Telegram Web Link
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

[ † እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት እና ለአቡነ ገብረ ማርያም ዘሐንታ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። †  ]

†በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


† 🕊 ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት  🕊 †  

† በሕገ ወንጌል የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው:: ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር::
ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ:: [ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ] ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ:: የወቅቱ ታላቅ መምሕር ገማልያል ይባል ነበር:: ይህ ሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕ.፭፥፴፫ ላይ ተጠቅሷል::

በትውፊት ትምሕርት ደግሞ ይህ ደግ ሰው በርካታ ቅዱሳንን [እስጢፋኖስን: ዻውሎስን: ናትናኤልን: ኒቆዲሞስን . ..] አስተምሯል:: በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር:: በፍጻሜውም አምኗል::

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ: ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ:: ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር::

በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሃ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ:: ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: ለ፮ ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ:: ለ፮ ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በኋላ ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠመቀ:: በወቅቱ የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው::

"ከእኔ ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው" በሚል ላከው:: ቅዱሱም ከጌታ ዘንድ ሔዶ: እጅ ነስቶ ተማረ:: [ሉቃ.፯፥፲፰] በዚያውም የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ:: ጌታም ከ፸፪ቱ አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው:: አጋንንትም ተገዙለት:: [ሉቃ.፲፥፲፯]

ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ:: ምሥጢር አስተረጐመ:: ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ ከተነሳ በኋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ባርኳል:: በዚህ ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን [ዽዽስናን] ተሹሟል:: በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ፸፪ቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት: ምሥጢርም የተገለጠለት የለም:: በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን ይሰብክ ገባ::

በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ ፯ ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: አልፎም የ፮ቱ ዲያቆናት አለቃ እና የ8ሺው ማሕበር መሪ [አስተዳዳሪ] ሆኗል:: ፰ሺ ሰውን ከአጋንንት ፈተና መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለማወቅ አባቶቻችንን መጠየቅ ነው:: አንድን ሰው ተቆጣጥሮ ለድኅነት ማብቃት እንኳ እጅግ ፈተና ነው:: መጽሐፍ እንደሚል ግን 'መንፈስ ቅዱስ የሞላበት: ማሕደረ እግዚአብሔር' ነውና ለእርሱ ተቻለው:: [ሐዋ.፮፥፭]

አንዳንዶቻችን ቅዱስ እስጢፋኖስ 'ሊቀ ዲያቆናት' ሲባል እንደዘመኑ ይመስለን ይሆናል:: እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው:: ዲቁናው ለእርሱ 'በራት ላይ ዳረጐት' ነው እንጂ እንዲሁ ዲያቆን ብቻ አይደለም::

ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ ለ፩ ዓመት ያህል 8ሺውን ማሕበር እየመራ: ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት 'እጠፋ እጠፋ': ወንጌል ደግሞ 'እሰፋ እሰፋ' አለች:: በዚህ ጊዜ 'ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው' ብለው አይሁድ በማመናቸው ሊገልድሉት አስበውም አልቀሩ ገደሉት::

እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው:: በመጨረሻውም ስለ እነሱ ምሕረትን እየለመነ በድንጋይ ወገሩት:: ደቀ መዛሙርቱም ታላቅ ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት::

ቅዱስ እስጢፋኖስ ካረፈ ከ፫፻ ዓመታት በኋላ በኢየሩሳሌም የሚኖር አንድ ደግ ሰው ነበር:: ስሙም ሉክያኖስ ይባል ነበር:: በተደጋጋሚ በራዕይ ቅዱሱ እየተገለጠ "ሥጋየን አውጣ" ይለው ነበርና ሒዶ ለዻዻሱ ነገረው:: ዻዻሱም ደስ ብሎት ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ ወደ አጸደ ገማልያል [የመምሕሩ ርስት ነው] ሔደ:: ቦታውንም በቆፈሩ ጊዜ ታላቅ መነዋወጥ ሆነ:: መላእክት ሲያጥኑ በጐ መዓዛ ሸተተ:: ዝማሬ መላእክትም ተሰማ:: ሕዝቡና ዻዻሱም በቅዱስ እስጢፋኖስ ፊት ሰግደው: በታላቅ ዝማሬና በሐሴት ዐጽሙን ከዚያ አውጥተው: በጽርሐ ጽዮን [በተቀደሰችው ቤት] አኖሩት:: እለ እስክንድሮስ የተባለ ደግ ሰውም ቤተ ክርስቲያን አንጾለት ወደዚያ አገቡት:: ከ፭ ዓመታት በኋላም እለ እስክንድሮስ ሲያርፍ በሳጥን አድርገው በቅዱሱ ጐን ስለ ፍቅሩ አኖሩት:: ሚስቱ ወደ ሃገሯ ቁስጥንጥንያ ስትመለስ የባሏን ሥጋ መስሏት የቅዱስ እስጢፋኖስን ቅዱስ ሥጋ በመርከብ ጭና ወሰደችው:: መንገድ ላይ ከሳጥኑ ውስጥ ዝማሬ ሰምታ ብታየው ያመጣችው የቅዱሱን ሥጋ ነው:: እጅግ ደስ አላት: አምላክ ለዚህ አድሏታልና:: እርሷም ወስዳ ለታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አስረከበች:: በከተማውም ታላቅ ሐሴት ተደረገ::

ሥጋውን ሊያኖሩት በበቅሎ ጭነው ሲወስዱትም በቅሎዋ በሰው ልሳን ተናግራ ማረፊያውን አሳወቀች:: በዚያም ላይ ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ታንጾለታል:: ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲመቱ ጥቅምት ፲፯ : ዕረፍቱ ጥር ፩ ፍልሠቱ ደግሞ መስከረም ፲፭ ቀን ነው::

† 🕊 አቡነ ገብረ ማርያም ዘሐንታ 🕊

ጻድቁ በ፲፬ኛው ክ/ዘመን ከተነሱ አበው አንዱ ሲሆኑ ገዳማቸው ደብረ ሐንታ ወሎ ውስጥ ይገኛል:: አቡነ ገብረማርያም በተጋድሏቸው: በተአምራቸውና በወንጌል አገልግሎታቸው ይታወቃሉ:: ይልቁኑ ግን የሚታወቁት ለእመቤታችን በነበራቸው ፍቅር ነው:: ያንን ጥዑም ማሕሌተ ጽጌ ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር ሆነው የደረሱ እርሳቸው ናቸውና:: በገዳማቸው ብርሃን እስኪበራ ድረስ በንጹሕ የማኅሌት አገልግሎታቸው ድንግል ማርያምንና ቸር ልጇን አስደስተው: በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

🕊 አባ ጴጥሮስ ዘጠራው 🕊

በደብረ ጠራው: ሠንሠለት ለብለው: ከእህል ተከልክለው: በጾምና ጸሎት ተወስነው ይኖሩ ነበር:: ፈጣሪን ፳፬ ሰዓት "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" እያሉ እያመሰገኑ ሲርባቸው ደረቅ ሣር ነጭተው ይበሉ ነበር:: ከብዙ ተጋድሎ በኋላም ያረፉት በዚህ ቀን ነው::
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
† አምላከ ቅዱስ እስጢፋኖስ በረድኤት ይጐብኘን:: ከወዳጆቹ በረከትም ተካፋዮች ያድርገን::

🕊

[ † መስከረም ፲፭ [ 15 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት]

፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት [ፍልሠቱ]
፪. አቡነ ገብረ ማርያም ዘሐንታ
፫. አባ ዼጥሮስ ዘሃገረ ጠራው

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
፪. ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ [አፈ በረከት]
፫. ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ
፬. ቅድስት እንባ መሪና
፭. ቅድስት ክርስጢና

† " እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር . . . አንዳንዶቹ ተነስተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር:: ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙዘንድ አልቻሉም:: በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ: በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሱ . . . በሸንጐም የተቀመጡት ሁሉ ትኩር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት::" † [ሐዋ. ፮፥፰-፲፭]


† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን። †

❖    መስከረም ፲፮ [ 16 ]   ❖


[  † እንኩዋን ለቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም: ለቅዱስ ጦቢት እና ለአባ አጋቶንባሕታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። †  ]


†  🕊   ሕንጸታ ለኢየሩሳሌም  🕊  †

ኢየሩሳሌም በብሉይም: በሐዲስም ቅድስት ሃገረ እግዚአብሔር ናት:: 'ኢየሩ' ማለት 'ሃገር' ማለት ሲሆን 'ሳሌም' ደግሞ 'ሰላም' ማለት ነው። ስለዚህ በቁሙ 'ሃገረ ሰላም': 'ሃገረ_ክርስቶስ' ማለት ነው።

ኢየሩሳሌም የሚለው ቃል በቁሙ ቅድስት ሃገርን ሲመለከት በምሥጢሩ ግን የቤተ ክርስቲያን: የመንግስተ ሰማያት እና የአማናዊት ሃገረ ሰላም ድንግል ማርያም መጠሪያ ነው:: ኢየሩሳሌምን በከተማ ደረጃ የመሠረታት ታላቁ ካህን መልከ_ጼዴቅ ሲሆን 'ንጉሠ ሳሌም' ተብሎም ኑሮባታል::

ይህች ቅድስት ሃገር በብሉይ ዘመን እግዚአብሔር በረድኤት ቢገለጥባት: ጻድቃነ ብሊት ቢኖሩባት ተቀድሳለች:: በሐዲስ ኪዳን ግን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማያት ወርዶ ፴፫ ዓመት ከ፫ ወር ያህል የድኅነ ትሥራውን ቢፈጽምባት: ለድንግል ማርያምና ለብዙ ቅዱሳን ቤት ብትሆን የበለጠ ተቀድሳለች::

ዛሬም ድረስ ከተለያዩ ክፍላተ ዓለማት በብዙ ድካምና ወጪ ሊያዩዎት ይጉዋዛሉ:: የቀደመው ዘመን አባቶቻችንም ይህችን ቅድስት ከተማ ለመሳለም እስከ ደም ጠብታ ከፍለዋል::

ወደ ዋናው ጉዳያችን እንለፍና የኢየሩሳሌምን መታነጽ እንይ:: ኢየሩሳሌም በአሕዛብ እጅ ብዙ ጊዜ ፈርሳ ታንጻለች:: እኛ ግን ዛሬ የምናከብረው የከተማዋን መታነጽ ሳይሆን በከተማዋ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መንገድ በአንድ ጊዜ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት መታነጻቸውን ነው:: ይሕስ እንደምን ነው ቢሉ :-

ከክርስቶስ ዕርገት ፫፻ ዓመታት በሁዋላ ለቤተ ክርስቲያን የተነሳችው ቅድስት ዕሌኒ በጐ ሃሳብ በሕሊናዋ ተመላልሷልና ተነሳች::

ጉባኤ ኒቅያ ከተጠናቀቀ በሁዋላ ልጇ ቆስጠንጢኖስ በነገሠ በ፳ ዓመቱ በ፪፻፳፯ዓ/ም አካባቢ ቅዱስ ዕጸ መስቀሉን ትፈልግ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ አደረገች::

መስቀሉን ፈልጋ ያገኘችበት ታሪክ ለነገ ይቆየንና መስቀሉን ካገኘችው በሁዋላ በሙሉ ከተማዋ ላይ አብያተ ክርስቲያናትን ለማነጽ ከልጇ ጋር ተስማማች::

ለሕንጻው የሚሆን ብዙ ወርቅ: ብርና እንቁ ጭና ማምጣቷን የተመለከቱት አባ መቃርስ [የኢየሩሳሌም ሊቀ ዻዻስ ናቸው] "ልምከርሽ! ቤተ ክርስቲያኑን በጠንካራ አለት ላይ ሥሪ:: ወርቅና ብሩን ግን ለነዳያን በትኚ" ስላሏት በአካባቢው ላሉ ነዳያን ታላቅ ፌሽታ ሆነ:: እጅግ ብዙ ሠራዊት: ብዙ ሺህ ሠራተኞች ታጥቀው ፹ አብያተ ክርስቲያናትን ያንጹ ጀመሩ::

ሥራው ረቂቅና ብዙ ሥለ ነበረ እጅግ አድካሚ ነበር:: ቅድስት ዕሌኒ ሃገሪቷን በቤተ መቅደሶች መሸፈን ስለ ፈለገች እንዲታነጽ ያዘዘችው የቤተ ክርስቲያን ቁጥር ፹ ደረሰ:: እነዚህም ጌታ ከጽንሰቱ እስከ ዕርገቱ የረገጣቸውና እመ ብርሃን የረገጠቻቸው ቦታዎች ናቸው::

ቤተ_ልሔም: ዮርዳኖስ: ደብረ ሊባኖስ: ደብረ_ታቦር: ደብረ_ዘይት: ጐልጐታ: ጌቴ_ሴማኒ: ቤተ_ሳይዳ: ጽርሃ_ጽዮን ደግሞ ዋና ዋናዎቹ ናቸው:: በአካባቢው ያሉ ነዳያን ሳይርባቸው: ሠራተኞችም ደሞዝ ሳይቸግራቸው: ፹ው አብያተ ክርስቲያናት በፈጣሪ ረዳትነት: በ፲ ዓመታት ታነጹ::

ቀጥሎም ንጉሡ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ በዓለም ያሉ ታላላቅ ቅዱሳን ሊቃነ ዻዻሳትን ጠርቶ: ሁሉም እስከ መስከረም ፲፭ ቀን ወደ ኢየሩሳሌም በተሰበሰቡበት የሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ቅዳሴ ቤት በአንድ ላይ ሲከበር ከዝማሬው ብዛት: ከአምላክ ጸጋ የተነሳ በከተማዋ ታይቶ የማይታወቅ ሐሴት ተደረገ::

ኢየሩሳሌም ፍጹም አጊጣ እስከ መከራ ቀን [አሕዛብ እስከ ተነሱበት] ቆይታለች::


†  🕊  ቅዱስ ጦቢት [ጻድቅ ነቢይ]  🕊 

ከክርስቶስ ልደት በፊት እሥራኤላውያን ክፋትን ሲያበዙ ጠላት መጥቶ ይማርካቸው: ንስሃ ሲገቡ ደግሞ በድንቅ ተአምር ይወጡ ነበር:: ሕዝቡ ሲማረክ ነቢያት እረኞች ናቸውና ያለ ጥፋታቸው አብረው ይማረኩ ነበር:: በዚያም ሕዝቡን ያስተምራሉ: ያጽናናሉ::

በተመሳሳይ እሥራኤላውያን ተማርከው ወደ ነነዌ በወረዱበት ወራት ጦቢት የሚሉት ደግ ሰው በመካከላቸው ነበር:: ይህ ደግ ሰው ከምርኮ በፊት መልካም አምልኮት የነበረው: አሥራቱን በኩራቱን የሚያወጣ: ለነዳያን የሚራራ ነበር::

ከተማረኩ በሁዋላም ሕዝቡ ከአሕዛብ ጋራ ሲቀላቀሉ እርሱ ንጽሕናውን ጠብቆ እግዚአብሔርን ያመልክ ነበር:: ቅዱስ ጦቢት በተለይ የሞተ ሰው ሲያገኝ ሳይቀብር እህል አይቀምስም ነበር:: በዚህም ምክንያት የዘወትር ጦመኛ ነበር::

ይሕ ቅዱስ እድሜው ፶፰ በሆነ ጊዜ ዓይኑ ጠፋ:: ብዙ በመሰቃየቱም ሞቱን ለመነ:: በሌላ አቅጣጫ ደግሞ ሣራ 'አስማንድዮስ' የሚባል ጋኔን ፯ ባሎቿን እየገደለ አሳቅቁዋት ነበርና እርሷም ሞቷን ተመኘች::

እግዚአብሔር ግን መልአኩን ልኮ: ቅዱስ ሩፋኤል አዛርያን መስሎ የጦብያና የሣራን ጋብቻ ባርኩዋል:: ጋኔኑንም በጥልቁ አስጥሞታል:: በዓሣ ሐሞትም የጦቢት ዓይኑ በርቶለት በእድሜው ላይ ፻ ዓመታት ተጨምረውለታል:: ቅዱስ ጦቢት ብዙ ሕብረ ትንቢቶችን ተናግሮ በ፻፶፰ ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፏል::


†   🕊  አባ አጋቶን ባሕታዊ   🕊  †

ይህንን ቅዱስ የማያውቅ የቤተ ክርስቲያን ሰው ይኖራል ብየ አልገምትም:: እርሱ ታላቅ ጻድቅ: ገዳማዊና የእግዚአብሔር ሰው ሲሆን አንደበቱን ከክፋት ይከለክል ዘንድ ለ፴ ዓመታት ድንጋይ ጐርሶ ኖሯል::

ይህንን ቅዱስ ሊቃውንት ሲገልጹት "ክምረ ክምር ጽድቁ እስከ አስተርአየ" ይሉታል:: ትእግስቱ: ደግነቱ: አርምሞው: ትሩፋቱ ከመነገር በላይ ነው:: በነበረበት በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመንም እንደ ኮከብ ያበራ ታላቅ አባት ነው::

አምላከ ቅዱሳን የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያንን ሰላምና ደስታ ያሳየን:: ከበዓላቱ ከሚገኘውም ጸጋ በረከት አይለየን::

🕊

[ †  መስከረም ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ሕንጸታ ለኢየሩሳሌም
፪. ቅድስት እሌኒ ንግሥት
፫. ቅዱስ ጦቢት ነቢይ
፬. ቅዱሳን ጦብያና ሣራ
፭. አባ አጋቶን ባሕታዊ

[  † ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. ኪዳነ ምሕረት [የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም]
፪. ቅድስት ኤልሳቤጥ [የመጥምቁ ዮሐንስ እናት]
፫. ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ [የቅ/ላሊበላ ወንድም]
፬. ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
፭. አባ አቡናፍር ገዳማዊ
፮. አባ ዳንኤል ጻድቅ
፯. ቅዱስ አባ ዮሐንስ ጻድቅ [ወንጌሉ ዘወርቅ]

" ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ
ደስ አለኝ። ኢየሩሳሌም ሆይ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ። ኢየሩሳሌምስ እርስ በርሷ እንደ ተገለጠች ከተማ ተሠርታለች . . . ስለ ወንድሞቼ ስለ ባልንጀሮቼም በውስጥሽ ሰላም ይሁን አልሁ። ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር ቤት ላንቺ መልካምነትሽን ፈለግሁ::
" [መዝ.፻፲፪፥፩-፱]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊                       †                           🕊

               
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ !



ኦ ! በመስቀልህ የተበላሸውን ዓለም ያሳመርከው !

                            🕊                   

" ኦ ! በመስቀልህ በቀኝ የተሰቀለውን ሽፍታ አንተን ወደ ማመን የመለስከው ፣ ወደ መንግሥተ ሰማያት አስቀድሞ መግባትንም የሰጠኸው ሆይ ፣ እኔንም ወደ ቅዱሳን የደስታቸው አዳራሽ አግባኝ ፤

ኦ ! በመስቀልህ በጎችህን የሰቡ እንዲሆኑ ያደረግካቸው ፣ በደምህም ነጠብጣብ ያተምካቸው ሆይ ፣ ለእኔም ሕይወት ሰጭ የሆነውን መስቀልህን ስጠኝ ፣ ያንተን ማኅተም ተሸክሜ በጠላት ላይ እበረታታበት ዘንድ ፤

ኦ ! በመስቀልህ የእሳትን ጦር ከሱራፌል እጅ ፣ የሚያስደነግጠውንም ሰይፍ ከሱራፌል እጅ ያስወገድህ ፣ አዳምንም ወደ ወጣበት ወደ ገነት ዐጸድ ይገባ ዘንድ ያበቃኸው ሆይ ፣ እኔንም ወደ ቅዱሳን ርስታቸው እንድገባ አብቃኝ ፣እኔ አገል ጋይህ ነኝና ፤

ኦ ! በመስቀልህ የተበላሸውን ዓለም ያሳመርከው ፣ የአረጀውንም ዓለም ያደስከው ፣ ያደፈውንም ዓለም የቀደስከው ሆይ ፣ የእኔንም ነፍሴንና ሥጋዬን አድስ ፤

ኦ ! በመስቀልህ በተቀደሰው ቀኝህ የተተከለችውን የወይንህን ተክል እንድታፈራ ያደረግካት ፣ አማንያንንም እንድታፈራ ያበቃሃት ሆይ ፣ እኔ ባርያህም የሃይማኖትን አበባ እንዳብብ ፣ የንስሐንም ፍሬ እንዳፈራ አብቃኝ ፤ "

               
🕊   { ውዳሴ መስቀል }   🕊


🕊 እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰን 🕊 † 


🌼    --------------- † ---------------    🌼
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞ 

[  ✞  🌼  እንኩዋን ለብርሃነ መስቀሉ እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ  🌼 ✞  ]


🕊  ✞ ቅዱስ ዕፀ መስቀል ✞  🕊

ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ ማርያም እግዝእት በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ መከራ መስቀልን ተቀብሎ:
¤ ከግራ ቁመት:
¤ ከገሃነመ እሳት:
¤ ከሰይጣን ባርነት:
¤ ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::

" እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ " እንዳለ ሊቁ::

ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም ራሷ አርአያ ትዕምርተ መስቀል ናት::

እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት [ዘፍ.፬፥፲፭]  ጀምሮ

¤ ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት [ዘፍ.፳፪፥፮]
¤ ቅዱስ ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል [ዘፍ.፳፰፥፲፪]
¤ ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ [ዘፍ.፵፰፥፲፬]
¤ ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው የሙሴ_በትር [ዘጸ.፲፬፥፲፭]
¤ የናሱ ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት [ዘኁ.፳፩፥፰]  ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::

ቅዱስ ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: [መዝ.፶፱፥፬]

በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት:: ስለዚህም "መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም: መሠረተ ቤተ ክርስቲያን" ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::

ቅዱስ_ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን ይነግረናል:: ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስም ስለ መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን ነውና:: [፩ቆሮ.፩፥፲፰  ገላ.፮፥፲፬]

አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል:: የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ: የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ: ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ በወዴት አለና::

ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን: እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት: ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን ተሻግረዋል::

በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ ምስክርን አንፈልግም::


†  🕊   በዓለ መስቀል  🕊  †

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ አይሁድ በአንድ ነገር ተቸገሩ:: የክርስቶስን ሐዋርያት እያሳደዱ ቢገድሉም ከመስቀሉና ሥጋ ክርስቶስ አርፎበት ከነበረው ጐልጐታ ላይ የሚደረገውን ተአምር ግን መግታት አልተቻላቸውም::

መቼም ለተንኮል አያርፉምና ቅዱስ መስቀሉን ሽፍቶቹ ከተሰቀሉባቸው ጋር ደርበው አርቀው ቀበሩት:: አካባቢው የጉድፍ መጣያ እንዲሆንም አዋጅ ነገሩ:: ለክፋት ሲሆን ተባባሪው ብዙ ነውና ለ፪፻፸ ዓመታት ያህል ቆሻሻ ቢጥሉበት ተራራ ሆነ::

ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ እናታችን ቅድስት እሌኒ [ሔለና] በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት: በቅዱስ ኪራኮስ መሪነት: በቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት ደመራ አስደምራ: እጣን አጢሳ መካነ መስቀሉን አገኘች::

መስከረም ፲፯ ቀን የተጀመረው ቁፋሮ መጋቢት ፲ ቀን ተጠናቆ: ንጹሕ መስቀሉ ወጥቶ ብርሃን በርቷል: ሙታን ተነስተዋል:: ከ፲ ዓመት በሁዋላም የመስቀሉ ቤተ መቅደስ ታንጾ መስከረም ፲፯ ቀን ተቀድሷል::

ይህ ቅዱስ ዕፀ መስቀልም በደጉ አፄ ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን መጥቶ: በጻድቁ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አማካኝነት በደብረ ከርቤ [ግሸን ማርያም] ተለብጦ ተቀምጧል::


†  🕊 ቅዱስ አውዶኪስ ቀሲስ  🕊 † 

ይህ ቅዱስ ሰው ለቅዱስ መስቀሉ ከነበረው ፍቅር የተነሳ በብዙ ድካም ወደ ኢየሩሳሌም በእግሩ ተጉዞ ነበር:: ከብዙ መንገደኞች ጋር በጐዳና ላይ ሳሉ ታዲያ አንድ አይሁዳዊ [ሰማርያዊ] ተቀላቀላቸው:: በወሬ በወሬ የት እንደሚሔዱ ሲጠይቃቸው "መካነ መስቀሉን ለመሳለም ወደ ጐልጐታ ነን" አሉት::

እሱ ግን ከት ብሎ ስቆ "እንዴት እንጨት ትሳለማላችሁ" በሚል አፌዘባቸው:: የፀሐዩ ሐሩር እጅግ ጠንቶ ነበርና ቅዱስ አውዶኪስ ኃይለ መስቀሉን ሊያሳይ ወደደ:: በመንገድም መርዝነት ያለው ውሃ ነበርና ቅዱሱ ቀርቦ ጸልዮ በመስቀሉ ባረከውና ፈጥኖ ወደ ጣፋጭነት ተቀየረ::

ምዕመናኑ ደስ ብሏቸው ሲጠጡ ያ አይሁዳዊ 'እጠጣለሁ' ብሎ ቢቀርብ ወደ ነበረው ተመለሰበት:: 'በኮዳ የያዝኩትን እማልጠጣ' ብሎ ቢከፍተው ደግሞ ተልቶ አገኘው:: እጅግ ደንግጦ አለቀሰ:: በጣም ጠማው: ግን ምኑን ይጠጣ!

አማራጭ ሲያጣ ወደ ቅዱስ አውዶኪስ ሒዶ እግሩ ላይ ወድቆ አለቀሰ:: በመስቀሉ ቢማጸን መራራው ጣፈጠለት:: በዚህ ምክንያትም ወደ ክርስትና ተመልሷል:: ቅዱሱ በመልካም ሽምግልና ሲያርፍ ውሃው የተቀየረበት ቦታ ላይ ቤተ መቅደስ ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል::


†  🕊  ቅድስት ታኦግንስጣ  🕊   †

በ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረችው ሮማዊቷ እናት መንገድ ላይ ቁማ ወንጌል ስታነብ በንጉሥ ወታደሮች ተማርካ ወደ ሕንድ ተወስዳለች:: በዚያም በመስቀል አማትባ ሙት በማስነሳቷ የሃገሩ ሰው ወደ ክርስትና ከነ ንጉሡ ተመልሰዋል:: እርሷም ገዳም አንጻ: ደናግሉን ሰብስባ በንጽሕና ኑራለች:: በዚህ ቀን ዐርፋ ሲቀብሯት የብርሃን መስቀል መቃብሯ ላይ ተተክሏል::

አምላከ ቅዱሳን በኃይለ መስቀሉ: በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን:: ከበረከቱ አሳትፎ በዓሉን የሰላም ያድርግልን::

🕊

[  †  መስከረም ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ዕፀ መስቀል
፪. ቅድስት እሌኒ ንግስት
፫. ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ
፬. ቅዱስ መቃርስ ሊቀ ዻዻስ
፭. ቅዱስ አውዶኪስ ቀሲስ
፮. ብጽዕት ታኦግንስጣ ሮማዊት
፯. ቅዱስ ዲዮናስዮስ ሊቀ ዻዻሳት

[   †  ወርኀዊ በዓላት  ]

፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት [ቀዳሜ ሰማዕት]
፪. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ ዘብዴዎስ]
፫. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
፬. አባ ገሪማ ዘመደራ
፭. አባ ዸላሞን ፈላሢ
፮. አባ ለትጹን የዋህ
፯. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ [ዘደሴተ ቆዽሮስ]

" የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና . . . መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ:: የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ:: እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን:: " [፩ቆሮ.፩፥፲፰-፳፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from M.A
ንግሥት እሌኒን እናወድሳት ዘንድ ይገባል፡፡ ክብር የሚገባውን የአምላካችንን የጌታችንን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክቡር መስቀል አገኝ እንደሆነ ብላ በእምነት ለመፈለግ ተግታለችና፡፡

የጌታችን መስቀል ቅዱስ ስጋው የተቆረሰበት ክቡር ደሙ የፈሰሰበት ከሁሉ የተለየ ከሁሉ የተቀደሰ ሁሉንም የሚቀድስ እንደሆነ አስቀድማ ተገንዝባለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፡፡

ንግሥትነቷን በዓለማዊ ቅምጥልናና ምቾት ታሳልፈው ዘንድ አልወደደችም፤ ይልቁንስ የተወደደውን መስቀል ትፈልግ ዘንድ በመንፈስ ብርቱ ሆና በስጋ ደከማለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

እጅግ የከበረውን መስቀል ትፈልግ ዘንድ ስትጀምር በራሷ መታመን አልታበየችም ይልቁንስ ሁሉን ስለክርስቶስ ትቶ የወጣ ባህታዊ ኪራኮስን ታማክር ዘንድ ወዳለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

በተዋህዶ የከበረ የአብ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ይዞ እንዳላስቀረው ሞትንም ድል አድርጎ እንደተነሳ ሁሉ ክቡር መስቀሉም ተቀብሮ ለዘላለም እንደማይኖርና ከተቀበረበትም እንደሚወጣ አምናለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

ከጌታችን መስቀል ጋር የተቀበሩት መስቀሎች ብዙ ናቸው የጌታየን እንዴት እለየዋለሁ? ብላ ሳትጨነቅ የክርስቶስ መስቀል ክብሩን ራሱ እንደሚገልፅ በልቧ ተማምና እስክታገኝው ደክማለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፡፡
2024/09/28 00:22:33
Back to Top
HTML Embed Code: