Telegram Web Link
Forwarded from Inclusiveness club HU main campus (Yohannes Moges)
አርብ የጀመርነው የRamp ስራ ነገም ስለሚቀጥል 2:00L.T በመምህራን ካሬ እንድትገኙ።
ማሳሰቢያ: አንድም አባል እንዲቀር አይፈቀድም!!
Hawassa University Students' Information Center pinned «አርብ የጀመርነው የRamp ስራ ነገም ስለሚቀጥል 2:00L.T በመምህራን ካሬ እንድትገኙ። ማሳሰቢያ: አንድም አባል እንዲቀር አይፈቀድም!!»
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚያሳትመው የአፍሪካ ኢኮኖሚክስ እና ቢዝነስ ሪሰርች ጆርናል በአፍሪካ ጆርናሎች ኦንላይን ድረ-ገጽ ላይ ተካቷል።

ዩኒቨርሲቲው የሚያሳትመው ጆርናል (African Journal of Economics and Business Research) በአፍሪካ ጆርናሎች ኦንላይን (AJOL) ድረ-ገጽ ላይ መካተት ችሏል።

ጆርናሉ በፋይናንስ፣ ቢዝነስ፣ ኢኮኖሚክስ እና ልማት መስኮች ላይ ትኩረት ያደረጉ የፖሊሲ እና ችግር ፈቺ ምርምሮች የሚቀርቡበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ ጆርናል በአፍሪካ ጆርናሎች ኦንላይን (AJOL) ድረ-ገጽ ላይ መካተቱ ተደራሽነቱንና ተነባቢነቱን የበለጠ እንደሚጨምረው ዩኒቨርሲቲው ግልጿል፡፡

👉https://www.tg-me.com/hugadssachannel
Forwarded from Inclusiveness club HU main campus (Ermias Worku)
በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ነባር ህንጻዎችን ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ለማድረግ የመወጣጫ (Ramp)  ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ተካሄደ።
**//**
ግንቦት 19/2016 ዓም
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተመሰረተው የ"Inclusiveness" ክበብ ከትምህርትና ስነ-ባህሪ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ነባር ህንጻዎችን ለአካል ጉዳተኞችና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ምቹ የማድረግ ስራን ግንቦት 16/2016 ዓ.ም አስጀምሯል።

በትምህርትና ስነ-ባህሪ ኮሌጅ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫና ማሻሻያ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አንተነህ ዋሲሁን በኮሌጁ ስር የሚገኘው የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ክፍል ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን እኩል ተጠቃሚ መሆን በሚችሉበት ዙሪያ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው ከሶስት አመት በፊት ይህንኑ ስራ በተደራጀ መልኩ ለመስራት እንዲቻል "Inclusiveness" የተሰኘ ክበብ በማቋቋም የትምህርት ከባቢውን ለአካል ጉዳተኞችና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች አመቺ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መርሃግብር መሆኑን ተናግረዋል።

የክበቡ መስራችና የበላይ ጠባቂ አቶ ጌታሁን ሰለሞን በበኩላቸው የአካል ጉዳት በማንኛውም ሰዓት ላይ በማንኛውም ሰው ላይ ሊከሰት የሚችል እንደመሆኑ ሁሉም ሰው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው አካታችነት በሁሉም አገልግሎቶች ላይ እንደዋና ግብአት ሊወሰድ ይገባል ብለዋል። የ "Inclusiveness" ክበብ በውስጡ ከ400 በላይ አባላት ያሉትና በፍጥነት ውጤታማ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ መሆኑን እና ይህንን ተሞክሮውን ለማስፋፋት ክበቡን በሀዋሳ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ማቋቋሙን ጨምረው ገልጸዋል።
Forwarded from Inclusiveness club HU main campus (Ermias Worku)
የ4ኛ አመት የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትግበራ ተማሪና የ"Inclusiveness" ክበብ ፕሬዚደንት ተማሪ ዮሐንስ ሞገስ የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች የተለያዩ የስነ-ልቦና ጫናዎች እንደሚገጥማቸውና ያንን ሁሉ በጥንካሬ የሚያልፉት ቢሆንም የህንጻዎችን አለመመቸት ተከትሎ የሚገጥማቸውን አካላዊ ተግዳሮቶች ህንጻዎቹን ለአጠቃቀም ምቹ በማድረግ ማስተካከል እንደሚገባ ተናግሯል። ተማሪ ዮሐንስ እንዳለው የመወጣጫ (Ramp) ግንባታውን በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች እያከናወኑት ቢሆንም ኮሌጁ በሁሉም አቅጣጫ እያደረገላቸው ስላለው ድጋፍና እርዳታ ምስጋናውን አቅርቧል።

በጎነት ለራስ ነው።
Inclusiveness Club

@inclusivness_club
Forwarded from Inclusiveness club HU main campus (Yohannes Moges)
የጀመርነው የRamp ስራ የመጨረሻ ቀን ዛሬ ስለሆነ ሁሉም አባላት መገኘት የግዴታ ነው።
ማሳሰቢያ:ዛሬ በቦታው ላይ ተገኝቶ Attendance ያላስመዘገበ ማንኛውም አባል ምንም አይነት Certificate አይኖረውም!!
ቦታ: ሴቶች ዶርም ካለው ካፌ
ሰዓት:7:30 ጀምሮ
Greate life time opportunity for 2nd year and 3rd year students

Apply 👇👇👇👇👇👇
https://ln.run/6VCFN

🔴🔴 Note 🔴🔴
This form is only valid for Technology Institute students

For more inquiries contact @Raguelshitu
@bubaahm
We are excited to announce the launching ceremony of the Hawassa University Governance and Development Studies Students Association(HUGaDSSA)🎉🎉.
The event will take place on 21/09/2016 E.C at 7:30 in main campus Africa Union Hall.

Join us as we celebrate the establishment of this new association....being the member of this great association have important credit.

There will be _
speeches😮
performances💯
networking opportunities👍
membership registration👏

We look forward to seeing you there!🎉


👉https://www.tg-me.com/hugadssachannel
2024/09/28 01:23:11
Back to Top
HTML Embed Code: