Telegram Web Link
ምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ - RVC


Life-Exemplary Talk Show

የምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ የሚያዘጋጀው የታላላቅ ሰዎችን የህይወት ልምድ ተሞክሮ የምንካፈልበት ፕሮግራማችንን

📌 በየሚስት ያለህ ና ስምንቱ ሴቶች ቲያትር እንዲሁም

📌 በገመና፣ ዳና እና እረኛዬ ድራማ ድርሰት ያስደመምችን

📌 የመጨረሻዋ ቀሚስ፣ የሌባ ልጅ፣ ደርሶ መልስ ና ሌሎችንም ፊልሞች ላይ በትወና የምናውቃት

📌 የአርት ወግ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ እና የሌሎች በርካታ ስራዎች ባለቤት  የሆነችው  ደራሲ፣ ተዋናይት፣ ተርጓሚ ፣አዘጋጅና ሁለገብ የኪነ ጥበብ ሰው አዜብ ወርቁ ከህይወት ተሞክሮዋ ተካፍለን በስነ-ፅሁፍ ምሽት ታጅበን አሳልፈነዋል።

 ጥሪያችንን አክብራችሁ የተገኛቹ ተማሪዎች አብራቹን ስለነበራቹ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።

RVCን መቀላቀል የምትፈልጉ ተማሪዎች ከናንተ የሚጠበቀው ዘወትር በየሳምንቱ ቅዳሜ ምሽት 1:00 ሰዓት በRVC ቤተ-መፅሀፍት መገኘት ብቻ ነው።

📍 አድራሻችን Main Campus Radio ጣቢያው ፊት ለፊት የሚገኘው አዳራሽ።


#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@RvcClub
@RvcClub
🙏3
Forwarded from Inclusiveness club HU main campus (Ermias Worku)
የኢንክሉሲቭነስ ክበብ ጋዜጣ.pdf
1.4 MB
በኢንክሉሲቭነስ ክበብ አማካኝነት የተሰሩ ስራዎች በጋዜጣ መልኩ ለህትመት በቅተዋል።

በኤርሚያስ ወርቁ (የኢንክሉሲቭነስ ክበብ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሀላፊ)

ኢንክሉሲቭነስ ክበብ
በጎነት ለራስ ነው!!

join our Channel 👇👇
@inclusivness_club
👏7👍1
Exciting news from New Generation! Our club held another engaging peer discussion today at the RVC Office, focusing on inclusiveness and women's rights. The students shared a variety of important ideas and perspectives, fostering a strong sense of camaraderie and understanding among participants. The program will continue next week with another group, so stay tuned for more updates. Keep the conversation going and join us in creating positive change in our community! #NewGeneration #PeerDiscussion #Inclusiveness #WomensRights

https://www.tg-me.com/Hu_new_generation_club
Forwarded from Inclusiveness club HU main campus (Yohannes Moges)
15ኛው አለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤ በቀጣዩ አመት በኢትዮጵያ ይካሄዳል

15ኛው አለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤ በ2017 ዓም በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በቀጣዩ አመት ዓለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ለማዘጋጀት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ጉባኤው ከጥር 6 እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል። ስምምነቱን የተፈራረሙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ትብብሩ ጉባኤውን በተሳካ መልኩ ለማካሄድ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል። በዚሁ ወቅት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የዓለም የምልክት ቋንቋ ጉባኤ በቀጣይ አመት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

ይህንን ተከትሎ ሚኒስቴሩ ጉባኤውን ከብሔራዊ መስማት ከተሳናቸው ማህበርና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለማካሄድ ዝግጅት መጀመሩን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ስም ከፍ የሚያደርጉና የአገራትን ትስስር ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራትን ዩኒቨርሲቲው እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ ረገድ ጉባኤው በኢትዮጵያ እንዲካሄድ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። የዩኒቨርሲቲው ምሁራን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በመተባበር ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ፡ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በጉባዔው ከተለያዩ የአለም አገራትና ተቋማት የተወጣጡ ከ600 በላይ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

