Telegram Web Link
የምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ (RVC)


ታህሳስ 5 ቀን 2ዐ17 ዓ.ም.

በዛሬው እለት የምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ ክበብ (rvc) የበጎ አድራጎት ክፍል ወንዶገነት የሚገኘውን መና የህጻናት መርጃ ማዕከል ጉብኝት አድርጓል።

እውነትም መልካምነት ለራስ ነው !!!
ወደ መና መርጃ ማዕከል ሄደን ህፃናቱን መጎብኘት እና ከእህት ከወንድሞቻችን ጋር ደስ የሚል ጊዜ ማሳለፍ ምንኛ መታደል ነው።

ማዕከሉን ማየት እና ታሪኩን በመስማት ስለ ህጻናቶቹ ማወቅ ቆም ብለን ያለንበትን እንድነንፈትሽ ያደርጋል ።

በእነዚህ ልጆች ህይወት ውስጥ እስከዛሬ የኛ አስተዋጽኦ ምን ነበር ? ፦

 # በጎ የሆነ ?
 # በጎ ያልሆነ ? ወይስ
 # ገለልተኛ ነበርን?

ያለፈው አንዴ ስላለፈ ነገስ ከኛ ምን ይጠበቃል ብለን ከራሳችን እንድንመክር መንገድ ይሆነናል።

እነዚህን ልጆች ለማገዝና ከመና መርጃ ማዕከል ጋር የበጎ ስራ ተሳታፊ ለመሆን ከኛ የሚጠበቀው በጎ ፈቃዳችን ብቻ ነው።

ሁላችንም ብዙ ለሌሎች እንድንተርፍ የሚያግዝ ዕውቀት፣ ጉልበት፣ ችግር ፈች ሀሳብ እንዲሁም የተለያየ ሙያ ይዘናል። ስለዚህ ያሉንን የህይወት ስጦታዎች ለሌሎች በማጋራት ደስታችንን እጥፍ እናድርገው።

☑️ አድራሻችን Main Campus, Radio ጣቢያው ፊት ለፊት በሚገኘው
አዳራሽ።

🔘የቴሌግራም አድራሻዎቻችንን ላልተቀላቀላችሁ በታች ባለው ሊንክ መቀላቀል እንዳይረሳ።
👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/rvc_charity_team

ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ!!

#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹🇪🇹

@RvcClub
@RvcClub
1
2025/07/09 12:54:28
Back to Top
HTML Embed Code: