Telegram Web Link
የገቨርናንስና ልማት ጥናት ተማሪዎች ማህበር በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመሰረተ::
*//***
ግንቦት 22/2016 ዓም
የዘርፉ ባለሙያዎች በጋራና በትብብር እንዲሰሩ ያስችላል በሚል የተቋቋመው ማህበር የምስረታ  መርሐግብር በክብር እንግዶች የህይወት ተሞክሮና የማነቃቂያ ንግግር ግንቦት 21/2016 ዓ.ም በዋናው ግቢ የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተካሂዷል።

የህግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ደብረወርቅ ደበበ መርሐግብሩን ባስጀመሩበት ንግግራቸው እንደገለጹት በሀገር አቀፍና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በርካታ የሙያ ማህበራት እንደሚገኙና እነኚሁ ማህበራት በቀጥታ በቀለም ትምህርት ከሚገኘው እውቀት በተጨማሪ የተለያዩ ልምዶችና ተሞክሮዎች ማግኛ መንገድ በመሆን እያገለገሉ እንደሆነ ገልፀዋል። "የገቨርናንስና ልማት ጥናት ተማሪዎች ማህበር" በራሳቸው በኮሌጁ ተማሪዎች ተነሳሽነት የተቋቋመ መሆኑን ያነሱት ዲኑ በዚሁ የሙያ ዘርፍ የሚሰሩ አካላትን በማቀራረብና የተሻለ ስራን መስራት እንዲችሉ በማድረግ ረገድ ተጨባጭ ስራ ይሰራል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

የሲዳማ ልማት ኮርፖሬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታሪኩ ለማ በመድረኩ ተገኝተው የህይወት ልምዳቸውን ባጋሩበት ወቅት እንደገለጹት ሁልጊዜም አዳዲስ ማህበራትና ተቋማት ሲመሰረቱ ፈተናዎች እንደሚገጥማቸውና በቀላሉ ሀሳቦቻቸውን የሚገዙ አባላት ለማግኘት የሚቸገሩ ቢሆንም ሰዎች ግን ለሚይዙት ሀሳብና ለሚከተለሉት አላማ ጽናትና ቁርጠኝነት ካላቸው ወደ ስኬት መድረሳቸው የማይቀር መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ታሪኩ አክለውም ሀገራችን ወጣትና አዳዲስ ሀሳብ ያላቸው መሪዎችን የምትፈልግበት ጊዜ ላይ እንደመገኘቷ መሰል የሙያ ማህበራት በእውቀትና በክህሎት የበቁ አመራሮችን ለማፍራት ጉልህ ድርሻ እንደሚጫወቱ ተናግረዋል።
👍2
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ምህረት ገነነ በበኩላቸው የኮሌጁ ተማሪዎች ይህንን የሙያ ማህበር ለማቋቋም የሄዱበት ርቀት ብበዙ የሚያስመሰግናቸው መሆኑን አንስተው ማህበሩና አባላቶቹ የተሰጡትን ስራዎች በታማኝነትና በመሰጠት ከሰሩ የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ማህበሩ ከአካታችነት አንጻር ጠንካራ ስራዎችን መስራት እንዳለበት ያነሱት ወ/ሮ ምህረት በተለይም ሴቶችን ወደ አመራር ቦታ በማምጣትና አቅማቸውን በማሳደግ ምሳሌ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል።

የማህበሩ ፕሬዚደንት ተማሪ ቶሌራ ሙሉጌታ ስለማህበሩ አጠቃላይ ያደረገ ሲሆን "ብቁ የሆነ አመራር ቀጣይነት ላለው ልማት" በሚል መሪ ቃል የሚመራና በአላማ ደረጃ የአካዳሚክ ድጋፍ ማድረግ፣ የማጠናከሪያ ወርክሾፖችን ማዘጋጀት፣ ሙያዊ እድገትን ማገዝ እንዲሁም የምርምር እድሎችን ማመቻቸትና የማህበረሰባዊ ተሳትፎን ማሳደግ ላይ እንደሚሰራ ገልጽዋል። የማህበሩ ራዕይ በሚቀጥሉት አምስት አመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ደረጃ በዘርፉ ግንባር ቀደም ማህበር መሆን መሆኑን ያነሳው ተማሪ ቶሌራ ይህንን ለማሳካት የአካዳሚክ ልህቀትን በማጎልበት፣ በስነ-ምግባር የታነጸ አመራርን ማስተዋወቅና ዘላቂ ልማትን በአዲስ የምርምርና የጥብቅና ተሳትፎ መስራትን እንደ ተልዕኮ መያዙን ጨምሮ ተናግሯል።

                     ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
                    ሁሌም ለልህቀት!
           
ሊያገኙን ቢፈልጉ:-
*
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://www.tg-me.com/HUCommunicationsoffice
Email: [email protected]
Telephone: +251462205168
P. O. Box: 05, Hawassa
👍3
Forwarded from Serve for Society HU
ለ GC ተማሪዎች አሪፍ እድል🎓🎉

የግቢ ቆይታችሁን የማይረሳ ለማድረግ አሪፍ አጋጣሚ ይዘንላችሁ መተናል😊 serve for society hawassa ከተለያዩ ክበብ እና አካላት ጋር በመተባበር የደም ልገሳ መረሀ-ግብር አዘጋጅቷል በዚህም መረሀ-ግብር በተለይ GC ተማሪዎች የመጨረሻ ቆይታቸው እንደመሆኑ መጠን አንድም ከጓደኞቻቸው ጋር ማስታወሻ ሚፈጥሩበት እንዲሁም የስራ አለም  ላይ የሚረዳቸውን የእውቅና ሰርተፊኬት የሚይዙበት እንዲሆን ታስቦ
በቀን 22/09/16 (አርብ) ተሰናድቷል።

በመረሀ-ግብሩ:

ደም ለጋሾች የእውቅና ሰርተፊኬት ያገኛሉ
serve for society ቴሌግራም ቻናል ላይ ለለጋሾች ምስጋና እና እውቅና ይዘጋጃል
ለ GC የማስታወሻ ፎቶ ፕሮግራም ይኖራል

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
በተለይ GC😊

ኑ!!! የሰው ህይወት እያተረፉ የማይረሳ ጊዜ ያሳልፉ

📍አድራሻ :main campus የተማሪዎች ፖሊስ ጣብያ ፊትለፊት

For more info:https://www.tg-me.com/serveforsocietyhu
👍5
የምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ
Reasonable Visionary's Collection (RVC)


ሰላም ውድ የRVC ቤተሰቦች እንዴት ቆያችሁን

  ተናፋቂዋ የ RVC ቅዳሜ ደርሳለች፤ ታዲያ እጅ ከምን ካላቹን፤ ዛሬ ሀሳብ ብቻ አደለም ተተኪ ኮሚቴዎቻችንን ለናንተ ለማስተዋወቅ እንሆ ቅዳሜ ምሽት 1:00 እየጠበቅን ነው።
የሀሳብ ማዕዳችንን አሰናድተን፤ እንደሀገራችን ባህል ቡናችንን አፍልተን እንጠብቃቹሀለንና እንዳትቀሩ።

  በዚህ ሳምንት ስለ ተፅኖ ፈጣሪዎቻችን እያወጋን የምናመሽ ይሆናል፤ እስከዛው ግን የሚከተሉትን ነጥቦች እያሰላሰላቹት ቆዩን።

ምንጭ: - ከዶሴ ( @RvcClub )
ተፅኖ ፈጣሪነት

1. ለእናንተ ተፅኖ ፈጣሪነት ምንድነው፤ እንዴት ትገልፁታላቹ
2. ከላይ በስዕል የምትመለከቷቸው ሰዎች ተፅኖ ፈጣሪነት መለክያው ምንድነው
3. እንዴት የአለምን ቅርፅ ላበላሹ ሰዎች የተፅኖ ፈጣሪነት መዓረግ እናጎናፅፋቸዋለን?

በሚሉና ተያያዥ ሀሳቦች እንመክራለን፤ በምክንያት ሀሳባችንን እየተቋደስን ቡናችንን እየጠጣን ለአዲሱ ኮሚቴ መልካም ጊዜ እየተመኘን አብረን እናመሻለንና፤ ሁላቹም ተጋብዛችኋል። ቅዳሜ ምሽት 1:00 ሰዓት በRVC አይቀርም።

ሰናይ ጊዜ ተመኘንላቹ!!!


📍🗺️ አድራሻችን Main Campus, Radio ጣቢያው ፊት ለፊት በሚገኘው አዳራሽ።

  የቴሌግራም ቻናላችንን ላልተቀላቀላቹ ከታች ባለው ሊንክ መቀላቀል እንዳይረሳ።


#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
@RvcClub
👍1
🔴🔴lost ID🔴🔴

+251977058261
የምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ (rvc)

‼️ በrvc ቤት በአባልነት ቆይታችሁ በዘንድሮው አመት ተመራቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ⁉️


በብዙ ቆይታችሁ የተማማርንበት፣ ፣ጠይቃችሁ የመለሳችሁበት፣ወዷችሁ እና  ወዳችሁት የቆያችሁበት ቤታችሁ ወዳጆቼንማ አመስግኜና መርቄ ልሸኝ እንጂ በማለት ሽርጉዱን ተያይዞታል ።

ታዲያ እንናንተም በዚሁ መሰረት :-


📌ላለፉት አመታት RVCን ያገለገላችሁ(በሁሉም ረገድ)


📌የአባልነት መታወቂያ ያላችሁ


📌በሳምንታዊው ውይይቶቻችን እና ልዩ ልዩ ዝግጅቶቻችን ላይ ስትሳተፉ የቆያችሁ (attendance ይታያል ታዲያ )

ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ቤተስቦቻችን የሰርተፍኬት ማሰሪያ 50 ብር በ👇1000532041019
(Melak girmaw) በተሰኘው account በሞባይል ባንኪንግ ብቻ ማስገባት ይኖርባችኋል!

🛑 ማሳሰቢያ 👉ሙሉ ስማችሁን እና ገንዘቡን ማስገባታችሁን የሚያረጋግጥ ምስል(screen shoot ) ከታች👇 በተቀመጡት በሁለቱም አድራሻዎች(username) እስከ ረብዕ ድረስ ብቻ በመላክ በተለመደው ትብብር መሰነባበቻችንን በጋራ እናዘጋጅ ።


የቤትና የቤተሰብ ትርጉሙ ይሄም ነውና እንደ ወጉ ቸር ይግጠማችሁ ብለን ቀድመን መርቀን እንሸኛችሁ ።

1) @AyinadisTarekegn
2)@Mom2306

🛑 እስከ ማክሰኞ(27/09/2016) ብቻ ቀኑን ማራዘማችንን እያሳወቅን ክፍያውን ባለመክፈላችሁ ምክንያት ሰርተፍኬት ሳይሰራላችሁ ቢቀር ተጠያቂነቱን እንደማንወስድ ቀድመን ለማሳወቅ እንወዳለን ‼️⁉️

#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
@RvcClub
👏3👍1
❗️ Reminder for Main Campus 2nd year and 3rd year students.

Today is the deadline for Ministry of Peace in coordination with the Ministry of Education in the 2016 year summer volunteer service program registration. See requirements and apply as soon as possible. Don't miss this opportunity

Read more...

https://forms.gle/ngY1rgQx7CSxdpuz7

| HU Main Campus Student Council
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
የምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ
Reasonable Visionary's Collection (RVC)



ሰላም ውድ የRVC ቤተሰቦች እንዴት ቆያችሁን

የFinal ፈተና ተጀምሯልና በቅድሚያ ለሁላቹም መልካም ፈተና እንዲሆን ቤተሰባዊ ምኞታችን ነው።

RVC ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የቤተ-መፅሀፍት አገልግሎቱ አንዱ መሆኑ ይታወቃል በመሆኑም በዚህ ዓመት መፅሀፍት ተውሳቹ ያልመለሳቹ ተማሪዎች በዚህ ሳምንት እንድትመልሱ ይሁን።

መፅሀፍቱን በRVC ቤተ መፃህፍት በመሄድ ወይም በ +251953622522 በመደወል እንድታስረክቡ።


መልካም የንባብ ጊዜ !!!
መልካም ፈተና !!!


📍🗺️ አድራሻችን Main Campus, Radio ጣቢያው ፊት ለፊት በሚገኘው አዳራሽ።


#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
@RvcClub
1👍1
🔴🔴Notice 🔴🔴
Opportunity released for 4th year and 5th year Veterinary students

Only limited spots are available. Hurry and be part of big lifetime experience



Apply 👇👇👇👇👇👇
https://ln.run/6VCFN

🔴🔴 Note 🔴🔴
This form is only valid for Technology Institute students only
👍3
Calling all 2nd and 3rd year hawassa university students! Are you ready to step up and take on an executive role in our club's new generation? If you believe you have the experience, skills, and passion for the job, we want to hear from you. This is an incredible opportunity to make a real impact and shape the future of our club.

We invite you to share your detailed plan, grade results, and any previous experience that showcases your leadership abilities and dedication. We are looking for individuals who are eager to contribute, innovate, and lead with excellence.

Please send your submissions to the following Telegram address. We can't wait to see what you bring to the table. Let's work together to create a vibrant and successful future for our club!
@yourbeautifulluck
Join our club
https://www.tg-me.com/Hu_new_generation_club
👍3
2025/07/09 06:01:40
Back to Top
HTML Embed Code: