስ የሌለዉ ጥያቄ እንዴት ልመልስ በሆዴ ታምቆ ተቀምጧል...ካሊድ ቀላል ህመም ነዉ ይሻለኛል ብየ እመልስለታለሁ ......
ለዉጥ ሲኖረኝ ወደ ክላስ ሂጄ ለCoc ዝግጅት አደርጋለሁ፡፡

እንደዚህ እያለ ሳምንቱ አልፎ ጁምአ ደረሰ ... ካሊድ የጠራኝን ምሳ እረስቸዋለሁ ትምህርት አልገባሁም.. ጁምአ ለመስገድ ቀደም ብየ አጅፕ መስጊድ ገብቼ ቁርአን እየቀራሁ ቀራሁ....ከዛም ጁምአ ተሰግዶ እንደጨረስን ....መፍቱሀ እኔም በተጨማሪ ሌሎች ሶስት ጓደኞቼ ጁምአ ጁምአ ምሳ የምንበላዉ አንድ ላይ ነዉ፡፡ በየተራ ሁላችንም እቤት እያዘጋጀን ዛሬ አንዷ ቤት ሳምንት ሌላ የጓደኛችን ቤት የእኔ ተራ ሲሆን እኛ ቤት እያልን ጁምአን ምሳ እንደዚህ ነዉ የምናሳልፈዉ...

ከዛም እኔ የካሊድን ቀጥሮ ረስቼ  መፍቱሀ ቤት ሆድኩ ፡፡ የሄድኩበትም ምክንያት የጁምአ ምሳ ተረኛ የሆነችዉ ጓደኛችን ቤት አብረን ለመሄድ ነዉ፡፡👇👇👇
2024/09/23 22:21:51
Back to Top
HTML Embed Code: