Telegram Web Link
Forwarded from HU Charity Sector
----------------------- ሜሪ ጆይ -----------------------

ሚያዚያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መማክርት የበጎ አድራጎት ዘርፍ ከምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ RVC ጋር በመሆን በሀዋሳ የሚገኘውን የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከል ሜሪ ጆይ ጎበኙ።

በጉብኝቱ ወቅት ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ጊቢውን እና የማደሪያ ክፍሎችን የማጽዳት ስራ፡ የአረጋውያንን ልብስ ማጠብ፡ ጊቢውን ማስዋብ፡ ከአረጋውያን ጋር ጊዜ ማሳለፍ የሚጠቀሱ ናቸው።

በዚህ ተግባር አረጋውያን ደስ እንዳላቸው እና ይህ ተንባር መበረታታት እንዳለበትም ጭምር  በመግለጽ ከማይጠገበው ባርኮታቸው አካፍለውናል።

ርህራሄን በተግባር
| የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መማክርት የበጎ አራጎት ዘርፍ
@husccs
@husccs

#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
@RvcClub
ንግስት/ሞቲቴ ፉራ ማነች

ምንም እንኳን ባግባቡ የተሰነዱ የፅሁፍ መረጃዎችን እንደልብ ማግኘት ባይቻልም ንግስት ፉራ በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ዛሬም ድረስ ምትነሳ ስመ ገናና ንግስት መሆኗ ማየት ይቻላል። ምንጮች እንደሚያስረዱት ሞቲቴ ፉራ በ16ኛው ክፍለ ዘመን የነበረችና የሲዳማን ህዝብ በንግስትነት እንዳስተዳደረች የሚነገርላት ስትሆን በግዜው እንደሚታሰበው እንደሴት ብልህ ነገር አዋቂ ብቻም ሳትሆን እንደወንዶቹም አዳኝ ጠንካራ ድፍረትና ጀግንነትን የተላበሰች  ንግስት እንደነበረች ይነገራል። ቀድመን አንደጠቀስነው ምንም እንኳን በግዜው የተከተቡ ድርሳናትን ማግኘቱ ቢያዳግትም የሲዳማ ህዝብ በአፈ-ቃሉ ከልጅ ልጅ እያወሳ ከመጣው ታሪክ በተጨማሪ  አሁን በዘመናችን የተፃፉና የተቀመጡትን ድረሳናትና ማስረጃዎች (ለምሳሌ: የሲዳማ ህዝብ ታሪክ፣ ንግስት ፉራ --- መፅሃፍ) ዋቢ ስናረግ ንግስት ፉራ በንግግርና በአስተሳሰብ በልጦ በመገኘት የምታምን የሴቶችን የበታችነት ወይም መጎዳት ለማስቀረት ትሰራ የነበረች በዚህም ሀሳቧ የደገፏትን ማትነካ የሚቃወሟትን ደግሞ የምትቀጣ መሪ እንደነበረች መናገር ይቻላል።  ሞቲቴ ፉራ ሴቶች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ያልነጠረ ቅቤያቸውን፣ ያልተፈተል ጥጣቸውን፣ያልበሰል የጎመን ቅንጥሳቸውን ለባሎቻቸው እንዳያሳዩ ትመክር ነበር ይህም ቅቤው ሲነጥር ሲጣራ መጠኑ ያንሳል፣ ጥጡም ሲፈተል አንደቀድሞው ክምር አይሆንም፣ ጎመኑን ሲቀቀል ሙሽሽ ይላል ታድያ ባሎች ይህን ሲያዩ ያን ሁሉ የት አረግሽው እያሉ ያስጨንቋችኋል ከሚል ህሳቤ ነው።

ሞቲቴ ፉራ ወንዶችን ከሩቅ ቦታ ትኩስ ወተት አልባችሁ ሳይቀዘቅዝ አምጡልኝ፤ ከምድር ከፍ ከሰማይ ዝቅ ያለ ቤት ስሩልኝ፤  አንድ የፀጉር ዘለላን ስድስት ቦታ ሰንቃችሁ አምጡልኝ እና መሰል ለማድረግ ብቻ ሳይሆን ለማሰብም ሚከብዱ ተግባራትን ታዝ እንደነበር ይነገራል። ይህንንና መሰል መረጃወችን በመጥቀስ ሞቲቴ ፉራ የሴቶችን አምባገነንነት ታስፋፋ ነበር የሚሉ የታሪክ ዘጋቢዎች ቢኖሩም  ንግስት ፉራ ሴቶች አቅማቸውን እንዲያወጡና ወንዶችም ይህን እንዲረዱ እንዲሁም እንዲቀበሉ ምታደርግና አንደ የትኛውም ገዢ መቅጣት አለብኝ ብላ ያሰበችው የምትቀጣ ያዘዘችሁም ትዕዛዝ ባይፈፀም እንኳን ብልሃት የታከለበት አሳማኝ መልስ ከተሰጣት ምህረትን የምታደርግ እንጂ ወንዶችን በሞላ ለመቅታት የወረደች ንግስት አልነበረችም ብለው ሚያስረዱ ብዙ  ምንጮችን እናገኛለን።

ሞቲቴ ፉራ በመጨረሻም አካሄዷን በሚቃወሙ    " አዋቂ" ሰዎች  በታሰበ ሴራ ቆርኬ ምትባለውን የዱር እንስሳ ስትጋልብ ህይወቷም ዘመኗም እንዳለፈ ቢነገርም ዛሬም ድረስ እናቶች ልጆቻቸውን እንዲህ እያሉ ስሟንም ታሪኳንም እያነሱ ያጫውቱበታል።

ኦሶ ሃዬ ሃዬ ፉራ ሜንቱ ቢሎ--- አኒ ዲ አፎማ
አፉ ኖሁ ይኖ---ቆርኬ ጊዲሲሴ
ቆሎ ውዲሲሴ --- ፉራ ጌርቹ ሺኖ
ፉራ ሺሁ ሺሞ ..... ይላሉ

ይህንንም እንጉርጉሮ አቻ ይሆናል ባልነው አማርኛ ስንተረጉመው:

ማሙ እሹሩሩ ማሙ እሹሩሩ
ፉራ የሴቶች ቁንጮ ካሉት በሃገሩ
አጋዘኗን ጭኖ ኮርቻ እንደፈረስ
አስጋለብኩኝ ብሎ አለባብሶ ግላስ
ፉራን ያስገደላት  አዋቂ ሰው ይነስ...


ባሁኑ ሰዓት ይህ የንግስት ፉራ ታሪክ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ  በመቅረዝ የኪነ-ጥበብ አፍቃርያን ህብረት በቴያትር መልክ እየተሰራ ይገኛል።

በዚው አጋጣሚ ይህን በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ ያላትን የንግስት ፉራን ታሪክ የሚያወሳ ስራ የተሳካና ያማረ ይሆን ዘንድ የምትችሉ ሁሉ የcostume በተለይም የሲዳማ ባህላዊ አልባሳትን የማዋስ ድጋፍ እንድታደርጉልን ስንል በአክበወሮት እንጠይቃለን።

የሚከተሉትን የtelegram account ማናገር ይቻላል 👉 @zewdnssh @Beli1223

ይህ ደግሞ ይፋዊ የመቅረዝ የtelegram group ነው 👉 https://www.tg-me.com/mekerezeactingstudents
የምድር ቀን

የዘንድሮው የምድር ቀን "ፕላኔት ከ ፕላስቲክ" በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

ዓላማውም ፕላስቲክ በጤናችንና በምድራችኝ ላይ የደቀነውን አደጋ ለማስገንዘብ ነው።

በየዓመቱ ሚሊዮኖች ቶን የፕላስቲክ ቆሻሻ ወደ ውቅያኖስና ካባቢያችን ይለቀቃል። ይህ የሚደፋው የፕላስቲክ ቆሻሻ ከባቢን ከመበከል ባሻገር የዱር እንስሳትን ህይወት ይጎዳል፤ በምግብ ሰንሰለት ላይም በመግባት ዘርፈ ብዙ አደጋ መንስኤ ይሆናል።

መፍትሄው

❶ ስንገበይ የወረቀት መያዣ መጠቀም
➋ ፕላስቲክን ደጋግሞ መልኮ መጠቀም
➌ እየጠገኑ ለረጅም ጊዜ መጠቀም
➍ የላስቲክ ምርት ያልሆኑ ዕቃዎችኝ መጠቀም
➎.በትምህርት ቤት በቤትና በአካባቢ ፕላስቲክ ያለመጠቀም ባህል መገንባት ይገባል።

Planet vs. Plastics

The theme for 2024 is "Planet vs. Plastics," highlighting the dangers that plastic poses to our planet and our health. Millions of tons of plastic waste end up in landfills and oceans every year. This plastic pollutes our environment, harms wildlife, and even enters the food chain.

#WorldEarthDay2024 #WorldEarthDay #plasticvsplanet #green #recycle #reuse #greenenvironment #Ethiopia


ከ Gotravel Facebook ገፅ የተወሰደ
Forwarded from UNA-ET HU CHAPTER (Raguel Shitu)
UN delegatee 2024 final.pdf
1.2 MB
🇺🇳 United Nations Association of Ethiopia Hawassa University Chapter Model United Nations Simulation Conference 2024

Position paper deadline:

➡️ First draft: Tuesday, April 23, 2024 ( for those who want their posion papers commented before final submission date)

➡️ Final submission date Wednesday, April 24, 2024

➡️ Submit to: @Raguelshitu


Join the MUN group for further guidance and inquiries
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/MUN_UNA_ET_HU
-------------------For GC Students -------------------

Hello hello guys,there is a registration for new DAAP trainees.

አዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች እንኳን ደስ አላችሁ! የምዝገባ ፎርም ስለተዘጋጀ እንድትሞሉ ለማሳወቅ ወዳለው።

👇👇👇👇👇👇👇
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdhj0oPUb9OjSCYq61szkXv7Bdctv0QJAHt6OuVxctI8ZQglg/viewform?usp=sf_link
Forwarded from UNA-ET HU CHAPTER (Raguel Shitu)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Throwback to our recent Aerobics program! It was such a good time! 💪 The energy, the moves, and the amazing people made it unforgettable. Can't wait for the next session! 🎵🔥 #ThrowbackSaturday #AerobicsFun

https://www.tg-me.com/UNA_ET
2025/07/07 03:29:31
Back to Top
HTML Embed Code: