Telegram Web Link
ISLAMIC SCHOOL pinned «  እዉነተኛ ታሪክ 😔 #የሕይወት_ምስቅልቅል       #የመጨረሻዉ_ክፍል ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ ሰብልየ.... ከሁለት ወር ቡሀላ የሰብለ አባት እና አጎቴ ከደሴ ከተማ ቀመርያ የምትባል ልጅ የሽማግሌ ልጅ አስተዋወቁኝ፡፡ አጎቴ ጋር እና የሰብለ አባት ጋር ሂጄ ልጅቱ ጋር በአካል አገናኙን ሁለታችንም ተስማማን ..ከዛም በሳምንቱ ሽማግሌ ተልኮ አጨሁ የሰርጉ ቀኑም ቆርጠዉ መጡ ፡፡ የሰብለ እናት…»
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞አስራ ሰባት ➊➐



እሷም ደንግጣ አሁን ቢመጡ ምን ልትላቸዉ ነዉ?... አላህ ልጂ ሊሰጠኝ ነዉ እላለሁ። እሽ እማ ላይ ደወልክ?.... ወይኔ ጉዴ ለብዙ ጊዜ እማ ነበረች ይህንን ቀን በጉጉት የምትጠብቀዉ ቆይ ልደዉልላት.... ብየ ልደዉል ስል ዶክተሮች የምን ጩኸት ነዉ የሰማነዉ? በሰላም ነዉ ብለዉ መጡ። እኔም ኧረ በሰላም ነዉ ሚስቴ እርጉዝ መሆንዋን ሰምቸ የደስታ ብዛት ነዉ ያስጨኸኝ። ነዉ እንዴ!.. ፍቅራቹህ ደስ ይላል ብለዉ እየሳቁ ሄድ እኛም በንግግራቸዉ ተሰሳቅን አልሀምዱሊላህ ያየን ሁሉ ሰዉ ፍቅራቹህ ደስ ይላል ይሉናል። ዶክተሮች ብቻ ሳይሆኑ የሰፈር ሰዎችም ጭምር.... አሁን እማን ልንገራት ብየ ደወልኩ እሷም.....


ልጀ እንዴት ናቹህ? ወላሂ ለብዙ ጊዜ ኡስታዝ በመሞታቸዉ አዝኛለሁ ግን አላህ የቀደረዉ ሁኗል... አወ እማ አላህ የቀደረዉ ሁኖል አሁን ግን ደስ የሚል ነገር ልነግርሽ ነዉ ምንድን ነዉ ልጀ? ሁል ጊዜ ለምን አትወልድም የምትይን አሁን ሊሳካልሽ ነዉ ዱአ አድርጊ...... ምን እያልከኝ ነዉ ልጀ መርየም እርጉዝ ናት። ይሄን ስነግራት የእማ ደስታ እንዴት እንደምገልፀዉ አላቅም እማ በቃ በሌላ ጊዜ እደዉልልሻለሁ።አሁን ሀኪም ቤት ስለሆንኩኝ ነዉ። በሰላም ነዉ ልጀ? አወ በሰላም ነዉ ትንሽ መርየምን አሟት ነበር ስትመረመር እርጉዝ ነሽ ተባለች። ቻዉ በይ ብየ ስልኩን ዘጋሁት.... ወዲያዉ ዶክተሩ መጦ ይዘሀት መሄድ ትችላለህ። ፅንሱም ቢሆን በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል አለኝ......


እኔም መርየምን ይዜ ወደ ቤት ተመለስኩ። እቤት ስደርስ ግን ያየሁትን ማመን አቃተኝ ደነገጥኩ መርየምም ግራ ተጋብታ ምንድን እያረጋቹህ ነዉ ብላ የኡስታዝን ልጆች ትጠይቅ ጀመር... ማንም መልስ የሚሰጣት የለም እኔም ግራ ገባኝ ወፍጫ ቤቱን የሚገዛ ሰዉየ ነዉ መሰል... እንዲህ አያዋጣኝም እሽ ትንሽ ጨምር እየተበባሉ ይጨቃጨቃሉ..... አንደኛዉ የኡስታዝ ልጂ ደግሞ እኛ የነበርንበትን ክፍል እንዳለ እቃዉን ያወጣል እኔም ምን እያረጋቹህ ነዉ አልኩት?...


በገዛ ቤቴ አንተ ምን አገባህ የፈለኩትን ማረግ መብቴ ነዉ! የመርየም እናትም ከአዲስ አበባ ለልቅሷዉ መጣ ነበርና ልጀ ቤቱን ካልሸጥነዉ ብለዉ እያስማሙት ነዉ ምን ቤቱ ብቻ.... መፍጫ ቤቱንም ሊሸጡት ነዉ እኔም ግራ ገባኝ ደነገጥኩ መርየምንም ዙሬ አየኋት.......

እንባዋ ይፈሳል.... መርየም በአላህ እንደዚህ አትሁኝ በቃ ተያቸዉ ዱንያ እንደሆነች እንደዚህ ናት ብየ እንባ ተናነቀኝ..... እኛም ያወጡትን እቃችንን ጠቅልለን ወደ እማ ቤት አመራን ምሽት ላይ ነበር የደረስን እማ ምን ሁናቹህ ነዉ ብላ ደነገጠች። ምንም አልሆንም እማ ድሮዉንምኮ ቢሆን ኡስታዝን ብለን እንጂ እዛ መኖር ፈልገን አይደለም ደሞ ናፈቃቹህን ብየ እዉነቱን መናገር አልፈለኩም። እኔምኮ እዛ መኖራቹህን አልወደድኩትም ነበር እንኳን ደህና መጣቹህ ኑ ግቡ ብላ ይዛን ገባች።..


እህቴም በመምጣታችን በጣም ደስ ብሏታል። ደሞ መርየም እርጉዝ ናት አለችኝ እማ አንተማ መቸም አትነግረኝ ግን ማሻ አላህ ... እህ ለእማ ነገርኳት ማለት ለአንችስ ነገርኩሽ ማለት አይደል እህቴ ኧረ እየቀለድኩ ነዉ ወንድሜ... ነዉ እንዴ! ብለን ስንሰሳቅ መርየም እስካሁን ድረስ እንዳዘነች ናት። መርየም እህቴ ምን ሁነሽ ነዉ እንደዚህ ያዘንሽ ብላ ሀያት ጠየቀቻት.... አይ እህቴ አላዘነችም ያደገችበትን ቤት ትታ ስለ መጣች ትንሽ ቅር ብሏት ነዉ እህ... ነዉ እንዴ አሁን ሁሉንም እርሽዉና እስኪ የምትወልጂዉ ወንድ ነዉ ወይስ ሴት እስኪ እንገምት ሁላቹህም ተሳተፉ መጀመሪያ መርየም ገምች እያለች ወሬ ጀመረች መርየምን ለማጫወት ይመስላል.....


መርየምም ወላሂ እህቴ አላህ የሰጠኝን በደስታ እቀበላለሁ ብላ ፈገግ አለች። በቃ እሽ ወንድሜ ገምት..... እኔም ሁለቱንም በደስታ እቀበላለሁ እንዴ ምርጫ ነዉ ሁለቱንም የሚባል መልስ የለም በቃ እሽ የኔን ልንገራቹህ ሴት ብትሆን ልክ እንደናቷ ደስ ይለኛል። ወንድም ቢሆን ልክ እንደ ወንድሜ ደስ ይለኛል ሀሀ...... እንዴ! እህቴ ሁለቱም የሚባል መልስ የለም ብለን ሁላችንም ሳቅንባት። እማየም አይ ሀያቴ በይ አሁን እራት አቅርቢላቸዉ እና መኝታቸዉንም አዘጋጂላቸዉ ከምንገድ ስለመጡ ይደክማቸዋል ጨዋታዉ ነገ ይደርሳል...


እህቴም ምግብ አቅርባልን በልተን ስንስቅ አምሽተን ነጋ እኔም በጥዋት ስራ ፍለጋ ወጣሁ ስፈልግ ስፈልግ..... ምንም ስራ ማግኘት አልቻለኩም እንዲህ በፍለጋ ብዙ ወራትን አሳለፍኩ መርየምም ስምንተኞ ወሯ ደርሳል ልትወልድ አንድ ወር ቀራት ። እኔም እስከዛሬ ድረስ ስራ እየፈለኩ ነዉ። በስተመጨረሻ ግን ስራ አግኘሁ አንድ ሱቅ ተቀጥሬ መስራት ከጀመርኩ አንድ ወር ሆነኝ መርየምም ዘጠነኛ ወሯ ስለገባ ሰሞኑን ትወልዳለች ብለን እየተጠባበቅን ነዉ....


በአላህ ፍቃድ
ክፍል1⃣8⃣
.................ይ
....................ቀ
......................ጥ
..........................ላ
..............................ል

join👇👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ አስራ ስምንት ➊➑




መርየምም ዘጠነኛ ወሯ ስለገባ ሰሞኙን ትወልዳለች ብለን እየተጠባበቅን ነዉ። ሰኞ ከምሽቱ ዘጠኝ ሰአት መርየም አመመኝ ብላ ቀሰቀሰችኝ። እኔም ደንግጨ ተነሳሁ እነማየንም ቀስቅሼ ወደ ሆስፒታል ይዘናት ሄድን አዳሪ ዶክተሮችም ነበሩ ወደ ዉስጥ ይዘዋት ገብ እኔ ጩኸቷን ላለመስማት ጀሮየን ጠቅጥቄ ያዝኩት። አላስችለኝ ብሎም ስለቀዉ አሁንም ዩሱፍ ዩሱፍ እያለች ትጮሀለች። ያረቢ ወዴት ልሂድ ጨነቀኝ እማም ከዛ እዛ ትመላለሳለች እህቴም ጨንቋታል....


ስአታት ተቆጠሩ መርየምም አልወጣችም። ያረብ እያልኩ እጀን ወደ ላይ አንስቸ ማልቀስ ጀመርኩ። ከትንሽ ደቂቃዎች ቡኋላ የሚያለቅስ የጨቅላ ህፃን ድምፅ ሰማን። ሁላችን ትኩረታችን ድምፅ ወደ ሰማንበት ክፍል ሆነ። እሩጠንም የክፍሉን መከፈት በጉጉት መጠባበቅ ጀመርን ትንሽ እንደ ጠበቅንም በሩ ተከፈተ ዳክተሩ ወጣ... እኛም ዳክተር እንዴት ናት መርየም አልነዉ። መርየም ደህና ናት...


ልጀስ... ልጂህ ደህና ናት... እንኳን ደስ አለህ። አልሀምዱሊላህ ዳክተር እሽ አሁን ወደ መርየም ክፍል መግባት እንችላለን? አወ.... ገብታቹህ ማየት ትችላላቹህ አለን። እኛም እሽ ብለን በፍጥነት ገባን እናቴም ልክ መርየምን አንዳየቻት አልሀምዱሊላህ አልሀምዱሊላህ.... እያለች በደስታ ልጀ ብላ ጠጋ አለች። እኔና እህቴም መርየም ደህና ነሽ እያልን አጇን ይዘን አጠገቧ ተቀመጥን። እኔኳ ደህና ነኝ አለች። ግን ድምጿ ደከም ብሏል ልጀን አያቹህልኝ እያለች አጠገቧ ያለዉን ትንሽየ አልጋ ጠቆመችም። ሁላችንም ወደ ተወለደዉ ህፃን ዟርን ማሻአላህ ሴት ናት። በጣም ደስ አለን...


ወደ ስድስት ሰአትም እቤታችን መሄን እንደምንችል ዶክተሩ ነገረን እኛም መርየምንና ልጀን ይዘን ወደ ቤት ተመለስን። ሁሉም ጎረቢቶች እንኳን ደስ ያላቹህ እያሉ መጡ እኔም የደስታየ ብዛት...... ሁሉንም ሚዜዎቸ የነበሩትን የሴት ልጂ አባት ሆንኩ እያልኩ ደወልኩላቸዉ። እንኳን ደስ ያለህ አሉኝ ሙሀሜ ማለትም የመጀመሪያ ሚዜየ ላይ ስደዉል ስዑዲ እንደሄደ ነገረኝ እኔም ሴት ልጂ አላህ እንደሰጠን ነገርኩት። ማሻአላህ አለኝ..... አንተንም አላህ በሰላም ለሀገርህ ያብቃህ ተበብለን ስልኩን ዘጋነዉ። እህቴም የልጃቹህ ስም ማን ይባል እያለች ታስመርጠን ጀመር ብዙ ስሞችን ብታስመርጠንም ፊርዶስ የሚለዉን ስም ሁላችንም ወደድነዉ በቃ ፊርዶሴ በሚለዉ ፀደቀ ቤቱ ከምን ጊዜዉም የበለጠ በደስታ ተዋበ። እኔም ደስ ብሎኝ ትንሽ ቀናትን እቤት አሳለፍኩ። ነገር ግን አንድ ቀን ተደዉሎ በስንት መከራ ካገኘሁት ስራ....

ልባረር መሆኑን ነገሩኝ እኔም የቀረሁበትን ምክንያት አስረዳኋቸዉ።ሌላ ስራ ስላጣሁ እንጂ ስራዉ ደሞዙ ትንሽ ነዉ በዛ ላይ እረፍት የማይሰጥ ስራ ነዉ። እኔም ሌላ ደሞዙ ጥሩ የሆነ ስራ እስከማገኝ እዘዉ እየሰራሁ ሌላ ስራ ማፈላለግ ጀመርኩ። እንግዲህ ሂወታችን እንዲህ እንዲህ እያለ ፊርዶሴም ሁለት አመት ሆናት እኔም ከምሰራበት ሱቅ ወጣሁ። ምክንያቱም ደሞዙ በጣም አነስተኛ ነዉ በዛ ላይ ፊርዶሴም እድጋለች ለሷ ለተለያዩ ነገሮች መግዣ ወጭ ያስፈልጋታል። ግን ምን መስራት እንዳለብኝ አላዉቅም እንዲህ ግራ እንደተጋባሁ ሙሀሜ ደወለልኝ። ሄሎ ሙሀሜ አሰላሙ አለይኩም "ዉአለይኩም እሰላም ወንድሜ ልጂህ፤ቤተሰብ፤ ሁሉ ሰላም ነዉ?"እያለኝ...... አወ ሰላም ናቸዉ..... እያልኩ ለብዙ ሰአት አወራን .... በመጨረሻም ስራስ? ብሎ ጠየቀኝ ምን ልመልስ እዉነቱን ከስራ ወጥቻለሁ ብየ ነገርኩት... በምን ምክንያት እንደወጣሁ ጠየቀኝ.... ሁኔታዉን እስረዳሁት አንተስ ስራ እንዴት ነዉ በማለት ተራየን ጠየኩት? ስራ ጥሩ እንደሆነ ቤትም እንደሰራ አሁን ደግሞ መኪና ሊገዛ እንደሆነ አጫወተኝ
ማሻ አላህ ጠንክር እያልኩት ስልኩ ተዘጋ....


በጣም ተሰማኝ....አይ እኔ!... ጓደኞቸ ሁሉ ቤት ሰሩ እኔ ግን እስከ ዛሬ ከእማ ጋር ተደርቤ እየኖርኩ ነዉ። እንደዚህ መሆንማ የለብኝም እንደ ሙሀመድ ስኡዲ መሄድ አለብኝ ብየ ወሰንኩ። ቤተሰቡን ሁሉ ሰብስቤ መሄድ እንዳለብኝ ነገርኳቸዉ ግን ማንም እንድሄድ ፍቃደኛ አልነበረም እኔ ግን ሀሳቤን አልቀይርም እሄዳለሁ ብየ ተነሳሁ። ግን እስከ ዛሬ የሰረሁበት ገንዘብ ትንሽ ነዉ ለመሄድ እንኳን አይበቃኝም አዲስ አበባ ያለዉን ወንድሜን አበድረኝ ብለዉ አያበድረኝም ምክንያቱም ስኡዲ ሂጀ እንድሰራ አይፈልግም ሙሀሜንም ማለት ደበረኝ በቃ የአለችኝን ብር ይዜ። በብሀር እሄዳለሁ ብየ ተነሳዉ። እማ ግን በፍፁም በብሀርማ አትሄድም አለችኝ። አማራጭ የለኝም እማ በብሀር እሄዳለሁ። እሷም ግራዉ ገብቷት እንግዲህ ቅር ብልህ እንቢ ብለሀል ከሄድክም በፕሌን ነዉ የምትሄድ... ግን እማ ብዙ ብር ያስፈልገኛል እኔ ደግሞ ትንሽ ገንዘብ ብቻ ነዉ ያለኝ በፕሌን መሄድ አልችልም... አታስብ ቤቱን በአራጣ አስይዜ እልክሀለሁ። የምር በጣም ደስ አለኝ መርየምና ሀያቴ ግን እያለቀሱ እኛም አብረንህ እንሄዳለን አሉኝ አይቻልም ብየ ብዙ ሰአት ተከራከርን መርየምማ እንደዉም ባሰባት ወላሂ ጥለኸኝ ከሄድክ እሞትብሀለሁ አለችኝ አኔም ግራ ገባኝ ደሞ ኡስታዝ አደራ እንዳትለያዪ ብለዉኛል ይዣት ልሂድ እንዴ... ደሞ እህቴስ ኧረ ያረቢ እያልኩ... እህቴ በቃ ሁላችንም እንሂድና ቶሎ ሰርተን እንመለሳለን ይሄ ሁላችንንም ያስማማናል ደሞ እወቅ ጥለኸኝ ብትሄድ ስትመለስ አታገኘኝም... ወይ ጉድ! መርየምንም ሀያትንም እንዴት ነዉ ይዛቸዉ የምሄድ እያልኩ ሳስብ መርየም ለኔ የራሴን ወጭ እሸፍናለሁ አለችን እንዴት? እናቴ አዲስ አበባ ሀብታም አግብታ ልጆችም ወልዳለች እሷን ስጭኝ ብላት አታሳፍረኝም ለናንተ ደግሞ እስከዛሬ የሰራህበትንና ቤቱን በአራጣ ከምንበደረዉ ጋር ይበቃቹሀል። ሁላችንም በመርየም ሀሳብ ተስማማን ግን ፊርዶሴን እንዴት ጥለናት እንሂድ። ያአላህ የእማ ነገርም ጨንቆናል ግን ችግር ነዉና ስደትን መረጥን ፊርዶሴንም የእማን እጂ ይዘን እንግዲህ እማ እኛ መሄዳችን ነዉ አላህ ብሎት ቶሎ ከተመለስን ተመለስን ካላለዉም እስከ መጨረሻዉ በዛዉ ወደ አሂራ ልንሄድ እንችል ይሆናል። መቸም ሰዉ ነንና መሞት አይቀርም ኡስታዝ ከመሞታቸዉ በፊት አላህ ብሎት ልጂ ከወለዳቹህ ባባ ማለትን ሳይሆን አሊፍ ባን አስቀድማቹህ አሳድጓቸዉ በኢማናቸዉ በትምህርታቸዉ ጠንካራ አድርጓቸዉ። አደራ ብለዉ ነዉ የሞቱ። እና.. አማ የኡስታዝን አማና(አደራዉን)አሳልፈን ሰጥተንሻል.... ብለን እየተላቀስን ጉዞችንን ወደ ሱኢዲ አረግን። አላህ ብሎትም ብዙም ፕሮሰሱ አላቆየንም ቶሎ አለቀልን እዛም እንደደረስን ሙሀሜ ላይ ደዉለን እንዲቀበለን ነገርነዉ እሱም መጦ ወሰደን ለትንሽ ጊዜ እረፍት አድርገን ስራ ማፈላለግ ጀመርን አልሀምዱሊላህ ስራ ማፈላለግ ትንሽ ቢያደክምም ሙሀሜ ስራ አገኘልን...


እኔም አክስቴን ፈዝዜ እያዳመጥኩ እያለ አጎቴ ዶክተሩን ይዞት መጣ ከወሬችን አቋረጡን። አሁን የተደረገልሽኝ ግልኮስ ጨርሽና መሄድ ትችላላቹህ ብሎን ወጣ። እሽ ቀጥይ ከዛስ አልኩ መጨረሻዉን ለመስማት ጓጉቻለሁ....
አክስቴም አባትሽ ገፀር እኔና እናትሽ አንድ አረብ ቤት ተቀጥረን ልጆችን መንከባከብ ጀመርን ታድያ ይሄ ሲሆን በየ ጊዜዉ እየደወልን እናናግርሽ ነበር። እንደዉም ለትንሽ ቀን ሳንደዉል ከቀረን ታኮርፊ ነበር እንዲህ እንዲህ እያልን ከሄድን አመት አስቋጠ
ርን ብድራችንንም ከፈልን ነገር ግን መርየምን በተደጋጋሚ ያማት ጀመር እኔና ወንድሜም ኢትዮጲያ መመለስ እንዳለባት ወሰን እሷ እሽ ባትልም ልጂሽን ስታይ ትድኛለሽ ብለን አልቅሰን ሸኘናት።


እሷም ሳትወድ ወደ ኢትዮጲያ መጣች እናቷ ነበረች የተቀበለቻት ነገር ግን በሽተዋ ትርፍ አንጀት ነበር አፍታም አልሰጣት እነ እማም ልትመጣ ነዉ እያሉ በጉጉት ሲጠባበቁ እዘዉ አዲስ አበባ እንዳለች ሂወቷ አለፈ.....


በአላህ ፍቃድ
ክፍል 1⃣9⃣
...................ይ
......................ቀ
........................ጥ
.............................ላ
.................................ል

join👇👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ አስራ ዘጠኝ ➊➒


እነ እማም ትመጣለች ብለዉ በጉጉት ሲጠብቁ አዲስ አበባ እያለች ሂወቷ አለፈ ወንድሜም መፀዳጃ ቤት ነበር ደዉለዉ የነገሩት ደንግጦ እዘዉ ተዘረጋግቶ ወደቀ።ከዛ ጀምሮ አይናገር፣አይበላ፣አይጠጣ ብቻ ለወራት ተሰቃይቶ ሞተ። እኔም ለብዙ ወራቶች ታምሜ ሆስፓታል ገባሁ። እማም በጣም አዝና እራሷን እስከመሳት ደርሳ ነበር። እኔም እማም ከአመት ቡኋላ አደራችንን መወጣት ስላለብን ወደ እራሳችን ተመልሰን አንችን መንከባከብ ጀመርን። እማም ለዛ ነዉ አደራየ የምትልሽ እኔም እየደወልኩ እናትሽ ነኝ የምልሽ እናትና አባት የለኝም ብለሽ እንዳይሰማሽ በማሰብ ነዉ። ወላሂ ባገባ ለራሱ ሀሳቤ ሁሉ ስላንች ነበር ደሞ ቶሎ ነዉ የተፋታሁ በቃ እኔ የተፈጠርኩ ለፊርዳስ እናት ሁኘ እማን ለመከባከብ ነዉ ብየ አስባለሁ ሁሌም እዉነቱን ብታቅስ ይቅር ትለን ይሆን ብየ እጨነቃለሁ...


እኔም በጣም ማልቀስ ጀመርኩ ሀያትም፣ አያቴም አብረዉኝ ያለቅሳሉ። ከድንገት አጓቴ በሩን አንኳኳዉ ሀያትም እንባዋን እየጠረገች ከፈተችለት አጎቴም ሲያየኝ ደንግጦ ምነዉ ፊርደሴ አመመሽ ዶክተሩን ልጥረዉ እያለ ወደ ዉጭ ሄደ። እኔ ደንዝዛለሁ እንባየ ብቻ ይፈሳል ማዉራት ለራሱ አቅቶኛል። ዳክተሩም መጦ ምነዉ ፊርዶሴ ደህና አይደለሽም እንዴ እኔ መልስ የለም ማልቀስ ብቻ..... ወደ አያቴ ዙሮ ምንድን ነዉ የተፈጠረ አለ? እነሱም የሆነዉ ሁሉ ነገሩት..... በጣም አዘነ በቃ እስከምትረጋጋ ለአንድ ሳምንት እዚህ መተኛት ይኖርባታል። የስነ ልቦና ዶክተሮች ስላሉን አይዟቹህ ትረጋጋለች ብሎ ሄደ።

እኔም ዝምብየ እያለቀስኩ ምግም መብላትየለ ማዉራት የለ በቃ ዝም ብየ ማልቀስ ከጀመርኩ ዛሬ ሳምንት ሆነኝ። አያቴም ሀያትም አብረዉኝ ሳምንት እንደ አዲስ አለቀሱ ዛሬ ከሀኪም ቤት ልወጣ ነዉ። ከእንግዲህ ቡኋላ ላለዉ ሂወቴ አልጨነቅም ምክንያቱም ለብዙ አመታት በጉጉት የጠበዃቸዉ እናትና አባቴ ተመልሰዉ ላይመጡ ወደ አሂራ ጥለዉኝ ሂደዋል። ዱንያ በጣም ታስጠላለች አንዱ ሲያገኝ አንዱ ሲያጣ አንዱ ሲያለቅስ አንዱ ሲስቅ አንዱ ሲወለድ ሌላኛዉ ሲሞት በቃ ዱንያን ጠላኋት። ምናለ እኔም በሞትኩ ብየ ተመኘሁ። አንድ ቀን መሞቴስ አይቀርም ቀኔ አልደርስ በሎ እንጂ እያልኩ ከራሴ ጋር እንደ እብድ ማዉራት ከጀመርኩ ወራትን አስቆጠርኩ ትምህርት የለ ቂርአት የለ ዝም ብየ እቤት መቀመጥ.....


ወደ ሀገራችን ከመጣን ሳስት ወራትን አስቆጠርን። ሀያትም አያቴም የኔ ነገር በጣም አሳስቧቸዋል። መምህሮቸም ቢሆኑ እየመጡ ለምን እንደዚህ ትሆኛለሽ አንችኮ ጀግናችን የነገተስፋችን ነሽ እያሉ በየ ግዜዉ መመላለስ ጀምረዋል። አያቴም እያለቀሰች ተይ አደራየ እኔ አደራየን እንድወጣ አትፈልጊም የእናትና የአባትሽን ህልም አታሳኪላቸዉም አንችኮ ጀግና የእናቷ ምትክ ነሽ እያለች ብዙ ብዙ መከረችን........... እኔም የማላወራይት ልጂ እማ እኔ ጎበዝ ብሆን እማ እና አባ ደስ ይላቸዋል.. አወ አደራየ ዉዴ እሽ እነሱ ደስ አንዲላቸዉ ምን ላድርግ? በትምህርትሽ እና በቂርአትሽ በርች የዛኔ እነሱን ደስ ታሰኛቸዋለሽ። በቃ እሽ ከነገ ጀምሮ ትምህርት ቤት እሄዳለሁ ቂርአቴንም እጀምራለሁ ስል.. ሀያትም እማም በጣም ደስ አላቸዉ....


እኔም የእናቴንና የአባቴን ህልም ላሳካ ትምህርቴን ጀመርኩ። ነገር ግን የማትሪክ ፈተና ሁለት ወራት ብቻ ነዉ የቀሩት በእነዚህ ወሮች ቀን ማታ ማንበብ ጀመርኩ መምህሮቸም ያለፉኝን ትምህርቶች ቅዳሜና እሁድ አንዳንዴ በእረፍት ሰአት ማስተማር ጀመሩ እኔም አላማየ የእናትና የአባቴን አደራ መወጣት ነዉና ደከመች ሰለቸኝ ሳልል ጥናቴን እያጠናሁ ነዉ። ሀያትም አይዞሽ በርች አያለች ሳመሽ አብረኝ ታመሻለች ለሊት ላጠና ስነሳ ብቻሽን እያለች አብረኝ ቁጭ ትላለች። የምር ሀያት በጣም ጥሩ እናትም አክስትም ናት። እኔም እናቴ በይኝ ሳትለኝ አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ስመለስ እማ አልኳት እሷም የሰማችዉን ማመን አቅቷት በደስታ አለቀሰች

እኔም እንባዋን እየጠረኩ አንችኮ እማ መባል ሲያንስብሽ ነዉ ግን ሌላ ቃል አንችን ለመግለፅ ስላጣሁ ነዉ እማ ያልኩሽ ይቅርታ.... በአላህ እናቴ ሁኝ አልኳት እሷም የደስታ እንባ እያነባች ልጀ የኔ ልጂ ብላ አቀፈችኝ እኔም አቀፍኳት በቃ ከዚህን ቀን ጀምሮ ያ የጠፋ ሳቅ እኛ ቤት ከተመለሰ ሁለት ወራት ተቆጠሩ እኔም ፈተናየን ተፈተንኩ ትንሽ ከበድ ቢልም አሪፍ ነበር በቃ የኛ ሂወት ሁሉንም እረስተን ልክ እንዳልተፈጠረ አልሀምዱሊላህ ብለን መኖር ጀመርን ተፈትነን ትንሽ ወራት እንደቆየንም ምደባና ዉጤት ተለቀቀ......


እኔም የአላህ ፍቃድ ሆነና ጥሩ ዉጤት አምጥቸ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደረሰኝ እማም አያቴም እኔም በጣም ደስ አለን ነገር ግን ሳስበዉ ከነእርሱ መራቄን ደስታየ በአንዴ ይጠፋል እማም ምን ሁነሽ ነዉ አሁን ደስ ብሎሽ በአንዴ ይከፋሻል? ደስ ያለኝ ዩኒቨርስቲ መግባቴን ሳስብ ነዉ የከፋኝ እናንተን ጥየ መሄዴ ነዉ። ወይ ልጀ እና እኛም አብረን እንከተል? አይ አማ ወላሂ እየቀለድኩ አይደለም እዉነቴን ነዉ። አዉቃለሁ ፊርዶሴ ነገር ግን አላማ አላማ ነዉ። ጠንክረሽ መማር አለብሽ አደራሽን ልትወጭ አይደልእንዴ! ለእንደዚህ አይነት ነገርማ እጂ አትስጭ አንች አሁን አድገሻል ወደ ፊትኳ የራስሽ ልጆች ይኖሩሻል እኛንም ጥለሽ ከባለቤትሽ ጋር ትኖሪያለሽ እና አሁን ከእኛ መለየቱ ለምን ከበደሽ ብላ መከረችን....


እሽ በቃ... ቃል እገባልሻለሁ አማ የማኳራ ልጂ አሆናለሁ። አያቴም አደራየ ዉዴ እዛ ሂደሽ ጓደኛ ስትመርጭ ተጠንቀቂ ጥሩ ከሆኑ አንችን ጥሩ ያረጉሻል። በተቃራኒዉ መጥፎ ከሆኑ አንችም እንደነሱ ማድረግ ይፈልጋሉ። ደሞ ጓደኛን ዉደደዉ እንጂ አትመነዉ ተብሎ የለ! ዉደጃቸዉ እንጂ አትመኛቸዉ ብላ ብዙ ብዙ መከረችኝ እኔም ምክራቸዉን ተቀብየ ልሄድ ሻንጣየን እያዘጋጀሁ ነዉ። አንዳንድ እማ ያመጣችልኝን ልብሶች ያዘጋጁልኝን ደረቅ ምግቦች ያዝኩ። አላማ ነዉና የእናቴን ቀለበት አደረኩ ምክንያቱም ማንኛዉም ወንድ አግብታለች ብሎ እንዳይቀርበኝ በማሰብ ነዉ። ጂልባቤን ለብሸ እየተላቀስን ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስገብተዉኝ ተመለሱ።


እኔም ጭንቅ ጭንቅ አለኝ በርግጥ ከጎጃም ነባር ተማሪዎች ነበሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀበሉኝ እነሱም አትፍሪ አይዞሽ አሉኝ። ግቢዉም ለአዲስ ተማሪዎች የምሳ ግብዛ ነበረዉ እኔም በልቸ ስጨርስ ነባር ተማሪዎች ግቢዉን እነሳይሽ ብለዉ ማሳየት ጀመሩ እኔም ሁሉንም በትዝብት ማየት ጀመርኩ ሴትናወንዶች አለባበሳቸዉ ደሞ ተቃቅፈዉ ነዉ የሚሄዱ አጃኢብ አላህ ከሀጂ ነቢ ጋር እንደዚህ ሁኑ ብሏል እንዴ! እያልኩ መታዘብ ጀመርኩ። እነሱም አይ አንች ምኑን አይተሽ አላህ አንችን እድለኛ አድርጎሽ በደህናዉ ጊዜ አግብተሻል እያሉ ቀለበቴን ያዩ ጀመር ደስ የሚሉ እህቶች ይመስላሉ። ትንሽ ትንሽም ቢሆን ለመግባባት እየሞከርኩ ነዉ።ስማቸዉንም ነግረዉኛል አንደኛዋ ሀዉለት ሌላኛዋ ደግሞ ሪሀና ትባላለች። ማሻ አላህ ጥሩ እህትማማች እንሆናለን ብያቸዉ ዳርሜንም አሳይተዉኝ ፍራሽ ይዜ ወደ ጠቆሙኝ ዶርም ስገባ........


በአላህ ፍቃድ
ክፍል2⃣0⃣

ይቀጥላል

join👇👇👇

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ ሀያ ➋ዐ



እዶርሜ ስገባ አዲስ ልጆች አልጋቸዉን እያነጠፉ ነዉ። እኔም ምንም ሳልል ታችኛዉ አልጋ ባዶ ነበር ፍራሼን አነጣፍኩ ማን ወሬ ይጀምር። ሁሉም አዲስ ነዉ በቃ እኔ ልጀምር ብየ እንተዋወቅ ፊርዶስ ዩሱፍ እባላለሁ። እናንተስ ብየ ጀመርኩ.... እኔ ሀይማኖት ፀጋየ አንደኛዋ ደግሞ እኔ ቤተልሄም አባይነህ እባላለሁ ብለዉ ከተዋወቅን ቡሀላ የመጣንበት ሀገር ስለትምህርት ቆይታችንን ስለቤተሰቦቻችን ብቻ ብዙ ብዙ ነገሮችን አወራን። እንዳዉም እኛን ላየ አዲስ ተማሪ አንመስልም። ነገ ክላስ እንጀምራለን ኢንሻ አላህ። እኔም እስከሚነጋ ቸኩያለሁ... የማይነጋ የለምነ ነጋ ኢላሂ ጥሩ መምህሮች ጥሩ ጓደኞች ስጠኝ እያልኩ ዱአ አድርጌ ገባሁ። መምህሮች ጥሩ ናቸዉ መሰል.... በእድሜቸዉ ትንሽ በሰል ያሉ ናቸዉ። ተማሪዎች እንኳን... ዩኒቨርስቲ መግባትን በጣም እያጋነኑ ያወራሉ እኔም በግርምት አያቸዉ ጀመር።በምህሮችም ራሳቸዉን አስተዋዉቀዉ ሳላስበዉ ክላስ ጨርሰን ወጣን።ስወጣ ከሀሙለትና ከእሪሀና ጋር ተገናኘን በጣም ጥሩ እህቶቸ ናቸዉ አብረ እንበላለን፤መስጊድ አብረን እንሄዳለን ብቻ ደስ ይላሉ።ዛሬ የምንዋደድ እህታማቾች ከሆን አንድ አመትን አስቆጠርን እነሱ በአንድ አመት ይበልጡኛል። በትምህርታቸዉም ግን ደከም ያሉ ናቸዉ ሁሌም ፈተና በመጣ ቁጥር ይጨናነቃሉ.....


..... ለምን ትጨነቃላቹህ ከመፅሀፉ እንዲሁም መምህር ካስተማራቹህ እኳ ነዉ ፈተናዉ የሚመጣዉ። ለምን አታነቡም? ብየ ስጠይቃቸዉ.... ብናነበዉ ያነበናል እንጂ መቸም አይገባንም ብለዉ ተስፋ ቆረጠዋል። ኧረ በአላህ ሁሉም ሰዉ አዉቆ አልተወለደም ኡቀቱን የሚያገኘዉ በመልፋት ቢሆን እንጂ እናንተም ጎበዝ መሆን ቀላል ነዉ ሁለቶችም እንዴት ጎበዝ መሆን እንችላለን እህቴ አሉ.... በመጀመሪያ ጎበዝ መሆን እንደምትችሉ እራሳቹህን አሳምኑ!
👉 የአምሮቹህን ሀቅም ተጠቀሙ
👉 እዉቀትን ከመምህሮቻቹህ ቅሰሙ(ሲያስረዱ በደንብ ተከታተሉ)
👉 አንብቡ አላህስ አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረዉ ጌታህ ስም(አል-ዐለቅ፡1) ብሎን የለ
👉 ጊዜቹህን በአግባቡ ተጠቀሙ
👉 በአላማ(በእቅድ)መመራትን ልመዱ
👉 በማንኛዉም ነገር ላይ ሚዛናዊ ሁኑ
👉 ፈፅሞ ለተፅዕኖ ተገዚ እንዳትሆኑ
👉 ጥበቦዊ (ስልታዊ)ሰዉ ሁኑ
👉 ነገሮችን በጥልቀት አስተዉሉ
👉 ስሜታቹህን እግር በእግር እንዳትከተሉ
👉 መወያየትን ልመዱ አንዱ ያላወቀዉን አንዱ ያቃልና
👉የሌሎች ዉድቀትና ስኬት ዞር ብላቹህ እዩ
👉 ጥረት አድርጉ በቃ ይህን ካደረጋቹህ ፈተና መጣ በተባለ ቁጥር አትፈሩም ተግባባን እሽ መቸ ማንበብ እንጀምር? ዛሬ እንጀምራለን ነገ የሚባል ነገር የለም ብለን ወደ ላይበራሪ ገባን።


ጎበዝ ለመሆን ትንሽ ቢከብዳቸዉም መቸም ተስፋ እንዳይቆርጡ ከአጠገባቸዉ ነበርኩ እነሱም ትግላቸዉም ተስፋ ሳይቆርጡ እየሞከሩ ነዉ። አልሀምዱሊላህ ጎበዝ የሚባሉ ባይሆኑም መካከለኛ ደረጃ ደርሰዋል ትልቅ ለዉጥ ነዉ መቸም በአንዴ ጎበዝ አይሆንም ቀስ በቀስ እያሸሻሉ ሲመጡ ጊዜ ቢወስድም አንድ ቀን ጎበዝ መሆናቸዉ አይቀርም ተስፋ ቆርጠዉ እስካልተዉት ድረስ... ወይ ጉድ!ዩኒቭ ከገባሁ አራት አመታትን አስቆጠርኩ እነሱም አሁን ላይ የመመረቂያ ፁህፋቸዉን እያዘጋጁ ነዉ። ጊዜዉም እየፈጠነ ነዉ እኔም ባልሽን ካላስተዋወቅሽን የሚል ብዙ ጥያቄዎች እየመጡብኝ ነዉ ኢላሂ ማንን ባሌነዉ ብየ እንደማስተዋውቃቸዉ ግራዉ ገብቶኛል......

እስከ ዛሬም እማ የሚለዉን ሀቢቢ ብየ ሴቭ አድርጌ ባሌ ደወለ ብየ ብዙ የፍቅር ቃላትን እማን ልክ እንደ ወንድ አወራት ነበር አንድ ቀን እንደዉም እማ ስትደዉል ስልኬን ትቸዉ ሂጀ ሲያዪት ሀቢቢ ይላል ባሏ ነዉ ብለዉ ሲያነሱት ልጀ እንዴት ነሽ.... የሚል የሴት ድምፅ ነዉ እነሱም ግራ ገብቷቸዉ ፊርዶስ ስልኳን እረስታዉ ላይበራሪ ገብታለች አለች ቤተልሄም እማም ደንገጥ ብላ ስትመጣ ባለቤትሽ ስልኩን ጥሎት ስለሄደ ለወንድሙ ደዉለሽ ስልኩ እማ ላይ እረስቶት እንደሄደ ንገሪልሽ እሽ ብላታለች።ስመጣም ለኔም ነገረችን
እንደዉ አላህ እየጠበቀኝ ነዉ እንጂ ብዙ ጊዜ ሀቢቢ ማለትን እረስቸ እማ እላለሁ። ግን እስካሁን የጠረጠረኝ አንድም ሰዉ የለም ዛሬ ግን በፎቶ ካላስተዋወቅሽኝ እያሉኝ ነዉ ምንም አማራጭ የለኝም እዚህ ስመጣ የአጎቶቸ ልጃች ማስታወሻ ብለዉ የተነሳነዉን አንደኛዉን ይሄ ነዉ ብየ አስተዋወዃቸዉ እነሱም የሰርጋቹህስ ፎቶ አሉኝ እኔም በኒካህ ቀለል ያለ ሰርግ ስለነበር ፎቶ የለም ነበር ብየ መለስኩላቸዉ። ሚስጥሬን ለነ ሀዉለት ለራሱ አልተነገርኩም ምክንያቱም እኔ መያዝ ያቃተኝን ሚስጥር ሌላ ሰዉ እንዴት ይጠብቅልኛል። ደሞም ሚስጥር ከአንድ ሰዉ ከወጣ ሚስጥር አይባልም ብለኝ ነበር አያቴ ስትመክረኝ...



እና ሀዉለትም ከጎበዞች ተራ ከተመደቡ ቆዩ እኔም በርትቸ ማንበቤን ተያይዜዋለሁ እንዳንዴ አጥንተን ስንጨርስ ሌሎች እህቶቻችን ላይ እየሄድ ብዙ ነገሮችን እንመክራቸዋለን። እንዳንዶቹ ምክራችንን ይቀበላሉ አንዳንዳቹ ደግሞ ምቀኛ ምን አወቅን አወቅን ትላላቹህ። ብለዉ በንቀቅ ያዪናል እኛም እሽ ያሉንን በማሰባሰብ እንዴት ስኬታማ መሆን እንዳለብን እንወያያለን አንዳንዴም ከትምህርት አለም ወጣ ብለን ከተመረቅን ቡኋላ ስላለዉ ሂወታችን እናወራለን ብቻ ደስ የሚል ጊዜያትን ከነሀዉለት ጋር አሳልፈን እና ሀዉለትም በጥሩ ዉጤት ተመረቁ.....


ጥለዉኝ በመሄዳቸዉ ባዝንም አላማ አላማ ነዉ ጉዞየን ወደ ፊት አድርጌለሁ በዛ ዉስጥም በጣም ሊነገር የማይችል መከራ አለ በዛ ላይ ከቤተሰብ እርቀን ነዉ ያለን በተለይበሴቶች ላይ ብዙ ጥቃቶች ይደርሳሉ አርግዘዉ ትምህርት እስከማቋረጥ ድረስ... ወንዶችም ቢሆኑ የተለያዪ አልባሌ ቦታዎች ላይ መገኘት ያበዛሉ ለምሳሌ የአንድ ጓደኛቸዉ ልደት ሲሆን እጭፈራ ቤት ሲጠጡ ያመሹና ከሴቶች ጋር ማደር፤ማጨስ፤ መቃም......ብቻ መጥፎ ጎኖች እንደሉት ሁሉ ጥሩም ጎኖች አሉት ለምሳሌ አላህ ብሎት ጥሩ ጓደኛ ላደለዉ በቂርአቱ በፀባዩ እንዲሁም በትምህርቱ ተሸሽሎ ይመረቃል አልሀምዱሊላህ እኔ ከጥሩ ጓደኞች አላህ ገጠመኝ የሚገርመዉ ቀለበት ለብሸ ለራሱ ምነዉ ለትዳር ቸኮልሽ የሚሉ ብዙ ወንዶች አሉ አንዳንዶችም ማሻ አላህ እህቴ ይላሉ ምነዉ ቸኮልሽ ሲሉኝ አይ ኢማኔን ቶሎ ልሙላዉ ብየ ነዉ እልና ቀልጀባቸዉ አልፋለሁ። አያቴ እንደዛ ዝምታን አስተምራ እንዳላሳደገችኝ አሁን ላይ የወጣላት ተናጋሪ ሁኛለሁ። ብቻ ብዙ የሀዘን ብዙ የደስታ ጊዜያቶች አለፉና በጥሩ ዉጤት ተመረቁ....


የአያቴንና የእማን ደስታ ወላሂ እንዴት እንደምገልፀዉ አላቅም ሁለቱም አደራየን ተወጣሁ እያሉ የደስታ እንባ ያነባሉ እኔም እናማእና አባ.. ባዩ ይህን ደስታ ግን አልሀምዱሊላህ እነዚህን የመሰለ ቤተሰብ ስለሰጠከኝ ብየ አላህን አመሰግነዋለሁ ስንት እናትና አባት አጥቶ የሚያስጠጋዉ ዘመድ ጠፍቶ የጎዳና ተዳዳሪ የሆነ አለ ብየ ሳስብ እፅናናለሁ ደጋግሜም አልሀምዱሊላህ እላለሁ። አሁን ቀጣይ ስራየ የሚሆን ስራ መፈለግና አያቴንና እማየን ይበልጥ ማስደሰት ነዉ። ጊዜ ሳላባክን ስራ መፈለግ ጀምሬለሁ ዛሬ አንድ የስራ ማስታወቂያ ወጣ ብለዉኝ ልፈተን እየሄድኩ ነዉ.....



ክፍል2⃣1⃣
ይ ቀ ጥ ላ ል
..........................ል

join👇👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ ሀያ አንድ ➋➊

ዛሬ አንድ የስራ ማስታወቂያ ወጣ ብለዉኝ ልፈተን እየሄድኩ ነዉ። ግን በጣም ጨንቆኛል። አላህየ አንተዉ አግዘኝ እያልኩ ተፈተንኩ። ግን ፈተናዉ ብዙም እንዳሰብኩት ከባድ አልነበረም። ዉጤት ነገ ተብለን ወደ ቤት ሄድን የማይደርስ የለም ነጋና ዉጤት ለማየት ሄድኩ። ዉጤቴ አሪፍ ነበር። ነገር ግን ዉጤቴ ዉድቅ ሆነ ምክንያቱን ባላቅም....ለስራዉ አትመጥኝም ብለዉ አሰናበቱኝ። እኔም ተስፋ ሳልቆርጥ ለብዙ ወራቶች የስራ ማስታወቂያ በወጣበት ሀገር ሁሉ እየሄድኩ ተወዳደርኩ። ነገር ግን ዉጤትሽ አሪፍ ነዉ አለባበስሽ ግን ለስራዉ አይመጥንም የሚል መልስ ይሰጡኛል። አለባበሴ ምን ሆነ የዉ ጂልባብ ነዉ የምለብስ።እኔ ግን ሳስበዉ አለባበሴ ብቻ ሳይሆን ብሄሬንና ሀይማኖቴንም ጭምር ጠልተዉት ነዉ። ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መታወቂያየን እያዩ አይ አንች እዚህ መቀጠር አትችይም ይሉኛል...


እንዲህ በስራ መፈለግ አንድ አመት አስቆጠርኩ። አንዳንድ ጓደኖቸ ለምን ጂልባብሽን አታወልቂም ምናልባት ከልብሱ ከሆነ አዉልቂዉና መቀጠር ትችያለሽ ይሉኛል። እኔም ጂልባቤንማ በፍፁም አላወልቅም ስራዉ ይቀራል እንጂ እያልኩ ዛሬ ድረስ ተስፋ ሳልቆርጥ እየፈለኩ ነዉ። ዛሬ ደግሞ አዲስ አበባ ስራ ወጣ ብለዉኝ መንገድ ጀምሬለሁ። ግን ተስፋየ አሁን ላይ እንደድሮዉ አይደለም በርጥ ሙእሚን በአላህ ላይ ተስፋ መቁረጥ እንደሌለበት አዉቃለሁ።


አያቴና እማም ሁል ጊዜ ተስፋ መቁረጥ እንደሌለብኝ ይመክሩኛል አዲስ አበባም አጎቴ ላይ አድሬ በጥዋት ልፈተን መንገዴን ጀመርኩ እየሄድኩም ያረቢ የዛሬዉም የመጨረሻየ አድርግልኝ ብየ ዱአ አደረኩ በስአቱ ደርሸ ለፈተና ቀረብኩ.....


ፈተናዉ አይከብድም ግን ዛሬም በልብሴ በብሄሬና፤ በሀይማኖቴ ስራዉን እንዳይከለክሉኝ ብየ ፈራሁ። አላህ ብሎት እዚህ ስራ ከገባሁ እማንና አያቴን እዚህ አዲስ አበባ አምጥቸ አኖራቸዋለሁ። እንደዉም እኔ እየሰራሁ በደስታ ሁሉንም አሟላላቸዋለሁ። ብየ ለራሴ ቃል ገባሁ። የፈተና ዉጤት ነገ እንደሚለቀቅ ተነግሮን እኔም አጎቴ ቤት አድሬ በጥዋት ዉጤት ለማየት ሄድኩ። ለስራ ካለፉት መካከልም የኔ ስም በአንደኝነት ተፅፏል እኔም አላምን ብየ ደጋግሜ አየሁት አልተሰሳትኩም ፊርዶስ ዩሱፍ ይላል። እዛዉ ሱጁድ ወረድኩ ይህንን የተመለከተዉ የመስርያ ቤቱ አሰሪ በግርምት ጠጋ ብሎ አሰላሙ አለይኩም አለኝ እኔም ደንግጨ ዉአለይኩም እሰላም አልኩት። በጣም ደስ ብሎሻል መሰል ሱጁድ ወረድሽ ማሻ አላህ አለኝ።


አወ በጣም ደስ ብሎኛል ታዉቃለህ በጣም በከፍተኛ ዉጤት ነዉ የተመረኩ ነገር ግን ስራ ስወዳደር ከፍተኛ ዉጤት አመጣና በብዙ ምክንያቶች ለስራዉ እንደማልመጥን ይነግሩኛል ዛሬ ግን አልሀምዱሊላህ እናንተ ተቀበላቹህኝ እያልኩ ወሬ ጀመርኩ።
እሱም በፈገግታ ነገ መጀመር ትችያለሽ አለኝ በጣም አመሰግናለሁ ብየዉ እየሳኩ ምንገዴን ጀመርኩ። አንዳንዳቹ ብቻዋን የምትስቅ እብድ ነት እያሉ ከኔ ይሸሻሉ እኔም ኧረ አትፍረዱብሽ ዛሬ ስራ ስላገኘሁ ደስ ብሎኝ ነዉ እብድ አይደለሁም ብየ አረጋጋቸዋለሁ እነሱም እንኳን ደስ ያለሽ ይሉኛል......


አሁን ደግሞ አያቴ፤ እማንና አጎቴን ስራ አገኘሁ ብየ ለመናገር ጓጉቻለሁ እቤት ደርሸ ቶሎ ካርድ ሞለሁና እማንና አያቴን አገኘኋቸዉ። ስራ ልጀምር መሆኑን ስነግራቸዉ ከኔ በላይ የተደሰቱ እነሱ ናቸዉ።


አጎቴም እነሱን አናግሬ ሳበቃ መጣ ለሱም ነገርኩት በጣም ደስ አለዉ አሁን እማንና አያቴን አዲስ አበባ ለማምጣት ቤት መከራየት አለብኝ ምክንያቱም አጎቴ ሚስትና ልጆችም አሉት አብሮ መኖር ደግሞ ይከብዳል ስለዚህ እነሱም ለማምጣት ቤት መከራየት ይኖርብኛል። ቢቻል ከስራ ቦታየ ቅርብ የሆነ... ይሄን ለማረግ ደግሞ ትንሽ ገንዘብ ያስፈልገኛል እያልኩ ብቻየን ማዉራት ጀመርኩ አይ የኔነገር ስራ ገና ትጀምሪያለሽ ተባልኩና እቅዴ በዛ ነግቶ ስራ እስከምሄድ እዉነት እዉነት አልመስለኝ አለ ስአቱንም እንዳላረፍድ እያልኩ አስሬ እየተነሳሁ ማየት ጀመርኩ እንቅልፍ ሳይወስደኝ ነጋ ዛሬ ስራ ለመጀመር የመጀመሪያ ቀኔ ነዉ ደስ ይላል እያልኩ ወደ ስራ ቦታየ በጥዋት ሄድኩ ገና ከመግባቴ አሰሪዉና አንድ ልጂ ይጨቃጨቃሉ እኔም ደንግጨ ምን ሁነዉ ይሆን እያልኩ ማሰብ ጀመርኩ....


ስራ ለመጀመር የመጀመሪያ ቀኔ ነዉ።ደስ ይላል እያልኩ ገና ከመግባቴ አሰሪዉና አንድ ልጂ ይጨቃጨቃሉ። እኔም ምን ሁነዉ ይሆን እያልኩ ማሰብ ጀመርኩ ከድንገት አሰሪየ ዞር ብሎ መጣሽ እንዴ ስአት ታከብሪያለሽ ማለት ነዉ። ከሁሉም ሰራተኞች አንች ነሽ የመጀመሪያይት እያለ ወደ ልጁዙሮ
ተተዋወቁ ብቸኛዉ ልጀ ሪድዋን ሙሳ ይባላል ብሎ ጥሎን ሄደ።

እኔም ፊርዶስ ዩሱፍ እባላለሁ ብየ ተተዋወኩት። ግን ልጁ የሆነ ዱርየ ነገር ይመስላል የፀጉሩ መፍተልተል፤ አለባበሱ ኢናሊላህ በጣም ነዉ የሚያስጠላ እንኳንስ የአቶ ሙሳ ልጂ ሊመስል ተራ በረንዳ አዳሪ ነዉ የሚመስል እያልኩ ሳስብ....... ነይ ቢሮሽንም ሌሎች ሰራተኞችንም ላስተዋውቅሽ ብሎኝ ይዞኝ ሄደ።

ቢሮየ ዋው! በጣም ደስ ይላል።ወንበሮቹ፤ ኮምፒዉተሩ.... ሁሉም ዘመናዊ እቃዎች ናቸዉ። ሰራተኞችም ቢሆኑ ደስ ይላሉ። በተለይ ሙባረክ የሚባለዉ ሰራተኛ ገና ሳየዉ ሱንይ ነዉ የመሰለኝ...ፁሙን አሳድጓል፤ሱሩዉን አሳጥሮል...ብቻ ቢሮዉም ሰራተኞችም በጣም ተመችተዉኛል።ደሞዙም ቢሆን በጣም አሪፍ ነዉ። ግን ስራዉ ትንሽ ከበድ ይላል።
ምክንያቱም የተለያዩ የመኪና መቀያየሪያ ማሽነሪዎች ከዉጭ ሀገር ሲገቡ በስንት እንደገቡ፤ በስንት እንደሚሸጡ፤ ትርፍና ኪሳራቸዉን ማሳወቅ የኔ ስራ ነዉ። ብዙ ጊዜ ሽያጭ ላይ የሂሳብ ስህተት ያጋጥማል ይሄ ነዉ በቃ የስራዉ ከባዱ ክፍል።


ቢሆንም ግን ሙባረክ ከጎኔ ሁኖ ስለ ስራዉ ባህሪ በደንብ ስለ ነገረኝ ስለ ስራዉ ለማወቅ ብዙ ጊዜ አልወሰደብኝም።

አንዳንዴ ሪድዋን እየመጣ እኔ ስለ ስራዉ አስረዳታለሁ አንተ ሂድ ወደ ስራህ ብሎ ሙባረክን ያዝዘዋል።ከዛ የተለያዪ ማሽነሪዎች የመጡበትንና የሚሸጥበትን ዋጋ ያስረዳኛል።
እኔ ግን ጭራሽ የሚለኝን አልሰማም ዝም ብየ የገባኝ እየመሰልኩ ራሴን አነቀንቃለሁ። በቃ! እሱን በጣም እጠለዋለሁ ጭራሽ ባላየዉ ሁሉ እንዴት ደስ ባለኝ! የሆነ ድርየ ነገር ነዉ። አንዳንዴማ እንደዉም መኪና ይዞ ነይ ልሸኝሽ ብሎ ሁሉ ይጠይቀኛል።እኔም ከስራ ቦታየ አቅራቢያ ስለሆነ ቤት የተከራየሁት መኪና እንደማያስፈልገኝ በእግሬ እንደምሄድ በተደጋጋሚ ነግሬዋለሁ። እሱ ግን ጭራሽ እኔን ለማናደድ እኔ በእግሬ ስሄድ እሱ በመኪና እቤቴ እስከሚገባ ድረስ ይከታተለኛል። ያላየሁት እየመሰለዉ እቤቴ ስገባ ይመለሳል።


የተከራየሁት ቤት የምኖር ለብቻየ አይደለም። እማና አያቴ ከጎጃም መጠዋል ከኔጋ ነዉ የሚኖሩ እንደዉም ከኔጋ መኖር ከጀመሩ ባልሰሳት ወደ አምስት ወር አካባቢ ይሆናቸዋል። አሁን ላይ ቤታችን ሁሌም በሳቅ በጨዋታ የደመቀ ነዉ።


ግን እኔን እያስጨነቀኝ ያለዉ የሪድዋን መከታተል፤ እቤሮየ ሁሌም መመላለስ፤ ከአባቱ ገንዘብ ለመቀበል የሚያደርገዉ ጭቅጭቅ.በቃ ሁሉም ነገሩ ግራ አጋብቶኛል። ለምን ይሆን ገንዘብ ከአባቱ ሁሌም የሚቀበለዉ? ቀርቤ ደግሞ እንዳልጠይቀዉ በጣም እጠለዋለሁ ጭራሽ እሱን ማየትም አልፈልግም ግን ለምን ሁል ጊዜ ገንዘብ እንደሚቀበል ከሙባረክ ጋር በደንብ ስለምንግባባ ይነግረኝ ይሆናል በዛ ላይ ቅርብ ጓደኛዉ ስለሆነ ያቃል እያልኩ👇👇
ሳስብ ነግቶ ወደ ስራ ቦታየ ሄድኩኝ። በቀጥታ ሙባረክን ማግኘት ነበረብኝ ስፈልገዉ አጣሁትና ወደ ቢሮየ ስገባ የሆነ ሰዉ ፊቱን ወደ ግርግዳዉ አዙሮ ተቀምጦ ሲጋራ እያጨሰ ነዉ ደሞ ጭሱ ብቻ እንጂ የሰዉየዉ ማንነት ከጀርባ ስለነበር አይለይም እኔም ጠጋ ብየ ፊቱን ሳየዉ.... ያየሁትን ማመን አቃተኝ


በአላህ ፍቃድ
ክፍል 2⃣2⃣

ይቀጥላል
join👇👇👇👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ ሀያ ሁለት ➋➋

ወደ ቢሮየ ስገባ የሆነ ሰዉ ፊቱን ወደ ግድግዳዉ አዙሮ ተቀምጦ ሲጋራ እያጨሰ ነዉ። ደሞ ጭሱ ብቻ እንጂ የሰዉየዉ ማንነት ከጀርባ ስለነበር አይለይም እኔም ጠጋ ብየ ፊቱን ሳየዉ.. ያየሁትን ማመን አቃተኝ.....
ሪድዋን ነዉ በጣም ደነገጥኩ!ጭራሽ እቢሮየ ሲጋራ!!! ያማሀል እንዴ! ይሄኮ ሳንባን ምን ያህል እንደሚጓዳ ታቃለህ? ብየ ሲጋራዉን ከአፉ አዉጥቸ በመስኮት ወረወርኩት። ብቻ ሳላስበዉ ብዙ ተናገርኩት። ይሄን ሁሉ ሳረግ ግን እንባዉን ከማፍሰስ ዉጭ ምንም ቃላት አልተናገረኝም።

የምር ገርሞኛል ይሄን ሁሉ ስለፈልፍ ተነስቶ ሄደ እኔም ያለበት ስሜት ጥሩ አይደለም ብየ ተከተልኩት። አባቱ ቢሮ ነበር በቀጥታ የገባ። እኔም እንደሁል ጊዜዉ ብር ሊቀበል ይሆናል ብየ እዘዉ ባለሁበት ቁሜ ጠበኩት። አልተሰሳትኩም ዛሬም ተጨቃጭቆ ቡሩን ይዞ ወጣ።


አባትየዉም ተከትሎት ሲወጣ አይን ለአይን ተያየንና አሰላሙ አለይኩም ልጀ አለኝ እኔም ዉአለይኩም እሰላም እያልኩ.. አቶ ሙሳን ቀረብኳቸዉ። የተነጋገሩትን ሁሉ የሰማሁ መስሎት እንደሆነ አላቅም ብቻ አንገታቸዉን ደፍተዉ አየሽዉ አይደል! ይህን ባለጌ ልጀን እያሉ እንባቸዉን ማፍሰስ ጀመሩ። እኔም እንባቸዉን ሳይ አላስቻለኝም እንባየ መጣ...በመቀጠልም ግን ለምንድን ነዉ ገንዘብ የሚጠይቅህ በማለት ጥያቄየን ጀመርኩ።


አቶ ሙሳም እይ ልጀ! ከነዛ መጥፎ ጓደኞቹ ጋር ሊቅምበት፤ ሊያጨስበት... ነዉ። በማለት ለጥያቄየ መልስ ሰጠኝ እኔ ግን ግልፅ አልሆነልኝም እሽ እናቱ ለምን አትመክረዉም በማለት በድጋሚ ጠየቁት

እይዉልሽ ልጀ ባለቤቴ ማለትም የሪድዋን እናት ገና እሱን ስትወልድ ነዉ ሂወቷ ያለፈዉ።እኔ ነኝ ሪድዋኔን እናትም አባትም ሁኘ ያሳደኩት። ወላሂ ልጀ ሪድዋኔን ሳሳድገዉ ጨዋ፤ታዛዥ፤ኢማነኛ፤ጓበዝ.....ብቻ ምን ልበልሽ ጥሩ ልጂ ነበር። አሁን እንኳን ብር ሲወስድ ከኔጋ ተጨቃጭቆ ካልሆነ አምስት ሳንቲም ብትሆንኳ እኔን ሳይጠይቅ ወስዶ አያዉቅም ደሞ ብዙ ጊዜ የገንዘብ ማስቀመጫ ካዝነየ ክፍት ነዉ። ነገር ግን አባ ገንዘብ እፈልጋለሁ ስጠኝ ይለኛል እንጂ ፈፅሞ ካለኔ ፍቃድ ወስዶ አያዉቅም።

ብቻ ሪድዋኔ አሁን ድርየ... የማላዉቀዉ ልጂ ሁነብኝ እንጂ ድሮማ.......እንዴት አይነት ልጂ ነበረ። እያለ ማስታወስ ጀመረ

እኔም እህ አሁን እሽ ምን እንዲህ ዱርየ አደረገዉ? በማለት ጥያቄየን አስከተልኩ

እይዉልሽ ልጀ ሪድዋኔ ገና ህፃን እያለ በጣም የሚወደዉ ጓደኛ ነበረዉ ስሙም አህመድ ይባላል። ፍቅራቸዉ... እኔ እንጃ በቃላት መግለፅ ይከብደኛል። በስማቸዉ ለራሱ አይጠራሩም ወንድሜ ነበር የሚበባሉ። ኢድ ሁኖ ልብስ ሲገዙ እንኳን አንድ አይነት ነበር የሚገዙ ካልሆነማ አይለብሱትም ነበር። በቃ ሁሉ ነገራቸዉ ልክ እንደመንትዮች ነበር። በዛ ላይ የነ አህመድ ቤት እኛ አካባቢ ስለነበር አህመድ አንዳንዴ እኛ ቤት ያመሻል ብዙ ጊዜም ያድራል። እሪድዋኔም አንዳንዴ እነሱ ቤት እየሄደ ያድራል ነግቶ ሲገናኙ ብዙ አመት እንዳልተገናኙ ነበር የሚሆኑ። ትምህርት ቤት እንኳን አይለያዪም አብረዉ ይሄዳሉ፤አብረዉ ይመጣሉ። ይሄ ሁኔታቸዉ የሰፈሩን ሰዉ አጃኢብ ያስብል ነበር።


እንዴት አድርጌ ፍቅራቸዉን እንደምነግርሽ አላቅም ብቻ ዩንቨርስቲ እንኳን ሪድዋኔ ባህርዳር ሲደርሰዉ አህመድ ደግሞ አርባምንጭ ነበር የደረሰዉ ግን ሁለቱም መለያየት ስለማይፈልጉ አንሄድም ብለዉ ቀሩ። እኔም እዚሁ አዲስ አበባ የግል እየከፈልጉ ማስተማር ጀመርኩ.....ከዛ ሁለቱም ሊመረቁ 1 አመት ሲቀራቸዉ አህመድ.......

ብሎ እየነገረኝ እንባዉን መቆጣጠር አልቻለም እንዴት ብሎ ይቀጥል ግን መጨረሻቸዉ ምን ይሆን ብየ እያሰብኩ

አቶ ሙሳ እንባዉን እየጠረገ አህመድና ሪድዋን ሊመረቁ 1 አመት ሲቀራቸዉ አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ሲመለሱ እየፈጠነ የነበረ አንድ ተሳቢ መኪና አህመድን ገጨዉ።

ሪድዋኔም አህመድን አቅፎት ስለነበር ቀኝ እጁ በጣም ተጎድቶ ለብዙ ጊዜ ሀኪም ቤት ነበር። ሪድዋኔን በጣም የጎዳዉ ህመሙ ሳይሆን አህመድ ሲገጭ ወንድሜ ወንድሜ.....እባክህ አድነኝ እያለ ወድያዉ እያየዉ ሂወቱ ማለፉ ነበር። ብቻ ልጀ ሪድዋን ለብዙ ጊዜ አህመድ አህመድ.....እያለ እንቅልፍ እንኳን አይተኛ፤ምግብ አይበላ፤ከቤት አይወጣ.... እኔ እንጃ ልጀ ያን ክፉ ጊዜ ማስታወስ አልፈልግም እያለ እንዳዲስ ማልቀስ ጀመረ እኔም የምር አዘንኩ። ግን የሪድዋን እንዲህ መሆን ከአህመድ ሞት ጋር ምን ያገናኘዋል በማለት ጠየኩት።
አቶ ሙሳም እንዴ ልጀ! ምን ነካሽ አህመድ ከሞተ ጀምሮ ሪድዋኔ የሚዉል ከመጥፎ ጓደኞች ጋር ነዉ እነሱም የሚቅሙበት፤ የሚያጨሱበት ሪድዋን ከኔ ተጨቃጭቆ በሚወስደዉ ገንዘብ ነዉ። ብቻ ሪድዋኔ በአህመድ ሞት ምክንያት ሱስ ዉስጥ ገባ ይሄዉ እንደምታይዉ ነዉ።


የምር ሪድዋን ያሳዝናል ግንኮ አቶ ሙሳ ምናልባት የስነልቦና አማካሪ ብትቀጥርለት ከሱስ ዉስጥ ሊወጣ ይችላል።
አይ ልጀ! ያላማከርኩት ዶክተር የለም። ለሱ ብዙ ወጭወችን አወጣሁ በሀገር ዉስጥም በዉጭም ለፋሁ ለፋሁ......መፍትሄ የለም።


አቶ ሙሳ በልጁ ተስፋ የቆረጠ ይመስላል ግንኮ ከነዚህ መጥፎ ጓደኞቹ ቢርቅና ጥሩ ጓደኞችን ቢይዝ ምናልባት ለዉጥ ሊመጣ ይችል ይሆናል። ከነሱ ጋር እየዋለ አይደል የሚቅም፣ የሚያጨስ.... በማለት አቶ ሙሳን አማከርኩት ልክ ነሽ በማለት በሀሳቤ ተስማማ ግን እንዴት ከነሱ እንዲርቅ ማድረግ እንዳለበት ግራ ገብቶታል።


ትንሽ ካሰበ ቡኋላ እባክሽ ልጀ በአላህ ልለምንሽ ልጀን አግዥዉ በርግጠኝነት ካገሽዉ ከሱሱ ኢንሻአላህ ይወጣል ደሞ የፈለግሽዉን ገንዘብ እሰጥሻለሁ በአላህ እያለ አለቀሰ.......

እኔ ግን ፈፅሞ በሀሳቡ አልተስማማሁም እንዴ! አይኑን እንኳን ማየት አልፈልግም በዛ ላይ እሱን ማገዝ አልችልም አልኩት

አቶ ሙሳ ግን ወላሂ ልጀ እመኚኝ ትችያለሽ ደሞስ ሴት አይደለሽ ሴትኮ የራሷ አላህ የሰጣት ጥበብ አላት ላስተካክል ካለችም ማስተካከል ትችላለች ላጥምም ካለችም አያቅጣትም በአላህ ልጀ እመኚኝ ትችያለሽ ደሞ ሪድዋንን ልቅረበዉ ካልሽ ቀላል ነዉ እኔ እንኳን እዚህ ቢሮ መስራት ከጀመርሽ ጀምሮ በሪድዋን ላይ የተወሰኑ ለዉጦችን አይቻለሁ አለኝ እኔም ምን አዲስ ነገር አየህበት በማለት ጥያቄ አነሰው
አቶ ሙሳም

ክፍል 2⃣3⃣
.
ይቀጥላል

Join👇👇👇

@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ ሀያ ሶስት ➋➌


እዚህ ቢሮ መስራት ከጀመርሽ ጀምሮ በሪድዋን ላይ የተወሰኑ ለዉጦችን አይቸበታለሁ አለኝ እኔም ምን አዲስ ነገር አየህበት በማለት ጥያቄ አነሰሁ
አቶ ሙሳም ለምሳሌ ከመምጣትሽ በፊት ማሽነሪዎች በስንት ገቡ፤ በስንትስ ይሸጣሉ ብሎ ጠይቆኝ አያዉቅም ነበር አሁን ግን ሂሳብ ላይ ፊርዶስ እንዳትሰሳት ንገረኝና እንዳስረዳት ማለት ጀምሯል። ምን ይሄ ብቻ ብዙ ጊዜ ቢሮ ሲመጣ ገንዘብ ተቀብሎኝ በፍጥነት ነበር የሚወጣ አሁን ግን አንች ቢሮ መመላለስ፤ እቤትሽ እስከምትገቢ መከታተል.... ብቻ ብዙ ለዉጦች አይቸበታለሁ ደሞ እንዴት አወቅክ እንዳትይኝ ብቸኛ ልጀ ስለሆነ ብቻዉን ሲወጣ ይጨንቀኛል እንደዉም ስራ ባይኖረኝ 24 ሰአት አብሬዉ ብሆን እንዴት ደስ ባለኝ እያለ ፈገግ ማለት ጀመረ።


እኔ ግን በጣም ጨንቆኛል አቶ ሙሳም መጨነቄን አዉቆ ነዉ መሰል የኔ ልጀ አይዞሽ አትፍሪ እሪድዋኔ ብቻ ሱሱን እንዲተወዉ ማድረግ ላንች ቀላል ነዉ። በዛ ላይ የፈለግሽዉን ገንዘብ እሰጥሻለሁ.......

አቶ ሙሳ ወላሂ እኔ ገንዘብ አልፈልግም። መርዳትም ከፈለኩ በህትነት አግዘዉ ነበር ግን አልችልም።
ሸህ ሙሳም እያለቀሰ ለብዙ ጊዜ ለመነኝ
የምር ሸህ ሙሳ በጣም አሳዝኖኛል።
ግን ማስተካከል እችል ይሆን ደሞ ቀለበቴን ከዩኒቨርስቲ እንደወጣሁ ነዉ ያወለኩት። ባላወልቀዉ እንኳን ጥሩ ነበር....ወላሂ አስተካክላለሁ ብሎ ሀላፊነት መዉሰድ በጣም ይጨንቃል።

ደሞ ሁል ጊዜ አቶ ሙሳ አዝነዉ ሳያቸዉ አላስቻለኝም። በቃ ሪድዋንን ላግዘዉ ፍቃደኛ እንደሆንኩ ለአቶ ሙሳ ነገርኩት እሱም በጣም ደስ ብሎት ከአሁን ቡሀላ የቢሮዉን ስራ ትተሽ እሱን መከታተል ጀምሪ ብሎኝ ተስማማን በዛዉም ስለኔ ሂወት ጠይቆኝ ቤት ተከራይተን እንደሆነ የምንኖር..... ብቻ ሁሉንም ነገርኩት።


አቶ ሙሳም አይዞሽ አብሽሪ እያለኝ በመሀል ሙባረክ ጠርቶት ሄደ።እኔም እንዴት ሪድዋንን ማገዝ እንዳለብኝ ሳስብ እሪድዋን ሲጋራ እያጨሰ አሰላሙ አለይኩም ፊርዶስ እያለ መጣ። እኔም ዉአለይኩም እሰላም ብየ መለስኩለት የምር ተገረመና ሊሄድ የነበረዉ ወደኔ ጠጋ ብሎ ምነሙ ዛሬስ ምን ተገኝቶ ነዉ በፈገግታ የመለሽልኝ ብሎ ጠየቀኝ በርግጥ ከዚህ በፊት አሰላሙ አለይኩም ሲለኝ እሱን ላለማየት ፊቴን ዝቅ አድርጌ ነበር መልስ የምሰጠዉ።

አሁንማ እየጠላሁትም ቢሆን ላባቱ ስል አንዴ ላግዘዉ ቃል ገብቻለሁ ምን አረጋለሁ። ሳልወድ ፈገግ እያልኩ ልቅረበዉ እንጂ! ብቻ እይዉልህ ሪድዋን ዛሬ ደስ ስላለኝ ነዉ ፈገግ ብየ መልስ የሰጠሁህ ብየ መለስኩለት።

እህ የምን ደስታ? በማለት ጥያቄ አነሳ
ምን ልበል እያልኩ ሳስብ ሙባረክ መጣ እኔም ሙባረክ መጣህ እንዴ እንካ እነዚህን ዶክሜንቶች ለአቶ ሙሳ ስጥልኝ ብየ ሳዝዘዉ ሪድዋን ተቀብሎ እኔ አደርሳለሁ ብሎኝ ዶክሜንቶችን ሊያደርስ ሄደ። አልሀምዱሊላህ እያልኩ ሪድዋን ከወጣ ቡኋላ ከሙባረክ ጋር ስለሪድዋን ሁኔታና ከአባቱ ጋር ስላወራነዉ ነገር በሙሉ ነገርኩት። እሱም ጥሩ ሀሳብ ነዉ አለኝ። ግን ትንሽ ይከብድሻል ደግሞ ብቻሽን.....ሲለኝ አንተ ለምን አታግዘኝም? ብየ ጥያቄ አቀረብኩለት ነገር ግን ሙባረክ ፍቃደኛ አልነበረም ምክንያቱም እኔ ከሪድዋን ጋር ስሆን እሱ ደግሞ የኔን ቦታ ሸፍኖ መስራት አለበት።


ብቻ እኔ እንዴት ሪድዋንን ከሱሱ ማራቅ እንዳለብኝ ብዙ ጊዜ ከሙባረክ ጋር እየተገናኘን እነወራለን። ምክንያቱም ሙባረክ ስለሪድዋን ባህሪ በደንብ ያዉቃል አንዳንድ የመፍትሄ ሀሳቦችንም ይነግረኛል። እንደዉም ዛሬ ስራ ስንጨርስ እዚህዉ ቆይተን እንነጋገራለን ብሎኝ ሄደ።

የማይደርስ የለምና ስራ ጨርሰን ሙባረክ እቢሮየ መጦ ስለመፍትሄ ሀሳቦች እያወራን እያለ በሩ ተንኳኳ እኛም ደንግጠን ስንከፍተዉ
ሪድዋን ነዉ።
.... ሪድዋን መጣህ እንዴ? ናግባ አልኩት እሱ ግን የተናደደ ይመስላል እኔንና ሙባረክን በትኩረት አይቶን በፍጥነት ወጣ። በጣም ተናዷል..... እንዲህ ሲሆን የመጀመሪያዉ አይደለም እኔንና ሙባረክን በማንኛዉም ቦታ አብረን ካየን ፊቱ ይቀያየራል/ በጣም ይናደድና ዝም ብሎን ይሄዳል።ቆይቶ ሲመለስ ሲጋራ ወይንም ጫት ይዞ ይመለሳል። በቃ ሲናደድ በጣም ያጨሳል ወይም ይቅማል ሲናደድ ይሄ የሪድዋን ባህሪ ነዉ።

ብቻ የተወሰኑ ቀኖችን ባህሪዉን እየተከታተልኩ ነበር ዛሬ ሪድዋንን ለማገዝ የመጀመሪያ ቀኔ ነዉ። እንደተለመደዉ ዛሬም እቢሮ ስገባ ሲጋራ እያጨሰ አሰላሙአለይኩም ፊርዶስ አለኝ.... እኔም ዉአለይኩም እሰላም ብየ መልስ ሰጠሁት በመቀጠልም ረጋ ብየ ሪድዋን ግን ለምን ታጨሳለህ?ለምንስ ትቅማለህ? በማለት ጥያቄየን ጀመርኩ......

ሪድዋንም በቃ ማጨስና መቃም ደስ ስለሚለኝ! አይመስልሽም በማለት ወደኔ አፈጠጠ።
አትዋሽ! ማንኛዉም ሰዉ ፈልጎ ሱስ ዉስጥ እንደማይገባ አዉቃለሁ። በቃ እሽ ምክንያቱን ተወዉና በምትቅመዉና የምታጨሰዉ ሳንባህንና ሌሎች የሰዉነት ክፍሎችህን እንደሚጎዳቸዉ አታዉቅም? በማለት ጥያቄየን ቀጠልኩ......



ሪድዋንም አወ እንደሚጎዳ በደንብ አዉቃለሁ ለዛም ነዉ የማጨስ፤የምቅም በማለት መልስ ሰጠኝ።
ቆይ እሽ ያንተን መጎዳት ተወዉና ቢያንስ ለአባት አታዝንለትም!!! ደሞ ብቸኛ ልጁ እንደሆንክ ነግሮኛል ብቻዉንም እንዳሳደገህ አዉቃለሁ። ሪድዋን በአላህ ልለምንህ ተወዉ አይጠቅምህም እድንያህንም፤ በአሂራህንም ያጠፋብሀል.......... እያልኩ ስመክረዉ ከመሀል ስልክ ተደዉሎለት ወጣ። በርግጠኝነት ጓደኞቹ ናቸዉ ስልክ የደወሉለት...ከጓደኞቹ መራቅ አለበት።በምክር ብቻ የሚስተካከል አይመስለኝም ምናልባትም ሊስተካከል የሚችል ከጓደኞቹ ሲርቅ ይሆናል በማለት አሰብኩ። ግን እንዴት ከነሱ ላርቀዉ እንደምችል አላዉቅም።


አሁንም ሙባረክን አግኝቸ እንዴት ከጓደኞቹ ላርቀዉ እንደምችል ብዙ የመፍትሄ ሀሳባችን ነገረኝ። እኔም እሽ ብየ ልሄድ ስል"ፊርዳስ ብቻ አንች ጓደኛየን ከሱስ እንዲርቅ ተስፋ ሳትቆርጭ አግዥዉ። ደሞ እርግጠኛ ነኝ ሪድዋኔ ከሱስ ወቶ አየዋለሁ ኢንሻ አላህ። የዛኔ እኔም 2 ከበድ ያሉ ጥያቄዎች ይኖሩኛል ጥያቄየን ትቀበይዉ አትቀበይዉ አላዉቅም".... እያለ ሲያወራኝ ደነገጥኩና የምን ጥያቄ? አልኩት አይ ሪድዋኔን ከሱስ ነፃ ስታደርጊዉ እጠይቅሻለሁ። በማለት መልስ ሰጠኝ እኔ ግራ ገብቶኛል። አሁን ሪድዋን እንዲህ ከአንተ ጋር ተቀምጨ ቢያየኝ ይናደዳል። የምር አግዘዋለሁ ብየ የባሰ ሱስ ዉስጥ እንዲገባ እያደረጉት ነዉ። መሄድ አለብኝ በቃ ቻዉ ብየ ወደቤቴ እየሄድኩኝ ሪድዋንን ምንገድ ላይ አገኘሁት።

እኔም ከሱ ጋር ለመቆየት አሪፍ አጋጣሚ ነዉ ብየ እያሰብኩ "ወዴት እየሄድሽ ነዉ"ብሎ ጠየቀኝ በርግጥ ወደ ቤቴ እየሄድኩ ነበር ግን የሆነ መፅሀፍ ፈልጌ አጣሁት አታፋልገኝም? አልኩት እሱም ፈገግ ብሎ ምን ስራ አለኝ አፋልግሻለሁ ነይ እንሂድ አለኝ። ቆይ እኔ አብሬህ የምሄድ አፍህ ዉስጥ ያለዉን ሲጋራ አዉጥተህ ጣለዉና አብረን እንሂድ አልኩት። እሱም ምንም ሳያቅማማ አዉጥቶ ጣለዉና አብረን መፅሀፍ ፍለጋ በየሱቁ ገብተን የተወሰኑ ስለሱስ አስከፊነትና ስለኢስላም የተፃፉ መስሀፍትን ገዝተን ስንወጣ ሪድዋን ተደዉሎለት መጠሁ ጠብቂኝ ብሎኝ ጥልኝ ሄደ እኔም እዘዉ እሱቁ አካባቢ ቁሜ እየጠበኩት ሁለት ወጣቶች በአትኩረት እየተመለከቱኝ "አይ! ይሄ ገንዘብ የማያደርገዉ የለ" በማለት በአሽሙር ይናገሩ ጀመር

Part 2⃣4⃣
ይቀጥላል
@Islam_and_Science
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ሀያ አራት ➋➍

አይ! ይሄ ገንዘብ የማያደርገዉ የለ" በማለት በአሽሙር ይነገሩ ጀመር እኔም ምን ለማለት ነዉ ብየ ጠየኳቸዉ "ባክሽ ያልገባሽ አትምሰይ! ከዚህ እብድ ጋር የሆንሽ ሀብታም ስለሆነ እንጂ ወደሽዉ አይደለም"እይዉስኪ ፀጉሩን ልብሱንም ተመልከች!.... እያሉ መሳቅ ጀመሩ።

እሪድዋንም ጓደኞቹ ስልክ ደዉለዉለት ሊያናግር ስለሄደ እንጂ እንደዚህ ያሉኝ ቢሰማ ኖሮ ልደባደብ ማለቱ አይቀርም ነበር።ወይም እንዲህ አይነት ስድቦችን ለምዷቸዉ ይሆናል..... ብቻ አልሀምዱሊላህ እንኳን አልሰማ እያልኩ ጓደኞቹን አናግሮ መጣ። እኔም የገዛነዉን መፅሀፍ ይዘን ቶሎ እንሂድ እነማ ይጨነቃሉ አሉኩት " እሽ"ልሸኝሽ ብሎኝ አብረን እየሄድን እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅም መቸም እንቢ እንደማትለኝ ተስፋ አደርጋለሁ። "የፈለግሽዉን ጠይቂኝ ወላሂ አንች ጠይቀሽም እንቢ አልልምሽም" አለኝ እኔም ሪድዋን የገዛነዉን መፅሀፍ አንተም እኔም እናንብበዉና ቶሎ የጨረሰ አንዱን የፈለገዉን መቅጣት ወይም የፈለገዉን መጠየቅ ይችላል አትስማማም?"ማለት"አለኝ ግልፅ የሆነለት አልመሰለኝም እይዉልክ ሪድዋን አሁን የገዛናቸዉ መፅሀፎችን አንተም እኔም እናነባቸዋለን። ከዛ ቶሎ አንብቦ የጨረሰ ቶሎ አንብቦ ያልጨረሰዉን የፈለገዉን ይቀጣል ወይም ይጠይቃል። ሲቀጥል ሌላ መፅሀፍ ደግሞ እንገዛለን አሁንም በዛዉ መልክ አሸናፊና ተሸናፊ እየሆንን እንቀጥላለን ትስማማለህ?"ግንኮ ፊርዶስ እኔ ቀን አይመቸኝም ከጓደኞቸ ጋር ፕሮግራም አለኝ" በቃ እሽ ማታ ማታ እናነባለን። አትስማም?"ከመቸ ጀምሮ "በማለት ጥያቄ አቀረበ ከዛሬ ማታ ይጀምራል እየተበባልን ሳላስበዉ እቤቴ ደረስኩ በቃ ቻዉ መልካም ንባብ ብየዉ ተለያየን።


ነግቶ እስራ ባታ ገና ከመግባቴ ፈገግ ብሎ አሰላሙ አለይኩም ፊርዶስ ጨረስኩ" አለኝ። ዉአለይኩም እሰላም ስንት ሰአት ጨረስክ በማለት ጠየኩት "ስድስት(6) ሰአት" አይ! ተቀድምሀል እኔ 4 ሰአት ነዉ የጨረስኩ ስለዉ በቃ እሽ ምንድን ነዉ ቅጣቴ? ብሎ ጠየቀኝ በመጀመሪያ አለባበስህ ኢስላም የተከተለ ይሁን ፀጉርህንም አታፍተልትለዉ አሳጥረዉ ይሄ የመጀመሪያዉ ቅጣትህ ነዉ መቸም አልተመቸኝም ቅጣቱ ይቀየር ማለት የለም "ግን ፊርዶስ" በማለት ትንሽ ከአቅማማ ቡኋላ ቆይ እኔ የዛሬዉን መፅሀፍ ቶሎ ጨርሸ ምን እንደምቀጣሽ ታያለሽ! አለኝ።


... ችግር የለዉም የፈለከዉን ትቀጠኛለህ አንተ ብቻ ቶሎ ለመጨረስ ያብቃህ.... ግን ሪድዋን ከአነበብከዉ ምን ተረዳህ በማለት ጠየኩት "በዋናነት ከመፅሀፉ የተረዳሁት ስለሱስ አስከፊነትና ስለሚያስከትለዉ መዘዝ" በማለት መልስ ሰጠኝ። ሪድዋን ግን ከእንግዲህ ቡኋላ አታጨስም አትቅምም አይደል መቸም የሚያስከትለዉን ጉዳት እያወቅክ ከእንግዲህ ቡኋላ ወደ ሱስ ዉስጥ አትገባም ። "አይ ቀደምምኮ ስለሱስ አስከፊነት ሳላዉቅ ቀርቸ አይለም ሱስ ዉስጥ የገባሁት በደንብ አዉቅ ነበር ግን በቃ ጓደኛየ ሲሞት በንዴት ጀመርኩ...አሁን ላይ ከሱስ ርቄ መኖር አልችልም ያመኛል ብዙ ጊዜ አባየ እያለቀሰ ሲለምነኝ ልተወዉ እልና አልችም ደሞ እኔ ብቻ አይደለሁም ሱስ ዉስጥ ያለሁ ከኔጋር ሁለት ጓደኞቸም አብረዉኝ አሉ። በአላህ ወሬ እንቀይር እና የዛሬዉ የመወዳደሪያ መፅሀፍ ርዕሱምን ይሁን? እያለ ወሬ ቀይሮ ማዉራት ጀመረ እኔም ስለ ኢስላም ምንነት በደንብ የሚያብራራ መፅሀፍ መርጨለት ተስማምቶ ጓደኞቸ ላይ ልሄድ ነዉ ቻዉ ብሎኝ ሄደ።
አሁን ላይ የተገነዘብኩት ቢኖር ከጓደኞቹ መራቅ እንዳለበት ነዉ ምናልባት መራቅ ከቻለ ቀስ በቀስ ከሱስ ነፃ እንደሚሆን አምናለሁ። እያልኩ ሳስብ አባቱ እቢሮየ መጣ። እኔም እስካሁን ያለዉን ነገር አስረዳሁት ወላሂ ልጀ ትልቅ ለዉጥ ነዉ መፅሀፍ ገልፆ የማያዉቀዉ ልጂ ትናንትና ማታ እስከ ስድስት ሰአት ሲያነብ ተገርሜ ነዉ አሁን ሪድዋኔ ሲወጣ ጠብቄ አንች ላይ የመጣሁ። በርግጥ የተወሰኑ ለዉጦች እየታዩበት ነዉ። አሁን ኢንሻአላህ አላባበሱንና ፀጉሩን እንዲያስተላክል ነግሬዉ ተስማምቷል። ግን አቶ ሙሳ እሪድዋን ከጓደኞቹ ከራቀ እንደሚስተካከል አምናለሁ። " እሱማ ልክ ነሽ ግን እንዴት ማራቅ አለብን?"በማለት ጥያቄ አቀረልኝ


ሲመስለኝ ቀኑን ሙሉ ቪዚ የሚያደርግ ስራ እንዲሰራ ማድረግ መቸም ማታ ማታ የመፅሀፍ ዉድድር ስላለ ከጓደኞቹ ጋር መገናኘት አይችልም ቀን ግን የሚሰራዉ ስራ ስለማይኖር መገናኘቱ አይቀርም በማለት ሀሳቤን ነገርኩት።

አቶ ሙሳም ቀኑን ሙሉ ቪዚ የሚያደርግ ስራ እያለ ሲያስብ ቆይቶ "ለምን ግን እጓደኛየጋ አይሰራም" አለ የምን ምን አይነት ስራ? በማለት ጠየኩት "እይዉልሽ ልጀ ጓደኛየ ባጃጂና የተለያዪ መኪናዎችን መገጣጠም ቋሚ ስራዉ ነዉ ብዙ ሰራተኞችም አሉት። ሰአቱም ቢሆን 2፡30 እስከ11፡30 ስለሆነ ይህን ስራ እሽ ብሎ ቢቀበል ወደ ከጓደኞቹ ጋር ለመገናኘት ስአት አያገኝም "።

ወላሂ ጥሩ ስራ ነዉ። ብለን ተስማማንና እጓደኛዉ ላይ ደዉሎ ስለልጁ ሁሉንም ያዉቅ ስለነበር እሱጋ እንዲሰራ ፈቀደለት።ግን ሪድዋን ስራዉን ይቀበለዉ ይሆን እያልን ስናስብ ሪድዋን መጣ ሁላችንም ያየነዉን ማመን አቃተን አባቱ ከተቀመጠበት ሮጦ አቀፈዉ የምር እሪድዋን መሆኑ አጠራጠረኝ እጠር ያለ ጀለብያ ለብሷል ፀጉሩንም ተስተካክሎል እንዴ!ጓደኞቸጋ ልሄድ ነዉ አልነበር ያልከኝ? በማለት ጠየኩት "አወ ወደ ጓደኞቸ እየሄድኩ እያለ ብዙ ጀለብያ የለበሱ ወጣቶችን አየሁ እኔም ያንች ቅጣት ትዝ አለኝና ለምን ጀለብያ ለብሸ ፀጉሬን ተስተካክየ ሰርፕራይዝ አላረጋቸዉም ብየ አሰብኩ ወዲያዉ ሙባረክን ላይ ደዉየ ሳማክረዉ ጥሩ ሀሳብ ነዉ ብሎ ጀለብያዉን ሰጠኝ ግን አሁን ላወልቀዉ ነዉ ይጨንቃል" አለን።

አባቱም ወላሂ ልጀ እንዴት እንዳማረብክ አታዉልቀዉ ደሞኮ ዛሬ ጁመአ ነዉ። ቢያንስ ስገድበት "እሽ ግን ሰግጀ እስከማበቃ ብቻ ከዛ ቡኋላ አወልቀዋለሁ"እሽ ተበብለዉ ተሰሳቁ። ደስ ሲሉ እያልኩ ሳስብ አቶ ሙሳ "እንግዲህ ልጀ ፊርዶስን ከዚህ መስሪያ ቤት ላሰናብታት ነዉ" አለ እኔም በጣም ደነገጥኩ ሪድዋንም እእእእ..... ምንድን ነዉ ምታወራ ቆይ እሽ ምን አጠፋች.... እኔ አለባበሴንና ፀጉሬ እንዳስተካክል ማድረጓ ነዉስ ምን? እያለ አባቱ ላይ አፈጠጠበት።

አባቱም ኧረ ልጀ ተረጋጋ እንደሱ አይደለም እንደዉም በተቃራኒዉ በጣም አመስግኛታለሁ። ግን ልጀ ኢብራሂም ወዳጀን አታዉቀዉም?"የትኛዉ የመኪና መገጣጠሚያ ያለዉ ሀብታሙ ሰዉየ?" አወ እሱ ሰሞኑን እናቱን ጥየቃ ወደ ክፍለ ሀገር ስለሚሄድ ሰራተኞችን የሚቆጣጠርና አብሮ ከሰራተኞች ጋር የሚሰራ 2 ታማኝ ሰራተኞች እፈልጋለሁ ብሎ ዛሬ ደዉሎልኝ ነበር። ለዚህ ደሞ ፊርዶስ ጓበዝ ናት።ደግሞም የፊርዶስን ቦታ ተክቶ ሙባረክ ስለሚሰራ ፊርዶስ እዛ ሰራተኞችን ልትቆጣጠር ትሄዳለች። ስለዚህ አንድ እሷ ትሆናለች

የሙባረክን ቦታ ተክተህ ከኔጋ መስራት ከቻልክ ደግሞ ሙባረክ አብሯት ይሄዳል። ምን ይመስልሀል? እያለ ወደ ልጁ ዞረ። ሪድዋንም አይ! እኔ አብሬት እሄዳለሁ ሙባረክ አንተን ያግዝህ። በማለት መልስ ሰጠዉ። የምር አቶ ሙሳ በጣም ብልህ አባት ነዉ።

ግን እኔ ትንሽ ተናድጀበታለሁ ቢያንስ ፍቃደኝነቴን ሳያረጋግጥ ከልጁ ጋር ሊልከኝ ነዉ እያልኩ ሳስብ "ምነዉ ፊርዶስ የደበረሽ ትመስያለሽ"
part 2⃣5⃣
ይቀጥላል
@Islam_and_Science
ኦርቱግሩል በአለም ላይ 3ቢሊየን በላይ ተመልካች ያገኘ ፊልም...የሌላ ሀይማኖት ተመልካቹ አንድ አግራሞት የፈጠረባቸው ነገር ቢኖር
☞" ኢስላም ማለት ይህ ነው ወይ?
☞የሽብር ሀይማኖት አራጅ እና ገዳይ ሀይማኖት እየተባለ በየሚዲያው ነጋ ጠባ የሚደሰኮርልን ኢስላም እንደዚህ አይነት የፍትህ እና የእዝነት ሀይማኖት ነው ወይ ? " የሚል ነበር!!

ይህ ፊልም ከብዙ ሚሊዮኖች ላይ የኢስላም ጥላቻን ገፏል! ቢሊዮኖችን ኢስላም የፍትህ የእዝነት የመከባበር እና የአንድነት ሀይማኖት መሆኑን አስተምሯል!!

🔰በታሪክ የዚህን ያክል ተመልካች ያገኘ ፊልም የለም! Game of Throne እንኳ Resurrection Ertuğrul ያገኘውን ያክል ተመልካች እና ተወዳጅነት ማግኘት አልቻለም!!
ይህ ታሪካዊ ፊልም ከ 40 ቋንቋዎች አካባቢ የተተረጎመ ሲሆን በሁሉም የአለማችን ሀገራት በሚባል መልኩ ቢሊዮን ተመልካቾችን ለማፍራት ችሏል። ከነዚህም ውስጥ
☞የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ
☞ የፓኪስኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ኻን እንዲሁም
☞የ ማሊዥያ ንጉሳዊያን ቤተሰቦችን ጨምሮ በርካታ ዝነኞች እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ይገኙበታል!!

🔰ይህ ፊልም አንድ ነገር አስተምሮናል
አሁን በአለማችን ለተስፋፋው ኢስላም ጠልነት (Islamophobia) ከምእራባዊያን እና ኢስላም ጠል ሚዲያዎች ዘመቻ በላይ የአኛ ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ መሆን እና እስልምናን በተገቢው እና ዘመኑ በሚጠይቀው መልኩ ለአለም ህዝብ አለማስተማራችን ያሳያል፡፡ እንድታዩት ጋበዝኳችሁ በጣም ትወዱታላችሁ


@Islam_and_Science
📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖
#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ሀያ አምስት ➋➎

ምነዉ ፊርዶስ የደበረሽ ትመስያለሽ" አለኝ ሪድዋን አይ እኔ አልደበረኝም አንተ የኔጋር ለመሄድ ተስማማህ? "
....አወ ተስማምቻለሁ በርግጥ ስራዉ ከባድ ነዉ ግን አብረን ስለምንሰራ አይዞሽ አይከብደንም" ግን ሪድዋን እዛ ስራ ቦታኮ ማጨስ፤ መቃም፤ ስአት ሳይደርስ ከስራ መዉጣት.... አይቻልም። "አዉቃለሁ ፊርዶስ ግን ለተወሰኑ ቀናቶች አይደል እዛ የምንቆየዉ? አይከብደኝም" በማለት መልስ ሰጠኝ። አባቱም የምትቆዩት ለተወሰነ ቀናት፣ ብቻ ላይሆን ይችላል ምናልባትም ሳምንታት፤ወራት፤ አመት.... ምን ያህል እንደምትቆዩ አላዉቅም ብቻ ጓደኛየ ከክፍለ ሀገር እስከሚመለስ ድረስ ትሰራላቹህ። አሀ ሪድዋን ከሱስ ሙሉ ለሙሉ መዉጣት እስከቻለ ድረስ ማለቱ ነዉ ቆይ እሽ በወራት ዉስጥ ከሱሱ መዉጣት ካልቻለ አመት ሙሉ እዛ መቆየታችን ነዉ እያልኩ ሳስብ "በሉ ጓደኛየ ነገ ስለሚሄድ ነገ ስራ ትጀምራላቹህ ተዘጋጁ"..ብሎን ሄደ። እኛም እሽ ብለን ለመሄድ ተስማማን።

ነገ አዲስ ስራ እንደምጀምር ለእማና ለአያቴ ነገርኳቸዉ እነሱም ተስማሙ። በመቀጠልም ስለ ሪድዋን ታሪክም አንድ በአንድ አጫወትኳቸዉ የምር አዘኑ ለሱ ብየ እንደሆነ አዲስ ስራ የምጀምር መናገር አቃተኝ ይቆጡኛል ብየ አሰብኩ ግን ከሱጋር ስሄድ ቢያዩኝ ወይም ሌላ ሰዉ ቢነግራቸዉ.... ብየ ፈራሁ እንደምንም ብየ ነገርኳቸዉ። እነሱም ማገዝ እንዳለብኝ አበረታቱኝ አሁን ጭንቀቴ ቀለለኝ።

እኔና እሪድዋን ዛሬ አዲስ ስራ ልንጀምር ነዉ። ተደዋዉለንም ተገናኘንና ወደ አዲሱ የስራ ቦታ ሄድን ዋዉ! በጣም ሰፊ ቦታ ነዉ በዛ ላይ ሰራተኞችን የሚያመላልሱበት የራሳቸዉ ሰርቪስም(መኪና) አላቸዉ።በር ላይም ዘበኛ አለ። እኛም ይህን እየተመለከትን ወደ ዉስጥ ገባን። ስንገባ በፈገግታ አንድ ወንድና አንድ ሴት ተቀበሉን ወድያዉም ተተዋወቅናቸዉ ሴቷ ሀናን ስትባል ወንዱ ደግሞ ኡስማን ይባላል ብቻ እንዲህ ስማቸዉን ነግረዉን እኛም ነግረናቸዉ የስራ ቦታዉን በደንብ አስጎበኙን። ማሻ አላህ በጣም ደስ ይላል ሁሉም ሰራተኞች በህብረት ይሰራል።

እንግዲህ እኛም ከዛሬ ጀምረን እዚህ መስራት እንጀምራለን። እኔ ግን ስለስራዉ ችሎታዉ የለኝም እኔ የማዉቅ የሂሳብ ስራዎችን ነዉ። ሪድዋን ግን በኢንጂነሪንግ ዘርፍ ስለነበር የተማረ ለሱ መኪናዎችን መገጣጠም ቀላል ነዉ ብቻ እኔም እለምደዉ ይሆናል። እያልኩ በመጀመሪያ የመገጣጠሚያ እቃወችን ስም ከዛ መኪነዎች እንዴት እንደሚገጣጠሙ፤ እንዴት በቀለም ተዉበዉ ለሽያጭ እንደሚቀርቡ በትኩረት መመልከት ጀመርኩ።

ስራዉ ትንሽ ከበድ ቢለንም እኔና እሪድዋን ጠንከር ብለን መስራት ጀመርን አንዳንዴ ሪድዋን በጣም እራሱን ያመዋል የዛኔ ንፋስ ልቀበልና መጣሁ ብሎ ከግቢ ይወጣል። ከትንሽ ቆይታ ቡኋላ ይመለሳል። ግን ንፋስ ሊቀበል ሳይሆን የሚወጣ ሊያጨስ እንደሆነ በደንብ አዉቃለሁ። ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ስከታተለዉ ነበር። እሱ ግን ሲጋራዉን ትቸዋለሁ እያለ ይዋሸኛል ደሞኳ እንደማያጨስ ቃል ገብቶልኝ ነበር። ግን በአንዴ ለመተዉ ከባድ ነዉ ቢያንስ ቀስ በቀስ ይተወዋል አሁን ለራሱ እዚህ ስራ ከጀመርን ጀምሮ ብዙ ለዉጦችን አይቸበታለሁ ቀደም ሁል ጊዜ ይቅማል፤ ያጨሳል አሁን ግን መቃሙን ትቶታል ማጨሱን ግን ሊተወዉ አልቻለም። እኔም ማጨሱን እንዲተወዉ ንፍስ ልቀበልና መጣሁ ሲል እንዲሄድ አልፈቅድለትም ነገር ግን በጣም ሲያመዉ ያሳዝነኝና ከሳምንት 2 ቀን ሂድ እለዋለሁ። በሳምንት 7 ቀን የሚያጨሰዉን ወደ 2 ቀን በመቀነስ ቀስ በቀስ እንዲተወዉ ማድረግ እንደምችል ሙባረክ በደንብ ነግሮኛል እኔም እንደነገረኝ እያደረኩ ነዉ። አንዳንዴ ጓደኞቹ ይደዉሉና ጫት ይዘህ ና ይሉታል። እኔም ምንድነዉ ያሉህ ብየ እጠይቀዋለሁ እዉነቱን ይነግረኛል ግን አንተ ሳትሄድ ጫቱን ላክላቸዉ እያልኩ ብዙ ጊዜ አስልኬዋለሁ። ጓደኞቹም ከዛን ጊዜ ጀምሮ ና ሳይሆን ጫት ላክልኝ ማለት ጀመሩ አየህ ሪድዋን! አንተን ፈፅሞ አይፈልጉህም እነሱ የሚፈልጉ ጫት እንድትገዛላቸዉ ብቻ ነዉ። ቆይ እሽ እነዚህ እዉነተኛ ጓደኛ ናቸዉ ወላሂ አይደሉም አንተ የጫት መቃሚያ ገንዘብ ባይኖርክ ዙረዉም አያዩህ ስለዉ.... ለማመን ቢከብደዉን በሂደት ግን እዉነቴን እንደሆነ ገብቶት ወደነሱ ሂዶም ጫት ልኮም አያዉቅም ስልክም ቢሆን አያነሳላቸዉም አላሀምዱሊላህ የመጀመሪያዉ እቅዴ ተሳካ።


በዛ ላይ እዚህ የሚሰሩ ሰራተኞች በጣም ጥሩዎች ናቸዉ ሌላጓደኛ አያስፈልግህም። ሪድዋንም እሽ ብሎ የሚዉል እዚህ ከሚሰሩ ወንዶች ጋር ነዉ። ማሻ አላህ ብዙዎቹ ሀፊዝ ናቸዉ።ብዙ ጊዜ ስራ ስንጨርስ ሴቶች ለብቻ ወንዶች በልብቻ እንሰበሰብና የተለያዩ ስለዲናችን፤ ስለሂወታችን፤ አንዳንዴም ስለ ትዳር እንነጋገራለን። በእኛ በሴቶች ጀመአ በተለይ ሀናን ደስ የሚል ፀባይ ያላት ልጂ ናት እኔና እሷም ቀስ በቀስ ጥሩ ጓደኞች ሁነናል ለሪድዋንንም ሀናንን
አስተዋዉቄዋለሁ። አንዳንዴ እሷም ትመክረዋለች እንግዲህ እንዲህ እንዲህ እያልን ስድስት(ወሮችን) አሳለፍን እሪድዋንም ከሳምንት አንዴ በጣም ሲያመዉ ያጨሳል።
እነማም እሪድዋንን እቤት ይዘሽዉ አትመጭም ወይ እያሉ እየጠየቁኝ ነዉ


እኔም ለሪድዋን እነማን ስላንተ ነግሬቸዉ መቸ ነዉ የምታስተዋውቂን እያሉኝ ነዉ እና እሁድ አይመችህም በማለት ጥያቄ አቀረብኩለት እሱም እሽ እመጣለሁ ብሎኝ ተለያየን።
የማይደርስ የለምና ዛሬ እሁድ ነዉ ሁላችንም .የሪድዋንን መምጣት እየተጠባበቅን እያለ ከድንገት ስልክ ተደወለልኝ። ሪድዋን ነበር የደወለ። እቤታችን እየደረሰ እንደሆነ ነገረኝና እኔም ወደ ዉጭ ወጥቸ እሱን መጠባበቅ ጀመርኩ። ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ ሪድዋን መጣ። ሰላም ብየዉ ወደቤት ይዤዉ ገባሁና እነማን አስተዋወኩት።

እነማም ተተዋዉቀዉት ምግብ በልቶ ሲጫወት ቆይቶ..... "አባየ ብቻዉን ስለሆነ መሄድ አለብኝ" ብሎ ተነሳ እነማም በቀጣይ ሳምንት እንደሚጠብቁት ነገረዉት "እሽ" ብሎ ሄደ።
በቃ ከዚህን ቀን ጀምሮ እሁድ እሁድ ሪድዋን እኛ ቤት ለእነማ የተለያዪ ስጦታዎችን ይዟላቸዉ ይመጣል።ሲጫወትም ቆይቶ ይሄዳል። ካስተዋወኳቸዉ ጊዜ ጀምሮ እነማም ከሪድዋን ጋር በደንብ እየተቀራረቡ መጥተዋል። በቃ እሱ ከመጣ የማይሰራ ምግብ የለም የማይወራ ወሬ የለም ቤታችንን እሁድ እሁድ ሪድዋን በሚያወራቸዉ ቀልዶች ሳቅ መድመቅ ጀምሯል። እነማም እሁድ ደርሶ ሪድዋን እስከሚመጣ ይናፍቃሉ ሲመጣም ይመክሩታል አይዞህ ይሉታል ብቻ እንደነትና ልጂ ሁነዋል።


እኔም አሁን ላይ ከሪድዋን ጋር በጣም ተቀራቤለሁ። የምር ሪድዋን እንደቀልድ እያረገ የሚያስቀን ቁም ነገር ያላቸዉ ቀልዶች እንዴት እንደሚያምሩ። አንዳንዴ ሪድዋን ግን ማን እየነገረህ ነዉ እንደዚህ አይነት ቀልዶችን? በማለት ጥያቄ አቀርብለታለሁ እሱም "ከመፀሀፎችና የተለያዩ ሰዎች ሲያወሩ የምሰማቸዉ ቀልዶች ናቸዉ።" በማለት ይመልስልኛል ደሞ የመፅሀፍ ዉድድራችንም ብዙ እንደጠቀመዉ በተደጋጋሚ ያጫዉተኛል። የምር አንዳንዴ ስለ ሪድዋን ሳስብ ከአንድ አመት በፊት እንደዛ እንደማልጠላዉ ሁሉ አሁን በተቃራኒዉ የደስታየ ምንጭ ሁኖ ከሱ መራቅ አልፈልግም።በርግጥ ቀደም የምጠላዉ በአለባበሱ እንጂ እንዲህ ቀርቤ አይቸዉ አልነበረም ብቻ ሰዉን በማየት ብቻ የሰዉን ማንነት ማወቅ እንደማንችል በደንብ አዉቄለሁ። ምክንያቱም አንዳንዶቹ ልብሳቸዉን አሳምረዉ ዉስጣቸዉ ግን የሚያስጠሉ ብዙ ሰዎችን አይቻለሁ።

ሰሞኑን ደግሞ ሪድዋን ካጨሰ 👇👇
አንድ ወር ሁኖታል። ደሞ አላመመዉም። በዛ ላይ ተንግዲህ ላያጨስ በአላህ ስም ቃል ገብቷልኛል። እኔም አላምን ብያለሁ።የምር በጣም ደስ ብሎኛል ሀናንም በጣም ደስ ብሏታል።ወይ ጉድ በስንት ሰዉ ልፋት በስተመጨረሻ ሪድዋን ማጨሱን ካቆመ ብዙ ወራትን አስቆጠረ። ለካ ተስፋ ካልቆረጥን የማይሳኩ የሚመስሉ ነገሮች ይሳካሉ ነገር ግን ትግስት ግድ ነዉ ደሞ በአንዴ ሳይሆን ቀስ በቀስ በሂደት እንደሚሳካ ጠንካራ አቋም ሊኖረን ይገባል። ብቻ በደስታ የመጣሁበትን አላማ ከአላህ ጋር አሳክቸ ወደ ቀልሞዉ ስራየ ስመለስ አቶ ሙሳ በደስታ ተቀበሉኝ። ልጃቸዉንም ሲያዩ ሲጋራ ማጨሱን አቁሞ ኢማነኛ ልጂ ሁኗል በርግጥ ማጨሱን እንዲያቆም ባግዘዉም ኢማነኛ ግን ያደረጉት የሚያነባቸዉ መፅሀፎችና በሚሰራበት ቦታ የነበሩ ሀፊዝ ጓደኞቹ ናቸዉ። ብቻ የአባቱን ደስታ በቃላት ለመግለፅ ይከብዳል...

....አቶ ሙሳ እኔን ከልብ አመሰግኖኝ ቁልፍ ሰጠኝ። እኔም የምን ቁልፍ ነዉ? ብየ ስጠይቀዉ"ባለፈዉ ትዝ ይለኛል ስለሂወትሽ ስትነግሪኝ በቤት ኪራይ እንደምትኖሩ አጫዉተሽኛል እና ይሄ ቁልፍ ሪድዋን ሲያገባ ብየ የሰረሁለት ቤት ቁልፍ ነዉ አሁን ላንች በስጦታ መልክ እሰጥሻለሁ በርግጥ እንደማይመጥንሽ አዉቃለሁ።ግን በአላህ ስጦታ አይናቅም ተቀበይ ብሎ ሰጠኝ።

እኔም አይቻልም አልቀበልም ብለዉም ሊሰማኝ አልቻለም። በስተመጨረሻ አመስግኘ ተቀበልኩት ያአላህ! ለኔ የዛሬዉ ቀን ልዩ ነበር አንደኛ ሪድዋን ተስተካከለ ሁለተኛ ከቤት ኪራይ ነፃ ወጣሁ። እያልኩኝ ሳስብ ሙባረክ መጣ


ሙባረክን በስልክ እንጂ በአካል ካገኘሁት ብዙ ጊዜ ሁኖኛል ብቻ ዛሬ እሱ እቢሮየ ድረስ መጦ "አሰላሙአለይኩም ፊርዶስ አለኝ"ሙአለይኩም አሰላም እንዴ ነህ ሙባረክ ስራስ እንዴት ነበር? እያልኩ መጠየቅ ጀመርኩ እሱም ጥሩ እንደሆነ ነገረኝ ደሞ በጓደኛዉ መቀየር በጣም ደስ ብሎት አመሰገኘኝ። በርግጥ የመቀየሩ ምንጭ እኔ ብቻ ሳልሆን ያንተሚናም ከፍተኛ ነበር እያልን ስናወራ..... ሙባረክ ትዝ ይልሻል ፊርዶስ ሪድዋን ከተስተካከለ ሁለት ጥያቄዎችን አጠይቅሻለሁ ትቀበይዉ አትቀበይዉ አላዉቅም ብየሽ ነበር" አለኝ

ምን አይነት ጥያቄ እንደሚጠይቀኝ ባላዉቅም አወ ትዝ ይለኛል እና ጥያቄዉ ምንድን ነዉ? በማለት ጥያቄየን ጀመርኩ ሙባረክም......



በአላህ ፍቃድ
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
የመጨረሻዉ ክፍል
🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

Join👇👇👇
@Islam_and_Science
@Islam_and_Science
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ የተከበራችሁ እና የተወደዳችሁ የቻናል ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ??
የደሀ ልጅ ፍቅር ታሪክ እንደጨረስኩ በግምት ከ8ወር በፊት አንድ እዉነተኛ ታሪክ ባለታሪኳ በስልክ እና በሪከርድ ነግራኝ ፅፌ አቀርባለሁ ብየ ቃል ገብቼ በተለያዩ ችግሮች እና አለመገጣጠም ምክንያት ይሄዉ ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ ይሄ ታሪክ 100% እዉነኛ ሲሆን የማይታመን ግን አሁን ላይ በጆሯችን በየቀኑ የምንሰማዉ ነገር ነዉ ምን ይሆን ታሪኩ የሚያተኩረዉ?? ስታነቡ ታገኙታላችሁ

📌📌 እዉነተኛ ታሪኩን ከመጀመራችን በፊት አንዳንድ ነገር ላሳዉቅ እፈልጋለሁ

☝️ይሄ እዉነተኛ ታሪክ ቢያንስ ከ1ሚሊየን ህዝብ እንዲደርስ ሰፊ ጥረት እያረኩ ነዉ በተለያዩ ቻናሎች ይነበባል..እናንተም ሼር በማድረግ እገዙኝ

☝️ቻናል ያላችሁ የኔን የታሪኩን ፀሀፊ አሚር ሰይድ ስም ሳታጠፉ እና አንድ ፊደል ሳጨምሩ ሳቀንሱ ማስተላለፍ ይቻላል፡፡

☝️ታሪኩ አራት ጊዜ edit የተደረገ ነዉ ..የባለታሪኮቹ ስም እና ቀጥታ ወደ ጅማ ተቀይሯል፡፡ እኔ ለእናንተ ቃል ገብቼ ከፃፍኩ ቡሀላ ባለታሪኳ ጋር ማብቂያ ላይ አንዱ ባለታሪኩ ጋር ያለዉ ፍቃደኛ አልሆነም በተቻለኝ አቅም አገሩን እና እሱ እንዳይባንን ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል...ኢንሻ አላህ 95% እንደማይቋረጥ ተስፋ አለኝ..

☝️ይሄ ታሪክ በመሀሉ በጣም ጥሩ ፍሬ ሀሳበች ይዟል፡፡ በታሪኩ ላይ 15% ያህል ታሪኩ ጋር ያተኮረ ጥሩ ምክሮች እና የነብዩ ሰዐወ ሀዲስ እና የሱሀቦች ተሞክሮ አስገብቸበታለሁ፡፡ እነዚህን ፁሁፎች ለማስገባት 4ወር ፈጅቶብኛል በተጨማሪ ከ6 የተለያዩ መፅሀፍት እያነበብኩ ለታሪኩ የሚመጥኑ ፁሁፎች ገብተዋል፡፡

☝️ታሪኩ በጅማ ከተማ ላይ ነዉ የተኮርኩት፡፡ በአዳማ በተለያዩ ሀገሮች ላደርገዉ ነበር ..የአባጅፋር ታሪክ ሳነብ ልቤን ነካኝ....በተጨማሪ ለጅማ ልጆች ያለኝን ክብር ይሄን የመጨረሻ ታሪኬን ለጅማ አርጊያለሁ....እኔ ከደሴ ከተማ ሁኜ ስፅፈዉ ጅማን ከተማ 70% ለተለያዩ ሰዎች በመደወል መረጃ ሰብስቢያለሁ.እንደ አጋጣሚ የሰፈር አገላለፅ ችግር ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ🙏

☝️ይሄ ታሪክ የሚቀርብበት ቋሚ ሰአት ላይኖር ይችላል ለምን admin በተለያዩ ምክንያት አሁን online ብዙ የሚገባ የለም ...እኔም ለዚህ ታሪክ ብየ ከተቻለ ከሱብሂ ቡሀላ ..ግን ካልሆነ ከቀኑ 3:00 እስከ 4:30 ባለዉ ሰአት ለመፓሰት አመቻቻለሁ..በዚህ ሰአት ካልተፓሰተ ያዉ አልተመቸኝም ማለት ነዉ ይሄን ለማቃለል ለመርዳት የፈለገ በአስተያየት መስጫ ቋሚ ሰአት ጊዜ ያለዉ ካለ ይንገረኝ admin አርጌዉ መፓሰት ይችላል፡፡ ማታ ማታ online ስለማልገባ ማታ ማታ ታሪኩ እንደማይፓሰት ላሳዉቃችሁ እፈልጋለሁ

☝️ይሄን ታሪክ እና እኔ ያዘጋጀሇቸዉ ታሪኮች በኦሮሞኛ ቋንቋ ለማስተርጎም እፈልጋለሁ....እናም በዚህ ቻናል ያላችሁ ኦሮመኛ ቋንቋ መፃፍ ማንበብ የምትችሉ በተለይ የመፃፍ ተስጥኦ ካላችሁ ..ታሪኮች ተፅእኖ ፈጣሪ ስለሚሆኑ በዚህ bot አናግሩኝ
👇👇👇
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot
T.me/Anws_bot T.me/Anws_bot

☝️ይህ እዉነተኛ ታሪክ ለሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ለራሱ በጣም ጠቃሚ ነዉ የሴት ልጅ በደል ግፍ የሚዳስስ ነዉ..ታሪኩም ላይ የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች እዉነተኛ ገፀ ባህሪ አለዉ

☝️በፁሁፍ ሳዘጋጅ የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች ያካተተ አድርጌ ነዉ፡፡ የሚገርማችሁ እኔ በልጅነቴ ብዙ ዘመዶቼ ክርስቲያን ናቸዉ እንዴት እኛ ሙስሊም ልንሆን ቻልን? ስፈጠር ኢስላምን ስለቀበልኩ ነዉ ማለት ነዉ ወይስ የቤተሰብን ሀይማኖት ስለሆነ ነዉ እንዴ? ብየ ደሴ ከተማ የሚገኙ ቤተክርስቲያን እና ሰንበት ትምህርት ቤት ሁለት አመት ያህል ጓደኞቼ ዘመዶቼ ጋር እየሄድኩ ጥናት አድርጌያለሁ...ስለሆነም እኛም የነሱን ብናዉቅ እነሱም የኛን ቢያቁ ጠቃሚ ነዉ ብየ አስባለሁ

☝️ይህ ታሪክ አፃፃፉ ግዴታ ከልጅነት ጀምሮ የገጠማት ወጥመድ ስለሆነ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ያለፈባት ዉጣ ዉረድ እስከ ኮሌጅ ድረስ ያተኮረ ነዉ፡፡ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች ብዙ ጊዜ የምወዱት የፍቅር ታሪክ መሰለኝ😉 ከ15 part ጀምሮ ያለዉ በዛ ላይ ያተኮረ ነዉ፡፡

☝️አንድ ነገር ላሳዉቃችሁ ይሄን ታሪክ ለማይረጋጋ ትዕግስት የሌለዉ እንዳይጀምር👌ታሪኩ ሰፊ ነዉ
☞የልጅነት በደል
☞የሴት ጭቆና
☞school life
☞የልጅነተ ፍቅር
☞ጥሩና መጥፎ ጓደኛ
☞መጥፎ ቤተሰብ ጫና
☞የትምህርት ቤት መጥፎ ጎኖች
☞የትምህርት ቤት ጥሩ ጎኖች
☞የመድረሳ መጥፎና ጥሩ ጎኖች
☞የትዳር process
☞ለትዳር የሚሆኑ የማይሆኑ ተስፋዎች
☞የኮሌጅ ላይፍ
☞ ስለሀይማኖት
ወ.ዘ.ተ በቃላት ለመግለፅ ይከብዳል ..ስታነቡት እናንተዉ ታዩታላችሁ

ዉድና የተከበራችሁ ቤተሰቦች በእኔ አሚር ሰይድ የተዘጋጀዉ
😔😢 #የሆድ_ዉስጥ_የፉም_እሳት🔥🔥
በእለተ #ጁምአ እንጀምራለን መልካም ንባብ

ከእናንተ የሚጠበቀዉ ለሶስት ሰዉ ሼር ማድረግ ብቻ ነዉ በተለይ የጅማ የአጋሮ ልጆች ሼር የማድረግ ግዴታ አለባችሁ👇👇
           `·. www.tg-me.com/Islam_and_Science
www.tg-me.com/Islam_and_Science
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ ..የተከበራችሁ የተወደዳችሁ የቻናል ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ

በቃላችን መሰረት ዛሬ ጁምአ ታሪኩን እንጀምራል..ይሄ እዉነተኛ ታሪክ አስተማሪ ስለሆነ ሁሉም ሰዉ ሊያነበዉ ይገባላልና ሼር ማድረግ እንዳረሱ..በተለይ ደግሞ የጅማ የአጋሮ ልጆች ሼር ማድረግ ግዴታም ጭምር ነዉ👌 ለምን ብትሉ ታሪኩ ወደ ጅማ ስቂየር በጣም ጊዜ እና ድካም ስላተርፍኩ ነዉ..ይሄን የድካም ዉጤት የምትክሱኝ ሼር በማድረግ ብቻ ነዉ፡፡

ሼር ማድረግ ቅንነት ነዉ መልካም ንባብ ተመኘሁ🙏
🔺አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ🔺
 
🎖የታሪኩ ርዕስ
😔😢
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት🔥🔥
      #ክፍል ☞ አንድ 1⃣

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ

በ08/12/2012 ተጀመረ

በሰዎች ዉሳኔና ፍላጎት ምኞት እና ጉጉት ብቻ ተፈፃሚ የሚሆን ነገር የለም የአሏህ ፍቃድ እስካልታከለበት ድረስ.. አንዳንዴ በሰዉ በዘመድ ተከበህ ሰዉ ይናፍቃል. እዉነት ነዉ በአለም ላይ በቢሊየን የሚሆን ህዝብ እያለ የዉስጡን የሆዱን የታፈነ ነበልባል አንድ ሰዉ ላይረዳህ ይችላል...የዚህን ጊዜ ብቸኝነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት ይቻላል ፡፡

ዉሀ ላይ ሁኜ ዉሀ ይጠማኛል
እሰዉ ጋር ሁኜ ሰዉ ይናፍቀኛል
የያዘኝ በሽታ ወንድም ያሰኘኛል
አንድ መንዙማ ላይ የሰማሁት ነዉ . እዉነት ነዉ ዉሀ ጠምቶህ ጠጥተሀዉ ሆድህ ቢገባም ዉሀዉ ጥምህን የማይቆርጥ ከሆነ
በሰዉ መሀል ተከበህ ሰዉ ሲያስፈልግህ ሰዉ ግን አንተን ለመረዳት ሳይፈልግ በአንተ ላይ የሚሳለቅ ከሆነ ሰዉ መሀል ተከበህ ጥቅሙ የሚሆነዉ የሰዉ ቆጠራ ጊዜ አብሮ ተቆጥሮ አለ ይሄን ያህል አለ ለማለት ያህል ካልሆነ በቀር .

የተፈጠርንበት ማንነት ዲነል ኢስላም በወንድምነት በእህትነት አስተሳስሮን ነገር ግን ዛሬ ጓደኛ ነገ ደግሞ ጥላት እየሆነ የመጣ ይመስላል. ታዳ መቼ ይሆን ለሰዉ እዉነተኛ ሰዉ የምንሆነዉ???..ለሰዉ ልጅ በሽታዉም ህመሙም ያዉ አላህ እንደቀደረዉ ሁኖ ታንቆም መርዝ ጠጥቶም የሚሞተዉ ያዉ በሰዉ ምክንያት ነዉ ..ምክንያቱም ይህን ዉሳኔ የወሰነዉ መቼም ሰዉ ነዉ እና ጥፋት አይቀርም..አጥፍቶ መሄጃ ሲያጣ በአማከረዉ ሰዉ ወይም ለልብ ጓደኛዉ የልቡን ነግሮት ግን የተናገረዉን ከጆሮ ባልዘለለ ከልቡ ሳያስቀምጠዉ ሲቀር ያኔ ከሰዉ በላይ አላህ ይጠብቀን ሸይጧን ይቀርበዋል ይሳሳታል ይታነቃል ወይ መርዝ ይጠጣል ..ይሄን ዉሳኔ የሚወስነዉ ዱንያን መሮት እንጂ ተመቸቶኝ ብሎ ራሱን የሚያጠፋ የለምና...

በጥናት ዉጤት ስናየዉ አሜሪካ በአንድ አመትብቻ 25,000 ሰዎች ራሳቸዉን ያጠፋሉ ቻይና በየዓመቱ 30,000 ሰዉ ራሱን ያጠፋል በአለም ላይ በየ20 ሰከንዱ ሰዎች ራሳቸዉን ያጠፋሉ ይህ ማለት በአለም ላይ ወደ በአንድ አመት ሁለት ሚሊየን ህዝብ እራሳቸዉን ያጠፋሉ ማለት ነዉ፡፡

ሁሉም ሰዉ ሊያወቀዉ የሚገባ የማይካድ ሀቅ ደስታ በዲነል ኢስላም አላህ ጋር ባለን ግንኙነት እንደሚወሰን መገንዘብ አለብን..የቁርአንን መመሪያ መከተል ለዚህ ያለእድሜዉ እራሱን ለሚያጠፋዉ እና በሂወት እያለ ሒወት እንደ ዥዋ ዥዌ ጨዋታ ለሆነችበት ቁርአን መፍትሄ እንደሆነ እርግጥ ነዉ . አሁን ጊዜ ላይ ያለነዉ የሁላችንም ጥፋት የቁርአን መመሪያ እኛ መከተሉን ትተን በእኛ መስመር እንዲከተለን መፈለጋችን ነዉ፡፡

ታዳ ለዚህ ሁላ ራሱን ላጠፋዉ ተጠያቂዉ ሰዉ አይደለም ብላችሁ ታስባላችሁ??? ሰዉ ከሚሳሳትባቸዉ ምክንያቶች ዋናዉ እና አንደኛዉ ባለፈዉ ጊዜ ምን ምን ነገሮች ነበሩ??ዛሬ ምን ይደረጋል?ነገስ ምን ይመጣ ይሆን? የሚሉትን ጥያቄዎች ሳያስተዉሉ ሁሉንም ነገር ለዛሬ ብቻ ሲሰጡ ነዉ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ደስታ የሚገኘዉ በብር ብቻ ነዉ ብለዉ የሚያምኑ አሉ ስህተት ነዉ ደስታ የሚገኘዉ በዲነል ኢስላም ነዉ .ዲነል ኢስላምን አዉቆ ያልሰራበት ደስታ በጭራሽ አያገኝም..ለምሳሌ አሜሪካንን እንዉሰድ የአለም ኢኮኖሚ 50% በአሜሪካ እጅ ይገኛል ነገር ግን በአለም ላይ በደስታ የሚኖሩ አገሮች ቁጥር ተርታ ስትሰለፍ 116 ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡በተዘዋዋሪ ደግሞ በአለም ላይ በደስታ የሚኖሩ ሀገሮች የመሪዎችን ደረጃ የያዙት ሙስሊም ሀገራት ሲሆኑ.ቁጥር 1 ናይጀሪያ ናት ..ናይጀሪያ እንደምናዉቀዉ የሙስሊም ሀገር ናት በኢኮኖሚዋ ዝቅተኛ ብትሆንም ግን የመጀመሪያ አላማቸዉ አላህን ማስደሰት ስለሆነ በአላቸዉ ተብቃቅተዉ በደስታ ይኖራሉ

የሰዉ ልጅ ብር ደስተኛ እንደማያረግ የጃፓኑን ትልቅ ድልድይ በቀን ከ300 መኪና በላይ የሚተላለፍበትን የገነባዉ ኢንጅነር በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ገቢ ያገኘ ቢሆንም ተመርቆ አገልግሎት በሚሰጥበት ቀን በትንሽ ቁራጭ ወረቀት ኑዛዜ አስቀምጦ ራሱን ከድልድይ ላይ በመጣል ራሱን አጥፍቷል...በኑዛዛዉ እንዳስቀመጠዉ """"እኔ የገንዘብ ችግር አላጋጠመኝም ደስታ በማጣቴ ብቻ ከዚህ አለም ለመሰናበት ፈልጊያለሁ"""" ነበር ያለዉ ፡፡

በአለም ላይ የሰዉ ልጅ ራሱን ለመቀየር 24ቢሊዮን ዶላር/ ሴቶች ለኮስሞቲክስ 18ቢሊዮን ዶላር /ፀጉርን ለመንከባከብ 38ቢሊየን ዶላር /ለሽቶ ደግሞ 15ቢሊዮን ዶላር በአመት ያወጣሉ... ታዳ ሰጥቶን ስጡ ለተባልነዉ ዱንያ የአላህ ወዴታን ለማግኘት ስንት አዉጥተናል?? ለተቸገረ ሰዉ ስንቶቻችን የችግሩ መፍትሄ ሁነናል??ስንቶቻችን ነን ደሀ እና ሀብታምን ሳንለያይ በአንድ አይን የምናየዉ???
ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ አንድ ሰዉ ጀሀነም እሳት ዉስጥ ለመግባት ሙስሊም ወንድሙን በዝቅተኛ አይን ማየቱ በቂ ነዉ ብለዋል..እስኪ ሆድ ይፍጀዉ

ይሄ ታሪክ ስለ ሁላችንም የሰዉ ማንት ያተኮረ ሲሆን እስኪ ሳይረፍድ ወደ ታሪኩ እንግባ ..ይሄ እዉነኛ ታሪክ እኔ ፀሀፊዉ ከደሴ ከተማ ሁኜ የተፃፈ ሲሆን የታሪኩ ገፀ ባህዉ ወደ ጅማ ከተማ ተቀይሯል..
    ቅድሚያ መተዋወቅ ይቀድማል እንተዋወቅ የእናንተን ባለቅም የእኔ ስም ነዋል እባላለሁ አሁን ላይ የኔ እድሜ አስራ ዘጠኝ ሲሆን ፡፡ እኔ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ ከእኔ በታች በሶስት አመት የምበልጠዉ አንድ ታናሽ ወንድም እና በጣም ታናሽ እህት አለችኝ..በጠቅላላ ለቤተሰቦቻችን ሶስት ልጆች ነን፡፡
ተወልጄ ያደኩት የፍቅር የመከባበር ሀገር በሆነችዉ የአባጅፋር ሀገር ጅማ ከተማ በአጂፕ ሰፈር አዲሱ ገቢዎች ግምሩክ አካባቢ ነዉ፡፡

ትንሽ ስለጅማ አንዳንድ ነገር ልበላችሁ....ጅማ በምዕራብ ኢትዮጵያ ካሉት ከተሞች በስፋት የምትታወቅ ከተማ ናት። ጅማ በኦሮሚያ ክልል ስትገኝ የቀድሞው ከፋ ክፍለ ሀገር ዋና ከተማ ሆና አገልግላለች። የአየር ፀባዯ ወይና ደጋ ስለሆነ ለኑሮም በጣም ምቹ ናት፡፡


” ጅማ በታላቁ ንጉሷ አባጅፋር፣ በፍቅር ከተማነቷ እንዲሁም በቡና ምርቷ የምትታወቅ የጥንት ከተማ ናት...
ጅማ ሲነሳ በዋናነት ሶስት ነገሮች አብረው ይነሳሉ፡፡ አንደኛው ጅማ ሲነሳ አብሮ የሚነሳው ቡና ነው፡፡ ጅማ የ ቡና በስፋት የሚመረትበት ከተማ ናት ፡፡ አብዛኛው ወረዳ ቡና በብዛት
ያመርታል፡፡ የህዝቡም ህይወት ቡና ላይ
የተመሰረተ ነው፡፡ ሁለተኛው ጅማ ሲነሳ
የሚነሳው ፍቅር ነው፡፡ ጅማ የፍቅር አገር ነው::
የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች አብረው በፍቅርና
በመተሳሰብ የሚኖሩባት ከተማ ብትኖር ጅማ
ናት፡፡
ሶስተኛዉ ደግሞ ጂማ ሲነሳ አባ ጂፋር አብረዉ ይነሳሉ...አባ ጅፋር ከሌላው የኢትዮጵያ
ንጉሶች የሚለዩበት ብዙ ነገር እያላቸው ብዙ
ያልተፃፈላቸውና ያልተነገረላቸው ንጉስ ናቸው፡፡
ስድስት ሚስቶችን ከተለያየ ብሔር አግብተዋል፡፡
በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው የሚታወቁ
ሲሆኑ በንግስና ዘመናቸው አንድም ጊዜ
ለጦርነት ያልተጋበዙ ንጉስ ናቸው፡፡

እንግዲህ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም
ደረጃ የሀገሬ ሰው ሳዑዲ ሲሄድ የሚያርፍበት
ቤት ልስራ ብለው ከዛሬ 152 ዓመት በፊት ቤት
የሰሩ የሚገርሙ ንጉስ ናቸወ፡፡ እስከ ዛሬም
ድረስ መካ መዲና የሄደ ማንኛውም
ኢትዮጵያዊ፤ እሳቸው በሰሩት በዚያ ቤት ውስጥ
ያርፋል፡፡ ከዚህም አልፎ ከተለያዩ የሩቅ ምስራቅ
አገራት ጋር ጥሩ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት
ነበራቸው::አባጅፋር በአጠቃላይ ለጅማና
ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጲያ ሙስሊሞች ትልቅ ዕሴት👇👇
2024/09/28 23:16:16
Back to Top
HTML Embed Code: