Telegram Web Link
የህግና ገቨርናንስ ኮሌጅ አመታዊ የምርምር ጉባኤ አካሄደ።
//
ሚያዚያ 30/2016 ዓም

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ከምርምርና ቴክ/ሽ/ም/ፕሬዚደንት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በ2015 ዓ.ም በኮሌጁ ተመራማሪዎች የተሰሩ የምርምር ስራዎችን ለመገምገም ያለመ ጉባኤ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ አካሂዷል።

የኮሌጁ ምር/ቴ/ሽ/ተባባሪ ዲን ዶ/ር አዲስወርቅ ጥላሁን የመድረኩን አላማ ባስረዱበት ንግግራቸው እንደገለጹት በ2015 በጀት ዓመት በኮሌጁ መምህራን የተሰሩ አራት የዲሲፕሊነሪ ምርምሮች በኮሌጁ አካዳሚክ አባላት ግምገማና ውይይት ይካሄድበታል ብለዋል። ዶ/ር አዲስወርቅ አክለውም ምርምር የሚሰራበት አላማ አዲስ እውቀትን ለመፍጠር ወይም ነባሩን እውቀት ለማሳደግ በተጨማሪም የማህበረሰቡን ችግሮች ለመፍታት መሆኑን አንስተው ይህንን አላማ ታሳቢ በማድረግ በዩኒቨርሲቲው የገንዘብ ድጋፍ አግኝተው ወደ ስራ የገቡ ጥናቶች ሰባት የኮሌጁን ተመራማሪዎች ማሳተፋቸውን ገልጸዋል።

የኮሌጁ ፕላንና ዳታ ማኔጅመንት አስተባባሪ አቶ ከድር ዳሮ በበኩላቸው  በመድረኩ የተሰሩት የምርምር ስራዎች የምርምር ስነ ምግባርን ተከትለው መሰራታቸው፣ ደረጃቸውን ማሟላታቸው፣ የሚጠበቅባቸውን ውጤት ማምጣታቸውና ምን አዲስ ግኝቶችን አስተዋወቁ የሚሉትን ነጥቦች እንደሚገመገሙበትና ጥያቄዎች እንዲሁም ግብረመልሶች እንደሚሰጡበት ተናግረዋል። በየአመቱ በኮሌጁ መምህራንና ተመራማሪዎች የሚሰሩ የምርምር ስራዎች በቁጥርም ሆነ በጥራት መሻሻሎችን እያስመዘገቡ መሆኑን  ያነሱት አስተባባሪው ለዚሁ ለውጥ መመዝገብ የምርምር ግምገማዎችና በአካዳሚክ አባላት መካከል የሚደረጉ ገንቢ ውይይቶች አይነተኛ ሚና መጫወታቸውን ገልጸዋል።
                   

https://www.tg-me.com/hugadssachannel
የሴኔት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያየ::
//
ሚያዚያ 30, 2016 ዓም

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የ2016 ዓም የተማሪዎች ምረቃ ቀን እና ሌሎች አጀንዳዎች ላይ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ውሳኔዎችን አሳልፏል::

ኮሚቴው ከትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠው የፈተናዎች መርሃግብር አንፃር በዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ የሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናቸውን እንዳጠናቀቁ ሐሙስ ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓም ምረቃ ሊደረግ እንደሚችል ውሳኔ ላይ ደርሷል::

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የመውጫ ፈተና ዝግጅትን በተመለከተ ሁሉም ኮሌጆችና የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እስካሁን የተሰሩ ሥራዎችን ሪፖርት ለኮሚቴው ያቀረቡ ሲሆን በሂደቱም የተገኙ ግብረ መልሶች: የታዩ ክፍተቶች: ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የተወሰዱ የማስተካከያ እርምጃዎች ላይ ሰፊ የልምድ ልውውጥና ውይይት ተደርጓል::

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በውይይቶቹ ማጠቃለያ ላይ ለተማሪዎች የመውጫ ፈተና ዝግጅት በቀረው ግዜ ሁሉም የሚመለከታቸው ክፍሎች ቀሪ ስራዎቻቸውን እንዲያጠናቅቁ እና ተማሪዎችን በሂደቱ ላይ በንቃት እንዲያሳትፉ መመሪያ ሰጥተዋል::

                    

https://www.tg-me.com/hugadssachannel
Forwarded from UNA-ET HU CHAPTER (Raguel Shitu)
🎉 Join our extraordinary magazine project at Hawassa University!

Experience the inspiring journey of UNA-ET-HU Chapter, from humble beginnings to remarkable achievements.

Positions available:
👨‍💼 Project Manager: Lead and coordinate our magazine project with finesse.

🎨 Graphics Designer: Bring our magazine to life with your creative talents.

🖋️ Content Creator: Craft captivating articles and content that will engage our readers.

Deadline: May 15th, 2024

Apply now! https://shorturl.at/enwX8


#UNAETMAGAZINE #HawassaUniversity
@UNA_ET
Forwarded from Hakim
Following in the footsteps of our esteemed Tikur Anbessa graduates, the GC Committee of Hawassa University's Medicine graduates has made the heartfelt decision to donate our remaining funds (34,600 Birr) from committee activities to support the medical expenses of Dr. Samson and Dr. Betelhem.

Our thoughts and prayers are with you during this challenging time.

Graduate Class of 2024, Hawassa University

@HakimEthio
Forwarded from Hakim
ለዶ/ር ሳምሶን እና ዶ/ር ቤቴል ህክምና ወጪ ለመሸፈን እየተደረገ ያለው ርብርብ እጅግ ያስደስታል። ሁላችንም የአቅማችንን በገንዘብም በፀሎትም ከጎናቸው እንደምንሆን አምናለሁ።

ግን እስከ መቼ ነው በዚህ በተበጣጠሰ መልኩ ለወገኖቻችን ችግር ለመድረስ የምንሞክረው?

ህይወታቸውን ለወገኖቻቸው ፈውስ መስዋዕት እያደረጉ ያሉ የጤና  ባለሙያዎች በመሰል ህመሞች ምክንያት ከባድ ችግር ውስጥ ሲወድቁ ማየት ከመቸውም ጊዜ በላይ እየተለመደ መጥቷል።

አሁን እያየን ባለው የችግሩ ጥልቀትና ስፋት ከተበጣጠሰ (fragmented) የእገዛ አሰባሰብ አካሄድ ወደ ተቋማዊ ምላሽ መሻገር አስፈላጊ ይመስለኛል።

ለወደፊቱ በተቻለ መጠን ሁሉምን እገዛ የሚያስፈልጋቸውን ባለው አቅም ልክ ተደራሽ ለማድረግና የባለሙያዎቻችን እንዲሁም ሌሎች ወገኖችን ህይወት በዘላቂነት ለመታደግ ዘርፈ-ብዙ ትብብር አስፈላጊ ይሆናል።

የሙያ ማህበራት፣የመንግስትና የግል ጤና ተቋማት ፣ በጎ አድራጊ ተቋማትና ግለሰቦች፣ እንደ ሀኪም ፔጅ ያሉ የማህበራዊ ትስስር ገፆች፣ ታዋቂ ግለሰቦች ፣ በጎ ፈቃደኞች ወዘተ በመተባበር  በቋሚነት ገቢ የሚሰበሰብበት፣የውጪ ሚኒዛሪ ከባንክ በቅድሚያ እንዲያገኙ የሚመቻችበት ፣ ከህክምና ቦርድ ጋር በትብብር አብሮ የሚሰራበት ፣ ውጪ ሀገር ህክምናውን ከሚሰጡ ተቋማት ጋር እንደተቋም ስለህክምናቸው ወጪ፣ ውጤትና ክትትል (outcome and follow up ) ንግግር የሚደረግበት platform ቢፈጠር ይህን አላማ ለማገዝ ብዙ ተቋማትና ግለሰቦች ወደ ፊት እንደሚመጡና ቋሚ መዋጮ እንደሚያደርጉ በፅኑ አምናለሁ።

የዚህ መድረክ መፈጠር ለሁላችንም ባለሙያዎች መተማመኛ (sense of security) ከመፍጠሩም በላይ እገዛውን ፈርጀ-ብዙ ያደርገዋል።

ይሄ መነሻ ሀሳብ ነው። ተገቢነቱ ከታመነበት ዝርዝሩ አፈፃፀም ሊዋቀር ይችላል። ሀኪም ፔጅ የሙያተኞች ድምፅ እንደመሆኑ ጉዳዩን ወደ ፊት ይወስዳል ብዬ አምናለሁ። እንደ ተቋም እንዲሁም እንደ ግለሰብ ወርሃዊ መዋጮ ለማድረግ ዝግጁ ነን።

የተጠናከረ የኢንሹራንስ ስርዓት እስከሚበጅና እነዚህን ህክምናዎች ሀገር ውስጥ የመስጠት አቅም እስከሚፈጠር ድረስ በግሌ ሌላ አማራጭ ያለን አይመስለኝም።

ለታመሙት እህት ወንድሞቻችን ፈጣን ፈውስን እመኛለሁ።

Dr. Girma Ababi
🔹Founder and CEO of Liyana Healthcare PLC [Yanet chain of Hospitals, Health sciences college and pharmaceuticals]
🔹Vice chairman of National private Health Facilities association and Ethiopian Healthcare Federation

@HakimEthio
Forwarded from Hakim
I have TWO ideas to effectively treat Drs Bethel & Samson.

1. To agressively contribute now (It is ALL & G-3 Brain tumor!) & when some cash is raised, why not to approach one if the abroad treatment destinations via MOH, great discount could be obtained if MoH write a letter requesting such cooperation.

ሆስፒታሎቹ ለስማቸው ይፈልጉታል።

Many years back our Intern Dr. Martha was treated by the letter MoH wrote. Thickets ET gave freely & colleagues visiting our department have arranged USA trip & Surgery.

I know MoH has MOU with great medical tourism destinations.
It requests REVERSE MEDICAL TOURISM &COOPERATION AT TIMES LIKE THE SITUATION WITH THESE TWO Doctors.

2. If HAKIM takes initative for a FOUNDATION or Charity license for such activities, it could be obtained. We did this in my constituency for Master Abenet Kebede. Many are treated at home&abroad. With this licence, you can run campaigns of REVERSE TOURISM anywhere in ETHIOPIA & raise funds.
ቋሚ መዋጮም ሁላችንም እናዋጣለን።

For now, I contributed my simple share, for each M.D.

*በነገራችን ላይ ይህ 25K የአንድ ፕሮፌሰር የጥቁር አንበሳ የወር ደሞዝ ነው (ከነጥቅማጥቅሙ)። ከቤተሰቤ ተማክረን የፋሲካን ወጪ ትተን ነው ያዋጣነው።
Weekend እኛ ቤት እንዳትመጡ።

ፋሲካ መልስ አለው!
Professor Biruk Lambisso Wamisho

@HakimEthio
2024/09/28 19:32:21
Back to Top
HTML Embed Code: