13/08/07
"ልዩነታችን ሳይገድበን አንድ ላይ ተሰባስበን በዚህ መልኩ የትንሳዔ በአልን ስናከብር የአንድነታችን ማሳያ ነው።በመካከላችን ያለውን መልካም ግንኙነትም አጠንክረን እንቀጥላለን" የአቤኔዘር ሳፖርቲንግ ኤንድ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን ባለቤት አቶ አርጋው አየለ ።
የአቤነዜር ሳፖርቲንግ ኤንድ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን የትንሳዔ በአልን አስመልክቶ ወደ ቤተሰቦቻቸው መሄድ ካልቻሉ የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሚኒኬሽን ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ጋር በትላንትናው እለት በአሶሴሽኑ ማዕከል በጋራ አክብረዋል።
"ልዩነታችን ሳይገድበን አንድ ላይ ተሰባስበን በዚህ መልኩ የትንሳዔ በአልን ስናከብር የአንድነታችን ማሳያ ነው።በመካከላችን ያለውን መልካም ግንኙነትም አጠንክረን እንቀጥላለን" ያሉት የአቤኔዘር ሳፖርቲንግ ኤንድ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን ባለቤት አቶ አርጋው አየለ ግብዣችንን ተቀብላችሁ በአልን አንድ ላይ ለማሳለፍ በመገኘታችሁ እናመሰግናለን ብለዋል።
የአንድነት እንዲሁም የመተሳሰብ ስሜት በታየበት በዚህ የትንሳዔ በአል ዝግጅት የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል ሃላፊ አቶ እያዩ አለማየሁ እና የትምህርት ክፍሉ መምህር ዩናታን ዘብዲወስ የተገኙ ሲሆን ከአሶሴሽኑ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነትን የሚያሳይ ተግባር ነው ከዚህ በኋላም ያለንን መልካም ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።
አያይዘውም አሶሴሽኑ ለተማሪዎች ምሳሌ የሚሆን ስራ እየሰራ መሆኑን አንስተው ለአሶሴሽኑ ምስጋና አቅርበዋል።
በእለቱም የተለያየ ሃይማኖት ተከታይ ተማሪዎች ለየራሳቸው ማዕድ አዘጋጅተው በአሶሴሽኑ ከሚገኙ ቤተሰቦች ጋር በአሉን በድምቀት አስበውታል።
ተማሪዎቹም በበኩላቸው የትንሳዔ በአልን በዚህ መልኩ ማክበራቸው የቤተሰባዊነት ስሜት እንደፈጠረባቸው በማንሳት ለተደረገላቸው ግብዣ አመስግነው በዝግጅቱ አብሯቸው ሙሉ ቀን ላሳለፈው መምህር ዩናታን ዘብዲዎስ በትምህርት ክፍሉ ሃላፊ አቶ እያዩ አለማየሁ እጅ የምስጋና ስጦታ አበርክተዋል ።
ዘጋቢ፦ አይንአዲስ ታረቀኝ (የ4ተኛ አመት የጋዜጠኝነት እና ኮሚኒኬሽን ተማሪ)
እዉነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!
https://www.tg-me.com/HU_JCSA_Group
HU_JC SA!(2017

👍1👏1