Telegram Web Link
Counting down 2 days for the big day!

Congratulations!
Forwarded from HU GC
👩‍🎓2024 GC 👨‍🎓  🎓
እንኳን አደረሳችሁ የምርቃት ቀናችሁ ላይ ደምቀት የሚሆኑ ባይደሮች እኛ ጋር ያገኛሉ
በግሩፕ ለምታዙ Discount እናደርጋለን
🎓BA
🎓MA
🎓PHD



🤳0918242665
-------- ማስታወቂያ ለተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ -------

የመመረቂያ ልብስ (ጋውን) የሚመለሰው ዓርብ 28/10/2016 መሆኑን እና ክሊራንስን ጨምሮ በጊቢ ያላችሁን ጉዳይ በእለቱ እንድትጨርሱ እያሳሰብን ቅዳሜ እለት በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምክንያት ጊቢው በፌደራል ፖሊስ ስር ስለሚሆን የመኝታም ሆነ የምግብ እና ማንኛውንም አገልግሎት እንደማታገኙ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

| የተማሪዎች መማክርት
Forwarded from Inclusiveness club HU main campus (Getahun)
🎉 Congratulations to Belete Butuna for achieving his BA degree from Hawassa University! Your perseverance and determination inspire us all. Despite challenges, you've shown that nothing can stand in the way of your dreams. Here's to your incredible journey and bright future ahead! 🌟👏 #Inspiration #Achievement #HawassaUniversity #Determination

When Everyone is Included, Everyone Wins!
Forwarded from Inclusiveness club HU main campus (Getahun)
Dear Graduates of Inclusiveness Club Members,

Congratulations on this momentous occasion! Today, we celebrate not only your academic achievements but also your exceptional commitment to inclusiveness and diversity through your invaluable service in the Inclusiveness Club at Hawassa University.
Your dedication to fostering an inclusive environment on our campus has been nothing short of inspiring. You have set a remarkable example for your peers and have played a crucial role in making our university a place where everyone feels valued and respected. Your efforts have not gone unnoticed, and we are immensely proud of each one of you.
As you step into the next chapter of your lives, carry with you the values of inclusion and acceptance that you have championed during your time here. The world needs more ambassadors for inclusiveness, and I have no doubt that you will continue to be shining examples of these principles in all your future endeavors.
Thank you for your hard work, your compassion, and your unwavering commitment to making a difference. Congratulations once again, and best wishes for a future filled with success, fulfillment, and continued advocacy for inclusiveness.
May God Bless You All!
07 - 03 - 2024
Getahun Solomon
Founder and Coordinator of Inclusiveness Club,
Hawassa University, Ethiopia
Hawassa University Students' Information Center pinned «Dear Graduates of Inclusiveness Club Members, Congratulations on this momentous occasion! Today, we celebrate not only your academic achievements but also your exceptional commitment to inclusiveness and diversity through your invaluable service in the Inclusiveness…»
መቅረዝ የኪነ-ጥበብ አፍቃርያን ህብረት ለመላው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ለ2016 ዓ.ም ምረቃ ቀን አደረሳችሁ ይላል።

እንኳን ደስ አላችሁ!
Congratulation!
አዎን ይቻላል‼️አካል ጉዳተኝነቱን ድል የነሳ አንበሳ!!

ይህ ከሰንሰለታማው ጋራምባ ተራራ ግርጌ በመነሳት በአካል ጉዳተኝነትና በሕይወት ፈተና ሳይበገር፣ ተፈትኖ ለሰኬት የበቃው፣ የወጣቱ በለጠ ቡቱና (የአርሶ አደር ልጅ) አጭር የሕይወት መንገድ ታሪክ ነው!
በለጠ ቡቱና (ያምቡሌ) ትውልድና እድገቱ አርቤጎና ወረዳ ሲዳማ ነው። በለጠ 1989ዓ.ም አርቤጎና ጎዋ ቀበሌ ልዩ ሥፍራ ቡላ ተወለደ። በለጠ ከልጅነቱ ጀምሮ በሁለት እግሩ መራመድ አይችልም ነበር። በዚህ ምክንያት እጆቹን እንደ እግርም እንደ እጅም ለመጠቀም ተገደደ። አካል ጉዳተኝነትን  እንደ የእግዚአብሔር ቁጣ ተደርጎ በሚታሰብበት በአብዛኛው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በገጠር ተወልዶ፣ አይደለም ተምሮ ለወግ ማዕረግ መብቃት በተሰፋ መኖር መቻል በራሱ ፈታኝ ነው።

በለጠ በህፃንነቱ በወላጅ እናቱና አባቱ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት በመለያየታቸው ሌላ የሕይወት ፈተና ለመጋፈጥ ተገዷል። የወላጆቹ መለያየት በአካል ጉዳተኝነቱ ላይ ታክሎበት ሕይወትን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ዓይነት አድርገውበታል። 

በለጠ ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ በአካባቢ ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱ ልጆችን እያየ "እኔም ከእነዚህ ልጆች ጋር ትምህርት ቤት በሄድኩ!" እያለ ይብሰለሰል ጀመር። ግና አካል ጉዳተኛነቱ፣ ትምህርት ቤት በአቅራቢያው አለመገኘቱ፣ የመንገድ መሠረተ ልማት ችግር፣ የመጓጓዣ እጦት፣ ማህበረሰቡ በአካል ጉዳተኞች ላይ ያለው አሉታዊ አመለካከት፣ ወላጅ እናት ቤት ውስጥ በማጣት እህል ውሃ የሚሰጥ ሰው መጥፋቱ ይህ ሁሉ ፈተና ከፊት ለፊት ተሰልፎ የሚጠብቀው ነበር። በለጠ ልቡ ኮስታራ ነበረና ፈተናዎቹን ሁሉ ለመጋፈጥ ቆርጦ ተነሳ። "አልችልም!" በይነትን ገና በጠዋቱ ቀበረ። "አዎን ይቻላል!" አለ። አባቱ  ከGowa (ጎዋ)  ጋራምባ ተራራ አከባቢ Fiide Fooliishsho (ፊዴ ፎሊሾ) ቀበሌ ወዳለው እርሻ ተዘዋውሮ መጥቶ እያለ ከእነሱ መንደር በ5 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኝ Shurro (ሹሮ) አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመግባት ወሰነ።

"የት ልትደርስ ትማራለህ? በዚህ ጭቃ በእጅህ እየ ደኽህ መከራ ከምታይ አርፈህ አትተኛም!" የአብዛኛው ማህበረሰብ ቅስም ሰባሪ አሰተያየት ነበር። በሌ ለአሉታዊ አሰተያየቶች ጆሮ አልሰጠም። የአንደኛ ክፍል ትምህርቱን አንድ ቢሎ ሹሮ ት/ቤት ጀመረ።

ጋራምባ ተራራና አከባቢው በሲዳማ ክልል የደጋማ ሥፍራዎች ቁንጮ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ተራራ አቅራቢያ የሚገኘው ሹሮ ት/ቤ ከአርቤጎና ወረዳ የሩቅ ት/ቤት ተብለው ከሚታወቁት አንዱ ት/ቤት ነው። የአከባቢው የአየር ንብረት በጣም ዝናባማ፣ መልካ ምድሩ ተራራማ፣ የመረት አቀማመጥ አይደለም ለአካል ጉዳተኛ ለጤነኛ ሰውም ፈታኝ ነው። በለጠ ለተፈጥሮ ፈተና እጅ ሳይሰጥ ከፊዴ ፎሊሾ ቀበሌ ከመኖሪያ በቤታቸው ለሊት 11:00 ወጥቶ 5 ኪ.ሜ ከ3-4 ሰዓት በእጁ እየተራመደ ትምህርት ቤት 2:00 ይደርስ ነበር። በዚህ መልኩ ወደ ት/ቤት ሲሄድ ብዙ ፈተና ገጥሞታል። በአንድ ወቅት ወንዝ ዘሎ ለመሻገር ሲሞክር ይዞት ሄዶ እግዚአብሔር እንዳሰጣለው አጫውቶኛል። በለጠ ከአብሮ አደጎቹ እጅግ ቀድሞ ጉዞ ሰለሚጀምር ዝናብና ብርድ ከማንም በላይ ተፈራርቆበታል። እሾህ፣ ጠጠርና ጭቃ እንደ እግር የሚጠቀማቸውን እጆቹን ጎድተውታል። ከማህበረሰቡ መገለል፣ መድሎ፣ ተሰፋ እስቆራጭ ንግግሮች ተፈታትነውታል።  በለጠን ግን ከአካል ጉዳተኝነቱ ጋር ይህ ሁሉ መከራ ታክሎበት ቢሆን የልጅነቱ  ህልሙ ምን ከመኖር አላገደውም።

በለጠ የአንደኛ ክፍል ትምህርቱን በብዙ ፈተና ሹሮ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቆ የተሻለ ሕይወትና ትምህርት በመሻት ወደ አርቤጎና ወረዳ አሰተዳደር መቀመጫ ወደ ሆነቺው Yayye (ያዬ) አቀና። ያዬ ከፊዴ ፎሊሾ (ከነበለጠ ገጠር) 14 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች። በለጠ ከ2-8 ክፍል ቁኒቻ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ከ9-12 አርቤጎና ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተምሯል።  ያዬ  ከተማም ከአዲስ አበባ ከተማ እኩል የቆረቆረች ዕድሜ ጠገብ የደጋ ሀገር ከተማ ብትሆንም ለአካል ጉዳተኛ የሚመች መሠረተ ልማት የላትም። የተፈጥሮ በረከቷ እንደተጠበቀ ሆኖ ቅዝቃዜ፣ ዝናብ፣ ጭቃ የተለመደ ነው። በመሆኑም በለጠን ሕይወቱን በከተማ ቢያደርግም ፈተናዎቹ እልፍ ነበሩ።

በሌ ያዬ ከተማ ገብቶ ሦስተኛ ክፍል እስክደርስ በባዶ እጆቹ ነበር የሚራመደው። ልብ በሉ በባዶ እግሩ ሳይሆን በባዶ እጆቹ። ለእጁ የመጀመሪያ ነጠላ ጫማ ሦስተኛ ክፍል ደርሶ ነበር ማድረግ የቻው። የያዬ ከተማ ጭቃና ፒስታ መንገድ አይደለም ነጠላ ጫማ ጫማም አይችለውም። በለጠ በእጆቹ ከመራመድ ነጠላ ጫማ ማድረጉ ከጠጠርና እሾህ ሰቃይ ትንሽ ያሽለው ቢሆን እንጂ ዘላቂ መፍትሄ አልሆነለትም።

በለጠ ሰባተኛ ክፍል ደርሶ ከነጠላ ጫማ ወደ ሸበጥ  ጫማ ከፍ ማለት ቻለ። በለጠ ለመማር ያለውን ጥረትና ከሰዎች ጋር በጣም ተግባቢ መሆኑን በዚያን ጊዜ ያዬ ከተማ የግል ክሊኒክ የነበረው አቶ ካሣ ካዬሶ ዊልቼር አምጥቶ እንደ ሰጠው ይናገራል። ያዬ ከተማ በዛ የጠጠር መንገድ፣ በዚያ ጭቃ እንዴት ይንዳው? ማንስ ይግፋው? በለጠ ተማሪዎች እየገፉት ለጥቂት ጊዜ ሕይወትን በዊልቼር ሞከረው። የአየር ፀባዩና የመሠረተ ልማት ችግር ሌላ ፈተና ሆኖበት ዊልቼሩን በመተው ወደ ሸበጥ ጫማው ተመለሰ።

በለጠ በክረምትና አንገብጋቢ ማህበራዊ ጉዳዮች ሲገጥሙት ከያዬ ፊዴ ፎሊሾ አንዳንዴ በፈረሰ፣ ሌላ ጊዜ ሰው ተሸክሞት ተመላልሷል። በአንድ ወቅት ከፊዴ ፎሊሾ እሰከ ያዬ ከቤት ከለሊቱ 11:00 ተነስቶ ከምሽቱ 1:00 ( ከ12 ሰዓታት) በላይ በእጆቹ ተጉዞ እንደደረሰ ያስታውሳል። በለጠ የጥንካሬው ጥግ፣ ለአካል ጉዳተኝነትና እሱን ተከትሎ ለሚገጥሙ ፈተናዎች ሁሉ እጅ ያለመሰጠት ልክ፣ የመንፈሰ ብርታቱ መጠን የሚደንቅ ወጣት ነው። በእውነቱ በዛ ገጠር፣ በዛ ማህበረሰብ ውሰጥ አካል ጉዳተኛ ሆኖ ተወልዶ እንደ በለጠ ለመሆን የሚታሰብ አይደለም። እሱ ግን መሆን የሚፈልገውን በእግዚአብሔር ኃይል ሆኖ አሳየ። ይደንቃል።

በለጠ የአሥራ ሁለተኛ ክፍል ካጠናቀቀ በኋላ በ2012 ሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በኤክስቴንሽን የትምህርት መርሃግብር በማኔጅመንት ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ድግሪ ትምህርቱን ጀመረ። ላለፉት 5 ዓመታት ኑሮውን በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በማድረግ፣ የማደሪያና የምግብ ድጋፍ ከዩኒቨርሲቲው በማግኘት ከምንም በላይ በእግዚአብሔር አቅም ጉልበት ሆኖለት ትምህርቱን ማጠናቀቅ ችሎዋል።

በለጠ ምንም እንኳን አካል ጉዳተኛ ቢሆንም ሥነ ልቦናው ጠንካራ ነው። በራሰ መተማመኑ ከፍ ያለ ነው። ባህሪው  ከሰዎች ጋር ቶሎ ተግባቢ፣ በግል ሕይቱ ዘናጭና ንፅህናን የሚወድ በጣም አራዳ ነው። በሌ የዋዛ አይምሰላችሁ። መብቱን ለማሰከበር ከማንም ጋር ከመጋፈጥ ወደ ኋላ የማይል ቆራጥ ተሟጋች ነው።  የሲዳማን ሀዮ (መላ) ያውቅበታል። ንቃተ ህሊናው የላቀ ነው። ሰው ሁሉ የሚደነቅበት ወጣት ነው። በለጠ የራሱ ብቻ አይደለም። ለማህበረሰቡ መብትና ጥቅም ጥብቅና ለመቆም አንደኛ ነው። በሌ ማህበራዊ ሕይወቱ ጠንካራ ነው። የታመመውን ሆስፒታል፣ የታሠረውን ማረሚያ ሄዶ ይጠይቃል። ለቅሶና ቀብር ቀድሞ ይደርሳል። በለጠ (ያምቡሌ) የስፖርት አፍቃሪ ነው። በአካል ጉዳተኞች ስፖርት በአትሌቲክስ ዘርፍ የቀድሞ ደቡብ ክልል በመወከል በልዩ ልዩ ዘርፎች ሜዳሊያ ተሸላሚም ነበር። በለጠ የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ቀንደኛ ደጋፊም ነው። በለጠ "አካል ጉዳተኛ አካሉ ቢጎዳም አሰተሳሰቡና ልቡ ጤናማ እሰከሆነ ድረስ ያሰበበት ከመድረስ የሚከለክል ነገር የለም!" ብሎ
ያምናል።

በለጠ ለዚህ ስኬት እንዲበቃ እግዚአብሔር እንደረዳው ይናገራል። የግል ጥረቱና ለፈተናዎች ሁሉ እጅ አለመሰጠቱ የስኬቱ ዋነኛ ምክንያት ነው። ሐዋሳ ዩኒቨርስቲ፣ የሲዳማ ክልል ሴቶችና ህፃናት ቢሮ፥ ለጋሽ ግለሰቦች፣ የተለያዩ ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች፣ ቀና ልብ ያላቸው የማህበረሰብ አካላት፣ ወጣቶች ከስኬቱ ጀርባ እንደሚገኙ ይናገራል።

ለወደፊት ምን መሆን እንደሚፈልግ ጠይቀው
እግዚአብሔርንና ማህበረሰብን ማገልገል ዋና የሕይወት ግቡ መሆኑን አጫውቶኛል።

የተከበራችሁ አንባቢን የበለጠ ቡቱና (ያምቡሌ) የሕይወት ውጣ ውረድና ስኬት ታሪክ ማንበብ የአንድ አካል ጉዳተኛ ሕይወት መሻሻል ምክንያት ሊሆን ይችላል። የሱ ታሪክ የአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተሰፋና ሞራል ሊያበረታታ ይችል ይሆናልና ጽሑፉን ለብዙዎች በማዳረሰ ማህበራዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ በፍቅር ላሳሰባችሁ እወዳለሁ።

በስተመጨረሻ በበለጠ የሕይወት ጉዞ ታሪክ የተመሰጣችሁ በሀገር ውስጥና በወጪም ያላችሁ ካላችሁ ቀጥሎ ባለው የግል የሰልክ ቁጥሩ በመደወል፣ እንድታበረታቱት በታላቅ አክብሮት እጠይቃችዋለሁ።

0918991011 [Belete Butuna]

ሳሙኤል በላይነህ ቃ'ሜ
ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ሐዋሳ፣ ሲዳማ | ኢትዮጵያ 🇪🇹
2024/09/28 19:35:05
Back to Top
HTML Embed Code: