Forwarded from የምክንያታዊ ባለራዕዎች ስብስብ (RVC) (Ayinadis Tarekegn)

27/08/2017
🎶ሸብ እረብ አለች ምድር አሆሆ አለች ምድር፤
RVC ልጆች ስትሾም አሃሃ አለች ምድር🎶
ወዳጆች እንዴት ቆያችሁ ጠፋሁ አይደል? 😁
ዛሬ ቤታችን ከወትሮ ደመቅመቅ ብላለች። ሽርጉድ ወዲህ ወዲያ በዝቶባታል ምነው አትሉኝም? ዛሬ አዳዲሶቹን አመራሮች ይሾማሉና ነው ። እናላችሁ ይህች ቅዳሜ ሲመት ናትና ስለ መሪነት ተወያይተን፤ አመራሮችን
ተዋውቀን ተለያየን።
እኔም ታዲያ ምን፣ምን ሃሳቦች እንደተንሸራሸሩ አጠቃላይ ሲመቱን ላቃኛችሁ ወደድኩ።
መሪነት ምንድነው ብለን ጀመርን ከብዙ እጆች መሃል፦
" ሙሴ እስራኤላውያንን መንገድ እንዳመላከታቸው ከፊት ሆኖ መንገድ ማመላከት ነው "
"እረኛ መሆን ማለት ነው ከኋላ ሆኖ ሳይሆን ከፊት ሆኖ በር መክፈት ነው "
መልካም ተመሪነትስ ምንድነው ቢባል ?
"ለመሪዎቻችን ቀና መሆን ማለት ነው"እንዴት አላችሁ? ወዲህ ነው ነገሩ።
"ባህል አስተሳሰብ የህዝቡን መልክ የያዘ ነው። ክፉ የሆነ ህዝብ አለ። ምቀኛ አግላይ ከዛ ውስጥ የሚወጣ መሪ ጨካኝ ክፉ ይሆናል። "ስለዚህ መልካም ተመሪዎች ካልሆንን ጥሩ መሪ አናገኝም ነው ።ሃሳቡ መቼ በዚህ በቃና 🙂ሁሉ ሰው መሪ አይሆንም አሁን ዘመን አመጣሹ ትችላለህና ትችያለሽን መልካም ተመሪ እንዳንሆን ያደረግን ቢባል አዎን ነበር የብዙዎች መልስ።
ሁሉም አዛዥ / አለቃ /መሪ መሆን ይፈልጋል። ምክንያቱም መልካም ተመሪ መሆንን እንደ ምንዝር መሆን እንድንመለከተው ስላደረጉን...
"መሪዎች ይፈጠረሉ /ይወለዳሉ
በተፈጥሮ መሪ የሆኑ ልጆች ይወለዳሉ በቃ ህፃን ሆነው ህፃናትን ሰብስበው የሚያሳምፁ ከፍ ሲሉም ከኋላቸው ሰው የሚያስከትሉ ስለዚህ መሪነት ለሁሉም አይደለም። "
"መሰጠት ያስፈልገዋል "
በተቃራኒው ደግሞ መሪ እንዲሆን ከፈለግን የሆነን ሰው ማድረግ እንችላለን "
ወዲህ ወዲያ በሃሳብ ስንሸራሸር ወደ ማገባደዱ ደረስን።
እኔም የመጨረሻውን ሃሳብ ለእናንተ ልተው
አለቃ ወይስ መሪ ?
እንዲህ እንዲህ እያልን ውይይታችን ወደ ማገባደዱ ደረስን የነበሩትን አመራሮች አመስግነን፣ አዲሶቹን አደራ ጭምር ሰጥተን፣ዳቦ በጋራ ቆርሰን፣የጥበብ ስራዎችን አይተን ዳግም በቀጣይ ሳምንት ልንገናኝ ተቀጣጥረን ተለያየን።
ውብ ውሎ 🙏
📝 በማክዳ ጸጋዬ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ (2017)
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@RvcClub

👍4