FEBRUARY 16, 2024
ዘጋቢ ስለእናት እስክንድር
👍7
Forwarded from Inclusiveness club HU main campus (Ermias Worku)
የኢንክሉሲቭነስ ክበብ መታወቂያ ለማውጣት ፎቶና ብር የሰጣችሁ አባላት መታወቂያችሁ ስለተዘጋጀ ከዛሬ 11 ሰአት ጀምሮ ቢሮ በመምጣት መታወቂያ መውሰድ ትችላላችሁ።

መታወቂያ ማውጣት እሚትፈልጉ አባላትም እስከ አርብ ድረስ ቢሮ በመምጣት ፎቶ እና 20 ብር በመስጠት መታወቂያ ማውጣት ትችላላችሁ።
ለበለጠ መረጃ: 0931294893
                     
ኢንክሉሲቭነስ ክበብ
በጎነት ለራስ ነው!!

join our Channel 👇👇
@inclusivness_club
👍6😢1
Hawassa University Students' Information Center pinned «የኢንክሉሲቭነስ ክበብ መታወቂያ ለማውጣት ፎቶና ብር የሰጣችሁ አባላት መታወቂያችሁ ስለተዘጋጀ ከዛሬ 11 ሰአት ጀምሮ ቢሮ በመምጣት መታወቂያ መውሰድ ትችላላችሁ። መታወቂያ ማውጣት እሚትፈልጉ አባላትም እስከ አርብ ድረስ ቢሮ በመምጣት ፎቶ እና 20 ብር በመስጠት መታወቂያ ማውጣት ትችላላችሁ። ለበለጠ መረጃ: 0931294893                       ኢንክሉሲቭነስ ክበብ በጎነት ለራስ ነው!!…»
Forwarded from UNA-ET HU CHAPTER (Raguel Shitu)
📢Announcement

we are very pleased to announce that a new executive has been assigned to manage UNA_ET_HU_CHAPTER Yirgalem Campus for the year 2024 academic calendar.

@UNA_ET
👏6👍21
የምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ (RVC)


ውድ የRVC ቤተሰቦች እንዴት ቆያችሁን፤ ሳምንቱ በመልካም እንዳለፈ እምነታችን ነው።

  እንሆ ቀዳሚት ደርሳለች እናንተስ ቤተሰቦቻችን ከፈተና ዝግጅት ከንባቡ ጥቂት እረፍት ለማድረግ ስታስቡ ለቅዳሜ ምሽት ከ RVC ውጪ ሌላ እንደማታስቡ እንተማመናለን።

  ቤታችን የሀሳብ ማዕዷን ዘርግታለችና፤ እኛም ኑ ከምክንያታዊነት ማዕድ እየተቋደስን የቆምንበትን መሰረት እንፈትሽ፣ ካነበብነው እናጋራ ብለን ሁላቹንም ጋብዘናል።

ዛሬ ከወትሮ በተለየ በአንድ ሀሳብ ላይ ለመወያየት ሳይሆን ብዙ ሀሳቦችን በያዘ አንድ ታሪክ ላይ ልንመክር ተዘጋጅተናል።
ለታሪኩና ለባለ ታሪኮቹ በRVC ችሎት ቆመን በአመክንዮ እንሞግታለን።

ታድያ ሞጋች በሰአቱ በችሎቱ ይሰየማሉና አደራ ችሎት እዳይጓደል እንዳታረፍዱብን! 🕐 1:00 ሲል በችሎቱ ሁሉም ይሰየማል



  📍 አድራሻችን Main Campus Radio ጣቢያው ፊት ለፊት የሚገኘው አዳራሽ።



#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@RvcClub
@RvcClub
1👍1
Forwarded from Hawassa Freshman (Asebe)
Announcement 🔊

Career Guidance and Counseling program for 1st year students Organized by Hawassa University Employability Development and Career Readiness Center in collaboration with Dereja.

All 1st year students were cordially invited to attend the orientation session

Hawassa University dereja Employability Development and Career Readiness Center

Date: 24/02/2024
Venue: B121 (In the front of law library)
Time: 8:30 AM (Morning)


@hawassa_fresh
👍21
Forwarded from Kedir Daro
2025/07/12 11:18:13
Back to Top
HTML Embed Code: